Benishangul Gumuz Education Bureau @bgeducation Channel on Telegram

Benishangul Gumuz Education Bureau

@bgeducation


ይህ ቻናል የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን ከክልል እስከ ትምህርት ቤቶች ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Benishangul Gumuz Education Bureau (Amharic)

በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ትምህርት ቤተሰብ አለበት! ህገ-መንግስት ገመፅን ለተመደቡት፣ ቢሮዎችን ለማስመለስና የቴሌግራም ቻናልን በእንግዳ የምታከብሩ ድረስ እናመታለን፡፡ 'bgeducation' ትምህርት ቻናል ያላችሁ ትምህርት ቤቶች ለእኛ በሚኖሩበት አድራሻዎች ጥቅምታቸውን እና መረጃዎቸን እንደታዳሰ ከምክር አገልግሎት ላይ ማህበረሰቡን እንችላለን፡፡ ይህ ትምህርት ቻናል የምግብና የስልጠና ተግባር እና መንፈሳዊ መከታተያነት ምክንያት ነው፡፡

Benishangul Gumuz Education Bureau

23 Nov, 15:43


በፓዊ ወረዳ የቀጠና ሁለት መንደር 131 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፤ ለተማሪዎቹ ምገባ ፕሮግራም አገልግሎት ጀምሯል።

Benishangul Gumuz Education Bureau

23 Nov, 10:03


በ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ወደ 50 ፐርሰንት ለማስጠጋት ቢሮው ይሰራል ፤ ለዚህም የትምህርት ቤት አመራሮችና መምህራን አበክረው ሊሰሩ ይገባል።የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር)
--- -------- ------- ------- ------------ -----------
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር) ለርዕሳነ-መምህራን ምን ምን ጉዳዮች አነሱ?
-ጥራቱንና ተገቢነት ያለው መረጃ ላይ ትኩረት መስጠት ተገቢ ነው።
-የመምህርነት ሙያ ፤ የሙያዎች ሁሉ የበላይ ነው። በዚህ ልክ መስራት ተገቢ ነው።
-የትምህርት ቤት አመራር ለመምህሩ መሪ ነው። በዚህ ልክ ለስራው ቁርጠኛ መሆን
-የትብብር መንፈስ ማሳደግ።
-ሴት መምህራን በአመራርና በመምህርነት እንዲበዙ ይደረጋል።
-ትምህርት ቤቶችን ባደረግነው በምልከታ ጉድለት እንዳለባቸው ተመልክተናል። ይህን ወደ ስራ ስተመለሱ ትምህርት ቤቶችን መፈተሽ አለባችሁ።
-የትምህርት ቤት አመራሮች ሃላፊነት ድርብርብ ነው፤ የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል ግንበር ቀደም ተጠያቂ ናችሁ።
-የትምህርት ቤት አመራሮች ለመምህራን ሞዴል መሆን አለባቸው
-የተማሪዎች ስነ-ምግባር የሚታነጸው በታችኛው የትምህርት እርከን ነው። እዚህ ላይ ስራ ይፈልጋል።
-የ8ኛ ክፍል ውጤት አስደንጋጭ ነው፤ ችግሩ የእኛ ማለት ይገባል።
-የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ላይ ከፍተኛ ችግር አለበት። ቢሮው በጥናት ለመመለስ እየሰራ ነው። ይህን ስራ የእናንተን እገዛ ይፈለጋል።
-የትምህርት ብክነት እንዳይኖር ጥንቃቄ ይደረግ።
-መምህሩ በበቂ ዝግጅት ማስተማር አለበት።
-መጽሐፍ በተቻለ መጠን ለተማሪዎች ተደራሽ አድርጉ።
-የውስጥ ገቢ ላይ ህብረተሰቡ ጋር በመሆን ማሳደግ።
-የትምህርት ቤት አመራሮች instructional leader መሆን አለበት። ዘገባው የቢሮው ኮሚኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው።

Benishangul Gumuz Education Bureau

23 Nov, 08:21


(Constructing the table of sepecifications)

Benishangul Gumuz Education Bureau

23 Nov, 06:46


🕺(ህዳር 14/2017 ዓ.ም )

🕺🕺የኢንዚ 1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ዛሬም በተመሳሳይ መልኩ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጲያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓልን በተለያዩ ኩነቶች ያከበረ ሲሆን በአሉን ምክንያት በማድረግና በተማሪዎችና መላው የት/ቤቱ ማህበረሰብ ዘንድ ልጆቻችን ከመደበኛው ት/ት በተጨማሪ የክፍል ለክፍል ተማሪዎችና መምህራን የሰላም ዋንጫ በማዘጋጀት ከጥሎ ማለፍ በኋላ መምህራን ከተማሪዎች ጋር በተደረገ ውድድር ተማሪዎች 8 ለ 4 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሰላም ዋንጫ ባለቤት ሆነዋል። Via Abdu

Benishangul Gumuz Education Bureau

23 Nov, 06:29


(ህዳር 14/2017 ዓ.ም) ተማሪዎችን የመማር ብቃታቸውን ከመመዘን ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እንዲያስችል ለአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ርዕሳነ መምህራን በተማሪዎች ምዘና (Constructing the table of sepecifications) የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።