ድምፀ ተዋሕዶ @demtsetewahido Channel on Telegram

ድምፀ ተዋሕዶ

@demtsetewahido


ይህ መንፈሳዊ ቻናል መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ያደረገ ማንኛውንም ታማኝ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን እና መንፈሳዊ ክንውኖችን ለምእመኑ በፍጥነት፤ በጥራት ያቀብላል።

የእግዚአብሔር ጸጋ እና በረከት በሁላችን ላይ ይደር።

ድምፀ ተዋሕዶ ለንደን
ለታማኝ መረጃዎ

ድምፀ ተዋሕዶ (Amharic)

ድምፀ ተዋሕዶ በልጅነት ያለው መንፈሳዊ ቻናል ነው። በመባልነት እንግሊዝ ለንደን ያደረገ ማንኛውንም ታማኝ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን እና መንፈሳዊ ክንውኖችን ለምእመኑ በፍጥነት በጥራት ያቀብላል። የእግዚአብሔር ጸጋ እና በረከት በሁላችን ላይ ይደር። ድምፀ ተዋሕዶ ለንደን ለታማኝ መረጃዎ ይሆናል።

ድምፀ ተዋሕዶ

21 Nov, 13:12


ለውዳሴከ ጥዑመ ዜና፤
ቅዱስ ሚካኤል ልማድከ ግብረ ትኅትና ፤
አንተኑ ዘመራሕኮሙ ፍና፤
ወአንተኑ ለእሥራኤል ዘአውረድከ መና፤
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል፤
ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ፤
አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዐቢይ፡፡


የሰላማችን መልአክ የሆንክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ
ስለ እኛ ስለምንማለድ፣
ጸሎታችንንም ወደ ታላቁ ንጉሥ መንበር ፊት አሳርግ !

በዓለ ሢመቱ ወበዓለ መራኄ ፍኖቱ ለቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት!

ሚካኤል ማለት «መኑ ከመ አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት ነው።
ሚካኤል የሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤
ሚ - የሚለው «መኑ» "ማን" ማለት ነው፥
ካ - የሚለው «ከመ» "እንደ" ማለት ሲሆን፥
ኤል - ማለት ደግሞ «አምላክ» ማለት ነው።

Hebrew: [mixaˈʔel]; Hebrew: מִיכָאֵל‎,
romanized: Mīḳāʾēl, Mīkā'īl, Mīkāl or Mīkhā'īl
lit. 'Who is like El?';
Greek: Μιχαήλ, romanized: Mikhaḗl;
Latin: Michahel;
Coptic: ⲙⲓⲭⲁⲏⲗ;
Arabic: ميخائيل ، مِيكَالَ ، ميكائيل‎,
☆ Michael is an archangel in Judaism, Christianity, and Islam.

The name Michael means "like unto God" or "Who is like unto God?"
Most Known passages about the Archangel Micahel in the bible: Rev 12: 7-9, Jude 1:9, Joshua 6: 1-5, Daniel 3: 25-28,

The Archangel Michael was also with all the saints and martyrs. He strengthened them and enabled them to endure patiently until they finished their strife. According to Holy Scripture and Tradition, he has interceded for humanity multiple times and continues to serve as the Defender of the Faith.


ይህን ማለትም የቅዱስ ሚካኤልን ስም በጠራን ቊጥር የምንመሰክረው ስለ እግዚአብሔር ነው፤ በመሆኑም እግዚአብሔርን በባሕርይ የሚመስለው፥ በሥልጣንም የሚተካከለው፥ በምድርም በሰማይም እንደሌለ የሚናገር ልዩ፥ ክቡር ስም ነው። የነቢያት አለቃ ሙሴ ባሕረ ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ሕዝቡን ያሻገረለትንና ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያሰጠመለትን አምላክ እግዚአብሔርን በመዝሙር ሲያመሰግን፥

"መኑ ፡ ይመስለከ ፡ እምነ ፡ አማልክት ፡ እግዚኦ ፤
ወመኑ ፡ ከማከ ፡ ስቡሕ ፡ በውስተ ፡ ቅዱሳን ፤
መንክር ፡ ስብሐቲከ ፡ ወትገብር ፡ መድምመ ። "


«አቤቱ በአማልክት መካከል (በስም አማልክት ከሚባሉ፥ በስመ አማልክት ከሚጠሩ፥ አንድም አማልክት ዘበጸጋ ከተባሉ ከነቢያት ከካህናት መካከል) አንተን የሚመስል ማነው?
በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማነው?» ብሏል። (ዘጸ 15፥11)
ቅዱስ ዳዊትም፦

" አልቦ ፡ ዘይመስለከ ፡ እምነ ፡ አማልክት ፡ እግዚኦ ፤
ወአልቦ ፡ ዘከመ ፡ ምግባሪከ"


«አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፤» ብሏል። (መዝ 85፥8 )

"ሰላም ለልብከ መዝገበ ርኅራኌ ወየዋሃት
ኅሩመ በቀል ወቅንዐት
ሚካኤል ሥዩም በዲበ ኃይላት
ለደቂቀ ያዕቆብ ዘአኅለፍኮሙ በማእከለ ባህር ግርምት
አኅልፈኒ ሊተ እምኀቡእ መስገርት።
"

የርህራሄ እና የየዋህነት መፍለቂያ ለሆነው ልብህ ሰላም እላለሁ። በነገደ ሃይላት ላይ የተሾምክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ
የያዕቆብ ነገድ ህዝበ እስራኤልን ሌሊቱን በብርሃን አምድ
ቀኑን በደመና ጋርደህ እየመራህ
በባህር መካከል እንዳሳለፍክ
እኔ ኃጥእ የምሆን ባሪያህንም ሰይጣን ከሸመቀው
ከእኔ ከተሰወረው አንተ ከምታውቀው የፈተና ወጥመድ ሁሉ አሻግረኝ።

"አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክእከ ኲሉ፤
ለለ አሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ፤
ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ፤
ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኀ ሰማያት ዘላዕሉ፤
ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ፡፡
"

ሚካኤል ሆይ ለእያንዳንዱ በየ ክፍሉ ለተነገሩ መልኮችህ ሁሉ የምስጋና እጅ መንሻ አቀርባለሁ፡፡
ልዑል መልአክ ሆይ እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልጽብህ ኃያል መልአክ ነህና የምስጋናዬን እጅ መንሻ ተቀብለህ ከላይ ከኢየሩሳሌም ሰማያዊት የጸሎቴን ዋጋ እጥፍ ድርብ አድርገህ ላክልኝ።

የቅዱስ ሚካኤል ልመናው እና አማላጅነቱ አይለየን፤ መልካም በዓል፡፡
አሜን !
May His Intercessions be with us all Amen.

ጴጥሮስ አሸናፊ
ድምፀ ተዋሕዶ

ድምፀ ተዋሕዶ

09 Nov, 13:53


ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ


እንኳን ለቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ዓመተ ክብሩ (ጥቅምት ፴) በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!
                                                      ጥቅምት ፴ ዕለት ከሰባ ኹለቱ አርድእት አንዱ የኾነው ወንጌላዊ ሐዋርያ ሰማዕት ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ የተወለደበት ዕለት ነው፡፡

ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም፣ አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ፡፡ እናቱ ማርያም ቁጥሯ ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ነው፡፡ በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል:: የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ፻፳ው ቤተሰብ በዕድሜ በጣም ትንሹ ነበር፡፡ ለሦስት ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ፣ በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል፡፡ ቅዱስ ማርቆስ ቁጥሩ ከሰባ ኹለቱ አርድእት አንዱ ሲሆን፤ በሃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደላቸው በማርቆስ እናት ቤት ሆነው ሲጸልዩ ነው፡፡ ቅዱስ ማርቆስ በተለይ የግብጽና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት


እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ ክብረ በዓል(ጥቅምት ፴) አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!!
                                                       ጥቅምት ፴ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቅድስት ራሱ በአየር ውስጥ እየበረረች ፲፭ ዓመት ስታስተምር ከኖረች በኋላ፤ ከተሰወረችበት የተገለጠችበት ዕለት ነው፡፡

ድምፀ ተዋሕዶ

05 Nov, 19:55


ድምፀ ተዋሕዶ

14,593

subscribers

4,020

photos

88

videos