የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት @ewketbirhan Channel on Telegram

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

@ewketbirhan

ይህ የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣ የሰ/ት/ቤታችንን የአገልግሎት እንቅስቃሴ እንዲሁም ወቅታዊ የቤተ-ክርስቲያን መረጃዎችን የምንለቅበት የቴሌግራም ገፃችን ነው።

ይቀላቀሉን👉 https://t.me/EwketBirhan

ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት
👉 @meaZina6 ይላኩልን
+251964013892

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Amharic)

በዚህ ቦታ የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት ላይ ይህ ታሪክ፣ ጽሑፍ፣ እና መረጃዎች እንዴት መልከፋችንን እንደምንሰራ፣ ወቅታዊ የቤተ-ክርስቲያኖችን መረጃዎች እና አገልግሎት ለማንኛውም ቴሌግሮች የቴሌግሮች አፕልኬሽን አንድ ቆንጆ ነበር። እናመሰግናለው። እዚህ ስከት በለጋ የቴሌግርራሊያውን ሰምራ ካቴድራል አገልግልን ለመዘጋጀት፣ በተጨማሪም እንችላለን።

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

26 Jan, 15:19

https://vm.tiktok.com/ZMkCcr88S/

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

26 Jan, 12:36

የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛ ፓትርያርክ በዓለ ሢመት ተከናወነ !

ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ /አዲስ አበባ)

የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ በዓለ ሢመት በአሥመራ ቅድስት ማርያም በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በበዓለ ሢመቱ ላይ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቅን ጨምሮ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ፤ ከግብፅ ፣ ከሩሲያ ፣ ከግሪክ ፣ ከአርመን ፣ ከሶሪያ እና ከሕንድ የተውጣጡ የውጭ ሀገር ልዑካን ፣ የሀገሪቱ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ፣ የዲፕሎማቲክ ቡድን አባላት ፣ የሁሉም አህጉረ ስብከትና የዋና ዋና ገዳማት ተወካዮችና ምእመናን ተገኝተዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ታኅሣሥ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ እንዲሆኑ መመረጣቸው ይታወሳል።

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

26 Jan, 09:42

ጥር ፳፩ አስተርዮን በደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምህረት ከጥር ፲፱ እስከ ፳፩ ቀን ልዮ ጉባዔ
https://youtube.com/watch?v=uJlRcvbk5nE&si=wiEj3iOUuNo23nBz

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

25 Jan, 05:33

✝️ የድጋፍ ጥሪ✝️

እኅታችን ኖላዊት መለሰ ባጋጠማት የልብ ሕመም ምክንያት ዶክተሮች ቀዶ ጥገና እንድታደርግ አዘዋታል፡፡ ለዚህም ከፍተኛ ወጪ ተጠይቃለች ይህም በሷ አቅም ሊደረግ ስለማይችል ስለዚህ ሁላችንም ተረባርበን እናድትድንና አብራን በሙሉ ጤንነት እንድታገለግል እንድናግዛት በመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ስም በትህትና እንጠይቃለን፡፡

  ▶️ መደገፍ ለምትፈልጉ
         - አቢሲኒያ ባንክ -
143265048
         - ቴሌ ብር -
0991667840
    - ንግድ ባንክ - 1000450190792

‹‹ እውነት እላችኋለሁ ከሁሉ ከሚያንሱ ከነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል፡፡›› ማቴ.25፡40

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

24 Jan, 11:27

https://www.facebook.com/share/1YCEAa7qrB/

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

24 Jan, 04:38

https://www.facebook.com/share/p/1E8JBjQud4/

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

24 Jan, 04:34

የ፳፻፲፯ ዓ·ም የጥምቀት በዓል ፎቶዎች
https://t.me/PhotoEwketBirhan/6562?single

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

23 Jan, 19:04

ዛሬ ካልሆነ መቼ እኛ ካልሠራን ማንም
ለበለጠ መረጃ
0927272753
0911470407
0915554558

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

22 Jan, 08:02

Channel photo updated

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

21 Jan, 18:27

ለበለጠ መረጃ
0927272753
0911470407
0915554558

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

20 Jan, 18:01

ጥምቀት
https://youtube.com/watch?v=XJyuxM9oSaw&si=C7RpWfybbkiM0HlG

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

20 Jan, 05:31

🕯እንኳን ለቃና ዘገሊላ አደረሳችሁ! 🕯
          🍃🌹🍃🍃🌹🍃🍃🌹🍃
        •════•❁❀❁•════•
         
🔔 ገጾቹን በመቀላቀል እና ለሌሎች በማጋራት  አገልግሎቱን ይደግፉ!!
🔴 ዩቲዩብ ገፅ፡ http://youtube.com/@EwketBirhan
⚫️ ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@ewketbirhan
🔵 ፌስቡክ ገፅ፡ fb.me/EwketBirhan21
⚪️ ቴሌግራም ገፅ፦
ትምህርትና መረጃዎች፡ @EwketBirhan
የፎቶ ማጋርያ፡ @PhotoEwketBirhan
      •════•💧❁❀❁💧•════•
               🕊መልካም በዓል!

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

17 Jan, 09:55

፭፻፵፫. ኵሎ ዘፈቀደ
ኵሎ ዘፈቀደ ገብረ እግዚአብሔር (፪)
ይኒ ወበምድርኒ ወበባሕርኒ በሰማይኒ
ወበኵሉ ቀላያት ቀላያት (፬)

(ቅዱስ ዳዊት)
(ምንጭ መዝሙረ ማኅሌት)

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

17 Jan, 09:55

፮፻፲፱. ይዌድስዋ

ይዌድስዋ መላእክት (፪) ለማርያም (፪)

በውስተ ውሳጤ መንጦላዕት ወይብልዋ በሃኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ

(ቅዱስ ያሬድ)
(ምንጭ መዝሙረ ማኅሌት)

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

17 Jan, 09:55

፪፻፸. አሁን ተገለጸ

አሁን ተገለጸ የማርያም ልዕልና(፪)
በርሷ ላይ አደረ ሰማያዊ መና (፩)

ዛሬ ስለ የው ምሥጢር (፪) ስለ ታየ ያልታየወ
እጅግ ደስ አላቸው ሰማይሰማይና ምድር (፪)

የኪሩቤል ግርማ አካላዊ ቃል (፪)
ባንቺ ላይ አደረ ማርያም ድንግል (፪)

ከሰማይ ወደ ምድር አብ ቢመለከት (፪)
ምንም አላገ አላገኘም እንዳንቺ ንጽሕት (፪)
መላእክት በሰማይ እኅታችን ይሉሻል
በንጽሕ በድንጋሌ ከእነርሱ በልጣሻል (፪)

(መዝሙረ ስብሐት)
(ምንጭ መዝሙረ ማኅሌት)

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

17 Jan, 09:55

፪፻፵፯, አንቺ ቤተልሔም

(በመቀባበል)

አንቺ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ መሬት ባንቺ ተወለደ የዓለም መድኃኒት (፪) ለአዳም ክብር ሲሻ፣ ቤተልሔም፣ ለሁሉም ሰላም፣ ቤተልሔም ዛሬ ተወለደ ቤተልሔም ከድንግል ማርያም ቤተልሔም

እጅ መንሻ አቀረቡ ቤተልሔም የምሥራቅ ነገሥታት ቤተልሔም በከብቶች በረት ቤተልሔም ተኝቶ ላገኙት ቤተልሔም

አዝ

እሥራኤል ሕዝቤን ቤተልሔም የሚጠብቃቸው ቤተልሔም ካንቺ ይወጣል ብሎ ቤተልሔም እንደ ነገራቸው ቤተልሔም
አዝ

(መዝሙረ ስብሐት)
(ምንጭ መዝሙረ ማኅሌት)

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

17 Jan, 09:55

፪፻፸፬. ተወልደ ኢየሱስ

ተወልደ ኢየሱስ በቤተ ልሔም በቤተልሔም ዘይሁዳ በቤተ ልሔም (፬)

አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ
አሜሃ ይሰግዳ በቤተልሔም (፪)

(ቅዱስ ያሬድ)
(ምንጭ መዝሙረ ማኅሌት)

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

17 Jan, 09:55

፮፻፲፮. የመላእክት እኅት

የመላእክት እኅት የሰማዕታት እናት የጻድቃን እመቤት(፪)
ለምኝልን (፪) ከልጅሽ ማርያም ቅድስት
(ምንጭ መዝሙረ ማኅሌት)

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

17 Jan, 09:55

፪፻፷፯. የምሥራች ደስ ይበለን

(በመቀባበል)

የምሥራች ደስ ይበለን (፬)

የዓለም መድኀኒት ተወለደልን

የምሥራች ደስ ይበለን (፬)

ጌታችን ተወልዶ አይተነው መጣን (፬)

ንጉሥ ሄሮድስ ይህነን ሲሰማ (፬)

ፈልጋችሁ አምጡት አለ በቀን በጨለማ (፬)

ሰብአሰገል እንደታዘዙት (፬)

በኮከብ ተመርተው ሕፃኑን አገኙት (፬)

ሰገዱለት ከመሬት ወድቀው (፬)

ወርቅና ዕጣኑን ከርቤውን ሰጥተው (፪)

የምሥራች ደስ ይበለን...

(ጌታቸው መዋ)
(ምንጭ መዝሙረ ማኅሌት)

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

17 Jan, 09:26

ሰላም እንደምን ዋላችሁ ነገ 10/5/2017 በጥምቀተ ባህሩ ሰርክ ጉባኤ ላይ ልዩ የዝማሬ መርሐግብር ስላለ እንዳትቀሩ። ወዳጅ ዘመዶቻችሁን እየጋበዛችሁ እንድትቆዩ በአክብሮት እንገልፃለን።

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

17 Jan, 05:38

https://youtu.be/pc0ekImZBwQ?si=XD5YKxDzru4GWzG_

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

16 Jan, 17:14

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

          በትናትናው ዕለት የጥምቀት ኤክስፖ የሰንበት ት/ቤቶች የጥያቄና መልስ ውድድር 2ተኛ ዙር የተደረገ ሲሆን በዚህ ዙርም የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል የእውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ሁሉንም ጥያቄ በመመለስ ወደቀጣይ ዙር አልፈናል፤ በቀጣይም እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገን ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማምጣት የምንተጋ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

ስለሁሉም ነገር የእግዚአብሔር ስሙ የከበረ እና የተመሰገነ ይሁን!!! 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

16 Jan, 14:01

ጥምቀት ባሕር እንዲህ ዝግጁ ሆኗል

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

01 Jan, 02:45

' ብርሃን ዘመፃ ' | ጥምቀትን በዝማሬ | ልዩ የጥምቀት መዝሙር ጥናት ቁ ፫
https://youtube.com/watch?v=bEQEhIKwYLQ&si=i7QsIsmlWmZafU3p

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

31 Dec, 03:14

ከቀሲስ ዘክርስቶስ ፀጋዬ ለእውቀት ብርሃን ቤተ መጻሕፍት የተለገሰ።

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

30 Dec, 02:11

የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል የእውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት የሕጻናትና ማዕከላውያን ሥነጥበብ ንዑስ ክፍል ከሐምሌ 13/ 2016 ዓ.ም እስከ ህዳር 17/ 2017 ዓ.ም ድረስ የመጀመሪያ ዙር የቅዱሳት ሥዕላት አሳሳል እና የመንፈሳዊ ተውኔት አዘገጃጀት  ሥልጠናን የወሰዱ ከ50 በላይ ተማሪዎችን ታህሳስ 20 2017 ዓ·ም ወላጆቻቸው በተገኙበት አስመርቋል። ልጆቻችንን እግዚአብሔር አምላክ በጥበብና በሞገስ ጠብቆ ያሳድግልን።

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

29 Dec, 19:46

በቤተልሔም ተወልደ | ጥምቀትን በዝማሬ | ልዩ የጥምቀት መዝሙር ጥናት ቁ ፪
https://youtube.com/watch?v=2scf85km88Y&si=iwUBjS-3Cu_G72Yd

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

28 Dec, 23:38

የስእለት ልጅ መንፈሳዊ ቴአትር
ታህሳስ 26 ቀን 9:00 ሰዓት

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

28 Dec, 09:18

የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዐል በሐዋሳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።
ፎቶ እውቀት ብርሃን ሚዲያ

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

28 Dec, 04:15

በአሶሳ ሀገረ ስብከት የአሶሳ መንበረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በ1990 ተመሰረተ

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

27 Dec, 22:42

የታህሳስ ቅድስ ገብርኤል ማሕሌት አገልግሎት በሐዋሳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገደም

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

27 Dec, 14:51

ሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በዓሉን አስመልክቶ ምዕመናን ከርቁም ከቅርብም ተሰብስበዋል።

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

27 Dec, 03:40

"ጥምቀትን በዝማሬ"

'' በበረት የተኛው '' ልዩ የጥምቀት መዝሙር ጥናት ቁ.፩
https://youtube.com/watch?v=tu-YuVAy-pY&si=2RSV7FuecUmnimfm

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

04 Dec, 11:25

ህዳር 29 አይቀርም

https://vm.tiktok.com/ZMkJ7bnBV/

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

02 Dec, 18:27

ትኬቱን ቦሌ አራብሳ
+251920487968

+251929008255
ይደዉሉ

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

02 Dec, 05:38

"ቤተክርስቲያንን አንተዉም"
ከ20 ሺህ ሰው በላይ የሚሳተፍበት
10ኛው ማዕዶት ለኢትዮጵያ
ልዩ ኦርቶዶክሳዊ የኪነጥበብ መርኃግብር
    ሕዳር 29 – 2017 ዓ.ም ይደረጋል፡፡
ቦታ ሰዓሊተ ምሕረት ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ በተዘጋጀ ልዩ ቦታ
   መግቢያ ዋጋ 200 ብር
ገቢዉ
የደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ለሚያሰራው ህንፃ የሚዉል

አዘጋጅ
ማዕዶት የኪነጥበብ እና መንፈሰዊ ኩነቶች አዘጋጅ ከእውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት ጋር በመተባበር
ከአሁኑ ቀጠሮዎን ያስተካክሉ፡፡

  ትኬቱን

  በቴሌ ብር
በአሐዱ ባንክ ቅርንጫፎች
- ጊዮርጊስ ምንሊክ አደባባይ ቅርንጫፍ
- አያት አያት ቅርንጫፍ
- ቦሌ ማተሚያ አፍሪካ ጎዳና ቅርንጫፍ
- ሣርቤት አፍሪካ ሕብረት ቅርንጫ አምስት ኪሎ መንበረ ፓትሪያርክ ቅርንጫፍ
- ቦሌ መድኃኔዓለም ቅርንጫፍ
- ፊላሚንጎ መስቀል አደባባይ ቅርንጫፍ
- ማዐድን ሚኒስቴር አጠገብ ሰአሊተ ምሕረት ቅርንጫፍ
- ሰዓሊተ ምህርት ቅርንጫፍ
- ጎሮ ቅርንጫፍ
- 5 ኪሎ ቅርንጫፍ
- አሐዱ ባንክ ጀሞ ቅርንጫፍ
- አሐዱ ባንክ ገርጂ እምፔሪያል

- መገናኛ ቤተልሔም ፕላዛ ካንጋሮ ጫማ
- 6 ኪሎ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን በር ላይ
- 4 ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ 1ኛ ፎቅ hanny mobile
- ልደታ ቤተክርስቲያን ጽናጽል መዝሙር ቤት
- አስኮ ኪያ በርገር
- መርካቶ ራጉኤል ልዳ( ዘአብ) መዝሙር ቤት
- ዑራኤል ቤተክርስቲያን ቤተ መርቆሪዎስ መዝሙር ቤት
- ሳሪስ አርጋኖን ነዋየት ቅድሳት

- ቦሌ አራብሳ በ +251920487968 ወይም
+251929008255

መርሐግብሩን ማገዝ እና መደገፍ ለምትፈልጉ
በ +251903411212 ወይንም በ +251938606162 ይደዉሉ

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

30 Nov, 18:49

https://forms.gle/fF8dWCUzdvM8A2bi7

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

30 Nov, 08:19

በሸርካ ወረዳ 11 ኦርቶዶክሳውያን በጥምቀት ማክበሪያ ቦታ ላይ ተገደሉ፡፡

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሽርካ ወረዳ ኅዳር 19/2017 ዓ/ም በታጣቂዎች 11 ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል፡፡

ከግድያው በእግዚአብሔር ፈቃድ ማምለጣቸውን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የገለጹት መረጃ ሰጭው የ13 ዓመት አዳጊና የ80 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 11 ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተወስደው በጥምቀተ ባሕር ማክበሪያው ላይ  መገደላቸውንና 6 ምእመናን ደግሞ ያሉበት አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡

እየተገደሉ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን አርሰው የሚያድሩና ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎና ግንዛቤ የሌላቸው መሆናቸውን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪ የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሞቱትን ከመቅበር ባለፈ የተሻለ መፍትሔ አላመጡልነም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በርካታ የአካባቢው ምእመናን ከአካባቢው የሸሹ መሆኑን ያነሱት መረጃ ሰጭው ሰው ተወልዶ ባደገበት ሀገር በሃይማኖቱ ምክንያት እየተገደለ ነው ያሉ ሲሆን ሀብት ንብረታችንን ጥለን ለመኖር ተገደናል ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ከ20 በላይ አብያተ ክርስቲያናት የተዘጉ ሲሆን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን በስደት ላይ ናቸው ሲሉም አክለዋል፡፡

በመጨረሻም ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በዚህ ወረዳ 140 የሚደርሱ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን ገልጸው መላው የዓለም ሕዝብና ኦርቶዶክሳውያን ሞታችንን ባታስቆሙልን እንኳን የነዚህን ሰማዕታት ምስክርነት በማሳወቅ የድርሻችሁን ተወጡ ሲሉ አሳስበዋል፡፡
©MK TV

🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚🎚

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

27 Nov, 07:57

ትኬቱን

  በቴሌ ብር
በአሐዱ ባንክ ቅርንጫፎች
- ጊዮርጊስ ምንሊክ አደባባይ ቅርንጫፍ
- አያት አያት ቅርንጫፍ
- ቦሌ ማተሚያ አፍሪካ ጎዳና ቅርንጫፍ
- ሣርቤት አፍሪካ ሕብረት ቅርንጫ አምስት ኪሎ መንበረ ፓትሪያርክ ቅርንጫፍ
- ቦሌ መድኃኔዓለም ቅርንጫፍ
- ፊላሚንጎ መስቀል አደባባይ ቅርንጫፍ
- ማዐድን ሚኒስቴር አጠገብ ሰአሊተ ምሕረት ቅርንጫፍ
- ሰዓሊተ ምህርት ቅርንጫፍ
- ጎሮ ቅርንጫፍ
- 5 ኪሎ ቅርንጫፍ
- አሐዱ ባንክ ጀሞ ቅርንጫፍ
- አሐዱ ባንክ ገርጂ እምፔሪያል

- መገናኛ ቤተልሔም ፕላዛ ካንጋሮ ጫማ
- 6 ኪሎ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን በር ላይ
- 4 ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ 1ኛ ፎቅ hanny mobile
- ልደታ ቤተክርስቲያን ጽናጽል መዝሙር ቤት
- አስኮ ኪያ በርገር
- መርካቶ ራጉኤል ልዳ( ዘአብ) መዝሙር ቤት
- ዑራኤል ቤተክርስቲያን ቤተ መርቆሪዎስ መዝሙር ቤት
- ሳሪስ አርጋኖን ነዋየት ቅድሳት
- ቦሌ አራብሳ በ +251920487968 ወይም
+251929008255
ለበለጠ መረጃ
በቴሉግራም https://t.me/maedot1212 እና 
በዌብሳይታችን www.etartmedia.com አድራሻዎችን ይጎብኙ
መርሐግብሩን ማገዝ እና መደገፍ ለምትፈልጉ
በ 09 03 41 12 12 ወይንም በ 0938 60 61 62 ይደዉሉ ወይንም በቴሌግራም ያናግሩን፡፡አሐዱ ባንክ

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

25 Nov, 16:46

"ቤተክርስቲያንን አንተዉም"
ከ20 ሺህ ሰው በላይ የሚሳተፍበት
10ኛው ማዕዶት ለኢትዮጵያ
ልዩ ኦርቶዶክሳዊ የኪነጥበብ መርኃግብር
    ሕዳር 29 – 2017 ዓ.ም ይደረጋል፡፡
ቦታ ሰዓሊተ ምሕረት ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ በተዘጋጀ ልዩ ቦታ
   መግቢያ ዋጋ 200 ብር
ገቢዉ
የደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ለሚያሰራው ህንፃ የሚዉል

አዘጋጅ
ማዕዶት የኪነጥበብ እና መንፈሰዊ ኩነቶች አዘጋጅ ከእውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት ጋር በመተባበር
ከአሁኑ ቀጠሮዎን ያስተካክሉ፡፡

  ትኬቱን

  በቴሌ ብር
በአሐዱ ባንክ ቅርንጫፎች
- ጊዮርጊስ ምንሊክ አደባባይ ቅርንጫፍ
- አያት አያት ቅርንጫፍ
- ቦሌ ማተሚያ አፍሪካ ጎዳና ቅርንጫፍ
- ሣርቤት አፍሪካ ሕብረት ቅርንጫ አምስት ኪሎ መንበረ ፓትሪያርክ ቅርንጫፍ
- ቦሌ መድኃኔዓለም ቅርንጫፍ
- ፊላሚንጎ መስቀል አደባባይ ቅርንጫፍ
- ማዐድን ሚኒስቴር አጠገብ ሰአሊተ ምሕረት ቅርንጫፍ
- ሰዓሊተ ምህርት ቅርንጫፍ
- ጎሮ ቅርንጫፍ
- 5 ኪሎ ቅርንጫፍ
- አሐዱ ባንክ ጀሞ ቅርንጫፍ
- አሐዱ ባንክ ገርጂ እምፔሪያል

- መገናኛ ቤተልሔም ፕላዛ ካንጋሮ ጫማ
- 6 ኪሎ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን በር ላይ
- 4 ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ 1ኛ ፎቅ hanny mobile
- ልደታ ቤተክርስቲያን ጽናጽል መዝሙር ቤት
- አስኮ ኪያ በርገር
- መርካቶ ራጉኤል ልዳ( ዘአብ) መዝሙር ቤት
- ዑራኤል ቤተክርስቲያን ቤተ መርቆሪዎስ መዝሙር ቤት
- ሳሪስ አርጋኖን ነዋየት ቅድሳት
- ቦሌ አራብሳ በ +251920487968 ወይም
+251929008255
ለበለጠ መረጃ
በቴሉግራም https://t.me/maedot1212 እና 
በዌብሳይታችን www.etartmedia.com አድራሻዎችን ይጎብኙ
መርሐግብሩን ማገዝ እና መደገፍ ለምትፈልጉ
በ 09 03 41 12 12 ወይንም በ 0938 60 61 62 ይደዉሉ ወይንም በቴሌግራም ያናግሩን፡፡አሐዱ ባንክ

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

24 Nov, 17:39

ሚናስ የስሙ ትርጓሜ ምን ማለት ነው ?

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

23 Nov, 03:58

ፆም እና አቀባበሉ
https://youtube.com/watch?v=bQSzctYXJs0&si=msdiPMt0hyms-va_

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

21 Nov, 19:14

"ቤተክርስቲያንን አንተዉም"
ከ20 ሺህ ሰው በላይ የሚሳተፍበት
10ኛው ማዕዶት ለኢትዮጵያ
ልዩ ኦርቶዶክሳዊ የኪነጥበብ መርኃግብር
ሕዳር 29 – 2017 ዓ.ም ይደረጋል፡፡
ቦታ ሰዓሊተ ምሕረት ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ በተዘጋጀ ልዩ ቦታ
መግቢያ ዋጋ 200 ብር
ገቢዉ
የደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ለሚያሰራው ህንፃ የሚዉል

አዘጋጅ
ማዕዶት የኪነጥበብ እና መንፈሰዊ ኩነቶች አዘጋጅ ከእውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት ጋር በመተባበር
ከአሁኑ ቀጠሮዎን ያስተካክሉ፡፡
ትኬቱን
ከሕዳር 13 ጀምሮ
በቴሌ ብር
በአሐዱ ባንክ ቅርንጫፎች
- ጊዮርጊስ ምንሊክ አደባባይ ቅርንጫፍ
- አያት አያት ቅርንጫፍ
- ቦሌ ማተሚያ አፍሪካ ጎዳና ቅርንጫፍ
- ሣርቤት አፍሪካ ሕብረት ቅርንጫ አምስት ኪሎ መንበረ ፓትሪያርክ ቅርንጫፍ
- ቦሌ መድኃኔዓለም ቅርንጫፍ
- ፊላሚንጎ መስቀል አደባባይ ቅርንጫፍ
- ማዐድን ሚኒስቴር አጠገብ ሰአሊተ ምሕረት ቅርንጫፍ
- ሰዓሊተ ምህርት ቅርንጫፍ
- ጎሮ ቅርንጫፍ
- 5 ኪሎ ቅርንጫፍ
- አሐዱ ባንክ ጀሞ ቅርንጫፍ
- አሐዱ ባንክ ገርጂ እምፔሪያል

- መገናኛ ቤተልሔም ፕላዛ ካንጋሮ ጫማ
- 6 ኪሎ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን በር ላይ
- 4 ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ 1ኛ ፎቅ hanny mobile
- ልደታ ቤተክርስቲያን ጽናጽል መዝሙር ቤት
- አስኮ ኪያ በርገር
- መርካቶ ራጉኤል ልዳ( ዘአብ) መዝሙር ቤት
- ዑራኤል ቤተክርስቲያን ቤተ መርቆሪዎስ መዝሙር ቤት
- ሳሪስ አርጋኖን ነዋየት ቅድሳት
- ስለዚህ ቦሌ አራብሳ በ 092 048 7968

መርሐግብሩን ማገዝ እና መደገፍ ለምትፈልጉ
በ 09 03 41 12 12 ይደዉሉ በቴሌግራም ያናግሩን፡፡አባንክ#

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

19 Nov, 01:13

"ቤተክርስቲያንን አንተዉም"
ከ20 ሺህ ሰው በላይ የሚሳተፍበት
10ኛው ማዕዶት ለኢትዮጵያ
ልዩ ኦርቶዶክሳዊ የኪነጥበብ መርኃግብር
ሕዳር 29 – 2017 ዓ.ም ይደረጋል፡፡
ቦታ ሰዓሊተ ምሕረት ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ በተዘጋጀ ልዩ ቦታ
መግቢያ ዋጋ 200 ብር

ትኬቱን
ከሕዳር 10 ጀምሮ በቴሌ ብር
በአሐዱ ባንክ በተመረጡ ቅርንጫፎች
እንዲሁም ከዚህ በፊት በሚገኙ ቦታዎች ያገኛሉ

ገቢዉ
የደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ለሚያሰራው ህንፃ የሚዉል

አዘጋጅ
ማዕዶት የኪነጥበብ እና መንፈሰዊ ኩነቶች አዘጋጅ ከእውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት ጋር በመተባበር
ከአሁኑ ቀጠሮዎን ያስተካክሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ
በቴሉግራም https://t.me/maedot1212 እና
በዌብሳይታችን www.etartmedia.com አድራሻዎችን ይጎብኙ
መርሐግብሩን ማገዝ እና መደገፍ ለምትፈልጉ
በ 09 03 41 12 12 ወይንም በ 0938 60 61 62 ይደዉሉ ወይንም በቴሌግራም ያናግሩን፡፡

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

17 Nov, 06:31

እናመሰግናለን
መልካም ሰንበት ይሁንለችሁ

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

25 Oct, 09:44

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
                 #መብሪተ_ጥበብ

እውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ከሥነ ጥበብ ክፍል ጋር በመቀናጀት መሠረታዊ #የድርሰት_አጻጻፍ ላይ ልዩ ሥልጠና ያዘጋጀን ሲሆን ስልጠናውን ለመሳተፍ የምትሹ ወንድምና እህቶች ምስሉ በተቀመጠው ስልክ ቁጥሮች ይመዝገቡ

#እውቀት_ብርሃን_ሰንበት_ት_ቤት

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

24 Oct, 16:24

ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ሁለገብ ህንጻ ብሎኬት በአባላት ሲወርድ

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

24 Oct, 06:33

የጥቅምት ፲፯ ማኀሌተ ጽጌ ፣ ወረብ ፣ ዚቅ እና መዝሙር

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

24 Oct, 05:56

ለብሎኬት መግዣ የተለገሰ ብር እናመሰግናለን እመብርሃን ትስጥልን

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

23 Oct, 18:09

ከአንድ ወላጅ ለብሎኬት መግዣ የተለገሰ እናመሰግናለን እመብርሃን ትስጥልን ።

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

23 Oct, 16:45

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ሰላም እንዴት ናችሁ፤ ነገ በ 14/02/2017 ዓ.ም በአንድ ወላጅ አማካኝነት የተገዛ 3000 ብሎኬት ስለሚወርድ የምንችል ወንድምና እህቶች ከ 10:30 ጀምሮ የሰንበት ት/ቤቱ ሕንፃ ጋር በመገኘት እንድናወርድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

" ዛሬ ካልሆነ መቼም
እኛ ካልሰራን ማንም "

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

23 Oct, 06:21

ለሀ/ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኅነት ሰንበት ትምህርት ቤት
እንኳን ለ56ኛ ዓመት የሰንበት ትምህርት ቤታችሁ የምስረታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

የእውቀት ብርሀን ሰንበት ትምህርት ቤት

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

23 Oct, 03:21

"ሕዝቡም ሊያደምጠንና ሊከተለን የሚችለው መስለን ሳይሆን ሆነን ስንገኝለት ነው"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

21 Oct, 23:08

ለሰበታ ጌቴሴማኒ የበኩላችንን እንወጣ

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

21 Oct, 16:32

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘአትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት;  ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ' የባሕርዳና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎችና አስተዳዳሪዎች ካህናት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው በነገው ዕለት በቅዱስናቸው የመክፈቻ ንግግር የሚጀምር ይሆናል፡፡
©eotc tv

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

20 Oct, 17:13

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች!
መብሪተ ጥበብ ልዩ ሥልጠና
እውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ትምህርትናሥልጠና ክፍል ከስነ ጥበብ ክፍል ጋር በመቀናጀት መሰረታዊ የድርሰት አጻጻፍ ላይ ልዩ ሥልጠና ያዘጋጀን ሲሆን ስልጠናውን ለመሳተፍ የምትሹ ወንድምና እህቶች
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ከጥቅምት 9 -16  2017 ዓ.ም በመደወል መመዝገብ ይቻላል
        በ0938035698፣0910430603፤0939665587
             ሥልጠናው ከጥቅምት 19 ጀምሮ  ለተከታታይ አራት ሳምንታት ዘወትር ማክሰኞ  የሚሰጥ ይሆናል  ፡
              ⏱️ሰዓት :- 11:50 - 1:30
              ⛪️ ቦታ :- ሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ
አዘጋጅ :- የደ/ም/ሰዓሊተ ምሕረት/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት ሥልጠና ንዑስ ክፍል ከ ከስነ ጥበብ ክፍል ጋር በመተባበር
ማሳሰቢያ
👉 በሰዓቱ ተገኙልን!
#እውቀት_ብርሃን_ሰንበት_ት_ቤት

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

19 Oct, 03:32

ማኅሌተ ጽጌ ፫ኛ ሳምንት

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

18 Oct, 18:05

11. ሙስና፣ ዘረኝነት፣ ጎሠኝነት፣ ቡድነኝነት፣ አድሎአዊነትና ግለኝት በተመለከተ በጋራ በአንድ ድምጽ በመነሣት ይኽንን ክብረ ነክና አጋላጭ፣ ለቤተ ክርስቲያን እድገትና ለሐዋርያዊ ተልእኮ እንቅፋት፣ የቤተ ክርስቲያን ማንነት ለሌላቸው ግለሰቦች መደበቂያ፣ በጥቂት ግለሰቦች በደልና ጥፋት በንጽሕና በቅድስና የሚያገለግሉ፣ ካህናትንና ሠራተኞችን የሚያሳፍሩ፣ ምእመናንን የሚያሸማቅቁ በመሆናቸው እነዚህን ክፉ ደዌያት ስም አጠራራቸውን ከቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለማስወገድ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በጥናትና በቁርጠኝነት ላይ የተመሠረተ፣ የጥፋት በራቸውን በዘላቂነት የሚዘጋ ሥልት እንዲቀይስ ጉባኤው ያሳስባል

12. በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት እስከ አሁን ቤተ ክርስቲያን በፈረሱባት ሕንፃዎችና ቤቶች ምትክ ቦታ በመስጠት ጉዳቷን ለመቀነሰ የተደረገውን ጥረት ጉባኤው እያደነቀ፤ በተሰጡት ይዞታዎች ላይ በአጭር ጊዜ ግንባታውን በማካሄድ የአባቶችቻንን አሻራ መልሶ በመትከል፣ ይዞታውን ማስከበርና የተቋረጠውን ገቢ ማስቀጠል እንዲቻል ብርቱ ጥረት እንዲደረግ ጉባኤው እያሳሰበ፤ የኮሪደር ልማት የተባለው ጉዳይ በሌሎች የክልል ከተሞችም እየተስፋፋ ስለሆነ በቀጣይ ለሚነሡ የይዞታ ጥያቄዎች ለሚከሰቱ ችግሮች ከወዲሁ ዝግጅት እንዲደረግ፣

13. አዳዲስ አማኞችን አሳምኖ ለሥላሴ ልጅነት ማብቃት፣ የአዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት መተከል፣ መታነፅና መባረክ የታየው ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ እመርታ ሁሉን ያስደሰተ በመሆኑ ከዚህ በበለጠ አጠናክረን ለመሥራት ቃል እንገባን፤ 

14. የቅዱስ ባኮስ የቅድስና ዕውቀና ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ስትዘግበው የቆየ ቢሆንም ጽላት ተቀርፆ እንዲከበር መደረጉ አስደሳች ሲሆን ለሀገር በረከት፣ ለትውልድ የመንፈሳዊ ሕይወት አርአያ፣ ለቅድስና ፍኖት የሆኑ ነገርግን የማይታወቁ የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ቅዱሳን ታሪክና ገድል በማጥናት እንዲዘከሩ እንዲደረግ ጉባኤው ያሳስባል፡

15. በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የተከፈቱ መንፈሳውያን ኮሌጆችና የካህናት ማሰልጠኛዎችም በአጥጋቢ ሁኔታ ሥራ መጀመራቸው፣ በዚህ ዘርፍ በእጥፍ እየጨመረ የመጣው ዕድገትና ውጤት ጉባኤው ያደነቀ ሲሆን ወደ ሥራ ለመግባት በሂደት ላይ ያሉት በርካታ መንፈሳዊ ኮሌጆች እየተስሳፉ ያሉ የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ ዘመናዊ የትምህርት ተቋማት በአጠቃላይ ሁሉም ትምህርትን የሚመለከት ጉዳይ በትምህርት ኮሚሽን ተቋቁሞ ጥናት በማድረግ እንዲስፋፉ ጉባኤው ያሳስባል፤

16. በሰላም መታጣትና በቀኖና ጥሰት ምክንያት መላው ወለጋ አህጉረ ስብከት ለበርታ ወራት ከማእከሉ ጋር ያለው ግንኙነት ተቋርጦ ከቆየ በኋላ በቅርቡ በሀገረ ሰብከቱ ሊቀ ጳጳስ ወደ መዋቅር መመለሳቸው ጉባኤውን በእጅጉ አስደስቷል፤ ስለሆነም ቀሪ ሥራዎች ተጠናቀው የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እንዲጠበቅ፣ በሌሎችም አካባቢዎች ለተፈጠሩት የመዋቅር ጥሰቶች ቀኖናዊ መፍትሔ እንዲበጅለት ጉባኤ ያሳስባል፡፡

17. ሐዋርያዊትና የክርስቶስ አገልጋይ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ቋንቋን በማክበር ታገለግልበታለች እንጅ በቋንቋም አትገደብም፤ ስለዚህ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ሐዋርያዊ ተልእኮ መፈጸሟ እንደተጠበቀ ሆኖ ለወደፊት የሁሉም መዓርገ ክህነት ሢመት፣ በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር ሥራ የኃላፊነት ምደባዎች፣ መሠረት እምነትን፣ ቀኖና ቤተክርስቲያንን፣ ዕውቀትና ሙያዊ ብቃትን ብቻ መሠረት ያደረገ ይሆን ዘንድ ጉባኤው በጥብቅ ያሳስባል፤   

18. ሰበካ ጉባኤን ማጠናከር፣ ሰንበት ትምህርት ቤትን ማደራጀት፣ አብነት ትምህርት ቤቶች ማጎልበትና ማስፋፋት፣ ሕጎችና ደንቦችን በማዘጋጀት የተደረገውን ጥረት የሚያስመሰግን ሆኖ አሁን ወቅቱን የጠበቁ ሕጎችና ደንቦችን በማውጣት ሁሉም እንዲሠራበት ማድረግን፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣ የራስ አገዝ ልማትን ማሳደግና በገቢ ራስን መቻል፣ በጸደቀው የዐሥር ዓመቱ መሪ ዕቅድ መሥራት የቤተ ክርስቲያናችን ዓይነተኛ ተልእኮ በመሆኑ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ለመፈጸም ቃል እንገባለን፡፡

19. የቤተ ክርስቲያናችን የውጭ ሀገር አገልግሎት እየሰፋና እያደገ መምጣቱ በጉልህ የሚታይ ሲሆን ይኽ እድገትና አደረጃጀት እንዲጠናከር፤ በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ተሳትፎ የበለጠ እንዲያድግ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ ጉባኤው ያሳስባል፤

20. ከውይይትና ከብፁዓን አበው መልእክቶች እንደተሰጠው መመሪያ የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና ለመመለስ፣ ለሀገራንችን ሰላምና ደኅንነት ለሰው ልጆች ሁሉ መልካም ግንኙነት የጋራ ጸሎት በኅብረት ይደረግ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ እንዲሰጥበት ጉባኤ በአክብሮት ይጠይቃል፤  

በመጨረሻም እስከ ዛሬ ስንሰበሰብበት ከነበረው መቃረቢያ አዳራሽ ወጥተን ይኽ ዛሬ የተገኘንበት አዳራሽ በአጭር ጊዜ አሁን ባለበት ደረጃ እንዲህ ጸድቶና ተውቦ የ43ኛውን አጠቃላይ ጉበኤ እንዲከናወንበት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አመራር መስጠታቸው ቁርጠኝነት ካለ ብዙ መሥራት እንደሚቻል ያሳየ፣ የሥራ ክትትልና አፈጻጸም አድናቆታችንን በመግለጽ ሐዋርያው እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖርና እንዳለው የአዳራሹ ቀሪው ሥራ ተጠናቆ በቅርቡ እንደሚመረቅ ተስፋችንን እንገልጻለን፤

ይሕ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲፈጸም ያደረጉ በቅዱስነታቸው አባታዊ ርእሰ መንበርነት፣ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በሳልና የተረጋጋ አመራር ሁሉም መርሐ ግብሮች በተያዘላቸው ሰዓትና ጊዜ ተጠናቀው እንዲፈጸሉ የመሩንን አባቶች በረከታችሁ ይድረሰን እያልን፤

የጉባአው ዋና አዘጋጅ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊና መላው ሠራተኞች፣ ሁሉም ተባባሪ አካላት በገንዘብም በጉልበትም ትብብር ያደረጉ ሁሉ በአጠቃላይ ጉባኤው አመስግኗል፡፡ 

ከሁሉም በላይ ለዚህ ለ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ ያደረሰንና ያስፈጸመን የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአሔር ምስጋና ይግባው አሜን ሎቱ ስብሐት ወባርኰት ወጥበብ፣ ወአኰቴት፣ ወኃይል ወጽንዕ ለአምላክነ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

18 Oct, 18:05

የአቋም መግለጫ፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ የአቋም መግለጫ

“ትውልደ ትውልድ ይንእዱ ምግባሪከ ወይዜንዉ ኃይለከ - የልጅ ልጅ ሥራህን ይናገራሉ፤ ያመሰግናሉ፣ ከሃሊነትህን ይናገራሉ ያስተምራሉ” መዝ 144 ቁ 4

ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት፣ ዓለምአቀፋዊት የሆነቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያዊ ተልዕኮዋ ረጅም ዘመናትን ሰማያዊውን ጥበብንና ምድራዊውን ዕውቀትን በማስተማር፣ የሀገርና የወገንን እምነትና ፍቅር ምንነት ከተግባር ጋር፣ ሰላምና አንድነትና በማስፈን፣ ለሰው ልጅ ዘለዓለማዊ ድኅነት ሌሌት ከቀን ያለማቋረጥ ሰዓት ሳይገድባት፣ መልክዓ ምድር ሳይገድት፣ የሰው ባህልና ቋንቋ ሳይወስኗት፣ ትውልድን፣ ከትውልድ፣ ዘመንን ከዘመን፣ ሰማያውያን ከምድራውያን፣ ፍጡራንን ከፈጣሪ ስታገናኝ ኖራለች፡፡ ለሰው ዘር ጥበብን፣ ለትወልድ ታሪክና ትውፊትን፣ ስትቀምር፣ ነፃነትና ሰብዓዊ ክብርን በዐውደ ምኅረቷ ስታውጅ፣ በአባቶችና በሊቃውንት በሕየወት ሰሌዳ፣ በደመቀ ቀለም በቃልም በመጽሐፍም ስታስተጋባ እስከ አሁን አለች ወደፊትም ትኖራለች፡፡

ከዚህ መሠረታዊ የታሪክ ዕሴት በመነሣት ለዛሬው 43ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ደርሰናል፡፡

በዚሁ ጉባኤው በቆየባቸው ቀናት ውስጥ የቅዱስነታቸውንና የብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ አባታዊ መልእክቶች፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሪፖርት፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር አህጉረ ሰብከት ዘገባዎች፣ ከውይይት ሐሳቦች፣ ከአበው ሊቃነ ጳጳሳት መልእክቶች፣ ከቡድን ውይይትና ዘገባ በመነሣት ከቃለ ጉባኤ ሐሳብ በተጨማሪ በቅዱስ ሲኖዶስ ትኩረት ተሰጥቶባቸው በአጀንዳ ተቀርጸው ውይይትና ምክክር ተደርጎባቸው ውሳኔና መመሪያ ይደረግባቸው ዘንድ እኛም ለተፈጻሚነቱ የራሳችንን ድርሻ መወጣት እንድንችል ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የአቋም መግለጫ አቅርበናል፤

1. በጉባኤው መክፈቻ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ያስተላለፉፉልንን ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተቀብሎታል፣ ለተግባራዊነቱ ቃል ይገባል 

2. ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፉልንን አባታዊ መልእክት ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ ቃል እንገባለን፤

3. በብዙ የሀገራችን ክፍል ባለው የሰላም እጦት የተፈጠሩት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንያት የካህናት፣ የመነኰሳትና የምእመናን ሞትና ስደት በጥብቅ እያወገዝን በዚህ ታሪክ የማይረሳው በምድር ወንጀል፣ በመንፈሳዊው ዓለምና በሰማይ ኃጢአት የሆነ እኩይ ተግባር የተሰማራችሁ ሁሉ ወደ ርኃራኄ ልብ እንድተመለሱ ጉባኤው በአጽንዖት ጥሪውን ያስተላልፋል፤ 

4. የሰላም ዕጦት ጉዳይ ምንም እንኳ ዓለም አቀፍ ቢሆንም ሀገራችንም በተከሰተው ግጭትና ጦርነት ምክንያት ሰላም ካጣች ሰንብታለች፣ ስለሆነም ቅዱስ ሲኖዶስ በዓለም የሚደነቅ፣ ለሀገር ተገን የሚሆን አስደነቂ ውሳኔ እንደሚወስን ተስፋች ጽኑ ነው፣ ጸሎታችንም ነው፤ የአገልጋዮች እንባ የሚታበስበት፣ ለነገ ታሪክ የትውልድ ተወቃሽ ከመሆን ይልቅ፤ የሰላምና እርቅ ምሳሌ የምንሆንበት ከፍተኛ የሰላም ሥራ ልዩ የሆነ የሰላም ኮሚቴ ተቋቁሞ ዘላቂ ሰላምን ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን የሚያመጣ ሥራ እንዲሠራ ጉባኤው ያሳስባል፤

5. የዚህን ዓለም ተድላ ንቀው፣ ደዋ ለብሰው ጤዛ ልሰው በገዳም ተወስነው ድምጸ አራዊቱን ግርማ ሌሊቱን ታግሰው ለመላው የሰው ዘር የሚጸልዩ ይህን ይደግፋሉ ያንን ይቃወማሉ የማይባሉ ገዳማውያን መነኮሳት ከየበአታቸው ተጎትተው ወጥተው የተገደሉበት ሁኔታ በሀገራችን መከሰቱ ጉባኤውን እጅግ አሳዝኖታል ይኽ ጉዳይ ቀጣይነቱ እየታየ ስለሆነ የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን የሕግ ሥራ በመሥራት የሰው ልጅ ከአምላክ የተሰጠውን የመኖር መብት፣ የእምነት ነፃነት፣ የመዘዋር ተፈጥሯዊና ሰብዓዊ መብት በሀገራች እንዲከበር ያሳስባል፤ 

6. በታሪካችን ያላየነው ከአባቶቻችን ያልሰማነው በመጻሕፍት ያላነበብነው ከኢትዮጵያ ባህልና ሥነ ልቡና ውጪ በሆነ መንገድ ሰዎችን ለገንዘብ ሲባል ማገት በተለይም ፊትና ኋላ ግራና ቀኝ እሳትና ውኃ ያለዩ ሕፃናት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው፣ ወጣቶችና አረጋውያን ሳይቀር እያተገቱ የሚሰቃዩበትና የሚደፈሩበት ሁኔታ የገጠመንን ፈተና ክብደቱን የሚያሳይ መሆኑ ይኽ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መፍትሔ እንዲበጅለት ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፤

7. ጥላቻና የጥፋት ቅስቀሳዎች፣ በዜጎች መካከል አለመተማመንና መለያየት፣ ለሀገር አንድነትና የሕዝብ አብሮነት ጠንቅ፣ ለወደፊቱ አስጊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች የበዙበት፣ የትውልዱ የወደፊት በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ የመኖር ዋስትና እየጠፋ፣ በርካታ ወጣቶች በስደትና በመፈናቀል ላይ ያሉበት ሁኔታ በመኖሩ የጥላች ንግግር፣ ዘለፋና ያልተገባ ትችትና መናናቅ ማንንም የማያንጽ ክፉ ትምህርት፣ ለሀገርም፣ ለሕዝብም የማይጠቅም ሁሉንም የሚያጠፋ ስለሆነ በእንዲህ ያለ ተግባር መገናኛ ብዙኀን በመጠቀም የተሰማራችሁ፣ ሁሉ በሚያፋቅርና በሚያዋድድ ተግባር እንድትሰማሩ ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፣ ቅዱስ ሲኖዶስም ለዚሁ ትኩረት ሰጥቶ መመሪያና ውሳኔ ያወጣ ዘንድ አጽንዖት እንጠይቃለን፤    

8. በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 20 በእንተ ሰማዕታት የጌታችንን ትምህርት መሠረት በማድረግ በተሠራው ቀኖና ካህናትና ምእመናን ሰማእትነትን የተቀበሉበትን ቀን መዘከርና ማክበር፣ የከበረ አጽማቸውን በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን በክብር ማስቀመጥ፣ ቤተሰቦቻቸውንና በእነሱ ሥራ ይተዳደሩ የነበሩ የሰማእታት ቤተሰብ በሚል መርዳት የተደነገገ ቀኖና ነው፤ ይኽን በማድረግ የሰማእትነት ዋጋን እናገኛለን፣ ቤተ ክርስቲያነን እናጸናለን፤ በዚህ ቀኖና መሠረትና ከሰብዓዊ ርኅራሄ በመነሣት በሰማዕትነት የተለዩን ወገኖች መታሰቢያቸው እንዲደረግ፣ ቤተሰቦቻቸውና ጉዳተኞችን ወላጆቻውን ያጡ የካህነትና የምእመንና ጨቅላ ሕፃናትና ያልደረሱ ልጆች፣ ያለጧሪ የቀሩ አረጋውያን የቤተ ክርስቲያንን እንክብካቤ በጥብቅ ይፈልጋሉ፤ ለዚህ መፍትሔ እንዲሆን በውጭና በሀገር ውስጥ ያሉ አህጉረ ሰብከት ያካተተ አስቸኳይ ዓለም አቀፍ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጥበት እያሳሰብን ለተግባራዊነቱም ሁላችንም ቃል እንገባለን፣

9. በአንዳንድ አካባቢዎች ሕግንና የአምልኮ ነፃነት ሰብዓዊ መብትን በመጣስ የመስቀል ደመራና የባሕረ ጥምቀት ቦታ መወሰድ ሃይማኖታዊ አለባበስና መስቀል መያዝን በመከልከል የአንገት ማዕተብን መበጠስ፣ በኦርቶዶክሳውያን ላይ እንግልትና ወከባ መፍጠር አሳዛኝ በመሆኑ ድገርጊቱን አጥብቀን እየተቃወመን በቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ውይይት እንዲደረግበት ጉባኤው ያሳስባል፤ 

10. ቤተ ክርስቲያን እንኳንስ ተናግራ ሰማች ሲባል የሚያስደነግጥ ግርማና መታፈር፣ መከበርና መወደድ የነበራት በመሠረተችው ሀገር የምትሳደድበት፣ የመሪዎቿ አባቶች ጥሪ የማይከበርበት፣ የሰላም ጥሪ ድምጽዋ የማይሰመባት፣ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በመፈተሸ ክብርና ልዕልናዋ እንዲመለስ በቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ውይይትና ጥልቅ ምክክር እንዲደረግ መፍትሔም እንዲፈለግለት ጉባኤ ያሳስባል፤

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

17 Oct, 17:47

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

"እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት" 1ኛ ጴጥ 5፥7

የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለተፈተናችሁ በሙሉ!

    በ2016 ዓ.ም የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ተፈታኝ  የነበራችሁ ወንድም እኀቶች  ዓርብ 08/02/2017 ዓ.ም 11፡30 ላይ  ልዩ  መርኃ ግብር ስለተዘጋጀ በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ እንድትገኙ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪችንን እናስተላልፋለን፡፡

ትኩረት፡ ያገኛችሁት ውጤት ከፍተኛ ፤ ሪሚድያል ፤ ዝቅተኛም ቢሆን  ከእናንተ የሚጠበቅ በሰዓቱ መገኘት ብቻ ነው፡፡

ወንድም እኀት ወዳጆቻችሁንና ጓደኛዎን ይጋብዙ!!

ለበለጠ መረጃ :-    0919-94-05-38 0923-52-27-34 0921-14-57-07

የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ቤተክርስቲያን
እውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት 

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

16 Oct, 03:19

የሰንበት ትምህርት ቤታችን ህነጻ ለመጀመሪያ ወለል የተሰራ ስራ እና ወጪ

☞የወለሉ ጠቅላላ ስፋት = 830 ካሬ

☞ እንጨት = 460 ሺ (በድጋሚ መጠቀም የሚቻል )
☞ፕለይ ውድ = 810 ሺ (በድጋሚ መጠቀም የሚቻል )
☞ብረት = 3.2 ሚልየን ብር በላይ
☞የብረት ሰራተኛ = 90 ሺ
☞የአናጺ ሰራተኛ = 147 ሺ
☞የኤሌክትሪክ ሰራተኛ = 10 ሺ በላይ
☞የተለያዩ ወጪዎች = 50 ሺ ብር በላይ
☞ጠቅላላ ሙሌቱ የፈጀው = 178 ሜ^3 (በ23 ሚክሰር ትራክ)
☞ለአርማታ ሙሌት ብቻ ከ 2.3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት
☞ለመሙላት የፈጀው ጊዜ ከምሽት 2:44 - 10 : 09

ጠቅላላ ወጪ ለስላብ ስራ= ከ7.1 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

15 Oct, 04:59

ለመላው የሰንበት ት/ቤታችን ዓባላትና ወላጆች በሙሉ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የመጀመርያውን ሕንጻ ወለል ለመሙላት ተችላል እንኳን ደስ አላችሁ የጀመርነውን ለመፈጸም ያብቃን። በዚ አገልግሎት የምትደክሙ ሁላችው ይበልጥ ለሊቱን ስትሰሩ ያደራችሁ የቤተክርስቲያን አምላክ ዋጋችሁን አይንሳችሁ። የድንግል ምልጃ  አይለየን።

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

15 Oct, 01:53

የሰንበት ትምህርት ቤታችን ሁለገብ ህንጻ ወለል የመጀመሪያ ሙሌት ከምሽቱ 02:44 ሰዓት ተጀምሮ ከለሊቱ 10:09 ሰዓት ተጠናቋል። ስለሁሉም ነገር የእግዚብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን። ቀን፦
ጥቅምት ፬ /፳፻፲፯ ዓ·ም
" ዛሬ ካልሆነ መቼም
እኛ ካልሰራን ማንም "

2,907

subscribers

4,054

photos

63

videos