አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ @abukelemsismedia Channel on Telegram

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

@abukelemsismedia


አቡቀለምሲስ ማለት ረአየ ኅቡኣት አበ ራዕይ አበ ትንቢት ማለት ሲሆን የተሰወረውን የተደበቀውን የተከደነውን የሚገልጥ ማለት ነው። መሠራታዊ ዓለማው በሀገረ ስብከታችን ብሎም በመላ ቤተ ክርስቲያናችን የተሰወሩ ገዳማትን የተደበቁ ሊቃውንትን የተከደኑ ታሪኮችን የተሸሸጉ ቅርሶችን ማውጣት እና የተንሸዋረረ ታሪክ ማስተካከልና የጎበጠውን አዲሱን ትውልድ ማነጽ ነው

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ (Amharic)

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ትምህርት ለመከላከል እና ለማስተካከል ያለው መሠረት ነው። በተለያዩ ለእናትዎ ለልጆችዎ ለእናቶችዎ ለሜሴንጀሊክ ላልሞድላቸው የሚያሳይ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገርና ሥርጭት ሰለፈና ሰለፍና ትምህርት ሰጪና አስማላን ተይዞሃል ብለን በአስፈላጊ ቁልፉ መግባት የሚችል የሥርጭት መረጃን ማክኮል ካለውና በአስፈላጊ የሚጠብቁ የሠላሜ ነው። ከዚህ በኋላ ካለው ጠቃሚ ብሶች ከአባልነት እንደ ተነሳስሁ ሕዝብ ቤተሰብ በማድረግ ሃሳብን ለማስተላለፊያና እንለዋዘውም ተበታት።

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

01 Feb, 18:05


https://youtu.be/ks5L13UVe2M?si=McteK3GqR59Mi6Rs

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

01 Feb, 18:03


https://youtu.be/7PEfQpUmFlo?si=4xT1i-qtz049rIgi

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

20 Jan, 18:14


የቃና ዘገሊላ በዓል በደብረ ብርሃን አንሳስ መንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከበረ።

ጥር ፲፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም(አቡቀለምሲስ ሚዲያ: ደብረ ብርሃን)

+++++++++++++++++

የቃና ዘገሊላ በዓል በደብረ ብርሃን አንሳስ መንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በታላቅ ድምቀት የተከበረ ሲሆን ታቦተ ሕጉ ከባሕረ ጥምቀቱ በካህናት አባቶች፣ በሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን እንዲሁም እጅግ በርካታ ቁጥር ባላቸው ምእመናን በዝማሬ እና በእልልታ ታጅቦ ወደ መንበረ ክብሩ ገብቷል።

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

19 Jan, 05:37


https://youtu.be/MwKerzDLn9Y?si=VoEqyFgmw1ioU6lM

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

11 Jan, 12:02


https://youtu.be/fG86ZQYXRYQ?si=W9EIe7NQ_jiPYPTy

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

11 Jan, 07:35


https://youtu.be/yNlYuRem4pU?si=5gdXUiHp9PWfJ_ib

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

11 Jan, 07:34


https://youtu.be/cofnmXsysOM?si=jYBWkm3v-LmcaYgF

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

06 Jan, 10:06


"በጠብና በመለያየት የቆለፍነውን የሰላምና የአንድነት በር ከፍተን ለፍቅርና ለሰላም መሥራት አለብን"

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል አስመልክተው ለመላው ምእመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል አስመልክተው ለመላው ምእመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ብፁዕነታቸው ያስተላለፉት ሙሉ መልእክት እነሆ!!!!
++++ ++++ ++++ ++++ ++++ +++++

ወናሁ እዜንወክሙ ዐቢየ ዜና ፍሥሐ ዘይከውን ለክሙ ወለኩሉ ዓለም” ለእናንተና ለዓለሙ ሁሉ የሚኾን ታለቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁ፡፡ (ሉቃስ 2÷14)

በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ በሌላው ዓለም የምትገኙ የክርስቶስ ቤተሰቦች ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያት ፣ ሁሉን ማድረግ የሚቻለው ልዑል አምላካችን እንኳን ለ2017 ዓ.ም ለዘመነ ማቴዎስ ብርሃነ ልደቱ በሰላምና በጤና ጠብቆ አደረሳችሁ፡፡

“ዛሬ በዳዊት ሀገር (አገር) መድኅን ተወልዶላችኋልና” ይኸውም ቡሩክ አምላክ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህን ቃል የሰሙት ከዛሬ 2017 ዓመታት በፊት በቤተልሔም አካባቢ በዛሬይቱ የልደት ሌሊት ተግተው መንጋዎቻቸውን ይጠብቁ የነበሩ እረኞች ናቸው፡፡

ቃሉንም የሰሙት በአጋጣሚ አልነበረም እነሱን መሰል የሆነ አዲስ ነገር ወደ ዓለም እንደሚመጣ አስቀድሞ ትንቢት ተነግሮ ምሳሌ ተመስሎ ነበር፡፡

“ትጉሕ እረኛ ይመጣል” በጐችንም በክንዱ ይጠብቃል ዋጋው ከእርሱ ጋር ነው፡፡ ሥራውም በፊቱ ተብሎ “የ፳ኤል እረኛቸው ሆይ አድምጥ” ተብሎ የተነገረለት እርሱ ቸር ጠባቂ ከእረኞች መካከል ተገኘ፡፡ ለምን? ቢባል በቸር ጠባቂነቱ መንጋዎቹን ለመጠበቅ ለመቤዥት ነው፡፡

ለመንጋዎቹም ሆነ ለእረኞች የተወለደላቸው ይህ መድኅን ክርስቶስ ነው፡፡ ወደ እረኞችም የተላከው መልእክተኛ ከዚህ በፊት ወደ ልዩ ልዩ ስፍራ ተልኳል፡፡ ነገር ግን መልእክቱ ለአንድ ሰው ለአንድ ቤተሰብ ለአንድ አገር ነበር፡፡ ዛሬ የተላከው ወደ ብዙዎች ሰዎች ወደ ብዙ ቤተሰቦች ወደ መላው ዓለም ነው፡፡

አነጋገሩም እንደቀድሞ መልእክቱ አነጋገር ሳይኾን “ለእናንተና ለመላው ዓለም የሚኾን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋላሁ” “ዛሬ በዳዊት አገር መድኅን ተወልዶላችኋል” ይኸውም ቡሩክ አምላክ ክርስቶስ ነው” ይላል፡፡

የምስራቹም ለመላው ዓለም ቢኾንም ሰምተው የሚናገሩት (የሚያሰሙት) እነርሱ ናቸውና ነው፡፡ “እነሆ እግዚአብሔር ምልክት ይሰጣችኋል” ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች፡፡ (ኢ.7÷14) ተብሎ የተነገረ ስለኾነ በዳዊት ከተማ መድኅን ተወልዶላችኋል አለ መድኅን ያለውም “ዝውእቱ እግዚእ ቡሩክ” ይኸውም ቡሩክ አምላክ ክርስቶስ ነው ብሎ ተርጉሟል፡፡

ወደ ቤተልሔም ሒዱ ሕፃን በበረት ተኝቶ በጨርቅ ተጠቅልሎ አውራ ጣቱን ታሥሮ ታገኛላችሁ ብሎአቸዋል፤ ድንግል በድንግልና የወለደችው በክንዷ የታቀፈችው በበረት ያስተኛችሁ እርሱ በሰማይ በመላእክት በምድር በሰው ልጆች ምስጋና የሚቀርብለት አምላክ መሆኑን አስረዳቸው፡፡

ከሰማየ ሰማያት መውረዱ ከድንግል ማርያም መወለዱ (ሰው መኾኑ) የትሕትና ሥራ መሥራቱ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እንዲሁም በሰዎችና በሰዎች መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ በምትኩ ሰላምን ለሰው ልጆች ፍቅሩንም ለሰው ልጆች ሁሉ ለመግለጽ ነው፡፡

በሰማይ ከመላእክት ምስጋና የሚቀርብለት አምላክ በሠራው የትሕትና ሥራ ፍቅሩ ሰው እንደኾነ ነገራቸው፡፡ ስለ ሕፃኑ መልአኩ ለእረኞች በሰጠው መልእክት “ለእናንተና ለመላው ዓለም ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁ ”ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ የሰላሙ ንጉሥ የሰላሙ አለቃ የሰላሙ አምላክ ነው፡፡

ልደቱም የሰላም ቀን ነው በልደቱ ለእኛ ለሰው ልጆች ሰላሙን ሰጥቷል፡፡ ሰላሙን መሥርቷል፤ ምክንያቱም በዚህ ዕለት መላእክትና የሰው ልጆች በአንድነት ሆነው “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ” በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም እርቅ ሆነ” (ሉቃ.2÷14) በማለት ዘምረዋል የጥበብ ሰዎች ገብረዋል፡፡ እረኞችም ሰግደዋል ማለት ነው፡፡

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት!!!

ሰላምን ፍጥረት ሁሉ የሚሻው የሚመኘው ነው፡፡ ሰላም ሊገኝ የሚችልበትም ምክንያትም አለው ይኸውም ሰው የሆነ ሁሉ ሰው መኾኑን ማሰብ ሲችል ነው፡፡

አንድ ሰው ሰው መሆኑን ማሰብ ከቻለ ለእርሱ ሊደረግለት ወይም ሊኾንለት የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ለሌላው ወንድሙ ወይም ለሌላይቱ እህቱ መሆን መደረግ እንዳአለበት ሊገነዘብ ይችላል ማለት ለሰላም ለፍቅር ለአንድነት ለመተሳሰብ ለርህራሄ ስፍራ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

ከጥል ሰላምን ከመለያየት አንድነትን ከጭካኔ ርህራሄን ከመራራቅ መቀራረብን ከችኮላ በትዕግሥት ማሰብን ይጠይቃል፡፡በአጠቃላይ ፍቅረ ቢጽ፣ ፍቅረ ሀገር፣ ፍቅረ አምላክ ናቸው፡፡

እነዚህ ነገሮች የሌሉት ማንኛውም የሰው ልጅ በዚህ በሚኖርበት ምድራዊ ዓለም ኋላም በሌላው በሚመጣው ዓለም ዋጋ ሊያገኝ አይችልም፡፡ የሰው ልጅ በዚህ ዓለም የሚዘራው ዘር የሚያቀርበው ምርት የሚያተርፈው ሀብት ሰላም ብቻ ነው፡፡

እግዚአብሔር ወልድ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ሰው ሆኖ ሥጋ ለብሶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሲወለድ የጥል ግድግዳ ተደምስሷል ፣ፈርሷል ፣ ሰላም ነግሧል ፍቅር አንድነት ተገልጧል፡፡ በመኾኑም የሰማይ መላእክት በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና በምድር ሰላምም ለሰው ልጆችም ብለው አመስግነዋል፡፡

እውነት ነው ከዚያ በፊት ተያይተው አያውቁ የነበሩ ሰዎችና ሰዎች፣ ሰዎችና መላእክት የተወለደውን የሰላሙን ንጉሥ ዜና ቃል ለቃል ተወያዩ፡፡

የምስራቅ ሰዎችም ተስፋ ልደቱን ለማየት በኮከብ እየተመሩ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ገቡ፡፡ አመጣጣቸውም እንደቀድሞው ቤተ መቅደስን ለማፍረስ ሀገሪቱን ለመደምሰስ ሀብቱን ለመዘርፍ አልነበረም፡፡

መንገዳቸው (ጉዞአቸው) የተወለደውን የሰላሙን ንጉሥ ለማየት ብቻ ነበር፡፡ እንደተመኙትም ቤተልሔም ደረሱ የፈለጉትን የተመኙትንም አገኙ፡፡ ከፈረስ ከሠረገላ ወርደው ለሰላሙ ባለቤት ለሰላሙ አምላክ ሰገዱ ሣጥኖቻቸውን ከፍተው ኮረጆቻቸውን ፈትተው ወርቅ ዕጣን፣ ከርቤ ገበሩለት፡፡

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያት!!!!

በዕለተ ልደቱ በኮከብ የተመሩትም በመልአኩ ቃል የተጠሩትም አንድ ሆነው በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰው ልጆች ብለው የዘመሩት ቃል መላውን የሰው ልጆች የሚያስተባብር የሰላም የአንድነት የፍቅር ቃል ነው፡፡

እርሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ሲያስተምር በነበረበት ጊዜ “ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ሰላሜንም እተውላችኋለሁ” "እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ሰላም አይደለም” (ዮሐ.14÷27-28) በማለት ተናግሯል፡፡

ዛሬ የዓለም ሁኔታ ከተሰጠው አምላካዊ ስጦታ ከኾነው ከፍቅር ፣ ከአንድት ፣ ከሰላም፣ ከመግባባት ከመተሳሰብ ወጥቶ ከሰላም፣ ከፍቅር መንገድ አፈንግጦ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትን፣ የትዕግሥት በርን አጠንክሮ በመዝጋት፡፡

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

06 Jan, 10:06


የሁከት ፣ የብጥብጥ፣ የጦርነት፣ የግጭት፣ ረሃብ እርዛት፣ የሰው ልጆች ፣ እንግልት በአጠቃላይ በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ ችግሮች ምድር እየተናጠች ትገኛለች፡፡ ሕፃናት፣ አረጋውያን ፣ እናቶች፣ ደካሞች የመከራው ገፈት ቀማሾች ሆነው ይገኛሉ፡፡ ምድር ለሰው ልጅ እንደ ሲኦል ሆናበት ይገኛል፡፡

ይኹን እንጂ እግዚአብሔር አምላክ በበደለው በሰው ልጅ ምክንያት የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የአንድት በር ለጊዜው ቢዘጋበትም ኋላ በአቀረበው የሐዘን የፀፀት ጩኸት ወደ ቦታው እንደሚመልሰው ቃል ኪዳን ገባለት ጊዜው ሲደርስ በፈፀመው የይቅርታ የድኅነት የምሕረትና የቸርነት ሥራ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ልጁን ልኮ ወደቀደመ ክብሩና ቦታው መልሶታል፡፡

እኛ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን እናቶቻችን ከሚታወቁባቸው መንፈሳውያን ከኾኑ የቅድስና፣ የመልካምነት፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት፣ የሰላም፣ የአንድነት የበጐነት፣ የደግነት የርህራሄ የሰላም የፍቅር መንገዶች ወጥተን አድራሻው ጠፍቶብን በመከራ፣ በችግር በአለመግባባት ውስጥ ገብተን እንገኛለን፡፡

ስለኾነም ከዓለም የሚገኘው (ክፉ አስተሳሰብ) ክፉ ድርጊት ለጊዜው ይጠቅም ይመስለን ይሆናል ውጤቱ ግን በጣም የክፉ ክፉ ነው፡፡ቁስሉም ቶሎ አይድንም፡፡

ስለዚህ ማንኛችንም የሚመለከተን ሁሉ ቆም ብለን አስበን ለአምላካዊ ሕግ ለሰላም ለፍቅር ለመልካምነት ስፍራ በመስጠት አምላካችን ክርስቶስ በዕለተ ልደቱ የጥል ግድግዳን አፈራርሶ ሰላምን ለሰው ልጅ መልሶ የሰውን ልጅ እንደአከበረው ለሀገራችን ለወገኖቻችን በአጠቃላይ ለሰው ልጅ ሰላም ፍቅር አንድነት መሥራት ፣ በጠብና በመለያየት የቆለፍነውን የሰላም የአንድነት በር ከፍተን መሥራት ይጠበቅብናል ማለት ነው፡፡

በመጨረሻም አምላካችን በልደቱ ትሕትናውን አብዝቶ እንደአሳየን እኛም በዓሉን ስናከብረው በልዩ ልዩ ችግር የተጐዱ ወገኖቻችንን በማሰብ በመርዳት እንዲሆን እያሳሰብን ፤ የጌታ ልደት ስጦታዎች ደስታ ፣ ዕረፍት፣ ጤናና ሰላም መሆናቸውን ትኩረት ሰጥተን ማሰብ አለበን፡፡

አምላከ ሰላም መድኃኔ ዓለም ኢትዮጵያን ሀገራችንን እና ሕዝቦቿን በዐይነ ምሕረቱ ይመልከትልን በረድኤቱ አይለይብን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አባ ቀሌምንጦስ
በመ/ፓ/ጠ/ ጽ/ቤት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ታኅሣሥ 28 ቀን 2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ ፤ ደብረ ብርሃን

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

04 Jan, 19:15


https://youtu.be/ifX-mMCzndk?si=mh7Hs8yCvIF6eYjX

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

04 Jan, 19:14


https://youtu.be/vhkjZa3L2hI?si=NARBcpy2Cw-CcFzv

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

01 Dec, 16:30


https://youtu.be/-hqTTgNwSqM?si=02rezW9cfDWSDUKv

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

11 Nov, 09:36


https://youtu.be/iigzc2aK0rw?si=AU98JxCzPavjpET4

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

28 Oct, 16:18


የአቡነ ኤፍሬም አጸደ ሕፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን በማብቃት ክልል አቀፍ ፈተና 100% ተማሪዎችን በማሳለፉ የዋንጫ ሽልማት እና የምስጋና የምሥክር ወረቀት ተበረከተለት።

ጥቅምት ፲፰ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም(አቡቀለምሲስ ሚዲያ: ደብረ ብርሃን)

++++++++++ +++++++++++ +++++++++++

የአቡነ ኤፍሬም አጸደ ሕፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ሥር ከሚገኙ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በ2016 ዓ.ም 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን በማብቃት ክልል አቀፍ ፈተና 100% ተማሪዎችን በማሳለፉ ከከተማ አስተዳደሩ የዋንጫ ሽልማት እና የምስጋና የምሥክር ወረቀት ተበርክቶለታል።

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ዲያቆን ዮሐንስ ተስፋዬ ውጤቱ የሀገረ ሰብከታችን ፣ የመምህራን፣ የተማሪዎች፣ የወላጆች እና የአጠቃላይ የትምህርት ቤቱ ማሕበረሰብ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ይህ ሽልማት የመማር ማስተማሩን ሂደት ከዚህ በበለጠ አጠናክረን የተሻለ ውጤት እንድናመጣ የሚያነሳሳ በመሆኑ ሁላችንም በጋራ ልንሠራ ይገባል ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

Follow Us On
Youtube www.youtube.com/@AbukelemsisMedia
Telegram:- t.me/Abukelemsismedia
Instagram:- www.instagram.com/Abukelemsis.nsd
Twitter:- www.twitter.com/Abukelemsis01

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

27 Oct, 10:19


የቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከብሯል።

የሰማዕቱ በረከት እና አማላጅነት አይለን!

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

27 Oct, 10:17


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን!!

ጥቅምት ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን የሀገረ ቀምስ ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ፊልያስ በመኮንኑ በቁልቁልያኖስ ዘመን ወደ ፍርድ አደባባይ አቀረቡት ቁልቁልያኖስም ለአማልክት ሠዋ አለው ፊልያስም ከብቻው እግዚአብሔር በቀር ለአማልክት አልሠዋም አለ።

ቁልቁልያኖስም እግዚአብሔር ምን አይነት መመሥዋዕት ይሻል አለ ፊልያስም ቅን ትሑት የሆነ ንጹሕ ልቡናን እውነተኛ ፍርድን ቁም ነገርን እንዲህ ያለ መሥዋዕት እግዚአብሔር ይወዳልና ብሎ ለጣዖት አልሰግድም በማለቱ ራሱን ተቆርጦ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ።

በዚችም ቀን የቅዱስ ባስልዮስ ወንድም ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው ነቢዩ ሳሙኤል እናት ሐናም ልደቷ ነው በቆዳ ገመድ የታሠሩ የደጋጎች ሰማዕታት መታሰቢያቸው ነው።

በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ አንደኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስት ቅዱስ አባት ዲዮስቆሮስ ካልዕ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

በዚችም ቀን የዲያቆናት አለቃ የሰማዕታት መጀመሪያ የሆነ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተሾመባት መታሰቢያ ቀን ናት።

ዳግመኛም በዚች ቀን በካቶሊካዊያን የተገደሉ የደብረ ሊባኖስ ሰማዕታት ፤ የቅዱሳን ሔራን ሰማዕታት ዓመታዊና
የቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ ፣ የቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቲዎስ እንዲሁም የአባ ገሪማ ዘመንደራ ወርኃዊ በዓላቸው ነው።

የቅዱሳኑ ጸሎትና በረከት ሀገራችንን ከጥፋት ሕዝባችንን ከሞትና ከስደት ይጠብቅልን አሜን!!!

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

26 Oct, 14:07


https://youtu.be/-1sNZC8uE0w?si=s-pBoQaXe13GdzDt

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

26 Oct, 14:06


https://youtu.be/muQ37Crj9jI?si=MPY3ghBLu7hlX-yl

2,397

subscribers

13,009

photos

160

videos