የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን @dbsixti Channel on Telegram

የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን

@dbsixti


የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን (Amharic)

የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን ከቀረበው የባለሙያው dbsixti በሙሉ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ እና በርሃብርሃና። የሻደመህ ጓደኛችትን እና የ633 ቱ የቤት ማሕበራትን በመርዳት ታካሄዳላችሁ ብቻ ሳለ በሰለጠኞች እና ላሞች መረጃ ላይ ቅርብ የጋለሞው ደብረብርሃን። እነዚህ አንድ ወንድ ምን እንደሚገዛችሁ ስለሆነ የቡና ወንድ ታስቡናል። dbsixti በቅንአት ለኦሮሞዉ መወያያ የለንደን ህዝብ ለመጠቀም እና በአንድነት።

የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን

13 Jul, 17:00


👋 Hello! ቢኒያም SMART SATLITE DISHE WORK!

Click 'Start Mining', and you can mine PEPE coins for free every second, withdraw them to your wallet at any time. Quickly invite your friends to join, let the whole world become our followers, all dogs are already outdated, now it's time for PEPE to reign.

የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን

26 Jun, 14:23


ቀን 19 / 10 /16 ሰላም እንዴት ሰነበታችሁ የ235 ማህበር አመራሮች እና አባላት
ጉዳዩ:-ፕሮግራም ማሳወቅን ይመለከታል//
@ በመጀመሪያ ስንጓጓለት የነበረው የመኖሪያ ቤት ጉዳይ እልባት አግኝቶ በዚህ ደረጃ በመድረሳችን ከልብ የመነጨ ደስታዬን እየገለፅሁ። ፕሮግራሙን አሳውቃለሁ።
1ኛ ከፑን ቁጥር 1 እስከ 120 ኩፖን ቁጥር ያላችሁ ሰኔ 20/10/2016ዓ.ም
2ኛ ከፑን ቁጥር 123 እስከ 235 ሰኔ 21/2016 ዓ/ም
የዝግ ኢሳብ አካውንት ቁጥርና የብር መጠን ይፃፍላችሗል።
ስትመጡ :-የ5ቱ ክፍለ ከተማ እና የመሰረተ ልማት የተጣራበትን ይዛችሁ ቅረቡ
አመሰግናለሁ!
ማሳሰቢያ:-
የብሩ መጠን 50100 መሆኑን አውቃችሁ ተዛጋጁ ያለን ጊዜ በጣም አጭር በመሆኑ እዳትዘናጉ።
እስከ ሰኔ 30 የእውቅና ሰርተትኬት ማግኜት እንድንችል ሁላችንም መረጃውን በማሰማማት እንፍጠን

የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን

23 May, 15:43


ቀን 15 / 9 / 16 ለጠቅላላው በተለምዶ 400 የ235 የቤት መሀበር አባላት እና ሊቀመንበሮች በተደጋጋሚ በተጠየቅነው መሰረት በየቀበሌው ብዙ ብር እየተጠየቅን ነው መላ በሉን ስንትስ ብር ነው የሚከፈለው ላላችሁ ለማታውቁም ሁሉ ከታች ባለው ደረሰኝ መሰረት መሆኑን እያሳወቅን ከዛ በላይ የሚጠይቅ ማንኛውም አካል ካለ በውስጥ መስመር በመረጃ ጠቁሙን ።

የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን

14 May, 17:34


ለጠቅላላው የ235 የቤት መሀበራት የመጨረሻው የማጣራት ቀነገደብ እስከ ግንቦት 9 / 9 / 16 ማለትም አበርብ ቀን እንደሆነ እናሳስባለን።

የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን

07 Apr, 18:58


ቀን 29 / 7 / 16 ሰበር ሰበር እንኳን ደስ አላችሁሁሉም ነገር በጊዜው ሆነ ።የተወደዳችሁ የ196ቱ ማህበራት አባላት እንኳን ደስስስስስ አላችሁ ።እነሆ ከብዙ ውጣውረድና ተስፋ መቁረጥ በኋላ ስንፈልገው እና ስንናፍቀው የነበረውን ቦታችንን በዕለተ ሰኞ ማለትም በ30/07/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 2:30 ከተራ ቁጥር 1 እስከ 30 ያላችሁ የየማህበር ሊቀመንበርና ፀሐፊዎች በተክለኃይማኖት ቤተክርስቲያን አካባቢ 6 የችካል እንጨት ይዛችሁ እንድትገኙ ሲል ጥምር ኮሚቴው ያሳውቃል።
ማሣሠቢያ ፦
1,በተባለው ቀን የማይገኝ የማህበር አመራር ኃላፊነቱን እራሱ ይወስዳል።
2,ከየማህበሩ ቢበዛ ከሶስት አመራር በላይ መምጣት አይቻልም።
3,ከተራ ቁጥር 31 በላይ ያላችሁ ማክሰኞ የሙስሊሞች በዓል ከልሆነ በቅደም ተከተላችሁ በስልክም በቴሌግራሙም የምናሳውቅ መሆኑን እና እስከዚያው በትዕግስት እንድትጠብቁን እናሳስባለን ።ቦታው ተቀይሯል እያላችሁ የምታሶሩ ከድርጊታችሁ ታቀቡ የተቀየረ ቦታ የለም።
4, በዕጣው ቅደም ተከተል በፕሮግራሙ ሁሉም የማህበር ሊቀመንበር ጋር ኮሚቴው እየደወለ ነው ነገር ግን የብዙዎቻችሁ ስልክ አይሰራም የማታነሱም አላችሁ እና የኢንተርኔት አክሰሱንም ሁሉም ስለማያገኝ ለምታውቋቸው መረጃውን አድርሱልን።
መጋቢት 28/07/2016ዓ/ም
ጥምር ኮሚቴው
ስለሁሉም ነገር እግዚዓብሔር ይመስገን።

የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን

03 Apr, 13:47


ቦታው በሶስት ደረጃ ተከፍሏል ከተራ ቁጥር 1እስከ61 ዞን አንድ ሲሆን ከ62 እስከ 130 ዞን ሁለት እንዲሁም ከ131 አስከ 193ድረስ ዞን ሶስት ላይ ነው ። ይህ ድልድልም በዕጣው ቅደም ተከተል ነው ።
ማሣሠቢያ ፦አንዳንድ የማህበር አመራሮች የተለያየ ምክንያትን በመጠቀም ከአባሎቻችሁ ገንዘብ እየሰበሰባችሁ መሆኑን ኮሚቴው ደርሶበታል ስለዚክ ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ ለማለት እንወዳለን ።
ሌላው በየግል እየደወላችሁ ቦታው ተቀይሯል ወይ ለምትሉ የተቀየረ ቦታ የለም ሶስቱም ዞን በዚያው በካራፊኖ ነው።

የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን

25 Mar, 15:36


ለጠቅላላው የ196 የቤት መሀበራት

የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን

20 Mar, 11:19


ሰላም የተከበራችሁ የ202 የቤት ማህበራት እንዴት ናችሁ የካሳ ክፍያውን ካስገባንበት ጊዜ አንስቶ ሁላችሁም ስራው ያለበት እና የደረሰበትን ሁኔታዎች ስትጠይቁን እኛም መረጃዎችን ስናደርስ ቆይተናል በእኛ በኩል ብሩ ገቢ ተደርጎ ከተዘጋበት ጊዜ ጀምሮ ደረሰኝ ያላስገቡ ማህበራት እንዲያስገቡ እና መረጃዎችን እንዲያሟሉ ከማድረግ አድራሻቸው የሌሉ እና የተበተኑ ማህበራትን ከማፈላለግ ጀምሮ እንዲሁም ባንኮች የሰበሰቡት የገንዘብ መጠን ለተሰጣቸው አርሶ አደር በስአቱ እንዲያዘዋውሩ ከማድረግም አንፃር ብዙ ስራዎችን በመስራት ዛሬ ላይ ሁሉም ባንኮች ለተነሽ አርሶ አደር የካሳ ክፍያቸውን አጠናቀው አስገብተዋል። በዚህም ትልቅ ደስታ ይሰማናል በዚህ ሳምንት ማለቅ ያለባቸውን ስራዎች ከሚመለከታቸው ጋር ሆነን በማጠናቀቅ ከቀጣይ ሳምንት ጀምር ወደ መሬት ሽንሻኖ የምንገባበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን
ለዚህም በትዕግስት ለጠበቃችሁ የማህበር ሊቀመንበሮች እና አባላት ከልብ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በቀጣይ የሚወጡ ፕሮግራሞችን የምናሳውቅ ሲሆን መረጃ እንድትከታተሉ እናሳስባለን።

ማሳሰቢያ:- አንዳንድ ሀላፊነት የማይሰማችሁ ግለሰቦች ከዚህ በፊት በሚኒሊክ አዳራሽ ስብሰባ ባደረግንበት ጊዜ ኮሚቴውን ለምን ስራውን ሲሰሩ እና ሲያሰሩ የነበሩ አካላትን ታመሰግናላችሁ በማለት እንዲሁም ከተማ አስተዳደሩ ካሳ የጠየቀን ብር ቸግሮት ነው ለመከላከያ ለድጋፍ ሊያውለው ነው ስትሉ የነበራችሁ ከ ሁለት እና ሶስት የማትበልጡ ግለሰቦች አሁንም እራሳችሁን እንደ ኮሚቴ በመቁጠር አንዳንድ አካላት ጋር እየሄዳችሁ ማስተዋል የጎደላቸውን ሀሳቦች ስትሰነዝሩ እና ኮሚቴው እንዳልሰራላችሁ እና መረጃ ከኮሚቴው መስማት እንደማትፈልጉ ጭምር ስታወሩ እንደነበር መረጃዎች ደርሰውናል ኮሚቴው ጉዳዩን እየተከታተለው ነው በዚህ አይነት ድርጊት ውስጥ ያላችሁ ሰዎች እጃችሁን ከኮሚቴው ላይ እንድታነሱ እንመክራለን
እናመሰግናለን።
ጥምር ኮሚቴው
መጋቢት11/2016
ደብረብርሐን

የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን

19 Jan, 15:04


ለ196 የመኖሪያ ቤት ማህበራት የመሬት ካሳ መጠንን ከተማ አስተዳደሩ የመጨረሻውን ውሳኔ ይፋ አደረገ

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ለ196 የመኖሪያ ቤት ማህበራት የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ በጥር 9 ቀን 2016 ዓ/ም በወሰነው መሠረት የመሬት ካሳ መጠን በማጽደቅ ገልጿል።

ስለሆነም በግለሰብ ወይም በፓርስል 122,000 /አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሺህ ብር/ እስከ ጥር 24 ቀን 2016 ዓ/ም የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ለማህበራት ካሳ ማስገቢያ በከፈተው የባንክ አካውንቶች እንድታስገቡ ሲል አሳውቋል።

የባንክ አካውንቶቹ ዝርዝር ከታች በፎቶ በተገለጸው ላይ የሚገኝ ይሆናል!👇👇

የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን

26 Dec, 12:59


ለቤት ማህበራት 187 ሄክታር መሬት የካሳ ግምት መዘጋጀቱን የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር አስታወቀ

ከተማ አስተዳደሩ ከ196 የቤት ማህበራት አመራሮች ጋር በካሳ ግምት ጥናት ዙሪያ ተወያየ

የደብረብርሃን ከተማ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ነቢዩ ባዩ እንደገለጹት በተለምዶ 633 የቤት ማህበራት እየተባሉ ከሚጠሩት ውስጥ ቦታ ሳይሰጣቸው ለቀሩ 196 ማህበራት 187 ሄክታር መሬት የካሳ ግምት መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡

የካሳ ገምቱ ዝቅ እንዲል ያሉትን አመራጮች ሁሉ ተጠቅመው የተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የካሳ ግምት ዋጋው የአባላትን የመክፈል አቅም ያገናዘበ አይደለም፣ዝቅ ሊል ይገባ ፤ለቀደሙት ጭማሪ ሳይደረግባቸው ከተሰጣቸው ለእኛም በተመሳሳይ ሊታሰብልን ይገባል የሚሉና ሌሎች መከራረከሪያ ሀሳቦችን አንስተው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የደብረብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ እንደገለጹት የወቅቱን ሁኔታና የኑሮ ውድነቱን ከማንም በላይ የችግሩን ጥልቀት እንደሚያውቁት አስረድተዋል፡፡

የቤት ማህበር አባላትም በወቅቱ ሁኔታ እንደሌላው ማህበረሰብ የችግሩ ተጋሪ በመሆናቸው የካሳ ግምቱ ዝቅ እንዲል ብዙ መሰራቱን አብራርተዋል፡፡አሁንም አማራጭ ካለ ግምቱ ዝቅ እንዲል እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

የደብረብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በበኩላቸው እንደገለጹት የቤት ማህበራት ቦታ ጥያቄ አንድ የመልካም አስተዳደር ችግር በመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ ችግሩን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ማድረጉንና አሁን እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በዚሁ መሠረት ከ633 የቤት ማህበራት ውስጥ ቦታ ሳይሰጣቸው ለቆዩ በስራቸው 4 ሺህ 355 196 ማህበራት 187 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱንና ከብዙ ልፋት በኋላ የካሳ ግምቱም መሰራቱን አመልክተዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ የካሳ ግምቱ እንዲያንስ የተጠቀሙበትን አማራጮች ሁሉ ዘርዝረው አስረድተዋል፡፡በቀጣይም አሁን ከተሰራው የካሳ ግምት በታች እንዲወርድ አቅም የፈቀደው ሁሉ እንደሚደረግ ጠቅሰው በየማህበራቸው አባላትን አወያይተው እንዲመጡ አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

የካሳ ግምቱ በአጠቃላይ 627 ሚሊየን 792 ሺህ 566 ብር መሆኑ ተገልጿል፡፡

የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን

26 Dec, 11:20


ቀን 16 / 4 / 16 አሁን በደረሰን መረጃ የ202 ጠቅላላ ክፍያ መቶ ሰላሳ ሺህ ተብሏል የሚሻሻል አዲስ ነገር ካለ የምናሳውቅ ይሆናል።

የ633ቱ የቤት ማሕበራት መወያያ ገፅ ደብረብርሃን

30 Nov, 15:03


አዲስ አዲስ አዲስ 19 / 3 / 16 ሰላም የተከበራችሁ የ202 ቱ የቤት ማህበራት በሙሉ እንደሚታወቀው ከሁለት ሶስት ወራት በላይ እስካሁን የኢንተርኔት አገልግሎት የሌለ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም የደረስንባቸውን ነገሮች መረጃ ለሚጠይቁን አባላት በሙሉ በስልክ ስናደርስ ቆይተናል በተጨማሪም ስራው ተሰርቶ ስለተጠናቀቀ ባለፈው ሳምንት ለሁሉም ሊቀመንበሮች ለመደወል እና ስብሰባ ለመጥራት ያሰብን ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል።
ለዚህም ምክነያቱ....
1, የካሳው ሁኔታ የተጋነነ በመሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ካሳው የሚቀንስበትን እና የማህበረሰቡን አቅም ያማከለ እንዲሆን እንዲሁም ተቆርጦ የቀረ ማህበር እንደመሆኑ ይህን ባገናዘበ መልኩ ካሳው የሚቀንስባቸውን ሁሉንም አማራጮች በማየት በድጋሚ ተሰርቶ እንዲቀርብ ስለተወሰነ ለዚህም ተጨማሪ ጊዜ ስላስፈለገ ካሳውን ማሳወቅ አልቻልንም ። መሬት መምሪያ እና መሰረተ ልማት የማስተካከያ ስራዎችን ሰርተው እንደጨረሱ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ በቅርቡ ካሳውን የምናውቅ ይሆናል። በተጨማሪም የደረስንባቸውን መረጃዎች በተለያዩ አማራጮች እንዲደርሳችሁ የምናደርግ ይሆናል::
ማሳሰቢያ:-እናውቃለን ስራው በታቀደለት ጊዜ ሊጠናቀቅ አልቻለም ነገር ግን ጥቂት ሰዎች እንደምትሉት ኮሚቴው ስራው ዘንግቶት ወይም ችላ ብለንው ሳይሆን በተለያዩ እክሎች ምክነያት ነው ስራው ሊዘገይ የቻለው
ኮሚቴው እየተገፋንም እየተሰደብንም ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት ስራውን እየሰራ ነው ለዚህም ብዙዎች በተለያየ ጊዜ ምን ያህል ጫናዎችን ተቋቁመን እየሰራን እንዳለ አይታችኋል አሁንም የተደረሰበትን ሁኔታ እስከምናሳውቃችሁ በትእግስት እንድትጠባበቁን ስንል እንጠይቃለን።

ጥምር ኮሚቴው
ህዳር 19/03/2016
ደብረብርሀን