ከውጊያ ባለፈ ባለ ምጡቅ አዕምሮ ባለቤቶች በሚል ፋሽስቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲያሞካሿቸው የነበሩት ህፃን ገዳይ ሴት ደፋሪ የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት ከዋጃ ከተማ በፋኖ የተከፈተባቸውን ጥቃት መቋቋም አቅቷቸው ወደ ጥሙጋ መፈርጠጣቸው ተሰምቷል።
ትናንት ለዛሬ አጥቢያ ለሊት ጀምሮ እስከ ንጋት ባለው በራያ አላማጣ ዋጃ ከተማ ላይ ከባድ ውጊያ ተከፍቶ የነበረ ሲሆን፡ በዚህም ከ20 በላይ የአየር ወለድ ኮማንዶዎች ተግድለዋል ተብሏል።
በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የሀውጃኖ ክ/ጦር ፋኖዎች ትናትና ጥር 4/2017 ዓ/ም ወደ ዋጃ ከተማ በመግባት ከእኩለ ለሊት ጀምሮ እስከ ንጋት የዘለቀ ጥቃት በመክፈት ድል መቀዳጀታቸውን የአማራ ፋኖ በወሎ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።
ከእኩለ ለሊት ጀምሮ እስከ ንጋት ድረስ በዘለቀው በዚህ ጥቃት የሪፐብሊካን ጋርድ አባላቱ ከባድ ኪሳራን አስተናግደዋል ተብሏል።
በዚህ ጥቃት በዋጃ ከተማ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ብቻ ከ20 በላይ ኮማንዶዎች ሲገደሉ ከ11 በላይ የሚሆኑት ቆስለው ንጋት ላይ ወደ አላማጣ ከተማ መወሰዳቸው ተነግሯል።
የትናንት ለሊቱ ኦፕሬሽን እጅግ ስኬታማ ነበር የተባለ ሲሆን በዚህም ሙትና ቁስለኛ ከሆኑት ወታደሮች በተጨማሪ በህይወት የተረፉት ኮማንዶዎች መሣሪያቸውን እያዝረከረኩ ወደ ራያ አላማጣ ጥሙጋ ቀጠና መሸሻቸውን የድርጅቱ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ ጨምሮ ገልጿል።
ወደ ጥሙጋ የሸሸው የፀረ አማራው ብልፅግና ፓርቲ አገልጋይ ጦር እንደገና ኃይሉን አደራጅቶ ዛሬ ማርፈጃውን ዙ23ና ሌሎች ከባባድ የጦር መሣሪያዎችን በመጠቀም ዋጃ ከተማንና በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ አከባቢዎችን ሲደበድብ መዋሉ ተሰምቷል።
በዚህም በአከባቢው ነዋሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱ ነው የታወቀው።
©አሻራ