ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo) @orthodoxtewahedoot Channel on Telegram

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

@orthodoxtewahedoot


በዚህ ቻናል ‘electronic (soft copy)’ ቅዱሳት መጻሕፍትና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምሮን መሰረት ያደረጉ ቪድዮዎችና ልዩ ልዩ ወቅታዊ መልዕክቶች ይተላለፉበታል።

ቀሲስ ዶ/ር ብዙአየሁ አምባዬ
ሲያትል ዋሽንግተን

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo) (Amharic)

ከዚህ በፊት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስለ 'orthodoxtewahedoot' የተጠቀሰ መረጃ ተከስቷል። ይህ ቡድኖች ጥቅም የምንፈልገውን ውይይት እና የድጋፍ ጥያቄዎችን አስተምሮን አወቅሾባቸው። ይህ መረጃ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የተጠቀሰ፣ የቻናል እና አስተምሮን መዝገበ-ቃላትን በምንፈልገውም ዜና፣ ሀበሻና መዝናኛነት እና ለውጥ ምልክቶች በተደጋገሙ ዌብ ጉዞችንና ልኩልነትን እንምራ። አለመረጃው በዪጧሩ ዶ/ር ብዙአየሁ አምባዬና ሲያትል ዋሽንግተን እነሆ። በቀሲስ የተዋሕዶ ከህዝቦች ምክትል እንዴት ለመስራት መደረጉን ይውላሉ።

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

06 Jan, 00:32


@Memhir_sirak

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

06 Jan, 00:32


@Memhir_sirak

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

06 Jan, 00:32


@Memhir_sirak

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

06 Jan, 00:32


@Memhir_sirak

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

06 Jan, 00:32


@Memhir_sirak

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

06 Jan, 00:32


@Memhir_sirak

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

06 Jan, 00:32


@Memhir_sirak

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

06 Jan, 00:32


@Memhir_sirak

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

06 Jan, 00:32


@Memhir_sirak

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

06 Jan, 00:32


@Memhir_sirak

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

06 Jan, 00:32


@Memhir_sirak

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

06 Jan, 00:32


ዋዜማ-ሰላም @Memhir_sirak

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

04 Jan, 07:36


https://astemhro.com/2025/01/01/10commandements_socialmedia/?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR0sh51T2m3oOcKuqxIuT3E_AbPBByAr0VoQPj3P8-bfVGnYzE5HzgXrQk4_aem_-fQFSt0g9CU2Fn-kODxObA

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

04 Jan, 02:41


ነፍሱን ስለ በጎች የሚያኖር (ዮሐ ፲÷፲፩)፣ ተኩላ ሲመጣ አይቶ በጎቹን ትቶ የማይሸሽ (ዮሐ ፲÷፲፪-፲፫)፣ በለመለመ መስክ የሚያሰማራና በዕረፍት ውኃና በጽድቅ መንገድ የሚመራ (መዝ ፳፪(፳፫)፥፪-፫)፣ የራሱን በጎች የሚያውቅ (ዮሐ ፲÷፲፬-፲፭)፣ ከመቶ በጎቹ መካከል አንዱ ቢጠፋ የጠፋውን የሚፈልግ (ሉቃ ፲፭÷፬)፣ የሚያሰማራ (ዮሐ ፲÷፱)፣ የሰላም አምላክ (ዕብ ፲፫÷፳)፣ በጎቹን የሚያሰማራ ፣ የሚያስመስጋቸው፣ የጠፋውን የሚፈልግ፣ የተበተኑትን የሚያድናቸው (ሕዝ ፴፬÷፲፪-፲፫)፣ ከበረቱ ያልሆኑ በጎቹን የሚያመጣና አንድ መንጋ የሚያደርግ (ዮሐ ፲÷፲፮) ፣ በሰማይና በምድር ሥልጣን ያለው (ማቴ ፳፰÷፲፰) ፣ ለበጎቹም የዘላለም ሕይወትን የሚሰጣቸው እውነተኛ እረኛችን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (ዮሐ ፲፥ ፲፩) ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱ ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን ፨ (ሮሜ ፲፩÷፴፮)

Join me for updates👇

📢 I’m sharing posts on Orthodox Church teachings – join me for insightful updates! 🙏📖

http://youtube.com/@OrthodoxTewahedo-?sub_confirmation=1

https://t.me/OrthodoxTewahedoOT

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

02 Jan, 20:36


''ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፨''ምሳ ፳፱፥፪ እንዳለ መጥምቁ ዮሐንስ ''በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፨''ሉቃ ፩÷፲፬ ተብሏል፨

ማርቆስ ሐዋርያና ወንጌላዊ በግብጽ ያሉ የላም አምልኮተ ጣዖትን በርቱዕ ትምህርቱ ሰባብሮ እንደጣለ ፡ ኢትዮጵያዊው ጻድቅና መናኝ አባ ተክለሃይማኖት ለኢትዮጵያ የወንጌል ብርሃን በመሆን፡ አምልኮተ ጣዖትን ያራቁ ዛሬ የልደት ቀናቸው ነውና ሕዝብ ሆይ ደስ ይበልህ፨

Salutation to thy birth, seeing that thy mother had long remained barren, O Takla Haymanot, the sun who conquereth time, with whose praise the earth is filled from one boundary to the other, and with whose righteousness heaven is covered.
(Synaxarion Tahisas 24)

እንኳን አደረሳችሁ፤አደረሰን፨

Join me for updates👇

📢 I’m sharing posts on Orthodox Church teachings – join me for insightful updates! 🙏📖

http://youtube.com/@OrthodoxTewahedo-?sub_confirmation=1

https://t.me/OrthodoxTewahedoOT

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

31 Dec, 14:10


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በጎርጎሮሳውያን የዘመን አቆጣጠር የ2025 አዲስ ዓመትን በማስመለክት ለመላው የዓለም ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።

ቅዱስነታቸው ለመላው የዓለም ማኅበረሰብእ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት የአማርኛ ትርጉም ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

ለመላው የዓለም ሕዝብ የተላለፈ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ 
አባታዊ መልእክት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !
‹‹ወሰላም በምድር ለዕጓለ እመሕያው ሥምረቱ:-
ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ ።” ሉቃ. 2፡14

ከሁሉ በማስቀደም በመላው ዓለም ለምትገኙ፤ የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ላከበራችሁና አዲሱን ዓመት 2025 ዓ.ም. ለምትቀበሉ ልጆቻችን የመልካም ምኞታችንን ለመግለጽ እንወዳለን ። 

ዘመን ከቊጥር ያለፈ ትርጉም ያለው የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ በዘመን ውስጥ ያጣነውን እናገኛለን ፣ ያገኘነውን እንመልሳለን ። በዘመን ውስጥ ሕፃናት ሲጠነክሩ ፣ ሽማግሌዎች ይደክማሉ ። አንዱ ዘመን ላንዱ ልደት ለሌላው ሞት ሆኖ ይውላል ። እግዚአብሔር አምላካችን ከጊዜ ውጭ ቢሆንም እኛን በጊዜ ሰሌዳ ውስጥ አስቀምጦናል ። ዘመን ሳያደክመው በዘመን ውስጥ በሚለዋወጥ ማንነት እንድናልፍ ተሠርተናል ። ከጠዋት እስከ ማታ ያለው ሂደት ከልደት እስከ ሞት ያለውን ረጅም ጉዞ የሚገልጥ ነው ። በየቀኑ ዕለቱን ብቻ ሳይሆን መላው ዘመናችንን እንኖራለን ። የሰው ልጅ በዚህ ዓለም በጊዜ የተለካ በሚመጣው ዓለም ከጊዜ ውጭ የሚኖር ፍጡር ነው ። በሚሞት ሥጋ የማይሞት ነፍስን ተሸክሟል፣ በሚያልፍ ጊዜም የማያልፍ ዘለዓለማዊነትን ይጠባበቃል ። በታሪክ ውስጥ ከፍታና ዝቅታ ቢፈራረቁም ፣ ሥልጣኔዎች መጥተው ቢሄዱም ፣ አንዱ ፍልስፍና ሌላውን ቢሽረውም የዘመናት መፈራረቅ ግን ቋሚ ሕግ ሁኖ ይኖራል ። የሰው ልጆች ከመከራ ቀናት የተነሣ መኖራቸውን የሚጠሉበት ጊዜ ቢገጥምም አዲስ ዓመትን መናፈቃቸው መኖርን እንደሚፈልጉ ማሳያ ነው ። ትልቅ የምስጋና ርእስ ቢኖር እርሱም አዲስ ዘመንን ማየት ነው ። አሮጌነትን እየተውን አዲስን ዓመት የምንቀበለው ፣ ያለፈውን አሮጌ ብለን ይህን አዲስ የምንለው በማያቋርጥ ለውጥ ውስጥ መሆንን ስለምንፈልግ ነው ። 


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመወለዱ የዓለምን ታሪክ ለሁለት ከፍሎታል ። ከክርስቶስ ልደት በፊትና ከክርስቶስ ልደት በኋላ እየተባለም ይጠራል ። በሃይማኖታችንም ዓመተ ፍዳና ዓመተ ምሕረት ተብሎ ለሁለት ይከፈላል ። ዓለምን ለመለወጥ ብዙዎች ወደ ዓለም መጥተዋል ። ጌታችን ግን የሰውን ሕይወት ለመለወጥ ወደ ዓለም መጥቷል ። አሁን ያለነው በጌታ ዓመት ፣ በምሕረት ዘመን ነው ። ፍርድ በሙሉነት መፈጸሙ ለዓለም ሰላም ወሳኝ ቢሆንም ምሕረት ግን እውነተኛውን የልብ ሰላም ታመጣለች ። ከእኛ ወደሚያንሱት የምናደርገው ጉዞ ፣ ራስ ወዳድነትን አሸንፈን ሌሎችን ለመርዳት የምንከፍለው መሥዋዕትነት ዓለምን የሚለውጥ ነው። ከተሞቻችን በማያቋርጥ ዕድገት ውስጥ ላያልፉ ይችላሉ ። ዕድገትም የሚቆምበት ጊዜ አለ። የሰው ልጅ የሞራል ከፍታ ግን መቆሚያ የለውምና አዲሱ ዘመን ክፉ ተግባር የሚወገድበት፤ መልካም ተግባራት የሚከናወኑበት ሊሆን ይገባዋል ። 
የተወደዳችሁ የዓለም ሕዝቦች! 
ያለፈው ዓመት 2024 ዓ.ም. እንደ ዓለም ብዙ ነገሮችን ብናተርፍም የከሰርንበትም ጭምር ነው ። ከተፈጥሮ አደጋዎች ይልቅ ሰው ሠራሽ በሆኑ ችግሮች ዓለምን እስር ቤት ውስጥ ቆልፈንባት ይታያል ። ሲጀመር በቀናት ውስጥ የሚያበቃ ይመስል የነበረው የራሽያና የዩክሬን ጦርነት ዓመታትን እያስቆጠረ ነው ። በመላው ዓለምም ለኑሮ ውድነትና ጫና ምክንያት ሆኗል ። ከሁሉ በላይ ሁለቱ ኦርቶዶክሳውያን ሕዝቦች የሰላም ረሀብተኛ ሆነዋል ። መካከለኛው ምሥራቅም በየዕለቱ በሚሰፋ ጦርነት ተውጦ ይታያል ። የዓለም የስበት ማዕከል በመሆኑም ብዙ ጫናዎችን እያሳደረ ይገኛል ። ስልጣኔው ይዞት የመጣው የግለኝነት ኑሮ ለብዙ የሰው ልጆች በጭንቀት ውስጥ ማለፍ ምክንያት እየሆነ ይገኛል ። መፍትሔን ከመፈለግ፣ እሳትን ከማጥፋት ይልቅ ችግሮችን የሚያባብሱ ነገሮች የዓለማችን መገለጫ ሆነዋል። ለይስሙላ የሚደረጉ የሰላም ስብሰባዎችም ተናግረን ነበር ለማለት ካልሆነ በቀር ቁርጥ ውሳኔ ያላቸው አይደሉም ። 
ምድራችን ሰላምን በጣም ተርባለች ። እንስሳትና አራዊት ያለምርጫቸው በመከራ ውስጥ እያለፉ ነው ። የዓለማችን ብርቅዬ እንግዶች የሆኑት ሕፃናት እየታወኩ ነው ። ራሳቸውን መከላከል ያልቻሉ ሴቶች ልጆቻችን በፍርሃት ውስጥ አሁንም አሉ ። ይህች ዓለም አስተማሪ ቅጣት እንደሚያድናት ስታምን ብትኖርም አሁን ግን አስተማሪ ምሕረት እንደሚያስፈልጋት ግልጽ እየሆነ ይመስላል ። ስለዚህ በዚህ የልደተ ክርስቶስ መታሰቢያና የ2025 ዓ.ም. መቀበያ ላይ ቆመን ይቅር መባባል፣ ለጋራ ቤታችን መሥራትና በሰዎች አለመግባባት የታወከችውን ዓለም በሰዎች ቁርጥ ውሳኔ እንድትረጋጋ የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይገባናል ።

በመጨረሻም አዲሱን ዓመት እየተቀበላችሁ ያላችሁ፤ አዲሱን ዓመት ከክርስቶስ ልደት ጋር አብራችሁ የምታከብሩ ወገኖቻችን ልደተ ክርስቶስ ትሕትና የተገለጠበት ነውና በትሑት ሰብእና ቆማችሁ የነደደውን እሳት እንድታጠፉ፤ ጦርነትን በሰላም ለመለወጥ የራሳችሁን ድርሻ እንድትወጡ ስንል አባታዊ የተማኅጽኖ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን ፡፡ 

እግዚአብሔር አምላክ መላውን ዓለም በሰላም ይጠብቅልን፤
ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን፡፡
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥር 1 ቀን 2025 G.C.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

29 Dec, 11:37


https://www.youtube.com/live/o_dHoA_I7Lk

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

29 Dec, 07:00


https://youtu.be/BeWkCggpqV4

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

29 Dec, 03:55


መዝሙር ዘብርሃን

ከታኅሣሥ ፲፬ - ፳

አቅዲሙ ነገረ በኦሪት ከመ ይመጽእ ወልድ በስብሐት ዘይዜንዋ ለጽዮን ቃለ ትፍሥሕት ወካዕበ ይቤ በአፈ ዳዊት ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም ዘያበርህ ላዕለ ጻድቃን መርዓዊሃ ለቤተ ክርስቲያን ይርዳእ ዘተኀጒለ ያስተጋብእ ዝርዋነ መጽአ ኀቤነ

ትርጉም፦

ለጽዮን የደስታ ቃልን የሚነግራት ወልድ በምስጋና እንደሚመጣ አስቀድሞ በኦሪት ተነገረ ዳግመኛ በዳዊት አንደበት በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው አለ ወደ ዓለም የመጣው ብርሃን ለጻድቃን የሚያበራ የቤተ ክርስቲያን ሙሽራ ነው የጠፋውን ይረዳ/ይፈልግ ዘንድ የተበተኑትን ይሰበስብ ዘንድ ወደእኛ መጣ

አጭር መግለጫ

፩ በኦሪት ዘፍጥረት ፫፥፳፪ "አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንዳንዱ ሆነ" ተብሎ የተነገረው፤

፪ በዘፍጥረት ፱፥፳፯ "እግዚአብሔር በሴም ድንኳን ይደር" ተብሎ የተነገረው

፫ በኦሪት ዘጸአት ፫፥፪ ጀምሮ በምሳሌ የተገለጠው

፬ በዘጸአት ፴፫፥፳፫ "ጀርባዬን ታያለህ ፊቴ ግን ለአንተ አይታይም" ተብሎ በምሥጢር የተነገረው

፭ በኦሪት ዘኊልቊ ፳፬፥፲፯ "ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል ከእስራኤል ሰው ይነሣል" ተብሎ በምሳሌ የተገለጠው

፮ በኦሪት ዘዳግም ፲፰፥፲፭ "አምላክህ እግዚአብሔር ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል እሱን ስሙት" ብሎ ሊቀ ነቢያት ሙሴ የተናገረው

፯ በትንቢተ ኤርምያስ ፴፩፥፲ "አሕዛብ ሆይ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩና እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል በሉ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶታል፥ ከበረቱበትም እጅ አድኖታል" ተብሎ የተነገረው የማጽናኛ ትምህርትና ሌሎችም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው እንደሚሆንና እኛን እንደሚያድነን አስቀድመው በኦሪትና በነቢያት መጻሕፍት የተመዘገቡ ናቸው። ሊቁም የዘመረው ይህንን እያነጻጸረ ነው።

የዕለቱ ምንባባት፦

ሮሜ ፲፫፥፲፩ - ፍ፤
፩ዮሐ ፩፥፩ - ፍ፤
ግብ ፳፮፥፲፪ - ፲፱

የዕለቱ ምስባክ፦

ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቅከ
እማንቱ ይምርሓኒ ወይሰዳኒ ደብረ መቅደስከ
ወውስተ አብያቲከ እግዚኦ መዝ ፵፪፥፫

ትርጉም፦

ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ
እነሱ ይምሩኝ
አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደማደሪያህ ይውሰዱኝ

ምሥጢር፦

ብርሃነ ረድኤትህን አንድም ቂሮስ ዳርዮስን ዮሴዕ ዘሩባቤልን ላክልኝ
እነሱ መመስገኛህ ወደምትሆን ወደ ኢየሩሳሌም መርትው ይውሰዱኝ

አንድም ብርሃን ልጅህን ላክልኝ። አንድም ብርሃነ ጽድቅ ክርስቶስ ሆይ ሥጋህን ደምህን ስጠኝ
አንድም ሐዋርያትን ሰባ አርድእትን ላክልኝ
እነሱ መርተው ወደ ገነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ያግቡኝ

የዕለቱ ወንጌል፦

ዮሐ ፩፥፩ - ፲፱

ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ

ከወንጌሉ ንባብ ውስጥ፦

ወሕይወትሰ ብርሃኑ ለእጓለ እመሕያው
- ሕይወት ግን ለሰው ብርሃን ነው ማለት ሕይወትነቱም ለሰው እውቀት መሆን ነው። እውቀት የሌለው ሕዝብ ይጠፋልና። ሆሴ ፬፥፮

አንድም ሕይወትነቱ ምግብ በመሆን ነው ሥጋውን የበላ ደሙን የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለውና

ማወቅ የሚገባንን አውቀን ሥጋውን ደሙን እየተቀበልን በተሰጠን ጸጋና በተፈቀደልን የአገልግሎት ዘርፍ ብንሰማራ በብርሃን እየተመላለስን ነው ሥራችን መልካም ስለሆነ ወደ ብርሃን እንቀርባልን በብርሃን እንመላለሳለን ከጨለማ ሥራ እንርቃለን ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ በተባለው መሠረት መልካሙን ሥራችንን ያዩ ሁሉ ይደሰታሉ እንደእኛ ለመሆንም ይመኛሉ የእግዚአብሔር ክብር ይገለጣል የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይሰፋል

በብርሃኑ ብርሃንን እናይ ዘንድ በብርሃን እንመላለስ ዘንድ በብርሃናዊ ዓላማ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንምጣ፨

#elamaba

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

27 Dec, 23:52


በዓለመ መላእክት በሃይማኖት መጽናት የሰበከና ዘንዶውን ከቅዱስ ሚካኤልና ከመላእክቱ ጋር የተዋጋ(ራዕ ፲፪÷፯)፣ የገነት ምስራቃዊ በር ጠባቂ-አቃቤ ገነት (ዘፍ ፫÷፳፬) ፣ ከቅዱስ ሚካኤል ጋር ሰዶምን ያጠፋ ኃያል መልአክ (ዘፍ ፲፱÷፲፪-፲፫)፣ ሲድራቅ፣ ሚሳቅንና አብድናጎን ከእግዚአብሔር ተልኮ ያዳናቸው (ዳን ፫÷፳፰)፣ ለነቢዩ ዳንኤል ጥበብና ማስተዋልን የሰጠው፣ በጸሎቱም ያበረታው (ዳን ፱÷፳፩-፳፪) በእባቦች፣ በጻድቃንና በኪሩቤል ላይ የተሾመ (ሄኖክ ፮÷፯)፣ አምነው ስለሚለምኑ ሰዎች የሚያማልድ የሚለምን (ሄኖክ ፲÷፯)፣ የቃልን ሥጋ መሆን ያበሰረን መጋቤ ሐዲስ ( ሉቃ ፩÷፳፮-፶፭) ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እንኳን በተወደደች ምልጃው ለዚህች ዕለት ለዚህች ዓመት ለዚህችም ሰዓት አደረሰን ፤ አደረሳችሁ ፨

Join me for updates👇

📢 I’m sharing posts on Orthodox Church teachings – join me for insightful updates! 🙏📖

http://youtube.com/@OrthodoxTewahedo-?sub_confirmation=1

https://t.me/OrthodoxTewahedoOT

#Saint #ቅዱስ #Gabriel #ገብርኤል #ቅዱስገብርኤል #ታኅሣሥ #saintgabriel #EOTC

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

27 Dec, 05:45


እግዚአብሔር ሆይ የሚሳንህ ነገር የለምና የራቀውን አቅርበህ የረቀቀውን አጉልተህ እየሰማነው ካለነው መርዶና ሰቀቀን ዕረፍተ ሥጋንና ዕረፍተ ነፍስን አትንሣን

ጸልዩ በእንተ ሰላም
ስለ ሰላም እንጸልይ
ስለ ሀገራችን እንጸልይ
በጭንቅ በመከራ ስላሉት እንጸልይ
በረሀብ በስደት ስላሉት እንጸልይ
በጽኑ ሕመም ተይዘው ስለሚሰቃዩት እንጸልይ
የሰላም የምህረት የቸርነት ባለቤት እግዚአብሔር ሰላሙን ምህረቱን ቸርነቱን አይንሳን

አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ
ዘዝዋይ ገዳም
ታህሣሥ 18/4/2017
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

27 Dec, 05:45


ሥርዓተ ማኅሌት ዘቅዱስ ገብርኤል "ታኅሣሥ ፲፱"
ዋይዜማ መልክዕ ዚቅ ወረብ ምልጣንና እስመ ለዓለም
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

ዋዜማ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ
አብሠራ ገብርኤል ለማርያም ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ፤ ተወልደ እምኔሃ።

ምልጣን
ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ።

አመላለስ፦
ወልድ ተወልደ እምኔሃ/2/
ወልድ ተወልደ እምኔሃ/4/

በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ፦
ገብርኤል አብሠራ ለማርያም፤ ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ገብርኤል አብሠራ ለማርያም።

እግዚአብሔር ነግሠ፦
ገብርኤል አብሠራ ለማርያም፤ ተፈሥሒ ይቤላ፤ ኢሳይያስ ይቤላ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ ሰሎሞን ይቤላ ደብተራ።

ይትባረክ፦
ገብርኤል መልአክ መጽአ፤ ወዜነዋ ለማርያም ጥዩቀ፤ ሠናየ ዜና ከመ ይመጽእ አምላክ ላዕሌሃ።

ሰላም፦
አመ ፲፱ ለወርሀ ታኅሣሥ አመ ይትጋብዑ መላእክት፤ መልአከ ሰላሞሙ ውእቱ ገብርኤል፤ ገብርኤል ይስእል ምሕረተ፤ ለእንስሳ ሣዕረ ለሰብእ ተግባረ፤ መልአከ ሰላሞሙ ውእቱ ገብርኤል፤ ሚካኤል በየማነ ምሥዋዕ ይቀውም ዓውዶ፤ መልአከ ሰላሞሙ ውእቱ ገብርኤል፤ መልአከ ኪዳኖሙ ውእቱ ገብርኤል ስሙ።

አመላለስ፦
መልአከ ሰላሞሙ ውእቱ ገብርኤል/2/
መልአከ ኪዳኖሙ ውእቱ ገብርኤል ስሙ/4/

🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
ሥርዓተ ማኅሌት ዘታህሳስ ቅዱስ ገብርኤል
💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ፤ ብዑላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ፤ እመትትሐየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ፤ ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ሥጋየ ጌሠ። ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ።

ዚቅ
አድኅነነ እግዚኦ አምላክነ፤ ረዳኤ ኲነነ ወኢትግድፈነ፤ ወኢትትሐየየነ በዕለተ ምንዳቤነ፤ ርድአነ በኃይለ መላእክቲከ፤ ከመ ኢንትሐፈር በቅድሜከ።

ነግሥ
ሚካኤል ዘትቀውም በየማና ለማርያም ድንግል፤ ወበጸጋማ ገብርኤል አብሣሬ ትስብእቱ ለቃል፤ ዕቀቡነ ዘልፈ ለለመዋዕል፤ እንዘ ትሰፍሑ አክናፊክሙ ዘነበልባል፤ ወረድኤትክሙ አድኅኖ ዘይክል።

ዚቅ
አብሠራ ገብርኤል ለማርያም ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ።

ነግሥ
ሰላም ለከ ገብርኤል ላዕክ፤ ትስብእተ ፈጣሪ ዘትሰብክ፤ ኀበ ማርያም ልደተ አምላክ፤ ለዳንኤል ዘገሠሥኮ ጊዜ መሥዋዕተ ሠርክ፤ ምስዋዒ ለለሳዑ ባርክ ባርክ።

ዚቅ
እስመ ተለዓለ ዕበየ ስብሐቲከ መልዕልተ ሰማያት፤ እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ፤ ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን።

መልክአ ገብርኤል
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢይተረጎም ምስጢር፤ ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር፤ ገብርኤል ኪሩብ ፀዋሬ ዓቢይ መንበር፤ ሕዝቅኤል ዘነጸረከ በአምሳለ ብእሲ ክቡር፤ ምስለ ገጸ ላህም ወአንበሳ ወቀሊል ንስር።

ዚቅ
ገብርኤል ብሂል ብእሲ ወአምላክ፤ እምኀበ እግዚአብሔር ዘተፈነወ ላዕክ፤ ሥጋዌ ቃል ለድንግል ይሰብክ።

ወረብ
ገብርኤል ብሂል ብእሲ ወአምላክ/፪/
እምኀበ እግዚአብሔር ዘተፈነወ ላዕክ/፪/

መልክአ ገብርኤል
ሰላም ለአዕዛኒከ ኆኃተ ቃለ አብ ሕያው፤ ወለመላትሒከ ሰላም አምሳላተ ጽጌ ዘበድው፤ ኦ ገብርኤል መልአከ አድኅኖ ፍንው፤ አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው፤ አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ፫ቱ ዕደው።

ወረብ
አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ ሊቀ መላእክት አድኅነኒ ሊቀ መላእክት ዘአድኃንኮሙ/፪/
፫ቱ ዕደው አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ዘአድኃንኮሙ/፪/

ዚቅ
ዘአድኃኖሙ እምዕቶነ እሳት፤ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል፤ ከማሆሙ ያድኅነነ፤ እምኲሉ ዘይትቃረነነ።

ወረብ
እምዕቶነ እሳት 'ዘአድኃኖሙ'/፪/ ገብርኤል ሊቀ መላእክት/፪/
ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ዘአድኃኖሙ/፪/

መልክአ ገብርኤል
ሰላም ለአቊያጺከ ወለአብራኪከ ገሃደ፤ እለ ያቄርባ ወትረ ለአምላከ ሰማይ ሰጊደ፤ እግዚአ አእምሮ ገብርኤል ዘኢትፈቅድ ዕበደ፤ ጥበብ ሐነጸት በወርኅከ ውስተ ልበ አብዳን ማኅፈደ፤ ወአቀመት ላቲ ፯ተ አዕማደ።

ዚቅ
እግዚአ አእምሮ ወዜናዌ ጥበብ ዘከሠተ ለነ፤ ዘኮነ ሥውረ ውስተ ማዕምቀ ጽልመት፤ ወሀቤ ቃለ ትፍሥሕት ለእለ ይሰብኩ ዕበየ ኃይልከ።

ወረብ
እግዚአ አእምሮ ገብርኤል ወዜናዌ ጥበብ ዘከሠተ ለነ/፪/
ዘኮነ ዘኮነ ሥውረ/፪/

መልክአ ገብርኤል
አልቦ እምሰብእ ዘከማየ ዘይቴክዝ ነግሃ ወሠርከ፤ ወአልቦ እመላእክት ናዛዜ ኅዙናን ዘከማከ፤ ወበእንተዝ ኃሠሥኩ አእሚርየ ኪያከ፤ ኦ ገብርኤል ናዝዘኒ ወአስምዓኒ ቃለከ፤ ዕሴተ ጸሎትየ ዝንቱ ዘአቅረብኩ ለከ።

ወረብ
ወበእንተዝ ኃሠሥኩ አእሚርየ ኪያከ/፪/
ኦ ገብርኤል ናዝዘኒ ወአስምዓኒ ቃለከ/፪/

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ፤ አርእየኒ ገጸከ አርእየኒ ገጸከ ወአስምዓኒ ቃለከ፤ ነፍስየ ጥቀ ኃሠሠት ኪያከ።

ወረብ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ገጸከ አርእየኒ/፪/
ወአስምዓኒ ቃለከ ሊቀ መላእክት/፪/

ማኅሌተ ጽጌ
ፈትለ ወርቅ ወፈትለ ሜላት አመ በአጽባዕትኪ ተባየጹ፤ አምሳለ መለኮት ወትስብዕት እንዘ ኢየሐፁ፤ ተአምረ ብርሃን ማርያም ለፀሐየ ጽድቅ አንቀጹ፤ ጸገይኪዮ እንበለ አብ በሰሚዓ ቃሉ ወድምፁ፤ ለገብርኤል መልአክኪ ዘፍሡሕ ገጹ።

ዚቅ
መልአከ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል፤ መልአከ ፍሥሐ በእሳት ሥዑል፤ ሰበካ ለድንግል ምጽአቶ ለቃል፤ ወርቀ ወሜላተ እንዘ ትፈትል።

አመላለስ፦
መልአከ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል መልአከ ኃይል፤
መልአከ ፍሥሐ በእሳት ሥዑል፤

ወረብ
ቅዱስ ገብርኤል መልአከ ኃይል መልአከ ፍሥሐ በእሳት ሥዑል/፪/
ሰበካ ለድንግል ምጽአቶ ለቃል ወርቀ ወሜላተ እንዘ ትፈትል/፪/

አንገርጋሪ
ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ አስተርአያ ገብርኤል ግብተ፤ ወይቤላ እስመ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር፤ ወትቤሎ ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ።

አመላለስ
ወትቤሎ ይኩነኒ/፪/
በከመ ትቤለኒ ይኩነኒ/፬/

ወረብ
'ወእንዘ ትፈትል'/፪/ ወርቀ ወሜላተ/፪/
አስተርአያ ገብርኤል አስተርአያ ለማርያም/፪/

ዓዲ ወረብ
ወእንዘ ትፈትል ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ አስተርአያ ገብርኤል ግብተ፤
ወይቤላ እስመ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር፤

ወቦ ዘይቤ፦
ወእንዘ ትፈትል ወእንዘ ትፈትል ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ፤
አስተርአያ ገብርኤል አስተርአያ ለማርያም ፤

👉 እስመ ለዓለም ዘቅዳሜ ((ሰበክዎ በአፈ ኩሎሙ ነቢያት ))
እስመ ለዓለም
ክብሮሙ ለመላእክት ከመ መንኮራኲር፤ ወረደ መልአከ እግዚአብሔር ኀበ ማርያም ድንግል፤ ዘተናገሮ ለሙሴ በኀበ ዕፀ ጳጦስ፤ ዕፀ ጳጦስ ይእቲ ማርያም፤ ገብርኤል ሰበከ ላ ዜና፤ ዘለአኮ ኲሎ ነገራ።

አመላለስ
ገብርኤል ሰበከ ላ ዜና ገብርኤል ሰበከ/፪/
ዘለአኮ ኲሎ ነገራ/፬/

ወረብ
ክብሮሙ ለመላእክት ከመ መንኮራኲር ወረደ መልአከ እግዚአብሔር/፪/
ኀበ ማርያም ድንግል ዘተናገሮ ለሙሴ በኀበ ዕፀ ጳጦስ/፪/

ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩም፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉም ዕዳ አለብኝ፤
በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።
ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና። ሮሜ 1÷14

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

25 Dec, 21:25


To all those celebrating Christmas on December 25, may the Nativity of our Lord Jesus Christ fill your hearts with peace, love, and blessings. As we in the Oriental Orthodox tradition prepare to celebrate on January 7, let us all share in the joy of His holy birth, uniting in faith and love during this blessed season.


Herewith, let me share with you Christmas greetings from the 1st century onward:

1st–3rd Century

1. "Glory to God in the Highest" – Proclamation from Luke 2:14, used in early Christian worship.


2. "The Lord is Born" – Celebratory declaration of Christ’s Nativity.


3. "Peace Be with You" – Common greeting from John 20:19, reflecting the peace of Christ's birth.



4th–5th Century

4. "Gloria in Excelsis Deo" – Liturgical phrase central to Christmas worship (Liber Pontificalis).


5. "Christus Natus Est" – Latin for "Christ is born," in hymns and liturgies (Roman Missal).


6. "Pax Christi Vobiscum" – "The peace of Christ be with you," from Rule of St. Benedict.



6th–8th Century

7. "Gaudete in Domino Semper" – "Rejoice in the Lord always" from Philippians 4:4, linked to Advent and Christmas.



9th–12th Century

8. "Blessed Feast of the Nativity" – Used in liturgies and sermons (St. Bernard of Clairvaux).


9. "The Light of Christ Has Come" – Reflecting Christ as Light of the World (St. Gregory of Nyssa).



13th–15th Century

10. "Noel" – From Old French Noël (Latin natalis), used in medieval carols.


11. "Christmastide Blessings" – Popular in devotional texts like the Book of Hours.



16th Century

12. "Happy Christmas" – Common in Tudor-era letters and greetings.


13. "Blessed Christmas" – Emphasized spiritual reflection during the Reformation.



17th–18th Century

14. "God Rest You Merry" – Popularized in English carol "God Rest You Merry, Gentlemen."



19th Century

15. "Merry Christmas" – Gained popularity through Dickens’ A Christmas Carol (1843).



20th Century

16. "Season's Greetings" – Inclusive phrase from mid-20th-century holiday cards.


17. "Happy Holidays" – Neutral greeting reflecting multicultural awareness (1930s–1940s).


18. "Merry Xmas" – Modern shorthand popularized in media, derived from 16th-century usage.


19. "Warm Wishes for the Holidays" – Informal greeting in modern holiday cards.



21st Century

20. "Merry Christmas and Happy New Year" – Common in e-cards and social media.


21. "Stay Safe and Merry Christmas" – Adapted during COVID-19 to emphasize health.


22. Emoji greetings – Shorthand like 🎄🎅 for digital messaging.


23. "Sustainable Christmas" – Promotes eco-conscious celebrations.


24. "Happy Festivus" – Humorous alternative from Seinfeld (1997).

N.B The list is not from academic journals and peer reviewed articles & books but ChatGPT

Join me for updates👇

📢 I’m sharing posts on Orthodox Church teachings – join me for insightful updates! 🙏📖

http://youtube.com/@OrthodoxTewahedo-?sub_confirmation=1

https://t.me/OrthodoxTewahedoOT

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

05 Dec, 19:28


የእኚህን ወጣት ሊቅ ቴሌግራም ቻናል ብትቀላቀሉ በብዙ ታተርፋላችሁ፨
https://t.me/betremariyamabebaw

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

02 Dec, 17:57


https://youtu.be/bojBH9-TSsI

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

01 Dec, 04:19


ሲገባህ እንደ እነ ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ ''እኔ ከአባቶቼ አልበልጥም...፨'' (መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ፲፱÷፬) ትላለህ፨ በዚያውም አባትህን አክብር በሽበታሙ ፊት ተነሣ ያለውን የአምላክህን ሕግ በመፈጸም ( ኦሪት ዘጸአት ፳÷፲፪፤ ኦሪት ዘሌዋውያን ፲፱÷፴፪) የጽድቅ መንገድህን ታቀናለህ፨ ባይልልህ፣ እንደ ካም የአባትህን እርቃን ለማየት እና ለመግለጥ በመዳዳት እንደ ልጁ ከነዓን ልጆችህ የተረገሙ ይሆናሉ፨ (ዘፍጥረት ፱÷፳፩) ''ምድር(ም) ከአንተ የተነሣ የተረገመች '' ዘፍጥረት ፫÷፲፯ ትሆናለች፨

እግዜር ከርግማን ይሰውረን፨ አባቶችን ሳናከብር ነገ በእርግናችን የሚያከብረን ሳይሆን የሚዘባበትብንና ከትህትና ይልቅ ትዕቢትን ገንዘቡ ያደረገ ትውልድ ምድሪቱን በቁጣ እንድትከደን ያደርጋታል፨

Join me for updates👇

📢 I’m sharing posts on Orthodox Church teachings – join me for insightful updates! 🙏📖

http://youtube.com/@OrthodoxTewahedo-?sub_confirmation=1

https://t.me/OrthodoxTewahedoOT

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

30 Nov, 18:54


ልጇን ጥዑመ ስም ኢየሱስ ክርስቶስን፡ አባታችን ሆይ ፣እናቱን ጽዮንን፡ እናታችን ማርያም ሆይ ብለን እንጠራለን፤ [ማቴ ፮፥፱፣መዝ ፹፮፥፭] ይህም በትውልድ ሁሉ የጸሎት ሁሉ መጀመሪያና መጨረሻ ሆኖ በአባቶቻችን ሥርዓት ሆኖ ተሰርቶአልና ለዘላለምም ጸንቶ ይኖራል፨ የአቡነ ዘበሰማያት እና የበሰላመ ቅዱስ ገብርኤል ጸሎት ኃያል ነው፨እንጠቀምበት፨
እንኳን ለጽዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤አደረሰን፨🙌

Join me for updates👇

📢 I’m sharing posts on Orthodox Church teachings – join me for insightful updates! 🙏📖

http://youtube.com/@OrthodoxTewahedo-?sub_confirmation=1

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

30 Nov, 12:04


እኛ ''መሠዊያ አለን፤'' (ዕብ ፲፫÷፲)

እኛ ''መሠዊያ አለን፤'' (ዕብ ፲፫÷፲) ያውም ''ከጥንት ጀምሮ ከፍ ያለ የክብር ዙፋን'' (ኤር ፲፯÷፲፪) ከክርስቶስ ደምና ሥጋ ጋር ኅብረት ያለውን (አንድ የሆነውን) የምንባርክበትና የምንቆርስበት (፩ኛ ቆሮ ፲÷፲፮)፣ሙሴን ያነጋገረበት(ዘጸ ፳፭÷፳፪)፣''ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤'' (ኢያሱ ፩÷፭) ተብሎ ቃል የተገባልን ፣እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን የሰጣቸው ጥበበኞች እንደ ሆኑ እንደነ ባስልኤል የሰሩት (ዘጸ ፴፩÷፪፣፴፭÷፴፣፴፮÷፩፣፴፯÷፩)፣የአዛጦን ሰዎች ከጣዖቱ ከዳጎን ጋር ቢያስተካክሉትም(፩ ሳሙ ፭)፣ ጌታችን ሕግንና ነቢያትን ሳይሽር ያጸናልን (ማቴ ፭÷፲፯ ) እነሱ ልብ ባይሉት፣ ባይጠሩት፣ባይሹትም (ኤር ፫÷፲፮) ለኛ ግን ''የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑ ታቦት'' (ኢያሱ ፫÷፲፮) ነው እንጂ ጣዖት አይደለም። ''ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?'' (፪ኛ ቆሮ ፮÷፲፬) ምን ይደረግ? ጊዜው ነው። አውሬው ማደሪያውንና በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን የሚከፍትበት። (ዮሐ. ራእይ ፲፫÷፮)

ቀናተኛው አምላክ ሆይ( ዘዳ ፬÷፳፬):-በሞዓብ ምድር እስራኤል ስላመነዘረና ስለረከሰ፣ ለብዔልፌጎርም ስለተለየ በመቅሰፍት ፳፬ ሺህ እንደገደልህ(ዘኁልቁ ፳፭÷፩-፱) ለኃጥአን የመጣ እንዳያጠፋን ተማጸንህ።ታቦትህን ባላከበሩ የውስጥ አካላቸውን በእባጭ የመታህ(፩ ሳሙ ፭÷፩) በደዌ ሥጋ በደዌ ነፍስ እንዳትመታን እንለምንሃለን።ደፋሮቹ የቤተ ሳሚስ ሰዎች ታቦትህን ገልጠው ቢያዩ 5 ሺህ ሰባ ሰዎች በመቅሠፍት የመታህ፣የገደልህ፣ ታላቅ ልቅሶ እንዲሆን ያደረክ (፩ ሳሙ ፮÷፲፱-፳፩ ) የምድርና የሰማይ አባት ሆይ፦ሃገራችን የለቅሶ መንደር እንዳትሆን እንለምንሃለን።እግዚአብሔር ያከበረውን ሙሴን የተናገሩት፣ ያሙት አሮንና እኅቱ ማርያምን በለምጽ እንደመታህ (ዘኁልቁ ፲፪÷፩-፲፭) ካህናቱን ባልዋሉበት ዋሉ፤ ባልሆኑት ሆኑ ብለን በረከሰ የሐጢአት ምች እንዳንመታ ለአፋችንና ለከፋ ልባችን ጠባቂ መላክን ላክልን። የአሮን ልጆች ናዳብና አብድዩ ከቤተልሔም ያልሆነውን ሌላ እሳት አምጥተው ከጥናው ላይ ቢጨምሩበት ከሰማይ እሳት መጥታ እንደበላቻቸው (ዘሌ ፲÷፩-፪) እኛ ባሪያዎችህን ከሚመጣው እሳት ጠብቀን። የማኅቶቱን ሥርዓት፣ የመሥዋዕቱን/የቁርባኑን ሥርዓት ያቀለሉ፣ ሴቶችንም በመቅደሱ ዙሪያ ሆነው ያረከሱ አፍኒንና ፊንሐስን በጦርነት እንዲሞቱ እንዳደረክ(፩ሳሙ ፬÷፩-፲፰) በእርስ በርስ ጦርነት እንዳንተላለቅ እርዳን። የክህነትን ሥልጣን አቃሎ ጥና ይዞ በማጠኑ በለምጽ እንደተመታ ንጉሥ ዖዝያን (፪ ዜና ፳፮÷፲፯) በትዕቢት ለምጽ እንዳንመታ በቅንነትና በፍርሀት እንድንገዛልህ ማስተዋሉን ስጠን። በንዋያተ ቅድሳቱ ተዘባብቶ እንደቀለለ ንጉሥ ብልጣሶር (ዳን ፭÷፩-፴፩ ) በመስቀል፣ በጽላቱ/በታቦቱ ተዘባብተን በምድር በሰማይ እንዳንቀል ለብዎውን ስጠን። እግዚአብሔር በመረጠው ሙሴ ላይ በማመጻቸውና በትዕቢታቸው ምድር አፍዋን ከፍታ እንደዋጠቻቸው የኤልያብ ልጆች ዳታንና አቤሮን፣ ቤተሰቦቻቸውን፣ ለቆሬም የነበሩ ሰዎች ከብቶቻቸውን ከዚያ ያጥኑ የነበሩትን ፪፻፶ ሰዎች እሳት ከሰማይ ወጥታ እንደበላቻቸው (ዘኁልቁ ፲፮÷፩-፴፭) በሰማይ እሳት እንዳንቃጠል ከክፉ ትዕቢት ሰውረን። የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ታቦት በድፍረት እጁን ዘርግቶ ብይዝ የእግዚአብሔር ቁጣ እንደነደደበት የአሚናዳብ ልጅ ዖዛ (፪ ሳሙ ፮÷፩-፲፩) ዕጣ እንዳይደርሰን ቁጣህን በምሕረት መልሰው። ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን።

ከ፭ ዓመት በፊት
በቀሲስ ብዙአየሁ አምባዬ
ሲያትል ዋሽንግተን
ሰሜን አሜሪካ

Join me for updates👇

📢 I’m sharing posts on Orthodox Church teachings – join me for insightful updates! 🙏📖

http://youtube.com/@OrthodoxTewahedo-?sub_confirmation=1

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

30 Nov, 06:25


የትዕቢተኞችና የጠላቶቻችንም ፍጻሜም እንዲሁ ነው። ''ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ...ራስ እጆቹም ተቈርጠው በመድረኩ ላይ ወድቀው...ደረቱ ብቻውን ቀርቶ ነበር።'' (፩ኛ ሳሙ ፭፥፬)

እንኳን የታቦተ ጽዮን ኃይልና ክብር ለተገለጠበትና ጣዖት-ዳጎን ለተዋረደበት የመታሰቢያ በዓል ቀን አደረሳችሁ፤ አደረሰን፨ 🙏

Join me for updates👇

📢 I’m sharing posts on Orthodox Church teachings – join me for insightful updates! 🙏📖

http://youtube.com/@OrthodoxTewahedo-?sub_confirmation=1

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

29 Nov, 15:24


አመ ፳፩ለሕ ጽዮን መኃትው ዋዜማ -ሰላም @Memhir_sirak

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

26 Nov, 05:11


በጾም ወቅት ሩካቤ ይፈቀዳልን?
በውስጥ ለጠየቃችሁኝ በአንድ ላይ ልመልስ።
ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 24 ቁጥር 926 "በአጽዋማት ጊዜ፣ በወር አበባ ጊዜ፣ በአራስነት ጊዜ" ሩካቤ ማድረግ አይገባም ተብሏል። አጽዋማት ለሚለው በተለየ በሰሙነ ሕማማት፣ በዓርብ ረቡዕና ቅዳሜና እሑድ ሩካቤ ማድረግ ኃጢአት መሆኑ ተገልጿል። በሌሎች አጽዋማት ግን ፍትወት የተነሣበት ሰው ሩካቤ ማድረግ እንደሚችል "ወእለ ተርፋሰ አጽዋም። እመቦ ዘተመውዐ እምፍትወት ነዳዲት ወዘኢይትከሀሎ ላዕለ ተጋድሎታ ይደልዎ ሎቱ ከመ ያጥፍእ ኪያሃ" ተብሎ በግልጽ ተጽፏል።

የቻለ ሁሉንም አጽዋማት ቢከለከል በረከትን ስለሚያገኝ በአጽዋማት ይከልከል ተባለ። ለሚከብደው ደግሞ ከአጽዋማትም በተለየ ሰሙነ ሕማማትን (ዐቢይ ጾምን)፣ ዓርብ ረቡዕን፣ ቅዳሜና እሑድን ይከልከል (ፍት.ነገ.15፥593)። በሌላው የፈቀደውን ያድርግ ተብሏል።

© በትረ ማርያም አበባው

© በትረ ማርያም አበባው

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Nov, 02:52


''ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል...'' ዳን ፲÷፲፫፤፳፩]
''የመላእክት አለቃ ሚካኤል...'' [ይሁዳ ፩÷፱]
እንኳን ለበዓለ ሲመቱ አደረሳችሁ፤ አደረሰን፨ 🙏

Join for updates👇

📢 I’m sharing posts on Orthodox Church teachings – join me for insightful updates! 🙏📖

http://youtube.com/@OrthodoxTewahedo-?sub_confirmation=1

#ቅዱስ #ሚካኤል #kidusmichael

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

19 Nov, 02:19


https://www.gofundme.com/f/support-surafel-shiferaws-funeral-costs

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

18 Nov, 18:28


https://youtu.be/i4TtD-xHggc

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

17 Nov, 13:42


https://www.youtube.com/live/sJRVevouRvI?si=521_Sl1BxzW1XqJP

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

16 Nov, 06:27


Join me for updates👇

📢 I’m sharing posts on Orthodox Church teachings – join me for insightful updates! 🙏📖

http://youtube.com/@OrthodoxTewahedo-?sub_confirmation=1

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

14 Nov, 07:49


ስሙን ይሸከም ዘንድ ለእግዚአብሔርም የተመረጠ
ዕቃ እንደሆነ ንዋየ ኅሩይ ጳውሎስ፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ወንድ ልጅ ኅሩይን ሰጥቶናልና፡ አሁንም ተመስገን፨ እንደስሙ የተመረጠ ሆኖ፡ የአባቱንና ንግሥቲቱ እሌኒ፡ አስቀድሞ ያወጣችውን-መስቀሉን ይሸከም ዘንድ፡ ከተመረጠችልኝ እናቱ ኅሩይ- ልጄ ወዳጄ፡ ዛሬ ተወለደ፨
ረቡዕ ኅዳር ፬ ፣ ፳፻፲፯ ዓ.ም  ( እ.ኤ.አ Nov 13, 2024)

በምልጃዋ የተራዳቻት እመ አምላክ-ኪዳነ ምሕረትና ፈታሔ ማኅጸን-ቅዱስ ሩፋኤል ምስጋናችን ይድረሳችሁ፨ የምሥራች ነጋሪ ፡አባቴ አብሳሬ-ትፍስሕት የራማው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ምልጃህ ስላልተለየን እናመሰግንሃለን፨ አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ፡ እግዚአብሔር አባታችን ሆይ አንተንስ በባሕርይህ ምስጉን ነህ፨

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

12 Nov, 00:32


https://youtu.be/09Kd3X-2-dc

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

11 Nov, 17:12


https://youtu.be/LCLzNTErrSc

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

09 Nov, 20:15


Title: The Diachronic Development of the Dǝggʷā: A Study of Texts and Manuscripts of Selected Ethiopic Antiphon Collections


https://ediss.sub.uni-hamburg.de/handle/ediss/11228?fbclid=IwY2xjawGcodhleHRuA2FlbQIxMQABHeReYUKEDDV430UgYb-EPHRPp8oUwy9-qBxuQgy1bA3wfysGuvQm8suUBw_aem_8aG1xfnwJIeyxMCb7k6_Ng

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

09 Nov, 20:05


ማርቆስ ሐዋርያ ወንጌላዊ ሰማዕት
ሰበከ በሮም በመላው ዓለም
ሰበከ በእስክንድርያ በመላው ግብጽ

የቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ የልደቱ መታሰቢያ በየዓመቱ ጥቅምት ፴ ይከበራል፨ ሚያዚያ ፴ በዓለ እረፍቱ ነው፨ በረከቱ ይደርብንና ከሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በሮም ወንጌልን ሰብኳል፨


''ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፨'' [፩ኛ ጴጥሮስ ፭÷፲፫]

Join me for updates👇

📢 I’m sharing posts on Orthodox Church teachings – join me for insightful updates! 🙏📖

http://youtube.com/@OrthodoxTewahedo-?sub_confirmation=1

https://t.me/OrthodoxTewahedoOT

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

06 Nov, 03:31


''እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም
ቍስል እኛ ተፈወስን፨'' ኢሳ ፶፫÷፭
እንኳን ለመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ንግሥ አደረሰን፨
Join me for updates👇

📢 I’m sharing posts on Orthodox Church teachings – join me for insightful updates! 🙏📖

http://youtube.com/@OrthodoxTewahedo-?sub_confirmation=1

https://t.me/OrthodoxTewahedoOT

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

05 Nov, 04:13


https://youtu.be/ZK1YOTxsoV8

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

04 Nov, 07:24


https://youtu.be/qdduW7ENASg

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

04 Nov, 06:14


https://youtu.be/LVkVCmQi2Io

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Oct, 06:36


https://youtu.be/cZS-2TwMYuo

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

21 Oct, 01:59


In just 3 years, Saint Cyricus proved that salvation is not about a long life but about faithfulness to God, for "the last will be first, and the first will be last" (Matthew 20:16).
S: Own summary from Betremariam Abebaw 's recent post on Oct 20, 24

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

20 Oct, 03:21


#እንደ_አንተ_ይቅር_ባይ_ማነው?

✍️እንኳን ለሦስተኛው ሳምንት ጽጌ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

በሦስተኛው ሳምንት የሚባለውን ቃለ እግዚአብሔር ከመዝሙር እስከ ሰላም ንባቡንና ትርጓሜውን ከማብራሪያውና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሱ ጋር እነሆ!

👇መዝሙር  ከ፲  እስከ ፲፮ ቀን የሚባል።

በ፫ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ወሥነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ወከመ ወሬዛ ኃየል መላትሒሁ ጕርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ሰማየ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
በከዋክብት ሰማየ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኵሉ ዕለት
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ወኵሉ ይሴፎ ኪያከ።

            💥ትርጉም
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ከኖኅ ጋር ቃል ኪዳንን ያቆምክ (ያደረግኽ)
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ከኖኅ ጋር ቃል ኪዳንን ያቆምክ (ያደረግኽ) ለእስራኤል ልጆችም መናን ያወረድኽ
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረድኽ በአበቦችም ምድርን ያስጌጥኽ
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
በአበቦች ምድርን ያስጌጥኽ የምድረ በዳ እንስሳት አራዊትንም ከቅዱሳንህ ጋር ያስማማኽ
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ጉንጮቹ እንደ ወይፈን (ለጋ) ዋላ ናቸው፤ ጉሮሮው ጣፋጭ ነው፤ አረማመዱ እንደ ፌቆ ነው
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ሰማይና ምድርን የፈጠርኽ አንተ ነህ፤ ጨሐይን ጨረቃን የአስማማኽ አንተ ነህ
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ሰማይን በከዋክብት ያጋረድኽ፤ ምድርንም በአበቦች ያስጌጥኽ
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ሰንበትን ቀደሳት (ለያት) አከበራት ከፍ ከፍ አደረጋት ከዕለታት ሁሉ በላይ አደረጋት
እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው?
ሁሉ አንተን ተስፋ ያደርጋል።
            👇ማብራሪያ
👉ጠቅለል አድርጎ ለማብራራት ያህል፦

✔️መጀመሪያ ላይ ሁለት ጊዜ "እንደ አንተ ይቅር ባይ ማነው? (፪)" ማለቱ ለአጽንዖተ ነገር ነው።
በብሉይም በሐዲስም ደጊመ ቃል የተለመደ ነው። "አዳም አዳም፣ አብርሃም አብርሃም፣ ማርታ ማርታ፣ አልዓዛር አልዓዛር ፣ አማን አማን እብለክሙ" እንዲል
ነገሩን ለማጽናት ለማጉላት ደጋግሞ ይነገራልና ከእዚህም ሊቁ የእግዚአብሔርን ይቅር ባይነት አጉልቶ ለመናገር ገና ሲጀምር በደጊመ ቃል ጀምሮ ያንኑ ኃይለ ቃል አዝማች በማድረግ ይዘልቀዋል።
በዚህ መዝሙር እግዚአብሔር በቸርነቱ ምድርን ዳግመኛ በጥፋት ውኃ እንደ ማያጠፋት ለኖኅ ቃል ኪዳን መግባቱን ያስረዳናል (ዘፍ፱፥፲፩) ለእስራኤላውያን መና ከደመና አውርዶ መመገቡን (ዘጸ፲፮፥፴፭) በአበቦች ምድርን ማስጌጡን የሰማይም የምድርም ፈጣሪ መሆኑን (ዘፍ፩፥፩)  እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰማይና ምድርን ፈጠረ ሲል ሙሴ እንደ ወርቅ አንከብሎ እንደ ሸማ ጠቅልሎ መሆኑን ልብ ይሏል።
ሰንበትን የቀደሳት ያከበራት ከሌሎች ዕለታት ይልቅ ከፍ ከፍ ያደረጋትና ለእኛም ዕረፍት ትሆነን ዘንድ የሰጠን እሱ ባለቤቱ እግዚአብሔር መሆኑን (ዘፍ፪፥፫) ገልጦ ከነገረን በኋላ፤
#ሁሉ_አንተን_ተስፋ_ያደርጋል!
በማለት የፍጡራን ተስፋቸው እሱ እግዚአብሔር መሆኑን መስክሮ ይፈጽማል።(መዝ፻፵፭፥፲፭)
እውነት ነው ከእሱ ውጪ ማን ተስፋ አለን ሰውንማ በእየለቱ እያየነው አይደል ወገኖቼ ሲያደማን ሲያሳድደን እንጂ ምን ተስፋ ይሆነናል። "ተስፋየ እምንዕስየ" (ቅዱስ ያሬድ) እንዲል ከእናታችን ማኅፀን ጀምሮ ይበላችው ተጭኖ ፣ የጠጣችው አንዝዞ እንዳይገድለን በማድረግ ተስፋ የሆነን እግዚአብሔር አሁንም ተስፋችን ነው።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም
“በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። (ሮሜ፭፥፭) ብሏል።


             👇ዓራራት
"በኵሉ ጊዜ ወበኵሉ ሰዓት በኵሉ ሌሊት ወበኵሉ መዓልት እግዚኣ ለሰንበት አኰቴተ ነዓርግ ለመንግሥትከ ምድረ በጽጌ አሠርጎከ"
              👇ትርጉም
የሰንበት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በጊዜው ሁሉ በሰዓቱም ሁሉ በሌሊትም ሁሉ በቀንም ሁሉ ለጌትነትህ ምስጋናን እናቀርባለን። ምድርን በአበባ አስጌጥህ።
              👇ማብራሪያ

" እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤
አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ።
እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ።
ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው።
በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ።
በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው።(ዘዳ፮፥፬-፱)  እንዲል
ጊዜ ሳንወስን በሁሉም ጊዜያት ማመስገን እንዳለብን ያስረዳል።

           👇ዕዝል
"ልዑል ውእቱ እምልዑላን፤ መሐሪ ውእቱ ዘየዓርፎ ለዓለም፤ ጻድቅ ውእቱ ይባርክ ጻድቃነ፤ ጠቢብ ውእቱ ይመይጥ ስሑታነ፤ ሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት፤ አሠርገዋ ለምድር በጽጌያት"

           👇ትርጉም
ከልዑላን ይልቅ ልዑል ነው፤ ዓለምን የሚያሳርፈው እሱ ይቅር ባይ ነው፤ የባሕርይ አምላክ ነው ጻድቃንን "ንዑ ኃቤየ ቡሩካኑ ለአቡየ" ብሎ ያመሰግናቸዋል፤ ጠቢብ ነው ስሑታንን ይመልሳል (አዳምና ሔዋን ስተው ዕፀ በለስን በልተው በበለስ ቅጠል በተሸሸጉ ጊዜ "አዳም አዳም ወዴት አለህ?" ብሎ በጥበብ ሳያስደነግጥ ጠርቶ መልሷቸዋል ንስሐ  እንዲገቡ አድርጓልና "ጠቢብ ነው ስሑታንን ይመልሳል" አለ ሊቁ) ሰንበትን ለዕረፍት ሠራ ምድርንም በአበቦች አስጌጣት"

          👇ሰላም
በ፫ ናሁ አስተርአየ ጽጌ ነው። እንደ መጀመሪያው ሳምንት ነው ትዌድሶ ላይ ተጽፏል ።

👉የሊቁ በረከት ይደርብን  የእመቤታችን ምልጃ አይለየን!!!

👇በዚህ ዕለት በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ቅዱሳት መጻሕፍት።
             ፩ኛ,  ፩ቆሮ ፲፥፩  እስከ ፲፬
             ፪ኛ,  ራእይ ፲፬፥፩ እስከ ፮
             ፫ኛ,  የሐዋ ፬፥፲፱  እስከ ፴፩

ምስባክ፦  ጻድቅሰ ከመ በቀልት ይፈሪ
               ወይበዝኅ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ
                ትኩላን እሙንቱ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር
ወንጌል፦ ማቴዎስ ፲፪፥፩   እስከ ፴፪
ቅዳሴ፦ ዘእግዝእትነ (ጐሥዓ)

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

19 Oct, 15:59


''ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤''፩ኛ ተሰ. ፭፥፲፬
''ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።''፩ኛ ቆሮ. ፲፬፥፵
https://youtu.be/9DoBH0Nya3E

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

19 Oct, 06:42


https://youtu.be/lqGJ6kx49DQ

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

19 Oct, 04:19


Saint Photius, Patriarch of Constantinople

Join for updates👇

youtube.com/@OrthodoxTewahedo-

https://t.me/OrthodoxTewahedoOT

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

19 Oct, 04:12


Blessed Theophylact, Archbishop of Ochrid and Bulgaria

Join for updates👇

youtube.com/@OrthodoxTewahedo-

https://t.me/OrthodoxTewahedoOT

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

18 Oct, 21:31


የአቋም መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ የአቋም መግለጫ

“ትውልደ ትውልድ ይንእዱ ምግባሪከ ወይዜንዉ ኃይለከ - የልጅ ልጅ ሥራህን ይናገራሉ፤ ያመሰግናሉ፣ ከሃሊነትህን ይናገራሉ ያስተምራሉ” መዝ 144 ቁ 4

ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት፣ ዓለምአቀፋዊት የሆነቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያዊ ተልዕኮዋ ረጅም ዘመናትን ሰማያዊውን ጥበብንና ምድራዊውን ዕውቀትን በማስተማር፣ የሀገርና የወገንን እምነትና ፍቅር ምንነት ከተግባር ጋር፣ ሰላምና አንድነትና በማስፈን፣ ለሰው ልጅ ዘለዓለማዊ ድኅነት ሌሌት ከቀን ያለማቋረጥ ሰዓት ሳይገድባት፣ መልክዓ ምድር ሳይገድባት፣ የሰው ባሕልና ቋንቋ ሳይወስኗት፣ ትውልድን፣ ከትውልድ፣ ዘመንን ከዘመን፣ ሰማያውያን ከምድራውያን፣ ፍጡራንን ከፈጣሪ ስታገናኝ ኖራለች፡፡ ለሰው ዘር ጥበብን፣ ለትወልድ ታሪክና ትውፊትን፣ ስትቀምር፣ ነፃነትና ሰብዓዊ ክብርን በዐውደ ምኅረቷ ስታውጅ፣ በአባቶችና በሊቃውንት በሕየወት ሰሌዳ፣ በደመቀ ቀለም በቃልም በመጽሐፍም ስታስተጋባ እስከ አሁን አለች ወደፊትም ትኖራለች፡፡

ከዚህ መሠረታዊ የታሪክ ዕሴት በመነሣት ለዛሬው 43ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ደርሰናል፡፡

በዚሁ ጉባኤው በቆየባቸው ቀናት ውስጥ የቅዱስነታቸውንና የብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ አባታዊ መልእክቶች፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሪፖርት፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር አህጉረ ሰብከት ዘገባዎች፣ ከውይይት ሐሳቦች፣ ከአበው ሊቃነ ጳጳሳት መልእክቶች፣ ከቡድን ውይይትና ዘገባ በመነሣት ከቃለ ጉባኤ ሐሳብ በተጨማሪ በቅዱስ ሲኖዶስ ትኩረት ተሰጥቶባቸው በአጀንዳ ተቀርጸው ውይይትና ምክክር ተደርጎባቸው ውሳኔና መመሪያ ይደረግባቸው ዘንድ እኛም ለተፈጻሚነቱ የራሳችንን ድርሻ መወጣት እንድንችል ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የአቋም መግለጫ አቅርበናል፤

1. በጉባኤው መክፈቻ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ያስተላለፉፉልንን ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተቀብሎታል፣ ለተግባራዊነቱ ቃል ይገባል ፡፡

2. ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፉልንን አባታዊ መልእክት ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ ቃል እንገባለን፤፡፡

3. በብዙ የሀገራችን ክፍል ባለው የሰላም እጦት የተፈጠሩት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንያት የካህናት፣ የመነኮሳትና የምእመናን ሞትና ስደት በጥብቅ እያወገዝን በዚህ ታሪክ የማይረሳው በምድር ወንጀል፣ በመንፈሳዊው ዓለምና በሰማይ ኃጥያት የሆነ እኩይ ተግባር የተሰማራችሁ ሁሉ ወደ ርኃራኄ ልብ እንድተመለሱ ጉባኤው በአጽንኦት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

4. የሰላም ዕጦት ጉዳይ ምንም እንኳ ዓለም አቀፍ ቢሆንም ሀገራችንም በተከሰተው ግጭትና ጦርነት ምክንያት ሰላም ካጣች ሰንብታለች፣ ስለሆነም ቅዱስ ሲኖዶስ በዓለም የሚደነቅ፣ ለሀገር ተገን የሚሆን አስደነቂ ውሳኔ እንደሚወስን ተስፋችን ጽኑ ነው፣ ጸሎታችንም ነው፤ የአገልጋዮች እንባ የሚታበስበት፣ ለነገ ታሪክ የትውልድ ተወቃሽ ከመሆን ይልቅ፤ የሰላምና እርቅ ምሳሌ የምንሆንበት ከፍተኛ የሰላም ሥራ ልዩ የሆነ የሰላም ኮሚቴ ተቋቁሞ ዘላቂ ሰላምን ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን የሚያመጣ ሥራ እንዲሠራ ጉባኤው ያሳስባል፡፡

5. የዚህን ዓለም ተድላ ንቀው፣ ዳዋ ለብሰው ጤዛ ልሰው በገዳም ተወስነው ድምጸ አራዊቱን ግርማ ሌሊቱን ታግሰው ለመላው የሰው ዘር የሚጸልዩ ይህን ይደግፋሉ ያንን ይቃወማሉ የማይባሉ ገዳማውያን መነኮሳት ከየበዓታቸው ተጎትተው ወጥተው የተገደሉበት ሁኔታ በሀገራችን መከሰቱ ጉባኤውን እጅግ አሳዝኖታል፤ ይህ ጉዳይ ቀጣይነቱ እየታየ ስለሆነ የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን የሕግ ሥራ በመሥራት የሰው ልጅ ከአምላክ የተሰጠውን የመኖር መብት፣ የእምነት ነፃነት፣ የመዘዋር ተፈጥሯዊና ሰብዓዊ መብት በሀገራች እንዲከበር ያሳስባል፡፡

6. በታሪካችን ያላየነው ከአባቶቻችን ያልሰማነው በመጻሕፍት ያላነበብነው ከኢትዮጵያ ባሕልና ሥነ ልቡና ውጪ በሆነ መንገድ ሰዎችን ለገንዘብ ሲባል ማገት በተለይም ፊትና ኋላ፣ ግራና ቀኝ፣ እሳትና ውኃ ያለዩ ሕጻናት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው፣ ወጣቶችና አረጋውያን ሳይቀር እያተገቱ የሚሰቃዩበትና የሚደፈሩበት ሁኔታ የገጠመንን ፈተና ክብደቱን የሚያሳይ መሆኑ ይህ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መፍትሔ እንዲበጅለት ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፡፡

7. ጥላቻና የጥፋት ቅስቀሳዎች፣ በዜጎች መካከል አለመተማመንና መለያየት፣ ለሀገር አንድነትና የሕዝብ አብሮነት ጠንቅ፣ ለወደፊቱ አስጊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች የበዙበት፣ የትውልዱ የወደፊት በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ የመኖር ዋስትና እየጠፋ፣ በርካታ ወጣቶች በስደትና በመፈናቀል ላይ ያሉበት ሁኔታ በመኖሩ የጥላች ንግግር፣ ዘለፋና ያልተገባ ትችትና መናናቅ ማንንም የማያንጽ ክፉ ትምህርት፣ ለሀገርም፣ ለሕዝብም የማይጠቅም ሁሉንም የሚያጠፋ ስለሆነ በእንዲህ ያለ ተግባር መገናኛ ብዙኃን በመጠቀም የተሰማራችሁ፣ ሁሉ በሚያፋቅርና በሚያዋድድ ተግባር እንድትሰማሩ ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፣ ቅዱስ ሲኖዶስም ለዚሁ ትኩረት ሰጥቶ መመሪያና ውሳኔ ያወጣ ዘንድ በአጽንኦት እንጠይቃለን፡፡

8. በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 20 በእንተ ሰማዕታት የጌታችንን ትምህርት መሠረት በማድረግ በተሠራው ቀኖና ካህናትና ምእመናን ሰማዕትነትን የተቀበሉበትን ቀን መዘከርና ማክበር፣ የከበረ አጽማቸውን በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን በክብር ማስቀመጥ፣ ቤተሰቦቻቸውንና በእነሱ ሥራ ይተዳደሩ የነበሩ የሰማእታት ቤተሰብ በሚል መርዳት የተደነገገ ቀኖና ነው፤ ይህን በማድረግ የሰማዕትነት ዋጋን እናገኛለን፣ ቤተ ክርስቲያነን እናጸናለን፤ በዚህ ቀኖና መሠረትና ከሰብዓዊ ርኅራሄ በመነሣት በሰማዕትነት የተለዩን ወገኖች መታሰቢያቸው እንዲደረግ፣ ቤተሰቦቻቸውና ጉዳተኞችን ወላጆቻውን ያጡ የካህነትና የምእመንና ጨቅላ ሕጻናትና ያልደረሱ ልጆች፣ ያለጧሪ የቀሩ አረጋውያን የቤተ ክርስቲያንን እንክብካቤ በጥብቅ ይፈልጋሉ፤ ለዚህ መፍትሔ እንዲሆን በውጭና በሀገር ውስጥ ያሉ አህጉረ ሰብከት ያካተተ አስቸኳይ ዓለም አቀፍ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጥበት እያሳሰብን ለተግባራዊነቱም ሁላችንም ቃል እንገባለን፡፡

9. በአንዳንድ አካባቢዎች ሕግንና የአምልኮ ነፃነት ሰብዓዊ መብትን በመጣስ የመስቀል ደመራና የባሕረ ጥምቀት ቦታ መወሰድ ሃይማኖታዊ አለባበስና መስቀል መያዝን በመከልከል የአንገት ማዕተብን መበጠስ፣ በኦርቶዶክሳውያን ላይ እንግልትና ወከባ መፍጠር አሳዛኝ በመሆኑ ድገርጊቱን አጥብቀን እየተቃወመን በቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ውይይት እንዲደረግበት ጉባኤው ያሳስባል፡፡

10. ቤተ ክርስቲያን እንኳንስ ተናግራ ሰማች ሲባል የሚያስደነግጥ ግርማና መታፈር፣ መከበርና መወደድ የነበራት በመሠረተችው ሀገር የምትሳደድበት፣ የመሪዎቿ አባቶች ጥሪ የማይከበርበት፣ የሰላም ጥሪ ድምጽዋ የማይሰመባት፣ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በመፈተሸ ክብርና ልዕልናዋ እንዲመለስ በቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ውይይትና ጥልቅ ምክክር እንዲደረግ መፍትሔም እንዲፈለግለት ጉባኤ ያሳስባል፡፡

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

18 Oct, 21:31


11. ሙስና፣ ዘረኝነት፣ ጎሠኝነት፣ ቡድነኝነት፣ አድሎዓዊነትና ግለኝት በተመለከተ በጋራ በአንድ ድምጽ በመነሣት ይህንን ክብረ ነክና አጋላጭ፣ ለቤተ ክርስቲያን እድገትና ለሐዋርያዊ ተልእኮ እንቅፋት፣ የቤተ ክርስቲያን ማንነት ለሌላቸው ግለሰቦች መደበቂያ፣ በጥቂት ግለሰቦች በደልና ጥፋት በንጽሕና በቅድስና የሚያገለግሉ፣ ካህናትንና ሠራተኞችን የሚያሳፍሩ፣ ምእመናንን የሚያሸማቅቁ በመሆናቸው እነዚህን ክፉ ደዌያት ስም አጠራራቸውን ከቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለማስወገድ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በጥናትና በቁርጠኝነት ላይ የተመሠረተ፣ የጥፋት በራቸውን በዘላቂነት የሚዘጋ ሥልት እንዲቀይስ ጉባኤው ያሳስባል ፡፡

12. በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት እስከ አሁን ቤተ ክርስቲያን በፈረሱባት ሕንጻዎችና ቤቶች ምትክ ቦታ በመስጠት ጉዳቷን ለመቀነሰ የተደረገውን ጥረት ጉባኤው እያደነቀ፤ በተሰጡት ይዞታዎች ላይ በአጭር ጊዜ ግንባታውን በማካሄድ የአባቶችቻንን አሻራ መልሶ በመትከል፣ ይዞታውን ማስከበርና የተቋረጠውን ገቢ ማስቀጠል እንዲቻል ብርቱ ጥረት እንዲደረግ ጉባኤው እያሳሰበ፤ የኮሪደር ልማት የተባለው ጉዳይ በሌሎች የክልል ከተሞችም እየተስፋፋ ስለሆነ በቀጣይ ለሚነሡ የይዞታ ጥያቄዎች ለሚከሰቱ ችግሮች ከወዲሁ ዝግጅት እንዲደረግ፡፡

13. አዳዲስ አማኞችን አሳምኖ ለሥላሴ ልጅነት ማብቃት፣ የአዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት መተከል፣ መታነጽና መባረክ የታየው ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ እመርታ ሁሉን ያስደሰተ በመሆኑ ከዚህ በበለጠ አጠናክረን ለመሥራት ቃል እንገባን፡፡

14. የቅዱስ ባኮስ የቅድስና ዕውቅና ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ስትዘግበው የቆየ ቢሆንም ጽላት ተቀርፆ እንዲከበር መደረጉ አስደሳች ሲሆን ለሀገር በረከት፣ ለትውልድ የመንፈሳዊ ሕይወት አርአያ፣ ለቅድስና ፍኖት የሆኑ ነገርግን የማይታወቁ የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ቅዱሳን ታሪክና ገድል በማጥናት እንዲዘከሩ እንዲደረግ ጉባኤው ያሳስባል፡፡

15. በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የተከፈቱ መንፈሳውያን ኮሌጆችና የካህናት ማሠልጠኛዎችም በአጥጋቢ ሁኔታ ሥራ መጀመራቸው፣ በዚህ ዘርፍ በእጥፍ እየጨመረ የመጣው ዕድገትና ውጤት ጉባኤው ያደነቀ ሲሆን ወደ ሥራ ለመግባት በሂደት ላይ ያሉት በርካታ መንፈሳዊ ኮሌጆች እየተስፋፉ ያሉ የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ ዘመናዊ የትምህርት ተቋማት በአጠቃላይ ሁሉም ትምህርትን የሚመለከት ጉዳይ በትምህርት ኮሚሽን ተቋቁሞ ጥናት በማድረግ እንዲስፋፉ ጉባኤው ያሳስባል፡፡

16. በሰላም መታጣትና በቀኖና ጥሰት ምክንያት መላው ወለጋ አህጉረ ስብከት ለበርካታ ወራት ከማእከሉ ጋር ያለው ግንኙነት ተቋርጦ ከቆየ በኋላ በቅርቡ በሀገረ ሰብከቱ ሊቀ ጳጳስ ወደ መዋቅር መመለሳቸው ጉባኤውን በእጅጉ አስደስቷል፤ ስለሆነም ቀሪ ሥራዎች ተጠናቀው የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እንዲጠበቅ፣ በሌሎችም አካባቢዎች ለተፈጠሩት የመዋቅር ጥሰቶች ቀኖናዊ መፍትሔ እንዲበጅለት ጉባኤ ያሳስባል፡፡

17. ሐዋርያዊትና የክርስቶስ አገልጋይ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ቋንቋን በማክበር ታገለግልበታለች እንጅ በቋንቋም አትገደብም፤ ስለዚህ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ሐዋርያዊ ተልእኮ መፈጸሟ እንደተጠበቀ ሆኖ ለወደፊት የሁሉም መዓረገ ክህነት ሢመት፣ በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር ሥራ የኀላፊነት ምደባዎች፣ መሠረት እምነትን፣ ቀኖና ቤተክርስቲያንን፣ ዕውቀትና ሙያዊ ብቃትን ብቻ መሠረት ያደረገ ይሆን ዘንድ ጉባኤው በጥብቅ ያሳስባል፡፡

18. ሰበካ ጉባኤን ማጠናከር፣ ሰንበት ትምህርት ቤትን ማደራጀት፣ አብነት ትምህርት ቤቶች ማጎልበትና ማስፋፋት፣ ሕጎችና ደንቦችን በማዘጋጀት የተደረገውን ጥረት የሚያስመሰግን ሆኖ አሁን ወቅቱን የጠበቁ ሕጎችና ደንቦችን በማውጣት ሁሉም እንዲሠራበት ማድረግን፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣ የራስ አገዝ ልማትን ማሳደግና በገቢ ራስን መቻል፣ በጸደቀው የዐሥር ዓመቱ መሪ ዕቅድ መሥራት የቤተ ክርስቲያናችን ዓይነተኛ ተልእኮ በመሆኑ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ለመፈጸም ቃል እንገባለን፡፡

19. የቤተ ክርስቲያናችን የውጭ ሀገር አገልግሎት እየሰፋና እያደገ መምጣቱ በጉልህ የሚታይ ሲሆን ይህ እድገትና አደረጃጀት እንዲጠናከር፤ በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ተሳትፎ የበለጠ እንዲያድግ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ ጉባኤው ያሳስባል፡፡

20. ከውይይትና ከብፁዓን አበው መልእክቶች እንደተሰጠው መመሪያ የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና ለመመለስ፣ ለሀገራንችን ሰላምና ደኅንነት ለሰው ልጆች ሁሉ መልካም ግንኙነት የጋራ ጸሎት በኅብረት ይደረግ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ እንዲሰጥበት ጉባኤ በአክብሮት ይጠይቃል፡፡

በመጨረሻም እስከ ዛሬ ስንሰበሰብበት ከነበረው መቃረቢያ አዳራሽ ወጥተን ይህ ዛሬ የተገኘንበት አዳራሽ በአጭር ጊዜ አሁን ባለበት ደረጃ እንዲህ ጸድቶና ተውቦ የ43ኛውን አጠቃላይ ጉበኤ እንዲከናወንበት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አመራር መስጠታቸው ቁርጠኝነት ካለ ብዙ መሥራት እንደሚቻል ያሳየ፣ የሥራ ክትትልና አፈጻጸም አድናቆታችንን በመግለጽ ሐዋርያው እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖርና እንዳለው የአዳራሹ ቀሪው ሥራ ተጠናቆ በቅርቡ እንደሚመረቅ ተስፋችንን እንገልጻለን፡፡

ይህ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲፈጸም ያደረጉ በቅዱስነታቸው አባታዊ ርእሰ መንበርነት፣ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በሳልና የተረጋጋ አመራር ሁሉም መርሐ ግብሮች በተያዘላቸው ሰዓትና ጊዜ ተጠናቀው እንዲፈጸሉ የመሩንን አባቶች በረከታችሁ ይድረሰን እያልን፡፡

የጉባአው ዋና አዘጋጅ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ኀላፊና መላው ሠራተኞች፣ ሁሉም ተባባሪ አካላት በገንዘብም በጉልበትም ትብብር ያደረጉ ሁሉ በአጠቃላይ ጉባኤው አመስግኗል፡፡

ከሁሉም በላይ ለዚህ ለ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ ያደረሰንና ያስፈጸመን የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአሔር ምስጋና ይግባው አሜን ሎቱ ስብሐት ወባርኰት ወጥበብ፣ ወአኰቴት፣ ወኃይል ወጽንዕ ለአምላክነ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ቴሌቪዥን

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

15 Oct, 16:15


https://youtu.be/_h6A1gZN6EA

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

15 Oct, 02:03


የቅዱስ ፓትርያርክ መልእክት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ብፁዕ አቡነ አብርሃም 
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ
የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ 
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤
የተከበራችሁ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያውና የየድርጅቱ ኃላፊዎች፤ 
የአዲስ አበበ ሀገረ ስብከት ኃላፊዎች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ተወካዮች፤
ከሀገር ውስጥና ከውጭ የመጣችሁ የየሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎችና ተሳታፊዎች፤ 
በአጠቃላይ በ43ኛው ዓመታዊ ዓለም ዐቀፍ የጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ ለመሳተፍ በዚህ የተገኛችሁ በሙሉ፤
“አሠንዩ ፍኖተ ዘተሰመይክሙ ኖሎተ ከመ ትርዓዩ መርዔተ ከመ ዐሠርቱ ወክልኤቱ ሐዋርያቲሁ እለ መሀሩ በስሙ፡- ኖሎት የተባላችሁ ሆይ በስሙ እንዳስተማሩ እንደ ዐሥራ ሁለት ሐዋርያት መንጋውን ትጠብቁ ዘንድ መንገድን አሳምሩ” (ቅዱስ ያሬድ)
በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው ሹመት ወይም ኃላፊነት ካለ ተጠያቂነት የማይቀር ጉዳይ ነው፤ ምክንያቱም ሹመት የሚሰጠው ስራ እንዲሰራበት እንጂ እንዲሁ ለከንቱ ስላልሆነ ማለት ነው፡፡
ሹመት የመፈጸምና የማስፈጸም ሕጋዊ መሳሪያ ነው፤ መሳሪያውን በአግባቡ ከተጠቀምንበት የምንመሰገንበት፣ ያ ካልሆነ ግን የምንወቀስበት፣ ምናልባትም የምንቀጣበት አጋጣሚ ሊያስከትል ይችላል፤ ይህም በየጊዜው በሥዩማን ላይ ሲደርስና ሲፈጸም የምናየው እውነታ ነው፡፡ እኛ ካህናትና ምእመናን የእግዚአብሔርን መንግሥት ተልእኮ ልናስፈጽም በሕዝበ እግዚአብሔር ላይ የተሾምን ሥዩማን ነን፤ የመንግሥተ እግዚአብሔር ተልእኮ ከሰው ወገን አንድ ስንኳ እንዳይጠፋ መጠበቅ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የልጅነት ሥልጣን የተሰጠን እኛ ወደ መንግሥቱ በረት ያልገቡትን የማስገባት፣ ገብተው የወጡትን መልሶ የማስገባት፣ በበረቱ ያሉትን በጥሩ ውሀና በለመለመ መስክ በማሰማራት የመጠበቅ ኃላፊነት አለብን፡፡
 
ይህንን ኃላፊነታችን በትክክል ለመወጣት ከሁሉ በፊት እኛ ሥዩማን ተልእኮአችንን በውል መገንዘብ አለብን፤ ለተመደብንበት ተልእኮም በጽናት መቆም አለብን፣ በትጋትም መስራት ይጠበቅብናል፤ ከዚህም ጋር በእምነት በሥነ ምግባር በሥራ አፈጻጸም ከምንጠብቃቸው መንጋዎች በእጅጉ የላቅን ሆነን መገኘት በጣም አስፈላጊያችን ነው፡፡ በመንግሥተ እግዚአብሔር ተሹሞ ወደሥራ የተሠማራ ሰው ሥራው ፍጹም የተቃና ይሆንለት ዘንድ “ራሱን ክዶ” መስቀሉን መሸከም ግድ ይለዋል፤ ያለዚያ ውጤታማ መሆን አይቻልም፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት!
የተከበራችሁ እንግዶች!
አሁን ያለነው ሥዩማን በዚህ ዘመን ላለችው ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያት ሆነን የተሾምን ነን፤ ወደ በረቱ ያልገባ፣ ገብቶም የወጣ ካለ ማስገባትና መመለስ ያለውም በተመቻቸ መልካም አስተዳደር፣ በለመለመ ትምህርተ ወንጌል፣ በጥሩ ሥነ ምግባር አርአያ ሆኖ መጠበቅ ከኛ ይጠበቃል፡፡ ታድያ ይህንን በተግባር መተርጐም ችለናል ወይ? በጎቻችን አልቦዘኑም ወይ? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ከሁላችን ይጠበቃል፡፡ 
ይህ ዓቢይ ጉባኤ የተሰበሰበበት ምክንያትም ይህንን ተልእኮ ለማስፈጸም በሚደረገው ጥረት ያጋጠሙ ነገሮች ካሉ ለመስማትና ለመገምገም እንደዚሁም የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ በተቀመጠው መሪ ዕቅድ አማካኝነት ተልእኮውን ለመወጣት ነው፤ ‹‹የሚደርስበትን የማያውቅ የሚሄድበትን አያውቅም›› የሚለው ብሂል በአሠራራችን ቦታ እንዳይኖረው መጠንቀቅ አለብን፡፡
በአሁኑ ጊዜ የቤተ ክርስቲያናችን መዳረሻ የማይታወቅ አይደለም፤ ቤተ ክርስቲያናችን በቀጣዮቹ ዐሥር ዓመታት የት ልትደርስ እንደምትችል ቅዱስ ሲኖዶስ ባጸደቀው መሪ ዕቅድ በግልጽ ተቀምጦአል፤ ይህ መሪ ዕቅድ ሁላችንም ትኵረት ሰጥተን ለተግባራዊነቱ መረባረብ ይኖርብናል፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት!
የተከበራችሁ እንግዶች!
እንደ እውነቱ ከሆነ አሁን ባለን ክህነታዊ አገልግሎትና አስተደደር ክፍተቶች እንዳሉን የማይካድ ነው፤ ዘመኑ የፈጠረብን ጫና ሳያንስ በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጐደላቸው አሰራሮችም ለተልእኮአችን ከባድ ዕንቅፋት እየሆኑብን ነው፡፡ ሰበካ ጉበኤ የተቋቋመው በተዘረጋው መዋቅር አማካኝነት ቤተ ክርስቲያንን በማኅበረ ካህናት ወምእመናን የጋራ ጥበቃ ለአዲሱ ትውልድ ለማሸጋገር እንደሆነ ሁላችን አንስተውም፡፡ ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያናችን ይህን ያህል የመልካም አስተዳደር ክፍተት እየታየ የሰበካ ጉባኤ ዓላማ ግቡን መትቶአል ለማለት ስለማያስደፍር በዚህ ዙሪያ ያሉትን ችግሮች በሙሉ ሊቀርፍ የሚችል አሰራር ቀይሶ ችግሩን ለመቀልበስ በጥናት ላይ የተመሠረተ ዘላቂና ፈጣን መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል፡፡ 
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት!
የተከበራችሁ እንግዶች!
ያለፈው ዓመት በዝቋላ ገዳምና በሌሎች አካባቢዎች አበው መነኮሳት፣ ቀሳውስት እንደዚሁም በርከት ያሉ ምእመናን በግፍ የተገደሉበት ሆኖ አልፎአል፤ አሁንም ችግሩ እየቀጠለ ነው፤ በቅርቡም በምሥራቅ ሸዋ ከነቤተሰባቸው የተገደሉ አዛውንት ካህን ሁናቴ የችግሩን ቀጣይነት ይጠቁማል፡፡ 
               በመጨረሻም፤
በሀገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ ካህናትና ምእመናን ልጆቻችን፣ የቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና ሃይማኖት፣ ቀኖና እና ሥርዓት ተጠብቆ እንዲቀጥል ለማስቻል በሚደረገው ጥረት ሁላችንም ተባባሪ እንድንሆን፣ በሀገራችን ያለው አለመግባባት በሰላምና በውይይት ተፈትቶ ፍጹም ሰላም ይሰፍን ዘንድ በጸሎትና በአንድነት እንድትተጉ አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፍን 43ኛው ዓመታዊ ዓለም ዓቀፍ ጠቅላላ መንፈሳዊ ሰበካ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተከፈተ መሆኑን እናበስራለን፡፡ 
መልካም ጉባኤ ያድርግልን፤
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን፡፡ 
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፤

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (Orthodox Tewahedo)

12 Oct, 16:09


https://www.youtube.com/live/FJCNmu9tGe0

1,475

subscribers

1,392

photos

9

videos