አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ @asrat_woldeyes1 Channel on Telegram

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

@asrat_woldeyes1


በካምፓሳችን ውስጥ ያሉ አዳዲስ መረጃወችን ያገኙበታል!
ማስታወቂያ ማሰራት ወይንም ማንኛውንም ጥቆማ ለመስጠት የምትፈልጉ በ @Abiemieliek ወይንም @Gethiopia21 ማናገር ትችላላችሁ

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ (Amharic)

በዚህ ወቅታዊ ግንባር ላይ ያሉ 'አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ' የቴሌግራም ክፍል ተወሳጅ የሚያደርግ አካባቢ ነን። ከዚህ በታች 'asrat_woldeyes1' የሚለው የቴሌግራም ክፍል የተፈጥሮ የቴሌግራም እና የጤና እይት መለወጫ የሚለው ረሲቨሮችን አስተያየቶችን እና በአጭር የሚሰራ የዲጂታል መረጃዎችን አቀናብራል። 'አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ' ተጨባጭ የሆነ ቴሌግራም እና ጤና እይት እንዲሁም የሚያሳውቁ መረጃዎች ለአይንስ ካምፓስ የሚገኙ ተቆጣጣ፡፡

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

08 Feb, 13:55


የመሀል ሜዳ ካምፓስ የተማሪዎች ቅበላ ዝግጅት በፎቶ

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

08 Feb, 07:28


በአንድ ሰዓት ተኩል ቀዶ ጥገና 20.6 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕጢ የተወገደላቸው እናት

#Ethiopia | በማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል ከአንዲት እናት 20 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም የሚመዝን አላስፈላጊ ዕጢ መወገዱን ሆስፒታሉ ገለፀ።

ታካሚዋ የቦራ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት የ63 ዓመት የዕድሜ ባለ ፀጋዋ ወይዘሮ ካሱ ረዳኢ ናቸው።

በማህፀናቸው የእንቁላል ማምረቻ አካል ውስጥ በተፈጠረ አላስፈላጊ ዕጢ ምክንያት ወደ ሆስፒታሉ ያመሩ ሲሆን፤ አንድ ሰዓት ተኩል የወሰደ የተሳካ ከባድ ቀዶ ጥገና አድርገው ላለፉት 5 ዓመታት አብሯቸው የቆየው ዕጢ ተወግዶላቸዋል።

የቀዶ ጥገና ቡድኑ በማህፀንና የወሊድ ስፔሻሊስት ዶ/ር አክሊል አለማየሁ የተመራ እንደነበር የሆስፒታሉ ስራአስኪያጅ አቶ ገብረእግዚአብሔር ኪሮስ ለኢቲቪ ተናግረዋል።

@ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

07 Feb, 14:22


Debre Berhan University Asrat Woldeyes Health Science Campus holds internal curriculum validation workshop
===============================================
Debre Berhan University Asrat Woldeyes Health Science Campus Nursing and Midwifery Education and Service Directorate and Public Health school held internal curriculum validation workshop on Doctor of Philosophy in Midwifery and women’s Health, BSc in Environmental Health and BSc in Dietetics on 7 February, 2025.

Opening the workshop, Dr.Tewodros Kifleyohanes, Asrat Woldeyes Health Science Campus CEO, said that though the preparation of the curriculum started two years ago, it was delayed by different reasons which is beyond their efforts. He added that as a country they have lack of human resource in the field of Doctor of Philosophy in Midwifery and women’s Health and the program will be important and unique.

Getinet Ashenafi (PhD), Debre Berhan University Academic vice president, stated that this internal curriculum validation workshop is a new approach to them and will be motivated. He advised the designers to include the stakeholders from the industries and service sectors which can help to improve the quality of education. He also recommended the designers to align the curriculum along with differentiation of the University.

Solomon Hailemeskel (PhD) presented the curriculum on Doctor of Philosophy in Midwifery and women’s Health. The internal reviewers and the participants forwarded different questions, opinions and comment for the presenters which would help them to enrich the curriculum. Finally, Solomon Hailemeskel (PhD) replied to the questions and pledged to take all the comments in to consideration.

In addition, the Public Health school presented curricula on BSc in Environmental Health and BSc in Dietetics for discussion and reviewing.

@ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

07 Feb, 07:43


ሁሉንም የጤና ተቋማት ይመለከታል

gentamycine 80mg injection ጥቅም ላይ እንዳይውል ስለ ማሳወቅ

@ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

06 Feb, 17:13


በ ፸፭ (75) ዓመታቸው ወንድ ልጅ የወለዱት የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ መድኅን ሓጎስ

@ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

05 Feb, 19:59


የአሜሪካው ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ)፣ በዓለም ዙሪያ በእርዳታ ሥራ ተሠማርተው የሚገኙ አብዛኞቹ አሜሪካዊያን ሠራተኞቹ በሙሉ ከቀጣዩ ዓርብ ጀምሮ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የአሜሪካ መንግሥት አዟል። የድርጅቱን ቁልፍ ሥራዎች የመምራት ሃላፊነት ያለባቸው የተወሰኑ ሠራተኞችና አመራሮች ግን በተመደቡባቸው አገራት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆዩ መንግሥት ፈቅዷል። የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ዩ ኤስ ኤ አይ ዲን ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ጋር ለመቀላቀል የወሰነ ሲኾን፣ ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ማርኮ ሩቢዮም የተቋሙ ጊዜያዊ ሃላፊ ኾነው ተሹመዋል። ድርጅቱ በኢትዮጵያ በስብዓዊ ዕርዳታ፣ በምግብ ዋስትና፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና፣ በሥርዓተ ምግብና ሌሎች በርካታ ዘርፎች ድጋፎችን በማድረግ ይታወቃል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካ የውጭ ዕርዳታ እንዲቋረጥ ያስተላለፉት ትዕዛዝ የነፍስ አድንና አስቸኳይ ዕርዳታዎችን አይመለከትም ቢባልም፣ በኢትዮጵያ የሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ግን የትኞቹ ፕሮግራሞቹ ሊቀጥሉ እንደሚችሉ እስካኹን ዝርዝር መረጃ ይፋ አላደረገም። [ዋዜማ]

@ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

05 Feb, 14:48


በካምፓሱ ያሉ 5 ትምህርት ቤቶች በስራቸው ካሉ መምህራን ጋር ውይይት አካሄዱ
==============================================
28/05/2017 ዓ.ም(አ/ወ/ጤ/ሳ/ካ)፡ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ስር የሚገኙ 5 ትምህርት ቤቶች በስራቸው ካሉ መምህራን ጋር የ2017 ዓ.ም የግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀምና የቀጣይ ስራዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት፣ የህክምና ትምህርት ቤት፣ የፋርማሲ ትምህርት ቤት፣ የሜዲካል ላብራቶሪ ትምህርት ቤት እና የነርሲንግና ሚድዋይፈሪ ትምህርት ቤት በስራቸው ካሉ መምህራን ጋር እስካሁን ያለውን የመማር ማስተማር፣ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን በጥልቀት መገምገም መቻላቸውን ተገልጿል፡፡

መ/ር አውግቻው ሸዋሲናድ በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የጤና ትምህርት ኮርፖሬት ምክትል ዳይሬክተር የውይይቱን አላማ አስመልክተው እንደገለጹት ትምህርት ቤቶች ያላቸውን እምቅ የሰው ሀብት እና ሪሶርስ ተጠቅመው በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ላይ ውጤታማ አፈፃፀም እንዲያስመዘግቡ ያግዛቸዋል ብለዋል፡፡ እያንዳንዱ የስታፍ አባላት ያሉትን ስራዎች በትክክል እንዲያውቅ እና ባልተሰሩ ተግባራት ላይ ድጋፍ ለማድረግና አብሮ ለመስራት እንዲህ አይነት የጋራ የውይይት መድረኮች ሊፈጠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

አክለውም ትምህርት ቤቶቹ በፕሮግራም እውቅና/Accreditation/ ላይ እየሰሩ ስላለው ነገር እያንዳንዱ መምህር እውቅና ኖሮት ተገቢውን አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅበታል ነው ያሉት፡፡ የፕሮግራሞች እውቅና ማግኘት እንዱ የትምህርት ጥራትን መለኪያ መንገድ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ከዕለት ተዕለት ስራዎች ባሻገር እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ትምህርት ቤቶች በስራቸው ካሉ መምህራን ጋር ጥልቅ ውይይት ማድረጋቸው ጥሩ ጅማሮ እንደሆነ ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል፡፡

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

25 Jan, 06:51


በመሰረታዊ የድንገተኛ አደጋ ጊዜ እንክብካቤ እና በላብራቶሪ የጥራት አስተዳደር ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ
===========================================
ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም(አ/ወ/ጤ/ሳ/ካ)፡፡ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሀኪም ግዛው ሆስፒታል ለታካሚዎች በመሰረታዊ የድንገተኛ አደጋ ጊዜ እንክብካቤ ለመስጠት የሚስችልና ክህሎትን የሚያስጨብጥ ስልጠና እንዲሁም በላብራቶሪ የጥራት አስተዳደር ዙሪያ ለጤና እና ላብራቶሪ ባለሙያዎች በካምፓሱ የስልጠና ማዕከላት ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡

በሁለት መልኩ ስልጠናዎች እየተሰጡ ሲሆን አንደኛው ድንገተኛ አደጋ ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል ለሚመጡ ታካሚዎች የጤና ባለሙያው ወዲያውኑ ህክምናውን ለመስጠት የሚያስችለውን ክህሎትና እውቀት እንዲኖረው ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ይህም የአለም ጤና ድርጅት እና አለማቀፍ ቀይመስቀል ማህበር ያዘጋጀውን መሰረታዊ የአደጋ ጊዜ እንክብክቤ ታሳቢ ያደረገ ስልጠና ነበር፡፡

ሌላኛው ስልጠና ደግሞ በአለማቀፍ የላብራቶሪ ጥራት (ISO)ስታንዳርድ መሰረት የሀኪም ግዛው ሆስፒታል ለታካሚዎች እየሰጠ ያለውን የላብራቶሪ አገልግሎት ጥራት ለማሻሻል፣ እርካታን ለማረጋገጥ፣ አመኔታን ለመጨመር የሚረዳ እና የባለሙያውን አቅም የሚያጎለበት ስልጠና መሆኑን በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የህክምና ላብራቶሪ ትምህርትና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዜናወርቅ ሳህሌ ገልጸዋል፡፡

በሆስፒታሉ ለሚገኙ የላብራቶሪና የጤና ባለሙያዎች፣ ከደብረብርሃን ከተማና ከሰ/ሸዋ ዞን ጤና መምሪያዎች ስር ካሉ ጤና ጣቢያዎች ለተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች እና ለካምፓሱ የተማሪዎች ክሊኒክ ባለሙያዎች ስልጠናው መሰጠቱ ታውቋል፡፡

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

24 Jan, 15:59


ማስታወቂያ
========
ቀን 16/05/2017

ለመ/ሜዳ ካምፓስ በተለያዩ የሥራ መደቦች ላይ ተወዳድራችሁ ከ70% የጽሑፍ ፈተና ወስዳችሁ 35 እና በላይ ውጤት ያመጣችሁ ቃለ መጠይቅ በ17/05/2017 ስለሚሰጥ በዋናው ግቢ ጧት 2:30 በብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ቢሮ እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡


https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1
https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1
https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

24 Jan, 08:37


በካምፓሱ የማስተማሪያ ንድፍና የኦንላይን ትምህርት አሰጣጥ ስልጠና ተሰጠ
===========================================
ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም(አ/ወ/ጤ/ሳ/ካ)፡ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የማስተማሪያ ንድፍና የኦንላይን ትምህርት አሰጣጥ ዙሪያ ለተመረጡ የካምፓሱ መምህራን የአራት ቀን ስልጠና ተሰጠ፡፡

ቴዎድሮስ ክፍለዮሐንስ(ዶ/ር) የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት የስልጠናው ዋናው ዓላማ ሰልጣኞች አሁን ያለውን ስርዓተ ትምህርት ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ በመታገዝ ወደ ኦንላይን ስልጠና የሚቀይሩበትን እውቀትና ክህሎት ለማሰጨበጥ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ሌላው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ካምፓሱ የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ማዕከልን በሚያስጀምርበት ወቅት በራሱ ባለሙያዎች ስርዓተ-ትምህርቱን እንዲቀርጽና ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎችን ተጠቅሞ አሰራሩን የማዘመን ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

ደረጀ አንዳርጌ(ዶ/ር) በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰርና የማስተማሪያ ንድፍ አውጭ እና እሱባለው ተስፋሁን(ዶ/ር) በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የአጋርነትና ትብብር ዳይሬክተርና ተባባሪ ፕሮፌሰር ስልጠናውን በጋራ ሆነው ሰጥተዋል፡፡ ዶ/ር እሱባለው ተስፋሁን እንደገለጹት እንደ ካምፓስ ለሚቋቋመው የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ማዕከልን ወደ ስራ ለማስገባት እና ደረጃውን የጠበቁ የስልጠና ማነዋሎችን ገፅ ለገፅና በኦንላይን ለማዘጋጀት እገዛ የሚያደርጉ ባለሙያዎችን ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል፡፡ አክለውም በስልጠናው ወቅት ሰልጣኞች በሰለጠኑት መሰረት የስልጠና ማነዋል እንዴት እንደሚዘጋጅ ተግባራዊ ልምምድ አድርገዋል ነው ያሉት፡፡

በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑት በካምፓሱ የህክምና ትምህርትና አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር አሰፋ ፋንታሁን በበኩላቸው አንድ መምህር ለተማሪዎቹ የሚሰጠውን የትምህርት አይነት በምን መልኩ መስጠት እንዳለበት ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ነበር ብለዋል፡፡ አያይዘውም ስልጠናው ራሳችንን እንድናዘምን፣ ወደ ፊት የተሻሉ ቴክኖሎጅዎችን ተጠቅመን ስራችንን ለማቃለል የሚያግዝ ተግባር ተኮር እንደነበር ተናግረዋል፡፡

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

22 Jan, 13:42


ሀኪም ግዛው ሆስፒታል ነፃ የጥሪ ማዕከል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ
====================================
ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም(አ/ወ/ጤ/ሳ/ካ)፡ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ስር የሚገኘው ሀኪም ግዛው ሆስፒታል በ8326 የጥሪ ማዕከል ነፃ የህክምና እና የጤና መረጃ አገልግሎቶችን መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ዶ/ር ክብረት ሀይለመስቀል በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሀኪም ግዛው ሆስፒታል የህክምና ባለሙያና የጥሪ ማዕከሉ አስተባባሪ እንዳሉት ሆስፒታሉ አሁን ላይ በ8326 ነፃ የጥሪ ማዕከል አገልግሎትን በማስጀመር ለህብረተሰቡ የጤና ትምህርትን መስጠት፣ የተለያዩ ጤና ነክ መረጃዎችን ማሰራጨት፣ የህክምና ቀጠሮ ማስያዝና ማስቀየር እና በሆስፒታሉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ባሉበት ቦታ ሆነው ለማወቅ እንዲችሉ አድርጓል ብለዋል፡፡

አክለውም ታካሚዎች ቀጥታ ወደ 8326 የጥሪ ማዕከል ላይ በመደወል የተለያዩ ጤና ነክ መረጃዎችን በቀላሉ የሚያገኙበት እንዲሁም የሚፈልጉትት ስፔሻሊስት ሀኪም ቀጥታ በማገናኘት ስለጤናቸው መረጃ የሚጠይቁበትና አጥጋቢ ምላሽ የሚያገኙበትን ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ነው ያሉት፡፡ ሀኪም ግዛው ሆስፒታል እየሰጠ ያለውን የህክምና አገልግሎት የበለጠ ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆን፣ ጥራቱን ተጠብቆ እንዲቀጥል እና የታካሚዎችን አላስፈላጊ ወጪና እንግልት የሚያስቀር አገልግሎት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አክሲስ(Healthcare System Impact Syndicate Africa - ACSIS) ከተባለው ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የጥሪ ማዕከሉ እንደተቋቋመና አሁን ላይ 2 የጤና ባለሙያዎችና 2 ረዳት ባለሙያዎችን ይዞ ከጠዋቱ 2፡30-11፡30 ሰዓት ብቻ አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ ገልጸው በቀጣይ 24 ሰዓት ሙሉ አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አስተባባሪው አስታውቀዋል፡፡

ይህን መሰል አገልግሎት በመንግስት ሆስፒታሎች ብዙም ያልተለመደና አዲስ አሰራር በመሆኑ ህብረተሰቡ በአግባቡ እንዲጠቀምበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

22 Jan, 10:45


አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሀኪም ግዛው ሆስፒታል የ2017 ዓ.ም የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ
===============================
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሀኪም ግዛው ሆስፒታል የ2017 ዓ.ም የ6 ወር እቅድ አፈፃፀምን የካምፓሱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሆስፒታሉ የስራ ኃላፊዎች፣ የትምህርት ክፍል ተጠሪዎች፣ የአስተዳደር ዘርፍ ስራ አስፈጻሚዎችና ቡድን መሪዎች በተገኙበት ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ሪፖርት ቀርቦ ግምገማ አካሄደ፡፡

የ6 ወር የስራ አፈፃጸሙን ሪፖርት ያቀረቡት በሀኪም ግዛው ሆስፒታል የጤና መረጃ ስርዓት ዳይሬክተር በአቶ አስማረ ማማር እና የሆስፒታሉ የአገልግሎት ጥራት የተመለከተ ሪፖርት ዶ/ር ተወደደው ባልከው ቀርበዋል፡፡ ሁለቱም አቅራቢዎች በሪፖርታቸው እንደገለጹት በሆስፒታሉ እተካሄዱ ያሉ የለውጥ ስራዎችን፣ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን፣ መስራት እየተቻለ ያልተከናወኑ ተግባራትን፣ ያጋጠሙ ችግሮችንና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን እንዲሁም በቀጣይ መስተካከል አለባቸው ያሏቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

የሆስፒታሉን የህክምና አገልግሎት ጥራት ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ አበረታች ስራዎችን፣ የመድሃኒትና ህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት፣ የቀዶ ህክምና አገልግሎት፣ የተመላላሽ፣ የተኝቶ፣ የድንገተኛና ፅኑ ህክምና፣ የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት፣ የላብራቶሪ አገልግሎት እና በመሳሰሉት የሆስፒታሉ አገልግሎቶች ላይ ጥሩ አፈፃፀም እንደነበር በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡ ሆስፒታሉ በሚሰጣቸው የህክምና አገልግቶች ጥራትን ቀዳሚ መስፈርት በማድረጉ ከሌሎች ተቋማት እውቅናን እንዳገኘ በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል፡፡

ከመድረኩ ተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎች እጥረት፣ የፋይናንስና የሰው ኃይል እጥረት፣ የአካዳሚክና ክሊኒካል ኢንተግሬሽንን ያመጣውን ለውጥ የመረዳት ችግር፣ የዳታ ጥራት ችግር፣ የክፍያዎች መለያየት፣ የመረጃ አያያዝ ሌሎች ችግሮች መኖራቸው ተነስቷል፡፡ ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የቀረቡትን ጥያቄዎችና አስተያየቶች በተገቢው መልኩ ምላሽ እንደሚሰጥባቸውና በቀጣይ እንደሚቀረፉ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ቴዎድሮስ ክፍለዮሐንስ እና በሀኪም ግዛው ሆስፒታል የክሊኒካል ኮርፖሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ዘመድ ገለታ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄና አስተያየት ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ሀላፊዎቹ በሰጡት ማብራሪያ በሪፖርቱ ግምገማ ወቅት የተነሱት አስተያየቶችንና ጥቆማዎች ትክክል የሆኑትን እንድትወስዱ፣ያልተካተቱትን እንድታካትቱ በማለት ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ የአካዳሚክ ክሊኒካል ኢንተግሬሽን ላለፉት ሶስት አመታት ሲሰራበት የቆየና በርካታ ልምድ የተወሰደበት መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው በምላሻቸው ገልጸው ይህንን የማያውቅ ካለ የስራ ክፍሎች ለሰራተኞቻቸው የማሳወቅ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ ለጤና ባለሙያዎች የሚከፈለው የክፍያ ሁኔታም ቢሆን ከማንኛውም የመንግስት ሆስፒታል የተሻለ እንደሆነ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1
https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1
https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

22 Jan, 10:39


From school of medicine

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

19 Jan, 18:50


ባህረ ጥምቀቱ በፎቶ

የዓመት ሰው ይበለን🥰

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

18 Jan, 12:46


ውድ የግቢያችን ተማሪዎች እንኳን ለከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ🥰

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

18 Jan, 11:07


Hey How Are you .Am Dr Walelign staff of Asrat weldeyes health sience college . I Am  doing My residency on Neurology at Addis Ababa University blacklion Hospital currently . I Am the Chief resident and final Year resident.  if you guys want Neulogical consultation , EEG reading , Electrophysiology consultation , Neurologic imaging and any help regarding neurology i am happy to help our college .
share for others also
thank you .

@Waleworku

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

17 Jan, 19:16


ኮስት ሼሪንግ‼️
መንግስት በዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የወጪ መጋራት ክፍያ መጠን ጭማሪ አድርጓል‼️


መንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች በወጪ መጋራት ፖሊሲ የሚከፍሉትን ክፍያ እስከ አምስት ዕጥፍ ገደማ አሳድጓል።
የወጪ መጋራት ክፍያ የተጨመረው፣ የአንድ ተማሪ የቀን የምግብ በጀት ከ22 ብር ወደ 100 ብር መጨመሩን ተከትሎ ነው ተብሏል። በአዲሱ ጭማሪ መሠረትም፣ ለአራት ዓመት የዩንቨርሲቲ ቆይታ አንድ ተማሪ ይከፍለው የነበረው ከ25 ሺሕ ብር የማይበልጥ ክፍያ ወደ 120 ሺሕ ከፍ ብሏል። 35 ሺሕ ብር ገደማ ይከፍሉ የነበሩት አምስት ዓመት የሚማሩ የምህንድስና ተማሪዎች ደግሞ ወደ 150 ሺሕ ብር አካባቢ እንዲከፍሉ ይደረጋል። ትምህርት ሚንስቴር አዲሱን የወጪ መጋራት ተመን ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገና ባይልክም፣ በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቅሷል። 

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

17 Jan, 12:20


አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በ4 ትምህርት ክፍሎች እውቅና ለማግኘት የተሰሩ ስራዎችን ግምገማዊ ውይይት አካሄደ
=======================================
ጥር 09/2017 ዓ.ም(አ/ወ/ጤ/ሳ/ካ)፡ ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በ4 ትምህርት ክፍሎች ማለትም በህክምና፣ በአንስቴዢያ፣ በነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ ፕሮግራሞችን በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማቅረብ ግምገማዊ ውይይት አካሄደ፡፡

የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ቴዎድሮስ ክፍለዮሐንስ የውይይት መድረኩን ሲከፍቱ እንደተናገሩት እውቅና የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የግድ ስለሆነ ጠንክረን መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡ እውቅና ማግኘት ሂደት ስለሆነ ይህንን ሂደት ደግሞ የተለያዩ የአሰራር ማኑዋሎችን፣ ስታንዳርዶችን፣ ፖሊሲዎችንና ጋይድላይኖቸን በመጠቀም የማዳበርና የማስተዋወቅ ስራ መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

አያይዘውም የውይይት መድረኩ ዓላማው የእርስ በርስ የመማማሪያ መድረክ መፍጠርና ለተቀሩት ስድስት ትምህርት ክፍሎች እውቅና ለማግኘት የሚያስችላቸውን አሰራር ከዚህ መድረክ ልምድና ተሞክሮ በመውሰድ መተግበር እንዲችሉ ግንዛቤ መፍጠር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አራቱም ትምህርት ክፍሎች ለእውቅናው የሚያበቃቸውንና ያከናወኗቸውን የቅድመ ዝግጅት ተግባራቶች በጥንካሬና በድክመት ያቀረቡ ሲሆን አሁን ላይ የደረሱበትን ደረጃና በቀጣይ የሚጠበቅባቸውን ተግባራቶች በዝርዝር ለውይይት አቅርበዋል፡፡

በመቀጠልም በቀረቡት የትምህርት ፕሮግራሞች የእውቅና የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ላይ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው በሚመለከታቸው የኮሚቴ አባላትና የስራ ሀላፊዎች ሰፋ ያለ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ካምፓሱ በሚሰጣቸው የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ የሚጠበቀውን የትምህርት ጥራት መስፈርት ለማሟላትና እውቅና ለማግኘት በትምህርት ክፍል ደረጃ፣ በኮሌጅ ደረጃ እና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ መሰራት ያለባቸውን ጉዳዮች እንዲሰሩ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡

ሁሉም የትምህርት ክፍሎች የሚጠበቅባቸውን መስፈርት አሟልታው በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ለማግኘት እና ከሌሎች አቻ ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ ለመሆን በኢትዮጵያ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ተመዝነው የብቃት ሰርተፍኬት ማግኘት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡ ለዚህም የመምህራን ቁርጠኝነትንና እና ለመማር ማስተማር ስራው አጋዥ የሆኑ የስራ ክፍሎችን ተሳትፎን ይፈልጋል ነው የተባለው፡፡

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

14 Jan, 14:44


Merry ምግብ ቤት

ምን ይፈልጋሉ ?

🍝ፓስታ በአትክልት
🍲ፓስታ በስልስ
🍜ሽሮ
🍛በየአይነት
🍜ተጋቢኖ
🫓እንቁላል ፍርፍር
🍱ስጋ ፍርፍር
🍲ጥብስ
🫕ቀይወጥ
🌭normal እርጥብ
🌭special እርጥብ

☕️🥤እንዲሁም ለስላሳ መጠጦች ከቡና ጋር, takeaway አለ

🩸🍔🍔🍔በተጨማሪም በርገር መጀመራችንን ስንገልጽ በደስታ ነው።

እሮብ ቀን ለሚመጡ የእርጥብ ደንበኞቻችን ታላቅ ቅናሽ አድርገን እየጠበቅን ነው።እንዳያመልጥዎ!

🕹አድራሻችን

ከአስራት ካምፓስ ወደ ምኒልክ አደባባይ በሚወስደው መንገድ ላይ ከዶ/ር ፍስሃ ክሊኒክ አጠገብ

☎️ስልክ   0945454551 ይደውሉልን።

https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1
https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1
https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

13 Jan, 13:37


ክፍት የስራ ማስታወቂያ
#ሼርር

https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

07 Jan, 18:09


በቃላችን መሰረት ኮሜንት ካደረጉት ተማሪዎች መካከል ዕጣው የወጣለትን የመጀመሪያ አካውንት የ25 ካርድ ሸልመናል። እናመሰግናለን

ቀጣይም በየወሩ ለመሸለም አስበናል እና channelun share እያደረጋችሁ ኮሜንት ማድረጋችሁን አትርሱ።

https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1
https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1
https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

06 Jan, 19:22


ሉቃ 2:
8" በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።
9 እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ።
10 መልአኩም እንዲህ አላቸው፡— እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
11 ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
12 ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።
13 ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ።
14 ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ፡ አሉ።
16 ፈጥነውም መጡ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ።
"


ለመላው የክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።

ቻናላችን በቀጣይ ታማኝ እና ፈጣን መረጃዎችን ማድረሱን እንደሚቀጥል እያሳወቅን በ comment እንኳን አደረሳችሁ ብሎ ከጻፉልን ውስጥ አንድ ሰው መርጠን የ25birr card የምንሞላ ይሆናል። እስከ 29/4/17 ማታ 12:00 ድረስ ኮሜንት መጻፍ ይቻላል። መልካም ዕድል።

ሊንኩን share ማድረጋችሁን አትርሱ

https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1
https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1
https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

06 Jan, 17:25


የካምፓሱ ተማሪዎች የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተፈናቃዮች የምግብ እና አልባሳት ድጋፍ አደረጉ
=========================================
ታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም (አ/ወ/ጤ/ሳ/ካ)፡ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ተማሪዎች አስተባባሪት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ በደብረብርሃን ከተማ ባቄሎ ቀበሌ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ለተጠለሉ ህጻናትን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና አረጋውያንን የምግብ እና አልባሳት ድጋፍ ተደረገ፡፡

በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የተማሪዎች ህብረት ተወካይ ፀሐፊ ተማሪ አቤኔዘር ሀይለማሪያም እንደገለጹት በተማሪ ህብረት አስተባባሪነት የካምፓሱን ተማሪዎች በማወያየት በዛሬው እለት ለቁርስ ተብሎ የተዘጋጀውን ዳቦ፣ ቅንጨ እና ፍርፍር በባቄሎ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ እና ቁጥራቸው ከ2000 በላይ የሆኑ ሰዎችን የመመገብ መርሃ-ግብር ተካሂዷል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ከተማሪዎች የተሰበሰቡ አልባሳትን ድጋፍ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡

በጎ ስራ ለመስራት ሰው መሆን ብቻ በቂ እንደሆነ የገለፁት ተማሪ አቤኔዘር ከዚህ ቀደምም በካምፓሱ ተማሪዎች አማካኝነት የአልባሳት፣ የገንዘብ፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ በተለያዩ የመጠለያ ካምፓ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል፡፡

አቶ አክሊሉ ጌታቸው በባቄሎ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፓ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ በበኩላቸው ከምስራቅ ወለጋና ከምዕራብ ሸዋ ከ16 ወረዳዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት የተፈናቀሉ ከ5 ሺህ 57 በላይ ሰዎች በካምፑ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ከነዚህ መካከል ከ3 ሺህ ሁለት መቶ በላይ የሚሆኑት ተፈናቃዮች ህፃናት፣ የሚያጠቡ እናቶች፣ አዛውንቶች እና አካል ጉዳተኞች መሆናቸውን ጭምር ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም አቶ አክሊሉ በካምፓሱ ተማሪዎች አማካኝነት በተካሄደው የምገባ መርሓ-ግብር እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ተባብረው በመጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚኖረውን ተፈናቃይ ከተረጅነት እንዲወጣና በቋሚነት ህይወቱን መምራት እንዲችል የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1
https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1
https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

05 Jan, 16:43


ደብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ እና አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት(A.H.R.I) በጋራ መስራት በሚያስችሏቸው ነገሮች ላይ ተወያይተው የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ደብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ እና አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት  በባዮሜዲካል እና በክሊኒካል ምርምር ፣ በምርት ልማት (ክትባት, በምርመራ እና በምርመራ መሣሪያዎች) ፣ የምርምር ቤተ ሙከራ ተቋማትን በጋራ ለመጠቀም፣ የአጭር እና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎች፣  የጋራ ምረቃ ፕሮግራሞችን በጋራ ለማከናወን የሚግዛቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ  ፡፡

አህሪ(A.H.R.I) የጤና ምርምር  ፣የጤና ፈጠራ ፣ የጤና የልማት እና የጤና የምርት ምርምሮችን ሲያድርግ 55 ዓመታትን ያቆጠረ አንጋፋ የሀገር ባለውለታ ተቋም ሲሆን በእንጻሩ ደብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሁለተኛው ትውልድ በመባል ከሚታወቁት  ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚመደብ የ16 ዓመት ልምድ ያለው አፕላይድ ዩኒቨርስቲ ነው፡፡ ዩኒቨርስቲው  ጤና ፣ ግብርና ፣ ኢንጂነሪንግ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ፕሮግራሞች ላይ በትኩረት  እንዲሰራባቸው የተሰጡት ሀላፊነቶች ናቸው፡፡
ምርምር ፣ፈጠራ ፣ልማትና ምርት አህሪ  በትኩረት የሚሰራባቸው ሲሆኑ እነኚህን ስራዎች የሚሰሩ ምሁራን የስራዎቻቸው ግኝቶች  ከኢትዮጲያ አልፎ ለዓለም የሰው ዘር የሚጠቅሙ ውጤቶች ሆነዋል ፡፡ እነኚህ ምሁራን ከሚገኙበት ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት በመምጣታችሁ ደስ ይለናል ያሉት የአህሪ ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ  እንደ አህሪ 55 ዓመታትን ያስቆጠረ ተቋማዊ ባህል አለን፡፡ በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ አካባቢ ከባህል ህክምና አንጻር ሰፊ ዕውቀት ያለው አካባቢ በመሆኑ በባህል ህክምናም ዙሪያ ሰፊ ስራዎችን በጋራ የምንሰራ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አክለውም በቀጣይ ከዩኒቨርስቲው ጋር በተለያዩ ጉዳዩች ላይ የተለያዩ ስራዎችን የምንሰራ ሲሆን ከዚህ ቀደም  በአንኮበር የተጀመረው  የሀገር በቀል ዕጽዋት  ማበልጸጊያ ማዕከል ጋር የክሊኒካል ሙከራ ስራ አለ እሱንና ሌሎች አዳዲስ የምርምር ስራዎችን በቀጣይ ከፍ ባለ ደረጃ የምናስቀጥል ይሆናል  ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር ንጉስ ታደሰ የደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት ሲሆኑ በኛ የትምህርት ስርዓት ላይ አንዱ የምንወቀስበት የትምህርት ስርዓታችን በሀገራችን ሁኔታ ላይ የተንተራሰ አለመሆኑ ነው፡፡  የሀገር በቀል ዕውቀቶችን እናበልጽግ ስንል ልጆቻችን አውቀውት ይዘውት እንዲያስቀጥሉት ለማድረግ  እና የእውቀቱ ባለቤቶችንም ዕውቅና ለመስጠት ነው ፡፡ ያደጉ ሀገራት ያላቸውን ይዘው የሌላቸውን በመጨመር  ለዕድገት የበቁ በመሆኑ እኛም ይህንን ተሞክሮ በማድረግ ያለንን በማዳበር ያሌለንን በመጨመር ለሀገር ዕድገት  በጋራ እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል ፡፡

የመገናኘታችን ዋናው ምክንያት ሁለቱ ተቋማት የጋራ የሚያደርጋቸው ስራዎች በመኖራቸው ነው፡፡ አስቀድመን  በጋራ የጀመርነው ዕፅዋታዊ መድሀኒት የማበልጸግ ጉዳይ ነው ፡፡ይህም እንደ ሀገርም እንደህዝብም ተስፋ የተጣለበት ጉዳይ ናውና  ያሉንን ዕፅዋቶች  ተጠቅመን መድሐኒቶችን ማምረት ከቻልን አንድ ስኬት ነው ብለን ነው ምናስበው በማለት ፕሬዘዳንቱ ተናግረዋል፡፡

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

05 Jan, 10:31


Channel photo updated

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

04 Jan, 11:46


የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
===============
ደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለመሐል ሜዳ ካምፓስ የሰው ሃብት ለማሟላት ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ለመወዳደር የተመዘገባችሁ እና ከዚህ በላይ በስማችሁ ፊት ለፊት ስለማሟላታችሁ የተገለፀ ተወዳዳሪዎች ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 በ ደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በመገኘት የሚሰጠውን መመዘኛ ፈተና እንድትወስዱ እናሳስባለን።

https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

01 Jan, 19:09


ውድ ተማሪዎች

በካምፓሳችን በበጎ ስራዎቹ የሚታወቀው የበጎ አድራጎት ክበብ( medical society charity club) ከመንደራቸው ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ወገኖቻችን የፊታችን ሰኞ ሁላችንም ቁርሳችንን ለነርሱ እንዲውል ድጋፋችሁን በፊርማ እንድትሰጡ እና  የዚህ መልካም ሐሳብ ተሳታፊ እንድትሆኑ በአክብሮት ጋብዘናችኋል።


ያልፈረማችሁ ተማሪዎች ነገ ቁርስ ሰአት በመመገብያ አዳራሽ በር ጋር መጥታችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ።

በተጨማሪም ለነዚህ ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ የሚውል ገንዘብ፣ ልብስ እንዲሁም የንጽሕና መጠበቂያ ግብአቶችን በመስጠት ለወገኖቻችን  አለን እንበላቸው።

በመልካምነት ወደፊት!


አ/ወ/ጤ/ሳ/ካ/ የተማሪዎች ኅብረት

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

27 Dec, 14:35


አስደሳች ዜና

ከዛሬ ጀምሮ  የምግብ ቤት የራት መዝጊያ ሰአት ወደ ነበረበት ተመልሶ ከምሽቱ 1:00 ሆኗል።

በተጨማሪም ነን ካፌ የምትመዘገቡ ተማሪዎች የምግብ ቤት አገልግሎትን እስከ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም ድረስ መጠቀም ትችላላችሁ። ከጥር 1/2017 ዓ.ም በኋላ ክፍያ ስለሚፈጸም መጠቀም አትችሉም።

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

27 Dec, 09:45


non cafe ምዝገባን ይመለከታል

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

27 Dec, 06:11


📌 Vacancy Announcements:-


Organization: Federal Civil Service Commission ( For Dire Dawa University Teaching and Referral Hospital)

Location: Dire Dawa

Minimum Experience: Vary (#0_year - 8 years)

Professionals needed:-

- 1 Masters in clinical Pharmacy

- 2 BSC in #Public_health

- 4 Level IV in health information technician (#HIT)

- 1 BSc in #Health_informatics

- 12 #Medical_doctor (General Practitioner)

- 2 Orthopedician

- 1 Emergency and critical care specialist

- 6 Bachelors in #Pharmacy

-  1 Level IV in the nursing

- 23 Bachelor's in #Nursing bachelors

- 4 Bachelors in #Pediatric_nursing

- 9 Bachelors in OR nursing

- 1 Nurse professional (administrative role)

- 1 Level 3 in autoclave and sterilization

- 3 Masters in Advanced professional nurse specialist

- 2 Masters in emergency, medical and Critical Care Nursing

- 1 Masters in cardiovascular nursing

- 4 Bachelors in #neonatal_nursing

- 2 Advanced diploma (level 5) Opthalmic nursing

- 1 #Opthalmic_nurse

- 2 Masters in Respiratory Care

- 1 Masters in Neonatal Advanced Life Support

- 4 BSC in #Anastasia

- 1 BSc in Histotechnology

- 4 Bachelors in Medical #Radiology Technology

- 8 Bachelor's in Medical #Laboratory Technology

- 8 BSC in #Midwifery

- 1 BSc in #Optometry

- 6 BSC in #Psychiatry

- 1 Bachelors and #Environmental_health/ #Occupational_health and safety


Deadline: January 1, 2024

https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

26 Dec, 17:03


ቴሌግራም ላይ የሚላኩላችሁ ሊንኮች ከመረጃ መንታፊዎች ሊሆን ስለሚችል ከማታዉቁት ሰዉ የሚደርሳችሁን የቴሌግራም ሊንኮች እንዳትከፍቱ - ኢንሳ ‼️

ዛሬ ማለትም ታህሳስ 17 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች ከላይ በተጠቀሰው የማስገሪያ (phishing link) እና ሌሎች ተጨማሪ ማስገሪያዎች አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ ስለሆነ ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከምታውቁትም ይሁን ከማታውቁት ) ግለሰብ ሊንክ ቢላክላችሁ መክፈት እንደሌለባችሁ እና ወዲያውኑ እንድታጠፉት እናሳስባለን‼️

©ኢንሳ

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

13 Dec, 16:26


መመዝገብያ ቦታ- ብሎክ 2 ቢሮ ቁጥር 16
ከታህሳስ 5 እስከ 7

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

29 Nov, 09:09


ሼር አድርጉት

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

16 Nov, 08:33


የአዲስ ገቢና የ 2016ዓ.ም ሪሜዲያል ወስዳችሁ ማለፊያ ነጥብ ላመጣችሁ ተማሪዎች ጥሪን ይመለከታል

ደብረብረሃን ዩኒቨርስቲ

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

15 Nov, 07:28


ለአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ተማሪወች በሙሉ:-


እያንዳንዱ የትምህርት ክፍል ተማሪዎች በወጣላችሁ መርህ ግብር መሰረት በግቢው ውስጥ በሚገኘው ድጂታል ቤተመፀሀፍት  በመገኘት orientation እንድትወስዱ።

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

14 Nov, 07:41


ለአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ተማሪወች በሙሉ:-


🩸በካምፓሳችን የሚገኘው #አስራት_ለጋሾች_ክበብ የ2017 የመጀመሪያ ዙር  የደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ  የተሳተፋችሁ ተማሪዎቻችን አጠቃላይ የደም ምርመራ ውጤት ከዛሬ ማለትም ሀሙስ 05/03/1207 እስከ 06/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ በግቢያችን ውስጥ በሚገኘው የተማሪዎች ህብረት ቢሮ (ህንፃ ቁጥር ሁለት basement ) ድረስ በመሄድ የምርምር ውጤታችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

04 Nov, 13:12


ምደባ!

የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን
Website: https://placement.ethernet.edu.et 
Telegram: https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል። ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

     https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

20 Oct, 16:14


👉👉👉👉ለ ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲደረግ የነበረው የደም ልገሳ መርሐ ግብር ዛሬ ተጠነቋል። ስለመልካም ተሳትፏችሁ ከ ልብ እናመሠግናለን። ይህን በጎ-ፍቃዳችንን ከ ሦስት ወር በኋላ በእጥፍ እንደምንጨምር በመተማመን ነው።
በአሁኑ ዙር  172 ዩኒት መሰብሰብ ተችሏል ይህ የሆነው በበጎፍቃድ ልቦች ምክንያት ነው።
   በማንም በምንም ልንተካው የማንችለውን የሰውን ሕይወት እንታደግ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ከልብ እናመሠግናለን።
የክለቡ አባል መሆን የምትፈልጉ ማንኛውም ተማሪ መመዝገብ ይችላሉ።


አስራት ደም ለጋሽ ክለብ
ስራ አስፈጻሚ።

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

10 Oct, 12:49


ለነገ ስልጠና የምትፈለጉ የክላስ ተወካዮች

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

17 Sep, 16:10


የሴቶች ዶርም ድልድል

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

17 Sep, 16:05


የወንዶች ዶረርሚተሪ ድልድል
መረጃውን ሼር አድርጉ

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

14 Sep, 14:06


9 and 10/2017 E.C.

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

11 Sep, 04:37


መልካም አዲስ ዓመት🥰

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

05 Sep, 08:48


ውድ የአ/ወ/ጤ/ሳ/ካ/ተማሪዎች


#የመግቢያ ቀንን በተመለከተ ከብዙ ተማሪዎች ጥያቄ እየደረሰን ነው።

ከ ካምፓሳችን ምንም አይነት የተወሰነ የመግቢያ ቀን ስለሌለ መረጃው እንደደረሰን በዚሁ ቻናላችን ይፋ የምናደርግ ይሆናል።

እስከዛው በትዕግስት እንድትጠብቁ ስንል በትህትና እንጠይቃለን።


ተ/ህብረት

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

22 Aug, 14:13


#ለነርሶች በሙሉ | በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት በተለያዩ የነርሲንግ ሙያ መስኮች ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት lmis.gov.et በመመዝገብ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በሚደረግ የምልመላ ሒደት የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን lmis.gov.et ላይ መመዝገብ እና አቅሪያቢያችሁ በሚገኝ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ በመገኘት የባዮሜትሪክስ መረጃ መስጠትና የሠራተኛነት መለያ ቁጥር ማግኘት ያስፈልጋል፡፡

ለአገልግሎቱ ምንም አይነት ክፍያ የማይጠየቅ መሆኑን አውቃችሁ ከአጭበርባሪዎች ራሳችሁን እንድትጠብቁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

አመዘጋገብ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይህንን ማብራሪያ ቅድሚያ ይመልከቱ ⬇️
https://youtu.be/e3Q5GziZDuE?si=hHtIVGy-2MyKZzIY

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

07 Aug, 15:13


የብቃት ምዘና ፈተና ለወሰዳችሁ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ ውጤት ተለቋል::
____

በMedicine, Nursing, Public Health, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing, Emergency & Critical Care Nursing, Surgical Nursing, Physiotherapy እና Human Nutrition ሙያዎች ተመርቃችሁ በሰኔ 19/2016 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር እና በጤና ሚኒስቴር በኩል የተሰጠውን የመውጫ እና ብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ ተመዛኞች ከነሀሴ 01/2016 ዓ.ም ጀምሮ http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን (username) በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936 በመደወል ወይም በኢሜይል [email protected] ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር(username) እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ማሳሰቢያ፦
በትምህርት ሚኒስቴር የማለፊያ ነጥብ አሟልታችሁ ዲግሪ የያዛችሁና የጤና ሚኒስቴርን የማለፊያ ነጥብ አሟልታችሁ ያለፋችሁ ተመዛኞች ስም ዝርዝራችሁን ከ03/12/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለክልል የጤና ተቆጣጣሪ አካላት የሚላክ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የማለፊያ ነጥብ አሟልታችሁ ዲግሪ የያዛችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ይህን ተከትሎ በሚወጣ ማስታወቂያ የተግባር ምዘና(OSCE) ፈተና የምዝገባ መርሃ ግብር ስለሚወጣ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እንዲሁም ለፈተናው ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

07 Aug, 12:03


የ 2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ካሪክለም

https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

31 Jul, 10:11


ማስታወቂያ | የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ

ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና  (NGAT) ምዝገባ የሚካሄደው ከሐምሌ 24 - ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ የመመዝገቢያው ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት በ https://NGAT.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

https://t.me/ASRAT_WOLDEYES1

አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ

30 Jul, 11:55


ውድ የ አ/ወ/ጤ/ሳ/ካ ተማሪዎች በሙሉ የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን ለእረፍት ወደ ቤተሰብ የምትሄዱ ተማሪዎች በየትኛውም አካባቢ ስትሄድ መንገዱን በትክክል አጣርታችሁ መሆን ይኖርበታል። እየሄዳችሁ ላላችሁ መልካም ጉዞ እንዲሁም እረፍት ይሁንላችሁ።

የተ/ፖሊስ