Abu Hiba (አቡ ሒባ) @abuhiba Channel on Telegram

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

@abuhiba


➊. በመልካም ቀደምቶቻችን ፋና፣
➋. ቁርኣንና ሓዲሥ ነክ መጣጥፎች፣
➌. አጫጭር የሰለፎች ንግግሮችና ምክሮች።

Abu Hiba (አቡ ሒባ) (Amharic)

Abu Hiba (አቡ ሒባ) አዲስ ፋና ብሔራዊ ምናሌነት ስብስብ በማውጣት ስለሆነ በመልካም ቀደምቶቻችንን ፋና በመከተል የታነቡ እና የምንማማርበት የሚታወሩ ሄደች። Abu Hiba (አቡ ሒባ) ማንኛውም ቃል፣ መንገደኛ፣ ሰይጣን ወይም እስካሁን አንድ የሚያምን አለመሆን ድርጅቶችዎን ጠብቁ። የስልክ ላይ ተጨማሪ መጣጥፎችንና ማህበረሰብን በአጫጭር ፡፡

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

06 Feb, 19:02


የሰላማዊ ትዳር ቀመር ይመስላል‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
አቡ ደርዳእ ለባለቤቱ ለኡሙ ደርዳእ
(ረድየል‒ሏሁ ዓንሁማ) እንዲህ አላት፦

«እኔ ስቆጣ አንቺ አስደስቺኝ፤ አንቺም ስትቆጪ እኔ አስደስትሻለሁ። ሁለታችንም እንዲህ የማንሆን ከሆነ ግን የምንለያይበት ጊዜ ምንኛ ፈጣን ሆነ።»
[ታሪኹ ዲመሽቅ ሊ'ብኒ ዐሳኪር (37/475)]
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

06 Feb, 17:47


ኢስራእ እና ሚዕራጅ‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
የነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለምን ታላቅነት ቁርኣን ሲቀር የትኛውም አንደበት ለመግለጽ ቢሞክር እንጅ ትክክለኛ ማንነታቸውን መግለጽ አይችልም።
لَقَدْ رَأَىٰ مِنْ آيَاتِ رَبِّهِ الْكُبْرَىٰ۝١٨
ከጌታው ታአምራቶች ታላላቆቹን በርግጥም አየ።
[አን‒ነጅም (18)]
-
ከመካ ወደ አል‒ቁዱስ፤ ከአል‒ቁዱስ ወደላይኛው ሲድረተል ሙንተሃ ያደረጉት ጉዞ የአላህ ኃይል እና የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ልዩ ደረጃ ማሳያ ናቸው።

ለዓለማት እዝነት ያላቸው ሚና ጎልቶ እዝትን እስኪሆን ወደር የለሽ ቅርበትን ሸለማቸው፤ የሰው ልጅ አዕምሮ ሊሸከም የማይችለውን ተዓምር በገሃድ አሳያቸው።

እዝነትን በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ምሳሌ አድርጉ።
ከጌታችን ከአላህ መገናኛ መስመር ተዘረጋ፤ ሶላት እንደስጦታ ለዚህ ኡማ ተሰጣቸው።

ይህ የዒባዳ ትስስር ጊዜ የማይሽረው ማስታወሻ እና ወደ አላህ መቃረቢያ መንገድም ሆነ።
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

26 Jan, 18:17


አምስት ነገሮች ከ5 ነገሮች በፊት‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) አንድን ሰው ሲመክሩ እንዲህ ብለዋል: አምስት ነገሮችን ከአምስት ነገሮች በፊት ተጠቀምባቸው፦

1. ወጣትነትህን ከማርጀትህ በፊት፤
2. ጤንነትህን ከመታመምህ በፊት፤
3. ሀብትህን ከመደህየትህ በፊት፤
4. ትርፍ ጊዜህን ከመጨናነቅህ በፊት፤
5. ሕይወትህን ከመሞትህ በፊት።
[ሶሒሑል ጃሚዕ (1077)]
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

19 Jan, 17:30


በደረጃ ታላቁና በላጩ አንቀጽ‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
የአላህን አንድነት-ተመላኪነት፣ ሕያውነት፣ ሉዓላዊነት፣ የበላይነትና የኃያልነት መገለጫ ባህሪያቱን ይናገራል። ስድስት የአላህ መልካም ስሞችን በውስጡ ይዟል።
-
ቁርኣን ውስጥ ካሉ አንቀጾች በላጭ አንቀጽም ነው። በአንቀጹ ውስጥ ተዓምራዊ የዓረፍተ–ነገር ትስስር እና አቀማመጥ ይታያል።

አያተል ኩርሲይ‼️

اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ۚ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ ۚ لَّهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ ۚ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ ۖ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِّنْ عِلْمِهِ إِلَّا بِمَا شَاءَ ۚ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ ۖ وَلَا يَئُودُهُ حِفْظُهُمَا ۚ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ۝٢٥٥

አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም። ሕያው ራሱን ቻይ ነው። ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም። በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው። ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል። በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)። መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ። ጥበቃቸውም አያቅተውም። እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው።
[አል–በቀራ'ህ (255)]
*
የአያተል ኩርሲይ ጥቅሞች‼️
---------------------------------------
➊) ከአላህ ጠባቂን ያሾማል ሸይጧንን ያስወገዳል።
➋) ቤት ሲነበብ ሸይጧኖች እዳይገቡ ይከላከላል።
➌) ከውዱእ በኋላ ሲነበብ ወንጀልን ያሰርዛል።
➍) ከመኝታ በፊት ሲነበብ ሸይጧንን ያርቃል።
➎) በሞት ግዜ ለነፍስ ቀላልነትን ያስገኛል።
➏) በጀነት የአማኝን ደረጃ ከፍ ያደርጋል።
➐) ለባሪያው የአላህን ታላቅነት ያስታውሳል።
➑) ሕሙማን ካነበቡት፤ አላህ ይፈውሳቸዋል።
❾) አዘውትሮ ሲነበብ የአላህን እዝነት ያመጣል።
➓) የሙእሚን ቀብርን ያበራል፤ ብርሃንም ይሆናል።
⓫) ሲሕርን ያዳክማል‒ያፈርሳል፤ ይሽራል፤ ያጠፋል።
⓬) ከሶላት በኋላ ሲነበብ ወደ ጀነት ይመራል።
--
የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) አሉ፦
مَنْ قرأَ آيةً الكُرسِيِّ دُبُرَ كلِّ صلاةٍ مكتوبةٍ، لمْ يمنعْهُ من دُخُولِ الجنةَ إلّا أنْ يمُوتَ.
«ከሁሉም ሰላቶች በኋላ አያተ-ል-ኩርሲይ'ን ያነበበ ሰው ቢሞት፤ ጀነት ከመግባት ምንም የሚከለክለው ነገር የለም።» [ሶሒሑል ጃሚዕ (6464)]
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

14 Jan, 20:36


የማዕቀድ ውቕሩ ጭቆና‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
የምዝገባ ጊዜው ሲያልቅ‒ሲዘጋ፤ ውሳኔ ያሉትን ቀጣይ የማዕቀድ ውቅራቸውን ይዘው መጥተዋል።

በርግጥም ለብዙ ዘመናት የመንግስት ሲሶ ኾኖ ለኖረ እምነት፤ የኃይማኖት እኩልነት እንደ ሬት ይመራል።

የታች የሙከራ አይጥ፤ የላይ ሰው ሃዘን ደራሽ፤ ነጋሽ!

ፍትሕም፤ ኣቋምም፤ ተቋምም ሲጠፋ እንዲህ ነው።

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

07 Jan, 18:30


አንደበቱ በዓይን ብሌን‒በልብ ዕይታ ከጨረቃ የፈካ፤
ብዕሮች ተባብረው ቢጽፉ ገልጸው ማይረኩበት ነቢይ

(አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሙሐመድ!)

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

07 Jan, 18:22


ከባዱ ቀን እና ከባዱ ቃል‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
በቁርኣን ውስጥ (ከባድ) ثقيلا የሚለው ቃል በሁለት ኣንቀጾችና በሁለት ዓውዶች ተጠቅሷል።
ከባድ ቀን (يَوْمًا ثَقِيلًا) እና ከባድ ቃል (قَوْلًا ثَقِيلًا) :
-
1–ከባድ ቀን (የቂያም ቀን):
إِنَّ هَٰؤُلَاءِ يُحِبُّونَ الْعَاجِلَةَ وَيَذَرُونَ وَرَاءَهُمْ يَوْمًا ثَقِيلًا
«እነዚያ ፈጣኒቱን ዓለም ይወዳሉ፤ ከባድን ቀንም በስተፊታቸው ኾኖ ይተዋሉ።»
[አል-ኢንሳን (27)]

በዚህ አንቀጽ የቂያም ቀን ከባድነት እንዲሁም ሰዎች ከሁሉ በላይ የቅርቧን ዓለም በመምረጥ የቂያም ቀንን በመዘንጋት ላይ እንዳሉ ተገልጿል።
:
2‒ከባድ ቃል (ቁርኣን):
إِنَّا سَنُلْقِي عَلَيْكَ قَوْلًا ثَقِيلًا
«እኛ ባንተ ላይ ከባድ ቃልን እንጥላለን።»
[አል-ሙዘሚል (5)]

በዚህኛወ አንቀጽ ደግሞ የቁርኣን ከባድነት ጎልቷል። 
--
ከዚያ ከባድ ከሆነው ቀን ለመዳን የሚፈልግ ሰው፤ ከአላህ ቃል ከኾነው ከከባድ ቃላት ጋር መጣበቅ እንዳለበት ትልቅ እና ጥልቅ አጽንዖትን ይሰጣል።
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

03 Jan, 17:47


የዋሻው ጓዶች‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬
አለትን ከትራስ በላይ አስመቻቸው። የተፈጥሮ ህግ ተለወጠ፤ ፀሐይ አቅጣጫዋን ቀየረች። ከ300 ዓመት በላይ አሸለባቸው። ከተኙበትም ነቁ፤ አሉም:

قَالَ قَائِلٌ مِّنْهُمْ كَمْ لَبِثْتُمْ ۖ قَالُوا لَبِثْنَا يَوْمًا أَوْ بَعْضَ يَوْمٍ ۚ
ከእነርሱ አንድ ተናጋሪ «ምን ያክል ቆያችሁ?» አለ።
«አንድን ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆየን» አሉ።
[አል‒ከህፍ (19)]
-
ስለ ዋሻዎቹ ወጣቶች ታሪክ አላህ በቁርኣን ሲነግረን (Private Conversation) የግል ወሬያቸውን ቀንጨብ አድርጎ አስፍሮት እናገኛለን።

በዙሪያቸው ታሪኽ ፀሓፊያን አልነበሩም። ማንም ታሪክ ፀሓፊ ስለነርሱ ልፃፍ ቢል፤ ይህን ንግግራቸውን በፍጹም ማግኘት አይችልም።

ከእንቅልፋቸው ሲነቁ የተናገሩትን‒ነገረላቸው አንድም ውዴታውን ሊገፅላቸው፤ ሁለትም እኛን ሊያስተምር፦

ልብ በደረት ውስጥ የደበቀችውን፣ ዓይን በርግብ'ታዋ ውስጥ ሰርቃ ምታየውን፣ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ አላህ ማየት፣ ማወቅ፣ መስማቱን ሊስተማረን ነገረን።

የወጣት ዒባዳ አላህ ዘንድ ዋጋው ምን ያማረ ኾነ⁉️
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

31 Dec, 19:29


የኣኽሱም ሙስሊሞች ጉዳይ‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
የኣኽሱም ሙስሊሞች ጉዳይ እንደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳሉት ውስን ሰዎች ጽንፈኝነት ብቻ ያለ ሳይሆን፤ ሃይማኖታዊ እና ሕዝባዊ ስር መሰረት ያለው ትልቅ ትግል የሚገልግ ጉዳይ ነው።
-
የመጨቆን ትርጉሙ ምን እንደሆነ ለማወቅ የሚፈልግ፤ በኣክሱም ሙስሊሞች ላይ እየተሰራ ያለውን ጭቆና'ና በደል ይመልከት።

ለኣኽሱም ሙስሊሞች ዘመን በወለደው ኣስተሳሰብ በኣዲሱ ትውልድ ተቀይሮ የመስገጃ እና የመቀበርያ ቦታ የማግኘት ሕልም ሩቅ ኣይሆንም ብለን ነበር፡፡

ይሁን እንጅ ትላንት ስለ ኣኽሱም ሙስሊሞች ጉዳይ ድምጽ ነን ያሉ ኹሉ ዛሬ ላይ ከና'ካቴው ኣልጠፉም እንጅ የሉም።

ለምን? ፍትሕ አገኛችሁ ወይስ ስኬት ደበቃችሁ?
ሴኩላሪዝም ያሉትን እንኳ ሴኩላር ማድረግ ገዘፈን?

በኣኽሱም ሙስሊሞች ዙርያ ያለን ጥያቄ ዛሬ ላይ ድንገት ብልጭ ብሎ የገነነው የሒጃብ ጉዳይ ብቻ አይደለም።

ጉዳዩ ከተነሳ ኣይቀር ቢያንስ እንኳን መሃል ኣክሱም ከተማ ላይ የመስገጃ ቦታ መስጅድና ለከተማ ቅርብ የሆነ የመቃብር ቦታ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

ፍትሕ ለኣክሱም ሙስሊሞች!

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

27 Dec, 16:22


ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ነበር‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ኢብራሂም (ዓለይሂ ሰላም) ለተሰጡት ፀጋዎች ሁሉ ያለማቋረጥ እውቅና'ና ምስጋናን ይሰጥ ነበር።
-
ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ነበር።  ۚشَاكِرًا لِّأَنْعُمِهِ
[አን–ነሕል (121)]

-> ለአላህ ታዛዥ ነበር።
-> በዒባዳ ትጉ ነበር።
-> ወደ ተውሂድ ጠሪ ነበር።
-> ለቤተሰቡ ቸር ነበር።
-> ለእንግዶቹ ለጋሽ ነበር።
-> ለሕዝቦቹ አዛኝ ነበር።
-> በተልዕኮው ቆራጥ ነበር።
-> አላህ ዘንድ ተወዳጅ ነበር።
-> የአላህ ወዳጅ፣ ጀግና ጥበበኛም ነበር።
-> ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ነበር።
-> የምስጋና አብነት አደርገው።
-> መመሪያ በረከቱን ሰጠው።
-> የጽናት መሰረት ተምሳሌቱን፤
-> ምስጋና የአማኞች ባሕርይነቱን ገለጸበት።
-> ምስጋናው የአላህን ልዩ ውለታ አስገኝቶታል።
-> ወደ ቀጥተኛው መንገድ መመራትን ሰጥቶታል።

የአላህ ጸጋዎች ስፍርም ቁጥርም የሌላቸው ናቸው፤ ኾኖም አላህ የኢብራሂምን ምስጋና ለሁሉም አማኞች ተምሳሌት አደረጎ አስቀመጠው።

ሙእሚኖች በ'ለት ተዕለት ሕይወታቸው ምስጋናን በማዳበር የአላህን ፀጋዎች እንዲያስታውሱ፣ እንዲገነዘቡ እና አመስጋኞች እንዲሆኑ አዘዘበት።

ሕይወትን በሙሉ የማይቋረጥ ምስጋና!
وَإِن تَعُدُّوا نِعْمَةَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ۗ አን-ነሕል (18)
«ጸጋዬንም ብትቆጥሩ አትዘልቋትም!» ባለበት ምዕራፍ ላይ ኢብራሂም ያለማቋረጥ እኔን አመስጋኝ ነበር፤ ብሎ አወደሰው።

ምስጋና ሁሉን አቀፍ፣ ቁሳዊ፣ መንፈሳዊ እና ስሜታዊ ሞገስን ሲሸፍን፤ የአላህን ሚታዩና ማይታዩ ፀጋዎችን ሁሉ እውቅና መስጠትን ሲያካትት ምስጋና ይሰኛል።
--
የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) አሉ፦
«አላህ እንደ ምስጋና የሚወደው ነገር የለውም።»
[ሲልሲለቱ ሶሒሐህ (4-404)]
والحمد لِلّه تملأُ الميزان
አልሓምዱሊላህ ('ምስጋና ለአላህ ነው' ማለት)
ሚዛን ትሞላለች። [ሶሒሁል ጃሚዕ (3957)]

ክብርና ምስጋና የዓለማት ጌታ ለኾነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፣ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

24 Dec, 21:55


«ዱንያ ጣፋጭና አረንጓዴ ናት። አላህም በርሷ ላይ ተክቷችኋል፤ እናም ምን እንደምትሰሩም ይመለከታል።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
[ሶሒሕ ሙስሊም (2742)]
الدُّنيا حُلوةٌ خضِرةٌ، وإنَّ الله مُستخلِفَكم فيها، فَيَنْظُرُ كيفَ تَعْمَلُونَ.
ዱንያ ጣፋጭ ነች፤ ማንም አጣጥሞ ያልጨረሳት።
ዱንያ አረንጓዴ ነች፤ ከዓይን ወደ ልብ ያልወረደ።
ለተወሰነ ግዜ ተጣቅመንባት ለተተኪዎች የምንለቃት፤ ከቀብር ሃያት ያጠረች መሸጋገሪያ ድልድይ ናት።

ዱንያ እንደ ጥልቅ ባሕርም ነች፤ በኢማን ጀልባ ያልተንሳፈፉ በ'ርሷ ውስጥ ብዙ ሰዎች የጠለቁባት።

ትልቁ ሰማይ እንዳይታይ፣ ትልቁን ዓለም ምትጋርድ፤ ዓይን ላይ እንዳረፈች ትንሽ ጠጠርም ነች።
-
በእርግጥም የቀረችው የዱንያ ሕይወታችን፤ የእኛን ምኞት ያህል አትረዝምም። ትርጉሟ ካ'ፍታ—ቅጽበት፣ ካ'ልፋነት አይዘልም።

ኾኖም...
የሕልውና ህይወት ዋስትናችን መገለጥ ሚጀምረው፤ ኻቲማችን ላይ በስንዝሯ የሕይወታችን ቅጽበት ነው።

አረንጓዴነቷና ልምላሜዋ ግዜ በሚባል የክስተት ልኬት ሲደርቅ፤ ጣፋጭነቷ በሞት ይቀጠፋል።

ማደግ ማነስን፣ መጨመር መጉደልን ከሚሆንባቸው ስሌቶች መካከል አንዱ፤ ወደ ሞት መቅረባችን ይኾን?
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

24 Dec, 21:23


ከትልቅ የሰደቃ አይነታዎች‼️

ነብዩ (ሶለሏሁ ​​ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-
ليس صدقة أعظم أجرا من ماء.
«ውሃ ከማቅረብ የበለጠ ምንዳ ያለው ሶደቃ የለም።»

[ሶሒሕ አት-ተርጚብ (2/566)]

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

21 Dec, 21:05


ሸይኽ አልባኒ (ረሒመሁ-ሏህ) እንዲህ ይላሉ፦
«አንድ ሰው ከሶላት በዃላ የሚደረጉትን ዚክሮች ቁጭ ብሎ ማለት ካልቻለ እና ከቸኮለ ሊተዋቸው አይገባም፤ አዝካሮቹን እየሄደም ቢሆን ሙሉ ሊላቸው ይገባል።»
[فتاوى جدة (24)]

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

17 Dec, 17:02


ግልጽ የኾነችን ጸያፍ (ዝሙትን) ካልሠሩ በስተቀር ከቤቶቻቸው አታውጡዋቸው፤ እነርሱም አይውጡ።
[አጥ-ጦላቅ (1)]
لَا تُخْرِجُوهُنَّ مِن بُيُوتِهِنَّ وَلَا يَخْرُجْنَ إِلَّا أَن يَأْتِينَ بِفَاحِشَةٍ مُّبَيِّنَةٍ ۚ
ከፍች በዃላ የመማለስ ነገር ይመጣ ዘንድ አላህ ዒዳቸውን በመቁጠር ይጠብቁ ማለቱ፤ የዒዳ ጊዜው ለትዳርና ለፍቺ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የናገራል።
-
ዒዳዋ እስከያልቅ ከ'ርሱ ቀርባ እንድትቆይ መታዘዙ:
በትዳር ውስጥ መራራቅ ልክ እንደ በረዶ መፍቀድን አሟምቶ ቋጥኝ–ትስስሮችን፣ ትንሽ ጠጠር ሊያደርግ ስለሚችል፤

በመካከላቸው የእዝነት ስሜት ዳግም እንዲያንሰራራ፣ ትዳርን የማደስ ሃሳብ ሕያው እንዲሆን ዕድል ለመስጠት ነው፡፡
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

15 Dec, 19:33


ነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) መካን ሲከፍቱ ወደ መካ የገቡበትን ሁነት ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁ-ሏህ) ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ፦

«በጌታቸው ፊት ካላቸው ትህትና እና ታላቅ ታዛዥነት፤ ፈረሳቸውን በማጎንበስ አገጫቸው የኮርቻውን ጫፍ እስኪነካ ድረስ አጎንብሰው ነበር ወደ መካ የገቡት።»

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

12 Dec, 16:31


ወላጆች በልጆቻቸው ምክንያት ደስታን ካገኙ፤
ሁሉን ቻይ የኾነው አላህ በወላጆች ደስታ ይደሰታል።
የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) አሉ፦

رضا الرَّبِّ في رضا الوالِدَيْنِ، و سَخَطُه في سَخَطِهِما.
«የአላህ ውዴታ የሚገኘው በወላጆች ውዴታ ውስጥ ሲሆን፤ ቁጣውም የሚገኘው በወላጆች ቁጣ ውስጥ ነው።» [አት-ቲርሚዚ (1899)]
-
ከዚህ ሐዲሥ አንድ ጥልቅ መልእክት እንረዳለን።
በቅርቢቷ ዓለም በልጆች ላይ ወላጅን የማስደሰት ሕልቆ፤ ብቸኛው መሳፍርት አልባ ገኒን ግብ መሆን እንዳለበት።

ሲያልፍም ከልጆች ታላቅ መልካምነት መካከል አንዱ በወላጆች ልብ ውስጥ ደስታ እንዲፈስ ማድረግ፤ ትልቁ ወደ አላህ መቃረቢያ መንገድ መሆኑን ነው።

የወላጆች ደስታ ከአላህ ውዴታ ጋር መቆራኘቱ ወላጆችን ማስደሰት ቤተሰባዊ ግዴታ ብቻ ሳይሆን፤ የአላህን እዝነት ማግኛ ከሆኑ ዒባዳዎችም ነው።

የሰው ልጅ በሕይወታዊ እንቅስቃሴው ኹሉ ሌት ከቀን ለማግኘት ሚታትርለት ግበ ተፈጥሮኣዊ ስሜት የኾነው ደስታ፤ ወላጆችን በማስደሰት ውስጥ ይገኛል።

ምናልባትም የደስታ መኖሪያው፤ የተደሳች ኗሪነት መኖሩ ሳይሆን አይቀርም።

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

10 Dec, 21:47


ዛሬ ላይ አድገናል በሚሉ ሃገራት ለማንነት ቅዋሜ መለያ የጣት አሻራ እንደ ቅድመ ሁኔታ ያገለግላል።

የአሻራ ልዩነት በዲጂታሉ ዓለም Data integrity እና ግላዊነት ላይ ግልጋሎትና ቅልጥፍናው በስራ ቦታዎች፣ በመጓጓዣዎች፣ በምርመራ ደህንነቶች ላይ የDNA ጣት ዘረመል አሻራ ከፍተኛ ሚና አለው።
-
አምላካችን አላህም ስለ ያንዳንዱ ሰው የጣት አሻራ መለያየት ከ1400 አመት በፊት ስለመቀስቀስ ሲናገር፤ አይደለም አጥንታችሁን መሰብሰብ፣ አሻራችሁን በመመለስም ላይ ቻይ ነኝ! ይላል።
بَلَىٰ قَادِرِينَ عَلَىٰ أَن نُّسَوِّيَ بَنَانَهُ
አይደለም ጣቶቹን (ፊት እንደ ነበሩ) በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንኾን (እንሰበስባቸዋለን)።
[አል-ቂያማህ (4)]

ሱብሓን አላህ! ከሰው ልጅ መፈጠር እስከ ቂያማ ድረስ፤ ስንት አይነትና ምን ያህል የጣት አሻራዎች አሉ?
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

08 Dec, 19:05


የሶሓቦች ዋና ከተማ፣ የሊቃውንቶቹ ሃገር፣ የዓለም ስልጣኔ ቀዳማይ ማዕከል፣ የታላቁ ሶሓባ የሙዓውያ'ህ ሃገር የሆነችው ሻም ከብዙ የሕዝቦቿ ትግልና ስደት በኋላ አላህ ረዳት።
-
አባት ለ30 ዓመት፣ ልጅ ለ24 ዓመት ፈራርቀው ለ54 ዓመት ያህል በመጨፍጨፍ የገዟት ሱሪያ፤ የነፃነት ታጋይ ግፍ በወለዳቸው ልጆቿ ድል አድርጋለች።

የተበዳዮች እንባ ታብሶላቸዉ፤ ነፃነታቸዉን ሊያዉጁ ይመስላል። አላህ ሚመጣውን የተሻለ፤ ደስታቸውን ዘላቂ ያርግላቸው።

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

06 Dec, 18:37


ነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦
«በሰጋጅ ፊት ለፊት የሚያልፍ ሰው ከወንጀል በርሱ ላይ ያለበትን ቢያውቅ፤ በሰጋጁ ፊት ለፊት ከማለፍ 40 ቢቆም ለርሱ በተሻለው ነበር።»

ቡኻሪ (510)

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

06 Dec, 18:29


«ሶላት እንዲሰገድ አዝዤ፤ ከዚያም ወደ ሶላተል ጀመዓ የማይመጡ ወንዶች ቤቶችን ሄጄ ላቃጥል አሰብኩኝ።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) | ቡኻሪ (4220)
لقَدْ هَمَمْتُ أنْ آمُرَ بالصَّلاةِ فَتُقامَ، ثُمَّ أُخالِفَ إلى مَنازِلِ قَوْمٍ لا يَشْهَدُونَ الصَّلاةَ، فَأُحَرِّقَ عليهم.

ለሰው ልጅ በጣም አዛኝ ከመሆናቸው ጋር ማገዶ እንዲሰበሰብልኝ አድርጌ፤ ሶላት ሚያሰግድልኝ ሰው ተክቸ፤ ለጀመዓ ሶላት ወደ መስጅድ የማይመጡ ቤቶችን ላቃጥል አሰብኩ ማለታቸው የሶላተል ጀመዓ ዋጅብነትን ከሚያመላክቱ መረጃዎች አንዱ ነው።

ግና ለደካሞች፣ ለሴቶች፣ ለሕጻናት ሲሉ ተውት!

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

04 Dec, 18:36


የሰማይ በሮች የተከፈቱለት የሶላት መክፈቻ ዱዓ‼️

ኢብኑ ዑመር (ረዲየ-ሏሁ ዓንሁ) ባስተላለፉት: የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ጋር ስንሰግድ ከሰዎች መካከል አንድን ሰው እንዲህ ሲል ሰሙ፦

«አላሁ አክበር ከቢራ፤ ወልሓምዱ ሊላሂ ከሲራ፤ ወሱብሓነሏሂ ቡክረተን ወአሲላ።»
الله أكبر كبيرا، والحمد لله كثيرا، وسبحان الله بكرة وأصيلا.
«አላህ ከሁሉም የላቀ ነው። ለአላህ ምስጋና በብዙው ይገባዋል። ጥራትም በጧት በማታ ለ'ርሱ የተገባ ነው።

የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለምም) :
«እንደዚህ አይነት ቃላትን ያለው ማነው?» ሲሉ ጠየቊ።
ሰውየውም፦ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ነኝ!» አለ።

ከዚያም እንዲህ አሉ፦ ለዚች ንግግር ተገረምኩኝ። የሰማይ በሮች ተከፈቱላት።

ኢብኑ ዑመር (ረዲየል'ሏሁ ዓንሁ) ይላሉ፦
«የአላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሬ እነዚህን ቃላቶች ከማለት አልተውኩም።»
[ሶሒሁል ሙስሊም (601)]
--
ሸይኽ አልባኒ (ረሒመሁ-ሏህ) ሲፈተ ሶላት ላይ ይህ ዚክር ሶላት ከሚከፈትባቸው ዱዓዎች መካከል አንዱና ከመጀመሪያው ተክቢራ በኋላ እንደሆነም ይጠቅሳሉ።
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

04 Dec, 18:21


ጀሓነም ውስጥ በምንም እፎይታ የለ አላህ ይጠብቀን!
فِي سَمُومٍ وَحَمِيمٍ
በመርዛም ንፋስና በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው፡፡
وَظِلٍّ مِّن يَحْمُومٍ
ከጥቁር ጭስም በኾነ ጥላ ውስጥ፡፡
لَّا بَارِدٍ وَلَا كَرِيمٍ
ቀዝቃዛም መልካምም ባልኾነ፡፡
[አል-ዋቂዓህ (41-44)]
--
በነዚ አያዎች በጣም ሞቃት በሚሆንበት ጊዜ በዚህች ዓለም ላይ የሰው ልጆች የሚጠቀሙባቸውን ነገሮች ሁሉ ያጠቃልላል። እነርሱም ሶስት ነገሮች ሲሆኑ ውሃ፣ አየርና ጥላ ናቸው።

ነገር ግን አላህ በነዚህ ጥቅሶች እነዚህ ነገሮች ለጀሐነም ሰዎች ምንም እንደማይጠቅሙ መሆናቸውን ይናገራል።

የጀሐነም አየር ስሙ፦ አስ-ሱሙም ሲሆን እርሱም በጣም ኃይለኛ ወደ ውስጥ ዘልቆ የሚገባ፣ በጥልቅ የሚያቃጥል ሙቀት ያለው መርዛማ ንፋስ ነው።

የጀሐነም ውስጥ ጥላ፦ አል-የሕሙም ሲሆን የጠቆረ፣ ወፍራም ጭስ፣ ከጀሐነም ጭሶች ውስጥ አንዱ ነው።

የጀሓነም ውሃ ስሙ፦ አል-ሓሚም ሲሆን ሊቋቋሙት የማይችል ሙቅ በጣም የፈላ ውሃ ነው።

📚አት-ተውቒፍ ሚነ-ናር (85)

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

02 Dec, 19:23


ነፍስ ከአካል የተዋሃደችውን ያህል ይህ የአላህ ኪዳን በልቦናዎች ማሕደር ውስጥ ቢሰርጽ፤ ልሳኖች ጌታቸውን ከማውሳት ባልተቆጠቡ ነበር። ሱብሓነ`ሏህ!
فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ
«አስታውሰኝ፤ አስታውሳችኋለሁ!»
ከጌታ ወደ ባሪያ የተጣለ ምን ውብ ያማረ ጥሪ ነው!?
-
ኢብኑል ቀይ'ዩም (ረሒመሁ-ሏህ) እንዲህ ይላሉ፦
«አላህን መዝከር በእርሱና በባሪያው መካከል ያለው ትልቁ የተከፈተ በር ነው። ባሪያው በመዘ'ናጋት ራሱ እስካልዘጋው ድረስ።»
‏قال الإمام ابن القيم رحمه الله تعالى:
الذكر هو باب الله الأعظم المفتوح بينه وبين عبده مالم يغلقه العبد بغفلته.
📚መዳሪጁ ሳሊኪን (2/4764)

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

02 Dec, 18:24


ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦
«ሰውየው 60 ዓመት ይሰግዳል ነገር ግን አንዲትም ሶላት እንኳን ተቀባይነት አያገኝም። ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያት ምናልባት ሩኩዑን አሟልቶ ሱጁዱን ባለማሟላቱ ወይንም ሱጁዱን ኣሟልቶ ሩኩዑን ባለማሟላቱ ይሆናል።»
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

28 Nov, 17:47


«ባሪያዬ! እየተራመደ ወደ'ኔ ሲመጣ፤ እኔ በፍጥነት እየገሰገስኩ ወደርሱ እጓዛለሁ።» ሶ/ጃሚዕ (8136)
ومن أتاني يمشي أتيته هرولة.
በማንኛውም ጊዜ ወደ አላህ ለመጓዝ ትግል አድርግ። በምታደርጋት ዚክር፣ በምትሰግዳት ሱና ሶላት ላይ፣ በምትሰጣት ሰደቃ፣ በምታደርጋት ዱዓ፣ በምታነባት ተጨማሪህ አንቀጽ፣ በምትሰራት ትንሽ መልካም ስራ ላይ፤ ወደ ጌታህ መቃረብህን ጨምር።
-
ተቀምጠህም ሆነ ቆማህ፣ ከሰዎችም ጋር ሆንክ ለብቻህ፣ ሁኔታህ ምንም ይሁን ምን፤ በምትችለው ዒባዳ ሁሉ ወደ አላህ ለመቅረብ ጥረት አድርግ።
ወደ ጌታህ መጓዝህን አታቋርጥ።

ምክንያቱም፦
ወደ ጌታው መቅረብን ያቋረጠ፣ ወደ አላህ መምጣት ያቆመ፤ አላህም ወደ እርሱ አልመጣለትምና። 

እርሱን በመቅረብ፣ እርሱን በማውሳት፣ እርሱን በመታዘዝ፤ ደስታ ሳይሆን ሀሴትን ያቀዳጃልና። 

አላህን የመፍራት ውበቱ ከይቀጣኛል ስጋት ሲያልፍ፤ ከይገ'ባዋል ባይነት ልብ ውስጥ ሲመነጭም ነውና።

አላህ ኸይራትን ኹሉ ገር ያ'ርግልን።
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

24 Nov, 23:03


በነቢዩ ﷺ ላይ አንድ ሰለዋት ብታወርዱ ፦

አላህ በእናንተ ላይ አስር እዝነቱን ያወርዳል።

መላኢካዎች ምህረትን ይጠይቁላቹኳል።

አስር መልካም ስራዎች ይፃፉላችኋል።

አስር ወንጀሎች ይሰረዝላችኋል ።

ደረጃችሁ በአስር ደረጃዎች ከፍ ይላል።

ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለመ ተስሊመን ከሢሯ

© : አቡ ረስላን

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

21 Nov, 17:36


ጥቆማ/ምክር ለእርስዎ‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
● በአካልህ ላይ ጤናን ትፈልጋለህ፤ ሰኞና ሐሙስን ፁም።
● ደህንነትንና ሰላምን ትፈልጋለህ፤ አያመል ቢዶ'ችን ፁም።
● ደስታን ትፈልጋለህ፤ በየቀኑ የአላህን ቃል-ቁርኣንን ቅራ።
● ፊትህ እንዲበራ፤ የሌሊት ሶላት 2 ረከዓም ቢሆን ስገድ።
● መረጋጋትን ትፈልጋለህ፤ አላህን ማውሳት (ዚክርን) አብዛ።
● ገንዘብንና ልጅን ትፈልጋለህ፤ ኢስቲግፋር ማለትን አብዛ።
● ጭንቀትን ማስወገድ ትፈልጋለህ፤ ዱዓ ማድረግን አብዛ።
● መቸገርን ማስወገድ፤ 'ላ ሃውለውላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ' በል።
● በረከትን ትፈልጋለህ፤ በሙሐመድ ላይ ሶለዋት አውርድ። (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም!)
● መከራን ማስወግድ ትፈልጋለህ፤ ሰደቃ ስጥ ትንሽም ብትሆን።
● የአላህን ውዴታ ትፈልጋለህ፤ ለወላጆች መልካምን ዋል።
● የአላህን ይቅርታ ትፈልጋለህ፤ የበደለህን ሰው ይቅር በል።
● የአላህን እዝነት ትፈልጋለህ፤ በምድር ላሉት ፍጡሮች እዘን።
● ውዴታውንና ጀነቱን ትፈልጋለህ፤ ተውበት አድርግ፣ ሶላትን በወቅቷ ስገድ።
● ኻ'ቲማህ እንዲያምር ትፈልጋለህ፤ 'ላኢላሃ ኢለ-ሏህ' ማለትን አብዛ።
● የማይቋረጥ ሓሰና ትፈልጋለህ፤ ሌሎች-ሰዎችን ወደ መልካም ስራ አመላክት።
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

19 Nov, 17:29


«አንተ የኣደም ልጅ ሆይ! አንተ የቀናት ስብስብ እንጅ ሌላ አይደለህም። አንድ ቀን በሄደ ቁጥር፤ ራስህ መጉደልህን እወቅ።»

[ሐሰኑ-ል-በስሪይ (ረሒመሁ'ሏህ)]

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

17 Nov, 17:25


⓲ የሶላት ጥቅሞች‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
በኢብኑ'ል ቀይ-ዩም (ረሒመሁል'ሏህ)፦
1. የፊት ገጽታን ያበራል።
2. አካላዊ ጤንነትን ይጠብቃል።
3. አካላዊ ጥንካሬን ይጨምራል።
4. ነፍስን ያስደስታል።
5. ልብን ያጠነክራል።
6. በሽታን ያስወግዳል።
7. በረከትን ይጨመራል።
8. ስንፍናን ያስወግዳል።
9. እግሮችን ንቁ ያደርጋል።
10. ጎጂ ነገሮችን ያስወግዳል።
11. አስተውሎት-ነፍስን ያሰፋል።
12. ለነፍስ ብርሃን ይሰጣል።
13. አደጋዎችን ይከላከላል።
14. በረከቶችን ይጠብቃል።
15. ሲሳይን ያስገኛል።
16. ልብን ያበራል።
17. ሸይጧንን ያርቃል።
18. ወደ አር-ረሕማን ያቃርባል።
📚ዛዱ'ል መዓድ (4/304-305)
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

16 Nov, 19:34


ሰደቃ ነፍስን ያጠራል። እዝነትን በልብ ይዘራል። የአላህን ቁጣ ያጠፋል። የቀብርን ግለት ያበርዳል። ነፍስን ከጀሐነም እሳት ይጠብቃል።
-
ነቢዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰላም) በሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፦ «በግማሽ የቴምር ፍሬ ሰደቃ ቢሆንም እንኳን፤ ነፍሳችሁን ከጀሐነም እሳት አድኑ።»
[ሶሒህ ሙስሊም (1016)]
اتَّقُوا النَّارَ وَلَوْ بِشِقِّ تَمْرَةٍ.
የአላህ ሰፊ እዝነቱ፤ በትንሽ ትልቅ መመንዳቱ ነው። አላህ ከምንምነት ኢምንት ምንነት፤ የላቀ አካላዊ ታላቅነትን፤ በኢማን ብርሃን ያጎናጽፋል። የአላህ ጸጋ ቢቆጠር፤ የእድሜ ልክ ምስጋናችንን ይገዝፋል። በሞት ሸካራ መዳፎች መዳ'በስን ከመጸየፍ፤ የገዘፈ ውዴታው ይልቃል።

የአላህ እዝነት ያልፈሰሰባት ነፍስና፤ ውሃውን ያጣ ወንዝ ቅላቸው አንድ ነው። ከለጋሽ ከከሪሙ፣ እጅግ አዛኝ ከረሒሙ፣ ለፍጥረት ለዓለሙ - እዝነት እንደመፈለግ ባለ መንገድ፤ ሪፍቅ አለመታደል...

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

13 Nov, 17:46


በአንድ ረከዓ ሙሉ ቁርኣንን ያነበቡ አራት ሰዎች፡-
1. ዑሥማን ኢብኑ ዓፋን (ረድየል'ሏሁ ዓንሁ)
2. ተሚም አድ-ዳሪይ (ረድየል'ሏሁ ዓንሁ)
3. ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር (ረሒመሁ'ሏህ)
4. አቡ ሐኒፋ (ረሒመሁ'ሏህ)

ምንጭ፦📚ተብይድ' አስ-ሶሒይፋህ (94-95)

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

11 Nov, 18:24


የእናታችን ዓኢሻ (ረድየል'ሏሁ ዓንሃ) ጸጋ‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
➊) እናታችን ዓኢሻ (ረድየል'ሏሁ ዓንሃ) በነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ዘንድ በጣም ተወዳጅ ባለቤታቸው ነበረች። ነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) በጣም የሚወዱት ማን እንደሆነ በተጠየቁ ግዜ፤ ለዓኢሻ (ረድየል'ሏሁ ዓንሃ) ጥልቅ ፍቅር እንዳላቸው ገለጸዋል። 

ዓምር ኢብ-ል-ዓስ (ረዲየሏሁ ዓንሁ) እንዲህ ይላል፦
«የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከሰዎች ይበልጥ አንቱ ዘንድ ተወዳጁ ማን ነው? አልኳቸው። 'ዓኢሻ' አሉኝ። ከወንዶችስ? አልኳቸው። 'አባቷ' አሉኝ።»
ምንጭ፦ቡኻሪ (3662)
عَنْ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ قَالَ: قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَيُّ النَّاسِ أَحَبُّ إِلَيْكَ؟ قَالَ: «عَائِشَةُ». قُلْتُ: فَمِنَ الرِّجَالِ؟ قَالَ: «أَبُوهَا»
➋) ነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ከእናታችን ዓኢሻ (ረድየል'ሏሁ ዓንሃ) በስተቀር ሌላ ባቱል የሆነች ሴት አላገቡም ነበር። ብቸኛዋ ባቱል ሚስታቸው እርሷ ነች።

➌) ብቸኛዋ ከነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሚስቶች ወላጆቿ ሙሐጅሮች የነበሩ ሚስታቸው ነበረች። የዓኢሻ (ረድየል'ሏሁ ዓንሃ) ቤተሰቦች የመጀመሪያዎቹ ሙሐጅሮች ከመካ ወደ መዲና ሽርክን ሸሽተው የተሰደዱ ናቸው።

➍) ንፁህናዋን በተመለከተ፤ አላህ (ሱብሃንሁ ወተዓላ) ወሕይ በማውረድ አረጋግጦላታል። ይህም ስለ ክብርና ስለ መልካም ምግባሯ መለኮታዊ ምስክር ነው።

وَلَوْلَا فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُ وَأَنَّ اللَّهَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ
«በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታውና እዝነቱ ባልነበረ አላህም ሩኅሩኅና አዛኝ ባልኾነ ኖሮ (ቶሎ ባጠፋችሁ ነበር)።» [አን-ኑር (11-20)]

➎) በዲን እውቀት ላይ - ጥልቅ እውቀት እንዳላት ከነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ምስክርን አግኝታለች። 2210 ሐዲሦችን ዘግባላች። ብዙ ጊዜ ሶሓቦች እንኳን እርግጠኛ ያልሆኑባቸውን ዲናዊ ጉዳዮች በማብራራት ረገድ ትልቅ ሚና ነበራት።
ነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
«ግማሹን ዲናችሁን፤ ከሑመይራ (ከዓኢሻ) ተማሩ።
ምንጭ፦አት-ቲርሚዚ (3888)
خُذُوا نِصْفَ دِينِكُمْ مِنَ الحُمَيْرَاءِ.
➏) በጅብሪል ትንቢት የተነገረላት ባለቤታቸው ናት። የነቢያችን (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሚስት ከመሆኗ በፊት፤ ነቢያችን (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) በሕላማቸው ሁለት ግዜ አይተዋት ነበር።

«ነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለውኛል፦ በህልሜ 2 ግዜ አይቼሻለው፣ ጂብሪል በሐር ልብስ ተሸክሞሽ፤ 'ይቺ የአንተ ሚስት ናት' አለኝ። ስገልጥም አንቺ ነበርሽ። እኔም ለራሴ 'ይህ ሕልም ከአላህ ከሆነ ይፈጸማል' አልኩኝ።»
ዓኢሻ (ረድየል'ሏሁ ዓንሃ) ፣ ምንጭ፦ቡኻሪ (3895)
أُرِيتُكِ فِي الْمَنَامِ مَرَّتَيْنِ، إِذَا رَجُلٌ يَحْمِلُكِ فِي سَرَقَةِ حَرِيرٍ فَيَقُولُ هَذِهِ امْرَأَتُكَ، فَأَكْشِفُهَا فَإِذَا هِيَ أَنْتِ، فَأَقُولُ إِنْ يَكُنْ هَذَا مِنْ عِنْدِ اللَّهِ يُمْضِهِ.

➐) ከነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ጋር ልዩ የሆነ መቀራረብ ነበራት። ከዚያም መካከል ባ'ንድ ገንዳ ውስጥ ይታጠቡ ነበር። ይህ ተግባር ከሌሎች ሚስቶቻቸው ጋር ያልተጋራ ነበር።

√ ዓኢሻ (ረድየል'ሏሁ ዓንሃ) ባስተላለፈችው ሓዲሥ፦
«እኔ እና ነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) አል-ፈረቅ በሚባል አንድ ገንዳ' እየቀዳን እንታጠብ ነበር።»
ምንጭ፦ቡኻሪ (298)
عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ مِنْ قَدَحٍ يُقَالُ لَهُ الْفَرَقُ‏.‏

√ ዓኢሻ (ረድየል'ሏሁ ዓንሃ) እንዲህ ትላለች፦
«ከነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ጋር በሰፈር ሳለሁ፤ ሩጫ ተወዳደሩኝ አሸነፍኳቸው፤ ያሸነፍኳቸው ሳልወፍር በፊት ነበር። ከወፈርኩ በኋላ ግን ተወዳደርኳቸው አሸነፉኝ። እንዲህም አሉኝ፦ ብድር መልሻለሁ!»
ምንጭ፦ሶሒህ አቡ ዳውድ (2578)
عَنْ عَائِشَةَ، رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّهَا كَانَتْ مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فِي سَفَرٍ قَالَتْ فَسَابَقْتُهُ فَسَبَقْتُهُ عَلَى رِجْلَىَّ فَلَمَّا حَمَلْتُ اللَّحْمَ سَابَقْتُهُ فَسَبَقَنِي، فَقَالَ: هَذِهِ بِتِلْكَ السَّبْقَةِ.‏
➑) በእርሷ ቤት ተደጋጋሚ ወሕይ ይወርድላቸው ነበር። የቁርኣን መውረድ ብዙ ጊዜ ይከሰት የነበረው፤ ከሌሎች ሚስቶች ይልቅ ነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ከዓኢሻ ጋር በነበሩበት ወቅት ነበር።
«የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ​​ዓለይሂ ወሰለም) ታፋዬ ላይ ሆነው ወሕይ ይመጣላቸው ነበር፤ እና ያጫውቱኝ (ይንከባከቡኝ) ነበር።»
ዓኢሻ (ረዲየል'ሏሁ ዓንሃ) ፣ ምንጭ፦ቡኻሪ (5369)
عَنْ عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا قَالَتْ: أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ يُوحَى إِلَيْهِ وَفِي حَجْرِي وَيُدَاعِبُنِي.

❾) በመጨረሻ እስትንፋሳቸው ከጎናቸው ነበረች።
ነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) በዓኢሻ (ረድየል'ሏሁ ዓንሃ) ቤት የመጨረሻ እስትንፋስ ሲተነፍሱ፤ በርሷ እቅፍ ላይ ተደግፈው ነበር። በዚህ ጸጋዋም ትፎክር ነበር።

«አላህ በ'ኔ ላይ ከለዋላቸው ጸጋዎች መካከል፤ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በ'ኔ ቤት፣ በ'ኔ ቀን፣ በደረቴና በአንገቴ መካከል ኾነው መሞታቸው እና ምራቄን ከምራቃቸው ጋር አላህ ማዋሐዱ ነው።»
ዓኢሻ (ረድየል'ሏሁ ዓንሃ) ፣ ምንጭ፦ቡኻሪ (4438)
إِنَّ مِنْ نِعَمِ اللَّهِ عَلَيَّ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ تُوُفِّيَ فِي بَيْتِي، وَفِي يَوْمِي، وَبَيْنَ سَحْرِي وَنَحْرِي، وَأَنَّ اللَّهَ جَمَعَ بَيْنَ رِيقِي وَرِيقِهِ عِنْدَ مَوْتِه.

➓) በርሷ ተራ፣ በርሷ ክፍል ውስጥ፣ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በኋላም በርሷ ክፍል ውስጥ ተቀበሩ።
[ምንጭ፦📚(1/237-241) جلاء الأفهام]
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

09 Nov, 23:07


የአባት መብት በልጁ ላይ‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
አል-ለይሥ ቢን ሰዐድ (ረሒመሁ-ል-ሏህ)
አባት በልጁ ላይ አስር ​​መብቶች አሉት ይላል።
➀) በስሙ ላይጠራው፣
➁) ምሕረትን ሊለምንለት፣
➂) በለሰለሰ አነጋገር ሊያናግረው፣
➃) አብረው ሲጓዙ ከኋላው ሊሆን፣
➄) ሲጠራው በትህትና ሊመልስለት፣
➅) ምግብ በሚፈልግበት ግዜ ሊመግበው፣
➆) አገልግሎቱን ሲፈልግ እርሱን ሊያስቀድመው፣
➇) የሚወደውን ሊወድለት የሚጠላውን ሊጠላ፣
➈) ልብስ በሚፈልግበት ግዜ ከቻለ ሊያለብሰው፣
➉) አላህን ማመጽ እስካልሆነ፤ ሲያዘው ሊታዘዘው።
ምንጭ፦📚ሙኽተሶር አል-ሑቑቅ ሓማድ (ص217)
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

06 Nov, 17:41


አቡበክር (ረድየ-ሏሁ ዓንሁ)‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
አቡበክር በረሱላችን (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ዘንድ በጣም ተወዳጅ ነበር። ውድጅታቸው ድሮ ነበር። ሆደ በሻሻ፣ ዝምተኛ ነበር። ውዴታ ራሱን ሲ'ያህል ይወዳቸው ነበር። ከጎናቸው አይጠፋም። ጉዳያቸውን ያዋዩታል። ያማክሩታል።
-
የወዳጅነት ትርጉሙ አቡበክር ነቢዩን (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) የሚወዳቸውን አይነት ነው ማለት ይቻላል። ሲወዳቸው ሙሐባ ሙሽራ ስትሆን፤ መሕሯ ነፍስ ናት ያህል ለነፍሱ አይሳሳም ነበር።

ሆኖም ወደ አኼራ ሲሄዱ አጠገባቸው አልነበረም። በመዲና ዳርቻ ላይ በምትገኝ አስ-ሱና በምትባል መንደር ባለቤቱን በመጎብኘት ላይ ሳለ ነበር፤ ወደ አኼራ የመሄዳቸው ዜና የደረሰው። 

ወዲያው ወደ መዲና ተመለሰ። እንደደረሰም በቀጥታ ወደ ነብዩ ክፍል ሄደና ተሸፍነው ተኝተው አያቸው።

የመለ'የት ሕመሙ እንዴት`ስ አድርጎት ይሆን⁉️
የልብ ወዳጅን እንደማጣት ምን ከባድ ነገር አለ⁉️
የድምፅ ፀጥታን እንደመቻል ምን ኃይል አለ⁉️

በዚያች ቀን ለአቡበክርም ሆነ ለሶሐቦች ሞት በቅርበት ሲመጣ የመጀመሪያው ነበር። ዓለም በፍርሃት ነገሰች። መዲና በሃዘን ተናጠች። በዚህ ዑማ ላይ ሐዘን ርብርብ አለ።
*
ተልዕኳቸውን ለማስቀጠል፣ ወዳጅነትን በተግባር ለማሳየት፣ የአላህን ዲን ለመጠበቅ ሲል አቡበክር ተረጋግቶ አረጋጋቸው። በርትቶ አበረታቸው። ጠንክሮ የማጠንከሩ፤ በርትቶ የማበርታቱ ፍጥነት ከአውሎ ንፋስ በኋላ እንዳለው የንፋስ መረጋጋት አይነት ነበር።

ይሁን እንጅ በርሳቸው ሞት ብዙዎች ወደ ክህደት እና ወደ ከፍተኛ ሃዘን ውስጥ ገብተዋል። አቡበክርም፦ «ሙሐመድን ሲያመልክ የነበረ ሙሐመድ በርግጥም ሞቷል፤ አላህን ሲያመልክ የነበረ ግን አላህ ሕያው ነው አይሞትም።» የሚል ጠንካራ አዋጅ አሰሙ።
من كان يعبد محمداً فإن محمداً قد مات، ومن كان يعبد الله فإن الله حي لا يموت.
በዚህ ንግግራቸው ሶሓቦችን በማረጋጋትና ከታላቅ የሐዘን ስሜት ወደ እምነታቸው እንዲመለሱ አደረጉ።
--
ሐዘን አይረሳም ልብ ውስጥ ይቀበራል እንጂ እንዲሉ፤ የነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሞት ለዚህ ኡማህ ለሶሓባዎችና ለተከታዮቻቸው እጅግ ትልቅ ሐዘን ጥሎ ቀጠለ። በርግጥም ከባድ ናፍቆት፤ ከመሬት ታች ላለ ሰው ነው።
(ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም!)
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

03 Nov, 17:00


ርቀቱ በስሙ ልክ በሁለቱ ዐይናችን መካከል ይገኛል። የሕይወትን ኣጭርነት ያስታውሳል። አላህን የመገናኛ በራችን ነው። ጠዋቶች ዳግም የመቀስቀስ ምልክቶች ሲሆኑ፤ ማታዎች የሞት ማሳያ ምልክቶች ናቸው። ወደ እውነተኛው ሕይወት የሚያሻግር ድልድይ እንጅ፤ የህይወት ፍፃሜ ኣይደለም። ወደርሱ ወሳጅ ቢሆን እንጅ ግዜ የለም። እያንዳንዱ መተንፈስም ሞት ነው። ለእያንዳንዳችን የተደገሰ በዙሪያችን ያለ ዝምተኛው መካሪያችን ነው።
-
√ አምላካችን አላህ እንዲህ ይላል፦
قُلْ يَتَوَفَّاكُم مَّلَكُ الْمَوْتِ الَّذِي وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ۝
«በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት ይገድላችኋል፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡
📒አሰ`ሰጀዳህ (11)
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

01 Nov, 17:55


➩የቀኑ ➌ቱ ሐዲሦች‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ክፍል፦ 290

➊) ሙዓዊያ'ህ ኢብኑ ሓይደህ (ረድየል'ሏሁ ዓንሁ) እንዲህ ይላል፦ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! የአንዳችን ሚስት (በባሏ) ላይ ያላት ሐቅ (መብት) ምንድን ነው?» አልኳቸው።
«ስትበላ ልታበላት፣ ስትለብስ ልታለብሳት፣ ፊቷን ላትመታት፣ (መልኳን) ላታጥላላ፣ እንዲሁም ቤት ውስጥ ቢሆን እንጂ ላታኮርፋት ነው» ኣሉኝ።
ምንጭ፦📒ሶሒሁ ኣቡ ዳውድ (2142)
«معاوية بن حيدة القشيري قال: قلت: يا رسولَ اللَّهِ، ما حقُّ زَوجةِ أحدِنا علَيهِ ؟، قالَ: أن تُطْعِمَها إذا طَعِمتَ، وتَكْسوها إذا اكتسَيتَ، أوِ اكتسَبتَ، ولا تضربِ الوَجهَ، ولا تُقَبِّح، ولا تَهْجُرْ إلَّا في البَيتِ.»
*
➋) «ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ ሴት ልጅ የጌታዋን ሓቅ አትወጣም፤ የባሏን ሀቅ እስካልተወጣች ድረስ።» ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:-📒ሶሒሁ ተርጚብ (3/100)
«والَّذي نفس بيدِه لا تُؤدِّي المرأةُ حقَّ ربِّها حتَّى تؤدِّيَ حقَّ زوجِها.»
*
❸)«ከሌሊቱ ክፈለ ጊዜ ከእንቅልፉ ነቅቶ፣ ሚስቱንም ከእንቅልፏ ቀስቅሶ ሁለት ረካዓ አብረው ከሰገዱ፣ አላህን በብዛት ካወሱት ተርታ ይፃፋሉ።»
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:-📒ሶሒህ ኣቡ ዳውድ (1309)
«إذا أيقظَ الرَّجلُ أَهلَهُ منَ اللَّيلِ فصلَّيا أو صلَّى رَكعتينِ جميعًا كتبا في الذَّاكرينَ والذَّاكراتِ.»
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

30 Oct, 20:30


የኢማን መስታወት፣ የዲን ነፀብራቅ፣ የሐያእ ልብስ፣ የውበት ቀንዲል፣ የዩኒቨርሱ ሚዛን መጠበቂያ፣ ዘመን ተሻጋሪ የሴት ልጅ ውበት ነው። ሰትሮ ይሰትራል። ራስንም ሆነ ሌሎችን ከወንጀል መጠበቂያ ጋሻም ነው። ሴትና ሒጃቧ፣ እንቁና ዘውድ ናቸው፤ አይነጣጠሉም።
-
ሰውነትን በኣደባባይ ተራቁቶ መሔድ ጥንት በጋርዮሽ ዘመን የነበረ ልማድ እንጅ ዘመናችን ያመጣው ነፃነት ወይም ስልጣኔ ኣይደለም። ይልቁንም ሂጃብ ያልሰለጠ'ነውን የጃሒሊያን ስርዓት የሻረ በመሆኑ ዘመን የማያልፍበት የተላቀና የተከበረ የኣለባበስ ስርዓት ነው።
*
ሒጃብ/ኒቃብ ሴት ልጅ ሐፍረተ-ገላዋን የምትሸፍንበት፣ ውበቷን የምትጠብቅበት፣ እምነቷን የምታንጽባርቅበት፤ ከራስ ጸጉር እስከ ታች ጥፍር የሚሸፍን ወፍራምና ሰፋ ያለ፣ የሰውነት ቅርጽ የማያሳይ፣ ዕይታ የማይስብ፣ ፋሽን ያልሆነ፣ ለኢ-አማኒያን ርጋጽኻነት ማሳያ፣ ሰማያዊ እሴትና ትዕዛዝ ያለበት ትልቅ ኣምልኮ ነው።

یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّبِیُّ قُل لِّأَزۡوَ ٰ⁠جِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاۤءِ ٱلۡمُؤۡمِنِینَ یُدۡنِینَ عَلَیۡهِنَّ مِن جَلَـٰبِیبِهِنَّۚ ذَ ٰ⁠لِكَ أَدۡنَىٰۤ أَن یُعۡرَفۡنَ فَلَا یُؤۡذَیۡنَۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورࣰا رَّحِیمࣰا۝
አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
📒አል-ኣሕዛብ (59)
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

28 Oct, 21:18


በዚች ምድር መኖርን ለማቅለም የወርቅ-ቀለም የለም። ሕይወት ዛሬም ነች። የቀረንን ግዜ ባወቅን ግዜያችንን በመልካም ስራዎች፣ በዒባዳ ወረፋ ላይ ባደረግን ነበር። እድሜያችን እንደ መብረቅ ብልጭታ ነጉዷል። ሆኖም በሞኝነታችን ብዙ ግዜ እንንዳለን። በማናውቀው ነገ ላይ እንኖራለን።
-
ዓለምን መናቅ፣ የላይኛውን ክብር ማሰብ፤ ሳይታወሰን ሲቀር፤ ሲታወሰን የሰጠን ምቾት ልብ ላይ ሃሴት ያፈሳል። ዱንያ ያ'ሮጊት ቆንጆ ናት። በዥንጉርጉር ቀለሟ፣ በተስረቅራቂ ድምጿ፣ ስታዜም ለተመለከታትና ላደመጣት፤ ኢማንን ታዶለዱማለች።

ስለ ፅልመት አጽብሃ፣ ስለ ዓለም ብርሃን ቀለም ሳንታትር፤ በዚህ ዘበት ዓለም ተመላልሰን። ለነፍስ ዘላለም የሚባል ነገር አላት። ከሁሉ በፊት የሕይወት ፍልስፍና ይቀድማል። ነፍስን ከእሳት የማዳን ፍልስፍና።
'
ቀደምንም፣ ዘገየንም፣ መጨረሻችን ወደ መቃብር ነው። አላህም ቀብርን ጉብኝት ብሏታል። ከመጭው ዓለም አንፃር ስትታይ፤ የቀብር ቆይታ ጉብኝት ናት።

أَلْهَاكُمُ التَّكَاثُرُ (1) حَتَّىٰ زُرْتُمُ الْمَقَابِرَ (2)
«በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ። መቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ።»
📒አት-ተካሡር (2)
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

28 Oct, 17:38


በሶላት ላይ የሚሳነፍ ሰው‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ሶላት በእስልምና ዋነኛው አላህ በባሮቹ ላይ የደነገገው ተግባር ነው። ውዱ ነቢያችን (ሶለዋቱ ረቢ ወሰላሙ ዓለይሂ) «የቂያማ ቀን የመጀመሪያው ሂሳብ ላይ የሚቀመጠው ሶላት ነው። ሶላቱ ጎደሎ የሆነ ስራው ሁሉ ይጎላል!» ብለዋል። ሶላት ዐቅል አስቦት፣ ዐይን አይቶት፣ ቀልብ ተመኝቶት የማያውቅ ፀጋ ያለበትን የጀነትን መንገድ ትመራለች።
-
ሶላት ላይ የሚሳነፍ ሰው ተከታዮቹን ዱዓዎች ያብዛ፦
رَبِّ اجْعَلْنِي مُقِيمَ الصَّلَاةِ وَمِن ذُرِّيَّتِي ۚ رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَاءِ
➊) «ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ዱዓዬንም ተቀበለኝ።»
اللهم يامقلب القلوب ثبت قلبي على دينك.
➋) «ቀልብን ገለባባጭ የሆንከው አላህ ሆይ! ቀልቤን ወደ ዲንህ ገልብጠው።»
اللهم إني أعُوذ بك من العجْز والكسل.
❸) «አላህ ሆይ! እኔ ከስንፍና እና ከመታከት በአንተ እጠበቃለሁ።»
اللهم أعني على ذكرك و شكرك وحسن عبادتك.
❹) «አላህ ሆይ! አንተን በመዝከር፣ በማመስገን እና አምልኮህን በማሳመር ላይ አግዘኝ።»
اللهم اجعل قرة عيني في الصلاة.
➎) «አላህ ሆይ! የዓይኔን ማረፊያ (እርካታዬን) በሶላት ውስጥ አድርግልኝ።»
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

24 Oct, 19:34


ዱንያ አንዷን ሲይዟት፣ አንዷ ጎዳ'ይ ናት። ሆኖም ለገዘፈው ችሮታው በአመስጋኞች ምንዳ ልክ፣ ለአላህ ምስጋና ይገባው ማለትና የተሰጠንን ማስታወስ የአመስጋኝነት ማማ ላይ ያደርሳል። ሁሌም ደስተኛነትን ያረጋግጣል።
-
አይደለም ምድርን ያለ ሶሌታ፣ ሰማይን ያለምሶሶ ላቆመ ጌታ፣ ሁሉን አስገኝ፣ ሁሉን ሰጭ፣ የአጽናፈ ዓለሙ ሁሉ የሁለንተና ምንጭና ባለቤት ለሆነው ለአላህ፤ ፍጡር ለሆነው ለሰው ልጅ እንኳን ግንባርህ አይታጠፍ! አለማለት ከንፉግነት ነው።

አልሓምዱሊላህ! ማለት የአማኝ መገለጫው፣ የመቃመ ሪዷው ቦታ ነው። ማመን ማለት በማይመች ሁኔታ ውስጥ ሆኖ አላህን ማሰብ ነው። አማኝ በደረሰበት ሙሲባ ላይ ማመስገኑ የአላህን ውሳኔ ከመውድድ ነው።

ነብዩል`ሏህ ኣዩብ (ዓለይሂ ሰላም) «መከራ ነካኝ!» ማለታቸው እርሱ የሰራውን አለመውደድ ይሆንብኛል ብለው ነበር።

በማመስገን ውስጥ ነገ ከዛሬ በላይ ውብ ነው። የሕይወትን ሙሉ ጣዕም ለማጣጣም፤ በምስጋና ስነ-ልቦና መታነፅ መታደል ነዉ።
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

21 Oct, 16:50


ዱዓ ተቀባይነት ይኖረዋል የተባለባቸው‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
በሐዲሥ የመጡ ዱዓ ተቀባይነት ይኖረዋል የተባለባቸው ሁነት፣ ቀንና ወቕቶች፦
①) ከውዱእ በኋላ፣
②) ሱጁድ ላይ፣
③) በእኩለ-ለሊት፣
④) የዓረፋ ቀን ላይ፣
⑤) ዝናብ ሲዘንብ፣
⑥) ፆመኛ ሲያፈጥር፣
⑦) ከፈርድ ሶላቶች በኋላ፣
⑧) ለሌሎች ዱዓ ስታደርጉ፣
⑨) የታመሙትን ሲትጎበኙ፣
⑩) በዩኑስ ዱዓ አላህን የለመነ፣
⑪) ከሓጅ ወይም ከዑምራ በኴላ፣
⑫) የዘምዘም ውሃ ከመጠጣት በፊት፣
⑬) በረመዷን በተለይ በለይለቱል ቀድር፣
⑭) በጁሙዓ ቀን ከዓስር ሶላት በኋላ፣
⑮) በአዛንና በኢቃም መካከል ባለው ጊዜ።
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

18 Oct, 18:46


ሶላት ለሰው ልጅ ከአላህ በርሱ ወዴታና መሻት የተሰጠ ድንጋጌ ነው። ወደ አላህ ለሚደረግ ምስጋናም ሆነ ውዳሴ የማቅረብ ይዘት በሶላት ይካተታል። ሶላት የመጀመሪያው ሒሳብ፣ ብቸኛው የዝቅታ ከፍታ ነው። በተቃራኒው ችላ ባዩንም ያስጠይቃል።
-
ሶላት አላህን የመገናኛ መስመርም ነው። ወቅቶቹን ለጠበቀ የሁሉም መክፈቻ ቁልፍ። የስኬት ትልቁ መንገድ አላህን በብዙ ማስተውስ እንደሆነው፤ የኣንድ ሰው የውድቀት መጀመሪያው ደግሞ የአላህ ተጣሪ፣ እየተጣራ ሶላት ላይ መዘናጋቱ ነው።

ሶላት ረፍትም ነው። ልብ በሶላት ታርፋለች። በርሷ ውስጥ አላህን ሸክዋ ማድረግ አለ። ነፍስ በርሷ ትረጋ'ጋለች። ቀልብም ከዱንያ ድካም ታርፋለች።
ለዚያም أرحنا بها يا بلال «ቢላል! እስኪ አዛን በልና እንረፍ!» ይሉ ነበር። (ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም!)

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

13 Oct, 19:44


ከብርሐን የተፈተለ፣ የኣድማስ ላይ መቀነት‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ኹበይብ ኢብኑ ዓዲይ (ረድየል`ሏሁ ዓንሁ) በበድር ጦርነት ታላላቅ የቁረይሽ መሪዎችን ገድሎባቸው ነበር። በመጨረሻም ወደ ዓድልና ቃራህ ትእዛዝ ተሰጥቷቸው ሲሄዱ ቁረይሾች ያዙት። የበድር በቀላቸውን ለመወጣት ሊገድሉት ወሰኑበት። ከመገደሉ በፊት ሁለት ረካዓ እንዲሰግድ ጠየቃቸው። ቁረይሾችም ፈቀደሉት። ሁለት ረከዓ ሰገደ። ሲሰግድ አጠር አደረገው። እንዲህም አለ፦ «አጠር ያደረኩት ሞት ፈርቶ አስረዘመው፤ ትሉኛላችሁ ብዬ እንጅ ረዘም ባደርግው ያስደስተኝ ነበር።
ولست أبالي حين أقتل مسلما...
ሙስሊም ሆኜ በመገደሌ ምንም ዋይ! አያስብለኝም።
አላህ ሆይ! ሰላምታዬን ወደ ነቢዬ ሙሐመድ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) አድርስልኝ።» እያለ የቴምር ዛፍ ላይ ሰቅለው ገደሉት።
የበድር የኡሑድ ተሰላፊው ኹበይብ መሬት ራሷን ለሕድ አደረገችለት። መላኢካዎች ቀበሩት።
(ረድየል'ሏሁ ዓንሁ!)
-
ሰብዓዊነትን ሰብኮ ሰውነትን ከነጠቀ፣ መብት ብሎ በፌሚኒዝም ኣፈር ያልነካትን እንቁ ካራቆተ፤ ሳይንስ ብሎ በቁርኣን የሰው ልጅ ካረ'ቀቀ፣ የፈጠረውን እንኳን በትክክል ካላወቀ፤ የበላይነት፣ ዘመናዊነት የቱ ጋ ነው?
በአላህ ምድር ላይ ሆኖ በኢስላም - በመዳ ኛው ማፈር መሳቀቅ፤ ከኢማን፣ ከየቂን ድክመት የመነጨ መታበል ነው። ሆኖም አላህ ባሪያነትን የሚያስንቁ ባሮች አሉት። አላህ የቂናችንን ይጨምርልን። ኢማናችንን በልባችን ላይ ያጽናልን።
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

13 Oct, 18:52


➩የቀኑ ➌ቱ ሐዲሦች‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ክፍል፦ 289

➊) አብደ'ል-ሏህ ኢብኑ መስዑድ (ረድየል`ሏሁ ዓንሁ)፦
«የአላህ መልክተኛን (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) አላህ ዘንድ የወንጀሎች ሁሉ ትልቁ ምንድን ነው ብዬ ጠየቅኳቸው: አላህ ፈጥሮህ ሳለ ሌላ ልታመልክ ነው። ከዚያስ ቀጥሎ አልኳቸው። ኣንተ ጋር እንዳይበላ በመስጋት ልጅህን መግደል። ከዚያስ ቀጥሎ አልኳቸው። የጎረቤትህን ሚስት ማማገጥህ።»
ምንጭ፦📒ሶሒሁል ቡኻሪ (476)
سَأَلْتُ -رَسولُ اللَّهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم: أيُّ الذَّنْبِ عِنْدَ اللَّهِ أكْبَرُ؟ قالَ: أنْ تَجْعَلَ لِلَّهِ نِدًّا وهو خَلَقَكَ. قُلتُ: ثُمَّ أيٌّ؟ قالَ: ثُمَّ أنْ تَقْتُلَ ولَدَكَ خَشْيَةَ أنْ يَطْعَمَ معكَ. قُلتُ: ثُمَّ أيٌّ؟ قالَ: أنْ تُزَانِيَ بحَلِيلَةِ جَارِكَ.
*
➋) አንድ ሶሓቢይ ወደ ነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ዘንድ መጥቶ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! የእስልምና ድንጋጌዎች በዝተውብኛል። የሙጥኝ የምዘው አንድ ነገር ይንገሩኝ ሲላቸው፤ አላህን በማስታወስ ምላስህ ከመርጠብ አይቆጠብ።» አሉት።
ምንጭ፦📒ሶሒህ አት-ቲርሚዚ (3375)
«أنَّ رجُلًا قال: يا رَسولَ اللهِ، إنَّ شَرائِعَ الإسلامِ قد كَثُرَت عليَّ، فأخبِرْني بشيءٍ أتشَبَّثُ به، فقال: لا يزالُ لِسانُك رَطبًا مِن ذِكرِ اللهِ تعالى.»
*
❸) የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦ «ከእኔ በፊት የነበረ አንድም ያልተሰጠውን 5 ነገሮችን ተሰጥቻለሁ አሉ: ጠላትን በማስደንገጥ ተረድቻለሁ አንድ ወር ርቀት የሚያስኬድ ያህል ሲቀር፤ መሬት የመስገጃ ማዕከልና ከውዱእ የምታፅዳዳ ተደርጋልኛለች፤ ከህዝቦቼ ማንኛውም ሰው ሶላት ከደረሰበት ይስገድ፡፡ ከእኔ በፊት ለኣንድም ያልተፈቀደ የምርኮ ገንዘብ ተፈቅዶልኛል፤ ሸፈዓ ተሰጥቻለሁ፤ ነቢያቶች ለህዝባቸው ብቻ ነበር የሚላኩት፣ እኔ ወደሰዎች ሁሉ በአጠቃላይ ተልኬያለሁ።»
ምንጭ፦📒ሶሒሁል ቡኻሪ (335)
«أُعْطِيتُ خَمْسًا لَمْ يُعْطَهُنَّ أحَدٌ قَبْلِي: نُصِرْتُ بالرُّعْبِ مَسِيرَةَ شَهْرٍ، وجُعِلَتْ لي الأرْضُ مَسْجِدًا وطَهُورًا، فأيُّما رَجُلٍ مِن أُمَّتي أدْرَكَتْهُ الصَّلَاةُ فَلْيُصَلِّ، وأُحِلَّتْ لي المَغَانِمُ ولَمْ تَحِلَّ لأحَدٍ قَبْلِي، وأُعْطِيتُ الشَّفَاعَةَ، وكانَ النبيُّ يُبْعَثُ إلى قَوْمِهِ خَاصَّةً وبُعِثْتُ إلى النَّاسِ عَامَّةً.»
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

11 Oct, 22:11


ስለ ዓይናችን አንድ ልበል‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
የዓይናችንን (Close Up Image) ሲቀርብ የሚያሳይ ምስል ተመለከትኩና ከታች ካለው ምስል ጋር አጋራኋችሁ። ምስሉን Zoom አድርጋችሁ ተመልከቱት፤ Its So Amazing! How الله Create Our Body. Indeed, Allah is the Best Architect! በአንዲት ትንሽ የሰውነት ክፍል ላይ ብቻ የተከማቸ የአላህ ተዕምር!
||
የአላህን ጥበብ፣ እንዲሁም ውለታውን ለመረዳት የሰው ልጅ አፈጣጠር አንዱን Structure መመልከት በቂ ነው። ከአይናችን ወደ አዕምሮአችን አንድ ናኖ-ሰከንድ በማይሞሉ ግዜያት ውስጥ የሚያደረጉትን የመረጃ ልውውጥ ማስተተን ወደ ምስጋና ከሚያቀኑ መንገዶች ውስጥ አንዱ ነው።
*
ዓይናችን እንዴት ይሰራል፤ እንዴትስ እናያለን⁉️
✔️ ዕይታችን በአዕምሯችን ላይ ነው። የምናየው፣ የምንመለከተውና የምንገነዘበው በአዕምሮችን ነው። ዓይናችን ልክ እንደ ካሜራ ብቻ የሚያገለግለን ሲሆን፤ Just Capturing Light (ምስሉንን ያነሳል)፣ ከዚያም ያነሳቸውንና የሰበሰባቸውን ምስሎች፣ ብርሃንን ተቀብሎ ምስልን ወደ አዕምሮ በሚልከው የዓይን ክፍል በሬቲና አማካኝነት ወደ አዕምሮኣችን ይልካል።

የተላከው ምስል አዕምሮአችን ላይ ይደርሳል።
ከዚህ ሁሉ ሒደት በኋላ በዓይናችን የተነሳውን ምስል አዕምሮአችን ከሬቲና የሚላኩ Signaሎችን Process አድርጎ የምናስተውለውን ወጥ የሆነ ምስል ይፈጥራል። ምን እንደተከሰተም አይቶ ይገነዘባል።

በዚህ መልኩ አዕምሮአችን ከውጭ ወደ ውስጥ በዓይናችን እገዛ የተላከለትን ምስል ተመልክቶና አገናዝቦ አስገራሚ በሆነ ፍጥነት ቅፅበታዊ የሆነ ምላሹን ወደሚመለከተው የሰውነታችን ሕዋስ ክፍል ያደርሳል።
°
ለዚህም ይህንን ፁሁፍ እስከዚህ ድረስ ለማንበብ ጣቶቻችን ስልኩን በመዳሰስ፤ ዓይኖች ከመስመር መስመር እየወረዱ ስራቸውን እዲሰሩ ከዓይን በሚላክለት መረጃዎች አዕምሮ ሲያዛቸው ነበር።
*
ዓይናችን ስራውን ያለ እረፍት ከሚሰሩት የሰውነታችን ክፍል ውስጥ አንዱን ድርሻ ይይዛል። ዓይናችን በምድር ላይ በምቾት እንድንኖር የሚያስችሉን ፍፁም ፍጥረታት ናቸው። ዐይናችንን ከሚጎዱ ነገሮች መካከል ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በላፕቶፕ፣ ስልክ ወይም ታብሌቶች ላይ ለረጅም ሰዓት መመልከት (የስክሪን አጠቃቀም)፣ በተሽካርካሪ ውስጥ እየተጓዙ ማንበብ፣ በቂ ብርሃን በሌለው ቦታ ማንበብ፣ በቂ እንቅልፍ አለመተኛት...ከብዙ በጥቂት ተጠቃሾች ናቸው።

ዓይኖቻችን በጣም አስደናቂ ከመሆናቸው የተነሳ በጣም ዘመናዊ በሆነ ቴክኖሎጂ እንኳን ታግዞ ከአንድ ሰው ሕልፈት በኋላ ወደ ሌላ ሰው ንቅለ ተከላ እንጅ፤ እስካሁን እነርሱን የሚመስል ነገር መተካት አልተቻለም።

በሰውነታችን ውስጥ ካሉን ከእያንዳንዱ የአካል ክፍሎቻችን ውስጥ ለእኛ ዓይናችን በጣም አስፈላጊ ከሚባሉት ቀዳሚው ነው። ዓይኖቻችን ባይኖሩ፤ Imagine! ቤተሰብ፣ እናት፣ ወንድም፣ እህት፣...
አለም ምን እንደምትመሰል እንኳን አናውቅም ነበር።
ለመሆኑ ስንቶቻችን ለዓይናችን ጥንቃቄ እናደርጋለን?
*
ስለ ዓይናችን እውነታዎች‼️
✔️ ዓይናችን ከ2 ሚሊዮን በላይ ክፍሎች አሏት። እያንዳንዱ ክፍል 107 ሚሊዮን ህዋሳት አሉት።
ዓይኖች ሳይጨፍኑ ማነጠስ ፈፅሞ አይቻልም።

✔️ ከሰውነታችን ክፍል ውስጥ ዓይናችን ከህፃንነት እስከ እድገት ድረስ መጠኑ የማይቀየርና የማያድግ ሲሆን አፍንጫና ጆሮ ደግሞ ማደጋቸውን አያቆሙም።

✔️ ዓይናችንን በአንድ ሰከንድ ውስጥ 5 ግዜ የመርገብገብ ችሎታ አለው። ለዚህም ነው ዓይን በሰውነታችን ውስጥ በጣም ፈጣኑ ጡንቻ (The fastest muscles in our body) የተባለው ምክንያቱም በፍጥነት የሆነ ነገር ሲፈጠር ዓይናችን ጭፍን እናደርጋለን።

✔️ ነገሮችን የማገናዘብ አቅማችን በዓይናችን ላይ ይወሰናል። ሃይላችን ሁሉ ዓይናችን ላይ ይገኛል። ወደ አዕምሮችን እውቀት ከምንስብባቸው የስሜት ህዋሳት በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰስ፣ በማሽተት ካሉ የስሜት ህዋሳቶች ቢሆንም ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አብዛኛው ዕውቀት መግቢያ በር ከ80-85% በዓይን ላይ የተመሰረተ ነው። ለዚህም ነው ዐይን የአዕምሮ መልክተኛ የተባለው፤

✔️ ዓይን የአዕምሮ ብቻም ሳሆን የልብ መልክተኛም ነው። ውጩ አለም ላይ ያለን ሁሉ ወደ ልብ ያደርሳል። ዓይን ብርሃን ነው ልብን ያበራል። ዓይን ቀስትም ነው። ድንገት ባየው ነገር ልብ ይታመማል።
ለዚህም ነው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "النظرة سهم" እይታ ቀስት ነው ያሉት።

✔️ በአማካይ በደቂቃ ውስጥ ከ15-18 ግዜ ዓይናችንን ስናርገበግብ፤ በ24 ሰዓት ውስጥ ለ21,000 ግዜ ያህል እናርገበግባለን።

✔️ የሰው ልጅ ዓይን ከዘመናዊው ዲጂታል ካሜራ ጋር ሲነፃፃር 576MP (ሜጋ ፒክስል) ጥራት ሲኖረው፤ ካሜራ እስካሁን ከ12 እስከ 100MP ጥራት ያላቸውን ምስሎች የመቅረፅ ችሎታ አለው።

✔️ 180⁰ ያክል የዓይን እንቅስቃሴን የሚቆጣጠሩ ስድስት (Eye Muscles) የዓይን ጡንቻዎች አሉ። ስድስቱም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ አላቸው። ከስድስቱ አንዱ ላይ መዘግየት ወይም መድከም ከተፈጠረ ዓይን Strabismus (የተሳሳተ አይታ)፣ Diplopia - Double Vision (ክልታተ-ምስል)፣ Amblyopia - Lazy eye (የአንድ ዓይን እይታ ድክመት) መሰል በሽታዎች ይከሰታሉ።
*
ውስብስቡ የሰውነታችን ከፍል ሳይዛባ በትክክል ይሰራ ዘንድ ላደረገልን፤ ካለምንም ክፍያ በነፃ ዓለምን እናይ ዘንድ ያስቻለን አላህ ምስጋና ይገባው። አል-ሐምዱ'ሊላህ‼️
በዚች በትንሿ የሰውነታችን ክፍል በዓይናችን ላይ ይህ ሁሉ ተዓምር ካለ፤ በሌላው ሰውነታችን ላይስ? በአፅናፈ ዓለሙስ ላይ?

የሚያሳዝነው የተሰጠንን ኒዕማ አላስታውስንም። ተገቢ የሆነን ምስጋናመ ለአላህ አልሰጠንም። ተገቢ የሆነውን አሐዳዊ ተመላኪነቱም ብዙዎች ዘንድ ተዘንግቷል። ማየት፣ መስማትና መገንዘብ ከታላላቅ የአላህ ውለዎች ውስጥ ቀዳሚዎቹ ናቸው።
አምላካችን አላህ (ሱብሃንሁ ወተአላ) ጥቂት አመስጋኝ ስለመሆናችን እንዲህ ይለናል:-

قُلْ هُوَ الَّذِي أَنشَأَكُمْ وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ ۖ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُونَ۝
«እርሱ ያ የፈጠራችሁ ለእናንተም መስሚያና ማያዎችን፣ ልቦችንም ያደረገላችሁ ነው፡፡ ጥቂትንም አታመስግኑም» በላቸው፡፡
📒አል-ሙልክ (23)
:
ይህንን ሁሉ አፈጣጠር ስንመለከት የአላህን ልዑልነት፣ ታላቅነትና፣ ድንቅ አፈጣጠሩን ስናይ የበለጠ የአላህን ሀያልነት ጥበብና ውለታውን እንረዳለን። ውለታውን ባንደርስም እንታገላለን። ለሚዛናችን እናመሰግናለን።
አልሐምዱ-ሊላህ‼️
*
አቡ ሒባ
-----------
ሐምሌ 25, 2014 E.C
ሙሐረም 3,1443 H.C
August 1, 2022 G.C
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

09 Oct, 18:05


የዘንድሮው ዐለም አቀፍ ይመስላል። አላህ ሲቆጣ ሁሉ ጁንድ ነው። የእርሱ ቁጣ ከርሱ ውጭ መላሽ የለውም። የቁጣዎች ሁሉ ቁንጮና በደል የአላህን ተመላኪነት ካለመቀበል ይጀምራል። አላህ እንደሰው ኣይደለም ሆኖም ሰዎች ክፋታቸውን ሲቀጥሉ፤ አላህ ትዕግስቱን ይቀይራል። በደቂቃዎች ኣውሎ ንፋስ ቤቶችና ተሽከርካሪዎች እንዳልነበሩ ሆነዋል። ጊዜው እየከፋ በሄደ ቁጥር መመኪያ አላህ ብቻ ይሆናል።
ኣዛኝ ነሕና እዘንልን‼️
وَاتَّقُوا فِتْنَةً لَّا تُصِيبَنَّ الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنكُمْ خَاصَّةً ۖ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ
«ከናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ፡፡ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን እወቁ።»
📒ኣል-አንፋል (25)

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

04 Oct, 16:52


በቁርኣን እንተዎወስ‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ክፍል፦143

ርቀቱ በስሙ ልክ በሁለቱ ዐይናችን መካከል ይታያል። የሕይወትን ኣጭርነት ያስታውሳል። አላህን የመገናኛ በራችን ነው። ጠዋቶች ዳግም የመቀስቀስ ምልክቶች ሲሆኑ፤ ማታዎች የሞት ማሳያ ምልክቶች ናቸው። ወደ እውነተኛው ሕይወት የሚያሻግር ድልድይ እንጅ፤ የህይወት ፍፃሜ ኣይደለም። ወደርሱ ወሳጅ ቢሆን እንጅ ግዜ የለም። እያንዳንዱ መተንፈስም ሞት ነው። ለእያንዳንዳችን የተደገሰ በዙሪያችን ያለ ዝምተኛው መካሪያችን ነው።
-
√ አምላካችን አላህ እንዲህ ይላል፦
قُلْ يَتَوَفَّاكُم مَّلَكُ الْمَوْتِ الَّذِي وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ۝
«በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት ይገድላችኋል፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡
📒አሰ`ሰጀዳህ (11)
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

02 Oct, 17:05


አኼራ የሚያስከብረው አላህን አውቆ በትክክል መገዛት ብቻ ነው። ከአላህ የመጣን፣ በፀጋው ያደርን፣ በእርሱው የኖርን ኾነን፤ ስለተሰጠን ሁሉ አስተውሎት ፍላጎትና ማስተንተን ጠፋን። በነገ ምርኩዝ ላይ ቆመን፤ ልብ ርቆ፣ ቀለም ሳበን። ወደ ውስጥ መመልከቻ መነፀራችንን ኣጣን። አበባችን ከውስጥ አልፈካ ኣለን። ለእኔ አንተ የሚገ'ድ አይነት መንገድ፤ በዓይን ለሚታይ በእጅ ለሚዳሰስ በገጸ ቁስ ላይ አደርን።
-
ተራችን ስንት ስዓት፣ በየትኛው ቀን ሂያጅ እንደሆን የማናውቅ ተሰላፊዎች ነን። ሆኖም ስለነጋችን መሳል፣ አርቆ ማሰብ ላይ ፕሮግራምድ ሆነናል።

የስኬት መነፀራችን፣ የመዘንጋት ተያዣችን፣ የኣርምሞው ፍፃሜያችን፣ የነገ ዋስትናችን፤ ምን ይሆን⁉️

الناس نيام فإذا ماتو انتبهوا
«ሰዎች እንቅልፍ ውስጥ ነው ያሉት፤ የሞቱ ጊዜ ይባትታሉ።»

መጨረሻችንን አላህ ያሳምርልን!

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

26 Sep, 20:25


ነቢያችን (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) «በላጭ ሰዋችሁ ብሎ ማለት ለባለቤቱ መልካም የሆነው ነው» እንዳሉት፤ መልካምነት ቤት ሲገለጥ ኩሉ ያምራል። ከምንም በላይ ለባለቤቱ መልካም ሰው ደስ ይላል። ቤተሰቧን ያከብራል። ሶስተኛ ወገንን አያስገባም። አይጨቃጨቅም። የብሽሽቅ ሰጋር ላይ ኣይቆናጠጥም። የአቀበት ኩርፊያ ላይ ኣይሳተፍም። ስለርሱ ብትጠየቅ «ነፍሳችን ይናበባል፣ ሳናወራ እንግባለን መልካም ሰው ነው!» የምትልለት አይነት ወንድ`ም ነው። ታታሪ ነው፣ ጠንካራ - በሃላሉ ለፍቶ አዳሪ፤ ሃላፊነትን መውሰድ ይችላል። ደጋግሞ መኖር፣ መልካም አኗኗር በነርሱ ትዳር ውስጥ ይታያል።

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

26 Sep, 20:11


➩የቀኑ ➌ቱ ሐዲሶች‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ክፍል፦ 288

➊) «ጁሙዓን አላህ ከሌሎች ሕዝቦች ጠብቆ ለሙስሊሞች ኣቆይቷል። ኣይሑዶች ቅዳሜን ክርስቲያኖች ደግሞ እሑድን ሓይማኖታዊ የእረፍት ቀኖቻቸው ኣድርገው ያዙ። አላህ እኛ ሙስሊሞችን ወደ በላጩ ቀን ጁሙዓ መራን። በቀናት ቅደም ተከተለም ጁሙዓ፣ ቅዳሜ፣ እሑድ ስንል ጁሙዓ ከ2ቱ ቀድሞ ይመጣል። ምድር ላይ እንደሆነው ሁሉ በፍርድ ቀንም መስሊሞች ከኣይሑድና ከክርስቲያኖች ቀድመው ወደ አላህ ፊት ይቀርባሉ። እኛ ሙስሊሞች በታሪኽ ከእነዚህ 2 ሓይማኖቶች በኳላ ላይ ብንመጣም በፍርድ ቀን ከፍጡራን ሁሉ ቀድመን እንዳኛለን።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦📒ሶሒህ ሙስሊም (856)
«أضَلَّ اللَّهُ عَنِ الجُمُعَةِ مَن كانَ قَبْلَنا، فَكانَ لِلْيَهُودِ يَوْمُ السَّبْتِ، وكانَ لِلنَّصارَى يَوْمُ الأحَدِ، فَجاءَ اللَّهُ بنا فَهَدانا اللَّهُ لِيَومِ الجُمُعَةِ، فَجَعَلَ الجُمُعَةَ، والسَّبْتَ، والأحَدَ، وكَذلكَ هُمْ تَبَعٌ لنا يَومَ القِيامَةِ، نَحْنُ الآخِرُونَ مِن أهْلِ الدُّنْيا، والأوَّلُونَ يَومَ القِيامَةِ، المَقْضِيُّ لهمْ قَبْلَ الخَلائِقِ.»
*
➋) ነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) በጁሙዓ ቀን በሰዎች አንገት ላይ ሲያልፍ የተመለከቱትን አንድ ሰው «ቁጭ በል! አርፍደህ መጥተህ ሰዎችን አታውክ።»
ምንጭ፦📒አቡ ዳውድ (1118)
«اجلسْ؛ فقدْ آذيتَ وآنيتَ.»
*
❸) «በጁምዓ ቀን የአል-ከህፍ ምዕራፍን ለቀራ ሰው በ2ቱ ጁሙዓዎች መካከል (ከአንዱ ጁምዓ እስከ ሌላኛው) ብርሃን ይሰጠዋል።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦📒ሶሒህ አት-ተርጚብ (736)
«من قرأ سورةَ الكهفِ في يومِ الجمعةِ أضاء له من النورِ ما بين الجمُعَتَين.»

||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

22 Sep, 21:06


የነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ስሞች‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ነብዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦
«እኔ 5 ስሞች አሉኝ: እኔ ሙሐመድ ነኝ፣ እኔ አሕመድ ነኝ፣ እኔ ማሒ ነኝ አላህ እኔን በመላኩ ክህደትን የማስወግድ የማብስ፣ እኔ ሐሽር ነኝ ሰዎች ሁሉ ከእግሬ ስር የሚቀሰቀሱት፣ እኔ ዓቂብ ነኝ ከእኔ በኋላ ነቢይ የለም።»
«لِي خَمْسَةُ أسْماءٍ: أنا مُحَمَّدٌ، وأَحْمَدُ، وأنا الماحِي الذي يَمْحُو اللَّهُ بي الكُفْرَ، وأنا الحاشِرُ الذي يُحْشَرُ النَّاسُ علَى قَدَمِي، وأنا العاقِبُ الذي ليس بعده نبيٌّ.»

ምንጭ፦📒ሙስሊም (2354)

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

22 Sep, 20:58


በቁርኣን እንተዎወስ‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ክፍል፦142

ዘመናዊ አስትሮ-ፊዚክስ የስበት ህግን በመከተል ፕላኔቶች፣ ጨረቃዎችና ኮከቦች በቋሚ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን የስነ-ፈለክ ተመራማሪዎች ይናገራሉ።
-
ይሁን እንጅ መሬት ፀሓይና ጨረቃ የየራሳቸው ሚናና እና የተለያዬ ምሕዋር አሏቸው። በዚህም ምክንያት የቀንና የሌሊት ዑደቱ ተፈራርቋል። ሌሊትና ቀን አንዳቸው ሌላውን ኣለማለፉ የምድርን መዞር ቢጠቁምም፤ የምድር መዞር አንዱ ሌላውን የማይቆጣጠርበት ሚዛንን ያረጋግጣል። የፀሓይ መውጫና መጥለቂያ ግዜም ከቦታ ቦታ ይለያያል።

√ ይህንን ክስተት የፀሓይ የመውጫና መግቢያ መፈራረቅ ለመግለፅ አንድ ምስራቅና፣ አንድ ምዕራብ ኖረው ሳለ፤ አላህ ቁርኣን ላይ:
'ربُ المشرقين ورب المغريبين'
«አላህ የምስራ ቆችና የምዕራ ቦች ጌታ ነው።» ይላል።

ለዚያም ነው የአፍሪካው ከአውሮፖው፣ የአውሮፖው ከአሜሪካው የፀሐይ መውጫና መጥለቂያ ጊዜ ተፋርቆ ለየቅል የሆነው።
'
ሌሊት ከመዓልታት አንዱ ሌላውን ሳይቀድም ሚዛኑን ጠብቆ መፈራረቁ፤ የአጽናፈ ሰማይ መዋቅር ለአላህ ያለውን ታዛዥነትና ተዓምሩን ያስገነዝባል።
*
✔️ የዘመናችን ጥናትና ምርምር ደረስኩበት ያለን የስነ-ፈለኮች ምርምር ኩሉ በዚህ አንቀፅ ታቅፏል።

«ሁሉም በራሳቸው ምሕዋር ላይ ይዞራሉ!»
لَا الشَّمْسُ يَنبَغِي لَهَا أَن تُدْرِكَ الْقَمَرَ وَلَا اللَّيْلُ سَابِقُ النَّهَارِ ۚ وَكُلٌّ فِي فَلَكٍ يَسْبَحُونَ۝
ፀሐይ ጨረቃን ልትደርስበት አይገባትም፡፡ ሌሊትም ቀንን (ያለ ጊዜው) ቀዳሚ አይኾንም፡፡ ሁሉም በመዞሪያቸው ውስጥ ይዋኛሉ፡፡
📒ያሲን (40)
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

19 Sep, 17:05


ሶለዋት ➝ የአላህን እዝነት ያስገኛል‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ለአለማት እዝነት ተደርገው በተላኩት በውዱ ነብያችን ሙሐመድ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማውረድ በጁሙዓ ዕለት ከሚወደዱ ዒባዳዎች መካከል አንዱ ነው። ሶለዋት ሱና ብቻ ሳይሆን የአላህን ትእዛዝ መታዘዝ ብሎም፤ የቂያም ቀን የርሳቸውን አማልጅነት ማገኛም መንገድ ነው።
-
በርሳቸው ላይ ሶለዋት ማውረድ የአላህን እዝነት ያስገኛል። አላህ ኸይር ነገር በርሳቸው ላይ አወረደ፤ እኛንም ከዚህ ኸይር ተጋሪዎች አደረገን። ኣንድ ሶለዋት ስናወርድ፤ አላህ በእኛ ላይ ዓስር ሶለዋት ያወርዳል። ከአላህ ዘንድ ለፍጥረታት የሚወ'ረድ ሶለዋት ደግሞ ከጨለማ ያወጣል። ብርሓንን ያስገኛል። የኣላህን እዝነትና ውዴታን ያጎናጽፋል።
*
በጁሙዓ ዕለት፣ ተሽሑድ ላይ፣ የርሳቸው ስም ሲነሳ፣ ኣዛን ሲባልና መስጅድ በምንገባበት ጊዜ በነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማውረዱ ይበልጥ ሙስተሓብ ከሚሆኑባቸው ወቅቶች ናቸው።

√ ሶለዋት አጭር ድካም ትልቅ ትርፍና የተነባበረ ፀጋ!
«በእኔ ላይ ኣንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ፤ አላህ በርሱ ላይ ዓስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:-📒ሙስሊም (384)
«مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلاَةً صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا.»

√ ሶለዋት ከነብዩ ጋር በቀጥታ ሰላምታን ያስገኛል።
«ማንም ሰው ለእኔ ሰላምታ (ሶለዋት) ካደረገ፤ አላህ ሩሔን ይመልስና ሰላምታውን እመልስለታለሁ።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦📒ሶሒህ አቡ ዳውድ (2041)
«ما من أحدٍ يسلِّمُ عليَّ إلَّا ردَّ اللَّهُ عليَّ روحي حتَّى أردَّ عليْهِ السَّلامَ.»

√ በተቃራኒው ደግሞ በነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማድረግን የሰሰተ፤ በራሱ ላይ ኸይር ነገርን ከማግኘት ሰስቷል። በነፍሱ ላይ ነፍጓል።
ነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦
«ስስታም ማለት ከርሱ ዘንድ እኔ እየተወሳሁ፤ በኔ ላይ ሶለዋት ያላወረደ ነው።»
ምንጭ፦📒ሶሒሁ ቲርሚዚ (3546)
«البخيلُ الذي من ذُكِرْتُ عندَه فلم يُصَلِّ عليَّ.»

✔️ የሶለዋት ነገር ከባድ ከመሆኑ የተነሳ አላህ ራሱ እኔ አወርዳለሁ፤ እናንተም ኣማኞች ሁሉ በነቢዩ ላይ ሶለዋት አውርዱ የሚል ትዕዛዛዊ–መልክትን በቁርኣን ነግሯል።

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا۝
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡
📒አል-ኣሕዛብ (56)
*
✔️ሶለዋት የምናወርደው እንዴት ነው⁉️
———
ከዕብ ቢን ዑጅረህ (ረድየል'ሏሁ ዓንሁ) እንዲህ ይላል፦
إنَّ النبيَّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ خَرَجَ عَلَيْنَا،
فَقُلْنَا: يا رَسولَ اللَّهِ، قدْ عَلِمْنَا كيفَ نُسَلِّمُ عَلَيْكَ،
ነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ወደኛ መጡ። የአላህ መልክተኛ ሆይ! በአንተ ላይ ሰላምታ እንዴት ማድረግ እንዳለብን አወቕን።
فَكيفَ نُصَلِّي عَلَيْكَ؟
“ሶለዋት የምናወርደው'ስ እንዴት ነው?” ብለን ጠየቕናቸው።
قالَ: فَقُولوا
እንዲህ በማለትም አስተማሩን፦
«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آل مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد.»
ምንጭ፦📒ሶሒሁል ቡኻሪ (6357)
“አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ነቢይና ሙሐመድ”
||
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me//AbuHiba

5,941

subscribers

90

photos

44

videos