ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር @bttsca Channel on Telegram

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

@bttsca


መጪው ጊዜ ብሩህ ነው

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር (Amharic)

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር በታሪክ ሽላሽ እና መረጃ እንዲወስኑ መረጃዎን ከሚያገኙ ተመሳሳይ ሴቶች አስታኝ ይሆናል። የብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር ልዩነት እና ሰዎች ሆና መጪው ጊዜ ለመገኘት በተዘረዘሩ የፈጠሩ እና እንስሳት፣ ብሩህ ስለ ሀገርና ስለ ዓለም የሚገኘው ውስጥ ለተማሪዎች እንሆናለን። በተጨማሪም የብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር አዘጋጅ በሚለዉ ሳቅ የሚሾር የለም። የብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር የተለያዩ መተግበሪያዎችን ለመሰረት እና የትምህርት ቦታዎችን ለመረዳት በመገኘት ከተጠቀሱት ሰዋላቸው ከበሩን በብቻ እንዲቀጥለው ጋር እያሉ ነው።

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

10 Oct, 08:56


ውድ አባላት
የ2017 ዓ.ም በዚህ ፕሮግራም መሠረት የምናስተናግድ ሲሆን እንደተለመደው ለውድ አባላት ሼር እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

17 Aug, 07:12


ለውድ አባላት በሙሉ
ከነሀሴ 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 1/2016 ዓ.ም ድረስ በአካል እየመጣችሁ የእንቁጣጣሽ በዓል ልዩ ብድር መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ለምዝገባ ስትመጡ
- የታደሰ የቀበሌ ወይም የመስሪያቤት መታወቂያ ኮፒ ከፊት ከጀርባ
- ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ እንድትመጡ በቅድሚያ እናሳውቃለን።

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

12 Jul, 10:49


ለውድ አባላት በሙሉ
የዓመቱን ሂሳብ ለመሥራትና ለማጠናቅ ባንክ አስገብታችሁ በጃችሁ ሪሲት ያለ አባላት ለኦዲት ስራ አስቸግሮናል በመሆኑም በአስቸኳይ ለፅ/ቤቱ እንድታስገቡልን እናሳስባለን።

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

10 Jul, 13:56


የ2017 ዓ.ም ፕሮግራም በቅርቡ የምንገልፅ ሲሆን የብድር ማመልከቻ ያስገባችሁ አባላት ብቻ በሚደወልላቹ ቀን መጥታችሁ ቼኮቻችሁን እንድትወስዱ ሲሆን ለመላው ውድ አባሎቻችን ለትምህርት የምትገቡ መልካም የትምህርት ጊዜ እንዲሁ መልካም የእረፍት እዲሆንላችሁ እንመኛለን።

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

06 Jul, 16:48


በድጋሚ ጥብቅ የስብሰባ ጥሪ
ሰኔ 26/2016 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤው ባለመሟላቱ ስብሰባው ለሁለተኛ ጊዜ መራዘሙ ይታወቃል።
ሆኖም በድጋሚ ቅዳሜ ሀምሌ 6/2016 ዓ.ም በተስፋ ኮከብ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከጠዋቱ 2:30 ይካሄዳል። ስለሆነም በዕለቱ ለውይይት የሚቀርቡት አጀንዳዎች

1.የማህበሩን 2017 ዓ.ም እቅድና በጀት ማፅደቅ
2.የትርፍ ትርፍ ክፍፍል መግለፅ
3.የሽምግልና ዳኞች መምረጥ
4.የአገልግሎት ክፍያን ማሳደግ
5.የመድህን ዋስትና አገልግሎት መወሰን
6.የሼር ግዢን አሳውቆ ማስወሰን መሆኑን በቅድሚያ እየገለፅን በማህበሩ ደንብ መሠረት በጉባኤው ላይ የማይገኝ አባል ብር 20 የሚቀጣ መሆኑን እናሳውቃለን።
                                             ኮሚቴው
  

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

03 Jul, 07:26


ለውድ አባላት በሙሉ
ሐሙስ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም አጣዳፊ ስራዎች ስለገጠሙን እንዲሁ ለ29/2016 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ መዘጋጀት ያለበት ጉዳዮች ስላሉብን በማንኛውም ጉዳይ እንዲሁ የሂሳብ ደብተር መሙላት  የማናስተናግድ ስለሆነ ውድ አባላት ይህንን አውቃችሁ እንዳትጉላሉ እንዲሁ ላልሰሙ አባላት መረጃውን እንድታሰራጩ እያሳወቅን በድጋሚ ከላይ በተገለፀው የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን።

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

01 Jul, 10:23


ጥብቅ የስብሰባ ጥሪ ለውድ አባላት በሙሉ
ማህበር በአዋጅ ቁጥር 985/2009 መሰረት በዓመት 2 ጊዜ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባ ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር ሰኔ 29/2016 ዓ.ም በተስፋ ኮከብ የመጀ/ደረጃ ት/ቤት ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ አባላት በሙሉ ስብሰባ እንደሚደረግ አውቆ እንዲገኝ እያሳሰብን በማይገኝ አባላት ላይ ደንቡ በሚፈቅደው ቅጣቱ ተፈፃሚ ሆኖ ከማህበሩ ሊያገኝ የሚገባውን ማንኛውንም አገልግሎት እንደማያገኝ በቅድሚያ እያሳወቅን በዕለቱ ለውይይት የሚቀርቡት አጀንዳዎች፦
1. የማህበሩን 2017 ዓ.ም እቅድና በጀት ማፅደቅ
2. የትርፍ ትርፍ ክፍፍል መግለፅ
3. የሽምግልና ዳኞች መምረጥ
4. የአገልግሎት ክፍያን ማሳደግ
5. የመድህን ዋስትና አገልግሎት መወሰን
6. የሼር ግዢን አሳውቆ ማስወሰን መሆኑን በቅድሚያ እንገልፃለን፡፡
ኮሚቴው

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

19 Jun, 10:18


ውድ አባላት

የ2016 ዓ.ም የብድር የመጨረሻ ፕሮግራም ማስታወሻ

     ማክሰኞ ሰኔ 25/2016


የ2016 ዓ.ም የሂሳብ  ደብተር መሙያ ቀናቶች ፕሮግራም ማስታወሻ

         በየሳምንቱ ሀሙስ

  ሰኔ 13/2016
  ሰኔ 20/2016
  ሰኔ 27/2016

ሲሆን በዚህ መሠረት እንድትስተናገዱ እናሳውቃለን።

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

08 Jun, 14:36


ለውድ የሙስሊም እምነት ተከታይ አባላት በሙሉ
እንኳን አደረሳችሁ እያልን የኢድ አልአድሃ አረፋ በዓል ልዩ ብድር ከሰኔ 3/2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 07/2016 ዓ.ም ድረስ እየመጣችሁ መበደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

08 Jun, 12:33


ውድ አባላት

የ2016 ዓ.ም የብድር ቀናቶች ፕሮግራም ማስታወሻ

ማክሰኞ ሰኔ 11/2016
ማክሰኞ ሰኔ 25/2016


የ2016 ዓ.ም የሂሳብ  ደብተር መሙያ ቀናቶች ፕሮግራም ማስታወሻ

         በየሳምንቱ ሀሙስ

  ሰኔ 06/2016
ሰኔ 13/2016
  ሰኔ 20/2016
  ሰኔ 27/2016

ሲሆን በዚህ መሠረት እንድትስተናገዱ እናሳውቃለን።

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

22 May, 10:12


ለውድ አባላት
በየሳምንቱ ሀሙስ ሀሙስ የምንሞላው የሂሳብ ደብተር ዓመታዊ የኢንስፔክሽን ስራ እና ግምገማ ከክ/ከተማ አመራሮች ጋር እያካሄድን ስለሆነ ውድ አባላት ይህን አውቃችሁ ነገ ሀሙስ ግንቦት 15/2016 ዓ.ም የነበረው ወደ ሳምንት የተዛወረ መሆኑን በትህትና እንገልፃለን።
ቴሌግራም ለማይጠቀሙ አባሎቻችንም ይህን መረጃ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን።

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

09 May, 04:53


☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
መደበኛ ብድር ለመውሰድ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር

02 May, 04:56


ውድ አባላት

የ2016 ዓ.ም የብድር ቀናቶች ፕሮግራም ማስታወሻ
ማክሰኞ ግንቦት 6/2016
ማክሰኞ ግንቦት 27/2016
ማክሰኞ ሰኔ 11/2016
ማክሰኞ ሰኔ 25/2016

የ2016 ዓ.ም የሂሳብ  ደብተር መሙያ ቀናቶች ፕሮግራም ማስታወሻ

         በየሳምንቱ ሀሙስ
ግንቦት 08/2016    ሰኔ 06/2016
ግንቦት 15/2016    ሰኔ 13/2016
ግንቦት 22/2016    ሰኔ 20/2016
ግንቦት 29/2016    ሰኔ 27/2016
ሲሆን በዚህ መሠረት እንድትስተናገዱ እናሳውቃለን።