🌿እነሆ ፍጥረትን ሁሉ የሚገዛ የመብረቅ ብልጭታ ሲከማችና የነጎድጓድ ድምፅ ሲጮህ ከደመናዎች ሆድ የዝናብ ጠብታዎችን የሚቀዳ፣ የፀሐይ ነበልባል ሲርገበገብ በብርሃን ቀን ጠንቅቆ እስኪመላ ድረስ በጠዋት በጨረቃ ክበብ ብርሃንን የሚመላ፣ የነፋስ ኀይል ሲነፍስ በሰማይ መስኮቶች ፀሐይን የሚያወጣ፣ በፀሐይ ክበብ በነፋሳት ሠረገላ የሚያደርግ እርሱ ዛሬ በኤፍራታ ምድር በቤተልሔም እንደ ምስኪን በእንስሶች በረት ተወለደ!
🌿ሠረገላ ኪሩብን ጫማ አድርጎ የሚጫማ በመባርቅት የሚረማመድ እርሱ ዛሬ በጨርቅ ተጠቀለለ! ዝቅ ብሎ ከፍ አደረገን። ከክብሩ ወርዶ ክብራችንን መለሰልን!
🌿እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ!!
©፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ