ለ15 ወራት በተደረገው ጦርነት የፋኖ ኃይሎች ወታደራዊ ጡንቻ በእጅጉ የፈረጠመበት፣ ፋኖ የስነ ልቦና የበላይነት የያዘበት፣ የብልፅግናን ሰራዊት መማረክም ሆነ መሳሪያውን መረከብ የፋኖ የዘወትር ተግባር የሆነበት ሁኔታ ተፈጥሯል። አልተሳካለትም እንጅ አብይ ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ ብዙ ሚሊዬን ዶላሮች አፍስሷል ፥ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን መከላከያውን የእሳት ራት አድርጓል።
ይህ ሁሉ የሚሆነው እንግዲህ ብልፅግናን አማራ ክልል ውስጥ መልሶ ለመትከል ነበር። ይህም ቅዥት ብቻ ሆኖ ቀርቷል። እግር ትከል የተባለው ካድሬም "የትኛውን እግሬን?፥ እግር ሳይኖረኝ?" የሚል ምክንያታዊ ጥያቄን ማቅረብ ጀምሯል።
ይህ ጉዳይ በእነ አብይ ቤት ሙሉ በሙሉ የመሸነፍን ፍርሃት ፈጥሯል።
እግረኛው ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ንፁሃንን መግደሉ የተለመደ ቢሆንም የአሁኑ የሚለዬው በራሱ በአብይ አህመድ ፊርማ በሚተኮሱ ድሮኖች ታስቦበት ህዝብ መጨፍጨፍ በመጀመራቸዉ ነው።
በሌላ በኩል አብይ ፋኖን አሸንፎ አገሩን መቆጣጠር ካልቻለ በስተቀር የዓለም ባንክ እና የIMF የዶላር ብድር ውል እና የፕሪቶሪያው ስምምነትም ሊተገበር እንደማይችል ተገንዝቧል።
በዚህ ወቅት የሚያደርገው የድሮን ጭፍጨፋ ዓለም አቀፋዊ ውግዘት እና ማዕቀብ ያስከትልብኛል ብሎ እንዳይሰጋ ደግሞ ምዕራባውያን በአሜሪካ ምርጫ፥ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት፥ በራሽያ ዩክሬን ጦርነት፥ በማይናማር ጉዳይ ትኩረታቸው መያዙን እንደ መልካም አጋጣሚ ወስዶታል።
የሚደረገው ጭፍጨፋ እነኝህን ነባራዊ ሁኔታወች መነሻ ያደረገ ሲሆን የአጭር ግዜ ግቡ ብልፅግና አየር ኃይልን በመጠቀሙ ከፋኖ የተሻለ ጉልበት እና መንግስታዊ ሞገስ ያለው መሆኑን በማሳዬት የካሬወችን ስነ ልቦና መጠገን ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ህዝቡ "መንግስትን" ማሸነፍ ለማትችሉት እኛን አስጨፈጨፋችሁን የሚል ጫና በፋኖ ላይ እንዲያሳድር ተፈልጎም ነው። ውጤቱ ግን በተቃራኒው ነው።
ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ከህዝብ ልብ መውጣቱን ስላረጋገጠ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል እንኳን ሲቪሊያንን መግደል እንደሌለበት በራሱ ካድሬ ሳይቀር የሚቀርበውን ጥያቄም መስማት አልፈለገም።
በአጭር አገላለፅ መንግስት መሆን እንደማይችል ያወቀው ብልፅግና የአሸባሪነት ሚናን እየተጫወተ እድሜውን ማራዘም ምርጫው አድርጓል።
አንዳንዶች የድሮን ጭፍጨፋውን ጉዳይ ደጋግመን ስንገልፅ ወታደራዊ ብልጫ ስለተወሰደብን አልያም ለተራ የጦርነት ፕሮፖጋንዳ ፍጆታ የሚመስላቸው አሉ። ዋነኛ ምክንያታችን ህዝብ የእነኝህን ሰወች ብልግና ማወቅ እና መታገልም ስላለበት ነው።
ከዚህ በተረፈ ብልፅግና ከፖለቲካዊ ሽንፈቱ ባሻገር ከተቆጣጠርነው ቀጠና ውስጥ አንድ ኢንች እንኳን ሊነጥቀን አልቻለም፥ አይችልምም። ይልቁንም ወሳኝ ኮሪደሮችን ተረክበነዋል። ገና በድሎችም እንደምቃለን!
ጠበቃና አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ