ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete @timehrt_bebet Channel on Telegram

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

@timehrt_bebet


ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete (Amharic)

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete በየትኛውም ክፍለ-መብት ውስጥ ስለሆነ እንዴት ጥናት ነው። እነሆ፣ ይህ በቤቴ የሚሆነው ትምህርት እንደሚገኝ እያሉ አስቸጋሪ ነው። በዚህ ትምህርት ክፍል ላይ በነነው 'Timehirtbebete' የሚበጠሱ ማንኛውንም ክፍል፣ መዳብና መሳሪያዎች ለመምረጥ ወደእንቅስቃሴ በሚል እንዴት ያለውን መሳሪያ አዘጋጅቷል። ይህ በመግባት 'Timehirtbebete' የቤቴ ምርት የሚሆነው፣ ለማስተናገያ ይህንን መሙላቂያዎች እና አዲሱ የእቃ ቁስል ያደረገዋል።

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

07 Apr, 19:39


.

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

11 Oct, 08:22


ስም እስከ አያት እና አድሚሽን Number አንድ ላይ ላኩ

https://t.me/+THq4GLLhocbPoSy-

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

10 Oct, 21:11


ውጤት ማየት ምትፈልጉ Admission number ግሩፖችን ላይ ይላኩልን ወዲያውኑ እናሳውቆታልን 🙏

https://t.me/+THq4GLLhocbPoSy-

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

09 Mar, 20:39


National Rank እና School Rank ማየት ምትፈልጉ Admission Number @FasilAds ላይ ይላኩልን ወዲያውኑ እናሳውቆታልን 🙏

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

17 Aug, 07:25


በፊዚክስ ትምህርት በጣም የታወቁ መምህራን ካሏችሁ ላይ ስልክ ቁጥራቸውን @Tmhrt_bebeteBot ላይ ያስቀምጡልን

ይፍጠን አስቸኳይ ነው 🙏

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

10 Aug, 17:20


Voice Chat ላይ በመግባት በድምፅ መወያት ትቻላላቹ

https://t.me/timehrt_bebet?voicechat=5d27b90ccd49b1bd8e

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

10 Aug, 17:18


Live stream started

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

13 Jul, 08:10


የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና እስከ ጥቅምት አጋማሽ ይሰጣል ተባለ ፤የኢኮኖሚክስ ትምህርት በፈተናው አይሰጥም ❗️

የ2013 ዓመት የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ማትሪክ እስከ ጥቅምት አጋማሽ እንደሚሰጥ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጅንሲ አስታውቋል።620ሺ ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ የተነገረ ሲሆን ከነዚህ መካከል 99 በመቶ የሚሆኑት ፈተናውን ለመወሰድ ተመዝግበዋል ሲሉ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሪ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ኤጀንሲው የፈተና ዝግጅት መጠናቀቁን የገለፀ ሲሆን ዘንድሮ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለኢኮኖሚክስ ፈተና እንደማይቀመጡም አስታውቋል።በአንዳንድ ክልሎች የኢኮኖሚክስ ትምህርት ባለመሰጠቱ ለፈተናው ተማሪዎች እንዳይቀመጡ ተወስኗል።.

ፈተናውን በክረምት ወቅት ለመስጠት ከብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ በወሰድነው መረጃ መሰረት አዳጋች መሆኑን ተረድተናል ሲሉ ዶ/ር ዲላሞ ተናግረዋል።ከ2200 በላይ የመፈተኛ ጣቢያዎች ዝግጁ የተደረጉ ሲሆን በክረምት ወቅት የፈተና አስፈፃሚዎች ለክረምት ትምህርት ስለሚሄዱ አስቸጋሪ ያደርገዋል ሲሉ ጠቅሰዋል።

በክረምቱ የፈተና ወረቀት ለማጓጓዝ እንደሚቸግር የገለፁ ሲሆን የመስከረም ወቅት የበዓላት በመሆኑ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲዎችን ቅበላ እና ክልሎችን በማማከር ወደ ጥቅምት አጋማሽ እንዲዘዋወር ተደርጓል።በጥቅምት አጋማሽ ከመቼ ጀምሮ የሚለውን በቀጣይ ይገለፃል ተብሏል።

ፈተናው የትግራይ ክልል ተፈታኞችን የማያካትት ሲሆን ከ2012 የትምህርት ዘመን ሳይፈተኑ የቀሩ 9446 ተማሪዎች መካከል 3300 ያህሉ ተመዝግበው ፈተናውን ያልወሰዱ ናቸው።እነዚህ ተማሪዎች ለማካተት ጥረት ይደረጋል ተብሏል።

በቤቴልሄም እሸቱ

[ዳጉ_ጆርናል]

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

13 Jul, 07:46


የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት ወር ይሰጣል።

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከጥቅምት 2014 ዓ.ም አጋማሽ በኋላ እንደሚሰጥ ገልጿል።

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ሳይጨምር 620 ሺህ ተማሪዎች ተመዝግበው ፈተናውን በመጠባበቅ ላይ ናቸው ተብሏል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ ኤጀንሲው በማንኛውም ሰዓት ፈተናውን መስጠት የሚያስችል ዝግጅት አድርጓል።

በሀገሪቱ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የኢኮኖሚክስ ትምህርት ባለመሰጠቱ ፈተናው የማይሰጥ መሆኑንም ገልጸዋል። #ኢዜአ

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

30 Apr, 05:15


ሰበር ዜና‼️

የ 2013 የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይሆኗል።

ተማሪዎች ምደባችሁን ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ።
ምደባችሁን ለማየት👇
http://result.neaea.gov.et/home/placement

ሌላኛው placement ያያችሁ ተማሪዎች የግቢያችሁን Logo Profile አድርጉ። ግሩፑ ላይ ተመሳሳይ logo ያላችሁ ተማሪዎች መተዋወቅ ትችላላችሁ ማለት ነው

@timehrt_bebet

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

29 Mar, 12:54


የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል።

የ2012 የ12ኛ ክፍል ፈተናን በተመለከተ ዛሬ በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦተሪ የተሰጠው መግለጫ በአጭሩ ሲጠቃለል ፦

- ከተፈተኑት ከግማሽ በላይ ተማሪዎች ከ350 በላይ አምጥተዋል።

- ፈተናውን ከወሰዱ አጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ 55.7 ፐርሰንቱ ከ350 በላይ አምጥተዋል።

- ከ600 በላይ ያመጡ ተማሪዎች 702 ናቸው።

- የዓመቱ ከፍተኛ ውጤት 669 ሆኖ ተመዝግቧል።

- #ከነገ ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታቸውን በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ድረገፅ እና በአጭር የፁሁፍ መልዕክት 8181 የፈተና መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት ይችላሉ።

- ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜን እና ማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተሰራ ነው።

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

27 Mar, 09:28


Live stream finished (14 minutes)

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

27 Mar, 09:17


https://t.me/timehrt_bebet?voicechat=3a1624221f7defa018

ይህን ሊንክ በመጠቀም በ Voice Chat ስለ ዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ..... በቀጥታ ( Live ) ከአሁኗ ሰከንድ ጀምሮ እንወያያለን...

በ Voice chat ለመሳተፍ Update የሆነው ቴሌግራም ሊኖራቹ ይገባል

ገባ ገባ በሉ ውይይቱ ተጀምሯል 👏👏👏

👇👇👇

https://t.me/timehrt_bebet?voicechat=3a1624221f7defa018

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

27 Mar, 09:14


Live stream started

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

07 Mar, 19:29


የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለምትወስዱ ወንድሞች እና እህቶታችን መልካም ፈተና እና እድል እንመኝላቹሀለን።

@timehrt_bebet

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

13 Feb, 05:03


የ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ጉዳይ ፦

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በ2013 ዓ/ም መጨረሻ (ሰኔ አካባቢ) ፈተናቸውን እንዲወስዱ ለማድረግ ከወዲሁ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

በ2012 ባች በታብሌቶች መዘግየት የቀረው የኦንላይ ፈተና የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ፈተናውን በኦንላይን እንዲወስዱ ለማድረግ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

አጠቃላይ የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ወደ 800,000 ይሆናሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር ለ74 ዓመታት ሲሰጥ የነበረውን የፈተና አሰጣጥ ሂደት በመቀየር ከ2012 ባች ጀምሮ በኦንላይ ለማስፈተን ጥረት ቢያደርግም ግዢ የተፈፀመባቸው 500 ሺህ ታብሌቶች በኮቪድ-19 ምክንያት ወደሀገር ባለመግባታቸው ሳይሳካ ቀርቷል፤ በ2013 ባች ግን ተግባራዊ ለማድረግ በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራ አሳውቋል።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ጫና የሚገኘውን የትምህርት ዘመን ከግምት ውስጥ አስገብቶ በ2013 ብሄራዊ ፈተና ላይ ችግር እንዳይገጥም ከወዲሁ እየሰራ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

11 Feb, 13:47


የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀት ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር በኦንላይን ሊሰጥ የነበረውን የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ ዛሬ አስታውቋል።

#በኦንላይን ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኮቪድ-19 ምክኒያት መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ነው በወረቀት ለመስጠት የታሰበው ብሏል ሚኒስቴሩ።

ከየካቲት 21 እስከ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ፈተናው እና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ወደ ዞኖች እንደሚደርሱ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ይሰጣል።

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

11 Feb, 13:47


#MoE

በትግራይ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚወስዱ ተገለፀ !

የትምህርት ሚኒስቴር የ 2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተናን በተመለከተ በዛሬው እለት መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒኤችዲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ ከ12ሺ ህ በላይ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በአካባቢው የትምህርት መሰረተ-ልማቶች ሙሉ ለሙሉ በመውደማቸው ፈተናቸውን በአካባቢያቸው በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እንደሚወስዱ ገልፀዋል፡፡

በዚህም መሰረት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተፈታኞች በአካባቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ትምህርት ቢሮዎች ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታትም ተፈታኞችን በክልሉ ወደሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የማጓጓዝ ስራዎች እንደሚሰሩ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ተፈታኞቹ ፈተናቸውን የሚወስዱባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም መቐለ ፣ አክሱም ፣ አዲግራት እንዲሁም ራያ የኒቨርስቲዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

05 Jan, 14:59


የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ2013 ዓ/ም በአማራ ክልል የተሰጠዉ የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡

ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከልም 96.85 % ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል ተዘዋውረዋል።

በዚህ አመት የተሻለ ውጤት የተመዘገበት መሆኑ ተገልጿል።

የፈተናዉ ውጤት ማለፊያ ነጥቡን በተመለከተ ለሁሉም ዞንና ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያዎች የተላለፈ ሲሆን ተማሪዎችም በየትምህርት ቤታቸው ውጤታቸውን በማየት የ9ኛ ክፍል ምዝገባ ከታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንዲያካሂዱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አሳስቧል።

ትምህርት በቤቴ / Timehirtbebete

05 Jan, 14:59


በኦሮሚያ የ8ተኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆኗል!

በኦሮሚያ ክልል የ8ተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱ 446,907 ተማሪዎች ውስጥ 417,411 የሚሆኑት ወደ ቀጣይ ክፍል መሸጋገራቸውን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በዚህም ከተፈታኞች ውስጥ 93.4% የሚሆኑት ማለፋቸው ነው የተነገረው።

29,096 (6.6%) የሚሆኑ ተማሪዎች የተሰጠውን ፈተና ወድቀዋል ሲል አክሎ ገልጿል።

የተማሪዎች ነጥብም ለየዞኑ ትምህርት ቢሮዎች እና ከተማ አስተዳድሮች በቴሌግራም መላኩ የተገለጸ ሲሆን እነሱም ለየወረዳ ትምህርት ቢሮዎች የሚያስተላልፉ ይሆናል።

ትምህርት ቤቶችም የተማሪዎችን ውጤት ከእነርሱ ወስደው ለተማሪዎች ያስታውቃሉ ተብሏል።

በሚቀጥለው ሳምንታት ውስጥ የ9ኛ ክፍል ትምህርት በክልሉ የሚጀመር ሲሆን የሚኒስትሪ ካርዶችን አትሞ የማሰራጨት ሥራም በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሰራል ሲል የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።