ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ @zerihungebrew Channel on Telegram

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

@zerihungebrew


በዚህ ቻናል ነባር እና አዳዲስ የጥበብ ሥራዎቼን የማቀርብበት ሲሆን እናንተም ሥራዎቼን በመመልከት ውስጣችሁን ታረኩበት ዘንድ እንሆ እላለሁ ።

አስተያየትዎን ገንቢ ሃሳብዎን እንዲሁም ማሣል ሲፈልጉ ከታች ባለው መረጃ ይጠቀሙ።
@zersh8
0929018509

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ (Amharic)

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ is a Telegram channel that focuses on providing daily devotional messages and teachings from the Orthodox Tewahedo Church. The channel's aim is to help followers of the Orthodox faith strengthen their spiritual journey through the guidance of the church's teachings and scriptures. Who is it? ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ is for individuals who follow the Orthodox Tewahedo Church and are looking for daily inspiration and guidance to deepen their faith. What is it? This channel provides daily devotional messages, teachings, and scripture readings from the Orthodox Tewahedo Church, aimed at helping followers stay connected to their faith on a daily basis. Whether you are looking for spiritual guidance, reflections on scripture, or simply seeking daily inspiration, ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ is the perfect channel for you. Join ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ today to start your spiritual journey with the Orthodox Tewahedo Church and receive daily inspiration and guidance to help you grow in your faith.

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

17 Jan, 10:14


ነገ ቅዳሜ ጋድ ነው ይጾማል

እንዴት ይጾማል...?

ነገ ጥር 10 ቀን የጥምቀት ጋድ ነው፡፡ አባቶቻችን እንዳይረሳ ጥምቀት ረቡዕ ወይም ዓርብ ሲውል ብቻ ሳይሆን ሁሌም በየዓመቱ እንዲጾም ወስነዋል፡፡ ከሰባቱ አጽዋማት ገብቶ መቆጠሩም ለዚህ ነው፡፡

ቅዳሜ (ቀዳሚ ሰንበት) ባይሆን እስከ ምሽት አንድ ሰዓት ጾሙ ይቆይ ነበር፡፡ እናቶች በጥምቀተ ባሕሩ ተገኝተው "የጥምቀት እራት" እያሉ ታቦት አክባሪ ካህናትን መመገባቸው ለምን እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡

ግን ዘንድሮ ቅዳሜ ጋድ በመሆኑ እንደ ዐቢይ ጾም ቅዳሜ ከጥሉላት መባልት (ሥጋ፤ ቅቤ፤ ወተት...) እንከለከልባታለን.... (ስንክሳር ጥር 10)

መልካም በዓለ ጥምቀት ይሁንላችሁ

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

23 Nov, 04:00


https://youtu.be/fAP7CO-XNC4?si=G4lvU3tThuwhNlR3

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

31 Aug, 08:13


ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት መጽሐፍ የተወሰነ ኮፒ በባኮስ እና በአርጋኖን 5 ኪሎ የሚገኙ መጽሐፍ መደበር ስለሚገኝ መውሰድ ትችላላችሁ።

ቅድመ ክፍያ የከፈለችሁ በውስጥ መስመር የሚመቻችሁን ስፍራ የሚቀመጥበትን ማሳወቅ ትችላላችሁ።


ክፍለ ሀገር ወይም በውጭ ለምትኖሩ የመቀበያ አድራሻ እና መንገድ ካመቻቻችሁ እልክላችኋለሁ።

በትዕግሥት ስለጠበቃችሁ አመሰግናለሁ። አንብባችሁ ደግሞ እውቀት የምታገኙበት የምትለወጡበት ያድርግላችሁ።

በቀጣይ ነገረ ሥዕል ክፍል 1 loading

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

05 May, 19:57


https://youtu.be/vXfv8taN9AA?si=m-zJ4j6nWB7vArTW

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

28 Feb, 06:00


ከቤተ ክርስቲያን ህልውና የምናስቀድመው ምንም ነገር የለም!
ማኅበረ ቅዱሳን
1. የተከበራችሁ አበው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፡፡ እንዳለ በዚህ ታላቅ የፈተና ወቅት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማስጠበቅ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጣችሁን ኃላፊነት ለመወጣት ምእመናንን አቅጣጫ በመስጠት የቀደሙ አባቶቻችሁን ፈለግ በመከተል ዛሬም በጽናት እንድትተጉ፤ ያከበረቻችሁን ቤተ ክርስቲያን በአንድነት ሆናችሁ እንድትጠብቁ በልጅነት መንፈስ በትሕትና እንጠይቃለን፡፡ በተጨማሪም የአባትነት የዋህ ልቦናችሁን በመጠቀም ያዘኑ፣ የጠቀሙ፣የተቆረቆሩ መስለው ቀርበው የግል ፍላጎታቸውን ለመፈጸም የሚጥሩ ስለሚኖሩ ሁሉንም በጥንቃቄ እንድትመረምሩ፤ቀኖች ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን በመዋጀት አንድነታችሁን እንድታጠነክሩና በቤተክርስቲያን ዙሪያ ስለሚፈጠሩ ችግሮች በጥልቀት እንድትወያዩና እንድትመካከሩ እናሳሰስባለን።
2. ከዚህ ውጭ ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅማት ጉዳይ የግል ፍላጎትንና ምድራዊ ዓላማን መሠረት አድርጋችሁ ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ውጭ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ለመተካት፣ ፓትርያርክ ለመሾምና የመሳሰሉትን ለመፈጸም የምትንቀሳቀሱ አንዳንድ አባቶች ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ማኅበራችን ይህንን ጉዳይ እየተከታተለ መረጃውን ለምእመናን የሚያደርስ መሆኑንም በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን፡፡
3. ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ መምህራነ ወንጌል፣ ካህናት ሆይ በጸሎትና በትምህርት ምእመናንን በማጽናናት፤ ከእውነት ጋር በመቆም እውነታውን በማሳየት ምእመናን ለቤተ ክርስቲያን ዘብ እንዲቆሙ በማድረግ ድርሻችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን።
4. ውድ ምእመናንና የማኅበራችን አባላት የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያንን ከአሳዳጆቿ የመጠበቁ ዋነኛ ኃላፊነት በዘመኑ ባለን ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርሰቲያን፣ ካህናትና ምእመናን ሁላችን እጅ ላይ ወድቆአል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ለአባቶችና ለካህናት ትተን “እኔ አያገባኝም፤ አይመለከተኝም” ልንል አይገባም፡፡ ሁሉም በየድርሻው ቤተክርስቲያኑን ለመጠበቅ መትጋት አለበት፡፡ በቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ጥፋትና ሊመጣ ያለውን ፈተና አስቀድሞ በመረዳት ቅዱስ ሲኖዶስ ቀደም ሲል በወሰነው መሠረት በየአጥቢያችን፤ በተለያየ መልኩ በመደራጀት፤ በቤተክርስቲያን ላይ ጥፋት ለማድረስ የሚመጡትን በመከላከል የቤተ ክርስቲያንን ስደት ለማስቆም መንፈሳዊ ግዴታችንን እንድንወጣ እንጠይቃለን፡፡
5. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በልዩ ልዩ አገልግሎት እየተሳተፋችሁ ያላችሁ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ማኅበራትና ሌሎችም ሁላችንም አንድነታችንን በመጠበቅ በጋራ አገልግሎቶችን በመፈጸም ድርሻችንን እንድንወጣ ለተግባራዊነቱ ጥሪ እናቀርባላን፡፡
6. ገዳም ድረስ ገብቶ መሣሪያ ያልያዙና: ራሳቸውን እንደሞቱ ቆጥረው እየኖሩ ያሉ መነኮሳት ላይ ግድያ የፈጸመ ማንኛውም የታጠቀ ኃይል (መደበኛም ይሁን ኢመደበኛ: በግልም ይሁን በቡድን: አማኝም ይሁን ኢአማኝ) ድርጊቱ ከሰውነት ተፈጥሮ የወጣ ነው፡፡ ምናኔንና የክህነት ክብርን በተቃረነ መልኩ ሰብእና የጎደለው ጥቃት ማድረስ ኢትዮጵያዊ ባህልም አይደለም፡፡ ጥቅም የሌለው ከንቱ ተግባር ነው፡፡ በዚህ የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ ይኖራል ብለን አናምንም፡፡ ጤነኛ በሆነ አእምሮ ታስቦ የተፈጸመ ነው ማለትም አይቻልም፡፡ ማስተዋል ተወስዶባቸው እውቀት ተሰውሮባቸው እንጂ ይህንን ማድረግ ቀርቶ ማሰቡም የሙት ሐሳብ ነው፡፡ ቀድሞ የሞተው ሟቹ ሳይሆን ገዳዩ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የቤተ ክርስቲያን አማኞች ሲበዙ እንጂ ሲያንሱ በታሪክ አልታየም:: ይህ ድርጊት ክርስቲያኖችን ሲያጠነክር እንጂ ሲያዳክም ታይቶ አይታወቅም፡፡ መጽሐፍ “ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንን ቤት ገፋው በዓለት ላይ ስለተመሠረተ አልወደቀም ” ባለው መሠረት ቤተክርስቲያን በጽኑ ዐለት ላይ የተመሠረተች ስለሆነ አታሽነፏትም። ዲዮቅልጥያኖስም አላጠፋትም:: ዲያብሎስም ዝናሩን እንዲሁ ጨረሰ:: ስለዚህ አትድከሙ: አትሳቱም እናንተ ሳትወለዱ የነበረች ቤተ ክርስቲያን እናንተ አልፋችሁም እንደ እናንተ ላሉት በስሑት መንገድ ለሚጓዙት ሁሉ እየጸለች ትቀጥላለች:: ሐሳቧም፣ ሥራዋም፣ ዓላማዋም፣ ግቧም ሰማያዊ ነውና።
በመጨረሻም ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ህልውና በላይ የሚያስቀድመው አንዳች ነገር የሌለ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና ለማለፍ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት ጋር በመናበብ የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን በዚሁ አጋጣማ እያሳወቅን፥ የሁላችንም የመሰባሰብና የአገልግሎት ማእከል ቤተ ክርስቲያን በመሆኗ ከሁሉም ነገር በፊት ቅድሚያ ሰጥተን ሊመጣ ካለው አደጋ ቤተ ክርስቲያናችንን የመጠበቅ ኀላፊነት በትጋት እንወጣ ሲል ማኅበረ ቅዱሳን በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል፡፡

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

10 Nov, 05:36


++++++++++ ጥቅምት_30 +++++++++

።። አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ።።


ጥቅምት ሠላሳ በዚህች ቀን ወንጌልን የጻፈ ሐዋርያው #ቅዱስ_ማርቆስ የተወለደበት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ማርቆስ_ወንጌላዊ

ጥቅምት ሠላሳ በዚህች ቀን ለእስክንድርያ ሊቃነ ጳጳሳት አለቃ የሆነ ወንጌልን የጻፈ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የተወለደበት ነው።

የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አርስጦቡሎስ ነው እርሱም ከአምስቱ አገሮች የሆነ የእናቱም ስም ማርያም ነው እርሷም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ተጽፋለች እርሱም አስቀድሞ ስሙ ዮሐንስ ነው። በግብረ ሐዋርያት ማርቆስ በተባለ በዮሐንስ እናት ቤት ሐዋርያት ይጸልዩ ነበር ተብሎ እንደ ተጻፈ። እርሷም ባለጸጋ ነበረችና የዮናናውያንን የሮማይስጥን የዕብራይስጥን ትምህርት ለልጅዋ ለማርቆስ አስተማረችው።

በአደገም ጊዜ በርናባስ ወንጌልን ለመስበክ ከጳውሎስ ጋራ ሲሔድ ይዞት ሔደ በእነርሱም ላይ የሚደርስባቸውን መከራ አይቶ በጵንፍልያ ከተማ ሳሉ ትቷቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።

ሐዋርያትም በተመለሱ ጊዜ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን አሕዛብ እንደ ተመለሱ እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ላይ ድንቅ ተአምራትን እንዳደረገ ተናገሩ። ይህ ብላቴና ማርቆስም ከእርሳቸው ስለ መለየቱ አዘነ ተጸጸተ።

ከዚያም አብሮአቸው ሊሔድ ፈለገ አስቀድሞ ትቷቸው ስለተመለሰ ጳውሎስ ሊአስከትለው አልወደደም በርናባስ ግን ወሰደው አጎቱ ነውና። በርናባስም ከአረፈ በኋላ ወደ ሮሜ አገር ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሒዶ ለእርሱ ደቀ መዝሙሩ ሆነ በዚያም ቅዱስ ጴጥሮስ የተረጐመለትን ወንጌልን ጻፈ በሮሜ አገርም አስተማረበት። ከዚያም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትእዛዝና በሐዋርያትም ትእዛዝ ወደ እስክንድርያ አገር ሔደ። በውስጥዋም የከበረ ወንጌልን አስተማረ ደግሞም በአፍራቅያና በአምስቱ አገሮች በርቃ በሚባልም አገር ወደ እስክንድርያ ከተማ በገባ ጊዜ ጫማው ተቆረጠ።

በዚያም በከተማው መግቢያ ጫማ ሰፊ ነበረ። ቅዱስ ማርቆስም እንዲሰፋለት ለርሱ ሰጠው ሲሰፋም ጣቱን ወግቶ ሰነጠቀው ከእርሱም ደም ፈሰሰ በዮናኒም ቋንቋ ኢታስታዖስ አለ ትርጓሜውም አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ማርቆስም ስሙን የምትጠራው አውቀኸው ነውን አለው እንጠራዋለን እንጂ አናውቀውም አለ።

እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ አባታችን አዳም ትእዛዙን እንደተላለፈ የጥፋት ውኃም እንደ መጣ ሙሴንም እንደላከውና እስራኤልን ከግብጽ እንዳወጣቸው ሕግንም እንደ ሠራላቸው ናቡከደነጾርም ወደ ባቢሎን ማርኮ እንደወሰዳቸውና ከሰባ ዓመት በኋላ ወደ አገራቸው ኢየሩሳሌም እንደ ተመለሱ ክርስቶስ ሥጋ በመልበስ ወደ ዓለም ስለ መምጣቱ ነቢያት ትንቢት እንደ ተናገሩ ያስተምረው ዘንድ ጀመረ።

ከዚያም በኋላ ወደ ምድር ምራቁን ትፍ ብሎ ጭቃ አድርጎ ጣቱን ቀባው ወዲያው ዳነ በጌታችንም አመነ። ያም ሰፊ ስሙ አንያኖስ ነው። ቅዱስ ማርቆስንም ወደ ቤቱ ወስዶ ልጆቹን ዘመዶቹንም ወደ ርሱ አቀረበ እርሱም አስተምሮ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው።

በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ሰዎች በበዙ ጊዜ የቅዱስ ማርቆስን ዜና ሰምተው የአገር ሰዎች ሊገድሉት ተሰበሰቡ እርሱም አንያኖስን ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሹሞ ልጆቹን ቄሶችና ዲያቆኖች አድርጎ ከዚያም ወደ በርቃ ወደ አምስቱ አገሮችም ወጥቶ አስተማረ። በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው በእርሳቸውም ዘንድ ሁለት ዓመት ኖረ ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው።

ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ተመለሰ ምእመናንም ተጨምረው በዝተው በታወቁ ቦታዎች ሁሉ በባሕሩም ዳር በላሞች መካበቢያ በሚባለውም አብያተ ክርስቲያን ሠርተው አገኛቸው።

ከሀድያንም የከበረ ሐዋርያን ይገድሉት ዘንድ በብዙ ድካም ፈለጉት እርሱም አምስቱን አገሮች ሲጐበኝ በሥውር ወደ እስክንድርያ ከተማ ይገባ ይወጣ ነበር። በአንዲትም ዓመትም ከአምስቱ አገሮች ተመልሶ ሚያዝያ ዐሥራ ሰባት ቀን በመድኃኒታችን የትንሣኤ በዓል ወደ ቤተክርስቲያን ገባ ሕዝቡም ሁሉ በዙሪያው አሉ። ከሀድያንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው በአንገቱ ውስጥ ገመዶችን አድርገው በከተማው ሁሉ ጎተቱት። እነርሱም ገና እንደፍየል ሙክት እንጎትተዋለን እያሉ ይጮኹ ነበር ። በላሞች መካበቢያና በሀገሪቱ አደባባይ በከተማውም ዙሪያ በየቀኑ ሲጎትቱት ኖሩ።

ሌሊትም በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐዋርያት ጋራ በነበረበት አርአያ ሁኖ ተገለጠለት ሰላምታም ሰጥቶ አጽናናው ቃል ኪዳንም ሰጠው። እነሆ አንተ ከወንድሞችህ ሐዋርያት ጋር ተካከልህ አለው። እርሱም በልቡናው ፈጽሞ ደስ አለው። በማግሥቱም ሁለተኛ ገመዶችን በአንገቱ አድርገው በአገሮች ሁሉ ጎተቱት በቀኑም መጨረሻ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።

ከሀዲዎችም ታላቅ እሳትን አንድደው የቅዱስ ማርቆስን ሥጋ ከውስጡ ጨመሩ ። በክብር ባለቤት ጌታችን ፈቃድም ንውጽውጽታ ጨለማ ቀዝቃዛ ነፋስ መብረቅና ነጐድጓድ ሆነ። ፀሐይም ጨለመ ከሀዲዎችም ሸሹ ምእመናንም መጥተው የሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስን ሥጋ ወሰዱ ምንም ጥፋት ሳይደርስበት ደኀና ሆኖ አገኙት በመልካም ልብስም ገንዘው በጥሩ ቦታ አኖሩት መታሰቢያውንም አደረጉ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።

ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምትና_ሚያዝያ
ጽሑፍ ከገድላት_አንደበት የተወሰደ

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

29 Sep, 21:09


የብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናት የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር እሁድ መስከረም ፳ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
********
ዛሬ መስከረም ፲፰ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት የብፁዕ አቡነ ሰላማን የቀብር ሥነሥርዓት በማስመልከት ቋሚ ሲኖዶስ ከቀትር በፊት አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት እሁድ መስከረም ፳ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ከቅዳሴ በኋላ የብፁዕነታቸው ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲፈጸም ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም መሠረት ነገ ቅዳሜ መስከረም ፲፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም ከቀኑ ፱ ሰዓት ላይየብፁዕነታቸው ክቡር አስከሬን ከሃሌ ሉያ ሆስፒታል በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአበው ቆሞሳትና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ጸሎት ከተደረገበት በኋላ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጉዞ በማድረግ ሥርዓተ ጸሎት ተደርሶ ሌሊቱን ሙሉ ጸሎተ ፍትሐትና ሥርዓተ ማኅሌት ሲደረግበት ያድራል።

በማግስቱ እሑድ መስከረም ፳ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ጠዋት ሥርዓተ ቅዳሴው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ከተካሔደ በኋላ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ አበው መነኮሳት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች ፣የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ታጅበው ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ገዳም በእግር ጉዞ ይደረጋል።

በካቴድራሉም ለብፁዕነታቸው የሚመጥን ሥርዓተ ጸሎት ተደርጎ የሕይወት ታሪካቸው ተነቦ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የማጽናኛ ቃለ ምዕዳን ተላልፎ ሲያበቃ ሥርዓተ ቀብሩ የሚፈጸም ይሆናል።

በሥርዓተ ጸሎቱ ላይ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ይገኛሉ።

የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን ።

መረጃው. የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

29 Sep, 20:58


Channel photo updated

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

21 Sep, 06:15


።።።።።።። +" በዓለ ሥዕለ አድኅኖ "+ ።።።።።።።።።።

።።።።።። መስከረም 10 ።።።።።።።።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

+ይህች ቀን በቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሳት ሥዕላት የሚነገርባት ክብርት ቀን ናት:: 'ሥዕለ አድኅኖ' ማለት 'እግዚአብሔር በረድኤት የሚገለጥበት: አንድም በቅዱሳኑ አማካኝነት ጸጋ የሚገኝበት: የሚያድን ሥዕል' ማለት ነው::

+ስለዚህ ነገር አንዳንዶቹ ሊነቅፉን ይፈልጋሉ:: እኛ ግን ከማን እንደ ተማርነው እናውቃለን:: ከመነሻው እኛ ሥዕልን አናመልክም:: ይልቁኑ አምልኮን እንፈጽምበታለን እንጂ:: ሥዕልን ለሰው ልጆች የሰጠ ራሱ ባለቤቱ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይመሠክራል::

+እንዲያውም የመጀመሪያው ሠዐሊ ራሱ አምላካችን ነው:: አዳምን እንደ መልኩ: በምሳሌው ሲፈጥረው መላእክት የእግዚአብሔርን ምሥል አዳም ላይ አይተዋልና:: (ዘፍ. 1:26) ለሙሴም ሥዕለ ኪሩብን እንዲሥል ያዘዘ ራሱ ነው:: (ዘጸ. 25:22) በዚያም ላይ ሆኖ ሙሴና አሮንን ሲነጋገራቸው ኑሯል::

+በመቅደሰ ሰሎሞንም ተመሳሳይ ነገርን እናገኛለን:: (2ዜና. 7:12, 1ነገ. 9:1) በሐዲስ ኪዳንም ጌታ ሥዕለ ኪሩብ ያለበትን መቅደስ ቤቴ (ማቴ. 21:13): የአባቴ ቤት (ዮሐ. 2:16) ሲለው: በቅዱስ ሰውነቱ ሲመስለውም (ዮሐ. 2:21) እንመለከታለን:: ቅዱስ ዻውሎስ ለገላትያ ሰዎች ስለ ሥዕለ ስቅለት ሲያስታውሳቸው (ገላ. 3:1): ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ በደም የተረጨች ልብስ ብሎ ያላትን መተርጉማን ያትታሉ:: (ራዕይ. 19:13)

+በትውፊት ትምህርት ደግሞ የመጀመሪያው ሥዕል በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ የተሳለ ሲሆን ሥዕሉም የእመቤታችን ነው:: "ሚካኤል በክነፊሁ ጾራ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ" እንዳለ ቅዱስ ያሬድ:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቃርዮስና ለቬሮኒካ (12 ዓመት ደም ይፈሳት ለነበረችው ሴት) መልክአ ገጹን ሠጥቷቸዋል::

('ቬሮኒካ' በላቲን 'ቬሮን-ኢኮን' 'እውነተኛ መልክ' እንደ ማለት ነው)

+ቀጥሎም ዮሐንስ ወንጌላዊ ለጢባርዮስ ቄሣር ሥዕለ ስቅለቱን ሲሥልለት ቅዱስ ሉቃስ ደግም የእመቤታችን 'ምሥለ ፍቁር ወልዳን' ሥሏል:: ከዚያም ሲያያዝ ይሔው ከእኛ ደርሷል::

+ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በከተሞች አካባቢ ቅርጾች በዝተዋልና ይሔ አላስፈላጊ መዋስ (ያውም ከመናፍቃን) ቢቀር መልካም ነው ባይ ነኝ:: ኋላ ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቁሞ ማውረድ ከባድ ነውና::

+" ጼዴንያ "+

+በዚህች ቀን ቅዱስ ሉቃስ የሣላትና ሥጋን የለበሰችው: ከፊቷም ወዝ የሚወጣትና ድውያንን የምታድነው የድንግል ማርያም ሥዕለ አድኅኖ ወደ ጼዴንያ ከወዳጇ ከብጽዕት ማርታ ዘንድ ገብታለች:: ቅድስት ማርታ ሀብት ንብረቷን በአብርሃማዊ ተግባር (በምጽዋትና እንግዳን በመቀበል) ላይ ያዋለች ክብርት ሴት ናት::

+ለእመ ብርሃን ካላት ፍቅር የተነሳ እንቅልፍ አልነበራትም:: ተግታ ታገለግላትም ነበር:: ሥዕሏን እንዲያመጣላት የላከችው ኢትዮዽያዊው መነኩሴ አባ ቴዎድሮስ የሥዕሏን ተአምራት ባየ ጊዜ ለራሱ ለመውሰድ ሞክሮ ነበር::

+ነገር ግን ከሁሉም በተሻለ የምትወዳት ቅድስት ማርታ ነበረችና በድንቅ ተአምር: በዚህች ቀን ወደ ጼዴንያ ገብታለች:: ቅድስት ማርታም ያለ ዕረፍት ስታገለግላት ኑራ ዐርፋለች::

+እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ጣዕሟን ፍቅሯን: ጸጋ በረከቷን: ከሥዕሏም ረድኤት ትክፈለን:: የቅዱሳኑም ክብር አይለየን::

ጽሑፍ ከ ወርቁ ፈንታው የተቀነጨበ

ቅድመ ሥዕልኪ እሰግድ ወለሥዕለ ወልድኪ እገኒ ማርያም ድንግል ማርያም እመ አዶኒ ማዕበለ ጌጋይ ጽኑዕ ሶበ ለአስጥሞ በጽሐኒ ሐመርየኒ ማዕዶትየኒ ሃይማኖትየኒ ማርያም ዘእንበሌኪ አልብየ ምንትኒ

በጽሒፍ ኢይፌጽሞ ለስብሐትኪ እንግዳ

ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ


‹‹‹‹ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ››››

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

13 Sep, 08:37


* ++ *

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

13 Sep, 08:36


።።።+++ ጥቂት ስለ አቡነ ሰላማ ከዓይን ምስክር+++።።።
ክፍል አንድ

ብፁእ አቡነ ሰላማ ጵጵስና ከመቀበላቸው ከዛሬ 18 ዓመት በፊት የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ አለቃ በነበሩበት ጊዜ የርሳቸው ሹፌር ለኔ ቤተሰብ ነበር አሁን ውጭ ነው።

እርሱ በስራ በነበረበት ጊዜ ገጠመኙን ያጫወተኝን ሁሌም ትዝ ይለኛል ላካፍላችሁ ።
በአንድ ወቅት ብፁእነታቸው ታመው ሆስፒታል አልጋ ይይዛሉ እናም እርሱ ስለሚወዳቸው እየሄደ እያደረ የሳስታምም ይላላክ ነበር ።

እና በአዳሩ ጊዜ ያለ እረፍት ለሌቱን ሙሉ ጸሎታቸው እንደማይቋረጥ በማየቱ ተገርሞ ሳይጨርስ በህክምና ቦታ ያሉ የታካሚ ቤተሰቦች የብፁእነታቸው ፀጋን ከሕይወታቸው ተረድተው በሃይላንድ ዕቃ ውሃ ከረፉበት አልጋ ስር በማስቀመጥ በቀጣዩ ቀን ሃይላንዱን በመውሰድ ለታማሚው በማጠጣት በመዳበስ ብዙ ታማሚዎች ተፈውሰው ወደ ቤታቸው ሲገቡ በዓይኑ በማየቱ አጫውቶኛል ።
።።።።።።+++።።።።
ሃብተ ፈውስ ከሃብተ ጸሎት እና ሁሉን ወዳድ የሁኑ አባቴ ብፁእ አቡነ ሰላማ እንኳን ለ 18ኛ ዓመት በዓለ ሲመትዎ እንኳን አደረስዎ !

በእድሜ በጤና ያቆይልን ጸሎትዎ አትለየን!
ይቆየን

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

13 Sep, 08:36


+++++ ++++++ ++++++

1,262

subscribers

384

photos

17

videos