የተዋሕዶ ልጅ @eotch Channel on Telegram

የተዋሕዶ ልጅ

@eotch


https://t.me/themonkintheworld

https://t.me/lllibrary

የተዋሕዶ ልጅ (Amharic)

ሰላም እና እንባ ለሚያስተዳደርበት ተጭኀት ያለው "የተዋሕዶ ልጅ" ቡድኖች ላይ ተመልከቱ። የተዋሕዶ ልጅ ቢሆን እናቴንቱ እንግዲህ ላይ ሊያሰማፋቸው ይችላሉ። ይህ ቡድን ለጥቅምቱ እንዲሆን በመዘጋጀት የሚገመገሙ ድረገጽዎችን በደጋሚ ያሸፍኑ። ከታከለው የትም ሰሞኑን ከተወላጁ ብንወዳደብ እኛን የደመቀ ምሽት ተደረገ። የተዋሕዶ ልጅ ቡድን በስልክ ላይ ያለው ወይም በደቂቃ ያለው በክፍለፊሽና በሴቶስ ለሃገራችን በተመረጡ ዛሬዎች እንወዳደም በሚሳተፍ ወር አካባቢ ብቻ ነው! ምክንያቱ ሊጫወት እንደሚችል አጠቃላይ ሊሆን ይችላሉ።

የተዋሕዶ ልጅ

11 Jun, 12:32


https://t.me/articlesfromsilouan

https://www.instagram.com/_silouan?igsh=ZWk3YWZiZngxczM2

የተዋሕዶ ልጅ

11 Jun, 12:32


"ላንተ እንደ መሰለህ እንደ ተለየችህ እንደ  ተነሣችህ የምትቀር አይደለችምና.... ።" [አረጋዊ መንፈሳዊ አራተኛ ድርሳን]

ከተወደደ ጌታ ጋር በተዋህዶ ለመኖር መናፈቅ በጎ የምትሆን ሕማም/መስቀል አላት። መስቀሉም ሁለት ወገን ነው እኒሁም ወደን ስለእርሱ(አንድም ሰለእኛው)የምንታመማቸው ናቸው። አንዱ ወገን ስለእርሱ መከራን መቀበል ነው። አንዱ ደግሞ ስለእርሱ ስጋዊ ደስታን/ፍትወታትን መተው ነው።

የመጀመሪያዋ(ስለእርሱ መከራን መቀበል) ለሁለተኛዋ(ስለእርሱ ፍትወታትን ለመተው) መንደርደሪያ ናት። ሕማም ከእርሱ ጋር ታዋሕዳለች ፍትወት ግን ከእርሱ ጋር ታለያያለች። ጌታችን ሕማማችንን ከሕማሙ ጋር  አንድ ሊያደርግ እንጂ ከስጋ ፈቃዳችን ጋር አንድ ሊሆን አልመጣም። ለዚም ነው ስለእርሱ ስጋዊ ደስታን መተው ስለእርሱ መከራን ከመቀበል የምትከብደው። በመከራ እርሱ አለ በስጋዊ ደስታ ግን እርሱ የለም።መኖር ስለማችል ሳይሆን መለኮታዊ ንፅሕናው ወደእርሱ ስለማታደርሰን ነው።

ስለዚህም ስለእርሱ መከራን ከተቀበለ ይልቅ ስለእርሱ ደስታውን/ፍትወቱን የተወ ይበልጣል።

ይህች ስለምን ሆነች?...

የክርስቶስ መንገድ ሲጀምሯት የምትጣፍጥ ናት። ስር ሲሰዱባት ግን እርሱን(ክርስቶስን) እስያገኙት የምታስመርር ናት።

ይህችስ ስለምን ሆነች?...

በክርስቶስ አዲስ ያልሆነች(አሮጌዋ) ማንነታችን ክርስቶስን ማፍቀር ስለማይቻላት ነው። በክርስቶስ ሕይወት ስር መስደድ ማለት በአሮጌው ማንነት ላይ ሞትን ማወጅ ማለት ነው። ሞት ደግሞ የምትመርር ናት። ክርሰቶስም የአሮጌው ማንነታችን መጎስቆል ምክንያት ከሆኑትን እናትም አባትም ሆነው ካሳያደጉን ፍትወታት ሊለየን መጥቷልና እንዲህ አለ "በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም። ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና"[ማቴ 10:34-34]

አባ መቃርስ በድርሳኑ አባ አግናጥዮስም በድርሳኑ(1) ጌታችን "አለም" ያለው የእኛን ስጋ እንደሆነ ተናግረዋል። ከክርስቶስ ጋር መኖር ለአሮጌው ማንነት ሞቱ ለአዲሱ ማንነት ትንሳኤው ነው።

አሮጌው ማንነትና ውሳጣዊ ሲኦል (the oldself and the inner hell)...

ይህቺኛዋ እንድንጀምር የተሰጠችን ፀጋ ለበጎ ስትወሰድብን ነው....

"ትሩፋትን  ስለተውህ ፤ መፈጸም ስለተሳነህ ዕረፍትን ፤ ጸጋን ስላጣህ ተስፋ  አታስቈርጻት። ይህች ተሰጥታህ የነበረች ጸጋ  የተነሣችህ  ልትገሥጽህ ፡ ልታስተምርህ ነው እንጂ ፤ ላንተ እንደ ፡ መሰለህ እንደ ተለየችህ እንደ  ተነሣችህ የምትቀር አይደላትምና ።መከራውን በመቀበል  ዐዋቂ ትሆን ዘንድ ልትፈትንህ  ነው እንጂ ።የምትሠራው  ትሩፋትህ ምግባርህ  ሁሉ በመከራው፡ ይፈጸምልሃልና ። በሷ ይቅርታ ከመከራው ታርፋለህ እንጂ..." አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን 4

አሮጌው የኀጢአት ማንነት ሊሞት ዳግመኛም ላይነሳ ሊቀር ብዙ የፈቃድ መስዋዕት ይፈልጋል።"“ከፈቃዴ እሠዋልሃለሁ...”[መዝ 54፥6]። በዚህ ጊዜ ግን ጌታችን ከእኛ የራቀ የሚመስልበት ጊዜ ነው ምክንያቱም ፈቃድዋን መሰዋት ለስጋችን ሞቷ ነውና።“ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል።”[ማቴ10፥39]

“የሲኦል ጣር ከበበኝ ...”[ መዝ18፥5]

የዚህን ጊዜ ያልታገሰ ወድቆበት በማያውቀው ራሱም በሚንቀው ሃጢአት ይወድቃል የዚህ ጊዜ ጌታችን እርሱ ያቀመሰንን ፀጋ ብቻ ፈልገን ሳይሆን የፀጋው ጣዕም ተወስዶብን እንኳን እርሱን በእርሱነቱ ብቻ እንፈልገው ዘንድ ሲያበረታን ነው ።ብዙዎች መንፈሳውያን በማያስቡት በሚንቁት ሃጢአት ወድቀው እራሳቸውን የሚያገኙት ከዚህ ውሳጣዊ ሲኦል ለመታገስ ብለው ለሃጢአት ደስታ ስለሚገዙ ነው ወደ ቀድሞውም ለመመለስ የሚከብዳቸውም ወደ ክርስቶስ ለመሄድ ወደ እርሱም ለመድረስ ልንሄድባት ግድ በሆነች ውጣችን ያለችው ሲኦል ወይም ፍትወታት እስኪሞቱ የመታገስን ጉዞ ታክተው ሃጢአትን ማጣጣም ስለሚጀምሩ ነው። ይህቺን ውሳጣዊ ሲኦል አስችለኝ ብሎ በቅዱስ ዳዊት ጩኸት(ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ።” መዝ139፥8) መሰወሪያው በጨለማ ባደረግ እግዚአብሔር አምኖ የሚታገስ ግን በክርስቶስ ብርሃን ይሰጥማል መልካም መዓዛውን አሸትታል መልኩንም አይቶ በተደሞ ይነጠቃል። ከእርሱም ጋር ላይለየው ይጣበቃል። ልቦናው በፍቅረ እግዚአብሔር ይነድዳል።


1 [Fifty Spiritual Homilies of St. Macarius the Egyptian] and [The Arena - Guidelines for Spiritual and Monastic Life, By Ignatius(Brianchaninov)]

✒️ ስልዋኖስ

የተዋሕዶ ልጅ

03 May, 17:49


ልብህ እሱን ከመዘከር አይለይ።(ልብህ) የጣዕሙ መገኛ ይሆን ዘንድ መልክህ በፍቅሩ ብዛት ከእሳት እንደገባ ብረት የተለወጠ ይሁን። ጣዕሙ በልቦናህ ያድር ዘንድ። ሕዋሳተ ነፍስ ሕዋሳተ ሥጋ ደስ በሚላቸው ገንዘብ፤ እሱን በመሻት ብታዝን አግኝተኸው ደስ ይልሃል። እያለቀስህ መከራ እየተቀበልህ እሱን ለማየት መንፈሳዊ ቅንዓትን ብትቀና መልኩን በዓነ ነፍስ ታየዋለህ። ሐዘንህን ትዘነጋለህ።
....
በተዘክሮ ጸንተህ የኖርህ እንደሆነ የፀሐይ ብርሃን ከክበቡ ጋር እንዲዋሐድ ብርሃኑን ተዋሕዶህ ታያለህ። ምሉእ ስፉሕ ወደሚሆን ወደ ጌትነቱ ብትገባ በነፍስ በሥጋ በውሥጥ በአፍአ መላእክት በብርሃናቸው ይሸፍኑሃል። ወዲያ ወዲህ ባልህ ጊዜ ምድርን በፊትህ እንደሌለች አድርጋት።

አረጋዊ መንፈሳዊ (ድርሳን 24)

የተዋሕዶ ልጅ

13 Feb, 20:22


ስለባልንጀራው በታመመ ልቦና የሚፀልይ ክርስቲያን ክርስቶስን የሚመስል ነው። ክርስቶስ በመስቀል የእኛን ሸክም እንደተሸከመ ልቦናውን ቀራኒዮ ላይ የተከለም፤በልቦናው መስቀልነት የባልንጀራውን ሸክም ይሸከማት ዘንድ ከጌታው ያያት ፍቅር ታስመኘዋለች። ያቺ ምኞት በሕማም እና ፍቅር የባልንጀራን መከራ ምነው ለኔ ባደረገው እያሉ የምንታመማት ቅድስት ሕማም ናት። በባልንጀራው ስቃይ ራሱን ጨምሮ ባልንጀራውን ማርልኝ ከሚል ሰው መዓዛ ክርስቶስ ይሸተታል።

የተዋሕዶ ልጅ

07 Jan, 19:31


"ፍቁር ክርስቶስ ሆይ ከሕዋሳትህ እንደ አንዱ አድርገኝ ... እንደ እግርህ...እንደ እጅህ...

ፍቅርህ ያዝለኛል  አንተን መዘከር ያቃጥለኛል ሁል ጊዜ ስራን ለመስራት ያነቃቃኛል አቤቱ ፍቅርህ በልቦናዬ ፈጥኖ አደረ በሰውነቴ ተሰራጨ ሕዋሳቴን ፀጥ አደረጋቸው።

አቤቱ ጌታዬ ሆይ ወዮልኝ። በፍቅርኽ መንደዴን የሚያበርድልኝ ማነው?... መወደድ ያለህ አቤቱ አንተን የሚወድኽ ንዑድ ነው እላለኁ። አንተን አይቶ የሚሰለች የለምና።"

አረጋዊ መንፈሳዊ

የተዋሕዶ ልጅ

07 Jan, 18:41


ስቃይ አምላካዊት...

በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ የደርሻለሁና የይበቃኛል ስሜት ላለመብቅታችን ትክክለኛ ማሳያ ነው። በእውነት ያለ ሐሰት ከክርስቶስ ጋር ሊዋሐዱ የሚወዱ ቅዱሳን አባቶች ደረስኩ በቃሁ ሲሉ አናቸውም እንዲያውም ቅዱስ ኤፍሬም "አኳዃንህ አይጠገብም... አንተን መጥገብ የሚቻለው ማነው?" ብሎ ይጠይቃል ክርስቶስን መውደድ የጀመረች ነብስ ትጠግበው ዘንድ አይቻላትም ይልቁንም እርሱን በመፈለግ ውስጥ ባለ አምላካዊ ስቃይ ውስጥ ትገባለች። ይህቺውም ስቃይ ከኃጢአት የምትለይ ቅድስት የምትሆን ስቃይ ናት። ነፍስ በተቀደሰ ስቃይ ውስጥ ሆና የምትናፍቀውን ጌታዋን እንዳታይ የሚያደርጋት ኃጢአት ነውና ስለ ህግ ብቻ ሳይሆን ስለእርሱ ፍቅር እራሷን ትቀድሳለች(ትለያለች)። ይህች አለም እሱን በመሻት የሚደክሙባት በቅዱስ ስቃይ የሚሰቃዩባት እንጂ እርሱን በምልአት የሚያገኙባት አይደለችም “ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን..”(1ኛቆሮ13፥12).. ቅዱስ ጳውሎስም በደማስቆ ያየውን ጌታውን በዚህ ምድር እርሱን በድንግዝግዝ ማየት አልበቃ ቢለው“ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤” (ፊል1፥23) አለ። "የፍጥረት ናፍቆት"(ሮሜ8:19) እርሱ ክርሰቶስ ነውና በእርሱ የሆኑቱ በተቀደሰ አምላካዊ ስቃይ ውስጥ ሆነው "ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።”(ራእ22፥20) ይሉታል።
"የሚሹትን ደስ የሚያሰኛቸውን የጎላ የተረዳ መገለጹን ይሻሉና።" አረጋዊ መንፈሳዊ


"እሱን በመሻት ብታዝን አግኝተኸው ደስ ይልሃል።...እያለቀስህ መከራ እየተቀበልክ እሱን ለማየት መንፈሳዊ ቅንዓት ብትቀና መልኩን በዓይነ ነፍስ ታየዋለህ።   ....አቤቱ ጌታዬ ሆይ ወዮልኝ። በፍቅርኽ መንደዴን የሚያበርድልኝ ማነው?... መወደድ ያለህ አቤቱ አንተን የሚወድኽ ንዑድ ነው እላለኁ። አንተን አይቶ የሚሰለችኽ የለምና።" አረጋዊ መንፈሳዊ
......
አንተን በመናፈቅ የሚሰቃየውም ንዑድ ነው እላለኁ...

የተዋሕዶ ልጅ

11 Sep, 19:20


ከአሮጌው ዘመን ጋር "አሮጌውን ሰው አስወግዱ" (ኤፌ 4፥22)

ዘመን መለወጫ ብዙ ነገሮችን የምንልውጥበት ወቅት ነው። የቤታችንንም እቃዎች ፣ አልባሳትን ሌሎችም ሌሎችም እንለውጣለን። ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ እውነተኛውን ቤት የእግዚአብሔርም ቤት/መቅደስ ስለሆነው ሰዉነታችን ግን ችላ እንላለን። “፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።” (1ኛቆሮ3፥17 )

"አቤቱ እኛ ስጋውያን የምንሆን የስጋን ነገር እናስባለን በስጋም መንገድ እንሔዳለን " (ኀዳፌ ነፍስ) ዘመንም ሲለወጥ የስጋን ነገር እናቅዳለን። እግዚአብሔርም ዘመንን እንደ ስጦታ ሲሰጠን ለምን እንደሆነ እንዘነጋዋለን። እርሱ " በልባችሁ መታደስ ተለወጡ '' (ሮሜ 12፥2) ብሎ ዘመንን ሲለውጥ እኛ ግን የቤቶታችንን እቃዎች ብቻ እንለውጣለን። "አዲሱን ሰዉ ልበሱ '' (ኤፌ 4፡24 ) ብሎ በአዲስ ዘመን ቅዱስ ልብስ ሲሰጠን እኛ ደግሞ እርሱን ችላ ብለን የስጋን ልብስ ብቻ እንለብሳለን። እኛ ሁሌ የስጋን ነገር ስለምናስቀድም አይሞላልንም። የነፍስ ነገር ግን ብናስቀድም የስጋን ነገር ያሟላልን ዘንድ የታመነ ነው። “ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።” (ማቴ 6፥33 )


እግዚአብሔር የተሻለውን የነፍስን ነገር ያስቀድማል። ለዛም ነው በወንጌል የስጋ ደዌያቸውን ብቻ አስበው ወደ እርሱ የመጡትን እርሱ ግን አስቀድሞ የነፍስን መድኃኒት ይሰጣቸዋል ። ከዛም ቀጥሎ የስጋን መድኃኒት ይሰጣቸዋል። "እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፦ አንተ ልጅ፥ አይዞህ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው።እነሆም፥ ከጻፎቹ አንዳንዱ በልባቸው፦ ይህስ ይሳደባል አሉ።ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ፦ ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከማለት ወይስ፦ ተነሣና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል?ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፥ በዚያን ጊዜ ሽባውን፦ ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ አለው።ተነሥቶም ወደ ቤቱ ሄደ። '' (ማቴ 9፥2-7 )

ዘመንም ሲለወጥ የስጋን ነገር እንለውጥ ዘንድ ብቻ ሳይሆን አስቀድመን የነፍስን ነገር እንለውጥ ዘንድ ነው እግዚአብሔር የንስሐ ጊዜ የሚሰጠን። "በልባችሁ መታደስ ተለወጡ " (ሮሜ 12፥2) ብሎ አሮጌውን ልባችንን አስወግደን የክርስቶስም ልብ ወደ መያዝ እናድግ ዘንድ አዲስ ዘመን ሲሰጠን እኛም እንጠቀምበት ። '' እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን '' (1ቆሮ 2፥16) ። ከአሮጌው ዘመንም ጋር ''አሮጌውንም ሰዉ አስወግዱ " ( ኤፌ4፥22) ብሎ አዲስ ዘመን ስለሰጠን እኛም '' ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥።” (ኤፌ4፥12-13) ክርስቶስን ወደ መምሰል እንደግ። እግዚአብሔርም የንስሐ ጊዜ ስለሰጠን ደስ ይበለን።

“በጌታ ደስ ይበላችሁ፤።”
“በጌታ ደስ ይበላችሁ።”
“በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።”ፊልጵስዩስ 4፥4

የተዋሕዶ ልጅ

09 Sep, 19:54


ፍቅርህ ያዝለኛል አንተን መዘከር ያቃጥለኛል ሁል ጊዜ ስራን ለመስራት ያነቃቃኛል አቤቱ ፍቅርህ በልቦናዬ ፈጥኖ አደረ በሰውነቴ ተሰራጨ ሕዋሳቴን ፀጥ አደረጋቸው።

አረጋዊ መንፈሳዊ

የተዋሕዶ ልጅ

11 Jul, 19:05


የናፍቆት ጉልበት

ከጌታው ጋር በፍፁም መዋሐድ የሚሻ የኃጢአትን ስር ነቅሎ ሊጥል ይገባዋል። ኃጢአት ወደ እግዚአብሔር መለኮታዊ ንፅህና እንዳንቀርብ ታደርጋለችና። ቅዱስ ጴጥሮስም "ጌታ ሆይ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከእኔ ተለይ።"ሉቃ5:8 ያለውም ስለዚሁ ነው። ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር አይደለም የምንለውም እርሱ ከእኛ ጋር ስላልሆነ ሳይሆን እኛ ከእርሱ ጋር ስላልሆንን ነው። ኃጢአታችን ወደ እርሱ መለኮታዊ ንፅህና እንዳንጠጋ ስለምታደርገን ነው። ወደ ጌታ መለኮታዊ ንፅሕና የምታቀርበን ከኃጢአት ጋር እየተጋደልን ልናገኛት የምትገባዋ ንፅሐ ልቡና ናት። ጌታን የሚማርክ እውነተኛ ውብ መልክ ሁላችንም ውስጥ አለች። ጌታ በመስቀል የተጠማት ይህቺ እርሷ ናት። ያያት ያድርባትም የናፈቃት ቅዱስ ቅናትም የቀናላት ይህቺ ናት። እርሱም የእርሱን መሻት ከሰማይ ወርዶ አሳይቷል። ለእርሷ ሲል ሰው ሆኗልና ሊያድርባት የማይናፍቃት ነፍስ የለችም። የእርሱ ፈቃድ/ናፍቆት ለሁሉ የተሰጠች ናት። ወደ እርሱ ፈቃድ መቅረብ ግን የሰው ልጅ ነፃ ፈቃድ ነው። በእነዚህ ሁለት ናፍቆቶች(እግዚአብሔር ከእኛ እኛም ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ለመሆን የምንናፍቀው) መኃል ያለች ግንብ ደግሞ ኃጢአት ናት። በውስጣችንም ያለች የናፍቆት ጉልበት ከኃጢአት የምትለየን ናት። የኃጢአት ብዛትም ይህቺን የናፍቆት ጉልበት ታዝላለች። ማለት የልቡናን መባረድ ታመጣለች። የልቡና መባረድም ደግሞ ከጌታ ፍቅር የኃጢአት ፍቅር እንዲያይል ታደርጋለች። የኃጢአት ፍቅርም የእግዚአብሔርን ህልውና እስከመካድ ታደርሳለች። የኃጢአት ፍቅርም ከጌታ መለኮታዊ ንፅህና አላደርስ ይላትና እርሱን ከማየት ትታወራለች። ቅርቧ ቢሆንም ኃጢአት ጋርጇታልና አታየውም።

የተዋሕዶ ልጅ

06 Jul, 07:38


አቡነ ሺኖዳ

የተዋሕዶ ልጅ

16 Apr, 14:44


ታድርበት ዘንድ እደርብኝ ብሎ የሚለምንህ ሰው ንዑድ ክቡር ነው። ልቡ በፍቅርህ እሳትነት ይቃጠላልና።ሥጋውም ነፍሱም በበጎ ፍቅርህ ይቃጠላልና። አንተን በማሰብ ሕዋሳቱ ጸጥ ያሉለት ሰው ንዑድ ክቡር ነው።

አረጋዊ መንፈሳዊ

የተዋሕዶ ልጅ

19 Jan, 17:34


" ቅጥሩም ወደቀ።”
— ኢያሱ 6፥20

የኢያሪኮን ቅጥር በእግዚአብሔር ታቦት እንዳፈረሱት ሰማሁ እኔም ከኢያሪኮ ግንብ የገዘፈ ኀጢአቴን ያፈርስልኝ ዘንድ በማስተዋል ወደ አዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ወጣሁ።

የተዋሕዶ ልጅ

07 Jan, 06:31


...ወገኖቼ ሆይ ድንቅ ለሚሆን ለዚህ ለደገኛ ፍቅር አንክሮ ይገባል።

አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን ፳፩

የተዋሕዶ ልጅ

05 Jan, 16:25


"በውስጥህ ወደሚገኘው ወደ ግምጃ ቤት(ልብህ) በጉጉት ግባ፣ ሰማያዊውን ግምጃ ቤት ትመለከታለህ። ሁለቱም ተመሳሳይ ናቸውና፣ ለሁለቱም አንድ ብቻ የሆነ መግቢያ በር ያላቸው ነው :: ወደ መንግሥቱ የሚመራህ መሰላል በውስጥህ ተሰውሮአል፣ በነፍስህ ውስጥም ይገኛል። ወደ ውስጥህ ጠልቀህ ግባ፣ በነፍስህም ውስጥ የምትወጣባቸዉን እርከኖች ታገኛለህ። "

ቅዱስ ማር ይስሐቅ


"አንዴ እግርህን በመሰላሉ ላይ ካሳረፍክ እግዚአብሔር ወደ ቀጣዩ የሚመራህ ነው፣ እየወጣህ ዝለቅ እያንዳንዱ እርከን እስከ ላይኛው የሚመራህ ነው፣ እግዚአብሔርን ማግኘት ማለት ሳይታክቱ እርሱን መፈለግ ነው፣ እግዚአብሔርን መመልከት ማለት እርሱን ከመሻት አለማቋረጥ ነው፡፡"

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

የተዋሕዶ ልጅ

02 Jan, 08:11


«አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ!
የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደተከፈተ ተውኩልህ . . . ደካማ ለሆንኩ ለእኔ
ለምፍገመገም ለእኔ ያለ አንተ ደጋፊ
ያለ አንተ የሚያፀናኝ የለም። ለወደቅሁ ለእኔ ያለአንተ የሚያነሳኝ የለም። ለአዘንኩ ለእኔ ያለአንተ የሚያረጋጋኝ የለም። ለድሀው ለእኔ ያለ አንተ መጠጊያ የለኝም፡፡»

ገድለ ተክለ ሃይማኖት ምዕ ፳፰ ቁ ፪

የተዋሕዶ ልጅ

16 Dec, 20:37


ሕሙማነ ልብ...

ስለባልንጀራው በታመመ ልቦና የሚፀልይ ክርስቲያን ክርስቶስን የሚመስል ነው። ክርስቶስ በመስቀል የእኛን ሸክም እንደተሸከመ ልቦናውን ቀራኒዮ ላይ የተከለም በልቦናው መስቀልነት የባልንጀራውን ሸክም ይሸከማት ዘንድ ከጌታው ያያት ፍቅር ታስመኘዋለች። ያቺ ህመም የባልንጀራን መከራ ምነው ለኔ ባደረገው እያሉ የምንታመማት ቅድስት ህማም ናት። በባልንጀራው ስቃይ ራሱን ጨምሮ ባልንጀራውን ማርልኝ ከሚል ሰው መዓዛ ክርስቶስ ይሸተታል።

የተዋሕዶ ልጅ

29 Nov, 12:34


ልብህ እሱን ከመዘከር አይለይ።(ልብህ) የጣዕሙ መገኛ ይሆን ዘንድ መልክህ በፍቅሩ ብዛት ከእሳት እንደገባ ብረት የተለወጠ ይሁን። ጣዕሙ በልቦናህ ያድር ዘንድ። ሕዋሳተ ነፍስ ሕዋሳተ ሥጋ ደስ በሚላቸው ገንዘብ፤ እሱን በመሻት ብታዝን አግኝተኸው ደስ ይልሃል። እያለቀስህ መከራ እየተቀበልህ እሱን ለማየት መንፈሳዊ ቅንዓትን ብትቀና መልኩን በዓነ ነፍስ ታየዋለህ። ሐዘንህን ትዘነጋለህ።
....
በተዘክሮ ጸንተህ የኖርህ እንደሆነ የፀሐይ ብርሃን ከክበቡ ጋር እንዲዋሐድ ብርሃኑን ተዋሕዶህ ታያለህ። ምሉእ ስፉሕ ወደሚሆን ወደ ጌትነቱ ብትገባ በነፍስ በሥጋ በውሥጥ በአፍአ መላእክት በብርሃናቸው ይሸፍኑሃል። ወዲያ ወዲህ ባልህ ጊዜ ምድርን በፊትህ እንደሌለች አድርጋት።

አረጋዊ መንፈሳዊ (ድርሳን 24)

1,043

subscribers

786

photos

20

videos