የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ @yaredzer Channel on Telegram

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

@yaredzer


◉►ይሄ channel የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የሚተላለፍበት channel ነው።

◉►81 የግእዝ መጻሕፍት ➥ብሉይና ሐዲስ
◉►81 የአንድምታ መጻሕፍት በሙሉ
◉►አዋልድ መጻሕፍት በግእዝ/አማርኛ

👉"ትፈቅድኑ/ዲኑ ታእምር/ሪ ልሳነ ግእዝ።"
👉"የግእዝን ቋንቋ ልታውቅ/ቂ ትፈልጋለህ/ጊያለሽ?"

https://t.me/joinchat/SWWiqKcuci79Brh9

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ (Amharic)

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ እንዴት እንደሆነ ምን ነው? እስከመቼ ሊቆይ እንችላለን? ይሄ channel የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ማለት ነው። እናዚህ channel በአማርኛ ተዋሕዶ መጻሕፍትን የሰላምና ኢፋርስ ማደብ እንዲረዳ ስለሚቀጥሉ በየቀኑ 81 የግእዝ መጻሕፍትን በማለት ተመልከቱ። በእዚህ channel ከሚሰሩት የእውነትና አትክልት ጋር በተወሰነው ሰሞን ውስጥ የሚተላለፍ ለበለጠ መልኩ በአንድ መለክ ብሉይና ሐዲስ እና አዋልድ መጻሕፍት ለመሆን ይረዳል። ገና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መጻሕፍትን በማገናኘት በዝቹ መልኩ ለሚቀረው እና በመስራት በመመልከት ስለሚወልድ አስተማሪ እና ሰልባ ምን እንደምንደርስ በመተከል እናድርጉ።

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

02 Dec, 17:18


Channel photo updated

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

02 Dec, 17:07


👉Share ቢያደርጉ መልካም ነው።

ቅኔን መቀኘትንና ቅኔን ማስመስከር ለሚፈልጉ ታስቦ የተጻፈ፥ ለቅኔ ተማሪዎች መማሪያና ማስመስከሪያ፥ ለቅኔ አስተማሪዎች ማስተማሪያ፥ የግእዝ ቋንቋን ለሚያጠኑ መሪ ሆኖ የሚያገለግል፥ ከዓሥር ዐመታት በላይ  እጅግ በጣም የተደከመበት ድንቅ የሆነ የመጀመሪያ መጽሐፍ ነው።

👉ቀድሞ መጽሐፉን ለመግዛት አልያም ድጋፍ ለማድረግ

Telephone፦ +251918609092

●●●
ስለ መጽሐፉ ሕትመት Comment ለመስጠት የሚከተለውን ጠቅ አድርገው ይግቡ👇

https://t.me/prepostion

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

01 Dec, 11:13


https://youtu.be/XKL0hGKDMGI?si=81gOH6xybOUFsVjL

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

24 Nov, 14:12


ከታኅዳር ፲፭ እስከ ታኅሣሥ ፳፰ የሚጾመው የ፵፬ ቀናት ብዛት ያለው ጾም የተለያዩ ስያሜዎቹ የሚከተሉት ናቸው።

ያሬድ ዘርአ-ቡሩክ

➊. የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ "ጾመ ነቢያት" እየ ተባለ ይጠራል፡፡

➋. ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም›› ይባላል፡፡

➌. ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት›› ይባላል፡፡

➍. የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት›› በመባል ይታወቃል፡፡

➎. እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡

➏. በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየ ተዘዋወረ በጌታችን፣ በአምላካችንና በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡

ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው ሥጋውን ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾምና በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱም የቅዱስ ፊልጶስ ሥጋውን ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል። ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየ ተባለ ይጠራል፡፡

➐. መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን  ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመማርያምም ›› በመባልም ይታወቃል፡፡

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

22 Nov, 15:53


https://youtu.be/kFD4bXClBgk?si=ACFvOWvQLFSUoh75

ዓለም እንዲያየው Share አድርጉት!!!

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

21 Nov, 14:40


ከሌሊቱ ፮ ሰዓት የተዘረፈ ቅኔ👇

፩. ግእዝ ጉባኤ ቃና
●ይቤ አንከርኩ ግብረ ምግባሩ ለወልድ፥
●ረኣዬ ሕቡኣት ዕንባቆም ዘእምነቢያት ዋሕድ። (ዕን. ፫፡፩)

፪.፩. ዕዝል ጉባኤ ቃና
●አበውየ ሊተ እመኒ ታፈቅሩኒ እምድሩ፥
●ትዕግሥቶ ለኢዮብ በላዕሌየ ግበሩ።

፩.፪. ዕዝል ጉባኤ ቃና
●ሊቀ ብርሃናት ለሊከ በብርሃንከ እንዘ ታግሕሥ ጽልመተ፥
●የማነ እዴከ ፈኑ ከመ ትባርከኒ ሊተ።

፪.፫. ዕዝል ጉባኤ ቃና
●በቡራኬሁ ለኤፍሬም ከመ ትባርክኒ ንዒ፥ (ትባርክኒ ምጽኢ፥)
●ፍካሬ ቅኔያት ድንግል ተስፋሁ ለዘአልቦቱ ረዳኢ።

፪.፬. ዕዝል ጉባኤ ቃና
●ሚካኤል መልአክ ምስጢረ ቅኔ እንዘ ትሰፍሕ አክናፈ፥
●ላዕሌነ ጸልል በከመ ታለምድ ዘልፈ።

፪.፭. ዕዝል ጉባኤ ቃና
●ዘንመ ምሕረትከ አውሕዝ ሚካኤል ለኢትዮጵያ አሓቲ፥
●ከመ ዘትረ ኰኵሕ አውሐዝከ ለነገደ ኅሬ መዋቲ።

፪.፮. ዕዝል ጉባኤ ቃና
●ሚካኤል አውርድ ኅብስተ ቅኔ ዘይሁበነ ጥዒና፥
●እስመ ኢነኀሥሥ ንሕነ ሐላፌ ዘህዝበ እስራኤል መና።

፪.፯. ዕዝል ጉባኤ ቃና
●ኀበ ደማስቆ ጳውሎስ ለለ ጌሰ ከመ በረቀ መብረቅ፥
●ላዕሌየ ወድቀ ግብታዊ መብረቀ ቅኔ ያሬድ ሊቅ።

፪.፰. ዕዝል ጉባኤ ቃና
●ማእደ ቅዱስ ወንጌል ዱራዎታዎስ  በሥጋ ዓሣ ተሠርዐ፥
●ወአመ በክብር ቀርበ በሊቀ መላእክት ተበልዐ።

፫. ዘአምላኪየ
●ለህዝበ እስራኤል ኵሎሙ እንዘ ይከይድ ደመና፥
●ሚካኤል ምስጢረ ቅኔየ መርሖሙ በፍና፥
●ወበውስተ ገዳም አውረደ ትርጓሜ መጻሕፍት መና።

፬. ሚ በዝሑ
●ማዕረረ ሃይማኖት ወጽድቅ ዱራታዎስ እክል ድሕረ ተዘርአ መሬተ፥
● ጽጌ ሃይማኖት ጸገየ ወፈረየ አ-ም-ኣተ፥
●ወቴዎብስታ ከረየት መዛግብቲሃ በምድር
ኀበ ታስተጋብእ ዘንተ።

፭. ዋይ ዜማ
●በማሕሌተ ያሬድ ክንክራኦስ እስመ ቦ ብፅዐት እንዘ ያማሓፅን ነፍሶ፥
● ጳውሎስ ልቡና ዚኣየ ተላጸየ ርእሶ። (ግብ. ፲፰፡፲፰)
●ወለአውጤክስኒ መጽሐፍ ድሕረ በእዴሁ ገሰሶ፥
●አንሥኦ እሞት ወፈወሶ፥ (ግብ. ፳፡፱-፲፪)
●ዱያን'ሰ ይትሜነዩ ልብሶ። (ግብ. ፲፱፡፭)

፮. ሐፂር ዋይዜማ
●ዐይነ ንስር ስብሐተ ማሕሌት ለጥበብ ርእያ፥
●ወለእመ ጥበብ ጳውሎስ ደብተራ ብርሃን ሰመያ። (ድጓ.)
(●ዐይነ ንስር ስብሐተ ማሕሌት ለጥበብ ርእያ፥)

፯. መስኮት ዋይ ዜማ
●ለጥበብ ምስለ አእምሮ አእምሮ ዘብከ ሀገሪተከ ረስያ፥ (ምሳ. ፯፡፬)
●ወጥበብ ዘእብል አቅሌስያ፥
●እስመ ሊተ ጥበብየ ነያ።

፰. ሥላሴ
●ዲያቆን ሚካኤል ሰራዊተ አጽንዕ ወተመሀር እስመ እስመ ለከ ታጽንዕ ትእምርተ ሰራዊት ኵሎ፥
●ሰራዊት ዘአልቦ ቅዳሴ ኢሀሎ፥
●ወለእመሂ ይትረአይ መምህረ ቅዳሴ መሲሎ፥
●ነሢአ ሰራዊት ዘኢተክህሎ፥
●ፍሬ ቅዳሴ ኢክህለ በተሐብሎ፥
●ቅዳሴየ እቄድስ ብሂሎ።

፱. ዘይእዜ
●ኵላ እከየ ማእከሌክሙ እንዘ እምአፉሁ ይዘሩ ወያስተጋብእ ኵነኔ፥
●መኑ አሕመመክሙ አንትሙ ሰብአ ገላትያ አቋቋም ወቅኔ።
●ከመ ኢትእመኑ ዘንተ እግዚአ ወመድሐኔ፥
●ወከመ ኢትግበሩ ዘንተ ግብረ አሓተኔ፥
●እስመ ተዋሕዶ ጽኑዕ አምሳለ ቄዳሕ ወቀኔ። (ሕዝ. ፳፱፡፲፱)
(●ወከመ ኢትግበሩ ዘንተ ግብረ አሓተኔ፥)

፲. ሣህልከ
●ሚካኤል ኀቤነ ከመ ትምጻእ፥
●ናስተቍዐከ እንከ በእግዚአብሔር እግዚእ፥
●ውስቴታ ለቤቴል እስመ አብቀዉ አፈ ዐማፂ ወአፈ ሓጥእ፥ (መዝ. ፻፰፡፩)

፲፩. ሐፂር ሣህልከ
●ከመ ጎሕ ትሔውጽ ደብረ ምሕረት፥
●እስመ በላዕሌሃ የኀቱ ስብሐተ መላእክት ማኅቶት።
(●ከመ ጎሕ ትሔውጽ ደብረ ምሕረት፥)

፲፪.፩. መወድስ
●ጣሕረ ክብረ ቅኔ ሕያው እጓለ አንበሳ በመንፈቀ ሌሊት ተሰምዐ እመልዕልተ አድባር ከኒሳ፥
●ወማእከለ አልሕምት ዘቤቴል እለ ፀንሳ፥
●ወፅአ እምገዳም ዘሐያል መዝራእተ እዴሁ መወድስ አንበሳ፥
●ወእንዘ ውእቱ ይጥሕር እንስሳ ገዳም ይጐዩ እንዘ ይከውኑ በበ ሓምሳ።
●አእላፈሂ ድሕረ ተሠይጡ ዘቤተ ልሔም እንስሳ፥
●ቅኔ ያሬድ ኢየሱስ አምጣነ ተሠይጠ በሠላሳ፥
●ትብክያ ንዓ ወሞጣሕተ ብካይ ልበሳ፥
●መጻሕፍት አዋልድየ እለ ትመጽኣ እምቲያሳ። (ኢሳ. ፳፯፡፲፩)

፲፪.፪. መወድስ
●በፍጹም ፍቅር ወበሃይማኖት ወበሣልሶን ምጽዋት ትሰረይ ሓጢአት፥ (ምሳ. ፲፭፡፳፯)
●ወለእለ ተምያን ቤትነ ወገዳምነ ጽልሑት፥
●ምጽዋት ወፍቅር ወሃይማኖት ሕቡረ ለእመ አልብነ አይቴኑ ክህነት፥
●ወጥበበ ሰሎሞን ትቤለነ ሀገር ጽንዕት ጥሪቶሙ ለአብዕልት፥ (ምሳ. ፲፡፲፭)
●ወእመ በተግሣጽ ኢተመየጥነ መንግሥተ ሰማያት ተምኔት/ርሕቅት፥
●እስመ ዘኢይዘለፍ በተግሣጽ ዘልፈ ይስሕት፥ (ምሳ. ፲፡፲፯)
●ወኢየአምሩ ሣህለ ፀረብተ እኪት፥
●ወአልቦሙ ለርእሶሙ ምሕረት ወየውሀት። (ምሳ. ፲፬፡፳፪-፳፫)

፲፫. ኵልክሙ መወድስ
●እሳተ ኑፋቄ (መከፋፈል) ይነድድ ወያንበለብል እስከ ፍሕመ እሳት ኮነት ጕንደ ወይነ ሕይወት ኢትዮጵያ፥
●ዝኒ እሳት ከመ የዐያ፥
●አላጲስ ጲስጢስ ወአጋጲስ ዘነደ በዐውደ ሙስና ዳግሚት ሮምያ፥
●ወበእንተ ስምዕ ሰማያዊ ደቂቃ መጠወት ቤተ ክርስቲያን ሶፍያ።
●አስተብቍዐቶሂ እንዘ ትብል ለገባሬ ኵሉ ኬንያ፥
●ምስለ ደቂቅየ ስምዐ ጽድቅ ከመ እኩን ሀበኒያ፥
●አዋልዲሃኒ መንግሥተ ከመ ተወፈያ፥
●ኮነት ስምዐ ጽድቅ ሞተ ተመንያ፥
●ወአክሊለ ክብር ነሥአት ከመ ተማሕፀነት ነያ።
(●ኮነት ስምዐ ጽድቅ ሞተ ተመንያ። ስንክሳር ጥር ፴)

፲፬. ሐፂር ኵልክሙ መወድስ
●ማእምንትየ ቤቴል እመ ረሣዕኩኪ ግብተ፥
●ፍጽምትየ የማነ እዴየ ትርስዐኒ ሊተ።

▰መጋቤ ምስጢር ያሬድ ዘርአ-ቡሩክ
▰ዛሬ ሕዳር ፲፪/፳፻፲፯ ዐ.ም
▰ድሬዳዋ ሚካኤል

👉ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት ለማግኘት https://t.me/yaredzer

ከባሕር ማዶ የምትኖሩ በተከታታይ ቅኔ ለመማር የሚከተለውን link ጠቅ አድርገው ይግቡ!!!
https://t.me/kineyared

በባሕር ማዶ የምትኖሩ በተከታታይ ቅኔ ለመማር የሚከተለውን link ጠቅ አድርገው በመግባት ይመዝገቡ👇
@yaredzeraburuk

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

20 Nov, 11:37


👉ቅኔ ዘዋይ ዜማ

ዋይዜማ
●እመ ኢተወለጠ ሀልዎቱ ለበዓለ ገዳም ሰብእ ነቢረ ገዳም ምንትኑ፥
●በገዳም ሥጋ ይሠራዕ አኮኑ፥
●ወገዳማውያን ለምንት ዐለማውያነ ኮኑ፥
●ዐለመ ግብጸ እምድሕረ መነኑ፥
●ምናኔሰ ትከውን ለመኑ።
(ዘፀ. ፲፮፡፲፩-፲፪ ፤ ዘኍ. ፲፩፡፴፩-፴፫ ፤ ጥበ. ፲፱፡፲፪ ፤ መዝ. ፻፬፡፵)

ዘይእዜ
●መኑ ንጹህ እምአድልዎቱ እስመ ለዘበስም ረቂቅ ሚካኤልሀ መሰሉ፥
●እስራኤል አዝማዲሁ ሚካኤል በዓለ ዘመድ በሥጋ ያደሉ፥
●ወርቱዕ ዘመድ ሚካኤል ለእመ ይብሉ፥
●እስመ ሚካኤል ዘመድ መቤዝወ ኵሉ፥
●ወእምነ ዘመድ ዘመድ እንተ ይትአመን በቃሉ።
(●እስመ ሚካኤል ዘመድ መቤዝወ ኵሉ፥)

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

05 Nov, 17:44


መወድስ ዘማዕበል ፈንቴ ዘዋሸራ - ጎጃም

በአንድ ወቅት ማዕበል ደሴ በሌሊት ሲሄዱ ሽፍታ በመንገድ ላይ አገኛቸውና ተኵሶ እጃቸውን ይመታቸዋል። ከመኖሪያ ቤታቸው እስኪደርሱ ድረስም ደማቸው ይፈስ ነበር፡፡ ይህንም አስመልክተው በራሳቸው ላይ የሚከተለውን ድንቅ መወድስ ዘርፈዋል፦

• ለመራር እዴየ ማየ ሰማርያ ቀሰማ በጼው ኤልሳዕ ድምፀ ብርት፤
• አኮኑ ትትናገር ሕጸጸ አካል መንግሥት፤
• ለብልጣሶር መዝራእትየ ዘተጽሕፈ በገጸ ፈጣሪ ዳንኤል ሐሜት፤
• ???
• እኩንሂ ጊዜ ምሳሌ ሆሳዕና ጠቢብ ዳዊት፤
• በዕለተ ዐርብ ቀነዉኒ እንዘ የዐግቱኒ ከለባት፤
• ወአመ ተንሣእኩ አነ እምአፈ መቃብር ጽንዕት፤
• ማርያም ተዋርዶ መጽአት በሌሊት።

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

04 Nov, 17:46


መወድስ ዘአለቃ #ዶሪ

●እምሀልዎትየ ሊተ በዐለመ ሐጕል ይሔይስ ወትረ ንብረተ ሙሴ ውስተ መሬት፥
●ወእምሀልዎትየ ካዕበ ውስተ ቤተ ሐሳር ጽንንት፥
●ትሔይስ እምኵሉ በአንጻር ቅርብት፥
●ሀልዎተ ዓሣ ውስተ ልጐት፥
●አምጣነ ይሰቲ ማየ ዘኢይሰፍሮ በዓለ ቤት፡፡
●ነቢረሰ ይነብሩ በዘዚኣየ ትእምርት፥
●ቈናጽል ውስተ ግበብ ወአዕዋፍ ውስተ ጾላዕት፥
●ባሕቱ፦ ለኵሉ ዓለም እንተ ከመዝ ሥርዐት፥
●ሀልዎ በኢሀልዎ ወመዊት እምቅድመ ሞት፡፡

አለቃ ዶሪ
በጎጃም ጎንጅ የጎንጅ ቅኔን ለ፴ ዓመታት ያስተማሩ የቅኔ፣ የመጻሕፍት፣ የአቡሻህር መምህርና የጸዋትወ ዜማ ሊቅ፥ በኋላም የመቐለ ደብረ ገነት አለቃ የነበሩ ሲሆን በስተእርጅናቸው እልቅናውን ትተው ወደ ሸዋ ደብረ ሊባኖስ በመምጣት በፍጹም ምናኔ ሳሉ ዐርፈው በታላቁ ገዳም በደብረ ሊባኖስ ተቀብረዋል።

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

03 Nov, 12:53


https://youtu.be/LQX7CnTKBfM?si=yOR-56K_iabr1EHE

የሊቀ ምሁራን ተስፋ ማርያም ደቀ መዝሙር

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

03 Nov, 09:26


ታዋቂው የፕሮቴስታንት ፓስተር ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተመለሰ።

ከ45,000 በላይ በተከፋፈለውና በተገነጣጠለው ፕሮቴስታንት የጸጋው ወንጌል ዐለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ቅጥረኛ ፓስተርና ነቢይ የነበረው ናትናኤል ቢተው ኦርቶዶክሳዊ ትምህርተ ሃይማኖትን በማጠናቀቅና ንስሓ ገብቶ ቀኖናውን በመጨረስ ከነሙሉ ቤተሰቡ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስና ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናትነት ተወልዶ ብቸኛ ቀጥተኛ የሕይወት መንገድ ወደ ሆነችው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት በረት በሰላም ገብቷል።

የካቶሊክ መነኵሴ የነበረው ማርቲን ሉተር  ቆቡን ጥሎ ወደ አመንዝራነት ከገባ በኋላ በኢየሱስ ስም ሽፋን በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፈበረከው የዲያብሎስ ሥርዐተ አምልኮ ውስጥ ላሉ ጨለምተኞች ሁሉ ኦርቶዶክሳዊ ብርሃን ይበራላቸው ዘንድ  Share አድርጉላቸው።

ለበለጠ መንፈሳዊ መረጃ👇

https://www.facebook.com/Yared.ZeraBuruk?mibextid=ZbWKwL

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

26 Sep, 11:25


ቅዱስ መስቀል አስቀድሞ ቅዱስ ጳውሎስ "ሐሰ ሊተ፥ ኢይዜኀር አነ ዘእንበለ በመስቀሉ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ● ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክሕት ከእኔ ይራቅ።" (ገላ. 6:14) በማለት እንደ ገለጸው እኛ ክርስቲያኖች ጠላት ዲያብሎስን ከነ ሠራዊቱ መክተን ድል የምናደርግበት ጋሻችን፣ በወደቅን ጊዜ መንፈሳዊ ኀይልን አግኝተን የምንነሣበት የኀይል ምርኩዛችን፣ በታመምን ጊዜ ከደዌ ሥጋና ከደዌ ነፍስ የምንድንበት ቤዛችን፣ በደከምን ጊዜ ጥንካሬያችን፣ የምንመካበት ልዩ መመኪያችን ነው፡፡

ይሄውም ይታወቅ ዘንድ ለእግዚአብሔር ሥርዐተ አምልኮን እናቀርብባቸው ዘንድ በምንሠራቸው አብያተ ክርስቲያናት ጕልላት ላይ ቅዱስ መስቀልን ከፍ አድርገን እናኖራለን፡፡ ይሄንም ከፍ ያደረግነውን ቅዱስ መስቀል ዐይቶ የማይሸበርና የማይደነግጥ የሰይጣን ወገን የለም፡፡ ያለ ቅዱስ መስቀልም ክርስቲያን ነኝ እያሉ በክርስትና ስም በትምክሕት መኖር አይቻልም፡፡

👉ጠ. ቅዱስ መስቀል ለጽድቅ ትዕግሥትን የምንማርበት መማሪያችን ነው፡፡

በክርስቶስ ስም ያመንን ክርስቲያኖች በምድር እስካለን ድረስ ጠላት ዲያብሎስ በተለያየ መንገድ የተለያዩ ፈተናዎችን ይዞ ብቅ ማለቱ የማይቀር ነው፡፡ በዚህም ጊዜ በሥሥዕት ቢመጣበት በትዕግሥት፣ በትዕቢት ቢመጣበት በትሕትና፣ በአፍቅሮ ንዋይ ቢመጣበት በጸሊአ ንዋይ ድል ነሥቶ በኋላም በቅዱስ መስቀል ራሱን ቀጥቅጦ ጠላት ዲያብሎስን ያዋረደ ክርስቶስን መመልከት ነው፡፡

በቅዱስ መስቀል ኀይል የሚታመን የትዕግሥትን ራስ ክርስቶስን በመመልከት ትዕግሥትን ገንዘብ ያደርጋል፡፡ መጽሐፍም "እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኀጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።" (ዕብ. 12:1-2) ይላል፡፡ ክርስቲያንም ሆነው ትዕግሥትን በመስቀል ሊማሩ ግድ ይልዎታል፡፡

👉የ. ቅዱስ መስቀል በመናፍቃን/ከሓድያን ዘንድ ዘንድ አይፈለግም።

ከክርስትና ውጪ የሆኑ አይሁድ ክርስቶስን ሰቅለው መግደለቸው አልበቃቸውም፡፡ በቅዱስ መስቀል የሚከናወኑ ተአምራትን ዐይተው ከማመን ይልቅ ጕድጓድ ቈፍረው በ34 ዓ.ም መስቀሉንም ቀብረውታል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ``ነያ ትቤሎ ዕሌኒ ለኪራኮስ ንግረኒ አፍጥን ኀበ ሀሎ መስቀሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ - ዕሌኒ ኪራኮስን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ያለበትን ቦታ ቶሎ ንገረኝ አለችው።`` እንዳለ በኪራኮስ ጠቋሚነት በ326 ዓ.ም በታላቋ ንግሥት በዕሌኒ አማካኝነት እስኪወጣ ድረስም ለ292 ዓመታት ተቀብሮ ሊቈይ ችሏል፡፡

በድጋሚም በ614 ዓ.ም በንጉሥ ኬርዮስ/ፎቃ ወደ ፋርስ/ባቢሎን የተወሰደ ሲሆን በ628 ዓ.ም በሮም ንጉሥ በሕርቃል አማካኝነት ወደ ቦታው ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሷል፡፡ በዓሥረኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የተለያዩ ሀገራት መስቀሉን ለበረከት ብለው በዕጣ ተካፍለውታል፡፡ በዓሥራ አራተኛውም መቶ ክፍለ ዘመን ግማደ መስቀሉ በንጉሥ ዳዊት ዘመነ ንግሥና ወደ ሀገራችን ሊገባ ችሏል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስን ከስም በዘለለና አንጠልጥለው ከመሄድ ባሻገር ጠልቀው ገብተው ሕያው ቃሉን ያላነበቡ በክርስትና ስም የሚሸቅጡ ከአይሁድ የከፉ ክርስቲያን ነን ባዮች ቅዱስ መስቀልን በጥላቻ ዐይን ይመለከታሉ፤ ከቅዱስ መጽሐፍም በማፈንገጥ በመስቀል ዙሪያ ያልተገባ ትርክትን ይተርካሉ፡፡

ቅዱስ ጳውሎስም "ወይእዜኒ ገሃደ እነግረክሙ ከመ እሙንቱ ጸላእቱ ለመስቀለ ክርስቶስ እለ ደሓሪቶሙ ለሕርትምና እለ ከርሦሙ ያመልኩ ወክብሮሙ ሐሳሮሙ እለ ይሔልዩ ዘውስተ ምድር ● ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉ፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ። መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ ዐሳባቸው ምድራዊ ነው።" (ፊልጵ. 3፡18-19) በማለት የእነዚህ የመስቀል ጠላቶች ሰይጣናዊ ጠላትነታቸውን አጕልቶ በዚህ መልኩ ይነግረናል፡፡

ዳግመኛም ““እስመ ነገረ መስቀሉሰ ዕበድ ውእቱ በኀበ ሕጉላን ወበኀቤነሰ ለእለ ድሕነ ሐይለ እግዚአብሔር ውእቱ ● የክርስቶስ መስቀል ከንቱ እንዳይሆን በቃል ጥበብ አይደለም። የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው።” (1ኛ ቆሮ. 1:17-18) በማለት በክሕደታቸው ምክንያት በሚጠፉ መናፍቃን/ከሓድያን ዘንድ ቅዱስ መስቀል ዕብደት/ሞኝነት መስሎ እንደሚታይ ይገልጻል፡፡ ሆኖም ግን ቅዱስ መስቀል እንደ እግዚአብሔር ፍጹም ቃል ለምናምን ለእኛ ኦርቶዶክሳውያን ኀይል ነው፡፡

👉ከ. ቅዱስ መስቀል እኛ ክርስቲያኖች በክርስትናችን ምክንያት የምናደርገው ተጋድሎ ነው።

ክርስትና አልጋ በአልጋ ሳይሆን ብዙ ፈተናዎች የሚበዙበት መስቀል ነው፡፡ በቅዱስ መስቀል ሥር የተቀጠቀጠው የጨለማው አባት ታላቁ ዘንዶ ዲያብሎስ በክርስቲያኖች ላይ የክፋት መርዙን በመርጨት በተለያየ መንገድ ለመከራ የምንዳረግበትን የፈተና ጦሩን ይወረውራል፡፡

መድሕነ ዓለም ክርስቶስም አስቀድሞ "በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ!" (ሉቃ. 9:23) ብሏል፡፡ በክርስትናም ሕይወት አልፈው ወደ ዘለዓለም ሕይወት ለመግባት መስቀሉን ሊሸከሙ ግድ ይልዎታል፡፡

“መስቀል ሐይልነ፣ መስቀል ጽንዕነ፣ መስቀል ቤዛነ፣ መስቀል መድሓኒተ ነፍስነ፣ አይሁድ ክሕዱ፥ ንሕነሰ አመነ፥ ወእለ አመነ በሐይለ መስቀሉ ድሕነ፡፡”
👇
👇
👇
እንኳን ለ2017 ዓ.ም የጌታችን፣ የአምላካችንና የአዳኛችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ቅዱስ መስቀል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን፤ አደረስዎ!

●በመጋቤ ምስጢር ያሬድ ዘርአ-ቡሩክ ተጻፈ።

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

26 Sep, 11:25


“ሐሰ ሊተ፥ ኢይዜኀር አነ ዘእንበለ በመስቀሉ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ● እኔ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንጂ በሌላ አልመካም፡፡” ገላ. 6:14

👉አ. መስቀል ማለት ምን ነው?

መስቀል በብሉይ ኪዳን ዘመን በኦሪት ዘዳግም 21፡22-23 እንደ ተጻፈው እስራኤላውያን አንድን ወንጀለኛ ሰው ሰቅለው የሞት ቅጣት የሚቀጡበት የወንጀለኞች መቅጫና የእርግማን ምልክት የሆነ ዕንጨይት ነበር፡፡ ሮማውያንም ብዙ ወንጀለኞችን በመስቀል ላይ ሰቅለው በመግደል ይታወቁ ነበር፡፡

👉በ. የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል

ቅዱስ መስቀል ጥል ተወግዶ ሰላም የተመሠረተበት፣ የዕዳ ትእዛዛት ሁሉ የተሻሩበት፣ የአምላክ እናት ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በአጠገቡ የምትወደስበት፣ በሐዲስ ኪዳን ያሉ ምእመናን/ት የሚመኩበት መመኪያቸው፣ ትዕግሥትን የሚማሩበት የትዕግሥት ፍጻሜያቸው፣ መንፈሳዊ ተጋድሎን የሚጋደሉበት ጋሻ፣ ለሚታመኑበት ሁሉ የክብራቸው መንገሻ፣ የጠላት ዲያብሎስ የተንኰል አሠራር ማርከሻ ነው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀልም ‹‹ዕፀ አዳም፣ ዕፀ ሎጥ፣ ዕፀ ሳኦል፣ ዕፀ ሰሎሞን፣ ዕፀ ድንባዝ፣ ዕፀ ሰግላ፣ ዕፀ በለስ›› ከሚባሉ ሰባት ዕፀዋት ተውጣጥቶ እንደ ተሠራ መጻሕፍት ይናገራሉ፡፡

👉ገ. ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ቁመት

ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ቁመት ምን ያህል እንደ ሆነ ድርሳነ ማሕየዊ የተባለው መጽሐፍ “ወአፆርዎ ዕፀ መስቀል ዘቆሙ ዐሠርቱ ወሰብዓቱ በእመት ወወሰድዎ ይስቅልዎ ● ቁመቱ ዐሥራ ሰባት (8.5 ሜትር) ክንድ የሆነ የመስቀል ዕንጨት አሸክመው ሊሰቅሉት ወሰዱት፡፡” (ድር. ማሕ. ዘዐርብ. 1፡11) ይላል፡፡ በዘመነ ብሉይ የተለያየ የመስቀል ቅርፅ የነበረ ቢሆንም ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ግን የተ ዓይነት ቅርጽ ነበር፡፡

👉ደ. በቅዱስ መስቀል ላይ የነገሠውና የሚነግሠው የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው።

ቅዱስ መስቀል ሁሉን በፈጠረ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የከበረ ክርስቲያን ለሆነው ሁሉ አርማ ነው፡፡ በእኛ በኦርቶዶክሳውያን/ት ዘንድም ቅዱስ መስቀል በአምላክ ቦታ ተተክቶ የአምልኮት ስግደት የሚቀርብለትና የሚመለክ አምላክ ሳይሆን "ወጸሐፈ ጲላጦስ መጽሐፈ ወአንበረ ዲበ መስቀሉ ወይብል መጽሐፉ እግዚእ ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሦሙ ለአይሁድ ● ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም ‹የአይሁድ ንጉሥ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ› የሚል ነበረ።" (ዮሐ. 19:19) ተብሎ እንደ ተጻፈ በላዩ ላይ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጎልቶ የነገሠበትና ክርስቶስን የምናነግሥበት የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ማንገሻችን ነው፡፡ ክርስቶስንም ለማንገሥ መስቀሉን መያዝ ግድ ይላል፡፡ ያለ ቅዱስ መስቀልም የሚነግሥ ኢየሱስ የለም፡፡

👉ሀ. በቅዱስ መስቀል ጥል ተወግዶ ሰላም ተመሥርቷል።

ቅዱስ መስቀል የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ባደረጉት ኀጢአት ምክንያት በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ ፈርሶ ወደ ዘለዓለም ሕይወት የምንደርስበት አማናዊ ሰላም የተመሠረተበት የማይናወጥ የሰላማችን መሠረት ነው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስም "እስመ ውእቱ ሰላምነ ዘረሰዮሙ አሐደ ለክልኤሆሙ ወነሠተ አረፍተ ማእከል እንተ ጽልእ በሥጋሁ ወሰዐረ ሕገ ትእዛዝ በሥርዐቱ ከመ ይረስዮሙ አሐደ ብእሴ ሐዲሰ ለክልኤሆሙ ወገብረ ሰላመ። ወአብጽሖሙ ለክልኤሆሙ በአሐዱ ሥጋሁ ለኀበ እግዚአብሔር በመስቀሉ ወለጽልእ ቀተሎ ቦቱ ● እርሱ ሰላማችን ነውና ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን ዐዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገደለ።" (ኤፌ. 2:14-16) በማለት በኀጢአት የመጣው ጥል ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቅዱስ መስቀል መወገዱን አስገንዝቦናል፡፡

ዳግመኛም "እስመ ሠምረ ቦቱ ፍጹመ ኵሉ ይሕድር ላዕሌሁ ወቦቱ ይሣሀሎ ለኵሉ ወገብረ ሰላመ በደመ መስቀሉ ለዘበምድር ወለዘበሰማያት ● በመስቀሉ ደም ሰላም አደረገ።" (ቈላ. 1:19-20) በማለት ሰላም የተከናወነበት የሰላም ዐደባባይ ቅዱስ መስቀል መሆኑን ያስረዳናል፡፡ የሰላም ሰው ለመሆንም መስቀሉን መያዝ ግድ ይላል፡፡

👉ወ. በቅዱስ መስቀል የዕዳ ትእዛዛት ተሽረዋል።

ቅዱስ መስቀል የዘለዓለምን ሕይወት ላለመውረስ ምክንያት የነበሩት የዕዳ ትእዛዛትና ሕገጋት የተሻሩበት፣ እንደ ኦሪት ሕግ ይፈስ የነበረው የእንስሳት ደም ያለፈበት የብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት ትእዛዛት መሻሪያ፣ የዘለዓለምን ሕይወት የምንወርስበት የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ የተቈረሰበት፣ ክቡር ደሙም የተቀዳበት የሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት መጀመሪያ ነው፡፡

አንድም ሥርዐተ ግዝረት አልፎ ከክርስቶስ ጎን በፈሰሰው ማየ ገቦ አማካኝነት የሥላሴን ልጅነት የምናገኝበት ሥርዐተ ጥምቀት የተጀመረበት የሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት መንበር ነው።

ቅዱስ ጳውሎስም የግዝረት ትእዛዛትና ሕገጋት በቅዱስ መስቀል ተወግደው አማናዊ ሥርዐተ ጥምቀት የተተካበት መሆኑን ሲናገር "ወደምሰሰ ለነ መጽሐፈ ዕዳነ በሥርዐቱ እም ዕድውነ ወአእተቶ እማእከሌነ ወቀነዎ በመስቀሉ ● በእኛ ላይ የነበረውን፥ የሚቃወመንንም፥ በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።" (ቈላ. 2:14) ብሏል፡፡

አንድም የዕዳ ትእዛዛት የተባሉት ዲያብሎስ አስቀድሞ አዳምና ሔዋንን በጨለማ ውስጥ አግዞ “አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ፥ ሔዋን አመቱ ለዲያብሎስ” ብለው በሁለት እብነ ሩካም እንዲጽፉ ካደረገ በኋላ አንዱን በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ፥ አንዱን ደግሞ በሲኦል ውስጥ ጥሎታል፡፡

ክርስቶስም በዮርዳኖስ ወንዝ የተጣለዉን የዕዳ ትእዛዝ በሚጠመቅበት ጊዜ፥ በሲኦል የተጣለዉን የዕዳ ትእዛዝ ደግሞ በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ ሥጋው መስቀል ላይ ሳለ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ አስወግዶላቸዋል፡፡ ከዕዳ ትእዛዛት ነፃ ነኝ የሚል ክርስቲያንም መስቀልን ልይዝ ግድ ይላል፡፡

👉ዘ. በቅዱስ መስቀል አጠገብ ድንግል ማርያምን እና ሌሎቹንም ቅዱሳን እናገኛለን።

ቅዱስ መስቀል በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘን ክርስቲያኖች ሁሉ የምንታመንበት የማይነቃነቅ ዐለታችን ነው፡፡ ወደ ቅዱስ መስቀልም በፍጹም እምነት ስንቀርብ በመስቀሉ አጠገብ የአምላክ እናት ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምን እና በእግዚአብሔር ቅድስና የከበሩ ቅዱሳንን ሁሉ እናገኛለን፡፡

ቅዱስ ዮሐንስም ይሄን ሲያስገንዝበን "ወይቀውማ ኀበ መስቀሉ ለኢየሱስ እሙ ወእኅታ ለእሙ ወማርያም እንተ ቀለዮጳ ወማርያም መግደላዊት ● በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር።" (ዮሐ. 19:25) ብሏል፡፡ ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያም እና ከሁሉም ቅዱሳን ጋር ለመዛመድ ቅዱስ መስቀልን መያዝ የግድ ይላል፡፡

👉ሐ. ቅዱስ መስቀል ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን/ት መመኪያችን ነው።

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

21 Sep, 09:55


ሊነበብ የሚገባው ዕፁብ ቅኔ👇
👉በድሬዳዋ ርእሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል አገልጋይ ዲያቆን የሆነው ዲያቆን ሙሉጌታ (ወልደ #ዐማኑኤል) አበበ ከወይዘሪት #ጽጌረዳ ተስፋዬ ጋር ዛሬ መስከረም ፲፩/፳፻፲፯ ዓ.ም በሥርዐተ ተክሊል ሥርዐተ ከብካብ ፈጽሟል። ይሄንም በማስመልከት የተቀኘሁትን ሙሉ ቤት ቅኔ እንዲህ ከትቤላችኋለሁ፦

፩. ግእዝ ጉባኤ ቃና
●ናሁ ሰሰለ ወተአተተ ጽልመት፥
●#በሊቀ_ብርሃናት ያስተርኢ እስመ ኀተወ ማኅቶት።

፪.፩. ዕዝል ጉባኤ ቃና
●ፍጡነ ረድኤት ዘኮንከ ሚካኤል ከመ ተሀበኒ ክብረ፥
●እም አፉየ ንሣእ #ጽጌረዳ ስብሐት ሥሙረ።

፪.፪. ዕዝል ጉባኤ ቃና
●ትንቢተ ነቢይ እሙነ ከመ ይኩን #ዐማኑኤልሀ ርኢነ፥
●ወበትርጓሜሁ እግዚእ እግዚአብሔር ምስሌነ። (ኢሳ. ፯፡፲፬)

፫. ዘአምላኪየ
●በደዌ እኩይ እምድሕረ ለጕንዱይ ጻመወ፥
●መፃጕዕ ብሕታዌ መርዓዊ በሰንበት ሐይወ፥
●እስመ አብ ወልደ ዋሕዶ ለቤዛ ኵሉ መጠወ። (ዮሐ. ፭፡፩-፲)

፬. ሚ በዝሑ
●መርዓዌ ስብሐት ወክብር እምነ መቅደሱ በክብር #ረድኤተ ለየሀብከ፥
●እግዚአብሔር ፍቅር ወእም #ጽዮን ይትወከፍከ፥
●ወእም ኀበ ተክሊል ዮሐንስ #ዕጹብ ነገር #በቢታንያ ተሰብከ። (ዮሐ. ፩፡፳፮-፴፬)

፭. ዋይ ዜማ
●ወላዲተ ክርስቶስ ደብረ ምሕረት እስመ ኢየሐፍር አነ ቅድመ ሥዕልኪ ቀዊመ፥
●አመ ኀልቀ ወርሐ #ጽጌረዳ እቀውም ዳግመ፥
●ወበቅድመ ኵሉ ፍጡር ለእመ ኮንኩ ደክታመ፥
●#ዐማኑኤልሀ እግዚአ ነሢእየ ቅድመ፥
●እንበሌኪ ኢየሥሥ እመ።

፮. ሐፂር ዋይ ዜማ
●አስተርአየ በውስተ ምድርነ ወወሀበ #ጽጌ፥
●መርዓዌ ስብሐት ቀንሞስ ዘኢይዘመዶ ኑታጌ።
(●አስተርአየ በውስተ ምድርነ ወወሀበ #ጽጌ፥)

፯. ሥላሴ
●ኢሳይያስ ክብረ ተክሊል ድንግል ትፀንስ በድንግልና ወትወልድ ወልደ ባሕታዌ በድንግልና ልዑል፥ (ኢሳ. ፯፡፲፬)
●ወይሰመይ እንተ ወለደቶ ዐማኑኤል ቃል፥
●እመ ይቤለነ ኮነ ነገሩ ትርጓሜ ሐዲስ ወንጌል፥
●ወትርጓሜ ስሙ ዐማኑኤል፥
●ዐቢይ ጥቀ ወአኮ ቀሊል፥
●ይቤለነ ሳዊሮስ ድንግል። (ሃይ. አበ. ዘሳዊ. ፹፯፡፲፪)
(●ወድንግል ይእቲ ድንግል።)

፰. ዘይእዜ
●ጽጌረዳሆሙ ሕዝብ አስተጋብኡ ወሦኩሰ ተርፈ በኀበ እኩያን አይሁድ፥
●ወሕጠተ ሥርናይ ድሕረ ተዘርአ ዐጸድዎ እለ ኢዘርእዎ በአሚን ማዕጸድ፥
●ወቤተ አይሁድ አፀረት አስካለ በረከት ውስተ ምክያድ፥
●እለ ውስተ ኣፍኣ ይስተዩ ስቴ ደመ ወልድ፥
●ወእለ በአፍኣ ቀሰሙ ፍሬ ጽሕፈተ ቃል ጕንድ። (ሃይ. አበ. ዘዮሐ. አፈ. ፷፮፡፳፩-፳፬)
(●እለ ውስተ ኣፍኣ ይስተዩ ስቴ ደመ ወልድ፥)

፱. ሣህልከ
●ኢትዮጵያ ዘቆምኪ በፍና ጋዛ፥
● እስመ አንብዕኪ በዝሐ ወንጉሥኪ ወሬዛ፥ (መክ. ፲፡፲፮)
●ከመ ንንግር ውዳሴኪ አንብዕኪ ለምእመናንኪ ይኩነነ ቤዛ።

፲. ሐፂር ሣህልከ
●ለደብረ ምሕረት ምዕዝት እም ጽጌረዳ፥
●መጋቤ ብሉይ ዐምዳ ወሊቀ ብርሃናት ድዳ።
(●ለደብረ ምሕረት ምዕዝት እም ጽጌረዳ፥)

፲፩. መወድስ
●ጸባብ ጥቀ እንተ ትወስድ ኀበ ዘለዓለም ሕይወት ወፍኖተ ሐጕል ርሒብ፥ (ማቴ. ፯፡፲፫-፲፬)
●ትቤ ወንጌል ምጽላለ አህዛብ ወህዝብ፥
●ወዘንተ ቃለ እም ድሕረ ሰምዐ ቦአ መርዓዊ በአንቀጽ ጸባብ፥
●ማርያምሰ እመ በግዑ ውስተ ከርሠ አዳም ተኀቱ ዓዲ መርዓተ አብ፥
●ወቆማ ከመ በቀልት ኀበ ሙሓዘ ማይ ርጡብ፥
●ከመ ወርሕ ክበበ ገጻ ወአዕይንቲሃ ከመ ኮከብ፥ (ድጓ.)
●ወከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ አርባብ፥
●ከመ #ጽጌ ረዳ ሥነ ላህያ ወጣዕመ ቃላ ከመ ሐሊብ።

፲፪. ኵልክሙ መወድስ
●ፈጣሬ ኵሉ ፍጡር መርዓዌ ስብሐት ፈጠሮ ለሰብእ አመ ሳድሲት ቀመር፥
●ወበዕለተ ዐርብ ፈጸመ ተግባረ ኵሉ ፍጡር፥
●ወአመ ዕለት ሳብዒት አዕረፈ እም ኵሉ ዘአሐዘ ግብር፥ (ዘፍ. ፪፡፪)
●ወእንዘ እትቀነይ ለሥላሴ ሥላሴ ትትረመም ወጽመ ትትነከር።
●ይረድሂ ነቢብየ መልዕልተ ይእቲ ደብር፥
●ዘከመ ዝናም በውስተ ምድር ወዘከመ ጊሜ በውስተ ፀምር፥ (ዘዳ. ፴፪፡፪)
●ወከመ ሐሊብ ቅኔየ ወትርጓሜየ መዓር፥
●ሠማዕተ ቃለ ጽድቅ ይኩነኒ ዮሐንስ መደብር፥
●ወዘንተ እብል ለበዓለ ረቂቅ  ምስጢር።
(●ሠማዕተ ቃለ ጽድቅ ይኩነኒ ዮሐንስ መደብር፥)

፲፫. ሐፂር ኵልክሙ መወድስ
●እምኔነ ይርሐቅ ጼና በድነ ሐጕል ኵነኔ፥
●ይትሜዐዝ ከመ ጽጌ ረዳ ቀናንሞስ ቅኔ።

👇👇👇
ለበለጠ መንፈሳዊ መረጃ የሚከተለውን Link ተጭነው ይግቡ!

ቴሌግራም ግሩፕ
https://t.me/kineyared

ዩቲዩብ
https://www.youtube.com/@yaredzera-buruktube8843

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/Yared.ZeraBuruk?mibextid=ZbWKwL

1,918

subscribers

693

photos

58

videos