ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية @islamic_universities Channel on Telegram

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

@islamic_universities


هذه قناة تهتم بنشر أخبار منحة دراسية للجامعات الإسلامية، راجين من الله تعالى أن تكون سببا لطلبة العلم للإلتحاق بها

ይህ ቻነል የሚያተኩረው በሳዑዲ ስኮላርሺፕ የሚሰጡ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎችን የምናስተዋውቅበት ነው። አሏህ ለጠለበተል ዒልም ሰበብ እንዲያደርጋት እንከጅላለን!

Islamic Universities Scholarship | منحة الجامعات الإسلامية (Amharic)

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلاميةnnይህ እናቴ በዓለምን ለተጎደፈ መከታ ወደ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች በተካሄደ መረጃ ያለ መረጃ የሚፈልገውን ማህበረሰብ ይዘን ወደምለዳበት ግዜ ነን። በእርስዎ ምንም ስኮላርሽን አትተሳትልን፡፡ ነገር ግን እኛ እናቴ ማረጋግ የምጠለፈያ ችግር አሎን። አንደኛውንም ለጠለበተል እናንተውን ማስመሰል እኛ ይህ ስኮላርሽን ማጣሪ ነፃን ጠብቀን፡፡ እባኮ ሲቆንር እኛየን።

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

09 Oct, 04:32


تعلن ⁧ #الجامعة_الإسلامية ⁩ عن بدء المرحلة الثانية؛ لاستقبال طلبات الدراسة لبرنامج (الشريعة) عن بُعد، للطلاب والطالبات الدوليين المقيمين خارج المملكة، مع تخصيص (100) مقعد مجاني منحة مدعومة بالكامل مقدمة من وقف خادم الحرمين الشريفين الملك عبدالله بن عبدالعزيز لوالديه.

‏يبدأ التقديم: يوم الثلاثاء 1446/4/5هـ، لمدة (10) أيام، عبر الرابط الآتي:

‏⁦ distancelearning.iu.edu.sa

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

29 Sep, 07:45


🌹 ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች!

ይህ ቻናል በሳዑዲ የውጭ ሀገራት ነፃ ኢስላማዊ የትምህርት እድል የሚሰጡ ጃሚዓዎችን ( ዩኒቨርሲቲዎችን)በየጊዜው የምናስተዋውቅበት ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ብዙ ጠለበተል ዒልም ( ደረሳዎች ) ፍላጎቱ እያላቸው የጃሚዓውን መስፈርት ወይም እንዴት እንደሚሞላ ባለማወቅ ይህ ዕድል ያመልጣቸዋል።

ስለሆነም በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻናል ጃሚዓዎችን እያስተዋወቅን፣ መስፈርቶቻቸውንም እያስቀመጥን እና የተቅዲም (Apply) ዘዴውንም እየገለፅን ለጠለበተል ዒልም ሰበብ ይሆናል ብለን እናስባለን።

ስለዚህ ውጭ ሄዶ ለመቅራት/ለመማር ፍላጎቱ እያላቸው መንገዱን ላጡ ይህ ቻናል ሁነኛ መንገድ ይሆናቸዋልና ቻናሉን እንዲቀላቀሉ ጋብዙዋቸው!

ጀዛኩሙላህ!

ቻናሉን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ ተጭነው #join ይበሉ 👇
👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAFUFDzHMVLZ7BanGuQ
---
https://t.me/joinchat/AAAAAFUFDzHMVLZ7BanGuQ
---
https://t.me/joinchat/AAAAAFUFDzHMVLZ7BanGuQ
🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺

መልካም ዱዓችሁን ከጃይ Abu Hanif RM ከሳዑዲ ዐረቢያ ከኢማም ሙሐመድ ቢን ሱዑድ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ፤ ሪያድ።
🗒 ረቢዑል አወል 26/1446 ሂ ፤ መስከረም 19/2017 ዓ.ል

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

28 Sep, 13:37


أيا طالب العلم قم لا تنم
فإن الزمان انقضى وانصرم
.
.
.

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

18 Sep, 16:06


🛑ምዝገባው አልቋል🛑

ውጤታችሁንም ከአራት ወር በኋላ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፤ በየ ወሩ ኢሜላችሁን እና ዌብሳይቱን ጎብኙ።

ለሞላችሁ አላህ ይወፍቃችሁ!
ላልሞላችሁ መረጃዎችችሁን በማሟላት ለቀጣይ ተዘጋጁ!

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

18 Sep, 03:33


🛑 ልብ በሉ! የሚዘጋው ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ነው። 🛑

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

18 Sep, 03:21


የማመልከቻ ሊንክ፦
https://si.ksu.edu.sa/
(ሊንኩን copy  አድርገው በ google chrome ይግቡ)

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

14 Sep, 12:13


ተራ ቁጥር 6 የግል ቅፅ በ adobe acrobat ያስቸገራችሁ፤ ከታች ባለው ilovePDF የሚለውን አፕ አውርዳችሁ መሙላት ትችላላችሁ!

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ilovepdf.www

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

13 Sep, 14:12


🗓 5 ቀን ቀረው ‼️

በሳዑዲ ሪያድ ከተማ የሚገኘው አንጋፋው መሊክ ሱዑድ ዩኒቨርሲቲ ለድግሪ መርኃ ግብር ስኮላርሺፕ ት/ት ማመልከቻ ጊዜ ሊያልቅ 5 ቀን ብቻ ይቀረዋል።

የሚያስፈልጉ መረጃዎች፦
① ፓስፖርት
② የ10፣ 11 እና 12ኛ ሰርተፊኬት
③ የሁለተኛ ደረጃ ውጤቶች የ10,11 እና 12ኛ
④  የመታወቂያ ካርድ
⑤ የመልካም ስነ–ምግባር ሰርተፊኬት
⑥ የግል ቅፁን በ Adobe acrobat ቀጥታ ሞልቶ መላክ (በመጀመሪያ ገፅ ላይ ያገኙታል እዛው ሞልቶ ሴቭ ማድረግ)

ምዝገባው የተከፈተው፦ነሐሴ 12/2016 ( Aug 18/2024)
የሚያበቃው፦ መስከረም 8/2016 (sep 18/2024)

የማመልከቻ ሊንክ፦
https://si.ksu.edu.sa/
(ሊንኩን copy  አድርገው በ google chrome ይግቡ)
.
አላህ ይወፍቃችሁ!

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

11 Sep, 12:06


በሳዑዲ ከሁለቱ ሐረሞች (መካና መዲና) ቀጥሎ ትልቁ መስጂድ፤ መስጂድ ኳዲሙል ሐረመይን መሊክ ፈህድ! ይህ በጃሚዓችን ኢማም ሙሐመድ ቢን ሱዑድ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኝ ግዙፍ መስጂድ ነው። ለ20 ሺ ሰጋጆች ይበቃል።
ለበለጠ መረጃ https://www.al-jazirah.com/2002/20021102/pl5.htm

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

11 Sep, 11:38


اللهم علمنا ما ينفعنا وانفعنا بما علمتنا ...
داخل القاعة في درس علم الفرائض
طلاب كلية الشريعة جامعة الإمام محمد بن سعود الإسلامية.

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

09 Sep, 09:07


እንቁጣጣሽ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

57፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ።
اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ጳጉሜ” የሚለው ቃል “ኤፓጎሜኖይ” ἐπαγόμενοι ከሚለው ከግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ “ተጨማሪ” ወይም “የተጨመረ” ማለት ነው፥ ጳጉሜ የወር ስም ሲሆን በነባሮች 12 ወራት ላይ የተጨመረ 13ኛ ወር ነው። ይህም ወር በነሐሴ እና በመስከረም መካከል የሚገኝ የመጨረሻው ወር ነው፥ ጳጉሜ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በዘመነ ሉቃስ ስድስት ቀናት ሲኖሩር በዘመነ ዮሐንስ፣ በዘመነ ማቴዎስ እና በዘመነ ማርቆስ አምስት ቀናት ይሆናል። ልብ በሉ! ይህ ወር ከግሪክ ሄለኒዝም የተጀመረ እና ከአሌክሳንድርያ ወደ ኢትዮጵያ የገባ እንጂ በዕብራውያን አቆጣጠር ላይ ወራት 12 ብቻ ናቸው። አምላካችን አሏህ የወሮች ቁጥር በእርሱ መጽሐፍ ሰማያትን እና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር እንደሆነ ነግሮናል፦
9፥36 አላህ ዘንድ የወሮች ቁጥር በአሏህ መጽሐፍ ዉስጥ ሰማያትን እና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር ነው።
إِنَّ عِدَّةَ ٱلشُّهُورِ عِندَ ٱللَّهِ ٱثْنَا عَشَرَ شَهْرًۭا فِى كِتَٰبِ ٱللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ

ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያው ዘመን መለወጫ በልምድ ከግሪክ የመጣ ሰርጎገብ እንጂ አገር በቀል አይደለም፥ ከዚያም ባሻገር መለኮታዊ ትእዛዝ ያለው ሳይሆን ሰው ሠራሽ ቢድዓህ ነው። ዓመተ ምሕረትን ያማከለ ዘመነ ሉቃስ፣ ዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ሰው ሠራሽ ሃይማኖታዊ አስተምህሮት ነው፥ በዛ ላይ የባዕድ አምልኮ የሚፈፀምበት ቀን ነው። በጳጉሜ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ፥ በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ ጌጦች እና የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ።

ይህ ቀን ሲያልቅ የቀኑ መጨረሻ ተጓግቶ ስለሚመጣ “እንቁ” ተባለ፥ የሚያመጣው ጣጣና መዘዝ ደግሞ “ጣጣሽ” ተባለ። በጥቅሉ “እንቁ ጣጣሽ” ተባለ፥ ጥንቆላና ድግምት ከትልቁ ሽርክ የሚመደቡ የአሏህን ሐቅ የሚነካ ትልቅ በደል ነው። እንቁጣጣሽን ማክበር አቆጣጠሩ አገራዊ ሳይሆን እምነታዊ መሠረት ያለው ሲሆን ከእርሱ ጋር የተያያዙት ባዕድ አምልኮ አስበን ከዚህ ሰው ሠራሽ በዓል እራሳችንን እንጠብቅ! እንግዲህ እንቁጣጣሽ ዓመታዊ በዓል ዓረማዊ እና ክርስትናን ቀላቅሎ የያዘ በዓል ነው፥ በዚህ ጊዜ "እንኳን አደረስን" ወይም "እንኳን አደረሳችሁ" ሲባል ይህንን በዓል ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው። ሙሥሊም ያሉት ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ እና ብቻ ናቸው፥ እነርሱም ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው ዐወቁ። እርሳቸውም፦ "እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፥ "ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ ”አሏህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፥ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን አሏቸው”።
عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃምዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፥ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው”።
عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃምዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” ”በሁለቱ በዓል በዒደል አደሐ እና ዒደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል”።
عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ስለዚህ ከአላህ የወረዱትን ቁርኣን እና ሐዲስ ብቻ ከተከተልን ሁለት በዓል ብቻ እና ብቻ አለን፦
7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ።
اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢትባዕ” إِتْبَاع‎ ማለት እራሱ የቢድዓህ ተቃራኒ "ከአሏህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል" ማለት ነው። "ቢድዓህ" بِدْعَة የሚለው ቃል "በደዐ" بَدَّعَ ማለትም "ፈጠረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ፈጠራ” ማለት ነው፥ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ የሌለ ነገር በዲን ላይ መጨመር "ቢድዓህ" ሲሆን ሙሥሊም ግን የተወረደውን ብቻ ሲከተል ሁለት  ዒድ ብቻ እና ብቻ ያከብራል። ስለዚህ "እንቁጣጣሽ" ስንባል "እንኳን ደህና መጣሽ" ከማለት ይልቅ "ማን አመጣሽ?" ብለህ በታሪካዊ ዳራ እና ፍሰት እንሞግታለን። በዓሉን ባለማወቅ ለሚያከብሩ አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
-----
ስለ እንቁጣጣሽ ያንብቡ እና ያስነብቡ!

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

07 Sep, 07:47


🛑 11 ቀን ቀረው 🛑

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

01 Sep, 15:04


🛑 ይህ የመሊክ ሱዑድ ዩኒቨርሲቲ ለዲግሪ ማመልከቻ 18 ቀን ቀረው‼️

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

27 Aug, 07:57


📌 ተራ ቁጥር 2 ላይ የ10ኛ እና 11ኛ ሰርተፊኬት ከሌለ የውጤቱን/ትራንስክሪፕት አስገቡ።

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

27 Aug, 07:20


የኮርሶቹ ዝርዝር!

ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስኮላርሺፕ | منحة الجامعات الإسلامية

27 Aug, 07:19


🛑 በሳዑዲ ሪያድ ከተማ የሚገኘው አንጋፋው ዩኒቨርሲቲ መሊክ ሱዑድ ለድግሪ መርኃ ግብር ለስኮላርሺፕ ተማሪዎች 4 የተለያዩ ኮርሶችን በነፃ ለመማር እንዲያመለክቱ በሩን ክፍት አድርጓል። 🛑

የሚያስፈልጉ መረጃዎች፦
① ፓስፖርት
② የ10፣ 11 እና 12ኛ ሰርተፊኬት
③ የሁለተኛ ደረጃ ውጤቶች የ10,11 እና 12
④  የመታወቂያ ካርድ
⑤ የመልካም ስነ–ምግባር ሰርተፊኬት
⑥ የግል ቅፁን በ Adobe acrobat ቀጥታ ሞልቶ መላክ (በመጀመሪያ ገፅ ላይ ያገኙታል እዛው ሞልቶ ሴቭ ማድረግ)

ምዝገባው የተከፈተው፦ነሐሴ 12/2016 ( Aug 18/2024)
የሚያበቃው፦ መስከረም 8/2016 (sep 18/2024)

የማመልከቻ ሊንክ፦
https://si.ksu.edu.sa/
(ሊንኩን copy  አድርገው በ google chrome ይግቡ)
.
መረጃዎቻችሁን በተገቢው አሟልታችሁ እንድታመለክቱ አደራ እንላለን!

አላህ ይወፍቃችሁ!

1,999

subscribers

196

photos

19

videos