🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)✍ @mustefatemam Channel on Telegram

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

@mustefatemam


@በእውቀት መስራትና መናገርን የተገጠመ ታድሏል!!!

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)✍ (Amharic)

በእውቀት መስራትና መናገርን የተገጠመ ታድሏል! ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን) የሚባለው ታሪክ ከዚህ በታች በዓለም ብቻ እንዲሆን ነው። ይህ ቦርድን በእሁድና በሶስት ተመሳሳይ አማራጮች እንዲያገኙበት በአሁኑ ጊዜ እንደተበናበነ በኢትዮጵያ በእርስዎ ቋንቋ እንዲሰራቸው ነው። ይህ ታሪኩ እንደሚሰማን እና ለሁሉም እንደሚያደርገን ላይ ተጠቃሚ ምርት የሚያርዳቸው እምነትም፣ የስራ ማህበረሰብና ኢትዮጵያ በርካታ ቀጣይ እንዲያደርጋቸው ፈጣራው ነው። አቡ ዐብዱረህማን ምንም ታሪኩ ለእኛ አስከብርበብን ለሚሆን የሚሆነውን አገልግሎትንና መከላከያን በመደገፍና ከሰው ከተለያዩ የእውቀት አማራጮች ጋር ለማምጣት ይህ ቦርድ ይጠጣል።

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

18 Jan, 11:06


አሁን ቀጥታ ስርጭት ስልጤ ዞን አልቾ ወረዳ ገድራት ቀበሌ አል አቅሳ መስጅድ

ሀገር አቀፍ የዳዕዋ ፕሮግራም

በሸይኽ አብድልሃሚድ አል ለተሚ



https://t.me/medresetulislah

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

17 Jan, 17:33


🔷  ልብ እንደ ድስት ነው በያዘው ነገር ይንተከተካል ።

قال يحيى بن معاذ – رحمه الله – :

"  القلوب كالقدور تغلي بما فيها ، وألسنتها مغارفها ، فانظر إلى الرجل حين يتكلم فإن لسانه يغترف لك بما في قلبه ، حلو وحامض ، وعذب وأجاج ، وغير ذلك ، ويبين لك طعم قلبه اغتراف لسانه ، أي كما تطعم بلسانك طعم ما في القدور من الطعام فتدرك العلم بحقيقته ، كذلك تطعم ما في قلب الرجل من لسانه ، فتذوق ما في قلبه من لسانه ، كما تذوق ما في القدر بلسانك ".

           الجواب الكافي   ص ( 159 )

🔹 የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ የተባለ ሊቅ ስለ አንድ ሰው ልብ ሲናገር እንዲህ ይላል : –

" ልብ እንደ ድስት ነው በያዘው ነገር ይንተከተካል ። ምላስ ጭልፋው ነው ። አንድን ሰው ሲናገር አዳምጠው ምላሱ ልቡ ውስጥ ካለው እየጨለፈ ነው ።
    ጣፋጭ,  የተበላሽ , ለዛ ያለው,  ጨዋማ ( ጎምዛዛ ) የመሳሰሉት,  የልቡን ቃና ምላሱ ይገልፅልሀል ። በምላስህ ቀምሰህ ድስት ውስጥ ያለውን ምግብ ቃና እንደምታውቀው ሁሉ በሰውየው ልብ ያለውን ደግሞ በምላሱ ታውቀዋለህ ። በልቡ ያለውን በምላሱ ትቀምሰዋለህ ። በድስት ያለውን በምላስህ እንደምትቀምሰው ሁሉ " ። !!!!!

     🔹 እዚህ ጋር ልብ ማለት ያለብን የሕያ እየተናገረ ያለው አንድ ሰው ስለሚናገረው ነገር ነው ። የሚናገረው በልቡ ካለው ስለሆነ ነው ታውቀዋለህ የሚለው እንጂ በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ያለውን ከአላህ ውጪ የሚያውቅ የለም ። የሕያ ግን ልብ ውስጥ ካለው ምላስ ግልፅ ያደረገውን ነው ታውቀዋለህ እያለ ያለው ይህም ቢሆን ሁሌ ልክ ይሆናል ማለት አይደለም ። ልክ ዓማር ኢብኑ ያሲር ልቡ በኢማን ተሞልቶ በምላሱ የኩፍር ቃል እንደተናገረው ሁሉ ። እንደነዚህ አይነቶቹ ክስተቶች በጣም ጥቂት ( ናዲር ) ስለሆኑና በአብዛኛው ሰው በልቡ ያለውን ስለሚናገር ነውና መልእክቱን በተዛባ መልኩ እንዳንረዳው ።

https://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

17 Jan, 17:01


https://t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk?livestream

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

17 Jan, 16:54


🕌  🕌 ልዩ የዳዕዋና ኮርስ ፕሮግራም

      በአላህ ፈቃድ የዲን ትምህርት ድግስ ከዛሬ ጥር 9/5/2017 የጁመዓ ኹጥባና ሰላት ጀምሮ  ለተከታታይ 3 ቀናቶች ተዘጋጅቷል ::

ቀናቶቹ በታላላቅ የሀገራችን  መሻይኾችና ኡስታዞች  የኮርስና የሙሃደራ ፕሮግራሞች ይደምቃሉ::

➡️  ቦታ

     በአሊቾ ዊሪሮ ወረዳ በገደራት ቀበሌ ልዪ ስሙ ጮል በተሰኘችው መንደር በአል-አቅሳ መስጂድና መድረሳ ተሰናድቶ ይጠብቃችኋል::

የፕሮግራሙ አዘጋጅ :-
     የገደራት ቀበሌ አል-አቅሷ መስጂድ እና መድረሳ ማህበረሰብ እና የአካባቢው ተወላጆች

በዝግጅቱ ላይ ከሚገኙ ውድና ብርቅዬ መሻይኾች መካከል:

↪️  አሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ቢን ያሲን አለተሚይ(ከለተሞ)

بعنوان :-  وقفات مع سورة نوح

ልዪ ቆይታ ከሱረቱ ኑህ ጋር

↪️  አሸይኽ ሙሐመድ ሀያት (ከወሎ ሐራ)

دورة مكثفة في المنهج
ልዩ ኮርስ በሚንሃጅ ዙሪያ

🕌 አሸይኽ ሁሰይን ከረም
 (ከወሎ ሐራ)
بعنوان:-الإعتصام بحبل الله
ርእስ:-በአላህ ገመድ መተሳሰር

↪️   አሸይኽ ሙሐመድ ጀማል (ከኮምቦልቻ)

بعنوان:-خطر البدع وأهلها في الإسلام

የቢድዐ እና የቢድዐ ባለቤቶች አደጋ በእስልምና ላይ

↪️ አሸይክ ሙባረክ አልወልቂጢይ (ከወልቂጤ)

بعنوان :- مجمع الشرك
   የሺርክ መናሀሪያዎች 

↪️ አሸይኽ ሁሰይን  ሙሐመድ አስልጢይ  (ከአዲስ አበባ)

بعنوان :- الصبر في الدعوة إلى الله

   ሰብር ወደ አላህ በመጣራት ላይ

↪️ አሸይኽ መህቡብ (ከሳንኩራ)     
 
بعنوان :- كن على بصيرة في ديك

   የቻሌ የንበሪ (በስልጢኛ ቋንቋ)

↪️ አሸይኽ አወል (ከዳሎቻ)

إن هذا الدين أمانة عظيمة

     ዲኒ እኮ የሮሬን አማነ (በስልጥኛ ቋንቋ)

🛜   አሸይኽ አቡ ዘር (ከሱኡዲ አረቢያ) በቀጥታ ስርጭት

📜ጣፋጭ የግጥም ስንኞች በወንድማችን ኢብኑ ኑሪ ተዘጋጅተዋል

በስልጥኛ
በአማርኛ
በአረብኛ
ይደመጣሉ::

🕌እንዲሁም በርካታ ውድና ተናፋቂ ሰለፍይ ኡስታዞች የሚታደሙበት ደማቅ ፕሮግራም ነው ።

ማሳሰቢያ:-ሁላችሁም ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ እና የማታ ልብስ እንዳትዘንጉ::

👌የሀቅ ወዳጆች ሁሉ በአክብሮት ተጋብዛችኋል እንዳትቀሩብን‼️

📲+251913890385
📲+251716270733
📲+251938306021

https://t.me/YeIslam_brhan_ye_ewket_maed

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

17 Jan, 16:54


በስልጤ ዞን አልቾዊሪሮ ወረዳ በገድራት ቀበሌ ልዩ ልዪ ስሙ ጮል ተብሎ በሚጠራ መንደር አል አቅሳ መስጂድ።።። ከቦዦባር እና ከጠረጋ ለምትመጡ  ከጠረጋ ወደ ቃዋቆቶ በሚያስኬደዉ ፒስታ መንገድ ኩተሬ ደርሳቹ ወደ ቂልጦ በሚየስኬደዉ መንገድ ላይ ከሾሞ ወደ ግራር ትምህርት ቤት በምያስኬደዉ መንገድ ተሻግሮ ከወራቤ ለምትመጡ ወንድሞች ከወራቤ ኩተሬ ደርሳቹ ወደ ቅልጦ በምያስኬደዉ መንገድ ከሾሞ ወደ ግራር ትምህርት ቤት በምያስኬደዉ መንገድ ተሻግሮ።።።ልዪ ስሙ ጮል ይባላል

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

15 Jan, 20:34


በወርቅ የሚፃፍ ንግግር !

የህያ ኢብኑ ሙዓዝ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላል

« القُلوب كالقُدور في الصُّدور تَغلي بما فيها، ومغارِفُها ألسِنَتُها، فانتظِر الرجُل حتى يتكلَّم، فإنَّ لسانَهُ يغتَرِفُ مِن قلبه، مِن بين حُلوٍ وحامِض، وعذب
وأجاج يخبرك عن طعم قلبه اغتراف لسانه

” ልቦች በደረት ውስጥ እንደ ድስት ነች በውስጡ ባለው ነገር ይፍለቀለቃል መጨለፊያው ምላስ ነው አንድን ሰው እስኪናገር ጠብቀው ምላሱ ከልቡ ይጨልፍልሃል ከጣፋጩም ከጎምዛዛውም ጣፋጭ የሆነውንም ከመርጋጋው ስለ ልቡ ጠዓም በምላስ መጨለፊያው ታውቃልህ“

ኢብኑል ቀይምም የሚከተለውን ይላል ፦
በድስት ውስጥ ያለን ነገር በምላስህ ቀመሰህ ሁኔታውን እንደምታውቀው ልክ እንደዚሁ ሰውን በምላሱ ትቀምሰዋልህ በድስት ውስጥ ያለውን በምላስህ እንደምትቀምሰው " ።

وَأَيْسَرُ حَرَكَاتِ الْجَوَارِحِ حَرَكَةُ اللِّسَانِ وَهِيَ أَضَرُّهَا عَلَى الْعَبْدِ.

ኢብኑልቀይም ረሂመሁሏህ እንዳለው ከአካል ቀላሉ እንቅስቃሴ የምላስ እንቅስቃሴ ነው እሷ ማለት በጣም ባሪያውን የምትጎዳ ነች ።


join #telegram ቻናል
https://t.me/abuabdurahmen

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

15 Jan, 20:34


🟢ብልጣብልጦች አይሸዉዱን

إعلم - رحمك الله-
ለኢስላም የሚሰሩ የሚመስሉ ሙናፊቆች ፣ ለሱነህ ታጋይ የሚመስሉ ሙብተዲዖች ፣ ሰለፊይ መሳይ ህዝቢዮች ይኖራሉ:: በውስጣቸው ያዘሉትን አዝለው ገፅታቸውን የሚያሳምሩት ስልጣን ለመቆናጠጥ ፣ ወይም ገንዘብ ለመሰብሰብ ፣ አሊያም ሴቶችን ለማደን ፣ ወይም ሌላ ድብቅ ሴራ ቋጥረው ሊሆን ይችላል::

👉ብልጣብልጦች ስላሸበረቁና ውርውር በማለታቸው ለላመታለል በአላህ ታግዞ መጠንቀቅ !!

ከሰለፎች ንግግሮች መካከል :
"لستُ بالخِبِّ ولا الخِبُّ يخدعني" 
" አታላይ (ብልጣብልጥ) አይደለሁም ብልጣብልጥም አይሸውደኝም::"

ከአላህ ንግግሮች ውስጥ:
﴿أَمْ حَسِبَ الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمْ مَرَضٌ أَنْ لَنْ يُخْرِجَ اللَّهُ أَضْغَانَهُمْ (٢٩) وَلَوْ نَشَاءُ لأرَيْنَاكَهُمْ فَلَعَرَفْتَهُمْ بِسِيمَاهُمْ وَلَتَعْرِفَنَّهُمْ فِي لَحْنِ الْقَوْلِ وَاللَّهُ يَعْلَمُ أَعْمَالَكُمْ (٣٠)

(እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው አላህ (በውስጣቸው የቋጠሩትን) ተንኮል አያወጣው መሰላቸውን? ። ብንፈልግ እነርሱን ባመላከትንህና በምልክታቸውም በእርግጥ ባወቅሃቸው ነበር፡፡ በእርግጥ በንግግር መንጋደድ  ታውቃቸዋለህ፡፡ አላህም ሥራዎቻችሁን ያውቃል፡፡)

 ( إِنَّ فِي ذَلِكَ لآيَاتٍ لِلْمُتَوَسِّمِينَ)
﴿٧٥ الحجر)
(በዚህ ውስጥ በጥልቀት ለሚመለከቱ በእርግጥ መገምገሚያዎች አሉበት፡፡)

👉ሸረኞችን በምልክታቸው ማወቅና መጠንቀቅ የነቢዩ (ﷺ) እና የሰለፎች ፈለግ ነው ::


  ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)
http://t.me/Abuhemewiya

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

01 Jan, 03:44


🔴 بشرى للسلفيين.

🎙 الشيخ محمد امان الجامي رحمه الله.

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

31 Dec, 18:25


https://t.me/YeIslam_brhan_ye_ewket_maed?videochat

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

28 Dec, 20:44


🔹በሙኻሊፎች ላይ ምላሽ መስጠት ሰለፎች ዘንድ ትኩረት የሚሰጠው አካሄድ ነው ። ከዚህ የሚፈራው የስሜት ባልተቤት ወይም በእውቀቱ ደካማ የሆነ ቢሆን እንጂ ሌላ አይደለም ።

https://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

28 Dec, 19:23


https://t.me/alislaahwomenonlineders?videochat

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

28 Dec, 11:27


https://t.me/medresetulislah?livestream

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

24 Dec, 16:53


🟢የተምዪዕ በሽታ እንዲህ ይጀምራል

🎤ከአሸይኽ ሙሀመድ አማን አልጃሚይ ፈትዋ

👉ጥፋት እና ጥፋተኛን እያዩ ኢንካር ከማድረግ (ከማስተካከል) ይልቅ ምክንያት መደርደር ::

👉የእነ አህመድ ኣደም እና ያሲን ኑር የተመዪዕ ስልት ነች::

👉የሀገራችን ተመዩዕ በሽታ::

👉ሰለፊይ ዑለማዎች አጥማሚዎችን እንዲህ አጋልጠው ኡማውን  በአላህ ፈቃድ ታድገዋል ::

👉የሙመይዓዎችን ፍልስፍና ትተህ በነቢዩ (ﷺ) ሀዲስ ስራ::
" مَنْ رَأَى مِنْكُمْ مُنْكَرًا فَلْيُغَيِّرْهُ بِيَدِهِ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبِلِسَانِهِ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبِقَلْبِهِ، وَذَلِكَ أَضْعَفُ الْإِيمَانِ ".
أخرجه مسلم في "صحيحه"، كتاب : الإيمان باب النهي عن المنكر من الإيمان (1/ 50) رقم (49).


https://t.me/FATTAWAS

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

17 Dec, 10:30


🟡ሀቅ እና ወርቅ

ከሸይኹልኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ ወርቃማ ንግግሮች

قال ابن تيمية
《…فَالْحَقُّ كَالذَّهَبِ ‌الْخَالِصِ، كُلَّمَا امْتُحِنَ ازْدَادَ جَوْدَةً، وَالْبَاطِلُ كَالْمَغْشُوشِ الْمُضِيءِ، إِذَا امْتُحِنَ ظَهَرَ فَسَادُهُ.》

አላህ የወደዳት
ወርቃማዋ እውነት
ስትፈተን በሳት
ዝቃጩን አራግፋ
ኮረፉን አረፋ
ጨለማውን ገፋ
ጠላት አሸንፋ
በተሻለ ሴራ
አስመሳይ ሲጣራ
ጥራቷን ጨምራ
እዩ ስታበራ
ሀቅን እንደወርቁ
ልባሞች እወቁ
ከባጢልም ራቁ

https://t.me/Abuhemewiya

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

14 Dec, 03:41


👉 ወንድማዊ ምክር ለእህቶችና ወንድሞች

መለኮታዊ የህይወት መመሪያን መሰረት ያደረገው ኢስላም ለሴት ልጅ ያጎናፀፈውን ክብርና የሰጣት ቦታ የሚታወቅ ነው ። ሴት ልጅ በኢስላም የተከበረች የእናት ፣ የልጅ ፣ የእህትና ሚስትነት ቦታ የያዘች የህብረተ ሰብ አካል ነች ። ይህ ክብሯ ተጠብቆ የሚቆየው አላህ ባዘዛት ቦታ ስትገኝና ከከለከላት ቦታ ስትርቅ ነው ። ከተከለከለችው ነገር ውስጥ አንዱ ከባዳ ወንድ ጋር መቀላቀልን ነው ።
በተቃራኒው ሴት ልጅ ቤቷ ላይ መሆን እንዳለባትና የመሀይማን አይነት መገላለጥ እንዳትገላለጥ አዟል ። የመሀይማን አይነት መገላለጥ የሚለውን ከፊል የኢስላም ሊቃውንቶች ጎዳና ላይ ወጥቶ ከባዳ ወንዶች ጋር መደባለቅ ብለው ፈስረውታል ። ከእነዚህ ውስጥ ታላቁ ታቢዕይ ሙጃሂድ ይገኝበታል ።
ይህ ክልክል የሆነው መቀላቀል በተለያየ መንገድ ሊሆን ይችላል ። ከእነዚህ ውስጥ በተለያዩ አንድ ወንድና ሴት ተለይተው ሊገናኙ በሚችሉባቸው ግሩፖች ላይ መቀላቀል ይገኝበታል ። የዘመናችን ትላልቅ የሱና ዑለሞች ሴቶች ለብቻቸው ግሩፕ መክፈት እንዳለባቸውና ከወንድ ጋር እንዳይቀላቀሉ ይከለክላሉ ። ምናልባት ግዴታ መቀላቀል ካስፈለገ ሴት መሆኗ በማያስታውቅ ስም ትቀላቀል ሀሳብ ስትሰጥም በዛው መልኩ ይሁን ይላሉ ። ይህ ሁሉ የፊትና በሮችን ለመዝጋት ነው ። ምክንያቱም ኢስላም አንድን ነገር እርም ሲያደርግ ወደዛ የሚያዳርሱ መንገዶችንም እርም ያደርጋል ( ይዘጋል) ። ዝሙትን እርም ሲያደርግ ወደዛ የሚያደርሱ መንገዶችንም እርም አደረገ ።
ሴት ሸሪዓዊ እውቀት ካላት ለሴቶች ማስተማር ትችላለች ምናልባት ወንዶች ዘንድ የማይገኝ እውቀት ካላት ሸሪዓ ባስቀመጠው መስፈርት ወንዶችን ማስተማር ትችላለች ። ነገር ግን አሁን እያየነው ያለው አይነት ኡሙ እገሌ እያለች ግሩፕ ወይም ቻናል ከፍታ እየፃፈች ወንዶች በተለያየ ቻናልና ግሩፕ ሼር ማድረጋቸው ፊትናን ለማስፋፋት እንደመተባበር ይቆጠራልና ከዚህ ተግባር እህቶችም ወንድሞችም ሊቆጠቡ ይገባል ። እንዲህ አይነት አደባባይ መውጣት በፍፁም ከሰለፍይ እህት የሚጠበቅ አይደለም ። ምክንያቱም እሙ እገሌ ማን ነች ስሟ ማን ነው ስልኳን እንዴት ማግኘት እችላለሁ የሚሉ የፊትና በሮችን ይከፍታል ።
ፈተና ይርቁታል እንጂ አያቀርቡትም ስለዚህ እንዲህ አይነት ተግባር ውስጥ የገባችሁ እህቶችና ሼር የምታደርጉ ወንድሞች ከዚህ ተግባራችሁ ተቆጠቡ እላለሁ ።
ለስሜታችን የሚከብድ ሊሆን ስለሚችል ጉዳዩን ወደ ዑለሞች ማድረስና መጠየቅ ጥሩ ነው ።
አላህ ሐቅን አውቀው ከሚሰሩበትና ባጢልን አውቀው ከሚርቁት ባሮቹ ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

12 Dec, 14:02


የአዲስ ደርስ ማስታወቂያ

ዘወትር ቅዳሜ፣ እሑድ፣ ሰኞ እና ማክሰኞ ከፈጅር ሶላት  በኋላ ሲሰጥ የነበረው

የአል-አርበዑን አንነወዊ ኪታብ ስላለቀ በቦታው የተተካው

📚 ሪያዱ አስሷሊሒን ሚን ከላሚ ሰዪዲል ሙርሰሊን

የኢማም አንነወዊይ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በተለመደው ሰአት የሚቀጥል ይሆናል።

🎙 ትምህርቱ የሚሰጠው  በአቡ ሐመዊያህ ሸምሱ ጉልታ (ሐፊዘሁላህ)



🕌 
አልኢስላሕ መድረሳ


አልኢስላሕ መድረሳ👇👇👇   የተለያዩ ደርሶችን በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል እና የሚለቀቁ ደርሶች ለማግኘት የመድሳውን ቻናል #join በማለት ይቀላቀሉ። https://t.me/medresetulislah

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

09 Dec, 10:07


👉 ራቁት ሆኖ ከመዝፈን በአላህ ላይ ማጋራት ይበልጣል !

ወንጀል በየትኛውም ሀገር በማንም ቢሰራ ወንጀል ነው ። የሆነ ሀገር ስለተሰራ ከወንጀልነት አያወጣውም ። ሪያድ ላይ በሆነ ፕሮግራም ላይ የነበረ አሳዛኝና አስቀያሜ ተግባር ሶሞኑን ሰዎች ሲያወሩ ሰምቼ ምንድነው ብዬ ለማየት ሞከርኩ ። ድርጊቱ በጣም ፀያፍና አላህን የሚያስቆጣ ተግባር ነው ። የካዕባ ምስል ተሰርቷል ለብሰዋል ለማለት የማያስደፍር ዘፋኝ ሴቶች በምእራባዊያን አኳኋል ያብዳሉ ። የዚህ አይነቱ ተግባር ፍፁም ከኢስላም አስተምሮ የራቀ አስቀያሚ ተግባር ነው ። ይህን ክስተት በተለይ የግብፅና የፍልጢን አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች የሳውዲን መሪዮች ለማክፈርና ለመርገም ምቹ አጋጣሚ ሆኖላቸው አየሁ ።
በጣም የሚገርመው አንድ የእናቱን ፊት የተዋሰ የሚመስል የግብፅ ጋዜጠኛ ከሱረቱል ق የተወሰኑ አንቀፆችን ቀርቶ አላህ ፊት የቂያማ ቀን ስለመቆምና ስለሚኖረው ጭንቅ ከተናገረ በኋላ ለሳውዲ መሪዮች ጥያቄ ያቀርባል ። ሱብሓነላህ እንዴት የሚገርም ለዲን መቆርቆር ነው በጣም ደስ ይላል ። በዚህ መልኩ ወንጀልን መፀየፍና ማውገዝ ከኢስላም መርሆች ውስጥ ዋነኛው ነው ።
ነገር ግን እኔ ለእነዚህ አካላት ጥያቄ አለኝ እነዚህ ወንጀሎች ሳውዲ ውስጥ ሲሰሩ ነው በዚህ መልኩ የምትቆረቆሩትና የምታወግዙት ወይስ ሀገራችሁም ላይ ? ለመሆኑ ከአላህ ውጪ ላለ አካል ለአላህ እንጂ የማይገቡ የአምልኮ አይነቶችን መስጠት አሁን እያወገዛችሁት ካለው ወንጀል እንደሚበልጥ ታውቃላችሁን ? በግብፅ ምድር ላይ የአሕመደል በደዊ ቀብር ከ3 · 5 ሚሊየን ህዝብ በላይ ጠዋፋ ሲያደርግበት ፣ የቀብሩን አፈር በጥብጦ ሲጠጣ ፣ ከአላህ እንጂ የማይጠየቁ እንደ ከጭንቅ አውጡኝ ፣ አፍያ ስጡኝ ፣ ርዝቄን አስፉልኝ ፣ ዘር ስጡኝ ፣ እና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ለአሕመደል በደዊና ለዱሱቂ ፣ ለዘይነብና ለመሳሰሉ ሙታኖች ሲጠይቁ የት ነበራችሁ? የዚህ አይነቱ የቀብር አምልኮ መንግስታችሁ ባጀት መድቦ ሰራዊት አሰልፎ እንደባአል እንዲከበር ሲያደርግ ታወግዛላችሁ ? ወይስ ይህ በናንተ ሀገር ሲሰራ ወንጀል አይደለም ? ቤቱ በመስታወት የሆነ ሰው በሰው ቤት ላይ ድንጋይ አይወረውርምና ተረጋጉ እንላለን ።
ሳውዲ ላይ የሚሰራ የትኛውም ወንጀል ከወንጀልነት ሊወጣ አይችልም ። በወንጀልነቱ ይወገዛል ። ነገር ግን መሪዮችን ለማክፈር መንገድ አድርጎ መጠቀም የኸዋሪጆች አካሄድ ነውና ተጠንቀቁ ነው የሚባለው ። የሳውዲ መሪዮች ደማቸው አረንጓዴ ነው አይነኩም ለማለት አይደለም ። ከመሪዮች የሚሰራ ስህተት የሚታረምበት መንገድ መልእክተኛው ነግረውናል ። ሰለፎችም ተግብረው አሳይተውናል ። የመሪዮችን ስህተት በኹጥባ ፣ በሙሓደራ ፣ በጋዜጣ ፣ በመፅሄት ፣ በተለያዩ ሚዲያዎች ማሰራጨት የነብዩና የሶሓቦች መንገድ የሚከተሉ ሰዎች አካሄድ አይደለም ።
መጥፎን ነገር ስንለካ በሸሪዓ መለኪያ እንጂ በስሜታችን መሆን የለበትም ። የወንጀሎችን ክብደትና ቅለትም እንደዚሁ ይህን መሰረት አድርገን ነው ሁሉንም በልኩ ማውገዝ ያለብን ። ሳውዲ በሽርክ ጉዳይ አንገት እየቀላች ድግምተኞችንና መተተኞችን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣች ከተለያየ ሀገር መውሊድ ለማክበር የተሰበሰቡ ሱፍዮችን እየበተነችና አሰተባባዮችን በቁጥጥር ስር እያዋለች ማየት ያልቻሉት ወይም አይተው አላየንም የሚሉት በሀገራቸው ላይ ከሚሰራው አመፅና ወንጀል ሊወዳደር የማይችል ወንጀል ሳውዲ ላይ ሲሆን መሪዮች ለማክፈር መንገድ አድርጎ መጠቀም በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም ።
መሪዮች ሲያጠፉ በግል ይመከራሉ ዱዓእ ይደረግላቸዋል ። እንጂ በአደባባይ ከበሮ አይደለቅም ። ምክንያቱም የዚህ አይነቱ ተቃውሞ መሪዮቹ አፀፌታውን እንወስዳለን ብለው የበለጠ ጥፋት ሊመጣ ስለሚችልና መሪና ተመሪ መካከል ያለው መተማመን ጠፍቶ ሀገር ስለሚበጠበጥ ነው ። ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ወንጀል ማንም የትም ቢሰራው ወንጀል ነው ይጠላል ይወገዛል ። ነገር ግን የሚወገዝበት መንገድ ሸሪዓው ባዘዘው መልኩ መሆን አለበት ነው ትልቁ ነጥብ ።
በአሁኑ ጊዜ ሰዎች የሆነ ሰው ነፍሰጡር ሴትን ገደለ ፣ እናቱን ተገናኘ ፣ ከእህቱ ወለደ ፣ አስገድዶ ደፈረ ፣ ህፃን አረደ ሲባል ቢሰሙ ይሰቀጥጣቸዋል ይዘገንናቸዋል በጣም ያወግዙታል እንደ ጭራቅ ያዩታል ። ይህ ባልከፋ ነበር ። ከባድ ወንጀል ስለሆነ ሊወገዝ ይገባልና ነገር ግን እገሌ የሚባል ሰው የቀብር አፈር በጥብጦ ጠጣ ፣ ቀብር ጋር ሄዶ ጫማውን አውልቆ ስልኩን ዘግቶ እያለቀሰ የሞተውን ሰው እርዱኝ ድረሱልኝ አለ ፣ ሌላኛው ለጂኒ አርዶ ደሙን ጠጣ ፣ ሌላኛው ልጅ ፍለጋ ጠንቋይ ቤት ሄደ ቢባሉ ምንም አይመስላቸውም ። ይህ ሊስተካከል ይገባል ሙስሊሞች በሽርክና በቀባባድ ወንጀሎች መካከል ያለውን ልዩነት እንዲያውቁ ማስተማር ያስፈልጋል ።
አላህ በሱ ላይ ማጋራትን በፍፁም አልምርም ሲል ከሽርክ ውጪ ያሉ ወንጀሎችን ለሻው ሰው እንደሚምር ነግሮናል ። ሽርክ ስራን በሙሉ አበላሽቶ የዘላለማዊ ጀሀነም ባለቤት ሲያደርግ ከባባድ ወንጀሎች ግን አላህ ለሻው ሰው የሚምር ሲሆን ከቀጣውም በወንጀሉ ልክ ተቀጥቶ ከእሳት እንደሚወጣና የጀነት እንደሚሆን ኢስላም ያረጋግጣል ።
ታዲያ ግብፅ ውስጥ ያለው የቀብሮች አምልኮ ሳውዲ ውስጥ ከተሰራው የሴቶች ተራቁቶ መዝፈን ጋር ሲነፃፀር የሰማይና የምድር ያክል ልዩነት አለው ። ነገር ግን ሁሉም ወንጀሎች በመሆናቸው ይወገዛሉ ይሁን እንጂ አይገናኙም ።

https://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

08 Dec, 06:43


🔹  ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም

    የፊታችን እሁድ ታሕሳስ 6/2017 በእነሞር ወረዳ ጉንችሬ ክ/ከተማ ጉንችሬ ማዞሪያ ዑመር መስጂድ ላይ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኃል ።
    ተጋባዥ እንግዶች
1ኛ – ሸይኽ ዐ/ሐሚድ
2ኛ – ወንድማችሁ ባሕሩ ተካ
3ኛ – ኡስታዝ ሱደይስ

    ፕሮግራሙ የሚጀመረው አላህ ካለ ጠዋት 2 : 30 ይሆናል ።
   
https://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

06 Dec, 04:59


🔸حقيقة منهج التمييع من غير إفراط ولا تفريط🔸

للشيخ العلامة المحدث
ربيع بن هادي المدخلي-حفظه الله-

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

06 Dec, 03:18


🟢መጅሊሳችሁን ገምግሙት

በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ መጅሊስ የቋቋማችሁ ፣ የምትመሩት ባለስልጣናቱ ፣ አባላቱ ፣ አጋሮቹ እና ደጋፊዎቹ ሁሉ : መጅሊሳችሁ ከሚስተዋሉበት ጥፋቶች ውስጥ:-

1⃣ሰለፊያን ቀብሮ ሱፊያን አክብሮ ለመንገስ የቆረጠ መጅሊስ

በተደጋጋሚ የመጅሊሳችሁ መሪዎችና ተቀጣሪዎች የነቢያት ፣ የሰሃቦች እና የዑለማዎች መንገድ የሆነውን የሰለፊያን ደዕዋ ለማጥፋት ቆርጠው መነሳታቸውን በግልፅ አውጀዋል:: ተቋማቸውም በተግባርም የሚችለውን ሁሉ እየጣረ ነው::የተዊሂድ ደእዋ ይከለክላል ፣ ቂርኣት ያግዳል ፣ ሀቅ ተናጋሪ ኢማሞችን እና ኡስታዞችን  ያባርራል እንዳይንቀሳቀሱ ያግዳል:: ይባስ ብሎም ለእስርና እንግልት አሳልፎ ይሰጣል :: በአላህ ይሁንብኝ ባጢል ሀቅን አያጠፋም:: ሱፊያ እና ድምሮቹ ፊርቃዎች ልብ ወለድ  ሲሆኑ ሰለፊያ ግን የአላህ ዲን ነውና የበላዓይነቱ የፀና ነው❗️
ነቢዩ (ﷺ) እንደተናገሩት:
( ... وَتَفْتَرِقُ أُمَّتِي عَلَى ثَلَاثٍ وَسَبْعِينَ مِلَّةً كُلُّهُمْ فِي النَّارِ إِلَّا مِلَّةً وَاحِدَةً ، قَالُوا : وَمَنْ هِيَ يَا رَسُولَ اللَّهِ ؟ قَالَ : مَا أَنَا عَلَيْهِ وَأَصْحَابِي )
(ህዝቦቼ ወደ ሰባ ሶስት መንገዶች ይላያያሉ:: አንዲት መንገድ ብቻ ስትቀር : ሁላቸውም የእሳት ናቸው:: ሰሃቦችም አሉ " ማነች እርሷ ያ ረሱለላህ ?"
አሉ : እኔና ባልደረቦቼ ያለንበት መንገድ::)

2⃣መውሊድን አድምቆ አክባሪ መጅሊስ
የሺርኮች እና ቢድዓዎች መናኸሪያ የሆነውን መውሊድን በድፍረትና በተደጋጋሚ ደምቆ እንዲከበር የሚሰራ መጅሊስ መሆኑን አሳያችሁ::
ነቢዩ (ﷺ) እንደተናገሩት:
(...وشرًّ الأمورِ محدثاتُها وكلَّ بدعةٍ ضلالةٌ  وكلَّ ضلالةٍ في النارِ )
(...የነገሮች ክፉ ፈጠራዎች ናቸው::ሁሏም ቢድዓህ ጥመት ነች ::ሁሏም ጥመት እሳት ውስጥ ታስገባለች::)

3⃣ሁሉም ለስሜቱ የመሰለውን እንዲሰራ የሚፈቅድ መጅሊስ
የፈለገ መወሊድ እንዲያወጣ ፣ የፈለገ ጫት እንዲቅም ያልፈለገ ሳይቃወም ሊተው ወዘተ እያለ ሸሪኣ በመደንገግ ከአላህ ጋር የሚፎካከር ደፋር ተቋም ነው::
قوله تعالى: ﴿أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُمْ مِنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَنْ بِهِ اللَّهُ وَلَوْلا كَلِمَةُ الْفَصْلِ لَقُضِيَ بَيْنَهُمْ وَإِنَّ الظَّالِمِينَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ ﴾
4⃣ በሸሪኣም ሆነ በሀገር ህግ ባልተሰጠው ስልጣን የሚጨቁን አምባገነን መጅሊስ

በመሰረቱ መጂሊሳችሁ አንድ ተቋም እንጂ አሚር ወይም መንግስት አልነበረም:: ነገር ግን መስጂዶችን አስገድዶ በቁጥጥሩ እያስገባ ፣ መድረሳዎችን እያዘጋ ፣ የግለሰብ መስጂዶችን ጭምር በጉልበት እያዘዘ ፣ ትእዛዙን አልቀበል ያለን እያሸማቀቀ ፣ ኡስታዞችና ደረሶችን እያስደበደበ ፣ እና እያሳሰረ በግፍ የተሞላ ጥቁር ታሪክ እያስመዘገባላችሁ ነው::

በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ  አጋዦች ፣ አድናቂዎች እና አጋሮች ሆነው ሲያበቁ መሰል የመጅሊሱን ጥፋቶችና ጉዶችን "እኛ አልሰራነውም" የሚሉ አይጠፋም:: በጋራ የገነባችሁት ቤታችሁ መሆኑን አትርሱ::

የሞተው ወንድምሽ
የገደለው ባልሽ
ሀዘንሽ ቅጥ አጣ
ከቤትሽም አልወጣ

አላህን ፈርታችሁ ተመለሱ :: በምድር ላይም አታበላሹ:: ከግፈኞች ታሪክ ተማሩ::

  ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊያ)
http://t.me/Abuhemewiya

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

04 Dec, 06:01


ታላቅ የሙሀደራ ግብዣ በጀብዱ ቀበሌ
በጣም አጓጊ እና ተናፋቂ የዳዕዋ ዝግጅት በጣም ተናፋቂ በሆኑ ኡስታዞች
         👉ኡስታዝ አብዱልቃድር ሀሠን ከአዳማ
           👉ኡስታዝ አብዱልቃድር ከንድላ
ሌሎችም ኡስታዞች ይኖራሉ
የፊታችን ጁምዐ በቀን 27/3/2017
ከጠዋቱ 2:30 የሚጀምር ይሆናል
ቦታ በቀቤና ወረዳ ጀብዱ ቀበሌ ስለዚህ በ4ቱም አቅጣጫ ያላቹህ ቀበሌዎች ተጋብዛቹሀል

ከተማ ያላቹህ ወንድም እና እህቶች ቤተሰቦቻችንን በስልክ በመቀስቀስ እንረባረብ
ኢን ሻእ አላህ ተውሂድ የበላይ የሚሆንበትና ሺርክና ቢድዓ በመረጃ የሚደመሠሡበት ቀን ይሆናል
https://t.me/DarAnnedwa

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

04 Dec, 03:25


ወንድማችሁ (አል–ፈቂር ኢለሏህ) ሷድቅ አወል አልወራቢይ





https://t.me/sadikawol

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

03 Dec, 11:31


‏مقطع صوتي من حسين عبد الله

شخص يقول عن نفسه أنه سلفي و لكنه يخالط الحزبيين و لا يحذر منهم بل يحذر من الردود فما حكمه ؟

لفضيلة الشيخ المحدث
أحمد بن يحيى النجمي رحمه الله

#join ⤵️ telegram
https://t.me/HussinAssilty
https://t.me/HussinAssilty

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

03 Dec, 06:23


🟢እውነተኛ ረባኒይ ዓሊም

قال شيخ الإسلام ابن القيم رحمه الله: ((فإن السلف *مجمعون* على أن العالم لا يستحق أن *يسمى ربانيا* حتى
*يعرف الحق*
*ويعمل به*
*ويُعلمه* ))
📚زاد المعاد في هدي خير العباد (3/ 9)

ኢብኑልቀይም አሉ:
ሰለፎች ሁሉ የተስማሙበት እውነታ አንድ ዓሊም ረባኒይ (ማህበረሰቡን በዲን የሚንከባከብ) ተብሎ ሊጠራ አይገባውም ሶስት ነገሮች ሲያሟላ እንጂ:
እውነትን (ሀቅን) ሲያውቅ ፣ በእርሱም ሲሰራበትና ሲያስተምረው ነው::

https://t.me/Menhaj_Alwadih

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

02 Dec, 06:02


ፈትዋ

🟢 ለሴት ልጅ ያለ ወሊይ ኒካህ (ጋብቻ) መመስረት ብይኑ!!

🔊አሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አልለተሚይ አላህ ይጠቃቸው።

https://t.me/Mustefatemam

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

02 Dec, 05:35


🔷 የጭፍን ተከታይነት ሙርከኛ አትሁን !


قال العلامة المحدث محمد بن علي آدم
الإثيوبي - رحمه الله -:

" فيا أيُّها العاقل اللبيب لا تكن أسير التقليد، فإنه حُجّة البليد، وملجأ العنيد، بل كنْ مع الحقِّ، ودُرْ معه حيثما دار؛ تنجُ من مخازي دار البَوارِ، أعاذنا الله منها الرّحيم الغفّار ".

        البحر المحيط الثجاج (1/418)

    🔷  ታላቁ የሐዲስ ሊቅ ኢትዮዽያዊ ዓሊም ሽይኽ ሙሐመድ አሊ ኣደም – ረሒመሁላሁ– እንዲህ ይላሉ : –

" አንተ የአቅል ባልተቤት ጮሌ ሆይ የጭፍን ተከታዩነት ሙርኮኛ አትሁን ።
ጭፍን ተከታይነት የቂሎች መረጃ ነው ።
የእንቢተኛ መሸሸጊያ ነው ።
ይልቁንም ከሐቅ ጋር ሁን ።
የትም ቢዞር ከሱ ጋር ዙር ።
ከመጥፈያው ሀገር ውርደት ትድናለህ ።
አላህ አዛኙና መሓሪው ከሷ ይጠብቀን "።


https://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

01 Dec, 14:52


#አስፈላጊ_ኪታብ
📖
📖📖📖📖

🔎 የኪታቡ ርዕስ፦ ➷➴➷
📚  حُكْمُ التَّصْوِيرِ وَالفِيدِيو.
📚 «የቀረፃ እና ተንቀሳቃሽ ምስል ፍርድ»

📝 ዝግጅት፦ ሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ አላህ ይጠብቃቸው

📷🤳 በፎቶ እና ቪድዮ ዙሪያ መሰረታዊ እውቀት የሚገኝበት ወሳኝ ስራ ነው።

👌ጉዳዩ በዘመናችን ያለ እና ልናውቀው የሚገባ በመሆኑ በትኩረት አንብቡት


👉 በአግባቡ አንብበን ለመረዳት አንችልም በማለት መሳቀቅ የለም! ምክንያቱም ሸይኹ ራሳቸው በቅርቡ በደርስ መልክ ያቀርቡታል። ማስታወቂያውን ጠብቁ!

➷➷➷➷➷
https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha/10970

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

01 Dec, 11:51


https://t.me/medresetulislah?livestream

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

30 Nov, 15:20


ቀጥታ ስርጭት
      >> በአካል መታደም ላልቻሉ


ቅዳሜና እሁድ
👉 ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

ኮርሱ የሚሰጥበት ኪታብ
الأربعون اللتمية في العقائد والمناهج السلفية
"አል አርበዑን አልለተሚየህ" 
አዘጋጅ:- ሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አል-ለተሚይ (ሀፊዘሁላህ)

ኮርስ ሰጪ:- የኪታቡ አዘጋጅ የሆኑት ሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አል-ለተሚይ (ሀፊዘሁላህ) ናቸው

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

30 Nov, 11:24


ተጀምሯል።



https://t.me/medresetulislah?livestream

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

30 Nov, 05:29


القول المستجاد في كشف مجازفات الحداد.
لفضيلة الشيخ الدكتور محمد أمان الجامي رحمه الله تعالى.

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

30 Nov, 03:15


https://t.me/medresetulislah?livestream

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

28 Nov, 09:11


‏حفظ الله تعالى ورعاه الشيخ العلامة ‎ربيع بن هادي المدخلي

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

25 Nov, 06:25


በኡስታዝ ባህሩ ተካ አቡ ዑበይዳህ ተቀርተው ከተጠናቀቁ ደርሶች መካከል በAudioና በApplication እና የተጠናቀቁ የቁርኣን ምዕራፎች ተፍሲርን በሚከተሉት ሊንኮች ያገኛሉ። ለሌሎችም ሸር በማድረግ ላልደረሳቸው አድርሱ!!!


❶ኛ 📚 የረውደቱል አንዋር
📚 روضة الأنوار في سيرة النبي المختار

ከክፍል 01–86


ከክፍል 1 ጀምሮ
➴➘➷➴➘⬇️↙️
https://t.me/bahirutekadurus/6


📚 ሉምአቱል ኢዕቲቃድ
📚 متن لمعة الاعتقاد.
ከክፍል 01–08

ከክፍል 1 ጀምሮ
➴➘➷➴➘⬇️↙️
https://t.me/bahirutekadurus/147

ኛ ሸርህ አልዓቂደቱል ዋሲጢያህ 
📚 شرح العقيدة الواسطية.

ከክፍል 01– 67

ከክፍል 1 ጀምሮ
➴➘➷➴➘⬇️↙️
https://t.me/bahirutekadurus/159

📚 መትኑ ሰላሰቱል ኡሱል
📚 متن ثلاثة الأصول.


ከክፍል 01—39

ከክፍል 1 ጀምሮ
➴➘➷➴➘⬇️↙️
https://t.me/bahirutekadurus/230

📚 ኪታቡ ተውሒድ
📚 كتاب التوحيد للشيخ محمد بن عبد الوهاب رحمه الله

ከክፍል 01 እስከ ክፍል 63

ከክፍል 1 ጀምሮ
➴➘➷➴➘⬇️↙️
https://t.me/bahirutekadurus/362

➏ኛ 📚 መትኑ ከሽፊ ሹቡሀት!
   📚 متـن كشـف الشبهـات


ከክፍል ❶ እስከ ⓰
↪️ ➴➷➴➷
https://t.me/bahirutekadurus/452

➐ኛ 📚 መትን አል-ኡሱሉ-ሲታህ!
📚 متـن
الأصول السّتة.

➘➘➘➘ pdf
https://t.me/bahirutekadurus/468

ከክፍል ❶ እስከ ➑
↪️ ➴➷➴➷
https://t.me/bahirutekadurus/469

📚 አል ኢርሻድ....
📚 الإرشاد إلى صحيح الاعتقاد والرد على أهل الشرك والإلحاد.

ከክፍል ❶~❶❶❽

📲 ➷➷➷➷
https://t.me/bahirutekadurus/610

      •┈┈┈┈•⊰✿❁✿⊱•┈┈┈•


📖 ቁርአን ትርጉም ማብራሪያ ❴ከበቀራህ-ማኢዳህ❵

📖 تَفْسِيرُ سُورَةِ آلفَاتِحَة.
📖 የሱረቱል ፋቲሃ ትርጉም


╭─••°─═•°•═─•••─╮
📖 ከክፍል  ❶~❸   📖
╰─••°─═•°•═─•••─╯

📲➘➘➘➘
https://t.me/bahirutekadurus/524

📖 تَفْسِيرُ سُورَةِ الْبَقَرَة.
📖 የሱረቱል በቀራህ ትርጉም


╭─••°─═•°•═─•••─╮
📖 ከክፍል ❶~➋➒ 📖
╰─••°─═•°•═─•••─╯

📲➘➘➘➘
https://t.me/bahirutekadurus/530

📖 تَفْسِيرُ سُورَة آل عِمْرَان
📖 የሱረቱል ኣል ዒምራን ትርጉም


╭─••°─═•°•═─•••─╮
📖 ከክፍል ❶~❶❺ 📖
╰─••°─═•°•═─•••─╯

📲➘➘➘➘
https://t.me/bahirutekadurus/560

                      
📖 تَفْسِيرُ سُورَة النِّسَاء
📖 የሱረቱ አን′ ኒሳእ ትርጉም

╭─••°─═•°•═─•••─╮
📖 ከክፍል ❶~❶❼ 📖
╰─••°─═•°•═─•••─╯

📲➘➘➘➘
https://t.me/bahirutekadurus/577


📖 تَفْسِيرُ سُورَة المَائِدَة
📖 የሱረቱ አል`ማኢዳህ ትርጉም

╭─••°─═•°•═─•••─╮
📖 ከክፍል ❶~❶❶ 📖
╰─••°─═•°•═─•••─╯

📲 ➷➷➷➷
https://t.me/bahirutekadurus/597

      •┈┈┈┈•⊰✿❁✿⊱•┈┈┈•

በ Application የተዘጋጁትን እንደሚከተለው ማግኘት ትችላላችሁ።

❶ኛ የነብያችን ﷺ የሕይወት ታሪክ ረውደቱል አንዋር #ያለኔት
 
➴➘➴➷➴➘➷
https://t.me/bahirutekadurus/277

❷ኛ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ #ያለኔት

  ➴➘➷➴➘➷➴➴
https://t.me/bahirutekadurus/297

➌ኛ ሉምዓቱል ኢዕቲቃድ በአፕልኬሽን #ያለኔት

➷➘➴➘➷➴➘
https://t.me/bahirutekadurus/299

    •┈┈┈┈•⊰✿❁✿⊱•┈┈┈•

♻️ «እነዚህ ናቸው ኢኽዋኖች» በሚል ርዕስ የተደረገ ተከታታይ ሙሐደራ

ከክፍል አንድ እስከ ሰባት
➷➴➘➷➴➘
https://t.me/bahirutekadurus/278

♻️የቪዲዮ ብይን በኢስላም” በሚል ርዕስ የተደረገ ተከታታይ ወሳኝ ትምህርት

ከክፍል አንድ እስከ አስር
➷➴➘➷➴➘➷➴➘
https://t.me/bahirutekadurus/287

♻️ በጉራጊኛ ቋንቋ በተለያዩ ርዕሶች የተደረጉ አርባ ሰባት ሙሐደራዎችን ከመጀመሪያው ጀምሮ በተከታታይ በቀጣዩ ሊንክ ታገኛላችሁ
ከመጀመሪያው ጀምሮ
➷➴➘➷➴➘➷➴➘
https://t.me/bahirutekadurus/300

❶ኛ ከጉራጊኛ ተካታታይ ሙሐደራዎች መካከል ❝ሒጃብሽን እህቴ❞ ከክፍል አንድ እስከ አራት

ከክፍል አንድ ጀምሮ ➴➘➷
https://t.me/bahirutekadurus/349

❷ኛ ከጉራጊኛ ተካታታይ ሙሐደራዎች መካከል ❝ለቅሶ በኢስላም❞ ከክፍል አንድ እስከ አምስት

ከክፍል አንድ ጀምሮ ➴➘➷
https://t.me/bahirutekadurus/355

❸ኛ ከጉራጊኛ ተካታታይ ሙሐደራዎች መካከል ❝ጋብቻ በኢስላም❞ ከክፍል 01 እስከ 04

ከክፍል አንድ ጀምሮ ➴➘➷
https://t.me/bahirutekadurus/428

❹ኛ በጉራጊኛ ከተደረጉት ተካታታይ ሙሐደራዎች መካከል ❝ሩቃ❞ በሚል ርዕስ የቀረበውን ከክፍል አንድ ጀምሮ እስከ ክፍል አምስት

ከክፍል አንድ ጀምሮ ➴➘➷
https://t.me/bahirutekadurus/434

❺ኛ በጉራጊኛ ቋንቋ ❝የአላህ ባሮች❞ በሚል ርዕስ የቀረበው ተከታታይ ሙሐደራ ከክፍል 1 ጀምሮ እስከ ክፍል 3

ከክፍል አንድ ጀምሮ ➴➘➷
https://t.me/bahirutekadurus/441

➡️ ጉራጊኛ ሙሐዶራዎች ስብስቦች በApplication

አፕሊኬሽኑን ለማግኘት ⬇️⬇️⬇️
https://t.me/bahirutekadurus/360

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

20 Nov, 20:21


🟢ማስጠንቀቂያ ለኢኽዋኖችና ለአጋሮቻቸው

በሀገራችን የኢኽዋን አንጃ መሪዎችና ተመሪዎች ብዙ የዲን መሰረቶችን እየናዱ ጉድ አስብለዋል:: ያሻቸውን ክልክል (ሀራም) ያሸቸውን የተፈቀደ (ሀላል) ሲያደርጉ ጭፍን ተከታዮችና አጋሮቻቸው ደንዝዘዋል::

🟢ጥያቄዎች
👉የሚከተሉትን የአላህን ንግግሮች አልተረዳችሁምን ?!

# يَقُولُ الله تَعَالَى﴿وَلا تَقُولُوا لِمَا تَصِفُ أَلْسِنَتُكُمُ الْكَذِبَ هَذَا حَلالٌ وَهَذَا حَرَامٌ لِتَفْتَرُوا عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ}
قال ابن كثير: "وَيَدْخُلُ فِي هَذَا كُلُّ مَنِ ابْتَدَعَ بِدْعَةً لَيْسَ لَهُ فِيهَا مُسْتَنَدٌ شَرْعِيٌّ،
أَوْ حَلَّلَ شَيْئًا مِمَّا حَرَّمَ اللَّهُ، أَوْ حَرَّمَ شَيْئًا مِمَّا أَبَاحَ اللَّهُ"

# { اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِنْ دُونِ اللَّهِ }

👉ጣጉት ምን እንደሆነ ቀጣዪን የኢብኑ ቀይምን ገለፃ አታውቁትምን ?!
-: (وَالطَّوَاغِيتُ كَثِيرُة، وَرُؤُوسُهُمْ خَمْسَةٌ: إِبْلِيسُ لَعَنَهُ الله، وَمَنْ عُبِدَ وَهُوَ رَاضٍ، وَمَنْ دَعَا النَّاسَ إِلَى عِبَادَةِ نَفْسِهِ، وَمَنْ ادَّعَى شَيْئًا مِنْ عِلْمِ الْغَيْبِ، وَمَنْ حَكَمَ بِغَيْرِ مَا أَنْزَلَ الله).

👉እወቁ ተጠንቀቁም: ህግ አውጪው አላህ እንጂ የመጅሊስ መሪዎች አይደሉም::
👉ሁሉም የመሰለውን ሳይሆን አላህ የደነገገውን ዲን ይከተል ::

http://t.me/Abuhemewiya

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

18 Nov, 09:21


📌አዲስ ሙሓደራ

ርዕስ {ُالدِّينُ النَّصِيْحَة}

(ዲን መመካከር ነው)

🎙ኡስታዝ አቡ ሀመዊያ ሸምሱ ጉልታ ሀፊዘሁሏህ

🕌 በአዳማ በኢብኑ ተይሚያ መስጂድ የተደረገ አሳሳቢ ሙሓደራ ነው

📅 በቀን 08/03/2017

https://t.me/abuabdurahmen

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

17 Nov, 05:17


{ففِرُّوا إلى اللهِ إنّي لكم مِنْهُ نذِيرٌ مُبِين}

قال ابن عثيمين رحمه الله:

"لا ينقذك من عذاب الله إلا أن تقوم بطاعة الله".

تفسير سورة الذاريات ص١٦٢

وجاء في أذكار النوم عن النبي ﷺ: (لا مَلجَأَ ولا مَنْجَى منْكَ إلا إليك) متفَقٌ عليه.
يُنظر: فقه الأدعية والأذكار للبدر ٣ /٦٤

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

16 Nov, 17:13


🟢እውቀት የሀቅ እና የሀሰት አራማጆችን ለመለየት

🎙️. قال العلامة محمد أمان الجامي -رحمة الله-:

*‏" لا تستطيع أن تفرق بين دعاة الحق ودعاة الباطل إلا بالعلم ، وإذا فقدت العلم التبس عليك الحق ومن التبس عليه الحق ضاع "*

📚. شرح قرة عيون الموحدين  ٣٦
https://t.me/Menhaj_Alwadih

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

15 Nov, 07:50


🟢በአንድ ድንጋይ ሁለት ሂዝቢይ

ከላይ ያለውን ድምፅ ሙመይዑ ኢብኑ ሙነወር
"ሐጃዊራ እና ሸይኽ ረቢዕ" ብሎ በለቀቀበት፡
እነ አብራር ሸይኽ ረቢዕን አስመልክቶ  ያንፀባረቁትን ሂዝቢያ ሲኮንን እንዲህ ብሎ  ነበር:"በአሁኑ ሰዓት የሐጁሪ ጭፍራዎች አጥብቀው ከሚኮንኗቸው ዑለማዎች ውስጥ ሸይኽ ረቢዕ አንዱ ናቸው። የውግዘታቸው ቀዳሚ ምክንያት ሸይኽ ረቢዕ የሕያ አልሐጁሪን ክፉኛ ማብጠልጠላቸው ነው። ይሁን እንጂ ለጀምዒያ ጉዳይ ሲሆን የኚህን ክፉኛ የሚያብጠለጥሏቸውን ሸይኽ ንግግር ከነ ኢብኑ ባዝ፣ ከነ ኢብኑ ዑሠይሚን እና መሰል ብዙሃን ዑለማኦች አቋም በተለየ ያስጮሃሉ። ለምን? የሳቸው ንግግር ለተብዲዕ ጥማታቸው ግብአት ይሆነናል ብለው ስለሚያስቡ። ደግሞኮ ንግግራቸውን በልኩ በተጠቀሙ። ..."

በአሁኑ ሰዓት ጠማማዎቹ ሙመይዓዎች ሸይኽ ረቢዕን እና መሰል የጀርህ ወተዕዲል ዑለሞችን የሚያጣጥሉበት ሚስጥር የመሪዎቻቸውን ጥመት አበጥረው በመረጃ ስላጋለጡ የተሀዙቡ ተቆርቋሪነት ይዟቸው ነው። እነ ኢሊያስና  ኢብኑ ሙነወር ራሱ፣መሰሎቻቸውም በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚተፋት ይሀው ለሙብተዲኦች  ያላቸውን ጥብቅና ነው። አቅምና አቋም ያለው ሸይኹ የለመረጃ የተቹትን ሰው በፍትህ ያምጣ።አልቻሉም አይችሉም።
ሚዛናዊ መሳይ የሙብተዲዕ ጠበቆች ሙግት ግን  ከንቱ ተሀዙብ መሆኑ ከተጋለጠ ውሎ አድሯል።
በዘመናችን ለሰለፊየህ ዘብ የቆሙ ፣ ለሂዝቢያ የእግር እሳት የሆኑ ታጋይ ኡለማዎችን የሚያንቋሸሽና የሚያማቃልል ሁሉ ማንነቱን እያጋለጠ እንደሆነ ልብ ይሏል።
قال أبو حاتم الرازي:
«علامةُ أهل البدع الوقيعةُ في أهل الأثر،...»[عقيدة السلف (١٠٥)]
"የቢድዐህ ሰዎች ምልክት ሀዲስና የሰለፎችን ፈለግ የሚከተሉትን (አህሉልአሰርን) ማንቋሸሽ ነው።"
https://t.me/Abuhemewiya/3609

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

13 Nov, 04:13


  ለሰርግ ብሎ ግሩፕ መክፈት

       አላህ ለሙስሊሞች ለደስታቸውም ለሐዘናቸውም ገደብ አድርጓል ። ሐዘን ሲገጥማቸው ወደ አላህ እንዲመለሱ ነገሮች ሁሉ የሚሆኑት በሱ ፍላጎትና ትእዛዝ እንደሆነ አውቀው ለሱ እጅ መስጠት እንዳለባቸው መክሯል ።
      በደስታቸው ጊዜ ደግሞ ደስታቸው እሱ በፈቀደው መንገድ እሱን በሚያስወድድ ሁኔታ መሆን ይኖርበታል ። ያ የደስታቸው ምንጭ የአላህ ኒዕማ ውጤት መሆኑን አውቀው ኒዕማውን በማስታወስ የኒዕማውን ባለቤት በማመስገን እሱ በሚወደውና በሚፈቅደው መልኩ መሆን አለበት እንጂ ሙስሊሞች ደስታቸውን ሲገልፁ ከአላህ ጋር በሚያራርቅ ሁኔታ መሆን የለበትም ።
     አንድ ሰው አላህ ዘር ሰጥቶት በሰላም ለወግ ማእረግ ሲበቃ ከምንም በላይ አላህን ሊያመሰግን ይገባል ። ልጅ አድርሶ ለትዳር በቅቶ ማየት የሚያስደስት ነገር ነው ። ታዲያ ለዚህ ያበቃንን አላህ በዛን ቀን ማመስገን እንጂ ማመፅ አይገባንም ።
      በኢስላም አንድ ወንድ ሲያገባ መደገስ የተወደደ ሱና ነው ። ይህ ታዲያ ወንዱ ቤት ነው ሱና ነው የሚባለው እንጂ ሴቷ ቤት አይደለም ። ምናልባት ሴቷ ቤት ሙባሕ ነው የሚሆነው ። በሰርጉ ቀን ሰርጉን ኢዕላን ማድርግ ( ማሳወቅ) አስፈላጊ ነው ። ኢዕላን የሚደረገው ሸሪዓውን በማይኻልፉ ሰርግ መሆኑ በሚታወቅባቸው ነገሮች ነው ። ከዚህ ውስጥ የሴቶች ከበሮ እየመቱ መጫወት ይገኝበታል ። ሴቶች መጫወት የሚችሉት በሙሽራዋ ቤትና በሙሽራው ቤት ሲሆን ከወንድ ተገልለው ለብቻቸው ሆነው ነው ። ሰርግ ነው ብሎ ዘፈንም ሆነ ነሺዳ መክፈት አይፈቀድም ። አንዳንድ አካባቢዮች ላይ የሚሰሙ አላስፈላጊ ግጥሞችን መጠንቀቅም ያስፈልጋል ።
      ሴቶች መጫወት ይችላሉ ሲባል ከላይ እንደተገለፀው በሙሽራዋና ሙሽራው ቤት የተጠሩ ቤተሰቦችና የልጅቷ ጓደኞች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዮችን ነው የሚያካትተው ።
      በኒካሕ ሰበብ ግሩፕ ከፍቶ ከተለያየ ሀገር በግሩፑ ተገናኝቶ ሰርግ ነው እንጨፍራለን ማለት ሸሪዓም ዐቅልም የማይቀበለው አዲስ መጤ ተግባር ነው ። ምክንያቱም በሸሪዓ ሙሽራዋ የጠራቻቸው ወይም ቤተሰብ የጠራቸው ሴቶች እዛው ተገኝተው መጫወት ይችላሉ ነው የተባለው እንጂ ሙሽራዋ ግሩፕ ከፍታ ግሩፕ ላይ ተሰባሰቡ ትበል አይደለም ። ከዚህ የሚገርመው ደግሞ ከሙሽራዋ ውጪ የሆኑ ሴቶች ለእገሊት ሰርግ እንጨፍር ብለው ግሩፕ ከፍተው ተሰባሰቡ ማለታቸው ነው ። የት ሆነው ነው የሚጨፍሩት ። ጅዳ ላለ ሰርግ ኩዌት ፣ በሕሬን ፣ ቤሩት ፣ ሪያድ ፣ መዲና ፣ ከዚህ አልፎ አሜሪካና ካናዳ ሆነው ነው ? ማን ቤት ያለው ጭፈራ ነው ለሰርጉ ተጠርተው ነው የምንለው ። በግሩፕ ላይ መጨፈር ማለት በእነዚህ ሀገሮች ላይ ያሉት ጭፈራዎች በኦንላየን ይተላለፋሉ ማለት ነው ። የዚህ ትልቁ መፍሰዳ እዚ ግሩፕ ውስጥ ካፊር ሴት ገብታ ጭፈራውን በኦንላየን ለወንዶች ልታሰማ ትችላለች ። አሌያም ሙስሊም ሆናም በስም ብቻ የሆነች ለተሰበሰቡ ወንዶች እንደመዝናኛ ልታቀርበው ትችላለች ። ይሄ በግሩፑ ላይ ወንዶች ከሌሉ ነው ። ነገር ግን በሴት ስም ወንዶችም ሊገቡ ይችላሉ ።
     በየትኛውም ዘመን የነበሩ ሰለፎች እኛ ዘንድ ሰርግ ስላለ እናንተ በያላችሁበት ተሰባስባችሁ ጨፍሩ አላሉም ። አሁን ባለንበትም ዘመን ኢስላምን ተረድተናል የሚሉ ሙስሊሞችም ሰርግ ሲኖራቸው ዘመድ አዝማድ ጓደኛ ጎረቤት ጠርተው ሴቶች ከወንዶች ርቀው እንዲጫወቱ ያደርጋሉ እንጂ በዐለም ላይ ያላችሁ ተሰባስባችሁ በያላችሁበት ጨፍሩልን አይሉም ። እንደርሱ አይደለም ካላችሁ ግሩፕ ከፍቶ መጨፈር የሚባል ነገር የለም ። ግሩፕ ከፍቶ አንድ ላይ መጮህ ካልሆነ በስተቀር ። በመሆኑም የዚህ አይነቱ ተግባር በየትኛውም መመዘኛ ወደ ኢስላም ማስጠጋት አይቻልም ። ኢስላም የሚያውቀው ስላልሆነ ። ይልቁንም ከላይ ለመግለፅ እንደተመኮረው ለብዙ ወንጀል በር ከፋች ነው የሚሆነው ።
     ስለዚህ እህቶች በያላችሁበት አንዷ ጓደኛችሁ ስታገባ እሷ ጋር ሄዳችሁ መጫወት ይናርባችኋል እንጂ ለእንደዚህ አይነት ፈሳድ በር እንዳትከፍቱ እላለሁ ።

          ወላሁ አዕለም ።

https://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

12 Nov, 14:08


🔵ዛሬ ምሽት

ዘወትር ሰኞ እና ማከሰኞ  ከመግሪብ እስከ ኢሻዕ

የሚሰጠው ኪታቡ ፡- አልፊቅሁል አልሙየሰር  

ደርሱን የሚሰጠው አቡ ሐመዊያ ሸምሱ ጉልታ ሐፊዘሁሏህ


በሰአቱ የሚቀጥል ይሆናል።


🕌 
አል ኢስላሕ መድረሳ


https://t.me/medresetulislah

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

12 Nov, 10:53


👉 ቀን ጥሎኝ ብታየኝ
­¯¯¯¯¯¯---_

👌 አንዳንድ ንግግሮች ባለቤታቸው ቦታ ሳይሰጣቸው ይናገራቸውና ዱንያውንም አኼራውንም የሚያበላሹ ይሆናሉ። ከእንደነዚህ አይነት ንግግሮች ውስጥ ምን ታረገው ቀን ጥሎኝ አይተኸኝ የሚለው ሲሆን ሀብታም የነበረ ወይም በጀግንነቱ የሚታወቅ የነበረ ወይም ትልቅ ስልጣን የነበረውና በኋላ ሁኔታዎች የተቀየረበት ሰው የሚናገረው ይገኝበታል። እንደዚሁ አንዳንድ እህቶች በተለይ ዐረብ ሀገር ያሉ ስራ ፈተው ለብዙ ጊዜ በመቀመጥ ሲቸገሩና ሲከሱ ሲጎሳቆሉ ይህን ንግግር ይጠቀማሉ።

በእነዚህና በሌሎችም ምክንያቶች የዚህን አይነት ንግግር መናገር ወንጀሉ በጣም የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ከዐቂዳ ጋር የሚገናኝ በመሆኑ ነው።

በመጀመሪያ አንድ ሙስሊም የሚናገረውን ንግግር አስቦና የሚያመጣውን ጥቅምና ጉዳት አመዛዝኖ መናግር ነው ያለበት። የአላህ መልእክተኛ ሳያመዛዝን የሚናገር ሰው ንግግሩ የሚያመጣውን መዘዝ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦
عَنْ أَبي هُرَيْرَةَ أَنَّهُ سَمِعَ النَّبيَّ – ﷺ – يَقُولُ : "إنَّ الْعَبْد لَيَتَكَلَّمُ بِالكَلِمةِ مَا يَتَبيَّنُ فيهَا يَزِلُّ بهَا إِلَى النَّارِ أبْعَدَ مِمَّا بيْنَ المشْرِقِ والمغْرِبِ".
📚 متفقٌ عليهِ
"አንድ ሰው አንዲትን ንግግር የሚያስከትለውን ሳያውቅ ይናገርና ከፀሀይ መውጫ እስከ ፀሀይ መግቢያ ርቀት ወዳለው እሳት ይወድቃል።"

🏝 ተመልከቱ እንደቀልድ በተናከርነው አንድ ንግግር የሚመጣው ውጤት። ቀን ጥሎኝ የሚለው ንግግር ደግሞ በጣም አደገኛና ዱንያንም አኼራንም የሚያጠፋ ነው። አንድ ሰው ይህን ንግግር ሲናገር ቀን መጣልና ማንሳት (ማበልፀግና ማደህየት) ይችላል የሚል እምነት ኖሮት ከሆነ ይከፍራል ከእስልምናም ይወጣል። ነገር ግን ይህ እምነት ሳይኖረው እንደቀልድ ከሆነ የተናገረው ትንሹ ሽርክ ነው። ይህ ማለት ከከባባድ ወንጀሎች ይመደባል። ምክንያቱም ቃሉ ቀን መጣል ይችላል የሚል መልእክት ስለያዘ።

🔦 በመሆኑም ሙስሊም የሆነ ሰው ከመናገሩ በፊት ስለሚናገረው ነገር ማወቅና ማመዛዘን ይኖርበታል። ከዚህ በተጨማሪ ቀኑን በመኮነን መልኩ ከሆነ ሌላ ጥፋት ነው። ምክንያቱም ቀን ምንም ነገር ማድረግ አይችልም። የአላህ ስራ የሚያርፍበት ብቻ ነው። ይህ ከሆነ የምንኮንነው አላህን ነው ማለት ነው። ቀን ይነጋል ይመሻል የሚያመሸውና የሚያነጋው አላህ ነው። ለዚህ ነው ዘመንን አትስደቡ የተባለው። ምክንያቱም ዘመን የአላህ ስራ ማረፊያ ከሆነና በቀኑ ውስጥ የሚከሰቱ ነገሮች የሚያስከስታቸው እሱ ከሆነ የምንሰድበው አላህን ነው ማለት ነው!!! ይሄ ደግሞ ዱንያንም አኼራንም የሚያጠፋ ወንጀል ነው።

🔍 አንድ ሰው በየትኛውም ጊዜ ምንም ነገር ቢደርስበት ይህ ነገር በአላህ ውሳኔ ነው የደረሰው ብሎ ማመን አለበት። ይህ በቀደር ማመን ይባላል። በቀደር ማመን ደግሞ የኢማናችን አስኳል ነው። በሌላ አባባል አሁንም ቀን ጥሎኝ የሚለው ንግግር ከቀደር ጋር ያጋጨናል ማለት ነው። ምክንያቱም በአላህ ውሳኔ ያመነ ሰው በማንም በምንም አያማርም። ይልቁንም አላህ ወስኖ ያሻውን ሰራ ነው የሚለው። በዚህም ወደ አላህ ይቃረባል የአላህንም ውዴታ ያገኛል። በቀን ማማረር ትርፉ ኪሳራ ነው።

👉 ሌላው መከራም ይሁን ችግር የሚያገኘን በሰራነው ወንጀል መሆኑን ማመን ይኖርብናል። የበሽታና የርዝቅ እጥረት መንስኤ የራሳችን ወንጀል ነው። በተለይ ዐረብ ሀገር ያላችሁ እህቶች መጀመሪያ ከሀገር ያለ መሕረም ስትወጡ ጀምሮ ወንጀል ላይ ወድቃችኋል። እዛ ሆናችሁ አላህን ፈርታችሁ ላለፈው ተፀፅታችሁ ወደ አላህ መቅረብ ይኖርባችኋል። በተለይ ኢጃዛ በምትወጡ ጊዜ አላህ ካዘነላት ውጪ አብዛኛዎች እህቶች ወንጀል ላይ ነው የሚዘፈቁት። ከአጅ ነብይ ወንድ ጋር አብረው ነው የሚሆኑት የዝሙትና የተለያዩ ወንጀል አይነቶች ይፈፀማሉ።

▷ አላህን ፈርተናል የሚሉ እህቶችም ቢሆን በራሳቸው ቤት መከራየት ስለማይችሉ አንድ ወንድ ከ20 – 30 ሴቶችን ይሰበስብና ያችንም እቺንም አገባሻለሁ እያለ እየበዘበዘ አላህን ካመፀ በኋላ እነርሱንም አይናችሁ ላፈር ይላል። በአብዛኛው እንደነዚህ አይነት ወንዶች የሚፈልጉዋቸውን እህቶች በተለያየ የኢጃዛ ጊዜ እንዲመጡ በማድረግ ነው የሚፈልጉትን የሚሰሩት። ያቺም ከኔ ጋር ነው ትላለች እቺም ከኔ ጋር ነው ትላለች እሱ ግን ከማናቸውም ጋር አይደለም ከገንዘባቸውና ከሸህዋው ጋር ነው። የዚህ ወንጀል መጨረሻ እህቶችን ቀን ጥሎኝ ነው ብለው ሌላ ወንጀል ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል።

ለማንኛውም አላህን ፈርተን ቀንን ከመተቸትና አላህን ከሚያስቆጣ ወንጀል እንውጣ።

https://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

11 Nov, 03:24


https://t.me/medresetulislah?livestream

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

10 Nov, 11:29


ታላቅ_የሙሃደራ_ግብዣ በአዳማ ከተማ
==========================

በጣም አጓጊ እና ተናፋቂው የሰለፊዮች የደዕዋ ድግስ በጣም ተናፋቂ በሆኑ ኡስታዞች ለየት ባለ እና በማረ መልኩ ተደግሶ ይጠብቀናል


🪑ተጋባዥ እንግዶች

1ኛ  ተወዳጁ ኡስታዝ ባሕሩ ተካ ((ሀፊዘሁሏህ)

2 ተወዳጁ ኡስታዝ አቡ ሀመዊየህ ሸምሱ ጉልታ ( ሀፊዘሁሏህ)

3ኛ አቡ አብዲረህማን አብዱልቃዲር ( ሀፊዘሁሏህ)

ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ይጠበቃሉ


    📅  የፊታችን እሁድ 08/04/2017

🕌ቦታ አዳማ 01 ቀበሌ በኢብኑ ተይሚያ መስጂድ

ሰዓት ከ 🕰2:30 ጀምሮ እስከ ዙህር

https://t.me/abuabdurahmen

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

07 Nov, 03:21


🟢ሙብተዲዕ
قال الامام البربهاري
-رحمه الله-:

" ومن خالف الكتاب والسنة فهو صاحب بدعة وإن كان كثير العلم والكتب ".

  📚شرح السنة ١٠٤
አል ኢማም አልበርበሃሪይ አሉ:
"ባለ ብዙ እውቀትና ኪታቦች ባልተቤት ቢሆን እንኳ: ቁርኣን እና ሱናን የተፃረረ ሁሉ እርሱ የቢድዐህ ባልተቤት ነው::"

https://t.me/Menhaj_Alwadih

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

06 Nov, 08:03


የኸይር ስራ ፈላጊ እህት ወንድሞቻችን ሆይ፦

ሸሪአችንን "በዚህች ምድር የወንድሙን ወይም የእህቱን እንዲሁም የእህቷን ወይም የወንድሟን ጭንቀት ያስወገደ/ች አላህ በአኸይራህ (በመጪው አለም) የሱን/ሷን ጭንቀት ያስወግድለታል" በማለት በኸይር ስራ አነሳስቷል። በመቀጠል ወደ መልካም ስራ እናመላክታችሁ። እሱም አንድ እህታችን የወንድም እህቶቿን እገዛ ትፈልጋለች።

እህታችን አጢባ ነጋሽ ትባላለች። በወራቤ ከተማ 02 ቀበሌ ነዋሪ ስትሆን በደረሰባት የልብ ህመም የወራቤ ኮምፕሬሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ወደ ህንድ ሀገር ሄዳ እንዲትታከም ፅፎላታል። ለህክምናውም 2,000,000 [ሁለት ሚሊዮን ብር] ያስፈልጋል ተብላለች። ነገር ግን በግል ህክምናውን ለመከታተል አቅም የሌላት በመሆኑ ከሀያሉ ጌታ ቀጥሎ የናንተን ወንድም እህቶቿን ድጋፍ ትፈልጋለች።

ይህች እህታችን ለበርካታ ጊዚያት በበሽታ እየተሰቃየች መሆኑን ተደጋግሞ እየሰማን ነው። አላህ ሁላችነንም ቤተሰቦቻችነንም እኛንም ከዱንያም ከአኸይራም ችግር ይጠብቀን!  በመሆኑም አላህ የመዋረጃው ቀን ጭንቀት ጊዜ ዘወር እንዲያደርገለት የፈለገ በተቻለው ይርዳት በማለት መልእክቱን ለማላስተላለፍ እንወዳለን።

❝ አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጐቹም ሰዎች እንድኾን ወደ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ፡፡ ❞

በዚህ መልካም ስራ መሳተፍ የምትፈልጉ በሙሉ የሚከተሉትን አካውንቶች መጠቀም ትችላላችሁ

የአካውንት ቁጥር
Commercial Bank of Ethiopia
1000036881589

Zamzam Bank
0050265620101

Awash Bank
01425562027700

የአካውንት ስም Hatiba Nagash Aman

ተጨማሪ መረጃ
📱 +251912011954
           ሐጢባ ነጋሽ አማን

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

04 Nov, 13:27




                 🔻الفرق بين🔻
        🔸 ([ الكافر والمشرك ]) 🔸

        🎙سماحة الشيخ العلامة🎙
          محمد أمان بن علي الجامي
               رحمه اللّٰه تعالىٰ

        📼 مدة المقطع: 📽 ٠٠:٥٨

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

02 Nov, 17:51


በሀበሻዊዩ ታላቅ ዓሊም

[لا إله إلا الله، كلمة التوحيد]
የተውሒድ ቃሏ «ላኢላሃ ኢለሏህ»

🎙 الشيخ محمد أمان الجامي رحمه الله.
🎙 በሸይኽ ሙሐመድ አማን አል-ጃሚ አላህ ይዘንላቸው!


🏝 በ«ላኢላሃ ኢለሏህ» ዙሪያ እንዲሁም ተውሒድና ሽርክን በተመለከተ ጥሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
👏 አረበኛቸው በጣም ገር ነው ሁላችሁም አዳምጡት!
ሀገራችን እንዲህ አይነት ምሁራንን የፈሩባት ነች። በጣም ደስ ይላል።

https://t.me/AbuImranAselefy/9335

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

02 Nov, 02:56


https://t.me/medresetulislah?livestream

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

01 Nov, 13:16


https://t.me/medresetulislah?livestream

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

01 Nov, 10:51


👉 ሸይኽ አልባኒን ያስለቀሰ ታሪክ

ዒሳም ሃዲይ የተባለ ተማሪ ሸይኽ አልባኒን በተኽሪጅ ያግዛቸው ነበር ። ከሳቸው ጋር ወደ አምስት አመት አካባቢ አሳልፏል ። የኢብኑ ሒባንና ኢብኑ አሳኪርን ኪታቦች ተኽሪጅ እየሰራ በነበረበት ጊዜ ሸይኽ አልባኒ በእነዚህ ኪታቦች ውስጥ ለየት ያለ ጠቃሚ ነገር ስታገኝ ንገረኝ አሉኝ ይላል ።
የሲቃት ኢብኑ ሒባንን ኪታብ እያነበብኩ ሳለ የአቡ ቂላባን ታሪክ በአምስተኛው ሙጀለድ መጀመሪያ ላይ ለሸይኻችን ማንበብ ጀመርኩ ። በጣም አስገራሚ ሶብሩን ይናገራል ወደ መጨረሻ አካባቢ ደርሼ ቀና ብዬ ሳይ ሸይኻችን በእንባ ታበዋል ። የለቅሶ ሀይል ከውስጣቸው ገንፍሎ ድምፃቸው እንዲወጣ ስላደረገው ተነስተው ወደ ቤት ገቡ ። ከቆይታ በኋላ ተመልሰው መጥተው በጎረነነ ድምፅ ሰላም ብለውኝ ስራቸውን ቀጠሉ ። ታሪኩ ጠቃሚ ስለሆነ ላቅርብላችሁ ይላል የሸይኽ አልባኒው ተማሪ ዒሳም ታሪኩ እንዲህ ነው ።
ኢብኑ ሒባን ከዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ይዞ እንዲህ ይላል : –
" አንድ ጊዜ ወደ ዳርቻ ሄጄ ዒባዳ ለማድረግ ወጣሁ ። ዳርቻ ላይ ማረፊያችን ከቅጠላቅጠል የተሰራ ዳስ ቢጤ ነው ። ወደ ዳርቻ ስደር አሸዋማ በሆነው በባሕር ዳር ባለው ዳርቻ ላይ የሆነ ድንኳን አየሁ ። ወደ ድንኳንኩ ጠጋ አልኩኝ ። በውስጡ የሆነ ሰው አለ ይህ ሰው ሁለቱም እጅና እግሮቹ የሉም ። አይኑም ተይዟል ፣ ጆሮውም ያስቸግሯል ፣ ከአካሉ ሙሉ ጤነኛው ምላሱ ብቻ ነው ። ጠጋ ስል እንዲህ እያለ ዱዓእ ያደርጋል : –
" አላህ ሆይ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋና ከብዙ ፍጥረታቶችህ ለማስበለጥህ የማሸኩርበት ምስጋና እንዳመሰግንህ አድርገኝ " ።!!!
ዐብዱላህም በአላህ ይሁንብኝ ይህን ሰው ቀርቤ መጠየቅ አለብኝ የትኛው ፀጋ ነው አላህ ከሌሎች አስበልጦ የሰጠው ? ፈህም ነው ወይስ እውቀት ወይስ ኢልሃም ነው አላህ በልቡ ላይ የጣለለት አለ ። ዐብዱላሂ ሄደና ሰላም ካለው በኋላ ስታደርገው የነበረውን ዱዓእና ምስጋና ሰምቻለሁ ከአላህ ፀጋዎች የትኛውን ነው የምታመሰግነው አልኩት ይላል ። እንዲህ ብሎ መለሰልኝ : –
" አላህ በኔ ላይ የዋለውን ፀጋ አታይምን አላህ ሰማይን እሳት እንድታዘንብብኝ አዞ ቢያቃጥለኝ ፣ ተራራን አዞ ቢያጠፋኝ ፣ ባሕርን አዞ ቢያሰምጠኝ ፣ ምድርን አዞ ቢውጠኝ አሁን ካለሁበት ምስጋና አልወገድም ነበር ። እሱን የማመሰግንበት ምላስ እስከሰጠኝ ድረስ !!!!! ነገር ግን እስከመጣህ ድረስ ካንተ አንድ ሀጃ አለኝ ። እንደምታየኝ እኔ ራሴን መጥቀም አልችልም አንድ ልጅ ነበረኝ የሶላት ሳአት ሲደርስ ውዱእ የሚያስደርገኝ ፣ ሲርበኝ የሚያበላኝ ፣ ሲጠማኝ የሚያጠጣኝ, ነገር ግን ከሶስት ቀን ጀምሮ አጣሁት እኔ እንደምታየኝ ነኝና እስኪ ፈልግልኝ አለኝ ። በአላህ ይሁንብኝ አንድም ሰው በሰው ሀጃ አይሄድም በምንዳ የላቀ በሆነ ባንተ ሀጃ ከመሄድ የበለጠ ብዬው ፍለጋ ቀጠልኩ ።
ብዙም ሳልቆይ በሁለት ኮረብታዎች መካከል አሸዋማ በሆነ ደለል ላይ አውሬ በልቶት አየሁ ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ብዬ በምን መልኩ ነው ቀርቤ የሆነውን የምነግረው ብዬ ጭንቀት ውስጥ ገባሁ ። የተወሰነ ጊዜ በሀሳብ ከተሰወርኩ በኋላ መመለስ ጀመርኩ ።
መንገድ ላይ እያለሁ የነብዩላሂ አዩብ ታሪክ ትዝ አለኝ ። ከዛም ደርሼ ሰላም አልኩት መለሰልኝ ቀጥሎም አንተ ጓደኛዬ ነህ አይደል አለኝ አው አልኩት ። ጉዳዬን ምን አደረከው አለኝ ።
እኔም አላህ ዘንድ አንተ ነህ ወይስ አዩብ ነው የበለጠ ቦታ ያለው አልኩት ።
እሱም አዩብ አለኝ ።
እሺ ጌታው ምን እንዳደረሰበት ታውቃለህ አይደል በአፍያው ፣ በልጆቹና በሀብቱ ፈትኖታል አይደል አልኩት ።
እሱም አው አለኝ ።
ታዲያ ጌታው እንዴት አገኘው አልኩት ።
እሱም ታጋሽ ፣ አመስጋኝ ሆኖ አገኘው አለኝ ።
አዩብ ጌታው በሱ ላይ ያደረሰበትን ቤተሰቦቹንና ጓደኞቹን እስከሚያስገርም ወዶ ተቀብሏል አይደል አልኩት ።
እሱም አው አለኝና አሳጥረው አላህ ይዘንል አለኝ ።
ልፈልገው የላክኸኝ ልጅ አውሬ በልቶታል አላህ አጅርህን ያብዛልህ ትእግስቱንም ይስጥህ አልኩት ።
የመከራው ባለቤትም እንዲህ አለ " ምስጋና ለዚያ ከዘሬ ውስጥ እሱን አምፆ በእሳት የሚቀጣው ያልፈጠረ ለሆነው ጌታዬ የተገባ ይሁን " ብሎ ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን አለና የማቃሰት ድምፅ አውጥቶ ሩሑ ወጣ ። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ብዬ ትካዜ ውስጥ ገባሁ ።
ትቼው ከሄድኩኝ አውሬ ይበላዋል ቁጭ ካልኩም ምን እንደማደርግ አላውቅም ብዬ በላዩ ላይ በነበረው ፎጣ ሸፍኜው ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ ። ብዙም ሳይቆይ አራት ሰዎች ሲያልፉ አዩኝና መጡ ። ምንድነው ነገርህ አሉኝ ታሪኩን ነገርኳቸው ። እስኪ ክፈተው አሉኝ ከፈትኩት ። ተንበርክከው በአይኖቹ መካከል ይስሙት ጀመር ሐራም ያላየ አይን ይላሉ ። እጅና እግሮቹን እየሳሙ ሰው ሲተኛ ለጌታቸው በመስገድ ያልተኙ አካሎች ይላሉ ። አላህ ይዘንላችሁ ለመሆኑ ይህ ሰው ማን ነው አልኳቸው ። እነርሱም አላህና ነብዩን በጣም ይወድ የነበረው አቡ ቂላባ የኢብኑ ዐባስ ባልደረባ ነው አሉኝ ።
አጥበን እኛ ጋር በነበረ ልብስ ከፍነን ቀበርነው ። ሰዎቹም ሄዱ እኔም ወደ ዒባዳ ቦታዬ ሄድኩ ። ማታ ላይ ጋደም አልኩኝ የተኛ ሰው እንደሚያየው ያን የአላህ ባሪያ በጀነት ጨፌ ላይ የጀነት ልብስ ለብሶ የሚከተለውን የቁርኣን አንቀፅ ሲቀራ አየሁት :–

«سَلَامٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى الدَّارِ»
الرعد ( 24)
«ሰላም ለእናንተ ይኹን፡፡ (ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር!» (ይሏቸዋል)፡፡

አንተ ያ ጓደኛዬ አይደለህምን አልኩት ። አው አለኝ ። ታዲያ ይህን ደረጃ እንዴት አገኘኸው አልኩ ። አላህ ደረጃዎች አሉት በመከራ በመታገስ ፣ በደስታ በማመስገን ፣ አላህን በድብቅም በግልፅም በመፍራት እንጂ የማይገኝ አለኝ " ።

አስሲቃት ሊብኒ ሒባን የአምስተኛው ሙጀለድ መጀመሪያ የአቡ ቂላባ ታሪክ

https://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

01 Nov, 10:03


🟢ዛሬ ይጀምራል

ወርሃዊው የእውቀት ድግስ ከዛሬ ጁመዐህ ከአስር ሰላት በኋላ ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት ይቆያል።
ኢን ሻእ አላህ

ትልቅ እድል ነው !!

https://t.me/medresetulislah/6610

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

28 Oct, 19:54


🟢ለአላህ የሆነው ይፀናል

አልኢማም ማሊክ "ሙወጠእ" የተባለውን ኪታብ በፃፉ ጊዜ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ "ሌሎች ተመሳሳይ ኪታቦች እያሉ ያንተ መፃፍ ምን ጥቅም አለው ? " ታሪክ በማይረሳው ድንቅ  ቃል እንዲህ ብለው መለሱ :
(ما كان لله يبقى = ለአላህ የሆነው ይቀራል)

وقال ابن عبد البر : (وبلغني عن مطرف بن عبد الله النيسابوري الأصم صاحب مالك أنه قال: قال لي مالك: ما يقول الناس في موطئي فقلت له: الناس رجلان محب مطرٍ وحاسدٍ مفتر، فقال لي مالك: إن مد بك العمر فسترى ما يراد الله به)
التمهيد لا بن عبد البر (1/85).
ኪታቡ ተጠናቆ ሰዎች ጋር ከደረሰ በኃላ ደግሞ ባልደረባቸውን ሰዎች ስለ ሙወጠእ ምን እንደሚሉ ጠየቁት:: እርሱም ሲመልስ:
"ሰዎች ሁለት አይነት ናቸው።አድናቂ ወዳጅ እና ምቀኛ ቀጣፊ።" ኢማም ማሊክ እንዲህ አሉ: "እድሜህ ረዝሞ ከቆየህ አላህ የተፈለገበትን ታየዋለህ።"

{...كَذَلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الْحَقَّ وَالْبَاطِلَ فَأَمَّا الزَّبَدُ فَيَذْهَبُ جُفَاءً وَأَمَّا مَا يَنْفَعُ النَّاسَ فَيَمْكُثُ فِي الأَرْضِ كَذَلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الأَمْثَالَ ﴾[الرعد ١٧]
{ልክ እንደዚሁ አላህ ለሀቅና ለባጢል (ምሳሌ) ያደርጋል።ኮረፉማ (ተንሳፋፊው ቆሻሻ) ተበታትኖ ይጠፋል። ሰዎችን የሚጠቅመውማ መሬት ላይ ፀንቶ ይቀራል። ልክ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ያደርጋል።}

  ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊያ)
http://t.me/Abuhemewiya

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

28 Oct, 05:39


*التلون ليس من شيمة أهل السنة*

قال الإمام مقبل الوادعي -رحمه الله-:

" السلفي لا يبيع السنة ولا يبيع الدعوة ولو أعطي ما أعطي فهي:أفضل من المال وأفضل من النسب وأفضل من كل شيء ".

📚:[الإمام الألمعي( 253 )]

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

28 Oct, 00:25


ደርሶቹ ሁሉም የሚሰጡት በሂጅራ አቆጣጠር በየወሩ መጨረሻ 3 ቀን ነው። ጁሙዓ ቅዳሜና እሑድ።
ከሚቀሩት 6 ኪታቦች ውስጥ 4ቱ ኪታቦች ማለትም
١. مقدمة في أصول التفسير
٢. بيان فضل علم السلف على علم الخلف
٣. متممة الآجرومية
٤. الأصول من علم الأصول


የሌላችሁ መድረሳ ላይ የሚገኙ ስለሆነ ከዚያው ትወስዳላችሁ። ሌሎቹን ሁለት ኪታቦች ግን ማዘጋጀት ይኖርባችኋል። ለመግዛት ያልተመቻችሁ ደግሞ በመድረሳው ስልክ ቁጥር
09 51 51 83 83 በመደወል መመዝገብ ትችላላችሁ።

https://t.me/medresetulislah

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

27 Oct, 18:08


https://t.me/Yalkasoenaakebabiwasalfyochgurup?videochat

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

27 Oct, 18:01


📍 قال الشيخ/ ابن عثيمين رحمه الله:

ونحن نعلم أن المسلمين ما ملكوا فلسطين في عهد الإسلام الزاهر إلا بإسلامهم؛ ولا استولوا على المدائن عاصمة الفرس، ولا على عاصمة الروم، ولا على عاصمة القبط إلا بالإسلام؛ ولذلك ليت شبابنا يعون وعيا صحيحا بأنه لا يمكن الانتصار المطلق إلا بالإسلام الحقيقي - لا إسلام الهوية بالبطاقة الشخصية -!

📚 تفسير سورة البقرة ١٧٠/١

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

27 Oct, 16:43


🟢سؤال : نريد ان توضيح الولاء والبراء في الاسلام



🔊 للشيخ_مقبل الوادعي رحمه الله

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

27 Oct, 08:20


📌አምልኮት በስድስት ነገሮች ከሸሪዓው ጋር መግጠም አለበት

ረሱልን - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - መከተል የሚረጋገጠው አምልኮታችን በሚከተሉት ስድስት ነገሮች ከሸሪዓው ጋር ተስማምቶ ሲገኝ ነው፡

1-     በምክንያቱ

2-    በዓይነቱ

3-    በመጠኑ/በቁጥሩ

4-   በአኳኋኑ

5-    በዘመኑ/በወቅቱ

6-   በቦታው

አምልኮታችን ከላይ በገለጽናቸው ስድስት ነገሮች ሸሪዓውን ገጥሞ ካልተገኘ አምልኮታችን ከአላህ ዘንድ ተቀባይነትን አያገኝም፡፡  በሸሪዓ ትዕዛዝ በሌለው ነገር ወደአላህ መቃረብ ቢድዓ ወይም አዲስ ፈሊጥ  ነው፡፡ እነዚህን ስድስት ነገሮች በምሳሌ እንደሚከተለው እናብራራለን፡-

1-     በምክንያቱ

አንድን አምልኮት ስንፈጽም ከሰበብ ጋር ቁርኝት ካለው ሰበቡ በሸሪዓ የተቀመጠ መሆን አለበት፡፡ ሰበቡ በሸሪዓ ባልተደነገገ መልኩ ወደአላህ መቃረብ ስራን ተቀባይነት ያሳጣል፡፡ ለምሳሌ፡ ሁሌም ቤታችን ስንገባ ሁለት ረከዓ መስገድን እንደ ሱና መቁጠር፡፡ ሶላት መስገድ በሸሪዓ የተደነገገ ቢሆንም አላህ ሰበብ ባላደረገው መንገድ በኢባዳ ላይ አዲስ ፈሊጥ መጨመር ክልክል ተግባር ነው፡፡ ስራንም ተቀባይነት ያሳጣል፡፡

ተጨማሪ ምሳሌ፡ ሙስሊሞች ድል ያደረጉበትን የበድር ዘመቻ ክብረ በአል አድርጎ መያዝ፡፡  ሙስሊሞች ድል ያደረጉበትን ቀናቶች በአል አድርጋችሁ ያዙ የሚል በሸሪዓ የተደነገገ ትዕዛዝ ባለመኖሩ ይህ ክብረ በዓል ቢድዓ ይሆናል ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል የሚፈጸሙ ማንኛውም ተግባራት ተመላሽ ይሆናሉ፡፡

2-    በዓይነቱ

አምልኮትን ስንፈጽም በዓይነት ከሸሪዓው ጋር ተስማምቶ መገኘት አለበት፡፡  ለምሳሌ ፡ አንድ ሰው በኢደል አድሃ ለኡዱሁያ የሚታረዱ እንስሳዎች ግመል ከብት ፍይልና በግ ብቻ ሆነው እያለ ፈረስ ቢያርድ ተቀባይነት የለውም፡፡

ለኡዱህያ አስቦ ሳይሆን ስጋውን ከፋፍሎ ለምስኪን ለመሶደቅ ከሆነ ግን ፈረስ ቢያርድ ችግር የለውም፡፡  

3-    በመጠኑ/በቁጥሩ

በሚፈጽማቸው ኢባዳዎች ሁሉ በመጠን ወይም በቁጥር ከሸሪዓው ጋር ተስማምቶ መገኘት አለበት፡፡ አንድ ሰው ሸሪዓው ከወሰነው የቁጥር መጠን በላይ ወደአላህ እቃረባለሁ ቢል ስራው ተመላሽ ነው የሚሆነው፡፡  ለምሳሌ፡ -አንድ ሰው ውዱእ በሚያደርግበት ጊዜ አራት አራት ጊዜ ቢያደርግ የውዱዕ ስርዓቱ ከነብያችን አስተምህሮ ውጭ በመሆኑ ተግባሩ ተቀባይነት የለውም፡፡

የአላህ መልክተኛ የውዱዕን ስርዓት ካስተማሩ በኋላ የሚከተውለውን ተናግረዋል፡-

"من زاد على ذلك فقد أساء وتعدى وظلم"

“ ከዚህ ላይ የጨመረ በእርግጥ አከፋ ወሰን አለፈ በደለ፡፡”

4-   በአኳኋን

የሚፈጽመው ኢባዳ  በአኳኋኑ ከሸሪዓው ጋር ተስማምቶ  መገኘት አለበት፡፡ አኳኋኑን ቀይሮ አምልኮት ከፈጸመ ኢባዳው ተቀባይነት የለውም፡፡ ለምሳሌ፡ ሩኩእ ከማደረጉ በፊት ሱጁድ ቢያደርግ ሶላቱ ተቀባይነት የለውም፡፡

ተጨማሪ ምሳሌ፡ ውዱእ ሲያደርግ በተቃራኒው ቢጀምር ከእግሩ ጀምሮ ከዚያም እጁን ከዚያም ፊቱን እያለ በሸሪኣው ተቃራኒ ውዱዕ ቢያደርግ አኳኋኑን በመቀየሩ ውዱኡ ተቀባይነት አያገኝም፡፡

5-    በዘመን

የሚፈጸሙ ኢባዳዎች በዘመን ከሸሪኣው ጋር ገጥመው መገኘት አለባቸው፡፡ ለምሳሌ፡ ወቅቱ ከመግባቱ በፊት ሶላት ቢሰግድ የተሰገደው ሶላት ሸሪዓው ከደነገገው ወቅት ውጭ በመሆኑ ሶላቱ ከአላህ ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡

ሶላተል ኢድ ከመሰገዱ በፊት ኡዱሁያ ቢያርድ ሸሪዓው የደነገገውን ወቅት በመቃረኑ ተቀባይነት የለውም፡፡

6-   በቦታ

የሚፈጽማቸው ኢባዳዎች በቦታ ከሸሪኣው ጋር ገጥሞ መገኘት አለበት፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ኢእቲካፍ ማድረግ የሚገባው በመስጊድ ውስጥ ሆኖ እያለ ከመስጊድ ውጭ በቤቱ ወይም በትምህርት ቤቱ ኢእቲካፍ ቢያደርግ ተቀባይነት አያገኝም፡፡ 

شرح الأربعين النووية لفضيلة الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين ص/117


https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

27 Oct, 02:55


قال الشيخ العلامة
أحمد بن يحي النجمي رحمه الله تعالى

"تحب الرجل الذي لا يقربك في النسب
ولا من جيرانك الذين تتعاون معهم ويتعاونون على جلب المصالح المشتركة بينك وبينهم
ولكنه رجل بعيد عنك في الدار بعيد عنك في النسب
يبلغك عنه بأنه صاحب سنة فتحبه في الله
إذا بلغت إلى هذا الحد فأنت مؤمن".

[فتح الرحيم الودود:59/1]
#درر_النجمي

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

25 Oct, 19:04


የአካውንቱ ባለቤት ወንድሙ ነው ። ስሙ ዐ/ሰመድ አሕመድ ይባላል ።

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

25 Oct, 19:00


👉 የአንድን ሰው ሕይወት ለማዳን ሰበብ መሆን የሰውን ልጅ ሕይወት ሁሉ እንደማዳን ነው ።

ውድ ቤተሰቦቻችን በየጊዜው የሚያጋጥሙ የህመም አይነቶች አንዱ ሌላውን እያስረሳ ውስጥን በሐዘን የሚሞላ አእምሮን የሚረብሽ ነው ። የተለያዩ ሰዎች በተለያየ በሽታ ይሰቃያሉ ። ከበሽታ ሁሉ አስከፊውና በአሁኑ ጊዜ እንደወረርሽኝ እየተዛመተ ያለው የካንሰ በሽታ ነው ። በዚህ በሽታ ሰበብ ብዙ ሰዎች ወደ አኼራ ይሄዳሉ ። የአላህ ውሳኔ እንዳለ ሆኖ ቤተሰብ በአቅም ማነስ ምክንያት ማሳከም ባለመቻሌ ነው በሚል ፀፀት ይሰቃያል ። ከእንደነዚህ አይነት ገጠመኞች አንዱ የሆነውን ዛሬ ወደናንተ ለማድረስ ወደድኩ ።
ይኸውም ወንድማችን ሙሀጅር አሕመድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በደም ካንሰር ተይዞ በአሁኑ ሰአት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይገኛል ። ይህ ወንድማችን የኬሞ መድሀኒት የጀመረ ሲሆን ያለበት ሁኔታ ሐኪሞች ተስፋ ሰጪ ነው ይላሉ ። ነገር ግን የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጅ በመሆኑ ለሕክምናው የሚያስፈልጉ ወጪዮችን መሸፈን የማይችሉ መሆኑን ሆስፒታሉ አረጋግጦ ፅፎለታል ።
ከሱ ጋር ያለው አርሶ አደር ወንድሙ በደረሰው ነገር ቅስሙ ከመሰበሩ ባሻገር የወንድሙም ህይወት በሱ ድጋፍ የነበሩ ቤተሰቦቹም ችግር ረፍት ነስቶት የይድረሱልኝ ጥሪ እያሰማ ነው ። ተስፋ የነበረውን ወንድሜ ሰበብ ሆናችሁ አድኑልኝ ይላል ። አይኑ ብቻ ሳይሆን ሁለመናው እያለቀሰ የደረሰበትን ሲናገር ማየት በጣም ይከብዳል ። በጣም ብዙ ጉዳዮች የሚመጡ ሲሆን ወደናንተ የማደርሰው በጣም አሳዛኝና ምንም ሰበብ ከሌላቸው ውስጥ ጥቂቶቹን ነው ። ስለዚህ በአላህ ፈቃድ ከተባበርን አላህ ካልቀደረበት ወንድማችንን ሰበብ ሆነን ማዳን እንችላለን ።
የአንድን ሰው ሕይወት ለማዳን ሰበብ መሆን የሰውን ልጅ ሁሉ ህይወት እንደማዳን ነው ። በመሆኑም ውድ እህትና ወንድሞች ለወንድማችን ጥሪ ምላሽ ሰጥተን ታማሚውን ለማዳን ሰበብ ሆነን የወንድሙን እንባ እንጥረግለት እላለሁ ። በምንም መልኩ አንብበን እንዳናልፈው የምንችለውን እናበርክት ።
የሆስፒታሉ የድጋፍ ደብዳቤ ላይ አካውንትና ስልክ አለ አብሬ አያይዘዋለሁ ።

https://t.me/bahruteka/5492

https://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

25 Oct, 11:48


🟢በእውቀትህ አትሸንገል

"فلا يكفي أن الإنسان يعرف العقيدة، فالعالِم يَزِل ويخطئ، فلا يغتر الإنسان بعِلمه، ولا يَأْمَن الفتن، فهل عِلمُه يُعادِل عِلم إبراهيم عليه الصلاة والسلام؟ وقد دعا الله فقال: {واجْنُبني وبنِيَّ أنْ نَعبُدَ الأصنام}".

التعليقات المختصرة على الطحاوية للعلّامة صالح الفوزان ص٢٦٣

ዓሊሙ አሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን እንዲህ አሉ:
"አንድ ሰው እኮ ዐቂዳን ማወቁ ብቻ አይበቃም:: አዋቂም ሊንሸራተትና ሊሳሳት ይችላልና::ማንም ሰው በእውቀቱ አይሸንገል (አይታለል):: ከፊትናም አይተማመን::
እውቀቱ የኢብራሂምን (አለይሂሰላቱ ወሰላም) እውቀት ይስተካከላልን!?
በእርግጥም አላህን እንዲህ ሲል ለምኗል "እኔንም ልጆቼንም ጣኦቶችን ከማምለክ አርቀን"

https://t.me/Menhaj_Alwadih

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

24 Oct, 06:34


قال شيخ الإسلام -رحمه الله- :

وليس كلّ من وجدَ العلمَ قدرَ على التعبير عنه والاحتجاج له؛ فالعلم شيءٌ، وبيَانُه شيءٌ آخر، والمُناظَرةُ عنه وإقامة دليلهِ شيءٌ ثالث، والجوابُ عن حُجَّةِ مُخالفِه شيءٌ رابعٌ!.

[جواب الإعتراضات المصرية: (ص٤٤)]

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

24 Oct, 03:23


አዲስ የተጠናቀቁትን 7 ኪታቦችን ጨምሮ በሸይኽ አቡዘር ሀሰን አላህ ይጠብቃቸው ከ35 በላይ ዱሩሶች በቅደም ተከተል ያለበት ሊንክ ነው።

1ኛ የኡሱሉ ሰላሳ (ሰላሰቱል ኡሱል)
👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/46

2ኛ  የ አርባዒን ሓዲስ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/74

3ኛ ኪታቡ አት– ተውሒድ  ሊሸይኽ ሙሀመድ  ብን አብደል ወሃብ
👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/190

4ኛ  "አዕላሙ ሱና "ሙሉ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/275

5ኛ  ሸርሁ ሱና ሊል በርበሃሪይ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/340

6ኛ  አል አጅዊበቱል ሙፊዳህ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/530

7ኛ  መንዙመቱል ሙቀዲመቱ አል ጀዘሪይ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/578

8ኛ  ቱህፈቱል አጥፋል
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/603

9ኛ  መስዓለቱ ዑዝር ቢል ጀሕል
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/811

10ኛ  ሙቀዲመቱ ኡሱሉ ተፍሲር
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/847

11ኛ አነ—ሕዉል ሙስተጧብ ክፍል
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/932

12ኛ አነ—ሕዉል ሙስተጧብ ክፍል
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1032

13ኛ አል መውሪዱል ዓዝቡ ዙላል 
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1205

14ኛ አል አቂደቱል አጡሓዊያህ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1262

15ኛ ሉምዓቱል ኢዕቲቃድ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1292

16ኛ አል በራሂኑል ሙረሰዓህ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1389

17 አል አቂደቱል ዋሲጢየህ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1448

18 ቡሉጉል መራም ሚን አዲለቲል አህካም
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1452

19 በሰዎች ላይ የ "አል-ጀርህ እና አት-ተዲል" ኢማሞች ንግግር በኢጅቲሃድ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በመረጃ ላይ የተመሰረተ ነው።
أقوال أئمة الجرح والتعديل في الرجال من باب الإخبار لا من باب الإجتهاد
ለኸድር ኬሚሴ የተሰጠ ምላሽ
ሙሉ ደርስ
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1815

20  የኪታቡ ስም = "ኪታቡ አት– ተውሒድ  ሊሸይኽ ሙሀመድ  ብኑ አብደል ወሃብ "ሙሉ ደርስ" ከአል ቀውሉል  ሙፊድ ማብራሪያ ጋር
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1880

21 መሳኢሉ አል-ጃሂሊያ مسائل الجاهلية
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1993

22 መንሃጁል-አንቢያእ منهج الأنبياء
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2027

23 ከሽፉ አሽ-ሹቡሃት
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2133

24 መጃሊሱ ሸህሪ ረመዷን
👇👇👇👇
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2165

25 አል ኡሱሉ አስሰላሳህ (አዲስ)
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2229

26 ቀዋዒዱል አልአርበዓህ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2257

27 አል ቀሲደቱ ላሚያህ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2263

28 የالدرة المضية ሙሉ ደርስ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2273

29 የ نخبة الفكر ሙሉ ደርስ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2303

30 ኢጅማዑል ኡለማዕ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2327

31 አርበዑነ-ነወውያህ (አዲስ)
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2452


32ኛ መንዙመቱበይቁኒይ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2505

33ኛ ቀሶሱሱከር ነዝሙ ኑኽበቲል ፊከር
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2520

34ኛ ቀሲደቱ ገዘልያህ ፊ አልቃቢ አልሀዲስ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2555

35ኛ አል
ወረቃት
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2559

36ኛ ተስሂል
ጡሩቃት ፊነስሚል ወረቃት
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2618

37ኛ ነዝሙል ቀዋኢድል ፊቅሂያህ
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2679

38ኛ አል˙ከሊማቱል ሂሳን ፊ′በያኒ ዑሉዊራህማን
➘➴➷➘➴➷
https://t.me/Abuzarehassenlmam/2712

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

23 Oct, 18:38


🟢 በሚገበ ለኢስላም የቆሙት እነዚህ ናቸው‼️ አላህ ይዘንላቸው።


قال ابن مسعود رضي الله عنه :
"مَنْ كان مُسْتنّا فَلْيَسْتن بمَنْ قَدْ مَاتَ أولئكَ أَصْحابُ مُحمد ﷺ كانوا خَيرَ هذه الأمَّة وأَبَرها قُلوبا, وأَعْمقَها عِلْما  وأَقَلّها تَكلفا ، قَوم اخْتارَهُمُ اللهُ لِصُحْبَة نبيهﷺ ونَقلِ دينه فَتَشبَّهوا بأَخْلاقِهِم وطَرائِقِهم ؛ فَهُمْ كانوا عَلَى الهَدْي المُستقِيم" 
📚 شرح السنة للبغوي [٢١٤/١]

🔸ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለት አለ: <<የሱነህ ፈለግ  የሚከተል  ሰው በእርግጥ የሞቱትን ሰዎች ፈለግ  ይከተል፤ከዚህ ትውልድ በላጮች (ምርጦች) እነዚያ የመልዕክተኛውﷺ ባልደረቦች ናቸው።ልበ መልካሞች፣በእውቀት የጠለቁ፣ከአጉል መጣጣር የጠሩ (በሌላቸው ከመመሰል የራቁ)፣ለመልዕክተኛውﷺ ጓደኝነትና ዲኑን ለማስተላለፍ አላህ የመረጣቸው። በነሱ [በሰለፎች] ስነ_ምግባርና በመንገዳቸው ተመሳሰሉ።እነሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነበሩ>>።
📚 ሸርሁ ሱነህ ሊልበገዊይ   (1/214)

  https://t.me/mustefatemam

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

23 Oct, 17:16


‏قال الشيخ صالح بن فوزان الفوزان حفظه الله :

والذي يربِّي أولاده تربية سيئةً يناله من إثمهم ما عاشوا على الضَّلال والانحراف وما مارسوا الإثم والفسوق والعصيان،
لأنه هو الذي عوَّدهم على ذلك ونشَّأهم عليه، أو أهْملهُم صِغاراً حتى ضَاعُوا كِبارا
.

[ الخطب المنبرية (4-ص110) ]

🔗رابط القناة على التيليجرام :
https://t.me/fawayidalfawzan

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

23 Oct, 10:31


👉   የኢኽዋን መሪዮች የመጅሊስ እንጂ የሀገር መሪዮች አይደሉም ።

     የሀገራችን የኢኽዋን መሪዮች የስልጣን ጥማት በቀን ቁጭ ባሉበት እንዲቃዡ አድርጓቸዋል ። ቅዠቱ በርግጥ በውስጣቸው ሲያልሙት የነበረ መሆኑን ያመላክታል ። የእነዚህ አካላት የቀን ቅዠት ልክ እንደ አንድ በረንዳ አዳሪ ነው ።  በቀን ጎዳና ላይ ቁጭ ብሎ እርጥብ እሳት ( ጫት) እየበላ የምርቃናው ሙቀት በሁለመናው ሲሰራጭ በምናቡ የመዋኛ ቦታ ፣ ሜዳ ቴኒስ ፣ የልጆች መጫወቻ ባለው በተንጣለለ ጊቢ ላይ በተሰራ ቪላ ውስጥ ራሱን አስቀምጦ በሐሴት ማእበል ሲናወጥ ምርቃናው እንደጠፋበት አምሳያ ነው ።
     እነዚህ የሀገራችን የኢኽዋን መሪዮች ለስንት አመት ሲመኙት የነበረውን የመጅሊስ ስልጣን ላይ ሲወጡ የተሰማቸው ሙቀት የሰራ አካላታቸውን ሲቆጣጠረው ቁጭ ብለው የሀገር መሪ ሲሆኑ በቀን በተቀመጡበት በምናብ ዐለም ማየት ጀምረዋል ። የሚገርመው ይህ ህዋ ላይ የሚያንሳፍፋቸው ቅዠት ወደ መሬት ለማውረድ ቆርጠው ተነስተው ማስፈራራት ጀምረዋል ።
    ከዚህ በፊት ሐረር ላይ በነበራቸው ጉባኤ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በሱ " የስልጣን ግዛት " ውስጥ ሰለፍይ የሚባል ነገር መስማት እንደማይፈልግ በመግለፅ ሰለፍዮች ወደዱም ጠሉም በአሁኑ ሳአት እዚህ ሀገር ላይ ( ኢትዮዽያ ላይ ) የሙስሊሙ መንግስት እሱ መሆኑን አውጇል ።
     ገርሞ ገርሞ ይገርማል ። ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንደሚሉት ወይም ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ነው ነገሩ ። ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ፣ የሙስሊሞች መሪ ፣  ከዶ/ር አብይ አሕመድ ደግሞ የክርስቲያኖች መሪ  እንዲሆኑና ኢትዮዽያ በሁለት መንግስታት እንድትመራ የተስማሙ ይመስል ። ይህን የሐጂ የቀን ቅዠት በተለይ ኦሮምኛ የምትሰሙ በሚከተለው ሊንክ ገብታችሁ አድምጡ :–
https://drive.google.com/file/d/1VZSVRvGK0tOrUTiP4z7vJXz_Mx28Qqi4/view?usp=drivesdk

     በዚህ ቅዠቱ ላይ በሚገርም መልኩ ሰለፍዮችን ያስፈራራል ። ውሀ ዝም ብሎ ሲሄድ የተኛ ይመስላል እንደሚበላ ሰው አያውቅም የሚል ምሳሌ አምጥቶ ዝም ስላልኩ የማላውቅ አይምሰላችሁ አጠፋችሇለሁ ይላል ።
    እኛ የምንለው መጀመሪያ ዙፋኑን አረጋግጥና ከዛ በኋላ ዛቻውን አምጣ ነው ። አሁንም የምንለው አንተ የአንድ ተቋም መሪ እንጂ የሀገር መሪ አይደለህም ነው ። እንደሙስሊም በቁርኣንና በሐዲስ በሶሓቦች አረዳድ እንደ ሀገር ደግሞ በህገ መንግስቱ ነው የምንመራው ። አንተም እኛም በህገመንግስቱ እኩል ነን ።
     ከኢስላም ሊቃውንቶች ጥበበኛ ንግግር አንዱ " ልኩን ያወቀን አላህ ይዘንለት " የሚል ነው ።
     ይህ የቀን ቅዠት በሱ ላይ ብቻ አላበቃም ዶ/ር ጀይላንም የአሕባሽ ሱፍይና ኢኽዋን ጥምር የሆነው የዑለማእ ፈታዋ ያልተቀበለ ኻሪጅይ ነው ( በመንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ የወጣ ) ነው ብሎ የጓደኛውን የማይጨበጥ ምናብ አጠናክሯል ።
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
       🔹 ይህ ከላይ ያለው ፁሑፍ ግንቦት 2016 ላይ ተፅፎ የነበር ሲሆን ኢኽዋኖችን በተለይ የመጅሊሱን አመራሮች ያበሳጨ ነበር ። አሁንም የምንለው የኢኽዋን ( የመጅሊስ ) አመራሮች የሙስሊሙ መንግስት አይደሉም ። ኢትዮዽያም በሁለት መንግስት እየተመራች አይደለም ። ነገር ግን ከመንግስት ጋር ሲጠጉ እውነተኛ የሀገር ተቆርቋሪ የህዝቡን ሰላም አስጠባቂ መስለው ከመንግስት ጋር ሲጋጩ ወይም መንግስት ፊት ሲነሳቸው ለግል ጥቅማቸው ህዝቡን ከዳር እስከዳር ቀስቅሰው ሀገር እንዲታመስ የሚያደርጉ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባዮች መሆናቸውን መግለፅ በተለይ ለምስኪኑ ተከታይ በጣም አስፈላጊ ነው ። ታዲያ ከላይ የተጠቀሰውን የሀገር መሪነት የምናብ ስካርና ሰለፍዮችን የማሸማቀቅ ጥማታቸው በፊት ለፊት ሳይሆን በመሰሪ አካሄድ ተግባራዊ ለማድረግ የማይቆፉሩት ጉድጓድ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም ። ለዚህ ዋነኛ መሳሪያቸው ሰለፍዮችን የሀገር ስጋት የሰላም ፀር እንደሆኑ አደርገው ለመንግስት ባለስልጣናት በማቅረብ ወደ አላማቸው መድረስ ትልቁ ስራቸው አድርገው ይዘውታል ።  ይሁን እንጂ ደመናው በፀሀይ እንደሚገፈፈው ሁሉ እነዚህ አካላት በሰለፍዮች ላይ የሚለጥፉት የስም ማጥፋት ታፔላ ተነስቶ እውነታው ፍንትው ማለቱ አይቀርም ።
     ስሙን ለሰው አወረሰው እንዲሉ ኢኽዋኖች የራሳቸውን ማንነት ለሰለፍዮች በመስጠት ስማቸውን ለማጠልሸት መሞከር በምንም መልኩ የእነርሱን እኛ የሙስሊሙ መንግስት ነን የሚለውን ምኞት አያሳካም ። ለጊዜው ለመንግስት የተሳሳተ ምስል በመስጠት የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስድ ሊያደርጉ ይችላሉ  ። ነገር ግን ይህ ማለት መንግስትን አዘዙ ወይም  ከመንግስት በላይ ሆኑ ማለት አይደለም ። ይልቁንም ማንነታቸውና ድብቅ አጀንዳቸውን እንዲረዳ ነው የሚያደርጉት ። እንኳን ሀገር የሚመራ መንግስት አንድ የቤት አባ ወራም ቢሆን እገሌ እኮ በጣም አደገኛ ነው ካልከው ከሱ ጋር የነበረውን ግንኙነት ቆም አድርጎ በራሱ መንገድ ማንነቱን ያጣራል ። በመጨረሻም ታማኝነቱና እውነትኝነቱን ሲያረጋግጥ በተቃራኒው ያንተን ድብቅ ፍላጎት ለማወቅ ፊቱን ማዞሩ አይቀርም ።
      በመሆኑም የኢኽዋኖች ሰለፍዮችን የማጠልሸት እንቅስቃሴ ለሰለፍዮች ክብርን እንጂ አይጨምርላቸውም ። ሌላው ኢኽዋኖችና የእንጀራ ልጆቻቸው ሊያውቁት የምንፈልገው ሰለፍዮች በመለኮታዊ ቃል የሚመሩ መሆናቸውና ከማንም ምንም ነገር ቢደርስባቸው በመለኮታዊው የሕይወት መመሪያ የአላህ ቃልና በነብዩ ንግግር መዝነው ተግባራዊ የሚያደርጉት መሆኑን ነው ። በስሜት ፈረስ እየጋለቡ ለግል ጥቃማቸው ወጣቱን ከጎናቸው  አሰልፈው ሀገር የሚያምሱ አይደሉም ። ስለዚህ አትድከሙ ህልማችሁ አይሳካም የአላህ ቃል የበላይ ይሆናል እንላቸዋለን ።
      https://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

22 Oct, 03:40


"የወላእ ( መረዳዳት ወይም መዋደድ ) እና የበራእ ( መራራቅ እና መቆራረጥ ) ክፍል ''
በሚል ርዕስ በዚሁ ቻናል በተከታታይ አምስት ክፍሎች ሲቀርብ የነበረዉ፣ በሸይኽ ሷሊሕ ዓብዱላህ አል ፈውዛን ተዘጋጅቶ በኡስታዝ ዩሱፍ አሕመድ የተተረጐመው ፅሁፍ በአላህ ፈቃድ ለንባብ በሚመች መልኩ በPDF ተዘጋጅቶ ቀረቦልዎታል ።

ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን!!

አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን!
የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

كن على بصيرة

https://t.me/alateriqilhaq

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

21 Oct, 18:52


🟢ይድረስ ለሰለፈዮች

ይህን የመሰለ ጠቃሚ ምክር ሁሌም ያስፈልጋል።።
نصائح وتوجيهات قيمة من الشيخ
أبي محمد ربيع بن هادي المدخلي حفظه الله تعالى
👆ከአሸይኽ ረቢዕ አልመድኸሊይ ምክሮች

👌 ተቅዋ (ጥንቁቅነት)
👌 ኢኽላስ (ዒባዳን ማጥራት)
👌 ኢስቲቃማ (በሀቅ ላይ መፅናት)
👌 አላህን ከሚያስቆጡ ነገሮች ሁሉ መራቅ
👌 ቁርኣን እና ሀዲስን ከመፃረር መቆጠብ
👌 አኽላቅ (መልካም ስነምግባር)
👌 ለአላህ ብሎ ከልብ መዋደድ
👌 ለሀቅ መተጋገዝና መተሳሰር
👌 የኺላፍና መለያየት ሰበቦችን መራቅ
👌 ሰብር እና ቻይነት
👌 ጀነት የሚያስገባ ኢማን
👌 ከልብ የመነጨ ሰላምታ ተላዋወጡ
👌አላህ የሚጠላቸውን ካፊሮች ፣ ሙሽሪኮች ፣ ሙብተዲዖች መጥላት
👌 ሰለፊዮች እንደ አንድ አካል ናቸው

https://t.me/Abuhemewiya

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

21 Oct, 16:59


https://t.me/almadkhalinet?livestream

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

19 Oct, 15:56


ሸይኽ አልባኒ በካሜራ በሚነሳ ፎቶና በእጅ በሚሳል ፎቶ መካከል መለየት የዘመናችን የመረጃ ቋንቋዊ ትርጓሜውን መከተል ( ዛሂሪየቱል ዐስር ) ነው ይላሉ ። ቀጥሎም በአምድ ተማሪና ሸይኹ መካከል የተከሰተን ክስተት ይናገራሉ ።
እሱም እንደሚከተለው ነው : –
አንድ ሸይኽ ተማሪያቸውን ለመዘይር ይሄዳሉ ተማሪያቸውም የሳቸውን ( በእጅ ) የተሰራ ፎቶ በፍሬም አሰርቶ ግድግዳ ላይ ሰቅሎ ያያሉ ። ተማሪያቸውን ይቆጡታል ምስል ሐራም መሆኑን አታውቅምን እንዴ ምስል ትሰቅላለህ ይሉታል ። ተማሪውም ምስሉን ያስወግዳል ። ከጊዜ በኋላ እንደገና ተማሪያቸው ቤት ይሄዳሉ ። የሳቸው በካሜራ የተነሳ በጣም የሚያምር ፎቶ ተሰቅሎ ያያሉ ። በጣም ይቆጡና ይህ ምንድነው ይሉታል ። ተማሪውም ለምን ይቆጣሉ በእጅ የተሰራ ፎቶ ሐራም ነው በካሜራ የተነሳ ከሆነ ችግር የለውም ብለው እርሶ እኮ ኖት ያስተማሩን ይላቸዋል
ሸይኽ አልባኒ ይህን ከኢብኑ ሐዝም የነብዩ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – " ከናንተ ውስጥ አንዳችሁ በማይሄድ ( በተኛ) ውሃ ላይ እንዳይሸና " ያሉበትን ሐዲስ አስመልክቶ በሌላ እቃ ላይ ሸንቶ በውሀው ላይ ቢደፋው ችግር የለውም ። እንዳለው ነው ይላሉ ።

https://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

17 Oct, 09:28


የበላይነት በፅናት እንጂ በብዛት አይደለም ።

በአሁኑ ጊዜ ኢኽዋኖች ብዛትና አቅም ስላላቸው ከእርነሱ ማስጠንቀቅ ይከብዳል ይላሉ ። እነዚህ ሰዎች ውስጣቸው ያለው ሱና ደክሞባቸው በራሳቸው ጊዜ የተሸነፉ ናቸው ። ምክንያቱም አላህ ዓለምን ከጨለማ ያወጣው በአንድ ነብዩ ነው ። ዐለሙ አቅም በነበራቸው ከሀዲያን ተጥለቅልቆ ሳለ ።
ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በሞቱ ጊዜ አብዛኛው ኢማን ሰርፆ ወደ ልቡ ያልገባ የገጠሩ ህዝብ ወደ ኩፍር ሲመለስ ዲኑ የተጠበቀው በአቡ በከር ፅናት ነበር።
የሙዕተዚላዎችም ቁርዓን ፉጡር ነው የሚለው ፈተና በኢማሙ አሕመድ ፅናት ተወግዶ አላህ ሱናን የበላይ አደረገው ። ይህ እንግዲህ ሙዕተዚላዎች ከነበራቸው አቅም ጋር ነው ።
እነደዚሁ አላህ ሱናን በሸይኹል ኢስላም ፅናት ከሞንጎሊያዎች ፣ ከሺዓዎች ፣ ከአሻዒራና አምሳዮቻቸው ፈተና ጠብቆታል ።
አሁንም በሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሀብ ፅናት ዱኑን እንዴት ህያው እንዳደረገው ለአሁኑ ትውልድ መንገር ለቀባሪ እንደማርዳት ነው። ታድያ እነዚህ ሰዎች ብዙ ሆነው ሳይሆ ተዓምር የሰሩት በአላህ እርዳታ ታግዘው በነበራቸው ፅናት ነው ።
እኛም በሱና ላይ ፀንተን ለሱና ዘብ ከቆምን የአላህ ርዳታ ታክሎበት ሱናን የበላይ ማድረግ እንችላለን ሜዳ ውስጥ ሳንገባ ተሸናፊ አንሁን ።

https://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

16 Oct, 23:23


👉   ለራስህ ታማኝ ሁን !

    አንድ ሰው በትክክል ሙስሊም ሲሆን ለራሱ ታማኝ ይሆናል ። በሌላ አባባል ሙስሊም መሆን ማለት እውነተኛ ራስህን መሆን ማለት ነው ። የዚህን ጊዜ ለራስህ ታማኝ ትሆናለህ ። አጠቃላይ ቁርኣንና ሐዲስ ላይ የመጡ ክልክል የሆኑ ነገሮችን የሚዘረዝሩ መረጃዎች አንተ ውስጥ ቦታ የሚኖራቸውና ስራ ላይ የሚውሉት እየአንዳንዱ ሙስሊም ለራሱ ታማኝ ሲሆን ነው ።
– ካልዋሸህ ለራስህ ታማኝ ነህ
– ካላታለልክ ለራስህ ታማኝ ነህ
– ካልሰረቅህ ለራስህ ታማኝ ነህ
– ሰው አላየኝም ብለህ ክልክል የሆኑ ነገሮችን ካልሰራህ ለራስህ ታማኝ ነህ ። የተኛውንም ወንጀል ስትሰራ ከማንም በፊት የምትሸውደው እራስህን ነው ።
– ለእዩልኝ ፣ ለመታወቅ ፣ ለይስሙልኝ ብለህ እየሰራህ ሙኽሊስ ለመምሰል ብትሞክር ለራስህ ታማኝ አይደለህም ።
– በዘረኝነት ገመድ ተተብትበህ ዘረኝነት ጥንብ ናት እያልክ በድምፅና ፁሑፍ ሚዲያ ብታጥለቀልቅ ለራስህ ታማኝ አይደለህም ።
– ለጥቅምህ ብለህ ሸሪዓን እየኻለፍክ ለዳዕዋ መስላሃ ነው ብትል ለራስህ ታማኝ አይደለህም ።
– ጅህልናህን ከማንም በላይ እያወቅኸው አዋቂ ለመምሰል ብትሞክር ለራስህ ታማኝ አይደለህም ።
– በምቀኝነት እሳት እየነደድክ እገሌን እንዴት በጣልኩት እያልክ ለሱና ብዬ ነው ብትል ለራስህ ታማኝ አይደለህም ።
– ከሁሉም ጋር እየተመሳሰልክ ማንነትህን ለመደበቅ ብትሞክር ለራስህ ታማኝ አይደለህም ።
– ሰዎችን ሁሉ በትንሽ አይን እያየህ ሙተዋዲዕ ለመምሰል ብትሞክር ለራስህ ታማኝ አይደለህም ።
– እንደማትፈፅመው እያወቅህ ቃል ኪዳን ብትገባ ለራስህ ታማኝ አይደለህም ።
– ሳታምንበት ሰለፍያ ሰለፍያ ብትል ለራስህ ታማኝ አይደለህም ።
  ለማንኛውም ለራስህ ታማኝ ለመሆን ወደ መግቢያችን እንመለስ ሁሌም እውነተኛ እራሳችንን መሆን ማለት ነው ። ይህ የሚመጣው የአላህን ስምና ባህርይ ጠንቅቀን ስናውቅ ነው ።
    አላህ ዐሊም መሆኑን ስናውቅ ተደብቀን የምንሰራው ነገር የለም ምክንያቱም ሁሉን አዋቂ ስለሆነ ያውቀዋል ። አላህ በሲር መሆኑን ስናውቅ ተሸሽገን የምንሰራው ነገር የለም ምክንያቱም የትም ብንሆን ያየናል ። አላህ ኸቢር መሆኑን ስናውቅ በምቀኝነት እሳት እየነደድን ያየነውን ሁሉ ለማጥፋት አናስብም ምክንያቱም አላህ ውስጥ አዋቂ ነውና ።
     በመጨረሻም እውነተኛ እራስን መሆን ወይም ለራስ ታማኝ መሆን ማለት በግልፅም በድብቅም አላህን መፍራት ማለት ነው ።
                አላህ ይወፍቀን ።

ጠቃሚ ስለሆነ በድጋሚ የተለቀቀ

https://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

14 Oct, 17:11


🛜ቀጥታ ስርጭት

https://t.me/almadkhalinet?livestream

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

13 Oct, 13:00


#الخطب المنبرية:

《اتبعوا ولا تبتدعوا》

فضيلة العلامة الشيخ:

أحمد بازمول حفظه الله تعالى.

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

13 Oct, 10:18


ተከታታይ ደርስ

                      ክፍል-1

📚  የተፍሲር አስሰዕዲ ማብራሪያ

🎙 በኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ሐፊዘሁሏህ

🕌   አል ኢስላሕ መድረሳ

t.me/medresetulislah

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

12 Oct, 15:00


🔹 የአላህ ጥበብ እያደር ግልፅ ይሆናል

ለኮንፈረሱ የመግቢያ ትኬት የተላከላችሁ
ወንድሞች የተሸጠው በአካውንቱ አስገብታችሁ ቀሪው ትኬት እናንተው ዘንድ አድርጉት ። በፕሮግራሙ መራዘም በተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች የወጣው የተወሰነ ገንዘብ ቢከስርም አብዛኛዎቹ አላህ ካለ የምንጠቀምባቸው ይሆናል ። ለአዳራሹ ተከፈለው ላይ የተወሰነ እዳ ይኑር እንጂ ፕሮግራሞች ሲስተካከሉ እንደምንጠቀምበት ነግረውናል ። ባጠቃላይ በፕሮግራሙ መራዘም የተገኙ ድሎችና የአላህ ሒክማ እኛ አሁን ያየናቸው ያሉ ሲሆን ወደፊት ደግሞ አብረን የምናየው ይሆናል ።
የአላህ መልእክተኛ 1400 ሶሓቦችን ለዛው በአላህ ትእዛዝ ወደ መካ ዑምራ ሊያደርጉ ሐርመው ይዘው መጥተው ለዘንድሮ ተመለስ በሚቀጥለው አመት ታደርጋለህ መባሉ በሶሓቦች ስነልቦና ላይ ያሳደረው ተፅኖና እናስታውስ ። ወደ መካ እየተመለሱ ሳሉ ድል መሆኑ በወሕይ ከመነገሩ ጀምሮ መካ እስከተከፈተና የተውሒድ ባንዲራ ከየአቅጣጫው ከፍ ብሎ እየተውለበለበ ወደ ካዕባ ሲያመሩ ሙሉ በሙሉ ሒክማው ለሁሉም ፍንትው ማለቱን ስናይ የድሉና የጥበቡ ውጤት በተስፋ እንድንጠብቅ ያደርገናል ።
መርሳት የሌለብን አላህ ያለ ሒክማ ምንም ነገር የማይሰራ መሆኑንና ሒክማውን ለባሮቹ በየደረጃው እንደየአስፈላጊነቱ ግልፅ የሚያደርግ መሆኑን ነው ።

http://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

12 Oct, 14:04


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ውድ የአል-ኢስላሕ መድረሳ ሳምንታዊ የእሑድ ደርስ ተከታታዮች:-
ዘወትር እሑድ በየሳምንቱ የሚሰጠው የኪታብ ቂርኣት ደርሳችን በሰዓቱ የሚቀጥል  ይሆናል።

1. የተፍሲር አስሰዕዲ ማብራሪያ (ሰአት ከ 2:30 እስከ 3:30)
በኡስታዝ አቡ ሐመውያ ሸምሱ ጉልታ ሐፊዘሁሏህ

2. ሙቀዲመቱል ኣጁሩሚየቲ ፊ ነሕው (ሰአት ከ 3:30 እስከ 4:00)
በኡስታዝ ዐብዱሶመድ ሙሐመድ ሐፊዘሁሏህ

3. አልሐቁል አውከድ ዐላ ጀሚዒል ዒባድ (ሰአት ከ 4:00 እስከ 5:00)
በኡስታዝ ዐብዱልቃዲር ሐሰን ሐፊዘሁሏህ

4. አል አጅዊበቱል ሙፊዳህ (ሰአት ከ 5:00 እስከ 6:00)
  በኡስታዝ በሕሩ ተካ ሐፊዘሁሏህ


https://t.me/medresetulislah?livestream

አል ኢስላሕ መድረሳ
t.me/medresetulislah

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

12 Oct, 03:41


قال تعالى :[[وَمَن يَعْصِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَإِنَّ لَهُۥ نَارَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا]]

<<አላህንና መልክተኛውንም የሚያምጽ ሰው ለእርሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪ ሲኾን የገሀነም እሳት አልለው፡፡>>

https://t.me/Mustefatemam

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

11 Oct, 07:59


🔷 ለዲን እውቀት ተማሪዮች

በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያላች ጡላበል ዒልሞች በሀገር አቀፉ ኮንፈረስ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉና መምጣት ከቻላችሁ የመግቢያ ትኬት ወንድሞቻችሁ ሊያመቻቹላችሁ ቃል የገቡ መሆኑን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው ። በመሆኑም አንድም የዲን እውቀት ተማሪ በትኬት እጦት ምክንያት እንደማይቀር ለመግለፅ እንወዳለን ። ነገር ግን በሚማሩባቸው መሻኢኾች በኩል መምጣት የሚኖሩባቸው መሆኑን እናሳውቃለን ።

http://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

11 Oct, 07:54


👉 በተለያዩ ቦታዎች ላላችሁ ኡስታዞችና መሻኢኾች

አንደሚታወቀው የፊታችን እሑድ በኢትዮጵያ አህሉሱንና ኢስላማዊ ማህበር አዘጋጅነት በሚካሄደው በዚህ ታላቅ ኮንፈረንስ ላይ ተሳታፊ መሆን እየፈለጉ የመግቢያ ትኬት ችግር የሚገጥማቸው ተማሪዎቻችሁን መዝግባችሁ ለአስተባባሪዎችና አድሚኖች እንድታሳውቁ ይሁን። ማንኛውም መሳተፍ የሚፈልግ ጧሊበል ዒልም እንዲሳተፍና ፈውዷ እንዳይሆን ስርዓት እንዲኖረው በማሰብ ነው። በተበታተነ መልኩ የሚመጡ ተማሪዎችን ማስተናገድ ከባድ ስለሚሆን ኡስታዞችና መሻኢኾች ብትተባበሩን።

https://t.me/conference1447

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

10 Oct, 08:01


ሰው በህመሙ ልክ ነው የሚጮኸው

አይግረማችሁ የኢኽዋን እንባ ጠባቂ የነሲሓ የእንጀራ ልጆች ይህ ፕሮግራም ቢያሳምማቸው ምን ይገርማል ? ሰለፍዮች ውጤታማ ስራ በሰሩ ቁጥር ያቅለሸልሻቸዋል ። ያስታውኩት ዝም በሏቸው ። ዝቅጠትን በጩኸት መሸፈን የሽንፈት ምልክት ነው ። ለማንኛውም በአላህ ፈቃድ ሰለፍዮች በወሬ ሳይሆን በተግባር ተውሒድና ሱናን የበላይ ያደርጋሉ ። የታመሙትን ህመማቸው በተውሒዱ ዳዕዋ የሚፈወሱ ያድርጋቸው ነው የምንለው ።

http://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

09 Oct, 12:24


👉 ውድ ሰለፍዮች ይህ ቀን አጋጣሚ የያዙት ሰዎች ለቀውት ነው የተገኘው ። ከዚህ ቀን ውጪ ወደ ታህሳስ አካባቢ ነበር ቦታ ያለው ። እኛ ደግሞ በአላህ ፈቃድ ከዛም በሰለፍዮች ርብርብ ይሳካል ብለን ይዘንዋል ። ነገ ሙሉ መክፈል አለብን ጊዜ ስለሌለ 30% አይሆንም ብለውናል ። ስለዚህ ሰለፍዮች አለን በሉ

http://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

08 Oct, 18:07


ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ ፕሮግራም አላህ እውን እንዲያደርገው እንለምነው ። ቀጥሎ ንያችንን እናስተካክል ። አላህ ተውሒድና ሱናን የበላይ እንዲያደርግና ለሰዎች ሂዳያ ሰበብ እንዲሆን ። ምክንያቱም ማንኛውም ስራ ኢኽላስና ሙታባዓ ከሌለው ከንቱ ልፋት ነውና ።
ሌላው ለተግባራዊነቱ ሁሉም የሚችለውን ያድርግ ። በመጀመሪያ ደረጃ አዳራሽ ለመከራየት ቅድሚያ 30% መክፈል ስለሚያስፈልግ ትኬት መግዛት ላይ እንበርታ ። ከሀገር ውጪ ያላችሁና አቅም ያላችሁ የሱና ቤተሰቦች በዚህ ፕሮግራም የመጀመሪያ ተጠቃሚ መሆን ያለባቸው የዲን እውቀት ተማሪዮች ናቸው ። እንደሚታወቀው እነርሱ ትኬቱን ገዝተው መግባት አይችሉም ስለዚህ ለጡላበል ዒልሞች እየነየትን አስመዝግበን ገቢ እንድርግና የመጀመሪያ እናድርጋቸው ።
ፕሮግራሙ የኢትዮዽያ አህሉ ሱና ኢስላማዊ ማህበር ጥቅምት ውስጥ ለማድረግ ነው ያሰበው ። ይህ እውን እንዲሆን በሁለት ቀን ውስጥ የሚፈለገውን ከፍሎ አዳራሽ መያዝ ያስፈልጋል ። ያውም ከተገኘ ። በመሆኑም በትኬቱ ሽያጭ ላይ እንረባረብ ።
በጣም የሚገርም ነገር ሶሞኑን በሚዲያ እንዳያችሁ እርግጠኛ ነኝ ። ይኸውም የአላሙዲን ወንድም ልጅ ሙሐመድ ሰዒድ ሊያገባ ለሰርጉ ሚሊኒየም አዳራሽ ለዲኮር አንድ ወር ወስዷል የሚል ። የሚገርመው ይህ አይደለም ለዲኮሩ ወደ 20,000000 ( ሀያ ሚሊየን ) አካባቢ የጨረሰ ሲሆን ላጠቃላይ ሰርጉ ስንት ጨርሶ ይሆን የሚለው ነው ? ተመልከቱ ሰዎች ገንዘባቸውን ለምን በምን መልኩ ወጪ እንደሚያደርጉ ። ታዲያ እኛ የአላህ ዲን የነብዩ ሱና የበላይ ለማድረግ አላህ ከሰጠን ላይ ምን ያክሉን ወጪ እናደርጋለን ?
አላህ መልካም ስራ ካገራላቸው ባሮቹ ያድርገን ።

http://t.me/bahruteka

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

08 Oct, 04:19


በአይነቱ ልዩ የሆነ ታላቅ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ

የኮንፈረንሱ መሪ ቃል “ዲናችንን ማወቅ መተግበርና ማስተማር”

🏝 የኢትዮጵያ አህለ ሱና ኢስላማዊ ማህበር ታላቅ ሀገር ቀፍ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ ጥቅምት ላይ   በአዲስ አበባ ከተማ ለማካሄድ አስቧል።
ለዚህ ፕሮግራም የአዳራሽ ኪራይ፣ ለተሳታፊዎች ሻይ ቡና ፣ ለዑለማዎች ትራንስፖርትና ማረፊያ ወዘተ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን እንዲቻል የአንድ ሰው መግቢያ ትኬት 1000 ብር ነው።

🔹 ስለሆነም ትኬት በአካል መግዛት ለምትፈልጉ፦
➡️  አል ኢስላሕ መድረሳ
➡️  ዳሩ ሱና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

🔹በባንክ አካውንት ለምትጠቀሙ
የባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000650550718
          ሙሒዲን ሳሊሕ እና ዩሱፍ ኸድር

የኢትዮዽያ አህሉ ሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

07 Oct, 03:19


https://t.me/medresetulislah?livestream

🎤ሙስጠፋ (አቡ ዐብዱረህማን)

06 Oct, 20:10


''የ ሙስሊሞች ተጨባጭ ሁኔታ እና ከገቡበት አረንቋ መውጫ መንገዱ - ከሸይኽ ረቢዕ ምክሮች'' በሚል ርዕስ በተከታታይ ስድስት ክፍሎች በቻናላችን ሲለቀቅ የነበረዉ የሸይኽ ረቢዕ ብን ሀዲ አልመድኸሊ ወቅታዊ ምክር የተተረጐመበት ፅሁፍ እነሆ በ PDF ተዘጋጅቶ ለአንባቢያን ቀረበ ።

ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን
አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን!
የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

كن على بصيرة

https://t.me/alateriqilhaq

2,060

subscribers

222

photos

31

videos