አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ @ewnet1nat Channel on Telegram

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

@ewnet1nat


በዚህ የንጽጽር አደባባይ በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክታት የተገለጸው እውነት ሲፈጸምና ይፈጸም ዘንድ በመላው ዓለም ሲንቀሳቀስ የሚከሰቱ ጉዳዮችን እናቀርባለን ! ስለእምነታችን እንማማራለን ! ስለመልዕክታቱ እንነጋገራለን !
➝ ይህ የአልፋና ዖሜጋ ( @christian930 ) ገጽ ቅርንጫፍ የንጽጽርና የመማሪያ ገጽ ነው።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (Amharic)

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ በዚህ የንጽጽር አደባባይ በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክታት የተገለጸው እውነት ሲፈጸምና ይፈጸም ዘንድ በመላው ዓለም ሲንቀሳቀስ የሚከሰቱ ጉዳዮችን እናቀርባለን! ስለእምነታችን እንማማራለን! ስለመልዕክታቱ እንነጋገራለን! ይህ የአልፋና ዖሜጋ (@christian930) ገጽ ቅርንጫፍ የንጽጽርና የመማሪያ ገጽ ነው።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

26 Jan, 11:12


📌 መስፈርቱ ግልጽ ነው።
ግልጽ ነው።

ኢትዮጵያዊነት

ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ እምነትን መጨበጥ

ሰንደቋን የቃል ኪዳን ምልክቷን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ታምኖበት መቀበል።

ከልብ ነው ከልብ መቀበል።

እግዚአብሔር የሰጠንን የቃል ኪዳን ቃሎች
ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር
ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ
እነዚህን አምኖ መቀበል ከዚህ የጎደለ እግዚአብሔር ያጸደቀውን የዘመኑን የቃል ኪዳኑን ተስፋ የናቀ ያቃለለ እንኳን ለትንሣኤ ተስፋ ሊያደርግ ኑሮ !!
አሁን ከሚመጣው መቅሰፍት እየተከናወነ ካለው መቅሰፍት ከሚከብደውም ቁጣ  ከዛ ሁሉ አያመልጥም ይህ ግልጽ የማያሻማ መስፈሪያ መሆኑን እንድታውቅ መላው የአዳም ዘር ኢትዮጵያዊ ሆንክ የውጭ ዜጋ ሆንክ ማንም ሆንክ የአዳም ዘር በሙሉ ይሄ መለኪያ  ተቀምጧል።ከፍታ ዝቅታ የለውም።
⚡️ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ማን ናት ?ከሚለው ትምህርት ክፍል 1 _መ  ላይ የተወሰደ።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

26 Jan, 11:11


ዮሐንስ 10 ፥20-21

20፤ ከእነርሱም ብዙዎች፡— ጋኔን አለበት አብዶአልም፤ ስለ ምንስ ትሰሙታላችሁ? አሉ።
21፤ ሌሎችም፡— ይህ ጋኔን ያለበት ሰው ቃል አይደለም፤ ጋኔን የዕውሮችን ዓይኖች ሊከፍት ይችላልን? አሉ።
=========================
ዛሬ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ከዚሁ ምዕራፍ ቁ 18 ላይ
እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።
ብሎ ስለነፍሱ ሲናገር ቁ 19 እንደሚነግረን

እንግዲህ ከዚህ ቃል የተነሣ በአይሁድ መካከል እንደ ገና መለያየት ሆነ።ይለናል።

ታድያ ዛሬ የምናየው ከቃሉ የተነሣ የተለያዩ ሰዎች የተናገሩትን በማንሣት አሁን ካለንበት ወቅት ጋር እያነጻጸርን እንመለከታለን።
በማያስተውሉት
ጎራ ያሉት  ጋኔን አለበት አብዶአል ስለምንስ ትሰሙታላችሁ?ሲሉ

በሚያስተውሉት በኩል  ያሉት ሌሎች ደግሞ ይህ ጋኔል ያለበት ሰው ቃል አይደለም ጋኔን የእውሮችን ዓይኖች ሊከፍት ይችላልን? አሉ።በእውነት አስተዋዮች ናቸው።
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ጎባጣ ሲያቀና ለምጽ ሲያነጻ ሙት ሲያስነሣ ብቻ ብዙ ታምራት ሲያደርግ እያዩ እነዛ የማያስተውሉት ጋኔን አለበት አትስሙት እብድ ነው አሉ።
አስተዋዮች ግን አይ ይሄማ የእብድ ቃል አይደለም አሉ።
ዛሬ ላይ እኮ የጠፋው እንደነዚህ ያሉ አስተዋይ ሰው ነው።
በውኑ ከ1998 ዓ,ም ጀምሮ በእግዚአብሔር ባሮች የተነገረው ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት ያለው ሁሉ እየሆነ ምልክቱ በሙሉ ታይቶ አሁን ላይ ወደ ፍጻሜው እየገሠገሠ አይደለምን?
ነገር ግን የማያስተውሉት መልእክቱን የእብድ ቃል መልእክቱን ሰምተው ንስሓ ገብተው በእምነትና በእውነት እየተመላለሱ ያሉትን ደግሞ እብዶች ናቸው ጸበል መጠመቅ ያስፈልጋቸዋል በሽተኞች ናቸው ይላሉ።
እንግዲህ እኛ የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች እድሜ ለእውነተኛ የእግዚአብሔር ባሮች ይሁን እና በመልእክታቸው በትምህርታቸው በመግለጫቸው በምክራቸውና ማሳሰቢያቸው። ቃሉን ሰምተን በእምትና በእውነት ሆነን እግዚአብሔርን እንድናመልክ እውነትን እንድንከተል ስላስተማሩን እና የመመዘኛ ቃሉንም ስለነገሩን።
ስም ዝና ትልቅነት
ቆብ እና ካባ   ረጅም ጺም አይሸውደንም
በእድሜም በትልቅ ሰውም አንሸወድም።
ዛሬ በተናገረው  የእውነት ቃል ብጹዕ ብንለውም መመዘኛ /የእውነት መስፈርቱን አውቀናልና አንታለልም።
ይህንም የተማርነው ከእኔ የተማሩ  ካለው ከመድኃኔ ዓለም ነው።
ያኔ ቅዱስ ጴጥሮስ መልካም በተናረበት ስአት ብጹዕ ነህ አለት ነህ
አለው ወዲያው የሰይጣን መጠቀሚያ ሲሆን ደግሞ ሂድ አንተ ሰይጣን  አለው በቃ እውነተኛ  እውነት አያዳላም አይ ትናንት ብጹዕ ብየው እንዴት ዛሬ ሰይጣን ልበለው አላለም። ምክንያቱም ፊት አይቶ የማዳላ እውነተኛ መምህር ነውና።

ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮቶስ ስዎች በላከው መልእክቱ እንዲህ አለ።


2 ቆሮንቶስ 5 ፥13 ላይ
እብዶች ብንሆን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆን፥ ለእናንተ ነው።
ሲል ተናገረ።
ዛሬም እኛ የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች እብዶች የተባልነው።
በመልእክቱ በተነገረን መሠረት አሻግረን አይተን እግዚአብሔር ለአባቶቻችን የገባውን ቃል ይፈጽመዋል ብለን አምንን
በፈጣሪቻን ስም በእናታችን ድንግል ማርያም ስም በቅዱሳን መላእክትና በቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ስም ጽዋ ስለጠጣን
የሊቀ ሊቃውንት አያሌው ውግዘት ይፈታ
ስላልን
አስራት በኩራታችንን ልክ አብርሃም ለካህኑ መልከ ጼዴቅ እንደሰጠ እኛም ለእውነተኛ አገልጋዮቹ ስለሰጠን
የቤተ ክርስቲያን ስርዓት ይከበር
ባልን እብዶች ተባልን። እብዶች ያሉን በጨበጥነው እውነት እንጅ ጤነኞች እንደሆንን ያውቃሉ።
ስለዚህ አሰመሳይነትን አድርባይነትን
ልማድን እና ግማሽ እውነት ግማሽ ሀሰት የተቀላቀለ መርዛማ ወይም ሽባና ፍሬ አልባ ንግግርን በቃን ብለን ስለተጸየፍን እብዶች ተባልን።
እንግዲህ ማን እብድ ማን በሽተኛ  ማንስ ጸበል መጠመቅ ያስፈልገዋል የሚለውን የሁሉ ፈጣሪ ደኛ ስላለ ለእሱ ትተነው።
በ26ኛ ታምረ ማርያም ላይ እንደተጻፈው ዲያብሎስ በመነኩሴው ቀንቶ  ጻድቅ መስሎ መነኩሴውን እንዴት ሊያሳስተው እንደነበርና እመቤታችን ደርሳ እንዳዳነቸው ስለተጻፈ ሁላችንንም ጻድቅ መስሎ ከሚያሳስት አፈ ጻድቅ ሰው እመቤቴ ትሰውረን።
ታድያ ዛሬም ሆነ ነገ ከነገ ወዲያም የሁላችን መመዘኛ እውነት ብቻና ብቻ ነው ይህም የሁልጌዜ መገለጫችን ይሆናል።

ሁሉ ነገር ተፈጽሞ እስኪጠናቀቅ ደረስ ተቺዎች ናቃፊዎች ጭምብላቸውን እየቀያየሩ አብድ ጋኔን እያሉ  ሲመጡ።
በዚህ መሃል ደግሞ አይ ይሄማ የእብድ ወይም ጋኔን ያደረበት ሰው ቃል አይደለም ብለው የሚያሰተውሉትን ያበዛልና እግዚአብሔር ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን እሱ ሳይፈቅድ የሚሆን ነገር እንደሌለ ተምረናልና።

ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር

ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን

ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ።
ትሆናለች። ሰይጣን ተቃጠል።

እንግዲህ እነዚህ ቃል ኪዳኖች ይከበራሉ።
እነዚህን ቃል ኪዳኖችንም ለማጣጣል እና ሰው እንዳይቀበላቸውጰለማድረግ
  እንዲህ የሚል የተጻፈ የለም ይላሉ።
ቆይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ አለም ከመምጣቱ በፊት በነቢያቱ ላይ አድሮ  ሲመጣ የሚያደርጋቸውን ሁሉ ሙሉ ለሙሉ ተናግራልን?
በቤተልሔም እንደሚወለድ ተነግሯል ግን በከብቶች በረት እንደሚወለድና በጨርቅ እንደሚጠቀለል ተጽፏልን?
እሺ ወደ ግብጽ እንደሚሰደድ ተነግሯል
ወደ ኢትዮጵያስ መጥቶ አክሱምን ጣናን ኤረርን መሳሰሉት እንደሚያይ ተጽፏል?
እሺ በ2 ዓሳ በ5 እንጀራ ብዙ ሕዝብ እንደሚያጠግብና ብዙ ትርፍራፊም እንደሚነሣ ተጽፏል?
እሺ ዶኪማስ የሚባል ሰው ሰርግ ጠርቶት እንደሚሄድና
ውሃውን ወደ ወይን ጠጅ እደሚቀይረውስ ተጽፏልን?
እሺ እንደው በወንጌል የተደረገው በሙሉ ተነገሯል?
ታድያ በወቅቱ የነበሩት ጸሀፍት ፈሪሳውያን
የጌታችንን ሥራ እያዩ በመጻፋቸው ያልተጻፈ እንግዳ ነገር ሲያዩ መቃወማቸውና ሰቅለው መግደላቸውስ ትክክል ነው ማለት ነው?
ምክንያቱም ሁሉ አልተጻፈማ!!
ዛሬ ላይ ታድያ አይሁድን የሚኮንነው ትውልድ ከአይሁድ የባሰ ሆኖ ሲታይ ይደንቃል።

አባት ሆይ የሚሰሩት አያውቁምና ይቅር በላቸው እንዳለው።
የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃንን መልእክት ፍጻሜ ሳያዩ ለሚነቅፉ ለሚተቹ ቤተሰቡን ለሚጠሉ ለሚያሳድዱ በሙሉ አስተዋይ ልቡና ይስጣቸው።
ምክንያቱም መተቸት የነበረባቸው ሁሉ አልቆ ተፈጽሞ በመልእክቱ እንደተባለው ሳይሆን ሲቀር ሰላሙም መጥቶ ምድር ሰላም ሆና የዲያብሎስ አገዛዝ አሸናፊ ሆኖ ሲጠናቀቅ ነበር በጣም ለመተቸት ቸኮሉ እንጂ!!
አሁንም አስተዋይ ልቡና ይስጣቸው።
ከዚህ ውጭ ሌላ ምን ይባላል።
18/5/2017 ዓ,ም

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

26 Jan, 04:59


🟢🟡🔴
ጥር 18 | በዚች ቀን የምናከብራቸው፦

#የሰማዕታት_አለቃ_የቅዱስ_ጊዮርጊስ ዐፅሙ ተቃጥሎ፣ ተደቁሶ የተበተነበት ነው፡፡

ይኸውም ሰባ ነገሥታት ማሰቃየት በሰለቻቸው ጊዜ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ መጭመቂያ ሆኖ ከተሠራ የስቃይ መሣሪያ ላይ አውጥተው ሰውነቱን ሰነጠቁት፡፡ አንጀቱም ወጥቶ ተዘረገፈ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከስቃይ ብዛት የተነሣ ነፍሱ ከሥጋው ስትለይ ሥጋውንም በሙሉ በእሳት አቃጠሉት፤ አመድም ሆነ፡፡

የሥጋውንም አመድ ይድራስ ተራራ ላይ በነፋስ ዘሩት። ሲመለሱም የሥጋው አመድ ያረፈበት ዕፅዋት ሁሉ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ አሉ። ጌታችንም ነፋሳትን አዝዞ ሥጋውን ሕያው አደረገው።
🌿

#ኢትዮጵያዊው_ጃንደረባ #ቅዱስ_ባኮስ ዕረፍቱ ነው፨

ይህም ለኢትዮጵያ ንግሥት በገንዘቧ ላይ የተሾመ፣ ኢየሩሳሌም እየሔደ የሚሳለም መልካም ሰው ነበር።

ተሳልሞ ሲመለስ ሲመለስ መንፈስ ቅዱስ ከፊልጶስ ጋር በጋዛ አገናኝቶታል። በዚያም ምሥጢረ ክርስትናን ተምሮ፣ በክርስቶስ አምላክነትና አዳኝነት አምኖ ተጠምቋል።

ክርስትናን ለኢትዮጵያ በ34 ዓ/ም አምጥቷል። "ጃንደረባው ለወገኖቹ ሐዋርያ ሆነ" ሲል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደ ተናገረው ወደ ሃገራችን ተመልሶ ስለ ክርስቶስ ሰብኮ በርካቶችን አሳምኗል።

ቀጥሎም መንኖ ከኢትዮጵያ እስከ ሕንድ ወንጌልን ሰብኮ በሰማዕትነት ዐርፏል (ተሰውሯል የሚሉም አሉ)።
🍀

የአልዓዛር እኅቶች #ቅዱሳት_ማርያ_እና_ማርታ መታቢያቸው ነው፨
🍀

#አቡነ_ቴዎድሮስ ልክ እንደ አቡነ ሐራ ድንግል በቃላቸው ገዝተው ነብርንና ሚዳቋን ያስማሙ ጻድቅ ዕረፍታቸው ነው።
🍀

#ቅድስት_ጸበለ_ማርያም የልደቷ መታሰቢያ ነው
🍀

#ቅዱስ_አባ_ያዕቆብ_ዘንጽቢን ዕረፍቱ ነው።

ይህ አባት ከ318ቱ ሊቃውንት አንዱ፣ የቅዱስ ኤፍሬም አስተማሪ ነው።

t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

25 Jan, 16:15


መጨረስ በራሱ ታላቅ ነገር ነው ወገኖቼ!!
-----/////////-------/////////--
በሩጫ የሚሮጥ ሰው ውድድር ውስጥ የገባ ሰው፡፡42 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውስጥ ገብቶ ከሆነ ያን ለመጨረሽ ብዙ ይሮጣል ብዙ  ይደክማል ፡፡ብዙዎች አስር ሺሆች ሆነው ሲሮጡ አይታችኀችኀል፡፡
ወደ መጨረሻ የሚመጡት  መቶ ሰው ሁለት መቶ ሰው   ምናምን ነው ወደ መጨረሻ የሚመጣው፡፡
መጨረስ በራሱ ታላቅ ነገር ነው፡፡ወገኖቼ !!
በማረግ በአንደኝነት በሁለተኝነት በሥስተኝነት በዓራተኝነት በአምስተኝነት በአስረኝነት እያለ መውጣቱን ተውት፡፡መጨረስ በራሱ በጎዳናው ላይ በሩጫው ላይ ተገኝቶ እፍጻሜው ድረስ መሄድ   ትልቅ ነገር ነው ወገኖቼ !!
📌 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
እምነት  ፤ ተስፋ ፤ ፍቅር ትምህርት  ክፍል -3ቀ ላይ የተወሰደ፡፡

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

25 Jan, 16:15


ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅም።
===================
ለነቢዩ ኢሳይያስ የተገለጸለት
ለነቢዩ ኤርምያስ የተገለጸለት
ለነቢዩ ሕዝቅኤል የተገለጸለት
እንዲሁም ለሁሉም ነቢያቶች የተገለጸላቸው ይለያያል።
ነገር ግን አንዱ ነቢይ ሁሉንም እኔ ብቻ ነው የማውቅ ብሎ ሌላውን ነቢይ ሲነቅፍ ሲተች አልታየም።
ለምሳሌ ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና እንደምትወልድ ስሙንም አማኑኤል እንደምትለው ለነቢዩ ኢሳይያስ ተገልጾለት።ተናገረ።
ለነቢዩ ኤርምያስ ደግሞ በሠላሳ ብር እንደሚሸጥና ክርስቶስ እንሚባልም ተገልጾለት ተናገረ።
ነቢዩ ሚክያስም ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም እንደሚወለድ ተገልጾለት ተናገረ።
ሁሉም እግዚአብሔር የገለጸላቸውን ተናገሩ።
እግዚአብሔር እኮ ሁሉንም ለነቢዩ ኢሳይያስ  ገልጾለት ሁሉንም መናገር ይችል ነበር የሁሉም ክብር ይገለጽ ዘንድ እንጂ።
እናም ነቢዩ ኢሳይያስ  ሁሉንም አውቃለሁ ብሎ ነቢዩ ሚክያስ የተናገረውን ውሸት ነው ክርስቶስ በቤተልሔም አይወለድም አላለም።
ስለዚህ ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅምና
ሁሉን አውቃለሁ ብሎ ምሥጢሩን ሁሉ ሳይመረምር ዝም ብሎ ከሚናገር ሰው በዚህ ዘመን መራቅ ብልህነት ነው።

ማቴዎስ 11፥6 ላይ እንደተጻፈው።ጌታ
ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።

ሲል ተናገረ።እውነት በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት የማይሰናከል ምንኛ ብጹዕ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይና ምድርን አሳልፎ ለፍርድ የሚመጣው እኮ ቀድሞ መጥቶ ተወልዶ ተጠምቆ ተርቦ ተጠምቶ ንስሓ ግቡ ብሎ የታመሙትን ፈውሶ ለምጻሞችን አንጽቶ ወንጌልን አስተምሮ ተሰቅሎ ሙቶ ተነስቶ አርጎ ይህንን ሁሉ አድርጎ ቃሉን በናቁት እና ባቃለሉት ላይ ነው የሚፈርደው።ይህንን ሁሉ ባያደርግ ኑሮ ለፍርድ ባልመጣም ነበር።
ታድያ ዛሬስ በዚህ አመጸኛ ትውልድ ላይ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን የተሠጠው ንጉስ ቴዎድሮስስ ቀድሞ ሳያስተምር የሚገሰጸውን ሳይገስጽ ሳያስጠነቅቅ እንዴት ይመጣል?
የሚፈርደው እኮ በዚህ መልእክቴ እንዲህ አላልኩህም ነበር?ለምን ቃሉን ሰምተህ ንስሓ አልገባህም ብሎ እኮ ነው?

እናም ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃንን መልእክትን  አጣጥሎ ልክ አዲስ እምነት እንደሆነ አድርጎ ህዝቡን ማሰናከል እጅግ ከባድ ፍርድ ውስጥ መግባት ነውና።
ሁሉም ሰው ሁሉን እንደማያውቅ ተረድተን መልእክቱ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን አምነን እስከ መጨረሻው ድረስ መጽናት ከመታደልም በላይ መታደል ነው።
የእግዚአብሔር እውነት ሁሌም አያዳላም።
ዲያቆን ቄስ ጳጳስ መነኩሴ መምህር ብሎ አያዳላም ካጠፋ አጠፋ ነው ንስሓ እንዲገባ ይገስጻል።ያማ ካልሆነ ምኑን እውነት ሆነ ታድያ?
ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅምና በማንኛውም ሰው መሰናከል ከእውነት ፈቀቅ ማለት እውነትን አለማወቅ ነውና እስከ ሞት ድረስ የታመንን እንሁን
እውነት አርነት ያወጣናል እና።
ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅም። አራት ነጥብ።
17/5/2017

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

25 Jan, 05:13


የሟቾቹ ቁጥር ከ40 በላይ ሆኗል❗️

በሰሜን ወሎ ዞን ዳውንት ወረዳ ኩርባ ከተማ መነሻውን ያደረገ የሕዝብ ማመላለሻ በተለምዶ "ቅጥቅጥ" አውቶብስ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ እስካሁን ባለው መረጃ ሹፌሩን ጨምሮ የሟቾቹ ቁጥር "ከ40 በላይ ነው" ያሉ አስከሬን ያነሱ ነዋሪ።

ትላንት ጥር 15 2017ዓ.ም   ከጥዋቱ 12:00 ከኩርባ ከተማ ተነስቶ ወደ ደሴ ከተማ ሲጓዝ ነው አደጋው የደረሰው።

የዳውንት ወረዳ ፖሊስ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ጌታቸው አራጌ ታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3-32917 የኾነ  የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከኩርባ ከተማ በግምት 9 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ልዩ ቦታው 04 ቀበሌ ሰጎራ ከተባለ አካባቢ "መታጠፊያ ስቶ" ወደ ገደል በመግባቱ አደጋው እንደደረሰበት ገልጸዋል።

ተሽከርካሪው 28 መንገደኞችን የማሳፈር አቅም ያለው ቢሆንም ከ60 በላይ መንገደኞች አሳፍሮ እንደነበር የተናገሩት አስተባባሪው "ሰው በሰው ላይ ተደራርቦ ነው የሚሄደው" ሲሉ ሁኔታው የተለመደ መሆኑን ተናግረዋል።

"መኪናው ሙሉ ለሙሉ ገደል ገብቶ፤ ገደሉን ጨርሶ እርሻ ላይ ነው ያረፈው" ያሉ ከአደጋው በኋላ ወደ ቦታው የደረሱ አንድ የዓይን እማኝ፤ ተሽከርካሪው የወደቀበት ስፍራ ከመንገዱ በ10 ደቂቃ የሚርቅ ነው ብለዋል።

መንገደኞቹ ለተለያየ ጉዳይ ወደ ደሴ ሲጓዙ የነበሩ የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውን የገለፁ አንድ ነዋሪ፤ በአብዛኛው ለህክምና የሚጓዙ ሰዎች፣ ተማሪዎች እና የመንግሥት ሠራተኞች እንደነበሩ ጠቁመዋል።

ከሰሜን ወሎ ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጂዎች በደላንታ እና  ደሴ ሆስፒታሎች ተወስደዋል።

አደጋው፣ እጅግ ዘግናኝና አሀዋሳው የሰርገኞች አደጋ ጋር ቢመሳሰልም፣ በአማራ ክልል የሆነ በመሆኑ ትኩረት አላገኘም።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

24 Jan, 20:18


'' ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።''
የዮሐንስ ወንጌል 1 : 5

ስለ ሁሉም ነገር ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን!

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

24 Jan, 17:56


ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
የኢትዮጵያንና የተዋሕዶን ትንሣኤ የሚመሰክር
መልዕክት እንጂ
እምነት አይደለም !!

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

24 Jan, 03:38


ዕለቱም ለ13 ሌሊት 7 ሰዓት ገደማ ነበር። በጣም ብዙ መኪኖችም ከስፍራው ለማስወጣት በተደረገ ጥረት ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተሰምቷል።

#ዘመኑ_የመቅሰፍት_ነው
t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

23 Jan, 17:43


https://telegra.ph/ስቃያችሁ-ጋብ-የሚለው-ለጥቂት-ደቂቃዎችም-ቢሆን-እንቅልፍ-የሚያሸልበው-በኔ-በልዑል-ባሪያ-የተላለፉትን-መልእክቶች-ከአንድ-ጀምሮ-እስከ-አሁኑ-ሰዓት-የወጡትን-መልእክቶች-በሙሉ-በይፋና-በአደባባይ-በማስሚዲያ--01-23

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

22 Jan, 17:44


ሁሉንም በአንድ የያዘ ስማርት ካርድ ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሰራ ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የፋይዳ መታወቂያ ቁጥር የያዘ፣ የመንጃ ፍቃድ ቁጥር ያለው እንዲሁም እንደ ኤቲ ኤም ካርድ የሚያገለግል ሁሉንም በአንድ የያዘ የነዋሪነት መታወቂያ ስማርት ካርድ ወደ ሥራ ለማስገባት በፕሮጀክት ደረጃ እየሰራ መሆኑን ጠቅሷል።

የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያን ስማርት አርጎ አሁን ከምንጠቀምበት የተሻለ ተደርጎ ሰዎች የተለያዩ ካርድ ይዘው ከሚንቀሳቀሱ ሁሉንም አገልግሎቶችን በአንድ የያዘ ካርድ በቀጣዮቹ 6 ወራት ውስጥ ወደ አገልግሎት ለማስገባት በእቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኤጀንሲው ሰምቷል።

ኤጀንሲው ለቲክቫህ እንደገለፀው ይህ ጉዳይ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ትስስር ሊኖር እንደሚገባና በአሁኑ ሰዓትም ፋይዳ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ለወደፊት ደሞ ስራው ተጠናቆ ካርዱ ወደስራ ሲገባ ባንኮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት የጋራ ትብብር እንደሚፈጠርም ተገልጿል።

ይህ አገልገሎት በሚቀጥሉት 6 ወራት ውስጥ ወደ ስራ ለማስገባት እቅድ የተያዘለት ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ማሳያዎች (Samples) እየተሰራ ይገኛል።

❗️ የዮሀንስ ራዕይ:- ም 13:16:- ታናናሾችና ታላላቆችም፣ባለጠጎችና ደሀዎችም፣ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግንባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፣የአውሬውን ስም ወይም የስሙ ቁጥር ምልክት የሌለው ማንም ሊገዛም ወይም ሊሸጥም እንዳይችል ያደርጋል፣ ጥበብ በዚህ አለ፣አእምሮ ያለው የአውሬውን ቁጥር ይቁጠረው፣ ቁጥሩ የሰው ቁጥር ነው፣ቁጥሩም 666 ነው" ይላል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

22 Jan, 17:27


🟢🟡🔴
ጥር 15 | #ቅዱስ_ቂርቆስ እና ቅድስት_ኢየሉጣ ሰማዕት ሆኑ፨

ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ብጽዕት ኢየሉጣ የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ናቸው። በጊዜው በሮም ግዛት ሥር እስክንድሮስ የሚሉት ክፉ ንጉሥ ነግሦ ነበርና ብዙ ክርስቲያኖች ተሰደዱ። ጣዖትን ላለማምለክም ተሰዉ።

እኚህም ቅዱሳን ለመከራ ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ። በግርፋት የጀመረ ስቃይ ሊሰሙት እስከሚጨንቅ መከራ ቀጠለ።

🌿 7 ብረት አግለው በዐይናቸው፣ በጆሯቸው፣ በአፋቸውና በልባቸው ከተቱ፣

🌿 በ4 ችንካሮች ላይ አስቀመጧቸው፣

🌿 በእሳት አቃጠሏቸው፣ ጸጉራቸውን ከቆዳቸው ጋር ገፈፉ...

ከብዙ ስቃይ በኋላ በእኩለ ሌሊት አንገታቸውን ሊሰየፉ ሲሉ ለስም አጠራሩ ስግደት የሚገባው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወረደ። ሕፃን ቂርቆስንም የምትሻውን ለምነኝ አለው።

ሕፃኑም፦ ሥጋዬ በምድር አይቀበር። ስሜን ለሚጠራ፣ መታሰቢያዬን ለሚያደርግ፣ ቤተ ክርስቲያኔን ለሚሠራ፣ የተጋድሎዬን መጽሐፍ ለሚጽፍና ለሚያጽፍ ወይም ለሚያነበው፣ ለቤተ ክርስቲያኔ መባ ለሚያገባ በውስጧም ለሚጸልይ ለሁሉም ፍላጎታቸውን ስጣቸው። ኃጢአታቸውንም ይቅር በል።

ስሜም በሚጠራበት በዚያች ቦታ የከብት ዕልቂት አይምጣ። በሰውም ላይ አባር ቸነፈር በእህልም ላይ ድርቅ የውኃም ማነስ አይሁን
።"

መድኃኒታችንም "የለመንከኝን ሁሉ እሰጥሃለሁ። አንተም በቀኜ ትኖራለህ። ሥጋህንም ኤልያስ በዐረገበት ሠረገላ ውስጥ አኖራለሁ አለው።" ሕፃን ቂርቆስም ገና በ2 ዓመት ከ9 ወሩ ለሰማዕትነት እጅግ ደስ ብሎት ጌታችንን አመሰገነው።

ከዚህም በኋላ በሌሊቱ እኩሌታም ከእናቱ ጋር አንገቱን ተቆረጠ። መድኃኒታችንም በማይጠፋ አክሊል ጋረደው ነፍሶቻቸውንም በታላቅ ክብር ከእርሱ ጋር አሳረገ።

T.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

22 Jan, 16:45


ከጅቡቲ የተነሳች ስደተኞችን የጫነች መርከብ የመን አቅራቢያ በደረሰባት የመስጠም አደጋ ቢያንስ 20 ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸው ማለፉን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ዐሳወቀ። ከአደጋው 15 ኢትዮጵያውያን እና ሁለት የመናውያን የጀልባዋ ቀዛፊ እና ረዳቱ መትረፋቸውም ተገልጿል። 35 ስደተኞችን አሳፍራ ከጅቡቲ የተነሳችው ጀልባ ዱባብ አቅራቢያ ባጋጠማት ብርቱ ነፋስ ለአደጋው መጋለጧን ዓለም አቀፉ ድርጅት አመልክቷል። በየመናዊ ካፒቴን እና ረዳቱ አማካኝነት ከጅቡቲ የባሕር ጠረፍ ጀልባዋ ስደተኞች አሳፍራ ቅዳሜ ዕለት በምሽት ነበር ጉዞ የጀመረችው። አደጋው በርካታ ስደተኞች የሚጋፈጡትን አሳዛኝ አደጋ እንደሚያሳይ የገለጸው ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለሕገወጥ ስደት መንስኤ ለሆኑ ችግሮች መፍትኄ እንዲፈልጉ ጥሪውን አቅርቧል። በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ፍለጋ በጅቡቲ በኩል ወደ የተለያዩ የአረብ ሃገራት እንደሚሰደዱ በተደጋጋሚ ይነገራል። ባለፈው ጥቅምት ወርም በተመሳሳይ አደጋ ከጅቡቲ የተነሱ 45 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የተሳፈሩበት ጀልባ በደረሰበት አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።  የየመን ባሕር አካባቢ ለስደተኞች አደገኛ ከሆኑ የባሕር መስመሮች አንዱ መሆኑን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አመልክቷል። ኢትዮጵያውን ስደተኞች ላይ ስለደረሰው አደጋ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተሰማ ነገር የለም። DW Amharic

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

22 Jan, 03:13


#ጥር_14
#አቡነ_አረጋዊ የተወለዱበት እና ቅድስት ደብረ ዳሞን የወጡበት በዓል ነው።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

21 Jan, 20:04


በሰሜን ምዕራብ ቱርክ ቦሉ ግዛት በሆቴል ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ ቢያንስ 66 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ
*****

በሰሜን ምዕራብ ቱርክ ቦሉ ግዛት በሆቴል ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ ቢያንስ 66 ሰዎች ሞተው 55 ሰዎች መጎዳታቸውን የግዛቲቱ ባለስልጣናትን ጠቅሶ አልጀዚራ ዘግቧል።

"በአደጋው የ66 ዜጎቻችንን ሕይወት አጥተናል፤ በጥልቅ ሀዘን ውስጥ ነን" ሲሉ የቱርክ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ዬርሊካያ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Jan, 16:29


🟢🟡🔴
ጥር 12 | #በዓለ_ቃና_ዘገሊላ

ቃና ከገሊላ አውራጃዎች አንዷ ናት። ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ በዚህች ሥፍራ ተገኝቶ በድንግል እናቱ ምልጃ ታላቅ ተአምርን በዚህች ዕለት ሠርቷል።

ትክክለኛው የቃና ዘገሊላ ቀን የካቲት 23 ነው። ጥር 11 ተጠምቆ፣ የካቲት 21 ቀን ከጾም ተመልሷል። ከዚያም የካቲት 23 ቀን ደቀ መዛሙርቱን ሰብስቦ ሒዷል። ነገር ግን አበው መንፈስ ቅዱስ እንደ መራቸው የውሃ በዓል ከውሃ በዓል ጋር ይስማማል ብለው ጥር 12 ቀን አድርገውታል።

በቃና ዘገሊላ ሙሽራው ዶኪማስ ሲሆን ባለ ሠርጉ ደግሞ አባቱ ዮአኪን ነው። ይህም ለሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል አጎቱ ነው። የልጁ ጋብቻ የተቀደሰ ይሆን ዘንድም ጌታ ክርስቶስን፣ ድንግል እናቱንና ባለሟሎቹ ሐዋርያትን ወደ ሠርጉ ጠራ።

ምንም እንኳ መድኃኒታችንና እመቤታችን ከድግሱ የማይበሉ ቢሆኑም (በትሕርምት ኗሪዎች ነበሩና) ጠሪውን ደስ ለማሰኘት ሠርጉን (ብቻውን) ለመቀደስና የጋብቻን ክቡርነት ለማሳየት አብረው ታደሙ።
🍀

በዚህች ቀን የከበረ መልአክ #የመላእክት_አለቃ_ሚካኤል እስራኤል ወደ ተባለ #አባታችን_ያዕቆብ እግዚአብሔር ላከው።

ከወንድሙ ከኤሳውም ፈርቶ ሳለ አዳነው። ዮርዳኖስንም አሻግሮት ወደ እናቱ ወንድም ወደ ላባ ሔደ።
🍀

ዳግመኛም #ቅዱስ_ሚካኤል በመከራው ሁሉ ሲያጸናው የነበረው #ቅዱስ_ቴዎድሮስ በናድሌዎስ ዕረፍቱ ነው፨

ኃያል ቅዱስ ቴዎድሮስ በናድልዮስ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በምሥራቅ (በአንጾኪያ) ያበራ፣ ድንግል፣ የሠራዊት ሁሉ አለቃ የነበረ፣ እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የሚያመልክ የወቅቱ ወጣት ክርስቲያን ነው።

በዚህች ቀንም ከቅዱሳን ለውንድዮስና ኒቆሮስ እንዲሁ ከ2.5 ሚሊየን ሠራዊቱ ጋር ለመከራ ተሰጥቷል። እርሱንም በ153 ችንካር ወግተው ገድለውታል።
🌿🌿

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Jan, 14:38


በካሊፎርኒያ ዋና የኃይል ማመንጫ ላይ የእሳት አደጋ ተከሰተ

እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ፤ በዓይነቱ ከዓለማችን ግዙፍ ተቋማት አንዱ የሆነው የሞስ ላንዲንግ ኃይል ማመንጫ፤ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሊቲየም ባትሪዎችን ይዟል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Jan, 14:37


🇪🇸 በስፔን አስቱን ሪዞርት የበረዶ መንሸራተቻ ሊፍት ወደቆ ​​በትንሹ 30 ሰዎች መጎዳታቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Jan, 14:36


🇳🇬 በሰሜን ናይጄሪያ የደረሰው አሳዛኝ የነዳጅ ታንከር ፍንዳታ ከ70 በላይ የሰዎች ህይወትን ቀጠፈ

በኒጀር ክልል የተከሰተው አደጋ ባለፈው ጥቅምት ወር በጂጋዋ ግዛት የ147 ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈው ተመሳሳይ ፍንዳታ በኋላ የመጣ ነው።

ብሔራዊ የድንገተኛ አደጋ መከላከል ባለስልጣን ከ70 በላይ አስከሬኖች መገኘታቸውን፣ 56 ግለሰቦች መቁሰላቸውን እና ከ15 በላይ ሱቆች መውደማቸውን አስታውቋል። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ሟቾችን የመፈለግ ስራ ቀጥሏል።

በኒጀር ክልል የፌደራል የመንገድ ደኅንነት ዋና አዛዥ ኩማር ሱክዋም፤ እንደተናገሩት አብዛኞቹ ተጎጂዎች የፈሰሰውን ነዳጅ ለመሰብሰብ የሞከሩ ደሃ የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው። የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን ማጥፋት እንደቻሉም ተገልጿል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Jan, 14:35


🇧🇷 🌪 ብራዚል ውስጥ የተቀረጸው አስደንጋጭ ነጎድጓዳማ ደመና

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Jan, 10:17


ይድረስ የሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ታምሩን የመንፈስቅዱስ ቃለ ግዝት ምንነትና ሁኔታ ሁሉን እያወቅን በመጣስ ላይ ላለንና ከውግዛን አባቶችና ከሌሎችም ጋር በየዋህነት ፤ በፍራቻ ፤ ቃለ ግዝቱን በማቃለልና ባለመረዳት (በቸልተኝነት) መስዋዕታችንን ፤ ፀሎታችንን ለምናቀላቅልና ሳናውቅ በፈሪ ምድር ለወደቅን ቤተሰቦች፦

#አስተውሉ_ወገኖቼ !
#ይሄ_ቃል_ቀድሞ_የተነገረ_ለእኛም_ነው !

«ቤተ ክርስቲያን ፤ የተዋህዶ ቤታችን ፍፁም በዲያብሎስ ተወራለች፡፡ በውስጧም ለዲያቢሎስ አገልጋይ የሆኑ ወርሰዋታል፡፡ ሁሉም አንዱ ቅባት ሌላው ፀጋ አንዱ ደግሞ ተሃድሶ፤ እንዲሁም መናፍቅ፤ ካቶሊክ በሚል ዶግማ ወትረው ይዘዋታል፡፡ ሁሉም መለያቸው ደግሞ አንድ ለአምስት በሚል የዲያቢሎስ አገልጋይ መንግስት ባዘጋጀው መረብ የተተበተቡ መሆናቸው ነው፡፡ የመንግስት ተብየው አባል ያልሆነ የለም ቢባል ይቀላል፡፡ መጪው ጠረጋ የሚከብደው ሂያጁ ስለሚበዛ ነው፡፡ ተራፊው እጂግ ጥቂት ነው የሚባለውም ያለምክንያት አይደለም፡፡

ዛሬ በቤተ ክርሰቲያን የሚሳተፉ ሊያውቁት የሚገባው ቢኖር ቅዳሴው ማህሌቱ ኪዳኑ ሁሉ ከቤተክርስቲያኑ ጣሪያ እንደማያልፍ ነው፡፡ ሊያውቁት ይገባልና እንዲያስተውሉ ይመከራሉ፡፡ ምክንያቱ ሺ ጊዜ ተነግሯል፡፡ አልሰማ ላለ ሲያይና ሲሰማ ቅበረው እንደሚባለው ተረት ይሆንባቸዋል፡፡ በቤተ እምነታችን ውስጥ የተሰገሰጉት የዲያቢሎስ ተጧሪዎች ጌታን ሰቅለው ቁስሉን የሚወጉ ናቸው፡፡ ጨለማ ከብርሐን ጋር ምን ሕብረት አለው ዛሬ መስዋዕታቸውን ከዲያቢሎስ አገልጋዮች ጋር ቀላቅለው መስዋዕት አቀረብን አስቀደስን የሚሉ ሁሉ ጌታን ከዓመፀኞች ጋር ሰቅለው ቁስሉን የሚወጉ እንደሆኑ ይወቁ፤ በግላቸው እንደኤልያስ መስዋዕታቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ለዲያቢሎስ እጅ ከሰጡ ጋር ከእርሱም ፍርፋሪ ከሚለቅሙ ጋር የፖለቲካው ታማኝ ኮኑ ዲያቆናትና ቀሳውስት ጋር አብሮ የሚደረግ ፀሎት ማረፊያው ከዲያቢሎስ እጅ ነው፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ስትሄድ በግል የግል ፀሎታችሁን አድርሱ አሊያም ሰላም ለኪ እምዬ ቤተክርስቲያን አምሳለ እየሩሳሌም ብላችሁ ተሳልማችሁ ተሰማሩ! በቂ ነው፡፡ አንድ ምሳሌ እንውሰድ

የብርሐን ሰራዊት የሆኑ ለውጊያ የተዘጋጁ በስተቀኝ ግንባር ሲሰለፉ በስተግራ ግንባር ደግሞ የጨለማ ሰራዊቶች ተሰልፈዋል፡፡ በሁለቱ መሐል የተተወ የፈሪ ምድር የሚሉት ሥፍራ አለ፤ በሁለቱ ኃይላት አንፃር ድጋፍ የሚሰጡ ወይም የሚተባበሩ ስፍራቸውን ከየሚደግፉት ሰራዊት ጎን ቆመው ውጤቱን ይጠባበቃሉ፡፡ አንድ እንግዳ ነገር በፈሪው ምድር ላይ ይታያል፡፡ ውስን ቁጥር ያላቸው ሰዎች በዚያ በተተወ ምድር ወደ ሥራቸው ይሄዳሉ ውለውም በዚያው ይመለሳሉ፡፡ በማናቸውም ሰዓት ውጊያ በሚነሳበት የውጊያ ወረዳ ላይ የሰላም ቀጠና ሳይሆን በነዚህ ሰዎች ግን ማንም የማይከሰትበት ምድር ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ውጊያው ሲነሳ ግን ከማንም በላይ አደጋው ውስጥ የሚወድቁ እነዚህ የዋሃን አለአስተዋዮች ናቸው፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ለቅዳሴውም ለኪዳኑም ማልደው የሚገኙ ሰዎች በቅንነት የሚያደርጉት ቢሆንም ከዚህ አዋጅ መውጣት በኋላ ከሥፍራው ራሳቸውን ቢያርቁና የግል ፀሎታቸውን በቤታቸው ቢያደርጉ መልካም እንደሆነ ይመከራሉ ።»


📌 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት 6 ገፅ 7
ተጻፈ 19/04/2007 ዓ.ም

#የሊቀ_ሊቃውንት_አለቃ_አያሌው_የመንፈስቅዱስ_ቃለ_ግዝት_ይከበር !!!

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Jan, 09:54


ሐ፤ ከአሁን ጀምሮ ማለት ይህ ቃል በነጻው ፕሬስ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቃልና እጅ፥ በሲኖዶሱ ዋና ጸሓፊ በአቡነ ገሪማ ቃልና እጅ፥ ይህን አሁን የተጻፈውን ሕግ የቤተ ክርስቲያን ሕግ ብለው አጽድቀው በተባባሪነት አሳልፈዋል የተባሉ ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት ሁሉ እውነት ሆኖ ከተገኘ የበደሉ ተባባሪዎች ናቸውና በነሱ ቃልና እጅ ቡራኬ እንዳትቀበሉ፥ እንዳትናዘዙ፤ ስማቸውን በጸሎተ ቅዳሴ የሚጠሩ አለቆች፥ ቀሳውስት፥ ካህናት ካሉም የአምልኮተ ጣዖት አራማጅ ናቸውና ተጠንቅቁባቸው፤ ምክር ስጧቸው፤ እንቢ ካሉም ተለዩዋቸው።

/ከቃለ ግዝቱ የሚነበብ/

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Jan, 09:44


ቃለ ግዝት ! (ሊቀ ሊቃውንት የእግዚአብሔር ካህን አለቃ አያሌው ታምሩ)

📌"⚡️INSTANT VIEW" በሚለው ሙሉውን ቃለ ግዝት ያንብቡ ! ለሌሎችም share ያድርጉ !👇

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Jan, 09:35


🇨🇬 በእንተ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ሣልሳዊ፦

👑 «...ንጉሠ - ነገሥት ቴዎድሮስ ኢትዮጵያዊ የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ልጅ ነው ፡፡ በመልእክቶቹ ሁሉ እንደተናገረው ድሃ ጎስቋላ ሊቅ ያልሆነ ምናምንቴ ሰው ነው ፡፡ ስለሱ መመረጥ የታወኩ ነውም ብለው ለመቀበል የተቸገሩ እንዳሉ ግልፅ ነው ፡፡

👑 በቁጥር ቀላል ያልሆኑ በብዙ ምክንያቶች እራሳቸውን ቴዎድሮስ ነን ብለው አምነው የቆሙ ሰዎች አሉ ፡፡ ይህ ምንም አይደለም ሁሉ ወደፊት ስለሚገለጥ ወደ ብርሃንም ስለሚወጣ እንደዚህ ያሰቡበትንና ያመኑበትን መንገድ ስለሚገለፅ ብዙም ከዚህ በላይ መግለፁ ወቅታዊ አይሆንም ፡፡

👑 ንጉሡና ሌሎችም አባቶች እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያሉት ፡፡ ከዋናው ከተማ ጀምሮ በሁሉም የአገሪቱ ክልል በተለያየ ጉዳይ እየተንቀሳቀሱ ሁሉንም ድርጊት ይከታተላሉ ፡፡ በመገለጡ ሰአት በቀዳማይ ምክትልነትና በምክትልነት በግራና በቀኝ የሚሆኑ በንጉሥ ማእረግ ያሉ ዛሬም አብረውት በሥራው ሁሉ እያገዙትና አብረውም እየሰሩ ነው ፡፡ ሌሎች 37 የሚሆኑ በንጉሥ ማእረግ ያሉ በየባእታቸው ሆነው ፤ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሕብረትና አንድነት በሁሉም እያገዙ የሚገኙ ናቸው ፡፡ ሁሉም ሊያውቀው የሚገባው ቢኖር ዘመናዊ መገናኛ እስካለ ድረስ ፤ በቴሌግራም የዮሐንስ ራእይ 20 ቻናል ላይ ስለሁሉም ሁኔታ በቀጥታ የሚገለፅበት ይሆናል ፡፡ የንጉሠ ነገሥቱም ፣ የንጉሦቹም ድምፅ የምትሰሙበት የሚገለጥበት ነው ፡፡ ከዚህ በተረፈ በኢትዮጵያ የአለም ብርሃን መልእክታት በግልፅ የምታገኙት ነው ። ቴሌግራሙም እስካለ ድረስ ነው የሚያገለግለው ፡፡ ከዚህ ውጪ የሚመጣ ነገር የለም ፡፡ ተስፋ የምታደርጉት የኢትዮጵያ ትንሳኤም ሆነ የንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስና አብረውት የሚገለጡት ንጉሦች እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ታላላቅ አባቶች መላውን ዓለም በተዋህዶ እምነት የሚመሩት በይፋ የሚገለፅበት የሚታወቅበት ይኸው መንገድ ብቻ ነው ፡፡ ከዚህ በዘለለ ሌላ እውነት አለን ካላችሁ በርቱ ቀጥሉበት እንላለን ፡፡ ዳኛው በሰማይ በመንበሩ ሆኖ ሁሉንም ስለሚመለከት እንደየታመንበት ፍርዱም ትእዛዙም አብረው ይገለጣሉ ፡፡

👑 በሌላ በኩል -- እንደ እውነቱ ከሆነ እኔን ለምትቃወሙ ቅሬታም የለብኝ እኔ ዛሬም ነገም የምለው የማምነው የምረዳው አምላኬም ያስተማረኝ እውነትና እውነትን ብቻ መግለፅ ነው ፡፡ ስለዚህ እኔ ከሁሉ የማንስ ነኝ ፡፡ በሁሉም ገፅታ ከኔ ትበልጣላችሁ ብዬ አስባለሁ ፡፡ ግን በምን መስፈርት እኔን እንደመረጠ እኔም ስለማልረዳ እናንተ ቅር የተሰኛችሁ ሁሉ መድሃኒያለምን ድንግልን ጠይቁ መልስን ታገኛላችሁ ፡፡ ይህን ያልኩት በዚህ ምክንያት እንዳትሰናከሉ በማሰብ ነው ፡፡

👑 ንጉሥ ዳዊትን ልኡል ሲመርጠው ታላላቅ ወንድሞቹን እንዳላስደሰተ ሁሉ ሳሙኤልንም ግራ አጋብቶአል ፡፡ ጌታ ግን ለሳሙኤል መልስ ሰጥቶታል መልሱም እግዚአብሔር ልብን እንደሚያይ ውጪያዊ ገፅታን እንደማይመለከት አረጋግጦለታል ፡፡ ነቢያትን በተለይም ሃዋሪያትን ጌታ የመረጠው ከተናቀው ሥፍራ እንደሆነ ሁሉም የሚያውቀው ነው ፡፡ በሥራዬ ለእግዚአብሔር ምንም የሠራሁት በምግባሬም ያስደሰትኩበት ሥራ የለኝም ። በአንድ ነገር ብቻ አስቦኝ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ ፡፡ እሱም የፈጠረኝን አምላኬን ከከፋው ሃጢያቴ ያዳነኝን እንደሰው የቆጠረኝን አምላኬን ውዳቂ ነው ብላ ያልተወችን እናቴን ድንግልን አብዝቼና በፍፁም ልቤ እወዳቸዋለሁ። ሌላ የማውቀው ሰርቼ ያስደሰትኩበት ምንም የለኝም ፡፡ እውነቱ ይህ ነው ፡፡

👑 እንግዲህ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ማነው ለምትሉ ሁሉ ፣ ለወዳጅም ለጠላትም ፤ ግራ ገባን ለምትሉ ከላይ ምንነቱን በመጠኑ እንድታውቁት ለማድረግ ጥሬአለሁ ፡፡ ጊዜው ሲደርስ የሱንም የሌሎችንም ማንነት በግልፅ የምታዩበት ጊዜ ይመጣል ፡፡ መታገሥ ነው ፡፡

👑 አንድ ነገር እርግጥ እንዲሆንላችሁ የምፈልገው ሁሉንም እውነት መገለፅም ቢሆን በራእይ ዮሐንስ 20 ቻናል ላይ በልጃችን በተከፈተው ገፅ ላይ የምትሰሙት ይሆናል ፡፡ መልእክታቱም ሁሉ አንዱ የኛ መግለጫ መስመር ናቸው ፡፡ እነዚህም ሁሉ በመከራው ክብደት ቢዘጉ ሌላ መንገድ እናዘጋጃለን ፡፡ በዚያን ሰአት መነቃነቅ ቀርቶ መደበቂያ የሚያጣው ከሃዲው ትውልድ ይጨነቅ እንጂ ! እኛ እውክታ የለብንም ፡፡

👑 ሌላው ጉዳይ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ እኔ ነኝ የሚሉ እጅግ ብዙ ሰዎች እንዳሉ ይገመታል ፡፡ ብዙም ሲናገሩ እየተሰሙ ናቸው ፡፡ እኔም እየሰማሁ ነው ፤ ከመገረም ውጪ ምን ይባላል ፡፡ እርግጥ ነው ሁሉም ወደ ብርሃን ሲወጣ ማ ምን እንደሆነ ልኡልና ድንግል ስለሚገልጡት መታገሥና መጠበቁ መልካም ነው ብዬ አምናለሁ ፡፡

👑 እንግዲህ እውነቱን ለናፈቃችሁ ይኸው እውነቱን ገልፀናል ፡፡ በኛ ዘንድ ትመዘገቡ ዘንድ ባስታወቅነው መሰረት የተመዘገባችሁ ፤ ስለአመንበት መዝግበናል ፡፡ መታወቂያ የወሰዳችሁ መልካም አድርጋችኋል ፡፡ ለአገልግሎት ስለሆነ የወሰዳችሁት በሰአቱ ትጠቀሙበታላችሁ ፡፡ በመታወቂያው ላይ ያለው ፊርማ የኔው መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ፡፡
...»

🇨🇬 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ዘጠነኛ መልዕክት ገጽ 49–50
ተጻፈ ታኅሣሥ 21/2013 ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Jan, 09:14


በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ የሰደድ እሳት መከሰቱን ተገለጸ
***

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ የሰደድ እሳት መከሰቱ ተገልጿል፡፡

በወንዶ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ቀን 10:00 ገደማ ላይ የሰደድ እሳት አደጋ መከሰቱ ተነግሯል።

ደረቃማውን የአየር ሁኔታ ተከትሎ ከወንዶ ተራራ ላይ የተነሰው የሰደደ እሳት በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ መሆኑን የኦቢኤን ዘገባ ያመላክታል፡፡

በወረዳው ጎቱ ኦሎማ ቀበሌ በተራራው ደን ላይ እሳት መቀጣጠሉ ነው የተገለጸው።

የሰደድ እሳቱ ከተነሳበት ዕለት ጀምሮ እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ እየተደረገ ነው ተብሏል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

18 Jan, 21:29


በምዕራብ አርሲ ዞን ዋንዶ ወረዳ የሰደድ እሳት ተነሳ

ዛሬ ጥር 10/2017 በ10:00 ሰዓት የተነሳው ሰደድ እሳት በህብረተሰቡ ትብብር ለማጥፋት ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

18 Jan, 16:45


🤔 ይናገራል ፎቶ!!

#ዛር_አንጋሾች!!

#ለታሪክ_ትቀመጥ!
10/ጥር/2017
t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

13 Jan, 13:06


አሜሪካ መግታት በተሳናት የሎስ አንጀለሱ የሰደድ እሳት የሟቾች ቁጥር 24 ደረሰ።  በአካባቢው ተጠናክሮ የቀጠለው ከባድ ንፋስ የሰደድ እሳቱን ሊያጠናክረው እንደሚችል መስጋታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

የሰደድ እሳቱ ባደረሰው አደጋ እስካሁን ከሞቱት በተጨማሪ በአስራዎቹ የሚቆጠሩ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ። በአደጋው እስከ 180 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት እና ንብረት ወደ አመድነት ተቀይሯል ነው የተባለው።

በአሜሪካ ሁለተኛ ትልቋን ከተማ  ለአንድ ሳምንት ያህል እያቃጠለ የሚገኘው እሳቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች እና ህንጻዎችን ወደ አመድነት ቀይረዋል፤ ከ100 ሺ በላይ ሰዎችን ደግሞ ከመኖሪያቸው አፈናቅሏል ።

አሜሪካን እያሳሳበ የመጣው እስካሁን የደረሰው ውድመት እና ጥፋት ሳይሆን ከዚህ በኋላ ከባዱ ነፋስ እሳቱን አስፋፍቶ ከዚህም የከፋ ውድመት እንዳያደርስ ነው።
የሀገሪቱ ብሄራዊ ሜትሮሎጂ ትንበያ እንዳመለከተው ከነገ ማክሰኞ ጥር 6 ጀምሮ በሰዓት 110 ኪ/ሜ የሚገሰግስ ከባድ ንፋስ ሊከሰት ይችላል።

ይህ ደግሞ አሜሪካ በታሪኳ ካየቻቸው ብርቱ የሰደድ እሳት አደጋዎች አስከፊው ነው የተባለለትን የሎስ አንጀለሱ አደጋ ወደ ተቀሩ የከተማዋ ክፍሎች እንዳይዛመት አስግቷል።
አሜሪካ ከዓለማችን ግዙፍ የእሳት መከላከያ ብርጌድ ያላት ሃገር ብትሆንም አሁን የመጣባትን ብርቱ እሳት ለማስቆም ተፈትና ወድቃለች። ከሀገሪቱ ከተለያዩ ግዛቶች የእሳት መከላከያ ብርጌዶች በእሳት ማጥፋቱ ላይ መሰማራኃቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል።

በተጨማሪም ጎረቤት ሀገር ሜክሲኮ የእሳት ማጥፊያ እና መከላከያ ቡድን ወደ ስፍራው መላኳ ተሰምቷል።

አሜሪካ ባላት ቴክኖሎጂ እና ግዙፍ የእሳት አደጋ መከላከያ ብርጌዷ እሳቱን ለማስቆም 24 ሰዓት እየሰራች ቢሆንም ተመራጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ  ትረምፕ የአካባቢውን ከመተቸት እና ከመዝለፍ አልተቆጠቡም።
 
ትራምፕ የአካባቢውን ባለስልጣናት «ብቃት የላችሁም» ሲሉ ወንጅለዋቸዋል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

13 Jan, 12:58


ደስ ይበላችሁ በአለም የሚያበራ ክብር ለኢትዮጵያ ተሰጥቷል!!!

#ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

13 Jan, 12:57


በሎስ አንጀለስ የሟቾች ቁጥር ሃያ አራት ደረሰ

በአሜሪካ ታሪክ ከባድ ሊሆን ይችላል በተባለው የተፈጥሮ አደጋ ቢያንስ 24 ሰዎች ሲሞቱ እና 100ሺ ሰዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል። ሎስ አንጀለስ አደገኛው ንፋስ ከመመለሱ በፊት ሰደድ እሳቱን ለማስቆም እየተጣደፈች ነው።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

13 Jan, 07:31


በዛሬው ዕለት 04/05/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 4:49 በመተሃራ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 5.1 የተመዘበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
ንዝረቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ አካባቢዎች ተሰምቷል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

13 Jan, 07:31


በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ በተከሰተው ሰደድ እሳት ምክንያት

የሞቱ ሰዎች ቁጥር 24 ሲደርስ ከ12 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችና ህንጻዎች በእሳት ተበልተዋል። በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳትም ወደ 150 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ ተነግሯል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

12 Jan, 16:39


"እንሸሻለን፣ አናመልጣለን ብላችሁ አታስቡ፤ ይህ ድሮ ቀረ። ከአሁን በኋላ ሰው አምልጦ የሚድነው  ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በመጠለል ብቻ ነው። ስለዚህ ሽሽት ወዴት! እናንተ መሸሸጊያ ይሆናሉ ብላችሁ  በሥጋችሁ ያደራጃችኋቸው እነባቢሎን (አሜሪካ)፣ እነአውሮፓ፣ ወይም ኤሽያ፣ አረቢያም ሁሉም በእዚህም  ጽዳት ይካሄዳል። ምሽጉ የትጋ ነው! ራሳችሁንና ሥራችሁን ይዛችሁ በፈጣሪ እጅ መውደቅ ቅን ፍርዱን  መጠበቅ ብቻ ነው።"

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ሁለት የተወሰደ ግንቦት 27/2000 ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

12 Jan, 16:32


«እግዚአብሔር የበቀል አምላክ ነው። የበቀል አምላክ ተገለጠ። የምድር ፈራጅ ሆይ፥ ከፍ ከፍ በል፤ ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው።»

መዝሙረ ዳዊት 93(94) ፥ 1-2

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

12 Jan, 10:30


እስካሁን ድረስ መቆጣጠር ባልተቻለው የአሜሪካ፣ ሎስ አንጀለስ  ሰደድ እሳት ምክንያት ቢያንስ 16 ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ ከ137 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

የበርካታ ሰዎች ቤት ወደ አመድነት ተቀይሯል።

ሰደድ እሳቱ ያደረሰው ውድመት 135 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ የተገመተ ሲሆን ከዚህም ከፍ እንደሚል ይጠበቃል።

እሳቱን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ቢቀጥልም ዝነኛ ወደሆነውና የአሜሪካ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ወደሚሰሩበት " ሆሊዉድ " እየተቃረበ ነው ተብሏል።

በቀጣይ ቀናት ምን ሊከሰት እንደሚችል በእርግጠኛነት መተንበይ ባይቻልም ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ ወይም ለመውጣት እንዲዘጋጁ እንደተነገራቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

12 Jan, 04:19


🟢🟡🔴
ጥር 4 | #ቅዱስ_ዮሐንስ ወንጌላዊ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓሉ ነው።

๏ በጌታ ደረት ላይ የተጠጋ፥
๏ እሳቱ ያላቃጠለው፥
๏ መለኮት የሳመው
๏ ድንግል ያቀፈችው፣ የሳመችው
[
ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ ] የዕረፍቱ (የተሰወረበት) በዓል ነው።

እርሱም ጌታችን እጅግ ይወደው የነበረው ሐዋርያ ነው። ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል።

ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ። ስንኳን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ።

ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል። ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል:: ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው

በከሃዲውና በጨካኙ በድምጥያኖስ ዘመን በጣዖት አምላኪዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ፡፡ በፈላ ውኃ ካሠቃዩት በኋለ በፍጥሞ ደሴት አጋዙት፡፡ በዚያም ሳለ ራእዩን ተመልክቶ ጻፈው፡፡ በዚያም በ90 ዓመቱ ተሰወረ።
▰ ▰ ▰

ቅዱስ አባ መልከጼዴቅ ዘዋሸራ ዐረፉ።

እኚህ አባት የጌታችንን ሕማም በማሰብ ለወፎችን እጅግ ልዩ ምግብ በመመገባቸው ይታወቃሉ።


ዲቁናንና ቅስናን ከግብፅ ተቀብለው በዋሽራ 30 ዓመት በሹመት አገልግለዋል፡፡ ጻድቁ የሚታወቁበት ትልቁ ተጋድሎአቸው በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ሁልጊዜ ዓርብ ዓርብ ያከፍሉ ነበር፡፡

የመድኃኔዓለምን 13ቱን ሕመማተ መስቀሎች በማሰብ አናታቸውን በድንጋይ እያቆሰሉ ቁስሉ ሲተላ ትሉን ለወፎች ይመግቡ ነበር፡፡
▰ ▰ ▰

ዳግመኛም ተጋዳይ የሆነ በጥላው ብቻ ከይሲን የገደለ የደብረ ቢዘኑ #አባ_ናርዶስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፡፡

«እርሱም እግሮቹ እስኪያብጡ ድረስ ቆሞ በመጸለይ የተጋደለ ነው›› በማለት ስንክሳሩ በአጭሩ የገለጸው ጻድቁ #አባ_ናርዶስ ዕረፍቱ ነው፡፡

◦ http://t.me/Ewnet1Nat ◦

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

11 Jan, 13:29


🇺🇸 ወደ 200 የሚጠጉ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በብሮንክስ ኒው ዮርክ በሚገኝ አንድ አፓርትመንት ውስጥ በከባድ ንፋስ የተነሳውን የእሳት ነበልባል ለማጥፋት እየታገሉ ነው

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

11 Jan, 13:27


🇧🇷✈️ በብራዚል ሳኦ ፓውሎ ግዛት የባህር ዳርቻ አነስተኛ አውሮፕላን ከመንደርደሪያው ተንሸራቶ ፈነዳ

በቅድሚያ መረጃዎች መሰረት አንድ ፓይለት የሞተ ሲሆን በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ አራት ተሳፋሪዎች እና ሶስት ግለሰቦች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

11 Jan, 08:12


🗣 እግዚአብሔር ይመስገን ! እኛ ስንናገር፤ ስንጮኽ ለማያምኑን ይኸው ማረጋገጫ !!

"አስቀድመን ብዙ ስለጮኽን ዛሬ እንኳን ዝም ከማለት በቀር ምንም አንልም"

📌 ሌላውን ዝርዝር ሁኔታ ወደጎን ላቆየውና በጣም የደነቀኝን ልጠቁማችሁ ...በጋራ (ከቫቲካን ካቶሊክ - ከነ ሰዶም ፍራንሲስ ጋራ) በጋራ ስርዓተ ጸሎት አድርሰዋል ይላል ይህ የማኅበረ ርኩሳን ድምፅ !!! አናንተ አርዮሳዊያን ፍርዳችሁን ጠብቁ ።።(ስምንት ነጥብ!)

📌 እንኳንም ወደወላጅ እናታችሁ ወደኢሉሚናቲ (ካቶሊክ) በሠላም ሄዳችሁ ¡ መልካም የሲዖል ጉዞ እነ ውጉዛን !!

#ለታሪክ_ትቀመጥ !!!
የካቲት 18/2015 ዓ.ም
t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

11 Jan, 07:50


በኬኒያ አውሮፕላን ተከስክሶ የ3 ሰዎች ሕይዎት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኬኒያ ማሊንዲ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በምትገኘው ክዋቾቻ ከተማ በደረሰ የአነስተኛ አውሮፕላን አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይዎት ማለፉ ተሰምቷል፡፡ የዐይን እማኞች አውሮፕላኑ በአካባቢው የነበሩ ሰዎችን መምታቱንና ከዚያም በእሳት መያያዙን ገልጸዋል፡፡ ሁለት ሰዎች በአውሮፕላኑ ስብርባሪዎች ተመትተው ወዲያውኑ ሕይዎታቸው ሲያልፍ፥ አንዱ በእሳት ከባድ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ መሞቱን የአካባቢውን ባለስልጣናት አሳውቀዋል ።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

11 Jan, 07:48


“በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።”
— ሶፎንያስ 1፥18

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

11 Jan, 07:47


ሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳቱን ለማጥፋት እስረኞችን አሰማራች

በደቡባዊ ካሊፎርኒያ፣ ሎስ አንጀለስ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለውን የሰደድ እሳት ለመግታት በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች መሰማራታቸው ተሰምቷል።

በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል የተባለውን ይህንን የሰደድ እሳት ለማጥፋት ወደ 939 የሚሆኑ እስረኞች በካሊፎርኒያ የማረሚያ እና መልሶ ማቋቋም መምሪያ (ሲዲሲአር) በሚመራው የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም ታቅፈው በግንባር ቀደምትነት እየተሳተፉ ነው ተብሏል።

ባለፈው ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም በሎስ አንጀለስ ተቀስቅሶ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት እየተሳተፉ ያሉ ታራሚዎች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ይገኛል።

ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ከ10 ሺህ በላይ ህንጻዎችን ያወደመው እና 37 ሺህ ሄክታር የሚሸፍን መሬት ያቃጠለውን ሰደድ እሳት ለመግታት በሺዎች የሚቆጠሩ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ተሰማርተዋል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

11 Jan, 04:44


በአንድ ሰዓት ውስጥ ሶስት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ‼️
ዛሬ አዳሩን ከተከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል ከፍተኛ 5.2 የተመዘገበ ሲሆን የተከሰተው ከለሊት 9:19 ከአዋሽ በሰሜን በ30ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው፣በዚህም አዲስ አበባን ጨምሮ ከፍተኛ የተባለ ንዝረት ተሰምቷል።
ዛሬ ለሊት የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ:-👇
1. ለሊት 8:42 በአፋር ገርባ ከአዋሽ ሰሜናዊ ምዕራብ በ12ኪ.ሜ ርቀት በሬክተር ስኬል 4.60 የሆነ

2. ለሊት 8:58 አማራ ክልል ብጨንቀኝ በሬክተር ስኬል 4.50 የሆነ

3. ለሊት 9:19 ከአዋሽ ባስተሰሜን በ30ኪ.ሜ ርቀት የምሽቱ ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.20 የሆነ

4. ለሊት 10:50 ከመተኻራ በደቡባዊ ምስራቅ በ25ኪ.ሜ ርቀት በሬክተር ስኬል 4.30 የሆነ

5. አሁን ጧዋት 12:22 ከመተኻራ በደቡብ አቅጣጫ በ28ኪ.ሜ ርቀት በሬክተር ስኬል 4.40 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግቧል።
አዩዘሀበሻ

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Jan, 19:57


📌 ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም
(ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ማን ናት በሚል ርዕስ ከተላለፈው ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ትምህርት ክፍል 2 መዝጊያ)

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Jan, 19:39


📌 ሁሉም ነገር ማብቂያ ስላለው እግዚአብሔር እያጣደፈው ነው።
እያፈጠነው ነው ፍርዱንም እያሯሯጠው ነው የመጣው አሁን
በአጭር ጊዜ ሩቅ ሳንሄድ በአጭር ጊዜ ሁሉም ወደ ብርሃን ይወጣል
የእኛም ምንነት ወደ ብርሃን ይወጣል እግዚአብሔር ማንን እንደሚወድ ማንን እንደሰማ ከማን ጋር እንደ ቆመ ልክ እንደኤልያስ ከማን ጋር እንደ ቆመ ወደ ፊት የምናየው ይሆናል።
ስለዚህ ጽኑ በርቱ ተጽናኑ አትደነቁ በሚሆነው ነገር ሁሉ አትደነቁ ምንም ሥፍራ አትስጡት ይሆን ዘንድ ግድ ነው ይሆናል በቃ!!
⚡️ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ማን ናት ?
ከሚለው ትምህርት ክፍል _2  -መጨረሻ  መዝጊያው ላይ የተወሰደ።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Jan, 17:55


ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን🌍 🔴መልእክት አንድ

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Jan, 10:14


Blast at firecracker factory triggered by chemical reaction kills 6 in Tamil Nadu's Virudhunagar

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Jan, 10:13


❗️ 8 KILLED, 15 Injured as devastating fire tears through North China food market

#China

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Jan, 09:49


" የአሁኑ ከእስከዛሬው ሁሉ ይለያል ፤ በጣም ያስፈራ ነበር " - ነዋሪዎች

በርካቶችን ለሊት ከእንቅልፍ የቀሰቀሰ ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ለሊት ተከስቷል።

ከለሊቱ 9:52 ላይ ከአቦምሳ 56 ኪሎ ሜትር ርቀት በሬክተር ስኬል 5.8 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

ንዝረቱ አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች በከፍተኛ ሁኔታ ተሰምቷል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Jan, 09:49


ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ቁጥር 8 ገጽ 47 ተፃፈ ታህሳስ 21 2011 ዓ.ም*

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Jan, 01:50


ከላይ የእሳት አይነት የአውሎ ንፋስ አይነት የጎርፍ የማዕበል የበረዶ አይነት እና ብዛት ፍፁም የሚጠርግህ  መቅሰፍት ይወርድብሀል። ውቅያኖሱ ይተፋሀል በማዕበሉ ይጠርግሀል። የምትጠጣው ውሀ መርዝ ሆኖ የስቃይ ሞት ያሳይሀል። የምትበላው የምድሩም ፍሬ ስጋውም የባህሩም አሳም የገሙ የበከተ መርዝ ሆነው የሚገሉህ በምንም ዘዴ የማታክማቸው ይሆኑብሀል። ከከርሰ ምድር እሳተ ገሞራው ይበሳጭብሀል። በቁጣውም ይገነፍላል።
ምሽጌ ያልከው ምድርህም በከፍተኛ ርዕደ መሬት ታይቶም ተሰምቶም በማያውቅ ማግኒቲዩድ መጠን እየወጣ ወደ እሳት ጉያው ይከትሀል።
ፍርድአዘል መግለጫ ጥቅምት 21 2017 ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Jan, 01:22


ከለሊቱ 9:52

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

03 Jan, 19:28


🔥🇬🇭 በጋና ዋና ከተማ አክራ በሚገኘውና ከምእራብ አፍሪካ ትልቅ ገበያዎች አንዱ በሆነው ካንታማንቶ የደረሰ የእሳት ቃጠሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ነጋዴዎችን ኪሳራ ላይ ጣለ

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

03 Jan, 19:24


📌 ታኅሣሥ 16/2017 ዓ.ም (ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ፍርድ አዘል መግለጫ ክፍል 3 መዝጊያ)

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

03 Jan, 19:02


በዛሬው እለት የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ አምስት ሰዎች በሰሜን ሸዋ ግድያ ተፈፀመባቸው

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዛሬ ጠዋት
ገደማ ለስራ እየተንቀሳቀሱ የነበሩ የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ አምስት ሰዎች በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መገደላቸውን ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ጠቁመዋል።

በተተኮሰባቸው ጥይት የሞቱት ግለሰቦች ለስራ ጉለሌ ወረዳ  3 ላይ ቆይተዉ ወደ ፍቼ ከተማ እየተመለሱ በነበረበት ወቅት ነው ተብሏል።

የዞኑ የውሃ ሀብት ቢሮ ሀላፊ፣ የመስኖና ተፋሰስ ሀላፊ፣ የቡሳ ጎንፋ ሀላፊ እንዲሁም አንድ የቀበሌ ሊቀንመበር እና ሹፌራቸው በአጠቃላይ አምስት ሰዎች በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ወይም መንግስት 'ኦነግ ሸኔ' በሚላቸው ታጣቂዎች መገደላቸውን ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን በቅርብ ወራት በመንግስት ጦር እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት መሀል ከፍተኛ የሆነ ግጭት እያስተናገደ ይገኛል።

ከዚህ በፊት በአንፃራዊ ሰላሙ የሚታወቀው ይህ የሰላሌ አካባቢ አሁን ላይ ከፍተኛ እገታ፣ ግድያ እና ተያያዥ ጉዳቶችን በህዝቡ ላይ እያስከተለ እንደሆነ ይታወቃል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

03 Jan, 19:00


የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተባቸው ካሉ ስፍራዎች ነዋሪዎችን ማዘዋወር ተጀመረ!

#ስደት ❗️

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

03 Jan, 18:47


እሳት‼️ Amazing🙀🙀
በአፋር ክልል ዱለቻ ወረዳ ሰንጋቶ ቀበሌ ዶፈን ተራራ ላይ ጠዋት ጀምሮ ጭስ እየወጣበት የነበረው ቦታ አሁን በምስሉ እንደምትመለከቱት እሳት 🔥እየወጣበት ይገኛል ሲሉ የአፋር የመረጃ ምችጮቼ ጠቁመዋል። ከአንድ ሰዓት በፊት 2:01 ደቂቃ ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ መነሻው (epicenter) እዚሁ አካባቢ ነው።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

07 Dec, 01:58


🟢🟡🔴
ኅዳር 28 | ከ9ኙ ቅዱሳን አንዱ #አቡነ_ሊቃኖስ ተሰወሩ።

እኚህ ቅዱስ እንደ 8ቱ ጓደኞቻቸው ከነገሥታት ቤተሰብ የተገኙ እና ምንኩስናን መርጠው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ናቸው።

"አባ ሊቃኖስ" የመጀመሪያ ስማቸው ሳይሆን በእውቀታቸው የተደመመ የአክሱም ሕዝብ ያወጣላቸው ስም ነው። ሊቃኖስን 'ሊቁ አባት' ማለት ነው ብለው የተረጎሙልን አበው አሉና።

አቡነ ሊቃኖስ ከዘጠኙ ቅዱሳን ውስጥ አቡነ ሊቃኖስ ለየት የሚሉበት ነገር ቢኖር ዓሥሩም የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው ጣቶች እንደፋና ያበሩ ነበር፡፡

ሁልጊዜም ለአገልግሎት ሲወጡ በትረ ሙሴአቸውን አይለዩም ነበር። ሲሰብኩም፣ ሲጸልዩም ተደግፈውባት ነበር። ታዲያ ከዘመን ብዛት የሚደገፉባት የእጃቸው መዳፍ መነደሉን አበው፦ "ወበእሒዘ በትር ዘተሰቁረ ዕዱ" ሲሉ ይናገራሉ።

የአቡነ ሊቃኖስ ገዳማቸው በደብረ ቁናጽል (የቀበሮዎች ተራራ) አክሱም ከጓደኛቸው ከአባ ጰንጠሌዎን ገዳም አቅራቢያ ይገኛል፡፡ ጻድቁ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደረጉ ነበር፡፡ መላእክትም ዘወትር ባለመለየት ይጎበኙዋቸው ነበር፡፡

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዘወትር እየተገለጠላቸው ይባርካቸውና ቃልኪዳን ይሰጣቸው ነበር፡፡ በገዳማቸውም ልክ በደብረ ታቦር እንደተገለጠ በግርማው ታይቷቸዋል።

በጸሎታቸውም አጋንንትን አውጥተዋል፣ ድውያንን ፈውሰዋል፣ ዕውራንን አብርተዋል፣ ሙታንን አንሥተዋል፡፡

ከተስዓቱ ቅዱሳን ውስጥ አራቱ ሞትን ሳያዩ ተሰውረዋል፡፡ አቡነ አረጋዊ ጥቅምት 14 ቀን ተሰወሩ፡፡ አቡነ ገሪማ ሰኔ 17 ቀን፣ አቡነ አፍጼ ግንቦት 29 ቀን፣ አቡነ ሊቃኖስ ኅዳር 28 ቀን ተሰወሩ፡፡
🍀

በአርያኖስ እጅ ሰማዕት የሆኑት ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ሰረባሞን በዓላቸው ነው።

T.me/Ewnet1Nat
                ◦🍀🍀🍀

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

06 Dec, 18:51


"ሃገር ሲያረጅ ጃርት ያበቅላል !"

#ከእነ_ፓትርያርካቹ_እሳት_ይበላችኋል!
#ለታሪክ_ትቀመጥ!
ኅዳር 27/2017 ዓ.ም


t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

06 Dec, 14:47


ማናቸውም ማምረቻዎች፤ፋብሪካዎች አገልግሎት ሰጪዎች የጤና ተቋሞች የግልም የመንግሥትም ድርጅቶች መስሪያ ቤቶች አለም አቀፍ ተቋሞች ፤ድርጅቶች በሙሉ ይከረቸማሉ።
⚡️ ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መንግሥት መልእክት 9 አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ገጽ 61 ላይ የተወሰደ።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

06 Dec, 14:47


ከስምንቱ የመንግሥት ስኳር ፋብሪካዎች መካከል ባኹኑ ወቅት በምርት ሥራ ላይ ያለው ወንጂ ስኳር ፋብሪካ ብቻ መኾኑን ዋዜማ ካሰባሰበቻቸው መረጃዎች ተረድታለች። መተሐራ፣ ፊንጫ፣ አርጆ ዲዴሳ፣ ከሰም፣ ጣና በለስ ቁጥር አንድ፣ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ እና ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ፋብሪካዎች ግን በተለያዩ ጊዜያት ምርት ካቆሙ መቆየታቸውን ዋዜማ አረጋግጣለች። አብዛኞቹ ፋብሪካዎች የስኳር ምርት ያቆሙት፣ ከማሽን ጥገና፣ ከኤሌክትሪክ አቅርቦትና ከጸጥታ ጋር በተያያዘ እንደሆነም ታውቋል

በሌላ በኩል ደግሞ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን፣ ሱሉለ ፊንጫ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው መንግሥታዊው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሸንኮራ አገዳ ተክል ላይ ትናንት ሌላ የእሳት ቃጠሎ አደጋ መድረሱን ዋዜማ ከፋብሪካው ሠራተኞች ሰምታለች፡፡ ትናንት ከቀትር በኋላ ጀምሮ እስከ ምሽት 2 ሰዓት ድረስ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ፣ በኸለት ማሳዎች ላይ የለማ ከ200 ሔክታር በላይ የኾነ የሸንኮራ አገዳ ተክል ሙሉ ለሙሉ መውደሙን ሠራተኞቹ ተናግረዋል፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊትም፣ የፋበሪካ ንብረት የኾነ ሰፊ የሸንኮራ አገዳ ተክልና እስከ 40 ሚሊዮን ብር የሚገመት ማሽን በእሳት አደጋ መውደሙን ዋዜማ መዘገቧ አይዘነጋም።
]

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

05 Dec, 04:57


🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል አምስት (5)

በድምፅ ንባብ (ትረካ)
(📌 ክፍል 1ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 2ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 3ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 4ን ለማዳመጥ 👈)


📌 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሰላማ ማን ናቸው?

🍀 ኅዳር 26 - የልደታቸው በዓል
🌼 ታኅሣሥ 18 - ለኢትዮጵያ ጳጳስ ሊሆኑ
                            የተሾሙበት በዓል
🌺 ሐምሌ 26 - የዕረፍታቸው በዓል

እንደ ተሰጣቸው ክብር ያላከበርናቸው፣ የዘነጋናቸው ባለውለታና ብርሃናችን የአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን፦
🍀 ሕይወትና ተጋድሎ
🌼 ልዩ ቃልኪዳን
🌺 ህያው ትሩፋት

ከዚህ ሥር አጭር ዜና ሕይወታቸውን እና ትሩፋታቸውን ያንብቡ👇

📌 https://telegra.ph/ብፁዕ-ወቅዱስ-አቡነ-ሰላማ-ከሳቴ-ብርሃን-11-14-2

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

05 Dec, 04:01


🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል አምስት (5)

(📌 ክፍል 1ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 2ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 3ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 4ን ለማንበብ 👈)

📌 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሰላማ ማን ናቸው?

🍀 ኅዳር 26 - የልደታቸው በዓል
🌼 ታኅሣሥ 18 - ለኢትዮጵያ ጳጳስ ሊሆኑ
                            የተሾሙበት በዓል
🌺 ሐምሌ 26 - የዕረፍታቸው በዓል

እንደ ተሰጣቸው ክብር ያላከበርናቸው፣ የዘነጋናቸው ባለውለታና ብርሃናችን የአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን፦
🍀 ሕይወትና ተጋድሎ
🌼 ልዩ ቃልኪዳን
🌺 ህያው ትሩፋት

ከዚህ ሥር አጭር ዜና ሕይወታቸውን እና ትሩፋታቸውን ያንብቡ👇

📌 https://telegra.ph/ብፁዕ-ወቅዱስ-አቡነ-ሰላማ-ከሳቴ-ብርሃን-11-14-2

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

05 Dec, 00:25


🟢🟡🔴
ኅዳር 26 | ዕረፍታቸው የሆነ እጅግ የከበሩ አባቶቻችን፦

ደሴ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምን የመሠረቱት የአባታችን #የአቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ በዓላቸው ነው፡፡

በጎንደር ክፍለ ሀገር ስማዳ ወረዳ ከአባታቸው ዘክርስቶስና ከእናታቸው እግዚእ ክብራ በ1210 ዓ.ም ተወለዱ።

የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ከሆኑት ዮሐኒ 2ኛ በፈተና ታግሠው በደብረ ዳሞ መነኰሱ።

አባታችን #አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ የአባቶቻችን፦
የተክለ ሃይማኖት (ደብረ ሊባኖስ) 
የኂሩተ አምላክ (ዳጋ እስጢፋኖስ)
የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ቦረና)
የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ዳውንት) 
የአቡነ አሮን(መቄት)
የአቡነ ዮሴፍ (ላስታ) ... የመንፈስ/የቆብ አባት ናቸው። ምንኛ ድንቅ አባት ናቸው!

ለዚህም ወላዴ አእላፍ - አእላፍን ቅዱሳንን የወለዱ ተብለው ይጠራሉ።
🍀

#_አቡነ_ሃብተ_ማርያም ጻድቅ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው። "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው።

ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ፣ እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች።

ገና በ5 ዓመት ዕድሜያቸው ሌሊት ሌሊት እየተነሡ "ማረን እባክህን" እያሉ ይሰግዱ ነበር።

➻ ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ
➻በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ
➻ በ40/በ80 ቀን አንዴ ብቻ ሣርና ቅጠል ይመገባሉ
➻ በየዕለቱ ያለ ማስታጎል ማዕጠንት ያሳርጋሉ
➻ በፍጹም ቂምን መከፋትን አያውቁም

በዚህች ቀን ሲያርፉም መድኃኔዓለም፦
"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጎን 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ። በስምህ የሚለምኑ፣ በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው።

በረከታቸው በዝታ ትድረሰን፨
T.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Dec, 17:38


🇬🇷 ቦራ የተሰኘ አውሎ ንፋስ በግሪክ ሮድ ደሴት ከፍተኛ ጎርፍ አደረሰ

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Dec, 16:16


🇪🇨 አስደንጋጭ የጦር አውሮፕላን መከስከስ ኢኳዶርን አንቀጠቀጣት

በአደጋው ፓይለቶቹ ሲሞቱ መኪና ውስጥ የነበሩት ሁለት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Dec, 16:06


በዲሞክራቲክ ኮንጎ ምንነቱ ያልታወቀ
ጉንፋን መሰል በሽታ 143 ሸዎችን መግደሉ የታወቀ ሲሆን።
በበሽታው የተያዙም ብዙ እንደሆኑ ሮይተርስ ዘግቧል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Dec, 16:06


📌ትላንት በአንድ በሽታ በአንድ ይህ ኮቪድ በሚባል የታመሰውና ግራ የገባው ዓለም ኢኮኖሚውም በዚህ ምክንያት ደቆ ባዶ የሆነበት ዓለም ትርምስምሳቸውን ያወጣቸው አንድ በሽታ አንድ  የአንድ   በሽታ ገጽታ  ነበር ፡፡

አሁን ደሞ ከበፊቱም የከፋ እጅግ የከፋ የበሽታዎች አይነት የተፈጥሮ አደጋዎች እጅግ በዝተው ከሰባት እጥፍ በላይም እየጨመሩ እንደሚመጡ ዛሬም ለሁሉም ሰሚና ጠፊ ሁሉ ትውልድ ግልፅ ሊሆንለት ይገባል፡፡

እግዚአብሔር ያለውን ሳይፈጽም የሚቆም ነገር የለም፡፡የተናገረው ሳይፈጸም ሳይከናወን የሚቀር ነገር የለም ፡፡ወረፋውን ነው የሚጠብቀው ወገኖቼ ምንም የሚቀር ነገር የለም፡፡

🇨🇬  በቀን 9 /12/2014 ዓ፡ም ከተለቀቀው፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
የሉቃስ ወንጌል ትምህርት ክፍል ሁለት ላይ ለግንዛቤ ያህል የተወሰደ፡፡

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Dec, 05:00


🟢🟡🔴
ኅዳር 25 | ኢትዮጵያዊው ሰማዕት አቡነ ሚካኤል ዐረፉ።

እኚህ ቅዱስ አባት ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ ቤተ ክርስቲያን ከአቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት ጋር የተጋደሉ ናቸው። ከመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት አንዱ ናቸው።

ኮሎኔል ማልታ እሥረኛውን ጳጳስ ከእሥር ቤት አስመጥቶ ሕዝቡ በተሰበሰበበት አደባባይ አቀረባቸው። «ለኃያሉ የኢጣሊያ መንግሥት ለመገዛት ቃል ይግቡና ሕዝቡም እንዲገዛልን ይስበኩልን። ይህንን ካደረጉ እንለቅዎታለን።» በማለት በልዩ ልዩ መደለያ ጭምር አባበሏቸው።

‹እኔ የማምነው በአንድ እግዚአብሔር ነው። የምቀበለው የነፃነታችን ምልክት የሆነውን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ብቻ ነው። ኢጣሊያ የሚባል ገዥ አላውቅም።

ለፋሽስት ኢጣሊያ የተገዛ እንደ አርዮስ የተረገመ ይሁን። እንኳንስ ሕዝቡ ምድሪቱም እንዳትገዛላቸው አውግዣለሁ።›
በማለት በዚያ ለተሰበሰበው ሰው ሁሉ ውግዘታቸውን አሰሙ።

የጠላት ጦር አዛዥ ኮሎኔል ማልታ የብፁዕነታቸው የዓላማ ፅናትና ቆራጥነት ተገነዘበ። እሳቸውን መሸንገል እንደማይቻል ሲያረጋግጥ በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ ወሰነ።

ከጎሬ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በታች አሮጌው ቄራ አጠገብ ጉድጓድ ተቆፈረ።

በዚህን ጊዜ አቡነ ሚካኤል ለጥቂት ደቂቃዎች ፀሎት እንዲያደርጉ ጠይቀው ተፈቀደላቸው። ጸሎታቸውን
አድርሰው ሲያበቁ መስቀላቸውን በግንባራቸው አድርገው ‹በል እንግዲህ የፈለከውን አድርግ› አሉ።

የወታደሮቹ አዛዥ የተኩሱን ትዕዛዝ ሰጠ። ከእነ አቡነ ሚካኤል ፊት ለፊት በተርታ ተደርድረው በአባታችን እና በአርበኞች ላይ ጠመንጃቸውን ያነጣጠሩት የጠላት ወታደሮች በእሩምታ ተኮሱ። ሰማዕትነታቸውንም ፈጸሙ።

የቀብራቸውም ሥነ ሥርዓት በአግባቡ አልተፈፀመም። አቶ ወልደአብ የተባሉ የአገር ፍቅር የነበረባቸው የአካባቢው ነዋሪ ናቸው በሌሊት የቀበሯቸው።

t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

03 Dec, 20:10


"በኢትዮጵያ ትንሣኤ የጸና ተስፋ ይኑርህ።

በቃ!! የምንመክርህ ይኸንን ነው። እኛ ያልነው ይኸንን ነው። ሌላ 'ምንለው ነገር የለንም።
"

🟢🟡🔴 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን 
መግለጫ እና የሉቃስ ወንጌለ ትምህርት ክፍል 13(ሀ) ላይ የተወሰደ።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

03 Dec, 18:56


🇨🇬 ለኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ብቻ 🇨🇬
            ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
           
             ▰  #የፍቅር_ዕዳ_አይኑርባችሁ !  ▰
  🇨🇬 የኢ.ዓ.ብ የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት ፫ 🇨🇬
           | 🕛 | ከ፶፯ ደቂቃ ከ፲ ሰከንድ ጀምሮ

× × ×
[ሮሜ 13፥8] የፍቅር ዕዳ ሲባል ምን ማለት ነው?

አዎ!
ወንድምን መጥላት፣ መቀየም፣ ወንድማችን ላይ ቅሬታን  ማሳደር፣ ማዘን፥ መከፋት በሰውዬው ላይ ፣ ቂምን ቋጥሮ መቆየት፣ ጥላቻን ማሳደር፣ እንቅፋትን ማኖር፣ ክፉ ክፉውን መናገር፣ በጎን አለማሰብ፣ ስለጭንቀቱ፥ ስለማዘኑ፥ ስለ መከፋቱ አለማዘን፣ አለመርዳት፣ በቅንነትና በፍቅር አለመመልከት እነዚኽ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር አያቀራርቡም።

ስለዚኽ እነዚኽን ሁሉ የምንሸከም ከኾነ #ዕዳ አለብን ማለት ነው።

ስለዚኽ የፍቅር ዕዳ እንዳይኖርብን ባልጀራችንን መውደድ አለብን። ቢጠሉንም እንኳ፥ ጠላቶቻችን እንኳ ቢኾኑ ሰው ናቸውና ልንወዳቸው ይገባል።

ወደው አይደለም እኮ ክፉ ሥራ የሚሠሩት ወገኖቼ! በላያቸው ላይ የሚያርፈው፥ በሥጋቸው ላይ የሚሠለጥነው ክፉ መንፈስ ነው ወደ ክፋት እየገፋ ፣ ወደ ጥፋት እየገፋ ለጥፋት የሚዳርጋቸው።

#እነሱ_እኮ_ደምና_አጥንት_ናቸው። #ዲያቢሎስ_ግን_መንፈስ_ነው። በእነርሱ ላይ አድሮ እኛን የሚዋጋ፣ እኛ ወደ ክፉ ሥራ ለመግፋት የሚያንደረድረን፣ ቂም በቀል ክፋት በልባችን እንድናሳድር በእነሱ ላይ አድሮ እኛን የሚዋጋ ዲያቢሎስ መኾኑን ልናምን ልናውቅ ልንረዳ ይገባል።

#መሠረታዊ_ጠላታችን_ማን_ነው? 
▸ ዲያቢሎስ ነው! የጨለማው ገዢ ነው! ክፉው መንፈስ ነው!

ስለዚኽ ወንድምኽን አትቀየመው! እኅትኽንም አትቀየማት! አንዳንድ ጊዜ በደካማነታቸው በእምነታቸው አለመጠንከር ወይ ሙሉ በሙሉ በዲያቢሎስ ተሸንፈው ባንተ ላይ ክፉ ሊሠሩ ይችላሉ።

ግን እዘንላቸው!
አንተስ አስተዋይ ኾነኻል፤ ነጻ ወጥተኻል። እውነትን መረዳት ችለኻል። በብርሃን ውስጥ ትመላለሳለኽ። ስለዚኽ በጨለማ ለታሰረው ወንድምኽ ልታዝንለት ይገባል!
~
t.me/Ewnet1Nat 🇨🇬
http://t.me/AlphaOmega930 🇨🇬

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

03 Dec, 16:00


🟢🟡🔴
ኅዳር 25 | #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ሰማዕትነት ተቀበለ።

#ቅዱስ_መርቆሬዎስ ስሙ ፒሉፓዴር (ፒሉፓተር) ይባላል። ትርጉሙም "የአብ ወዳጅ" ማለት ነው። በኋላ ሊቃውንት መርቆሬዎስ  አሉት። መርቆሬዎስ ማለት ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ (የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ) ነው።

የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ደግሞ ለሰማዕቱ ያላቸውን ፍቅራቸውን ጨምረው አቡ ሰይፊን (Abu Seifin- ባለ ሰይፉ አባት) ይሉታል።

ቅዱስ ገብርኤል በርበሮችን እንዲያጠፋ ከንጉሥ ዳኬዎስ ጋር ሲዘምት ሰይፍ ያቀዳጀው፣ ገጸ ከልብ (ፊቱ የውሻ፣ መኻሉ የሰው፣ እግሩ የአንበሳ፣ ታቹ የጋለ ነሐስ የሆነ ፍጡር) ጓደኛው የሆነ፣ እርሱ ሰማዕት ከሆነ በኋላ ጥቁሩ ፈረሱ ወንጌልን የሰበከ ቅዱስ ነው።

ከበርበሮች ጋር ጦርነቱ በእግዚአብሔር ኃይል ከተፈጸመ በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን ሊያደርግ ወደደ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን አብሮት አልወጣም ወደ ቤቱ ሔደ እንጂ። በዚያንም ጊዜ ንጉሥ መልእክተኞችን ልኮ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወደርሱ አስመጥቶ ለአማልክት ዕጣን አሳርግ እና ስገድ አለው።

በዚያንም ጊዜ ትጥቁንና ልብሱን ወረወረለትና ንጉሡን እንዲህ አለው፦ "እኔ ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም! ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም።"

ንጉሥ ዳኬዎስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ። እርጥብ በሆኑ የሽመል በትሮች እንዲደበድቡት አዘዘ። ሁለተኛም ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ይገርፉት ዘንድ አዘዘ።

በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ስለ ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳይነሡበት
ፈርቶ ወደ ሆነች ወደ ቂሣርያ በብረት ማሠሪያ አሥሮ ላከው። በዚያም እንዲአሠቃዩት አዘዘ።

ከአሠቃዩትም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና ተጋድሎውን ፈጽሞ በመንግሥተ ሰማያት የሕይወት አክሊልን ተቀበለ።

◦◦🌿◦◦
T.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

25 Nov, 17:58


🟢🟡🔴
ኅዳር 17 | ልናከብራቸው የሚገባን፦

#ቅድስት_ወለተ_ጴጥሮስ ዕረፍቷ ነው።

የተወለደችው በ16ኛው መ/ክ/ዘ ዳውሮ አካባቢ ነው።  ወላጆቿ ባሕር አሰግድና ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ። ክርስትናን በሚገባ አጥንታ አደገች።

ወላጆቿም ግድ ብለው ሥዕለ ክርስቶስ የተባለ የሱስንዮስን የጦር መሪ አጋቧት። እስከ 24 ዓመቷም 3 ልጆችን ወለደች።

"ፈጣሪዬ ሆይ እነዚህ 3 ልጆቼ አንተን የማያስደስቱ ከሆነ በሞት ውሰዳቸው" ብላ ብትጸልይ 3ቱም በሞት ተወስደዋል፡፡

ባሏ እጅግ እየወደዳት እርሷ ግን ከሞላ ሀብቷ ከሞቀ ቤቷ ተለይታ ወጥታ በጣና ባሕር ላይ ቆማ መጸለይ ጀመረች፡፡ በዛም ልብሷ ለገዳሙ ያበራ ነበር።

ባሏም እምነቱን ቀይሮ ከካቶሊኮች ጋር ስለተዛመደ ቅድስቷን በገመድ አስረዋት በጎንደር ከተማ ጎዳና ላይ ጎትተው አሠቃይተዋታል፡፡

ከዚህ በኋላ እየዞረች መና* ፍቃን ስታሳፍር፣ ሕዝቡን ስታጸና ዓመታት አለፉ። በሷ ስብከትም ብዙ መነኮሳትና ምዕመናን ሰማዕት ሆኑ። እሷም በየገዳማቱ ተንከራተተች። በደዌ ተሰቃየች። በንጉሡ ተይዛ 2 ጊዜ ወደ በርሃ ተሰደደች።

በተወለደች በ50 ዓመቷም በ1630ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ዐርፋ ተቀብራለች። የተጋድሎ ዘመኗም 26 ዓመታት ናቸው። ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ሰማዕትም ጻድቅም ናት።

ከመነነችበትም ጊዜ ጀምሮ ምግቧ የመረረ ቅጠል፣ ኮሶና አመድ ነበር።
🌿

"በግ ጅብ ገደለ፣ ቅል ድንጋይ ሰበረ" የሚባልላቸው፣ እንኳን መኻን ሰው በቅሎን ባለ ልጅ ያደረጉ፣

በተቆረጠው እጃቸው ፋንታ የብርሃን እጅ የተሰጣቸው፣ በጌቴሰማኒ ያለችው (ቅዱስ ሉቃስ የሣላት) የእመቤታችን ሥዕል በየጊዜው የምታነጋግራቸው፣

ሰው የሚገበርለትን ዘንዶ የገደሉ ጻድቅ እና ሰማዕት
#አቡነ_ሲኖዳ_ዘጽሙና ዕረፍታቸው ነው።
🌿

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ የሥጋው ፍልሰት ነው።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

25 Nov, 13:43


በፒያሳ ደዳች ውቤ ሰፈር ከፍተኛ መጠን ያለው የእሳት አደጋ ተከሰተ

ሕዳር 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ፤ አራዳ ክፍለ ከተማ ራስ መኮንን አካባቢ፤ በተለምዶ ፒያሳ ደጃች ውቤ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ከፍተኛ መጠን ያለው የእሳት አደጋ ተከስቷል።

አደጋው በአካባቢው በሚገኘው በቻይና ጃንጉዜ የኮንስትራክሽን ሥራ ድርጅት ላይ ሲሆን፤ እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

24 Nov, 21:31


ሂዝቦላህ በእስራኤል ላይ ባደረሰው የሮኬት ጥቃት በቴል አቪቭ እና ሃይፋ ከተሞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

24 Nov, 17:02


👉 በምንዝርና፣ በውሸት፣ በጭካኔ፣ በሌብነት፣ በነፍሰ ገዳይነት፣ የተበከልክ ሥራህም ያደረግህ ወንድም ሆንክ ሴት በፈጣሪ እሳት ትበጠራለህ። ማንም የሚያመልጥ የለም። መልካሙን ዘመን የሚያዩት በፈጣሪአቸው ሕግ የተመሩ፣ የኖሩ፣ ሲወቀሱ ፈጥነው ንስሐ የገቡ ብቻ ናቸው። ከጥፋት ወደ ጥፋት ለምትነጉደው፣ ተግሳጽና ምክር ለናቅከው፣ ለጠፋኸው ትውልድ፣ የጨለማ ልጅ ከጨለመ ሥራው ጋር ጨለማው ሲጠረግ አብሮ ይወገዳል። የብርሃን ልጅ ደግሞ በብርሃን ዓለም ተባርኮ ይኖራል።

👉
ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ሁለት ላይ የተወሰደ!

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

24 Nov, 10:16


🇪🇸 🌥 በቅርቡ በጎርፍ በተመታችው የስፔኗ ቫሌንሺያ ከተማ ያልተለመደ የሰማይ ገጽታ ታይቷል

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

23 Nov, 07:46


📌  ዓለምም ታመሰ ተቆላ ተፈጨ ኢትዮጵያም እንዲሁ በምታዩት መልኩ ተጨነቀች ተጠበበች ፍጅቱም ጦርነቱም እልቂቱም ዘረኝነቱም ርሃቡም አጥለቀለቃት።

📌 ደጋግመን እንደተናገርነው ኢትዮጵያ ቀድማ ነጻ ትወጣለች ከላይዋ ላይ የበቀለው የጨለማው ኃይል ሁሉ  በአብዛኛው በእግዚአብሔር ኀይል ቀሪው በታማኝ ባሮቹ ሰይፍ ተጠርጎ ይወገዳል።

🌍 ዓለም ደግሞ እግዚአብሔር ለሚተክለው የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት እየተረገጠች እየተፈጨች እየተቆላች በእሳት እየተበላች የሚትርፉት ጥቂት ሳይወዱ በግድ እጃቸውን ለእግዚአብሔር በሚሰጡ ሰዎች በስተቀር የተቀረው እየተበላ ለዛም እጃቸውን የሰጡትን ሰዎች ተቀብሎ በመላው ዓለም የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥቱን አገዛዝና  እና አስተዳደሩን አስፍኖ ይቆማል።

❗️ይህ ሲታይ ሲፈጸም ነው ከዚያን በኃላ የእግዚአብሔር ሰይፍ እና ቁጣው መቀዝቀዝ መብረድ ቀስ በቀስ መቀነስ የሚጀምረው እግዚአብሔር ይህንን እውነት ፈቃዱን ሳያረጋግጥ "ይቀራል፣ ሰላም ይመጣል፤ በዚህ እንዲህ አድርገን ሰላም እናመጣለን፤ በዚህ እንዲህ ተደርጎ እረፍት  እናደርጋለን፤ እድገት እናደርጋለን በዚህ..." ይህን ተረታችሁን እሱ እዛው ቀረ በቃ !!

🔥 አበቃ የሱ እድሜ አብቅቷል ! ተዘግቷል የእግዚአብሔር ሕዝብ ዘመን ደግሞ የብርሃን ዘመን ይመጣል ።

ያ ደግሞ ፈቅዳችሁ የምታደርጉት አይደለም እግዚአብሔር የሚጠረገውን ጠራርጎ የሚጸዳውን አጽድቶ ለሕዝቦቹ ምድሪቱን ያስረክባል።

☀️ በረከት ፣ሰላም ፣ ፍቅር ፣ ቸርነት ፣ በጎነት ከሱ ትፈሳለች። ለዓለም ብርሃን ይሆናል ከኢትዮጵያ የሚፈሰው ብርሃን
እግዚአብሔር በምድሪቱ  ይከብራል ድንግል ትከብራለች ።

የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ እምነት  ደግሞ ለዓለም ሁሉ ብርሃን ሆና ታበራለች። ለሕይወትም ለነፍስም ለሥጋም የሚሆነውን ቃል ሁልጊዜ ያለማቋረጥ ትመግባለች ።

🇨🇬 ኢትዮጵያ በተረጋገጠ በተደላደለ መልኩ ዓለምን እየገዛች ታስተዳድራለች ።

ይሄ ቃል አይናወጽም ይህ እስከሚፈጸም የእግዚአብሔር  ቃል ይህ ቃል እስከሚከናወን ድረስ የጥፋቱ እርምጃ ይቀጥላል።

♻️ መቅሰፍቱ ይቀጥላል መጠኑ ይጨምራል በ7፣ በ49፣ በ400 በምን... እያለ ይቀጥላል ሙልጭ ብለህ እስክትጠናቀቅ ድረስ ይሄንን ደጋግመን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን ከወዲሁ❗️

🔜 ልብ ብለህ አድምጥ ከዚህ ውጪ የሚመጣ አለ ብለህ የምትደክም ወይም የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምትጻረር ከወዲሁ እርግጠኛ ሁን ! መጥፋትህን አረጋግጥልሃለው። እኔ የሥላሴ ባርያ የድንግል ባርያ  አሁንም ደግሜ እነግርሃለው መጥፋትህን አረጋግጥልሃለው።

🔈 ትከናወናለህ ትጠረጋለህ ትሰናበታለህ።
ዓለማችንም ኢትዮጵያም በኢትዮጵያዊነት በተዋሕዶ ኦርቶዶክስ እምነት በእውነተኛይቱ  እምነት ፤ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ በቃልኪዳኑ ምልክት እንዲሁም በቃል ኪዳኑ ቃሎች፦

🟢 ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር
🟡 ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም
🔴 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
🔴 ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ

እነዚህ ማንኛውንም የአዳም ዘር በኢትዮጵያም በመላው ዓለምም ኖርክ እምትበጠርበት የእሳት ወንፊት ይህ ቃል ነው እምትለካበት ሚዛን ይሄው፦  ቃሉነው ❗️

💯 የከበረው የእግዚአብሔር ቃል በቃ አበቃ ሌላ መንገድም ማምለጫም መፍትሔም የለም ።

📝 ከ1--10 የተጠቀሱት መልእክታቶች ትምህርቶች  መግለጫዎች በሙሉ አንዳቸውም ሳይቀሩ ነጥቧም ሳትጎል
የእግዚአብሔር ውሳኔና ትዕዛዝ ነውና ይፈጸማል  ይከናወናሉ፦

🔐 ጠፊውም እየጠፋ ተራፊውም እየተጸጸተ የጠላችኋቸውም የናቃችኋቸው ያሳደዳችኋቸው ብርቱ መከራን ያፈሰሳችሁባቸውም የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች እና የዋህ ትሁት ቅን  ሕዝቦች በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቀዳማይ እረኞች እየተመሩ ደግሜ ነው የምነግርህ እየተመሩ! በእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት ጸጋ  ተከበው በድንግል እቅፍ ሆነው፡ በሊቃነ መላእክቱ ታጅበው ምድርን እያንቀጠቀጡ ይመጡልሃል❗️ አሁንም ነው የምነግርህ ይመጡልሃል❗️ እኔ የሥላሴ ባርያ እየነገርኩህ ነው። የድንግል ባርያ እየነገርኩህ ነው።

የዛሬ 18 ዓመት ጀምሬ አይደል እየገርኩህ ያለውት አሁንም እየነገርኩህ ነው ይህንን እውነት ዛሬም ደጋግመን የምናዳኝብህና የምናረጋግጥልህ እኛ እኛ የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን  ቀዳማይ እረኞች ነን።

⚡️ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግለጫና የጥያቄዎቻቹ መልስ ክፍል- 5 --1:00 ስዓት ደቂቃ 14 -38 ሰከንድ ጀምሮ ካለው መግለጫ የተወሰደ።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

22 Nov, 08:50


🟢.ስደተኛ ይብዛብሽ ።

🟡.ልጆችሽ እረግተው አይቀመጡ ።

🔴.እንደተንከራተቱ ይኑሩ።

🟢.ሕይወታቸው በስደት ይለቅ።

🟡.ያንችን ትንሳኤ እንዳያዮ ለዘላለም ረገምኳቸው።

🔴.በረከትሽ ፈጽሞ አይድረሳቸው።

🟢.ሚስጥርሽም ይሰወራቸው ።

🟡.ያንች የሆነውን ሁሉ ጠላቶችሽ ይጠቀሙበት።

🔴.ልጆችሽ ግን ይሰወራቸው።

🟢.የባዕዳን ሃይማኖት እና ትምህርት ይውረራቸው።

🟡.የቅዱሳንሽ ቃል ኪዳን አይድረሳቸው ።

🔴.በፍቅረ ንዋይ አይናቸው ዝንተ ዓለም እንደታወረ ይኑር

በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

🟢.ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር ።

🟢.ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም

🟡.ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን

🔴.ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ
     
➻ሠላም እንዴትሰነበታችሁ እኛ ደና ነንን ልዑል እግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን።ዛሬ አንድ የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ አባት ገድላቸው ላይ የተገለጸውን እስኪ አንብበነው እንማርበት ከበረከታቸውም እናገኝ ዘንድ እንማጸናቸው።

➻እንደ ነብዩ ኤርምያስ በእናታቸው ማህፀን የተመረጡ ናቸው ብሉይንና ሀዲስ ኪዳንን ያጠናቀቁት በ12 ዓመታቸው ገዳም ለመግባት ወስነው ወላጅ እናታቸውን አሰናብችኝ ብለው ጠይቀዋል ቅድስት እናታቸውም መርቀው ሸኟቸውና ትግራይ ውስጥ ወደ ሚገኘው ደብረ ፀራቢ ወደ ሚባል ገዳም ገቡ።

➻ የገዳሙ አስተዳዳሪ አቡነ በኪሞስ የምንኩስና ቀንበሩና ሸክሙ እጅግ የከበደ መሆኑን በመንገር ወደ እናታቸው እንዲመለሱ ቢነግሯቸውም አቡነ ፊልጶስ ግን ለምንኩስና የታጩ ሙሽራ መሆናቸውን ነግረዋቸው ከብዙ ፈተና በኋላ ጽናታቸውን አይተው አመንኩሰዋቸዋል።

 ➻በገዳሙ እንጨት እየለቀሙ ውኃ እየቀዱ የክርስቶስን ሕመሙንና ሞቱን እያሰቡ በፀሎት ከኖሩ በኋላ ጌታችን ተገልጦ ወደ ሽሬ እንዲሄዱ ከነገራቸው በኋላ በሽሬ አዲ አቦ በተባለ ስፍራ ሂደው ብዙ አስደናቂ ታምራትን ካደረጉ በኋላ ወደ ደብረ ቢዘን እንዲሄዱ ተነግሯቸው የእሳቸውን በረከት ለመቀበል ከመጡት 16 መነኮሳት ጋር ወደ ደብረ ቢዘን ሄዱ።

    ➻ጻዲቁ የሐይቅ እስጢፋኖስን ባህር በታምራታቸው ያቃጠሉ አባት ናቸው።
በንጉሡ በአፄ ዳዊት ዘመን ሰንበት አንዲት ናት እያሉ በሰንበት ስራ እንደሚሰሩ ሰምተው ሰንበት አንዲት ናት የሚሉትን ሁሉ ተቃወሟቸው ከግብፅ የመጡት ጳጳሳትም ቀደም ብለው ከአባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ አሁን ደግሞ ከአቡነ ፊልጶስ ጋር ንጉሡ አፄ ዳዊት አከራከሯቸው ጳጳሱም ተረቱ ።

➻ክፉዎችም በአቡነ ፊልጶስ ላይ በክፋት ተነሱባቸው በአቁማዳ ጠቅልለው ሀይቅ ውስጥ ጣሏቸው።በዚህ ጊዜ እሳቸው የተጣሉበት ባህር በእሳት ተቃጥሎ እንዲታይ አደረጉ።በጽኑ ሥልጣን ህዝቡንም መንግሥቱንም ረገሟቸው።

🟢.ስደተኛ ይብዛብሽ ።

🟡.ልጆችሽ እረግተው አይቀመጡ ።

🔴.እንደተንከራተቱ ይኑሩ።

🟢.ሕይወታቸው በስደት ይለቅ።

🟡.ያንችን ትንሳኤ እንዳያዮ ለዘላለም ረገምኳቸው።

🔴.በረከትሽ ፈጽሞ አይድረሳቸው።

🟢.ሚስጥርሽም ይሰወራቸው ።

🟡.ያንች የሆነውን ሁሉ ጠላቶችሽ ይጠቀሙበት።

🔴.ልጆችሽ ግን ይሰወራቸው።

🟢.የባዕዳን ሃይማኖት እና ትምህርት ይውረራቸው።

🟡.የቅዱሳንሽ ቃል ኪዳን አይድረሳቸው ።

🔴.በፍቅረ ንዋይ አይናቸው ዝንተ ዓለም እንደታወረ ይኑር

➻ይህ ውግዘት ለቀድሞዋ ኢትዮጵያ ለአሁኗ ደግሞ ኢትዮጵያና ኤርትራ (ባህረ ነጋሽ) ልጆች የተላለፈ እርግማን ነው።

 ➻ በዚህ ጊዜ ንጉሡም ህዝቡም ሁሉም ተረበሸ።
እንደ ምጽአት ቀን ያስፈራ ነበር። እርግማናቸው ከመባርቅት ጎልቶ በሚያስፈራ ነጎድጎድ ይሰማ ነበር።

 ➻.ዛሬም ድረስ በሐይቅ እስጢፋኖስ ባህር ዳርቻ ላይ የተቃጠሉ ድንጋዮች ይገኛሉ።

➻.በወቅቱም የንጉሡ ሚስት በዋናተኞች አስፈልጋ ከሐይቁ ውስጥ አሰወጥታቸው እግራቸውንም አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ ጠጣችው።ወዲያውም ከማህፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ይወጣል ብለው ትንቢት ተናግረዋል።በትንቢቱም መሰረት ንጉሡ አፄ ዘርዓያዕቆብ ተወለደ።

➻.በወቅቱ በተፈጠረ አለመግባባትና ክፉዎችም በባህር ውስጥ ስለጣሏቸው እርግማንን በህዝቡ ላይ አምጥተዋል።
ንጉሡ አፄ ዳዊትም አቡነ ፊልጶስን ከልብ ይቅርታ ጠይቀው ወዲያውም ታርቀዋል።
በዘመናቸውም ርሃብ ስለነበረ ፃዲቁን ከገዳማቸው አስጠርተው ምን ባደርግ ይሻለኛል ብለው አማክረዋቸዋል።
ጻዲቁም የጌታችንን መስቀል ያስመጡ ብለው መከሯቸው ንጉሥ አፄ ዳዊትም በአቡነ ፊልጶስ ምክር መሠረት ከእየሩሳሌም መስከረም 10 ቀን አስመጥተውታል።

➻.አቡነ ፊልጶስ በደብረ ቢዘን ገዳም በታላቅ ተጋድሎ ኑረው ከጌታችን ዘንድ ታላቅ ቃልኪዳን ተቀብለዋል።
ላንተ የተሰጠህ ቃል ኪዳን ለማንም አልተሰጠውም
➻.ክብርህ ገናና ነው።

➻.በቃል ኪዳንህ ለተማፀነ የማልፈጽምለት የለም።
➻.ገዳምህን ዘወትር በበረከት ደመና ከብቤ አኖረዋለው ።

➻.ምሕረትን ፈልጎ ደጅህን ለረገጠ አንተን ባከበርኩበት ልክ አከብረዋለሁ።
➻.አስተዋይ ልቦናን እሰጠዋለው።

➻.የኢትዮጵያን ምስጢር እገልጥለታለው ብሎ ጌታ ቃል ገብቶላቸዋል ።

➻.ነሐሴ 5 ቀን በታላቅ ክብር አርፈዋል !!!
           
➻.እንግዲህ ዛሬም እየሆነ ያለውን ማየት ነው እየተፈጸመ ነው እንሰደዳለን :ሀገር እንጠላለን ከውስጥ ይልቅ ውጭነት ይማርከናል ።

➻.እንደ ሀገር እንደ ህዝብ ታመናል ብሎ የሚመረምር ትውልድ እንኳ ጠፍቷል።

 ➻. የእውነተኛ አባቶቻችን ውግዘት ምን ያህል ከባድና ለቅጣት እንደሚዳርግ ከዚህ መረዳት ይቻላል።ዛሬም በዚህ ዘመን የተላለፈውን የአባታችን ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ውግዘትን የማናከብር ከሆነ ከዚህ የከፋ መከራ ውስጥ እንገባለን ማለት ነው።ያው እንደምናየው ህዝቡም እያከበረው አይደለም ያው የሚሆነውን ማየት ነው እንግዲህ።
➻. እግዚአብሔር ይመስገንና እኛ ግን እውነትን ሰምተናል በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን እውነት እስከመጨረሻው ያጽናን!
➻.የጻዲቁ አቡነ ፊልጶስ በረከታቸው ይደርብን።

➻.በአንድ ወንድም ምክንያት ገድላቸውን ሠማሁና ለሁሉም አስተማሪ ስለሆነ ነው ያጋራሁአችሁ


.ሠላመ እግዚአብሔር ቅን፣ የዋህ፣ ትሁት ከሆነ ኢትዮጵያን ከልቡ ከሚወዳት ጋር ይሁን።
13/03/2017 ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

22 Nov, 01:26


🟢🟡🔴
ኅዳር 13 | በዚህች ቀን #የቅዱሳን_አእላፍ_መላእክትን የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙን።

እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የሆኑ ለዓለሙ ሁሉ የሚማልዱ ናቸው።

ይህ ዕለት በሊቃውንት አንደበት "አእላፍ" እየተባለ ይጠራል። በሃይማኖት  በተልእኮትና በምስጋና የሚኖሩ 99ኙ ነገደ መላእክት በአንድ ላይ የሚከበሩበት ቀን ነው።

እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100)፣ በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጓቸዋል። አቀማመጣቸውንም በ3 ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጓል።

መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር፣ ራማና ኢዮር" ይባላሉ። አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነዋና ሊቃነ መላእክታቸው ይህንን ይመስላሉ፦

1. አጋእዝት (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል፥ አሁን የተረፉት #በቅዱስ_ሚካኤል ሥር ናቸው)

2. ኪሩቤል (አለቃቸው ቅ/ኪሩብ)

3. ሱራፌል (አለቃቸው ቅ/ሱራፊ)

4. ኃይላት (አለቃቸው ቅ/ሚካኤል)

5. አርባብ (አለቃቸው ቅ/ገብርኤል)

6.መናብርት (አለቃቸው ቅ/ሩፋኤል)

7. ሥልጣናት (አለቃቸው ቅ/ሱርያል)

8.መኳንንት (አለቃቸው ቅ/ሰዳካኤል)

9. ሊቃናት (አለቃቸው ቅ/ሰላታኤል)

10. መላእክት (አለቃቸው ቅ/አናንኤል) ናቸው።

ከእነዚህም አጋእዝት፣ ኪሩቤል፣ ሱራፌልና ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው።

አርባብ፣ መናብርትና ሥልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው።

መኳንንት፣ ሊቃናትና መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው።

ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም። ዕረፍታቸው ምስጋና፣ ምስጋናቸው ዕረፍት ሆኖላቸዋልና። በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም ለመዓትም ይላካሉ።
🍀

t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

21 Nov, 05:32


🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል አራት (4)

በድምፅ ንባብ (በትረካ)

(📌 ክፍል 1ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 2ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 3ን ለማዳመጥ 👈)

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ማነው?

🌿 ሕይወቱና ተጋድሎው
🌻 ቃልኪዳኑና
🌹 ሰማዕትነቱ
...

📌 ቁጥር 1) ከዚህ ሥር አጭር ዜና ሕይወቱንና ከመድኃኔዓለም የተቀበለውን ልዩ ቃልኪዳን በፅሑፍ ያንብቡ👇

🫴 https://t.me/Ewnet1Nat/14510

PDF ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ (በ1988 ዓ.ም የታተመ)👇

https://t.me/kidusan_page/50

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

21 Nov, 03:25


💚💛❤️ ኅዳር 12. በዓለ ሲመቱ ለክቡር ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል

እንኳን አደረሳችሁ !

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

20 Nov, 17:01


👆👆👆 ዋኖቻችንን እንወቅ ❗️
#ክፍል_4

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ማን ነው?

በድምፅ ንባብ (በትረካ) የተዘጋጀው ነገ (ኅዳር 12/2017) በአመታዊ መታሰቢያው ዕለት ይለቀቃል !

#እንኳን_አደረሳችሁ !

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

20 Nov, 15:30


🟢🟡🔴
ኅዳር 12 | በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ፣ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ #ቅዱስ_ሚካኤል የተሾመበት የበዓሉ መታሰቢያ ነው።


ዳግመኛ በዚህች ዕለት #ቅዱስ_ሚካኤል #ኢያሱ_ነቢይን የተራዳበት መታሰቢያ ነው።

ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሁኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው ከእኛ ሰዎች ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ አለው። እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወዳንተ መጥቻለሁ አለው።

ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል አለው። የእግዚአብሔር የሠራዊቱም አለቃ ሚካኤል ኢያሱን የቆምክባት ምድር የከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው ኢያሱም እንዳለው አደረገ።

እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ በውስጧ ያለውን ንጉሧን ከኃያላኑና ከአርበኞቹ ጋር በእጃችሁ ኢያሪኮን እነሆ አስገባታለሁ።

ይህም የከበረ መልአክ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር በመሆን ገድላቸውን እስከሚፈጽሙ የሚያጸናቸውና የሚያስታግሣቸው ነው ።

ስለ ልዕልናውና አማላጅነቱ በየወሩ በ፲፪ ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠራለት።

እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲአወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲአደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲአደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናል።


#ቅዱሳን_ዱራታኦስ_እና_ቴዎብስታ የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ናቸውና በዚህች ዕለት ይታሰባሉ።


በዚችም ቀን የኢትዮጵያ ንጉሥ #የጻድቁ_በእደ_ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። እኚህም የመጀመርያውን #መልክአ_ማርያም የደረሱ ናቸው።
 ◦🍀

+ የመጥምቁ
#ቅዱስ_ዮሐንስ ራስ በደብረ ማህው የታየችበት ዕለት መሆኑን ስንክሳሩ ይጠቅሳል፡፡

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

20 Nov, 14:21


🇮🇱🇵🇸 እስራኤል በዌስት ባንኳ ጀኒን ከተማ መሰረተ ልማቶችን አወደመች

ከሰኞ ምሽት ጀምሮ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ጀኒን ከተማ እና ካምፖችዋ ላይ ጥቃት ፈጽሟል።

በፍልስጤማውያን ታጣቂዎች እና በእስራኤል ኃይሎች መካከል ያለው ግጭት የቀጠለ ሲሆን እስራኤሎች በዶዘሮ ተሽከርካሪዎች የከተማዋን ዋና ዋና መንገዶችና መሠረተ ልማቶች አፈራርሰዋል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

20 Nov, 05:54


📌 እኛ ከእንግዲህ ድርሻችንን ተወጥተናል።

እግዚአብሔር ያዘዘንን ገልጸናል። አድርሰናል።

ግዳጃችንን ተወጥተናል።

እንግዲህ ወገኖቼ እዳ የለብንም።

የፍቅር እዳ የለብንም።

የታዘዝንበትም እዳ የለብንም።

ሁሉንም ነገር በጊዜውና በሰአቱ በዚህ ክፉ ሰአት ውስጥ ሁሉ
ሊደርስ ወደ ሚገባው ሁሉ አድርሰናል ማለት ነው።

ከእንግዲህ በየበዓታችን ሆነን መጪውን የእግዚአብሔርን እርምጃ ማየት ብቻነው።

ኖህ በመርከቡ አይደል! የተካተተው?
አዎ እኛም በእምነት መርከባችን ተካተን  ውጤቱን መከታተል ብቻ ነው።

መቼም ለምታስተውሉ አለም ወዴት እየሄደች እንደሆነ ግልጽ እያየን ስለሆነ
ምንም ድብቅም ስለሌለ።
ከእንግዲህ ለአዳም ዘር አስተዋሽ አያስፈልገውም ።ፍርዱ ሁሉ ከደጁ ነው።
የቁጣው እሳት ሲያጠልመው ሲለበልበው ሲያቀልጠው ያኔ የእግዚአብሔር ፍርድ ነውና ይገበዋል።በ ፍርዱም ይካተታል።
እኛ ደግሞ እግዚአብሔርንን እያመሰገንን በየበዓታችን መቀመጥ ነው።
እኛ የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች
ልንበረታ ይገባል
ከነበረን የእምነት ጥንካሬ ልንላላ አይገባም።እውነትን ከተረዱ በኋላ ወደ ኃላላ በሚያፈገፍግ ነፍስ እኔ ደስ አልሰኝም አዝናለሁ ነው የሚለው ቸሩ መድኃኔዓለም ስለዚህ ይህንን ቃል እያስታወሳችሁ በጀመራችሁበት መንፈሳዊ ጥንካሬ ተመላለሱ።ምንም አይነት ፈተና ቢገጥማችሁ ምንም አይነት ችግር ቢታይ በእምነት እለፉት እንጂ ከእምነታችሁ አትጉደሉ።
⚡️ለአለም መንግሥታት እና ሕዝብ ይደርሱ ዘንድ በቀን 7/5/2016 ዓ,ም ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንሥት ከተጻፉት ደብዳቤች መካከል
በንባብ  ከተላለፈው ክፍል 1 መግቢያ እና ማብራሪያ ላይ የተወሰደ።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

20 Nov, 05:54


የኔቶ አባል ሀገራት ህዝባቸውን ለጦርነት በማዘጋጀት ላይ ናቸው

ዜጎች ለጥቂት ጊዜያት ሊያገለግሉ የሚችሉ መሰረታዊ ግብአቶችን ገዝተው እንዲያከማቹ ታዘዋል።
👇👇👇

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Nov, 09:20


በትግራይ ክልል በየሳምንቱ 17 ሺህ ሰዎች በወባ እየተያዙ ነው

በትግራይ ክልል ባለፉት 3 ወራት በወባ በሽታ ምክንያት 13 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። የትግራይ ጤና ቢሮ በተለይም ወባን ለመካለከል እና ለመቆጣጠር ከፌደራል መንግስቱ የአቅርቦቶች ድጋፍ እንደሚሻ የሚገልፅ ሲሆን እስካሁን ግን የሚጠበቀው እንዳልተገኘ የክልሉ ጤና ቢሮ የበሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ቡድን መሪ አቶ አረጋይ ገብረመድህን ጠቅሶ ዶቼቬሌ ዘግቧል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Nov, 09:13


«ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የሻረው ሕግ!»
— አለቃ አያሌው ታምሩ —
ስለውግዘቱ የሰጡት አስደናቂ ማብራሪያ !

🟢🟡🔴 t.me/AlphaOmega930

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Nov, 08:47


📌 በጉቦ የተቀጠረም የቀጠረም ክህነት የሰጠም የተቀበለም ሁሉ ዲያቆንም ይሁን ቄስም ይሁን ጳጳስም ይሁን ምንም ይሁን ምን #ክህነት የለውም !! መቀደስ፤ ማቁረብ፤ ማጥመቅ ወዘተ በክህነት የሚፈጸሙ ሚስጥራትን ሁሉ የመፈጸም ስልጣን ፈጽሞ የለውም። ይሄንን በድፍረት ቢያደርገውም አይሰምርለትም!! በሐዋርያት የተወገዘ ነውና በነፍሱም አይድንም ! ቃሉ ነው እንግዲህ ምን ይደረግ!? አራት ነጥብ ።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

18 Nov, 10:29


📌 ኢትዮጵያዊነትን አስቀድም❗️

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

18 Nov, 09:36


የሦስት ሜትር ርዝመት ያለው "የጥፋት ቀን አሳ" ተብሎ የሚጠራው ዓሳ በካሊፎርኒያ የባህር ዳርቻ ላይ ተገኝቷል -

በሦስት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው በካሊፎርኒያ የታየው

ይሄ ዓሳ እንደ የመሬት መንቀጥቀጥ ወይም ሱናሚ ያሉ የተፈጥሮ አደጋዎችን ጠሪ ነው ይባላል::

እ.ኤ.አ. በ 2011 ከእነዚህ ዓሦች ውስጥ 20 የሚሆኑት በጃፓን የተገኙ ሲሆን ብዙም ሳይቆይ በታሪክ ውስጥ በጣም ኃይለኛ ከሆኑት የመሬት መንቀጥቀጦች አንዱ ተከስቶ ነበር::

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

18 Nov, 07:05


🟢🟡🔴
ኅዳር 9 | እጅግ የከበሩ ሃይማኖታቸው የቀና #318ቱ #ቅዱሳን_አበው ሊቃውንት በ325 ዓ.ም በኒቅያ አርዮስን ያወገዙበት ዕለት ነው፡፡

በዚህም ወልድ በመለኮቱ ከአብ ጋር ትክክል እንደሆነ እያስረዱ የቀናች ሃይማኖትን አስተማሩ የተረገመ አርዮስንና በረከሰች ትምህርቱ የሚያምነውን አውግዘው ለዩ

የሠሩዋት ያስተማሩዋትም የሃይማኖት ትምህርት ይህች ናት። እንዲህ ብለው፦

ሁሉን በያዘ ሰማይና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። .....

ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን።.....

ከዚህም በኋላ የመንፈስ ቅዱስ ጠላት ስለሚሆን ስለመቅዶንዮስ በቊስጥንጥንያ ከተማ መቶ ሃምሳው ኤጲስቆጶሳት በተሰበሰቡ ጊዜ ከዚህ የቀረውን ሠሩ። እንዲህም አሉ፦

ጌታ ማሕየዊ በሚሆን ከአብ በሠረፀ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን። እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋራ በነቢያት የተናገረ። ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እናምናለን። ኃጢአትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀትም እናምናለን። የሙታንንም መነሣት የሚመጣውንም ሕይወት ተስፋ እናደርጋለን።

በረከታቸው ትድረሰን።
t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

17 Nov, 15:39


የሄዝቦላህ ዋና ቃል አቀባይ መሐመድ አፊፍ በእስራኤል የአየር ጥቃት ተገደለ
****

የሄዝቦላህን ባለስልጣን ጠቅሶ አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘበ፥ የሄዝቦላህ ዋና ቃል አቀባይ መሐመድ አፊፍ እስራኤል ዛሬ ባልተለመደ ሁኔታ በማዕከላዊ ቤይሩት በፈፀመችው የአየር ጥቃት ተገድሏል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

17 Nov, 11:18


መርካቶ ሽንኩርት ተራ የተነሳው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉን ሰምተናል::

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

17 Nov, 10:00


📌 2ኛው ዙር...

- እነማን ይተከላሉ--- አዎን እግዚአብሔር ወደትንሳኤው ይሻገሩ ዘንድ የወደዳቸው ሁሉ በመላው ዓለም ይተከላሉ። የሚበዙ የምድራችን ከተሞች ሁላችሁም እንደምታውቁት ሰንበትን በመጣስ የተገነቡ፤ ዲያብሎስን በአንድም በሌላም መንገድ ለማንፀባረቅና ለማስረፅ የተሰሩ ናቸውና ሙሉ በሙሉ ይጠረጋሉ በምትካቸውም በተቀደሱ እግዚአብሔርን ባከበሩ ቅድስናቸውን በጠበቁ ሰንበትን  በሚያከብሩ የልኡልን ሕግ በሚያከብሩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በአስደናቂ ሁኔታ መልሰው ይገነባሉ።...»

👉ሙሉውን ያንብቡ!👈

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

17 Nov, 07:55


https://vm.tiktok.com/ZMhtYF2PL/

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

17 Nov, 07:17


🟢🟡🔴
ኅዳር 8 | በዚህች ቀን ልናከብራቸው የሚገባን የቅዱሳን ክቡራን #አርባዕቱ_እንስሳ እና #የቅዱስ_አፍኒን_ሊቀ_መላእክት በዓላቸው ነው።

✥ ዳግመኛም እሱ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያህል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የሌለ #ቅዱስ_ቆስጠንጢኖስ_ንጉሥ አዳኝ መስቀሉ የተገለጠለት ቀን ይህ ነው።

T.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

17 Nov, 07:17


🟢🟡🔴
ኅዳር 8 | ቅዱሳን አርባዕቱ እንስሳ (ኪሩቤል) የቅድስት ሥላሴን መንበር ለለሸከም የተሾሙበት መታሰቢያ በዓል ነው።

በእውነት ያለ ሐሰት #የቅዱሳን_አርባዕቱ_እንስሳን ነገር መናገር፣ ማክበርና መዘከር ለእኛ ለክርስቲያኖች ይገባል።

ከቅዱሳን መላእክት መካከል ትልቁን ሥፍራ ዛሬ የምናከብራቸው ነገደ ኪሩቤል (ዐርባዕቱ እንስሳ) ይይዛሉ። መንፈሳውያን ከመሆናቸው በላይ መንበረ ጸባኦትን እንዲሸከሙ ስላደላቸው ክብራቸው ታላቅ ነው። ከመላእክት ወገንም ቅሩባን እነርሱ ናቸው።

ዘወትርም ስለ ፍጥረታት (ሰዎች፣ እንስሳት፣ አራዊትና አዕዋፍ) ምሕረትን ይለምናሉ። ለዚህም ነው በ4 (በሰው፣ በንስር፣ በላምና በአንበሳ) መልክ የተሳሉት። ቅዱስ መጽሐፍም ስለ እነርሱ ብዙ ይላል። (ሕዝ. 1:5፣ ራዕ. 4:6፣ ኢሳ. 6:1)

በተለይ ግርማቸው እንደሚያስፈራ ተጽፏል። "ምሉዓነ ዐዕይንት - ዐይንን የተሞሉ" ይላቸዋል። ይህንንም መተርጉማን "ምሥጢር አዋቂነታቸውንና ግርማቸውን ያጠይቃል" ሲሉ ተርጉመውታል።

ዐርባዕቱ እንስሳን 4 ሆነው በሥዕል ብናያቸውም "ከመ ርዕየተ እለ ቄጥሩ" እንዲል እያንዳንዱ ከወገብ በላይ አራት በመሆናቸው ተሸካሚዎቹ 16 መልክ አላቸው። በ2 ክንፋቸው ፊታቸውን፣ በ2ቱ እግራቸውን ሸፍነው በ2 ክንፋቸው ይበራሉ። ይህም ብዙ ምሥጢር ሲኖረው ዋናው ግን አርአያ ትእምርተ መስቀል ነው።

4ቱ እንስሳ (ኪሩቤል) በሐዲስ ኪዳንም ልዩ ክብር አላቸው። 4ቱ ወንጌል ሲጻፍ እየተራዱ ስላጻፉ በስማቸው ተሰይሟል። ቅዱስ ማቴዎስን ገጸ ሰብእ፣ ቅዱስ ማርቆስን ገጸ አንበሳ፣ ቅዱስ ሉቃስን ገጸ ላህም፣ ቅዱስ ዮሐንስን ገጸ ንስር እየተራዱ ስላጻፏቸው እነሆ እስከ ዛሬ ድረስ ዘብእሲ ማቴዎስ፣ ዘአንበሳ ማርቆስ፣ ዘላሕም ሉቃስ እና ዘንስር ዮሐንስ እየተባሉ ይጠራሉ።

እነዚህ ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን ስለ መራዳታቸውም በብዙ ገድላትና ድርሳናት ላይ ተጽፏል። የራሳቸውን "ድርሳነ ዐርባዕቱ እንስሳን" ጨምሮ በገድለ አባ መቃርስና በገድለ አባ ብስንድዮስ ላይ በስፋት ግብራቸው ተጽፏል።
🍀

ዳግመኛም በዚህች ዕለት #ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_አፍኒን የተሾመበት ዓመታዊ በዓሉ ነው፡፡

ይህም #ከሱራፌልና_ከኪሩቤል ጋር የልዑልን የጌትነቱን ዙፋን የሚጠብቅ ነው፡፡

ስለዚህም ክቡር መልአክ ሄኖክ እንዲህ አለ፡- "…ያንን ቤት #ሱራፌልና_አፍኒን ዙሪያውን እየዞሩ ይጠብቁታል፣ እነርሱም የልዑልን የጌትነቱን ዙፋን ሲጠብቁ የማያንቀላፉ ናቸው" እንዳለ።
🍀

ይህቺ ቀን ታላቁ ንጉሥ በፈለገ ኮቦር #ቅዱስ_መስቀልን የተመለከተባት ናት። መክስምያኖስን ሊወጋ ወደ ሮም በተጓዘ ጊዜ በሰማይ ላይ መድኅን መስቀል ተዘርግቶ በላዩ ላይ "ኒኮስጣጣን" የሚል በዮናኒ ልሳን ተጽፎበት ተመልክቷል።

ይህንንም "በዚህ ጠላትህን ድል ታደርጋለህ" ማለት ነው ብለው ተርጉመውለታል። ለእርሱም በጋሻው፣ በጦሩ፣ በሰይፉ፣ በፈረሱ ላይ የመስቀል ምልክትን አድርጎ ማኅደረ ሰይጣን መክስምያኖስን ድል ነሥቶታል። እኛንም በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን።

               ◦🍀🍀🍀

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

16 Nov, 11:33


Vehicle Inferno: Diesel tanker triggers massive fire in Lebanon

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

16 Nov, 11:32


Pakistan terrorist attack: 24 killed in train station tragedy

Police believe the blast early Saturday in the city of Quetta - which also left at least 50 more people injured - was sparked by a suicide bomber.

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

16 Nov, 11:23


🇱🇧🇮🇱 የእስራኤል ጦር ጄት በቤይሩት ጣዩነህ አካባቢ በሚገኝ ባለ 12 ፎቅ ህንፃ ላይ ከባድ ጥቃት ፈፀመ ❗️

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

16 Nov, 11:22


🇮🇱🇱🇧 የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻ የአየር ጥቃት አካሄደ ❗️

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

15 Nov, 09:19


"የእኛ አምላክ ስለባሮቹ ስለቃሉ ስለትዕዛዙ ስለሥርዓቱ ሲል በቅናት እና በቁጣ ካልተነሳ እርምጃውንም በማትገምቱት በማታስቡት መልኩ ይዞት ካልመጣ በእርግጥ እንዳላችሁት እኛ አምላክ የለንም ውሸታም ነንን ማለት ነው።

ስለዚህ የእናንተ አምላክ ከእግዚአብሔር ታግሎ ከአሸነፈ እኛም ተሸንፈናል ማለት ነው። እንግዲህ ሜዳውም ፈረሱም እነሆ ተዘርግቷል ሁሉንም እናየዋለን። ሲድራቅ: ሚሳቅ : አቢዲናጎምን ከእሳት ያወጣው አምላካችን: በእርግጥ ለአምላክነቱ: ለስሙ: ለክብሩ: ለፈቃዱ ቀናይነቱን ለልጆቹ ፈራጅነቱም በግልጽና በማትክዱበት መልኩ ሲውጣችሁ ተረት ብላችሁ የናቃችሁት ቃሉ ሲተገበርባችሁ አይ ተሳስተናል ማሩን እ ከልሉን አስጥሉን ማለት የለም። የለም የለም። መዳንም የለም። ከእነ ክህደትህ ከእነ ትዕቢትህ ሰዶሞን የበላው እሳት በሺ እጥፍ ተባዝቶ  ይበላሃል። ፌዝህ ንቀትህ ያድንህ በቃ እሱኑ ተማመን ። ያ የተማመንህበት ዲያብሎስ እሱ ያድንህ በቃ።

ያሳደድኸን የገደልኸን የአሰርኸን እኛ የልዑልም የድንግልም ታማኝ ባሮች ብትጮህ ብታቅራራ ሺ ጊዜ ብትኳትን ከእንግዲህ አታገኜንም ለአንዴም ለመጨረሻም ተሰነባብተንሃል።"


📌 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ፍርድ አዘል መግለጫ ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም ላይ የተወሰደ!

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

15 Nov, 09:17


🟢🟡🔴
ኅዳር 6 |
#በዓለ_ደብረ_ቁስቋም

ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ኹሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሤትን እናድርግ። የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ በዚህች ቀን ተመልሷልና። ስደቷን አስበን ካዘንን፥ መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና።


የአርያም ንግሥት፥ የፍጥረታት ኹሉ እመቤት ድንግል ማርያም ከባሕርይ አምላክ ልጇ ጋር ስደት ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች።

ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅ/ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አምላክ ልጇን አዝላ፣ በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቋጥራ፣ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች።

▸ የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች፣
▸ ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች፣
▸ የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች፣
▸ የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች፣
▸ የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች፣ ደከመች፤ አለቀሰች፤ እግሯ ደማ።

ለሚገባው ይኽ ሁሉ የተደረገው ለኛ ድኅነት ነው። በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው።
🌹

#አረጋዊው_ቅዱስ_ዮሴፍና #ቅድስት_ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል። ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና። ይህች ቀን መታሰቢያቸው ናት።
🌹


ዳግመኛም ዛሬ ከክርስቶስ ስደት 400 ዓመታት በኋላ #የግብጿ_ደብረ_ቁስቋም ታንጻ ተቀድሳለች።

ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድንግል እናቱን፣ ቅዱሳን ሐዋርያትን፣ አእላፍ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን፣ አስከትሎ ወረደ።

የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ቤተ ክርስቲያኑን አንጸው፥ ሕዝቡን ሰብስበው ይጠብቁት ነበርና ወርዶ ቀድሶላቸው ታላቅ ደስታ ሁኗል።

🌹🌹🌹
T.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

14 Nov, 16:25


🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል አምስት (5)

(📌 ክፍል 1ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 2ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 3ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 4ን ለማንበብ 👈)

📌 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሰላማ ማን ናቸው?

🍀 ኅዳር 26 - የልደታቸው በዓል
🌼 ታኅሣሥ 18 - ለኢትዮጵያ ጳጳስ ሊሆኑ
                            የተሾሙበት በዓል
🌺 ሐምሌ 26 - የዕረፍታቸው በዓል

እንደ ተሰጣቸው ክብር ያላከበርናቸው፣ የዘነጋናቸው ባለውለታና ብርሃናችን የአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን፦
🍀 ሕይወትና ተጋድሎ
🌼 ልዩ ቃልኪዳን
🌺 ህያው ትሩፋት

ከዚህ ሥር አጭር ዜና ሕይወታቸውን እና ትሩፋታቸውን ያንብቡ👇

📌 https://telegra.ph/ብፁዕ-ወቅዱስ-አቡነ-ሰላማ-ከሳቴ-ብርሃን-11-14-2

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

14 Nov, 15:31


🌿 ዋኖቻችንን እንወቅ❗️
ክፍል 5 (በፅሑፍ)

👇 ዛሬ ይለቀቃል!👇

t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

13 Nov, 08:16


❗️የአባ ጳውሎስ ኑፋቄ እና የአባ ማትያስ ውጉዝነት ከአንዳንድ ያልታዩ ማስረጃዎች ጋር❗️

1▹ ያልተፈታው የአለቃ አያሌው ውግዘት ተቀባይነት አለው?

2▹ #_መንፈስ_ቅዱስን የሻረው የአባ ጳውሎስ (1987ቱ) ሕገ ቤ/ክ አሁን ላይ ተሻሽሏል?

3▹ ያሁኑስ (የአባ ማትያስ) ሕገ ቤ/ክ #መንፈስ_ቅዱስን ያከበረ ነው? ከውግዘት ያነጻቸዋል?

➻ አንዳንድ በስፋት ያልታዩ ማስረጃዎችን የያዘ፥
በአልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ የቀረበ፥

👇ሙሉውን የመብረቅ ምልክቱን በመንካት ከነማስረጃዎቹ ይመርምሩ።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

13 Nov, 08:15


ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመናን እና ካህናት፣ ጳጳሳት ለ29 ዓመታት  ያህል ያልተፈታውን ውግዘት ያላዳመጣችሁት አዳምጡት።

📌 ራሳቸው ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ታምሩ ከምዕመናን ስለውግዘቱ ምንነትና ምክንያት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በወቅቱ የሰጡት መልስ ነው።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

13 Nov, 08:15


📌 #ክፉውን_ከመካከላችሁ_አውጡት ❗️
📌
#ያልተፈታው_ውግዘት_ይከበር ❗️👇👇👇

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

13 Nov, 03:20


🟢የአብርሃሙ ሥላሴ እናቱን ያዳምጣል አንዲት ነጥብ ከእናቱ እንድትወድቅበት አይፈልግም።

🟢
ፍላጎቷ የሆነውን ሁሉ እግዚአብሔር ፈጻሚ ስለሆነ ይህን ልብ ልትሉ ይገባል።አታማልድም እያልህ ምትጨማለቅ የዲያብሎስ ግልገል ጠፊ ትውልድ ሁሉ ዋጋህን ታገኛለህ እዚህ ላይ ነው የምነግርህ።በድንግል ላይ አላግጠህ በድንግል ላይ አሹፈህ ክብሯውን ሁሉ ቀንሰህ ያፌዝህ ሁሉ ትውልድ ሁሉ በዚህም ሰዓት አረጋግጥልህአለሁ ዘር ማንዘርህ ሁሉ አያልፍም ትጠረጋለህ።
🟡
እኔ ባሪያው የእግዚአብሔር ባሪያ ለአንዳችሁም አላልፋችሁም። ስትጠናቀቅ ነው ሕሊናዬ ሚያርፈው በእናቴ በድንግል ድርድር አላቅም። ወዮልህ እኔ ፊት አትድረስ ያኔ የሞትህን ብዜት ነው እንጅ ምታየው እሳት እንደሚበላህ ነው እንጅ ምታየው ሌላ ከእኔ ምሕረት የምትባል ለሰንከንድም አትታለምም።
🟡
በእናቴ የመጣ ርህራሄ የለኝም በአይኔ የመጣ ነው።በእምነቴ የመጣ በአይኔ የመጣ ነው።ይህንን እንድናገር አልፈልግም ነበር ግን ሰዓቱ ነውና ግድ መናገር ያስፈልጋል።
እግዚአብሔር እንደ ቃሉ በአደረሰኝ ስፍራ ላይ ስደርስ ወይም አገልግለኝ ባለኝ ቦታ ላይ ሳገለግለው ይህ መመሪያ ነው የማይናወጽ አቋሜ ነው።ዛሬም እንደ አቅሜ በትንሽነቴ አገለግላለሁ እግዚአብሔርን ።
🔴
እግዚአብሔር ደግሞ ነገ እዚህ ጋ ስፍራ አገልግል ባለኝ ስፍራ ስሆን ግን የእምነቴ ጠላት የሆናችሁ በእናንተ በተለይ እናንተ መናፍቃን እናንተ ካቶሊካውያን በተለይ በክርስትና ስም ያላገጣችሁ ክፉ ጠላቶች በቤቱም በልጽጋችሁ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ውስጥም ሁናችሁ ይህንን እርኩሰት ያነገሣችሁ ሁሉ ውዮላችሁ።
🔴
አሁንም ደግሜ ነው ምነግርህ ወዮልህ ለዘርህ ሁሉ ለራስማ ተወው ለዘር ማንዘርህ የሚተርፈውን እሳት ትቀበላታለህ።ደግሜ ነው ዛሬ ምነግርህ ምንም ርህራሄ እንደለለ እስከ ዛሬም እስከዚች ሰዓት ድረስ እግዚአብሔር በትዕግስት እጁን የያዘው መጪውን እሳት ክፋቱን ጥንካሬውን ብርታቱን ስለሚያውቀው የሚያደርጋትን ስለሚያቅ ነው።እኛ ባሮች እጅ ደግሞ የእግዚአብሔር ኃይል ገባ ማለት ወዮልህ ወዮልህ መጥፊያህ...

4/03/2017 ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

12 Nov, 16:56


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ የኮሜዲ ጨዋታ ተደግሶ ተላግጧል። ዛሬ ዛሬ ቤቱ የቀበሮዎች፣ የእሽኮኮና የአይጦች መፈንጫ መራገጫ ለመሆኑ ምስክሩ እናንተው ባለጊዜዎች ናችሁ። ማሳያውም ዕለት ዕለት የምናየው የምንሰማው ጆሮን ጭውውው የሚያደርገው የእናንተ ጉድ ነው። "ቤተክርስቲያን አገልጋይ ነን" ባዮች ግብዣና በ"ምዕመናን ነን" ባዮች ድጋፍ ቅድስት ቤተክርስቲያን በይፋ የኮሜዲ ሾው አዘጋጅ ሆናለች፤ "ሲኖዶስ" ተብየውም የዚህ ተባባሪ ነው!!

#ለማንኛውም...
#ለታሪክ_ትቀመጥ !
ሕዳር 3/2017 ዓ.ም
t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

12 Nov, 06:24


እስቲ ይህንን ጉድ ስሙ ☝️☝️

አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንሥቶ ወደ ባሕር ወረወረው እንዲህ ሲል፦ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።

ዮሐንስ ራዕይ 18፡21

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

12 Nov, 06:06


👆👆👆የአምልኮት መልክ አላቸው ኀይሉን ግን ክደዋል ከነዚህ ደግሞ ራቅ።
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡5

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

12 Nov, 06:06


👆👆👆እንዲህ ያሉት ለገዛ ሆዳቸው እንጂ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አይገዙምና፥በመልካምና በሚያቈላምጥ ንግግርም ተንኰል የሌለባቸውን ሰዎች ልብ ያታልላሉ።
ወደ ሮሜ 16፡18

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

10 Nov, 18:16


መልክአ ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት .

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

10 Nov, 16:21


አመራሩ ተገደሉ‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የቆቦ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ የነበሩት ደርቤ በለጠ ዛሬ ረፋድ ላይ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

10 Nov, 13:18


አዋጁ ከታወጀበት ከሚያዝያ 7/2007ዓ.ም ጀምሮ ራሱን ለመትከል እንደ ልዑል ፍርድ ዓለምን በየደረጃው እያበጠራት ይገኛል፡፡ለዚህ ምስክሩ አገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበት ሁኔታ ነው፡፡ ቀድማም የምትወጣውና በአዋጁ የተገለፀው የሽግግሩም ሆነ ቋሚው ሕግጋተ ሥላሴ በመጀመሪያ የሚፀናው እዚሁ ኢትዮጵያ አገራችን ላይ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሕግጋተ ሥላሴ በአገራችን ዙሪያ ባሉ አገሮችም ጭምር የሚፀናና ለመላው ዓለም እንደ ፀሐይ የሚያበራ ሆኖ ይቆማል፡፡ ይህንን ለማየት በውስጡም ለመኖርና እድሜን ለመቀዳጀት የሚታደለው ማን እንደሆነ የሚያውቀው ማንም አይደለም ልዑልና ድንግል በግንባሩ ያተሙበት ብቻ ነው፡፡ ለዛሬው ከሃዲ ትውልድ ይህ ተረት ነው፡፡ለዚህ ነው አዋጁም የማይገለጠው ፤ ወገኖቼ የእግዚአብሔር ሕዝቦች እምነት አሻግራችሁ ለማየት የታደላችሁ ወንድም እህቶቼ እናንተ ተስፋችሁ የፀና የማይናወፅ ነው፡፡ ራሳችሁን ከዚህ ዓለም ጉድፍ ስለጠበቃችሁ ሕይወታችሁ ሥጋዊ ኑሮአችሁ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሆነ እኔም የምመሰክረው ነውና ፅኑ እንጂ አትናወጡ፡፡
የሚጠፋው ጠፍቶ ፤ የሚሻገረው ደግሞ የተፈቀደለት ብቻ ይሆናል፡፡የመከራው ክብደት ተስፋን ያጨልማል ሥጋ ነንና እንደክማለን እንወድቃለን ፤ ነገር ግን የምንታመንበት አምላክ የምንወዳት እናታችን በቃላቸው የታመኑ ስለሆኑ ብንወድቅም ያነሱናል፤ ብንቆስል ብንጎዳ ይጠግኑናል፡፡
📌ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቁጥር-8 ከገጽ 3-4

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Nov, 15:46


ጥቅምት 25 ቀን የሚጸለይ

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Nov, 11:48


ከመዓድ በኋላ የሚጸለይ
🍀 ስብሐት በልሳነ ግእዝ ከነንባብ ስልቱ 🍀

t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Nov, 07:06


...ዛሬ ቤተክርስቲያንን መንግሥት ነው የሚያሽከረክራት ፥ መንግሥት ነው የሚመራት ። ሲኖዶስ ወይም ጳጳሳት ሣይሆኑ ፥ ልብ አድርግ ! ጳጳሳት ብራቸውን ከመብላት ፣ በመኪናቸው ከመሽከርከር ፣ ኧ! የወር ደሞዛቸውን ከመጠበቅ ፣ በስልጣናቸው በኢትዮጵያ መኃይም ህዝብ ከመከበር በቀር ምንም ሥልጣን፣ ሥራ የላቸውም የእኔ ጌታ ።

ለዚህ ደግሞ ተምረናል ብለዋል ተምረው ከሆነ ፣ አውቀናል እናውቃለን ይላሉ አውቀው ከሆነ ፣ ዳዊቱን ጠዋት ማታ ይደግሙታል እየደገሙት ከሆነ አስቀድሞ ነብዩ ዳዊት ትንቢት ተናግሮባቸዋል ወንድማለም ! ትንቢት ተናግሮባቸዋል ። ይኸውም በመዝሙር 49 ነው ከቁጥር 1 ጀምሮ ቢያነቡ ያገኙታል፤ ዳዊቱን ከነሱ የበለጠ የተማረው የለም የሚደግሙት ከሆነ ወ ይ ም ቢደግሙትም ምስጢሩን የሚያውቁት ከሆነ ። ኧ! በመዝሙር 49 ከቁጥር 1 ጀምሮ እስኪ ይመልከቱት ስለማን ነው የተፃፈ ? ስለነሱ ነው። ይኸውም ምንድነው ባጭሩ አንድ ቃል ልንገርህ ☞ አስተጋብኡ : ሎቱ : ፃድቃኑ ፥ እለ : ይገብሩ : መሥዋዕት : ዘበሕጉ የሚል ኃይለቃል አለ አስተጋብኡ : ሎቱ : ፃድቃኑ : እለ : ይገብሩ : መሥዋዕት : ዘበሕጉ ። ይህ ምንድነው ነብዩ ዳዊት አስቀድሞ በዚህ ዘመን ስለሚመጡት የሃይማኖት አባቶች ፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሃይማኖት ባለሟሎት፣ የሃይማኖት ባላደራዎች ስለሚባሉት ከዲያቆን እስከ ጳጳሳት ስላሉት ስለ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች የተናገረባቸው ትንቢት ነው። ይኸውም ምንድነው?፦ እነሆ በዚያን ሰዓት ለእርሱ ማለትም ለእግዚአብሔር ለፈጣሪ ንፁሀንን፣ ደጋጎችን፣ ቅዱሳንን፣ ካህናቱን ሰብስቡለት ! ሰብስቡለት ። ማለትም መሥዋዕቱን፣ ቅዳሴውን ፣ ሠዓታቱን፣ ማህሌቱን .. ሁሉ ሰዓትን ጠብቀው ፣ ዕለትን ጠብቀው ፣ ቀንን ጠብቀው መርጠው የሚሰውለትን፣ የሚቀድሱለትን፣ የሚያመሰግኑትን፣ የሚያገለግሉትን እውነተኛ ቅዱሳን ካህናትን ሰብስቡለት ነው ያለ። ሥለዚህ እኒህ ትንቢት የተነገረላቸው ቅዱሳን ካህናት፣ ቅዱሳን ዲያቆናት፣ ቅዱሳን ጳጳሳት በትንቢቱ መሠረት ጊዜው ደርሶ እስኪመጡና እውነተኛ ቤተክርስቲያንን ተረክበው እውነተኛ መሥዋዕት እስኪሰው፤ እውነተኛ ጻድቃን ህዝበ ክርስቲያንን የሚያገለግሉት እስኪመጡ ድረሥ አሁን ያለው በሙሉ በቤተክርስቲያን ውስጥ የተጎደጎደው የዲያቢሎስ አሻንጉሊት ነው ። እንዴ ! የዲያቢሎስ መሣሪያ ነው ። የዲያብሎስ አገልጋይ ነው ።...


📌 አባ አምኃኢየሱስ ገብረዮሐንስ ከዛሬ 9 አመት በፊት በኢሳት ድምፅ ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቆይታ ላይ ተቀንጭቦ የተወሰደ !

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Nov, 06:38


🇨🇬🇨🇬
#_ተግሣጽ_፲፫ { ለኢ.ዓ.ብ ቤተሰብ ብቻ }
#_የተጠራችሁት_በጽድቃችሁ_አይደለም

🇨🇬 የሐዋርያት ሥራ ትምህርት ክፍል ፯-ለ 🇨🇬
| 🕛 | ከ ፶፭ ፡ ፶፩ ጀምሮ

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች፥ ያላችሁበትን እወቁ። እግዚአብሔር እንዴት እንደወደዳችሁ እወቁ፤ አስተውሉ

በታመናችሁበት ልክ እናንተም ታመኑ። በተወደዳችሁበት ልክ፤ ከናንተ ጋር ከነ ነውራችሁ፣ ከነ ጥፋታችሁ፣ ከነ ጉድለታችሁ እግዚአብሔር ተሸከሟችሁ እያጓጓዛችሁ ነው ያለው።

በቃ እግዚአብሔር ሲመርጥ፥ ሲወድድ፥ ሲያጸድቅ፥ ሲተክል "አላጠፋንም፤ ስህተት የለብንም፤ ጉድለት የለብንም፤ ፍጹማን ነን" አ ይ ደ ለ ም። አ ለ ብ ን። ባለ ጉድለቶች ነን። ጥፋትም ይኖርብናል። ግን ዘወትር በንስሐ በፊቱ የምንወድቅ ሕዝቦች ነን።

በተሰበረ ልብ በእንባ በፊቱ ቀርበን እግዚአብሔርን በፍቅሩ ፊት ስንወድቅለት ፍቅሩን የምናገኝ የምናሸንፍ ሕዝቦች ነን።

▯ t.me/Ewnet1Nat 🇨🇬
▮ http://t.me/AlphaOmega930 🇨🇬

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Nov, 06:37


🟢 🟡 🔴
ጥቅምት 25 | #አቡነ_አቢብ (አባ ቡላ) የዕረፍቱ በዓል ነው፨

ይህም ቅዱስ አባት፦

✦ ከቅዱሳን ቤተሰብ በጸሎት የተገኘ፥

✦ በተፀነሰ ዕለት ማንም ያልተከለው ዛፍ አደገና በዛፉ ላይ "ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ" የሚል ጽሑፍ የተገኘለት፥

✦ 1 ዓመት ከሆነው በኋላ የተጠመቀ፣ ተጠምቆ ሲጨርስ ከሰማይ ኅብስት ወርዶ የቆረበ፥

✦ ሕፃን ሳለ በ10 ዓመቱ ሰማዕትነትን የተቀበለ፣ ገነት ከገባ በኋላ ግን በቅ/ጊዮርጊስ እጅግ ተደንቆ "ደግሞ ወደ ምድር ለተጋድሎ ልመለስ ብሎ" የለመነ፥

✦ ስለጌታ ፍቅር ብሎ በተጋድሎ ሕይወቱ 10 ጊዜ በአሰቃቂ ሁኔታ ሞቶ የተነሣ ሰማዕት ነው።

ዕድሜውንም ፈጽሞ ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ጊዜ ሲደርስ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ በእጁ ልዩ የሆኑ አክሊሎችን የሚያበሩ ልብሶችንም ይዞ ተገለጠለት።

«ወዳጄ አቢብ ሆይ በማያልቅ ተድላ ደስታ ደስ አሰኝህ ዘንድ ወደእኔ ና።

ስምህን ለሚጠራ፣ መታሰቢያህን ለሚያደርግ እኔ ኃጢአቱን አስተሠርይለት ዘንድ በራሴ ማልኩልህ፤ ወይም ለተራቆተ የሚያለብሰውን ለተራበም የሚያጠግበውን ለተጠማ የሚያጠጣውን የገድልህን መጽሐፍም የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውንና የሚሰማውን በጸሎትህም የሚታመኑትን ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እምራቸዋለሁ።


๏ አቅም ቢያጣ 'አምላከ አቢብ ማረኝ' ብሎ 3 ጊዜ በዕለተ ዕረፍትህ የሚለምነኝን፣

๏ በስምህ እንኳ ቁራሽ የሚበላውን ሁሉ እምርልሃለሁ (ከመዓድ በኋላ "በእንተ አቡነ አቢብ መሐረነ ክርስቶስ" ብለን 3 ጊዜ የምንቀምሰው ለዚህ ነው)»

ይህንም ብሎ አፉን ሳመው። በደረቱም ላይ አድርጎ ወደአየር አወጣው። የመላእክትንም ምስጋና በሰማች ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ገባች።

t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Nov, 06:27


ገድለ ቅዱስ አቡነ አቢብ
ጥቅምት 25 የአቡነ አቢብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ነው።በዚች ቀን አምላከ አቡነ አቢብ ማረኝ (፫ ጊዜ) ብሎ በሠላም ለኪና በአቡነ በዘሰማያት ያሰውን የጸለየውን ኃጢአቱ ሁሉ ይሰረይለታል።በተሰጣቸው ቃል ኪዳን ልዑል እግዚአብሔር ይማረን። በረከታቸው ይደርብን።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Nov, 06:27


መልክአ አቡነ አቢብ

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

04 Nov, 06:26


መልክአ ቅዱስ መርቆሬዎስ

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

03 Nov, 17:10


❗️ዋኖቻችንን እንወቅ❗️(የጥያቄና መልስ መርሐ ግብር)

ውድ ቤተሰቦች፥ ዋኖቻችንን እንወቅ በሚል መርህ የቅዱሳንን ዜና ሕይወትና ገድል በጥቂቱ ማሳወቅ መጀመራችን ይታወቃል። ዋና ዓላማው ቅዱሳኑን ጠንቅቆ ማወቅ ብቻ ሳይሆን በሕይወትም እነሱን መምሰል እንድንለምድ ነው።

ለዚህም እንዲያግዘን በየዙሩ ከሚለቀቁት የቅዱሳንን ዜና ታሪኮች የተውጣጡ ጥያቄዎችን አዘጋጅተናል።

ጥያቄዎቹ የተዘጋጁበት ዓላማ ያነበብነውን ምን ያህል እንደያዝነው፣ ምን ያህል እንደተዋወቅናቸው ራሳችንን እንድንመዝንበት ነው። በተጨማሪም በነገሮች ምክንያት ልብ ሳንል ያለፍነውን ታሪካቸውን መልሶ እንዲያስተምረን ነው። ስለሆነም፦


🍀 ጥያቄዎቹን ለመመለስ መልስ ነው ያላችሁትን ፊደል ወይም ከፊደሉ አጠገብ ያለውን ክብ ◌ ምልክት መንካት ትችላላችሁ።

🍀 ጥያቄዎቹን ስትመልሱ ማንነታችሁን ሆነ መልሳችሁን ከራሳችሁ ሌላ ማንም ሰው አያውቀውም።

🍀 ትክክለኛውን መልስ ጥያቄውን ከሞከሩ በኋላ በአረንጓዴ ቀለም (ራይት) ተደርጎበት ያዩታል።

🍀 ስለ ጥያቄው ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት መልስ ከመለሳችሁ በኋላ የአምፖል (💡) ምልክቱን በመንካት ጥቆማን ማግኘት ትችላላችሁ።

🍀 መልሱን ባያውቁትም ከጥያቄ ችና ከማብራሪያው ይማሩበታልና ይሞክሩት።

ሁላችሁም የቅዱሳኑን ታሪክ እና ጥያቄዎቹን እንድትጠቀሙበት እንወዳለን። የቅዱሳኑ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን፨

t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

03 Nov, 12:53


ሪፖርተር 👆

“10.8 ሚሊዮን ህዝቦች የምግብ እጥረት ገጥሟቸዋል!
5566 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል!
በአማራ ክልል 85 ሺህ የቤት እንስሳት ሞተዋል!

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

03 Nov, 07:01


መልክአ ቅዱስ ተክለሃይማኖት

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

03 Nov, 07:00


መልክአ ቅድስት ፀበለ ማርያም

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

02 Nov, 06:04


"አጋቾቹ ከጠየቁት 2 ሚሊዮን ብር 1.4 ሚሊዮን ብር ከፍለን ሌላውን እየፈለግን ነበር ግን ቀድመው ጀናዛቸውን ላኩልን"

- በኦሮሚያ ክልል ደራ የተገደሉት የመስጅድ ኢማም ቤተሰቦች‼️

📌 ፍርድ አስፈጻሚ አካላት የማናችሁንም፦
#አቤቱታ_የሚሰሙ
#ይግባኝ_የሚቀበሉ አይደሉም!!

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

02 Nov, 05:54


ጥቅምት 23/2017

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ትናንት በሰሜን ሸዋ ዞን ወጫሌ ወረዳ በኹለት ቦታዎች ላይ በፈጸመው ጥቃት 120 የመንግሥት ወታደሮችን መግደሉን አስታውቋል። ካራ ከተማ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ በፈጸመው ጥቃት 67 ወታደሮችን መግደሉን የገለጠው ቡድኑ፣ ባጮ ፋሉሚ በተባለ ቦታ በወታደራዊና በትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ላይ በፈጸምኩት ጥቃት ደሞ 53 ወታደሮችን ገድያለኹ ብሏል። ቡድኑ፣ ሕዝቡን ያሰቃዩ ነበር ያላቸውን የአካባቢ አስተዳዳሪዎች ጭምር መግደሉን ገልጧል። በጥቃቱ የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪ ንጉሴ ኮሩ እና ከ50 በላይ ጸጥታ ኃይሎች እንደተገደሉ ዋዜማ ከምንጯ ሰምታ መዘገቧ ይታወሳል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

02 Nov, 05:50


♡ ጊዮርጊስ እሱ ነው ♡

በተጠራ ጊዜ ፈጥኖ የሚደርሰው
በአማላጅነቱ ዘወትር የማይለየው
የኢትዮጵያ ገበዝ ጊዮርጊስ እሱ ነው
የኔ መታመኛ ጊዮርጊስ እሱ ነው


ዱድያኖስ እና ሰባው ነገሥታት
አንድ ሆነው መጥተው ስቃይ ቢያበዙበት
በአልተናወጸ እምነት አንተን ያመለከው
የልዳው ሰማዕት ጽኑ ምስክር ነው


ለዘንዶ ተሰጥታ መስዋዕት እንድትሆን
ጊዮርጊስ አዳናት ቤሩይታዊትን
የሰው ዘር ተጨንቆ ጻድቃን ከተጠሩ።
ፈጥኖ የሚደርሰው ጊዮርጊስ ኃያሉ


በደረቅ እንጨት ላይ ቢታሰር በገመድ
ለምልሞ ተገኘ የታሰረበት ግንድ
ሥጋውን ቆራርጠው ቢዘሩት በምድር
ገልጾ መሰከረ የፈጣሪውን ክብር


በሰው ችግር ሁሉ ፈጥነህ የምትደርሰው
የልዳው ሰማዕት ጊዮርጊስ ኃያል ሰው
በኪዳንህ አምነን በተሰጠህ ጸጋ
ስምህን እንጠራለን እንድናገኝ ዋጋ

መዝሙር
ቀሲስ ዳዊት ፈንታዬ

💚💛❤️ https://t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

02 Nov, 02:52


🍀🌼🌹
"አክሊለ ጽጌ ማርያም
ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ
ክበበ ጌራ ወርቅ"

- አባ ጽጌ ድንግል

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

01 Nov, 20:21


በሬክተር ስኬል 4.8 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ አካባቢ ተከሰተ፣ እስከ አዲስ አበባ ንዝረቱ ተሰምቷል

(መሠረት ሚድያ)- ዛሬ ከምሽቱ 3:55 ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ አካባቢ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አስታወቀ፣ በአዲስ አበባ ሁሉም ስፍራዎች ንዝረቱ እንደተሰማ ታውቋል።

ይህ በቅርብ ቀናት ውስጥ ለአራተኛ ግዜ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲሆን ሁሉም አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የተከሰቱ ሆነው ተመዝግበዋል።

ይህን የሰሞኑን ክስተት ተከትሎ በርካታ የጥንቃቄ መልእክቶች እየተላለፉ ይገኛሉ።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

01 Nov, 18:50


📌ማስታወሻ፦

👑 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ቀዳማይ የልዑል ባሮች ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም ከተላለፈው "ፍርድ አዘል መግለጫ" ከ46ኛው - 51ኛው ደቂቃ ተቀንጭቦ የተወሰደ!

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

01 Nov, 18:42


"... ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ። ..."

🫴 ትንቢተ ሕዝቅኤል 9፥6

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

01 Nov, 18:41


" ህጻናት ፣ እናቶች፣ አሮጊቶች ፣ ሽማግሌዎች ተነስታ መሮጥ የማትችል አራስ እናት ሳትቀር ነው የተገደለችው " - ነዋሪዎች

በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን ከመቂ ከተማ 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ታጣቂዎች በርካታ ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

01 Nov, 18:38


በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ አካባቢ በኦነግ ሸኔ ታግተው የነበሩት የመስጅድ ኢማም ከ12 ቤተሰቦቻቸው ጋር መገደላቸው ተሰማ‼️

በደራ ወረዳ ገንዳ አረቦ ተብሎ በሚጣራው አካባቢ ከሀጂ አህመድ መስጅድ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩት የሀጂ አህመድ መስጅድ ኢማም ሼይኽ ሙሀመድ መኪን ሸይኽ ሙሀመድ አሪፍ አብረዋቸው ታግተው ከነበሩት 12 ቤተሰቦቻቸው ጋር በዛሬው ዕለት መገደላቸው ተሰምቷል።

ሼይኽ ሙሀመድ ከሳምንታት በፊት የሱብኺ ሶላት አሰግደው በሚመለሱበት ወቅት ነበር ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ከ30 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ሰዎች ታግተው በሸኔ ሀይሎች መወሰዳቸው የተገለፀው። ከቀናት በኋላ በተደረገ የገንዘብ ድርድር የኢማሙን እናት እና ባለቤት ጨምሮ ጥቂት ሰዎች መለቀቃቸው የተገለፀ ሲሆን ኢማሙን ጨምሮ 12 ቤተሰቦቻቸው  በዛሬው እለት መገደላቸው ተሰምቷል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

01 Nov, 16:27


#NewsAlert
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የወጫሌ ወረዳ አሥተዳዳሪ የሆኑት ንጉሤ ኮሩን ጨምሮ ከ ሃምሳ በላይ የሚሆኑ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ዛሬ ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም ማለዳ ላይ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው አማጺ ቡድን በተከፈተባቸው ጥቃት መገደላቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

01 Nov, 15:13


📌ማስታወሻ

ክፉ ትውልድ እንዲህ ይላል እስከ ዛሬ ለ18 ዓመት ለፍልፋችኋል የምትመኩበት አምላክ እስከ ዛሬ መቸ መጣ :ምንስ አደረገን:እናንተ ትጮሃላችሁ የእግዚአብሔር ቁጣ ፍርድ ትላላችሁ ጆሮአችን እስከሚታክተው ሰማናችሁ ምንም የሚመጣ የለም።እኛም ለሥልጣኔአችንም ስለሥልጣኔአችንም ጉልበታችንም ሀብታችንም በዓለም የዘረጋነው ሥርዓታችንም ሁሉ አንዳች የሚነካው የለም።የእናንተን ሥላሴ: የእናንተን መድኃኔዓለም: የእናንተን ማርያም:የእናንተን መልአክ:የእናንተን ቅዱሳን ታሪክም ገድልም ሁሉንም አናውቃቸውም ።ግብረሰዶምነት መብታችን ነው ዓለምንም ሁሉ ከድኗል የምንሻውን ከመፈጸም የሚያግደን የለም።ዘወር በሉ አናውቃችሁም ብላችሁ ቁማችኋል ዲያብሎስን ታምናችኋል አምላካችሁ አድርጋችሁታል ፤በአዘዛችሁም ቁማችኋል ያዘዛችሁንም ፈጽማችኋል።ልብ በሉ ምስክሩ እኛም ነንን ምስክሩ እራሳችሁም ናችሁ :ምስክሩ እራሳችሁም ናችሁ እንግዲህ እውነቱ ይለያል።እኛ የሥላሴ ባሮች: የድንግልም ልጆች:የሊቀ መላእክቱም ወዳጆች የቅዱሳንም ፍሬዎች የታመንበት አምላክ የአብርሃሙ ሥላሴ በእኛ አንደበት እንደተናገረው እንደ መልዕክቱ አገላለጽ :እንደ ደብዳቤዎቹ አገላለጽ:እንደ መግለጫዎቹ እንደ ትምህርቶቹ እውነትነት:የእኛም ታማኝ አገልጋይነት ይታወቅና እና ይገለጽ ዘንድ እግዚአብሔር በታላቅ የበቀልና የፍርድ ሂደት በታላቅ ቁጣ ትቢያ ሊያደርጋችሁ ደርሷል በደጃችሁም ነው።
ከዲያብሎስ የታጠቃችሁትን ትዕቢታችሁ ክህደታችሁ ንቀታችሁ እኒህ ሁሉ በምድር እንደጸኑ ያኖሯችኋል እንደሆነ እነሆ ልናይ ነው።የእኛ አምላክ ስለባሮቹ ስለቃሉ ስለትዕዛዙ ስለሥርዓቱ ሲል በቅናት እና በቁጣ ካልተነሳ እርምጃውንም በማትገምቱት በማታስቡት መልኩ ይዞት ካልመጣ በእርግጥ እንዳላችሁት እኛ አምላክ የለንም ውሸታም ነንን ማለት ነው።
ስለዚህ የእናንተ አምላክ ከእግዚአብሔር ታግሎ ከአሸነፈ እኛም ተሸንፈናል ማለት ነው።እንግዲህ ሜዳውም ፈረሱም እነሆ ተዘርግቷል ሁሉንም እናየዋለን።ሲድራቅ: ሚሳቅ :አቢዲናጎምን ከእሳት ያወጣው አምላካችን: በእርግጥ ለአምላክነቱ: ለስሙ: ለክብሩ: ለፈቃዱ ቀናይነቱን ለልጆቹ ፈራጅነቱም በግልጽና በማትክዱበት መልኩ ሲውጣችሁ ተረት ብላችሁ የናቃችሁት ቃሉ ሲተገበርባችሁ አይ ተሳስተናል ማሩን እ ከልሉን አስጥሉን ማለት የለም።የለም የለም።መዳንም የለም።ከእነ ክህደትህ ከእነ ትዕቢትህ ሰዶሞን የበላው እሳት በሺ እጥፍ ተባዝቶ ይበላሃል።ፌዝህ ንቀትህ ያድንህ በቃ እሱኑ ተማመን ።ያ የተማመንህበት ዲያብሎስ እሱ ያድንህ በቃ።
ያሳደድኸን የገደልኸን የአሰርኸን እኛ የልዑልም የድንግልም ታማኝ ባሮች ብትጮህ ብታቅራራ ሺ ጊዜ ብትኳትን ከእንግዲህ አታገኜንም ለአንዴም ለመጨረሻም ተሰነባብተንሃል።

📌የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች በእምነታችሁ ጽናት በምክር መስማታችሁ ምክንያት አሸናፊ ሁናችኋል።ዓለምን አሸንፋችኋል። ኮንናችሁታል ታገሱ በጾም በጸሎት ትጉ።ለእኛም ደካማ አገልጋዮቻችሁ ጌታ ምሕረቱን :ቸርነቱን :ፀጋውን አብዝቶልን በትህትና እንድናገለግላችሁ ፀልዩልን።

📌ክርስቲያን መሠል አስመሳዮች ከፈጣሪ ይልቅ ሰውን የምታመልኩ ወዮላችሁ! የሚገርም ክርስቲያን ተብየ ምዕመን ፡በተለይ ሴቶች አንድ ሊቅ ነኝ ሊቃውንት ነኝ የሚሉ እግር ስር ወድቃ አባቴ በእርስዎ እግር ሥር በመባረኬ እጅግ ተደስቻለሁ ብላ እንደ ምሳሌ በማሕበራዊ ሚዲያ ስታስተጋባ ሰማናት።እሺ አምላክስ መቼ ነው እግሩ ስር ወድቀሽ የሚባርክሽ እ የእግዚአብሔርን ክብር ለሰው የሰጠሽ አባት ተብዮች ያጠፉሽ ከንቱ ትባያለሽ።እንደ እሷ መሰል የሆናችሁ ሁሉ ከንቱ ተብላችሁ ፍርዳችሁን ታገኛላችሁ።
በቀን 21/02/2017 ዓ.ም ከወጣው ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ፍርድ አዘል መግለጫ ከ46 እስከ 51 ደቂቃ ላይ የተወሰደ።
22/02/2017 ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

01 Nov, 11:15


👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት አምስት የተወሰደ
ተጻፈ በ21/01/2004 ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

01 Nov, 11:13


⛳️ በቦሌ ቡልቡላ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

01 Nov, 11:13


⛳️ #ኮንታ

ዛሬ በኮንታ በደረሰ የመሬት መሸራተት አደጋ 6 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጫሬ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

31 Oct, 17:44


UPDATE: At least 140 people dead after floods in eastern Spain, dozens still missing — local media

#Spain

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

27 Oct, 17:21


💧🇸🇦 በሳውዲ አረቢያ ታይፍ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ በጎዳናዎች ላይ የነበሩ መኪናዎችን ጠራርጎ ወስዷቸዋል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

27 Oct, 11:36


ግራኝን ከእነ ሰራዊቱ ያሳደደው የቅዱስ እስጢፋኖስ ሠራዊት!

ግራኝ የተባለው አሕዛባዊ ዓመፀኛ በተነሣና በክርስቲያኖች ላይ ጦርነትን በዐወጀ ጊዜ በየአውራጃውና በየመንደሩ ፍጅትና ሁከት ሆነ።

ግራኝም የረከሰች ሃይማኖታቸውን ያልተቀበለውን ኹሉ እንዲገድሉ ለሰራዊቱም ኹሉ ትእዛዝ ሰጠ። ብዙዎች ክርስቲያኖችም በግፍ በጭካኔ በሰይፍ ተገደሉ።

በእሳትም የተቃጠሉ አሉ፤ በመጋዝ የተሰነጠቁ አለ፤ ወደጥልቅ ጉድጓድ ተጥለው የሞቱ አሉ፤ ከየመንደራቸውም ወጥተው ወደተራራዎችና ዋሻዎች የተሰደዱ አሉ።

ጠንበላ በምትባል የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ባለችበት አውራጃም የግራኝ ሠራዊቶች ደርሰው ይኽችን የጠንበላን አውራጃ ከበቧት። የሀገሪቱም ሰዎች ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ገብተው ሰማዕቱን ይማጸኑት ጀመር።

የግራኝም የወታደሮች አለቃ ለመሸመቅ አስቦ ወደ አንድ ዋሻ ሲገባ ዋሻው በተአምር ተደርምሶ ገደለው፤ በውስጡም ቀበረው።

ርጉም ግራኝም እሳት ይዞ ጠንበላ አውራጃ የምትገኘውን የቅዱስ እስጢፋኖስን ቤተ ክርስቲያን ሊያቃጥላት ቀረበ። ነገር ግን ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤቱን እንዲያቃጥል አልፈቀደለትምና ሊያቃጥላት አልቻለም።

ይልቁንም በቅዱስ እስጢፋኖስ ትእዛዝ በቤተ ክርስቲያኑ ጠፈር ላይ የነበሩ ንቦች ተነሥተው ከነሠራዊቱ እስከሩቅ አውራጃ ድረስ አሳደዱት። ግራኝም ከነሠራዊቱ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ፈጥኖ ሸሸ።

የጠንበላ ሀገር ሰዎችም ከግራኝ ያዳናቸውን የቅዱስ እስጢፋኖስን አምላክ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

ሊቀ ዲያቆናት ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዘመኑ ግራኞች ሀገራችንን ይታደግልን።

T.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

27 Oct, 11:35


🟢🟡🔴
ጥቅምት 17 | የሰማዕታት ቀዳሚ #ቅዱስ_እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆንነት ተሾመ።

#ቅዱስ_ፊልያስ_ሰማዕት

ሰማዕቱ የነበረበት ዘመን 3ኛው መቶ ክ/ዘ (ዘመነ ሰማዕታት) ሲሆን የግብጽ አውራጃም ጳጳስ ነበር። የመከራው ዘመን ሲመጣ በቃሉ ያስተማራቸውን እንደ በጎ እረኝነቱ በተግባር ይገልጠው ዘንድ ወደ መኮንኑ ሔደ።

ሕዝቡ በአንድነት ተሰብስበው ሳለ መኮንኑ ቁልቁልያኖስ ቅዱስ ፊልያስን 4 ጥያቄዎችን ጠየቀው። ምላሾቹ ለእኛ ሕይወትነት ያላቸው ናቸው።

1. "የእናንተ እግዚአብሔር ምን ዓይነት መስዋዕትን ይሻል?" ቢለው "እግዚአብሔርን ትሑት ልቦና፣ የዋህ ሰብእና፣ የቀና ፍርድና ቁም ነገር ደስ ያሰኘዋል" ሲል መለሰለት።

2. "የምትወዳቸው ሚስትና ልጆች የሉህም?" ሲለው ደግሞ "ከሁሉ የእግዚአብሔር ፍቅር ይበልጣል" አለው።

3. "ለነፍስህ ትጋደላለህ ወይስ ለሥጋህ?" ቢለው "ለ2ቱም እጋደላለሁ። አምላክ በአንድነት ፈጥሯቸዋልና። በትንሣኤ ዘጉባኤም ይዋሐዳሉና" ብሎታል።

4. "አምላካችሁ የሠራው ምን በጎ ነገር አለ?" ብሎትም ነበር። ቅዱስ ፊልያስ መልሶ፦ "አስቀድሞ ፍጥረታትን በጥንተ ተፈጥሮ ፈጠረ። በኋላም በሐዲስ ተፈጥሮ ያከብረን ዘንድ ወርዶ ሞተልን፣ ተነሣ፣ ዐረገ" ቢለው መኮንኑ "እንዴት አምላክ ሞተ ትላለህ!" ብሎ ተቆጣ። ቅዱሱም "አዎ! በለበሰው ሥጋ ስለ እኛ ሙቷል" ብሎ እቅጩን ነገረው።

ወዲያውም "እስከ አሁን የታገስኩህ በዘመድ የከበርክ ስለሆንክ ነው" ቢለው ቅዱሱ መልሶ "ክብሬ ክርስቶስ ነው። መልካምን ካሰብክልኝ ቶሎ ግደለኝ" አለው። በዚያን ጊዜ የሃገሩ ሰዎች "አትሙትብን! እባክህን ለመኮንኑ ታዘዘው?" ሲሉ ለመኑት።

ቅዱስ ፊልያስ "እናንተ የነፍሴ ጠላቶች ዘወር በሉ ከፊቴ! እኔ ወደ ክርስቶስ ልሔድ እናፍቃለሁና" ብሎ ገሠጻቸው። መኮንኑም ወስዶ ከብዙ ስቃይ ጋር ገድሎታል።
🍀

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

26 Oct, 18:57


ለ5ኛ ጊዜ መሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተከሰተ‼️

በአፋር ክልል አዋሽ 8:16  እና 8:51 ደቂቃ ላይ ከፍተኛ ንዝረት ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ታውቋል፣ በሌላ በኩል አዲስ አበባ ሰሚት፣አያት እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ዞን አንኮበር፣አልዩ አምባ 9:25 ላይ የተከሰተ ሲሆን በሌሎች ቦታዎችም ንዝረቱ እንደተሰማ ተገልጿል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

25 Oct, 18:31


t.me/Amharic_Messages

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

25 Oct, 15:29


❗️ዋኖቻችንን እንወቅ❗️(የጥያቄና መልስ መርሐ ግብር)

ውድ ቤተሰቦች፥ ዋኖቻችንን እንወቅ በሚል መርህ የቅዱሳንን ዜና ሕይወትና ገድል በጥቂቱ ማሳወቅ መጀመራችን ይታወቃል። ዋና ዓላማው ቅዱሳኑን ጠንቅቆ ማወቅ ብቻ ሳይሆን በሕይወትም እነሱን መምሰል እንድንለምድ ነው።

ለዚህም እንዲያግዘን በየዙሩ ከሚለቀቁት የቅዱሳንን ዜና ታሪኮች የተውጣጡ ጥያቄዎችን አዘጋጅተናል።

ጥያቄዎቹ የተዘጋጁበት ዓላማ ያነበብነውን ምን ያህል እንደያዝነው፣ ምን ያህል እንደተዋወቅናቸው ራሳችንን እንድንመዝንበት ነው። በተጨማሪም በነገሮች ምክንያት ልብ ሳንል ያለፍነውን አስተማሪ እንዲሆነን ነው።

● ጥያቄዎቹን ለመመለስ መልስ ነው ያላችሁትን ፊደል ወይም ከፊደሉ አጠገብ ያለውን ክብ ◌ ምልክት መንካት ትችላላችሁ።

● ጥያቄዎቹን ስትመልሱ ማንነታችሁ እና መልሳችሁን ከራሳችሁ ሌላ ማንም አያውቀውም።

● ትክክለኛውን መልስ ጥያቄውን ከሞከሩ በኋላ በአረንጓዴ ቀለም (ራይት) ተደርጎበት ያዩታል።

● ስለ ጥያቄው ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት መልስ ከመለሳችሁ በኋላ የአምፖል (💡) ምልክቱን በመንካት ጥቆማን ማግኘት ትችላላችሁ።

ሁላችሁም የቅዱሳኑን ታሪክ እና ጥያቄዎቹን እንድትጠቀሙበት እንወዳለን።

t.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

25 Oct, 04:33


🟢🟡🔴
ጥቅምት 15 | አባቶቻችን #ቅዱሳን_ሐዋርያት ከመንፈስ ቅዱስን መሞላት በኋላ ምድርን 12 ቦታ በእጣ የተካፈሉት ቀን ነው።

እሊህም፦
#ጴጥሮስ የተባለ ስምኦን፣
#እንድርያስ (ወንድሙ)፣ #ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ፣ #ዮሐንስ (ወንድሙ)፣ #ፊልጶስ፣ #በርተሎሜዎስ፣ #ቶማስ፣ #ማቴዎስ፣ #ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ፣ #ታዴዎስ (ልብድዮስ)፣ #ናትናኤል (ቀናተኛው ስምዖን) እና #ማትያስ (በይሁዳ የተተካው) ናቸው። (ማቴ. 10፥1)

ክብራቸውንም መድኃኔአለም በወንጌል እንዲህ ተናግሯላቸዋል።

በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ፦ "እነሆ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ። እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን?" አለው።

ጌታ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው:- "እውነት እላችኋለሁ! እናንተስ የተከተላችሁኝ በዳግመኛ ልደት፣ የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእሥራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ።
[ማቴ. 19፥27]

🍀 #ቅዱስ_ሲላስ ሐዋርያ ዕረፍቱ ነው።

በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር።

ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።

የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።

ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ። ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ።

መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤

ወደ ውጭም አውጥቶ፦ ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? አላቸው።

እነርሱም፦ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

23 Oct, 19:22


🟢🟡🔴
ጥቅምት 14 | በዚህች ቀን

🍀 #ቅዱስ_ፊልጶስ ዐረፈ።

በዘመነ ሐዋርያት በዚህ ስም የሚጠሩ አባቶች 2 ነበሩ። አንደኛው ከ12ቱ ሐዋርያት ሲቆጠር ዛሬ የምናከብረው ደግሞ ከ72ቱ አርድእት ይቆጠራል። ከቅዱስ እስጢፋኖስ ጋር ከተመረጡት ዲያቆናት አንዱ ነው።

ቅዱስ ፊልጶስ ያደገው የኖረውም በቂሣርያ አካባቢ ሲሆን ባለ ትዳር የልጆች አባት ነው።

ለኢትዮጵያውያን አባታችን፣ መምህራችን፣ ክርስትናን ያገኘንበት ቅዱስ ሰው ነው። (ሐዋ. 8፥26)

ቅዱስ ባኮስ ጃንደረባውን ያጠመቀ የነፍስ አባቱ ነው። ከ4 ደናግላን ልጆቹ ጋር ሲሰብክ ኖሮ በዚህ ቀን ዐርፏል።

🍀 #አቡነ_አረጋዊ ተሰወሩ

ወላጆቻቸው ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረ አምላክ ተብለዋል። በኢትዮጵያ ደግሞ አረጋዊ ይባላሉ። አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ።

በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ጳኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል።

8ቱን ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ እየመሩ ያመጡአቸውም እሳቸው ናቸው። የቅዱስ ያሬድና ዓፄ ገ/መስቀል የቅርብ ወዳጅም ነበሩ።

🍀 #ሙሽሮቹ_ገብረ_ክርስቶስ እና #ቅዱስ_ሙሴ ዕረፍታቸው ነው።

በተለያየ ሀገርና ጊዜ ቢሆንም ሁለቱም ከጫጉላ ቤት ወጥተው፣ ራሳቸውን ምስኪን አድርገው፣ የአባታቸው ደጅ ላይ ነዳይ ሆነው ሳይታወቁ እየለመኑ የኖሩ ተጋዳይ ቅዱሳን ናቸው።

ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ በሃገራቸው ልሳን 'አብደል መሲሕ (የክርስቶስ ባርያ)' ይባላል። ለቅዱስ ሙሴና ለሌሎችም ሙሽርነትን ትቶ መመነንን ያስተማረ እርሱ ነው። ታላቁ አቡነ ኪሮስ አጎቱ ናቸው።

ቅ/ገብረ ክርስቶስ በአባቱ ቤት ደጃፍ 15 ዓመታት፣ ቅዱስ ሙሴ ደሞ 12 ዓመታት እየለመኑ ኖረው አርፈዋል።

T.me/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

23 Oct, 10:45


"ይሁ ሁሉ የእግዚአብሔርን ስራ ማደናቀፍ ያለ ዋጋ ክፍያ ይታለፋል ማለት ስህተት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ስራ ማንም በስጋ ጥበብና ጉልበት ሊያደናቅፈው የሚቻል አይደለም፡፡ ሲሞክርም ቅጣቱ ይሰነዘራል፡፡"

📎 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ቁጥር 5 ፡ ገፅ 38 * ተጻፈ መስከረም 21/2004 ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

23 Oct, 04:36


◦◆◦
እውነተኞቹ ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆችና መጪው ዕጣቸው፨
◦◆◦

ቀንና ጊዜ ባለፈ ቁጥር ሥጋ ለባሽ በመከራ ክብደት ይደክማል፡፡ ኃያል ጌታ ግን ለበረከቱ፣ ለምሕረቱ ያተማቸውን ልጆቹን ያጸናል፡፡ የሰጠውን ( የገባውን) ቃል ኪዳን ያከብራል፡፡

ሰው በድካም ዝሎ የተገባለትን ተስፋ ሁሉ ይተዋል፡፡ በብርቱ ድካም ዝሎ ይወድቃል፡፡ ልዑል ግን ያኔ ድካሙን ሁሉ ከድኖ፣ አድሶ፣ በብርታት ሞልቶ በደስታ እንዲቦርቅ ያደርገዋል፡፡

የታመንበት የሠራዊት ጌታ ሁሌም እስከ ዘለዓለሙ የታመነ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ፍቅሩ፣ መታደጉ፣ በረከቱ ልቡን የሞላው ዳዊት እንዲሁ አለ፦

እግዚአብሔር ወገኖቹን እንደ አይን ብሌን ይጠብቃቸዋል፡፡ በማንኛውም የዲያበሎስ ዘዴ ይወድቁና ይጠፉ ዘንድ በፍፁም አይፈቅድም፡፡

ወገኔ የልዑል ልጅ፤ የቅዱሳን የከበሩት መላእክት ልጆች ብዙ ብትሰቃዩም ይድረሳችሁ የተገባችሁን ነጭ ልብስ ለበሳችሁ፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ ልዑል ዙፋኑን የሚዘረጋባት፣ ልጆቹን እንቁዎቹን በዙፋኑ የሚያኖርባት፣ ድንግል ልጆችዋን በበረከቷ፣ በፍቅሯ የምታረሰርሳት፣ ኢትዮጵያ ቅዱሳን የከበሩት መላእክት ዙሪያዋን በእሳት አጥረው የሚጠብቁአት፣ የሚባርኳት ኢትዮጵያ፣ የፀናችው አንዲቷ የተዋሕዶ እምነት እንደፀሐይ የምታበራባት ኢትዮጵያ ለልዑል የሰራዊት ጌታ ሌትም ቀንም ለክብሩ ለስሙ ምስጋና እንደጅረት የሚፈስባት ድንግልና ቅዱሳን የከበሩት መላእክት፣ ቅዱሳን ሰማእታት፣ ነቢያት፣ሐዋርያት፣ ስማቸው የሚከብርባት፣ የሚመሰገኑባት ኢትዮጵያ በክብሯ ጥግ ማንም የማይደርስባት የእግዚአብሔር የስስት ልጁ ናት፡፡

ከዚህ ድንቅ አገር የተፈጠራችሁ፣ ለአባታችሁ ለልዑል፣ ለእንቁዋ ለአገራችሁ ኢትዮጵያ ዋጋ ከፍላችሁ በጭንቅ እዚህ ለደረሳችሁ ወገኖቼ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡ በእምነት ድሉን ተቀዳጅታችኋልና!

◆ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 5 ◆

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

22 Oct, 09:01


◦[ የቅዱስ ዳዊት የቀደመ መዝሙሩ ]◦
{ከቍጥር የወጣ መዝሙር ስለራሱ}

¹ ከወንድሞቼ ይልቅ እኔ ትንሽ ነበርሁ፤ በአባቴ ቤት ወጣት ነበርሁ፤ የአባቴንም በጎች እጠብቅ ነበር


² እጆቼ መሰንቆ ይመቱ ነበር፤ ጣቶቼም በገና ይደረድሩ ነበር።

³ ለጌታዬ ማን ነገረው እርሱ እግዚአብሔር እርሱ ሰማኝ።

⁴ እርሱ መልአኩን ልኮ አዳነኝ። የአባቴን በጎች ከምጠብቅበት ወሰደኝ፤ የተቀደሰ ቅባትን ቀባኝ።

⁵ ወንድሞቼ ግን ያማሩና ያደጉ ነበሩ፤ እግዚአብሔር ግን በእነርሱ ደስ አላለውም።

⁶ ልዩ ወገንን ልገጥመው ወጣሁ፤ በረከሱ ጣቶቹ ረገመኝ።

⁷ እኔም ከወንዝ ሦስት ድንጋዮችን አነሣሁ፤ ግንባሩንም በወንጭፍ መታሁት። ያንጊዜም በእግዚአብሔር ኀይል ወደቀ።

⁸ በላዩ የነበረውን ሰይፍ ወሰድሁ፤ የጎልያድን ቸብቸቦ ቆረጥሁት፤ ከእስራኤል ልጆችም ስድብን አራቅሁ።

▰ ▰ ▰

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

22 Oct, 05:13


ከፍተኛ ውድመት ያደረሰውን እና ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ገደማ የተነሳውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር የተቻለው፣ ከምሽቱ 5:00 ሰዓት በኋላ እንደነበር ታውቋል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

21 Oct, 20:05


❗️ለሰዓታት የቆየው የእሳት አደጋ አሁንም መቆጣጠር አልተቻለም

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

21 Oct, 19:30


🔥 ☝️☝️☝️☝️☝️
"...እሳቶች ከተነሱ የማይጠፉ ፤ አውሎ ነፋስ አዘል ሆነው ብዙ ከተሞችን ያወድማሉ።''
⚡️ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት -5 ገጽ-29* ተፃፈ 21/01/2004ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

21 Oct, 19:29


Update

1 ሰዓት ላይ የጀመረዉን እሳት እስካሁን
መቆጣጠር አልተቻለም

ሌባውም እያስቸገረ ነው።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

20 Oct, 10:50


ታላቁ ጻድቅ አባ ዘወንጌል ዘኢትዮጵያ አመታዊ መታሰቢያ ቀን ዛሬ ጥቅምት 10 ነው ።

እንኳን ለታላቁ አባታችን አባ ዘወንጌል ዘኢትዮጵያ 5ኛ አመት የዕረፍታቸው መታሰቢያ ቀን አደረሰን አደረሳችሁ። የአባታች በረከት ረድኤት በሁላችንም ላይ ይደርብን።

ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

20 Oct, 07:05


🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል ሦስት (3)


🔊 በትረካ (በድምፅ) የቀረበ

(📌 ክፍል 1ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 2ን ለማዳመጥ 👈)

ጻድቁ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ ማነው?
ቃልኪዳኑስ?

1) ከዚህ ሥር አጭር ዜና ሕይወቱን ያንብቡ👇

🫴 https://telegra.ph/ቅዱስ-ላሊበላ-ንጉሠ-ኢትዮጵያ-10-13

2) ከመድኃኔዓለም የተቀበለውን ልዩ ቃልኪዳን ያንብቡ👇

🫴
https://telegra.ph/ለቅዱስ-ላሊበላ-የተሰጡት-ልዩ-ቃልኪዳኖች-10-13

📌 ሙሉውን ታሪክ በማስተዋል ያንብቡ /ያዳምጡ/

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

20 Oct, 07:03


👇👇👇👇👇👇👇👇

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Oct, 19:16


🇨🇩 በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዋና ከተማ ህይወት በጎርፍ ሳቢያ ቆሟል  ሲል የሀገር ውስጥ ራዲዮ ጣቢያ ዘግቧል

🌧 በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዋና ከተማ ኪንሻሳ የጣለው ከባድ ዝናብ የጎርፍ አደጋ አስከትሏል። የ18 ሚሊዮን ህዝብ መኖሪያ ከተማ አብዛኛዎቹ ወረዳዎች በጎርፍ ተውጠዋል ፣ የትራፊክ ፍሰት በትላልቅ መንገዶች ላይ ቆሟል ፣ ነዋሪዎቹ በታዋቂው የጎምቤ ወረዳ ያሉ ነዋሪዎች እንኳን ወደ ውጭ መውጣት አልቻሉም ። ትምህርት ቤቶች፣ የገበያ ሥፍራዎች፣ሱቆች፣ ፋርማሲዎች እና ቢሮዎች መዘጋታቸውን ኦካፒ ሬዲዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በአለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ምክንያት ኪንሻሳ በተደጋጋሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የመጥፋት ስጋት እንዳለባት ሳይንቲስቶች አስጠንቅቀዋል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Oct, 14:30


🇳🇬 በሰሜን ናይጄሪያ በነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ በደረሰ ፍንዳታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ170 በላይ መድረሱ ተነገረ

የፖሊስ ሪፖርቶችን በመጥቀስ ቢያንስ 70 ሰዎች ከፍተኛ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል

አደጋው የደረሰው ማክሰኞ እለት በጂጋጋ ክልል ማጂያ በምትባል ከተማ ሲሆን በግጭት ምክንያት ከታንከር የሚፈስ ነዳጅ ለመሰብሰብ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ፍንዳታ በደረሰበት ወቅት ነው።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

19 Oct, 13:35


📌 ዋኖቻችንን እንወቅ ክፍል 3☝️☝️
ቅዱስ ላልይበላ ንጉሠ ኢትዮጵያ

በድምፅ (በትረካ) ነገ ይለቀቃል !

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

18 Oct, 19:56


📗📙📕 አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ፥ የኢትዮጵያንና የተዋሕዶን ትንሣኤ እንመሰክራለን !

👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
🟩
t.me/AlphaOmega930 (👨‍👧‍👦ግሩፕ)
🟨
t.me/christian930 (👩‍👧‍👦ቻናል)
🟥
t.me/Ewnet1Nat (🗣ንጽጽር)
🟢
t.me/ethioBirhan (በልዩ ልዩ ቋንቋዎች)
🟡
t.me/Amharic_messages (🔑በአማርኛ ብቻ)
🔴
t.me/EthioLightContents (🗞ማውጫ)
💚
t.me/aleqayalew (አለቃ አያሌው ታምሩ)
💛
https://www.facebook.com/joseph.ethiopia1 (📲በፌስቡክ)
❤️
https://youtube.com/channel/UCfoPIJgkHyihgUwMhvOzWXw (📡በዩቱብ)

💡 እነዚህን አማራጮች ማግኘት ያልቻላችሁ ወገኖቼ በማስፈንጠሪያቸው (Link) በመቀላቀል (Join) በማድረግ አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ ድኅረ ገጽን መከታተል፤ ከልዑል እግዚአብሔር በቀጥታ ለመላው የአዳም ዘር የሚተላለፉ የቅዱሳን አባቶችን መልዕክታት ማግኘትና የዓለምን መጻኢ እጣፈንታና የፍርድ አፈጻጸም ሒደት መከታተል ትችላላችሁ ።

🔐 ድኅረ ገጾችን በመከታተል፦
#Like #Share #Add_Member #Subscribe #Comment ማድረግ ይቻላል ።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

18 Oct, 17:03


🌍🦠 የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (ሲዲሲ) ኃላፊ በአህጉሪቱ እየጨመረ ያለውን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ​​ወረርሽኝ ቀውስ አስጠንቅቀዋል

የአፍሪካ ሲዲሲ በ18 የአፍሪካ ሀገራት ከ42,000 በላይ ኢንፌክሽኖች መታየታቸውን እና 1,100 ሰዎች መሞታቸውን ወረርሽኙ በሚያስገርም ሁኔታ መጨመሩን አስታውቋል።

🇨🇩🇿🇲🇿🇼 የአፍሪካ ሲዲሲ ኃላፊ ዣን ካሴያ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ብዙ ቢሆንም ቫይረሱ አሁንም መስፋፋቱን ቀጥሏል በዛምቢያ እና ዚምባብዌ አዳዲስ በወረርሽኙ የተጠቁ ሰዎች መገኘታቸው ገልጸው፤ ወረርሽኙ ዙሪያ አፋጣኝ እና ውጤታማ ዕርምጃዎች እስካልተወሰዱ ድረስ “ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

17 Oct, 17:38


#_ስለ_ዘመኑ_አትታወኩ

~ ወገኖቼ ፧
በስተመጨረሻ የምመክራችሁ ስለ ዘመኑ አትታወኩ። ሁሉም እግዚአብሔር ባላት መሠረት ትፈጸማለች፡፡ በእጃችሁ መልእክታቶች አሉ፤ በእጆቻችሁ ትምህርት  አለ፤ በእጃችሁ መግለጫዎች ሁሉ ነገር አለ። ወደ ኋላ መለስ እያላችሁ ማየት ብቻ ነው። #_መነጽሩ_እሱ_ነው፡፡

አንድም ከእግዚአብሔር ቃል ወጥታ፥ በእኛ በደካሞቹ በታናናሽ ባሮቹ በኩል የተነገረችው በሙሉ የምትቀር ነጥብ እንኳን የለችም፡፡ ይሄንን ላረጋግጥላችሁ ነው የምወደው።
#_በፍርድ_የምትካተቱ_በእኛ_ተግሣጽ_የተሰነዘረባችሁ_አይቀርም_ይፈጸማል። #_ለኢትዮጵያ_ምድር_የተጻፈው_ሁሉ_ይፈጸማል #_ለዓለም_የተጻፈው_ይፈጸማል። #_የማይፈጸም_የእግዚአብሔር_ቃል_የለም፡፡

እንዳሻህ ብትጮኽ፥ ያሻህ መሣሪያ ይሄ የሚድያ ጩኸት፣ ሬድዮ፣ ቴሌቭዥኑ፣ ሚድያው ሁሉ ቢንጫጫ #_የእግዚአብሔርን_እውነት_የሚቀይር_ምንም_ኀይል_በምድርህም_በሰማይም_የለም! ፈቃዱ ነው የሚጸናው!

#_በርቱ_ወገኖቼ፤ ስለ ወቅቱ አትፍሩ።
#_ባላችሁበት_ጸንታችሁ_ቁሙ። ወጀቡ ጩኸቱ ሁካታው አያውካችሁ። ይህ ሁሉ የመጣው ለእናንተ አይደለም። ለናቁት፣ ላቃለሉት፣ አልሰማ ላሉት፣ በትዕቢት ለታጀሉት፣ ለጠፉት ትውልዶች እግዚአብሔርን ለናቁና ላቃለሉ ነው ፍርዱ እየመጣ ያለው።

#_ስለዚህ_እሳቱ_አያልፋቸውም፤ ይወስዳቸዋል። በርቱ!  ተጽናኑ! በእግዚአብሔር በወደዳችሁ ተጽናኑ! በድንግል ተጽናኑ! በሊቀ መላእክቶቹ ሁሉ ተጽናኑ! በቅዱሳን አባቶቻችን ተጽናኑ! በምክሮቻቸው ተደሰቱ፤ ተጠቀሙበት! እግዚአብሔር ይባርካችሁ፤ አሜን፨

🇨🇬 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የዮሐንስ ወንጌል ትምህርት ክፍል- 7 --ሐ ከትምህርቱ መዝጊያ ቃል ላይ የተወሰደ፡፡

t.me/Ewnet1Nat  🇨🇬
http://t.me/AlphaOmega930  🇨🇬

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

17 Oct, 16:05


❗️Death toll in Gaza rises to 42,438 people — approaching 100,000 injured — Health Ministry

#IDF -

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

17 Oct, 16:01


Tragic tanker explosion kills over 100 in Nigeria

A petrol tanker crash in Jigawa State resulted in over 100 fatalities and more than 50 people hospitalized, local outlet The Nation reported.

The accident happened on Wednesday when the tanker overturned, prompting villagers to scoop up the spilled fuel before an explosion ignited.

#Africa -

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ

17 Oct, 16:00


❗️Israel conducting large-scale strikes in southern Lebanon — Local media

#IDF