የሰዎች ወደ ውስጥ ወይም ወደ ውጭ የመመልከት ዝንባሌ ከስብእና ዋና መገለጫዎች አንዱ ሲሆን በአንድ ግለሰብ ላይ በወጥነት ይስተዋላል። ወደ ውጭ የሚመለከቱ ሰዎች
1 #Extroverts
ተጫዋች/'ወሬኛ' ከሰዎች ጋር መቀላቀል የሚፈልጉ ሲሆኑ ወደ ውስጥ የሚመለከቱ::
2 #Introverts
በተቃራኒው ደስተኛ የሚሆኑት ለብቻቸው ሲሆኑ ነው። ሁለቱም የየራሳቸው ጥቅምና ጉዳት አላቸው። ወደ ውጭ የሚመለከቱ ሰዎች አዳዲስ ነገሮች የሚፈልጉ ሲሆን ከሌሎች ሰዎች ጋር ግንኙነት የሚፈጥሩላቸው አጋጣሚዎች ያስደስታቸዋል። ይሁን እንጂ ለረጅም ጊዜ ለብቻቸው የሚያሳልፉ ከሆነ መሰላቸትና ጭንቀት ሊታይባቸው ይችላል። በፓለቲካ፣ በመዝናኛ ዘርፍ ሲሰማሩ ስኬታማ ይሆናሉ። ወደ ውስጥ የሚመለከቱ ሰዎች ከሰዎች ጋር ግንኙነት መፍጠር ቢቸገሩም በጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ ውጤታማ ይሆናሉ። በመጨረሻም ሙሉለሙሉ ወደ ውስጥ ወይም ወደ ውጭ የሚመለከቱ ሰዎች ጥቂቶች ሲሆኑ አብዛኛው ሰው ከሁለቱም የተውጣጣ #Ambivert ነው
የፍቅር ግንኙነትን በተመለከተ "እንደማግኔት ተመሳሳይ ዋልታዎች ይገፋፋሉ፤ ተቃራኒ ዋልታዎች ይሳሳባሉ።" ከሚለው ይልቅ ሌሎች
የስብእና መገለጫዎችን ያካተተ 'አጠቃላይ መጣጣም' የተሻለ ይገልጸዋል። የራስን ስብእና መረዳት ውጤታማ የሚሆኑበትን መስክ ለመረዳት ወሳኝ ነው።
From :- UoG
#Share If You Love it Guys
@ye_fkr_psychology