Ibnu Muhammedzeyn @ibnumuhammedzeyn Channel on Telegram

Ibnu Muhammedzeyn

@ibnumuhammedzeyn


ይህ ቻናል በአላህ ፍቃድ አቅም
በፈቀደ መልኩ ትክክለኛው
ኢስላማዊ አስተምህሮት፦
① ከቁርኣን፣ ② ከሐዲሥ
√ በሰለፎች አረዳድ
እንድሁም
③ ከቀደምት እና በዘመኑ
ካሉ የሱናህዑለሞች
ንግግር ይቀርብበታል።

Ibnu Muhammedzeyn (Amharic)

እንኳን ወደ Ibnu Muhammedzeyn ቻናል በአላህ ፍቃድ አቅም እንደሚመለከቱ በገንዘብ ጊዜ እንገልፃለን ። Ibnu Muhammedzeyn የኢስላማዊ አስተምህሮት ነው፦ መሠረት 1 ፣ መድብ 2 ፣ በሰለፎች አረዳድ ወይም ቀደምት እና በዘመኑ ካሉ የሱናህዑለሞች ንግግር ይቀርብበታል። ስለ ቻናል፣ እንዴት አይደለም? ሰላም ይባላል! Ibnu Muhammedzeyn በቻናል ወደ አሳሪና አለም ካለ በቻናል መሠረት የምንቀርበውን ፕሮግራም እና ከልክሓቱ የሚሻሻልበት የሰላም አገልግሎቶች ያሉትን የሚወጪውን ንቅናቄዎች ለማድረግ እና ለትኩስ ቀላል ማስተማር ለመላኩ ምን ማድረግ እንችላለን።

Ibnu Muhammedzeyn

24 Oct, 05:25


سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ وَبِحَمْدِكَ ، أشهد أن لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ ، أَسْتَغْفِرُكَ وَأَتُوبُ إِلَيْكَ

Ibnu Muhammedzeyn

24 Oct, 05:23


ጧሊበል ዒልም መሆን እደለኝነት ነው👍

︎‏لو لم يكن في طلب العلم سوى إشغال النفس بما ينفعها والانشغال عن الفتن وغوائلها والترفع عن السفاسف والتوافه؛ لكفى !

فكيف وطلبه سببٌ لعبادة الله على بصيرة ورفعٌ للجهل وطريقه من أيسر الطرق إلى الجنة، ومذاكرته عبادة.

ففز بعلمٍ ولا تطلب به بدلا ..
فالناسُ موتى وأهلُ العلمِ أحياءُ

#منقول

​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/IbnuMuhammedzeyn

Ibnu Muhammedzeyn

24 Oct, 05:13


አላህን ከማውሳት ማነው ያዘናጋን?!

ለምን አላህን ከማውሳት እንደዘነጋን? ማን እንዳዘነጋን ማወቅ ከፈለግክ እሄን የቁርኣን አንቀፅ አንብብ መልሱን ታገኘዋለህ

{اسْتَحْوَذَ عَلَيْهِمُ الشَّيْطَانُ فَأَنسَاهُمْ ذِكْرَ اللَّهِ ۚ أُولَٰئِكَ حِزْبُ الشَّيْطَانِ ۚ أَلَا إِنَّ حِزْبَ الشَّيْطَانِ هُمُ الْخَاسِرُونَ}

«በእነርሱ ላይ ሰይጣን ተሾመባቸው፡፡ አላህንም ማስታወስን አስረሳቸው፡፡ እነዚያ የሰይጣን ጭፍሮች ናቸው፡፡ ንቁ! የሰይጣን ጭፍሮች ከሳሪዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡» [ሙጃደላ (19)]

በዚህ ገፍላችን ሙተን ከመንፀፀት በስተፊት ወደአላህ እነመለስ ለጊዚያው ደስታ ብለን የዘላለም ሂወታችንን አናጨልም።

ኢብኑ ሙሐመድዘይን (ሰኞ ረቢዑል አወል 28/1444 ሂ)
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/IbnuMuhammedzeyn

Ibnu Muhammedzeyn

24 Oct, 05:01


ለነገህ ምን አዘጋጅተሃል?

አዎ ለቀብር ጨለማ !!
ለቂያማ ጭንቀት !!
በሲራጥ ለማለፍ !!
አላህ ፊት ቁመን ስንጠየቅ ላለው ጭንቀት !!
በጥቅሉ ከሞት በሗላ ላለው ሂወታችን ምን አዘጋጅተናል?

አላህ (ሱብሓነሁ ወተዐሰላ) እንድህ ይላል:-

{ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ }

« እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ » [ሐሽር (18)]

ኢብኑ ሙሐመድዘይን
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/IbnuMuhammedzeyn

Ibnu Muhammedzeyn

23 Oct, 18:03


የሱና ሰዎች መንገዳቸው ግልፅ ነው።

🎙በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ (ሐፊዞሁሏህ)
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/Muhammedsirage
t.me/Muhammedsirage

Ibnu Muhammedzeyn

23 Oct, 17:46


📌 جديد التفريغات

📖 [ العقيدة الصحيحة وآثارها على الفرد والمجتمع ]

🎙لفضيلة الشيخ أ.د. صالح بن عبدالعزيز سندي - حفظه الله - أستاذ العقيدة بكلية الدعوة وأصول الدين بالجامعة الإسلامية بالمدينة النبوية

🔴 تنبيه : الشيخ لم يراجع التفريغ

ا═•═📚═•═ا
🔹فوائد أ.د. صالح سندي🔹
https://t.me/Drsalehs

Ibnu Muhammedzeyn

23 Oct, 17:41


‏‌
‏يقول ابن الجوزي -رحمه الله- [أتطمع مع حب الوسادات في لحاق السادات]؟!

Ibnu Muhammedzeyn

22 Oct, 13:21


በጥቅሉ ይህ መርህ ከኢስላም ውጭ ባሉ በተለያዩ ከሀዲያን በኢስላም ላይ ለሚነሱ ውዥንብሮችም ይሁን እንድሁም በኢስላም ውስጥ ላሉ የተለያዩ የጥመት አንጃዎች ለሚያነሱት ሹብሀዎች ለምሳሌ አህባሽ፣አሻዒራህ፣ሱፍይ፣ኢኽዋን፣ተብሊግ፣ሱሩርያህ፣ተክፊር፣ሐዳድያህ፣ሐጁሪያ፣እንድሁም በሰለፊያው ውስጥ የተለያዩ ረብሻዎችን የሚቀሰቅሶ ሰዎች በጥቅሉ የማንኛውም የጥመት አካል መልኩ ቢቀያየርም የጥመቱ ክብደት ቢለያይም በሰለፊያው ላይ (በሐቅ ባለቤቶች ላይ) ለሚያመጣው ማንኛውም ሹብሀ(ማምታቻ) ወሳኝ መልስ የሆነች መርህ ናት።
አንተ በዝርዝር ሹበሀዎቻቸውን ለመበታተን አቅም ቢያጥርህም ለማስረዳት ችሎታው ባይኖርህም አንተ መመለስ ስላልቻልክ የያዙት አቋም ትክክል ነው ማለት አይደለም ምክኒያቱም አን ሐቅን ቀድመህ በመረጃ ካወቅክ ሐቅ አንድ ነው ስለዚህ ከያዝከው ሐቅ ውጭ ያለ ነገር ባጢል እንደሆነ በማወቅ በውስጥህ ምንም አይነት ጥርጥር በአቋምህ ምንም አይነት መዋለል ሊፈጠር አይገባም ይልቅ ከኛ የሚጠበቀው በእያንዳንዱ የዐቂዳ፣የመንሀጅና ሌሎችም የዲን ጉዳዮች ከቁርኣንና ሐዲሥ በሰለፎች አረዳድ በሆነ ትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ እምነትና አቋም እንዲኖረን ብቻ ነው። እሄን ታደረግን ከማንኛውም የጥመት አካል ለሚመጡ ማንኛቸውም ማምታቸዎች(ሹበሀዎች) ከሐቅ በሗላ ጥመት እንጅ ምን አለ በማለት ባጢል በመሆኑ እርግጠኛ መሆን አለብን። አዎ ከሐቅ በሗላ ያለው ሁሉ ጥመት ነው። በዐቂዳችን በመንሀጃችን በማንኛውም የዲናችን ጉዳይ ጯሂ በጮኸ ቁጥር በፍፁም ልንጠራጠር ልንዋልል አይገባንም።

በተለይ ላለንበት ኺላፍ ለበዛበት በዲን ስም ሁሉም የአንጃውን እና የመሪውን እምነት በሚያራምድበት ሹብሀው በበዛበት ጊዜ እጅግ በጣም ወሳኝ የሆነች ቃዒዳ(መርሕ) ናት። በደንብ በመረዳት ተግባራዊ እናድርጋት በአላህ ፍቃድ ከሹብሀ ትጠብቀናለች። ወላሁ አዕለም

ወንድማችሁ ኢብኑ ሙሐመድዘይን (ቅዳሜ ረቢዑል አወል 26/1444 ሂ)
•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/IbnuMuhammedzeyn

Ibnu Muhammedzeyn

22 Oct, 13:21


በሐቅ ላይ ለመፅናት ሰበብ የሚሆንና ከጥመት ሰዎች የሚወረወሩ ሹብሀዎች እንዳያደናግሩን የሚረዳ ወሳኝ ቃዒዳ(መርሕ)

ማሳሰቢያ:- ((በተለይ ይህ መርህ ከስደት ወደሀገራቸው ለሚመለሱ ከእነርሱም ውስጥ በተለይ ወደገጠሩ የሀገራችን ክፍሎች ለሚመለሱ እህቶች እና ለተራው የሰለፊይ ክፍል ወሳኝ መርህ ነው። ከፅሁፌ መጨረሻ ላይ እሄን ያልኩበትን ምክኒያት አስቀምጣለሁ)) እሄን ወሳኝ ቃዒዳ አብረን እንመልከት

👉 ሹብሃ እንዳይበግርህ ሙብተዲዕ እንዳያምታታህ የባጢል ባለቤት ከያዝከው ሐቅ እንዳያዋልልህ ከፈለግክ እሄን ሸሪዓዊ መርህ በጥርስህ ነክሰህ ያዝ!!
ሁሌም በሒወትህ ውስጥ ተግባራዊ አድርገውም። የዛኔ ሹብሀ አይብግርህም በዐቂዳህም ሆነ በመንሀጅህ በጥቅሉ በሐቅ ላይ የባጢል ባለቤት በፍፅም ሹብሀ ሊጥሉብህ አይችሉም በአላህ ፍቃድ በዲን ላይ መገለባበጥም አታበዛም በሐቅ ላይ ፅናት ይኖረሃል።


እሄን ቃዒዳ እውቁ የተፍሲር ሊቅ የዚህ ዘመን ታላቅ ዓሊም (የኢብኑ ዑሠይሚን አስተማሪ የሆኑት) ዐብዱረሕማን አስ–ሲዕዲይ (ረሒመሁሏህ) የሚከተለውን የቁርአን አንቀፅ ሲያብራሩ እሄን ገራሚ ቃዒዳ እንድህ በማለት ያስቀምጣሉ:-
አላህ(ሱብሐነሁ ወተዓላ) እንድህ አለ:-

{ الْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُن مِّنَ الْمُمْتَرِينَ }

«ይህ ከጌታህ ዘንድ የኾነ እውነት ነው፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትኹን፡፡» [አል ዒምራን (60)]
ኢማሙ አስ–ሲዕዲይ እንድህ በማለት ያብራራሉ:-

«ጌታህ በእርሱ ከነገረህ በሆነ ነገር ጠርጣሪ አትሁን ማለት ነው።

በዚህና ቀጥሎ በሚመጣው አንቀፅ ውስጥ በጣም ትልቅ ለሆነች (ኢስላማዊ) መርሕ መረጃ አለ። እርሱም:- በዐቂዳም ይሁን በሌላ ጉዳይ ላይ ሐቅ በመሆኑ ላይ መረጃ የቆመበትና ባሪያ ቆርጦ ያመነበት (ማንኛውም የዲን) ጉዳይ ከእርሱ ተቃራኒ የሆነው ማንኛውም ነገር ባጢል ለመሆኑ ቁርጥ ተደርጎ ሊታመን ይገባል። በእርሱ(በባሪያ) ላይ የሚያመጧት ማንኛዋም ሹብሀ( ማምታቻ) ብልሹ (በመሆኗ ቁርጥ ተደርጎ ሊታመን ይገባል) ይህ ባሪያው ያን (ከባጢል ሰዎች) የመጣበትን ሹብሃ (ማምታቻ) መፍታት(መመለስ) ቻለም አልቻለም (ከሐቅ ውጭ ያለ ማንኛውም ነገር ባጢል በመሆኑ ቁርጥ አድርጎ ሊያምን ይገባዋል)
እሄን ሹበሀ(ማምታቻ) መመለስ አለመቻሉ (በመረጃ) ባወቀው (ሐቅ ላይ) ምንም አይነት ትችት ሊፈጥርበት አይገባም።
ምክኒያቱም ሐቅን የተቃረነ(የተኻለፈ) ማንኛውም ነገር ባጢል ነውና። አላህ እንድህ ይላል:-
{ فَمَاذَا بَعْدَ الْحَقِّ إِلَّا الضَّلَالُ }
«ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ» [ዩኑስ 32]

በዚች ሸሪዓዊ በሆነች መርህ (ምክኒያት) ፈላስፋዎች ከሚያመጡትና የመንጢቅ(የሎጂክ) ባለቤቶች ከሚያደራጁት ብዙ ችግሮች ከሰው ላይ ይፈታሉ።

قال الإمام المفسر العلامة عبدالرحمن السِّعدِّي في تفسير هذه الأية :-

{ الْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُن مِّنَ الْمُمْتَرِينَ } [ آل عمران 60]
ﺃﻱ: اﻟﺸﺎﻛﻴﻦ ﻓﻲ ﺷﻲء ﻣﻤﺎ ﺃﺧﺒﺮﻙ ﺑﻪ ﺭﺑﻚ، ﻭﻓﻲ ﻫﺬﻩ اﻵﻳﺔ ﻭﻣﺎ ﺑﻌﺪﻫﺎ ﺩﻟﻴﻞ ﻋﻠﻰ ﻗﺎﻋﺪﺓ ﺷﺮﻳﻔﺔ ﻭﻫﻮ ﺃﻥ ﻣﺎ ﻗﺎﻣﺖ اﻷﺩﻟﺔ ﻋﻠﻰ ﺃﻧﻪ ﺣﻖ ﻭﺟﺰﻡ ﺑﻪ اﻟﻌﺒﺪ ﻣﻦ ﻣﺴﺎﺋﻞ اﻟﻌﻘﺎﺋﺪ ﻭﻏﻴﺮﻫﺎ، ﻓﺈﻧﻪ ﻳﺠﺐ ﺃﻥ ﻳﺠﺰﻡ ﺑﺄﻥ ﻛﻞ ﻣﺎ ﻋﺎﺭﺿﻪ ﻓﻬﻮ ﺑﺎﻃﻞ، ﻭﻛﻞ ﺷﺒﻬﺔ ﺗﻮﺭﺩ ﻋﻠﻴﻪ ﻓﻬﻲ ﻓﺎﺳﺪﺓ، ﺳﻮاء ﻗﺪﺭ اﻟﻌﺒﺪ ﻋﻠﻰ ﺣﻠﻬﺎ ﺃﻡ ﻻ ﻓﻼ ﻳﻮﺟﺐ ﻟﻪ ﻋﺠﺰﻩ ﻋﻦ ﺣﻠﻬﺎ اﻟﻘﺪﺡ ﻓﻴﻤﺎ ﻋﻠﻤﻪ، ﻷﻥ ﻣﺎ ﺧﺎﻟﻒ اﻟﺤﻖ ﻓﻬﻮ ﺑﺎﻃﻞ ﻗﺎﻝ ﺗﻌﺎﻟﻰ {ﻓﻤﺎﺫا ﺑﻌﺪ اﻟﺤﻖ ﺇﻻ اﻟﻀﻼﻝ}
ﻭﺑﻬﺬﻩ اﻟﻘﺎﻋﺪﺓ اﻟﺸﺮﻋﻴﺔ ﺗﻨﺤﻞ ﻋﻦ اﻹﻧﺴﺎﻥ ﺇﺷﻜﺎﻻﺕ ﻛﺜﻴﺮﺓ ﻳﻮﺭﺩﻫﺎ اﻟﻤﺘﻜﻠﻤﻮﻥ ﻭﻳﺮﺗﺒﻬﺎ اﻟﻤﻨﻄﻘﻴﻮﻥ، ﺇﻥ ﺣﻠﻬﺎ اﻹﻧﺴﺎﻥ ﻓﻬﻮ ﺗﺒﺮﻉ ﻣﻨﻪ، ﻭﺇﻻ ﻓﻮﻇﻴﻔﺘﻪ ﺃﻥ ﻳﺒﻴﻦ اﻟﺤﻖ ﺑﺄﺩﻟﺘﻪ ﻭﻳﺪﻋﻮ ﺇﻟﻴﻪ.. اهى


ከላይ ያሳለፍነው የሸይኽ ሲዕዲይ ተፍሲር ሀሳብ በአጭሩ ሲጨመቅ : «ሐቅን በመረጃ ካወቅክ ከባጢል ባለቤቶች የተለያዩ ሹብሀ ቢመጡብህ በያዝከው አቋም በፍፁም ልትጠራጠርም ሆነ ልትዋልል አይገባህም ምክኒያቱም ከሐቅ ውጭ ያለው ማንኛውም ነገር ባጢል ነው። አላህ እንድህ ይላል «ከእውነት በሗላ ጥመት እንጅ ሌላ ምን አለ» [ዩኑስ (32)] ከሐቅ ውጭ ያለ ማንኛውም ነገር አንተ መመለስ ቻልክም አልቻልክም ባጢል(ውድቅ) ነው። እንድሁም ለሚነሳው ባጢል ሁሉ መመለስ አለመቻልህ በየዝከው ሐቅ ላይ ምንም የሚፈጥረው ተፅእኖ አይኖርም» ማለት ነው።

እሄን ቃዒዳ በደንብ እንድንረዳ በምሳሌ እንመልከት
ለምሳሌ:-
አንተ አላህ ከዐርሽ በላይ መሆኑን ታምናለህ መረጃህም
{الرَّحْمَٰنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَىٰ}
«አል–ረሕማን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ፡፡»

የዚህ የቁርኣን አንቀፅ ትክክለኛውን ትርጉም በመረጃ ካወቅክ በዚህም መረጃ መሰረት አሏህ ከዐርሽ በላይ መሆኑን ታረጋገጥክ

ከዚህ በሗላ ሱፍይ፣አሻዒራ፣አህባሽና መሰል የቢዳዓ ባልተቤቶች የማታውቀውን ነገር እይዘበዘቡ እዚህኮ የተፈለገበት «መጃዝ ነው» ወይንም «ኢስተዋ ቢማዕና ኢስተውላ ነው ለዚህም መረጃችን ቀድኢስተዋ ቢሽሩን…» እያሉ ቢዘበዝቡብህና አንተ ደግሞ እሄን ከሸረሪት ቤት የደከመ መረጃ ለመመለስ እውቀቱ ቢያጥርህ በያዝከው አቋም በፍፁም አትጠራጠር የእነርሱም አቋም እውነት መስሉ በፍፁም አይታይህ ከላይ ባሳለፍነው መርህ መሰረት አንተ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን በመረጃ ካወቅክና ካረጋገጥክ ከእርሱ ውጭ ያለው ባጢል መሆኑን በእርግጠኝነት እወቅ።

ይህን እንደምሳሌ ነው የጠቀስኩት ሌሎችም በዐቂዳና በመንሀጅ ዙሪያ የሚነሱ ማንኛቸውንም ማደናገሪያዎች በዚሁ መሰረት መመለስ ትችላለህ።

ይህ መርህ ወሳኝ መርህ ነው በተለይ ደግሞ አላህ የሐቅን ጎዳና ለመራቸው ግን ሰፊ እውቀት ለሌላቸው ወንድም እና እህቶች ደግሞ በጣም አስፈላጊ ነው።

በተለይ ከላይ መግቢያዬ ላይ እንደጠቀስኩት ወደውጭ ሀገር በስራ ምክኒያት ተሰደው ያላቸውን ክፍት ጊዜ በመጠቀም በሚዲያ ጠቃሚ የዲን ት/ቶችን በመከታተል ሐቁን ለተማሩ እህቶች በጣም አስፈላጊና ሆሌም ሊረሱት የማይገባ ወሳኝ መርህ ነው።

ስደተኛ እህቶችን የለየሁበት ምክኒያት:-
ብዙ እህቶች በስደት ሂወታቸው ትርፍ ጊዚያቸውን በመጠቀም በሚዲያ ጥሩ የሰለፊይ እውቀት ሲማሩ ቆይተው ወደሀገር ሲመለሱ በተለይ የገጠር አከባቢ ልጆች ከሆኑ የሱና ኡስታዞችና ዱዓቶች በአከባቢው ብዙም ላያገኙ ይችላሉ እንድሁም ካለው የኔትና የመብራት ችግር አልያም በቤተሰብ ጉዳይ ቢዚ በመሆን ከሚዲያም ይርቃሉ በዚህ ጊዜ ከቤተሰብም ይሁን ጎረቤት እንድሁም ከአከባቢ ሰዎች በተለይ በዝምድና ከሚቀርቧቸው ቅርብ ቤተሰቦቻቸው በተለያዩ ቢድዓ የተመረዙ አካሎች በያዙት የሰለፊያ አቋም ላይ ጧት ማታ ሹብሃ በመልቀቅ እራሳቸውን ዒልም ያላቸው በማስመሰል ከያዙት ሐቅ ለማስለቀቅ የሚፈታተኗቸው ብዞዎች ናቸው። ታዲያ የዛኔ ሹብሀቸውን የመመለሱ አቅም ባይኖራችሁም የሚያብራራላችሁ የሰለፊይ ኡስታዝ ባታገኙም በመረጃ በያዛችሁት አቋም በፍፁም አትጠራጠሩ ይልቁንም ከሐቅ በሗላ ጥመት እንጅ ምን አለ የሚለውን መርህ በመተግበር በአቋማችሁ ላይ ፅኑ።

Ibnu Muhammedzeyn

22 Oct, 08:32


ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አልበድር የታላቁ ሙሐዲሥ ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድ ልጅ ናቸው። ሸይኽ ዐብዱረዛቅ ስክነታቸው ይማርካል። ኹሹዐቸው ከአድማጭ ይጋባል። ለቅሷቸው ያስለቅሳል። ትምህርታቸው አንጀት ያርሳል። ኪታቦቻቸው ተመርጦ የሚታለፍ የላቸውም። የተባረከ ሸይኽ፣ ከተባረከ አባት። አላህ ከክፉ ይጠብቃቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Muhammedzeyn

22 Oct, 04:58


👆 ‏أقول : من حببت إليه ‎#القراءة فقد حببت إليه نعمة كبيرة من فوائدها : رفع الجهل ، كثرة العلم ، زيادة المعرفة ، توسيع مدارك العقل ، تقوية الذاكرة ، تقويم اللسان ، ومن أكبر فوائدها الإنشغال بالنافع عن القيل والقال وجميع ما لا ينفع .

Ibnu Muhammedzeyn

22 Oct, 04:54





👆ሐቂቃ ለሁላችንም አስፈላጊ የሆነ ምክር ነው እናንብበው ደግሞ አሁንም ረጅም ፅሑፍ ማንበብ አልወድም ብለን እንዳንዘለው👆

Ibnu Muhammedzeyn

22 Oct, 04:52


ስንፍና እሹሩሩ
~
ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከሚታዩ አስቀያሚ ሃሳቦች አንዱ "እኔ ረጅም ፅሑፍ አልወድም" የሚል የስንፍና አዋጅ ነው። ደግሞኮ በዚህ በሽታ የተለከፈው ብዛቱ! ለምን ግን ነውር ጌጡ እንሆናለን? ሁለት ሶስት ገፅ ፅሑፍ ረዝሞ ነው "ረጅም ፅሑፍ" እያልን የምንገልፀው? ደግሞስ አለማንበብ ቁምነገር ሆኖ ነው እንደ ጀብድ የምናወራው? እኛ በዚህ ዓይነት ገዳይ ስንፍና ውስጥ ከሆንን ማነው ልጆቻችንን መስመር የሚያሲዛቸው? እንዴትስ ነው ከልብ ሆነው ኪታብ እንዲቀሩ፣ ትምህርት እንዲማሩ የምናደርጋቸው? ለመሆኑ ክፉ ምሳሌ እንዳንሆን ቦታ እየመረጥን ነው "ረጅም ፅሑፍ አልወድም" የምንለው? ነው ወይስ ለታዳጊዎችም ስንፍናችንን "በክብር" እያወረስን ነው?
እንዲያው ክፉ በሽታ ቢጣባን እንጂ እንደ ማንበብ የሚያረካ ምን አለ? እንዴት ነው ሳናነብ የአስተሳሰብ አድማሳችንን የምናሰፋው? እንዴት ነው ያለ ንባብ ራሳችንን የምንለውጠው? እንዴት ነው ያለ ንባብ ትውልድ የምንገነባው? ጭራሽ ባደባባይ ተወጥቶ "እኔ ረጅም ፅሑፍ አልወድም" እያሉ እንደ ጀብድ ይቀባበሉታል። እሺ አትወድም። ሰው ነውሩን ባደባባይ ያሰጣል? "የንባብ ባህላችን ሞተ ምን ይሻላል?"፣ "የንባብ ፍቅር የለኝም፤ ምን ባደርግ ይሻለኛል?" የሚል ሰው መፍትሄ ፍለጋ ይናገር። "እንዴት ችግሬን ልቅረፍ?" ለማለት። በጋራ መፍትሄ ለመፈለግ። ዛሬ የሚታየው ግን ሌላ ነው። አንዱ "እኔ ረጅም ፅሑፍ አልወድም" ሲል ሌሎችም እንደ ቁም ነገር እያከታተሉ "እኔም"፣"እኔም" እያሉ የኮሜንት ዶፍ ያወርዳሉ። ይሄ ነውር ነው፤ ነውር ጌጡ! ለአኺራም ይሁን ለዱንያ የሚሆኑ ቁምነገር አዘል ዳጎስ ያሉ ኪታቦችንና መፅሐፎችን ማንበቡ ቀርቶ ጭራሽ ሶስትና አራት ገፆችን ለማንበብ ልባቸው ጉሮሯቸው ስር ይወተፋል። ከዚያ ህፃን ይመስል ፕራንክ እያሯሯጡ፣ እንቶፈንቶ የቴክቶክና የዩቲዩብ ቪዲዮ እያሳደዱ ይውላሉ። ይሄ ሊታከሙት የሚገባ በሽታ ነው። ሰው እንዴት ፕራንክ የሚሉት የጅላጅል ስራ ላይ ሲያገጥ ይውላል? ሱብሓነላህ!
በተለይ ጦለበተል ዒልም (ደረሶች) እንዴት ነው ኪታብ ሳታነቡ የምትውሉት? እስኪ በዚህ አመት ስንት ኪታብ እንዳነበብክ ራስህን መለስ ብለህ ታዘበው? የዒልም ጉዞህ እንዲህ የተንዘላዘለ እንዲሆን ነው የምትፈልገው? ትርጉም ያለው የዒልም ትጥቅ መታጠቅ የሚፈልግ ሰው እንዴት ያለ ንባብ ካሰበበት እደርሳለሁ ብሎ ያስባል?! ይሄ የግድ መታረም ያለበት ክፉ ልማድ ነው።
ለማንኛውም ነፍስ እንደ ያዟት ነው የምትሆነው። ለቁርኣን ጊዜ የማይሰጥ ሰው 30 ደቂቃ ቁጭ ብሎ መቅራት ትእግስቱን ይፈታተነዋል። ከሶላት ጋር ልቡ ያልተዋሀደ ሰው አራት ረከዐ ለመስገድ አስሬ ያዛጋል። ችግሩን ለመፍታት ግን ከአላህ ጋር ቀላል ነው። በቅድሚያ የችግሩን አሳሳቢነት እንመን። ከዚያ ቁርጠኝነት እንታጠቅ። ከዚያ ተደጋጋሚ ጥረት እናድርግ። ከዚያ ለውጣችንን እንገምግም። አንዴ ህይወታችን ጋር ከተዋሀደ ወላሂ እያጣጣምነው ነው የምንኖረው። ስንፍናችንን እሹሩሩ እያልን የምንቀጥል ከሆነ ግን እድሜ ልካችንን በድንቁርና እያጌጥን ነው የምንኖረው። አላህ ይሁነን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Muhammedzeyn

22 Oct, 03:51


سبع وصايا مهمة عظيمة لطلبة العلم

لفضيلة الشيخ المبارك صالح بن عبد العزيز سِندِي حفظه الله

Ibnu Muhammedzeyn

22 Oct, 03:48


ሁሌ ውስጣችንን ቢዚ የሚያደርገን ምንድን ነው?

እውነት በውስጣችን ሌላን የዱኒያ ጉዳይ እንደምናስበው ያክል አላህን እናወሳልን?

የዱኒያ ጉዳይ አሳስቡ እንደሚያስጨንቀን ሁሉ የቀብራችን የነገ አኼራችን ጉዳይ ያስጨንቀናልን?

ኢማሙ ኢብኑልቀይም ረሒመሁሏህ እንድህ ይላሉ

«(ከጌታህ ጋር) በመለያየት የወረደብህን አደጋና (ከጌታህ) የጋረደህን የውረደት ሂጃብ(ግርዶ) ማወቅ ከፈለግክ: ቀልብህ ለማን ባሪያ፣ አካልህ ለማን አገልጋይ እንደሆነ ተመልከት ውስጥህ በምን ጉዳይ ቢዚ እንደሆነ የመተኛ ቦታህን የያዝክ (ለመተኛት በጎንህ ጋደም ባልክ) ጊዜ ቀልብህ የት እንደሚያድር ከእንቅልፍህ ስነቃ ቀልብህ ወደየት እንደሚበር ተመልከት? ያ(እንድህ ውስጥህ ቢዚ የሆነለት ነገር) ነው (በትክክል) አምላክህ።
የቂያማ እለት ሁሉም (በዱኒያ ላይ) ሲያመልክ የነበረውን ይከተል መባልን በሰማህ ጊዜ (ይህ ውስጥህን እንድህ ቢዚ ያደረገው ነገር) የሆነውም ቢሆን ከእርሱ ጋር አብረኽ ትሄዳለህ። [መዳሪጅ ሳሊኪን (3/308)]


ሐቂቃ ይህ በጣም ያስደነግጣል የሁሌ ጭንቀታችን ሀሳባችን የነገ አኼራ ወይንስ እች ርካሿ ዱኒያ? ሁላችንም ቆም ብለን እራሳችንን እንፈትሽ?
_
قال الإمام ابن القيم رحمه الله

إِذَا أَرَدْتَ أَنْ تَعْرِفَ مَا حَلَّ بِكَ مِنْ بَلَاءِ الِانْفِصَالِ، وَذُلِّ الْحِجَابِ، فَانْظُرْ لِمَنِ اسْتَعْبَدَ قَلْبَكَ، وَاسْتَخْدَمَ جَوَارِحَكَ، وَبِمَنْ شَغَلَ سِرَّكَ، وَأَيْنَ يَبِيتُ قَلْبُكَ إِذَا أَخَذْتَ مَضْجَعَكَ؟ وَإِلَى أَيْنَ يَطِيرُ إِذَا اسْتَيْقَظْتَ مِنْ مَنَامِكَ؟ فَذَلِكَ هُوَ مَعْبُودُكَ وَإِلَهُكَ، فَإِذَا سَمِعْتَ النِّدَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ: لِيَنْطَلِقَ كُلُّ وَاحِدٍ مَعَ مَنْ كَانَ يَعْبُدُهُ، انْطَلَقْتَ مَعَهُ كَائِنًا مَنْ كَانَ. [مدارج السالكين (٣/ ٣٠٨)]

ኢብኑ ሙሐመድዘይን
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/IbnuMuhammedzeyn
t.me/IbnuMuhammedzeyn

Ibnu Muhammedzeyn

22 Oct, 03:48


ምርጥ ጓደኛህ ብሎ ማለት በሁኔታዎች መቀያየር የማይቀያየር ነው።

ኢብኑ ሙሐመድዘይን
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/IbnuMuhammedzeyn

Ibnu Muhammedzeyn

22 Oct, 03:48


ታሞ ለደከመ በተለይ ሞት አፋፍ ላይ ላለ ሰው የተለያዩ የህክምና እና መሰል እንክብካቤዎችን እንደምናደርግለት ሁሉ ሶላት እንዲሰግድም እንተባበረው።

ታሞ ለደከመ በተለይ ሞት አፋፍ ላይ ላለ ሰው የተለይዩ ያድኑታል ያልነውን ነገር ሁሉ ለማድረግ እንጥራለን። አቅማችን በፈቀደ መልክ ይሻላል የተባለ ሆስፒታልና የህክምና ባለሙያ ዘንድ ይዘን እንሄዳለን ግን ብዙዎች ዘንድ አንድ ከባድና ሊዘነጋ የማይገባ ነገር ይዘነጋሉ እርሱም 👉 ሶላት

የታመሙ ሰዎችን በሌሎች ነገሮች እንደምንከባከበው ሁሉ ሶላትም እንዲሰግዱ ልናስታውሳቸውና ልንተባበራቸው ይገባል።
ለምሳሌ ውዱእ ማድረግ የማይችሉ ከሆነ ተይሙም የሚያደርጉበት አፈር በማምጣትና ተይሙም በማስደረግ እንድሁም በራሳቸው መዞርና የቂብላን አቅጣጫ መያዝ የማይችሉ ከሆነ ወደቂብላ አዙረን በማስተኛት ልንተባበራቸው ይገባል።

ይህ በጣም ብዙ ሰዎች ሲዘነጉት ይታያል በተለይ በሽታው ከበድ ያለ ከሆነ ወይንም በድንገተኛ አደጋ የተከሰተ ከሆነ ሰዎች በመደናገጥ ስለህክምና እንጅ የሚያስቡት ስለሶላት አላህ ካዘነላቸው ውጭ ብዞዎች ትዝ አይላቸውም።

እንድሁም ታማሚው አካል በዲኑ ደካማና ያን ያክል ካልሆነ እርሱም በዚያ የበሽታ ስቃይ ላይ ሁኖ ሶላት ትዝ አይለውም የግድ አስታማሚ ሊያስታውሰው እና ሊተባበረው ይገባል።

ብዙዎች ሂወታቸውን ሁሉ ሲሰግዱ ቆይተው ግንሳ ሲታመሙና በመጨረሻ ዱኒያን ሊሰናበቷት ሲሉ በተለይ በዚህ ሳዐት ካለፈ ወንጀላቸው መቶበት እና መልካም ስራን ማብዛት ያለባቸው የመጨረሻ ወሳኝ ጊዜ ቢሆንም የሚያሳዝነው ሶላትን ያክል ከባድ ነገር ትተው እችን ዱኒያ ተሰናበተው ወደዚያ የጨለማ ቤት ይሄዳሉ። ልብ በሉ ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) «ስራ በመጨረሻ ነው ይላሉ» ስለዚህ ሁለት ነገሮችን በደንብ እናሰተውል:-
አንድ አስታማሚ ስንሆን ቤተሰብ ጎረቤት ሲታመም ልክ ለማሳከም እንደምንጥረው ሁሉ የሶላት ወቅትም ሲደርስ እንዲሰግዱ በማስታወስ ተገቢውን ትብብር እናድርግ ላቸው
ሲቀጥል ሁላችንም እችን ዱኒያ መልቀቃችን አይቀርም እና ስንታመም ቤተሰብ እኛን ለማሳከም ደፋ ቀና ሲል ሶላት እንድንሰግድ ውዱእ የማንችል ከሆነ ተይሙም እንዲያስደርጉን እንጠይቅ

ሶላት በሂወት እስካለን እና አቅላችን እስካለ ድረስ በኛ ላይ የተንጠለጠለ ግዴታ ነው። የበሽታ ክብደትና ስቃይ የሶላትን ዋጅብነት አያስቀረውም ምናልባች አቅማችን የማይችል ከሆነ አፈፃፀሙ ይቀልልናል ማለት ቁሙ መስገድ ያልቻለ ቁጭ ብሎ ቁጭብሎ ሩኩዕና ስጁድ ማድረግ ያልቻ በጭንቅላቱ እየጠቀሰ ቁጭብሎ የማይችል በቀኝ ጎኑ በመተኛት ወደ ቂብላ ዙሮ መስገድ አለበት እንደውም አንድ ሰው በሽታ ጠንቶበት በጥና ታሞ ከአጠገቡ የሚያስታመው ሰው ባይኖረና ወደቂብላ መዞር የማይችል ቢሆን ባለበት አቅጣጫ ሁኖ ሊሰግድ ግድ ነው እንድሆም ውዱእም ሆነ ተየሙም የሚያስደርገው ቢያጣም ያለ ውዱ ባለበት ሁኔታ ላይሁኖ ሊሰግድ ግድ ነው ፉቀሃዎች እንድህ አይነቱን ሰው (فاقد الطهرين ሁለት መጡሀሪያዎችን ያጣ ውሃና ተየሙም የሚያደርግበት ነገር ማለት ነው) በማለት ይጠሩታል።

እንግድህ በሂወት እስካለንና አቅላችን እስካልተወገደ ድረስ ሶላት መቸም የማይለቀን ግዴታ መሆኑን ታወቅን ከላይ እንደገለፅኩት ሰው ሲታመምብን ሶላት እንዲሰግዱ የበኩላችንን ጥረት ልናደርግ ይገባል እንድሁም እኛ ስንታመም ሶላትን ልንዘነጋ አይገባም
ወቢላሂ ተውፊቅ ወሏሁ ተዓላ አዕለም

ወንድማችሁ/ ኢብኑ ሙሐመድዘይን
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/IbnuMuhammedzeyn
t.me/IbnuMuhammedzeyn

Ibnu Muhammedzeyn

21 Oct, 10:07


ከአሊሞች አንደበት ቁ (48)

ሸይኽ ሷሊህ አል–ኡሰይሚን እንዲህ ይላሉ:-
"በአንድ ሰው መዝገብ ውስጥ አንድ ተሰቢህ ከዱኒያ እና እውስጧ ካሉት በላጭ ናት ምክኒያቱም ዱኒያ እና በውስጧ ያሉት ጠፊዎች ሲሆኑ ተስቢህ እና መልካም ስራ ግን ቀሪዎች ናቸው።"
[ሸርሁ ሪያድ (3/478)]
https://telegram.me/IbnuMuhammedzeyn

Ibnu Muhammedzeyn

21 Oct, 06:53


#لطيفة:  | سعة العلم وسرعة النظم.

١_ نظم العلامة السيوطي تـ911هـ (عقود الجمان في البيان والمعاني) في علوم البلاغة  في يومين وهي 1600بيت .

٢_ ونظم (الفريدة في النحو) في علوم النحو والصرف في ثلاثة أيام  وهي 1000 بيت .

٣_ ونظم (نظم الدرر في علم الأثر) في مصطلح الحديث في خمسة أيام.

٤_ نظم السيوطي ( الكوكب الساطع نظم جمع الجوامع) في علم أصول الفقه في خمسة أيام وهي 1480بيتا .

4,096

subscribers

218

photos

94

videos