ጦቢያ የግጥም መድብል @was143 Channel on Telegram

ጦቢያ የግጥም መድብል

@was143


አማራ ነኝ ያውም ትግሬ
እንደ ሮሃ ተፈልፍዬ፣ልክ እንደ አክሱም ተገትሬ
ምጠብቅሽ እልፍ ዘመን፣በጣይ እና በጨረቃ
ስቀልድ ነው ኦሮሞ ነኝ፣ከተናገርኩ በሀቂቃ
እንደውም ሁሉን ብሔር ነኝ፣ዘረኝነትን የምደቃ
ዘሬ ሰው ነው፣ብሔሬም ሰው፣ሰው ነኝ በቃ
።።።።።።።።።።
@WAS143 ይጎብኙ
@WAS143
@WAS143
በቀጥታ ለማግኘት
@WASYA
@WASYA
ማንኛውንም መልዕክት ለመላክ
@WASYA

ጦቢያ የግጥም መድብል (Amharic)

ጦቢያ የግጥም መድብል በአምራችን ሰሞኑ እና ሎሚያችን መድብል ነው። ይህ መድብል የሚደርገውን እንዲሆን እየሆነ የግጥም መረጃዎችን እና መድብሎችን የሚጠቀሰውን ነው። ይህ መድብል ረቂቅ በበቂ እና በተለያዩ ስነስርአት ላይ በሚታክልበት ምንም መረጃ ነው ታላቅና ውዴታና ማፍናቅ እንዲሆኑ ነው። ጦቢያ የግጥም መድብል የተናገረ ሰው እና ብሔሬን ተመልክቶ እንዲቀጽል እና ውዴታ እንዲሆን ለአንድ በሰጡት የጥፋት መንገዶች እንደ ክፉት ድምፅ አስተምረናል።

ጦቢያ የግጥም መድብል

15 Nov, 11:11


በመኖር አጸድ ውስጥ
(በእውቀቱ ስዩም)

ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::

እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
-ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤

ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

30 Oct, 03:25


አልቃሽና አጫዋች
(በእውቀቱ ስዩም)

ቦጋለ በሚባል ስም የሚታወቁ ሁለት ስመጥር ሰዎችን አውቃለሁ፤ የመጀመርያው የ”ፍቅር እስከመቃብሩ” ገበሬ፥ ቦጋለ መብራቱ ነው፤ ሁለተኛው በገሀድ ኖሮ አልፏል፤ድሮ በጎጃም ሽማግሌዎች ክፉ ሰው ሲራግሙ፥ “ ቦጋለ ያይኔ አበባ ስምህን ይጥራው “ይሉ ነበር ይባላል፤

ቦጋለ ያይኔ አበባ ስመጥር አልቃሽ ነበር፤ የጥንት አልቃሾች ቀላል ሰው እንዳይመስሏችሁ፤ በለቅሶ ወቅት የሚታየውን ትርምስ እና ጫጫታ ወደ ኪነጥበብ ትርኢት የሚቀይሩበት ተሰጥኦ ነበራቸው ::

ቦጋለ ያይኔ አበባ በወጣትነቱ ያገሩን መሬት አርሷል፤ እንዲሁም ያገሩን መሬት በእግሩ አዳርሷል፤ ወደ አልቃሽነት ሙያ እስኪገባ ድረስ ግን የረባ ስኬት አላገኘም ነበር፤ ይህንን በማስመልከት፥ እንደ ግለ-ታሪክ እና Cv በምትቆጠርለት እንጉርጉሮው እንዲህ ብሎ ነበር፤

“አርሼም አየሁት ፥
ነግጄም አየሁት
አልሰሰመረም ሀብቴ
አልቅሼ እበላለሁ እንደ ልጅነቴ “

ቦጋለ ያይኔ አበባ ከዘመናት ባንዱ ወግ፥ ደርሶት ሴት ልጁን ዳረ፤ እንጀራ ሆኖት የቆየው ሞት አሁን በሌላ ገጹ ተከሰተ፤ ሙሽሪት በሰርጓ በሳምንቱ ተቀጠፈች፤ እልልታው ወደ እሪታ የተቀየረበት ቦጋለ በተሰበረ ልብ ይቺን ውብ እንጉርጉሮ ወረወረ፦

“እንዲህ ያለ አምቻ፥ ክብሩን የዘነጋ
በፈረስ ሰጥቼው ፥ መለሰልኝ ባልጋ”

ኪነጥበብ ፥ አስቀያሚ መከራን ወደ ውበት መቀየር እንደምትችል ይቺ እንጉርጉሮ ምስክር ናት፤

ከሞት ሁሉ ቅስም ሰባሪው የልጅ ሞት ይመስለኛል ፤ ከወሎ የፈለቀች ከወዳጄ የሰማሁዋት ፥አንድ ጨዋታ ትዝ ትለኛለች፤ አያ ሙሄ የተባለ ገበሬ ልጁ ሞቶበት ፥ጎጆው በርንዳ ላይ ከርትም ብሎ ይቆዝማል ፤ ባለንጀራው አዋ ይመር አጠገቡ ተቀምጧል፤ አዋ ይመር ወዳጁን በቃል ማጽናናት በቂ ሆኖ አላገኘውም ፤ የወዳጁን ልጅ የቀሰፈውን ፈጣሪ ለመበቀል ስለፈለገ ፥ ጠመንጃውን አነጣጥሮ ወደ ሰማይ ተኮሰ፤

ተኩሱ በረድ ሲል አዘንተኛው አያ ሙሄ ወዳጁን እያየ እንዲህ አለ፤

“ካገኘከው ገላገልኸን፤ ከሳትኸው ግን አስፈጀኸን”🙂

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

01 Oct, 18:20


የህልሜ በር ቁልፍ
(በእውቀቱ ስዩም)

ከመንገዷ ሸሸሁ
በማትውልበት ዋልሁ
በማታመሽበት፤ ሰፈር ውስጥ አመሸሁ
ፎቶዋን አክስየ
ፊት የሌለው ምስል በላዩ ላይ ስየ፥

“ይደምሰስ ስራዋ
ይወድም አሻራዋ ፥
የሰደድ ነበልባል እንደበላው ሰፈር
የመታሰቢያዋ አመዱ ይሰፈር
ወግ ታሪኳ ያክትም
ከንግዲህ በሁዋላ
እንኳን ወደ ቤቴ፤ ወደ ትዝታየ፥ ድርሽ አትላትም”

ብየ ፎከርኩና አልጋየን አነጠፍኩ
የሰራ አከላቴን፥ እንደ ጃንጥላ አጠፍኩ
አበባ ይመስል ፥ጉልበቶቼን አቀፍኩ፤

ታድያ ብዙም ሳይቆይ፥ በእንቅልፌ ስረታ
ኮቴዋን አጥፍታ
እንደ መንፈስ ገባች
ከትራሴ ግድም ከተማ ገነባች፤

ነግቶ ብንን ስል ፥ ያ ሁሉ ሙከራ
ከንቱ እንደ ሆን ገባኝ ፤ ሳይገድሉ ፉከራ
ሳይጥሉ ቀረርቶ
የህልሜ በር ቁልፍ ፥ መዳፏ ላይ ቀርቶ::

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

20 Jun, 12:19


ምሽት በረንዳ ላይ
(በእውቀቱ ስዩም)

አገር ምድሩ መሽቶ
ሌቱ ምጣድ ሆኖ ፥ በኮከብ ተሟሽቶ
የጎዳናው መብራት ፥ጨለማው ላይ ሲገን
ከመስኮት አምልጦ ፥የወጣ ወጋንን
ሳር ቅጠሉን ሲያሳይ
አጥብቄ ስፈልግ ፥የእለት ያይኔን ሲሳይ
የሌት አይኔን ሲሳይ

በኩርማን ገላዋ፤ እራፊ ደርባ
የራሷ ሻጭ ሆና ፤ለሸመታ ቀርባ
በሌት ይፋ ሆና፥ በቀን ልትደበቅ
ያልቀጠረችውን ፥የምትጠባበቅ
አንዲት ሴት እያየሁ
አሰላስላለሁ ፤

“ አብረዋት ያደጉ፤ ብጤዎቿ ሁሉ
በድሜና በውበት እሷን የሚያክሉ
ተድረው እንደ ሴት፥ ተከብረው እንደ ሰው
የባሎቻቸውን ደረት ተንተርሰው
ፍቅር ሲያጣጥሙ
ወይ በንቅልፍ ሲሰጥሙ
ይች ወገን አልባ
የሌሊት አበባ
በቀትር ተኝታ ለውድቅት የነቃች
የቱን ፍሬ በልታ ለዚህ ፍዳ በቃች ?”

እያልሁ አስባለሁ፥



ደሞ ከደጃፌ ትንሽ ማዶ ርቆ
የመሸበት ለማኝ ፤ መንገዱ ዳር ወድቆ

በግልጥ ይታየኛል
“ ረፍትን ላክልኝ ፥ወይ እንጎቻህን ጣል
በራብ እና በንቅልፍ ሰው እንዴት ይቀጣል"
የሚል ይመስለኛል ፤

በረንዳ ላይ ቆሜ፥ በሌሊት ስምሪት
ከመስኮት በወጣ፥ የብርሀን ቅሪት
አይቼ ማልዘልቀው
ያገሬ ጎዳና የት ላይ ነው የሚያልቀው
መከራና ውበት የሚያፈራርቀው::

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

24 Apr, 10:25


ቀጣዩ ‘ስቴፕ”
(በእውቀቱ ስዩም)

እንደ ቀነኒሳ አይነት ልእለ-ሰብ ሰዎችን ስታይ የእድሜ መገስገስ አያስፈራህም፤ እድሜ ሆይ መውጊያህ ወዴት አለ? ብለህ ትፎክራለህ ፤

“ ቀነኒሳ አንበሳ “ ይላል ጀግና አሞጋሹ ጀግና ቴዲ አፍሮ፤ አንበሳ በምን እድሉ ነው ቀነኒሳን የሚስተካከለው ? አንድን አንበሳ በሀያ አመቱ በአጸደ ስጋ አታገኘውም፤ ካገኘኸው ጭርጭስ ብሎ፥ ጎብጦ ቁርበቱን እየላሰ ተኝቷል፤ ቀነኒሳ ግን በአርባ ሁለት አመቱ ማራቶን ያሸንፋል፤


ዋናው ጥያቄ- ለእድሜ ትገብራለህ ወይስ እድሜን ታስገብራለህ?” የሚል ነው፤

ርግጥ ነው እኔ በዚህ እድሜየ እንኳን ማራቶን ልሮጥ ውድድሩን በቲቪ ጨርሶ ለማየት ራሱ አቅምና ትግስት የለኝም፤ አንዳንድ ቀን፥ ከባለንጀሮቼ ጋር ኳስ ለማየት እቀመጣለሁ፤ በተቀመጥኩበት ሶፋ ላይ አራት ዙር ግልገል እንቅልፍ (ናፕ ) እተኛለሁ፤

በቀደም ከስንት ጊዜ በሁዋላ ጂም ሄድኩ፤ አሰልጣኙ ተቀብሎ ገና የስነልቦና ምክር እንኳ ሳይሰጠኝ “ ሀያ ጊዜ ቁጭ ብድግ ስራ “ አለኝ ፤” ቁጭ ማለቱ ላይ ችግር የለብኝም ብሮ ! ብድግ ማለቱ ላይ ግን እገዛህን እሻለሁ “ ብየው ፥ ትንሽ ወልመጥ ወልመጥ አልሁ ፤

ቀጠለና አስር ፑሽ አፕ አዘዘልኝ፤ አምስቱን ወገቡን እንደተመታ እባብ እየተቅመደምድሁ ሰራሁ፤ በተረፈች፥ ጉልበቴ ምንጣፉን እየሳምኩ ተነሳሁ፤ በመጨረሻ ሳልፈልግ ፥በርከክ ብየ ለወጫጫ ተራራ ሰገድሁ፤

ማጠቃለያው ላይ፥ አምስት ኪሎ ድምቤል አሸከመኝ፤

ከዚያ መስታውት ፊት ቆሜ ፥ ከክርኔ በላይ ያለውን ክንዴን ክፍል እየዳበስኩ ገመገምኩት፤
ብዙም ሳይቆይ አሰልጣኙ ከተፍ አለና፥

“አሁን አሟሙቀሀል፤ ቀጣዩ ስቴፕ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ” ሲል ጠየቀኝ፥



“ ቀጣዩ “ ስቴፕ”ማ ንቅሳት እሚሰሩ ሰዎችን ማፈላለግ ነው ዠለስ“

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

03 Apr, 15:33


የክረምት መባቻ ወግ

(በእውቀቱ ስዩም)

ወንድ ልጅ ግን በክረምት ገንዘብና ጺም አይጣ!

በነገራችን ላይ፥ ንግድ ባንክ ባለፈው ብር እንደ መስኖ ጠልፈው ያስቀሩ ሰዎችን ፎቶ መበተኑ በቂ አይደለም ፤ በፎቶው ላይ የሚታዩ ሰዎችን ለምንጠቁም ሰዎች የክረምቱን የሚያወጣ ጉርሻ ቢለቅልን አሪፍ ነው፤ ህግ የማስከበር ዘመቻውንም ያቀላጥፈዋል !

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ ጃንጥላ እሚይዝ ወንድ ፋራ ነው ብሎ ያወጀው ዠዝባ ማን ነው? ባለፈው ጃንጥላ ልገዛ ስጠይቅ ፥ ሻጩ “ለእናትህ ነው ለሚስትህ ?” ብሎ ጠየቀኝ ፤

" ለአናቴና ለሚስቴ በህየወት እንድቆይላቸው እሱን አራት ሄክታር ጃንጥላ ስጠኝ ፤
ሰገጤ ላለመባል የተነከረ ባቄላ መስየ ቤቴ እንድገባ ፈልገህ ከሆነ ትልቅ ስተት ሰርተሀል ፤
ቢመቸኝ ፥ እንኩዋን ጃንጥላ እጀታ ያለው ድንኩዋን እዘረጋለሁ ፤ “ልለው ፈልጌ ተውኩት፤

እሚገርመው፥ የሆነ ዘመን እርድና በሌላው ዘመን ላይ ስግጥና ይሆናል፤ ነዋይ ደበበ ’ ጥላ ይዤ ልከተልሽ?” የሚል ሁሉ ዘፈን ነበረው፤

እኔ ሲመስለኝ ወንዶች ጃንጥላ መያዝ የለባቸውም ብሎ የደነገገው ሰውየ “አስጠልይኝ “ በሚል ሰበብ ከሴቶች ጋራ መተሻሸት የሚፈልግ ይመስለኛል ፤

ጃንጥላ በመያዝ ራሳችንን ችለን እንቁም! ሳይፈቀድልን በሴቶች ራዳር ውስጥ አንግባ! አመሰግናለሁ!

ክረምት መባቻ ላይ ትዝ እምትለኝን የወዳጄን ገጠመኝ አካፍየ ምሳየን ላብስል፤

ከአያሌ አመታት በፊት ጌትነት እንየውና ጉዋደኞቹ ለአንድ የገጠር ቀበሌ ህዝብ መስክ ለይ ተውኔት ያሳያሉ፤ ህዝቡ መስኩን ከበብ አድርጎ ያያቸዋል፤ ተውኔቱ የታሪኩ አማካኝ ላይ ሲደርስ ዝናብ ማካፋት ጀመረ፤ ግማሹ ተመልካች ከተቀመጠበት ፥ተነስቶ እየተግበሰበሰ፥ ባቅራቢያ በሚገኘው ዋርካ ዛፍ ስር ተጠለለ፤ የኪነጥበብ ፍቅራቸው የዝናቡን ያስረሳቸው ሰዎች ብቻ ሜዳው ላይ ቀሩ፤ ትንሽ ቆይቶ በረዶ ብቻ ሳይሆን በራሪ ኮከብ የቀላለቀለ ዝናብ አካባቢውን ይወቅጠው ጀመር ፤ ተዋናዮች ከዚህ በላይ ለኪነጥበብ መስዋእትነት መክፈል አልፈለጉም፤ እየሮጡ ዋርካው ስር የተጠለሉትን ሰዎች ተቀላቀሉ፤

ከተጠለሉት ተመልካቾች መካከል አንድ ወዝ የጠገበ ከዘራ የያዘ ጎረምሳ ወደ ተዋናዮች እያየ

“ ጎበዝ ! ዛሬ ሰንጢ ይዘንባል እንጂ አምስት ብራችንን የከሰከስንበትን ትያትር መጨረሻ ሳናይ አንሄድም”

ይሄኔ ጌትነት እንዲህ አለ፤

“ በመጨረሻ! ሙሽራውና ሙሽራይቱ ወንድምና እህት መሆናቸውን ይደርሱበታል፤ አሁን በሰላም ወደ ቤታችሁ መሄድ ትችላላችሁ “

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

28 Mar, 18:25


ያንድ ምሽት ሀሳብ
(በእውቀቱ ስዩም)

ልማድ ሆኖበት፥ ሌቱ ቢገፋ
ምን ሊጠቅመኝ፥ ነው የማንቀላፋ
ህልም ሸክም ነው፥ ፈቺው ከጠፋ፤

ሳይጎድለኝ ለዛ
ሳያንሰኝ ውበት
የቀን ጨረቃ፥ ላይንሽ ሆኘበት፥
ቀልብን የማይስብ፥ የሳር ቀለበት
መወደዴ ብላሽ
ምኞቴ ዘበት፤

የአሻንጉሊት ላም፥ ጡት እንደማለብ
የፈረስ ሀውልት፥ እንደመጋለብ
ሲሳይሽ ፈልቆ፥ ጣት አያርስም
የትም ብትኖሪ፥ የትም አልደርስም፥

የሚፈሰውን አልፎ ገደቤን
-እንባየን ልሼ
ደረቴን ሰብሮ ፥ የሸሸ ልቤን
ቦታው መልሼ
በፍቅር ፈንታ ፥እረፍት ሸመትሁኝ
ቁርጤን አወቅሁኝ ፤

ለካ ሰው ቢማር፥
ከሊቅ፥ ከመጻፍ፥ ከኑሮ ከእድሜ
ቁርጥን ማወቅ ነው የእውቀት ፍጻሜ;:

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

17 Feb, 10:35


ነገረ አድዋ (ቁጥር 1)
(በእውቀቱ ስዩም)

በቀደም ጳውሎስ ኞኞ ስለ አድዋ የጻፈውን ስገርብ እንዲህ እሚል አንቀጽ አገኘሁ፥

“የአድዋ ጦርነት የተካሄደው በገናና በሁዳዴ ጾም ጊዜ ነው፤ ክርስትያን ዘማች በዚያንጊዜ እንደነበረው አጽዋጽዋም እስከሚቀጥለው ጀንበር መጥለቅ ድረስ ምንም አይቀምስም፤ ውሀ እንኳን አይጠጣም ነበር፤ ይህንን የተገነዘቡት አጤ ምኒልክ ጳጳሱን አቡነ ማቴዎስን “ጦርነት ላይ መሆናችንን ያውቃሉ፤ ሰራዊቱ በጦርነትም በጦምም ተደራራቢነት ጉዳት እንዳይደርስበት ያገኘውን እየበላ እንዲዋጋ ይፍቱት ፤ ቢፈለግ ከጦርነት መልስ እጾማል ቢሏቸው “ አቡኑ ግብጻዊ ነበሩና የኢትዮጵያ ጉዳይ ጉዳያቸው ስላልሆነ “አልፈታም “ ብለው እምቢ አሉ፤ ምኒልክም በዚህ አዝነው “እግዚአብሄር የየዋህ አምላክ ይፈርዳል “ አሏቸው፤"

(ጳውሎስ ኞኞ፥ አጤ ምኒልክ፥ ገጽ 172)

እስቲ በዚች አንቀጽ ትንሽ እንቆዝም!

ጳውሎስ ኞኞ በሀገር ፍቅር ስሜት የተቃጠለ ጸሀፊ መሆኑ ጥርጥር የለውም፤ ይሁን እንጂ ለአቡነማቴዎስ በትክክል የፈረደላቸው አይመስለኝም፤ አቡኑ በትውልድ ግብጻዊ ቢሆኑም ታማኝነታቸው ለሀይማኖታቸው እና ለኢትጵያ ንጉስነገስት መንግስት ነበር፤ ያም ሆኖ፥ ባጋጣሚ፥ ከሀይማኖታቸውን ሚቃረን የመንግስት ሀሳብ ቢገጥማቸው ለሀይማኖታቸው ማድላታቸው የመርህ ሰው ያስኛቸዋል እንጂ ከሀዲ አያስብላቸውም ፤ ስለዚህ ፥“የኢትዮጵያ ጉዳይ ጉዳያቸው ስላልሆነ” የሚለው የጳውሎስ ኞኞ ክስ ምንም መሰረት የለውም፤

በንጉሰነገስቱና በፓትርያርኩ መካከል ልዩነት አለ፤ ንጉሱ ካለው ሁኔታ አንጻር የሚያዋጣውን የሚመርጡ” ፕራግማቲስት” የፖለቲካ ሰው ናቸው፤ ሐቀኛ የሀይማኖት መሪ ከሆንህ ግን ሁኔታው ተለወጠ ብለህ የምትለውጠው አይኖርም!

በጊዜው ንጉሱ ሰይፍ ታጥቂያለሁ ብለው “ አንተ የምስር ነጫጭባ ! ትፈታለህ ብያለሁ ትፈታለህ ? “ ብለው አለመሳፈጣቸው እርፍና ይመስለኛል ፤ ቤተመንግስት በሰራዊቱ ተማምኖ በቤተክሀነት ውስጥ አለመግባቱ ስልጣኔ ነው፤

አጼ ምኒልክም ሆነ ተራኪው ጳውሎስ የበላ ወታደር ከጾመ ወታደር የተሻለ ይዋጋል የሚል አስተሳሰብ ነበራቸው ፤ ዘመናዩ ሳይንስ ግን ጾም የተሻለ ጉልበት እንደሚያጎናጽፍ ደርሶበታል፤ ስትጾም ለጽሞና፥ ለእርጋታ የሚያግዙ ሆርሞኖችን ማምንጨት ትችላለህ! አንዱ የምግብ ምርምር ሊቅ በቅርቡ ሲናገር እንደሰማሁት፤ “ ተራበ ተኩላ እና የጠገበ አንበሳ ቢታገሉ ተኩላው ያሽንፋል፤ የተራበ ተኩላ በሙሉ ሀይልና ቁርጠኝነት ነው የሚፋለመው፤ የጠገበ አንበሳ ግን ማረፍ እና መተኛት ነው የሚፈልገው “

ምናልባት የአድዋ ላይ አርበኞች፥ ከጠላቶቻቸው በሚልቅ ጉልበት እና ወኔ የተዋጉበት ምክንያት ስለጾሙ ይሆን? እንዲያ ከሆነ ደሞ አቡነ ማቴዎስም( ባለማወቅም ቢሆን) ለአርበኞች ተጨማሪ ጉልበት አለፋፍለዋል ማለት ነው፤

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

13 Feb, 13:58


እማማ አፀደ የሚባሉ ጎረቤት አሉን የእናቴ ጓደኛ ናቸው። እማማ አፀደ አመም አድርጓቸው ህመማቸው በባሰ ቁጥር እናቴን ጠሏት።

ይሰድቧታል ሌባ ናት ይላሉ።
መሰሪ ናት ይላሉ።
ልትገለኝ ትፈልጋለች ይላሉ።
መርዝ አበላቺኝ ይላሉ ። አትምጣብኝ ብለው ስሞታ ይናገራሉ ሌሊት እቤቴ ልትገባ ነበር ይላሉ ።

ሰው እንዳትመስላችሁ ይላሉ ። እናቴ ቤታቸው መሄድ አቆመች ።

ከቤት መውጣት እያቆሙ ግቢያቸው መዋል ጀመሩ ....

እናቴ እሷ መሆኗን አትንገሩ ብላ ፤ ምግብ ትልክላቸዋለች ። በእህታቸውን ልጅ ፤ ምን ጎደለ ጤናቸው እንዴት ነው እያለች ትሰልላቸዋለች...

ንዴት ሊገድለኝ ይደርሳል ። እቆጣታለሁ << ስምሽን እያጠፉሽ እየሰደቡሽ እየጠሉሽ አትተያቸውም ወይ?>> እላታለሁ!!

<<ጭንቅላታቸው እጢ ወጥቶባቸዋል እሱ ነው ትንሽ ቀየር ያደረጋቸው እንጂ ፤ እሳቸው እንኳን ሳልበድል ብበድላቸው እንኳን በክፉ አያነሱኝም>> ትለኛለች።

ምግብ ትልክላቸዋለች ። በእህታቸው ልጅ በኩል የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት መግዣ ከኛ ወስዳ ... ተበድራም ቢሆን ትገዛላቸዋለች ። እሳቸው ያቺ ምናምንቴ ፣ ድግምታም ያቺ ነጠላ እያሉ ጮክ ብለው እናቴን ሲሰድቧት ይውላሉ ።

ጠላኋቸው !!

አንድ ቀን ለምን ግን እንዲ ስምሽን እያጠፉ እየጠሉሽ እያልፈለጉሽ አልጠላሻቸውም? ብዬ እናቴን ጠየቅኋት።

<<ጓደኛዬ ናቸው! እዚህ ሰፈር ስመጣ እሳቸው ናቸው ያለመዱኝ ። እድር ያስገቡኝ ፥ የሌለኝን እቃ ያዋሱኝ ፥ የተቆረቆሩልኝ ፥ የአረሱኝ ፣የመከሩኝ...

እንዲህ አይባልም እያሉ መንገድ ያሳዩኝ እርሳቸው ናቸው ። ድንገት ታመው ነው የተቀየሩት ።ከሁሉም ጋር ነው መጣላት የጀመሩት እኔ ላይ ትንሽ ጠንከር አሉ እንጂ ...

በክፉ ግዜ እንኳን ወዳጅ ላይ ጠላት ላይ አይጨከንም!!

የጨዋ ሰው ልክ የሚታየው ሲጣሉት ነው ። በፍቅር ግዜ ሰው አይመዘንም ክፉ ግዜ ነው ሰው የሚያጠለው ....

አፀዱ እንዴት አይነት ጥሩ ሰው መሰሉህ ዛሬ ህመም ተጣብቷቸው እን'ጂ ። ስንት ቀን መሰለህ እጦት በሳቸው ሳብያ ከቤታችን የተባረረው ።
አፀደ ደግ 'ሩህሩህ ናቸው...

እናንተ ሳትወለዱ ማንም ሳይኖረኝ ነው ከኔ ጋር የነበሩት...

የአፀደ ውለታ አለብኝ !>>
© Adhanom Mitiku
@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

10 Feb, 18:08


ሴት አይቅናው !

ሄዱ አብረው ጊዜና እሱ
ወዴት ቆሙ የት ደረሱ ?
ማን ተጠጋው ?
ማን አወጋው?
ማን አለፈው ?
ማን አቀፈው ?

ይጨንቀኛል ....

የለሁበት በህይወቱ የለሁበት በመንገዱ
ይቃዠዋል ልቤ እብዱ

ምን ቤት ቤቴ ? ምን ቤት ጣሪያው?
የሚስለው ዙሪያ ገባው
ለሄደ ሰው ምን አገባው

ምን ቤት ልቤ ምን ቤት አይኔ እየሳቡ የሚያመጡት
ምን ይገዳል ምንስ ቢሆን ከእጅ ያወጡት??

እንጃ..!!

ብቻ..
የተኛበት እንዳይሞቀው
እመኛለሁ ሴት ባያውቀው
እመኛለሁ ሴት ባያቅፈው
ሄዋን ሳያውቅ እድሜ ቢያልፈው

እመኛለሁ ባይዳበስ
እመኛለሁ ባይታበስ
እመኛለሁ ለፍቅር ያለው ባይሳካ
እንኳን ገላው የፀጉሩ ጫፍ ባይነካ

ይጨንቀኛል ...

ቁርጥ አርጎ ለሄደ ሰው ልቤን ሐሳብ እየጠናው
እመኛለሁ በደፈናው
እመኛለሁ ሴት ባይቀናው...
.
.
.
ሴት አይቅናህ ..... 😞

ሊና አርጋው ✍️

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

03 Jan, 15:48


ግብይት
(በእውቀቱ ስዩም)
ሰሞኑን ለዲያስፖራ ወገኖቻችን አገራቸውን እንዲጎበኙ ጥሪ ተደርጓል፤ እኔ ለዲያስፖራ ወገኖቻችን ቦታ ለመልቀቅ ብየ ወደ አሜሪካ መጣሁ፤
ሰልስትና (ከሶስት ቀን በፊት) ዲሲ በእግሬ እየተወዘወዛለሁ፤ ዋይታውስ አጠገብ ስደርስ በብዙ ያለም ቋንቋዎች መሀል ጎልቶ የሚታይ የአማርኛ ጽሁፍ ተመለከትኩ፤ “ ፕሬዚዳንት ባይደን ሆይ ! የሚደረግብንን እያየህ ስለምን ዝም ትላለህ! “ የሚል መፈክር ነበር የጠበቅሁት፤ ጠጋ ብየ ሳየው “ የአላባ በርበሬ እዚህ ይገኛል “ የሚል ማስወቂያ ነው፤

ወደ ሱቁ ገባሁና ፥

“ደና ዋላችሁ?”

“I am good” አለኝ ፥ አንድ በደብረ ብርሀን ብርድልብስ ላይ የሳይቤሪያ ቡሉኮ የደረበ አበሻ፤

“ እስቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚሄድ አንድ ፈረሱላ በርበሬ መዝኑልኝ “፤

----------

መንግስቱ ሀይለማርያም " ሰው በላው ካፒታሊዝም " ቢልም እንኳ ያሜሪካ ካፒታሊዝም የቸርነት ገጽታም አለው፤ የሚበዘብዝህን ያህል እንድትበዘብዘው እድል ይሰጥሀል! ለምሳሌ የሆነ ልብስ ከሱቅ ገዝቼ አንድ ሳምንት ዘንጨበት ሳበቃ ፥ አልመጠነኝም ብየ ለሻጮች መመለስ እችላለሁ፤ ሳያንገራግሩ ገንዘቡን ይመልሱልኛል ፤

ይሄ አሰራር ኢትዮጵያ ውስጥ የሚጀመረው መቼ ነው?

ከጥቂት ጊዚያት በፊት ሽሮ ሜዳ ፎቅ ላይ ወደሚገኝ የባህላዊ ልብስ መሸጫ ሱቅ ጎራ ብየ ነበር፤

“ምን ነበር?” አለኝ ሻጩ!

“አንድ ጓደኛየ ከዚህ ቤት ቆንጆ የዶርዜ ሸሚዝ ገዝቶ ስጦታ ሰጥቶኝ ነበር”

“ የተባረከ ጓደኛ ነው ያለህ "

“ ምን ዋጋ አለው፤ ሰሞኑን ትንሽ ወፈር ስላልሁ ጠበበኝ “

“ ምንችግር አለው ታድያ !” አስቀምጠውና ስትከሳ ትለብሰዋለህ” ሲል መለሸ ሻጩ፤

“ መመለስ አልችልም?”

“ ምኑን ነው እምትመልሰው?”

“ልብሱን ነዋ”

“ ያንተን አንጋፋ ላብ የጠገበ ልብስ ተቀብየ ልሸጠው ነው ሙዝየም ላስቀምጠው?”
ሰውየው አንባረቀብኝ ፤

በጣም ተናድጄ ከሱቁ ወጥቼ አምስት ፎቅ ወረድኩ ፤ ታች ከደረስኩ በሁዋላ ሰውየው በረንዳው ላይ ሆኖ በፉጨት ጠራኝና ስዞር ፥

“ ተነጋግረን አልጨረስንምኮ “ አለኝ’

ከምኔው ሀሳቡን ቀየረ ብየ ወደ ላይ መወጣት ጀመርኩ፤ ፎቁ ሊፍት እንደሌለው ልብ ያልሁት አሁን ነው፤ በርግጥ ባህላዊ ልብስ ሻጩ ባህላዊ ፎቅ መምረጡ አግባብ ነው፤ እያንዳንዱን ደረጃ በምጥ እና በመራራ ትግል ከወጣሁ በሁዋላ እንደገና ሱቁ በር ላይ ተገተርኩ፤

“ እኔ እምልህ” አለ ሻጩ፥

“ እህ”

“ እህቴ የሚያከሳ አረቄ ትሸጣለች ፤ ቀብድ ከከፈልህ ላስመጣልህ እችላለሁ”

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

17 Dec, 16:05


ስፍራው እዚህ ላይ ነው
( በእውቀቱ ስዩም)

የተገናኘነው
ስፍራው እዚህ ላይ ነው፤
በጋዜጣ ቅዳጅ፥ መታ መታ አድርገን
አቧራውን ጠርገን
ከሰፈ ጀርባው ላይ
የተቀመጥንበት፤ አረጋዊ ድንጋይ
አካሉ በከፊል ፤ ወደ መሬት ሰጥሞ
እንደነበር አለ፤ የሳር ሻሽ ጠምጥሞ

ላልፎ-ሂያጅ ተመልካች፥ ፍቅር ለጎደለው
ምንም ነገር የለው፥
ቀልብን የሚያሸፍት
በሀያል አድናቆት፥ አፍን የሚያስከፍት ፤

በግርማ ሞገሱ ፥ተሪስት የሚጠራ
ጥንታዊ ሰገነት፥ አለት -ለበስ ጣራ
ተምዘግዛጊ ውሀ፤ ረጅጅጅም ተራራ
አቤት የሰው ጥበብ
አቤት የግዜር ስራ
የሚያሰኘ ድንቃድንቅ ፥ የለም ከዚህ ስፍራ፤

ለኔ መሳዩ ግን
ላንድ የፍቅር መናኝ
ወርቅ የሚሆንለት፥ ትቢያውን ቢዘግን
አንዲት የሳር ብናኝ
አንዲት ያፈር ቅንጣት
አመት የሚያወጉት፥ ታሪክ ነው ሚወጣት ፤

በምነት የተመካ
ተጓዥ ያገሬ ሰው
ወደ ኢየሩሳሌም፥ ወይም ወደ መካ
ቀን ቆርጦ ሲሳፈር፥ ወደ ተቀደሰው
እኔ ግን እዚህ ነው የምመላለሰው ::

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

11 Dec, 18:07


ወላጅ እናትህ - ድንገት ብትከዳህ
ያፀድቃል ያልከው - ሲኦል ቢነዳህ
ለፈውስ የዋጥከው - አጉል ቢጎዳህ
የእስካሁን ውሎህ
የእስካሁን ኑሮህ
ቅዠት ነው ቢባል
አስበኸዋል ?

አለህ ወይ ትከሻ ?
አለህ ወይ መሸሻ - ህመም ማስታገሻ ?

አለህ ወይ "ምናልባት"
ማረፊያ ምትሆንህ በዚያ ጭንቅ ሰአት ?

ሙሉ አለም አትስራ ፥ አበጅለት ክፍተት
ልክ ሆነህ አትኑር ... አክልበት ስህተት

ነፍስህ ይደናበር
ዝግ ልብህን ስበር
አፍርስ ግዳግዳውን
ለመስኮትና በር
ህይወት ፀጋ ስትቸር
ያኔ እንድትቀበል ።

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

18 Nov, 15:29


አየር ላይ
(በእውቀቱ ስዩም)

ትናንት ከፓሪስ ወደ አዲስአበባ የሚበረውን የኢትዮጵያ አውሮፕላን ተሳፈርሁ፤
የአውሮፕላኑ ነጂ ከፊትለፊቱ የተደቀኑትን የግብጽ እና የሴኔጋል አውሮፕላኖች ደጋግሞ “ ክላክስ “ በማድረግ ከፊትለፊቱ ገለል እንዲሉ ካደረገ በሁዋላ ለማኮብኮብ ተዘጋጀ፤

ሰማይ ላይ እንደተደላደልን ካፒቴኑ ፤ “ ክቡራን እና ክቡራት መንገደኞቻችን ዛሬ ወደ አዲስአበባ በምናደርገው በረራ፤ በመካከላችን አንድ የተከበሩ እንግዳ ይገኛሉ” በማለት አወጀ፤
እሰይ! ኢትዮጵያ በመጨረሻም ለልፋቴ የሚመጥን ክብር ሰጠችኝ፤ ሀብቱ እና ንብረቱ ደግሞ ቀስ ብሎ ይደርሳል! “ ብየ አስቤ ደስ አለኝ፤

ካፒቴኑ ግን “ እኒህ የተከቡሩ እንግዳ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ሳህለ ወርቅ “ ብሎ በመጀመር የደስታየን እድሜ አሳጠረው፤

በግሪክ አየር ክልል ውስጥ እንደገባን አንድ ወጣት የበረራ አስተናጋጅ ቀረበኝና በትህትና
“ እንኩዋን ደና መጣህ! ምን እንጋብዝህ አለኝ?”

“ አመሰግናለሁ! ግን አትቸገር !”

“ የምትፈልገውን ንገረኝ”

‘ ከተቻለ ወደ ፈርስት ክላስ ብታሻግሩኝ ደስ ይለኛል"

“ ፈርስት ክላስ እድሳት ላይ ሲሆን ቢዝነስ ክላስ ደግሞ ሙሉ ነው”

“ መንገድ ላይ እሚወርድ ወይም እሚዘል የለም?”

“ርግጠኛ አይደለሁም”

“ እሺ! ቀይ ወይን አምጣልኝ '፤ ሞቅ ሲለኝ ኢኮኖሚክ ክላስ ውስጥ እንደተቀረቀርሁ እረሳለሁ"

ብዙ ሳይቆይ አንዲት ትንሽየ ጠርሙስ ወይን እና ሰሀን ሙሉ ቆሉ አቀረበልኝ
የአውሮፕላኑ ተሳፋሪዎች በግርምት ያዩኛል፤ የንጉስ ልጅ ሳልመስላቸው አልቀረሁም! ቆሎውን አፈፍ አርጌ አጠገቤ የተቀመጡትን እንግሊዛዊና ፈረንሳዊ ፥

“ Let us mange “ አልኩዋቸው ( “ እንብላ “ ማለቴ ነው)
ፈረንሳዩ፤ “ የተባረከ ይሁን” ይለኛል ብየ ስጠብቅ፥

“ ከሌላው መንደኛ ሁሉ ለይቶ ወይን ያቀረበልህ ለምንድነው ?” ሲል አፋጠጠኝ፤

“ ታዋቂ ሰው ስለሆንኩ ነው”

“ እውቅናህ በምን ዘርፍ ነው?”

“ ታዋቂ ጸሀፊ ነኝ ልልው አሰብኩና ጽሁፍህ ስለምንድነው ፤ እስቲ ተርጉምልኝ እያለ ሊያደርቀኝ ታየኝ፤

“ታዋቂ የወይን ቀማሽ ነኝ ዠለስ” አልሁት!

ፈረንጁ በጣም ተደንቆ ፓስፖርቱ ላይ አስፈረመኝ ፤

ከራት በሁዋላ ከፊትለፊቴ ባለው ስክሪን ፥ በሞንጎልያ አርብቶ አደሮች ዙርያ የሚያጠነጥን ዶክመንታሪ ማየት ጀመርሁ፤ በመሀል ግን ወደ ቢዝነስ ክላስ አካባቢ፥ የበግ ጩኸት የሰማሁ መሰለኝ! ወድያው አስተናጋጁዋን ጠርቼ “ ለእኛ ሩዝ በቲማቲም ቅንጣቢ አቅርባችሁልን ለፕሬዚዳንትዋ ሙክት ማረዳችሁ ከህገ መንግስቱ አንጻር አግባብ ነው ? “ ብየ ልሞግታት ተሰናዳሁ፤ ወድያው ግን የበጉ ጩኸት ፥ ከማየው ዶክመታሪ እንደመነጨ ተገንዝቤ አደብ በቅናሽ ገዛሁ፤
( ትግስት ካለዎት የዙረቱን ታሪክ በቀጣይ አቀርብልዎታለሁ)

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

30 Oct, 21:40


ከአንዲት ቆንጆ ልጅ ጋ ነበርኩ። መኪና ውስጥ ነበርን ፒዛ እየጋበዝኳት አስተናጋጁ ሲያልፍ በእጄ ቢል እንዲያመጣልኝ ነገርኩት

ቢል ይዞ መጣ

እያየኝ ከፊት ከኃላ ኪሴ አውጣጥቼ ሂሳብ ከፈልኩ ...
ሄደ
መልስ መጠበቅ ጀመርኩ አልመጣም ጠበኩት አልመጣም ተበሳጭቼ ክላክስ አስጮህኩ

(ሱሰኛ ይመስላል ፣ የቀረውን ገንዘብ ለማስቀረት አስቦ ነው ፣ ጉርሻ በፍቃደኝነት የሚሰጥ እንጂ በብልጠት የሚዘገን አይደለም ፣ ሲቆይብን ሰልችቶን እንድንሄድ ነው )

ያስጮኩትን ክላክስ ሰምቶ መጣ

"መልስ ስጠን እንጂ ጌታው "አልኩት

"የሰጠኸኝ አራት መቶ ነው ሂሳቡ ደሞ አራት መቶ ሰላሳ አምስት ብር ነው "አለኝ ( ስበረብር ስላየኝ የለው ይሆናል በማለት ተሳቆ ነው እንዳልገረጣ ይጎላል ያላለው )

ከሌለህ ብዬ ነው አይነት ፊት አሳየኝ ። አንዳንድ አድራጎት የሚያገዝፈው አደራረጉ ነው ።

ይቅርታ ቢሉን በደንብ ስላላስተዋልኩት ነበር።
በጣም አመሰግናለሁ አልኩት

እንደገና ኪሴን በርብሬ ድፍን ሁለት መቶ ብር ሰጠሁት እንዲመጣልኝ እንዳልቸኮልኩ እንዲሄድልኝ ቸኮልኩ
መልስ ሊያመጣልኝ ሄደ

ሳይነግሩን ለዋሉልን እየነገርን መዋል ነውር ነው አይደል ?
ሳይመጣብኝ ሄድኩኝ ።
© Adhanom Mitiku

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

27 Oct, 17:33


ተማጽኖ
(በእውቀቱ ስዩም)

አቤቱ
የጠፈር ባለቤቱ
በየብስ ነህ፥ በባህር፥ በምድር ነህ በሰማይ?
በቅጡ ለማናውቅህ ፥ በድንግዝግዝ ለምናይ

አቤቱ የፍጥረት አባት
ከሰማኸኝ ምናልባት
ኮረብታውን ሜዳ አድርገው ፤ ኮረኮንቹን አለስልሰው
የፎይታየን አድራሻ፥ ርቀቱን ቀንሰው
አልልህም!

ጽናት ስጠኝ ፤ ብርቱ አድርገኝ! በየርምጃው እንዳይደክመኝ
ከቀንበሮች ሁሉ መርጠህ፥ ምችለውን አሸክመኝ

አቤቱ! የጠፈሮች ሁሉ መስራች
አፈራርቀህ የምትሰጥ፥ መርዶና የምስራች !
ተወስነህ የማትገኝ ፤ በጊዜና በቦታ
ወሰን የሌለህ ዝምታ
እኔ ልጅህ-ሲመቸኝ ፤ ሲመቸኝ አማኝ
ባይመችህም ስማኝ

ካደፈጠው እዳ ሁሉ፥ በየበስ፥ ባየር በቀላይ
ከአውሎ ነፋስም በላይ
ከመሬት መራድም ይልቅ
ሰው ነው ሰውን ሚያሳቅቅ
ሰው ነው የሰው አደጋ
ደግሞ በሌላ ገጹ፥ ሰው ነው ለሰው ልጅ ጸጋ
ከስጦታው አካፍለኝ ፥ ካደጋው አስመልጠኝ
አልሳሳት አልልህም፥ የሚታረም ስህተት ስጠኝ !

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

21 Oct, 18:36


አባቴ ድሃ ታግሎ ኗሪ ነበር ። ነፍስ እስካውቅ የሆነ ኮት ነበረው ፤ ዘወትር ነበር የሚያደርገው ፤ እሱን ኮት ሳይለብስ ከመንገድ ባገኘው የማልፈው ሁላ ነው የሚመስለኝ ።

ረጋ አባባሉ የሞላለት ያስመስለዋል ።
በትንሽ በትልቁ አይናደድም ፤ በትንሽ በትልቁ አይመክረኝም ። ከሰው ጋ ሲጣላ አጋጥሞኝ አያውቅም ።

ሰላማዊ ሰው ነው ፤ ሁሉንም ሰው በሙሉ ስም ነው የሚጠራው እኔንም ጭምር ። እናቴን ግን ያቆላምጣታል ። እሷ ጋ ሲደርስ የሚሆነው መሆን ለየት ይላል ፤ ይቀልዳል ፣ ያሾፍባታል ግንባሯን ይስማታል ።

አጠገባችን ላሉ እጅግ ከእኛ የበለጠ ደሃ ለነበሩት እማማ አዛሉ እና ከእኛ ቤት ፊት ለፊት ሰፊ ትልቅ ግቢ ላላቸው ለዲታው ጋሽ ይልማ የሚሰጠው ሰላምታም ተመሳሳይ ነው።

አባቴ ችግር ሲያወራ አይቼው አላውቅም ፤ ዝም ብሎ የቻለውን ያደርጋል ፤ ምን አልባት ለእኔ ማውራት አያበድረኝ ፣ አይሞላልኝ ብሎ ይሆናል እንዳልል ስራ ላለው ለታላቅ ወንድሜም እንኳን አያወራም ።

ስራ በያዝኩ በሶስተኛ ወሬ በአንዴ አራት ሙሉ ልብስ ገዛሁለት ። ደስ አለው በጣም ።
እጄን ይዞ
አትጣ
ሞገስ ልበስ
የአንተ የሆነ ሁሉ ይባረክልህ ብሎ መረቀኝ

በአራተኛው ቀን ........ከገዛህልኝ ሁለቱን ሙሉ ልብስ ለወዳጄ እና ለበሪሁን መስጠት ፈልጌ ነበር አለኝ (ወዳጄ እና በሪሁን ወንድሞቹ ናቸው)

ቅር ይልህ ይሆን ብሎ አይን አይኔን አየኝ

አጠያየቁ አስተያየቱ የሆነ የሚያሳዝን ነው ፤ አንጀቴን በላው

ከእነሱ ጋ በጋራ መዘነጥ ፈልጎ ከእነሱ ተለይቶ ላለመድመቅ ነው መሰለኝ

ሌላ ቃል ስላጣው አይ ጋሼ ብዬ እጁን ሳምኩት!!!
Adhanom Mitiku

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

13 Oct, 21:39


ያፍቃሪው እርግማን
(ባሮክ)

አንቺ     ፍቅር የማይገባሽ
           ጠግቧይደር ልበሽ
            ሰላም ካንቺ ይራቅ
           በልብሽ ሰው ይሳቅ
ከእይምሮሽ በልጦ ደመኛሽ ይራቀቅ
ክህደት በዝቶበት ልብሽ ሁሌ ይሳቀቅ
መውደዴን ለመንገር በደወልኩልሽ ስልክ
አስቀምይሽኛል ነግረሽኝ እስከ ልክ
ባንቺ ለቆሰለው ለልቤ ክህደት
ይሁዳን አፍቅሪው ውረጅ ከሰገነት
ተቃጥሎ ላረረው ለሚስኩኑ አናቴ
ትሁንብሽ እሳት ያቺ ምስኪን ቤቴ
እንባዬ ጎርፍ ይሁን ይውሰድሽ ጠራርጎ
ስላስካፋሽ ልቤን ቢሆንልሽ በጎ
     ኪሴን ላራቆትሺው
እቆያለው ብለሽ ጥለሽኝ ለሄድሽው
እጣፋንታሽ ይሁን ከኩዬችሽ ማነስ
ፈገግታሽ ተገፎ እምባሽ በጥፍ ይርከስ
         ካለሽ ጋር አትርጊ
ቅዥ ቅዥ ይበል ልብሽ ከቶ አትረጋጊ
ሺ ይናፍቀሽ በቀን
ልብሽ በሰው ይብገን
በኔ ላይ ዶልቶ ልበሽ ስላሴረ
በረከት ጠፋበት ካፌ እርግማን ቀረ
ስላስጠላሽ መዋል መኖር ከኔ ጋራ
ችግር ይጠፍንግሽ ይብዛብሽ መከራ
በዋልንበት ቦታ በኖርንበት አብረን
ልብሽ ስለጠላኝ ሳንጣጣም ቀረን

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

13 Oct, 21:27


ከእለታት አንድ ማታ!
(በእውቀቱ ስዩም)

ነግቶ፥ ተነሳሁኝ ካልጋየ
ከሰገባው የሚመዘዝ ፤ የንጉስ ሰይፍ መስየ
የሚያብረቀርቅ ፊቴን
የተትረፈረፈ ጉልበቴን
ያዝኩና ከቤቴ ወጣሁ
ቡናየን በደስታ ጠጣሁ፤


የማለዳ ቡናየ ጢስ
እንደ ንግስት እሌኒ ደመራ
ወደ ምኞቴ አቅጣጫ ፥ ልቦናየን ሲመራ
ሺህ እቅዶች ነድፌ
ለሺህ ትግል ተሰልፌ

እምነት ኖሮኝ ፤ ቁና ሙሉ ሰናፍጭ ያክል
ከስጋጃ ልቆጥረው፥ የመንገዴን መሰናክል
ለድል ተሰናድቼ
ደረቴን ለመዳልያ፥ ኪሴን ላዱኛ አጭቼ
ጅንን እንዳልኩ፥ እንደኮራሁ
ወደ ኑሮ ተሰማራሁ፥

ከዚያ ትንሽ ቆይቶ
የሰከነው ጎዳና፤ በትርምስ ጨቅይቶ
እንቅፋት ከየቤቱ ፥ እንደ ጥራጊ ወጥቶ
አሳር እና አሳርኛ ፥ በየርምጃው ተሰጥቶ
ሳፊው አየር ተበርዞ
የኑሮ ሰልፍ ረዝሞ፤
ወረፋው ተበውዞ
ደረስሁ ስል እየጀመርሁ
በርምጃየ ጣልቃ መሀል፥ የምቧይ ጡቤን እየከመርሁ
የምችለው ባይሳካ፥ የማልችለውን ሞከርሁ::

ከዚያ መሼ
የተረፈ ተስፋየን ፤ እየቀበርሁ አፈር ምሼ
ድምጤን አጥፍቼ አነባሁ፤
እንደ ሰይፍ ተመዝዤ ፥ እንደ ቀንዳውጣ ገባሁ ::

@WAS143
@WAS143

ጦቢያ የግጥም መድብል

12 Oct, 17:21


አለሁ እንደ ሾላው
(በእውቀቱ ስዩም)

በገዛ ጆሮና ፥ በገዛ አይኖችሽ ላይ
ሙሉ ስልጣን ያለሽ
ከቶ እንደምን አለሽ?

አለሁ እንደ ሾላው
እንደ ወፍ መነሻው
እንደ ወፍ መሸሻው
ጸሐይ እየሞቀ ከመተንፈስ በቀር፤ ሌላ እንደማይሻው፤

መኖር ብቻ ሲሆን ፥ የሰው ልጅ እቅዱ
በሲኦልም ቢኖርም፥ አይቀርም መልመዱ
እኔም ከመበላት፥ መብላት ይሻል ብየ’
‘ፍሪደም ‘ ቢርቀኝ፥ ፍሪዳየን ጥየ
ነጻነት ቢርበኝ፥ እየበላሁ እህል
አለሁ ይህን ያህል ፡ ፡

( ከ"የማለዳ ድባብ " የተወሰደ)

@WAS143
@WAS143