የልባም ሴት አገልግሎት @lebamsetministry123 Channel on Telegram

የልባም ሴት አገልግሎት

@lebamsetministry123


🎯ሴቶች ልባም ሴት ወደ መሆን ራሳቸውን እንዲያሰለጥኑ የሚረዳ መንፈሳዊ ቻይናል ነው።

👁ራዕይያች ልባምነትን በስፍራው ሁሉ መግለጥ ነው

🔆የምንሰጣቸው አገልግሎት
✔️Training ➻ስልጠና
✔️Counseling ➻ምክር
Prayer ➻ጸሎት

🔆አገልግሎቱን ለማግኘት👇
@Ashenafiwinner

የልባም ሴት አገልግሎት (Amharic)

ልባም ሴት አገልግሎት ለሴቶች በመሆን ራሳቸውን እንዲያሰለጥኑ መንፈሳዊ ቻይናል ነው። ይህ አገልግሎት ልባም ሴትን ከክርስቶስ ጋር ስራ ምልክት ያለውን በመገባት በሚሆኑት አለያቾች ለማውጣት ያግዛል። ይህም የምንሰጣቸው አገልግሎት መፈናከልናን እና ምሕረታን ይስጥልናል። ከመስራትዎ ጋር እና ማለት ከክርስቶስ ጋር እንስማማለን ይህን እና አስከፊልን ከሆነ በመገኘት እና ከሰማያት ሌሎች ትምህርቶች ጋር ካሉት የህጻናት ደህንነት ጋር በአገልግሎቱ በመገኘት እና የአድራጎት በጎ ሀሳብ እናትን ያረጋል። ለማስጠንቀቂያ አብዛኛና የልክ ሰዩቶችን እቃዎች በመጠቀም ገራሚና ህጻናትን ለመያዝ ይህንን አገልግሎት እና ጭምቱን ለማግኘት ይጫኑ። እባኮትን @Ashenafiwinner ን ማስጠንቀቂያ ያግዛል።

የልባም ሴት አገልግሎት

16 Feb, 06:19


    ምሳሌ ምዕራፍ አምስት

       ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧

የልባም ሴት አገልግሎት

15 Feb, 18:31


ምሳሌ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሌም ጆሮህን አዘንብል።
²¹ ከዓይንህ አታርቃት፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃት።
²² ለሚያገኙአት ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና።

       ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧

የልባም ሴት አገልግሎት

15 Feb, 05:37


    ምሳሌ ምዕራፍ አራት

       ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧

የልባም ሴት አገልግሎት

14 Feb, 18:47


ምሳሌ 3

⁵ በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤
⁶ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።

@lebamsetministry123
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

14 Feb, 06:29


    ምሳሌ ምዕራፍ ሶስት

       ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧

የልባም ሴት አገልግሎት

13 Feb, 10:07


“ጥንቃቄ ይጠብቅሃል፥ #ማስተዋልም_ይጋርድሃል፥”
— ምሳሌ 2፥11

የልባም ሴት አገልግሎት

13 Feb, 03:52


    ምሳሌ ምዕራፍ ሁለት

       ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧

የልባም ሴት አገልግሎት

12 Feb, 20:09


“የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።”
— ምሳሌ 1፥33

የልባም ሴት አገልግሎት

12 Feb, 18:42


    ምሳሌ ምዕራፍ አንድ

  ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧

የልባም ሴት አገልግሎት

12 Feb, 17:16


➻ዛሬ የምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጀምረናል‼️
#አንችሳ

ያልጀመራችሁ ጀምሩ
💫ምዕራፍ አንድ ጥናት

“ጠቢብ እነዚህን ከመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል።”
— ምሳሌ 1፥5

የልባም ሴት አገልግሎት

11 Feb, 19:17


ሰላም የተወደዳችሁ ይህ የልባም ሴት አገልግሎት tiktok account ነው
ገብታችሁ Join እና Share አድርጉ🙏

https://vm.tiktok.com/ZMkGhySdP/

የልባም ሴት አገልግሎት

10 Feb, 05:15


#Day 7

👑ልባም ሴት
#ለፈለጉዋት ሁሉ #አትገኝም

➻ልባም ሴት ለማን ለምን መገኘት እንዳለባት ጠንቅቃ ታውቃለች‼️

👑ልባም ሴት
#ለምክርና_ለመፍትሄ ትፈለጋለች።

➻Story ላይና ለጋደኞቻችሁ Share አድርጉላቸው🙏

@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

09 Feb, 05:00


#Day 6

👒ሴት አለች 👑ልባም ሴት አለች

#የሴትነት ልኩዋ ሴት መሆን ብቻ ሳይሆን #ልባም_ሴት መሆን ነው‼️

#ልባምነት በመወለድ ሳይሆን በማስለመድ ነውና ራስሽን #ልባም_ሴት ለመሆን አስለምጅ።

➻Story ላይና ለጋደኞቻችሁ Share አድርጉላቸው🙏

@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

08 Feb, 04:17


Day 5

✍️ብዙ ሰዎች ዋጋ መክፈል በሌለባቸው ጉዳይ ላይ ዋጋ ስለምከፍሉ ዋጋ መክፈል ያለባቸው ጉዳይ ላይ  ደግሞ ዋጋ መክፈል ያቅታቸዋል ከዚህም የተነሳ ሕይወታቸው ሳይለወጥ ይኖራል‼️

➻ልባም ሴት ምን ላይ ዋጋ መክፈል እንዳለባት ጠንቅቃ ታወቃለች።

➻Story ላይና ለጋደኞቻችሁ Share አድርጉላቸው‼️

@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

07 Feb, 16:03


👉ምን አይነት ቻናል ይፈልጋሉ? ‽🤔

👉What kind of channel do you want? ‽🤔

👉Chaanaalii akkamii barbaadda? ‽🤔
wave @seer_lewi

የልባም ሴት አገልግሎት

07 Feb, 14:33


🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯
ክርስቲያን የሆነ ሁሉ መቀላቀል ያለበት  ተወዳጅ መንፈሳዊ ቻነል ነው
👇👇👇👇👇 join ያድርጉ
➨Wave ለመግባት የምትፈልጉ
👉ከ5K በላይ Subscriber ያላችሁ
📥inbox 👉 @seer_lewi
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

የልባም ሴት አገልግሎት

07 Feb, 05:21


Day 4

ልባም ሴት ነገሮችን ሁሉ ከእግዚአብሔር ቃል አንጻር ትመለከታለች👁

➻Make it story & Share for friends.

@Lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

06 Feb, 16:55


👑   ዋና ሁነኝ 🧎‍♀

የእድሜ ቀናት ሲጨምሩ ስላቀቅ ከህፃንነት አለማወቅ ርቆኝ ሲሄድ ያጠበኩት ከልጅነት
የፈለኩት ዋጋ ሲያጣ ያገዘፍኩት ሲኮስስብኝ በዘመኔ ሁሉ አንተ ግን ዋና ሁነኝ

ዋና ላርግህ ከእልፎች በላይ
ኑዋሬ ሁን ፊትህን እስካይ
ይከልከል ስጋና ደም
አንተ አውራኝ ከአርያም
ዋና ላርግህ ዋና ሁነኝ
እኔ አልታይ ሲቻል አጥፋኝ

ዋጋ ልስጥህ እንዲገባህ እንደ ልክህ
እንደ ልጅህ ልኑር ምሳሌህ ይብዛ
መልኬ ይጥፋ ከፊቴ ላይ አንተው ውዛ
ውልደቴ ይፍጠን በመንፈስ የገነነ
ባላደራህ ይላቅ ወላፈን የሆነ

ይወለድ ይደገም ዋና የሆንክለት አዲሱ አዳም የዘመኔ ጳውሎስ የዘመኔ ኢሳያስ ለራስህ የሚኖር በህላዌ ሚፈስ
የዘመኔ ዮሐንስ የዘመኔ ማርያም
ደስታ እንዲሆን በምድር አርያም

ዋና ላርግህ ዋና ሁነኝ
አንተን ልወቅ እንደልቤ አስረዳኝ
የደስታዬ ጥጉ የሀዘኔ ጥልቀት
አብሮነትህ እንዲሆን የአንተ መገኘት
ልጅነቴ አልቆ ወደ አንተ ልጠጋ
እንዲገባህ ልኑር እንደ ከፈልክ ዋጋ

🧎‍♀🧎‍♀🧎‍♀🧎‍♀🧎🧎🧎🧎‍♀🧎‍♀🧎🧎

  ሳምሪ

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

06 Feb, 04:46


Day 3

በሌሎች ላይ ከመፍረድ ይልቅ #በራስሽ ጉዳይ ላይ #እያተኮርሽ ከሆነ #አስተዋይ ሴት ወደ መሆን እየመጣሽ ነው።

➻Story ላይና ለጋደኞቻችሁ Share አድርጉላቸው‼️


@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

05 Feb, 05:57


Day 2 join Challenge
➻make Story & Share it

የልባም ሴት አገልግሎት

04 Feb, 04:18


➻Profile challenge ጀምረናል #ተቀላቀሉን 👇 ከስር ያለውን Post story ላይ በማድረግና ለወዳጆቻችሁ Share በማድረግ አብራችሁን ተሳተፉ‼️

የልባም ሴት አገልግሎት

03 Feb, 13:52


ስላም ይብዛላችሁ የተወደዳችሁ የልባም ሴት አገልግሎት ቻናል ተከታታዮች

በአገልግሎታችን እየተጠቀማችሁ እንደሆነ ከብዙዎቻችሁ እየሰማን ነው።

👇ከማክሰኞ እስከ ሰኞ ድረስ አንድ Profile Challenge ስለሚንጀምር እድትቀላቀሉን በፍቅር እጠይቃችኋለን

➻ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ እስከ ቀጣይ ሳምንት ሰኞ ይቀጥላል‼️

➻ራእይያችን
#ልባምነትን #በስፍራው_ሁሉ_መግለጥ ነው‼️

የልባም ሴት አገልግሎት

01 Feb, 17:24


አባት ሴት ልጁን የመከረው #ምክር
➻ክፍል
#ሁለት

☞አበድኩ አፈቀርኩ ብሎ ኃላ የጥላቻ ቁንጮ የሆነውን አሲድ ከሚደፋ ወንድ ጋር ህብረት አታድርጊ አሲድ ባይደፋም  በእርኩሰቱ  ወደ ሲኦል የሚመራሽ ከዚያ ይብሳልና ተጠበቂ !
☞ከማታውቂው መልአክ የምታውቂው ሰይጣን ይሻላል እየተባለ ከሚወራ ተረት ራቂ  ለሞትና ለጥፋት የሚያዘጋጅ ነውና።
☞ ይልቅ ለፈጠረሽ አምላክ ለእግዚአብሔርን የተሰጠ እውነተኛ ወንድም ከእግዚአብሔር እጅ ለመቀበል ጸልይ ከአምላክሽ ጋር የጠበቀ ሕብረት ይኑርሽ ! በጸሎት በአምልኮ በቃል ጥናት በመንፈስ ቅዱስ ሙላትና ምሪት የተቃኘ ሕይወት ይኑርሽ !
☞ የተፈጠርሽበትን ዓላማ ለማሳካት ጌታን በሚያስከብር ሕይወት የአገልግሎት ጸጋሽን በመለየት አገልግይ!
☞ የሚገርመው ጌታ በውስጥሽ ያስቀመጠው የሚገርም የተዳፈነ ፀጋ አለሽ በጸሎት በቃሉና በመንፈሱ ሙላት ይገለጣልና ቀድሞ ከነበረሽ ይልቅ በጌታ ፊት ወድቆ የመጮህ ጊዜ ይብዛልሽ ! 

☞ጸጋው በተገለጠ ጊዜም ለሰጪው ክብር በማብዛት በስርዓት ወደ መድረክ ይዘሽው ውጪ ለብዙዎች መዳን ምክንያት ትሆኛለሽና !
☞በትንቢት ቃል አትታሰሪ/ትዳር/ አትመስርቺ ለነብይ የነገረው አባትሽ እግዚአብሔር ከሆነ ላንቺ በቀጥታ ይነግርሻል ልጁ ነሽና እንደ ነጎድጓድ የሚነገር ልሳን አትፍሪ አትደንግጪ !

☞አንቺ ከመውለድ ልጅ ከማሳደግ ንብረት ከመሰብሰብ ያለፈ መለኮታዊ ፕሮግራም ያለብሽ በደሙ የተገዛሽ ዕንቁ ልጁ ነሽ !
☞ የአምላክሽ ዋና ዓላማና ግብ ማግባት ብቻ አይደለም ለዘላለም ሕይወት ክብር በክርስቶስ መመረጥሽ እንጂ !

በምድር ከሚሆንልሽ እና ከሚደረግልሽ ያለፈ ክብር አለሽ !
☞ የሰርጉ ሆታ ጭፈራ እልልታና ሽብሸባ የአንድ ቀን ነው። በክርስቶስ የተዘጋጀው ክብር ግን የዘለዓለም ነው !
☞  በአምላክሽ የታሰበልሽን ግብና የተሰጠሽን ተስፋ አስቢ !
☞በጊዜው የሚመጣ ክብርሽ የሚሆንልሽ የትዳር አጋር ዘውድ የምትሆኚለት ወንድ በእግዚአብሔር እንደተወሰነልሽ አስቢ፤
☞☞☞ይህ ከሆነ በእውነት ልባሟ ሴት አንቺ ነሽ ! ተባረኩልኝ።


▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

29 Jan, 18:05


➻አባት ሴት ልጁን የመከረው #ምክር‼️
➻ክፍል
#አንድ

   በምድር እንድትኖሪበት የተሰጠሽን ሕይወት ዳግመኛ ተመልሰሽ አትኖሪበትም የተፈጠርሽበትን ዓላማ ከፈጠረሽ አምላክ ጠይቂ ! በተሰጠሽ ዘመን ለፈጠረሽ አምላክ ፈቃድ ተገዢ !
☞ሴት ልጅ ውድ ነች ርካሽ ብትሆን ለውዷ ቤተክርስቲያን በምሳሌ አትሰየም። በእግዚአብሔር ላንቺ የተመዘነው ዋጋ የክርስቶስ ደም ነው። ራስሽን ማየት ያለብሽ እግዚአብሔር በሚልሽ እንጂ ሰይጣንም፣ ሰውም፣ ሁኔታም፣ በሚገልጽሽ ማንነት አይደለም። በእግዚአብሔር እንተወደደች እንደ ውድ ዕንቁ ሴት ራስሽን ቁጠሪ ፤
☞ እግዚአብሔር በልጁ ሞት ሕይወት የሰጠሽ የከበርሽ ልጁ ነሽ  !
☞ እግዚአብሔር በዓላማ ፈጥሮሻል !!
☞ እግዚአብሔር ለአላማ ፈጥሮሻል !!
☞  ከእግዚአብሔር ሐሳብ ወደ ግራም ወደ ቀኝም እንዳትይ ተጠንቀቂ !
☞ በሰይጣንና በሰው የሚሰጥሽን መደለያ ፈጽሞ አትቀበይ ወጥመድ ነውና !
☞ ክብርሽ ስኬትሽ ደስታሽ ያለው በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ነው !
☞ ለገንዘብ ራሳቸውን የሸጡትን ምክር አትስሚ ! ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችይምና ! አምላኬ ገንዘብ ሳይሆን እግዚአብሔር ነው በያቸው !
☞ ሁል ጊዜ ነፍሱን ሰጥቶ ያዳነሽን የጌታን ፍቅር አስቢ !
☞የእግዚአብሔርን የፀጋ ክብር በሙላት ይሙላብሽ !
☞ሰይጣን በላከው ተራ ወንድ አትሸወጂ ስላንቺ ያለው እይታ ከቤት ዕቃ አያልፍምና !
(የቤቱን እቃ አሟልቶ አሁን ደግሞ ሚስት ብሎ ከሚያቅድ ነገ እንደ ቁምሳጥን፣ እንደ መኪና የቤት እቃ አድርጎ ሊቆጥርሽ ከሚችል እይታው ከጠበበ ወንድ ተጠበቂ)፤

☞እግዚአብሔር ፀጋውንና የክርስቶስን ልብ ሰጠን እንጂ ለእባብ የሚስቅ የሄዋንን ልብ አልሰጠንምና የቀረበሽ ወንድ ሁሉ ያንቺ አይደለምና ተጠንቀቂ።
☞ፍቅር ያዘኝ ብሎ ለሚፈጥነውም  ረጋ በል ብሎ መመርመር ይገባል። ወዲያው አፈቀርኩ አበድኩ ነደድኩ ብሎ የሌለን አለም ታሪክ ዲስኩር ከሚቀድ ወንድ ተጠበቂ ተጠንቀቂ ውድቀትሽን ስብራትሽን ሐዘንሽ ለማፈጠን ከሰይጣን የተላከ የስሜት ፈረስ ጋላቢ ሊሆን ይችላልና።
 
  👇ይቀጥላል

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

28 Jan, 18:03


ልባምን ሴት ልባም ያስባላት🤔 ያደረገችው መልካም ተግባር ማለትም፦ ለባሏ ታዛዥ መሆኗ፣ ቅን አስተዋይ፣ ነገዋን አዋቂ መሆኗ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም የሚበልጠውን እግዚአብሄርን መፍራቷ ነው🙏

፨" ብዙ ሴቶች መልካም አድርገዋል፣አንቺ ግን ሁሉንም ትበልጫለሽ" ምሳ 31,2

ይህን ቃል👆 ልባም ሴት መልካምን ተግባር ከማድረግ ያለፈችና ከመልካም ነገር በላይ የሆነ አንድ 🤔ልባምና ጀግና ያስባላት ነገር እንዳለ ይጠቁመናል
እርሱም ምንድን🤷‍♀ ነው ስንል እዚሁ ክፍል ወረድ ብለን እንዲህ የሚል ቃል እንመለከታለን

""ቁንጅና አታላይ ነው፣ ውበትም ይረግፋል፣ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን የተመሰገነች ናት" ሲል ይነግረናል

ስለዚህ ለአንድ ልባም ሴት ልባምነቷን የገለፀው ይሄ እግዚአብሔርን የምትፈራበት ፀጋን በውስጧ መያዟ ነው🙏 እርሱኑ ከመፍራቷ በላይ ሌላ ምን ይኑራት! ውበት እንደሆነ ከንቱ🙅 ሀብትም አንደሆነ ጠፊ ጥበብም ቢሉት እግዚአብሔርንር መፍራት ነውና☹️

"የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው" ምሳ 9,10

ታዲያ እርሱን መፍራቷ ከእነዚህ ሁሉ ከላቀ ከዚህ በላይ ልባም ሊያስብላት የሚችል ነገር ምን ይሆን🤷‍♀⁉️

"የሚገባትን ሽልማት ስጧት ፤ ስራዋም በአደባባዩ ያመስግናት" ምሳ 31,31
 
                 ✍️ቦና

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

27 Jan, 19:30


“መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤”
—ኤፌሶን 5፥18

➻ልባምነት በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት የምገለጥ ባህር ነው።

➻ልባሞች መንፈስ ቅዱስ ይሙላባችሁ‼️

የልባም ሴት አገልግሎት

26 Jan, 19:45


“እግዚአብሔርን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤ የሚፈራውም ጠግቦ ይኖራል፥ ክፉ ነገርም አያገኘውም።”
— ምሳሌ 19፥23


✍️እግዚአብሔርን መፍራት የልባም ሴት መገለጫ ነው
ልባም ሴት እግዚአብሔር ስለሚትፈራ ጠግባ ትኖራለች ከፉ ነገርም አያገኛትም‼️

የልባም ሴት አገልግሎት

25 Jan, 20:44


ኑ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን፤ ለአምላክ ለመድኃኒታችን እልል እንበል።

—መዝሙረ ዳዊት 95:1                                                   

የልባም ሴት አገልግሎት

24 Jan, 16:58


ግዜአችሁን  አታጥፉ
    ፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ንስርን የሚገዳደር ብቸኛው የወፍ ዝርያ ቁራ ነው።
ቁራ በንስሩ ጀርባ ላይ ይቀመጥና አንገቱን ይነክሰዋል። ንስሩ ምላሽ አይሰጥም ፣ ከቁራ ጋር አይጣላም ፣ ከቁራ ጋር አይታገልም ፣ በቁራ ላይ ጊዜና ጉልበቱን አያጠፋም ይልቁንም ክንፉን ዘርግቶ ወደ ሰማይ ከፍ በማለት መብረር ይጀምራል።

በረራው ከፍ ባለ መጠን ቁራው ለመተንፈስ ይቸገራል። በመጨረሻም ቁራው በኦክሲጅን እጥረት ምክንያት ይወድቃል።

ዛሬ በህይወታችሁ የሚገዳደራችሁን ምንም አይነት ነገር አትታገሉት ፣ ጉልበታችሁን እና ጊዜአችሁን በእርሱ ላይ አታጥፉ ይልቁንም ከፍ ባለ አስተሳሰብ በልጣችሁ ውጡ ፣ በእውቀት ጠንክሩ ፣ መልካም ሥራችሁን ጨምሩ።
ንስሩ በጀርባው ላይ የተንጠለጠለውን ቁራ ትቶ ከፍታው ላይ እንደሚያተኩር የሌሎችን አሉባልታ ፣ ሀሜት ፣ ማስፈራሪያ ወደታች ትታችሁ ከፍታችሁ ላይ አተኩሩ።

ቁራው ከፍታውን መቋቋም እንዳቃተው እናንተም ከነገሮች በላይ ከፍ ስትሉ የእናንተም ተግዳሮት ከፍታውን መቋቋም አቅቶት ቁልቁል ይፈጠፈጣል‼️

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

23 Jan, 12:28


✍️አማራጩ መጠንከር ብቻ ሲሆን‼️

ያላችሁ ምርጫ ብርቱና ጠንካራ መሆን ብቻ ሲሆን፣ ያን ጊዜ በእርግጥም ምን ያህል ብርቱና ጠንካራ ሰዎች እንደሆናችሁ ታውቁታላችሁ፡፡  

ሁሉም ነገር ተስፋ አጥቶ፣ አንዱን ችግር ተወጣሁት ስትሉ ሌላው ችግር ሲተካና ግራ ሲያጋባችሁ፡፡ ከሰዎች የምትጠብቁትን መልካም ነገር ሳታገኙ ስትቀሩና የማትጠብቁትን ጥሩ ያልሆነ ነገር ስታገኙ፣ ያላችሁ አማራጭ መጠንከር ብቻ ነው፡፡

ያን ጊዜ ነው ምን ያህል ብርቱና ጠንካራ እንደሆናችሁ የምታውቁት፡፡ ሁሉም ነገር የከዳችሁና መስመር የሳተ ሲመስላችሁ ምን ያህል ጠንካራና ጎበዝ እንደሆናችሁ የምታውቁበት ጊዜ ነውና ተስፋ አትቁረጡ፡፡

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

22 Jan, 13:56


“እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።”
— መዝሙር 1፥6

የልባም ሴት አገልግሎት

21 Jan, 17:25


“የምገዛው ራሴን ነው”

የታላቂቱ ፕሩሺያ ንጉስ የነበረው ታላቁ ፍሬደሪክ አንድ ጊዜ በበርሊን መንገድ ላይ ሲሄድ ሳለ አንድ በእድሜው እጅግ የሸመገለ ሰው ልክ እንደሱ በመንገድ ላይ ሲሄድ አገኘው፡፡ ይህ እድሜ-ጠገብ ሰው የነበረው አረማመድ የንጉሱን ትኩረት ሳበው፡፡ ይህ ሰው ቀና ብሎ፣ ደረቱን ገልብጦና አይኖቹ በትኩረት እያዩ ግርማ-ሞገስ ያለው ገዢ አይነት አካሄድ እየሄደ ነበር፡፡ ንጉስ ፍሬደሪክ የሰውየውን በራስ መተማመን በመመልከት ለማነጋገር ፈለገ፡፡

ንጉስ ፍሬደሪክ፡- “አንተ ማን ነህ?”

ሽማግሌው፡- “እኔ ንጉስ ነኝ”

ንጉስ ፍሬደሪክ፡- “ግዛትህ ምንድን ነው?

ሽማግሌው፡- “የምገዛው ራሴን ነው”

ይህ ታላቅ ገዢና ንጉስ በዚህ አዛውንት አነጋገር የማይረሳውን ትምህርት አግኝቶ መንገዱን ሄደ፡፡

ለካ፣ የገዢነት ሁሉ ገዢነት ራስን መግዛት ነው‼️

ለካ፣ የአመራር ሁሉ አመራር ራስን መምራት ነው‼️

ለካ፣ የኋላ ቀርነት ሁሉ ኋላ ቀርነት ራስን ሳይገዙ ሰውንና ሕብረተሰብን ለመግዛት መሞከር ነው‼️

➻ለካ፣ የውድቀት ሁሉ ውድቀት ራስን ሳይመሩ ሌላውን ለመምራት መሞከር ነው‼️

“ታጋሽ ሰው ከጦረኛ፣ ስሜቱን የሚገዛም ከተማን በጒልበቱ ከሚይዝ ይበልጣል።”
— ምሳሌ 16፥32 (አዲሱ መ.ት)


          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

20 Jan, 12:00


➻የሰጠኽኝ እንዳይወስደኝ 😭

አዝኖላቸው አምስቱን እንጀራ አምስት ሺ አድርጎ ካበላቸው በኃላ በንጋታው ሰጪውን ረስተው የተአምር እንጀራ ፍለጋ  ኢየሱስን ይፈልጉት ጀመር ትናንት የተሰጣቸው እንጀራ በአንድ ቀን ከሰጪው ወሰዳቸው ዛሬስ እኛን ምን ይሆን የወሰደን ተጠቀሙበት ብሎ የሰጠን ገንዘብ ወይስ አገልግሉበት ብሎ የሰጠን መድረክ ? የቱ ይሆን ? አሁን ላይ ሰይጣን ከወሰደብን ነገር ይልቅ ትናንት  ከጌታ ተቀብለነው ዛሬ ላይ እኛን የወሰደን ነገር ይበልጣል። ሰለሞን ጥበብን ፣ ሳምሶን ሀይልን ፣ ይሁዳ ደግሞ ደቀ-መዝሙርነት የተቀበሉት ከጌታ ነበር ነገር ግን ሁሉም የተሰጣቸውን ነገር እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ባለማወቃቸው ምክንያት  ኃላ ላይ የተሰጣቸው  ስጦታ ከሰጪ እንደበለጠባቸው መጽሐፍ ይነግረናል፤  እናንተ ቤት ግን  ሰጪው ንጉስ ይሁን።🔥

✍️bete

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

18 Jan, 17:25


🩸ወርቅና አልማዝ💰 ከፍተኛ ዋጋን ከማውጣታቸው አልፎ ውብና አሸብራቂ ጌጤም ጭምር ናቸው👍 ነገር ግን አንቺ ወርቅ ከቶውን ሊደርስበት ከማይችለው ማማ ላይ የተቀመጥሽ ውድና ክቡር ያለሽ ሴት ነሽ🙋 ይህን እወቂ‼️

🩸ብር አልያም ገንዘብን የማይፈነቅለው ድንገይ የለም የፈለጋችሁትንም ያሟላላችኋል፣ቀዳዳችሁን ይደፍናል የተንደላቀቀ ኑሮም ያከናንባችኋል☹️ ታዲያ ግን ይህ ብር ለሰው ልጅ እጅጉን ጠቃሚ ቢሆንም ነገር ግን ከአንቺ አይበልጥም አንቺ ከገንዘብ በላይ ትጠቅሚያለሽ ታስፈልጊያለሽ ም/ክቱም ብር አይደለሽምና‼️ ይህንንም እወቂ

አንቺ ሴት ራስሽን ከቶ ከቁሳቁስ ጋር አታስተያዪ መመዘኛም አታድርጊው🤷‍♀ በእግዜሩ አምሳል የተፈጠርሽ ውድ ክብርም ያለሽ ሴት ነሽና‼️ "ልብሽ ወደ እንቁው አይሳብ የልብ አይንሽም ገንዘብ ላይ አያማትር" ከእነርሱ ሁሉ የበላይ ነሽ አንቺ እነርሱን ግዢ አንጂ ከቶውኑ አይግዙሽ🙏

➻ለራስሽ ዋጋ ስጪ ዝቅ ያለ የወረደ ቦታ ላይም አትገኚ🙅‍♂ ለምታወሪው፣ለምታስቢው፣ ለምትለብሽው ለውሎሽም ተጠንቀቂ ነገ ለብዙ ሴቶች አርኣያ እንደምትሆን ሴት ተመላለሺ‼️

             ✍️ቦና

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

17 Jan, 05:11


➻መሥዋዕት
      
         🎤 ሀና ተክለ

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

15 Jan, 18:16


“እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው?
እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?”
— መዝሙር 27፥1

የልባም ሴት አገልግሎት

14 Jan, 18:17


👇ከእግዚአብሔር የሚበልጥ አንድ ነገር አላውቅም
ይህ እንደዚህ ነው አንደዚያ ነው አልልም
ግን እርግጠኛ ነኝ አንድ ነገር አውቃለሁ
የማምልከው አምላክ ከዚህ ሁሉ በላይ ነው (፪x)

በላይ በላይ ፣ በላይ በላይ (፬x)

የልባም ሴት አገልግሎት

13 Jan, 18:16


“እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ
#ኢየሱስ_ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ።”
— ዕብራውያን 4፥14

➻ትልቅ ሊቀ ካህናት የሆነ ኢየሱስ አለን‼️

የልባም ሴት አገልግሎት

12 Jan, 17:49


ማራናታ ኢየሱስ ሆይ ልናይህ ናፍቀናል‼️

የልባም ሴት አገልግሎት

11 Jan, 10:37


የልባም ሴት አገልግሎት pinned «»

የልባም ሴት አገልግሎት

09 Jan, 17:56


🎧🎧🎧ስሚ📢  📢  📢 

❝እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን፦ አንሄድባትም አሉ።❞
  —ኤርምያስ 6: 16

                ቁሙ! 🔴

              ተመልከቱ! 👀

                ጠይቁ!

                እወቁ! 🔐

                 ሂዱ! 🟢

👇እስቲ ዛሬ ለአንድ አፍታ ቁሚና የምሄደው መንገድ የምጓዝበት ጎዳና ትክክለኛ ይሆን አካሄዴስ የእውነት እግዚአብሔርን የሚያከብር ነው ወይስ እንደፍላጎቴ? ብለሽ ራስሽን መርምሪ፤ ደግሞም ተምልከቺው አይንሽን ክፈቺው የልቦናሽም አይኖች የተከፈ ይሁን ራሱን የተመለከተ ብዙ ነገሩን ለማስተካከል እድል ያገኛልና። እስቲ ጠይቂ በራሴ የሚባል ነገር የለም ልክ ነኝ ብለሽ የምትጓዢው መንገድ ልክ ባይሆንስ መጨረሻሽ ድካም ቢሆንስ እህቴ!? እስከመቼ በራስሽ ፈቃድና ምኞት ተጉዘሽ ትዘልቂዋለሽ ንቂ እንጂ!! የጠየቀ አጥብቆ ያሸ እውነተኛውን መልካሙንም መንገድ መከተል በዛም መራመድ ይጀምራል መጨረሻውም የዘላለም ህይወት። እህቴ ምናልባት ዛሬ ይህ ቀን የአንቺ ቢሆንስ🤷‍♂⁉️

👇መንገድ ጠፍቶብኛል መሄጃውን አላውቅም፣ ከዚህስ ቡሃላ የእውነት መልካም ህይወት ይኖረኝ ይሆን🤔⁉️ የምትይ አንቺ አዎን ይሆን ዛሬ ቁሚ፣ ተመልከቺ፣ እወቂ፣ እወቂውና በዛም መንገድ ሂጂ❤️🙏

                ✍️ቦና

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

08 Jan, 04:17


➻የህይወቴን በረት

🎤 ነጻነት

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

07 Jan, 05:13


➻የማይደገም ታሪክ
      
         🎤 አድስክዳን

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

06 Jan, 04:21


9.አልተረሳሁም

       🔊ሀና ተክለ

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

05 Jan, 06:58


ጠባቡና ሰፊው መንገድ

➻መንገድ ማለት ከሆነ ቦታ ተነስተን ወደሆነ ቦታ ለመድረስ ምንገለገልበት የእለተ ተለት መሄጃችን ነው። የተለመደው ይሄ የህይወት ስርአታችን  በራሱ መነሻ እና መድረሻ ከሌለው መንገድ በራሱ ትርጉም አልባ እንደሆነ ያስረዳናል። መንገድ ስለሆነ ብቻ አይኬድበትም ግን መድረሻው ሲታወቅ ይኬድበታል።
ሌላው መንገድ ሲኬድ ሚጠየቀው ጥያቄ ሰፊ ነው?? ጠባብ ነው ?? አስፓልት?? ኮብል??
እየተባለ ሚነሳ ነው  ሁሉም የራሱ መልስ አለው  ምናልባትም ከዚህ መልስ ተነስቶ መድረሻውን ለማግኘት የሚንደረደርም ደሞም ልክ ሚሆንም አይታጣም። የመንገዱ መጥበብ እና መስፋት ወይም ምቾት መድረሻችንን ከመጠቆም በላይ መንገዱ ላይ ሚኖረንን አካሄድ እና ቆይታ ይወስነዋል። የመንገዱ ባህርይ መረዳት  ለመድረስ ወሳኝነት አለው ::
በእየሱስ ትምህርት ውስጥ የተነሱት ሁለቱም መንገዶች እነዚህ ናቸው:- ጠባብ እና ሰፊው:: ሁለቱም የራሳቸው ባህሪ እና መድረሻ እንዳላቸው መድኃኒታችን አስተምሯል::

ሰፊው :-   ለአካሄድ እና ነፃነት ተስማሚ ምናልባትም በዘመነኛው ደሞ snack እና resting place ያለው ለእግር ማይጎረብጥ እና ውጣውረድ ማይበዛው ነበር ::

ጠባቡ :- ትንሽ ለአካሄድ ምታስቸግር እና ለመድረስ እልህ አስጨራሽ ትግል ሚደረግበት ውጣውረድ እና ትግል ምናልባት ከመንገዱ ባህሪ የሆነች ናት::

የመንገዶቹ ባህሪ እና ምቾት ሚለያይ ቢሆንም ግን መድረሻቸው እንደ ምቾታቸው አይደለም ትምህርቱ ሲያልቅ ጠባቡ ወደ እግዚአብሔር መንግስት እና ሰፊው ወደ ገሃነም ብሎ ያልቃል:: የእየሱስ ትምህርት ሲጠቀለል ምቾታችን ሳይሆን መድረሻውን ጊዜያዊ ሳይሆን ዘላለማዊውን መመልከት ነው::
የመድኃኒታችን ምክር እንቀጥል ... በጠባቡ መንገድ ሂዱ... ትንሽ ወጣውረድ ቢበዛውም መጨረሻው የእግዚአብሄር መንግስት ነው::
ተመችቶህ መንገዱ ገሃነም ከሆነ መድረሻው በቀጭኗ መንገድ ታግሎ መንግስቱ መግባት መታደል እና ሽልማት ነው::

በጠባቧ መንገድ ሂዱ እሷም በእየሱስ ክርስቶስ የተገለጠች የእግዚአብሄር የፅድቅ ህይወት ናት::

       #HOREB_DS

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

31 Dec, 19:29


➻ልባም ሴት የጸሎት ሴት ናት‼️

የምንጸልየው ለመኖር ሳይሆን የተፈጠርንበትን አላማ ለመኖር ነው።
ከተፈጠርንበት አላማ ጋር ለመገናኘት የግድ ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ልናደርግ ይገባናል። የተፈጠንበትን አላማ  የመኖርን አቅም እና ጥበብን ለማግኘት በጸሎት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አማራጭ የለለው ምርጫ ነው።

ሁልጊዜ ለምንድነው የምንጸልየው ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት የምናደርገው እግዚአብሔር እኛን የፈጠረበትን አላማ ለመረዳትና ለመኖር ነው እለት እለት እግዚአብሔር ለእኛ አላማ አለው ያንን አላማውን  የመረዳትና የመኖርን አቅም ለማግኘት ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ልንቀርብ ይገባናል።

📿ጸጋ ይብዛላችሁ‼️

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

30 Dec, 17:33


⚠️ህይወት አዘል አጠር ያሉ ምክሮች‼️

🔹ከዘመንሽ ቅድስና አይታጣ ፍሬ ያለው ቅድስና ውስጥ ነውና!

🔹ሰው ለመሆኑ ኑሪ ሰው መሆን የፈጣሪን የልብ ፈቃድ ፈፅሞ ማለፍ ነውና!

🔹 ክርስቶስን ልበሺ በሄድሽበት ስፍራ ሁሉ ስኬትና ሞገስ አለሽና!

🔹ትህትና ዝቅ ማለት ከዘመንሽ አይታጣ፤ ለታታላቆችሽ ዝቅ ስትይ በረከት ለታናናሾችሽም ዝቅ ስትይ ትውልድ አለና!

🔹ሁሉንም ሰው ውደጂ ግን ደግሞ ምረጪ!

🔹 በተሰማራሽበት ስራ/ትምህርት ትጉ ሰራተኛ ሁኚ ትጋት የሰዋዊ ባህሪ ነውና!

🔹በራስሽ ተስፋ አትቁረጪ በአንቺ ተስፋ የማይቆርጥ እግዚአብሔር አለና!

🔹መውደቅና መሳት ሞት አይደለም መነሳትም መመለስም አለና!

🔹ርካሽ አይደለሽም ዋጋ እንዳላት ሴት ኑሪ፤ ዋጋሽ ከዚህ አለም ውድ ከተባሉት ወርቅና እንቁ የላቀ የከበረም ነውና!

🔹 በአለባበስሽ እግዚአብሔርን አልፎም ሰውን አክብሪ ገላሽን በአደባባይ አታሳይ ደበቅ ሸፈን በይ በአደባባይ አክባሪሽ ብዙ ነውና!

🔹 በራሴ፣ በኔ ማን ምን አገባው አትበይ ቀድሞውኑ የራስሽ አይደለሽምና!

➻"እህቴ ዋጋ አለሽ ዋጋ እንዳላት ሴት ተመላለሺ!"🙏

       ✍️ቦና

             ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

29 Dec, 18:54


ጠያቂ ፦ ቢሊ ወደኋላ ተመልሰህ ያሳለፍከውን ጊዜ አስተካክል ብትባል ምናልባት "እንዲህ አደርግ ነበር" የምትለው ነገር ይኖር ይሆን?

ቢሊ ፦ አዎ! በአገልግሎት ያሳለፍኳቸውን ጊዜያት ቀንሼ ከጌታዬ ጋር ሰፊ ጊዜ እወስድ ነበር። ብዙ ጊዜዬን ከጌታ ጋር በመዋል አሳልፍ ነበር።

  
        ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

28 Dec, 20:33


➻ኢየሱስ ልናይህ እንፈልጋለን‼️

የልባም ሴት አገልግሎት

27 Dec, 18:27


🩸 ቂም ነው‼️

          👇👇
በጀርባዬ አንግቤ
        ጎባጣ ያረገኝ
እግሬ እንዳይራመድ
        አስሮ ያስቀመጠኝ
በልቤ ላይ ገዝፎ
        የሚያንገዳግደኝ
ቂም ነው ከበረከት
        መንገድ እኔኑ ያራቀኝ‼️

                                  ✒️ ቦና 🐆

🔹"እኔን ለጎዱኝ ከማደርግላቻው ይቅርታ ለኔ የተደረገልኝ ይቅርታ ይበልጣል!"🐆

ብዙ የተወና ብዙ ያሳለፈ ብዙ ክብር ይጠብቀዋል በቂም የተሞላ ግን ዘመኑን በከንቱ ልፋትና ድካም ያሳልፋል፤ መስፈርት አታውጡ የተበደላችሁበትን ልክ ይቅር በተባላቹበት ልክ ይቅር በሉ

🔹"በደልን አትቁጠሩ ያልተቆጠረባችሁ ናቹና!"

ይቅር በሉት በልባችሁ ለቂም ትንሽ ስፍራ አትስጡ ዘሩ ያደገ ለት ለትውልድ እንዳትሆኑ አድርጎ ከመንገድ ያስቀራችዋልና። በቀል አታስቡ በቀል የእግዚአብሔር ነው ይልቅስ ለዛ ሰው ምህረትን እንዲያደርግ አጥብቃችሁ ፀልዩ "ሰው" መሆን ማለት ይህ ነውና🙏

🔹"እውተኛ ስኬት ይቅርታን መልበስ ነው!"

ሰው መሆንን የመሰለ ውበትየ የለም "የሰው" ባህሪ ደግሞ አንዱ ይቅርታ፤ ሰው የሆነ የአለም አይደለም ስለዚህ የቂም ልብ ሊኖረው አይገባም ሲተው ይቅር ሲል ሲፀልይለት መንገዱ የቀና በፈጣሪውም ዘንድ ሞገስን ያገኛ 🙏
         
                     ✍️ ቦና

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

26 Dec, 17:13


“ነፍሴ መድኃኒትህን ናፈቀች፤
በቃልህም ታመንሁ።”
— መዝሙር 119፥81

የልባም ሴት አገልግሎት

26 Dec, 15:01


#Day_5
#strategy_1

መልካም እረኛና በር

አምላክ በስጋ ተገልጦ መሬት ሲመላለስ እራሱን ከገለጠባቸው ምሳሌዎች መሀል፦ መልካም እረኛ እና በር ናቸው። የሁለቱም ምሳሌዎች መሰረታዊ አላማ መንጋዎቹን መጠበቅ ነው ። እንዳይጠፋ፣እንዳይባዝኑ ና በጎቹን የሚጠብቅበትን መንገድ በምሳሌ አስረድቶናል።ነፍሱን ስለ በጎቹ የሚሰጥ መልካም እረኛ፣ ለእረኛው ካልሆነ ማይከፈት አስተማማኝ በር ኢየሱስ ነዉ።
➻መልካም እረኛና በር ኢየሱስ ነው‼️

         ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

25 Dec, 17:59


#Day_4
#strategy_1

መንገድ እውነት ህይወት

የሰው ልጅ በመሰረታዊነት ሲኖር ሶስት መሰረታዊ ስጋዊ ፍላጎቶች እንዳሉት ሁሉ፣ በመንፈሳዊም አቅጣጫ ሶስት መሰረታዊ ፍላጎቶች አሉት። መንገድ፣እውነት እና ህይወት። ከጠፋበት የእግዚአብሔር አለም መመለሻ መንገዱን ሲፈልግ፣ ስለተጣላው አምላክ እውነቱን ለማወቅ ሲታገል በትንሹ በበራለት የአምላክ ማንነት ለመኖር ህይወትን ሲፈልግ ግን ሳያገኝ በትግል ለነበረ የሰው ልጅ አብን ማግኛ መንገድ አብን ምንረዳበት እውነት እንዲሁም ከአብ ጋር ህብረት መቀጠያ ህይወት ሆኖ እግዚአብሔር ወልድ በሰጋ ተገለጠ።

➻መንገድና እውነት ህይወትም ኢየሱስ ነው‼️

         ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

25 Dec, 08:13


#Day_3
#strategy_1

የአለም ብርሀን

በዘመናዊው አለም ብርሀን እጅግ በሚፈልግበት እና አዳዲስ ፈጠራዎች በተበራከቱበት፣ ብርሀን ሰጪ እንዲሆን የፈጠርናቸው ትልልቅ ፈጠራዎቻችን እንኳን፣ የግለ-ሰብ ወይም የሆነ ድርጅት ከመሆን የዘለሉ አይደሉም። ብርሀን ሲባል እንኳን የምናስታውሳት ፀሀይ እንኳን በአንዱ በኩል ስታበራ፣ ሌላውን የአለም ክፍል ታጨልማለች። የአለም ብርሀን ሊባልለት የሚችል ፍጥነት ባይኖርም፣ ፈጣሪ ግን አለ። ኢየሱስ እራሱን ካስረዳበት ትልቁን መንገድ አንዱ የአለም ብርሀን ነኝ ነው። ለማንም ሳይለይ የህይወት ብርሀን ሚያበራው እውነተኛው ብርሀን እየሱስ ነው።

➻የአለም ብርሃን ኢየሱስ ነው‼️

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

24 Dec, 17:47


👸👸 ሴት የድርሻዋን👸👸
      👉ክፍል ሁለት

          📿ሰናይት ነጋሽ

         ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

24 Dec, 15:25


➻ሴት የድርሻዋን በሚል የጀመርነው መልዕክት የመጨረሻ ክፍል ሁለት ዛሬ ማታ 2:00 ሰዓት ይለቀቃል‼️

➻ጸጋ ይብዛላችሁ🙏

የልባም ሴት አገልግሎት

24 Dec, 09:49


በእርግጥ በህይወት ስንኖር ፈተና አንዱ የህይወታችን ክፍል ነው ብዬ አምናለሁ። ፈተና ከሌለ ማለፍ መሻገር አንችልም።
ምንም ያህል ብንፈተን ግን ከምንችለው እና ከአቅማችን በላይ ላይፈትነን እግዚአብሔር የታመነ ነው።

“ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 10፥13
ከምንችለው በላይ አይፈትነንም ደግሞ ከፈተናው ጋር መውጫ ያደርግልናል‼️
ስለዚህ እህቴ ይህን ቃል በማመን በእግዚአብሔር ላይ ባለሽ እምነት ፀንተሽ ያለሽበትን ሁኔታ ከምስጋና ጋር ለአምላክሽ አስታውቂ ከዚህ ነገር ትወጫለሽ። ደግሞ ያለአላማ ዝም ብሎ ቁጥር ለመሙላት አልተፈጠርሽም
መዝ 139-14 ግሩምና ድንቅ ሆነን ነው የተፈጠርነው በዛ ላይ እግዚአብሔር በእኛ ያለው ሃሳብ እጅግ የከበረ ነው።
➻ስለዚህ እህቴ አንቺ ግሩም ነሽ፣ ድንቅ ነሽ፣ ትችያለሽ፣ ትጠቅሚያለሽ። ደግሞ መኖርሽ ለጌታ፣ ለራስሽ፣ በዙርያሽ ላሉ ሁሉ ይጠቅማል። 
አንቺ ትጠቅሚያለሽ‼️

     ✍️Senayit Yishak

             ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

22 Dec, 07:55


#Day_2
#strategy_1

የህይወት እንጀራ

እንጀራ መብላት እስትንፋስ ለመቀጠል የምናደርገው እንደሆነ የዕለት ዕለት ህይወታችን ይመሰክራል። ግን ለምን እየሱስ እንጀራ ነኝ አለ? በብሉይ-ኪዳን በጥላው ዘመን፣ ህዝብን ከ ፈርዖን ቀንበር ነጻ ለማውጣት ብቻ ሳይሆን፣ አላማው ከንአንንም ማድረስ ነበር። መዳን፣ መውጣት ብቻ ሳይሆን መድረስና፣መውረስም የእግዚአብሔር አላማ ነበር። ነጻ መውጣት በመስዋእቱ ቢሆንም፣ መንገድ መጨረስ ግን አቅም እና ምግብ ይፈልግ ነበር።አሀ መና! 
በአዲሱ-ኪዳን በ አካሉ ዘመን ነጻ ከወጣንበት ከሀጥአት ቀንበር፣ በኋላ ለምንከተለው የእየሱስ መንገድ አቅም የሚሰጠው የህይወት እንጀራ ነው። የህይወት እንጀራ የእየሱስን መንገድ የመከተል የሀይል ምንጭ ነው
‼️

             ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

19 Dec, 17:34


👸👸 ሴት የድርሻዋን 👸👸
➻እህቶች ልትሰሙት ይገባችኋል

👉ክፍል አንድ

        📿ሰናይት ነጋሽ

         ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

19 Dec, 13:08


#ሴት_የድርሻዋን በሚል ሀሳብ 📿ከሰናይት ነጋሽ ጋር የእግዚአብሔርን ቃል ዛሬ ማታ 2:00 ሰዓት ላይ እንማራለን‼️

#ሴት_የድርሻዋን ድንቅ መልዕክት ለወዳጆቻችሁ Share አድርጉላቸው‼️

የልባም ሴት አገልግሎት

18 Dec, 18:24


ሰላም ይብዛላችሁ የተወደዳችሁ የልባም ሴት አገልግሎት ቤተሰቦች ሀሙስ ማታ #ሴት_የድርሻዋን በሚል ርዕሰ ከተወደደችው እህታችን 👉ሰናይት ነጋሽ  ጋር የእግዚአብሔርን ቃል እንማራለን‼️

➙ሀሙስ ማታ 2:00 ላይ ጠብቁን‼️

👉Share our message for your friends

የልባም ሴት አገልግሎት

17 Dec, 18:53


ጭራሹኑ ካለመንቃት ዘግይቶ መንቃት በጣም የተሻለ ነው። እድሜ ልክ ከመሰቃየትም... ለጥቂት ጊዜም ቢሆን በጣም የከፋውን ስቃይ ተቀብሎ የቀረውን ጊዜ ያለህሊና ወቀሳ መኖር እጅጉኑ የተሻለ ነው።

💒 ከእግዚአብሔር ቤት ሙሉ በሙሉ ከመውጣት እየተንፉአቀቁም ከእግሩ ስር መቆየት ለነብሳችን ትልቁን ውለታ መዋል ነው።
   
   ከድካማችን በላይ ያድርገን
  
✍️Mercy

             ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

16 Dec, 16:46


“ገና ደካሞች ሳለን #ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ #ኃጢአተኞች_ሞቶአልና።”
— ሮሜ 5፥6

እኀህቴ አንድ ነገር ላስታዉስሽ ክርስቶስ ገና ደካሞች(ሀጥያተኞች) ሳለን ነዉ የወደደን ደግሞ መዉደድ ብቻ ሳይሆን👉እግዚአብሔር የመረጣቸውን የሚከስ ማን ነው? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፤  ታዲያ የሚኰንን ማን ነው? የሞተው፣ እንዲሁም ከሞት የተነሣው፣ በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠው ክርስቶስ ኢየሱስ፣ ስለ እኛ ይማልዳል።
ሮሜ 8:33-34

       ስለዚህ እራስሽን ፈቅደሽ ለሰራሽ ጌታ ስጭዉ ምን ማድረግ እና ለምን መጠቀም እንዳለበት ባለቤቱ(ሰሪሽ) ያዉቃል።
➻ተስፋ መቁረጥ ማለት እግዚአብሔርን አለማመን ነዉ የጠላትም ትልቁ መሳሪያዉ ተስፋ ማስቆረጥ ነዉ ስለዚህ ለምን እራስሽን ለዕርሱ ትሰጫለሽ የወደደሽ ያፈቀረሽ እራሱን የሰጠሽ ጌታ እያለልሽ አሁን ካለሽበት ሁኔታ ለመዉጣት ብቸኛ መንገዱ ሕያዉ የሆነዉን ቃሉን በማንበብ ከእርሱ ጋር ሕብረት ማድረግ ነዉ አደራ በርቺ እንወድሻለን።
   
          
              ✍️ሩት

             ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123
           🫧🔸JOIN🔸🫧
     ♡       ⎙      ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

የልባም ሴት አገልግሎት

14 Dec, 18:10


🚨 ከጥሞና የራቀ ህይወት...

👉 ሰው ለሚታዘዝለት ለዚያ ነገር ባሪያ ነው። ለዛም ነው የኔ ህይወት ለማን እየተገዛ ነው አሁን ላይ የህይወቴ ጌታ የሆነው ማነው ብለን መጠየቅ ያለብን አንዳንዴ እንዳንድ ነገሮች ከጌታ በላይ ህይወታችንን እየነዱ እናገኛቸዋለን በህይወታችን ገነው አሸብርቀው "ጌታዋ እኔ ነኝ" የሚል ድምጽ እያሰሙ እናገኛቸዋለን። ታድያ ከጥሞና የራቀ  ህይወት በነገሮች ወደ መነዳት ህይወት እንደሚወስደን ግልጽ ሊሆንልን ይገባል።

ስለዚህ እህቴ ግቢ ወደ እልፍኝሽ ከጌታሽ ጋር ጊዜ ውሰጂ ስሚው የሚልሽን አድምጭ። ይህንን ስታደርጊ ኑሮሽ ይረጋጋል ነገሮች እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ቦታ ቦታቸውን መያዝ ይጀምራሉ።

✍️ኤፍራታ

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

13 Dec, 19:19


ዝም ብዬ እቆማለሁ
Eyerusalem Worku and Kenessa Bula

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

12 Dec, 18:10


1ኛ ሳሙኤል 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ እነሆ፥ አንተ ሸምግለሃል፥ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም፤ አሁንም እንደ አሕዛብ ሁሉ የሚፈርድልን ንጉሥ አድርግልን አሉት።

… 
¹⁸ በዚያም ቀን ለእናንተ ከመረጣችሁት ከንጉሣችሁ የተነሣ ትጮኻላችሁ፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር አይሰማችሁም።
¹⁹ ሕዝቡ ግን የሳሙኤልን ነገር ይሰማ ዘንድ እንቢ አለ። እንዲህ አይሁን፥ ነገር ግን ንጉሥ ይሁንልን፥
²⁰ እኛም ደግሞ እንደ አሕዛብ ሁሉ እንሆናለን፤ ንጉሣችንም ይፈርድልናል፥ በፊታችንም ወጥቶ ስለ እኛ ይዋጋል አሉት።

☝️ይህን ቃል እያየሁ በጣም ስገረም ነበር። እንዴት የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደ አሕዛብ መሆንን ይፈልጋል?  .... በዚህ ክፍል ላይ ሌላም የሚያስገርም ነገር አለ፤ እሱም፦ እግዚአብሔር በነብዩ ሳሙኤል በኩል እንዲህ የሚል ምላሽ ሰጥቶ ነበር
“በዚያም ቀን ለእናንተ ከመረጣችሁት ከንጉሣችሁ የተነሣ ትጮኻላችሁ፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር አይሰማችሁም።”
  — 1ኛ ሳሙኤል 8፥18
ከዚህ መሪ(ንጉሥ )👑  የተነሳ ወደ እግዚአብሔር ፀሎት ቢያደርጉም መልስ እንደማይሰጣቸው ተናግሮ ነበር። በዚህ ሁሉ ግን እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ሀሳብ አልተመለሱም !!!
👉ዛሬ እስቲ አንድ ነገር ቆም ብለን እናስብ ምን አይነት ልመና ነው በእግዚአብሔር ፊት እያቀረብን ያለነው? ምንድነው ካልሰጠኸን ብልን የሙጥኝ ብለን የያዝነው ? ፀሎታችንን እንፈትሽ !!!
👉የጠየቅነው ጥያቄ ተመልሶ እግዚአብሔርን ከእኛ ዘንድ የሚያሸሽ ምንም አይነት ልመና ከእኛም ከቤታችንም ይራቅ !!! እንደ አሕዛብ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ መመላለስ ይሁንልን !!!

        ✍️kali

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን

            👇👇👇👇👇
 @lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

11 Dec, 14:20


“የአምላክ መንገድ #ፍጹም ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል #የነጠረ ነው። መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ፣ እርሱ #ጋሻ ነው።”
— መዝሙር 18፥30 (አዲሱ መ.ት)

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

10 Dec, 18:37


እግዚአብሔር የሚናገር አምላክ ነው። እርሱ ወዶናል፤ መልእክቱንም በቃሉ በኩል እንዲደርሰን መርጧል።  በመጀመሪያ አባቶች እና ታላላቅ ነቢያት ነበሩ።
ከዚያም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የተጻፉ ጽሑፎች ነበሩ።
ነገር ግን የእግዚአብሔር ኃያል ቃላት እና ታላቅ መልእክት ቃላት ብቻ አልነበሩም፤ ነገር ግን የናዝሬቱ ኢየሱስ የተባለው፣ እርሱም ክርስቶስ የሁሉ ጌታ የሆነው ሰው ነው።
እኛ ክርስቲያኖች፣ ኢየሱስ እንድንሆን የሚፈልገውን ለመሆን ቅዱሳት መጻሕፍትን ብቻ ሳይሆን እርሱን መመልከት አለብን።
ቅዱሳት መጽሐፍት ስለምን እንደሚያወሩ፣ ደግሞም እንዴት መኖር እንዳለብን የሚያስረዳን ኢየሱስ ነው።

✍️GCH telegram

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

08 Dec, 08:20


የማንን ሙሉ አልበም ወይም ነጠላ ይፈልጋሉ
የፈለጉትን የዘማሪ ስም ይምረጡ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

የልባም ሴት አገልግሎት

05 Dec, 18:15


ወደራስሽ መለስ በይ

•  ስለሰዎች የግል ጉዳይና ሁኔታ ለማወቅ በሞከርን ቁጥር ራሳችንን የማወቅና የማሻሻል ብቃታችን እየቀነሰ ይሄዳል፡፡

•  ስለሰዎች ጉዳይና ሁኔታ የመስማት ጥማታችን በጨመረ ቁጥር ራሳችንን የማድመጥና ከራሳችን ጋር የመግባባት ብቃታችን እየወረደ ይሄዳል፡፡

•  ስለሰዎች ስኬትና ውድቀት የማውጣትና የማውረድ ፍላጎታችን በበዛ ቁጥር የራሳችንን የስኬት ደረጃ የማወቅና ከዚያ አንጻር የመስራት ምልከታችን ይጠፋብናል፡፡    

•  ስለሰዎች ማሰብንና ማውራትን በለመድን ቁጥር ሰዎች ስለ እኛ ስለሚያስቡትና ስለሚያወሩት ነገር መጨነቅና መናወጥ እንጀምራለን፡፡

•  ሰዎች ያደረጉብሽን ያላደረጉልሽን እየቆጠርሽ መራራ በሆንሽ ቁጥር፣ ራስሽን የምታርግያቸው መልካም ነገሮች ላይ የማተኮር አቅምሽን እያጣሽ ትሄጅያለሽ፡፡

➻ወደራስሽ መለስ ስትይ አኝች ማድረግ ባለብሽ ነገር ላይ ትኩረት የማድረግ አቅም ይሰጥሻል‼️

✍️ልባሞች ወደራሳችሁ መለስ ማለትን ተለማመዱ‼️

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

03 Dec, 17:18


መፈለግ ወይም አንድን ነገር ለማግኘት የምንከፍለው ዋጋ አስደስቶን አያውቅም!! ምክንያቱም ያንን ነገር ስንፈልግ፤ ለዛ ነገር ዋጋ ስንከፍል  በልባችን ሁለት ነገር እናስባለን፤ ይህም እናገኛለን ወይም እናጣለን!!! ተማሪ ለፈተና እያጠና ጥሩ ውጤት አመጣ ይሁን ብሎ ይጨነቃል። እናትም በምጧ ጊዜ እጅግ ትጨነቃለች።
እነዚህ ከላይ ያነሳውት ሂደት ወደ ደስታ ሚቀየሩት ውጤቱ መልካም ሲሆን ብቻ ነው። ተማሪው ውጤት ሲመለከት ፤እናትም ልጇን ስትመለከት ሀዘኗን ትረሳለች‼️

  ሰማይ ግን አንድ የተለየ ሀሳብ ይነግረናል እሱም በፍለጋ መደሰት እንደምንችል‼️ 
ጌታ ጋር ሆነን ሂደቱ ጭምር ደስ ይላል ምክንያቱም እሱ ጋር ስንቀርብ ይሆናል፤ አይሆንም በሚል ሀሳብ አይደለም!!! መፅሐፍ ቅዱስ በአንድ ስፍራ እንዲህ ይላል ፦
“...
#እግዚአብሔርን_የሚፈልግ_ልብ #ደስ_ይበለው።”
  — 1 ዜና 16፥10 
➻እንደሚገኝ እርግጠኛ ሆኖ ነው የቀጠረን‼️
ሁልጊዜ እሱን በመፈለግ ውስጥ ያለውን ደስታ ማጣጣም ይሁንልን‼️
                ✍️kali

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

02 Dec, 12:28


#ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን #እርሱ_እንደ_ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው።
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥10

@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

01 Dec, 18:31


✍️ዋጋሽ ከእግዚአብሔር ነው‼️
ክፍል ሁለት 2️⃣

➫ስኬታችሁ ወደዚህ ዓለም የመጣችሁበትን
#ዓላማ_መኖር እንጂ ባገኛችሁት ቦታ ሁሉ #መስሎ_መኖር አይደለም።

➫የምትኖሩለት ብቻ ሳይሆን የምትሞቱለት አላማ ከሌላችሁ ለዚህ አለም አስፈላጊ ሰዎች አይደላችሁም።

🔵 ሁሌ የሚያስፈልገን ጨዉ እንጂ ወርቅ አይደለም።

📌ወርቅ ሁሌም አያስፈልገንም ብለን ዋጋዉን አናረክሰዉም፥
#ወርቅ_በጊዜዉና_በቦታዉ ሲሆን ነዉ #ዉድነቱን የምናዉቀዉ።

📌ሁሌ ስለሚያስፈልገን የጨዉን ዋጋ ዉድ አናደርገዉ፤ ለህይወት ማጠፈጫነት ካሉን ግብአቶች አንዱ ነዉ።
ሁሉም በቦታቸዉና በጊዜያቸዉ ዋጋቸዉን ይተምናሉ።

➫ወርቅን በእንጀራ እንደማትበሉት ሁሉ ጨዉንም ጌጥ አታደርጉትም።

አለ ቦታችሁ ስትገኙ ዋጋችሁን ሰዎች ያወርዱታል፣ አለ ጊዜያችሁም ከተገኛችሁ ቦታ አይኖራችሁም።

📌በትክክለኛዉ ጊዜና ቦታ ስትገኙ
#ትክክለኛ_ክብር_ይሰጣችኃል

“ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ፦ ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው አሉ። በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ያነግሡት ዘንድ ሊመጡና ሊነጥቁት እንዳላቸው አውቆ ደግሞ ወደ ተራራ ብቻውን ፈቀቅ አለ።”
  — ዮሐንስ 6፥14

“ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን
#አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።”
  — 1ኛ ዮሐንስ 2፥15-16

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

30 Nov, 18:48


ዋጋሽ ከእግዚአብሔር ነው¶¶
ክፍል አንድ1️⃣

🔵 በፍፁም ተሸናፊ ሆነሽ አትገኚ።
አንቺን ደካማ ያደረገሽ ጭንቅላትሽ ዉስጥ የተዘራዉ የአልችልም ባይነት ዘር እንጂ እንደማትቺ የሚገልፅ ቃል እግዚአብሔር አልነገረሽም።

📌
#ራስሽን_ሁኚ፣ የተፈጠርሽበት አላማ ተረጂ፤ ህልምሽ ቤት፥ መኪና፥ ወርቅ፥ ዝና፥ መብለጭልጭና ፋሽን አይሁን ለምን እንደተፈጠርሽ የገባሽ ቀን ያለሽ ሳይሆን አንቺ ራስሽ ዉድ መሆንሽ ይገባሻል።

➫እኩል ነኝ፣ ተራ አይደለሁም፥ እችላለሁ ስላልሽ ምንም አታመጪም ማን እንደሆንሽና ለምን እንደተፈጠርሽ እስካልገባሽ ድረስ ሴትን በተመለከተ የሚነገረዉ ሁሉ አንቺን አይገልጥም። ስለ አንቺ እግዚአብሔር ያለዉን እዉነት ብቻ ተረጂ፤ ሳትናገሪ ትሰሚያለሽ፥ ሳትፈልጊ ታገኚያለሽ።

📌 ዋጋሽን ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰዉም ከአለም
#አትጠብቂ

🔵 የህይወታችሁ ስኬት መሆን ያለበት ለተፈጠራችሁለት እውነት መኖር እንጂ በምታገኙት ዕድልና በምታገኙት አጋጣሚ ሁሉ መዘፈቅ አይደለም።
➫የሆናችሁትን ባለመሆን ማርፈድ ኪሳራ ያስከትላል።

📌የሆናችሁትን ሁኑና ነጋችሁን በበለጠ የተሻለ ለማድረግ ትጉ እንጂ ዛሬ ባገኛችሁት ስኬት አትሟሟቁ፥ በገጠማችሁም ችግር ተስፋ አትቁረጡ እላያችሁ ላይ ያለዉን አራግፉና ወደ ፊት ፍጠኑ።

የሆናችሁትን አለመሆን ያለሆናችሁትን እንድትሆኑና ከተፈጠራችሁበት ዓላማ ውጪ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል።

📌እግዚአብሔር ናችሁ ያላችሁን ጥሪ ትታችሁ ሰዎች ሁኑልን በሚሉአችሁ ተስባችሁ የኪሳራ ሳጥን ውስጥ እዳትገኙ ተጠንቀቁ።

➫ምክንያቱም ኢየሱስ የዓለም ቤዛ ለመሆን መጥቶ ንጉስ ሁንልን ብለውት ነበርና።.......

➻ይቀጥላል
          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

28 Nov, 21:30


“..ንቁም፤ ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራል።”
  — 1ኛ ጴጥሮስ 5፥8 (አዲሱ መ.ት)

✍️ሰይጣን እንዳለ እና እንደሚዋጋን ነፍስ ካወቅኩ ጊዜ ጀምሮ የማውቀው እውነት ቢሆንም ትናንት ማታ ግን ሰይጣን በእርግጥ እንዳለ አወቅኩ። መንፈሳዊ አካል ያላቸው መናፍስት Literally በዙራያችን አሉ። የተሸነፉ እና ስልጣን የሌላቸው አድርገን ስለሳልናቸው ብዙ ትዝ አይሉንም። እርግጥ ነው የተሸነፉ ቢሆንም አሁንም ችግር የመፍጠር አቅም አላቸው። ጌታ ኢየሱስም ሆነ ሐዋርያቱ ምን ያህል ለጨለማው ኃይላት ንቁ እንደነበሩ ማስተዋል ቀላል ይመስለኛል።

➻የሚታዩ ነገሮች ሁሉ ከማይታየው አለም የመጡ ናቸው። የማይታየው አለም ከሚታየው አለም በላይ real ነው። የማይታየው አለም ላይ በየሰከንዱ ሽርፍራፊ ብርቱ ጦርነት አለ። የማይታየው አለም ነገሮችን ወደሚታየው አለም ለመውለድ ምጥ ላይ ነው። ውግያችን ከስጋ ለባሽ ጋር አይደለም የተባለው ቃል በእርግጥ እውነት ነው። የጨለማው አለም ኃይላት ስልጣናት ገዢዎች አሉ።
🤲 ጸሎት ጸሎት ጸሎት‼️

✍️Naum

     ♻️Share♻️Join♻️

       ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
          👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

26 Nov, 20:42


“እግዚአብሔርም የለመንሁትን ልመናዬን ሰጥቶኛል፤ እኔም ደግሞ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፤”
  — 1ኛ ሳሙኤል 1፥28

ለሃና ሳሙኤል ከጣውንቷ ማስቆጣትና ብስጭት ያረፈችበት የፅኑ እንባዋ ፍሬ የፅሎቷ ውጤት በልቧ ጌታዋን በማውራቷ ብዛት እንደሰከረች ከተቆጠረችበት መንደር ስሟ የተቀየረበት ማስረሻዋ በሀዘኗኗ በጭንቀቷ ብዛት እንደ ምናምንቴ በታየችበት ስፍራ የስለቷ ደስታ በእግዚአብሔር የመታሰቧን ማሳያ ቢሆንም ከእግዚአብሔር የተቀበለችውንን ሳትሰስት የሰጥታዋለች  ለእኔ ይሁነኝ ብላ ወደ ኋላ አልሸሸገችውም እናተዬ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ሳታስቀሩ ስጡት እሺ ከእሱ አትሸሸጉ አይ ካላችሁም ለራሳችሁ ጥቅም ሁሉ ታጣላችሁ‼️

✍️Samri Getu

       ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
          👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

23 Nov, 21:16


“ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፤ ደፍሮትስ በደኅና የሄደ ማን ነው?”
                                  -- ኢዮብ 9፥4

  አንዳንዴ በህይወታችን ከባድ በምንላቸው ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ፣ እምነታችን በገጠመን ፈተና ሲፈተንብን፣ እንደው ከእግዚኣብሔር ጋር ተሟግተን ተሟግተን ሊ'ረዳን ያልቻለ ሊመስለን ይችላል። ልክ ኢዮብ እንዳለው፦ 

“ትካዜዬ ምነው በተመዘነ ኖሮ! መከራዬም ሁሉ ምነው በሚዛን ላይ በተደረገ ኖሮ!”-ኢዮብ 6፥2
  
   ኢዮብ ማንም የተረዳው ሳይመስለው ሲቀር ይህን👆 አለ። ያለበት ሀዘን እና ትካዜ በመመዘኛ ተመዝኖ በቁጥር መጠኑ ቢታወቅለት ተመኘ።
 
   ክርስትናችን በእግዚኣብሔር ጠቢብነት እና በሃይሉ ታላቅነት ላይ ያልረጋ፣ እርግት ያላለ እና ያላረፈ እንዲሁም ያልተደላደለ ከሆነ የጊዜ ጉዳይ እንጂ በብርቱ መፈተናችን የማይቀር ነው። በእግዚኣብሔር ሁሉን አዋቂነት፤ በእርሱ ሁሉን ቻይነት ላይ ስር የሰደደ መደላደል እንዲኖረን ዕለት ዕለት በፊቱ የበረታን እንድንሆን ጌታ ይርዳን!

   ኢዮብ በስተመጨረሻ “እነሆ፥ እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም እርሱም በማስተዋል ብርታት ኃያል ነው።”.. እንዳለ፣ በራሳችን ወይም በሰው ማስተዋል ላይ ተደግፈን ራሳችንን ሳናገኘው በፊት በእግዚኣብሔር ኃይል እና ማስተዋል ላይ መረጋጋት፣ መደላደል ይሁንልን። አሜን!

“በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤”
ምሳሌ 3፥5

       ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
          👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123
     👇👇👇ይቀላቀሉን👇👇👇
        
@jesusofscriptures
        
@jesusofscriptures

የልባም ሴት አገልግሎት

20 Nov, 22:30


🎲Jaalala keessatti " 😀" wanti guddaan miira walii ciminaan hubachuudha. Sababni isaa... ↪️ See More

▶️ See More
See More

Ergaalee Jaalalaa 10...➡️ See More

የልባም ሴት አገልግሎት

20 Nov, 22:28


1. To get motivational and inspiration education channels click here and Join

👇👇

💗 Click here
Click here

2. To get spiritual and books by pdf join us now ☺️

👇👇

 💖  Click here
Click here
.
3K+ Free Promotion addlist: @Getu_Abera

የልባም ሴት አገልግሎት

20 Nov, 18:25


የልባም ሴት አገልግሎት pinned «በዘመናችን በጣም የምንወደው ፣ የምንሳሳለት፣ ባላጣነዉ ከእኛ ባይለየን ብለን የምናስበው ነገር ምንድነው .....? ያን የምንሳሳለትን ነገርስ እግዚአብሔር ይፈልገዉ ይሁን ..? ብቻ እርሱን ደስ ካለዉ ፤ ወዶ ስጡኝ ካለን ያንን የምንወደውን ነገር፤ በህይወታችን ርካሽ የሆነዉን ሳይሆን ዉድ ነገራችንን ለእግዚአብሔር መስጠት እና ማስገዛት ይሁንልን ።🙏😭          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁        👇👇👇👇👇»

የልባም ሴት አገልግሎት

19 Nov, 20:32


🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
ሰበር ዜና በ አጭር ግዜ ተወዳጅነትን የገኙ በአማርኛ በኦሮሚኛ እና በእንግሊዝኛ የሚለቀቁ አስተማሪ ና አዝናኝ ቻነሎችን ይ🀄️🀄️👇👇
Free promotion የሚትፈልጉ
Channel ያላችሁ በ @seer_lewi አነግሩኝ 👇👇👇

የልባም ሴት አገልግሎት

19 Nov, 19:22


በዘመናችን በጣም የምንወደው ፣ የምንሳሳለት፣ ባላጣነዉ ከእኛ ባይለየን ብለን የምናስበው ነገር ምንድነው .....? ያን የምንሳሳለትን ነገርስ እግዚአብሔር ይፈልገዉ ይሁን ..? ብቻ እርሱን ደስ ካለዉ ፤ ወዶ ስጡኝ ካለን ያንን የምንወደውን ነገር፤ በህይወታችን ርካሽ የሆነዉን ሳይሆን ዉድ ነገራችንን ለእግዚአብሔር መስጠት እና ማስገዛት ይሁንልን ።🙏😭
 
       ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
       👇👇👇👇👇
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

18 Nov, 19:01


"አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ፤ አቤቱ፥ አንተ አባታችን ነህ፥ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 63:16)

የልባም ሴት አገልግሎት

17 Nov, 18:39


ልክ እንደ ማርያም

ሰላም😍 ሲስተርስ እንዴት ናችሁ?

³⁸ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ መንገድ ሲሄዱ፣ ኢየሱስ ወደ አንድ መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤቷ ተቀበለችው።
… 
⁴¹ ጌታ ግን እንዲህ ሲል መለሰላት፤ “ማርታ፣ ማርታ፤ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ትዋከቢአለሽም፤
⁴² የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያም እኮ የሚሻለውን ድርሻ መርጣለች፤ ይህም ከእርሷ አይወሰድም።”
ሉቃስ 10 (አዲሱ መ.ት)

ከአንድ ጥያቄያችን ልጀምር ከመንገድ ወደ ቤታችሁ ለገባ እንግዳ ምን አይነት  መስተንግዶ ታድርጉለታላችሁ? እንዴት ትቀበሉታላችሁ? የሚበላዉን ሰርታችሁ ታቀርቡለታላችሁ? ወይስ እሱ እጅ ላይ ያለው ይሻለኛል ብላችሁ እግሩ ስር ቁጭ ትላላችሁ?

➻ማርታ  ከመንገድ ወደ ቤቷ የመጣው ኢየሱስ ምናልባት እርቦት ይሆናል ደግሞ ምትወደው ኢየሱስ ነው እና ቤቷ ሲመጣ ወደ ጓደዋ ገባች ልታሳረፈው ከዛ በምትሰራው ምግብ ልታጠግበው ፣ ልታስደስተው አሰበች ። እንደ አንድ ሰው ሚጠበቅባትን ነው ያደረገችው እኔ የገረመኝ የማርያም ነው ቤቷ ለመጣ ከመንገድ ለመጣ እንግዳ ልታስተናግደው ሲገባ እሷ ግን እግሩ ስር መቀመጥ መረጠች።እሷ ከምታቀርበው ይልቅ እሱ ላይ ያለውን መረጠች የማርያም ደንቆኛል እየሱስን እንዴት አይታው ነው?

በማርታና በማርያም መካከል ያለው ልዩነት ኢየሱስ ቤታቸው የመጣበትን ምክንያት የተረዱበት መንገድ ይመስለኛል። ለማርታ ኢየሱስ የቅርብ ሰው ከመንገድ ደክሞት መጥቶ እሷ በምትሰጠው ምግብም ምታስደስተው ነበር የመሰላት።

➥ለማርያም ግን ኢየሱስ እንደዛ አልነበረም ከሩጫ ይልቅ መቀመጧን፣ ከስራው ይልቅ ከእሷ ጋር ያለን ህብረት ፈልጎ ፣እንጀራ ሳይሆን ህይወት ሊሰጣት ፈልጎ እንደሆነ ገብቷት  ነው  የሆነ ነገር ከማቅረብ ይልቅ ኢየሱስ ጋር መቅረብን የመረጠችው።

ቤታችን የገባው ኢየሱስ ከእኛ አንዳች ነገረ ፈልጎ ሳይሆን  ከኛ ጋር ህብረትን ለመመስረት ፈልጎ ነው።  ስለዚህ አንድ ነገር ልበላችሁ ኢየሱስ ከሩጫችን በፊት እንድንቀመጥ ይፈልጋል ከእርሱ ጋር እንድንቆይ እንድንሰማው ይሻል።

አንድ ነገር ብያችሁ ልጨርስ ኢየሱስ በምናቀርብለት ሳይሆን በመቅረባችን ይደሰታል። አብዝተን መጠጋት ይሁንልን።ተባረኩ

              ✍️ሀና

       ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
          👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

16 Nov, 19:43


"ከትያጥሮን ከተማም የመጣች ቀይ ሐር ሻጭ እግዚአብሔርን የምታመልክ ልድያ የሚሉአት አንዲት ሴት ትሰማ ነበረች፤ ጳውሎስም የሚናገረውን ታዳምጥ ዘንድ
#ጌታ_ልብዋን_ከፈተላት።"
(የሐዋርያት ሥራ 16:14)

የልባም ሴት አገልግሎት

15 Nov, 19:42


"ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥
ጎልምሱ ጠንክሩ።"
(1ኛ ቆሮንቶስ 16:13)

"Watch! Stand firm in the faith! Be courageous! Be strong!"
(1 Corinthians 16:13)

የልባም ሴት አገልግሎት

12 Nov, 17:34


በገደላ ገደል በጪቃ መንገድ ላይ በሚጓጓዝ አለም፣ የፊት ቀዳሚህ ሰው የረገጠበትን ከመርገጥ የሚዘል ብሩህ ተስፋ የለም።

ክርስትናም ልክ እንዲሁ ነው የክርስቶስን ኮቴ ተከትለን የምንጓዘው ረጅም የህይወት ጉዞ፤ በክርስትናችን ውስጥ ቀዳሚ ሰው የምንለው ኢየሱስን ነው። በዚህ ውጥንቅጡ በጠፋበት ገደል እና ጪቃ በበዛበት ዘመን በድጡ ላለመዘፈቅ፣በገደሉ ተውጦ ላለመቅረት አንድ ያለን ተስፋ የቀዳሚውን ሰው የእየሱስን ኮቴ ተከትለን መጓዝ ብቻ ነው።

ኢየሱስ በምድር ላይ የምንመላለስበትን ኮቴ አሳርፎል ቢያልፍም መንገድ ጠቋሚ ሳይሆን እራሱ ወደ አብ መድረሻ  መንገድ ነው። የኢየሱስ መንገድነት የሳተ መድረሻ የለውም መስመሩን ጠብቆ ለተጓዘበት ያለጥርጥር አንድ ፍጻሜ ላይ ያደርሳል፤ እሱም እግዚአብሔር አብ ነው።

የራሱን ኮቴ ተከትለው መንገድ በሆነው በክርስቶስ ላይ የተጓዙ "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተ ደግሞ እኔን ምሰሉ" ለማለት የሚያስችልን ህይወት ኖረው ለማለፋቸው መፅሀፍ ቅዱሳችን ምስክር ነው።

ለጨለማ አለም ብርሀን፣ጣእም ላጣው ህይወት ጥፍጥና፣በሞት መንደር ውስጥ የህወት ሽታ የሚሆንን ህይወት ኖሮ ለማለፍ መንገድ በሆን በክርስቶስ ላይ የራሱን ኮቴ ተከትሎ ከመራመድ የሚዘልቅ ሌላ ጥበብ የለም‼️

“እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።”
ዕብራውያን 12፥1-2

✍️አድስክዳን

     ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
        👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

09 Nov, 19:29


“እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት፤ እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማ።”
— መዝሙር 40፥1

➻ልባሞች እግዚአብሔርን በመጠበቅ የሚባክን ጊዜ የለም‼️
➻ነገራችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቆዩት እርሱም መልካም አድርጎ ይሰራላችኃል‼️
 
 ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
       👇👇👇👇👇
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

08 Nov, 16:47


♨️መኖር በኢየሱስ ለኢየሱስ♨️

በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።
(2ኛ ቆሮንቶስ 5:15)

 አንድ ሰው የሆነ ዋጋ ከከፈለላችሁ ለዚያ ሰው ብላችሁ ብዙ ነገር ልታደርጉለት ትችላላችሁ ነገር ግን
#ነፍሱ_ስለ_እናንተ_አላልፎ_ለሰጠው እናንተን ለማኖር ራሱን አሳልፎ በመስቀል የውርደትን ሞት ለሞተላችሁ በእናንተ  ምትክ ለሞተው ምንድነው ምላሻችሁ

 አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች በችግራችሁ ደረሰው ስለረዱአችሁ ብቻ የእነርሱን ውለታ ለመመለስ ብላችሁ ብዙ የማትፈልጉትን ነገር እንኳ ታደርጋላችሁ
#ለሞተላችሁ_ከዘላለም_የሞት_ፍርድ ላስመለጣችሁ በእናንተ ምትክ ለሞተላችሁ ምንድነው  ምላሻችሁ

#ክርስትና_በመንፈስ_ቅዱስ አማካይነት ስለ እኛ #ለሞተውና_ለተነሣው #ለኢየሱስ_መኖር ነው።

➻መንፈስ ቅዱስ ነው በኢየሱስ እያኖረን ለኢየሱስ የምያኖረን እኛ ያለ መንፈስ ቅዱስ በራሳችን በፍጹም በኢየሱስ እየኖርን ለኢየሱስ መኖር አንችልም ለዚህም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር መጣበቅ የግድ ይለናል‼️

#መኖር በኢየሱስ  ነው‼️
➻መኖር
#ለኢየሱስ  ነው‼️

✔️መኖር ትርጉም የምያገኘው በኢየሱስ በመኖርና ለኢየሱስ በመኖር ነው‼️🔆🔆

➻በቀሪው ዘመናችሁ ስለእናንተ ለሞተላችሁና ለተነሳላችሁ ለኢየሱስ ብቻ መኖር ይሁንላችሁ‼️

➻ልባም ሴት የምትኖርለትን ጠንቅቃ ታወቃለች‼️

➻ለወዳጆቻችሁ Share አድርጉላቸው

@lebamsetministry123
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

06 Nov, 18:45


“በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ....”
  — ኤፌሶን 2፥1

➻ሙት በየትኛውም ዘመን ዋጋ ሲያወጣ ወይም ለሽያጭ ሲቀርብ ተይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ምክንያቱም ሙት ነውና ።የገዛው አካል ከወሰደው በኃላ ምንም ስለ ማይጠቅመው..እንኳን በውድ በርካሽም አይገዛውም !!ምክንያቱም ሙት ነዎ!!!!! ከገዛው በኃላ ምን ያደርገዋል ??🤔🤔....ነገር ግን ሰማይ ይህን ሀሳብ አይቀበለውም እጅግ በጣም ነው የሚያስገርመው 🤭🤭🤭

👉“ በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።”
  — 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥20
ይህን ቃል ስናየው እጅግ ክርስትናችን ሊገርመን ይገባል ሙትን ለመግዛት ዓምላክ ሰው ሆነ ይህ ብቻ አይደለም እኔ ለማዳን ሰው የሆነው አምላክ ሞተ‼️

➻እስቲ አስቡት 🤔🤔እጅግ በጣም ይገርማል‼️   ቆይ ምን ያደርግልኛል ብሎ ነው የገዛው?....ይህን እያሰብን ክርስትናን የምንኖር ከሆነ ይህ ሕይወት አይቀልብንም ...በስጋችን በነፍሳችን እንዲሁም በመንፈሳችን እሱ ማክበር ይሁንልን‼️

➻የሚያስገርመውን የእግዚአብሔር ማዳን እያሰብን መኖር ይሁንልን‼️

#ክርስትና_አይቀልብኝም_ገረመኝ_ማዳንህ‼️

✍️Kali

         ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
         👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123
@jesusofscriptures

የልባም ሴት አገልግሎት

05 Nov, 17:17


FEMINISM\ ዕንስትነት 
       
➻ክፍል ሦስት 3


🎯 ለምንድን ነው ክርስትና እና feminism አብሮ የማይሄደው?

👉🏽የ feminism camp ከሆነው ውስጥ አንደኛው equality feminism እናም ብዙ ክርስቲያን ሴቶች ወደ feminism ሃሳብ እንዲገቡ የሚገፋፋውን ይህን ሃሳብ እንመልከት... ተከተሉኝ...
Equality feminism መልካም ሃሳብን የያዘ ሴቶችን ወደተሻለ እደል የሚጠራ ቢመስልም ከበስተጀርባው ግን ሌላ ነው። Equality feminism ትኩረቱ ሴቶች እና ወንዶች በሁሉም ማዕከል እኩል እንዲሆኑ ላይ ነው( ስራ፣ ቤት ውስጥ፣ ህግ፣ ስነ ጾታ)... ይሄን ማለት በአብዛኛው feminists አመለካከት ሴቶች እና ወንዶች እኩል እና ተመሳሳይ ስራ አላቸው የሴቶች እና ወንዶች ሚና ሳይቀር ተመሳሳይ እንደሆነ ይናገራሉ።

 👉ሌላው feminist ነኝ የሚሉ ዕንስቶች ፈታኝ ጥያቄ የሚሆነው በኤፌሶን “ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤” እንደሚል ለባልሽ ለመገዛት ፈቃደኛ ነሽ? የሚለው ጥያቄ ነው፣ መልሳቸው ሊሆን የሚችለው “no” ነው ምክንያቱም ሴቶችና ወንዶች ፍጹም እኩል ናቸው የሚል እምነት ስላላቸው ነው።

➻From  Hu sister ministry

         ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
         👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

04 Nov, 12:26


FEMINISM\ ዕንስትነት 
        ➻ክፍል አንድ

    Feminism የሚለው ቃል የመጣው ከፈረንሳይ ሲሆን (it is derived from a latin word "femina") ትርጉሙም ሴት ይሰኛል።

የ Feminism ፅንሰ ሃሳብ የተጀመረው ከአውሮፓ በ18ኛ ክፍለ ዘመን ሲሆን ይህ የ Feminism እንቅስቃሴ ዘመቻ በዋናነት የሚያጠነጥነው እና እስካሁን ሲጋደልበት የኖረው ለሴቶች መብት ማለትም:-
👉🏽የመመረጥና የመምረጥ፣ የሕዝብ አስተዳደር ስልጣኖች ለማግኘት፣
እኩል ተከፋይ ለመሆን፣ የራሳቸውን ንብረት ለማፍራት፣ በቂ የትምህርት እድሎች ለማገኘት፣ ስምምነቶች (contracts) ላይ ለመግባት፣ በትዳር ውስጥ እኩል መብት ለማግኘት፣ የስራ እረፍት ከወሊድ በፊት እና በኋላ ለማግኘት (maternity leave )፣ የወሊድ መቆጣጠሪያ እና የዕርግዝና መከላከልያ(contraception) ፣ ህጋዊ ፅንስን የማስወረድ መብት( legal abortion) ፣ የሴቶችና የህጻናት ጥቃቶችን መከላክል፣ ወሲባዊ ጥቃት (sexual harassment) እና Domestic violence ፤ ከዚህም በተለየ አቅጣጫ ደግሞ የሴቶች የአለባበስ ሰነስርዓትቶችን እና ደንቦችን መቀየር እና ሌሎችም ጉዳዮች ናቸው። 
ይህ የፌሚኒዝም ሃሳብ ትኩረት የሚያደርገው ምንም ያህል ሴቶች ላይ ቢሆንም በተወሰነ ደረጃ የወንዶችን የነፃነት መብትን ለማካተት ይሞክራል። እንዲህ እንዲህ እያለ ታድያ ብዛት ያላቸውን የfeminist እንቅስቃሴዎች፣ የፖለቲካ ዘይቤዎች ይዞ እያደገ መጣ


➻በቀጣይ ክፍል ጠብቁን

➻From Hu sister ministry

         ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
         👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

03 Nov, 18:28


✝️ኢየሱሴ አንተ ማለት በእኛ ህይወት
ምንሞቅብህ ፀሀያችን ነህ
ምናበራብህ ከዋክብታችን ነህ
ምንደምቅብህ ኮከባችን ነህ
ምንጓዝብህ መንገዳችን ነህ
ምንታይብህ መታያችን ነህ
ምንጠራብህ ስማችን ነህ
ምንቆምብህ ድጋፋችን ነህ
ምንከናወንብህ ስኬታችን ነህ
ምንከበረብህ ክብራችን ነህ
ምንኖርብህ መኖሪያችን ነህ
ምንተነፍስብህ አየራችን  ነህ
ምንኩራራብህ ኩራታችን ነህ
ምንሸሸግብህ መሸጊያችን ነህ

➻ኢየሱስ አንተ ሁሉ ነገራችን ነህ‼️
              
✍️hana

         ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
         👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

02 Nov, 17:36


“ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ
እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ።”
  — ፊልጵስዩስ 1፥9-11

በዚህ ክፍል ሦስት ነገር  መመልከት እንችላለን ይህም የአብን ክብር ፤በክርስቶስ በኩል ፍሬን ማፍራትን እንዲሁም ከእኛ የሚጠበቀውን ሀላፊነትን....

በየትኛውም ዘመን ያለ ገበሬ የሚከበረው በእርሻው ስፋት ሳይሆን በሚያመጣው ፍሬያማነት ነው።  ስለዚህ እኔም እንዲሁ እናንተ አብ የምናከብረው ከምናፈራው ፍሬ ነው። ይህ ደግሞ በእራሳችን ማድርግ እንደማንችል  ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ቤ.ያን  በፃፈው ደብደቤ ላይ አይተናል፤የጽድቅን ፍሬ ማፍራት የምንችለው በክርስቶስ እየሱስ ብቻ ነው!!

👉በክርስቶስ በኩል ፍሬን ስናፈራ የምንጠቀመው ጥቅም

1 አብ በእኛ ይከብራል!!
“ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።”
  — ዮሐንስ 15፥8
2 የጌታ መሆናችንን በዚህ ይታወቃል!

“እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።”
  — ዮሐንስ 13፥35
3 በምፃቱ (በመጣቱ) ጊዜ አለ ነውር እንድንሆን ያደርገናል ።
“ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ ........
  — ፊልጵስዩስ 1፥9-11

#እግዚአብሔር_በክርስቶስ_በኩል በሆነ ፍሬያማነት ይባርከን‼️

✍️kali
@lebamsetministry123

         ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
         👇👇👇👇👇
 
@jesusofscriptures

የልባም ሴት አገልግሎት

29 Oct, 18:46


        
          ▷ድንቅ ዝማሬ◁

        ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
         👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

28 Oct, 17:21


እንደ ሰው ቢቀርበኝም ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደኔ  ቢመጣ
ከላይ ከሰማያት ከከበረ ስፍራ ወርዶ እንደመጣ
ይህንን አምናለው እኔ እቀበላለሁ
መንደሬ ቢገኝም እሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው
እኔን ሊያድን ብሎ በደዌ ቢደቅም
ሰው ብቻ ነው እሱ ብዬ አልታለልም
ይህን አምናለው እኔ እቀበላለሁ
መንደሬ ቢገኝም እሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው!! 🙏🙏

                 ✍️kali

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

27 Oct, 18:29


✝️ምህረቱ አይቀልብኝም‼️

⁴ ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥
⁵ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥
➻ኤፌሶን 2፡4-5

#የምህረት ብዛት የትላንት ማንነቴን በነበር አስቀረው ....

#ሙት ለነበረው ማንነቴ ሕይወትን ሰጠኝ ምህረት አይቀልብኝም‼️

✍️kali

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

26 Oct, 19:27


"እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:10)

የልባም ሴት አገልግሎት

25 Oct, 18:07


⁴ እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ።
⁵ ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ ፊታችሁም አያፍርም።

መዝሙር 34፥4-5

የልባም ሴት አገልግሎት

24 Oct, 18:42


✝️የመስቀሉ ፍቅር✝️

"ጎልጎታ ነኝ:: አንተ ተሰቀልህ የተባልህበት ስፍራ:: እናትህ ማሪያም ተስፋ ያደረገሁ ደቀመዝሙሮችህ ቆመው ተስፋቸው በእንጨት ከወንበዴዎች እንደ አንዱ ተንጠልጥሎ ያዩበት ስፍራ እዛ ተሰይሜያለሁ:: ስላልገባኝ ነው የመጠሁት:: ሰው መሆኔን እስክጠራጠር ድረስ ሌሎች ልብ ላይ ገብቷቸው ከአይናቸው እንባ ሲፈስ ልቤ ላይ የማስመሰል እና የመመሳሰል መረዳት ካልሆነ ይሄ የመስቀልህ ሚስጥር ከልቤ አልገባ ስላለኝ ነው የመጣሁት:: በቤትህ ነው ያደግኩት በጓዳህ ተሸሽጌ:: እየታዘዝኩህ አለምን ለአንድ አፍታ ሳላስባት:: ግና እራሴን እያታለልኩ እንደሆነ አልታወቀኝም ነበር:: ለምንድነው የማይገባኝ ብዬ አውቃለሁ:: መፅሐፍ ቅዱሴን አንብቤያለሁ ከፊት ዘምሬያለሁ:: አሜን ብያለሁ:: ግን አሁን አልክድህም የመስቀልህ ፍቅር ከቃላት ውጭ አልገባኝም:: ሲሰበክ ሞቅታ እንጄ ስሜቱ ከውስጤ የለም:: ይሄ ታዲያ ጴጥሮስ ሶስቴ ከካደህ ይተናነሳልን.... ከይሁዳ ዲናርስ የከፋ አይደለምን?..... ሳላምንህ አመንኩሁ አልኩህ ወይስ የሆነ የተላለፍነው ነገር አለን?..... ብቻዬን ያልገባኝ እኔ ሆንኩኝ ወይስ አብረውኝ አሉ..... የመስቀሉ ፍቅር ያልገባኝ ከርታታው ልጅህ ነኝ እና ያልተሰበረውን ልቤን ስበርልኝ እና ልጅነትህን ልኑርረው::"

#ይሄ ጩሀት የአንድ ሰው ይሆንን?

✍️Mercy

       ♻️Share♻️Join♻️
❇️
@lebamsetministry123❇️
❇️
@lebamsetministry123❇️

የልባም ሴት አገልግሎት

23 Oct, 18:52


መዝሙር 63

¹ አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።
² ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ።
³ ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።
⁴ እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፥ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።
⁵ ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች፥ ከንፈሮቼም ስምህን በደስታ ያመሰግናሉ።
⁶ በመኝታዬም አስብሃለሁ፥ በማለዳም እናገርልሃለሁ፤
⁷ ረዳቴ ሆነኸኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ ደስ ይለኛልና።
⁸ ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች፥ እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ።

       ♻️Share♻️Join♻️
❇️
@lebamsetministry123❇️
❇️
@lebamsetministry123❇️

የልባም ሴት አገልግሎት

22 Oct, 20:16


የለበትም‼️

➢የለበትም በሚክራቸው መሀል
 
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

22 Oct, 18:42


ይህን ታሪክ በማንበባችሁ አትቆጩም‼️

አንድ ቀን መምህሩ ወደ ማስተማሪያ ክፍሉ ከገባ በሁዋላ ተማሪዎቹን ለድንገተኛ ፈተና እንዲዘጋጁ ይነግራቸዋል። ተማሪዎቹ ያልጠበቁት ፈተና ስለሆነ በጭንቀት ጥያቄውን ይጠባበቁ ጀመር።

መምህሩ፣ ጥያቄ የሰፈረባቸውን ወረቀቶች ለተማሪዎቹ በጠረጴዛ በጠረጴዛቸው ላይ አስቀመጠላቸው፡፡ ከዚያ ወረቀቱን ለሁሉም ተማሪዎች ካዳረሰ በሁዋላ፤

‹‹አሁን መጀመር ትችላላችሁ›› አላቸው፡፡

ሁሉም እየተጣደፉ ወረቀቱን ገልብጠው ሲያዩት አንድም ጥያቄ የለም፡፡ ደነገጡ። ከዚያ ልብ ብለው ሲያጤኑ ወረቀቱ መሐል ላይ አንዲት ጥቁር ነጥብ አለች... ከእሷ ውጭ ሌላ ነገር የለም፡፡ ዞር ዞር እያሉ እርስ በእርስ ተያዩ፡፡ መምህሩ ይሄን ግዜ እንዲህ አላቸው፡፡

‹‹ወረቀቱን ስታዩ እንደተደነቃችሁ እያስተዋልኩ ነው፡፡ በሉ ያያችሁትን ጻፉ... ፈተናው ምን እንዳያችሁ በትክክሉ መጻፍ ነው፡፡››

ተማሪዎቹ በድጋሚ ተያዩና ወደ ወረቀቱ አቀርቅረው የመሰላቸውን መሞነጫጨር ጀመሩ።

ለፈተናው የተመደበው ጊዜ አለቀና ወረቀቱ ሁሉ ተሰበሰበ። ከዚያ መምህሩ እያንዳንዱን ወረቀት እያነሳ ተማሪዎች የሰጡትን መልስ ጮክ ብሎ ያነብላቸው ጀመር። የሚደንቀው ነገር ሁሉም ተማሪዎች ለማብራራት ሲጣጣሩ የነበረው ስለዚያች ጥቁር ነጥብ እንጂ ስለሌላ ነገር አልነበረም፡፡

ነጥቧን በተመለከተ እያንዳንዳቸው፥ ስለ ጥቁረቷ፣ ስላለችበት ቦታ፣ ስለ ግዝፈቷ፣ ስለሌላም ሌላም ጥቁሯን ነጥብ ስለተመለከቱ ጉዳዮች ትንታኔዎችን አቅርበዋል፡፡

መምህሩ አንብቦ ሲጨርስ ዐይኑን መለስ ቀለስ እያደረገ የተማሪዎቹን ፊት ሲያስተውል ቆየ፡፡ ከዚያም ‹‹ተማሪዎች አንዳችሁም ትክክለኛ መልስ አልሰጣችሁም። ስለዚህ ይሄን ፈተና ውጤት አልሰጥበትም፡፡ ነገር ግን አንድ ነገር ላስተምራችሁ እፈልጋለሁ›› አላቸው፡፡

ሁሉም ተማሪ መምህሩ የሚናገረውን ለመስማት ጓጉተው መጠበቅ ጀመሩ። መምህሩም ንግግሩ ቀጠለ።

‹‹ከመካከላችሁ አንዳችሁም ስለነጩ ወረቀት አልጻፋችሁም፡፡ ሁላችሁም ትንሽዬዋን ነጥብ ዐይታችሁ፥ ትልቁንና ሰፊውን ወረቀት እስከናካቴው ረሳችሁት፡፡

በሕይወታችሁም ላይ አንዲት እንከን ስታገኙ በዚህ መልኩ ያላችሁን ጸጋ ሁሉ ጠቅልላችሁ የምትረሱ ከሆነ በጣም ትጎዳላችሁ።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ መልካም ስጦታዎች እያላችሁ ስለ አንዲቷ እንከን አብዝታችሁ የምታስቡ ከሆነ እውነቴን ነው የትም አትደርሱም፤ ቆሻሻ ውስጥ ትቀራላችሁ።
የገንዘብ ማጣቱ አስጨንቋችሁ ታማርሩ ይሆናል፤ ነገር ግን ከገንዘብ የበለጠ ጥሩ ፍቅር፣ ጥሩ ጤና፣ ጥሩ ሰላም፣ ጥሩ ቤተሰብ ወዘተ ካላችሁ ዓለም ላይ ተዓምር መሥራት ትችላላሁ።

ስኬታማ ሕይወት ለመምራት ዋናው ነገር ያላችሁ ዐቅም ስፋት ላይ ማተኮር ስትችሉ እንጂ የጎደላችሁ ኢምንት ነገር ላይ ስታተኩሩ አይደለም፡፡

እንዲህ ማሰብ ከጀመራችሁ ያለጥርጥር እንደ እናንተ ደስተኛ ሰው አይኖርም፡፡ በተቃራኒው ጉድለት ብቻ ተመልካች ከሆናችሁ ምንም ብታገኙ እርካታ የሚባል አይኖራችሁ፡፡››

ወዳጆቼ ባላችሁ ነገር ደስተኛ መሆን ስትጀምሩ ነው ባናቱ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገር የሚጨመርላችሁ...

✍️መሳፍንት
 
         ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
         👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

21 Oct, 17:23


🔐ብቸኛው መፍትሄ ራስን ማሻሻል ነው‼️

➻አምናችሁትና ሁለንተናችሁን ሰጥታችሁት ሳለ፣ የከዳችሁ ሰው ካመጣባቸው የስሜት ቀውስ አልፎ የመሄጃው ብቸኛው መፍትሄ ራስን ማሻሻል ነው፡፡ ቁጭ ብሎ ያ ሰው እንዲወድቅና ክፉ ነገር እንዲገጥመው መመኘት ኋላ ቀርነትን ያስከትላል፡፡

➻በየጊዜው እየተለዋወጠና እየከበደ ከሚሄደው የኑሮ ሁኔታ ባሻገር የማደጊያው ብቸኛው መፍትሄ ራስን ማሻሻል ነው፡፡ ቁጭ ብሎ የኑሮ ሁኔታ እስኪስተካከል መጠበቅ ኋላ ቀርነትን ያስከትላል፡፡

➻በምንም አይነት አቀራረብ ብትቀርቡ እጅጉን አስቸጋሪ ባህሪይ ካለው ሰው በላይ ተሽሎ የመገኛው ብቸኛው መፍትሄ ራስን ማሻሻል ነው፡፡ ስለሰውየው ክፋት ሲያስቡና ሲያወሩ ውሎ ማደር ኋላ ቀርነትን ያስከትላል፡፡

➻ምንም ያህል በታማኝነት ብትሰሩላቸው ከምንም የማይቆጥሩና ስለራሳቸው ጥቅም ብቻ እንጂ ስለእድገታችሁ ግድ ከማይሰጣቸው ሰዎች አልፎ የመሄጃው ብቸኛው መፍትሄ ራስን ማሻሻል ነው፡፡ ሰዎች ለምታሳይዋቸው ታማኝት ዋጋን እስኪከፍሏችሁ ድረስ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ኋላ ቀርነትን ያስከትላል፡፡

➻ካለፈው ምርጫና ውሳኔችሁ አሉታዊ ተጽእኖ አልፎ በመሄድ ዓላማን የማሳኪያው ብቸኛው መፍትሄ ራስን ማሻሻል ነው፡፡ ስላለፈው ሲያወጡና ሲያወርዱ መዋል ኋላ ቀርነትን ያስከትላል፡፡

የአብዛኛዎቹ ችግሮቻችን ብቸኛውና ዘላቂ መፍትሄ፣ ራስን ማሻሻል ነው‼️

✍️Dr eyob mamo

       ♻️Share♻️Join♻️
❇️
@lebamsetministry123❇️
❇️
@lebamsetministry123❇️

የልባም ሴት አገልግሎት

20 Oct, 20:02


"መልካሙን ሥራችሁን አይተው
በሰማያት ያለውን
#አባታችሁን #እንዲያከብሩ_ብርሃናችሁ
እንዲሁ
#በሰው_ፊት_ይብራ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 5:16)

የልባም ሴት አገልግሎት

19 Oct, 21:55


♻️Share♻️Join♻️
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

18 Oct, 18:41


“ማርያምም፣ “እነሆ፤ እኔ የጌታ ባሪያ ነኝ፤ #እንደ_ቃልህ #ይሁንልኝ” አለች።.......።”
— ሉቃስ 1፥38 (አዲሱ መ.ት)

#ጌታ_ይፈጸማል_ብሎ_የነገራትን #ያመነች_እርሷ_የተባረከች ናት!””
— ሉቃስ 1፥45 (አዲሱ መ.ት)

የልባም ሴት አገልግሎት

18 Oct, 18:35


"ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።"
(የሉቃስ ወንጌል 1:49)

የልባም ሴት አገልግሎት

16 Oct, 18:35


👉👉#ምክር_ለወጣት_ሴቶች👈👈

ሁለት ወጣት ሴቶች የሰውነታቸውን ክፍል አጋልጦ የሚያሳይ ልብስ ለብሰው ወደ አንድ ስብሰባ ደረሱ፡፡
የስብሰባው መሪ በደንብ ካያቸው በኋላ እንዲቀመጡ አደረገ፡፡ ከዛ በኋላ የተናገራቸው ንግግር ምናልባት በህይወት ዘመናቸው ሙሉ የማይረሱትን ንግግር ነው፡፡
አይን አይናቸውን እያየ እንዲህ አላቸው
"እናንተ ሴቶች እግዚአብሄር በምድር ላይ የፈጠራቸው ውድ ነገሮች በሙሉ በደንብ የተሸፈኑና ለማየትም ሆነ ለማግኘት የሚከብዱና ዋጋ የሚያስከፍሉ ናቸው፡፡

👉አልማዝ የት ነው ምታገኙት? በመሬት ጥልቅ ውስጥ! ተሸፍኖና ተጠብቆ

👉ዕንቁ የት ነው ምታገኙት በውቅያኖስ የታችኛው ጥልቅ ክፍል ውስጥ!

👉ወርቅንስ ከየት ነው ምታገኙት? ወደታች ብዙ ቆፍራችሁ፣ በአለቶች ተሸፍኖ ነው! እሱን ለማግኘት ብዙ መልፋት አለባችሁ"

ኮስተር ብሎ አያቸውና ንግግሩን ቀጠለ
"ሰውነታችሁ ውድና እና ልዩ ነው፡፡
ከወርቅ ከአልማዝና ከዕንቁ ሁሉ ይልቅ እጅግ ውድ ነው፡፡ ስለዚህ እናንተም መሸፈን አለባችሁ፡፡

የከበረውን ማዕድናችሁን እንደ ወርቅና አልማዝ በደንብ ከደበቃችሁት የማዕድን አውጪ ድርጅቶች ከአስፈላጊ ማሽኖች ጋር
#በጨረታ ተወዳድረው የአመታት ፍለጋ ለመድረግ ይሰለፋሉ፡፡

በመጀመሪያ መንግስታችሁን (
#ቤተሰባችሁን) ይጠይቃሉ፡፡ ከዛም ሙያዊ ኮንትራት ይፈርማሉ(#ሰርግ) በመቀጠል በሙያቸው መሠረት ማዕድን የማውጣቱን ስራ ይቀጥላሉ(ህጋዊ #ትዳር)

ነገርግን ውዱን ማዕድናችሁን ካልሸፈናችሁትና በግልጥ ካስቀመጣችሁት ማንም ህገወጥ ማዕድን አውጪ መጥቶ በማይረባ መሳሪያ ነካክቶ እንደ ጠጠር በቀላሉ ይወስድበችኋል፡፡

#ሰውነታችሁ_እንቁ_ነውና_ደብቁት

ወንድሞች እህቶቻችሁን ፣ ባሎች ሚስቶቻችሁን ፣ እናም ወላጆችም ሴት ልጆቻችሁን መልካም አለባበስ እንዲለብሱ አበረታቷቸው።🙏🙏🙏

🔊ለሚመለከተው ሁሉ
#ሼር

✍️ልባም

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
❇️
@lebamsetministry123❇️
❇️
@lebamsetministry123❇️

የልባም ሴት አገልግሎት

16 Oct, 08:07


19፤ የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ #እግዚአብሔርም_ከሁሉ #ያድናቸዋል

20፤ እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥ ከእነርሱም አንድ አይሰበርም።

(መዝሙረ ዳዊት 34)

የልባም ሴት አገልግሎት

15 Oct, 19:42


💥💥💥"የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤ #በብርሃንህ #ብርሃንን_እናያለን።"
💥💥💥
(መዝሙረ ዳዊት 36:9)

የልባም ሴት አገልግሎት

15 Oct, 19:38


💥💥💥" ... እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም.. ።"
(1ኛ ዮሐንስ መልዕክት 1:5)

የልባም ሴት አገልግሎት

14 Oct, 18:24


።።።።።።።ማንነት።።።።።።

ማንነት የአንድ ሰው መገለጫ ነዉ ባሕሪ ግልጽነት ቁጣ ነጻነት ወዘተ። እራስን ማወቅ እና ራስን መሆን አንቺ ማን እንደሆንሽ ማወቅ ማለት ነው ለኔ 🤔
ማንም ሰዉ አንድ አይነት አደለም ልክ እኔን ሚመስል ማንም ሰዉ የለም እንደኔ አይነት የጣት አሻራ ያለዉም የለም። ብዙ ሰዎች ማንነታቸውን አይወዱትም አይቀበሉት። የራሳችንን ማንነት ሳንወድና ሳንቀበል የሌላዉን ማንነት መቀበልና መዉደድ አንችልም። ማንነታችንን መቀበል መዉደድ አለብን ምክንያቱም ያ ለእኛ የተሰጠን ማንነት ስጦታችን ስለሆነ ልንወደውና ልንቀበለው ይገባል።
ያ ማለት ግን ማሻሻል ያለብንን ባህሪ አናሻሻልም ማለት ግን አይደለም።
እኔ እኔነቴን ማንነቴን እወደዋለሁ
እናንተስ

               ✍️ሕሩት

       ♻️Share♻️Join♻️
          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
❇️
@lebamsetministry123❇️
❇️
@lebamsetministry123❇️

የልባም ሴት አገልግሎት

13 Oct, 14:29


“ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥
በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።”
— መዝሙር 23፥6


@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

12 Oct, 18:14


“ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ #ትቀደሱም _ዘንድ _ፈልጉ፥
ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።”
— ዕብራውያን 12፥14

የልባም ሴት አገልግሎት

11 Oct, 18:39


"ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው።"
(መዝሙረ 34:17)

የልባም ሴት አገልግሎት

09 Oct, 18:28


🎗️ምክንያት ወይስ ዲሲፕሊን?

“ምክንያት (excuses) ዛሬን ቀላል ቢያደርግልንም ነገን ግን ከባድ ያደርገዋል፡፡ ዲሲፕሊን ዛሬን ከባድ ቢያደርግብንም ነገን ግን ቀላል ያደርግልናል”

ማድረግ እንደሚገባችሁ እያወቃችሁ ዲሲፕሊን ለማዳበር ከባድ እንደሆነ ስላሰባችሁ ብቻ ላለማድረግ ምክንያት በማብዛት ችላ ያላችኋቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው?

➙ግድ የላችሁም፣ ቢከብድም ጀምሩት፣ ቢያለፋም ቀጥሉት፣ አድካሚ ቢሆንም ፈጽሙት‼️

➙ትንሹን ነገርን ማድረግን አትናቁ ምክንያቱም ድስፕሊን የምዳብረው ከትንሹ ነገር በመነሳት ነውና ወደ ትልቁም ድስፕሊን ለማደግ ድልድይ ይሆናችኃልና‼️
✍️ነገሽ የሚወሰነው (Deterimine ምደረገው) ዛሬ ላይ ባለሽ ነገር ወይም ባለሽበት ሁኔታዎች ሳይሆን ዛሬ ላይ ሆነሽ ባለሽ ድስፕሊን ነው።

ሕይወት ዛሬ ቀለል ብሏችሁ ነገ ከሚከብዳችሁ፣ ዛሬ ከበድ ብሏችሁ ነገ ቀለል ቢላችሁ ይሻላል፡፡

#ልባም ሴት የድስፕሊን ሴት ናት‼️

       ♻️Share♻️Join♻️
          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
❇️
@lebamsetministry123❇️
❇️
@lebamsetministry123❇️

የልባም ሴት አገልግሎት

07 Oct, 18:11


♨️ወደ ጸጋው ዙፋን ቅረብ♨️

✍️የብርታትሽ ምንጭ ወደ ጸጋው መቅረብ ስሆን የድካምሽ ምንጭ ከጸጋው መራቅ ነው።

✍️አማኝ ከሆንሽ ከጸጋው ውጭ ለላ ምንም አይነት መበርቻ የለሽም‼️

✍️ደክሞሻል መጸለይ፣ ቃል ማጥናት ፣ መንፈሳዊ ሕብረት ማድረግ አቃተሽ አይዞሽ የእግዚአብሔር ፀጋ አለልሽ ወደ ፀጋው ዙፋን በእምነት ብቻ ቅረብ የምያበረታሽን ጸጋን ትቀበያለሽ ከዚያስ ስትይ ሰማው ልበል👂 ከዚያማ ኃይለሽ ይታደሳል እንደ ንስር 🦅🦅🦅 ትበርያለሽ፣ ትሮጭያለሽ አይታክትሽም፣ ትሄጅያለሽ አይደክምሽም ሀሌሉያ ‼️

#ጸጋው_ሁልጊዜ_ዝግጁ
(available)ነው‼️

"እንግዲህ
#ምሕረትን_እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ #የሚረዳንን_ጸጋ እንድናገኝ ወደ #ጸጋው_ዙፋን_በእምነት #እንቅረብ።"  (ዕብራውያን 4:16)
    
♨️አሁን በእምነት ወደ ጸጋው ዙፋን ቅረቡ በኢየሱስ ስም ዛሬ የምያበረታችሁን ጸጋ በእምነት መቀበል ይሁንላችሁ‼️

    ♻️Share♻️Join♻️
         ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
❇️
@lebamsetministry123❇️
❇️
@lebamsetministry123❇️

የልባም ሴት አገልግሎት

06 Oct, 18:45


♨️ብልህ ሴት♨️

👉ልባም ሴት ብልህ ሴት ናት‼️

🧠 ብልህ ሴት እልህ ሳይሆን እምነት
ችኩል ሳትሆን ትዕግስተኛ
ስሜታዊ ሳትሆን መንፈሳዊ
ታማኝ ብቻም ሳትሆን አማኝም
ሰነፍ ሳትሆን ታታሪ: 🧠
የቅርቡን ብቻ ሳይሆን የሩቅ አሳቢ ነች።
ብልህ ሴት ጎጆዋን አትበትንም ቶሎ ተስፋ አትቆርጥም አመለኛ ሳትሆን ብልሃተኛ  ነች ቶሎ ብሽቅ ብላ የሰበሰበችውን አትበትንም።

👉ልባም ሴት ብልሃተኛ ሴት ናት
የምታደርጋቸውን ነገሮች በብልሃት የምታደርግ ነች።

"ብልሃተኛ ሴት ቤትዋን ትሠራለች፤ ሰነፍ ሴት ግን በእጅዋ ታፈርሰዋለች። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 14:1)

✔️እግዚአብሔር በብልሃት መንፈስ ይባርካችሁ‼️
  
         ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
@lebamsetministry123
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

04 Oct, 18:57


“በየትኛው መንገድ ልሂድ?”

“አንድት ሴት በመንገድ ላይ ስትሄድ ወደ መስቀለኛ መንገድ ላይ ደረሰች። አንድ ሰው በመንገድ ስሄድ አገኘችውና እንድህ ብላ ጠየቀችው፣ በየትኛው መንገድ ልሂድ? ብላ ጠየቀች። በመንገድ ይሄድ የነበረውም ሰው  ወዴት መሄድ ትፈልጊያለሽ ብሎ ጠየቃት? የእሷም ምላሽ፣ የምሄድበትን አላውቅም የሚል ነበር፡፡ ከዚያም ያገኘችው መልስ፣ እንግዲያው በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብሽ ማወቅሽ ትርጉም የለውም  የሚል ነበር”

ምን አይነት መንገድ መከተል እንዳለብን ፣ ጊዜያችንን ምን ላይ ማሳለፍ እንዳለብን፣ . . . ግራ ከገባን ቀድሞውኑ የምንሄድበትን አቅጣጫ አውቀን ስላልተነሳን ነው፡፡

የምትሄዱበትን መንገድ ለይታችሁ ካላዎቃችሁ የደረሳችሁበት ስፍራ ሁሉ መቆሚያችሁ ልሆን ይችላል።

የምትሄዱበትን መንገድ ለይታችሁ ማወቅ የጉልበትን፣ የጊዜን፣ የገንዘብን የዕድሜን ብክነት እንድትቀንሱ ያደርጋችኋል።

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

03 Oct, 10:13


ቶሎ ቶሎ ያረጅብኛል የምሰማው የሚያወሩኝ በዙሪያዬ መቼም #መቼም_ማታረጅብኝ_ኢየሱስ ነህ ያንተ ክብርህ ጌታዬ...

የልባም ሴት አገልግሎት

01 Oct, 17:14


🙏በመንፈስ መፀለይ🙏

√ፀሎት ለአማኝ ዋናውና ቁልፉ ከሆኑ መንፈሳዊ መርህዎች አንዱ ነው 
√የሚመለስ ፀሎት በእምነት የተፀለየ ፀሎት ነው
√እግዚአብሔራዊ እምነት የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ይፈጠራል
√ውጤታማ ፀሎት እንደ እግዚአብሔር ቃል የተፀለየ ፀሎት ነው
√ፊሊ 4÷4-7
√ፀሎት ከአባታችን ከእግዚአብሔር ጋር በመንፈስ ህብረት የምናደርግበት እንጂ ጎዶሎ ነገራችንን ለመሙላት ወይም የምንፈልገውን ለመናገር የምናደርገው ነገር አይደለም
√ፀሎት እግዚአብሔር ስለእኛ የማያውቀውን ነገር የምናሳውቅበት  ሳይሆን በመንፈስ ከጌታ ጋር ህብረት የምናደርግበት በመንፈስ የምንነካካበት ነው።
√በእኛ ውስጥ በማይነገር መቃተት የሚማልደው መንፈስ ቅዱስ ነው።
ሮሜ 8÷26-27
√መንፈስ ቅዱስ በተጋበዘበት ህይወት ይሰራል፤ነገር ግን በር በተዘጋበትና ባልተጋበዘበት ህይወት አይሰራም
√ማንም ያለ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፀለይ አይችልም
√መንፈስ ቅዱስ ሃይል ይሰጣል፣በድካም ያግዛል እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መኖር ምንችልበትን ፀጋ ይሰጠናል...!!

👉በመንፈስ መፀለይ ከእግዚአብሔር  ጋር ያለን ሕብረት እና ጌታ ለኛ ያለውን ሀሳብ ማወቅ ያስችላል።

👉አብዝተን በመንፈስ መፀለይ ይብዛልን...!!!!!  አሜን 🙏ተባረኩ

✍️ሩት ካሱ

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

29 Sep, 16:40


🚨ህልምሽን ኑሪው እንጂ በህልም ውስጥ አትኑሪ‼️

📌 ህልምን መኖርና በህልም ውስጥ መኖር በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው።
ህልምን መኖር ማለት ውሳኔን፣ድርጊትን/ተግባርን፣አቅም፣ጉልበት፣ሀይልን፣ፅናትና ተስፋ አለመቁረጥን የሚጠይቅ ሂደታዊ ነገር ነው።
በተጨማሪ ትልቅ የሆነ ትጋትና ዋጋ መክፈልን ይጠይቃል። መጨረሻውም ያማረና  ፍሬ ያለው ይሆናል ። 🍊🍇
   
    በህልም ውስጥ መኖር ማለት
የሰውን ልጅ በጣም ደስተኛ ያደርጋል 😄መትጋት ፣መጣር ፣ምንም አቅምና ፅናት አይጠይቅም እራስን ማስነፍ ፣ከመጠን በላይ መተኛትና ለብቻ ሆኖ ማሰብን እንጂ 🤔።የሆነ ነገር በድንገት እንዳገኘን አና እንዲኖረን የፈለግነው ነገር እንዳለንና ምኞታችን እንደተፈፀመለት እያሰብን ምንም የተጨበጠ እውነታ በሌለበት በሀሳብ ብቻ እንድንነጉድ ያደርገናል ።   ይሄ ሁኔታ ለዛች ላሰብንባት ደቂቃ ደስተኛ ያደርገናል ።ውጤቱ ግን  እጅግ የከፋ ነው
#1 የማይጨበጥ የማይዳሰስ የሀሳብና የምኞት ጉዞ ውስጥ ብቻ እንድንዋዥቅ/እንድንሳፈፍ ያደርገናል።🚣‍♀
#2 ብቸኛና ምንም የሌለን ባዶ በሁሉ ምናማርር በአምላክም በሰውም ምናጉረመርም በብዙ ተስፋ መቁረጥና በdipretion ውስጥ እራሳችንን እናገኘዋለን ።🤦‍♀
   ነገር ግን ከሁሉ ሚከፋው በህይወታችን ውስጥ ውድና ምንም ብንቆጭ ልንመልሰው የማንችለውን ነገር ይውስድብናል እሱም ጊዜ ጊዜያችንን እድሜያችንን ያሳጣናል ይሄ ያለና የአብዛኞቻችን እውነታ ነው።

🔆በስተመጨረሻ ይህን ልበላቹ

አንተ ታካች፥እስከመቼ ትተኛለህ?
ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሳለህ ?
ጥቂት ትተኛለህ ፥ጥቂት ታንቀላፋለህ ፥ ትተኛም ዘንድ ጥቂት እጅህን ታጥፋለህ ፣ እንግዲህ ድህነት እንደ ወንበዴ ችጋርህም  ስይፍ እንደታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።
(ምሳሌ 6:9-11)

እግዚአብሔር በሰነፍ ሰው አይደሰትም በተቻለን መጠን ንቁና ታታሪ እንድንሆን ይፈልጋል።
በህልም ውስጥ መኖር ትተን ህልማችንን ለመተግበር እንጨክን/እንወስን እግዘብሔርም ከእኛ ጋር ይሆናል ።

       By lidiya
#Share

         ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
           👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

27 Sep, 17:49


🔊 የጓደኝነት የምርጫ

  ✍️አመለካከትሽ የምትመርጭውን ጓደኛ ይወስናል፤ አብረሽ የምትከርምው ጓደኛ ደግሞ በተራው አመለካከትሽን የመወሰን ጉልበት ስላለው ወደ ሕይወትሽ ዘልቆ እንዲገባ የምትፈቅጅላቸውን ሰዎች በጥንቃቄ መምረጥ መቻል አለብሽ፡፡

“ጓደኝነት እንደ ሊፍት (Lift / Elevator) ነው፡፡ ወይ ወደላይ ያወጣሻል ወይም ደግሞ ወደታች ያወርድሻል” የሚል አባባል አለ፡፡

ሌላ ረዘም ላለ ጊዜ የከረመ አባባል፣ “በአጠገብህ የሚገኙ የአምስቱ ቅርብ ጓደኞችህ ጭማቂ ነህ” ይባላል፡፡

  ✍️እነዚህ አባባሎች ልቦናን የሚያነቃ እውነት ይዘዋል፡፡ የቅርብ ጓደኞችሽ የያዥሽበት የራስሽ የሆነ ምክንያት ቢኖርሽም፣ ለውጥ ለማምጣት በምትፈልግበት ጊዜ በዙሪያሽ የሚገኙት ሰዎች ምን አይነት ሰዎች አንደሆኑ ማሰብ መጀመርሽ አይቀርም፡፡

"ብረት ብረትን ይስለዋል፥ ሰውም ባልንጀራውን ይስላል። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 27:17)

🔊ልባሞች ጓደኞቻችሁ እኔማን ናቸው

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123

የልባም ሴት አገልግሎት

25 Sep, 17:52


➧➧አትበደሪ‼️

"ብርታትና ከበሬታ ልብስዋ ነው፤ በኋላም ዘመን ላይ ትስቃለች።"
(መጽሐፈ ምሳሌ 31:25)

*ነገ ስለሚሆነዉ ነገር ለማወቅ ዛሬ መኖር የግድ ነዉ፡፡
ዛሬ መሉ ትኩረት የሚፈልግ
      ሙሉ ሕይወት የሚሻ
     ሙሉ ጊዜን የሚወስድ
እራሱን የቻለ ሙሉ ቀን ነዉ፡፡

➢ ዛሬ ሳይኖሩ ነገን በሀሳብ ስበት ጎትተን ዛሬ ካልኖርነዉ አይባልም
ትናትዛሬ ፣ ዛሬነገ ተብሎ ቀን አይቆጠርም  ዛሬ ፣ነገ እንጂ ! (እራሱን የቻለ ሙሉ ቀን)
ልባም ሴት ዛሬ የምትኖር ናት፡፡

አንዳንዴ ዛሬን እንደ ድልድይ ወይም መሻገሪያ ብቻ እንደሆነ በማሰብ ለማለፍና ነገን ለመድረስ ብቻ ይታሰባል
" ...ነገም ሲደረስበት ዛሬን ሆኖ ይገኛል" እንዲሉ ዛሬን ድልድይ ብቻ ያረገና ሙሉነቱን ያላመነ በቀኑ መወሰን አይችልም ፡፡

ዛሬ የሚኖርበት ሳይሆን መሻገሪያ ብቻ ከሆነ ነገም እንዳ'ይኖር ነገም ዛሬ ነዉ ፡ ስለዚህ  ሕይወት በመሻገር ምኞት ነገር ግን በማሻገር እና ባለመሻገር ያልቃል(ቀኑን አሻግሮ ሳይሻገሩ መቅረት)
ምክንያቱም መሻገር ➱ አዲስ እይታ ፣አዲስ ጅማሬ ፣ተስፋን፣አዲስ ነገርን ያዘለ ነዉ ፡፡

➢ ዛሬ እንዳይኖር ካረገ አንዱ መጨነቅ ነዉ‼️
👉ጭንቀት ብድር ነዉ
ምን ይፈጠር ይሆን?
ምን ላድርግ ?
መች ይሆናል?
ቢሆንስ ? ባይሆንስ?
ቢሳካስ? ባይሳካስ?
ብከስርስ ?
ብታመምስ?
ብሞትስ....???

➢ጭንቀት ገና ሊሆን ስላለዉ ነገር አብዝቶ ማሰብና ለዛ ነገር ጊዜን ፣ አቅምንና ገንዘብን መሰዋት ነዉ፡፡
"ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።"
(የማቴዎስ ወንጌል 6:34)


ልባም ሴት ዛሬ የምትኖር በኃለኛውም ዘመን የምትስቅ ብርቱ ሴት ናት፡፡

➧ጭንቀት በእግዚአብሔር ተስፋ የመቁረት ምልክት ነዉ
➧ልባም ሴት ግን በእግዚአብሔር ትታመናለች (ፊል 4:6-7)

አትበደሪጭንቀትን ፣ ስጋትን፣ ተስፋ መቁረጥን፣ ዉድቀትን

ዛሬን ኑሪ ለነገም ትረፊ‼️

✍️ ፍጹም ክበቡ

          ▷ይ🀄️🀄️ሉን◁
            👇👇👇👇👇
 
@lebamsetministry123
 
@lebamsetministry123