የስልጤ ዞን ውሃ መዕዲንና ኢነርጂ መምሪያ የ2016 በጀት አመት ጉባኤና የቀጣይ የስድስት ወራት የንቅናቄ መድረክ አክመል ሸህ ሳሎ መታሰቢያ አዳራሽ ላይ ተካሄደ!
ታህሳስ 26/2017 ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን
የስልጤ ዞን ውሃ፣ መዕዲንና ኢነርጂ መምሪያ የ2016 በጀት አመት ጉባኤና የቀጣይ የ2017 በጀት አመት የስድስት ወራት የንቅናቄ መድረክ በስልጤ ዞን ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ አካሄዷል።
የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ሳሊያ ሀሰን የሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎት አንዱና ዋነኛው የሆነው ውኃ እንደሆነና ከውኃ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የመስኖ ስራዎች እንዲሁም አላቂ የሆነው ማዕድንና የኢነርጂ አማራጮች አንዱ ነው ብለዋል።
በዞናችን የሚገኙ የውሃ አገልግሎቶች እና የውሃ ተቋማት ለማህበረሰቡ ጥራት ያለው አገልግሎት ከመስጠት አንፃር ራሱን ቆም ብሎ ማየት ይጠበቅበታል ብለዋል።
የስልጤ ዞን ውሃ መዕዲንና ኢነርጂ መምሪያ ዋና ኃላፊ አቶ ጨፋ ከድር በበኩላቸው ጉባዔው ያለፈውን ዓመት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ በበጀት አመቱ በተለይም በመጠጥ ውኃ ዘርፍ ተደራሽ ባልሆነባቸው አካበቢዎች ሴክተሩ ግብ አስቀምጦ እየሰራ እንደሆነ አንስተዋል።
በማዕድንና አማራጭ ኢነርጂ ዘርፎች እና የሶላር ተደራሽነትን ከገጠር ኮሪደር ልማት ጋር በማስተሳሰር ማስፋት ይገባል ያሉት አቶ ጨፋ ለዚህም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።
በበጀት አመቱ ተቋሙ የንፅሁ መጠጥ ውሃን ተደረሽ ለማድግ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ አንስቶ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ለማስመረቅ እየተሰራ እንደሆነ አንስተዋል።
በመድረኩ የአማራጭ ኢነርጂ የሶላር አጠቃቀም አስመልክቶ የሶላር ሽያጭ ባለሙያ ለተሳታፊዎች ገለፃና ማብራሪያ አድርጓል።
የስልጤ ዞን ውሃ ማዕዲንና ኢነርጂ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ኑረዲን መሀመድ ባለፈው በጀት አመት የተከናወኑ መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋት ተግዳራቶች ላይ ሰፊ ርብርብ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
የጉባዔው ተሳታፊዎች በየ ውሃ ተቋማት እና የውሃ አገልግሎት እንዲሁም ጽ/ቤት ላይ የሚስታወሉ ጉድለቶችን በማረም ማህበረሰቡን የንፅሁ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚነትና የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል።