የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል @yeilyaswedaje Channel on Telegram

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

@yeilyaswedaje


(በአላህ ፍቃድ የሸይኽ ኢልያስ አህመድ (ሀፊዘሁላህ) ደርሶች : ሙሀደሮች በዚህ ቻናል እናቀብሎታለን ። አስተያየት ካላቹ በጉሩፑ ዙሪያ በሩ ክፍት ነዉ ከታች ባለዉ ሊንክ አሳዉቁኝ
https://t.me/mesud16

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል (Amharic)

በአላህ ፍቃድ የሸይኽ ኢልያስ አህመድ (ሀፊዘሁላህ) ደርሶች ሙሀደሮች፣ በዚህ ቻናል በጉሩፑ ዙሪያ እናቀብሎታለን። ማግኛ ቻናል ሊንክ ካራት አለዉ አሁን እንኳዉ ይህ ሊንክ እኛን እንሂፃለን። ከታች የተመረቀ ሊንክ እናቀብሎታለን: https://t.me/mesud16

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

14 Jan, 18:14


👆🏻👆🏻👆🏻
📚 #ወጣትነት እና ስኬት

🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

🔗 ቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/ustazilyas/1374

🔗 ቪዲዮውን ለመከታተል
https://web.facebook.com/share/v/1F2JduhPqR/
____
🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ የትምህርት መድረክ
https://www.facebook.com/ustathilyas

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

14 Jan, 09:46


ፅናትና መቻሉን ስጣቸው !

አላህ ሆይ ፍትህ ከአንተ ዘንድ ነውና የሚገኘው ለአክሱምና በተለያዩ ቦታዎች ላይ በሒጃባቸው ምክንያት መብታቸውን ለተነፈጉ ሙስሊም ተማሪዎች፣ በፂምና ባለባበስ ምክንያት ሥራ መስራት ለተከለከሉ ወገኖቻችን በሙሉ ፍትህን አንተው አምጣላቸው! መብታቸውንም አስከብርላቸው! ፅናትና መቻሉንም ስጣቸው !
ለግፈኞችም የሚገባቸውን ቅጣት አንተው አቅምሳቸው❗️
ኣሚን🤲

ዛዱል-መዓድ https://telegram.me/ahmedadem

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

14 Jan, 07:24


አየያዙ ብርቱ የሆነው የአለማቱ ጌታ!

ነቢዩ (🤍) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنَّ اللَّهَ عزَّ وجلَّ يُمْلِي لِلظّالِمِ، فإذا أخَذَهُ لَمْ يُفْلِتْهُ، ثُمَّ قَرَأَ وكَذلكَ أخْذُ رَبِّكَ، إذا أخَذَ القُرى وهي ظالِمَةٌ إنَّ أخْذَهُ ألِيمٌ شَدِيدٌ﴾

“የላቀውና ከፍ ያለው አላህ በደለኛን ያቆያል፤ የያዘው ግዜ ግን እንዲሁ አይለቀውም (አይቀጡ ቅጣት ነው የሚቀጣው)። ከዛ ይህን የቁርዓን አንቀፅ አነበቡ፦ ‘የጌታህም ቅጣት የከተሞችን ሰዎች እነሱ በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ እንደዚህ ነው። ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው።’”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2583

😵🤔🙁😝😤☹️🙁☹️

✔️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

14 Jan, 06:28


ሚጠቅመህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ

🎙 ሸይኽ ኤልያስ አህመድ

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

13 Jan, 13:12


ጊዜ አጠቃቀም

🎙 ሸይኽ ኤልያስ አህመድ

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

10 Jan, 06:05


በጋዛ  ወንድሞች እና እህቶቻችን መንገላታትና በቤቶቻቸው መቃጠል ሲሳለቁ የነበሩ የሆሊውድ ዱርየዎች የዘነጡ ቤቶቻቸው  ሲነድዱ እና እነሱም ሲነፋረቁ  ማየት ምንኛ ያስደስታል ?!!

አልሐምዱሊላህ  !!

አላሁ አክበር !! 

ገና አላህ ብዙ ያሳየናል - አንጠራጠርም !

አሜሪካን ያሉ ወንድሞች  እና እህቶችን አላህ ይጠብቃቸው

Muhammedsirage

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

09 Jan, 13:59


የመሬት መንቀጥቀጥ ጥንቃቄው 3 ነው። 1) ከወንጀል ተውበት ማድረግ 2) ዱአ ማድረግ 3) በሸሀዳ በውዱእ አዝካር ብሎ መተኛት
👉 ከዛ ውጭ መንግስትም በለው ማን መላሽ የለውም።

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

09 Jan, 07:47


ሙስሊም ተማሪዎችን ከትምህርት ተቋማት ማገዳቸው ሲገርመን ጭራሽ ህዝበ ሙስሊሙን ከአክሱም እናባርራለን እያሉ እየዛቱ ነው። የነዚህ ሰዎች ድን.ቁ ^ርና ደግሞ የተለየ ነው። ሙስሊሙ ምን በወጣውና ነው ለናንተ የእርስ በርስ ሽኩቻ ማወራረጃ የሚሆነው? ለምን በዚህ ዘመን የጅ.ል ፖለቲካ ትጫወታላችሁ?
IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

08 Jan, 11:27


🤲 በታላቁ አላህ ስሞችና መገለጫዎች ተማፅኖ ማድረግ ለዱዓእ ተቀባይነት ወሳኝ ነው!

ከቡረይዳ (📿) ተይዞ፡ እንዲህ ይላል፦

ነቢዩ (📿) አንድ ሰው እንዲህ በማለት አላህን ሲማፀን ሰሙት፦

﴿اللهم إني أسألُك بأني أشهدُ أنك أنت اللهُ لا إلَه إلا أنتَ الأحدُ الصمدُ الذي لم يلدْ ولم يولدْ ولم يكن له كُفُوًا أحدٌ. قال فقال والذي نفسي بيدِه لقد سألَ اللهَ باسمِه الأعظمِ الذي إذا دُعيَ به أجابَ وإذا سُئِلَ به أعطى﴾

“‘አላህ ሆይ! (ጉዳዬን ትሞላልኝ ዘንድ) አንተ አላህና ከአንተ ውጪ ሌላ አምላክ የሌለ መሆኑን፣ አንድና ብቸኛ፣ የፍጡራን ሁሉ መጠጊያ፣ ያልወለድክም ያልተወለድክም፣ አንድም ቢጤ የሌለህ አምላክ መሆንህን በመመስከሬ እማፀንሃለሁ።’ ይህን ግዜ ነቢዩ (📿) እንዲህ አሉ፦ ‘ነፍሴ በእጁ በሆነችው አላህ እምላለሁ! በርግጥም አላህን ትልቅ በሆነ ስሙ (መገለጫው) ተማፅንከው (ጠየከው)፤ የጠየከውን ዱዓእ መልስ በሚያሰጥና የጠየከውን የሚያሰጥ በሆነ።’”

📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል፡ 3475

▫️▫️▫️▫️🎀🎀▫️▫️▫️▫️

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📱፦ https://bit.ly/486xnrS

📱፦ https://bit.ly/41zEZkk

📱፦ https://bit.ly/4arMbTx

📱፦ https://bit.ly/41tIUPv

📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

06 Jan, 12:51


ወጣትነት እና የጊዜ አጠቃቀም
በሸይኽ ኢልያስ አህመድ
ዛሬ ምሽት 02፡30
በነሲሓ ቲቪ ይጠብቁን !!

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

05 Jan, 05:09


ይህ በመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተ ክስተት ነው በትላንትናው እለት
فَأَخَذَتْهُمُ ٱلرَّجْفَةُ فَأَصْبَحُوا۟ فِى دَارِهِمْ
جَٰثِمِينَ
«ወዲያውም የምድር መንቀጥቀጥ (ጩኸትም) ያዘቻቸው፡፡ በቤቶቻቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አነጉ፡፡»  (አል አዕራፍ 7:78)

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

04 Jan, 16:28


ፖለቲከኛ ሆደ ሰፊ ሲሆን ጥሩ ነው
~
በዚህ ባንዲራ ሰበብ ወንድሞች እየታሰሩ እንደሆነ ከአንድ ወንድም መረጃ ደረሰኝ። በዚህ ፖስት አንዱ ማስተላለፍ የፈለግኩት ነጥብ ይሄ ነው። ጥንቃቄ እንድታደርጉ።
በርግጥ ይህንን ባንዲራ እኔም አልወደውም። ይህን ብቻ ሳይሆን ቢጫውና ቀዩ ቀለማት የተጣመሩባቸው ባንዲራዎች ሁሉ የየትኛውም አካል ቢሆኑ አልወዳቸውም፡፡ ይሄ የግል ስሜቴ ነው።

ግን ፖሊቲከኞች (ፖሊሶች) በዚህ ሰበብ ሰዎችን ማሳደድ ለምን? መንግስትን በምትወክሉበት ስልጣን ላይ ሆናችሁ ግለሰባዊ የሚመስል እልህ ባታሳዩ መልካም ነው። በተለጠፈው ምስል በዋናነት ማስተላለፍ የተፈለገው መልእክት "በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው በደል ይቁም። ፍትህ ይስፈን" የሚል ነው። በዚህ መሰረታዊ ጉዳይ ላይ አይኑን የጨፈነ አካል ኮከብ አለ የለም እያለ ሰው ሲያሳድድ ማየት የሚገርም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

04 Jan, 11:11


🖋የመሬት መንቀጥቀጥ የትንሳዔ መቅረብ ምልክት ነው። ቢሆንም ነገሩ ሲከሰት ወደ አላህ በተውበት (በንስሃ) መመለስ እንዳለብን ዑለማዎች ይመክራሉ። በተረፈ ለጥንቃቄ ይረዳን ዘንድ ከባለሙያዎች የሚተላለፉ መልዕክቶችን ከማድመጥ ባለፈ፤ ያገኙትን ሁሉ ከሚያወሩ የሶሻል ሚዲያ ገፆች በሚተላለፉ መልዕክቶች ልንረበሽ አይገባም!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا تَقُومُ السّاعَةُ حتّى يُقْبَضَ العِلْمُ، وتَكْثُرَ الزَّلازِلُ﴾

“ሰዓቲቱ ‘ትንሳዔ’ አትቆምም እውቀት እስከሚነሳና የመሬት መንቀጥቀጥ እስከሚበዛ ድረስ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 1036

🙁🙁🙁🙁🙁🙁☹️🥳

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

04 Jan, 09:44


ትንሽ እንኳ አንደነግጥም አይደል⁉️

መሬት ደጋግማ እየተንቀጠቀጠች ነው። ይህ ከባዱ ማስጠንቀቂያ ነው። መሬት የተንቀጠቀጠችው ውስጧ እንዲህ እንዲያ ስለሆነ የሚለው የሞኝ ትንታኔ ወደ ጎን ትተን ሀሊቁ አላህን እንስማ ወደ እርሱም እንመለስ!

አላህ በቁርዓኑ አመፀኞቹ የነብዩላህ ሷሊህ (ዐሰ) ህዝቦች በመሬት መንቀጥቀጥ እንዴት እንደቀጣቸው ሲገልፅ:

فَأَخَذَتْهُمُ ٱلرَّجْفَةُ فَأَصْبَحُوا۟ فِى دَارِهِمْ جَٰثِمِينَ
«ወዲያውም የምድር መንቀጥቀጥ (ጩኸትም) ያዘቻቸው፡፡ በቤቶቻቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አነጉ፡፡» (አል አዕራፍ 7:78)

ወደ አላህ ከመሸሽ ውጭ ምንም አማራጭ የለም። ወንጀላችን ሲበዛ፣ በደል ሲበዛ፣ የተበዳዮች እንባ ሲበዛ የአላህ ቁጣ መምጣቱ የማይቀር ነው። ተውበት በማድረግ ወደ አላህ እንመለስ፣ ሰደቃ በማድረግ የተቸገሩትን እንርዳ፣ የተበዳዮችን ይቅርታ እንጠይቅ፣ መበዳደል ይብቃን፣ ይቺ በሰከንዶች ለምትጠፋ አለም መስገብገብ ይብቃን

.....

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

04 Jan, 03:57


ያ አላህ! ኸረ እንዳንጠፋ ኢስቲግፋር እናብዛ! ምንም ነገር ላይ ሆነን ኢስቲግፋር ማለት እንችላለን። አስተግፊሩላህ ወአቱቡ ኢለይሂ!

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

03 Jan, 16:12


እስቲ እንታረቅ❗️

🔅ምድር የሰው ልጆች ሆይ በቃኝ! ከዚህ በላይ አልታገሳችሁም!ከዚህ በላይ እኔ ላይ በሰላም መኖር አትችሉም!  ግፋችሁ በዛ!ከስሬ አድርጌ የዋጋችሁን እሰጣችኋለሁ! እያለች ይመስላልና እስቲ ወደ አላህ እንመለስ!

🔅እርሱ ይቅር እንዲለን እኛም ይቅር እንባባል/አውፍ እንባባል!

🔅አላህ እንዲታረቀን እስቲ እኛም እንታረቅ!

  🔅 መሪና ባለስልጣኖቻችንም
በየቦታው  እየፈሰሰ ያለውን ደምና የተበዳይ እምባን ለማስቆም ከመቼውም በላይ ጥረት ያድርጉ!

🔅ምድር እንደወትሮዋ ቀጥ ብላ እንድትቆምና ያለ ስጋት እንድንኖርባት ግፍና በደልን ከምድራችን ላይ እናስቁም።

🔅የዛሬ የጁሙዓ ልዩ ዱዓችን ላይም የሀገራችን የሰላምና ፍትህ ጉዳይ ላይ ይበልጥ ያተኮረ ብናደርገው መልካም ነው።

ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ጁሙዓ ረጀብ 3/1446 ዓ.ሂ

@ዛዱል መዓድ

🔹🔸🔹🔸🔹🔸

💥 በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶች የሚተላለፉባቸውን ገፆች ለመቀላቀልና ዌብሳይታችንን ለማግኘት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ

🌐 https://zadalmead.com/

✔️ https://telegram.me/ahmedadem

✔️https://facebook.com/yenegew

✔️http://youtube.com/c/ZadulMaad

✔️ http://x.com/zad_al_mead

✔️https://instagram.com/zad_al_mead

አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

03 Jan, 08:11


የአማን አሰፋ ጀናዛ ታጥቦ ተከፍኖ ከእናቱ ቤት ወደ አወሊያ በማቅናት ላይ ነን አወሊያ እንገናኝ

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

03 Jan, 07:24


መፅሀፉ ሳውዲ ጅዳ ይገኛል
0530812977
Ismail adem

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

03 Jan, 04:23


የአማን አሰፋ ክቡር ገላ ሚኒሊክ ሆስፒታል ደርሷል ምርመራ ከተደረገለት በኋላ ጠዋት አወሊያ ታጥቦ እዚያው አወሊያ ተሰግዶበት ኮልፌ ክቡር ገላው ያርፋል ኢንሻ አላህ።

በአላህ መንነድ ሲታገል ከርሞ በፆመኛ አንጀቱ አላህን የተገናኘውን ሙጃሂድ ገጣሚና ፀሐፊውን አማን አሰፋን እንሸኘው


  

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

03 Jan, 04:22


ያኔ በ"ድምፃችን ይሰማ" ጊዜ ጂهاዳዊ ሓረካት ፊልም ተሰርቶ ታስሮ የነበረውን ወንድማችን አማን አሰፋ ልንዘይር ሂደን አጊኝቸው ነበር። እርጋታው እና ለዲኑ ያለው ፍቅር top flight ነው። رحمة الله عليه

بإذن الله في زمرة الشهداء والمتقين

ነገ በአላህ ፈቃድ አወሊያ ተሰግዶበት ኮልፌ ይቀበራል

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

02 Jan, 13:46


اللهم صل وسلم على نبينا محمد ..

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

01 Jan, 13:47


📣 ከእንኳን አደረሳችሁ ይልቅ ይህን መልዕክት ንገራቸው!

ከአቡ ሁረይራ (📿) ተይዞ: ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿وَالَّذِي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بِيَدِهِ، لَا يَسْمَعُ بِي أَحَدٌ مِنْ هَذِهِ الْأُمَّةِ يَهُودِيٌّ وَلَا نَصْرَانِيٌّ، ثُمَّ يَمُوتُ، وَلَمْ يُؤْمِنْ بِالَّذِي أُرْسِلْتُ بِهِ إِلَّا كَانَ مِنْ أَصْحَابِ النَّارِ﴾

“የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው እምላለሁ! አንድም ከዚህ ኡመት (ህዝብ) አይሁድም ይሁን ክርስቲያን ስለእኔ መላክ አይሰማም። ከዚያም በእርሱ በተላኩበት ሳያምን የሚሞት አይኖርም። እርሱ የእሳት ባለቤት የሚሆን ቢሆን እንጅ፡፡”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 153

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

💬፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

💬፦ https://bit.ly/486xnrS

💬፦ https://bit.ly/41zEZkk

📷፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

📺፦ https://bit.ly/3UTTSwh

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

01 Jan, 13:47


💡መላእክቶች ዱዓእ እንዲያደርጉልህ ትፈልጋለህ?

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿أَحَدُكُمْ مَا قَعَدَ يَنْتَظِرُ الصَّلَاةَ فِي صَلَاةٍ مَا لَمْ يُحْدِثْ، تَدْعُو لَهُ الْمَلَائِكَةُ : اللَّهُمَّ اغْفِرْ لَهُ، اللَّهُمَّ ارْحَمْهُ﴾

“ከናንተ መካከል አንዳችሁ ሶላት የሰገደበት መስገጃው ላይ እስካለና ውዱእ አስካላጠፋ ድረስ፤ መላእክቶች ለሱ ዱዓእ ያደርጋሉ። አላህ ሆይ! ወንጀሉን ማረው፤ አላህ ሆይ! እዘንለት ይላሉ።”

📚 ቡኻሪ (3229) ሙስሊም (649) ዘግበውታል

▫️▫️▫️▫️🎀🎀▫️▫️▫️▫️

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

27 Dec, 12:12


ዑመር (ረዐ) በንግድ ጉዳይ ላይ ሸሪዓዊ እውቀት የሌለው ሰው መነገድ የለበትም ይሉ ነበር። ስለዚሁ ሲናገሩም ❝ኢስላምን ያልተረዳ ሰው በገበያ ውስጥ ሊሸጥ አይገባውም። ካልሆነ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሪባ ሊበላ ይችላል።❞ ይላሉ።
(ሸሂድ አል-ሚህራብ 209)
አብዛኛው የኢትዮጵያ ሙስሊም ደግሞ ነጋዴ ነው። ስለዚህ ከሁሉም አስቀድሞ ስለ ንግድ ማወቅ አለበት። ካልሆነ አውቆም ይሁን ሳያውቅ የአላህን ሃቅ ያጠፋና የዱንያንም በረካ ሊያጣ በአኼራም ቅጣት ሊጠብቀው ይችላል።
ሰሞኑን ሸይኽ ኤልያስ ❝ገንዘብና ወለድ❞ የተሰኘ መጽሐፍ አሳትመዋል። ይሄን መጽሐፍ ፈልጋችሁ አንብቡት። ይሄን የምለው ለማስታወቂያ ሳይሆን አንዴ በምታነቡት የዘላለም እውቀት ልታገኙ ስለምትችሉ ትጠቀሙበታላችሁ በሚል ነው።
በሚከተሉት መደብሮች ይገኛል
➤ ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር (18 ማዞርያ)
➤ አት-ተውባ መጽሐፍት መደብር (አንዋር መስጂድ)
➤ አት-ተቅዋ መጽሐፍት መደብር (ቤተል)
➤ ዛዱል መዓድ መጽሐፍት መደብር (ፋሪ)
ዋጋ= 400 ብር

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

26 Dec, 18:27


#ለጥንቃቄ

በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር / ኢንሳ አሳውቋል።

ኢንሳ በዛሬው ዕለት በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል አሳስቧል።

ኢንሳ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች በተለያዩ ማስገሪያ (ፊሺንግ ሊንክ) አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ እንደሆነ ገልጷል።

በመሆኑንም ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከሚያውቁትም ሆነ ከማያውቁት) ግለሰብ ሊንክ ቢላክ መክፈት ተገቢ እንዳልሆነ እና ወዲያውኑ ማጥፋት እንደሚገባ አሳስቧል።

@tikvahethiopia

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

26 Dec, 12:31


ፍልስጤማውያን ያለቁት አልቀው የተረፉት ደግሞ በፈራረሰ መንደራቸው እንኳን የመኖር መብት ተነፍጓቸው በዚህ መልኩ ይንከራተታሉ። "የሰለጠነው" ዓለም አይኑንም፣ ጆሮውንም ደፍኖ እልቂት ወስኖባቸዋል። ኢንሻአላህ ነገ ሌላ ቀን ይመጣል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

26 Dec, 04:38


ፍትሕ ለአክሱም ሙስሊሞች

ሙስሊም መሆን ወንጀል አይደለም

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

25 Dec, 09:57


"ሒጃብ ለብሳችሁ መማር አትችሉም" በሚል በአክሱም የሚኖሩ ሙስሊም ሴቶች ከፍተኛ እንግልት ውስጥ ናቸው። የክልሉ መጅሊስ የቻለውን ያክል ቢጥርም የሚሰማው እንዳጣ በደብዳቤ ገልጿል። እምነቱን ተንተርሶ የራስን ወገን የመጨቆን የከረመ በሽታ መቸ ይሆን የሚለቀን?ተማሪዎቹ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ ከተከለከሉ 3 ሳምንት አልፏቸዋል፣ ለማትሪክ ፎርም እየተሞላ ቢሆንም ሙስሊም ተማሪዎች ግን መሙላት አልቻሉም። በዚህ አዳፋ ተግባራችሁ መጻፍ የምትፈልጉት ታሪክ ምንድን ነው?

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

24 Dec, 13:32


አዲስ መፅሐፍ በገበያ ላይ...

ገንዘብና ወለድ - እውነታ እና ብዥታ

በሸይኽ ኢልያስ አህመድ የተዘጋጀ በአይነቱ ልዩ ጥናታዊና ወቅታዊ መፅሐፍ

ዋጋ = 400 ብር

በሚከተሉት መደብሮች ይገኛል
1) ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር (18 ማዞርያ)
2) አት'ተውባ የመጻሕፍት መደብር (አንዋር መስጂድ)
3) አት'ተቅዋ የመጻሕፍት መደብር (ቤተል)
4) ዛዱል መዓድ የመጻሕፍት መደብር (ፋሪ)

الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات!

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

23 Dec, 08:54


🚫 ያጠፋችሁ ነበር!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لَوْ لَمْ تُذْنِبُوا لَذَهَبَ اللَّهُ بِكُمْ، وَلَجَاءَ بِقَوْمٍ يُذْنِبُونَ، فَيَسْتَغْفِرُونَ اللَّهَ فَيَغْفِرُ لَهُمْ﴾

“ነፍሴ በእጁ በሆነችው አላህ እምላለሁ!  እናንተ ሀጢያት የማትፈፅሙ ቢሆን ኖሮ አላህ ያጠፋችሁ ነበር። ከዛ ሀጢያት የሚፈፅሙ ህዝቦችን ያመጣና በሀጢያታቸው ምክንያት አላህን ምህረት ይጠይቁታል እሱም ይምራቸዋል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2749

☹️☹️😭🙁😭🙁☹️🙁

🤖በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

22 Dec, 18:17


ጀምዕ የሚደረጉ ሶላቶች
~
1- ጀምዕ ማለት ሁለት ተከታታይ ሶላቶችን በአንደኛው ወቅት መስገድ ነው። ጀምዕ የሚደረጉት ሶላቶች የሚከተሉት ናቸው፦
- ዙህር እና ዐስርን በአንደኛው ወቅት
- መግሪብ እና ዒሻእን እንዲሁ በአንደኛው ወቅት መስገድ ይቻላል።
ከዚህ ውጭ ጀምዕ የለም። የሱብሕ ሶላት ከየትኛውም ሶላት ጋር ጀምዕ አትደረግም። እሷም ወደ ሌላ ወቅት አትውወሰድም። ሌሎችም ሶላቶች ወደሷ አይውወሰዱም። 0ስርን ከመግሪብ ጋር ጀምዕ ማድረግም አይቻልም።

2- ጀምዕ በሁለት መልኩ ሊፈፀም ይችላል።
1ኛው፦ የኋለኛውን ሶላት ወደ መጀመሪያው በማምጣት። ይሄ ጀምዑ ተቅዲም ይባላል። ዐስርን ከዙህር ጋር በዙህር ወቅት ፤ ወይም ዒሻእን ከመግሪብ ጋር በመግሪብ ወቅት መስገድ ነው።
2ኛው ጀምዑ ተእኺር ይባላል። የመጀመሪያውን ሶላት ወደ ኋለኛው ወስዶ መስገድ ነው። ይህም ዙህር እና ዐስርን በዐስር ወቅት ፤ መግሪብንና ዒሻእን በዒሻእ ወቅት መስገድ ነው።

3- ጀምዕ ከሐጃ ጋር የተያያዘ ነው። መንገደኛም ይሁን በሃገሩ ኗሪ ሶላትን በወቅቱ መስገዱ የሚከብደው ከሆነ ሁለቱን ሶላት በአንደኛው ሶላት ወቅት ጀምዕ ማድረግ ይችላል። ህመምተኛ፣ ነፍሰ ጡር፣ አጥቢ፣ ሌሎችም እያንዳንዱን ሶላት በወቅቱ መስገዳቸው የሚከብዳቸው አካላት በዚህ መልኩ ሊፈጽሙ ይችላሉ። ልብ በሉ! ያለ ተጨባጭ ምክንያት ልማድ እንዲያደርጉ አይደለም።

4ኛ፦ በጀምዕ ጊዜ የሶላቶቹን ቅደም ተከተል መጠበቅ ይገባል። ዙህር እና ዐስርን ጀምዕ የሚያደርግ ሰው ጀምዑ ተቅዲምም ይሁን ጀምዑ ተእኺር መጀመሪያ ዙህርን ያስቀድማል። ካሰላመተ በኋላ 0ስርን ይሰግዳል። መግሪብ እና ዒሻእን ጀምዕ የሚያደርግም ሰው እንዲሁ መጀመሪያ መግሪብን ይሰግዳል። ካሰላመተ በኋላ ዒሻእን ያስከትላል።

5ኛ፦ ጀምዕ እና ቀስር ተያያዥ አይደሉም። ቀስር ማለት ባለ አራት ረከዐ ሶላቶችን ሁለት አድርጎ አሳጥሮ መስገድ ነው። ይሄ ጉዞ ላይ ላለ ሰው ብቻ የሚፈቀድ ነው። በሃገሩ ኗሪ የሆነ ሰው አራቱን ረከዐ ሁለት አድርጎ ማሳጠር አይፈቀድለትም። እንዲሁም ማሳጠር ሱብሕ እና መግሪብን አይመለከትም። በየትኛውም ሁኔታ የረከዐቸው ቁጥር አይቀየርም።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

22 Dec, 18:15


ትራንስፖርት ላይ ሆኖ የሶላት ወቅት እንዳያልፈው የሰጋ ሰው ምን ያድርግ?
~
1- በመጀመሪያ በወቅቱ ለመስገድ መጣር አለበት። ለምሳሌ ከመሳፈሩ በፊት መስገድ ከቻለ ይሰግዳል። ወይም ጉዞውን ቀደም ብሎ በመፈፀም ከዚያ ሶላቱን በወቅቱ ይሰግዳል። ባጭሩ እስከቻለ ድረስ ጉዞውን ከሶላቱ ወቅት ጋር በማይጋጭ መልኩ ያመቻች። ሾፌሩን አናግሮ ወርዶ የሚሰግድበት እድል ካለ የአፈፃፀም ስርአቶቹ ያልተጠበቀ ሶላት መኪና ውስጥ ሊሰግድ አይገባም። ስለዚህ ለሶላቱ ትኩረት ይስጥ።

2- በወቅቱ ለመስገድ ካልቻለስ? ጀምዕ ማድረግ የሚቻል ሶላት ከሆነ ለምሳሌ ዙህር እና ዐስር ወይም መግሪብ እና ዒሻእ ከሆኑ በማስቀደም ወይም በማዘግየት ሁለቱን ሶላት በአንደኛው ወቅት በስርአት መስገድ ይችላል። ሙሳፊር ቢሆንም ባይሆንም። ወይ ወደ መጓጓዣው ከመግባቱ በፊት አስቀድሞ ወይ ደግሞ ከመጓጓዣው ሲወርድ አዘግይቶ በስርአቱ ይሰግዳል። በስርአቱ ስል በወቅቱ ለመስገድ ብሎ መኪና ውስጥ አርካኖችን ሳያሟላ እንዳይሰግድ ነው።

3- ሶላቱ ጀምዕ ለማድረግ የማይመች ከሆነስ? ለምሳሌ የሱብሕ ሶላት ወቅት ሳይገባ ተሳፈረ። ወይም ከዙህር በኋላ ቀድሞ ያልታሰበ ጉዞ ጀምሮ ትራንስፖርት ላይ እያለ የዐስር ወቅት ሊወጣበት ሆነ። መኪናው ወቅት ሳይወጣ የማይቆም ከሆነበት ምን ያድርግ? ወቅቱ ሳይወጣ መኪናው ላይ ይሰግዳል። መኪናው ላይ መቆም ከቻለ ይቆማል። ካልቻለ በተቀመጠበት ሆኖ ይሰግዳል። ሩኩዕ እና ሱጁድ ለማድረግ ካልተመቸ ጎንበስ እያለ ይፈፅማል። ለሱጁዱ ከሩኩዑ ይበልጥ ዝቅ ይላል። ውዱእ ከሌለው ተየሙም ያደርጋል።

4- ቂብላን በተመለከተ በሙሉ ሶላቱ ወደ ቂብላ መዞር ከቻለ ለግዴታ ሶላት ቂብላን መቅጣጨት ግዴታ ነው። ካልቻለ ሶላቱ ሲጀምር ወደ ቂብላ ዙሮ ይጀምራል። ከዚያ በኋላ መኪናው ቂብላውን ቢለቅም ባለበት ይሰግዳል።

(ሼር ብታደርጉት ባረከላሁ ፊኩም።)
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

22 Dec, 18:12


ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ ሌሎችም ባጠቃላይ እያንዳንዱን ሶላት በወቅቱ ለመስገድ የሚቸገሩበት ሁኔታ ከገጠማቸው ዙህርን እና ዐስርን በአንዱ ወቅት፤ መግሪብን እና ዒሻእንም እንዲሁ በአንደኛው በሚመቻቸው ወቅት መስገድ ይችላሉ። መንገደኞች ባይሆኑ እንኳ ማለቴ ነው። ስለዚህ ለምሳሌ አንድ ተማሪ ከመግሪብ ሶላት ቀደም ብሎ 12:00 ላይ ለፈተና እንዲቀመጥ ቢገደድና የፈተናው ጊዜ እስከ ዒሻእ ወቅት የሚረዝም ከሆነ ፈተናውን ካጠናቀቀ በኋላ በመጀመሪያ መግሪብን ይሰግዳል። ካሰላመተ በኋላ እንደገና ዒሻእን ይሰግዳል። ይሄ ሶሒሕ ሐዲሥ የመጣበት ነው። ለተጨማሪ የሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚንን ድምፅ አያይዣለሁ።

ተጨባጭ ምክንያት ካልገጠመው ግን ሁሉንም ሶላት በወቅቱ ነው መስገድ ያለበት። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ إِنَّ ٱلصَّلَوٰةَ كَانَتۡ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِینَ كِتَـٰبࣰا مَّوۡقُوتࣰا }
''ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና።" [አኒሳእ፡ 103]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

20 Dec, 13:17


👆🏻👆🏻👆🏻
#የጁሙዓ_ኹጥባ ! በኦዲዮ (mp3)

🔖የገንዘብ ፈተና

🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ


https://t.me/huda4eth

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

20 Dec, 13:17


👆🏻👆🏻👆🏻
#የጁሙዓ_ኹጥባ ! በኦዲዮ (mp3)

🔖የገንዘብ ፈተና

🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ


https://t.me/huda4eth

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

20 Dec, 07:49


አለም ችላ ብሎህ አንዲት የጌታህ አንቀፅ ታፅናናሀለች
😍 "አትዘን አላህ ከኛ ጋር ነው"😍
አላህ ከሱ ጋር የሆነው ከቶ ምን ሊያጣ

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

20 Dec, 07:18


ሙሉ ትምህርቱን በYouTube ይከታተሉ
https://youtu.be/xYkmKCPBndc

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

19 Dec, 04:00


▪️ገንዘቤ!

🔻ከዐብደሏህ ኢብኒሽሺኪኪር - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ ነብያችንን - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - { ألهاكم التكاثر } እየቀሩ ወደነሱ መጣው እናም እንዲህ አሉ ፦ " የአደም ልጅ ንብረቴ ንብረቴ ይላል ፤ አንተ የአደም ልጅ ሆይ! ከንብረትህ በልተሀው ያጠፋሀው ወይም ለብሰህ ያበሰበስከው ወይም ደግሞ ሰደቃ አውጥተህ ለአኺራህ ያሳለፍከው ካልሆነ በስተቀር ምን ንብረት አለህ? " (ሙስሊም ዘግቦታል).

@ibnyahya777

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

18 Dec, 12:44


ዛሬ ዛሬ የብዙዎቻችን መነጋገሪያ ጭንቀት የሆነው የዋጋ ግሽበት
የኑሮ መክበድ ||
በሸይኽ ኢልያስ አህመድ
ቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ይበሉ
https://t.me/yeilyaswedaj

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

16 Dec, 12:25


የገንዘብ ፈተና
የጁምዓ ኹጥባ ||
በሸይኽ ኢልያስ አህመድ

NesihaTv

https://youtu.be/xYkmKCPBndc

ነሲሓ ቲቪ...
ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!

YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCX2E30J71sKpnLQuGr7kt6w
Facebook፡ facebook.com/nesihatv
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaaWvl5CXC3Ic7glOv3U

@nesihatv

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

16 Dec, 10:28


አስታወሳቹት ሩህ ሩህ እሱም ዛሬ ወደ አኼራ ተሸጋግሯል አላህ ሩሂ ሩሂ ሲላት ከነበረችው እንቦቀቅላው ጋር በጀነት ያገናኛቸው
ዛሬ ኻሊድ ነብሓን ( አቡ ዲያዕ ) ሸሒድ ሆኖ ወደ አኼራ ሔደዋል አላህ ይዘንልክ ማረፊያክንም በጀነት ያድርግው 💔😔
ኢናሊላሒ ወኢና ኢለሒ ራጂዑን

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

15 Dec, 18:17


የቴሌ ብር ቋሚ መዋጮ አከፋፈል

ለሌሎችም በማጋራት የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ።
‐‐‐‐‐‐‐‐‐‐‐‐‐‐‐
https://t.me/nesihatv

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

15 Dec, 11:05


በቴሌብር ነሲሓን እናሻግር

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

05 Dec, 08:45


እኛስ ቁርኣን ስንቀራ ምን ይሰማናል?
~
"የነብዩ ﷺ ሶሐቦች ቁርኣንን ሲሰሙ እንዴት ነበረ?" ተብላ የተጠየቀችው አስማእ ቢንት አቡበክር መልሷ እንዲህ የሚል ነበር:–
"تدمع أعينهم وتقشعر جلودهم، كما نعتهم الله".
"አይኖቻቸው ያነባሉ። ቆዳዎቻቸው ይኮማተራሉ። ልክ አላህ እንደገለፃቸው!" 📚أخرجه البيهقي ٢/٣٦٥.
እኛስ በምንድን ነው የምናለቅሰው? ለመሆኑ ቁርኣንን ስንቀራ በዛቻው እንርዳለን? በተስፋ ቃሉ እንቋምጣለን? ታሪኩን እናጣጥማለን?

ሲጀመር ቁርኣን እንቀራለን ወይ? መልሱ "አዎ" የሆነ ሰው ምንኛ የታደለ ነው? ግን መቼ ነው የምንቀራው?
★ በየቀኑ?
★ በሳምንት ጁሙዐ?
★ በአመት ረመዳን ወር? መቼ?
አላህ ይድረስልን።

ነገ አዋጅ አለ! እንዲህ የሚል ነብያዊ አዋጅ!
(وَقَالَ الرَّسُولُ يَا رَبِّ إِنَّ قَوْمِي اتَّخَذُوا هَٰذَا الْقُرْآنَ مَهْجُورًا)
[ الفرقان 30]

"መልክተኛውም ‘ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት’ አለ፡፡" [አልፉርቃን: 30]
ያኔ ምን ይሆን መልሳችን?
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

04 Dec, 11:02


👆🏻👆🏻👆🏻
📚 #ፈታዋ ምን ማለት ነው?

🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

🔗 ቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/ustazilyas/1323

🔗 ቪዲዮውን ለመከታተል
https://fb.watch/weVH7IZvk9/

____
🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ የትምህርት መድረክ
https://www.facebook.com/ustathilyas

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

04 Dec, 08:28


የሸሪዓ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን እሴት የጠበቀ ተቋም አይደለም።

- የአመቱ ገብሬል የሚከበርበት
- መዝሙር የሚከፈትበት
-ለበአላት ቄጤማ የሚጎዘጎዝበት

ሙስሊሞች ለሸሪዓ ፍርድ ሲመጡ የሙስሊም ተቋም እንደገቡ የሚጠራጠሩበት ተቋም ሆኗል።

#ተሀድሶ
#Reformation

በኡስታዝ አህመዲን ጀበል የተነሳ ሃሳብ

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

26 Nov, 16:29


የሸይኻ ፋጢማ የአይነ ስውራን ት/ቤት ጉዳይን በተመለከተ መጅሊሱ አንድ እርምጃ መሄዱ መልካም ነገር ነው። ከንቲባዋ ይስተካከላል ብላ ቃል መግባቷን መጅሊሱ አሳውቋል። ጉዳዩን እንደሚከታተሉና እስከ ፍጻሜው እንደሚያደርሱት ተስፋ እናደርጋለን። የሁሉም ሙስሊም ጭንቀት የልጆቹ እንባ መታበሱ ነው። አላህ ሲስቁ እንዲያሳየን ዱዓችን ነው።

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

25 Nov, 04:01


በቅርቡ…
ኢን ሻአ'ላህ
በሸይኽ ኢልያስ አህመድ (hafizehullah)

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

23 Nov, 11:09


በቅርብ ቀን

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

20 Nov, 09:30


🚫 የሞት አደጋ ለገጠመው!

“ኡሙ ሰለማ (📿) ረሱል (📿) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ ትላለች፦ አንድ ባሪያ አንድ ሙሲባ (መከራ) ችግር በሚገጥመው ግዜ፦

﴿إنا للهِ وإنا إليه راجعونَ، اللهمَّ أجرْنِي في مصيبتِي واخلفْ لي خيرًا منها﴾

‘እኛ የአላህ ነን ወደርሱም ተመላሾች ነን። አላህ ሆይ! ባገኘኝ መከራ ምንዳን ለግሰኝ። ከርሱ የተሻለንም ተካልኝ’ ካለ አላህ ለደረሰበት መከራ ይመነደዋል። ከርሱ የተሻለንም ምትክም ይለግሰዋል። ከዛ እንዲህ ትላለች፦ ባለቤቴ አቡ ሰለማ በሞተብኝ ግዜ ረሱል (📿) ይህን ዱዓ እንድል አዘዙኝ። አልኩኝ። አላህ በዚህ መከራ የተሻለን ረሱልን (📿) ተካልኝ (በትዳር አጣመረኝ)።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 918

😵🤔🙁😝😤☹️🙁☹️

✔️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📱፦ https://bit.ly/486xnrS

📱፦ https://bit.ly/41zEZkk

📱፦ https://bit.ly/4arMbTx

📱፦ https://bit.ly/41tIUPv

📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

18 Nov, 10:27


🎁 በተሰጠህ ፀጋ እገዛ ያድርግ…

ከአቡ ሰይድ አልሁድሪ (📿) ተይዞ፡ ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَن كان معه فضلُ ظَهْرٍ، فَلْيَعُدْ به على مَن لا ظَهْرَ له، ﴾

“በግልፅ የሚታይ ፀጋ የተዋለለት ሰው። በግልፅ ላልተዋለለት ሰው እገዛ ያድርግ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1728

😵🤔🙁😝😤☹️🙁☹️

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

17 Nov, 12:31


መርካቶ ዛሬም ቃጠሎ ደረሰ እየተባለ ነው። ግራ የገባ ነገር። ለማንኛውም ነጋዴዎች አደጋውን በመከላከልም ይሁን ጉዳትን በመቀነስ ላይ ማድረግ የምትችሉት ጥንቃቄ ካለ አስቡበት። እቃ መቀናነስ፣ በተለየ ትኩረት የሚፈልጉ በጣም ውድ እቃዎችን ወይም ዶክመንቶችን ማራቅ ሊሆን ይችላል። ብቻ የሚቻላችሁ ካለ አስቡበት። መርካቶ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አካባቢዎች ያላችሁ ትኩረት አድርጉ።
የተጎዳችሁን አላህ ይተካችሁ። ሌሎቻችሁን አላህ ይጠብቅላችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

15 Nov, 11:11


💡ሚስጥር መጠበቅ!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إِذَا حَدَّثَ الرَّجُلُ الْحَدِيثَ، ثُمَّ الْتَفَتَ فَهِيَ أَمَانَةٌ﴾

“አንድ ሰው ግራ ቀኙን ተመልክቶ የሆነ ወሬ
ከነገረህ አማና (ሚስጥር) ነው ማለት ነው።”

📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል: 1959

🙁☹️😭🙁😭🙁☹️

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

14 Nov, 12:31


አላህ ሆይ! የስሜታችን ተከታይ (ባሪያ) አታድርገን!

ፉደይል ኢብኑ ዒያድ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦

﴿لَيْسَ فِي الأَرْضِ شَيْءٌ أَشَدُّ مِنْ تَرْكِ الشَّهْوَةِ﴾

“በዚህ ዓለም ውስጥ ስሜትን (የግል ዝንባሌን) አንደመተው የበረታ (የከበደ) የሆነ አንድም ነገር የለም።”

📚 [አል‐ሂሊያ (98/8)]

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

09 Nov, 14:56


ምንኛ ደስ የሚያሰኝ ስራ ነው! ከሀረር የተፈናቀሉ ወንድሞቻችን እህቶቻችን  ከባዶ ተነስተው በመንግስት እርዳታ ውስጥ ሆኖ ለሚበሉት ለሚጠጡት ይህንን የምትመለከቱትን መስጅድ እዚህ ለማድረስና ለመጨረስ የሚችሉትን እያደረጉ ነው። በዚህ የመስጂድ ግንባታ ላይ የሶደቀቱል ጃሪያ ድርሻ እንዲኖረው የሚሻ ያቅሙን በማገዝ ለአኼራው ስንቅ ያስቀምጥ።
መስጅደል አቡበክር ሲዲቅ  በለገጣፎ ከተማ  140 መናኸሪያው ወደ ውስጥ ገባ ብሎ  መሪሳ የሀረሪ ተፈናቃዬች ካምፕ ውስጥ  ላይ እየተሰራ ያለ መስጂድ ነው። መስጂዱ ለአካባቢው  ድምቀትም አካባቢው ላይ ከነሱ ውጪም ላለው ሙስሊም መሀበረሰብ ያለ ብቸኛ መስጅድ  ነው። በተጨማሪም ብዙ ደረሶች የሚቀሩበት እና  ጥሩ የደዕዋ መነቃቃት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፣ ኢንሻአላህ።

መርዳት ለምትፈልጉ ከታች በተለጠፈው አካውንት ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ።
❗️❗️ማሳሰቢያ በግል አሰራለሁ ለማመንም ይቸግራል መጥተን በአካል  ማየት አለብን ለምትሉ አህለል ኸይሮች ካላቹ  ጥርጣሬ  ለሚፈጥርባቹ
በዚህ ስልክ ቁጥር ማናገርና በቀጠሮ ማየትም ማሰራትም ትችላላችሁ ስቁ 0988504999 ወይም 0934492187
የአቅማቹን ገቢ ለማድረግ
ንግድ ባንክ - 1000388791369
Oromia bank:-1017500029076

መልእክቱን በማሰራጨት ተባበሩን። ምናልባት በናንተ በኩል ተሳትፎ የሚያደርግ ቢኖር ከአጅሩ ተካፋይ ትሆናላችሁ።
{ مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ }
"ሌሎችን ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የተገበረውን ሰው አምሳያ ምንዳ ይኖረዋል።"
=
ቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/mesud22

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

07 Nov, 04:22


ሴት ልጅ ለሶላት ፀጉሯን መሸፈን አለባት። ብቻዋን እንኳ ብትሆን። ካጠገቧ ማንም ባይኖር እንኳ።
እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ ባስተላለፈችው ሐዲሥ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لا يقبل الله صلاة حائض إلا بخمار
"አላህ ለአቅመ ሄዋን የደረሰችን ሴት ያለ ጉፍታ ሶላቷን አይቀበላትም።" [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 596]
ፀጉሯን የምትሸፍንበት ልብስ ስስ ሆኖ ፀጉርን አሳልፎ የሚያሳይ መሆን የለበትም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

04 Nov, 12:28


መህዲ ተብሎ በሚጠራው በዐባሲያው ኸሊፋ ዘመን አንድ ሰው ነብይ ነኝ ብሎ ተነሳ። ወታደሮች አሰሩትና ኸሊፋው ዘንድ አቀረቡት።
* ኸሊፋው፦ "አንተ ነብይ ነህ?" ብሎ ጠየቀው።
- "አዎ" አለ ሰውየው።
* ኸሊፋው፦ "ወደ ማን ነው የተላክከው?" አለው።
- ሰውየው፦ "ወደ ማንስ እንድላክ መቼ ፋታ ሰጡኝ። ረፋድ ላይ ተልኬ ከሰዓት በኋላ አሰሩኝ።

[ረቢዑል አብራር፣ አልባቡ ታሲዕ]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

04 Nov, 05:21


⚠️⚠️ አንተስ ሲበዛ ለታመመው ቀልብህ ምን ያህል ግዜ እስቲግፋር ታደርጋለህ?

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنَّه لَيُغانُ على قَلْبِي، وإنِّي لَأَسْتَغْفِرُ اللَّهَ في اليَومِ مِائَةَ مَرَّةٍ﴾

“ልቤ ይጋረድብኛል በዚህ የተነሳ በቀን ውስጥ መቶ ግዜ እስቲግፋር አደርጋለሁ (ጌታዬን ምህረት እጠይቃለሁ)።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2702

🙁🙁🙁🙁🙁🙁☹️🥳

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

03 Nov, 14:12


አንዱ ደግ ሰው እንዲህ ይላል፦
* "በስራ ከተማ ስገባ ገበያዎቹ ተዘግተዋል። መንገዶቹ ባዶ ናቸው። 'የበስራ ሰዎች ሆይ! እኔ የማላውቀው ዒድ አላችሁ እንዴ?' አልኩኝ።
- ' እንደሱ አይደለም። ነገር ግን ሐሰኑል በስሪይ መስጂድ ውስጥ ሰዎችን እያስተማረ ስለሆነ ነው' አሉኝ።"
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

30 Oct, 13:36


እንቁ መልክት
ተማሪዎችን ሂጃብ መከልከል???
በሸይኽ ሙሐመድዘይን ዘህረዲን
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/mesud22

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

30 Oct, 03:41


«በትምህርት ቤቶች በየጊዜው የሚያገረሸው የኒቃብ ክልከላ ጉዳይ ቋሚ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል።

ፊትን ከባዕድ ወንዶች መሸፈን ግዴታ መሆኑ የአብዛኛዎቹ ዑለማዎች አቋም ነው።
ሆኖም ሴቶች ፊትና በማይሰጋበት ሁኔታ ለአስፈላጊ ጉዳይ ፊታቸውን ለወንዶች ማሳየት  እንደሚችሉ የሁሉም የፊቅህ ሊቃውንት ንግግር ያሳያል።

በዚህ መሰረት ተማሪዋ ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ስትገባ፣ ወደ ፈተና ማእድ ስትገባ፣  አጠራጣሪ ሁኔታ ሲኖር ወይም በማንኛውም ጊዜ ማንነቷን ማጣራትና ከመታወቂያዋ ጋር ማመሳከር ሲያሰፈልግ ፊቷን ገልጣ አሳይታ መልሳ መሸፈን ትችላለች።
«ሙሉ በሙሉ ተገልጠሽ ካልቆየሽ አትገቢም!» ማለት ግን ሀይማኖታዊ መብትን በግልፅ የሚጋፋ፣ ሴኪዩላሪዝም ራሱ የማይደግፈው… ምንም አግባብነት የሌለው የግለሰቦች ድርቅና ነው።»

#ሒጃብ #ኒቃብ #ትምህርት
#ሀገራዊ_ምክክር

ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

29 Oct, 05:16


ብሶት ደም ያስነባል
ፈርተን አይደለም የምናለቅሰው !!!
ፍትህ ለኒቃብ ለባሽ ተማሪ እህቶቻችን

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

29 Oct, 05:07


ሙዘኒይ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ አሉ፦

ሻፊዒይ ዘንድ ገባሁ። በሞቱበት ህመማቸው ላይ ሳሉ ነው። "እንዴት አደርክ የ0ብደላህ አባት?" አልኩኝ።
እራሳቸውን ቀና አደረጉ። ከዚያም:
"ዱንያን እየለቀቅኩ፣ ወንድሞቼን እየተለየሁ፣ ክፉ ስራዬን ለመገናኘት፣ ወደ አላህ ለመጓዝ የቀረብኩ ሆኜ አድሬያለሁ። ሩሔ ወደ ጀነት ሆና የምስራች የምላት ትሁን፣ ወደ እሳት ሆና የማረዳት ትሁን አላውቅም" አሉና አለቀሱ።

📚 [አሲየር : 10/75]
IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

27 Oct, 05:21


#ጥያቄና_መልስ

የምንቀሰቀሰው በነፍሶቻችን ነው በአካላችን አይደለም ብሎ የሚያምን ሰው እንደ ካፊር ይቆጥራልን?

🔖 በኦዲዮ (MP3)

🔗 ቪዲዮውን ለመከታተል
https://www.facebook.com/share/v/oZiDG5x15v5uYWjX/

🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

____
🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ የትምህርት መድረክ 
https://www.facebook.com/ustathilyas

t.me/ustazilyas

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

26 Oct, 04:36


የልብ ድርቀትን ለመከላከል
~
በዚህ ዘመን በልብ ድርቀት ያልተጠቃ ይኖር ይሆን? ሃሳብ ጭንቀታችን ዱንያ ብቻ ሆነ። ዒባዳችን ለዛ አጣ። መተዛዘን ጠፋ። ስግብግብነት ነገሰ። ስስት ከደም ከስጋችን ጋር ተዋህደ። የዱንያ ምኞታችን ከመርዘም አልፎ ተንዘላዘለ።
ወንድሞች እህቶች ወላሂ! የልብ ድርቀት በጣም ሊያስጨንቀን የሚገባ ህመም ነው። የልብ ድርቀት አደገኛ ውጤት የሚያስከትል የአላህ ቅጣት ነው። ከዚህ ህመም ልባችንን እንዴት እናክም? ከዚህ የአላህ ቅጣት እንዴት እንውጣ? ጥቂት ሰበቦችን ልጠቁም። ራሴም ጤነኛ ሆኜ አይደለም። ከማጨስ እንደሚያጠነቅቅ አጫሽ፣ ከህመም እንደሚያስጠነቅቅ ህመምተኛ ቁጠሩኝ።
1- አላህን በማሰብ ራስን አጠቃላይ ከወንጀል መጠበቅ፣ የቅርብም ይሁን የሩቅን ሰው ከመበደል መጠንቀቅ፣ ግብይታችንን፣ ገቢያችንን ሐላል ማድረግ፣ የሰው ሐቅ እንዳይመጣብን መጠንቀቅ
2- ምላስን ከውሸት፣ ከመጥፎ ንግግር፣ ከሃሜትና መሰል ክፍቶች መቆጣጠር፣ ጆሮዎቻችንን ሐራም ነገሮችን ከማዳመጥ፣ አይኖቻችንን ሐራም ነገሮችን ከመመልከት፣ እጆቻችንን ለሐራም ነገሮች ከመጠቀም፣ ልባችን በክፋት፣ ምቀኝነት፣ ጥላቻ፣ ... ላይ ከመጥመድ መቆጣጠር
3- ዚክር ማዘውተር፣ በቋሚነት የቁርኣን ዊርድ መያዝ፣ ደጋግሞ ከልብ ዱዓእ ማድረግ፣ ተደቡር፣ ተፈኩር ማድረግ፣ በዱዓእ፣ በቁርኣን ማልቀስ
4- ከሰላት፣ ከፆም፣ ከሶደቃው፣ ... ከግዴታው ባለፈ ነፍል ዒባዳዎችን ማዘውተር
5- ሞትን፣ ቀብርን፣ ሂሳብን፣ ሲራጥን፣ ... ኣኺራን ማሰብ
6- ደግሞ ደጋግሞ ኢስቲግፋርና ተውበት ማድረግ
7- ቁርኣን በእርጋታ መቅራት፣ ኹሹዕ የሚያጋባ አቀራር ያላቸውን ቃሪኦች ማዳመጥ፣
8- ቀብር መዘየር፣ የታመመን መጠየቅ፣ ወላጆችን፣ ዘመድ አዝማድን፣ ጎረቤትን አቅም በፈቀደ መጠየቅ
9- ችግረኛን በገንዘብም፣ በሃሳብም፣ በጉልበትም፣ በእውቀትም መርዳት፣ ሶደቃ ማድረግ
10- የዙህድና የረቃኢቅ ኪታቦችን ማንበብ፣ ውስጥን ሰርስረው የሚገቡ ሙሓደራዎችን እየፈለጉ ማዳመጥ፣ የነብዩን ﷺ ስራዎች፣ ራስን ለመታዘብ የሚያግዙ የሰለፎችን አስገራሚ ታሪኮች፣ የዑለማኦችን ጣፋጭ ወጎች በትኩረት መከታተል
11- በየትኛውም የዒባዳ መስክ ላይ ኢኽላስን አጥብቆ መፈተሽና ማቃናት።
12- ከራስ ጋር መተሳሰብ። ጊዜ አልፎ ጊዜ በተተካ ቁጥር ወደ ሞት እየቀረብን ነው። ከአምና ዘንድሮ፣ ከባለፈው በዚህኛው፣ ሳምንታችን፣ እለታዊ ውሏችን መሻሻል አለው? ወይስ ያው ነው? ወይስ ጭራሽ እየባሰበት ነው? ከዱንያችን በላይ ኣኺራችን ያሳስበናል? ድንገት ብንሞት ያለንበት ሁኔታ በፀፀት ጣት የሚያስነክስ አይደለም? ራሳችንን ለመለወጥ የምር እንታገል።

እኔ የራሴን ድክመቶች በመመልከት ድንገት የመጣልኝን ነው የፃፍኩት። ሁሉም ነገን አስቦ ዛሬ ራሱን ይመልከት።
﴿بَلِ الْإِنْسَانُ عَلَى نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ﴾
"በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡" [አልቂያመህ ፡ 14]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

26 Oct, 04:34


በጊዜ ተንፍስ
~
አንዳንድ ወንድሞች በሆነ የዒልም ዘርፍ ከእኩዮቻቸው ሲበልጡ ወይም የበለጡ ሲመስላቸው ትእቢት ሲፈትናቸው ይታያሉ። አንዱን መናቅ፣ ያኛውን ማጣጣል፣ ሌሎችን በመገምገም ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ ላይ ይጠመዳሉ።
የሸሪዐ እውቀት አላህን መፍሪያ መሳሪያ መሆኑ ሁሌም ሊዘነጋ አይገባም። ማወቅህ ትእቢት ካወረሰህ፣ በማወቅህ ለሌሎች ንቀትን ካዳበርክ ወላሂ ማወቅህ ጎድቶሃል። ጅህልና ላንተ የተሻለ ነበር። ሰው ቴኳንዶ ሰልጥኖ ቀድሞ ያልነበረውን አደብ ሲላበስ በምናይበት ጊዜ የሆነን ዒልም ሲማር እብሪትና ንቀትን የሚያዳብር ማየት አሳፋሪ ነው።
ወንድሜ ሆይ! መከበር ከፈለግክ ሰዎችን አክብር። ሌሎችን መናቅ ምናልባት ጥቂት ጊዜ ቢያስከብር ነው። ወይ ሰዎች እስከሚነቁ፣ ወይ ደግሞ ማንነትህ እስከሚገለጥ ድረስ ቢዘልቅ ነው። ከዚያስ? ከዚያማ መናቅህ መንናቅን ነው የሚያስከትልብህ። መተንፈስህ ላይቀር አፀፋ ሳያስተነፍስህ በፊት አላህን ፈርተህ ተንፍስ። በጊዜ ተንፍስ። አዎ መተንፈስ ይሻልሃል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

25 Oct, 16:50


የእነርሱን ብቻ ሳይሆን የሁላችንንም ልብስ ገፈው እርቃነ ገላ አድርገውናል።
ሩህማከ ያ አላህ

Mahi Mahisho

ቴሌግራም
👇👇👇
t.me/yesheh_kalidrashid_daewawoch

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

25 Oct, 05:15


በጁሙዐ ቀን ከሚወደዱ ተግባሮች ውስጥ አንዱ በነብዩ ﷺ ላይ ሰላት ማውረድ ነው። ምን ያህሎቻችን ይሄ ልማድ አለን?
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

24 Oct, 08:22


⚠️⚠️ የሚስትህን ድብቅ ሚስጥሮች ጠብቅ!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنَّ مِن أَشَرِّ النّاسِ عِنْدَ اللهِ مَنْزِلَةً يَومَ القِيامَةِ، الرَّجُلَ يُفْضِي إلى امْرَأَتِهِ، وَتُفْضِي إِلَيْهِ، ثُمَّ يَنْشُرُ سِرَّها﴾

“በትንሳዔ ዕለት ከሰዎች ሁሉ መጥፎ ሆኖ አላህ ዘንድ የሚመጣው፤ ሰውዬው ከሚስቱ ይጣቀምና (ግብረ ስጋ ግንኙነት ያደርግና) እሷም ትጣቀምና ከዛ ሚስጥሯን (ገመናዋን) የሚዘራ ነው።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 1437

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

⬇️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

💬፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

💬፦ https://bit.ly/486xnrS

💬፦ https://bit.ly/41zEZkk

📷፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

📺፦ https://bit.ly/3UTTSwh

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

23 Oct, 04:10


"ዱዓ ለተከሰተም ገና ለሚከሰትም መከራ
እጅግ ጠቃሚ ነው።
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ! ከዱዓ እንዳትዘናጉ አደራ!!"
ረሱል (ﷺ)
(ሰሂህ አልጃሚዕ: 3409)

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

22 Oct, 05:47


🔻በመጀመርያ መርካቶ በነበረው የእሳት አደጋ ንብረታችሁን ላጣችሁ ወንድሞቻችን አሏህ በተሻለ ይተካችሁ። ሶብሩንም ይስጣችሁ።

🔻በመቀጠል መርካቶም ሆነ ሌላም የንግድ ቦታዎች ላይ ያለን ሰዎች የትናንቱ እሳት ካለንበት የማጭበርበር ወንጀል ወደአሏህ እንድንመለስ ማንቅያ ደውል ነው። ሰዎችን ሸውደን ያልሆነ እቃ ሽጠን ምናካብተው ሀብት በደቂቃ እንደሚጠፋ ማሳያ ነው። ወደአሏህ እንመለስ!

@ibnyahya777

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

22 Oct, 04:38


በመርካቶው ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባችሁ ወገኖች ሁሉ። ከምንም በፊት ሶብር አድርጉ። አላህ ሰጠ። አላህ ነሳ። ሙስሊም በደስታውም በሀዘኑም ጌታውን ያስባል። ጌታችን እንዲህ ይላል፦

{ وَلَنَبۡلُوَنَّكُم بِشَیۡءࣲ مِّنَ ٱلۡخَوۡفِ وَٱلۡجُوعِ وَنَقۡصࣲ مِّنَ ٱلۡأَمۡوَ ٰ⁠لِ وَٱلۡأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَ ٰ⁠تِۗ وَبَشِّرِ ٱلصَّـٰبِرِینَ (155) ٱلَّذِینَ إِذَاۤ أَصَـٰبَتۡهُم مُّصِیبَةࣱ قَالُوۤا۟ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّاۤ إِلَیۡهِ رَ ٰ⁠جِعُونَ (156) }
"ከፍርሃትና ከረሃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር። እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ፡ 'እኛ ለአላህ ነን፤ እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን' የሚሉትን።" [አልበቀረህ፡ 155-156]

አልሐምዱ ሊላህ በሉ። የሙእሚን ወጉ ይሄ ነው። በመከራውም በደስታውም ጊዜ ጌታውን አይረሳም። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
عَجَبًا لأَمْرِ المُؤْمِنِ، إنَّ أمْرَهُ كُلَّهُ خَيْرٌ، وليسَ ذاكَ لأَحَدٍ إلَّا لِلْمُؤْمِنِ، إنْ أصابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ، فَكانَ خَيْرًا له، وإنْ أصابَتْهُ ضَرَّاءُ، صَبَرَ فَكانَ خَيْرًا له.
"የሙእሚን ነገሩ ይደንቃል። ሁለ ነገሩ መልካም ነው። ይሄ ለሙእሚን እንጂ ለማንም አይደለም። አስደሳች ነገር ቢያገኘው ያመሰግናል። ይሄ ለሱ መልካም ነው። ጉዳት ቢያገኘውም ይታገሳል። ይሄ ለሱ መልካም ነው።" [ሙስሊም፡ 2999]

በማመስገን ታተርፋላችሁ እንጂ አታጡም። በአይነ ህሊናችሁ ቃኘት ቃኘት ብታደርጉ አገር ምድሩ በፈተና ተጥለቅልቆ ታያላችሁ። የባሰ የገጠማቸውን ተመልከቱ። ንብረት ብቻ ሳይሆን ሙሉ ቤተሰብ ያለቀበት ስንት ጉድ አለ። አስቡ። ለመፅናናት ይጠቅማችኋል። ከተስፋ መቁረጥ ይታደጋችኋል። ከባሰ ሁሉ በላይ የባሰ አለ። ከባሰው ያዳናችሁን አመስግኑ። ተስፋ መቁረጥ፣ አጉል ብስጭት ያለፈውን ላይመልስ ከሁለት ያጣ ያደርጋል። ደግሞም እወቁ! አያልፍ የመሰለው ሁሉ ያልፋል። ኢንሻአላህ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ከምንም በላይ ግን ዱንያ ነው። ትልቁ ኪሳራ የኣኺራ ኪሳራ ነው። ጌታችን እንዲህ ይላል፦
{ قُلۡ إِنَّ ٱلۡخَـٰسِرِینَ ٱلَّذِینَ خَسِرُوۤا۟ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِیهِمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۗ أَلَا ذَ ٰ⁠لِكَ هُوَ ٱلۡخُسۡرَانُ ٱلۡمُبِینُ }
" 'ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በቂያማ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ንቁ! ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው' በላቸው።" [አዙመር፡ 15]

አላህ ሶብሩን ይስጣችሁ። በተሻለ ይተካችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

19 Oct, 11:19


👆🏻👆🏻👆🏻
📚የቴሌ እና ሌሎች አክሲዮኖችን ስለመግዛት


🔗 ቴሌግራም ሊንክ
https://t.me/ustazilyas/1279

🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

____
🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ የትምህርት መድረክ 
https://www.facebook.com/ustathilyas

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

15 Oct, 11:28


ከሶላት በኋላ የተስቢሕ አፈፃፀም
~
1- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 33 ጊዜ። 100ኛ "ላ ኢላሀ ኢለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ። ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ማለት። [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]
2- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 34 ጊዜ ማለት። ድምሩ 100 ይሆናል። [ሙስሊም]
3- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 33 ጊዜ ማለት። ድምሩ 99 ይሆናል። [ሙስሊም]
4. ሱብሓነላህ 10 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 10 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 10 ጊዜ ማለት። ድምሩ 30 ይሆናል። [ቡኻሪይ]
5. ሱብሓነላህ 11 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 11 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 11 ጊዜ ማለት። ድምሩ 33 ይሆናል። [ሙስሊም]
6. ሱብሓነላህ 25 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 25 ጊዜ፣ ላ ኢላሀ ኢለላህ 25 ጊዜ እና አሏሁ አክበር 25 ጊዜ ማለት። ድምሩ 100 ይሆናል። [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።]

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

14 Oct, 12:42


⚠️ያለፍቃዳቸው የሰዎችን ወሬ ከማድመጥ ተጠንቀቅ❗️

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَنِ اسْتَمع إلى حَديثِ قَوْمٍ وهُمْ له كارِهُونَ، أوْ يَفِرُّونَ منه؛ صُبَّ في أُذُنِهِ الآنُكُ يَومَ القِيامَةِ﴾

“ሰዎች ሳይፈልጉ የነሱን ንግግር ያዳመጠ ሰው በዕለተ ትንሳዔ ጆሮው ዉስጥ የቀለጠ እርሳስ ይፈሰስበታል (ይደፋበታል)።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 7042

▫️▫️▫️▫️🎀🎀▫️▫️▫️▫️

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📱፦ https://bit.ly/486xnrS

📱፦ https://bit.ly/41zEZkk

📱፦ https://bit.ly/4arMbTx

📱፦ https://bit.ly/41tIUPv

📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

12 Oct, 09:05


ሙሐደራ ቁ.8 ... በድራማና ፊልም ዳዕዋ ማድረግ .. 👇👇

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

12 Oct, 09:05


▪️ሙሐደራ ቁ.8

🔻ርእስ ፦ በድራማና ፊልም ዳዕዋ ማድረግ

🗣 አቅራቢ ፦ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
____
©ዲን መመካከር ነው - الدين النصيحة
https://t.me/ibnyahya7/10004

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

07 Oct, 07:58


በዑመር ኢብኑ ኸጣብ ዘመን የመሬት መንቀጥቀጥ ገጥሞ ነበር

ዑመር እንዲህ አሉ ! ወይ እኔ ወይ እናንተ አላህን አምፀናል ወንጀል ተዳፍረናል አዲስ ነገርን ፈጥረናል .....

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

07 Oct, 07:28


በሀገራችን አነስተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። መሬት መንቀጥቀጥ አላህ ባሮቹን ከሚያስፈራራበት እና ከሚያስጠነቅቅበት ክስተቶች መካከል አንዱ ነው።
በእኛ እግር ዘወትር የምትረገጠው መሬት በጌታዋ ትዕዛዝ ትንቀጠቀጣለች። ህዝቦች በወንጀል ሲዘፈቁ፣ ሽርክ እና ጥፋት ሲንሰራፋ፣ በምድራችን ብክለት ሲስፋፋ ጌታችን አላህ ሰዎች ከጥፋታቸው ታርመው ወደሱ ይመለሱ ዘንድ ማስጠንቀቂያዎችን ይልካል።
ከነዚህ ማስጠንቀቂያዎች አንዱ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው። ይህ ማስጠንቀቂያ ካለንበት የወንጀል አረንቋ በመውጣት ወደ አላህ እንድንመለስ የማንቂያ ደውል ነው።
በሀገራችን የተከሰተው መሬት መንቀጥቀጥ በትንሹ ተከስቶ ያለፈ ቢሆንም ከበድ ያለ ሆኖ ቢከሰት ባለንበት የወንጀል አረንቋ እንደተዘፈቅን ወደ ጌታችን ፊት የምንቀርብበት ሁኔታ ይፈጠር ነበር። ይህ ከመሆኑ በፊት አሁን ላይ እድል አግኝተናል። ወደ አላህ እንመለስ። ጌታችንን አብዝተን ምህረትን እንለምን። አላህ እንዲታረቀን፣ በእዝነቱ እንዲያየን በዱኣ ልንበረታ ይገባል። አላህ ምህረቱን ይለግሰን!!

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

30 Sep, 07:52


⚠️⚠️ ስራህ ብቻውን ከጀነት አያደርስህም…

ከአቡ ሁረይራ (▫️) ተይዞ፡ ረሱል (🤲) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لن يُدخلَ أحدًا منكُم عملُه الجنةَ قالوا ولا أنت يا رسولَ اللهِ قال ولا أنا إلا أن يَتَغَمَّدَنِيَ اللهُ منه بفضلٍ ورحمةٍ﴾

“አንዳችሁም በሚሰራው መልካም ስራ ብቻ ጀነትን አይገባም። ሶሃበቹም አሉ፦ አንተም ብትሆን የአላህ መልዕክተኛ? እኔም ብሆን! አላህ በእዝነቱና በትሩፋቱ ሸፍኖኝ ቢሆን እንጂ።”

📚 ቡኻሪ (5673) ሙስሊም(2818) ዘግበውታል

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📱፦ https://bit.ly/486xnrS

📱፦ https://bit.ly/41zEZkk

📱፦ https://bit.ly/4arMbTx

📱፦ https://bit.ly/41tIUPv

📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

20 Sep, 08:13


ራስህን ማንም የማይፈልገው ተራ ፍጥረት አድርገህ አትገምት። በእርግጠኝነት የምነግርህ ማንም ሰው ላያስታውስህ ይችላል። የፈጠረህ አላህ ግን በየቀኑ «ባርያዬን በምን ሁኔታ አገኛችሁት?» እያለ መላኢካዎቹን ይጠይቃል።
አላህ ስለ አንተ ለመጠየቅ የስራህ ጥሩነት ወይም መጥፎነት አያግደውም። መጥፎ ስራ ብቻ ብተሰራ እንኳን እኔን ረስቶኛል ብሎ ፈፅሞ ችላ አይልህም። መልካም ከሚሰራው እኩል በየቀኑ ሁኔታህን ይጠይቃል።
ታዲያ የሚያኖርህና የሚረዝቅህ አላህ በዚህ ልክ አስፈላጊ ሆነህ ከተከታተለህ ሌላው ችላ ቢልህ ምን ይቀርብሃል? ይልቅ እሱ እንደሚያስታውስህ አንተም በየቀኑ አስታውሰህ አመስግነው።
وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا فَوۡقَكُمۡ سَبۡعَ طَرَآئِقَ وَمَا كُنَّا عَنِ ٱلۡخَلۡقِ غَٰفِلِينَ
«በእርግጥም ከበላያችሁ ሰባትን ሰማያት ፈጠርን። ከፍጥረቶቹም ዘንጊዎች አይደለንም።»
(ሙዕሚኑን 17)

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

19 Sep, 07:28


★ እስኪ ይህን የነብዩ ሙሀመድ ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም ሀዲስ ልብ ብላችሁ አንብቡት
*አብደላህ ብኑ ኡመር አላህ ይውደዳቸውና እንዲህ ይላሉ ፣ (( አንድ ቀን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ወደ እኛ ዞሩና እንዲህ አሉን " እናንተ የስደት ህዝቦች ሆይ አምስት ነገሮች አሉ በነሱ ከተፈተናችሁ ኸይር የለውም እንዳያገኙዋችሁ በአላህ እጠበቃለሁ
1— ብልግና በህዝቦች መሀል በአደባባይ አይስፋፋም አላህ በነሱ ላይ ወረርሽኝ በሽታ ያመጣባቸው ቢሆን እንጂ ፣ እንዲሁም ከነሱ በፊት በነበሩ ህዝቦች ያልነበሩ በሽታዎች የሚመጡ ቢሆን እንጂ
2— ሰዎች ሚዛንንና ስፍርን አያጎድሉም በድርቅ፣ በቸነፈር እና በባለስልጠን አምባገነንነት ቢፈተኑ እንጂ
3— ሰዎች ከሀብታቸው ዘካን አይከለክሉም ከሰማይ ዝናብን የተከለከሉ ቢሆን እንጂ ፣ እንስሳዎች ባይኖሩ ኖሮ አንድም አይዘንብላቸውም ነበር
4— የአላህንና የመለእክተኛውን ቃል አይጥሱም በውጭ ጠላት የተወረሩና ከይዞታቸውም የሚወስዱባቸው ቢሆን እንጂ
5— መሪዎቻቸው በአላህ ባወረደው ኪታብ ካልመሩና አላህ ከወረደው መመሪያ የሚመቻቸውን ብቻ አይመርጡም አላህ ጦርነትን በመሀላቸው የሚያደርግባቸው ቢሆን እንጂ ።))
عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ قَالَ : أَقْبَلَ عَلَيْنَا رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ : " يَا مَعْشَرَ الْمُهَاجِرِينَ، خَمْسٌ إِذَا ابْتُلِيتُمْ بِهِنَّ، وَأَعُوذُ بِاللَّهِ أَنْ تُدْرِكُوهُنَّ : لَمْ تَظْهَرِ الْفَاحِشَةُ فِي قَوْمٍ قَطُّ حَتَّى يُعْلِنُوا بِهَا إِلَّا فَشَا فِيهِمُ الطَّاعُونُ، وَالْأَوْجَاعُ الَّتِي لَمْ تَكُنْ مَضَتْ فِي أَسْلَافِهِمُ الَّذِينَ مَضَوْا، وَلَمْ يَنْقُصُوا الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ إِلَّا أُخِذُوا بِالسِّنِينَ وَشِدَّةِ الْمَئُونَةِ وَجَوْرِ السُّلْطَانِ عَلَيْهِمْ، وَلَمْ يَمْنَعُوا زَكَاةَ أَمْوَالِهِمْ إِلَّا مُنِعُوا الْقَطْرَ مِنَ السَّمَاءِ، وَلَوْلَا الْبَهَائِمُ لَمْ يُمْطَرُوا، وَلَمْ يَنْقُضُوا عَهْدَ اللَّهِ وَعَهْدَ رَسُولِهِ إِلَّا سَلَّطَ اللَّهُ عَلَيْهِمْ عَدُوًّا مِنْ غَيْرِهِمْ، فَأَخَذُوا بَعْضَ مَا فِي أَيْدِيهِمْ، وَمَا لَمْ تَحْكُمْ أَئِمَّتُهُمْ بِكِتَابِ اللَّهِ، وَيَتَخَيَّرُوا مِمَّا أَنْزَلَ اللَّهُ إِلَّا جَعَلَ اللَّهُ بَأْسَهُمْ بَيْنَهُمْ ".
رواه ابن ماجه
حكم الحديث: حسن
★ አይ ሰው
ምን ያላጠፋው ጥፈት አለ
*ያ ረቢ ማረን
★ያረቢ ይቅር በለን
*ያረቢ ወዳንተ መልሰን

የሸይኽ ኢልያስ አህመድ ደርሶች ማግኛ ቻናል

17 Sep, 13:23


#ጥያቄና_መልስ

በሃሜት ያማናቸውን ሰዎች ማግኘት ካልቻልን ምን እናድርግ?

🔖 በኦዲዮ (MP3)

🔗 ቪዲዮውን ለመከታተል
https://www.facebook.com/share/v/DyKXKW2aB7Qd1H3f/?mibextid=oFDknk

🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

____
🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ የትምህርት መድረክ 
https://www.facebook.com/ustathilyas

t.me/ustazilyas

9,246

subscribers

262

photos

143

videos