እግዚአብሄር ሙሴን አስፈሪው
የእግዚአብሄር ቁጣ ከእስራኤል
እንዲመለስ የሕዝቡን አለቆች
ሁሉ ወስደህ ግደልና በጠራራ
ጸሀይ ላይ በእግዚአብሄር ፊት
ስቀላቸው አለው። ሙሴም
የእስራኤልን ዳኞች እያንዳንዳ
ችሁ የፌጎርን በአል በማምለክ
የተባበሩትን ሰዎቻችሁን ግደሉ
አላቸው።" ከዚህ በሁዋላ ሙሴና
መላው የእስራኤል ማህበር
በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ
እያለቀሱ ሳለ፣አንድ እስራኤላ
ዊ እነርሱ እያዩት አንዲት ምድ
ያማዊት ሴት ይዞ ወደ ቤተሰቡ
መጣ።
የካህኑ የአሮን ልጅ የአልአዛር
ልጅ ፊንሀስ ይህን ባየ ጊዜ ማሕ
በሩን ትቶ ጦሩን በእጁ በመያዝ
እስራኤላዊውን ተከትሎ ወደ
ድንኳኑ ገባ ጦሩንም ወርውሮ እስራኤላዊውንና ሴቲቱን አጣምሮ ወጋቸው፤ከዚያም በእስራኤላውያን
ላይ የወረደው መቅሰፍት ተከለከለ፤
ሆኖም በመቅሰፍቱ የሞተው
ሰው ቁጥር ሀያ አራት ሺህ
ደርሶ ነበር። እግዚአብሄር
ሙሴን እንዲህ አለው፤የካህኑ
የአሮን ልጅ የአልአዛር ልጅ
ፊንሀስ እኔ ለክብሬ በመካከ
ላቸው እንደምቀና ስለ ቀና
ቁጣዬን ከእስራኤላውያን
መልሶታል፤ስለዚህ እኔም
በቅናቴ ጨርሶ አላጠፋሁዋ
ቸሁም ስለዚህ እነሆ እኔ የሰ
ላም ቃልኪዳኔን ከእርሱ ጋር
እንደማደርግ ንገረው። ለአም
ላኩ ክብር ቀንቶ ለእስራኤላ
ውያን ስላስተሰረየላቸው እር
ሱና ልጆቹ ዘላቂ የክህነት ቃል
ኪዳን ይኖራቸዋል።
(ዘህ25፥1-13)
🚨እግዚአብሄር ቁጣው እንዲ
በርድ ያዘዘው አንድ ነገር ነው
እሱም የሕዝቡን አለቆች በአ
ደባባይ እንዲሰቀሉ ለሙሴ
ትእዛዝ በመስጠት ነበር።
👉 የእግዚአብሄር ቁጣ ደግሞ
መቅሰፍትን በእስራኤል ላይ
አመጣ በመቅሰፍቱም 24.000
ሺህ ሰዎች ሞቱ። በዚህ መሀል
የካህኑ አልአዛር ልጅ ፊንሐስ
ከእስራኤላውያን ጋር በምንዝር
ሀጢአት የወደቁትን የምድያ
ም ነገድ አለቃ ልጅ የሆነችውን
ሴት እና እስራኤላዊ መትቶ ገደ
ላቸው በዚህ ጊዜ በእስራኤል
ላይ የወረደው መቅሰፍት ተከ
ለከለ የእግዚአብሄር ቁጣ
መጥቶ በዘለአለም ፍርድ
መቅሰፍት ተወስኖብን የነበር
ነውን እኛ እንደ ፊንሐስ ኢየ
ሱስ መሀል ገብቶ ከዘላለም
ሞት መቅሰፍት አስመልጦና
ል በዚህም እግዚአብሄር በፊ
ንሐስ እንደተደሰተው ብቻም
ሳይሆን ከዚያም በላይ ረክቷል
በልጁ መስዋእት ለአንዴና
ለመጨረሻ ጊዜ ረክቷል።
ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥በክ
ርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን
የማስታረቅሞ አገልግሎት
ከሰጠን፥ከእግዚአብሄር ነው፤
እግዚአብሄር በክርስቶስ ሆኖ
አለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ
ነበርና፥በደላቸውን አይቆ
ጥርባቸውም ነበር፤በእኛም
የማስታረቅ ቃል አኖረ።
(2ኛቆር5፥18-19)
በእነዚህም ልጆች መካከል
እኛ ሁላችን ደግሞ የስጋችንና
የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን
በስጋችን ምኞት በፊት እንኖር
ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ
ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች
ነበርን። (ኤፌ2፥3)
🚨 እግዚአብሄርን እንደ ልጁ
መስዋእት ያረካው ነገር የለም!
የእግዚአብሄር ቁጣ እንዲበርድ
ካልበረደ ግን መቅሰፍት እንደ
ሚወርድ ብዙዎችን እንደሚያ
ጠፋ እንዲሁ እኛ ከፍጥረታችን
ከአዳም በወረስነው ሀጢአት
ልንጠፋ እና ቁጣው በእኛ ላይ
ነዶብን ነበር ስጋን የለበሰው
እግዚአብሄር ግን በመሀል
ገብቶ መካከለኛችን ኢየሱስ
እንደ ፊንሐስ የማስታረቅን ስራ
ሰራልን። ፊንሐስ እነዛን ሰዎች
በመግደል ሀጢአትን አስተሰረየ
ኢየሱስም ለኛ በደሙ አስተሰረ
የልን የኢየሱስ ደም ከሀጢአት
ሁሉ ያነጻናል።(1ኛዩሀ4፥10እና
1ኛ ዩሀ1፥7)።
@christology_GC
@christology_GC