ቅዱስ ያሬድ ዛሬ በሚዘመረው መዝሙር ላይ ''ወረደ መንፈስ ቅዱስ ላእለ ሐዋርያት........''
ስለመንፈስ ቅዱስ መውረድ ከዚህ በፊት ባጭሩ ለመማማር ሞክረናል ዛሬ ግን የመንፈስ ቅዱስንና የቤተ ክርስቲያንን ግንኙነት ባጭሩ እንነጋገራለን ጌታ መንፈስ ቅዱስ ማስተዋሉን ያድለን
ቅዱስ ሉቃስ ስለ ጰራቅሊጦስ በጻፈው ምእራፍ
ሐዋርያት 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥
² ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።
ተቀምጠውበትም የነበረውን ቤት ሞላ የሚለውን ቃል በማስተዋል እንየው በመጽሐፍ ቅዱስ የመንፈስ ቅዱስ ምልዓት ከተገለጸባቸው ሁለት ነገሮች አንዱ ሐዋርያት የተሰበሰቡባት ቤት ናት እሷም የሐዲስ ኪዳኗ ቤተክርስቲያን ነች እኛ የክርስቶስ ተከታዮች የምንሰበሰብባት የመንፈስ ቅዱስን ፀጋ የምንቀበልበት ቤት ነች እንግዲህ መንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለም በቤተክርስቲያ ሞልቶ ለዘለዓለም ይኖራል ለዚህ ነው ቅዱስ ዮሐንስ ራእዩ ላይ እግዚአብሔርን በመቅደሱ መልቶ አየሁ ሲል የተናገረው ከዚህም በኋላ በቤቱ መንፈስ ቅዱስ ከመላ በኋላ በያንዳንዱ ሐዋርያት ላይ ወረደባቸው እኛም በልጅነት በሰማንያና በአርባ ቀናችን በቤተክርስቲያን መልቶ ካለው መንፈስ ላይ እንካፈላለን
ይህ እንዳለ ሆኖ ቅዳሴ ለምን ገቡ ይባላል ለሚለው ጥያቄ መልስ ስንሰጥ በቤተ መቅደስ መልቶ ሁሌ የሚኖረው ጌታ መንፈስ ቅዱስ ሁሌ በመላእክት የተመሰገነ እንዲሁም ሁልጊዜ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ያልተቋረጠባት ነች እነሆ አባቶቻችን ካህናትም ከዚህ በረከት ሁላችንንም ሊያሳትፉን ከዚህ ምስጋና ሊሳተፉ ወደ ቅዳሴ ይገባሉ ተጀመረ የሚባል ነገር ያልተጀመረ ነገር ወይም ተቋርጦ የነበረ ነገር ነው በቤተመቅደስ በካህናት የሚቀርበው ምስጋና ግን ሁሌ በመላእክት የሚቀርብ ነውና አባቶች ካህናት ገብተው ከምስጋናው አሳትፈውን ድካመ ስጋ አለባቸውና ድካም ስጋቸው ለማሳረፍ ይወጣሉ በዚህ ምክንያት ቅዳሴ ገቡ ይባላል
ወዳጆቼ እኛ የምንመጣባት ቤት በመንፈስ ቅዱስ የተመላች እንጂ ባዶ በግንብና በወርቅ ብቻ የተለበጠች ቤት አይደለችም ይልቁንስ ህይወት የሆነው ጌታ መንፈስ ቅዱስ የሚገኝባት ነች 🥰🥰