Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission @southpolicecommission Channel on Telegram

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

@southpolicecommission


This is central Ethiopia Regional police commission official Page/ይህ የማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን የቴሌግራም ቻናል ነዉ/

South Police Commission Telegram Channel (Amharic)

ምን ነዉ? ምን ነው? እንዴት አይደለም? በዚህ ገጽ እስከ በርካታ ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ቻናሎች በቴሌግራም አባል የተገኘው "South Police Commission" በመጀመሪያ እና በአሁኑም ሰአት እንዴት ለሚከተለው ነው። እንደተካሄደ አንባቢዎች ያገኙት ዜናዎችና ቁጥሮችን ድምጽም እስከ እናቶች ስንዝህ በተለያዩ እና አገራችን ጨምሮ በምንከተለውም ታሪካዊ ችግሮች ካለ ግንባታ ላይ ታወቁና። በአሁኑ ጊዜ ሁለቱን ከተለያዩ ዜና ከዜና መካከል ስለማለት ጥቅም ለውስጡ መጠቀም አስቀድሞ ይሄን ማሰባሰብን አትልቀኝም ላይ ነው።

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

05 Feb, 16:49


በተፋሰስ ልማት ስራ ላይ ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ፖሊስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱ ተገለፀ

ሆሳዕና ጥር 27 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል በተቀናጀ አኳሀን የተፋሰስ ስራ እየተሰራ ነዉ።

ይህንን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ፖሊስ የወንጀልና የትራፊክ አደጋን በህብረተሰቡ እገዛ አሰቀድሞ መከላከል ይችል ዘንድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ መሆኑንና የፖሊስ አባላትም በልማት ስራዉ ለይ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ።

የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ፣ የ3ቱም ወረዳ እና የቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አመራርና አበላት ተሳታፊ መሆናቸዉ ተነግሯል።

የሀላባ ዞን ፖሊስ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነትን ለመጠበቅና ሁለንተናዊ ልማትን ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው ከፀጥታ አካለት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን ከዞኑ ፖሊስ የደረሰን መረጃ አመላክቷል።

##ሰላም

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

03 Feb, 17:40


የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስና ጤናማ የሆነ የትራንስፖርት ፍሰት እዉን ለማድረግ ባለ ድርሻ አካላት በተቀናጀ መንገድ ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸዉ ተገለፀ

ሆሳዕና ጥር 26 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) ይህ የተገለፀዉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስና ጤናማ የሆነ የትራንስፖርት ፍሰት እዉን እንዲሆን ለማስቻል የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ከክልሉ ሶስት ዞኖች ለተወጣጡ የፖሊስና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት የስራ ኃላፊዎች የተሳተፉበት ስልጠና በዛሬዉ እለት በሆሳዕና ከተማ ሲጀመር ነዉ።

ስልጠናዉ ሲጀመር የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና ትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰንበቶ አበበ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመደጋገፍ የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን በተቀናጀ አኳሀን ለመከላከል ያልተቋረጠ ጥረት ቢደረግም የአደጋዉ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ መምጣቱን ተናግረዋል።

በመሆኑም ክልላችን የሚያደርገዉ ጥረት የተፈለገዉ ዉጤት እንዲያመጣ ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል የሚያደርገዉ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት በክልላችን ያዘጋጀዉ ስልጠና እንደ ክልል የትራፊክ አደጋን በሂደት ለማመናመንና ዜሮ ደረጃ ለማድረስ የጀመርነዉ ጥረት የተፈለገዉ ዉጤት እንዲያመጣ የአሰራር ክፍተትን ለመድፈንና የማስፈፀም አቅማችን ከፍ ለማድረግ ስልጠናዉ ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።

ምክትል የቢሮ ኃላፊዉ በመጨረሻም ፖሊስ ፣ጤናና ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ሶስቱ ተቋማት በጋራ በመሆን በድሀረ አደጋ ላይ የሚደርሰዉ የሞት መጠን ለመቀነስ ተቀናጅተን እየሰራን እንገኛለን ይኸዉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መሀመድ ሀሰን በበኩላቸዉ በርካታ የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ ከደረሰባቸዉና የንፁሀን ዜጎች ህይወት ከጠፋባቸዉ አካባቢዎች የቡታጅራ፣ ወራቤ ሆሳዕና ኮሪደር አንዱ ሆኖ በመገኘቱ ለሙከራ መመረጡና የተግበራ ስራዉን ለማስጀመር ለባለድርሻ አካላት ስለጠና መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ሌሎች ሀገራት የሚደመሙበትና ምስክርነትም የሚሰጡበት ልማት ተመዝግቧል ያሉት አቶ መሀመድ ሀሰን በትራፊክ አደጋ ምክኒያት የሚደርሰዉ የሰዉ ህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉድለትና የንብረት ዉድመት በዚዉ ልክ አንገታችን የሚያስደፋን ጉዳይ ስለሆነ አደጋዉን አስቀድሞ ለመከላከል የጋራ ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል።

ኃላፊዉ አክለዉም አደጋ ከደረሰ በኃላም ተጎጂዎችን አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜዉስጥ ወደ ሆስፒታል ደርሰዉ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ በማድረግ የትራፊክ ፖሊሶች፣ የትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የዜጎች ህልፈት ለመቀነስ የጋራ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅባችሁዋል ብለዋል።

የሙከራ ስራዉን ለማስጀመር ታስቦ በህግ ማስከበርና በድህረ አደጋ ምላሽ አሰጣጥ ዙሪያ ላይ በተዘጋጀዉ ስልጠና ለመካፈል ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ፣ ከሀዲያ፣ከስልጤና ከምስራቅ ጉራጌ፣ ዞኖች የፀጥታ፣ የፖሊስ፣ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎች ታድመዋል።

##ሰላም!!

በታጁ ነጋሽ(ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

01 Feb, 17:25


በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚደርሰዉ የንፁሀን ሞትና አካል ጎደሎነትን ለመቀነስ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና በሆሳዕና ከተማ መሰጠቱ ተነገረ

ሆሳዕና ጥር 24 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በመንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ላይ ያተኮረ ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።

የትራፊክ አደጋን በዲጅታል/በGps And Gis/ በመጠቀም የቁጥጥር ስራዎችን ለማዘመንና ለማጠናከር ስልጠናዉ አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

የትራፊክ አደጋዎች ሲመዘገቡም መረጃዎችን በማደራጀት በተለያየ ጊዜ የሚስተዋለውን የመረጃ መበላሸትና መጥፋት ችግሮችን ለማቀረት የሚያስችል ሲሆን ስልጠና መሰጡቱ የትራፊክ ዘርፋን አሰራር ያዘምናል ነዉ የተባለዉ።

በመንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር ላይ ያተኮረ ስልጠና ሲሆን በክልሉ ከሚገኙ ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ የትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪዎች በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ስልጠና መሰጠቱ የክልሉ ፖሊስ ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

ስልጠናዉ የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑ ተገልጿል።

##ሰላም!!

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

24 Jan, 17:22


በሀላባ ዞን በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 18 ኩንታል አደንዣዥ ዕፅ መያዙ ፖሊስ ገለፀ

ሆሳዕና ጥር 16 ቀን 2017(ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ፖሊስ ባደረገዉ ድንገተኛ ፍተሻ መነሻዉን ሻሸመኔ አድርጎ ወደ ወላይታ ሶዶ ሊገባ የነበረ 18 ኩምታል ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዞኑ ፖሊስ ገልጿል።

የነዋሪዉን ህዝብ ሠላምና ደህነነት ለመጠበቅ ሲባል በቁሊቶ ከተማ በሮንድ ስራ ላይ የነበሩ የፖሊስ አባላት ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከለሊቱ 10:00 ግድም የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 -A04171 አዲስ አበባ በሆነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ ተጠራጥረዉ በማስቆም ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ 18 ኩምታል ካናቢስ የተሰኘ አደንዣዥ ዕፀ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋላቸዉ የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ኑርዬ ከድር ተናግረዋል።

ፖሊስ የወንጀሉ ምንጭ ለማወቅና በተያዘዉ አደንዛዥ ዕፅ ዝዉዉር ተጠርጥረዉ በተያዙት ሁለት ግለሰቦች ላይ ምርመራ የማጣራቱ ስራ መጀመሩን ነዉ አዛዡ የገለፁት።

ኮማንደር ኑርዬ በመጨረሻም የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ በለሊት የሮንድ ስራ ላይ ተሰማርተዉ በተመደቡበት ቀጠና የተጣለባቸዉ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁነት ሳይለያቸዉ አደንዣዥ ዕፀን መያዝ ለቻሉት ለሀላባ ዞን እና ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አባላትን አመስግነዋል ሲል ከዞኑ ፖሊስ የደረሰን መረጃ አመላክቷል።

ሀላባ ቁሊቶ በርካታ መዉጫና መግቢያ በሮች ያሏት ከተማ እንደመሆኗ በዛዉ ልክ ከተማዋን መነሻና መድረሻ ሊያደርጉ የሚችሉ ህገወጦች እኩይ አላማቸዉን ማሳካት እንዳይችሉ ፖሊስ ሌት ተቀን በእግረና በፓትሮል ተሽከርካሪ የተደገፈ የሮንድ ጥበቃ ስራ እየሰራ ይገኛል።

የተጣለባቸዉ ኃላፊነት ለአፍታ ሳይዘነጉ በትጋትና በጥንካሬ ኃላፊነታቸዉ የሚወጡት የሀላባ ዞን ፖሊሶች ተግቶ ለህዝብ ሰላም ዘብ መቆሙ ይኸዉ ተሞክሮ በክልላችን ሁሉም አካባቢዎች ቢለመድ መልእክታችን ነዉ። በርቱ ተበራቱ እንላለን።

##ሰላም!!
በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

23 Jan, 09:36


በስልጤ ዘን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአንድ ሰዉ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገለፀ

ሆሳዕና ጥር 15 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዘን በሁልባረግ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአንድ ሰዉ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ሌፎ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ከአዲስ አበባ ወደ አርባ ምንጭ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ (ዘመን ባስ) ከሳንኩራ ወደ ሁልባረግ ስምንት ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ ከነበረ ባጃጅ ታክሲ ጋር በመጋጨቱ የ8 ሰዎች ህይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ ከባድ የአካል ጉዳት የዳት የደረሰበት የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብስ ሾፌር ለህክምና እርዳታ ወደ ወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ሪፈራል ሆስፒታል ሆስፒታል መላኩን በክልሉ ፖሊስ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ባልደረባ ኢንስፔክተር ታምራት ደሳለኝ ገልፀዋል።

አደጋዉ ዛሬ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:30 ከሰላሳ መድረሱን የገለፁት ኢንስፔክተር ታምራት ከሟቾች ዉስጥ 1 ሴትና 7ቱ ወንዶች ሲሆኑ አንድ መምህርና ሁለት የግብርና ሰራተኞች መሆናቸዉ ገልፀዉ የአደጋዉ መንስኤ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር መሆኑን ነዉ የገለፁት።

##ሰላም!

በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

22 Jan, 17:47


በህገ -ወጥ የነዳጅ ግብይት ስራ ላይ በተሰማሩ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች ላይ የፀጥታ ኃይሉ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ትዕዛዝ ተሰጥቷል

ሆሳዕና ጥር 14 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በህገወጥ የነዳጅ ግብይት ስራ ላይ በተሰማሩ የነዳጅ ማደያዎች እና ቸርቻሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታዉቋል።

የቢሮዉ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ እንደገለፁት ሰዉ ሰራሽ በሆነ ምክንያት በተፈጠረ የነዳጅ እጥረት ህብረተሰቡ ለዕንግልትና ላልተፈለገ ወጪ ተዳርጓል፤ ከተሞችም ለፀጥታ ስጋት መጋለጣቸዉ ተናግረዋል።

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በክልሉ ባሉ ሁሉም ከተሞች የነዳጅ ማደያዎችን እንቅስቃሴ ተዘዋዉሮ የሚመለከት ግብረ -ኃይል አቋቁሞ ባደረገዉ ክትትል በአንድ አንድ ማዲያዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ተሽከርካሪዎች ተሰልፈዉ መስተዋላቸዉና በአግባቡ ያለመስተናገድ ችግር መስተዋሉ በምልከታዉ ተረጋግጧል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ነዳጅ ለማግኘት የሚሰለፉ ሰዎች ቁጥር መጠኑ እያሻቀበ መምጣቱ የክልሉን ፀጥታ ስጋት ዉስጥ ሊጥል እንደሚችል በዘርፉ ዳሰሳ ያደረገዉ ግብረ-ሀይሉ ማረጋገጥ ችሏል ነዉ የተባለዉ።

በተለየ ሁኔታ ቀን ቀን ነዳጅ የለንም ብለዉ በተዘጉ ማዲያዎች ማታ ማታ ለህገ-ወጥ ቸርቻሪ ነጋዴዎች በጀረኪና ሲቀዱ መገኘታቸዉ የተረጋገጠ በመሆኑ ህብረተሰቡን ለልተፈለገ ወጪ ከመዳረጉም በላይ የተስተዋለዉ ህገወጥነት በእንጭጩ መቅጨት ካልተቻለ ችግሩ ተባብሶ የፀጥታ ስጋት ሊሆን እንደሚችል ተገምግሟል።

መንግስት ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት በድጎማ ወደ ሀገር ዉስጥ ያስገባዉን ነዳጅ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በሚባል ደረጃ አንድ ሊትር ቤንዝል በአማካይ ከ250 እሰከ 350ና 400 ብር በድፍረት እየተሸጠ የህገወጦች ኪስ እየደለበ የነዋሪዉ ህዝብ እንቅስቃሴን በመገደብ ኢኮኖሚያዊ ቀዉሱን አባብሶታል።

የነዳጅ ማደያ በሌለባቸዉ አካባቢዎች የተሰጠዉ የችርቻሮ ፈቃድ ላይ የሚደረገዉ ቁጥጥርና ክትትል ልል መሆን ፈቃድ በተሰጣቸዉ ግለሰቦች ስም ከማድያ የሚቀዳዉ ነዳጅ ለህገወጥ የነዳጅ ቸርቻሪዎች በተሻለ ትርፍ ሲሸጥ ማደያዎችም ይህንን ክፍተት ተጠቅመዉ ነዳጁን በህገወጥ መንገድ ሲሸጡ መቆየታቸዉ ለነዳጅ እጥረቱ መባባስ ምክንያት መሆኑ ተደርሶበታል።

በሆኑም በዚህ አይነት ህገወጥ ድርጊት የተሳተፉ የሚሳተፉ ማደያዎች ከድርጊታቸዉ ፈጥነዉ ካልወጡ ቢሮዉ አስፈላጊዉን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ተገልጿል።

ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ለህገወጥ ቸርቻሪዎች ነዳጅ የሚያቀብሉና በህገወጥ ተግባር ላይ ተሳትፎ ያባላቸዉ ግለሰቦች ላይ በተለያየ የመንግስት መዋቅር ላይ የሚሰሩ አካላት የእርምት እርምጃ ካልወሰዱ ለህገ የበላይነት መከበርና ለህዝብ ጥቅም ሲባል ጠንከር ያለ ህጋዊ እርምጃ ለመዉሰድ ቢሮዉ የሚገደድ ይሆናል።

በመሆኑም በክልሉ በየደረጃዉ ተዋቅሮ የሚሰራዉ የፀጥታ ኃይል ጠንካራ ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ ህገወጥነትን ለማስቆም ሲባል አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

በክልላችን የተፈጠረዉን ሰዉ ሰራሽ የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ የፀጥታ ኃይሉ የሚያደርገዉ ክትትልና ቁጥጥር የተፈለገዉ ዉጤት እንዲያመጣ መላዉ የክልላችን ህዝብ እንደቀደመዉ ጊዜ ሁሉ ህገወጦችን አጋልጦ በመስጠት የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን ሆኖ አስፈላጊዉ እገዛና ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ መቅረቡ ከክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ፌስቡክ ገፅ የተገኘዉ መረጃ አመላክቷል።

##ሰላም!
በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

17 Jan, 09:08


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲዉል አስፈላጊዉ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ

ሆሳዕና ጥር 9 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዐከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሰባቱ ዞንና ሶስት ልዩ ወረዳዎች የ2017 ዓ.ም የከተራና የጥምቀት በዓል ያለምንም የጸጥታ ስጋት ተከብሮ እንዲዉል ፖሊስ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ወደ ተግባር መግባቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሺመልስ ካሳ አስታውቀዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሺመልስ ካሳ እንደገለፁት የከተራና የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴትነቱ ጠብቆ በሰላም ተከብሮ እንዲዉል በየደረጃዉ ባሉ የፖሊስ መዋቅሮች በተዘጋጀ አጭር የፀጥታ እቅድ ላይ ከሰባቱ ዞንና ከሶስቱ ልዩ ወረዳ የፖሊስ የስራ ኃላፊዎች በሆሳዕና ከተማ በተገኙበት መድረክ ምክክር ተደርጎ ወደ ተግባር መገባቱ ነዉ የተናገሩት።

ኮሚሽነር ሺመልስ አክለዉም በክልሉ 957 ታቦታት ከማደሪያቸዉ ወደ ጥምቀተ ባህር ይወሰዳሉ ብለዋል።

በዓሉ ያለምን የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲዉል የክልሉ መደበኛና አድማ ብተና ፖሊስ ፣የፌደራል ፖሊስ ፣የሚሊሻ እና ሌሎችም ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ተቀናጅቶ በመስራት የተጣለባቸዉ ኃላፊነት እንደሚወጡ እምነቴ ነዉ ብለዋል።

በተለይም በዓሉ በስፋት በሚከበሩባቸው አካባቢዎች ሁሉም የጸጥታ አካላት ወጣቱን በማሳተፍና ስምሪት በመስጠት አስተማማኝ የጸጥታ ጥበቃ ሥራዎች ይከናወናል ሲሉም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

ከሚሽነር ሺመልስ ህብረተሰቡ በየ-አካባቢዉ ተመድበዉ ከሚሰሩ የፀጥታ ኃሎች ጎን ሆኖ በመደገፍ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የድርሻዉ ሊወጣ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ህብረተሰቡ ለፀጥታ መደፍረስ አጠራጣሪ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ሲመለከትም በአቅራቢያዉ ለሚገኙ የጸጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ትብብር ሊያደርግ ይገባል ማለታቸዉ የክልሉ ፖሊስ ሚድያ ክፍል ዘግቧል።

##ሰላም!!
በታጁ ነጋሽ(ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

13 Jan, 10:46


የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ይበልጥ አስተማማኝ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተጠቆመ

ሆሳዕና ጥር 5 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6ወራት እቅድ ክንውን ረፖርት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሄድዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ እንደገለጹት በክልሉ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ይበልጥ አስተማማኝ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት የክልሉን ሰላም በአስተማማኝ ደረጃ ላይ ለማድረስ ከጸጥታ ዘርፍ አካላት ጋር ቅንጅታዊ ስራ ተግባራዊ በመደረጉ የላቀ ውጤት መመዝገቡን አብራርተዋል።

በክልሉ ወንጀልን አስቀድሞ መከላከል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የተጀመሩ ስራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ፣በወልቂጤ ከተማና በዙሪያው ባሉ ቀበሌዎች፣ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳና ከኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች፣ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ወረዳ እና በማረቆ ልዩ ወረዳ አጎራባች ቀበሌዎች የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት በተደረገ ጥረትየመህዝቡንዊ ሰላም ማስፈን ስለመቻሉም ኮሚሽነሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

በጉራጌ ዞን እኖር ኤነር መገር ወረዳ ቆሴ ከተማና አዋሳኝ ቀበሌያት ያለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ቀሪ ስራዎች እንደሚጠብቁ ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት።

በክልሉ የተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት መስጠታቸውን የተናገሩት ኮሚሽነሩ በየደረጃው ያለው አመራር ፣የጸጥታ አካላት እና መላው የክልሉ ህዝብ የላቀ ጥረት ማድረጉን ጠቁመዋል።

በክልሉ የታየው አንጻራዊ ሰላም የ24 ሰዓት የሰዎች እንቅስቃሴ እንዲኖር አስችሏል ያሉት ኮሚሽነር ሽመልስ በቀጣይ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባም አመላክተዋል።

##ሰላም!!

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

06 Jan, 12:59


ዉሃ ዉስጥ ገብቶ ሞቶ የተገኘን ግለሰብ ማንነት ለምታዉቁ ከፖሊስ የተላለፈ ጥሪ

ሼር በማድረግ ተባበሩን!!

ሆሳዕና ታህሳስ 28 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ለጊዜዉ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ ዉሃ ዉስጥ ገብቶ ህይወቱ አልፎ ዋልጋይ ወንዝ ዉስጥ በድንገላዉ መገኘቱ የወረዳዉ ፖሊስ ገልጿል።

ማንነቱ ያልታወቀዉ ግለሰብ ታህሳስ 27 ቀን 2017 ዓ.ም በቤደር ቀበሌ መሀል ዥጎድ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ከሚገኝ ዋልጋይ ወንዝ ዉሃ ውስጥ ሲገባ በቅርብ ርቀት የተመለከቱት የአካባቢዉ ነዋሪዎች ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መነሻ የሟችን አስክሬን አንስቶ ለምርመራ ወደ ሚኒልክ ሆስፒታል መላኩን የወረዳዉ ፖሊስ ገልጿል።

ሟች የአእምሮ ህመምተኛ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ አለኝ ያለዉ ፖሊስ የሟች ማንነት ለጊዜው ባለመታወቁ ከዚህ በታች የተለጠፈዉ የሟችን ፎተግራፍ በማየት ማንነቱን የምታዉቁ የገፃችን ተከታታዮች ለወረዳዉ ፖሊስ ስልክ ቁጥር በመደወል +251 46 17 86 360 አሊያም
መረጃዉን ለቤተሠቡ በማድረስ ትብብር ታደርጉ ዘንድ የወረዳው ፖሊስ ለህብረተሰቡ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ሼር በማድረግ መረጃዉ ተደራሽ እንዲሆን ትተባበሩ ዘንድ እንጠይቃለን!

##ሰላም!!

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

06 Jan, 12:04


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለመላዉ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት (ለገና) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ ሲል መልካም ምኞቱን ገልጿል

ሆሳዕና ታህሳስ 28 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በከፍተኛ ድምቀት ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል አንዱ ለሆነው የእየሱስ ክርስቶስ የልደት (ለገና በዓል) እንኳን በሰላም አደረሳችሁ በማለት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የመልካም ምኞት መግለጫና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሉ በሚገኙ 7 ዞኖችና 3 ልዩ ወረዳዎች ተዋቅሮ የሚሰራዉ የፖሊስ ተቋም የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉን ያለምንም የፀጥታ ስጋት አክብረዉ እንዲዉሉ ፖሊስ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለማስከበር በቂ ዝግጅት አድርጎ ወደ ተግባር ገብቷል።

የክልላችን ነዋሪዎች ለፀጥታ ስጋት አጠራጣሪ የሚሆኑ ጉዳዮችን ሲመለከት በአቅራቢያዉ ተመድበዉ ለሚሰሩ የፀጥታ ኃይሎች ጥቆማ በማድረስ የዜግነት ግዴታዉን እንዲወጣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ለመላዉ የክልሉ ህዝብ ጥሪ እያቀረበ በዓሉ የሰላም፣ የጤና ፣የመተሳሰብ፣ የአንድነትና የፍቅር እንዲሆን ተመኝቷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
ሆሳዕና

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

30 Dec, 18:49


በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ

ሆሳዕና ታህሳስ 21 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የተገኘ 1000(አንድ ሺህ) የሽጉጥ ጥይት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ ገልጿል።

የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ሙሰማ ጀማል በዛሬው እለት ረፋድ ላይ መነሻውን አዲስ አበባ መዳረሻውን ሆሳዕና አድርጎ በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከበቆሎ ጋር በመቀላቀል በድብቅ ተጭኖ ሲዘዋወር የነበረ 1000 የሽጉጥ ጥይት በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፀዋል።

ከተያዘዉ ተተኳሽ ጥይት ዝውውር ጋር በተያይዞ የመኪናው አሽከርካሪን ጨምሮ 6 ግለሰቦች ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ የማጣራቱ ስራ መጀመሩን አዛዡ አክለዉ ገልፀዋል።

በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለው ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጋር በጋራ ባደረገዉ ክትትል መሆኑን አዛዡ አክለዉ መግለፃቸዉ ከከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

##ሰላም!!

በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

28 Dec, 18:18


በትራፊክ አስተናባሪነት የፖሊስ አጋዥ ሆነዉ የሚሰሩ ተማሪዎችን ስልጠና ሰጥቶ ማሰማራቱን የላንፉሮ ወረዳ ፖሊስ ገለፀ

ሆሳዕና ታህሳስ 19 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በስልጤ ዞን በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ስልጠና የተሰጣቸዉ የተማሪ ትራፊክ አስተናባሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አጋዥ ሆነዉ እንዲሰሩ ወደ ተግባር መግባታቸዉ ለአደጋዉ መቀነስ አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ሲል የላንፉሮ ወረዳ ፖሊስ ገልጿል።

የላንፉሮ ወረዳ ፖሊስ ከትራንስፖርት መንገድ ልማት ጽህፈት ቤት ጋር በጋራ በመሆን ለተማሪ ትራፊኮች በመንገድ ደህንነት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል ።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የላንፉሮ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ጀማል ባሙድ እንደገለፁት የመንገድ ትራፊክ ዘርፉ ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት መሠረት እንደመሆኑ መጠን ከአደጋ ስጋት ነፃ ማድረግ እንዲቻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ ገልፀዋል ።

ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ ጥንቃቄ በመውሰድ የመንገድ አጠቃቀም ስርአት በመከተል የተማሩትን የትራፊክ ደህንነት ትምህርት ለቤተሠቦቻቸውና ለአካባቢው ህ/ተሰብ ስለ አደጋ አስከፊነት እንዲያስተምሩ ፣ ራሳቸውን ከአደጋ እንዲከላከሉና ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር ማድረግ የስልጠናው ዋና አላማ መሆኑን የላንፉሮ ወረዳ የመንገድ ትራንስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዳንኤል ወግአየሁ ገልፀዋል።

የላንፉሮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ዋሲል ጀማል አክለውም ስልጠናው በዘርፉ የሚከሰቱ አደጋዎችን በመቀነስ የዜጎችን ህይወት፣አካል እንዲሁም ንብረትን ከጉዳት መታደግ እንዲቻል ፋይዳው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም እንደ-እኛ አካባቢ የአስፓልት መንገድ መሠረተ ልማት እየተገነባ መሆኑን ተከትሎ ከበፊቱ በተለየ ሁኔታ ህ/ተሰቡ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ስለዚህ የተማሪ ትራፊኮችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ጠቁመዋል።

በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ ከወረዳው ካሉ ት/ቤቶች የተወጣጡ የተማሪ ትራፊክ ክበብ አባላት ፣ የት/ቤት ርዕሰ-መምህራን ፣የትራፊክ ክበብ ተጠሪ መምህራን ፣ የትራፊክ አባላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈው ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን ከውይይቱ በተጨማሪ የመስክ ስልጠና መሰጠቱም ተገልጿል።

##ሰላም!!

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

25 Dec, 18:48


በሀላባ ዞን ሚስቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለ ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት

ሆሳዕና ታህሳስ 16 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ሚስቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለ ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ ተገለፀ።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ሱልጣን ሙንዲኖ በሞት እንዲቀጣ ሲል የወሰነዉ በጫጉላ ሽር ሽር ላይ የነበረችዉን ሙሽራ ሚስቱን ሟች ሪባቴ ያሲንን በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት በፈፀመዉ የግድያ ወንጀል በተመሰረተበት ክስ ነዉ።

ፍርድ ቤቱ በግድያ ወንጀሉ በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ ተሳትፎ አላቸዉ በተበሉ ስምንት ሰዎች ተከሳሾች ላይ እንደየ ተሳትፏቸዉ የክብደት ደረጃ የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

1ኛ ተከሳሽ ሱልጣን ሼህ ሙህዲን በጫጉላ ሽር ሽር ላይ የነበረችዉን ሙሽራ ሚስቱን ሪባቴ ያሲን አሰቃቂ በሆነ መልኩ በፈፀመዉ የግድያ ወንጀል በሞት ቅጣት እንዲቀጣ ውሳኔ ተወስኖበታል።

ከ2ኛ -7ኛ ያሉትን ተከሳሾችን ደግሞ (3ኛ ተከሳሽ ሲቀር) ሌሎቹን ተከሳሾች በ6 ወር ቀላል እስራት እንዲቀጡ ውስኗል።በ3ኛ ደረጃ ስሙ ተጠቅሶ ክስ የተመሰረተበት ተከሳሽ ፍርድ ቤቱ በነፃ አሰናብቶታል።

8ኛ ተከሳሽ የጨቅላ ህፃን እናት መሆኗን ከግምት ውስጥ በማስገባት የ2 ዓመት የፈተና ጊዜ ተሰጥቷት ከማንኛውም የወንጀል ተግባር ታቅባ እንዲትቆይ የተወሰናባት የ6 ወራት ቀላል የእስር ውሳኔው ለሁለት ዓመት ታግዶ እንዲቆይ ብይን መሰጠቱ ከዞኑ ፍትህ መምሪያ የተገኘዉ መረጃ አመላክቷል።

##ሰላም!!
በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

25 Dec, 15:02


የምእመናን ጫማዎችን ሰርቆ ከቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ሲወጣ የተያዘዉ ተከሳሽ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

ሆሳዕና ታህሳስ 16 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ሙህር አክሊል ወረዳ ቤተ-ክርስቲያ ውስጥ ዘልቆ በመግባት የምእመናን ጫማዎች የሰረቀው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት።

ተከሳሽ ደምሴ ደሳለኝ በእስራት ሊቀጣ የቻለዉ በጉራጌ ዞን በሞህር አክሊል ወረዳ ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም በግምቱ ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ግድም በሀዋርያት ከተማ ወንጀል ለመፈፀም እንድያመቸው የተወሰኑ የማብራት ቆጣሪዎችን ካጠፋ በኋላ ሀዋርያት ፅርሀ ፅዮን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ዘልቆ በመግባት ለህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ለክብረ በዓል መጥተው ቤተ-መቅደስ ገረንገር ላይ ጫማቸው አውልቀው ቤተመቅደስ የገቡ የ9(ዘጠኝ ) ሰዎች ጫማ በለበሰው ጃኬት ሸክፎ ሲወጣ በክትትል በመፈፀሙ ከባድ የስርቆት ወንጀል በተመሰረተበት ክስ ነዉ።

ተከሳሹ የወንጀል ሪከርድ ያለበት መሆኑንና ፍርድ ቤት ቀርቦም የእምነት ክህደት ቃሉ እንዲሰጥ ተጠይቆ ክሱን እንደማይቃወም ወንጀሉን መፈፀሙ አምኖ በዝርዝር ያስረዳ በመሆኑና በሰጠዉ የእምነት ቃል መሰረት ፍርድ ቤቱ በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።

የሞህር አክሊል ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ደምሴ ደሳለኝን በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ ከምሁር አክሊል ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት የተገኘዉ መረጃ አመላክቷል።

##ሰላም!!

በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

19 Dec, 18:10


በለሊት የመኖሪያ ቤት በር ገንጥሎ በመግባት ስምንት የቀንድ ከብቶችን የዘረፈ ተከሳሽ በ15 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

ሆሳዕና ታህሳስ 10 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን እኖር ኤነር መገር ወረዳ በምሽት የመኖሪያ ቤት በር ገንጥሎ በመግባት ስምንት የቀንድ ከብቶችን የዘረፈ ተከሳሽ በ15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ የጉራጌ ዞን ፖሊስ ገልጿል።

ተከሳሽ ማሞ አበበ አብሬ በእስራት ሊቀጣ የቻለዉ ለጊዜዉ ካልተያዘዉ ግብረ አበሩ ጋር በመሆን ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 7 ስዓት ግድም በጉራጌ ዞን እኖር ኤነር መገር ወረዳ ኤነር ቆላ ቀበሌ ልዩ ስፍራው ማሳ ተብሎ በሚጠራው መንደር የግል ተበዳይ ሞላልኝ ኤርጣሞ መኖሪያ በር ገንጥለው በመግባት እቤት ውስጥ ተኝተው የነበሩትን 2 ሰዎች በመደብደብና አንድ ላይ እጅና እግራቸውን በገመድ በማሰር የይድረሱልኝ ጥሪ እንዳያሰሙ በማገት ከቤቱ ውስጥ የነበሩት ስምንት የቀንድ ከብቶችን በማዉጣት በተሸከርካሪ በመጫን ወደ ሀድያ ዞን ሆሳህና ከተማ ወስደዉ ለመሸጥ ሲሞክሩ በክትትል ከተዘረፉ የቀንድ ከብቶች ጋር እጅ ከፍንጅ ቸይዞ በተመሰረተበት ክስ ነዉ።

የተሰረቁት የቀንድ ከብቶች ግምታዊ ዋጋ በገንዘብ ሲተመን 288,000/ ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ሺ ብር/ የሚያወጡ መሆኑ የክስ መዝገቡ የሚያስረዳዉ።

የተከሳሹን የክስ መዝገብ የተመለአተዉ የጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተከሳሽ ጥፋተኝነት በማስረጃ በማረጋገጡ ታህሳስ 09 ቀን 2017 ዓ .ም ባስቻለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ በ16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ የጉራጌ ዞን ፖሊስ ያደረሰን መረጃ አመላክቷል።

##ሰላም!!
በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

18 Dec, 15:51


በስልጤ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት ሲያልፍ በውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ

ሆሳዕና ታህሳስ 9 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በስልጤ ዞን ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ቢላሎ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት ሲያልፍ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ የወረዳዉ ፖሊስ ገለፀ።

ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 10:00 ሰአት አከባቢ ላይ በወረዳው ቢላሎ ቀበሌ ልዩ ቦታው ጡቅ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ አሸዋ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ኮድ ET25018 ሲኖ ትራክ መኖርያ ቤት ጥሶ በመግባት በሰውና በእንሰሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማደረሱን የወረዳው ፖሊስ ገልጿል።

በጉዳቱም የተሽከርካሪዉ ረዳት ወዲያው ሲሞት ሹፌሩን ጨምሮ በሁለት ሰዎች ላይ እንዲሁም በቤትንና በእንሰሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

የወረዳው ፖሊስ እንዳስታወቀው በጉዳቱ በ4 ሰዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረሱን እንዲሁም 6 የቤት እንስሳት ላይ ሞት ማስከተሉን ገልጿል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሆሳዕና ከተማ በሚገኘዉ ንግስት እሌኒ ሆስፒታል በህክምና እየተረዱ ይገኛሉ ሲል የገለፀዉ የምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ከወረዳው የመንግሥት የኮሙኒኬሽን የተገኘዉ መረጃ አመላክቷል።

##ሰላም!!

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

17 Dec, 16:23


በከባድ ዉንብድና ወንጀል የተከሰሰዉ የ18 ዓመት ወጣት በ6 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት

ሆሳዕና ታህሳስ 08 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አብሽጌ ወረዳ በከባድ ዉንብድና ወንጀል የተከሰሰዉ የ18 ዓመት ወጣት በ6 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ ከዞኑ ፍትህ መምሪያ የተገኘዉ መረጃ አመላክቷል።

የ18 ዓመቱ ወጣት ተከሳሽ ጌታነህ እሺበል በእስራት ሊቀጣ የቻለዉ በጉራጌ አበሽጌ ወረዳ ዳርጌ ገጠር ቀበሌ ልዩ ስሙ ጎጥ 3 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለጊዜዉ እጁ ካልተያዘዉ ግብራአበሩ ጋር በመሆን ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 2፡30 በሚሆንበት ጊዜ የግል ተበዳይን የግራ ጆሮ በጩቤ በመውጋት እና ያልተያዘው ግብራአበሩ ደግሞ በያዘው ዱላ የኋላ በኩል ማጅራቱን በመምታት መከላከል እንደማይችል ከተረዱ በኋላ በኪሱ ውስጥ የነበረ 5000 (አምስት ሺህ) ጥሬ ብር እና የዋጋ ግምቱ 13000(አስራ ሶስት ሺ) ብር የሚያወጣ ሳምሰንግ የዕጅ ስልክ በመዉሰድ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀመዉ ከባድ የውንብድና ወንጀል በመከሰሱ ነዉ።

ፖሊስ በተከሳሹ ላይ ያጣራዉን የምርመራ መዝገብ ተቀብሎ ዐቃቤ ህግ የመሰረተዉ ክስ የተመለከተዉ የጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ዉሳኔ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ታህሳስ 08 ቀን 2017 ዓ.ም ባስቻለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ጌታነህ እሺበልን በ6 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ ከዞኑ ፍትህ መምሪያ የተገኘዉ መረጃ አመላክቷል።

##ሰላም!!
በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

17 Dec, 11:30


አስገድዶ ለመድፈር ሙከራ ያደረገው ግለሰብ በ8 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት

ሆሳዕና ታህሳስ 8 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ አስገድዶ ለመድፈር ሙከራ ያደረገው ግለሰብ በስምንት አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን የሁልባራግ ወረዳ ፖሊስ ገለፀ።

ተከሳሽ ሸምሱ አልዬ በ8አመት ፅኑ እስራት ሊቀጣ የቻለው ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 5:00 ግድም በሁልባራግ ወረዳ ኬራቴ ከተማ ልዩ ስሙ መንደር ሶስት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የቤቱ አባወራ ድምፅ ሰምቶ ከቤት ወደ ጓሮ በወጣበት አጋጣሚ ወደ ግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ዘው ብሎ በመግባት የቤቱን በር ከዉስጥ ዘግቶ በዕጁ ይዞት በነበረ ስለት አስፈራርቶ ለመድፈር ሙከራ በማድረጉ የግልተበዳይ ባሰማችዉ የይድረሱልኝ ጩኸት ምክኒያት የወንጀል ተግባሩ ከሽፎ በፈፀመዉ የሙከራ ወንጀል በመከሰሱ ነዉ።

ተከሳሹ በያዘው ስለት የግል ተበዳይን ጭንቅላቷ ላይ ጉዳት ሲያደርስባት የመራቢያ አካሏ ላይም በእጁ ጉዳት አድርሶባታሎል።

የግል ተበዳይን ጩኸት ሰምተው የመጡ የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለቤቷ የቤቱን በር ገንጥለው በመግባት ተከሳሽን ዕጅ ከፍንጅ በመያዝ ለወረዳው ፖሊስ አስረክበውታል።

የሁልባራግ ወረዳ ፖሊስ በተከሳሹ ላይ ያጣራዉን የምርመራ መዝገብ ተረክቦ የሁልባራግ ወረዳ ዐቃቤ ህግ ተከሳሹን በአስገድዶ መድፈር ሙከራና በቀላል የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል የመሰረተዉ ክስ የተመለከተዉ የወረዳው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ዉሳኔ ንጥቷል።

የሁልባረግ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ባስቻለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ሸምሱ አልዬን በስምንት አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲል ከሁልባራግ ወረዳ ፖሊስ የተገኘዉ መረጃ አመላክቷል።

ከሴት ተፈጥሮ በሴት ላይ መጨከንና ለጊዜያዊ ስሜት ተብሎ የሚደረግ ማንኛውም አረመናዊ ተግባር የሚያስከትለው ጉዳት የከፋ መሆኑ እየታወቀ ህሊናዊም ሆነ ማህበራዊ ቅቡልነት የሌለውን ተግባር መፈፀም ማለት ለዘመናት የሚቆይን ጠባሳ በሰዎች ላይ ጥሎ እንዲያልፍ ምቹ ሁኔታን እንደ መፍቀድ ነው።

በመሆኑም ውድ የፔጃችን ተከታታዮች ተሰርቶ በፀፀትና በእስር ከሚያስቀጣ የወንጀል ተግባር እራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል እንላለን።

##ሰላም!!በብሩክ አሰፋ(ረ/ኢንስፔክተር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

14 Dec, 15:46


ቤተ እምነት (መስጊድ) በማቃጠል ወንጀል የተከሰሰዉ ግለሰብ በ13 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት

ሆሳዕና ታህሳስ 5 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ሙህር አክሊል ወረዳ ቤተ እምነት (መስጊድ) በማቃጠል እና በሌሎች ሁለት የወንጀል ተግባራት ክስ የተመሰረተበት ግለሰብ በ13 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ ከዞኑ ፍትህ መምሪያ በተገኘዉ መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

አለማየሁ ጥሩኃ የተባለዉ ተከሳሽ በእስራት ሊቀጣ የቻለዉ በጉራጌ ዞን በምሁር አክሊል ወረዳ በመቆርቆር ቀበሌ ልዩ ቦታው ዙር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ግድም ጥንታዊ በሆነዉ የዙር መስጊድ ክብሪት ጭሮ በመለኮስ በመስጊድ ዉስጥ ከነበሩ ንብረቶች ጋር በእሳት እንዲወድም በማድረግ በፈፀመዉ የቃጠሎ ወንጀል በመከሰሱ ነዉ።

ክስ 2 ተከሳሽ በንብረት ላይ ጉዳት/አደጋ ለማድረስ በማሰብ ከላይ በክስ 1ላይ በተጠቀሰዉ ቦታ እና ጊዜ ንብርትነቱ የግል ተበዳይ አብድረዛቅ ኪዳኔ የሆነው ሳር ቤት በጎን በኩል ክብሪት በመለኮስ እንዲወድም/እንዲቃጠል ሲያርግ በሰዎች ርብርብ ቤት የዳነ በመሆኑ ተከሳሽ አስቦ በመፈፀሙ የእሳት ቃጠሎ ማድረስ ሙከራ ወንጀል ተከሷል።

ክስ 3 ተከሳሽ በሰው ንብረት ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ በክስ 1 በተጠቀሰዉ ቦታ እና ጊዜ ንብረትነታቸው የግል ተበዳይ ሠኢድ አህመድ የሆኑ 12‚620(አስራ ሁለት ሺ ስድስት መቶ ሃያ) ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸዉን ንብረቶች እንዳያገለግሉ በማድረጉ ሰው ንብረት ላይ ጉደት ማድረስ ወንጀል ተከሷል።

ፖሊስ በተከሳሹ ላይ ያጣራዉን የምርመራ መዝገብ ተቀብሎ ዐቃቤ ህግ የመሰረተዉ ክስ የተመለከተዉ የሙህር አክሊል ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሹ የተመሰረተበት ሶስቱም ክሶች የወንጀል ተግባሩን እንደፈፀመ ፍርድ ቤቱ በቀረበለት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች በማረጋገጡ ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል።

በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ታህሳስ 04 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ አለማየሁ ጥሩኃን በ13 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ ከጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ የተገኘዉ መረጃ አመላክቷል።

##ሰላም!!
በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

14 Dec, 14:48


የአጎቱን ልጅ የገደለ ተከሳሽ በሃያ አንድ አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት

ሆሳዕና ታህሳስ 5 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በድንበር ይገባኛል መነሻ በተፈጠረ አለመግባባት የገዛ የአጎቱን ልጅ በእንጨት መፍለጫ (ፋስ) ደብድቦ ገድሏል የተባለ ተከሳሽ በ21 (ሀያ አንድ አመት) ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን የቸሀ ወረዳ ፖሊስ ገልጿል።

በዞኑ የቸሀ ወረዳ ዱቢሳና ቀፍ ቀበሌ ልዩ ስሙ ቆቶ ዱቢሳ ተብሎ በሚጠራው መንደር ነዋሪ የሆነው በላቸው ኢደሳ ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ግድም ከሟች ጋር በነበራቸው በድንበር ይገባኛል የተነሳዉ ጭቅጭቅ ወደ ግጭት አምርቶ ተከሳሽ በጊዜዉ በዕጁ ይዞት በነበረ የእንጨት መፍለጫ (ፋስ)ጭንቅላቱንና የቀኝ ዕጁን በመምታት ከባድ ጉዳት አድርሶበታል።

ከደረሰበት ጉዳት መነሻ በስፍራው ላይ እራሱን ስቶ የወደቀውን ተጎጂ ቤተሰቦቹ አንስተው ወደ ወልቂጤ ዩንቨረስቲ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቢወስዱትም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

ተከሳሽን በቁጥጥር ስር ያዋለው የቸሀ ወረዳ ፖሊስም በተከሳሽ ላይ የጀመረውን የምርመራ መዝገብ በሰውና በሰነድ ማስረጃ አደራጅቶ በማጠናቀቅ ለዞኑ ዐቃቤ ህግ መምሪያ ልኳል።
የምርመራ መዝገቡ የደረሰው የዙኑ ዐቃቤ ህግ መምሪያ በተከሳሽ ላይ የሰው መግደል ወንጀል ክስ በመመስረት ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል።

በተከሳሽ ላይ የቀረበውን የክስ መዝገብ ሲከታተል የቆየው የጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ባስቻለው የወንጀል ችሎት ላይ ተከሳሽን በሰው መግደል ወንጀል ጥፋተኛ ነው በማለት በሀያ አንድ አመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲል የቸሀ ወረዳ ፖሊስ ያጋራው መረጃ አመላክቷል።

ዉድ የፔጃችን ተከታታዮች በውይይትና በንግግር ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን በሀይልና በፀብ ለመፍታት የሚደረጉ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች ሁለቱንም ወገን ለከፋ ጉዳት የሚዳርግ መሆኑ የማይካድ ሀቅ ነው።
ዛሬ ላይ ሁለቱ የአጎትማማቾች ልጆች የተጋደሉበትና ደም የተቃቡበትን መሬት ትተው አንዱ ወደ መቃብር ሲወርድ ሌላኛው ደግሞ ወደ ማረሚያ ቤት ወርዷል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ በጊዜያዊ ስሜት በመነዳት አንዱን ለሞት አንዱን ደግሞ ለእስር ከሚዳርጉ የሀይል እርምጃዎች እራሱን ሊጠብቅ ይገባል እንላለን።

##ሰላም!!
በብሩክ አሰፋ (ረ/ኢንስፔክተር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

12 Dec, 18:31


በድንጋይ የገዛ ወንድሙን ጥርስ አዉልቋል የተባለ ተከሳሽ በ4 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት

ሆሳዕና ታህሳስ 3 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ድንጋይ በእጁ ጨብጦ በሰነዘረዉ ቦክስ የወንድሙን ጥርስ ያወለቀው ተከሳሽ በአራት አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ገለፀ።

በዞኑ ዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር አዳሻ ዚኮ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኡመር ኩንቢ ተብሎ በሚጠራው መንደር ነዋሪ የሆነዉ ተከሳሽ ጀማል ሸረፋ በእስራት ሊቀጣ የቻለዉ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 4:00 ሰዓት ግድም ኢብራሂም ሸረፋ ከተባለዉ ወንድሙ ጋር በድንበር ይገባኛል በተነሳ ጭቅጭቅ ነገሩ ወደ ግጭት አምርቶ ተከሳሽ በእጁ ጨብጦ በያዘው ድንጋይ የግል ተበዳይን ደጋግሞ በመምታት አንድ ጥርሱ እንዲወልቅ፣ አንድ ጥርሱ እንዲሸረፍና ሁለት ጥርሶቹ ላይ መጠነኛ ጉዳት አድርሷል በሚል በተመሰረተበት ክስ ነዉ።

የግል ተበዳይ ባቀረበዉ አቤቱታ መነሻ የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ በተከሳሹ ላይ ምርመራ አጣርቶ መዝገቡን ለከተማ አስተዳደሩ ዐቃቤ ህግ ልኳል።
ዐቃቤ ህግም የምርመራ መዝገቡን ተቀብሎ በተከሳሹ ላይ የመሰረተዉ ክስ የተመለከተዉ የዓለም ገበያ ከተማ ፍርድ ቤት ተከሳሹ የወንጀል ተግባሩን እንደፈፀመ በቀረበለት የሰዉና የሰነድ ማስረጃ በማረጋገጡ ተከሳሹን ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል።

የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ባስቻለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ጀማል ሸረፋን በአራት አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲል የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ያደረሰን መረጃ አመላክቷል።

የሰው ልጅ በመሀከሉ ለሚፈጠረው አለመግባባት ፀብንና ሀይልን የመፍትሄ አማራጭ ማድረጉ የቅርቡን የሚያርቅ የለፋበት የሚያባክን ወደ ማረሚያ ቤት አዉርዶ ዕድሜን በከንቱ የሚቀማ ለፀፀትም ይዳርጋልና መታገስና ከወንጀል በብዙ እርምጃ ትርቁ ዘንድ ይድረስ እንላለን።

##ሰላም!!
በብሩክ አሰፋ (ረ/ኢንስፔክተር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

10 Dec, 18:35


በሆሳዕና ከተማ ወንጀልን ለመቀነስ ፖሊስና ህዝብ ባደረገዉ ርብርብ አስተማማኝ የሆነ ሰላም መረጋገጡ ፖሊስ ገለፀ

ሆሳዕና ታህሳስ 1 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) ከከተሞች እድገት ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችልን የወንጀል ተግባር በህዝብ አጋርነት አስቀድሞ ለመከላከል ፖሊስ ያደረገዉ ጥረት ዉጤታማ ሆኖ በሆሳዕና ከተማ አስተማማኝ የሆነ ሰላም ማስፈን ተችሏል ሲል ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ ከከተማዋ እድገት መፋጠን ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችለዉ መልከም እድል የመኖሩን ያህል በዚያዉ ልክ የወንጀል ተግባር እያሻቀበ ሊመጣ እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ በከተማዋ ስድስቱም ቀበሌያት በክፍለ ከተማ እስታንደርድ የፖሊስ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን አዋቅሮ ወደ ተግባር መግባታቸዉ የሆሳዕና ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ጥጋቡ ቀጭኔ ተናግረዋል።

በፖሊስ ማዕከላት በቂ የሰዉ ኃይል በመመደብ ቀልጣፋ የሆነ ፖሊሳዊ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ለዋሪዉ ህዝብ ስጋት የሆኑ የወንጀል ተግባራትንና ወንጀል ተደጋግሞ የሚፈፀምባቸዉ ቦታዎችን በመለየት ወንጀልን ዜሮ ደረጃ የማድረስ አላማና ግብ አንግቦ ሆሳዕና ለነዋሪዎችዋም ሆነ ለእንግዶችዋ ሰላማዊና ምቹ ከተማ ሆና ለማየት ራዕይ አንግቦ በመስራት አበረታች የሆነ ዉጤት ማስመዝገብ ችለናል ሲሉ አዛዡ አክለዉ ገልፀዋል።

በስድስቱም ቀበሌ ማዕከላትየተመደቡ የፖሊስ አመራርና አባላት ህብረተሰቡን በቅድመ ወንጀል መከላከሉ ስራ ላይ ንቁ ተሳታፊ ሆኖ ለአካባቢዉ ሰላም መረጋገጥ ከፖሊስ ጎን ሆኖ እንዲሰራ በመነጋገርና በመወያየት የነዋሪዉ ህዝብ ይሁኝታ በመገኘቱ የፀጥታ እቅድ አዘጋጅተን ወደ ተግባር ተገብቷል ያሉት የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ የወንጀል መከላከል ማስተባበሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ብርሃኑ ሞሎሮ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ጫኝና አዉራጅ ማህበራትን፣በሞተር ብስክሌት እና በባጃጅ ትራንስፖርት ማህበራትን ፣የንግዱ ህብረተሰብን በወንጀል መከላከል የተለያዩ ክበባት በማደራጀት የስጋት ቀጠናዎች እና ተደጋግሞ የሚፈፀሙ የወንጀል አይነቶችን በመለየት ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ያልተቋረጠ የለሊትና የቀን ሮንድ ጥበቃ ስራ መጀመሩ የወንጀል ተግባር ለተጠናወታቸዉ ግለሰቦች ምቾት የነፈገ ሆኖ በሂደት ለዉጥ ማስመዝገብ ችለናል ብለዋል።

የጀሎናረሞ ቀበሌ ቀደም ሲል በሞተር ብስክሌት የተደገፈ ንጥቂያ፣ የቡድን ፀብ፣የግድያና ጨለማን ተገን በማድረግ በሚፈፀሙ ወንጀሎች ምክንያት ለነዋሪዉ ህዝብ ስጋት ለፖሊስ ተቋም እራስምታት ሆኖ እንደነበር የገለፁት አስተባባሪዉ የጀሎ ናረሞ ቀበሌን ሙሉ በሙሉ ከወንጀል ስጋት ነፃ በማዉጣት ዛሬ ላይ በሰላማዊነቱ በሞዴልነት ተጠቃሽ ለመሆን በቅቷል ነዉ ያሉት ምክትል ኮማንደር ብርሃኑ።

የጀሎናረሞ ቀበሌን የወንጀል መከላከል ስልት በተቀሩትም አምስት ቀበሌያት ተግባራዊ ተደርጓል ያሉት አዛዡ ምክትል ኮማንደር ጥጋቡ ቀጭኔ የተፈለገዉ ዉጤት እንዲመዘገብ የሀድያ ዞንና የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ክትትልና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

በሁሉም አካባቢዎች የወንጀል አፈፃፀም ተግባርን በጊዜ ሂደት ማመናመን ተችሏል።አስተማማኝ የሆነ ሰላም ተገንብቷል ያሉት አዛዡ በህዝብ ተሳትፎ ወንጀልን ዜሮ ደረጃ ለማድረስ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ከፖሊስ ጎን ሆነዉ ወንጀልን ለመከላከል የሚያደርጉት እገዛ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ሁለቱም የስራ ኃላፊዎች ለህብረተሰቡ ጥሪ አቅርበዋል።

አንዳንድ ያነጋገርናቸዉ የከተማዋ ነዋሪዎች ቀደም ሲል ወንጀልን በመስጋት በጊዜ ወደየቤታቸዉ ለመግባት ይገደዱ እንደነበር ገልፀዉ አሁን ወንጀልን ለመከላከል ፖሊስና ህብረተሰቡ ተቀናጅቶ በመስራቱ ከወንጀል ስጋት ተላቀን ሰላምን ማጣጣም ችለናል የተገኘዉ ሰላም ዘላቂ እንዲሆን ከፖሊስ ጋር እጅና ጓንት ሆነን መስራቱን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ነግረዉናል።

##ሰላም!!
በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

07 Dec, 13:45


በህገ-ወጥ ንግድ ከተሰማሩ ግለሰቦች የተያዘን የሺሻ ዕቃ በቃጠሎ ማስወገዱን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ገለፀ

ሆሳዕና ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም (ማ.ኢ.ክ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በስልጤ ዞን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ለተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች መንስኤ በመሆን የሚያገለግለውን ህገ-ወጥ የሺሻ ማስጨስ ተግባር ለመቆጣጠር ባደረገው ህጋዊ ፍተሻ የያዛቸውን የሺሻ ዕቃዎች በቃጠሎ ማስወገዱን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ እንደ ገለፀው ከህብረተሰቡ ባገኘው ጥቆማና ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ህገ-ወጥ የሺሻ ማስጨስ ተግባር ላይ ተሰማርተው በሚያስጨሱ ቤቶች ላይ በተለያዩ ቀናት ባደረገው ድንገተኛና ህጋዊ ፍተሻ 65(ስልሳ አምስት) የሺሻ ማጨሻ ዕቃዎችን ይዞ በዛሬው ዕለት ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም የከተማው ህብረተሰብና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቃጠሎ አስወግዷል።

በከተማው ውስጥ የሚካሄዱ ማናቸውንም ህገ-ወጥ ተግባሮች እንደማይታገስ የገለፀው ፖሊስ ይህንኑ ህገ-ወጥ ተግባር ለመከላከል ህብረተሰቡ ጥቆማ በመስጠት ያደረገውን ከፍተኛ ትብብር አመስግኖ ወላጆች የልጆቻቸውን ውሎ በመቆጣጠርና በስነ-ምግባር አንፆ በማሳደጉ ረገድ ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

በተጨማሪም የከተማው ወጣቶች ውድ የወጣትነት ዘመናቸውን አልባሌ ቦታ ከማሳለፍ ይልቅ ለአካባቢው ማህበረሰብና ለራሳቸው በሚጠቅም መልኩ ሊያሳልፉ ይገባል መባሉን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ያደረሰን መረጃ ያስረዳል።
##ሰላም!!
በብሩክ አሰፋ (ረ/ኢንስፔክተር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

06 Dec, 17:54


በስልጤ ዞን በሌለበት በ19 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበት ሲፈለግ የነበረዉ ተከሳሽ በቁጥጥር ስር ዋለ

ሆሳዕና ህዳር 27 ቀን 2016 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ በህገወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀል ተከሶ በሌለበት ፍርድ ቤት በ19 አመት ጸኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበት ሲፈለግ የነበረዉ ተከሳሽ ፖሊስ ከህብረተሰቡጋር በመሆን ባደረገዉ ብርቱ በክትትል ተፈላጊዉን በቁጥጥር ስር አዉሎ የፍርድ ዉሳኔዉን ተፈፃሚ ይሆን ዘንድ ወደ ወራቤ ማረሚያ ተቋም ተልኳል ሲል የስልጤ ዞን ፖሊስ ገልጿል።

በስልጤ ዞን በስልጢ ወረዳ ዳጨ ግስላ ቀበሌ ነዋሪ የሆነውና በሌለበት በእስር እንዲቀጣ ተወስኖበት ታድኖ የተያዘዉ ተከሰሽ ከድር አህመድ በ2013 ዓ.ም ከላይ በተጠቀሰዉ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ አምስት ወጣቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ የናጠጠ ሀብታም ትሆናላችሁ ህይወታችሁም ይለወጣል ሲል በማታለል ሀገር ጥለው ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዲሰደዱ ሲያደርግ ከምስትም ወጣቶች ከያንዳንዳቸዉ 160,000(አንድ መቶ ስልሳ ሺህ ብር በድምሩ 800000 (ስምንት መቶ ሺህ ብር) ተቀብሎ ለግል ጥቅሙ ማዋሉ ተነግሯል።

ተከሳሹ በህገወጥ መንገድ እንዲሰደዱ ገፋፍቶ የሸኛቸዉ ወጣቶች በኬኒያ በኩል መዳረሻቸዉን ደቡብ አፍሪካ አድርገዉ በጉዞ ላይ ሳሉ ታንዛኒያ እንደደረሱ በባዕድ ሀገር ፖሊስ ተይዘዉ መከራና እንግልት ከበዛበት ከ2 አመት ከ6ወር እስር ቆይታ በኋላ ወደ ሀገር ተመልሰዋል ይላል መረጃዉ።

በመሆኑም የግል ተበዳዮች ለፖሊስ በቀረቡት አቤቱታ መነሻ የስልጢ ወረዳ ፖሊስ ተከሳሽ ከድር አህመድን በቁጥጥር ስር አውሎ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ምርመራ በማጣራት መዝገቡን አደራጅቶ ለዞኑ ዐቃቤ ህግ ልኳል።

ከፖሊስ የምርመራ መዝገቡን የተቀበለዉ የስልጤ ዞን ዐቃቤ ህግ በተከሳሹ ላይ የመሰረተዉ ክስ የተመለከተዉ የስልጤ ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ተከሳሽ ከድር አህመድ የቀረበበት ክስ ዉጭ ሆኖ እንዲከታተል የዋስትና መብት ይፈቅድለታል።

በዋስ የተለቀቀዉ ተከሳሽ ፍርድቤቱ በሰጠዉ መብት ተጠቅሞ የክስ ሂደቱን ዉጭ ሆኖ መከታተል ሲገባዉ ከፈፀመዉ የወንጀል ተግባር ለማምለጥ በማሰብ አካባቢዉን ለቆ ይሰወራል።

ፍርድ ቤቱም ተደጋጋሚ በሆነ ቀጠሮ ተከሳሹ እንዲቀርብ ጥሪ ቢያደርግም ሳይቀርብ በመቅረቱ መጋቢት 04 ቀን 2016 ዓ.ም ባስቻለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ከድር አህመድ በሌለበት በ19 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል።

የስልጢ ወረዳ ፖሊስ ተከታትሎ በያዘዉ ፍርደኛ ቀደም ሲል ፍርድ ቤቱ የወሰነዉ የቅጣት ዉሳኔ ተፈፃሚ ይሆን ዘንድ ተከሳሹን ወደ ወራቤ ማረሚያ ተቋም የተላከ መሆኑን ከስልጤ ዞን ፖሊስ ህዝብ ግንኙት ክፍል የደረሰን መረጃ አመላክቷል።

ይህ የወንጀል ዘገባ ወንጀል ፈፅሞ ተሸሽጌ እኖራለሁ ብሎ ማሰብ ዘበት መሆኑ ማሳያ ነዉና ብራቮ የስልጢ ወረዳ ፖሊሶቹ በርቱ ተበራቱ የዝግጅት ክፍላችን መልእክት ነዉ።

##ሰላም!!
በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

02 Dec, 16:02


በጉራጌ ዞን አንድ የሳር ክዳን መኖሪያ ቤት ከ11 የቤት እንሳት ጋር በቃጠሎ እንዲወድም ያደረገ ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ

ሆሳዕና ህዳር 23 በን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ሙህር አክሊል ወረዳ የግል ተበዳይን ሆን ብሎ ለመጉዳት አስቦ አንድ የሳር ክዳን መኖሪያ ቤትና እቤት ዉስጥ የነበሩ 11 የቤት እንሳት ጋር በቃጠሎ ያወደመ ተከሳሽ በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት።

የ28 ዓመቱ ተከሳሽ እዉነቱ ይልማ በእስራት የተቀጣዉ መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም ለሊት የግል ተበዳይ አቶ ይልማ በርታ የሳር ክዳን መኖሪያቤት ላይ በለኮሰዉ እሳት ቤት ዉስጥ የነበሩ ሶስት ላሞች፣ሰባት በጎችና አንድ ፈረስ በደረሰዉ የቃጠሎ አደጋ ሲወድሙ በደረሰዉ ቃጠሎም 1,720.000, (አንድ ሚሊየን ሰባት መቶ ሀያ ሺህ ብር የሚገመት ንብረት በለኮሰዉ እሳት መዉደሙ በማስረጃ ተረጋግጦ በተመሰረተበት ክስ ነዉ።

ተከሳሹ በፈፀመዉ የቃጠሎ ወንጀል በማስረጃ አስደግፎ ምርመራ ያጣራዉ የሙህር አክሊል ወረዳ ፖሊስ ያደራጀዉን የምርመራ መዝገብ ለወረዳዉ ዐቃቤ ህግ ልኳል።

ከፖሊስ የምርመራ መዝገብ የደረሰዉ የወረዳዉ ዐቃቤ ህግ በተከሳሹ የመሰረተዉ ክስ የተመለከተዉ የሙህር አክሊል ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሹን ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል።

ፍርድቤቱ ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ባስቻለዉ የወንጀል ችሎት ።ከሳሽ እዉነቱ ይልማን በሰባት አመት እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ከጉራጌ ዞን ፖሊስ የደረሰን መረጃ አመላክቷል።

##ሰላም!!
በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

29 Nov, 19:43


ከ60 ሚሊዮን ብር በሚልቅ የገንዘብ ወጪ የሚያስገነባዉ ባለአራት ወለል የቢሮ ህንፃ ግንባታዉ መጀመሩ የከምባታ ዞን ፖሊስ ገለፀ

ሆሳዕና ህዳር 20 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን ከ60 ሚሊዮን ብር በሚልቅ የገንዘብ ወጪ የግምባታ ስራዉ የተጀመረዉ ባለአራት ወለል የቢሮ ህንፃ ምንም አይነት የመንግስት ሀብት ሳይታከልበት በህብረተሠቡ ተሳትፎ የሚገነባ መሆኑን ነዉ መየዞኑ ፖሊስ የገለፀዉ።

የከምባታ ዞን ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ታገሰ አርፊጮ እንደገለፁት በዞኑ ከሚገኙ ባለ ሀብቶች እና የገልባጭ ተሽከርካሪ ባለቤቶች ጋር በመተባበር አዲሎ ዙሪያ ወረዳ ከሚገኘው የዲንጋይ ማምረቻ ካባ በአምራቾች ማህበራትና በህብረተሠብ ተሳትፎ ለህንፃ ግንባታዉ ከ320 ሜ/ኪ በላይ ድንጋይ እና አሸዋ መረከብ ጀምረናል ብለዋል።

በህዝብ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማንኛውም የልማት አጀንዳ ማሳካት እንደሚቻል እተማመናለሁ ያሉት ረዳት ኮሚሽነር ታገሠ አርፊጮ ከዞኑ ህዝብ የጋራ ተግባቦት በመፍጠር ዘመኑን የሚመጥን ሁለንተናዊ አገልግሎት መስጠት የሚችል እና ለፖሊሳዊ አገልግሎት ይዉላል የተባለዉ ባለአራት ወለል ህንፃ ተገንብቶ ለአገልግሎት እንዲበቃ ስራዉ መጀመሩና ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል።

በህብረተሠብ ተሳትፎ የሚገነባው የፖሊስ የቢሮ ህንፃ ግንባታ እውን እንዲሆን አሻራቸውን እያኖሩ ያሉትን የህብረተሠብ ክፍሎች ምስጋናቸውን ያቀረቡት ኮሚሽነሩ የተጀመረው ግንባታ እንዲጠናቀቅ የሚደረገዉ ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ ኮሚሽነሩ መተናገራቸዉ የዞኑ ፖሊስ ኢንዶክቲሬሽንና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ያደረሰን መረጃ አመላክቷል።

##ሰላም!
በታጁ ነጋሽ(ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

27 Nov, 17:12


የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በዞንና ልዩ ወረዳ ያለዉን የፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥ የተሻለ ለማድረግ ድጋፍና ክትትል እያደረገ ይገኛል

ሆሳዕና ህዳር 18 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥን የተሻለ ለማድረግ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በዞንና በልዩ ወረዳዎች ለድጋፍና ክትትል የተዋቀረዉ ቡድን በሀድያ ዞን ፖሊስ መምሪያና በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ተገኝቶ ያደረገዉ ምልከታ የሚያስቃኝ ፎተግራፍ።

##ሰላም!!

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

26 Nov, 11:11


ጨለማን ተገን በማድረግ የስርቆት ወንጀል በፈፀሙ 5(አምስት)ተከሳሾች ላይ የእስራት ቅጣት መተላለፉን የላንፉሮ ወረዳ ፖሊስ ገለፀ።

ሆሳዕና ህዳር 17 ቀን 2017(ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በስልጤ ዞን ላንፉሮ ወረዳ ወንቴ ሎላ ቀበሌ ውስጥ በተለያዩ ቀናትና የግል ተበዳዮች ላይ ጨለማን ተገን በማድረግ የስርቆት ወንጀል በፈፀሙ አምስት(5)ተከሳሾች ላይ የዕስራት ቅጣት መተላለፉን የላንፉሮ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ።

1ኛ ተከሳሽ በህረዲን ቦባሳ 2ኛ ተከሳሽ መሀመድ በርገናና 3ኛ ተከሳሽ መሀመድ ገመዳ የተባሉ ተከሳሾች በላንፉሮ ወረዳ ወንቴ ሎላ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኮርጆ ኤዴዳ ተብሎ በሚጠራው መንደር ውስጥ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ዕለተ ዕሁድ በግምት ከምሽቱ 7:30 በሚሆንበት ጊዜ ንብረትነቱ የግል ተበዳይ ወ/ሮ ሸመቴ ሹክሬ በሆነ ማሳ ውስጥ የዋጋ ግምቱ 5500(አምስት ሺህ አምስት መቶ) ብር የሆነ በርበሬ ስርቀው በመውሰድ ሽጠው ተከፋፍለዋል በማለት በግል ተበዳይ አማካኝነት ለወረዳው ፖሊስ አቤቱታው ቀርቧል።

በሌላ መዝገብ 1ኛ.ተከሳሽ ወግበላ ራህመቶና 2ኛ.ተከሳሽ ጨፋ መንጃ የተባሉ ተከሳሾች በላንፉሮ ወረዳ ወንቴ ሎላ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኮርጆ ኤዴዳ ተብሎ በሚጠራው መንደር ውስጥ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ዕለተ አርብ ከንጋቱ 11:30 በሚሆንበት ጊዜ ንብረትነቱ የግል ተበዳይ ነጃ ኤርጊቾ በሆነ ማሳ ውስጥ የዋጋ ግምቱ 14'000(አስራ አራት ሺህ)ብር የሆነ በርበሬ ለቅመው በመውሰድ ሽጠው መከፋፈላቸውንና 1ኛ ተከሳሽ በዚሁ ቀበሌ ውስጥ ልዩ ስሙ ኤዴዳ አንድ ተብሎ በሚጠራው መንደር ውስጥ ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም ዕለተ ዕሮብ ከምሽቱ 7:30 በሚሆንበት ጊዜ ንብረትነቱ የግል ተበዳይ ተቁቴ ሀጂ ለምኑሮ የበርበሬ ማሳ ውስጥ በመግባት የዋጋ ግምቱ 1'750(አንድ ሺህ ሰባት መቶ አምሳ)ብር የሆነ በርበሬ ለቅሞ በመውሰድ ሲንቀሳቀስ በአካባቢው በነበሩ የማህበረሰብ ሮንዶች አማካኝነት ዕጅ ከፍንጅ ተይዞ ከነ ኤግዚቢቱ ለወረዳው ፖሊስ አስረክበውታል።

የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት የወንጀል ምርመራ ክፍል የቀረበለትን የክስ ጥቆማ ለማጣራት እስከ ቦታው ድረስ በመሄድ ተከሳሾች የተጠረጠሩበትን የወንጀል ድርጊት ስለመፈፀማቸው ሊያስረዳ የሚችል በቂ የሰው ማስረጃ አሰባስቦ በማደራጀትና በማጠናቀቅ የምርመራ መዝገቡን ለወረዳው ዐቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ልኳል።

በተከሳሾቹ ላይ የተጣራው የምርመራ መዝገብ የደረሰው የላንፉሮ ወረዳ ዐቃቤ ህግ ፅህፈት ቤትም የምርመራ መዝገብን በአግባቡ ከተመለከተ በኋላ በተከሳሾቹ ላይ የስርቆት ወንጀል ክስ በመመስረት ለወረዳው ፍርድ ቤት አቅርቧል።

በተከሳሾቹ ላይ የቀረበውን የክስ መዝገብ ሲከታተል የቆየው የላንፉሮ ወረዳ ፍርድ ቤት ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም ባስቻለው የወንጀል ችሎት ላይ ተከሳሾችን ያርማል ሌሎችንም ያስጠነቅቃል ብሎ ባመነው መሰረት በ1ኛው መዝገብ ላይ ጉዳያቸው ሲታይ የቆዩት 1ኛ ተከሳሽ በህረዲን ቦባሳ 2ኛ ተከሳሽ መሀመድ በርገናና 3ኛ ተከሳሽ መሀመድ ገመዳን በሶስት አመት ቀላል ዕስራት እንዲቀጡ በማለት ወስኖባቸዋል።

በሁለተኛው መዝገብ ላይ ጉዳያቸውን ሲከታተሉ በቆዩት 1ኛ.ተከሳሽ ወግበላ ራህመቶና 2ኛ.ተከሳሽ ጨፋ መንጃ ላይ 1አመት ከስድስት ወር ሲወሰንባቸው በዚሁ መዝገብ ላይ 1ኛ ተከሳሽ ዕጅ ከፍንጅ በተያዘበት ጉዳይ በድጋሚ አንድ አመት ከስድስት ወር የተወሰነበት በመሆኑ በልዩነት የሶስት አመት ፍርደኛ ሆኖ ሁሉም ተከሳሾች የቅጣት ጊዜያቸውን ሊጨርሱ ወደ ማረሚያ ተቋም ተልከዋል ።

የፖሊስ ተግባር የወንጀል ድርጊት እንዳይፈፀም አስቀድሞ ከመከላከል ባለፈ የወንጀል ድርጊት ተፈፅሞም ሲገኝ በተገቢው መንገድ አጣርቶና ማስረጃ አሰባስቦ አጥፊዎችን ማስቀጣት የሚጨምር በመሆኑ የረዳው ምርመራ ክፍል ያከናወነው የምርመራ ሂደትና ውጤቱ ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ተመልክተንበታል።

በተጨማሪም ወጣቶች አልባሌ ቦታ ከማሳለፍና በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ላይ በመሳተፍ ዉድ የወጣትነት ጊዜያቸውን በማረሚያ ቤት እንዳያሳልፉ የዝግጅት ክፍላችን መልዕክት ነው።
መረጃውን ከላንፉሮ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት አገኘነው።

##ሰላም!!

በብሩክ አሰፋ(ረ/ኢንስፔክተር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

25 Nov, 18:38


በከባድ ስርቆት ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በ4 (በአራት) አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት

ሆሳዕና ህዳር 16 ቀን 2017 (ማ."ኢ.ፖ.ኮ) በጉራጌ ዞን አብሽጌ ወረዳ በከባድ የስርቆት ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በ4 (በአራት) አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ የዞኑ ፍትህ መምሪያ ገልጿል።

ተከሳሽ ብርሀኑ አሽኔ በእስራት ሊቀጣ የቻለዉ መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 11:00 ሰአት በሚሆንበት ጊዜ በአበሽጌ ወረዳ ምችሌና ጠረቆ ቀበሌ ልዩ ቦታው ከሎጀቢ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ንብረትነቱ የግል ተበዳይ የሆነና ጠባቂ የሌለው የበርበሬ ማሳ ውስጥ በመግባት በተለያየ ቀንና ጊዜ የዋጋ ግምቱ 12000 ( አስራ ሁለት ሺህ) ብር የሚያወጣ ቃሪያ ለቅሞ በመዉሰድ በመሸጥ ላይ ሳለ በክትትል እጅ ከፍንጅ ተይዞ በተመሰረተበት ክስ ነዉ።

ፖሊስ ምርመራዉን በማስረጃ አስደግፎ ያጣራዉን የምርመራ መዝገብ ተቀብሎ ዐቃቤ ህግ በግለሰቡ ላይ ክስ መስርቷል።

በተከሳሹ ላይ የተመሰረተዉ ክስ የተመለከተዉ የአበሽጌ ወረዳ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ ባቀረበው የሠውና የሠነድ ማስረጃ ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሙ በማረጋገጡ የጥፋተኝነት ዉሳኔ ሰጥቷል።

የአብሽጌ ወረዳ ፍርድ ቤት ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ብርሀኑ አሽኔን በ4 (አራት) አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ የዞኑ ፍትህ መምሪያ የወረዳዉን ፍርድ ቤት ዋቢ አድርጎ በቴሌግራም ቻናሉ ያሰፈረዉ መረጃ አመላክቷል።

##ሰላም!!
በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

25 Nov, 11:40


ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቂ ውይይት ማድረጉን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ገለፀ።

ሆሳዕና ህዳር 17 ቀን 2017(ማ.ኢ.ፖ.ኮ)
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ስልጤ ዞን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል እና ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረጉን አስታወቀ።

ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ዕለተ ዕሁድ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ከከተማ አስተዳደሩ ፀጥታ ፅህፈት ቤት ጋር በጋራ በመቀናጀት ባዘጋጁት የውይይ መድረክ ላይ የገለልተኛ አማካሪ ምክርቤትና የፖትሮል ቅኝት አባላት ተገኝተው የከተማ አስተዳደሩን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ምን እንደሚመስል ገምግመዋል።

በውይይቱም ወቅት የከተማ አስተዳደሩን ሠላምና ደህንነት ጠብቆ ከማቆየት ባለፈ በአካባቢው ተለይተው የሚታወቁና በስጋት ደረጃ የተቀመጡ የወንጀል ድርጊቶች፣ በትራፊክና በጋውን ተከትሎ የሚከሰቱ የዕሳት አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል ያመች ዘንድ ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር ያለውን ግንኙነት ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በመረጃ ልዉዉጥና በወንጀል መከላከሉ ስራ ላይ በቀጥታ በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ተጠይቋል።

በውይይቱም መጨረሻ ሁሉም ተሰብሳቢዎች የየራሳቸዉን ድርሻ አዉቀዉ ወደተግባር በመግባት ኃላፊነታቸዉን በመወጣት በከተማዋ አስተማማኝ ሠላም እና ደህንነት እንዲረጋገጥ እና የወንጀል ድርጊትም ወደ ዜሮ ደረጃ ላይ ለማድረስ ሁሉም የድርሻዉን ለመወጣት ቃል መግባቱን መረጃዉን ያደረሰን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅህፈት ቤት ነው።

##ሰላም!!

በብሩክ አሰፋ (ረዳት ኢንስፔክተር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

19 Nov, 16:17


በጉራጌ ዞን በከባድ የዉንብድና ወንጀል የተከሰሰዉ ግለሰብ በ16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት

ሆሳዕና ህዳር 10 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በከባድ የዉንብድና ወንጀል የተከሰሰዉ ግለሰብ በ16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ ተገለፀ

ተከሳሽ ጠብቀዉ ይበይን በእስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በጉብሬ ክፍለ ከተማ ዶሮ እርባታ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ግንቦት 01 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡00 ግድም በጥበቃ ስራ የሚተዳደረዉ የግል ተበዳይ ከስራ ቦተዉ ወደ መኖሪያ ቤቱ ለማቅናት በጉዞ ላይ ሳለ ተከሳሽ እጁ ካልተያዘ ሌላ ግብራበሩ ጋር በመሆን መንገድ ዘግተው ያስቆሙታል።

ተከሳሽ ጠብቀዉ ይበይን ይዞት በነበረ ሽጉጥ ንቅንቅ ካልክ እደፋሀለሁ ብሎ በማስፈራራት የግል ተበዳይ በኪሱ ይዞት የነበረ 100/ አንድ መቶ/ ብር ከወሰዱ በኋላ የግል ተበዳይ በእጁ ይዞት የነበረ 1500 ብር ግምታዊ ዋጋ ያለዉን የእጅ ስልክ ሊወስድበት ሲሞክሩ የግል ተበዳይ ስልኩን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ ከዘራፊዎች ጋር ግብ ግብ ዉስጥ ገብቶ ተያይዘው ወድቀዉ ሲነሱ ተከሳሽ የያዘዉ ሽጉጥ ተኩሶ የግል ተበዳይን ግራጉንጩን በአንድ ጥይት ይመታዋል።

በዚህም በተፈጠረዉ ትንቅንቅ መሀከል የግል ተበዳይ ባሰማዉ ጩኸት የአካባቢዉ ነዋሪዎች ወደ ስፍራዉ ሲደርሱ ለጊዜዉ እጁ ያልተያዘዉ የተከሳሹ ግብረአበር ወንጀሉ የተፈፀመበት የጓደኛዉ ሽጉጥና የግል ተበዳይ አልሰጥም ብሎ የተናነቀላት አነስተኛ የእጅ ስልክ ይዞ የተሰወረ ሲሆን አንደኛዉን ተከሳሽ በቁጥጥር ስር አዉለዉ ለፖሊስ በማስረከባቸዉ ተገልጿል።
የዞኑ ዐቃቤ ህግ በተከሳሽ ላይ የመሰረተዉ ክስ የተመለከተዉ የጉራጌ ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት የተከሳሹን ጥፋተኝነት በማስረጃ በማረጋገጡ የጥፋተኝነት ዉሳኔ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ ጠብቀዉ ይበይንን በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እነዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ ከዞኑ ፍትህ መምሪያ የተገኘዉ መረጃ አመላክቷል።

##ሰላም!!

በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

15 Nov, 06:25


በስልጣን ያለአግባብ በመገልገል ወንጀል የተከሰሱ 7 ሰዎች ከ4 እስከ 16 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወሰነባቸዉ

ሆሳዕና ህዳር 6 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ሰንኩራ ወራዳ በአምስት ቀበሌያት ዉስጥ የተደራጁ 15 መሀበራት ስም የተቆጠበ ገንዘብ ወጪ አድርገዉ ለግል ጥቅማቸዉ አዉለዋል የተባሉ 7 ሰዎች በስልጣን አለአግባብ መገልገል ወንጀል ተከሰዉ ከ4 እስከ 16 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጣታቸዉን የስልጤ ዞን ፖሊስ ገልጿል።

የወረዳዉ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ኃላፊን ጨምሮ በመንግስትና በግል ስራ የሚተዳደሩት እነ ኤርሱላ ሱልጣን ሁሴን ሰባት ተከሳሾች በእስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ የተወሰነባቸዉ በሳንኩራ ወረዳ ከሚገኙ አምስት ቀበሌያት በገጠር ስራ እድል ፈጠራ የተደራጁ 15 ማህበራት በኦሞ ማይክሮ ፈይነስ ተቋም በሰንኩራ ቅርንጫፍ የቆጠቡት ብር 615,206 (ስድስት መቶ አስራ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ስድስት ብር) ኃላፊነታቸዉን ተጠቅመዉ አባሪ ተባባሪ በመሆን ከየካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም እሰከ ጥቅምት 01 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በተለያዩ ቀናት ገንዘቡን ውጪ አድርገዉ ለግል ጥቅም አዉለዋል በመባላቸዉ ነዉ።

የ15 መሀበራት ገንዘብ ያለ አግባብ በሰባቱ ግለሰቦች መመዝበሩ መረጃ የደረሰዉ የስልጤ ዞን ፖሊስ የተፈፀመዉ የወንጀል ተግባር አረጋጋጭ የሆኑ ማስረጃዎች አሰባስቦ ያጣራዉን የምርመራ መዝገብ ከፖሊስ የተረከበዉ የዞኑ ዐቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ ክስ መስርቷል።

ዐቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ በስልጣን አላግባብ መገልገል ወንጀል የመሰረተዉ ክስ የተመለከተዉ የስልጤ ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ተከሳሾች የወንጀል ድርጊቱን መፈፀማቸዉ በቀረበለት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች በማረጋገጡ በሰባቱም ተከሳሾች በወንጀሉ ባላቸዉ ተሳትፎ ልክ የጥፋተኝነት ዉሳኔ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ህዳር 02 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ኤርሱላ ሱልጣንን በ12 ዓመት ፅኑ እስራትና 2000 (ሁለት ሺህ ብር) 2ኛ ተከሳሽ ሙበሸር ከድር በ15 ዓመት ፅኑ እስራትና 2000 (ሁለት ሺህ ብር) 3ኛተከሳሽ ቃልኪዳን ኮርማ በ14 ዓመት ፅኑ እስራትና 2000 (ሁለት ሺህ ብር) 4ኛ ተከሳሽ ተውፊቅ አማን በ6 ዓመት ፅኑ እስራትና 2000 (ሁለት ሺህ ብር) 5ኛ ተከሳሽ መሀመድ አብደላ በ5 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራትና በብር 2000 (ሁለት ሺህ ) 6ኛ ተከሳሽ ነጅብ ተማም በ9 ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 10,000 (አስር ሺህ) 7ኛ ተከሰሽ ቃሉ ደምሴ መብራቴ በ4 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራትና በብር 1000 (አንድ ሺህ ) እንድቀጡ የተወሰነባቸዉ መሆኑ ከዞኑ ፖሊስ ያገኘንዉ መረጃ አመላክቷል።

##ሰላም!!
በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

13 Nov, 14:28


በቡድን ተደራጅተዉ ከ10 በላይ መኖሪያ ቤቶችን በለሊት ሰብረዉ ስርቆት ፈፅመዋል የተባሉ አራት ተከሳሾች በእስራት መቀጣታቸዉ ተገለፀ

ሆሳዕና ህዳር 4 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በቡድን ተደራጅተዉ ከ10 በላይ መኖሪያ ቤቶችን በለሊት ሰብረዉ ስርቆት ፈፅመዋል የተባሉ አራት ተከሳሾች ከ3 እስከ 12 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ የተወሰነባቸዉ መሆኑ የጉመር ወረዳ ፖሊስ ገልጿል።

የጉመር ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አብዶ መሀመድ እንደገለፁት ከሆነ ሀሺም መላ ፣ሙላቱ ጀማል ፣አብድልከሪም ከማል እና ቦጋለ ካሳ የተባሉት አራቱ ተከሳሾች በጉመር ወረዳ ቡርደድና ደንበር እንዲሁም አበሱጃ በተሰኙ ሁለት ቀበሌያት ዉስጥ ነዋሪ የሆኑ የ10 ግለሰቦችን መኖሪያ ቤት በለሊት ሰብረዉ በመግባት ከአራት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለቸዉ አልባሳትና ቁሳቁስ ሰርቀዉ በመዉሰዳቸዉ ተናግረዋል።

የግል ተበዳዮች በ2016 ዓ.ም ጀምሮ ለፖሊስ ቀርበዉ ማሳወቃቸዉ የገለፁት ኮማንደር አብዶ ተከሳሾቹን ለመያዝ መጠነ ሰፊ ክትትል ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል።

ፖሊስ በህብረተሰቡ እገዛ ባደረገዉ ክትትል 1ኛ ተከሳሽ ሀሺም መላ ሸገር ሲቲ ዉስጥ ፀበል ማዶ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በቁጥጥር ሲዉል በፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በተደረገ ፍተሻ የሰረቀዉ ንብረት ለማከማቸት ከተከራየዉ መጋዘን ዉስጥ ሶስት መቶ ሺህ ብር የሚገመት ንብረት መያዝ እንደተቻለ አዛዡ ተናግረዋል።

በለሊት ተሰብሮ ስርቆት የተፈፀመባቸዉ 10 ተበዳዮች ለፖሊስ አቤቱታ ቢያቀርቡም ፖሊስ የሶስት የግል ተበዳዮች ንብረት ከተከሳሾች እጅ መያዙን ነዉ አዛዡ የተናገሩት።

ሀሺም መላ የተባለዉ ተከሳሽ ከሸገር ሲቲይ ተይዞ ከመጣ በኋላ ለፖሊስ በሰጠዉ ጥቆማ መነሻ ሶስቱ ተከሳሾች በጉመር ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች በፖሊስ ታድነዉ መያዛቸዉ ተገልጿል።
ፖሊስ በተከሳሾች ላይ ያጣራዉን የምርመራ መዝገብ አደራጅቶ ለወረዳዉ ዐቃቤ ህግ በመላኩ ዐቃቤ ህግም የጥፋተኝነት ዉሳኔ ለማሰጠት ክስ መስርቷል።

በተከሳሾች ላይ የተመሰረተዉ ክስ የተመለከተዉ የጉመር ወረዳ ፍርድ ቤት የተከሳሾችን ጥፋተኝነት ዐቃቤ ህግ ባቀረባቸዉ ማስረጃዎች በማረጋገጡና ተከሳሾችም ክሱን ማስተባበል ባለመቻላቸዉ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ዉሳኔ ሰጥቷል።

የጉመር ወረዳ ፍርድ ቤት ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም ባስቻለዉ የወንጀል ችሎት ሀሺም መላ የተባለዉ ተከሳሽ ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑ በመረጋገጡ በ12 ዓመት ፅኑ እስራት ፣ሙላቱ ጀማልና አብድልከሪምከማል እያንዳንዳቸዉ በ9 አመት እስራት አራተኛዉ ተከሳሽ ቦጋለ ካሳ በ3 ዓመት እስራት እንዲቀጡ የተወሰነባቸዉ መሆኑ ኮማንደር አብዶ መሀመድ መናገራቸዉ ጠቅሶ የጉመር ወረዳ ፖሊስ በደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል።

##ሰላም!
በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

11 Nov, 12:56


በህገወጥ መንገድ ከሀላባ ቁሊቶ በአይሱዚ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ተጭኖ ሲጓዝ የነበረ 36 ኩምታል ቡና መያዙን የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ ገለፀ

ሆሳዕና ህዳር 2 ቀን 2016 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን በህገወጥ መንገድ ከላባ ቁሊቶ በአይሱዚ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ተጭኖ ሲጓዝ የነበረ 36 ኩምታል ቡና መያዙን የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ገልጿል።

የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ሙሰማ ጀማል እንደገለፁት ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 5:00 ሰአት ላይ በከተማዋ የተቀናጀ የፓትሮልና የእግረኛ የሮንድ ጥበቃ ቅኝት በማድረግ ላይ ለነበሩ የፖሊስ አባላት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መነሻ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 -B 6996አ.አ የሆነዉ ተሽከርካሪ ከነጭነቱ በከተማዋ 05 ቀበሌ ሴራሚክ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በቁጥጥር ስር ማዋላቸዉ ገልፀዋል።

የተያዘዉ ቅሽር ቡና በገንዘብ ሲተመን ግምታዊ ዋጋዉ 1,260,000 (አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ስልሳ ሺህ) ሊሆን እንደሚችል የገለፁት አዛዡ የመኪናዉ አሽከርካሪና ረዳት ሾፌር ተሽከርካሪዉን አቁመዉ ለጊዜዉ ቢሰወሩም ፖሊስ ህገወጦችን ከንፁሀን ለይቶ ህግ ፊት ለማቅረብ እንዲችል ተቀዳሚ ተፈላጊ የሆኑት አሽከርካሪና ረዳቱን አድኖ ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ምሽት የተያዘዉ ቡና በቁጥጥር ስር እንዲዉል የከተማ አስተዳደሩ ሰላምና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ጉልህ ድርሻ እንደነበረዉ የገለፁት አዛዡ በከተማዉ ፖሊስ ህገወጥነት ለመከላከል የሚያደርገዉ እንቅስቃሴ በቅርበት ሆኖ በመደገፍ ስራዉ ዉጤታማ እንዲሆን በአካል ጭምር ከፖሊስ ጋር ሆኖ በመስራት ላይ ይገኛል ያሉት ምክትል ኢንስፔክተር ሙሰማ ጀማል ሀገርና ህዝብን ሊጎዳ የሚችል በከተማዋ ዉስጥም ሆነ ከተማዋን አቋርጦ የሚያልፍ ማነኛዉም ህገወጥ የሆነ ተግባር የማይቻልና ቀይመስመር መሆኑ ገልፀዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች በቅድመ ወንጀል መከላከሉ ስራ ከፖሊስ ጎን ሆኖ በመስራታቸዉ ስራችን ዉጤታማ ሆኖ በከተማዋ ወንጀል ስፍራ እንዳይኖረዉ አስችሏልና በከተማ አስተዳደሩ ፖሊስና በራሴ ስም መላዉን የከተማችን ነዋሪዎች ላመሰግን እወዳለሁ ብለዋል።

አዛዡ በመጨረሻም የከተማችን ሰላም ከዚህም በላቀ የህዝባችን የቀደመ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሲሉም ለህብረተሰቡ ጥሪ አስተላልፈዋል።

##ሰላም!!

በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደ)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

08 Nov, 11:08


የላንፉሮ ወረዳ ፖሊስ ከወንጀል ነጻ ለወጡ ቀበሌያት እውቅና መስጠቱ ተገለፀ

ሆሳዕና ታህሳስ 29 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በስልጤ ዞን የላንፉሮ ወረዳ ፖሊስ ከወንጀል ነፃ ለወጡ ስድስት ቀበሌያት ቀበሌያት ዋንጫና ምስክር ወረቀት በማበርከት ላስመዘገቡት መልካም የስራ አፈፃፀም እዉቅና መስጠቱ የወረዳዉ ፖሊስ ገልጿል።

ወንጀልን አስቀድሞ በመከላከል በዞኑ ካሉ ቀበሌዎች አንደኛ በመውጣት የወንጫ ተሸላሚ በሆነው የሉቄ ቁዱሳ ቀበሌ ተገኝተው ዋንጫና ሽልማት ያበረከቱት የላንፉሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ጉንዳ ባሰሙት ንግግር ወንጀልን በመከላከል ግንባር ቀደም የሆኑ ቀበሌያት ተሞክሮ ወደ ሌሎችም ቀበሌዎች እንዲሰፉ በማድረግ የህብረተሰቡ ሰላምና ደህንንነት ሲረጋገጥለት ሙሉ ጊዜውንና አቅሙን ተጠቅሞ በልማት ማዋል እንዲችል ሁሉም አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የላንፉሮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ዋሲል ጀማል በበኩላቸው በወረዳው ካሉት 18 ቀበሌያት መካከል ስድስቱ ቀበሌያት ላይ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ከወንጀል ነጻ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን ገልጸው እነዚህንም በማትጋት ተሞክሯቸውን ወደ ሌሎች ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከወንጀል ነጻ የሆኑት ቀበሌያት አደረጃጀቶች በተገቢው ተግባራቸውን እንዲወጡ ማድረጋቸው ወንጀልን በመከላከሉ ረገድ ውጤታማ እንዳደረጋቸው የገለጹት ኢንስፔክተር ዋሲል ጀማል በዚህም የድርሻቸውን ለተወጡ ቀበሌዎች፣የቀበሌ አመራሮች፣የሚሊሻ አባለት፣የቀጠናና ልማት ቡድን አመራሮች የዋንጫና የምስክር ወረቀት በማበርከት ለላቀ ተግባራቸው የማትጋት ስራ መሠራቱን ገልጸዋል ሲል የወረዳዉ ፖሊስ ያደረሰን መረጃ አመላክቷል።

##ሰላም!!

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

07 Nov, 15:53


የራሱን የሳር ክዳን መኖሪያ ቤት ለማቃጠል ሙከራ አድርጓል በሚል የተከሰሰ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱ ተገለፀ

ሆሳዕና ጥቅምት 28 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ የራሱን ቤት ለማቃጠል ሙከራ አድርጓል በሚል የተከሰሰ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱ ተገለፀ።
በወረዳዉ ጃቱና ራዳሼ ቀበሌ ልዩ ስፍራው አራዳሼ በተባለው አካባቢ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ አድነው ቢረዳ በሰው እና በንብረት ላይ አደጋ ለማድረስ በማሰብ የሳር ክዳን የመኖሪያ ቤቱን በእሳት ለማቃጠል ያደረገዉ ሙከራ በአካባቢው ነዋሪዎች ርብርብ እሳቱን ማጥፋት ቢችልም በንብረት ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል ነዉ የተባለዉ።

ይህን የሰማዉ የቸሀ ወረዳ ፖሊስም ወደ ስፍራዉ ድረስ በመሄድ ምርመራውን በማስረጃ አስደግፎ በማጣራት ለወረዳው ዐቃቤ ህግ የምርመራ መዝገቡን ልኳል።

የወረዳው ዐቃቤ ህግ የቀረበለትን የምርመራ መዝገብ በጥልቀት የመረመረ ሲሆን ተከሳሹ የራሱ የሆነ የሳር ክዳን ቤት ሶስት የተለያየ ቦታ ላይ በለኮሰዉ እሳት ቤቱም ሙሉ በሙሉ ሳይቃጠል የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተረባርበዉ እሳቱን ማጥፋት በመቻላቸዉ 10,000 /አስር ሺህ/ ብር የሚገመት ንብረት ላይ ብቻ ጉዳት መድረሱን ገልፆ በቃጠሎ ማድረስ ወንጀል ሙከራ ክስ መስርቷል።

የተከሳሹ የክስ መዝገብ የተመለከተዉ የቸሀ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር ማቅረብ እንደማይችል ለፍርድ ቤቱ በማሳሰቡ ተከሳሽ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፏል።

የቸሀ ወረዳ ፍርድ ቤት ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ተከሳሽ አድነዉ ቢረዳን እጁ ከተያዘበበት ቀን ጀምሮ በ2 ዓመት ከ4 ወር እስራት እንዲቀጣ ሲል መወሰኑ ከዞኑ ፍትህ መምሪያ ያገኘንዉ መረጃ አመላክቷል።

የራሴ የሆነን ሀብት ባቃጥል ማን ያገባዋል ለምትሉ:-በኢፊድሪ የወንጀል ህግ ዐአንቀፅ 494/1/ ማንም ሰው በሰዎችም ወይም በንብረት ላይ የጅምላ አደጋ ለማድረስ አስቦ የራሱን ወይም የሌላውን ሰው ህንፃ ወይም ማናቸውም ዓይነት ግዙፍ ስራን ሰብሎችን የግብርና ምርቶችን ፣ ደኖችን ፣ ዛፎችን ወይም ማናቸውም ሌሎች ዕቃዎችን በእሳት የለኮሰ እንደሆ ከአስር አመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት እንደሚያስቀጣ መደንገጉ ስንቶቻችን ነን እዉቀቱ ያለን።

##ሰላም!!

በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

03 Nov, 14:36


በስልጤ ዞን የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የፖሊስ ተቋማት ዕውቅና ተሰጠ

የላንፉሮ ወረዳ ፖሊስ በተሻለ የስራ አፈፃፀም ለተከታታይ አምስት አመታት ከዞኑ ቀዳሚ ሆኖ ዘንድሮም ተሸላሚ ሆኗል

ሆሳዕና ጥቅምት 24 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤቶች ላስመዘገቡት ዉጤት እዉቅና የተሰጣቸዉ ሲሆን የምስክር ወረቀትም ተበርክቶላቸዋል።

የዕለቱን መርሃ ግብር በንግግር ያስጀመሩት የስልጤ ዞን የመንግስት ርዕዮታለም ዋና ተጠሪ አቶ ሸረፋ ሌገሶ ሲሆኑ በንግግራቸውም ሠላም ለሠው ልጆች እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ፖሊስ ደግሞ ሠላምን በሁሉም መልኩ ማሰፈንና የዜጎችን ደህንነት አስተማማኝ ማድረግ ዋነኛ ተግባሩ በመሆኑ ግንባር ቀደም ሚና መጫወት አለበት ብለዋል።

በፖሊስ ስራ ላይ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የቀበሌ ማዕከላትን በማስገንባትና ምድብተኛ የፖሊስ አባላትን በተመደቡበት ቀበሌ ተተክለዉ እንዲሰሩ በማድረግ፣የቀንና የሌሊት የሮንድ ጥበቃን አጠናክረዉ በህዝብ ተሳትፎ ሰርቶ በማሰራት፣የወንጀል ተግባርን አስተማማኝ በሆነ መልኩ የመከላከል ተግባር በማከናወናቸዉ በመቻል፣የተለያዩ አጋዥ ኃይሎችን በማደራጀትና ስልጠና ሰጥቶ ወደተግባር በማስገባት ፣ከአጎራባች ክልልናወረዳዎች ጋር የጋራ ኮሚቴዎችን በማደራጀት የክትትልና የግንኙነት እንዲሁም የግምገማና የሪፖርት አቀራረብ ስርዓት በመዘርጋት ችግር እንዳይፈጠር በትኩረት በመስራትና የሚፈጠሩ ችግሮች በቀላሉ በአደረጃጀቱ የፈቱበትና ለቀጣይ ያስቀመጡት የጋራ አቅጣጫ ለሌሎችም መዋቅሮች አርአያ በመሆናቸዉ እዉቅና ተሰጥቷቸዋል።

በሌሎችም ፖሊሳዊ ተግባራት የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ ቀዳሚ በመሆን የላንፉሮ ወረዳ ፖሊስ የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የጦራ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤቶች ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን አግኝተዉ ዋንጫና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

በዘንድሮዉ በጀት ዓመት የምስራቅ ስልጢ ወረዳ ፖሊስ 08 ማዕከላትን በህዝብ አስገንብቶ ለአገልግሎት በማብቃት እንዲሁም የስልጢ ወረዳ ፖሊስ 05 ማዕከላትን አስገንብቶ ለአገልግሎት በማብቃት ዕውቅና የተሰጣቸው ሲሆን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት በቀበሌ ማዕከል የፖሊስ አባላቱ የ24 ሰዓት ፖሊሳዊ አገልግሎት ለህብረተሰቡ በመስጠት እና 04 ቀበሌዎችን ከወንጀል ነፃ በማድረግ በህዝብ ያስመረቀ በመሆኑ ልዩ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በስነስርዓቱ ላይ የዞኑ ፖሊስ ፣ የፀጥታና ሰላም መምሪያ እናሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አካላት፣የወረዳና የከተማ አስተዳደር ሰላምናፀጥታ፣ፖሊስ እና ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ማኔጅመንት አካላትና የዞኑ ሀይማኖት ተቋማት ሀላፊዎች መገኘታቸዉ ተገልጿል።

በመጨረሻም የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት በማድረግ ከስምምነት ላይ ተደርሶ ጉባዔው ተጠናቋል ሲል ከዞኑ ፖሊስ የደረሰን መረጃ አመላክቷል።።

##ሰላም!!

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

30 Oct, 19:49


በጉራጌ ዞን የህበረተሰቡን ሰላምና ደህነት ከምንጊዜዉም በላይ አስተማማኝ ለማድረግ የፀጥታ አካላት ከነዋሪዉ ህዝብ ጋር ተደጋግፈዉ ሊሰሩ ይገባል ተባለ

ሆሳዕና ጥቅምት 20 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ ኮ) በጉራጌ ዞን የህበረተሰቡን ሰላምና ደህነት ከምንጊዜዉም በላይ አስተማማኝ ለማድረግ የፀጥታ አካላት ከመሀበረሰቡ ጋር ተደጋግፎ መስራት እንዳለባቸዉ የተጠቆመዉ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የ2017 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ከፖሊስ አባላትና ከባለድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ በገመገመበት ወቅት መሆነ ተገልጿል።

የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ገና ደገሙ እንዳሉት በዞኑ የሚፈለገዉ ሰላም እንዲመጣ በቅድመ ወንጀል መከላከሉ ስራ ህብረተሰቡን ተሳታፊ በማድረግ ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑ አስረድተዉ
ባለፉት ሶስት ወራት በህብረተሰቡ ተሳትፎ በተሰሩ ስራዎች አበረታች ዉጤት መገኘቱን ገልፀዋል።

በበሽጌ ወረዳ አጋጥሞ የነበረዉ የጸጥታ ችግር በዘለቄታዉ እንዲቀረፍ ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ነዉ ዋና ኢንስፔክተሩ የገለፁት ማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ስራዉ አጠናክሮ በማስቀጠል በዘርፉ የሚፈለገዉን ዉጤት ለማስመዝገብ መትጋት እንደሚገባም አሳስበዋል።

የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ የልማት እቅድና ኢኮኖሚ ዲቪዥን ሀላፊ ኮማንደር ሰለሞን መርሻ ባቀረቡት የአፈፃፀም ሪፖርት እንዳሉት የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ትምህርት ሽፋን ለማሳደግ በተሰራዉ ስራ ለ183 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ መፍጠር እንደታቸለም ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ በማደራጀት በቅድመ ወንጀል መከላከሉ ስራ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን መደረጉ ወንጀልን በመከላከል ረገድ ዉጤታማ ስራዎች እየሰሩ እንደሆነም አብራርተዋል።
በተለያዩ የዞኑ አካባቢዎች በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለ ሲሆን በድርጊቱ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ምርመራ ርጥረዉ እየተጣራ መሆኑም አስታዉሰዋል።

በአፈጻጸም መድረኩ የተገኙ አስተያየት ሰጪዎች እንዳሉት በሩብ አመቱ የተሰሩ ስራዎች የሚበረታታና የሮንድ ጥበቃ ጋር በአንዳንድ አካባቢዎች ክፍተት መኖሩም አንስተዉ ለዚህም ትኩረት ቢሰጠዉና ችግሮች እንዳይፈጠሩ በቅንጅት መሰራት እንዳለበትም አመላክተዋል።

የጸጥታ ሀይሉ ከማህበሰቡ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የዞኑን ሰላም በዘላቂነት ማረጋገጥ እንደሚገባም አብራርተዉ በየአካባቢዉ የሚሰሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች በወንጀል እንዳይደናቀፉ ፖሊስ የተጣለበት ኃላፊነት በብቃት ሊወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በአበሽጌ ወረዳና በወልቂጤ ከተማ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝዉዉርን ለመከላከል የቁጥጥርና የክትትል ስራዉን የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል መባሉ የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

##ሰላም!!

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

27 Oct, 11:35


የማርቆ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ከልዩ ወረዳዉ መንግስት ጋር በመቀናጀት ከዳዕዋ ተመላሽ እንግዶችን በቆሼ ከተማ ተቀብሎ አሸኛኘት እያደረገ መሆኑ ተገለፀ።

ሆሳዕና ጥቅምት 17 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማርቆ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ከልዩ ወረዳዉ መንግስት ጋር በመቀናጀት በቡታጅራ ከተማ ለሶስት ቀናት በተደረገዉ የዳዕዋ መርሃግብር ተሳትፈዉ ወደየመጡበት ተመላሽ ለሆኑ የዉጭና የሀገር ዉስጥ እንግዶች ቆሼ ከተማ ሲደርሱ ተቀብሎ አሸኛኘት እያደረገ መሆኑ የልዩ ወረዳዉ ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ ከልዩ ወረዳዉ የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉን የታሸገ ዉሃ ለተመላሽ እግዶች በማደል ያለዉን አክብሮትና ፍቅር እየገለፀ መሆኑን ነዉ ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ እንዳስረዳዉ ከሆነ ።

ሰላምና የፖሊስ ተቋም በመላዉ አለም ቁርኝታቸዉ የጠበቀ በመሆኑ እንዲህ አይነቱ መልካም ተግባር ህብረተሰቡ የፖሊስን በየኔነት ስሜት ሊመለከተዉ ለተቋሙም የተለየ አክብሮትን የሚያሰጥ በወንጀል መከላከሉ ስራ ላይ ህዝቡ ተሳታፊ እንዲሆን ዋጋ አለዉና የማረቆ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ያከናወነዉ ተግባር በአረአያነት የሚጠቀስ በመሆኑ በርቱ ተበራቱ ብራቮ ብለናል።

##ሰላም!!
በታጁ ነጋሽ(ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

27 Oct, 11:32


አለም አቀፉ የዳዕዋ መርሃግብር በሰላም ተጠናቋል ሲል የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ገለፀ

ሆሳዕና ጥቅምት 17 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ከጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተካሄደዉ አለምአቀፍ የዳዕዋ መርሀግብር በሰላም መጠናቀቁ ፖሊስ ገለፀ።

ከአንድ ሚልዮን የሚልቁ እንግዶችን ተቀብለን ከሶስት ቀናት መስተንግዶና ሰላማዊ ቆይታ በኋላ ወደየመጡበት በሰላም ተሸኝተዋል።

የመስቃንና የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ፣ የሚሊሺያና የህዝባዊ ሰራዊት አባላት ከነዋሪዉ ህዝብ ጋር ተቀናጅቶ በመሰራቱ አንድም የወንጀልም ሆነ የትራፊክ አደጋ ሳይመዘገብ የዳዕዋ መርሃግብሩ በሰላም ማጠናቀቁን የገለፁት የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ሙሰማ ጀማል ለሀገራችን ኢትዮጵያ የተለየ ትርጉም የሚያሰጥ መልካም ተግባር ማከናወን መቻሉ ነዉ የተናገሩት።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰራ አስፈፃሚዎችና የአለም አቀፉ የኡለሞችና የዳዕዋ ዓሚር ሴክሬታሪ ጀነራል የተገኙበት መድረክ እንደነበር ነዉ የተገለፀዉ።

ከአሜሪካ፣ ህንድና ምዕራባዊያን ሀገራትን ጨምሮ ከ110 የአለም ሀገራት የተወጣጡ 720,000 ( ሰባት መቶ ሀያ ሺህ) የዉጭ ሀገራት ዜጎችና ከሀገራችን አራቱም ማዕዘናት የመጡ 600,000 (ስድስት መቶ ሺህ) በአጠቃላይ ከ1ሚሊየን 3መቶ ሺህ በላይ እንግዶች የተገኙባት ቡታጅራ ካለምንም ሳንካ እንግዶችዋን በሰላም አስተናግዳ ሸኝታለች በማለት አዛዡ ተናግረዋል።

የቡታጅራ ከተማ ነዋሪዎች ሙስሊም ክርስቲያኑ የእምነት ልዩነት ሳይገድባቸዉ ወደ ከተማዋ ለመጡት እንግዶች የመኖሪያ ቤታቸዉን በር ክፍት አድርገዉና አንጥፈዉ በመቀበል ደህንነታቸዉን በመጠበቅ ያደረጉት መስተንግዶ አስደሳች ነዉ ያሉት ምክትል ኢንስፔክተር ሙሰማ የከተማዋ ነዋሪዎች ሰላምን ለማረጋገጥና የሀገርን ገፅታ በሚገነባ ሰዉ አክባሪነት ያከናወኑት መልካም ተግባር ሀገራችን ኢትዮጵያ እንግዳ ተቀባይና የመልካም ስነምግባር ባለቤት የሆኑ ህዝቦች መኖሪያ መሆኗ አስመስክረዋል።

ኢትዮጵያ ሰላማዊ ሀገር መሆኗን በተግባር ማሳየት ያስቻለ ገፅታ መግንባት የሚያስችል ተግባር ማከናዉናቸዉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ምክትል ኢንስፔክተር ሙሰማ ጀማል ለዚህ ስራ ዉጤታማ መሆን የከተማ አስተዳደሩ ስራ አስፈፃሚዎች፣ የከተማቸን ነዋሪዎች ፣ የከተማ አስተዳደሩ ህዝባዊ ሰራዊትና የሚሊሺያ አባላት የመስቃን ወረዳ ፖሊስና የሚሊሺያ አባላት እንዲሁም የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ከነዋሪዉ ህዝብ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የላቀ አስታዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ሁሉ በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፖሊስና በራሴ ስም እጅግ ከፍ ያለ ምስጋና እያቀረብኩኝ ለመላዉ የቡታጅራ ከተማ ነዋሪዎች ያለንን ታላቅ አክብሮት ለመግለፅ እወዳለሁ ብለዋል።

##ሰላም!!
በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

19 Oct, 16:07


በላንፉሮ ወረዳ ህብረተሰቡ የፖሊስ አጋር መሆኑ ያስመሰከረበት የለሊት ሮንድ ጥበቃ ስራ ላይ እያደረገ ያለዉ ተሳትፎ መሀበረሰቡን ከወንጀል ስጋት ነፃ ማድረጉ ተጠቆመ

ሆሳዕና ጥቅምት 9 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ላንፉሮ ወረዳ ጨለማን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ለመከላከል ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጎን በመሆን በለሊት የሮንድ ጥበቃ ስራ በመሰራቱ ህብረተሰቡ ከወንጀል ስጋት ነፃ ማድረግ ተችሏል ሲል የወረዳዉ ፖሊስ ገልጿል።
በወረዳው ባሉ ሁሉም ቀበሌያት ህብረተሰቡ የማታ ሮንድ ጥበቃን አጠናክሮ በትኩረት እየሰራ በመሆኑ የወንጀል መከላከሉ ስራ የተሻለ ዉጤት ተመዝግቧል ያሉት የላንፉሮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ዋሲል ጀማል ይህ ቅንጅታዊ አሰራር ቀጣይነቱ አያጠራጥርም በማለት ነዋሪዉን ህዝብና መላዉን የፖሊስ አባላት አመስግነዋል ሲል ከወረዳዉ ፖሊስ በደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል።

##ሰላም!!
በታጁ ነጋሽ (ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

19 Oct, 13:33


ከፖሊስ ጋር ተታኩስ ተለዋዉጠዉ ለማምለጥ ከሞከሩ ዘራፊዎች አንድ ተጠርጣሪን ከነ ጦር መሳሪያዉ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሀላባ ዞን ፖሊስ ገለፀ

ሆሳዕና ጥቅምት 9 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ቁሊቶ ከተማ መተር ብስክሌት ሰርቀዉ ለማምለጥ በጉዞ ላይ የነበሩ ሶስት ተጠርጣሪዎች ከፖሊስ ጋር የተኩስ ልዉዉጥ አድርገዉ ለማምለጥ ሙከራም ያደርጋሉ።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች ከሰረቁት ንብረት ጋር ለማምለጥ ቢሞክሩም ፖሊስ በተተኮሰበት ጥይት ሳይሸበር በተኩስ ምላሽ እየሰጠ በፓትሮል ተከታትሎ አንድ ተጠርጣሪን ከአንድ አዉቶማቲክ ሽጉጥና ስለታም ሳንጃ ጋር እንዲሁም የተሰረቁ ሁለት ፐልሰር ሞተር ብስክሌት ጋር በቁጥጥር ሲያዉል ያሰቡትን እኩይ የወንጀል ተግባር የከሸፈባቸዉና ለጊዜዉ እግሬ አዉጪኝ ብለዉ ያመለጡትን ሁለት ተጠርጣሪዎች አድኖ ለመያዝ የተጠናከረ ክትትል እያደረገ መሆኑ የሀላባ ዞን ፖሊስ ገልጿል።

ሙሉቀን ተደሳ የተባላው ተጠርጣሪ አሁን ለጊዜዉ እጃቸዉ ከልተያዙት ሁለት ግብራበሮቹ ጋር በመሆን ጥቅምት 07 ቀን 2017 ዓ ም ከሌሊቱ 10:00 ግድም በቁሊቶ ከተማ በተለምዶ አዲሱ ማዘጋጃ ፊትለፊት ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ የአንድ ግለሰብ ቤት መኖሪያ ጊቢ ሰብረዉ በመግባት ሁለት ሞተር ብስክሌቶችን ከግቢ ይዘው ይወጣሉ።

ምን-አልባትም በር ሰብረዉ ወደ ዘለቁበት ጊቢ ከዉስጥ ድምፅ ሰምቶ ማነህ የሚላቸዉ ሰዉ ቢኖር ከተቻላቸዉ ድምፅ አልባ በሆነዉ ስለት ነገሩ ከበድ ቢል በጥይት ተኩሰዉ ሊገላግሉት በቂ ዝግጅት ያላቸዉ ቢሆንም አልሰመረም እንጂ በደቂቃ ለሚለካ ጊዜ የወንጀል ድርጊቱ መፈፀም ማንም ሳይሰማ ማሳካት ችለዉ ነበር።

የሀላባ ዞን ፖሊስ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ነዋሪዎችን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ ከተማዋ ለእንግዶችዋም ሆነ ለነዋሪዋችዋ የተመቸች ከወንጀል የፀዳችና ፍፁም ሰላማዊ ከተማ ትሆን ዘንድ በፓትሮል ተሽከርካሪ የተደገፈ የሮንድ ጥበቃ ማድረጉ የፖሊስ የእለት ተእለት ተግባር ሲሆን በዚህ ረገድ በቅድመ ወንጀል መከላከሉ ስራ ላይ ህብረተሰቡ በንቃትም የሚሳተፍበት መሆኑን ነዉ የተገለፀዉ።

በመሆኑም ሶስቱ ተጠርጣሪዎች በሁለት ሞተር ብስክሌት እየጋለቡ ከከተማዋ ለመዉጣት የነበረዉ እሳቤ የሚገታ ድንገተኛ የፖሊስ ፓትሮል መተረኞች ይቆሙ ዘንድ የተጠየቁት በከተማዋ ሮጲ አካባቢ ነበር።

እነሱ የፖሊስን ትዕዛዝ አክብረዉ ለመቆም አልፈቀዱም ጥሰዉ መፈርጠጣቸዉን ቀጠሉ።የፖሊስ ፓትሮል አሽከርካሪዉ መኪናዉን አስነስቶ ተስፈነጠረ።
በነገሩ የተደናገጡት ሶስቱ ሞተረኞች በመጋለብ ላይ እያሉም የተፈናጠጠዉ ዘራፊ ወደ ፖሊሶች ጥይት መተኮሱ ተነግሯል።

በፓትሮል ላይ የነበሩት የፖሊስ አባላት የተኩስ ሽፋን እየሰጡ ሞተረኞችን ተፈትልኮ በመቅደም በተሽከርካሪ መንገድ ዘግተዉ ከተሽከርካሪዉ ወደ መሬት ዱብ ዱብ ሲሉ ሶስቱም ተጠርጣሪዎች ሞተሩን ጥለዉ መፈርጠጥን መረጡ።

ቢሆኑም ትጥቅ ይዞ ለመከላከል የሞከረዉን ተጠርጣሪ ከበዉ በመያዝ ከእጁ ሽጉጥ ከጎኑ የሻጠዉ ስለታም ሳንጃ ተረክበዉ አንዳንድ ጥያቄዎችን ሲጠይቁት ከአርባምንጭ ነዉ የመጣንዉ ሲል የጓደኞቹን ስምና አድራሻቸዉ መግለፁን ነዉ የተነገረዉ።

ለመሆኑ ለዚህ የወንጀል ተግባር ከአጎራባች ዞኖች ወይስ ተጠርጣሪዉ እንዳለዉ እዉነትም ከአርባምንጭ ይሆን የመጡት?ሁሉንም እዉነታ በፖሊስ በሚያደርገዉ ማጣራት የሚያረጋግጠዉ ይሆናል።ብራቮ የሀላባ ፖሊሶች!!ለመረጃዉ የሀላባ ዞን ፖሊስ ህዝብግንኙነት ባልደረባ የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር አብዱሰላምን አመሰግናለሁ

##ሰላም!!

በታጁ ነጋሽ(ምክትል ኮማንደር)

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

18 Oct, 07:55


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የዉይይት መድረክ በዛሬዉ እለት በሆሳዕና ከተማ ተጀምሯል

ሆሳዕና ጥቅምት 8 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ልዩ ልዩ ክፍሎች የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎች ፣ የ7 ዞንና የ3 ልዩ ወረዳ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት መድረክ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ ስራ አፈፃፀም የግምገማ ና የዉይይት መድረክ በዛሬዉ እለት በሆሳዕና ከተማ ተጀምሯል።

በዉይይት መድረኩ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሺመልስ ካሳ ባሰሙት ንግግር ኮሚሽኑ በበጀት አመቱ መጀመሪያ ከዞንና ልዩ ወረዳ የፖሊስ የስራ ኃላፊዎች ጋር በአመታዊ የስራ ዕቅድ ለይ ለተፈፃሚነቱ መፈራረማቸዉን አዉስተዋል።

በመሆኑም ፖሊስ ባከናወናቸዉ ተግባራት ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫን ለማስቀመጥ የግምገማ መድረኩ አስፈላጊ መሆኑነዉ ኮሚሽነሩ የተናገሩት።
የክልሉ ፖሊስ 2017 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለተሰብሳቢዎች በንባብ ቀርቦ ዉይይት እየተደረገበት ነዉ።

##ሰላም!!

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

17 Oct, 17:22


የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ አጋዥ የፀጥታ ኃይል ሆነዉ የሚሰሩ የህዝባዊ ሰራዊት አባላትን አሰልጥኖ አስመረቀ

ሆሳዕና ጥቅምት 7 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) ቡታጅራ ለነዋሪዎችዋም ሆነ ለእንግዶችዋ ሰላማዊና ምቹ ከተማ ትሆን ዘንድ አጋዥ የፀጥታ ኃይል ሆነዉ የሚሰሩ የህዝባዊ ሰራዊት አባላትን አሰልጥኖ ወደ ስራ ማስገባቱን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ገለፀ።

በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን ከጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በቡታጅራ ከተማ ለሚካሔደዉ ሀይማኖታዊ የዳዕዋ ኮንፍረስ ከመላዉ አለም የተወጣጡ የእስልምና እምነት ተከታዮች ወደ ከተማዋ ይገባሉ።

በመሆኑም በከተማዋ የሚደረገዉ የዳዕዋ ፕሮግራም ያለ አንዳች ሳንካ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የከተማው ፖሊስ ሰላምና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር የፖሊስ አጋዥ ሆነዉ የሚሰሩ ከህብረተሰቡ መሀል የተመለመሉ 550 የሚሆኑ የህዝባዊ ሰራዊት አባላትን አሰልጥኖ ወደ ስራ ማስገባቱን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ሙሰማ ጀማል ተናግረዋል።

ፖሊስ ስነ-ስርዓቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ በሚያከናወነው ስራ ባለድርሻ አካላት እና ሌሎችም መንግስታዊና ህዝባዊ መዋቅሮች አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ አዛዡ ጥሪ አቅርበዋል።

350 ከማህበረሰቡ የተውጣጡ ህዝባዊ ሰራዊት እና 200 የመንግስት እና የግል የጥበቃ ሰራተኞች ናቸዉ።

ለሰልጣኞች የመስክ፣የአመለካከት፣ የአካል ብቃት፣የተኩስና ከጥበቃ ጋር የተያያዘ ስልጠና መሰጠቱን ዋና አዛዡ አስታውቀዋል።

ከፖሊስ ጎን በመሆን እንግዳ ለመቀበል ሰላምን በማስጠበቅ ወንጀልን ለመከላከል እንዲሁም በእንግዶች ማረፊያ አካባቢ የጥበቃ ስራ ይሰራሉ ነዉ የተባለዉ።

መላው የቡታጅራ ከተማ ነዋሪ ከባለፈው ተመሳሳይ መርሃ ግብር ተሞክሮ በመውሰድ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ እንግዶችን በመቀበል አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ም/ል/ኢ ሙሰማ ጀማል ጥሪ አቅርበዋል።

በከተማዋ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች በተለይ ስርቆትና መሰል ወንጀሎችን በከፍተኛ መጠን መቀነስና ማስቀረት እንደተቻለ የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ቃሲም ግርማ መናገራቸዉ የከተማዉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።

ወንጀልን በጋራ እንከላከል!!

Central Ethiopia police commission/ማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን/ http://www.central Ethiopia region police commission

10 Oct, 18:03


በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋዋር የተገኘ መድሐኒትና የአፈር ማዳበሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ

ሆሳዕና መስከረም 30 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ኳርተም የተሰኘዉ የወባ በሽታ መድሐኒትና የአፈር ማዳበሪያ እንዲሁም በዝዉዉሩ የተጠረጠሩ ሶስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ገለፀ።

መነሻቸውን ወልቂጤ መድረሻዉ ቡታጅራ ከተማ አድርጎ በአይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ተጭኖ በመጓዝ ላይ የነበረ 46 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ከሶስት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋላቸዉ የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ሙሰማ ጀማል ተናግረዋል።

ንብረትነቱ የመንግስት አንቡላንስ በሆነ ተሽከርካሪ ከወላይታ ሶዶ ከተማ በህገዘጥ መንገድ ተጭኖ ወደ አዲስ አበባ ሊወሰድ የነበረ 863 ዶዝ ኳርተም የወባ መድሐኒት ሲያዝ በድርጊቱ የተጠረጠረዉ አሽከርካሪ በሽተኛ በመጫኑ በፖሊስ ዋስ ጠርቶ እንዲለቀቅ መደረጉ አዛዡ አክለዉ ገልፀዋል።

በህገ-ወጥ መንገድ የአፈር ማዳበሪያ ሲያዘዋውሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሶስት ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸዉ ፖሊስ ምርመራ በማጣራት ላይ ይገኛል።

በከተማዋ ህገ-ወጥ ድርጊት መፈፀምና ማዘዋወር "ቀይ መስመር" በሚል መሪ ሀሳብ ከሰላምና ፀጥታ በመተባበር በልዩ ኦፕሬሽን እየተሰራ እንደሆነና ለዚህም የከተማዋ ህዝብ ድጋፉ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ይኸዉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሲሉ በማሳሰብ ለከተማ ነዋሪዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

##ሰላም!!