Ethiopian Embassy in Rome @ethiopiainitaly Channel on Telegram

Ethiopian Embassy in Rome

@ethiopiainitaly


Official channel for the Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, Rome, Italy.
Website: https://rome.mfa.gov.et

Ethiopian Embassy in Rome (English)

Are you interested in staying updated on the latest news and events related to the Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in Rome, Italy? Look no further than the official Telegram channel, @ethiopiainitaly! This channel serves as the primary hub for all information regarding the embassy's activities, announcements, and initiatives.

The Ethiopian Embassy in Rome plays a crucial role in fostering diplomatic relations between Ethiopia and Italy. It serves as a key link between the two countries, facilitating communication and collaboration on various political, economic, and cultural matters. As such, staying informed about the embassy's work is essential for anyone interested in Ethiopian-Italian relations.

By following @ethiopiainitaly on Telegram, you'll gain access to a wealth of valuable content, including updates on official visits, cultural events, and important announcements from the embassy. Whether you're a member of the Ethiopian diaspora living in Italy, a business professional looking to explore opportunities in Ethiopia, or simply someone with a keen interest in international relations, this channel is a must-follow.

Additionally, the Ethiopian Embassy in Rome's website (https://rome.mfa.gov.et) provides further resources and information for those looking to deepen their understanding of the embassy's work and its role in Ethiopia-Italy relations. From visa services to cultural exchanges, the website offers a comprehensive overview of the embassy's functions and services.

Don't miss out on the chance to stay informed and engaged with the Ethiopian Embassy in Rome. Follow @ethiopiainitaly on Telegram today and join a community of individuals who share a common interest in promoting strong ties between Ethiopia and Italy. Whether you're looking to attend embassy events, learn about Ethiopian culture, or simply stay updated on diplomatic developments, this channel has something for everyone. Join us now and be a part of the conversation!

Ethiopian Embassy in Rome

23 Nov, 12:50


በአሜሪካ እና አውሮፓ ወረዳ፣ የአውሮፓ የብልጽግና ፓርቲ መሠረታዊ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በድምቀት ተከበረ።
==========

(ህዳር 14 ቀን 2017) ዓ.ም) በአሜሪካ እና አውሮፓ ወረዳ፣ የአውሮፓ የብልጽግና ፓርቲ መሠረታዊ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች የብልግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን በድምቀት በበይነመረብ አክብረዋል።

በወቅቱም የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል "የኃሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ኃሳብ የመወያያ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

በጣሊያን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር እና የአሜሪካ እና አውሮፓ የብልጽግና ወረዳ ሰብሳቢ ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር
ብልጽግና ፓርቲ በርካታ ተግዳሮቶችን በጽናት በማለፍ ተምሳሌታዊ የሆኑ ስኬቶችን መቀዳጀቱን በንግግራቸው አቅርበዋል። አክለውም የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ባለፉት አምስት ዓመታት በተለይም በዲፕሎማሲያዊ ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ በማበርከት ፓርቲው ለተቀዳጃቸው ድሎች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።

በአውሮፓ የሚሲዮኖች አባላት እና ደጋፊዎች በቀረበው ሰነድ ላይ በሰጡት አስተያየት ፓርቲው እስካሁን ያረጋገጣቸው ስኬቶች በቀጣይ የያዘውን ራዕይ በማሳካት ብልጽግናን እውን ማድረግ የሚቻል ስለመሆኑ አመላካች መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል።
በቀጣይም ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እና የተረጋገጡ ድሎችን የበለጠ ለማስፋት በሚደረጉ ጥረቶች በከፍተኛ በትጋት በመንቀሳቀስ አስተዋጽኦቸው አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።

በዓሉ በየኤምባሲው የሚገኙ አባላት እና ደጋፊዎች በዓሉን አስመልክቶ የተዘጋጀውን ኬክ በመቁስና ሌሎች ዝግጅቶችን በድምቀት ተከብሯል።

Ethiopian Embassy in Rome

21 Nov, 17:50


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የጣሊያኑ አጀንዚያ ኖቫ የዜና ወኪል መካከል የትብብር ስምምነት ተፈፀመ፣
==================
(ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም.): የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የጣሊያኑ አጀንዚያ ኖቫ የመረጃ ወኪል መካካል ትብብር ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በበይነመረብ ተፈራርመዋል።

ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ባደረጉት ንግግር ስምምነቱ ሁለቱ አንጋፋ ሚዲያ ተቋማት ያላቸውን ልምድ በመለዋወጥ በጋራ በመስራት የሁለቱን አገሮች ግንኙነት የበለጠ ከማጠናከር አኳያ የላቀ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አሰፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ፣ የጣሊያኑ አጀንዚያ ኖቫ መረጃ ወኪል ዋና ስራ አስፈጻሚ Mr. Fabio Squillante በሁለቱ የሚዲያ ተቋማት መካከል በአቅም ግንባታ፣ የመረጃ ልውውጥ እና በጋራ የፕሮዳክሽን ስራዎችን በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ በኢትዮጵያ የጣሊያን ኤምባሲ አምባሳደር H.E Amb. Agostino Palese እንዲሁም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዳ/ጄ ክቡር አምባሳደር ሽብሩ ማሞ በመገኘት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Ethiopian Embassy in Rome

18 Nov, 16:44


2ኛው የ2024 በጀት አመት የአለም የምግብ ፕሮግራም የኤግዝኩቲቭ ቦርድ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ፤
=========================================
(ህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም):  2ኛው የ2024 በጀት አመት የአለም የምግብ ፕሮግራም የኤግዝኩዩቲቭ ቦርድ በወቅታዊ እና ቀጣይ አስቻይ እንዲሁም ፈታኝ ሁኔታዎች ላይ የሚመክረው ስብስባ ሮም በሚገኘው የWFP ዋና መስሪያ ቤት በኖቬምበር 18 ቀን 2024 ዓ.ም. መካሄድ ጀምሯል።

በስብስባው ላይ በሮም መቀመጫቸውን ያደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያ ምክትል ቋሚ ተጠሪ የሆኑት ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ  በስብሰባው ላይ ንግግር ያደርጉት ሲሆን  የአለም የምግብ ፕሮግራም  በኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ስራ የኢትዮጵያ መንግስት እውቅና እንደሚሰጥ ገልጸው፣ ድርጅቱ ይህንኑ ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ በኩልም ከድርጅቱ ጋር በቀጣይ አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

Ethiopian Embassy in Rome

18 Nov, 16:43


ክቡር ዶ/ር ደረጀ ድጉማ ከጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
=================

(ህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም): የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ደረጀ ድጉማ ከጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር H.E Mr. Edmondo Cirielli ጋር በሮም ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ክቡር ዶ/ር ደረጀ ኢትዮጵያ ከጣሊያን ያላትን ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ እና ስትራቴጂካዊ ግንኙነት አውስተዋል። አክለውም የጣሊያን መንግስት በጣሊያን የልማት ትብብር አማካይነት ከሀገሪቱ ትኩረቶች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ በጤናው ዘርፍ ለሚሰጠው ያልተቋረጠ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

H.E Mr. Edmondo Cirielli በበኩላቸው ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ጠንካራ ግንኙነት አንስተው, በሀገራቸው በኩል ትብብሩን የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

Ethiopian Embassy in Rome

15 Nov, 13:55


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከሰሜን ሜቅዶንያ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ጋር ተወያዩ።
=====================

(ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም): ተቀማጭነታቸው በሮም ሆኖ በሰሜን ሜቅዶንያ  የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ክብርት ደሚቱ ሀምቢሳ ከሰሜን ሜቅዶንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር H.E Mr. Timcho Mucunski ጋር  በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በስኮፔ፣ ሰሜን ሜቅዶንያ ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸውም በሁለቱን አገራት መካከል በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን መድረኮች ያለውን ትብብር አበረታች መሆኑን አንስተው፣ ሀገራቱ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ  ለማጠናከር እንዲቻል በከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ደረጃ የጉብኝት ልውውጦች ለማካሄድ ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።

በተያያዘም ክብርት አምባሳደር ከሰሜን ሜቅዶንያ የንግድ ምክር ቤት ዳይሬክተር ከሆኑት Ms. Biljana Peeva Gjurikj ጋር በመገናኘት በኢትዮጵያ ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎችን በተመለከተ አብራርተዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከርም በሁለቱ ሀገራት የንግድ ምክር ቤቶች መካከል  የጋራ ትብብር  ለመመስረት የሚስችል የጋራ ውይይት ለማካሄድ ከስምምነት ደርሰዋል::

Ethiopian Embassy in Rome

15 Nov, 13:53


ሚሲዮኑ በአፍሪካ - ጣሊያን የኢኮኖሚ ፎረም ተሳትፎ አደረገ፣
=====================
(ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም): የአፍሪካ -ጣሊያን የኢኮኖሚ ፎረም በሮም የተካሄደ ሲሆን ሚሲዮናችንም ሀገራችን ከማቴ ዕቅድ አኳያ ያለውን አተገባበር ለተሳታፊዎች የሚሲዮኑ ምክትል መሪ አቶ አሰፋ አብዩ አቅርበዋል።
አክለውም በማቴይ ፕላን ፕሮግራምን ተጠቅመው የጣሊያን ባለሃብቶች በአገራችን ኢንቭስት እንድያደርጉ ጥሪ አቅርቧል::

በፎረም ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር Edmondo CIRIELLI ጣሊያን ከአፍሪካ ጋር አብሮ ለማደግ በምታደርገውን ጥረት ሀገራቸው የምትሰጠውን ድጋፍ አጠናክራ እንደሚትቀጥል አረጋግጠዋል።

በፎረሙ ተሳታፊ የሆኑ የጣሊያን የሚመለከታቸው አካላት እና የፎረሙ ተሳፊ የሆኑ የአፍሪካ ሀገራት የማቴይ ፕላን ትግበራ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ በአጽንኦት ገልጸዋል።