Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ @fantahun_wakie Channel on Telegram

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

@fantahun_wakie


ወሳኝ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የሚነኩ አገራዊ ጉዳዮችን የውይይት አጀንዳ እንዲሆኑ በማቅረብ አስተያየትና የመፍትሔ ምክረ ዐሳብ ይቀርቡበታል። የሚያወያዩ የቤተክርስቲያንና ስለአገር የሚቆረቆሩ ወገኖች የሚያቀርቡትን ሀሳብ እንጋራታለን።

https://www.facebook.com/fwakie

Join me also here https://www.youtube.com/@Orthodox_Secular_Fant

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ (Amharic)

በተከሰተ ቦታ እስከሚኖረው ቦታ አስተዳደር ስራውን ለመረዳት ፈጣን የሆነው Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ ታሪክ ፕሮማች በዓይነ አማርኛ የማንም አብሮንን ያስተዋትር ሲሆን እና በእንስሳት ፣ መረጋችሁን ያዳምጡዋታል። ይህ ታሪክ በደስታ ላይ ለመመልከት የተጠቀሰው ድምፅ ብቻ ነው። ለሚጠቀሙት መረጃዎች እና አስተዳዳሪዎች፣ ጉዳይነትና ተለዋዋጮች ያለችውን ሳይንስ አማራን በቸሩባት ለእኔ በሚቆጠሩበት ፈላጊ የቴሌግራም መዋብያ በተከታታይ ስህተቶች ውስጥ እንዲሁም አትሌት የስለስም እና ዕውቅ ሆነ። በተጨማሪም የታምራታው ቦታ ምንም አይሆንም። በዚህ ቦታ አካሂዳ የበለጸግ ታሪኩን እና ምክረ ቀስነው እንኮች በእንቅስቃሴ እንስላችሁ።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

21 Jan, 04:54


https://youtu.be/FPK_5VqTQe0?si=Zb0kh-BDDs1ZWMRZ

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

21 Jan, 03:20


https://vm.tiktok.com/ZMk9WDTuS/

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

18 Jan, 01:18


https://www.youtube.com/live/V4TnqM1kX_I?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

14 Jan, 03:55


የማያምኑ ጳጳሳት እና ሊቃውንት እንዴት ልና ፈራ ቻልን?

ምንፈሳዊነት እየተዳከመ ሙያተኛነት በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዴት አደገ?

የእኔ ምልከታ እንሆ https://youtu.be/oUKxbVsYRC0?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

11 Jan, 04:56


ያማራን ሕዝብ ተጋድሎ የሚያኮላሹ ኣስተሳሰቸ ችይገቱ!!

በጎጥ ጠባብ አእምሮ እና በግል የሥልጣን ፍተወት፤ ከኢትዮጵያዊነት፣ ከኦርቶዶክሳዊነትና አማራነት ጋር ቋሚ ጠላትነት ካላቸው ሀገራት የስለላ ድርጅቶች እና ዲፕሎማቶች ጋር ከአማራ ሕዝብ ጀርባ የሚዶልት፤ የዘር ክልሉን እንጂ ሌላውን አማራ ለማሰብ የማይፈልግ፤ በመላው ዓለም የአንድ ጎጥ መዋቅር በምዘርጋት የአማራን አቅም የሚከፋፍል፤ በአዴን ቁጥር 2 ለመሆን የተሰለፈ ሤረኛ የፋኖ አመራር ለአማራ ሐዝብ ህልውና ሁለተኛ ዙር አደጋ የሚጠራ እንጂ አማራን ለድል አያበቃም። አገሪቱንም ጠቅልሎ በማጥፋት ለኣማራ በሀገርነተ የተደራጁ ዘላቂ ጠላት ያፈሩለታል።

ሰለዚህ የግለሰብ፥ የጎጥ፥ የሤራ፥ በድብቅ ከጠላት ጋር ስለመሞዳሞድ ሕይወቱን የሚሰጠው የፋኖ ሠራዊት፥ መከራ ውስጥ የቀጠለው ያማራ ሕዝብ ቁጭ ብሎ ተነጋግሮ ሥርዓት ሊያበጅለት ይገባል።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

08 Jan, 18:30


እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በደህና አደረሳችሁ።
የጸሎት ዋናው ክፍሉ ምስጋና ነው። ሰው እግዚአብሔርን ሲያመሰግን መልካም ነገሮች ሁሉ ይበዙሉታል። ክፉ ነገሮች ሁሉ ይወገደሉታል። የጸሎት ሁለተኛው ክፍል ንስሐ (ይቅርበለኝ) ነው። ይህም የነፍስና የሥጋን ንጽሕና ያስገኛል። ሦስተኛውም የጸሎት ክፍል ልመና ነው። ሰው የልቡን መሻት ከማንም በፊት መንገር ያለበት በዘላለማዊ ፍቅሩ ለወደደን ለእግዚአብሔር ነው።
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በመወለዱ የሰውን ሥጋ በመልበሱ ያገኘነው ጥቅም እስከ በማይባል ሀብት የተሞላ ነው።
እግዚአብሔር በአምላክነቱ ሰውን ወደደው። ሰው ቢበድልም በቸርነቱ አዳነው። ሞት በሰው ሥጋ ገብቶ ተሸሸገ። በሰው ሥጋ የተደበቀውን ሞት ከተደበቀበት ከሰው ሥጋ ውስጥ ገብቶ ያጠፋው ዘንድ ጌታችን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ተወለደ። በሰማይም በምድርም ምሉእ የሆነው አምላካችን አዳምን በቃሉ ማዳን ይችል ነበር። በሩቅ በቃል ከመናገር ይልቅ ሰውን መስሎ ሰውን ተዋሕዶ የቅርብም ቅርብ ዘመድም ወዳጅም ሆኖ ሥግው ቃል ለሕውሰታ በቀረበ በሚታይ በሚሰማ በሚዳሰስ ሥጋመለኮት ያድነን ዘንድ ፈቀደ። አካላዊ ቃል ሰው በሆነ ጊዜ ሰው ሁሉ ሙሉ ምሕረትንና ደኅንነትን አግኝቷል።
ጌታችን በሥጋ በመገለጡ እሱን የምናከብርበት እሱን የምንዘክርበት ቀናት በድርጊት በቃል ብቻ የተነገሩ ሳይሆን በድርጊት የተገለጡ እንዲሆኑ አደረገ። ለምሳሌ በ29 ፅንሰቱን ልደቱን እናከብራለን። በ6 ግዝረቱን ታቦተ ኢየሱስ ባለበት ሁሉ ጥር 6 ቀን በዓለ ንግሡ ይከበራል። (ግዝረቱ በግብረ መንፈስቅዱስ ማለትም ምላጭ ሳያርፍበት ከቀራንዮ በፊት ደሙ ሳይፈስ መሆኑንም ልብ እያስተዋልን እናከብራለን)
በ10 መስቀሉን በሀገራችን ከልዩ ታሪካዊና መንፈሳዊ ኩነት ጋር እናከብራለን።
ጥር 11 ልዩ ሦስትነቱን የገለጠበትንና ልጅነት (የኃጢአት ሥርየት) ያገኘንበትን የጥምቀትን በዓል እናከበራለን።
ጥር 12 ቀን በቃናዘገሊላ ወሃውን ወደ ወይንጠጅ የለወጠበትን ተዓምሩን እናከብራለን። ውሃ ቀለም መዓዛ ጣዕም የለውም። ጌታችን ቀለም ግሩም መዓዛ ጣፋጭ ጣዕም ሰጠው። የእኛንም ከቅድስና የተራቆተ ባዶ ሕይወት በእመብርሃን አማላጅነት የቅድስና ቀለም የጽድቅ መዓዛ የመንፈሳዊነት ጣዕም ይሰጠን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።
ቸሩ ፈጣሪያችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ክብር ይግባውና በሥጋ በመገለጡ በሆሣዕና በዓል ከሕፃናት ዝማሬ መቀበሉንና ቤተመቅደሱንም የጸሎት ቤት መሆኗን ያሳየበትን እንድናከብር አድርጎናል።
በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትን በዓል የምናከብረውም በሥጋ በመወለዱ የተገኘ የቸርነቱ ሥራ ነው።
በደብረዘይት ያስተማረበትን በመዘከራችንም ምስጋና ይግባውና ለዳግም ምጽአቱ እንድንዘጋጅ ያደርገናል።
በሥጋ በመገለጡ በቀራንዮ የተሰቀለበትንና በሥጋወደሙ ያዳነበትን በዓል እንድናከብር አድርጎናል። ሞትን በሞት አሸንፎ በቅድስት ትንሣኤው ትንሣኤ ብርሃንን ሰጥቶናል።
በሥጋ በመገለጡ እርገቱን እንድናከብር እሱን የማክበር ዕጣ እንዲደርሰን እርሱንም በማክበር በሚገኝ በረከት እንድንሳተፍ አድርጎናል።
የዚህች የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጅ መሆን ምንኛ መታደል ነው!!!!!
እግዚአብሔር ይመስገን።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

08 Jan, 18:28


https://youtu.be/NjQglypFD6I?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

06 Jan, 23:54


ይህን መስማት የቻልነው በጌታችን ልደት ነውና በዚህች ዕለት ደስ ይበለን
"  እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።" (ራእ 21:4)

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

06 Jan, 21:47


https://youtube.com/shorts/l3WTgsINbvY?feature=shared

አምላክ ሰው ሆኖ ከድንቁርናችን በብርሃኑ እንድንገልገል በጸጋው ካጥለቀለቀን በኃላ እንኩአን በገዛ ፈቃዱ በዲያብሎስ የባርነት ጨለማ የሚማቅቅ ትውልድ አለ::

ሕወሃትና ኦነግ ያደነቆሩት ዘረኛ ሲገርመኝ ባህር ማዶ ራሱን እንደ እንሰሳ የሚቆጥርና ዘራችን አንሶ የነጮች ይብዛ የሚል ሽበት ያበቀለ ጥቁር ሰማሁ::

አረ እንድረስላቸው!! ልል ብዬ መልሼ አፈርኩ::

የራሱአ አሮባት የሰው ታማስላለች እንዲሉ ---- በቤተመቅደስና በሲኖዶስ ደረጃ አዲሱን የጥምቀት ዘራችንን ጥለን በትግራዋይነትና ኦሮሞነት ከተዋረድን ከኛ ምንም አይጠበቅምና ይቅርታ ----- ዝንጀሮ ዝንጀሮን እየመራ ወደ ገደል ይቀጥል ብዬ ዝም አልኩ::

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

06 Jan, 18:17


👆👆👆አምላክ ሰው የሆነለትን ፍጡሩን በዘርና በቋንቋና በእምነት ዘውግ ፈርጀው ከምድረገጽ ለማጥፋት ሕግጽፈውና ተዋቅረው ፍጅት የጀመሩትን የምትፋለሙ የአማራ ልጆች በመከራም ውስጥ ቢሆ የአምላክን የልደት በዓል ለማክበር እንኳን ከደረሳችሁ።

ወንድም: ልጅ: አባት: እናታችሁን በሕወሃትና ኦነግ ኦሮሙማ ድቅል ልጅ ብልጽግና ጭፍጨፋ የተነጠቃችሁ፤ የዘራችሁት ሰብል፣ የረባችሁት እንስሳ የወደመባችሁና በችግር ላይ የምትገኙ ወገኖቼ የጌታችን የልደቱ ብርሃን ያጽናናችሁ።

ሲራክ እንደጸለይ እንዲህ እያልን ሰውሠራሽ ሀዘናችንን በሰማያዊ ጸጋ ደስታ የበላይነት ሸፍነን እንጸልይ

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

03 Jan, 20:10


https://youtu.be/5s8_a1MA-Fg?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

01 Jan, 21:37


https://youtu.be/xtevEFx6ok8?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

01 Jan, 21:28


https://youtu.be/66O3t7CxqsE?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

01 Jan, 07:08


በሰው ደም የትጋገር፣ በስው ዕንባ የትጨማልቀ፣ በተፈናቃዮች ሃብት የተገዛ፣ በሐሰተኛ ትርክትና ጥላቻ ሐሞት የመረረ ከክረስቲያን ሥጋና ደም ቀለም "እንኳን አደረሳችሁ" የሚል ጽሑፍ የተጻፈባት የዘር አጥፊዎች ኬክ እየቆረሱ፣ አልፀፀትም የሚል መጽሐፍ የሚያሳትሙ ህሊና ቦሶች ዛሬ እንደ ሰው ልብስ ለብሰዋል ። ይገርማል!! ዛሬም አጨብጫቢዎች መኖራቸው ወሰጣችን አራዊትነት መንገሡን ያሳያል።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

01 Jan, 04:21


https://youtube.com/live/8E2pOPqCuTk?feature=share. ላይቭ ልገባ ነው። መሥመር ላይ የምትገኙ ግቡና እንወያይ። ሌሎችንም ጋብዙ

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

31 Dec, 19:22


https://youtu.be/8AWQK5XhDEY?feature=sharedቆ

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

31 Dec, 02:26


ይህ ቤት እየተመራ የሚገኘው ከኢአማኒና ከሐዲ ቤተመንግሥት ደብዳቤ ተቀብሎ ፥ የሐዋርያትን ቀኖና ሽሮ "ንጹሕ እገሌ ብሔር ሾምኩ" የሚል፥ የጥምቀት ልጆችን ከዘረኛ ሥርዓት ጋር ተባብረው ያስፈጁ፥ ክህነት የማይገባቸ ውክህነት አልባዎች ሁሉ ጳጳስ"ብፁዕ" (ለምሳሌ ከተወገዘ በሗላ መልሶ የክህነትን ሥራ የሰራ (በወሰሶ ከተወገዜና ክህነታቸውን ከአጡ በኋላ ወደ ኋላ ያወገዙ ጳጳሳት) ተብለው የሲኖዶስ አባላት በሚባሉበት የሕገወጦች ጉባኤ አንድ መልካም ሰው ለውጥ ያመጣል የሚለው የዋህነት ልክ አብይ አህመድ አንድ በወቅቱ በብወቸ ችየዋሃ ንአእምሮ በመልካምነት የሚታይን አቶ "ዳንኤል ክብረትን" አስጠግቶ ሚሊዮቸችን የኦእቶዶክስ ተከታዮች ቢያን ስለ6 ዓመታት ያደነዘዘበት አይነት የማታለል እርምጃ ነው።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

31 Dec, 02:25


መምህር የምሰማው እውነት ከሆነ እግዚአብሔር ያውጣዎት።

ተወዳጅ መምህር የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አደረጓቸው ሲባል ሰማሁ። እጅግ ደነገጥሁ፣ እጅግም አዝናለሁ።

ያ ቦታ ህሊና ላለው፣ እምነት ላለው፣ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ለገባው፣ ከዘረኝነት ደዌ ለሚሸሽ፣ ሙስናን ለሚጸየፍ፣ አድርባይ ለማይስማማው፣ ለቤተመንግሥቱ ለማያሸረግድ፣ የሰማዩን አባት እግዚአብሔርን "አባቴ" ብሎ ራሱን በልጅነት ለመግለጥ ለሚፈልግ ሰው እንደማይሆን ባለፉት ፲፯ ዓመታት በቀጥታ በመሳተፍ አይቼዋለሁ።

እንደኔ ሙሉው የቤተ ክህነት አስተሳስብ፣ አሠራር፣ የሙስናው ማኅበር፣ የዘር ፖለቲካ አገልጋዮች ተጠራርግው እንዲወጡ ማድረግ እስከሚቻል ድረስ እንዲህ አይነቶች መልካም ወገኖቻችን ምንም ለውጥ ላያመጡ ሄደው ረገረጉ ውስጥ በመግባት ራሳቸውን ባያበላሹ የሚል ምኞትና ምክር አለኝ።

መምህር እግዚአብሔር ያውጣዎ። ምንም አይነት ለውጥ ማምጣት እንደማይችሉ ብቻ ሳይሆን እርስዎም ችግር እንደሚደርስብዎ ላረጋግጥልዎ እወዳለሁ።

======== በእኔ መረዳትና ልምድ
መዋቅራዊ ለውጥ የሚመጣው አንድ ደህና ግለሰብ በመሳብ ሳይሆን ጨክኖ የጠፋውን ቀነኖና ወደ ቦታው በመመለስ፥ የዘር ጳጳሳትን መሻር፥ የከተማ መነኮሳትን ወደ ገዳም መመለስ፥ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ከከሀድያን ማፍያ እጅ ነጻ አድርጎ በትርህምት በሚኖሩ አባቶችና ምእመናን ተሳትፎ መምራት ሲቻል ብቻ ነው።

ቤተ ክህነታነን እንድን ጤናማና ተወዳጅ ሰው ወደ ተበላሸ ረገረግ አስገብቶ አሳምሞ የማስወጣት ፋብሪካ ነው ከመሰለ ቆይቷል።👇👇👇

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

29 Dec, 16:47


https://youtu.be/NMlIo4DpPJU?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

29 Dec, 09:09


https://youtu.be/pOdoI4FND8c?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

27 Dec, 17:40


https://www.youtube.com/live/_9doP2J8SZM?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

27 Dec, 13:34


የኦሮ-ዉሀቢዝምና ብልጽግና ወንጌል አስተባባሪነት የጎነድርን ካህንና ቤተሰቦቹን የጨፈጨፈው ቡድን ይህ ነው https://rumble.com/v25xqcy-january-17-2023.html

"የኢትዮያ ኢስላኣም" የሚባል የለም የሚሉቱ ዑስታዞችና የጂሃድ አቀንቃኞች፥ የቱርክ ተላላኪው ግራኝ አህመድ መሸነፍ ፀፀተኞች ሶማሊያ ድረስ ተጉዘው ከአልሸባብ ጋር ተባብረውና የሁሉንም ጎሣዎች ጽንፈኛ የአልቃይዳና አይሲስ መንፈስ ወራሾች በማሠልጠን ወደ ክርስቲያኖች ጭፍጨፋ ያሰማራሉ።

ሽመልስ አብዲሳና አብይ አህመድ፥ ጀዋር መሀመድና ሌሎች ጽንፈኞች ይህን የውቃሉ። ነገር ግን የዋሁን የኦሮሞ ሕዝብ በብሔር ስም እያጃጃሉ ጂሀድ ያካሄዳሉ። ከሚሴና አጣዩ፥ ከበደኖ እስከ አርባባ ጉጉ፥ አርሲ፥ ሰሞኑን ሽርካ ከኦሮሚያ የጸጥታ ቢሮ እየታዘዘ የሚያርደው ሠራዊት የዚህ የጂሃድ አካል ነው።

አዲስ አባባ የኦርቶዶክሳውያንን ቤት እያስፈረሰ አሰፋፈር የሚቀይረው፥ ክርስቲያኖችን ለማደኸየት የሚሠራው የአብይ አህመድ ፕሮጄክት የዚህ የጂሃድ ስውር እጅ ነው።

እንቅልፍ አልቀው ያለው ክርስቲያንና አንዳንድ ዑስታዞች "ኢትዮጵያዊ የሚባል ኢስላም የለም" ብለው በንዴት የሚናገሩበት ምክንያት አዲሱን ይህን በማረድ የተሰማራውን "እስልምና" ለማበረታታት ነው። ተጠያቂ መሆን አለባቸው።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

26 Dec, 16:40


https://youtube.com/live/EBg-3MzCfE4

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

26 Dec, 05:08


ዓርብ ታህሳስ 18 ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ እንገናኝ https://youtu.be/NMlIo4DpPJU

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

26 Dec, 04:25


ከ5 ዓመት በፊት ፋይናነሺያል ታይምሰ ያወጣው ምስል አውዱ አብይን ለማድነቅ፥ ለምእራባውያን መልካም ጊዜ እንደመጣ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያ ልትሻገር ነው በሚል ማታለያ ከተጻፈ አርቲክል የተወሰደ ነው። እውነቱ ግን አገራችን ለሽያጭ እኛ ለእልቂት መዳረጋችን የጀመረው ወያኔና ኦነግ የዘር ሕገ መንግሥት በጸደቀ ጊዜ ነበር።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

26 Dec, 00:45


የኦነግ-ኦሮሙማ/ብልጽግና እና የሕወሃት አፈጣጠር ኦርቶዶክሳዊነትም፥ ኢትዮጵያዊነትን፥ አንድነትን፥ ታሪካዊነትን የማጥፋት ግብ ላይ ነው። ምንም በመቀባባትና በመሽኮርመም ይህን ማንነታቸውን ማስለወጥ ኤእቻልም። መፍትሔው ሁለቱን ካንሰሮችና ለካነሰሮቹ በቤተ ክህነት መዋቅር ውስጥ የተሰለፉትን ምንደኞች መጋፈጥ ብቻ ነው።

አቅም ካጣን ሰው እንሁን፥ ከበተረታን ክርስቶሳዊ እንሁን።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

26 Dec, 00:42


https://www.youtube.com/live/HP87cx8KWdY?si=OlAZ5vASnRwp6JDN

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

25 Dec, 21:14


https://www.tiktok.com/@mdawitsamuel/video/7452420519695027478?_r=1&_t=8sWBXU2Hjz4

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

25 Dec, 21:14


ይህን ማስተዋል ይጠቅማል https://vm.tiktok.com/ZNewB3JxP/

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

25 Dec, 03:21


https://x.com/VoiceFano2/status/1840104006451876302 ለምሳሌ ይህን የዘር ማጥፋት ጥሪ ያድረገን ግለሰብና ሚዲያ የከሰሰ የአማራ ልጅ ወይንም ህሊና ያለው ኢትዮጵያዊ የለም!!

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

25 Dec, 02:48


ለምሳሌ ይህን የዘር ማጥፋት ጥሪ ያድረገን ግለሰብና ሚዲያ የከሰሰ የአማራ ልጅ ወይንም ህሊና ያለው ኢትዮጵያዊ የለም!!

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

24 Dec, 20:05


https://youtu.be/8cvwlxHZXiQ

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

24 Dec, 03:33


https://youtu.be/DZFgLyeiHZE?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

22 Dec, 04:57


https://youtu.be/h18NN6wHACk?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

21 Dec, 04:50


Telegram: https://t.me/+io2m-XA1OBE2NmM0

YOUTUBE:- https://www.youtube.com/@Orthodox_Secular_FantahunWakie/videos

ትዊተር፦ @fwakie

FB:- https://www.facebook.com/fwakie

Blog:- https://ethiopiaorthodoxchristian.blogspot.com

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

20 Dec, 21:24


https://youtu.be/rBDzDv2a6bY

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

20 Dec, 06:00


Fantahun_Wakie

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

19 Dec, 22:02


🖕የቀጠለ
👉. የክርስቲያኖች ምፍዘዝ፣ መደንዘዝ እና የምንደኛ ሰባኪዎች "በኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት" ሽፋን ክርስቲያን ለመብቶቹ እንዳይሟገት ልቡን መከፋፈል።

ስለዚህ በመፍትሄ ፍለጋ የተሰለፋችሁ ወገኖች ሁሉ መንስኤዎቹን ታሳቢ ያደረገ ርእዮት፣ አሰላለፍ፣ ቅንጅት መርህ፣ በየደረጃው የሚመዘን የድል አንጓዎች መስፈሪያ በግልጽ መስመር ይጠበቅባቸዋል።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

19 Dec, 22:02


የዚህ እልቂት ዋና መንስዔ የ፮ ነገሮችን ተዋንያን ቅንጅት ይመስለኛል። እነዚህም:-
👉 ገንጣይ አስገንጣይ የሰሜን ነጻ አውጭ ነን ባዮቹና በድብቅ ዘር የማጥፋት በሽታ የተለከፉት ሕወሐትና ኦነግ ያዘጋጁት የዘር ሕገ መንግሥት፣ የዘር ክልል፣ የዘር እምነት፣ የዘር ባንዲራ፣ የዘር ትርክት ፣ የዘር መንግሥት፣ የዘር መዋቅር፣ የዘር የፍትህ ሥርዓት፣ የዘር ሚዲያ፣ የዘር ልዩ ኃይል የተባሉ ታጣቂዎች ናቸው

👉 ለኑሮ ምቾትና ድሎት ሲሉ የተካኑ፣ የመንኮሱና የጰጰሱ የዘር ጣዖት አገልጋዮች ቤተ ክህነቱን በመቆጣጠራቸውና ከዘር አጥፊ ሥርዓት ጋር በግልጽና በተግባር በተባበር ክርስቲያኖች እምዲዘናጉ በበዓል፣ በሕንፃ ምረቃ፣ በአደባባይ መዝሙር፣ በአውደ ምህረት እልልታና ጭብጨባ ወዘተ ማደንዘዝ፣ የሚደርሰው እልቂት በኦርቶዶክስ ሚዲያ እንዳይነገር በማድረግ በሕዝቡ መካከል የጋራ ግንዛቤ እንዳይደርሱ ማድረግ

👉 በሲኖዶስ የኦርቶዶክስ እልቂት አጀንዳ ሆኖ እንዳይቀርብ በማድረግ የሚሠሩ የዘር ጳጳሳት መብዛት

👉 የአብይብአህመድ አጀንዳ፣ የኦሮ-ዉሀብያ ጂሀዲስቶች፣ የጀርመን ክርስትና ጸሎት ቤት የፈለፈላቸው ጥቁር ናዚዎች ኦነግ፣ የውሃ ዳር አጋንንት አምልኮ ፈጻሚዎች የጋራ አጀንዳ ኦርቶዶክስንክርስትንስናን እናንአማራን በማጥፋት ላይ በመስማማት በብልጽግና ወንጌል ቅዠት በሚመራው ሥርዓት ሥር መደራጀቱ

👉 የጣልያን በአድዋ መሸንፍ ያቆሰሳሳቸው ቅኝ ገዥነት የተፈጥሮ መብታቸው የሚመስላቸው ምእራባውያንና የቱርክ ተላላኪው የግራኝ አህመድ መሸነፍ የሚቆጫቸው አረቦች ዘር አጥፊውን ሕወሃትና ኦነግ ብልጽግና መደገፋቸው👇

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

19 Dec, 06:39


https://t.me/Fantahun_Wakie

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

18 Dec, 08:41


ከ4 ዓመታት በፊት የተረዳሁትን በማጋራት አስጠንቀቄ ነበር። አሁንም ከተኛበት ያልነቃ አለ።

https://www.youtube.com/live/UbMox9WJT1M?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

18 Dec, 05:08


https://youtu.be/ft9sgzwZiFg?feature=shared

👉👉 እውነት፣ ፍትሕ፣ ሰብአዊነት፣ ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋሉ!!!

👉👉ዘረኝነት፣ ኢፍትሐዊነት፣ ሐሰተኝነት፣ ኢሰብአዊነት፣ ስግብግብነት፣ ዘር አጥፊነት ይሸነፋሉ!!!

ሁሉም ሙሉ ሰብእና ያለው፣ የሰውን ክቡርነት የሚቀበል ከዘረኝነት ነጻ ሆኖ የህልውናና የፍትህ፣ የእውነትንና የሰብአዊነትን ተጋድሎ ይደግፍ!!!

በክርስትና መንፈሳዊነት ሥር ተደብቆ ዘርአጥፊዎችን ሳይገስጹ ድሎትና ምቾታቸውን የሚያስጠብቁ አባቶችና ሰባኪዎች የዘር ማጥፋት ፕሮጀክት ድብቅ ደጋፊዎች ናቸው። በተለይ በዓል፣ ሕንጻ፣ ጫጫታ እያደመቁ የሚያዘናጉ የህልውና ተጋድሎው እንቅፋቶች ናቸው!!

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

17 Dec, 01:40


ታፍኖ የጠፋው ልጆችን የትብደረሰ
https://youtu.be/3pxMY0gS_RM?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

09 Dec, 21:35


"በፊት ታጣቂዎች ፣ አሁን ደግሞ እራሱ መንግሥት እየገደለን ነው!" ነዋሪዎች! #ከደራ_እስከ_ ሽርካ! #የማያባራው_የቁማር_ፖለቲካ_ሰለባዎች! #ልዩ_ዘገባ https://youtu.be/GvGeI1MX8rw?si=91cE80Fb5xnkr5ua

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

08 Dec, 20:38


የነፍስ እና የዘላለማዊ ሕይወት ጉዳይ በይሉኝታ አይታለፍም!!!!

"የአማራ ጳጳስ" ነኝ የሚል መነኩሴ ክርስቶስን የካደ ከአሕዛብ የከፋ የሰይጣን ልጅ ነው።

የኦሮሞናን የትግሬብ ጳጳስ ነኝ፣ የብሔር ብሔረሰብ ሲኖዶስ የሚሉትን ነውረኞች ሁሉ "ብፁዕ" ሲል የቆየው ሲኖዶስ በአብይና ዳንኤል ሴራ የአማራ የሚባል ሌላ የከሀዲዎች ቡድን ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ነውና

ይህ ከሆነ ሲኖዶሱ የክርስቶስ ሳይሆን ሌላ ነገር ስለሚሄን ምእመናን አውግዘው፣ ካህናትና ሊቃውንቶቻቸውን ለይተው በመንቀሳቀስ ወድ አኀት አብያተክርስቲያናት ማመልከቻ በመላክ እንደ አዲስ ክርስቲያን የሆኑ፣ ከጎሣ ጣዖት አምላክነት ነጻ መሆናቸው እየተጣራ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾምልን መጠየቅ ይገባል።

https://youtu.be/-zQb5hbg9cQ?si=pxEMfXHcAN_SdphA&sfnsn=mo

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

07 Dec, 00:45


"የትግራይ ወጣት የሞተው አገር ለመፍጠር ነው፥ እኛም የመነኮስነው ለትግራይ አገር መሆን ነው። ክርስቶስም የተሰቀለው ለትግራይ ነው። ቤተ ክርስቲያንም የምታገለግለው የሕወሃትን ርእዮት ዓለም ነው" የሚሉት የዚህን አይነት በነፍስም በሥጋም የሞተን ከሀዲ " አቡነ" የሚል ሕዝብ ክርስቲያን ነኝ ብሎ ማሰብ ኤእገባውም። ክርስቲያን ለመሆን ከዘር ፖለቲካና ዕሳቤ ነጻ በመሆን ሰው ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

06 Dec, 22:52


https://x.com/ASN_Amhara/status/1864724902567137303?t=jJmKcMOtXyXKJg81Zue1PA&s=08

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

06 Dec, 07:11


https://youtu.be/cDbclFnEdgQ

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

03 Dec, 05:44


https://www.youtube.com/live/4Hz_gCjOyys?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

02 Dec, 20:33


https://youtube.com/live/O562lMAvawk?feature=share

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

01 Dec, 19:05


https://youtu.be/TP0ZSis0e2w

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

01 Dec, 05:25


https://youtu.be/5HuFYgTI6OU?si=vAiPG34x-_caluUf

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

01 Dec, 05:25


https://youtu.be/HGJzxLHgdws?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

29 Nov, 21:38


ወታደሩ ይህን የምትሰሙትን ይላል።

ነገር ግን አብይ አህመድና አማካሪዎቹ ያለ ኦርቶዶክስ ክርስቲያንና ያለ አማራ ደም ውለው ማደር ስለማይችሉ አያደምጡትም።
https://www.facebook.com/share/v/1Dzkgjpuh9/

መፍተሔው ይህን የአራዊት ሥርዓት ማሸነፍ ብቻ!

ታዳያ ጀግና ጀግና መጫወቱን ብቻ ሳይሆን በሌላ አሜሪካ ሰራሽ አውሬ እንዳይተካ በተጻፈና በተተለመ መንገድ ላይ መሄድ።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

29 Nov, 20:49


አብይ አህመድ አሊ ኦርቶዶክሳውያንን በጅምላ እያስፈጀ በጅምላ ማስቀበሩ ቀጥሏል።

አረኛው በዳንኤል ክብረት እየተመከረ የገዛ ልጆቹን እልቂት በመሸፋፈን ቀጥሏል።

በየሀገረስብከቱ የሚገደሉ፥ የሚፈናቀሉና የሚሳደዱ ክርስቲያኖችንና ካህናት ዕለት ዕለት እየተመዘገበ በዜና እንዳይነገር የኦርቶዶክስ ተዋህዲኦ ቤተ ክህነት ፈቃደኛ አይደለም።

ጳጳሳቱ የየሀረገ ስበከታቸውን ጥፋት እንዳይነገር ቀጥተኛ አፈና በማድረግ ለ6 ዓመታት ከፖለቲካው የተቀበሉትን አደራ እየተወጡ ነው።

መንግሥት መሩን እልቂት ለምእመናንና ለዓለም ማስታወቅ ብቻ ሳይሆን ለሚሞቱት የሰማዕታት ክብር ለመስጠት በዐመታዊ ጉባኤዎች የቀረቡትን አቤቱታም ውድቅ አድርገዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እልቂቱን ለመሸፋፈን ከሚደረጉ አሳፋሪና ተግባራት አንጻር ጎላ ተደርገው እንዲቀርቡ የሚደረጉ አጀንዳዎች፦

1) ሙስና ማጣራት ነገር ግን ሙሰኛውን መዋቅር አለመንካት

2) የአእላፋት ዝማሬ ዝግጅት መዝሙር ማጥናት ነገር ግን የወገኖችህን እልቂት በምንም መልኩኡ በአውደምህረትና በሚዲኣ እንዳይነገር ማገድ

3)፥ በዓል ማድመቅና ምእመናኑ እየተካሄደ የሚገኘውን ብቻ ሳይሆን እየመጣበት ያለውን እልቂት እንዳያውቅ ማድረግ

4) ሕንጻ መሠረት ማስቀመት፥ ማሠራት፥ መመረቅ፥ በጨረታ ላይ መባላት፥

5) አህያ ይበላል ኤእበላም፥ በጫማ ቤተ መቅደስ ይገባል አይገባም ወዘተ የሚሉትን የተሐድሶ የሰለቹ ጭቅጭቆች ወደ ሜዳ አውጥቶ መነታረክ

ቀጥሏል ----

ምእመኑ ዛሬም በጫጫታና በሐሰት የሰላም ተስፋ ማንቀላፋቱን ቀጥሏል

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

29 Nov, 04:43


https://youtu.be/lPu0SUyf1MA

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

27 Nov, 18:38


https://www.youtube.com/live/C76jBSxNC5w?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

26 Nov, 03:17


አሁን ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለው ፈተና እና ምንጩ እና ጥምረቱ (አገልጋዮቹ የሚገለጡበት ድርጅት ሕወሃት፥ ኦነግ/ኦሮሙማ/ብልጽግና፥ የቤተ ክህነት ምንደኞች፥ ጽንፈኛ የግራኝ አህምድ ናፋቂ ጂሃዲስቶች)
1. የሮማ ካቶሊክ ኑፋቄ (ፋሺዝም) የወለደው የባንዳ ልጆች ድርጅትና አገር ጠሉ የሕወሃት፥ የጣሊያን ባርነት የሚያኮራውና የ3000 ዓመት የነጻነት ታሪኩን በ60 ዓመታት ቅኝ የመገዛት ባርነቱ የሚኮራ የጀበሃ/ሻዕብያ (መለያየትን ከነጻነት የሚቀጥረው የጨለማ ፖለቲካዊ ርእዮት)፥ የግብጽና የአረቦች ፍላጎት አገልጋይ ፖለቲካ
2. የጀርመን ክርስትና (ናዚዝም) ያስፋፋው ከግንቢ ወለጋ ሆስፒታል ተነስቶ ኦነግን የወለደው ዝር አጥፊ ፖለቲካ
3. መሀመዳዊ የአረብ እምነትና (በተለይ አክራሪው)
4. ምዕራባዊ ለቅኝና ለባርያ ፍንገላ መንግድ ሲጠርግ የኖረው፥ አሁን በማደንዘዣነት የሚያገለግለው (ሥኩላር ሊበራል፣ ሴኩላር ኮሚኒስት፣ ፕሮቴስታንቲዝም)
5. በአእምሮ እጥበት ላይ ሁለገብ ጥገኝነት እና ንቀዘት ሲጨመር የአፍሪካ መሪዎች የባዕዳን ማሽን የሆኑ፥ ሰውነት የተለያቸው መሪዎች።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

26 Nov, 02:53


ቱንቢ ሚዲያን (1) ሰብስክራይብ ፥ (2) አባል በመሆን፥ (3) ብዙዎች ጓደኞቻችን እንዲሳተፉና አባል ከመሆን ጀምሮ እንዲራዱ በመጋበዝ (4) በስፋት በማስተዋወቅ — ሚዲያውን እንዳሳድግ https://www.youtube.com/@TunbiMedia_

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

25 Nov, 02:18


በዚህ ሠላሳአምስት ዓመት ውስጥ የሥልሳዎቹ በግፍ መረሸን ተደጋግሞ ስለተነገረ የሁላችንንም ሕሊና ያደማ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ከዚያ የግፍ አገዳደል በብዙ እጥፍ ናዚዎችንና ፋሽስቶችን የሚያስመስግን ሒትለር ቢኖር የሚደነግጥበት ዘግናኝ ግድያ እየተፈጸመ አይደለም ወይ!!!!!!! አልቃይዳና አይኤስን የሚያስንቅ ግድያ በምን ቃላት ይገለጻል። ደርግ ያጠፋውን ጥፋት መዘከሩ ለማስተማሪያነት ጥሩ ነው። ደርግን አረመኔም ፋሽስትም እንበለው። ነገር ግን ወያኔና ኦነግ የፈጁትን አውሬያዊ ፍጅት የዓለም የቋንቋ ጠበብት ቢሞክሩት እንኳ ፍጅቱ በቃላት ከሚገለጸው በላይ ነው። ደርግ ንጹሓንንም ቢገድል እንኳ መርጦ ነበር የሚገድለው። እነ ወያኔና ኦነግ ግን ምንም ጦርነት ሳይኖር ፈረንጆቹ Clearing earth የሚሉት ዓይነት ግድያ ነው ትናንትም ዛሬም የሚፈጽሙት። እነሱ የሚገድሉት ፖለቲካቸውን ያልነካውን ሁሉ በማንነቱ ብቻ ነው የረሸኑት። ያውም ምንም የጦርነት ኮሽታ በሌለበት በቤቱ በተኛበት የዕድሜም የፆታም ልዩነት ሳያደርጉ ነው። ያውም የእናቶችን ሆድ እየቀደዱና ፅንስ እያረዱ!!!!! ያውም ራሳቸውን መከላከል የማይችሉትን ካህናት አባቶችን በቤተመቅደስ በቅዳሴ ላይ እያሉ። ያውም በሟቾች ላይ (በሕይወት የተረፉት እንደመሰከሩልን)ግብረሰዶም እየፈጸሙ ነው።
ሒትለር የግፍ ግፍ የፈጸመው በወጭ ጠላቶቹ ነው። እነ ወያኔና ኦነግ ትናንትም ዛሬም የግፍ ግፍ የሚፈጽሙት በገዛ ዜጎቻቸው ላይ ነው። ሒትለር የገደለው ታላቋን ጀርመንን ለመገንባት ነው። ሙሶሊኒም የጨፈጨፈው ታላቋን ሮማን ለመመለስ ነው። ይሄ በራሱ ጥፋት ነው። እነ ወያኔና ኦነግ የገደሉት ግን ታላቋን ኢትዮጵያን ለማፈረስ ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ ክብርና ነፃነት የሀገራችንንም ሉዓላዊነትና አንድነት ለማጥፋት ነው።
የደርግ መንግሥት አረመኔ ነው። ሥልሳዎቹን የሀገር ባለውለታዎች መግደሉ ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ ነው።
እስኪ አንድ ነገር እንመልከት። ደርግ ሥልሳዎቹን የቀኃሥ ባለሥልጣኖች ለምን ረሸነ? ጭፍን ጥላቻ ወይስ ገፊ ምክንያቶች አሉ? መግደለ በምንም ሁኔታ ደርግ ከወንጀለኛነት ሊያድነው የሚችል ሕጋዊ ሚዛን የለም። ደግሜ እላለሁ ለምን ገደለ??????
በበኩሌ ገፊ ምክንያቶች የምላቸውን ልጥቀስ። አንደኛው የባለሥልጣናቱ ደርግን የመደምሰስ ያልተሳካ ሙከራ ነው። ደርግን አራተኛ ክፍለጦር ግቢ ውስጥ በስብሰባ ላይ እንዳለ እንግደል ብለው ንጉሡን ጠይቀዋል። አስርቤት ከገቡ በኋላም በእነ ጣሰው ሞጆም በሌሎችም አማካይነትብዙ ሞክረዋል። ያውም እቅዳቸው ከደርግ አባላት መካከል ቀንደኛ የሚባሉትን መርጠው ሳይሆን በጅምላ መደምሰስ ነበር። እነሱስ ተሳክቶላቸው ቢሆን ኖሮ የሰው ደም አላፈሰሱም ማለት ይቻላልን????? ወይስ የደርግ አባላቱ ደም ውሀ የእነሱ ደም የተለየች ናትን????? ሌላ ገፊ ምክንያት ልጨምር። የደርግ አባላቱ እነ መንግሥቱ ኃይለማርያም ፍሰሐ ደስታ ብርሐኑ ባይህ በመጽሐፍም በቃለመጠይቅም የሕግ ምሁሩ ፕሮፌሰር በረከትና ፕሮፌሰር መስፍን ደርጎች "የባለሥልጣናቱን ጉዳይ እንዴት እናድርግ" ብለው ሲጠይቋቸው "ጠመንጃው በእጃችሁ ነው" የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው በአጽንኦት ገልጸዋል። ይሄ ቃል እነሱን (ደርጎችን) ንጹሕ ያደርጋቸዋል ለማለት አይደለም። ነገር ራሱን የቻለ ገፊ ምክንያት ነው። በእርግጥ ሁለቱ ፕሮፌሰሮች ሲጠየቁ አስተባብለዋል። እውነቱን እግዚአብሔር ይወቅ። ወደፊት የታሪክ ባለሙያዎች መርምረው ይደርሱበታል ሌላም ገፊ አለ።
ሌላው ገፊ ምክንያት የጀኔራል አማን ጦሩ በደርግ ላይ እንዲነሣ መቀስቀሳቸው ገፊ ነው።ከንዑስ ደርጎችም ሆነ ከአንዳንድ የሠራዊቱ አካላት "እነዚህን የሕዝብ ደም መጣጮች አስራችሁ የምትቀልቡት እስከመቼ ነው" የሚለው ግፊት ለዚያ የግፍ አገዳደል ራሱን የቻለ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ከሥልሳዎቹ ቀጥሎ የደርግ የግፍ አገዳደል ሰለባ የሆኑት የኢሕአፓ ወጣቶች ናቸው። የእነሱንም ገዳይነት አብረን እንመስክር። ደርግ ብዙ እናቶችን ልጅ አልባ ብዙ ልጆችን ወላጅ አልባ አድርጓል። ከዚያ በፊት ኢሕአፓ ብዙ እናቶችን ልጅ አልባ ብዙ ሕፃናትን ወላጅ አልባ አድርጓል። ኢሕአፓ የጋየው ራሱ በለኮሰው የግድያ እሳት ነው። በእውነት የኢሕአፓ ነጭሽብር ባይኖር ኖሮ የደርግ ቀይሽብር ይኖር ነበርን!!!!!! ይሄንንም ሐቅ አብረን እንመስክር።
ነገር ግን ከሚረሸኑት የኢሕአፓ ወጣት አባላት መካከል አንዷ ነፍሰጡር ሆነው ተገኙ። በማሕፀን ያለችው ሕፃን ያለጥፋቷ መሞት የለባትም በማለት እንዲተርፉ ተደርጓል። ሴትዮዋ በኋላ ሚኒስትርም አምባሳደርም ለመሆን የበቁና ታሪካዊ ምስክርነት ያለውን መጽሐፍ አበርክተዋል። ልጃቸውም ተምራ በጥሩ ውጤት ተመርቃ ለእናቷ የመጽናኛና የደስታ ምንጭ ሆናለች። ሌሎችም በዚህ መንገድ የተረፉ ብዙዎች ናቸው።
የደርግ መንግሥት ከሥልሳዎቹ ጀምሮ ያን ሁሉ የኢሕአፓ ወጣት መረሸኑ ታሪካዊ ጥፋት ነው። ነገር ግን የዘር ድርጅቶች የሚገድሉት እና ደርግ የሚገድለው የብርሐንና የጨለማን ያህል ይለያያል። ዛሬም የእሱን ጥፋት የሚጮሁት የነሱን ሌብነት ዘረኝነትና የሀገር ክህደት ለመጋረድ ነው። እንጂማ ወያኔና ኦነግ ለቀኃሥ ባለሥልጣኖችም ለኢሕአፓ ወጣቶችም አዝነው አይደለም። ምክንያቱም ሻዕቢያም ወያኔም ኦነግም ራሱ ኢሕአፓም ቀኃሥን ለመዋጋት በቀኃሥ ዘመን ተነሥተዋል። ወያኔ በትግራይ ኦነግ በሲዳሞና በባሌ ኢሕአፓን ወግተው ከየአካባቢው አስወጥተውታል። እንዴት ነው ለቀሐሥም ለኢሕአፓም ለደርግም ተቆርቋሪ የሚሆኑት??? ስለዚህ በቀኃሥ ባለሥልጣኖች መረሸን እነ ወያኔና ኦነግ ደስተኞች እንጂ አዛኞች አይደሉም። ጩኸቱን የፈለጉት የነሱን ባንዳነት ለመሸፈን ነው።
ሌላ ሐቅ እንመልከት። ደርግ ከኢድዩ በቀር አንድም ያፈራው ጠላት የለም። ጀበሐ ሻዕቢያ ኢሕአፓ መኢሶን ኦነግ ወያኔና ሌሎች የዘር ድርጅቶች ሁሉም በቀኃሥ ዘመን የተነሡ የአገር ጠላቶች ነበሩ። ስለዚህ ቀሐስ የወዘፉት እዳ የደርግ ትክሻ ላይ መወደቁንም አበረን እንይ።
ደርግን ከተቃወሙት መካከል ከመኢሶን በስተቀር ሁሉም የሀገር ገንጣይ ድርጅቶች ናቸው። "ደርግ ለእነሱ ሥልጣኑን መልቀቅ ነበረበት" ብሎ የፈረደ ታሪክም የሕይወት ታሪክም የጻፉም በአፍም የፈረዱ ብዙዎች ናቸው። እነዚያ የታሪካዊ ጠላቶቻችን ቅጥረኛ ባንዳዎች ሀገራችንን ምን እንዲያደርጓት ነበር የተፈለገው!!!!!! የፈራጆችን ማንነት መጠራጠር እንደሰው አስፈላጊ ነው።
ደርግን ለሃያሰባት ዓመት ጭራቅ አድርጎ ሲያብጠለጥሉት የነበሩት እነ ሻዕቢያ ወያኔና ኦነግ ናቸው። እነሱ በእውነት ስለቀኃሥና ባለሥልጣኖቻቸው አዝነው አልነበረም። የደርግን አንዲት ጠንካራ ጎን (ለምሳሌ ከዘረኝነት ከሌብነት ከሀገር ክሕደት ነፃ መሆኑ) ቢመሰክሩ በዚያ ሚዛን ሲመዘኑ ከዜሮ በታች በብዙ የጥፋት ርቀት ስለሚገኙ ነው።
ይሄን ሁሉ ያመጣሁት ደርግ ገደለ ብቻ ሳይሆን ለምን ገደለ ብለን ማየትም አስፈላጊ መሆኑን ለመጠቆም ነው። አዎ ደርግ ኢሕአፓንም ሻዕቢያንም ወያኔንም የገደለው አገር ለማዳን ነው። እነሱ ደግሞ የገደሉት አገር ለማጥፋት ነው። አገር ከማዳንና አገር ከማጥፋት የቱ ይሻላል??????
እርግማን ብቻ ሳይሆን እንደዚህ ዓይነት እውነታዎችንም አብረን እንዘክር ብየ ነው። 
ደርግ ሰው መግደሉ ታሪካዊ በደል ነው። ነገር ግን የደርግን መንግሥት በሌብነት በዘረኝነት ማንም አይወቅሰውም። ጠላቶቹም ሁሉ በዚህ አይከሱትም። በሀገር ሉኣላዊነትና በኢትዮጵያ አንድነት ማንም አይወነጅለውም።
የዘመናችንን ገዳዮች በዚህ መስፈርት መዝኑና ፍርድ ስጡ።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

23 Nov, 07:19


በሰላሌ ምሰው ታረደ። "በአሰቃቂን ሁኔታ"


ይህ ነውር የነውረኛው መንግሥት መሆኑን ለማወቅ ምርምር አይጠይቅም። ይህ መንግሥት ፮ ዓመታት ሙሉ መደበኛና መደበኛ ናልሆነ መንገድ ከሚሊዮን በላይ ሰው አርዷል።

አልረካ ሲል በምእራባውያን ብድርና በኤሜሬቶች ድጋፍ መግደል ሮቦት አሰማርቶ በገዳማትና አብነት ትምህርት ቤት ውስጥ ሳይቀር አርዷል።

አዲስ አበባ ቀድሶ የወጣ ቄስ በድንጋይ አስወግሮ ግድሏል።

በዚህ ሁሉ :-
፩) አብይ አህመድ አሊና የኦሄዴድ/ብልጽግና የደም ጓዶቹ የሀዘን መግለጫ አላወጡም። ዛሬ ግን ፋኖን ለመልሰስና ግጭቱን ከፖለቲካ ሥርአት ውንጀለኝነት ወደ ጎሣ ለማዞር ተንጫጩ

፪) በ፮ቱ ዓመታትብየኦርቶዶክስና የአማራ ጭፍጨፋ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አልተነፈሱም፣ ዛሬ ግን በኦሄዴድና በጀዋር የተለመደው አስተባባሪነት በሁሉም የኦሮምያ ዞኖች በሚገኙ ት/ቤቶች ሰልፍ ተደረገ።

፫) የኦነግ ኦሮሙማ ጋዜጦችና ሚዲያዎች ፮ ዓመታት ከአይራ ጉሊሶ እስከ አርሲና አዲስ አበባ የሚካሄደውን እልቂት አላወገዙም፣ ዛሬ ግን ምድር ቁና ሆነች።

ጥያቄው:-
፩- እነዚህ ለዓመታት ሰው ሲጨፈጨፍ አድፍጠው ዛሬ የተነሱት ሁሉ በሌላው ጭፍጨፋ የጋራ እቅድ አልነበራቸውም ማለት ይቻላል

፪- የእንዚህ አካላት ፍልስፍና ሰውን ከሰው ለይቶ ማክበርና ማንን የሚፈቅድ ከሆነ የናዚ ጀርመን ርእዮትን በአፍሪካ እየፈጸሙ ነው ማለት ስሕተት ሊሆን ይችላል?

፫- የአብይብአህመድ አሊ መንግሥት ከዜጎች መካከል የሚታዝነለትና እልቂት ሊፈጸምበት ወገን ለይቶ የሚሠራ የስልጣን መንግሥት ነው ቢባል ስህተት ይሆናል?

፬- ፓርላማው ፮ ዓመት ሙሉ ሰው እያሳረደ ደሞዝ የሚቀበልና ለዜጌች ዋስትና መሆን ያልቻለ መሆኑን አይተን የስው ስብስብ ሳይሆን የአብይ የእጅ ሥራ ሮቦቶች በስውር አምሳል የሚታዩበት የሚተነፍሱ አስክሬኖች ጉባኤ ነው ቢባል ያስነውራል?

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

22 Nov, 16:14


ብልህ ከጉረቤቱ ይማራል::

የግሩክ መነክሳት በኢንተርኔትና በስማርት ስልክ ምክንያት ምንከስናቸው አደጋ ላይ እየወደቀ መሆኑ ይነገራል::

የከተማ አውደልዳይ ወደልችን ትተን ተሐራማሚዎች ገዳማውያን መነኮሳት ስልክ እፕጠቃቀም በኢትዮጵያ ምን አይነት መንፈሳዊ አደጋ እያመጣ እንደሆነ በማጥናት መፍትሄ መፈለግ እንደሚገባ አስባለሁ::

ግን በሕንጻ ግንባታ: በበዓላት ድምቀት: በፓለቲካ ለዚያውም በጎሣ ጣዖት አገልግሎት የተጠመደው ቤተክህነትና የንጹሕና ዲቃላ ዘር ቆጠራ እየተሰያየመ "ብፁዕ" እየተባባለ የእግዚአብሔርን ቤተሰብ በመከፋፈልየተጠመደው ሲኖዶስ ይህን ማድረግ እንደማያስብ እርግጠኛ ስሆን ምእመናና ተሐራምያንንሊቃውንት ካህናት አዲስ መላ ማሰብ እንደሚጠበቅባቸው አስባለው::

እንወያይ

https://youtu.be/gXX2XHo_sK8?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

22 Nov, 05:15


አባታችን ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል

በወቅቱ አብይ ለኢትዮጵያና መልካም ሰው መስልዎት ጥብቅና ቆሙለት ብለንንእንመን። አሁን አገርና ሃይማኖትን አጥፊ መሆኑ ገሀድ ሲሆን ልሳንዎ ለምን ታሠረ?

https://vm.tiktok.com/ZMh7HpwFj/

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

16 Nov, 06:12


Addisu Media አንዳንድ ነገሮች //ቤተ ክርስቲያንን ለመታደግ..." Friday Nov 15, 2024
https://youtube.com/live/omUhktJReaQ?feature=shared

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

15 Nov, 17:21


አማርኛ ተናጋሪ አልሸባብ እንዳለ አስበው ይዘጋጁ። በመግደል ክህደት የሆነውን እምነት ለማስፋፋት ሺ ዘመን የዘለቀው አጋንንታዊው አስተምህሮ ራሱን አድሶ እየመጣ ነው።

ግራኝን ቅዱስ ንጉሥ በሉልኝ ብሎ የሚንጫጫው፤ ብሔርና እምነትን ደባልቆ ደም የሚያፈስሰው፣ አብይንና ጓዶቹን የተቆራኘው ርኩሱ መንፈስ እነሆ አማርኛም ይናገራና ነቃ እንበል!!!

ትግርኛም፤ ኦሮምኛም ይናገራል። እንደ ሊቢያው አራጅ አረብኛ፣ እንደ ሶማሊያው አልሻባብ ሱማልኛ ብቻ አንጠብቅ!!!

እንደ ትግራዩ መንበረ ሕወሃት ጳጳስም ስመሥላሴን ይጠራል፤ አገር አጥፊውን የእለቂት ድግስ ሲበላ የሞተውንም "ቅዱሳን የክርስቶስ ሰማዕታት" በማለት የሚሰይም፣ የጥምቀቀት ልጆችን ንጹሕና ዲቃላ ብሎ የሚፈርጅ መስቀል የጨበጠ የአጋንንትና የመለያየት አገልጋይም እንደአለ አንዘንጋ!!!


https://rumble.com/v25xqcy-january-17-2023.html

በማጋራት ግንዛቤ ያሳድጉ

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

15 Nov, 16:10


በዚህ አይነት ደንቆሮ ለመመራት መፍቀዳችን የውድቀታችንን ደረጃ ጥልቀትን ያሳያል::

ከሁሉም በላይ ክርስቶስን የዘነጉ ድንዙዛን ጳጳሳት ቤታችንን መሙላታቸውን በደማቁ ይምሰክራል::

እነ "አንገቴን ሰጣለሁ" እና "ችግር የለም እንጂ አትገዙ ማለት እንችላለን" ባዮቹ አድርባ የሐሰት እረኞች በዚህ ንግግር አለመቆጣታቸው ምን ያህል የሐሰት እረኞች እንደሆኑ ያሳያል።

"አጨብጭቡ፣ እልል በሉ፣ ጣል ጣል አድርጉ፣ የድንጋይ ሕንጻ ገንቁ፣ የአእላፍ ዝማሬ አቅርቡ፣ ወዘቸ" እያሉ እልቂቱን ለማስቀረት ሳይሆን አዘናግተው ለማስቀጠል በቅጠረኝነት የሚያገለግሉትን እግዚአብሔር ይበቀላቸዋል።

እንኳን አባት: መምህር፣ እረኛ ተብለው ተሰይመው የሕዝብን እልቂት እያዩ ዝም ማለት፤ በዚያም ላይ በማዘናጋት ቀርቶ የግለሰብን መጥፋት እየተመለከተ በዝምታ የሚያልፈው ምእመን እግዚአብሔር ይቀጣዋል።

እግዚአብሔ በራሱ በሕቅኤል አንደበት እንዲ ብሏል፦
"3:18  እኔ ኃጢአተኛውን፦ በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ፥ አንተም ባታስጠነቅቀው ነፍሱም እንድትድን ከክፉ መንገዱ ይመለስ ዘንድ ለኃጢአተኛው አስጠንቅቀህ ባትነግረው፥ ያ ኃጢአተኛ በኃጢአት ይሞታል፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
3:20  ደግሞ ጻድቁ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱም ዕንቅፋትን ሳደርግ፥ እርሱ ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል ያደረጋትም ጽድቅ ነገር አትታሰብለትም፤ ደሙን ግን ከእጅህእፈልጋለሁ።
33:8  ኃጢአተኛውን፦ ኃጢአተኛ ሆይ፥ በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ፥ ኃጢአተኛውን ከመንገዱ ታስጠነቅቅ ዘንድ ባትናገር ያ ኃጢአተኛ በኃጢአቱ ይሞታል፥ ደሙን ግን ከእጅህእፈልጋለሁ።"

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

14 Nov, 23:10


https://www.youtube.com/live/LhxFeuvTqMo?si=ikF9vfw_SzNcfopp

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

14 Nov, 19:26


በዚህ አይነት ደንቆሮ ለመመራት መፍቅድልችን የውድቀታችንን ደረጃ ጥልቀት ያሳያል:: ከሁሉም በላይ ክርስቶስን የዘነጉ ድንዙዛን ጳጳሳት ቤታችንን መሙላታቸውን በደማቁ ይምሰክራል:: እነ "አንገቴን ሰጣለሁ" እና "ችግር የለም እንጂ አትገዙ ማለት እንችላለን" በዚህ ንግግር አለመቆጣታቸው ምን ያህል የሐሰት እረኞች እንደሆኑ ያሳያል

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

14 Nov, 19:07


https://t.me/Defend_Orthodoxy_EOTC_Discussion

እዚህ ላይ መረጃ ይልጥፉ:
ካልሆነ [email protected] ይጠቀሙ

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

14 Nov, 19:02


https://www.bbc.com/amharic/articles/c5y3l8vkldlo

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

14 Nov, 18:58


“. . . ግድያው “በሦስት ዓይነት መልክ” እንደተፈጸመ ተናግረው፤ ቤት ለቤት እና መንገድ ላይ ከተገደሉት በተጨማሪ አዝመራቸው ውስጥ የተገደሉ አርሶ አደሮችም እንዳሉ አመልክተዋል።”
https://www.bbc.com/amharic/articles/czd5yz0pq39o
“ሻይ ቤት ተሰብስበው የነበሩ ሰዎችን በር ከፍተው አውጥተው ረሽነዋል። መንገድ ላይ ያገኙትን ረሽነዋል። መኖሪያ ቤትም ተከትለው ገብተው በር ከፍተው ጊቢ ውስጥ ያገኙትን ገድለዋል” ሲሉ ስለ ግድያው ተናግረዋል።
ሌላ የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነ የሰፈሩ ልጅ እንዲሁ “ቀለብ ለመውሰድ ወደ ቤተሰብ ሲመጣ” በመንግሥት በተመሳሳይ ሁኔታ መገደሉንም ተናግረዋል።
“የባጃጅ ሠራተኛ [ሹፌር] የነበረ፣ አንደኛው አረቂ የሚሸጥ፣ ተማሪ፣ አንዱ ሱቅ የከፈተ ነጋዴ” ከተገደሉት ውስጥ እንደሚገኙበት አንድ ነዋሪ አመልክተዋል።
“አብዛኞቹ [ሟቾች] ምንም የማያውቁ፣ የፖለቲካ ግንዛቤ የሌላቸው፣ ለፍተው የሚድሩ፣ የቀን ሥራ የሚሠሩ ናቸው” ያሉ ሌላ ነዋሪ ደግሞ ግድያውን “የሚያሳዝን” ብለውታል።
“ልጅ ያለው ነው ይሄን ሊረዳው የሚችለው። አልፎም ደግሞ የመጀመሪያ ልጅ። ሳይታሰብ፤ ሳይታለም. . .” በማለት ስለተጠማቸው ሐዘን የቤተሰብ አባላቸው የተገደለባቸው ነዋሪ ለቢቢሲ እንባ እየተናነቃቸው ተናግረዋል።
“. . . ህጻናት እና ወጣቶች ናቸው” ሲሉ የሰለባዎቹን የዕድሜ ክልል የገለጹ ነዋሪው፤ አንድ የ11 ዓመት ታዳጊ ልጅ ከሟቾች ውስጥ እንደሚገኝበት ተናግረዋል።
“ከፋኖ ኃይል ጋር ተኩስ ሲለዋወጡ፤ ሕዝቡን መጥተው ይመታሉ። ለእኛ ሊገባን ያልቻለው ይሄ ነው። ሕዝቡ የራሱን ኑሮ ነው የሚኖረው። የገጠማቸው ኃይል አለ፤ ለእርሱ ማወራረጃ የሚያደርጉት ሕዝቡን ነው” ሲሉ አንድ ነዋሪ በምሬት ተናግረዋል።
በአዲስ ቅዳም ከተማ የመንግሥት ኃይሎች እንደዚህ ዓይነት ጥቃት ሲፈጽሙ ይህ የመጀመሪያው እንዳልሆነ የተናገሩት ነዋሪዎች፤ ባለፈው ዓመት በፋሲካ በዓል ማግስት ከ11 እስከ 15 የተገመቱ ሰዎች “በዓል እያከበሩ እያለ” ተገድለዋል ብለዋል።
“ያገኙትን ወጣት በለው፣ ድፋው፣ አስተኛው እያሉ ነው [የገደሏቸው]። ህጻናት ናቸው፤ የ18 ዓመት፣ የ20 ዓመት የሚሆኑ ወጣቶች ናቸው። በአጋጣሚ ተኩሱ ያባራ መስሏቸው ወደ ውጭ የወጡትን አስፓልት ላይ እንዲሁም ቤት ገብተው መቷቸው” ብለዋል።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

14 Nov, 01:35


ተበታትኖ ማልቀስ፥ በተቃራኒው ሚሊዮኖች ነን ብሎ መፎክር ጥቅም የለዉም። ጥቂት የተደራጁ የአገርና የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ለ50 ዓመታት አስለቀሱን፥ አጠፉን፥ አዋረዱን፥ አገር አልባ አደረጉን፥ በጅምላ እየፈጁ ቀበሩን፥ አፈናቀሉን፥ ቤተ ክርስቲያናች በዘር መነኮሳት አድመኞችና ቀበኞች እንድተመራ አደረጉ። ብዙኃኑ ባለመደማመጡና የበኩሉን መልካም ባለማድረጉ ምክንያት ብዙኃን ሳለን እንደ አናሳ ማልቀሱን ቀጥለናል።

በቤተ ክርስቲያን፥ በቤተ መንግሥት፥ በዲፕሎማሲ፥ በሁሉም የሕይወት ዘርፎች ስለማንደማመጥና ስለማንተባበር በጠላቶቻችን ተወክለን እየተመራን እንገኛለን። ለዚህ ጠንካራ ምስክሬ በዚህ ፎርም መሠረት በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ እየመዘገብን እንድንልክ ጥሪ አድርገን በሚገርም ሁኔታ አንድም ሰው ምላሽ አልሰጠም።

በየ ቲክ ቶኩና ዩ ቲዩብ ላይ የወገደኑን እልቂት እያየ የሻማ ምስል የሚለጥፍ ግን በሺዎች ይቆጠራል። ዋጋ ቢሰ ጥረት ነው።
መፍትሔ በሚሆን ጥረት ላይ እንተባበር!!!

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

14 Nov, 01:35


እያንዳንዱ ክርስቲያን (መጻፍ የማይችል አፅፎ) በዙሪያ የሚደረገውን ማንኛውንም መዋቅራዊና ሥርዓታዊ መዋቅር በተመለከተው ቅፅ መሠረት እየሞላ በአቅራቢያው ወደሚገኝ የሞዐ ግብረ ኃይል አባል ወይንም በኢንተርኔት ማስፈንጠሪያው ላይ በማስቀመጥ ግዴታውን ይወጣ። https://moaorthodox.com/home/report
እስከአሁን መረጃውን በጥራት ሰብስባችሁ ለምትልኩ ሁሉ የግፉአን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ዋጋችሁን ይክፈላችሁ።
ይህንን የመረጃ መላኪያ መንገድ ለክርስቲያኖች ሁሉ በማጋራት ይተባበሩ።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

13 Nov, 23:08


Enat Party condemns massacre in East Shoa : 38 burned to death locked in their house. Read more
https://borkena.com/2024/11/02/enat-party-condemns-massacre-in-east-shoa-38-burned-to-death-locked-in-their-house/ @zborkena #Ethiopia #News #humanrights 

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

10 Nov, 12:00


የብልጽግና የባህልና ማንነት አፓርታይድ! ኦርቶዶክስ ጠልናትና ፍጅ*ትን ከስውር ሴራነት ወደ ግልጽ ፖሊሲነት ያወጣው...
https://youtube.com/live/tkm9iCzZGfA?si=fqXEOThFcv6tbBnu

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

09 Nov, 02:05


አማራን የማምከን ሤራ https://youtu.be/-TJKyNVAAqw?si=c5r9HE-isfPdb9i-

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

09 Nov, 01:17


በህግ አምላክ! ክርስትናና እስልምና ምን ጠቀመን?
ያሬድ ኃይለመስቀል
[email protected]
የኢትዮጵያ ታሪክ ከክርስትና; ከእስልም እና ይሁዳዊነት (Judaism) እምነትቶች ውጪ ማሰብ አይቻልም? ማሰብ ይቻላል የሚል ካለ ቢያስተምሩን በጎ ነው።
የኢትዮጵያ እምነቶች ጥቅማቸው በጣም ብዙ ነው፤ አንድ መጽሀፍም አይበቃውም፤ ለቅምሻ ያህል የኢትዮጵያ እምነቶች ለነጻነት፤ ለፍትህ፤ ለትምህርት፤ ለብልጽግና፤ ለስነ ህንጻ፤ ለህክምና፤ ለሰላም፤ ለታሪክ፤ ለስነ ጥበብ፤ ስነ እጽዋት፤ ስነ ፍጥረት፤ ስነ ከዋክብት፤ ስነ ቀመር፤ ስነ ፍልስፍና፤ ስነ ምግባር ያበረከቱትን በአጭር በአጭር እንይ።
መጽሀፍ ለሚያነብቡ ስዎች መቼም ሀገርን ከተቋም ውጪ ማሰብ እንደ ትልቅ ደፋርነት እንጂ እንደ እውቀት አያዮትም። የኢትዮጵያ እምነቶች ቤተ እምነት ብቻ ሳይሆኑ ተቋማትም ነበሩ።
1. ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለሺ አመታት ብትኖርም እስከ መስከረም 14 1900 ድረስ የመከላከያ ሚኒስቴር አልነበራትም ግን ለሺ አመታት እራሷን ተከላክላ ቆይታለች። ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ የመጀመሪያው የጦር ሚኒስቴር ነበሩ።
2. እስከ 1930ዎቹ ድረስ ኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር አልነበራትም ይሁንና ትምህርት ለሺ አመታት ነበራት። ማን አስተማረ?
3. ኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር እስከ 1930ዎቹ አልነበራትም ይሁንና እንደ “የህዳር ወረርሽን” (Spanish flue) ያለውን ተከላክላለች። ማን ተከላከለ?
4. መዘጋጃ ቤት እስከ ቅርብ ግዜ አልነበራትም ይሁንና ሰው ይወለዳል፤ ያድጋል፤ ሰው ሲሞት በስርአት ይቀበራል። ማን ይቀብራል?
5. መአከላዊ ፍርድ ቤት እስከ 1950ዎቹ አልነበራትም ይሁንና ወንጀለኛ የሚተዳደር ሀገር አልነበረችም። ማን ነበር ፍርድ የሚሰጠው?
6. የአራዳ ፓሊስ በአጼ ሚኒሊክ ቢቋቋምም መሀበረሰቡ ለሺ ዘመን “ፍትህና ወንጀል፤ ትክክልና ስህተት፡ መጥፎና ጥሩን” የሚመዝንበትና የሚፈርድበት የሀይማኖት ህግጋት ነበሩት።
7. ኢትዮጵያ ቤተ መዘክር እና መዝገብ ቤት በአጼ ኃይለስላሴ ግዜ ነው ተመሰረተ ይሁንና መዛግብቶች ለሺ አመታት ጠብቀው ያቆዮ ተቋማት ነበሯት። ማን ጠበቀ?
እነዚህ ሁሉ ተግባራትን የሚያከናውኑት ተቋማት እነማን ነበሩ። ቤተ እምነቶች አልነበሩም። በተለይ የኦርቶዶክስ ሁለቱ የተወቀሱት ቤተ ክርስቲያንና የእስልምና እምነቶች አይደሉም ይሄንን ተሸክመው የኖሩት። ወደ ዝርዝሩ እንግባ።
1ኛ ነጻነት

ለምሳሌ Why Nations Fail በሚለው የ Daron Acemoglu and James A. Robinson መጽሀፍ ገለጥ ብናደርግ “ተቋም” ለአንድ ሀገር በነጻነት ለመኖር ብቸኛ መመዘኛ አድርገው ጽፈዋል። ለምሳሌ እነዚህ ጸሀፊዎች ኢትዮጵያንና ሱማልያን ያነጻጽሩና በሱማልያ ውስጥ ተቋማት ተገንብተው ስላልነበረ አስተባብሮ ቅኝ ገዢዎችን መከላከል የሚችል ተቋም አልተፈጠረም ነበር ይላሉ። “The absence of cohesive and inclusive institutions made it easier for these colonial powers to exert their influence and impose their rule”። ይህ እንግዲህ በመላው አፍሪካ ታይቷል። ተቋም ያላቸው እንደ ዙሉ ንጉስ ያሉ ቢያንስ ቢያንስ ተዋግተው ተሸንፈው ነው የተገዙት። ብዙዎቹ ግን ምንም ሀይማኖታዊም ሆነ አለማዊ ተቋማት በግዜው ስላልነበራቸው አስተባብሮ ነጻነታቸውን ማስጠበቅ አልቻሉም።
በኔ እይታ ኢትዮጵያ አምስት ተቋማት ነበሩዋት። አንደኛ ንጉስ፤ ሁለተኛ የክርስትና ቤተእምነት፤ ሶስተኛ የእስልምና ቤተእምነት፤ አራተኛ የይሁዳዊነት ቤተእምነት፤ አምስተኛ ገበያ ናቸው።
እነዚህ አምስት ተቋማት ናቸውን የኢትዮጵያን ነጻነት ያስጠበቁት። እነዚህ ተቋማት ባይኖሩ ህዝቡ ሀገሩ እንደተወረረ እንኳን የሚሰማበት እድል አልነበረውም። መረብ ምላሽ ላይ ጠላት ሲያርፍ ኢሊባቡር ባሌ ኦጋዴን የሚሰማው በቴሌቭዥን ወይንም በቲዊተር አይደለም። ከዋናው ፓትሪያርክ እስከ አጥቢያ ድረስ ሰንሰለት ያለው እዝ ያለው ተቋም ነበር። በእስልምናም ከዋናው ኢማም እስከ አንድ አጥቢያ ትምህርት ቤት ድረስ የተሳሰረ ተቋም ነበር። ንጉሶቹና ተጓዥ ንጉስ ስለነበሩ ቋሚ ቤተመንግስትም፤ ሞባዬል ስልክም የፓስታ ሳጥን ቁጥርም አልነበራቸውም። ንጉስ ኖረም አልኖረም መስጊስና ቤተ ክርስቲያን ሁሉም ቦታ አለ። ለጅ ሲወለድ ክርስቲያኑ ያጠምቃል፤ እስላሙ መርቆ ቆጥሮ ልጁን ይንከባከባል፣ ፊደል ስላለው ያስተምራል፤ ሲሞት ደግሞ ቆጥሮ ለይቶ ይቀብራል እንጂ ለጂብ አይተወውም። ሀገር ሲወረር ጠላት ሲመጣ በቲዊተር ወይንም በቴሌቭዥን አልነበረም መለክት የሚነገረው። ነጋሪት ተጎስሞ ተዘጋጅ ታጠቅ ዝመት የሚባለው በቤተ እምነቶች ከዛም በገበያ ነበር። በነጻነት መኖርን ጥቅሙ ካልገባን በስተቀር ታድያ የኢትዮጵያ ክርስትናና እስልምና ለኢትዮጵያ ምን አበረከቱ ብሎ ማቃለል በዘንድሮ ወጣቶች እባባል “አረ ሼም ነው” ያስብላል። ለሺ አመታት የብልጽና ወይ የኢህአዴግ መዋቅርና ካድሬ ይሆን ተቋም ሆኖ ሀገር ያስጠበቀው?
2ኛ የትምህርት ሚኒስቴር

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

09 Nov, 01:17


ሰው መቼም ጤነኛ አይምሮ ያለው ትምህርት ቤት መሰልጠን አይደለም ብሎ የሚያስብ ያለ አይመስለኝም።
ኢትዮጵያ እስከ 1940ዎቹ ድረስ የትምህርት ሚኒስቴር አልነበራትም ግን ትምህርት ቤቶች ነበሩዋት፣ ብልጽግና ቀረጥ ሰብስቦ ትምህርት ቤት ከፍቶ አይደለም ትምህርት ያስጀመረው።
ኢትዮጵያ እንደውም በአለም ላይ ትልቁ የጽሁፍ ክምችት ያላት ሀገር ናት። በወሎ፤ በጎንደር እና በሀረር ያለውን የእስልምና መጽሐፍት ሳይቆጠሩ በኦርቶዶክስ ቤተ እምነትዎች ውስጥ ብቻ ከ300 ሺ በላይ በብራና የተጻፏ መጽሀፍት አሏት። እኔ አይደለሁም ይሄንን የምለው፤ ጥናት ያሳተሙት ፕሮፌሰት ሪቻርድ ፓንክረስት ናቸው። ሶስት መቶ ሺ ምናላት የሚሉ የብልጽግና ካድሬ ካለ በንጽጽር እንየው። ፕሮፌሰር ሪቻርድ ይህ 300ሺ ከኢሮፕያውያን ጋር ሲወዳደረው ኢሮፓውያን የዚህን 10 በመቶ ማለትም 30ሺ አልጻፏም ይላሉ።
እነዚህ የብራና ጽሁፎች የጽሎት ብቻ አይደሉም። የሀይማኖት (Theology) ፤ የታሪክ (History)፤ ገድል (Biography (እስቲ አስቡት የ12 ደቀ መዝሙሮች ከውልደት እስከ ሞት ተርጉሞ ጠርዞ ያስቀመጠ ሀገር አለ?); ስነ እጽዋት (Botany)፡ ስነ ከዋክብት (Astronomy): ስነ ህክምና (medicine)፡ ስነ ቀመር (Binary mathematics): ፍልስፍና (philosophy)፡ ስዕል (Painting)፤ እደ ጥበብ (Arts and Crafts): ቀለምና ማዘጋጀት (Chemistry): ሙዚቃ (Music)፡ መድሀኒት መቀመም (pharmacology) ውዝዋዜ (choreography)፡ ስነጽሁድ (Literature): ኮኮብ ቆጠራ (numerology)፡ አርምሞ (meditation); ቋንቋ (ግዕዝ አረብኛ፤ ግሪክ፤ ላቲን) (Languge)፤ ትርጉም (transilation) ወዘተ።
እነዚህ እውቀቶች ትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን ልዮ መሰልጠኛዎች ነበሯቸው (Sub specialization)። ዜማ የሚማርና ትርጉም የሚማር በአንድ ትምህርት ቤት አይደለም። በዘመኑ የታወቁ እንደ አሁኑ ፕሮፌሰቶች በአንድ ነገር ላይ ጥልቅ እውቀት ያላቸው ሰዎች ያሉበት (Specialization) ትምህርት ቤቶች ነበሩ። በዛ ዘመን እንደ አሁኑ በ C ወይንም በ 50% ማለፍ የለም። አንድ ልጅ ሀሁን ሙሉ በሙሉ ሳያውቅ ግማሹን አውቋል ተብሎ አቡጊዳ አይሰጠውም። እንግዲስ እንዲህ ጽድት ያለ የትምህርት ስርአት የነበረው ሀገር በትምህርት ሚኒስቴር ወይስ በነጻ የሚያስተምሩ ቤተ እምነቶች። ይህ እውቀት በነጻ በእስልምና እና በክርስትና ቤተ እምነቶች አይደለም። ታድያ በምን መመዘኛ ነው ይሄንን የዕውቀት ማመንጫ የነበሩ ተቋማት በምን ብቃት ነው ለማቃለል የምንሞክረው። አረ በህግ አምላክ?
እነዚህ የዚህ እውቀት ባለቤቶችስ በአለም ላይ ተፎካካሪ እንደነበሩ እስቲ ሁለት ሰዎችን እንይ። አንደኛው አባ ተስፋጽዮን ይባላሉ። ሁለተኛው ዲያቆን ሚካኤል ይባላል። አባ ተስፋጽዮን ደብረ ሊባኖስ በግራኝ መሀመድ ሲፈርስ ተሰደው ወደ ሮም የሄዱ ምሁር ናቸው። እኛ እምነት ምን ሰራልን ስንል የካንብሪጅ (Cambridge) ዮኒቨርስቲ ደግሞ የኢትዮጵያ መንኩሴና ዲያቆን እንዴት በኢሮፕ እምነት ላይ ተጽዕኖ እንዳሳረፏ መጽሀፍ ጽፈው ኣንድ ወር ቦሀላ ገበያ ላይ ይውላል። የመጽሀፏ አጭር መግለጫ በእንግሊዘኛ እንዲህ ይላል።
This Element examines the life and legacy of the sixteenth century Ethiopian intellectual Täsfa Ṣeyon. It reconstructs his formative years in the the Horn of Africa and his diasporic life in the Holy Land and Italian peninsula, where he emerged as a prominent intermediary figure at Santo Stefano degli Abissini, an Ethiopian monastery within the Vatican. He became a librarian, copyist, teacher, translator, author, and community leader, as well as a prominent advisor to European humanist scholars and Tridentine Church authorities concerned with the emerging field of philologia sacra as it pertained to Ethiopian Orthodox (täwahedo) Christianity. We reconstruct his wide-ranging contacts with the Roman Curia and emerging orientalist academy, and then scrutinize his editio princeps of the Ge'ez Gospels. A final section traces his modern influence, erasure, and rediscovery by later generations of Western orientalists, Ethiopian writers, and Catholic thinkers.
አንድ ከደብረሊባኖስ ወደ እስራኤል ከዛ ወደ ቫቲካን የሄዱት አባ ተስፋጽዮን የፈርንጅ ትምህርት ሳይማሩ የኢሮፕ Humanist Scholar መስራች እንደሆኑና እንዴት ኢሮፕን እንደቀየሩ ይናገራል። መጽሀፏ በDec 12, 2024 ስለሚወጣ ግዙት።
https://www.cambridge.org/core/elements/abs/many-lives-of-tasfa-soeyon/E18E06F8FB5C91EDEF4286FBD448F1D8

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

09 Nov, 01:17


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት በካቶሊክ እምነት ላይ ያሳረፈችውን ተጸኖና እንዲሁም በማርቲን ሉተር ተሀድሶ ንቅናቄ ላይ ተጸኖ እንደነበራት Ian Campbell, Holy War: The Untold Story of Catholic Italy’s Crusade Against the Ethiopian OrthoDdox Church ብሎ ባሳተመው መጽሀፍ ውስጥ አባ ተስፋጽዮን በካቶሊክ እምነት ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ እንዳሳደሩና የካቶሊክም እምነት ከኢትዮጵያ 81 መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን 73ቱን እንዲቀበል እንደረጉ ያመላክታል። ይህም በThe Council of Trent in 1546 በሚባለው ላይ 73 መጽሐፍት ተቀባይነት እንዳገኝ ተገልጻል።
የማርቲል ሉተርን 1517 ተቃውሞ ተከትሎ አባ ተስፋጽዮን ለካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋነኛ መከላከያ መሳርያ ሆነው ነበር ብሎ ኢአን ካምፔል ጽፏል (“he saw Ethiopianist scholarship as a useful intellectual weapon in the unfolding politico-relgious showdown with the Protestants) ። ይህ የካቶሊክና የኦርቶዶክስ መቀራረብ ወዲያው ፓርቹጋሎቹ መጥተው ንጉሱን ወደ ካቶሊክ ስለቀየሩት ልዮነቱ በጦርነት ሻከረ እንጂ በዛው ቢቀጥል ኖሮ ምናልባትም ካቶሊክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ላይ ከሚኖረው ተጽዕኖ በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት በካቶሊክ እምነት ላይ ከፍ ያለ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችል ነበር። (ይህ Ian Campbell መጽሀፍ Hilton Hotel አለ ገዝታችሁ አንብቡት በጣም የማናውቃቸው ታሪኮች አሉት)።
በሌላ በኩል ደግሞ ማርቲል ሉተት ኢትዮጵያዊውን ዲያቆን ሚካኤል የሚባልን በ1534 በዊተንበርግ ጀርመን ተነጋግረው ማርቲን ሉተር የሱ ተቃውሞ በመጀመሪያይቱ የክርስቲያን ቤተ እምነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ አስተምህሮ የታገዘና ያደረገውም ትክክል እንደሆነ ጽፏል።
Martin Luther’s Fascination with Ethiopian Christianity፡ https://www.christiancentury.org/blog-post/guest-post/martin-luthers-fascination-ethiopian-christianity

ከዲያቆን ሚካኤል ጋር ከተገናኘ ቦሀላ ማርቲን ሉተር ይሄንን ጽፋል “Ethiopian Christians practiced elements of the faith absent in Roman Catholicism, elements Protestants would later adopt: both bread and wine at Communion, vernacular Scriptures and married clergy. Absent from Ethiopian Christianity were practices Protestants would dismiss: the primacy of the Roman pope, indulgences, purgatory, and marriage as a sacrament. Luther’s theological fascination with the Ethiopian Church was illuminated in 1534 in his face-to-face dialogue with an Ethiopian cleric, Michael the Deacon, in which Luther tested out his theological portrait of the Ethiopian Church.
Recalling the dialogue with Michael the Deacon, Luther later stated: “We have also learned from him, that the rite which we observe in the use of administration of the Lord’s Supper and the Mass, agrees with the Eastern Church. … For this reason we ask that good people would demonstrate Christian love also to this (Ethiopian) visitor.”
እንግዲህ እነዚህ ሁለት ሰዎች እንደ አጋጣሚ ከሀገራቸው ወጥተው ሀሳባቸውን በመግለጻቸው ፈረንጆቹ ከአምስት መቶ አመት ቦሀላ እየቆፈሩ እያወጡ እንዴት በኢሮፕ ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደሩ መጽሀፍ እየጻፏ ነው። እና ሀገር ደግሞ ክርስትናና እስልምና ምን ጠቀሙን የሚሉ ድፍረቶች ተነስተዋል።
የአፍሪካ ህዝብ በ1800 ዓመተ ምህረት 85 ሚሊዮን ይገመት ነበር። ከዛ ውስጥ 12 ሚሊዮኑ ታፍኖ ተወስዶ በአሜሪካ ባርያ ተደርጓል። እኛ ለምን እንደ ምዕራብ አፍሪካው በቀላሉ አልተጫንም ካልን ተቋማት ነበሩን። አስባስበው የሚያዋጉን። እነሱም ዋነኞቹ ቤተ እምነቶች ነበሩ።
በክፍል ሁለት የኢትዮጵያ እምነቶች እንዴት የፍትህ፤ የጤና፤ የመሀበራዊ ጉዳይ እና የበርካታ ሚኒስቴሮች ተቋማት ሆነው እንደሰሩ ያሳያል።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

03 Nov, 10:37


https://www.youtube.com/live/LXND-yjyqgQ?si=WYDr_5BqR-cXyBha

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

03 Nov, 05:50


ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 9: 39-39 -41 ጌታችን እንዲህ አለ፦

"39 ኢየሱስም፦ የማያዩ እንዲያዩ የሚያዩም እንዲታወሩ እኔ ወደዚህ ዓለም ለፍርድ መጣሁ አለ።

40  ከፈሪሳውያንም ከእርሱ ጋር የነበሩት ይህን ሰምተው፦ እኛ ደግሞ ዕውሮች ነንን? አሉት።
41  ኢየሱስም አላቸው፦ ዕውሮችስ ብትሆኑ ኃጢአት ባልሆነባችሁም ነበር፤ አሁን ግን፦ እናያለን ትላላችሁ፤ ኃጢአታችሁ ይኖራል።"

እንግዲህ ሊቃውንት ነን፣ አባቶች ነን፣ መምህራን ነን፣ የአገር መሪዎች ነን፣ ነጻ አውጭዎች ነን ወዘተ እያሉ ነፍሳትን ወደ ሲዖል፣ ዜጎችን ወደ እልቂት እየመሩ የሚገኙት ዕውራን እናያለን ስለሚሉ ስሕተታቸውን ለማረም፣ ኃጢአተቸውን ለመተው፣ ዕውርነታቸውን ለመታከም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ተገኝተዋል።

ምእመናን ክርስቶሳውያን፣ አእምሮ ሰብእ ያላቸውና ሃይማኖት ባይኖራቸው ስንኳ በሕገ ተፈጥሮ የጸኑ ሰዎች ራሳቸውንና አገራቸውን የማዳን ከፍተኛ ኃላፊነት ወድቆባቸዋል።

ቅዱሳት መጽሐፍትን ማንበብ፣ የቅዱሳንን የቅድስና ሕይወት ማጥናት፣ የተመሰገኑ ነገሥታት አመራርና አስተዳደርን ማጥናት፣ ቅዱስ ትውፊትንና ታሪክን እያጠኑ መመራራት። አባቶችና መሪዎች በተጠሩበት ልክ የተገኙትን ፈልጎ አብሮ መተባበር። መደራጀትና ለሕዝብና አገር ለህልውና መጋደል።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

02 Nov, 10:57


በእንደዚህ አይነት ፕሮፓጋንዳ ቀመስ የሤረኞች ስልት አትታለሉ!!!‼️


እንዲህ አይነት ዜናዎችን ስሰማ አእምሮዬ በሚከተሉት መንገድ መሥራት ይጀምራል፦
1) የአደጋው ሰለባን ሰው ህመም ሰውነቴ ይጋረዋል። በእርሱና በቤተሰቦቹ ቦታ ሆኜ ስሜቱን እካፈላለሁ። አንዴንዴ በለቅሶ ፈነዳለሁ
2) ይህን ግፍ በቀጥታ የፈጸመ ወታደርን ከንቱነትና ህሊና ባስነት፣ እርሱን ያዘዘ የሀገር መሪን እረግማለሁ፣ ፍትሕ እንድታገኘው ጸልያለሁ
3) የዘር ሥርዓት ዘርግቶ ለዚህ መከራ የዳረገንን ወያኔንና ጭፍን ተከታዮቹን እረግማለሁ። ፍትሕ እንድታገኛቸው ጸልያለሁ
4) የመከራውን መነሻና ዋና መንስዔ ወያኔን ደብቀው አሁን የሚሆነው ብቻ ዜና በማድረግ ከመፍትሔ የሚያርቁንን የፕሮፓጋንዳ ሚዳያዎች ክፋት አስባለሁ። ሕዝቡ የክፋት ምንጩን ከማሰብና መፍትሔ ከመስጠት በውጤቱ ላይ አተኩሮ አዳዲስ ጠላት እየፈጠረ መከራውን እንዳያራዝመው ዓይነ ልቦናው እንዲገለጥ እጸልያለሁ።

በዚህ ዜና ተጠያቂው ትግራይን አገር ከደርጋለሁ ብሎ ለሁላችንም መከራ የቀፈቀፈ የአብይ አህመድ ወላጅ አባት ወያኔ እና ኦነግ ላይ ማተኮር የመፍትሔ መንገድ እንደሆነ በቀጥታ እናገራለሁ።

በሤረኛው ወያኔና ኦነግ የተፈጠረውን ሥርዓት፣ አስተሳሰብ፣ ሕገ አራዊት/መንግሥት፣ የዘር ክልል በመደምሰስ ፍትሕ የሚበየንበት፣ ሰው ከዘረኛ ነጻ አውጭ ነን ባይ አራዊቶች የሚገላልበትን ቀን ለማቅረብ መሥራት። ጎኖ ለጎን በሂደቱ የፈረሱ ቤተሰቦች፣ አካላቸው የጎደለ ወገኖችን ከጎሠኝነት ነጻ ሆኖ በመርዳት ሰብአዊነት ምን ማለት እንደሆነ ለእነዚህ የዘር አረመኔዎች ማሳየት።

👇👇👇👇👇
#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
“ከትምህርት ቤት ስመለስ እግሬን በፍንዳታ አጣሁ” የትግራዩ ታዳጊ
በትግራይ ገጠራማ መንደር ነዋሪ የሆነው ብርሃነ ሐይሌ ከትምህርት ቤት ሲመለስ አንዲት ቅጽበት መላ ህይወቱን ላይመለስ ቀየረችው።የ16 ዓመቱ ታዳጊ የተረገጠው መሬት ላይ የተረገጠው መሳሪያ ፈንድቶ ግራ እግሩን መታው።ስጋና አጥንቱ ተለያይቶ በደም አበላ ተጥለቀለቀ። ከፍተኛ ህመም ሰቅዞ ያዘው።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

02 Nov, 09:46


https://vm.tiktok.com/ZMhCqHmyM/

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

02 Nov, 09:46


👆👆👆👆
የብልጽግና ፖለቲካና የአብይ አህመድ አስተዳደር ተግባራዊ መገለጫ ይህ ነው።

የሚገርመው ይህ ሥርዓት እንደማውገዝ ትዕዛዝ እየተቀበለና ቀኖና ሐዋርያትን እየቀየረ ዘረኝነትን የሚያጸኑ ተጨማሪ ጳጳሳት የሚያመር ቅዱስ የሚባልና ተቃራኒውን የሚሠራ ሲኖዶስ በቅዶስት ሐዋርያዊትና ኲላዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መፈጠሩ ነው።

ተነስተን ለመፍትሔው እንሥራ!!!

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

01 Nov, 15:19


ውጭ የሚኖሩ ወገኖቻችን መሥራት የሚገባቸው እንዲህ አይነት ወነጀለኞችን የሚያጋልጥና ወዳጅ የሚያሳጣ ሥራ ነው። አርስ በርስ መወቃቀስና ጊዜ ማጥፋት ሳይሆን ተቻችሎ፥ ተደማምጦ፥ ተከባብሮ የህልውና አደጋ የተደቀነበትን ሕዝብና ሃይማኖት ማዳን ቅድሚያ መስጠት በፈጣሪም የተወደደ ነው

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

01 Nov, 12:24


የክርስቲያኖች ውይይት ግቡ በተሰቀለው በጌታችን አካልነት ላይ ብልት ሆኖ ለመዋሐድ ነው! (ፋንታሁን ዋቄ/ Fan...
https://youtube.com/watch?v=57yXb1Z0WGc&si=Q0TSQ2GgholLwzYD

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

30 Oct, 10:50


MK TV || ወቅታዊ ጉዳዮች || 421 አብያተ ክርስቲያናትን ያወደመው ጦርነት
https://youtube.com/watch?v=drPa6zeYucg&si=Gq2FOqDgskG_xyGJ

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

30 Oct, 07:09


Orthodoxy and Secularism
https://youtube.com/@orthodox_secular_fantahunwakie?si=Fjg2otJN9EbttgCv

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

30 Oct, 06:26


Can you add your signature? �
chng.it/PXtQ7rkm4R

ፈርሙ፣ አጋሩ!!!
የዘር ማጥፋት መንግሥታዊ  ዘመቻ ሀማጋለጥ አለማድረግ የማንችለው ትንሹ አስተዋጽኦ ይኽ ነው።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

29 Oct, 20:49


ለጳጳሳት ይህ አጀንዳ አይሆንም። ዋናው ገንዘብ ስለሆነ ሲኖዶሱ ሁለት ቀን ሙሉ አጀንዳው ገንዘብና ሠርቆ የሚያከፋፍል ሥርዓት ስለማጽናት ነው።

በነፍስ ከእምነት እየወጣ፣ በሥጋ በአብይ አህመድ እየተጨፈጨፈ  የሚያልቀው ክርስቲያን ሳይሆን የሚገዳቸው፦
1) አመቺ ሀገረ ስብከት መቀየር
2) ሕነጻ ለራሳቸው ገቢ እና መኖሪያ መገንባት
3) በአውሮፕላን አሜሪካ እየተመላለሱ ዶላር መቀፈልና የሕክምና ምርመራ ማድረግ
4) የብሔር ኮታ ለመሙላት የምንኩስና ልብስ የለበሰ ኢአማኒ ዘረኛ መልምሎ መሾም
5) የዘረፉትና ወደፊትጰየሚዘርፉበት አሠራር በሕግ ቁጥጥር እንዳይደረግበት ሌብነትን ለማስቀጠል  ሤራ መጎንጎን
6) በክርስ ፈንታ ተክተው የሚያገለግሉትን የሕወሃትና የኦነግ ኦሮሙማ ጌቶቻቸውን ካባ ማልበስና ወንጀሎቻቸውን መሸፋፈን
7) ምእመኑ አንድ ሆኖ ጠላቱ የሆነውን ይህን መንግሥት እንዳይዋጋው ብልጣብልጠ አነጋገር "ለሃይማኖቴ ሞታለሁ፣ አትገዙ ለማለት ችግሩ ገና ቀላል ነው፣ ከየተመካከርን እንፈታለን፣ በአል አደመቁልን፣ ሕግጻ ሊሸሩልን ነው።" ወዘተ እያሉ ማደንዘዝ ተግባራቸው ነው።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

28 Oct, 17:55


https://vm.tiktok.com/ZMh9WDFpU/

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

28 Oct, 17:46


4 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ገብተን እንጠናቀቅና እንወያይ። በቲክ ቶክም በዮኡ ቲዩብም እንገናኛለን https://youtube.com/live/4GYn2z1uivE?feature=share

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

27 Oct, 16:26


ሰራቄ ነፍሳት አቡነ ሕወሃት.mp4

"መፍቀሪተ እግዚአብሔር?"  ወይስ መፍቀሪት ሕወሃት?

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

27 Oct, 11:58


ሰራቄ ነፍሳት አቡነ ሕወሃት.mp4

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

26 Oct, 19:03


https://www.youtube.com/live/kO5NtvB0p3w?si=wuV2PSU84TyZwr5k

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

26 Oct, 07:50


ከእግዚአብሔር እምልኮ ወደ ጎሣ ጣዖ አጣኝነት ያሽቆለቅሉት ካህናተ-ሕወሐትን የሚከተል ሕዝብ እርጉም ጣዓት አምላኪብይሆናል::

የጥምቀትልጆች ምርጫችሁን አሳንምሩ:: ከክርስቶስ ጋር ኑሩ::

ጌታችን በማቴዎስ ወንጌል እንደተጻፈው 19:29፤ ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል።

ያለውን እናስተውል!!!

https://youtu.be/T4cvmV5xZcw?si=Fwc_jxQsEFqdAzY1

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

25 Oct, 18:59


https://youtu.be/m9Y1t6gBZqQ.

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

25 Oct, 12:26


በአንድ ቅዲስ ሲኖዶስ የሚመራ ቤተ ክርስቲያን (ሕዝቡ በእምነቱ፥ በማኅበራዊ መስተጋብሩ፥ በመንፈሳዊ ትሩፋቲ፥ አገርን ሰላም በማድረግና ኃላፊነት በውሰድ) አደገ የሚባለውን ለመበየን እነዚህ 5 መመዘኛዎች ይዘን። በአምስቲም እንዴት እየደቀቅን እንደምንገኝ እንመለክት። የሰሞኑን ሌቦችና ዘረኞች አጀንዳ የሚቀርጹለትና ብያኔውን የሚበይኑለት ሲኖዶስ ትትን አጠቃላዩን ሁኔታ እንገምግም ፡

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

25 Oct, 10:01


ሰበር የድል ዜና | ወልድያ ከተማ ፋኖ የሰራው ኦፕሬሽን | ሸዋና ጎጃም አዲስ ስትራቴጅ | Amhara Fano
https://youtube.com/watch?v=8YlHa1n5sg4&si=-hB1Y4Pd9m9-kZ-w

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

25 Oct, 04:01


ስገንዘብ ኦዲት የሚያደርገው እርኛ ይተጣሰውን ቀኖና ወደ ቦታው ለመመለስ ስለምን ዳተኛ ሆነ?

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

25 Oct, 04:01


ወርቅ በሌቦች መወሰዱ ያስለቀሳችው ስለእነዚ ነፍሳትስ ያለቅሱ ይሄን??

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

24 Oct, 10:58


EOTC TV | ዐውደ ስብከት | እውነትን ተጸየፉ
https://youtube.com/watch?v=4fiF6OEPCic&si=UIyq9TavGaKn4tR4

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

23 Oct, 18:40


https://www.youtube.com/live/vPrNhwiAho4?si=YGnIiPJ1BDd2sj3v

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

23 Oct, 06:06


"በዚህች ምድር  ጨለማውን ብርሃን : ርኩሳንን ቅዱሳን ታደርግ ዘንድ የጥምቀት ውሃን ባረክህ::
ይህችም የኃጢአት ሸለፈት ከሰው ፈጽማ የምትቆርጥ: ያረጁ ልማዶችንም የምታስወግድ ከመለኮት የሚገኝ አዲስ ልብን የምትሰጥ የመንፈስ ቅዱስ ሰይፍ እሳት ናት:: "

ይህን በጸሎቱ የተናገረው ቅዱስ ማር ኤፍሬም ሶሪያዊ ነው:: በረከቱ ትደርብን:: አሜን::

==============

እስቲ እናስብ! የተጠመቁትን በእረኝነት ለመጠበቅ የተሾሙት የዚህ ዘመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጳጳሳትና ካህናት የሚይያሳዩት ጎሠኝነት  እንኩአን ለእረኝነት ለምእመንነት ከሚያበቃ መሠርት ምን ያህል ርቀዋል?

ትግሬ : ኦሮሞ : አማራ: ቤንች ነኝ የሚል ጳጳስ ይህችን ጥምቀት ክዶ ወደ ሥጋ ዘር የተለወጠ ክሀዲ ነው ቢባል አይገልጸውም ትላላችሁ?

በጥምቀት የሚቆረጠው የኃጢአት ሸለፈትና የኖረ ልማድ ያልቀቃቸው የኢሬቻ ጳጳሳትና ካህናት የክርስቶስን ቤተመቅደስ  እንዴት ይሾሙበታል?

የጎሣ ጣዖት እጣን አጣኝ እንዴት የሲኖዶስ አጀንዳ ይቀርጻል?

ጥምቀትን ክዶ ጎሣን መንግሥተ ሰማይ አድርጎ የሚያገለግል እንዴት ብፁዕ ይባላል?
የጸሎቱን መልእክት እዚህ ተመልከቱና ፍረዱ👇👇👇

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

22 Oct, 20:26


https://youtu.be/QMlC_WffDiM?si=QuWjzMm13UZxHDvu

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

22 Oct, 17:36


https://youtu.be/Lm3G1GcYIQI

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

21 Oct, 16:57


https://youtube.com/live/vJJHgouwFW4?feature=share

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

20 Oct, 21:22


👆👆👆👆አንድን ቤተ ክርስቲያን እመራለሁ የሚል ሲኖዶስ የልጆቹን በጥይት ማለቅ: በመንግሥታዊ ዘምቻ ከእምነት መፍለስ: ቤተክርስቲያቱን ኦርቶዶክስ ያሰኘውን ቀኖና መደምሰስ አንዳው ካላደረገ ለምን ይሰበስባል?

👉🏾 ለቦታ ምደባ?
👉🏾ለደሞዝ ጭማሪ?
👉🏾 የመንግሥትን ተቀባይነት ልማጠናከር?
👉🏾 ከቤተ ክርስቲይን የተነጠለ የጵፕስናን ክብር ለማስጠበቅ?
👉🏾 ምእመናንን በማደንዘዘና ባዶ የሰላም ተስፋ በመመገብ ጥፋቱን ልማጠናከር?

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

20 Oct, 21:22


የሲኖዶስ ዋና ተግባሩ ምንድንነው?
ልጆቹን እያሳረደ: እይስመረረ: ወንቤዴና ዘረኛውን የጎሣ ፖለቲካ ሹመኛውን ሁሉ ብፁዕ እያስባለ መቀጠል እስከ መቼ?👇👇👇

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

20 Oct, 18:00


https://youtube.com/playlist?list=PL9bju67hIGKqxvW8DEqDWULoL02PJXEqP&si=1hb53LQUFEGN_M__ አሁንም ይህ ጥያቄ አልተመለሰም?

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

20 Oct, 16:50


https://youtu.be/3KnRJTHWmpw?si=5Y-nqiIMAfLUjYQS

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

20 Oct, 14:53


https://youtu.be/RcGE1d-uWhs?si=SHK-8073eNU_-Qks

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

20 Oct, 14:53


https://youtu.be/g9Lc78YZ6U4?si=oyuDdKlVHakVFvFe

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

20 Oct, 14:50


https://youtu.be/6CZ6EjVE1uo?si=nxOeMXc4Y3Ks6O8p

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

19 Oct, 20:20


https://x.com/astuka12/status/1847202912780407160?s=52&t=iXjh2MQ7cod3hrLaEcf5Aw

ሰው ነው ቤተ መንግሥት ያለው?
ይህን ንው ጳጳሳት የሚያወድሱት ሥርዓት?

ጌታ ሆይ ቶሎ ና!!!

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

19 Oct, 19:43


https://www.youtube.com/live/IXceUvnegiU?si=PNkmPKPn6c3xxVtQ

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

19 Oct, 04:34


ይህል ሊንክ ይከተሉ https://youtu.be/oMmAoH-hBN8?si=gLf-krwhPLcGfvTO
ለተፈጠረው የቴክኒክ ስህተት ይቅርታ ጠይቃለሁ

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

19 Oct, 04:33


የእኔን ኢትዮጵያ ለማግኘት እኔ በግሌ የምችለውን አደርጋለሁ። አንተስ? አንቺስ? በጋራስ ምን እናድርግ? ስመው ከሚነክሱ፥ አገር ከሚያፈርሱ፥ ከሚኣናክሱ ቁማርተኞች፥ ሕሊና ቢሶችና የድንቁርና ነገሥታት ነጻ ለመውጣት ምን እያሰብን ይሆን? https://youtu.be/oMmAoH-hBN8?si=gLf-krwhPLcGfvTO ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ክፍል 5 ለ ይቀርባል

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

19 Oct, 03:55


እንድሚታወቀው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መግላጫ በአብዛኛው ወቅቱን ያገናዘበ ቢሆንም

ቅዱስ ሲኖዶስ ዋጋ ሰጥቶ አጀንዳና እቅድ አያደርገውም::

የፖለቲካ ትእዛዛት መቀበል: ጳጳሳትን እንደ ወታደር ከቦታ ቦታ ለጥቅም ማዘዋወር: ከቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ጋር ቀጥተኛ ግኑኝነት ብሌላቸው ጉዳይ በጀት መደልደል: ዘራኛና ከሀዲ መግሥታት ሽፋን አግኝተው ምእምናንን እንዲያጠፉ በሚያስመስል ደርጃ ስለ ሰላም የይስሙላ ጥሪ በማድረግ ፕሮፓጋንዳ መሥራት: ነው::


ይህ ግምገማ ስህተት ከሆነ በዚህ ሳንት ሲኖዶሱ የሚያወጣውን አጀንዳ ከዚህ መግለጫ አንጻር በመገምገም እኔ ልቀጣ

https://www.youtube.com/live/6MjyRfdU1RQ?si=P9hTbue23B79NEoK

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

19 Oct, 03:34


One app for all your Word, Excel, PowerPoint and PDF needs. Get the Microsoft 365 app: https://aka.ms/GetM365

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

19 Oct, 03:01


እየገደሉ "የምሥራች"

የድንቁርናና ሕሊና-ቢነስት ያነገሣቸው የጎሣ ልሂቃን "የምሥራች" ትርጉም ተቀይሯል። ሕዝ ብተንቋል፥ ትውልድ ረክሷል!!

አምባገነን፥ ቁማርተኛና የወሮበሎች መንግሥት የሚመራውን ሕዝብ መከራ "የምሥራች" እያለ ያለማምደዋል። የሕወሃት/ኢሕአዴግና ብልጽግና በዚህ ሞትና መከራን ድልና እድገት አድርገው በማቅረደብ አንድ አይነት ናቸው።

ስዩም መስፍንና አሊ አብዶ የሕወሃትና የሻዕብያ የዘረፋ ሀበት ክፍፍል ግጭት በባድሜ እንደ ምክንያት ትርጉም-የለሽ ከ120 ሺህ ሕዝብ በላይ ወገን አስፈጅተው፥ ይግባኝ በሌለው የአልጀርስ ስምምነት "የምሥራች፥ እንኳን ደስ ያላችሁ" ብለው ሕዝቡን አስጨፍረዉታል።

የፈረደበትን ዐመሓራና ኦርቶዶክስ ክርስትናን በማጠፋት አጀንዳ ላይ ቢስማሙም ነገር ግን በተለመደው የሀብት፥ የብሔር ግዛት በሰስፋት፥ ዲሞግራፊ በመቀየር፥ አሰስ አገር የመፍጠር እና የበላይነት ለማስፈን ባደረጉት ግጭት ሕወሃትና ብልጽግና በየበኩላቸው ወደ ጦርነት የመሩትን ወገን ድል አግኝተናል፥ የባሰ አደጋ እንዳይመጣ አድርገናል ብለው "የምሥራች" ብለዋል።

ብልገግና የአባይ ግድብ ከደ ጋየወረደው የክረምት ጎርፍ ስለ ሞላ የምሥራች በሚ ልሕበቡን በተለይ አሰስ አበባ ውስጥ አስጨፈሩ ፥ ግን የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውለበለቡ ወጣቶችን የኦሮሙማው ፖሊስ ሠራዊት ቀጠቀጠው፤

አብይ አህመድ የአዲስ አበባ፥ የደብረ ዘይት፥ የናዝሬትና ሌሎች ከተሞች ነዋሪችን የሕዝብ አሠፋፈር ለመቀየር ኦርቶዶክስ ክርስቶያቸኖችን፥ ጉራጌዎች፥ ኮንሶዎች፥ ወላይታና ጋሞዎች ወዘተ ዒላማ ያደረገ ማፈናቀል እያካሄደ "ከተሞቻችን እያማሩ ነውና የምሥራች" ብሏል።

የአማራን ሕዝብ በምድርና በረር ኃይል ሕዓናትን፥ ካህናትን፥ ገዳማውያንን፥ ገበሬዎችን በመጨፍጨፍ ላይ የሚገኘው የአብይ አህመድ አስተዳደር "ጽንፈኛው ፋኖ እየተመታ ለስሆነ የምሥራች" የሚሉ በበሉበት የሚጮኹ ሕሊና ቢስ ሰዎችና የጎሣ አደረጃጀቶች እንዲጮኹ ታዘው እያደረጉት ነው።

የአፍሪካ አንድነ ትድርጀት የግዛት አንነድትን የሚመለከት የቻርተሩን አንቀጽ የሚጥስ የእውር ድንብር ውሳኔ በመወሰን ከሶማሌ ላንድ ጋር የቀጠናውን አጠቃላይ ሰላም ያወከ፥ ቱርክ ናግብጽን ወደ ምሥራቅ አፍሪካ በመጎተት ኢትዮጵያን ባመስከበብ አደጋ የደቀነው የአብይን እብደት "የባህር በር አገኘሁላችሁ – የምሥራች" ብሏል።

ሕዝቡ ፈዝዞና ደንዝዞ እየገደለው፥ አገሩን እያፈረሰበት፥ እያፈናቀለውና እያሳደደው "የምሥራች" እያለ ከቀሚልድበት ድንቁርናና ሕሊና-ቢስነት ካነገሣቸው የጎሣ ቁማርተኛ ልሂቃን ራሱን ነጻ ማውጣት ይኖርበታል።

አንድ ሕዝብ በመተማመን አንድ ሆኖና ጠንክሮ ከግፈኛ ሥርዓት ነጻ እንዳይወጣ እንቅፋት የሚሆኑት ጆሮ ጠቢ፥ ዘረኛ፥ ጉበኛ፥ ሳይሠራ ለመበልጸግ የሚሰለፍ፥ ባንዳ፥ ሆድ አደርና ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌላቸው አድርባዮች በመካከሉ ሲንሰራፉ ነው። እናም እነዚህ አይነት ሰዎች መራቅ ብቻ ሳይሆን በመቅጣት ራሱን እያጸዳ ሕዝቡ ለክፉ ሥርዓት መወገድ የሚቻለውን በግልና በወል ማድረግ አሁን፥ ዛሬ የሚጀመር ጉዳይ ነውና ---- ነጻ አውጭና መፍትሔ ሰጭ ከመጠበቅ ተላቅቆ ወደ ትግል ይግባ!!!
https://draft.blogger.com/blog/post/edit/2715952571427384699/3684569661507759193

አሁን ለሚካሄደው እልቂት መጋለጥ ይፈርሙ ያስፈርሙ https://chng.it/FVx7DH2gRK
*እንፈርም እናስፈርም። ማድረግ የማንችለው ትንሹ ነገር ይኽ ነው። ወገን እያለቀ መሆኑን አውቀህ/ሽ አለመፈረም ግዜ ሳይሆን የምታጣው በእልቂቱ የመስማማት ያህል በደል ነው*

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

18 Oct, 19:41


https://youtu.be/Qn9ilms_TnQ?si=SuxDldClfe7zLHUR

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

18 Oct, 12:52


አዲስ አባባ ገና ይፈርሳል!!

አትነጫነጩ ማፍረሱ ይቀጥላል። እንደ ደነገጡና እንደፈዘዙ ሳለ consistency ሊኖረው ይገባል። እነርሱ ሲባንኑ ሀገሩ ፈርሶ ፎቅ ቆሞ እነርሱ ሲደኽዩ ተለይቶ የተሸጠላቸው መኖር ይጀምራሉ። አዲስ አባባን እንቁልልጭ ማለት ነው።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

18 Oct, 08:32


https://youtu.be/xHFjvTTaI0k?si=uEtLMPN4HTDz0wsw ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ የቱንቢን ትክክለኛ የቴሌግራም ገጽ ይቀላቀሉ! ያስተዋውቁ!
https://t.me/tunbi_media
🎥💻📺🎙 YouTube በዩቲዩብ ዝግጅቶቻችንን 👁👁👂🏽👂🏽ይታደሙ!
www.youtube.com/@TunbiMedia_
በራምብል
rumble.com/c/c-3688912
በቲክቶክ
tiktok.com/@ethiotunbi

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

17 Oct, 15:46


https://youtu.be/mAo3tLmCuOE

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

16 Oct, 19:13


https://www.youtube.com/live/4upYe2px7ao?si=rajqcZr8nDDTpq6M

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

16 Oct, 15:01


ግዙፍ አካልን እንጂ የተዋሐደቸውን ነፍስ የማያውቅ፥ ከሰው ችግኝና የላስቲክ ዘንባባ የሚበልጥበት፥ ሰማእ ስለማእታየው ገነት መናፈሻ የሚመስለው፥ መንግድ አሰፋለሁ ብሎ በመንገድ የሚገለገለውን ሰው መኖሪያ የሚኣሳጣው --- በአጠቃላይ ከሰውነት የወጣውን መሪ የሚከተል፥ የሚደግፍና አብሮ የሚሠራ ሁሉ ጨለማና ብርሃንን መለየት የማይችል የደንቆሮዎች ሁሉ ደንቆሮ ነው።

ከሁሉም በላይ የአግዚአብሔር ዓይኖች፥ ብርሃን፥ ጨው፥ ባለ ሰማይ ደጅ መክፈቻ ተሸካሚ የተባሉ ጳጳሳትና መነኮሳት ይህን ጨለማ ሲደግፉ፥ መመሪኣ ሲቀበሉ፥ ልጆቻቸው እያስፈጁ ሲኣመሰግኑ --- ከድንቁርና በላይ ክፋት፥ ከክፋት በላይ ሰይጣንነት የሚጠሩበት የግብር ስማቸው ቢሆን አይመጥናቸዉም። እነዚህን አባት ብሎ የሚከተል እንደዚሁ!!🦴🦴🦴🦴

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

14 Oct, 21:37


https://youtube.com/live/ConlDSAteLY?feature=share

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

14 Oct, 14:05


ዛሬ ሰኞ ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ ክፍል 3 "የእኔ ኢትዮጵያ? የእናንተስ?" ብለን ቤኦኡ ቲዩብና በቲክቶክ ላይ እንወያያለን። ሁለቱም ሊንኮች እነሆ፦ በሚመቻችሁ ተጠቀሙ
እግዚአብሄር ለሰዓት ሁላችንንም በሰላም ያድርሰን። ለሰው ልጆች መልካም ዐሳብ መነሻ፥ ለመልካም ስነምግባር መነሳሻ ቃል እንዲወጣን እና በነፍስም በሥጋም እንድንጠቀም ይርዳን ።

ዩቲዩብ https://youtube.com/live/nbM7CaUMBJA?feature=share

ቲክቶክ ፦ https://www.tiktok.com/live/event/7425631381881323525?enter_from=share_link

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

14 Oct, 14:04


https://youtube.com/live/nbM7CaUMBJA?feature=share

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

14 Oct, 12:50


ክርስቲያኖች አብይ አህምድ ክርስቲያኖችን ከመፍጀት ጎን ለጎን ከቢልጌትስና ከዓለም ባንክ ጋር ሆነው ምን እንዳቀዱልን አስተውሉ https://www.youtube.com/live/ssO1rFXZM30?si=_u8K-hfx-WoDCieh

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

13 Oct, 20:15


https://www.youtube.com/live/Ip85tRWPm1o?si=nVonwGKpcqxNGR2_

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

13 Oct, 14:57


ድጓ እና ዲግሪ፥ ፒኤች ዲ እና ጵጵስና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለ2000 ዓመታት በባለ ድጓዎቹ፤ የገዳም ሊቃውንት ጸንታ ኖራ ዛሬ ግን በመኪናና በአውሮፕላን እየተንሸራሸሩ ለስላሳ ፍራሽ ላይ ተኝተው፥ የላመ የጣመ በልተው ዶክትሬት እና ጵጵስና ይዘው እያፈረሷት ይሆን?
ጫማ የማይጫሙት የሰበሰቡትን የክርስቶስ በጎች ባለ ፒኤቺዲ እረኞኛ መሆን አቅቷቸው በተኑት።

እነዚያ በየ ገዳሙና በየ ደብሩ እያገለገሉ ከ300ሺ መጽሐፍ በብራና ላይ ጽፈው ጠርዘው ለትውልድ አስተላፈዋል፤

እነዚህ አንብበው ተርጉመው ከመስበክ ይልቅ ቃሉን ሳይሁን ጥራዙን ለቱሪስት ገቢ አደረጉት ይሆን?

ሁሉም ከገዳም ጀምረው ነው የፈረንጅ የጨመሩበት። ታድያ ጭማሪው ዋናውን አቀጠንው ይሆን?

እነዚያ በዲግሪ ሳይሆን በቅዳሴና በመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ፤ እነሱ በቀቧቸው ነገሥታቶቻቸው እየተመሩ አለቱን እና ጫካውን ወደ ቤተ መቅደስ ቀየሩት። አሁን ጫካ መንጥረው ድንጋይ ጠርበው ሳይሆን የተሰሩት ቤተ ክርስቲያን ሲፈርሱ፡ ዙሪያው የከበበው ጫካ ሳይሆን ሰው ሲመነጠር እረኞቹ አናይም አንሰማም ዝምታ ነው መልሴ ብለዋል።

👉 👉 እነዚህ በዓት ጥለው ከተማ ከትመው ከአረማውያን ገዥዎቻችን ካባ እያለበሱ አቢያተ ክርስቲያናትን ወደ ሙዚየም እና የኢአማንያን ቱሪስት መዝናኛ አስለወጡት፤

👉 እነዚያ ዕውቀታቸው በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ነውን፤

👉 👉 እነዚህ ዕውቀታቸው ለመንሰፈስ ቅዱስ ጀርባውን የሰጠ፥ ደድ ንታሳቢ ያደረገ አእምሮአዊ ነው፤

👉 እነዚያ አሕዛብን ክርስቲያን አድርገው በክርስቶስ መስቀል አዋሐዱ፤

👉 👉 እነዚህ በጥምቀት አንድ የሆኑትን በጎሣ ተካፍለው ይበትኑታል፤

👉 እነዚያ በቅድስና ያሉትን፥ ፍቀረ ሲመት የጠፋላቸውን በልመናና በማስገደድ ለአገልግሎት የሾማሉ፤

👉 👉 እነዚህ የከተማ ጮሌና የጎሣ ተወካዮችን በኮታና በክፍያ ይሾማሉ፤

ይህን ስናይ እንዲህ መጠየቅና መራመር ይገባ ይሆን?
1. የባእዳን ድግሪና ቆብ እርስበርሱ ይቀዋወም ይሆን? ቆቡ ተንሰቶ የዲግሪ ሲጫን ወደ ቆብ መመለስ ይቻል ይሆን?

2. ቀደምት አባቶች የገነቡትን ማኅበረሰብና እምነት የሚኣፈርሱ፥ ድንበር የሚያፈልሱ አሁንም እንደእነዚኣዎቹ "አባቶች" መባል ይገባቸለል?

3. አሁን የገዳሙን ጨርሰው የፈረንጅቹን ዶክትሬው ሲጨምሩ ምርታቸው ከገዳማውያኑ ያነሰ እረኞች ሆኑ።

አሁን ይህ ሁሉ ባለ ዲግሪ ባለ ዶክትሬት ጳጳሳት ኖርዋት ለምን አንድ እረኛ የሚሆን ጳጳስ አጣች። ምናልባት መንፈስ ቅዱስና ፒኤችዲ አይጣጣሙ ይሆን?።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

12 Oct, 20:33


የብልጽግና መንግሥት የሕንጻ፥ የሣር፥ የአስፋልት፥ የመናፈሻ ልማትን በእነዚህ የልማት መመዘኛዎች አይታችሁ አስተያየት ስጡ

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

12 Oct, 18:57


https://www.youtube.com/live/8tI-onkStnU?si=PtKnn1DJUsRi82qL

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

12 Oct, 18:26


https://www.youtube.com/live/HBerkzDgFvc?si=ip-tBu_7_J_25xel

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

12 Oct, 17:25


👆 (የቀጠለ)

በዚህ ቪዲዮ የምትመለከቱት የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ መቶ ዓመታትን ሰፍረው የልጅ ልጅ ያዩ ቤሰቦች እንዲነሱ ተደርገዋል። ይህንን ከቅዱስ ፓትሪያሪኩ፥ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ አቡነ አብርሃም፥ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳሳ አቡነ ሄኖክና ሌሎቹ የሚመለከታቸው ሁሉ በአደባባይ የኮሪደር ሊማቱን እያመሰገኑ፥ አፍራሹን መንግሥት የአቤል መስዋዕት የሚያቀርብ ቅዱስ መንግሥት እያሉና ምእመናኑን በአንነድት ራሱን እንዳእከላከል በማዘናጋት፥ በመከፋፈል፥ በስብከትና በበዓል መምቀት በማደብዘዝ፥ በሞንታር ቦጩኸትና እልልታ በአርምሞና በክርስቲያናዊ ጥልቅ የማሰብ አቅም እንዳእጠቀም በጫጫታ እየተባበሩ ነው።

ምእመናን አሁንም ከጥልቅ እንቅልፍ አልነቁም። አውቃችሁ ለተኛችሁ ትሳይሆን ላልገባችሁ፥ በቤተ ክህነት ምንደኞችና በዴማሳውያን ትብብር የሚፈጸመውን የአብይን ፕሮጄክት ዓላማ በስሱ ልንገራችሁ፦

፩) "የኦርቶክስ ሃይማኖት የነፍጠኛ/አማራ ነው" በሚለው የኦነግ-ኦሮሙማ/ብልጽግና የአፓርታይድ የፖለቲካ እምነት መሠረት ኦርቶዶክስን ከወለጋ፥ ከአርሲ፥ ከሐረርጌ በአጠቃላይ ኦረሚያ ተብሎ ወደፊት ከሚመሠረተው አገር አስቀድሞ ኦርቶዶክስ ክርስቲያንና አማራን፥ ጉራጌን፥ ትግሬን፥ ባርነት/ገርባነት የማይቀበሉ የደቡ ብማኅበረሰቦችን ማጽዳት ፕሪጄክት አካል ነው፤

፪) አዲስ አበባ አሻራዋ 90 ከመቶ የክርስቲያን ነው፥ ኦርኦቶዶክሳውያን በጎሣ ሳይለያዩ አዋህዳ ያስቸገረችን ቤተ ክርስቲያን መዳከም አለባት፥ ለዚህ ሰንበቴዎች፥ እድሮች፥ ቤተሰቦች፥ መፍረስ አለባቸው፥ መለያየትና መበትን አለባቸው የሚለውን አብይ አህመድ ከሕወሃት ተረክቦ ያስቀጠለው የኦነግ-ኦሮሙማ/ብልጽግና ፕሮጄክት አካል ነው፤

፫) ኦነግ-ኦሮሙማ/ብልጽግና "የኦሮሚያ ከተቸችን ዲሞግራፊ እንቀይራል" በሚል በተለይ በጁነዲን ሳዶ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘደንት በግልጽ አዳማ ተጀምሮ በለማ መገረሳ ተጠናክሮ በአብይ አህመድ ከማፈናቀል በጅምላ እስከማስጨፍጨፍና በእቅድ የማደኸየት ፕሮጄክት ማጠናቀቂያ ነው ----

በዚህ ሂደት ምንደኞቹ የቤተ ክርስቲያን ከተኩላ የከፉ እረኞች ተብዬዎች በማደንዘዝና የምእመናንን የአንነድት ንቅናቄ በማክሸፍ ዋና ተዋንያን ናቸው።

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

12 Oct, 17:25


ነባር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሕንጻዎች የአብይ አህምድ አሉ ሙዚየም እየሆኑ ነው
02-02-2017 ዓ/ም

በአብይ አህመድና ዳንኤል ክብረ ትየጋ ራእቅ ድመሠረት ጠቅላይ ቤተ ክህነቱና የሚመለከታቸው ጳጳሳት ታላላቅ ነባር አድባራትን አቢያተ ክርስቲያናትን ለሙዚየምነት አስተላልፈው እየሰጡ ነው።

ቀጥሏል👇

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

12 Oct, 16:16


https://youtu.be/qs4DWx6H5So?si=zksdajYcDuQvTTdb

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

11 Oct, 18:49


ሚዲያ ላይ ምሁራንን፥ አክቲቪሰቶችን፥ ፖለቲከኞች እየጋበዛቸሁ ለምታወያዩ ቅን ጋዜጠኞች ይህችን ትንሽ የታናሽ ወንድም አስተያየት ዋጋ ስጡልኝ

50 ዐመታት ያሰቃየን የዕሳቤ ማኅቀፍን ግን አፍርሳችሁ ለመውጣት በቂ ጥረት ያደረጋችሁ አይመስለኝም።

አሁን እየኖርን ያለነው በመከራ ውስጥ ነው።

ለምሳሌ በንዑስ-ማእነት ርእዮት ተወልደው፥ መለያየትን ከነጻነት አስተካክለው፥ ሕግ ጽፈው የትግራይን ሕዝብ ወደ መሣሪያ ቀይረው፥ ኦነግና/ኦፒዲኦን ተመርኩዘው፥ ( የአማራ ምናምንቴዎችን ጋልበው የመከራ ቋት ላይ ጣዱን።

መወያየት የሚያስፈልገው እነዚህ የመከራ ምንጮች በሚሰጡን አጀንዳ ልክ ሳእሆን ከእነርሱ እሤቶችና ነጽሮተ ዓለም የሚቃረን መሆን አለበት።

እነርሱ የማይወዱትና እያጠፉት ያለው ሰብአዊነትን፥ ፍትሕን፥ እኩል በዓለ-አገርነትን፥ አገር-ፈለቅ (በነባር እምነትና ባህል፥ ረዥም የውጣ ውረድ ታሪክ) ዕውቀትና ብዝኃነትን በጠቅላይነት የሚያስተሳሥር የጋራ እሤት አዲስ ብዝኃነትን (ከማዋጋት በተቃራ ኒበተመጋጋቢና የመሞሏሏት) ተዋህዶን መሠረት ያደረገ አዲስ ጎዳና ላይ ሰውን ብታወያዩ ምን ይመሰላችኋል?

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

10 Oct, 12:49


https://amharic.borkena.com/2024/10/06/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8B%A8%E1%8B%B5%E1%88%85%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%88%98%E1%8A%95%E1%88%B5%E1%8A%A4-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%88%8D-%E1%88%98%E1%89%A5%E1%8B%9B/

Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ

10 Oct, 08:19


http://chng.it/PXtQ7rkm4R
ፈርመዋል? ካልፈረሙ አሁን ይፈርሙ። ለወዳጅ ሁሉ ያጋሩ

10,553

subscribers

1,314

photos

177

videos