ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል @senhome Channel on Telegram

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

@senhome


ይህ ቻናል ብቁ የሆኑ የልዩ-ፍላጎት፣የስነ- ልቦና፣ እና ሌሎች ባለሙያዎች የሚገኙበት ሲሆን የተለያዩ ትምህርታዊ፣ ስነ ልቦናዊ፣ የባህሪ እና ሌሎች ድጋፎችን በሰለጠኑ ባለሙያዎች እንሰጣለን።

📲 0954842701 (ትዛዙ አበበ)
በውስጥ ለማግኘት @Tizaabebe

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል (Amharic)

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል የአማርኛ ቋንቋን በማገናኘት መስራት ይፋ ተወኝተዋል። ይህ ቻናል ብቁ የልዩ-ፍላጎት እና የስነ-ልቦና ማዕከል ነው። ማባልቅታሮችን ስነ ልቦናና ትምህርት መሠረት የሚጠብሰውን ለማስጠንን እና የሚጠቀምባቸውን ጥያቄዎች ለመጭንን ዘላቂ መረጃዎችን ማንበብ የሚችል ነው። እናቶችን ለሳላም በስነ ልቦና የሚሰጣቸውን ከዝህ ማምለኪያና መነሻ ጋሎችዎን ለመጠቀም ባህሪያት ላይ ያስጨናነው ለማየት። በከባድ ቁጥር 0954842701 ይደውሉ፣ ለመልቀቃቸውም @Tizaabebe ብሎ የመጠቀም መረጃዎችን ለማስጠንን ትልቅ ቀጥል ደግሞ ብሎ እንደተገኙ መጠቀም እና ገራርና ያላቸው መረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉበት ቻናል ነው።

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

10 Nov, 10:37


መልካም ዜና ወደ አያት፣ሲመሲ፣ሰሚትና አካባቢው ለምትኖሩ ወላጆች

የተለያዩ ልዩ-ፍላጎት ላላቸው ልጆች አገልግሎት መስጠት የጀመርን መሆኑን ስለማሳዎቅ

የምንሰጣቸው የቴራፒ አገልግሎቶች

👉የስነ-ባህሪይ  ቴራፒ /Applied Behavior Analysis – ABA
👉የንግግር እና ቋንቋ ቴራፒ/ Speech and Language Therapy
👉የክዋኔ ቴራፒ /Occupational Therapy
👉የስሜት ህዋሳት ውህደት ቴራፒ/ Sensory Integration Therapy


አድራሻ
ከአያት አደባባይ ወደ አራብሳ መገንጠያ

0954842701
0932710374


https://t.me/SENhome

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

08 Nov, 12:25


📌ከታች የቀረቡት አምስት ተግባራት የልጆችን የአዕምሮ እድገት ለማጎልበት ወሳኝ ናቸው፣

1. ልጁ ትኩረት ያደረገበትን ነገር ወይንም ሁኔታ ልጁን ተከትሎ ትኩረት መስጠት

👁የልጁን ትኩረት በመጋራት ከልጁ ጋር በተለያየ መንገድ ግንኙነት መፍጠር፡፡

👁ለምሳሌ ጥያቄ በመጠየቅ ወይንም ትኩረቱን ስለሳበው ነገር መግለጫ በመስጠር (የምናወራው ነገር ልጁ ባይገባውም)፡፡

2. ለልጁ ድጋፍ መስጠትና ማበረታታ

👊ልጁ የሚያሳየውን በሀሪ ወይንም እንቅስቃሴ ተከትሎ ድጋፍ ወይንም ማበረታቻ መስጠት፡፡

👊ለምሳሌ ልጁ እቃ ሊያቀብለን ቢሞክር ጎበዝ እያሉ ማበረታታት፤ ድጋፍ የሚፈልግ ከሆነም ድጋፍ መስጠት፡፡

👊ወይንም ልጁ ለሚያሳየው እንቅስቃሴ የተለያየ አካላዊ እንቅስቃሴ (ለምሳሌ ፈገግታ፤ ማጨብጨብ) በማሳየት ለልጁ ትኩረት መስጠት፡፡

3. ልጁ ትኩረት ያደረገበትን ወይንም የሚነካካውን እቃ ስም መጥራት
   
🗣ለምሳሌ ልጁ የእንስሳት ስዕል ላይ ትኩረት ቢያደርግ የእንስሳውን ስም መጥራት፡፡ ይህም ለልጁ ቋንቋ እድገት ከፍተኛ አስተቃጽኦ ያደርጋል፡፡

4. ከልጁ ጋር ተራ እየጠበቁ የሚያከናውኑትን ስራ/ጨዋታ መፍጠር

👉🏿ከልጆ ጋር ተራ እየጠበቁ ነገሮችን መከወን ልጆ እራስን መግዛትንና ከሰዎች ጋር እንዴት መኖር እንዳለበት መማርን ጨምሮ በርካት ክህሎቶችን ይማርበታል፡፡

👉🏿ለምሳሌ ተራ ጠብቆ ማጨብጨብ፣ ትናንሽ መጫወታዎችን በየተራ ማስቀመጫ ውስጥ መጨመር እና ሌሎችም፡፡

5. ልጁ የጀመረውን ስራ/ጨዋታ መጨረሱንና ዓዲስ ጨዋታ ለመጀመር መፈለጉን መረዳትና በዚህ የሽግግር ሂደት ውስጥም የልጁን ፍላጎት መረዳትና አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት


© Fiseha Teklu


https://t.me/SENhome

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

04 Nov, 12:03


ልብ የሚያሞቅ ዜና ለወላጆች🙏

በደንብ የዘራ በደንብ ያጭዳል!!!

https://youtu.be/9UO41Bdn87c?si=fdn1dryLZnIcGH1r

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

01 Nov, 19:09


የዛሬው ውይይት ይህን ይመስል ነበር !!!
👉 ወ/ሮ የምስራች ለሰጠሽን ግንዛቤ  እናመሰግናለን!!🙏

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

01 Nov, 19:08


Live stream finished (1 hour)

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

01 Nov, 17:30


Live stream scheduled for

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

01 Nov, 17:29


Live stream started

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

30 Oct, 13:34


🌟 የስልጠና እድል ለወላጆች እና ባለሙያዎች!/Training Opportunity for Parents and Experts!🌟

Join us for an insightful session on:

1. Autism Diet Plan
2. Detoxification in Holistic Approach
 

For detial:
0911735569
0901087882

Enhance your knowledge and support strategies! Don’t miss out!


#Autism #HolisticHealth #TrainingOpportunity

https://t.me/SENhome

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

29 Oct, 15:04


መልካም ዜና ወደ አያት፣ሲመሲና ሰሚት ለምትኖሩ ወላጆች

የተለያዩ ልዩ-ፍላጎት ላላቸው ልጆች አገልግሎት መስጠት የጀመርን መሆኑን ስለማሳዎቅ

የምንሰጣቸው የቴራፒ አገልግሎቶች

👉የስነ-ባህሪይ  ቴራፒ /Applied Behavior Analysis – ABA
👉የንግግር እና ቋንቋ ቴራፒ/ Speech and Language Therapy
👉የክዋኔ ቴራፒ /Occupational Therapy
👉የስሜት ህዋሳት ውህደት ቴራፒ/ Sensory Integration Therapy


አድራሻ
ከአያት አደባባይ ወደ አራብሳ መገንጠያ

0954842701
0932710374


https://t.me/SENhome

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

27 Oct, 07:56


🌟 Dear Parents, Teachers, and Significant Others,

"የኦቲዝም ሚስጥሮች" by Dr. Hadiya Yimam is an invaluable resource that can transform your understanding and approach to supporting a child with autism. Here are some highlights that make it a must-read for you:

💖 Empathy and Understanding: This book emphasizes the importance of seeing the world through the eyes of a child with autism. It fosters deeper empathy and connection, helping you relate more effectively to their experiences.

🛠️ Practical Strategies: Dr. Hadiya provides actionable strategies that you can implement in daily interactions, enhancing communication and making everyday life smoother for both you and the child.

🤝 Community Support: The book highlights the significance of building a support network. It encourages you to connect with others facing similar challenges, reminding you that you’re not alone on this journey.

📖 Personal Stories: Real-life experiences shared in the book offer comfort and relatability, helping you feel more connected and understood in your own experiences.

Whether you’re a parent navigating daily challenges, a teacher striving to create an inclusive classroom, or a significant other seeking to provide support, this book is a powerful tool for fostering understanding and creating a nurturing environment for children with autism.

Together, we can make a difference! 💖

https://t.me/SENhome

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

23 Oct, 01:30


ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል pinned «»

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

21 Oct, 05:49


የሕፃናት እድገት ላይ ወሳኝ ከሆኑት ነገሮች አንዱ መንፈሳዊ እድገት ነው። ልጆችን መጸለይን ማስተማር በህወታቸው ውስጥ ትልቅ ሚና አለው። ከሃይማኖታዊ ትርጉሞቹ ባሻገር፣ ጸሎትን መረዳት ልጆች ለአጠቃላይ ደህንነታቸው እና ለግል እድገታቸው የሚያበረክቱ ጠቃሚ የህይወት ክህሎቶችን ይሰጣል።

ልጆችን ስለ ጸሎት ማስተማር ለምን አስፈላጊ ነው?
♦️ከ ፈጣሪ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያጠነክሩ
♦️ስሜታቸውን እንዲገልጹ  እድልን ይከፍታል። ይህም በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ጽናትን ይሰጣቸዋል።
♦️ስለሌሎች እንዲያስቡ፣ ርህራሄን እና የማህበረሰብ ስሜትን እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል።
ጸሎት እንደ ደግነት፣ ታማኝነት እና ምስጋና ያሉ ዋና እሴቶችን ያጠናክራል፣ ይህም ልጆች ጠንካራ የስነምግባር መሰረት እንዲያዳብሩ ይረዳል።
♦️ልጆች እራሳቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ እና እራሳቸውን እንዲያውቁ ይረዳቸዋል።
♦️ልጆችን በአዎንታዊ እይታ የህይወትን እርግጠኛ አለመሆን እንዲመሩ ይረዳቸዋል።

ወላጆች፣ አስተማሪዎች እና ተንከባካቢዎች፣ ልጆች ጸሎትን ከህይወታቸው ጋር እንዲያዋህዱ መምራት እንችላለን። ቀጣዩ ትውልድ በጸሎት ልምምድ ጥንካሬን፣ ዓላማን እና ግንኙነትን እንዲያገኝ እናበረታታ።

ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው (ጠቅላላ ሀኪም እና ሁለንተናዊ የህጻናት እድገት ባለሞያ)

https://t.me/SENhome

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

18 Oct, 19:15


የዛሬው ውይይት ይህን ይመስል ነበር !!!
👉 ወ/ሮ ሳምራዊት ለሰጠሽን ግንዛቤ  እናመሰግናለን!!🙏

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

18 Oct, 19:14


Live stream finished (2 hours)

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

18 Oct, 17:01


ጀምረናል ገባ ገባ በሉ!!!

Share It

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

18 Oct, 17:00


Live stream started

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

18 Oct, 17:00


Live stream scheduled for

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

18 Oct, 13:34


👉ሰላም ቤተሰቦች🙏🙏🙏

የዛሬ ውይይታችንን የምናደርገው ከወ/ሮ ሳምራዊት መኩሪያ
ጋር ሲሆን አጠቃላይ በልጆቻችን ዙሪያ ያካበቱትን እውቀት፣ልምድና ተሞክሮ እንዲሁም ያላትን ምልከታ  " አላስፈላጊ ንጥረ-ነገሮችን ከልጆቻችን ሰውነት ውስጥ ማስዎገድ (Detoxification)" በሚል ርዕሰ ጉዳይ የምንወያይ ሲሆን ሁላችሁም በውይይቱ ንቁ ተሳታፊ እንድትሆኑ ከአሁኑ ተጋብዛችኋል ፡፡

👉  Share 👉Share 👉Share

👉ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/SENhome

👉የውይይቱ  ሊንክ

https://t.me/SENhome?livestream=ae4c195da3a00dd82c

         👉ምሽት 2:00 ጀምሮ 👏👏👏

    
           ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!!
           👉 ቻናሉን እያጋራን🙏

https://t.me/SENhome


#GohCenter #SpecialNeedsSupport #InclusiveEducation #DisabilityAwareness #Empowerment #SpecialNeedsCommunity #TherapeuticPrograms #IndividualizedCare #LifeSkillsDevelopment #FamilySupport #AutismAwareness #SpecialEducation #Advocacy #InclusionMatters #PositiveImpact

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

14 Oct, 18:14


ልጆች አቅማቸው በሚፈቅድ ስራ ውስጥ እንዲሳተፉ ፍቀዱላቸው

ልጆች በአካባቢያቸው ያዩትን ሁሉ መሞከር ይፈልጋሉ፡፡ አካባቢያቸውን ለመረዳትና ነገሮች እንዴት እንደሚሰሩ ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሳ ያዩትን ሁሉ ይሞክራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ወላጆች ልጆች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከመስጋት የተነሳ ልጆች ብዙ ነገር እንዳይሚክሩ ሲከለክሉ ይስተዋላሉ፡፡ ይህም ሁኔታ በልጆችና በወላጆች መካከል የጸብና የጭቅጭቅ ምንጭ ሲሆን ይታያል፡፡ ከዚህም ባለፈ የልጆችን የመማር፣ የተለያዩ ክህሎቶችን የማዳበር፣ ለስራ መልካም አመለካከት የማዳበርን፣ በራስ መተማመንን /እችላለሁ የሚል ስሜትን፣ ወላጆችንና ሌሎች ሰዎችን በስራ የመርዳት ፍላጎትን እንዲሁም በሙላት የማደግ እድልን እንዳያገኙ ያደርጋል፡፡ 

ልጆች እንዲሞክሩ መፍቀድ ያለብን ለምንድነው

1.  ለልጆች አስደሳች ስለሆነ
2.  የሚማሩበት መንገድ ስለሆነ
3.  መሞከር የእድገታቸው አካል ስለሆነ-
የወላጆች ዋንኛ ግብ መሆን ያለበት ልጆች ነገሮችን በተሳካ መልኩ መፈጸማቸውና ውጤታማ መሆናቸው ሳይሆን በመሞከር ሂደት በስኬትና ወድቆ በመነሳት ውስጥ ማለፋቸውን ነው፡፡
4.  በልጅነት እድሜ መሞከርና ሌሎች ሰዎች በሚሰሩት ስራዎች ውስጥ መሳተፍ መፈለግ የልጆች ተፈጥሮ ስለሆነ፡፡
5.  አቅማቸውን ያገናዘበና ለአደጋ የማያጋልጣቸው ስራ ውስጥ እንዲሳተፉ መፍቀድ የስራ ባህልን እንዲለምዱ ያግዛቸዋል፡፡


© Fiseha Teklu

https://t.me/SENhome

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

11 Oct, 19:15


የዛሬው ውይይት ይህን ይመስል ነበር !!!
👉 ዶ/ር አሊ ለሰጠኸን ግንዛቤ  እናመሰግናለን!!🙏

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

11 Oct, 19:13


Live stream finished (1 hour)

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

11 Oct, 17:30


ጀምረናል ገባ ገባ በሉ!!!

ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል

11 Oct, 17:30


Live stream started