Kolfe education official channel🇪🇹 @kolfekeranioeducationbureau Channel on Telegram

Kolfe education official channel🇪🇹

@kolfekeranioeducationbureau


We are delighted to inform our members about kolfea keranio Education bureau.🇪🇹

Kolfe Education Official Channel (English)

Are you looking for a reliable source of information and updates on education in Kolfe Keranio? Look no further, as the Kolfe Education Official Channel is here to provide you with all the latest news and updates from the education sector in this region. As the official channel of the Kolfe Keranio Education Bureau, we aim to keep our members informed about the latest developments in the education system, upcoming events, important announcements, and much more. Whether you are a student, teacher, parent, or simply interested in education in Kolfe Keranio, this channel is the perfect place for you to stay connected and updated. By joining our channel, you will have access to exclusive content, such as educational resources, tips for students, job opportunities in the education sector, and much more. Our goal is to create a community of individuals who are passionate about education and are committed to making a positive impact in the lives of students in Kolfe Keranio. So, what are you waiting for? Join the Kolfe Education Official Channel today and be a part of this thriving community dedicated to promoting education in Kolfe Keranio. Together, we can work towards building a brighter future for the students in our region. We look forward to having you on board!

Kolfe education official channel🇪🇹

22 Nov, 12:28


የተማሪዎች ምዝገባን በተመለከተ
በምዝገባ ወቅት Resubmit እንዲያደርጉ ተጠይቀው ነገር ግን ሲስተም ላይ የምዝገባ ፎርማቸው ሳያጠናቅቁ ትምህርት የጀመሩ ተማሪዎች ያሏችሁ ትምህርት ቤቶች በሙሉ ተማሪዎች በአስቸኳይ STATUS ላይ ገብተው Admission ID እንዲሁም በምዝገባ ወቅት የተጠቀሙትን ስልክ በማስገባ Re-Apply የሚለውን አማራጭ ተጠቅመው የምዝገባ ፎርማቸው አጠናቀው እንዲያስገቡ አስገዳጅ መመሪያ እንድትሰጡ እየጠየቅን::
የምዝገባ ፎርም ተቀብላችሁ የማፅደቅ ስራ ያላጠናቀቃችሁ ትምህርት ቤቶችም እንድታጠናቅቁ እናሳስባለን::
ማሳሰቢያ:-
በትምህርት ቤታችሁ እየተማሩ ያሉ ተማሪዎች በሙሉ በሲስተም መመዝገባቸውን ያረጋግጡ::

Kolfe education official channel🇪🇹

22 Nov, 06:15


የማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

ህዳር 13/2017 ዓ.ም

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ጽ/ቤት ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር በክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ሠራተኞች የእርስ በርስ የውቀት ልውውጥ መርሃ-ግብር ማድረግ ችለዋል።

የእለቱን የምርጥ የእውቀት ሽግግር ሠነድ ገለፃ ያቀረቡት አቶ ፀጋዬ ተስፋዬ በትምህርት ሊደርሽብ አፕሮች ዙሪያ በተግባር ተሰርቶ የተገኙ ልምዶችን በተቋማቶቻችን እንዴት እንተግብረው በሚል ለውይይት አቅርበው ሠፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው የሥራ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሠይፈሚካኤል ባርጠማ ይህ መርሃ ግብር አንዳችን ለአንዳችን ያለንን መልካም ተሞክሮ ልምድ የምንለዋወጥበት መድረክ ስለሆነ ሁሉም ሠራተኛ በየሳምንቱ በንቃት መሳተፍ ይጠበቅበታል ብለዋል።

Kolfe education official channel🇪🇹

21 Nov, 14:29


#አስተዳደሩ_የመልካም_አስተዳደር_ጥያቄዎችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራና በቅንጅት ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያደርገውን ርብርብ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።አቶ ገነነ ዘውዴ
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ

ህዳር 12/2017ዓ.ም

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ከአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ መካኒሳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን በትንቢተ ኤርሚያስ ት/ቤት የከርሰ ምድር ዉሃ የጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ ዘውዴ፣የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ምስጋናው፣ የወረዳው አመራሮች ፕሮጀክቱ ያለበትን ሁኔታ ድንገተኛ ምልከታ በዛሬው እለት አድርገዋል።

ፕሮጀክቱ 400 ሜትር ጥልቀት ያለው ሲሆን አጠናቆ በአጭር ጊዜ አገልግሎት ለማስጀመር በእቅድ ተይዟል፡፡

ፕሮጀክቱ የዉሃ አቅርቦት ችግርን በትንቢተ ኤርሚያስ ት/ቤት እና የአካባቢውን ነዋሪ ችግር በዘላቂነት የሚፈታ ፕሮጀክት ነው ሲሆን በቅርቡ ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚጀምር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እንዲፈታና ለማህበረሰቡ ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዲያስችል የወረዳው ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤትና ትምህርት ፅ/ቤት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የቅርብ ድጋፍና ክትትል እያደረጉ ነው።

🙏ኮልፌ ወረዳ 09 ኮሚዩኒኬሽን