Arada education office @av12c Channel on Telegram

Arada education office

@av12c


Arada education office (English)

Welcome to the Arada Education Office! Our Telegram channel, @av12c, is dedicated to providing valuable educational resources and information to students, parents, and educators. Whether you're looking for study tips, guidance on career paths, or updates on educational events, our channel has got you covered. Who are we? We are a team of experienced educators and professionals who are passionate about empowering individuals through education. Our goal is to create a supportive community where everyone can access the resources they need to succeed academically and professionally. What do we offer? On our channel, you can expect to find a wide range of content, including study guides, exam tips, career advice, and information on scholarships and internships. We also organize virtual events, workshops, and webinars to help you enhance your skills and knowledge in various fields. So, whether you're a student looking to improve your grades, a parent seeking guidance on your child's education, or an educator searching for new teaching strategies, the Arada Education Office is here to support you every step of the way. Join our channel today and start your journey towards a brighter future!

Arada education office

04 Jan, 15:43


አስቸኳይ መልዕክት

የድህረ እውቅና አገልግሎት ተሰርቶላችሁ ግብረመልስ ያልወሰዳችሁ የትምህርት ተቋማት 4 ኪሎ ድንቅ ስራ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 704 በመገኘት ግብረመልስ እንድትወስዱ እናሳስባለን።




የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እውቅና ፈቃድ እድሳት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

Arada education office

31 Dec, 14:59


22/04/17
በአራዳ ክፍለ ከተማው ስር ለሚገኙ ለ21 የመንግስት እና ለ26 የግል ትምህርት ቤት ርእሰ መምህራን እንዲሁም ለ47 አይሲቲ ባለሙያዎች የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል "ኦን ላይን" ምዝገባ ገለጻ ተሰጠ፡፡ በክፍለ ከተማችን 6ኛ ክፍል 3,714 እንዲሁም 8ኛ ክፍል 3,841 በጥቅሉ 7,555 ተፈታኝ ተማሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ ይገመታል፡፡

Arada education office

30 Dec, 11:46


ቀን 21/04/2017 ዓ.ም
ለመንግሥት ት/ቤት ር/መምህራን በሙሉ ነገ ማክሰኞ 2:00 አድዋ 00 እንድትገኙ እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ: መወከል:ማርፈድና መቅረት የተከለከለ ነው።

Arada education office

26 Dec, 05:02


የሪፖርት ቢጋር

Arada education office

25 Dec, 13:06


የስልጠና ጥሪን ይመለከታል
ተሳታፊዎች
1. የክፍለ ከተማና የወረዳ ክላስተር አስተባባሪዎች
2. የወረዳ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች
3. የወረዳ ቡድን መሪዎች (2)
ቦታ ትምህርት ቢሮ 12ኛ ፎቅ
የስልጠና ቀን 17/04/2017 ዓ.ም
ሰዓት 2፡00

Arada education office

25 Dec, 08:03


ቀን 16/04/2017 ዓ.ም
ለወረዳ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች
የሪፎርም ሪፖርት ቢጋር መሰረት የተገመገመ ሪፖርት ዛሬ እስከ 9:00 ሰዓት ገቢ እንድታደርጉ እያልን በተመሳሳይ የ6 ወር ሪፖርት የተገመገመ እስከ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም እንድትልኩ በጥብቅ እናሳስባለን።

Arada education office

23 Dec, 17:15


ማክሰኞ 7:30 የተጠራው የስፖርት መምህራን ስልጠና ቦታው አራዳ ክፍለ ከተማ 1ኛ ፎቅ አይሲቲ አዳራሽ መሆኑን ር/መምህራን መልዕክቱን በአግባቡ እንድታስተላልፉ እናሳስባለን ።
ሰዓት ይከበር
መልካም አዳር!!!

Arada education office

23 Dec, 17:03


አስቸኳይ መልእክት
ለት/ቤት ር/መምህራን

ከዚህ ቀደም የማህደረ ተግባር  ምዘና ወስደው የማለፊያ ነጥቡን ያሟሉ አመራርና መምህራን መረጃ በሀርድ ኮፒ በት/ቤቱ ርዕሰ መምህራን ተረጋግጦ የሁሉም መምህራን በጋራ ተደርጎ በፖስታ ታሽጎ እስከ 15/04/2017ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ድረስ ድንቅ ስራ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 704 ገቢ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

Arada education office

22 Dec, 02:27


የሙያ ብቃት ምዘና ላጠናቀቃችሁ ተመዛኞች

Arada education office

06 Dec, 08:38


ለውድ ርዕሳነ መምህራን !
ስላማችሁ ይብዛ!
ዛሬ አርብ ከሰዓትና ነገ ቅዳሜ ይዘነው የነበረው የሪፎርምና የሌሰን ስተዲ ስልጠና በአሰልጣኝ አለመመቸት ምክንያት ለቀጣይ ሣምንት ያዞርነው መሆኑን በትህትና እንገልፃለን ።

Arada education office

05 Dec, 12:42


ለመጨረሻ ጊዜ የወጣ ማስታወቂያ


በመምህራንና የትምህርት አመራር ሙያ ብቃት የፅሁፍ ምዘና 62.5 እና በላይ ላመጡ ተመዛኞች የነበረው የክዋኔ ማህደረ ተግባር ምዘና የተጠናቀቀ ቢሆንም

በተለያየ ምክንያት ምዘናውን ያልወሰዱ ተመዛኞች ጥያቄ እና ምክንያት መነሻ በማድረግ ለመጨረሻ ጊዜ ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው ፕሮግራም ቅዳሜ 28/03/2017 ዓ.ም ከ2:30 -11:00 ድረስ ብቻ የክዋኔ ማህደረ ተግባር (ፖርትፎሊዮ) ምዘና ስለሚሰጥ አራት ኪሎ ድንቅ ስራ ህንፃ በሚገኘው ቢሯችን 8ኛ ፎቅ አዳራሽ መረጃችሁን ይዛችሁ በመገኘት የክዋኔ ማህደረ ተግባር ምዘና እንድትመዘኑ በጥብቅ እናሳስባለን።


የት/ቤት ር/መ/ራን ማስታወቂያ ለመምህራን በሚታይ ቦታ በመለጠፍ መረጃው እንዲደርሳቸውና በእለቱ መጥተው እንዲመዘኑ ይደረግ።





የአራዳ ቂርቆስ ቅ/ጽ/ቤት

የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እውቅና ፈቃድ እድሳት ዳይሬክቶሬት

Arada education office

03 Dec, 04:31


ቀን 24/03/2017 ዓ.ም
የስብሰባ ጥሪ
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ዋና ር/መምህራን፣ የወረዳ ት/ጽ/ቤቶች ዛሬ 8፡00 ሰዓት ላይ ስብሰባ ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
በውይይት ላይ ስትገኙ፡-ድጋፍና ክትትል ከተደረገ በኃላ በሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት፣ በሪፎርም በክፍተት ተለይተው የተስተካከሉ እና በተጨማሪ የተሰሩ ስራዎችን መረጃ በሪፖርት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- መቅረት፣ ማርፈድ፣ መወከል የማይቻል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ቦታ ትምህርት ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ

Arada education office

02 Dec, 19:52


ማሳሰቢያ ፡- ለመዛኞች የመመዘኛ ቼክሊስቱን የትምህርት ቤት ር/መምህራን ፕሪንት አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እናሳስባለን። ቼክሊስቱ የእውቅና ፈቃድ ምዘና መስፈርት መሆኑን እንገልፃለን።

Arada education office

02 Dec, 11:02


ቀን 23/03/2017ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ር/መምህራን
ከ24/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ የእውቅና ምዘና በባለሙያዎች የሚካሄድ በመሆኑ መዛኞች ስመጡ አስፈላጊውን መረጃ እንድታሳዩ እናሳውቃለን።

Arada education office

29 Nov, 12:51


አስቸኳይ
ቀደም ተብሎ ሲከናወን የነበረውን መምህራን online በመመዝገብ ወደ ሲስተም የማስገባት ስራ እሰከ መጪው ሀሙስ እንዲጠናቀቅ መግባባት ላይ ስለተደረሰ በት/ት ቤት ያሉ መምህራን ልማት ም/ል ርእሳነ መምህራኖች በየቀኑ የተመዘገቡ መምህራንን እስከ
6:00 ሪፖርት ለክፍለ ከተማ የተደረሰበትን በጾታ ተለይቶ እንዲቀርብ ይደረግ እኛ ደግሞ እሰከ 8:00 በየቀኑ የክ/ከተማዉን መረጃ እየጠመርን ለቢሮ የምንልክ ስለሆነ ከትላንት እስከ ዛሬ በአለዉ የላከ ባለመኖሩ መረጃዉን ጠምረን መላክ አልቻለንም ስለሆነም የደረሳችሁበትን መረጃ ቶሎ ላኩልን ። አንድም መምህር ሳይመዘገብ እንዳይቀር ጉዳዩን በልዩ ትኩረት አስተባብሩ። ስለ ትብብራችሁ እናመሰግናለን፡፡

Arada education office

28 Nov, 12:54


ቀን 19/03/2017 ዓ.ም
ማሳሰቢያ፡-
የስብሰባ ጥሪ የቀን ለውጥ መደረጉን ማሳወቅን ይመለከታል፡፡
ተሳታፊዎች
1ኛ. ሁሉም የመንግስት ዋና ር/መምህራን
2ኛ. የወረዳ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች
3ኛ. የ2ኛ ደረጃ እና የመ/ደረጃ ክላስተር ሱፐርቫይዘር አስተባባሪዎች
ቅዳሜ በ21/03/2017 ዓ.ም ጥዋት 2፡30 ተጠሪቶ የነበረው ወደ አርብ 20/03/2017 ዓ.ም 7፡00 ሰዓት አራዳ ክፍለ ከተማ ትልቁ አዳራሽ የተቀየረ በመሆኑ ተሳታፊዎች በተባለው ሰዓት እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ሰዓት ይከበር!!!

Arada education office

28 Nov, 07:08


ቀን 19/03/2017 ዓ.ም
የስብሰባ ጥሪ
ተሳታፊዎች
1ኛ. ሁሉም የመንግስት ዋና ር/መምህራን
2ኛ. የወረዳ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች
3ኛ. የ2ኛ ደረጃ እና የመ/ደረጃ ክላስተር ሱፐርቫይዘር አስተባባሪዎች
ቅዳሜ በ21/03/2017 ዓ.ም ጥዋት 2፡30 በ2ኛ ዙር በሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርቶች በተደረገ ድጋፍና ክትትል የጋራ የሚደረግ ሲሆን ተሳታፊዎች ቂርቆስ ክፍለ ከተማ አዳራሽ በተባለው ሰዓት እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ሰዓት ይከበር!!!

Arada education office

26 Nov, 09:04


ቀን 17/03/2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ር/መምህራን በሙሉ
የተቋም የውስጥ የእውቅና ፈቃድ ምዘና መደረጉ ይታወቃል፡፡ በምዘናው መሰረት በእያንዳንዱ በስታንዳርድ የተቀመጠ መስፈርት የታዩ ክፍተቶች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ (17/03/2017 ዓ.ም - 21/03/2017 ዓ.ም) ድረስ ግብዓት የማሟላት ስራ የሚሰራበት ሳምንት በመሆኑ ልዩ ትኩረት በመስጠት ተግባሩን እንድትመሩና የተጓደሉ ጉዳዮችን በማሟላት የተቋማችሁን ደረጃ እንድታሻሽሉ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ የተጓደሉ ስለመሟላቱ በክትትል የሚናረጋግጥ መሆኑን ጭምር እናሳውቃለን፡፡

Arada education office

21 Nov, 10:17


ማሳሰቢያ፡-
የእውቅና ምዘና ግብረ መልስ ያልላካችሁ ት/ቤቶች በአስቸኳይ ግብረ መልሱን እንድትልኩ እያሳሰብን ቅዳሜ በክፍለ ከተማ ደረጃ ግብረ መልሱ የጋራ ስለምደረግ ፈጥናችሁ ላኩ፡፡ ግብረ መልሱን ስትልኩ በሀርድና በሶፍት ኮፒ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

Arada education office

20 Nov, 08:49


የእውቅና ፍቃድ ምዘና ግብረመልስ ማድረግያ ፎርማት

Arada education office

19 Nov, 07:38


ቀን 10/03/2017 ዓ.ም
ለሁሉም ት/ቤት ር/መምህራን
የእውቅና ፈቃድ የውስት ምዘና እያካሄዳችሁ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም በምዘናው መሰረት ኮሚቴዎች ግብረ መልስ ሰርተው ለ12/3/2017 ዓ.ም ለክፍለ ከተማ ገቢ እንድያደርጉ በእናንተ በኩል መልዕክት እንድታስተላልፉ በጥብቅ እናሳስባለን።

Arada education office

18 Nov, 09:28


ሰላም የተከበራችሁ ርመምህራን በ2016 ዓ.ም በሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርቶች ዙሪያ ጥናትና ምርምር የሠሩ መምህራንን ስምና የጥናቱን ርዕስ እንድትልኩልን ይሁን

Arada education office

18 Nov, 06:41


የእውቅና ፈቃድ መመዘኛ ቼክሊስት ነው፡፡

Arada education office

18 Nov, 06:39


Checklist For Government Gen. Secondary Schools (Edited)

Arada education office

18 Nov, 06:23


ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ዛሬ የእውቅና ፈቃድ ምዘና ስለሚካሄድ ቅዳሜ ስልጠና የወሰዱ የሲፕ ኮሚቴዎች የውስጥ ምዘና እንድያካሂዱና መረጃ እንድታደርሱን እናሳስባለን።

Arada education office

15 Nov, 10:03


ቀን 06/03/2017 ዓ.ም
የስልጠና ጥሪ
1. ሁሉም የመንግስት የት/ቤት መሻሻል ም/ር/መምህራን
2. የተመረጡ የሲፕ ኮሚቴ 2ቱ መምህራን
3. የኬጅ አስተባባሪዎች
4. የወረዳ ቡድን መሪዎችና የሲፕ ባለሙያዎች
ቅዳሜ 2፡30 ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ተገኙ።
ሰዓት ይከበር

Arada education office

14 Nov, 07:41


እንዴት አደራችሁ!

በትምህርት ቤቶች ዘውትር ዓርብ የጽዳት ዘመቻ ባህል እየሆነ መምጣቱ ይታወቃል።

ስለሆነም የብልጽግና ፓርቲ የተመሰረተበት 5ኛ ዓመት በተለያዩ ኩነቶች የሚከበር ሲሆን የዚህ አካል የሆነው የጽዳት ዘመቻ ከወትሮ በላቀ ንቅናቄ ነገ ዓርብ ጠዋት በሁሉም ት/ቤቶች ቅጥር ግቢ እና ውጪ የጽዳት ዘመቻ የሚካሄድ ስለሆነ አመራሩ ለተግባሩ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ የጽዳት ዘመቻ እንዲካሄድና የጽዳት ዘመቻዎቹ በኮሚኒኬሽን እንዲታጀብ በማድረግ አፈጻጸሙን ሪፓርት እንድታደርጉ እናስታውቃለን።

በዕለቱ የሚተላለፉ መልዕክቶች
1. ቆሻሻ በማቃጠል አካባቢያችንን አንበክልም
2. ትርክታችን ጽዱ መሆናችን
3. ውስጣችን ከጥላቻ አካባቢያችንን ከቆሻሻ እናጽዳ

መልካም ቀን

Arada education office

14 Nov, 07:02


እንዴት አረፈዳችሁ!

የፊታችን ቅዳሜ ጠዋት 2:00 ሰዓት ላይ የክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎችና የ1ኛ ደረጃ ት/ቤት ዋና ር/መምህራን በአዳዋ ሙዚየም እንዲገኙ ጥሪ ይተላለፍ።

አጀንዳው:- የቀዳማይ ልጅነት

መቅረትና ማርፈድ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።

Arada education office

14 Nov, 02:35


ለሁሉም የመንግስት የመ/ደረጃ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ር/መምህራን
ቅዳሜ ስልጠና ላይ የሚሳተፉ
1ኛ. የት/ቤት መሻሻል ም/ር/መምህር
2ኛ. ከሲፕ ኮሚቴ አባላት ውስጥ 2 መምህር
3ኛ. የቅድመ አንደኛ ደረጃ አስተባባሪ 1 ሰው ስም ዝርዝራቸውን ዛሬ ሀሙስ እስከ 6 ሰዓት ላኩልን።
ማሳሰቢያ፡- ቅድመ አንደኛ ላላቸው ብቻ ነው አስተባባሪ ስም የሚላከው።

Arada education office

13 Nov, 15:05


ለሁሉም ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊዎች!
ለሁሉም የሁለተኛ አንደኛና ቅድመአንደኛ ትምህርት ቤት ርእሳነ መምህራን!
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ነገ ሃሙስ ህዳር 5/2017 ዓ.ም በሁሉም የወረዳ ጽ/ቤቶች እና ትምህርት ቤቶች የሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ስትራቴጂ አፈጻጸም ያለበት ደረጃ በሱፐርቪዥን ምልከታ በከተማው በተዋቀረ ቡድን ከጠዋቱ 2፡00 ሰአት ጀምሮ ይከናወናል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ጽ/ቤት ሃላፊና ርእሰ መምህር ለዚህ ጉዳይ የተለየ ትኩረት በመስጠት የስትራቴጂውን አተገባበር በንቃትና በበቂ ዝግጅት ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ ያለበትን ደረጃ እንዲያሳይ እያሳወቅን ለዚህ ስትራቴጂ አተገባበርና ሱፐርቪዥን ላይ መዘናጋት ማሳየት ከፍተኛ ተጠያቂነት ያለበት ጭምር በመሆኑ በበቂ ጥንቃቄና ዝግጅት እንዲከናወን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
ደሳለኝ ደበሌ
የአራዳ ክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ

Arada education office

13 Nov, 13:28


ቀን 04/03/2017ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶች እና ወረዳዎች ሐሙስ (05/03/2017) የሕሳብና እንግሊዘኛ ትምህርቶች ዙሪያ ድጋፍና ክትትል የሚደረግ በመሆኑ ከቢሮ ተልከው የሚመጡ ባለሙያዎችን ተቀብላችሁ እንድታስተናግዱ እናሳስባለን።
ከርፎርም ክትትል ጋር ተደራራቢ የሆነባችሁ ት/ቤቶች ሁለቱን አጣጥማችሁ እንድታስተናግዱ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን።

Arada education office

12 Nov, 15:33


ቀን 03/03/2017 ዓ.ም
የፕሮግራም ማሻሻያ መደረጉን ስለማሳወቅ
ረቡዕ የ2ኛ ደረጃ እና ወረዳ ት/ጽ/ቤት ብቻ ተብሎ የነበረው የ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶችንም የሚያካትት መሆኑን አውቃችሁ ድጋፍና ክትትል የሚያደርጉ ባለሙያዎችን ተቀብላችሁ አስፈላጊውን መረጃ እንድታሳዩ እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ:- አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶችም ነገ ክትትልና ድጋፍ ትደረጋላችሁ።።

Arada education office

11 Nov, 14:38


ቀን 02/03/2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ዋና ር/መምህራን በሙሉ
ማክሰኞ 7፡30 ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ ስብሰባ ላይ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።

Arada education office

11 Nov, 07:12


ቀን 02/03/2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግት ት/ቤቶችና የወረዳ ት/ጽ/ቤቶች በሙሉ፡-
የሪፎርም አተገባበር ዙሪያ ክትትልና ድጋፍ ለማድረገ ከረቡዕ ጀምሮ ከከተማ ባለሙያዎች የሚመጡ በመሆኑ ቅድመ ዝግጅት አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡
መልካም ቀን

Arada education office

08 Nov, 12:24


Photo from Desalegn Debele

Arada education office

08 Nov, 12:20


29/02/17

በ28/02/17 የስልጠና ጥሪ እንዲተላለፍ የለጠፍነው ማስታወቂያ ላይ የቦታ ለውጥ የተደረገ መሆኑ ተነግሮናል። በዚህ መሠረት የስልጠናው ቦታ ከንቲባ ጽ/ቤት በሚገኘው አዳራሽ ሆኗል። ስለዚህ በስልጠናው ላይ የሚሳተፈውን አንድ መምህር እና አንድ ተማሪ በተቀየረው ቦታ መሆኑን አሳውቃችሁ በሰአቱ እንድትገኙ።
ማሳሰቢያ፣ ተማሪዎች ዩኒፎርም መልበስ አለባቸው
መምህራን መታወቂያቸውን መያዝ አለባቸው
በስልጠናው ላይ የሚሳተፉት ማን ማን እንደሚሆኑ ደብዳቤ መያዝ አለባቸው

Arada education office

01 Nov, 11:49


Photo from Desalegn Debele

Arada education office

01 Nov, 11:49


ማሳሰቢያ፡-
በክፍለ ከተማችን ስር ለሚትገኙ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የክዋኔ ማህደረ ተግባር ምዘናው የአራዳ በሙሉ ዳግማዊ ሚኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሲሆን የምዘና ቀናት ቅዳሜና እሁድ (ከ23-24/02/2017 ዓ.ም) መሆኑን አውቃችሁ በተባለው ት/ቤት በመገኘት እንድትመዘኑ እናሳስባለን፡፡

Arada education office

01 Nov, 11:17


አስቸኳይ መልዕክት

እንዴት ዋላችሁ

ትላንት በነበረን የተመዛኞች ኦረንቴሽን እና  ጥቅምት 09/2017 በዚህ ቴሌግራም ቻናል ባሳወቅነው መሰረት ከነገ ቅዳሜ 23_24/02/2017 ጀምሮ የክዋኔ ማህደረ ተግባር ምዘና የሚጀመር ስለሆነ

ከኮተቤ ዮኒቨርሲቲ ፕሮግራም ጋር በማጣጣም ቅዳሜና እሁድ የነበረው ስልጠና አራዳ ክ/ከተማ ቅዳሜ እሁድ ቂርቆስ በሚል ስለተሻሻለ በተቀራኒው ስልጠና የምትገቡት መምህራን አራዳ እሁድ ዳግማዊ ምኒልክ ቂርቆስ ደግሞ ምስራቅ ጎህ የተመደባችሁ ለመመዘን ስለሆነ

ስልጠና የማትገቡት ተመዛኞች ነገ ከ2:30  ጀምሮ ምዘና ስለሚጀምር በየክ/ከተማችሁ በተመደባችሁት መሰረት በት/ቤቱ በመገኘት የተመደባችሁበትን ክፍል በማየት ምዘናውን እንድታከናውኑ እየገለፅን

ትላንት የገለፅንላችሁ ያለፉ ተመዛኞች ቁጥራችሁ ውስን የሆነበት የትምህርት አይነት ወደ ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስለተመደባችሁ ስም ዝርዝራችሁን እስክንለቅ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን


ር/መምህራን ተመዛኝ መምህራንና ትምህርት አመራሮች በት/ቤታችሁም በማስታወቂያ ቦርድ ላይ በመለጠፍ አሳውቁ
በተጨማሪም ሁሉም ተመዛኝ የዚህ ቴሌግራም ቻናል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሊንኩን ሼር አድርጓቸው

https://t.me/licencingAradakirkos

እናመሰግናለን

ማሳሰቢያ:- የፕሮግራም ለውጥና አዲስ መረጃዎችን ስለምንለቅ ቴሌግራሙን ተከታተሉ

የመመዘኛ ጣቢያ አድራሻ

ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አራት ኪሎ
ከአራዳ ክ/ከተማ የምትመጡ ተመዛኞች


ምስራቅ ጎህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ካሳንቺስ ቶታል   ፊት ለፊት
ከቂርቆስ ክ/ከተማ የምትመጡ ተመዛኞች

Arada education office

01 Nov, 07:39


ቀን 22/02/2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ር/መምህራን በሙሉ፡-
በዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መፅሐፍት እየተሰራጨ በመሆኑ ሰው በመላክ መፅሐፍት ዛሬውኑ እንድትወስዱ እያሳሰብን ከዛሬ በስተቀር መፅሐፍት የማንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

Arada education office

01 Nov, 05:50


ብሐራዊ ቤተ መንግስት
ትምህርት ብልጭታ
መሃል ግንፊሌ
አፍሪካ ቁጥር 1
ገነት አፀደ ህፃናት
ኢትዮጵያ እድገት
ደግማዊ ሚኒልክ መሰናዶ
አበበችጎበና
ቤተሊሂም
ቅለም ወርቅ
መስከረም 2ኛ ደረጃ

Arada education office

01 Nov, 05:13


ሰላም ወንድምና እህቶች
በየትምህርት ቤታችሁ የጥቅምት ወር ደሞዝን በአዲሱ ስኬል መሰረት ሰርታችሁ እንድትልኩ ለሰው ሃይል ባለሙያዎች በፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሓይል ጽ/ቤት በኩል እስከ ጥቅምት 2/2017 እንዲላክ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ምላሽ ያልሰጣችሁ በመሆኑ ደሞዝ ለመስራት አስቸግሯል፡፡ ስለሆነም ርእሳነ መምህራን የየራሳችሁ ት/ቤት በትክክል መሰራቱን አረጋግጣችሁ እስከ ዛሬ ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም አስከ ቀኑ 5፡00 ተጠናቆ ለክፍለከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ ገቢ እንድታደርጉ እያሳወቅን የማይልክ ትምርት ቤት ለሚፈጠረው ችግር ሃላፊነቱን በራሱ የሚወስድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

Arada education office

01 Nov, 02:46


ቀን፡21/02/2017
ማስታወቂያ
ለሁሉም የ12ኛ ክፍል አስፈታኝ ት/ቤቶች እና በግል ለተፈተናችሁ ተፈታኞች በሙሉ
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያስፈተናችሁ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና በግል ለተፈተናችሁ ተፈታኞች የውጤት ካርድ ስለመጣ እስከ ከ 22/02/2017 ድረስ ብቻ አንድትወስዱ ፡፡ ትምህርት ቤ/ቶች የትምህርት ቤቱ ር/መምህራን ወይም በደብዳቤ የተወከለ ሰው መጥቶ እንዲወስድ እናሳስባለን፡፡

Arada education office

01 Nov, 01:50


አስቸኳይ የስልጠና ፕሮግራም ማሻሻያ መልክት
==============================
አማርኛና አፋን ኦሮሞን እንደ 2ኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ መምህራን ስልጠና ለሁለት ቀን (23-24/02/2017) ያልነው ወደ 1 ቀን ስለተቀየረ ክ/ከተሞች ከዚህ ቀጥሎ በወጣላችሁ ፕሮግራም መሠረት ሰልጣኞችን ትልኩልናላችሁ
ቅዳሜ:- አዲስ ከተማ ፣አራዳ ፣ኮልፌ ፣የካ እና ጉለሌ
እሁድ:- ልደታ፣ ቦሌ፣ አቃቂ፣ ን/ስልክ፣ ለሚኩራ፣ ቂርቆስ፣ መነንና ገላድ አዳሪ
የቦታ ለውጥ የለም እዛው ኮተቤ የት/ት ዩኒቨርሲቲ ነው

Arada education office

30 Oct, 14:17


ቀን 20/02/2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት የመ/ደረጃ ት/ቤት ር/መምህራንና ለሁሉም የግል ት/ቤት ር/መምህራን በሙሉ
በቀን 21/02/2017 ዓ.ም ቀኑ 8 ሰዓት ላይ የውይይት መድረክ የተዘጋጀ በመሆኑ ትምህርት ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ ላይ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።

Arada education office

30 Oct, 14:12


በአራዳ ክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የሚከናወነውን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የተመለከቱ የምዝገባ ቅድመ ሁኔታዎች
1. የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ መላው ትምህርት ቤቶች ከ5 አመት በላይ ያሉ ተማሪዎችን፣ መምህራንን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችን፣ የምገባ ማዕከላት ሰራተኞችን የመመዝገብ ዘመቻ ላይ ያተኮረ ነው፤
2. የምዝገባው ሂደት ስልክ ቁጥር አስፈላጊ በመሆኑ ስልክ የሌላቸው ልጆች በወላጆች ወይም በአሳዳጊዎች ስልክ እንዲመዘገቡ ይደረግ፤
3. እድሜያቸው ከ 5- 16 የሆኑ ተመዝጋቢዎች የፍቃድ መስጫ ቅጽ በወላጅ ወይም በአሳዳጊ መሞላት ስላለበት ከምዝገባው አንድ ቀን አስቀድሞ የምዝገባ ቅጹን ለወላጆች በመላክ ተሞልቶ ወደ ትምህርት ቤት ይላክ፤ (መምህራን እና ርዕሰ መምህራን የልደት ምዝገባ ወረቀቱ የልጆቹ ስለመሆኑ እንዲሁም የፍቃድ መስጫ ቅጹ በወላጆች በትክክል ስለመሞላቱ በማረጋገጥ ይኖርባቸዋል)፤
4. ከ5 እስከ 16 ዓመት የሆኑ ተመዝጋቢዎች የወላጅ ወይም የአሳዳጊ መታወቂያ ኮፒ ይዘው መገኘት አለባቸው፤
5. እድሜያቸው ከ16 በላይ የሆኑ ወጣቶች ለመመዝገብ የሚያስፈልገውን የፍቃድ መስጫ ቅጽ እራሳችው በመሙላት መመዝገብ ይችላሉ፤
6. ወላጆች አስቀድመው ከተመዘገቡ የፋይዳ ቁጥራቸውን በፍቃድ መስጫ ቅጹ ላይ መሙላት ይኖርባቸዋል፤
7. በክረምት ዘመቻ የልደት ምዝገባ መከናወኑ ይታወሳል፤ የልደት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው በሙሉ ምስክር ወረቀቱን በማምጣት እንዲመዘገቡ መረጃው ይውረድ፤ የልደት ምዝገባ ምስክር ወረቀት የሌላቸው ብቻ በትምህርት ቤት መታወቂያ ይመዝገቡ፤
8. የዘገየ የፋይዳ መለያ ቁጥር ማረጋገጫ ወደ ስልካቸው በአጭር የስልክ መልዕክት (SMS) ለማስላክ እባክዎን id.et/help ወይንም 9779 ይጠቀሙ፤
9. .የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ሂደት ክፍያ የለውም፣ ዲጂታል መታወቂያ ማለት ባለ 12 አሀዝ ልዩ ቁጥር በመሆኑ ካርድ ማሳተም ግዴታ አይደለም፤

Arada education office

30 Oct, 09:56


አስቸኳይ መልዕክት

በአራዳና ቂርቆስ ክ/ከተማ ስር ለምትገኙ ርዕሰመምህራን እና መምህራን በሙሉ

ግንቦት 2/ 2016ዓ.ም ላይ የመምህራንና የትምህርት አመራር የሙያ ብቃት የፅሁፍ ምዘና መስጠታችን ይታወቃል።

በተሰጠው የፅሁፍ ምዘና ውጤት መሰረት 62.5 እና በላይ ያመጡ የመምህራንና ትምህርት አመራሮች የክዋኔ ማህደረ ተግባር ምዘና ለማካሄድ ለተመዛኞች ኦሬንቴሽን ስለሚሰጥ ሐሙስ ማለትም በ21/2/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የት/ቤት ር/መምህራን መልዕክቱን እንድታደርሷቸው እያልን ጥሪውን በት/ቤቱ የማስታወቂያ ቦርድ ላይ በመለጠፍ በሰአቱ እንዲገኙ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እውቅና ፈቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት

አራዳና ቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Arada education office

30 Oct, 08:42


ቀን 20/02/2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት እና የግል ት/ቤት ር/መምህራን በሙሉ
በ2016 ዓ.ም የሙያ ብቃት ምዘና ተመዝነው 62.5 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ሐሙስ ማለትም በ21/2/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በማህደረ ተግባር ዙሪያ ኦሬንቴሽን ስለምሰጣቸው የት/ቤት ር/መምህራን መልዕክቱን እንድታደርሷቸው እያልን ጥሪውን በማስታወቂያ ቦርድ ላይ በመለጠፍ መምህራን እንድገኙ አድርጉዋቸው።

Arada education office

28 Oct, 11:14


በድጋሚ
ለአራዳ ክ/ከተማ የመንግስት ት/ቤቶች በሙሉ
የሙያ ፍቃድ ፖርት ፎሊዮ መዛኝ መምህራን የሙያ ፍቃድ ያለቸውን ዲግሪና ማስተርስ ያለቸው እንድመዘገቡ ማሳወቃችን ይታወቃል። በመሆኑም የተፈለገው የሰው ሀይል ያልተሟላ ስለሆነ
ጂኦግራፊ 2 ፣ አማርኛ 4፣እንግሊዘኛ 8፣ ስቴቲክስ 1፣ አርት 1፣ አ/ሳይንስ 1፣ ISS 1 ሙዚቃ አፋን ኦሮሞ 1፣ ቋንቋ ለአማርኛ 1፣ አፋን ኦሮሞ enviromental Science ፣ 1፣ ነገ እስከ 6:00 መምህራን ልማት መጥተው እንዲመዘገቡ በድጋሚ በማስታወቂያ እንድታሳውቁልን እንጠይቃለን ።

Arada education office

28 Oct, 05:12


ቀን 18/02/2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶች በሙሉ
አፋን ኦሮሞ እና አማርኛ ትምህርት እንደ ሁለተኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ መ/ራን ስም ዝርዝር እስከ 8፡ 00 ሰዓት ድረስ ለስርዓተ ትምህርት ቡድን እንድታሳውቁ እናሳስባለን፡፡
መልካም የስራ ቀን!!!

Arada education office

24 Oct, 15:42


👍አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ:-
👍የስብሰባ ቀን ዓርብ 15/2/2017ዓ.ም
👍ሰዓትን=7:30
👍ቦታ =ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት
👍ተሳታፊዎች=ሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህራን

Arada education office

23 Oct, 16:04


ለአራዳ ክ/ከተማ የመንግስት ት/ቤቶች የሙያ ፍቃድ ፖርት ፎሊዮ መዛኝ መምህራን የሙያ ፍቃድ ያለቸውን ዲግሪና ማስተርስ ያለቸው ነገ እስከ 6:00 መምህራን ልማት መጥተው እንዲመዘገቡ በማስታወቂያ አሳውቁልን አሰቸኳይ ነው።

Arada education office

23 Oct, 11:30


በቦሌ ክ/"ከተማ ተጠርቶ የነበረው የሰው ሀይል ቡድን መሪዎች ስብሰባ ስለቀረ ር/መምህራን በእናንተ በኩል ጥሪው መሠረዙ ይነገራቸው።

Arada education office

23 Oct, 05:19


ለሁሉም የመንግስት ተ/ቤት ር/መምህራን
ነገ ጥዋት 2፡30 የት/ቤት የሰው ሀይል ቡድን መሪዎች ቦሌ ክፍለ ከተማ ስብሰባ ላይ እንድገኙ በእናንተ በኩል ጥሪው እንድደርሳቸው አድርጉ፡፡
መልካም ቀን!

Arada education office

20 Oct, 08:32


የሰዓት ማስተካከያ መደረጉን ማሳወቅን ይመለከታል። ለሰኞ ጥዋት 3፡00 የተጠራው ስብሰባ ወደ ከሰዓት 7:30 የተቀየረ በመሆኑ የተጠራችሁ በሰዓቱ ተገኙ።

Arada education office

19 Oct, 19:04


የስብሰባ ጥሪን ይመለከታል
በቀን 11/2/2017 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም እና የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ በጋራ ግምገማ ይደረጋል። በዚህም መሰረት
1ኛ. የመንግስት ት/ቤት ሁሉም ዋና ር/መምህራን
2ኛ. የ2ኛ ደረጃ ሁሉም ሱፐርቫይዘሮች
3ኛ. የመ/ደረጃ ክላስተር አስተባባሪዎች
ሰኞ 3፡00 ት/ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ እንድትገኙ እናሳስባለን። መቅረትና ማርፈድ በፍፁም የተከለከለ ነው። በተደጋጋሚ ስብሰባ ላይ የማትገኙ አመራሮች ጽ/ቤቱ ለሚወስደው እርምጃ ተጠያቂ የማንሆን መሆኑን እየገለፅን ም/ር/መምህራን የሒሳብና እንግሊዘኛ ቀን በዕለተ ሰኞ ተግባራዊ መሆኑን እንድከታተሉ አድርጉ። ሶስት ሰዓት የሚጀመርበት መሆኑን አውቃችሁ በሰዓት ተገኙ።

Arada education office

19 Oct, 12:21


አስቸኳይ መልዕክት

በአራዳና ቂርቆስ ክ/ከተማ ስር ለምትገኙ ርዕሰመምህራን በሙሉ

ግንቦት 2/ 2016ዓ.ም ላይ የመምህራንና የትምህርት አመራር የፅሁፍ ፈተና መስጠታችን ይታወቃል።

የፅሁፍ ፈተና ውጤት የደረሰ በመሆኑ መጥታችሁ እንድትወስዱ  የት/ቤት ር/መ/ር በድንቅ ስራ ህንፃ 7ኛ ፎቅ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እውቅና ፈቃድ እድሳት ዳይሬክቶሬት በመገኘት ከመምህራን ሙያ ብቃት ባለሙያዎች በስማቸው በፖስታ የታሸገውን የተፈታኞች ውጤት በቁጥራቸው ልክ በመረከብ በቀን 11/02/2017ዓ.ም ለተፈታኞች እንደታሸገ እንድትወስዱ እያሳሰብን

1. ውጤታችሁ ላይ ቅሬታ የሚኖራችሁ መምህራንና የትምህርት አመራር በተያያዘው የቅሬታ ማቅረቢያ ፎርም በመሙላት እንድታቀርቡ

2. ተፈትነው ስም ዝርዝራቸው ያልተገኙ ካሉ ለማመሳከር እንዲመች ር /መ/ራን ወደ ተቋማችን ስትመጡ በት/ቤታችሁ ምዘናውን የወሰዱ አካላት መረጃን በማጥራት ይዛችሁ እንድትገኙ (ከስራ ክፍሉ ከተያዘው ጋር ለማመሳከር )

3. ውጤታችሁ በመረከብ ከ62.5 በላይ ያመጣችሁ ተፈታኞች የማህደረ ተግባር ፈተና ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ስለሚሰጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታካሂዱ እናሳስባለን።

ስልክ ሲደወል ስልካቸው ያልሰራ ር /መ/ራን ስለአጋጠመን መረጃው እንዲደርስ ይህን መልዕክት ያያችሁ አካላት መረጃውን  ለር/መ/ራን አካፍሉ


የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እውቅና ፈቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት

አራዳና ቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Arada education office

16 Oct, 17:22


የስብሰባ ጥሪን ይመለከታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ የሂሳብ እና እንግሊዘኛ ትምህርት ውጤት ለማሻሻል ስትራቴጂ በመንደፍ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወቃል፡፡ በዚህም ትግበራውን ለመከታተል የሱፐርቪዥን ቡድን በማዋቀር የትምህርት ተቋማት ክትትል መደረጉ ይታወቃል።በመሆኑም በቀን  08/02/2017 ዓ.ምከቀኑ 7፡00 ሰዓት በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ በቢሮ ኃላፊ የሚመራ ውይይት ስለሚከናወን
1ኛ. የመንግስት 1ኛ መካከለኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ዋና ርዕሳነ መምህራን ፤ 2ኛ.የክፍለከተማ እና ወረዳ ሱፐርቫይዘር አስተባባሪዎች
3ኛ. ድጋፍና የክትትል ስራ ላይ የተሳተፋችሁ በተባለው ቀን እንዲትገኙ እናሳስባለን፡፡
መቅረትና ማርፈድ አይቻልም።
ሰዓት ይከበር
ት/ጽ/ቤት

Arada education office

13 Oct, 19:29


ለመንግስት ት/ቤት ር/መምህራን
የሂሳብ እና እንግሊዘኛ የትምህርት ዓይነቶች በተመለከተ ከጥቅምት 4 ጀምሮ ድጋፍና ክትትል የሚያደርጉ ባለሙያዎች ወደ ተቋማችሁ የሚመጡ በመሆኑ አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉላቸው እንጠይቃለን።

Arada education office

13 Oct, 19:24


ለሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤት ር/መምህራን ጥቅምት 4 የሰንደቅ ዓላማ ቀን በመሆኑ ዕለቱን አስመልክቶ በተለያዩ ፕሮግራሞች እንድታከብሩ እናሳስባለን።

Arada education office

12 Oct, 12:50


ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶች የሂሳብና የእንግሊዘኛ ትምህርትን ማሻሻል ከመምህሩ እስከ አመራሩ ጭምር አንዱ የተሙማ ዕቅድ ሆኖ እንዲሰራበት ከወዲሁ እናሳስባለን።

Arada education office

12 Oct, 12:50


ሂሳብና እንግሊዝኛ በት/ት ዘመኑ የት/ት ማህረሰቡ የርብርብ መአከል ሆኖ በትኩረት ይሰራበታል ይህ ማለት የሌላ ሳብጀክት መምህራኖች በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ የCPD ፍላጎት ለይተው ያቅዳሉ ይተገብራሉ ምክንያቱም እንደስሙ ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ስራ ስለሆነ።

Arada education office

09 Oct, 16:50


ለመንግስት ት/ቤቶች የኦን ላይን ተማሪን መረጃን ለማጥራት የክፍል ድልድል ለመሰራት የመምህራን መረጃ ለማሰገባት ነገ 30/1/17  ከሰአት 8:00 ላይ ሰልጠና ሰለምንሰጥ 1ኛ.ምዝገባውን ሲከታተል የነበረ 1 ር/መምህር 2ኛ.ምዝገባውን ሲከታተል የነበረ 1 የict ባለሙያ ወይም  ተወካይ እንድትገኙ እያሳሰብን መቅረት የማይቻል መሆኑን እንገልጻለን ት/ጽ/ቤት
ቦታ ት/ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ

Arada education office

25 Sep, 11:32


ለወረዳ ት/ጽ/ቤቶችና ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ር/መምህራን በቢጋሩ መሰረት በተባለው ቀን በሀርድና በሶፍት ኮፒየ 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እንድትልኩ እናሳስባለን።

8,713

subscribers

4,033

photos

43

videos