ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC @mistirekewakibt Channel on Telegram

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

@mistirekewakibt


ምን አይነት ስራ ብሰራ ይዋጣልኛል? ከማን ጋር ብጣመር አሪፍ ነው ? በዋናነት ደግሞ እኔ ምን አይነት ባህሪ ነው ያለኝ የሚሉትን እና ሌሎች ጥያቄዎችን ለመመለስ አስትሮሎጂ ቁጥር አንድ ተመራጩ ነው። ይሄ ቻናል በዋናነት ስለ አስትሮሎጂ የሚያወራ ነው ጆይን በሉ።

ጥያቄዎችን ለመጠየቅ እና ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ በእዚህ አናግሩን 👉 @Nebazelideta
ለ cross 👉 @Ne113

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC (Amharic)

ሚስጥረ ከዋክብት ከዚህ ይፈቅር። በዚህ ቻናል ከላይ የሚለቅሰው የአስትሮሎጂ ምርጥ ዝውውር መሆኑን ይፈልጋል። የአስትሮሎጂ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ እና ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ በዚህ ቻናል የሚያደርጉን ዝውውሮችን ከጆይን እና ሌሎች ቴሌግራም ተመልከቱ። እናገራለን ጆይን ገላጭና ሁኔታ ቴሌግራም በምርጫ ለመከላከል ወይም በሚጠቀሱ ቴሌግራሞችን ለመቀጠል እና ተጨማሪ ነገሮች እዚህ፣ ሌሎችም በ cross ቆሞ የቀረቡና በአምስተኛው ወር የተከፈቱ ዜሮ ቴሌግራሞች ለመረጋጋ ገለጹ። እናውራረጃለን አወዳድሮ ከሆኖ፣ አሁን ከእርስዎ ዝውውሮች ገምጸና ያድርጉ።

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

22 Nov, 16:26


በቶሎ ወደጋብቻ የሚገቡ ኮኮቦች ከአንድ እስከ አምስት በደረጃ

፩.ሐመል እሳት (ኤሪስ)፦ ኤሪሶች ስሜታዊ እና በስሜታዊነታቸው የሚታወቁ ኮኮብ ነው፣ ብዙውን ጊዜ በግንኙነት ውስጥ መጀመሪያ ጠልቀው ይገባሉ እናም ጋብቻ ለመፈፀምም ፈጣን ናቸው።

፪.ሠውር መሬት (ቶረስ)፦ መረጋጋት እና የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነትን ከፍ አድርጎ የሚመለከት ነው፣ ይህም ከታማኝ አጋር ጋር ቀደም ብለው አግብተው እንዲቀመጡ ያደርጋቸዋል።

፫. ሸርጣን ውሃ(ካንሰር) ፦ቤተሰብን ያማከሉ እና ተንከባካቢዎች ናቸው ።ካንሰሮች የስሜት ደህንነት ይፈልጋሉ እናም ከዚህ በመነሳት በህይወታቸው መጀመሪያ ላይ ጎጆ ለመገንባት ይፈልጋሉ።

፬.ሚዛን ንፋስ (ሊብራ)፦ አጋርነትን እና ስምምነትን ይፈልጋሉ፣ ብዙውን ጊዜ ፍቅርን እና ጓደኝነትን ለማግኘት ቀድመው ወደጋብቻ ይገባሉ።

፭.አሰደ እሳት፦ ሊዮ ታላቅ ምልክቶችን እና ፍቅርን ይወዳሉ እና ብዙ ጊዜም ግንኙነታቸውን በማይረሳ ሰርግ ይፋ ለማድረግም ይፈልጋሉ።

በቀጣይ በምን ጉዳይ ላይ እንስራላችሁ ኮሜንት ላይ ፃፉልን

በእየቀኑ አስትሮሎጂ ቪዲዮዎች በየቀኑ እንዲደርሳችሁ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን follow አድርጋችሁ ተከታተሉን

https://www.tiktok.com/@mistrekewakibt?_t=8rbvEkNiyjI&_r=1

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

22 Nov, 14:41


በቶሎ ወደ ጋብቻ የሚገቡ ኮከቦች እነማን ይመስላችኋል?

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

21 Nov, 04:38


ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረበዓል በሰለም አደረሳቹ ❤️

በቻናላችን ሚስጥረ ከዋክብት ስም በዓሉ የሰላም የፍቅር እንዲሆንላቹ እንመኛለን መልካም በዓል

@MISTIREKEWAKIBT
@MISTIREKEWAKIBT
@MISTIREKEWAKIBT

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

19 Nov, 16:56


ስለ የዞዲያክ ምልክቶች 🔺 አስገራሚ እውነታዎች

🔵 ሊብራ ብቻ የዞዲያክ ግዑዝ ምልክት ነው።
🔵 ጀሚኒዎች የወንድማማችነት ፍቅር መገለጫዎች ናቸው።
🔵 ምርጥ ሚስት ከህብረ ከዋክብት ካንሰር ሴት ተደርጋ ትወሰዳለች።
🔵 በጣም ህልም ያለው ምልክት ፒሰስ ነው።
🔵 በጣም ወሲባዊው አሪየስ ነው።
🔵 በጣም ተንኮለኛው ስኮርፒዮ ነው።
🔵 በጣም ታማኝ - ታውረስ ፣ ቪርጎ።
🔵 በጣም ማራኪው ሳጅታሪየስ ነው።
🔵 ደግ የሆነው ታውረስ ነው።
🔵 እድለኛው ጀሚኒ ነው።
🔵 በጣም ራስ ወዳድ የሆነው ሊዮ ነው።
🔵 በጣም አነጋጋሪው ሊብራ ነው።
🔵 በጣም ሚስጥራዊ የሆነው Capricorn ነው።
🔵 በጣም ጎበዝ አኳሪየስ ነው።
🔵 አሪየስ ከሌሎች ይልቅ አጋራቸውን ያታልላሉ።
🔵 ታውረስ ከሌሎች ምልክቶች ይልቅ ከመጠን በላይ ውፍረት የተጋለጠ ነው።
🔵 የአኳሪየስ ጣእም በጣም የተለየ ስለሆነ ከየትኛውም ማዕቀፍ ጋር አይጣጣምም።

ድጋፋቹ አይለየን 👍

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

17 Nov, 10:58


ስለ ሁሉም ኮኮቦች በሰፊው እንድታውቁ ይሄንን አንብቡ የፈለጋችሁትን ኮኮብ እየመረጣችሁ


ኤሪስ (ሐመል እሳት) ክፍል ፩👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5918

ኤሪስ(ሐመል እሳት) ክፍል ፪👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5925

ኤሪስ(ሐመል እሳት) ክፍል፫ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5926

አኳሪየስ(ደላዊ ንፋስ) ክፍል ፩ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5931

አኳሪየስ(ደላዊ ንፋስ) ክፍል ፪ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5935

አኳሪየስ(ደላዊ ንፋስ) ክፍል ፫ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5940

ፓይሰስ(ሁት ውሃ) ክፍል፩ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5942

ፓይሰስ(ሁት ውሃ) ክፍል፪ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5943

ፓይሰስ(ሁት ውሃ) ክፍል፫ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5951

ካፕሪኮርን(ጀዲ መሬት) ክፍል ፩👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5966

ካፕሪኮርን(ጀዲ መሬት) ክፍል ፪👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5968

ካፕሪኮርን(ጀዲ መሬት) ክፍል ፫👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5972

ሠውር መሬት  (ቶረስ) ክፍል ፩👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5987

ሠውር መሬት  (ቶረስ) ክፍል ፪👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5988

ሠውር መሬት  (ቶረስ) ክፍል ፫👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/5991

ሰንቡላ መሬት (ቪርጎ) ክፍል፩ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6006

ሰንቡላ መሬት (ቪርጎ) ክፍል፪ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6008

ሰንቡላ መሬት (ቪርጎ) ክፍል፫ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6012

አሰደ እሳት (ሊዮ) ክፍል፩👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6015

አሰደ እሳት (ሊዮ) ክፍል፪👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6019

አሰደ እሳት (ሊዮ) ክፍል፫ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6020

አቅራብ ውሃ(ስኮርፒዮ) ክፍል ፩ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6023

አቅራብ ውሃ(ስኮርፒዮ) ክፍል ፪ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6024

አቅራብ ውሃ(ስኮርፒዮ) ክፍል ፫ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6027

ሚዛን ንፋስ(ሊብራ) ክፍል፩👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6028

ሚዛን ንፋስ(ሊብራ) ክፍል፪👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6029

ሚዛን ንፋስ(ሊብራ) ክፍል፫👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6030

ሳጁታሪየስ (ቀውስ እሳት) ክፍል ፩👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6043

ሳጁታሪየስ (ቀውስ እሳት) ክፍል ፪👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6045

ካንሰር(ሸርጣን ውሃ) ክፍል ፩👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6056

ካንሰር(ሸርጣን ውሃ) ክፍል ፪ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6058

ጄሚናይ (ገውዝ ንፋስ) ክፍል ፩ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6062

ጄሚናይ (ገውዝ ንፋስ) ክፍል ፪ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6063

ጄሚናይ (ገውዝ ንፋስ) ክፍል ፫ 👇

https://t.me/MISTIREKEWAKIBT/6066

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

17 Nov, 06:13


ሲንግል የሆናችሁ ኮሜንት ላይ መፃፍ እንዳይረሳ 😜

እንዚህ አይነት አዝናኝ የቲክቶክ ቪዲዮዎች እንዲደርሳችሁ ይሄንን 👇👇👇 እየነካችሁ ፎሎ አርጉ

https://www.tiktok.com/@mistrekewakibt?_t=8rShTnxP3m3&_r=1

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

10 Nov, 17:00


ክፍል፬

የውሃ ኮኮቦች

የውሃ ኮኮብ ያላቸው ሰዎች ልክ እንደ ኮከባቸው እንደ ውሃው ሁሉ ጥቂት ነገር ይበቃቸዋል:: በጥቂት ነገር መናወጥ እና መደነቅ ያብዛሉ። በዚህም ምክንያት ለደህንነታቸው ቅድሚያ ይሰጣሉ። ቀንድ አውጣን ይመስል ትንሽ ነገር በተነከሳቸው ጊዜ ፈጥነው ወደዛጎላቸው ይገቡና ከዚያ በሁዋላ የሚይገኙ ይሆናሉ። ስሜታቸው በትንሽ ነገር ይጎዳል።

የካንሰር፣ የስኮርፒዮም ሆነ የፓይሰስ ከኮብ ያላቸው ግለሰቦች በጣም ስሱ እና በጣም ስሜታዊ የሆኑ ናቸው። ስሜታቸው ጥልቅ ነው።በአእምሯቸው ሳይሆን በስሜታቸው ነገሮችን ሁሉ ገልጸው ማየት ይችላሉ:: ይህ ተፈጥሯቸው ትንግርታዊ ነው :: ትከሻቸው በሚነግራቸው ይንቀሳቀሳሉ። ህልማቸውም ከመሬት ጠብ አይልም።

አዛኝ እና የሌሎችን ሀዘንና ደስታ፣ ጭንቀትና ተስፋ በቀላሉ መረዳት የሚችሉ ናቸዉ። የራሳቸውን ሰው እንደ አራስ ነብር ከማንኛውም ጠላት ተዋድቀው መጠበቅ ይችላሉ። በአእምሯቸው ሳይሆን በልባቸው ያስባሉ። እግራቸው እርጥብ ነው።

የእሳት፣ የመሬት፣ የንፋስ እና የውሃ ኮኮቦች አጠቃላይ ባህሪ ከላይ የተመለከተውን ይመስላል። እርስ በርሳቸው ያላቸውን ግንኙነት ደግሞ በአጭሩ እንመልከት።

ብዙ ዝርዝር ውስጥ ሳይገባ እሳት ከንፋስ ይገጥማል፣ መሬት ደግሞ የተሻለ ከውሃ ይስማማል።

እሳትን፦ አየር ያቀጣጥለዋል ፣ ውሃ ያጨፋዋል፣ መሬት ይገድበዋል ::

መሬትን፦ ውሃ ያለመልመዋል፣ እሳትና ነፋስ ያደርቁታል ::

አየርን፦ እሳት ይፈልገዋል ፤ ውሃናመሬት ይገድቡታል።

ውሃን፦ መሬት ይይዘዋል ፤ አየርና እሳት ያሟጥጡታል፡

ኮከቦችን ከእሳት፣ ከመሬት ፣ ከንፋስ እና ከውሃ ንጥረነገር አንፃር ስንመረምር ልንጠነቀቅበት የሚገባን ጉዳይ አለ:: አንድ ግለስብ ዋናው ኮከቡ የእሳት ሆኖ (ኤሪስ፣ሊዮ ወይም ሳጅታሪየስ )በልደት ሰንጠረዡ ውስጥ ግን ከአራቱ ንጥረ ነገሮች ውስጥ በዛ ብለው የሚታዩት የውሃ ኮኮቦች ሊሆን ይችላሉ። ስለዚህ ግለሰብ መፈረጅ ያለበት በውሃ ኮከብ ነው። በሌላ መልኩ ደግሞ የግለሰቡ ዋና ኮከብ የውሃ ሆኖ የልደት ሰንጠረዡ ግን በአመዛኙ የንፋስ ኮኮቦች የሞሉበት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ የአንድን ሰው ኮከብ በቅጡ ለመገንዝብ ከዋናው ኮከብ ይልቅ ሙሉ ሰንጠረዡን ሰርቶ ወይም አሰርቶ ማየት የበለጠ ተመራጭ እና አስተማማኝ ይሆናል። በነገራችን ላይ ተሻለ የታደለ ኑሮ የሚኖሩ ሰዎች የልደት ሰንጠረዣቸው ውስጥ የእሳት፣ የመሬት የንፋስ እና የውሃ ኮኮቦች በተመጣጠነ ቁጥር ተሰባጥረው ይታያሉ።

በልደት ሰንጠረዥ ውስጥ ያልተመጣጠነ የንጥረ - ነገሮች ስርጭት ሲንኖር ግለሰቡ ወደ አንድ ጎን ያጋደለ ህይወት ሲመራ ይስተዋላል። ብዙ እሳት ያለው ፈጣን እና <ያራዳ ልጆች እነ ድንጋይ ኳሱ ከምኔው ተጩሆ ከምኔው ደረሱ> የሚባልለት አይነት ይሆናል።ጥቂት ወይም ምንም የእሳት ኮኮብ ያለው ሰው ደግሞ ወደ ድርጊት ለመግባት ብዙ ቆሶቋሽ የሚፈልግ ቀሰስተኛ ይሆናል። ብዙ መሬት ያለው ለሚበላና ለሚጠጣ፣ ለቁሳቁስና ለገንዘብ ብቻ ሲራወጥ ይታያል። ጥቂት ወይም ምንም መሬት ኮኮቦች የሌሉት ከሆነ ደግሞ ኑሮውን በቅጡ ለመምራት ብዙ ጥንቃቄና ጥረት የሚያስፈልገው ይሆናል። ብዙ የንፋስ ኮኮቦች ያለው ተናግሮ ማሳመን የሚችል መሪ ወይም የሥራ አስኪያጅ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ዜሮ ወይም ጥቂት የንፋስ ኮከብ ካለው ሰው ጋር ተነጋግሮና ተወያይቶ ስምምነት ላይ ለመድረስ ያስቸግራል። ከዚህ ሰው ጋር የሚደረግ ውይይት ሁሉ በጥቁር ድንጋይ ላይ የፈሰሰ ውሃ ነው ብትሉት ይሻላል። ብዙ የውሃ ኮኮቦች በልደት ሰንጠረዥ ውስጥ ያለው ሰው በጣም ስሜታዊ የሆነ አዛኝ ፣ አዳማጭ እና የተጨነቁትን አፅናኝ ይሆናል። የውሃ ኮኮቦቹ ያነሱበት ሰው ደግሞ ደረቅ፣ ርህራሔ አልባ እና ገደቢስ የሚሉት አይነት ሰው ይሆናል።

የሦስትዮሾችን ምደባ በዚሁ እናብቃ ነገ ወደ አራትዮሾች ምደባ እናመራለን።

በየቀኑ አዝናኝ ቪዲዮዎች ለማግኘት የቲክቶክ አካውንቴን follow ያድርጉ 👇👇👇

https://www.tiktok.com/@mistrekewakibt?_t=8qfUQ0i3r09&_r=1


         ምንጭ፦ የኢትዮጲያ ኮኮብ መፀሃፍ

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

08 Nov, 16:00


ክፍል ፫
የመሬት ኮኮቦች

የመሬት ኮኮብ ያላቸው ግለሰቦች ሁሉ ባህሪያቸው እንደኮከቸው መሬት ነው:: "እገሊት መሬት ናት ወይም አገሌ መሬት ነው "ብለን የምንገልጻቸው ሰዎች በአብዛኛው የመሬት ኮኮብ ባለቤቶችን ነው። ለማወደስም ሆነ ለመውቀስ ፣ለመቆጣትም ሆነ ለመደስት አይቸኩሉም። በጣም ትእግስተኛ እና አስተዋይ ናቸው። ከዛሬ አላፊ ደስታ ይልቅ ለነገ እና ለተነገ ወዲያው ዘላቂ ጥቅም ይተጋሉ። ቶረስ፣ ቪርጎ ወይም ካፕሪኮርን ኮከብ ያለው ሰው ባስቀመጥንበት የምናገኘው አስተማማኝ ፍጡር ነው::

የመሬት ኮብቦች ረጋ ያሉ እና ሁሉንም ነገር በጥንቃቄ የሚያዩ እና የሚይዙ ሰዎች ናቸው:: ነገን የሚጸጸቱበትን ነገር ዛሬ አያደርጉም። አስቀድመው ሳያመዛዝኑ እርምጃ አይመስዱም። በእንቅስቃሴያቸው ሁሉ ዝግ ያሉ ናቸው። በአባካኝነት የማይታሙና እኔ ነኝ ያሉ ቆጣቢ ናቸው:: በዚህ ሳቢያ ብዙዎቹ ከችግርና ከረሃብ ፣ ከማጣትና እና የሰው እጅ ከማየት ርቀው ይኖራሉ:: የዚሁ ሁሉ መነሻው ከመንፈሳዊነት ይልቅ ወደ ቁሳዊነት የሚያደላው ተፈጥሯቸው ነው።

የመሬት ኮኮቦች በኑሯቸው ውጤት ተኮር አይነቶች ሲሆኑ ምናልባት ከደማቸው የተዋሐደ የሚመስለው አባባል < ለወሬ የለውም ፍሬ> የሚሰኘው ብሂል ሳይሆን አይቀርም::

የንፋስ ኮኮቦች

የንፋስ ኮኮብ ያላቸው ግለሰቦች ንፋስ እንደሆነው ኮከባቸው ሁሉ ባህሪያቸውም ንፋስ ነው። እንደ < እፉየ ገላ > ሁሉ የሚጨበጡ አይደሉም። በሰሜን ሲሏቸው በደቡብ፣ በምስራቅ ሲሏቸው ደግሞ በምእራብ አቅጣጫ ሆነው የሚገኙ ናቸው። ኮከባቸው ተንቀሳቃሽ ነው። የቤት ሰዎች አይደሉም። ውጭውጭውን ያስወድዳቸዋል። አርፈው አይቀመጡም :: ቁንጥንጥ ናቸው። ኮከባቸውም ተንቀሳቃሽ አንቀሳቃሽ እና ዘዋሪ ነው።

የጂሚናይ፣ የሊብራም ሆነ የኢኳሪየስ ኮኮብ ያላቸው ሁሉ አፍ የማያስከድኑ ተጫዋቾችና አንድበተርቱእ ተናጋሪዎች ናቸው ተፈጥሯቸው ጋግርታም እና ዝግ አይደለም። አንጎላቸው ክፍት ነዉ። ሐሳብን እንደ ፋብሪካ ማምረት ስለሚቻላቸው ጥሩ የሐሳብና የእቅድ አመንጪዎች ናቸዉ። ተጨባጭ ውጤት ላይ ሲመጣ ግን ደከም ይላሉ።

በልባቸው ሳይሆን በአእምሯቸው የሚያስብ ደረቆች ናቸው። ከስሜታዊነት በበለጠ ምክንያታዊነት ይገዛቸዋል ሰሜታቸው ስሱ የሆነን ወይም በጣም ጠንቃቃ የሆኑ ሰዎችን አይቀርቡም ከማንኛውም አይነት ሰው ጋር በቀላና በፍጥነት መግባባት ይችላሉ ። ወሬና ክርክር፣ ሙግትና ጭቅጭቅ የሚመዱ አይነት ናቸው።

የመሬትን እና የንፋስ ኮኮቦችን በእዚው አብቅተናል በቀጣይ የውሃ ኮኮቦች እና የሶስትዮሽ ምደባ ማጠቃለያይን እናቀርባለን

በየቀኑ አዝናኝ ቪዲዮዎች ለማግኘት የቲክቶክ አካውንቴን follow ያድርጉ 👇👇👇

https://www.tiktok.com/@mistrekewakibt?_t=8qfUQ0i3r09&_r=1


         ምንጭ፦ የኢትዮጲያ ኮኮብ መፀሃፍ

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

06 Nov, 17:03


ክፍል ሁለት

የሦስትዮሽ ምድብ

አስራ ሁለቱ ኮኮቦች በአራት የእሳት፣የመሬት፣የነፋስ እና የውሃ ምድብ ሲከፈሉ ሦስት ሦስት ሆነው ይጣመራሉ። በዚህም በዛ ያሉ የጋራ ባህሪዎቻቸውን እንማራለን።በጋብቻ ጥምረት ግርድፍ የሆነ አሰራርን የሚከተሉ የጥንቱ የአስትሮሎጂ ባለሙያዎች ባልና ሚስት ሁለት ወይም የእሳት፣የመሬት፣የነፋስ ወይም የውሃ ኮኮብ ቢኖራቸው ጥሩ ነው ብለው ይመከራሉ።ይህ አካሄድ ብዙ እውነት አለበት ።የፍቅርናየጋብቻ ጉዳይ ግን በዘመናዊው ኢስትሮጂ በዝርዝር ማቲማቲክስ የሚሠራ ነው። ወደ ዋናው ጉዳይ ግን በዘመናዊው አስትሮሎጂ በዝርዝር ማቲማቲክስ የሚሠራ ነው።ወደ ዋናው ጉዳይ እንመለስና ቀጥሎ ያለውን ምድብ እንመልከት

የእሳት ኮኮቦች

ኤሪስ 👉👉👉ሐመል እሳት
ሊዮ 👉👉👉 አሰድ እሳት
ሳጁታሪየስ 👉👉👉ቀውስ እሳት

የመሬት ኮኮቦች

ቶረስ 👉👉👉 ሰውር መሬት
ቪርጎ 👉👉👉 ሰንቡላ መሬት
ካፕሪኮርን 👉👉👉 ጀዲ መሬት

የንፋስ ኮኮቦች

ጄሚናይ 👉👉👉 ገውዝ ንፋስ
ሊብራ 👉👉👉 ሚዛን ንፋስ
አኳሪየስ 👉👉👉 ደላዊ ንፋስ

የውሃ ኮኮቦች

ካንሰር 👉👉👉 ሸርጣን ውሃ
ስኮርፒዮ 👉👉👉 ዐቅራብ ውሃ
ፓይሰስ 👉👉👉 ሁት ውሃ

የእሳት ኮኮቦች

የእሳት ኮከብ ያላቸው ሰዎች ተፈጥሯቸው ውስጥ የእሳት ባህሪ ይታያል። እንደ እሳት ሁሉ የቀዘቀት ሳይሆን ሞቅ ያለ ተፈጥሮ አላቸው:: ቆጣ ማለት የሚችሉና ኃይለኛ የሆኑ ተናጋሪዎች ናቸው። በገንዘብ አያያዛቸው ለነገ የማይሉ ቸሮችና አለፍም ሲል አባካኝ አይነት ናቸው። የሌሎችን ደጋፍ የማይፈልጉና በራሳቸው መንቀሳቀስ የሚችል ብርቱዎች ናቸው:: ደፋር እና ንቁ በመሆናቸው ምክንያትም የነገሮች ሁሉ ጀማሪ የሆኑ ፋናዎጊዎች ናቸው። ለህይወት ያላቸው አመላካከት ብሩህ የሆነና በተስፋ የተሞሉ ሲሆኑ በጣም ጉጉ የሆኑ ፍጡሮች ናቸው። ፍንድቅድቅያለው ባህሪያቸው ፎልፍላ እና ከሁሉ ተግባቢ ያደርጋቸዋል ፈጣንነታቸው በብልህትና በችኮላ የተሞላ ነው :: ዝቅ እና ቅዝቅዝ ለሚሉ ሰዎች ትዕግስት የላቸውም ችኩልነታቸው አሁን ተጣልተው ወዲያው ያቅር የሚሉ ያደርጋቸዋል ::

ብሩህ አእምሯቸው በብዙ ስራ ሁለገብ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል:: የእሳት ባህሪያቸው ዙሪያቸው ሁሉ የሚያምቁ ፍጡሮች እንዲሆኑ ይረዳቸዋል። በዚሁ እንደ እሳት በሚቀላቀል ተፈጥሯቸው ሌሎችን ወደ ድርጊት በቀላሉ ማነሳሳት የሚችል ቆስቋሾች ያደርጋቸዋል።

ኤራስ፣ ሊዮም የሳጅታሪየስ ኮኮብ ያላቸው ሁለ ጀብደኞችና አስተማማኝ ጉባት ያለ ሀይለኛ ሰዎች ናቸው:: ብልህና አዋቂዎች ስለትም በፈጠራ ሥራ የተሳካላቸው ይሆናሉ።

የእሳትን በእዚሁ ጨርሰናል በቀጣይ የመሬት ኮኮቦችን ይዘን እንመጣለን እስከዛ like and share ማድረጋችሁን አትዘንጉ ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ ኮሜንት አድርጉልን እስከ በየቀኑ አዝናኝ ቪዲዮዎች ለማግኘት የቲክቶክ አካውንቴን follow ያድርጉ 👇👇👇

https://www.tiktok.com/@mistrekewakibt?_t=8qfUQ0i3r09&_r=1


ምንጭ፦ የኢትዮጲያ ኮኮብ መፀሃፍ

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

05 Nov, 17:00


የኮኮብ ምደባዎች

ክፍል አንድ

አስራ ሁለቱ ኮብቦች በሦስት ዘርፍ እየተለዩ ይመደባሉ እነሱም በሁለትዮሽ፣ በሦስትዮሽ እና በአራትዮሽ ነው ። ሁሉንም አንድ በአንድ እናያቸዋለን ለዛሬ ግን የሁለትዮሽን ይዘን መጥተናል

ሁለትዮሽ

አስራ ሁለቱ ኮኮቦች ኔጋቲቭ እና ፖዘቲቭ ወይም ደግሞ አንስታይ እና ተባእታይ ተብለው በሁለት ይከፈላሉ። ተባእታይ ያቦች ተናጋሪዎችና አቀባዮች ሲሆኑ አንስታይ ኮኮቦች ደግሞ አድማጮች ፣ ዝምተኞችና ተቀባዮች ናቸው። እዚህ ላይ ግን ጥንቃቄ ልናደርግ የሚገባን ተባእታይ ኮከብ ያላት ሴት መንዳወንድ ነች ማለት አይደለም። አንስታይ ኮኮብ ያለው ወንድም ሴት ሴት ነው ማለት አይደለም። የበላይና የበታችነትም በምድብ ውስጥ የለም

ተባእታይ ኮኮቦች ፦ ኤሪስ፣ ጄሚናይ፣ ሊዮ ፣ ሊዮ፣ ሊብራ ፣ ሳጁታሪያስ እና አኳሪየስ

አንስታይ ኮኮቦች፦ ደረስ፣ ካንሰር ፣ ቪርጎ፣ ስኮርፒዩ፣ካፕሪኮርን እና ፓይስስ ናቸው

በቀጣይ የሶስትዮሽን ይዘን እንመጣለን እስከዛ ያላችሁን ሃሳብ አስተያየት ፃፉልን በተጨማሪም ብዙ ሰዎች ጋር እንዲደርስ ላይክ እና ሼር ማድረግዎን አይዘንጉ።

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

03 Nov, 18:22


የእያንዳንዱ ምልክት 5 አወንታዊ ባህሪዎች

♉️አሪስ፡
- ደፋር;
- ዓላማ ያለው;
- ገለልተኛ;
- ስሜታዊ;
- ብሩህ ተስፋ።

♉️ታውረስ፡-
- አስተማማኝ;
- ታማኝ;
- እንክብካቤ;
- የተረጋጋ;
- የሚወደውን ነገር በተመለከተ ጠንክሮ መሥራት።

♊️ ጀሚኒ፡
- ወዳጃዊ;
- ገር;
- አስቂኝ;
- የሚችል;
- አፍቃሪ።

♋️ ካንሰር;
- ደግ-ልብ;
- ጥበበኛ;
- መደገፍ;
- ታማኝ;
- ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ።

♌️ሊዮ:
- ለጋስ;
- ስሜታዊ;
- ብልህ;
- ማራኪ;
- የሥልጣን ጥመኞች።

♍️ድንግል:
- የተደራጀ;
- ተግባራዊ;
- አስተማማኝ;
- የሚያነሳሳ;
- በትኩረት.

♎️ሊብራ፡-
- ወዳጃዊ;
- ስሜታዊ;
- ዲፕሎማሲያዊ;
- ፍትሃዊ;
- ማጽናኛ.

♏️ ስኮርፒዮ:
- ስሜታዊ;
- አስቂኝ;
- ጥበቃ;
- እንክብካቤ;
- በእርግጠኝነት.

♐️ሳጅታሪየስ፡-
- ጀብደኛ;
- ደፋር;
- ጉልበት ያለው;
- ግቦቹን ማሳካት የሚችል;
- ቀልደኛ።

♑️ ካፕሪኮርን:
- ኃላፊነት ያለው;
- ሐቀኛ;
- በራስ መተማመን;
- በራስ ተነሳሽነት;
- ዓላማ ያለው.

♒️አኳሪየስ፡-
- ተራማጅ;
- ገለልተኛ;
- ታዛቢ;
- የሚለምደዉ;
- ፈጣን ተማሪ።

♓️ ፒሰስ:
- እንክብካቤ;
- በተጠንቀቅ፤
- ገር;
- ተግባቢ;
- ጥበበኛ.

የሚስማማ ኮኮብ ካላ👍

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

03 Nov, 18:16


እያንዳንዱ ምልክት የሚገርምባቸው ምክንያቶች

♈️ አሪየስ፡ ሴኪ፣ በጣም ልከኛ፣ ማንንም ሆነ ማንኛውንም ነገር ጣልቃ እንዲገባ አይፈቅድም።

♉️ ታውረስ፡- በጣም ጎበዝ፣ በጣም ማራኪ፣ ላመነበት ማንኛውንም ነገር ያደርጋል።

♊️ ጀሚኒ፡ ይህ እምነት የሚጣልበት፣ በጣም ተናጋሪ፣ ማንንም ሰው ማንነቱን እንዲወድ ሊያደርግ ይችላል።

♋️ ካንሰር፡ እጅግ በጣም አሳቢ፣ የሚያስደስት ስሜታዊ፣ ማንም ሰው ጓደኞቹን እንዲጥል አይፈቅድም።

♌️ ሊዮ፡ የተፈጥሮ መሪ ነው፡ ሁሌም ደግ ነው፡ ምንም ነገር እንዲያደናቅፍ አይፈቅድም።

♍️ ቪርጎ፡ ቆንጆ፣ እጅግ በጣም ጣፋጭ፣ እና እርስዎን ለመርዳት ሁሉንም ነገር ያደርጋል።

♎️ ሊብራ፡ ብሩህ፡ ትልቁ ልብ ያለው፡ ስትጨነቅ ጥሩ ስሜት እንዲሰማህ ያደርጋል።

♏️ ስኮርፒዮ፡ ሳያውቅ አስቂኝ፣ በጣም አስተዋይ፣ ቆንጆ ነው፣ ሁልጊዜም ለእርስዎ ይሆናል።

♐️ ሳጅታሪየስ፡- አስቂኝ፣ ምርጥ ምክር ይሰጣል፣ ፈገግ ሊል ይችላል።

♑️ Capricorn: አንዳንድ ጊዜ ደስተኛ, ከፈገግታ ወደ ቁም ነገር መዝለል ይችላል, ለአለም ትልቅ ሀሳቦች አሉት.

♒️ አኳሪየስ፡ ቆንጆ፣ ጠንካራ ኦውራ ይሸከማል፣ በጭራሽ አያሳዝንሽም።

♓️ ፒሰስ፡ የማይተካ፣ ምርጥ ቀልድ፣ በጣም የሚያምር ፈገግታ አለው።

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

30 Oct, 18:14


በቀጣይ ስለምን እንዲለቀቅላችሁ ነው የምትፈልጉት ኮሜንት ላይ ፃፉልኝ

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

30 Oct, 17:01


የእናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???

♓️♓️♓️ፓይሰስ (ሁት ውሃ)♓️♓️♓️♓️

( ከየካቲት 13 እስከ መጋቢት 11 የተወለዱ)

»» ፓይሰሶች የዞዳይኩ ህልመኞች ናቸው፣ መቼም ቢሆን ማለምን አያቆሙም፣ ስለወደፊቱም ሆነ ስለ ማንኛውም ነገር በአይነህሊናውቸው ይስላሉ፣ ብዙዎች ራሳቸውን update እንዳልሆኑ አይነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ ነገር ግን ጥሩ የፈጠራ ተነሳሽነት አላቸው።

ጫጫታ፣ ጥብቅ የዲሲፕሊን ቁጥጥርና ድግግሞሽ የሚበዛበት ሞያ ለፓይሰስ አይስማማውም፡፡ ብዙ የርህራሄ መንፈስ የጎደለበት የሥራ ባህሪም ፓይሰስን ይጎዳዋል፡፡ ወይም ይገድለዋል፡፡ ሰላም የሰፈነበት ሙያ የግድ ያስፈልገዋል፡፡

የፓይሰስ የሙያ ምርጫ ሰፋ ይላል፡፡ የህክምና ሙያ ተቀዳሚው ነው፡፡ ሴቶቹ ፓይሰሶች ድንቅ ነርሶች ይወጣቸዋል፡፡ ወንዶቹም ሆነ ሴቶቹ ፓይሰሶች የህክምና ዶክተሮች ይሆናሉ፡፡ በተለይ የእድሜ ባለፀጋ ለሆኑ ታካሚዎች የፓይሰስ ሀኪሞች ከሰማይ የተላኩ መላእከት ይመስላሉ፡፡

»» ባህላዊ ነገሮች ላይ ጥሩ ናቸው፣ ሩህሩና ነገሮችንም በአስተዋይነት ስለሚያዩ፣ ፈጠራ የሚጠይቁ ስራዎች ላይ ጎበዝ ናቸው፣ ነገር ግን አደባባይ ላይ፣ በግንዘብ የተጠላለፈና ትልቅ ትኩረት የበዛበት ስራ ባይሰሩ ይመረጣል። ጠንቃቃ ናቸው፣ ነገር ግን የሆነ ግዜ በሀሳብ እልም ሊሉ ይችላሉ።

ወደ ኪነጥበቡ ያዘነበሉ ፓይሰሶች ደግሞ “ማይም" በማድረግ ጥበብ ወደር የለሾች ይሆናሉ፡፡ ብዙ ዳንሰሪዎች፣ ብዙ የመድረክና የፈልም ተዋናዮችም ፓይሰሶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሙያዎች ግን አስተማማኝ የገቢ ምንጮች አይደሉም፡፡ በዚህም ሳቢያ ትላንት ሀብታም፤ ዛሬ ደሃ፣ ነገ ደግሞ ሀብታም እየሆኑ የሚኖሩትን ፓይሰሶች ቤት ይቁጠራቸው፡፡

በዲዛይን ሥራ የሚሠማራ ፓይሰስ የጫማ ንድፎችን ወደ ማዘጋጀቱ ሊያደላ ይችላል፡፡ በሽያጭ ሥራ ከተሠማራ ጫማ መሸጥ የበለጠ ያስደስተዋል፡፡ በህክምናው ዘርፍም ወደ እግር ህከምናው (ኪረፐዲ) ያዘነብላል፡፡ የእግር ጉዳይ ለፓይሰስ የተለየ ነው፡፡ ኮከቡም ይህንኑ የአካል ክፍል ይገዛል፡፡ ፓይሰሶችን መንፈሳዊ ህይወት አጥብቆ ይማርካቸዋል፡፡ በዚህ ሳቢያም በታላላቅ የሀይማኖት ምኩራቦች ምሥረታ ፡ ላይ ፡ ይሣተፋሉ፡፡ ሀይማኖተኝነታቸው ወደር አይገኝለትም፡፡ ፓይሰሶችን የባህር ላይ ሥራም ይማርካቸዋል፡፡ የውትድርናን ጥብቅ ዲስፕሊን ቢጠሉትም ባህሩን ይወዱታልና በባህር ኃይል ውስጥ በብዛት ይቀጠራሉ፡፡

የፎቶግራፍ ሙያም ይስባቸዋል፡፡ ማለፊያ ፎቶግራፈሮችም ይሆናሉ፡፡ በራሳቸው ጊዜ መንቀሳቀስ ስለሚወዱም ሙያውን በፍሪላንስ ደረጃ ይይዙታል፡፡ የቅርጫት እራት ከመሆን ከዳኑም የፓይሰስ ሥነግጥሞች ነፍስን በሃሴት የሚያረሰርሱ ዓይነቶች ይሆናሉ፡፡

»» የእንቅልፍ ስራአታቸው፣ ሊለወዎጡ ስለሚችሉ፣ ቤት ውስጥ በነፃነት የሚሰሩ ስራዎች የበለጠ ያነሳሷቸዋል። ፓይሰሶች ውስጣዊ ጥንካሬና ውዥንብር ስላለባቸው ትክክለኛ ፍላጎታቸውንና አውነተኛ አላማቸውን ከሰው ለመሰወር ይገደዳሉ። በስራቸው ከተደሰቱ በደንብ ይሰራሉ፣ ካልሆነ ግን አልምጥ ነው የሚሆኑት። ቶሎ መከፋታቸውን ለመቆጣጠር ከቻሉ፣ አንፀባራቂ ነገር ማምጣት ይችላሉ። በጣም ስሜተ ስስ ስለ ሆኑ ።

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ሩህሩህ፣ አስተዋይ፣ ተስማሚ፣ ስሜታዊ፣ ባለ ረዕይና ሀሳባዊ ናቸው፣ በሀሳብ የሚያስቡትንም ነገር ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ።

√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» አርቲስት፣ ሳይኮሎጂስት፣ ሆስተስ፣ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ፣ ነርስ፣ ቴራፒስት፣ ፎቶግራፈር፣ ፊልም ሜከር፣ ሙዚቀኛ፣ ሼፍ፣ ኢንጂነሪንግ፣ህክምና፣  ማይም፣ ዳንሰር፣ ተዋናይ፣ የጫማ ንድፍ ማዘጋጀት(ዲዛይን)፣ የባህር ሀይል፣ ገጣሚዎች፣ የማስታወቂያ ባለሞያና የመሳሰሉት።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» ማንኛውም አይነት ስራ ይሁን፣ ከሰው ጋ የሚያጋጩና የሚያቀያይሙ ከሆነ መቼም አይፈልጉም።

የኮኮቦች ተስማሚ የስራ በስክ በእዚህ አበቃን በቀጣይ ስለምን እንስራ ኮሜንት ላይ ፃፉልኝ

በየቀኑ አዝናኝ ቪዲዮዎች ለማግኘት የቲክቶክ አካውንቴን follow ያድርጉ 👇👇👇

https://www.tiktok.com/@mistrekewakibt?_t=8qfUQ0i3r09&_r=1

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

29 Oct, 17:00


የእናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???

♒️♒️♒️አኳሪየስ(ደላዊ ንፋስ)♒️♒️♒️♒️

ጥር13 - የካቲት 12 የተወለዱ

»» አኳሪየሶች የፈለጉትን የእጣ ካርድ ያንሱ፣ ያገኙትን እጣ እንዳለ ወደፈለጉበት መውሰድ ይችላሉ፣ የሁሉም እጣዎች ጆከር ናቸው። በፈለጉት ሞያ ቢገቡ ነጥሮ መውጣት ይችላሉ፣ ከሕይወታቸው ጠንቅቀው ልምድ መውሰድ ይችላሉ። ያገኙትንም እውቀት ምንም ሳይሰስቱ ይሰጣሉ፣ በስራ አካባቢ ላይ በጎ አድራጎት ያበረታታሉ፣ ስለ ፍትህና እኩልነትም ይቆማሉ።

የአኳሪየስ ሰው ወጥ የሆነ የፈጠራ ችሎታውን ተግባር ላይ የሚያውልበትን ሙያ እንዲመርጥ ይመከራል፡፡ እንቆቅልሾች በማይፈቱባቸው አሠልቺ ሥራዎች ከተሠማራ ለራሱም ሆነ ለወገኑ የማይጠቅም ተራ ሰው ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜ አኳሪየስ ለራሱም ሆነ ለሌላው ሰው እንቆቅልሽና ጠማማ ፍጡር ይሆናል፡፡
አስገዳጅ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ እርግጥ ነው።አኳሪየስ አሰልቺና ተደጋጋሚነት የበዛባቸውን ሥራዎችም ይሰራል፡፡ ይህ ሲሆን ግን የግሉን ተግባራት የሚያከናውንበት በቂ ጊዜ ይፈልጋል፡፡

አኳሪየስ ማሕበራዊና ፖለቲካዊ ፍትህ በተዛባበት ሁሉ እየገባ የማቃናት ሥራ ለመሥራት የተመቸ ፍጡር ነው:: በዚህም ዩኒሴፍን የመሳሰሉ ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች ውስጥ ሊሰማራ ይችላል። በበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥም የመስክና የማስተዳደርን ሥራ ይሰራሉ፡፡ የጥገናዊም ይሁን የሥር ነቀል ለውጥ አራማጅነት ዝንባሌ ስላላቸው የማህበራዊ ደህንነት ሠራተኞችም ይሆናሉ፡፡

»» አዳዲስና ጀብዱ የተሞላበት ነገሮችን ይናፍቃሉ፣ ይወዳሉ እንዲሁም ያልማሉ። በአንድ ወኪል ወይም ማህበር ብቻ መታሰርን ይጠላሉ፣ በዚ አጋጣሚም፣ እድሉን የሚያገኙ ከሆነ ብዙ ስራ ይለዋውጣሉ። ነፃነታቸው ሕይወታቸው ነው፣ ከተለመደ ስራና ነገር ራሳቸውን ማላቀቅ ይፈልጋሉ። ተሞክሮ የማያቅ በማንም ለመስራት የማይገመት ስራ መስራትና መሞክርን ይወዳሉ።

»» ኦርጂናል ናቸው ነገር ግን በሁለት ሐሳብ መሀል ሲሆኑ ይስተዋላል፣ የሆነ ግዜ ላይ ሀይለኛ ሀይልና ፍላጎት ከዛን ደግሞ ቀዝቀዝና ድክም ወደ ማለት ይመጣሉ። ይሄም በገዥያቸው ኡራኖስ ምክንያት ይከሰታል።

በሳይንስ መስክ ብዙ አኳሪየሶች የድርብርብ ዲግሪዎች ባለቤቶች ናቸው፡፡ ታዲያ በዚያው በተራቀቁበት መስክ ጠንክረው ሊሠሩ ይገባቸዋል፡፡ ይህ ሲሆን እነሱም ይሰክናሉ፤ ማህበረሰባቸውንም ይጠቅማሉ፡፡ ብዙ አኳሪየሶች በአመለካከታቸው ያፈነገጡ ሳይንቲስቶችም ይሆናሉ፡፡ እንግዳና ለየት ያለ ነገር ይስባቸዋል፡፡ መስሎ መኖርን አይፈቅዱትም፡፡ ይህ ዝንባሌያቸው ጠቃሚ የሚሆነው ግን በሙያቸው ላይ ሲያውሉት ብቻ ነው፡፡ ወደ ኪነጥበቡ የሚያዘነብሉ አኳሪየሶች በተውኔት፣ በፊልምና በአጠቃላይም በሥነጽሑፍ ሙያ ይሠማራሉ፡፡ ይዋጣላቸዋልም፡፡

አስትሮኖሚም የአኳሪየስ አንዱ ግዛት ነው፡፡ በተለይ ደግሞ አስትሮሎጂ አኳሪየሶችን ይስባቸዋል፡፡ በአስተሮሎጂ የጥናት መስክ ከተከበሩ ባለሙያዎች ውስጥም አኳሪየሶች በብዛት ይገኛሉ፡፡ ድርሻቸውም የኋላ ሆኖ ታይቷል፡፡

የአኳሪየስ ኮከብ ንጥረ ነገሩ አየር ነው፡፡ የአየር ነገር በአኳሪየሶች የሙያ ምርጫ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አለው፡፡ በራዲዮና በቴሌቪዥን ማሰራጫዎች ውስጥ ጥቂት የማይባሉ አኳሪየሳዊ ባለሙያዎች ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ በሌላ አነጋገር የራዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን በአየር ላይ ከሚያውሉት ባለሙያዎች ውስጥ አኳሪየሶች በዛ ብለው ይገኛሉ።

የአየር ንጥረ ነገሩ አኳሪየሶችን ወደ አየር ላይ መጓጓዣዎችም ይስባቸዋል፡፡ በዛ ያሉ አኳሪየሶችም የአውሮፕላን አብራሪዎችና የአየር ላይ ሆስቴሶች እንደሚሆኑ ተስተውሏል፡፡

ለአኳሪየሶች የሙያ ምርጫ የመነሻ ሐሳብ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ የመነሻ ሐሳቡ በጊዜ ቀመር ላይ ያጠነጥናል፡፡ ያለፈውንም ሆነ የመጪውን ጊዜ በሚመለከት የሚያደርጉት ምርምርና ጥናት የሚጠቅም ነገር ይወጣዋል ማለት ይቻላል፡፡ የመጪው ጊዜ አንዱ መገለጫ የሳይንስ ልቦለድ ነው፡፡ ያለፈው ጊዜ ደግሞ በአርኪዎሎጂ የጥናት ዘርፍ ይካተታል፡፡

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ጥሩ ተንታኝ፣ ጎበዝ፣ ፈጠራ ላይ እንዲሁም ጓደኝነትና ከማንም ጋር ተግባብቶ መኖር ይችላሉ፣ ምንም አይነት ሰው ይሁን።

√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» አፕ ዲቨሎፐር፣ ሳይንቲስት፣ የእንስሳት ሀኪም፣ ኢንጂነር፣ ዲዛይነር፣ ሙዚቀኛ፣ የህዋ ተመራማሪ፣ተውኔት፣ ፊልም፣ ሥነ ጽሑፍ ፣ አስትሮኖሚ፣የሬዲዮና የቴሌቪዥን ስራ፣ ፓይለት፣ ሆስተስ፣ የነፃነት ተከራካሪ፣ ሶሻል ሚዲያ ላይና የመሳሰሉት ላይ ምርጥ ናቸው።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» ምንኛውም አይነት ስራ ይሁን፣ ተለምዷዊ ሆኖ፣ ነፃ ሆኖ ማሰብንም ሆነ ልዩነትን የሚቃወም የስራ ኢንቫይሮመንት ከሆነ ትዕግስት የላቸውም።

በየቀኑ አዝናኝ ቪዲዮዎች ለማግኘት የቲክቶክ አካውንቴን follow ያድርጉ 👇👇👇

https://www.tiktok.com/@mistrekewakibt?_t=8qfUQ0i3r09&_r=1

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

28 Oct, 17:01


የእናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???

♑️♑️♑️ካፕሪኮርን(ጀዲ መሬት)♑️♑️♑️♑️

( ከታህሳስ 13 እስከ ጥር 12 የተወለዱ)

የካፕሪኮርን ኮከብ ያለው ሰው አስተማማኝ ገቢ ወይም ደመወዝ ሊኖረው የግድ ነው። የግሉን ሥራም መጀመር ይችላል፡፡ በትንሹ የጀመረው ንግድ ቀስ በቀስ ወደ ኤምፓየርነት ያድጋል፡፡ የዚህ ሰበቡ የካፕሪኮርን ጠንቃቃ ተፈጥሮና የረዥም ጊዜ እቅድ የማውጣት ክሂሉ ነው፡፡ገንዘቡን ሥራ ላይ ሲያውል በብዙ ይጠነቀቃል፤ አርቆ ያስባል፡፡

በንግድ ሥራ ካፕሪኮርንን የሚተካከለው ኮከብ የመኖሩ ዕድል ጠባብ ነው::ተቀጥሮ ለሚሠራለት ድርጅት ከፍተኛ ገንዘብ የሚካተትባቸውን ውሎች ዝርዝር ለማዘጋጀት ካፕሪኮርን በብዙ ይተጋል፡፡

»» ሁነኛውና የሌላ ኮኮብ ተፅኖ ጎልቶ ማይታይበትን ካፕሪኮርን፣ ማግኘት ከፈለጋቹ፣ በእርግጠኛነት ትልቅ ክብር ያለው ስራ ላይ ወይም ደግሞ ትልቅ ሽልማት ሲጎናፀፉ ተገኛቿላቹ። ካፕሪኮርኖች በሕይወታቸው እንድ ትልቅ ነገር ማግኘት ይፈልጋሉ፣ እሱም ስኬትን። ትልቅ ስኬት ሚገኝበት ስራ ሲያገኙም ትልቅ ሀሴት ነው ሚሰማቸው፣ ያማልላቸዋል። ነገር ግን ስሜታቸውን ያገናዘበ የተወሰነ ፕሮሞሽን ይፈልጋሉ፣ ትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ፕሮሞሽን።

»» ትላልቅ ተልኮና ግብ ተሰቷቸው ሚሰሩትን ስራ ይወዱታልም በአስተማማኝ ሁኔታም ይጨርሱታልም። ለምሳሌ የFBI አለቃ J.edgar hoover አስተማማኝ ምሳሌ ነው። ካፕሪኮርኖች ትልቅ ምኞት አላቸው፣ ደስተኛ መሆንንም ከልብ ይፈልጉታል፣ ገደብ ያላቸውና በአቋማቸው ፅኑ ናቸው፣ የፈለገውን ግዜ ይወሰድ አንዴ ከቆረጡ፣ ቆረጡ ነው። ለመለወጥ ይሰራሉ።

»» ሁሉም በህግና ደንብ ቢሆን ይመርጣሉ፣ ህግና ደንብንም የማክበር ዝንባሌ አላቸው። አሪፍ የቢዝነስ ሀሳቦችን መጀመር ላይ ጎበዝ ናቸው። በአከባቢያቸው ያሉትን ሀሳቦችንም ሆነ ሰዎችንም፣ ወደ አንድ ያመጣሉ።

የግንባታ ሥራም ይስማማዋል፡፡ አርክቴክቸር (ሥነሕንጻ)፣ የከተማ ፕላን ሥራና ምህንድስናን የመሣሠሉት ሙያዎች ገንዘቡ ናቸው፡፡ የባንክና የኢንሹራንስ ሙያዎችም ይሆኑታል፡፡ በተቀጣሪነት ከሠራ እስከ ጡረታ መውጫው በታማኝነት ያገለግላል፡፡

በሁሉም ጊዜ ጠንቃቃ ቆቅ ስለሆነ በሥራው ላይ የማይረባ ስህተትን አይፈጽምም፡፡

እርሱን የቀጠረ ድርጅት ምንኛ የታደለ ነው!

ወደ ኪነጥበቡ የሚያዘነብሉ ከሆነ ካፕሪኮርኖች ፕሮፌሽናል የሙዚቃ ሰዎች ይሆናሉ፡፡ ሙዚቃ ካፕሪኮርንን የሚስብ ሙያ መሆኑ እንቆቅልሽ ሳይሆን አይቀርም፡፡ አንዱ ምክንያት ካፕሪኮርኖች በማቲማቲክስ የላቀ ችሎታ ያላቸው ስለሆኑና የሙዚቃም ተፈጥሮ ማቲማቲክስ በመሆኑ ነው የሚል ግምት አለ፡፡

ካፕሪኮርን ልበ ትልቅ ነው፡፡ ከፍ ካለ ደረጃና ማእረግ ለመድረስ ይጥራል፡፡ ክብርን ይናፍቃታል፡፡ በዚህ ሳቢያም ወደ ፖለቲካ ጎራ ሊል ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ታዲያ ካፕሪኮርን ሚኒስትር፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ወይም ፕሬዚዳንት ሆኖ ብቅ ይላል፡፡ ወደ ህከምናው ያዘነበለ ካፕሪኮርን ደግሞ የቆዳና የአጥንት ህክምና ስፔሻሊስት ይሆናል፡፡ ሴቶቹ ካፕሪኮርኖችም በአጥንት እና በማሳጅ ህክምና በተሠማሩ ጊዜ ብቁ ባለሙያ ይሆናሉ፡፡

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ጥሩ ምኞት፣ ትልቅ አቅም፣ ታጋሽ፣ በህግ የሚመሩ፣ አካሄድን አዋቂና ተወዳዳሪ አንዲሁም ማንኛውንም ስራ ቢሰጣቸው፣ አሪፍ አድርጎ መስራት ይፈልጋሉ።

√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» ፋይናንስ ላይ፣ ቢዝነስ አስተዳደር፣ ዶክተር፣ አሰልጣኝ፣ ማናጀር፣ ባንከር፣ የኮምፒተር ባለሙያ፣ ስቶክ ኤክስፐርት፣ ኢንቨስተርና እንዲሁም ጥሩ የፈጠራ ሰው መሆን ይችላሉ። በዛ ላይ ደግሞ ውክልናና ፕላን ላይ ምርጥ ስለሆኑ፣ ሰውን ጥንቅቅ አድርገው ማማከር ስለሚችሉ፣ ኮንሰልታንሲ ላይ አሪፍ ናቸው፣ንግድ፣አርክቴክቸር(ሥነ ሕንጻ)፣የከተማ ፕላን ሥራ ና ምህንድስና፣ የባንክና የኢንሹራንስ ሙያዎች፣ሙዚቃ ፣ማቲማቲክስ፣ ፖለቲካ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር እና ፕሬዝዳንት፣ የቆዳና የአጥንት ህክምና ስፔሻሊስት፣ማሳጅ እነዚህ ላይ ብትሰሩ በጣም አሪፍ ነው።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» ምንም ጥቅሙ ሳይታወቅ በድፍረት ሚገቡበት ስራም ሆነ ቢዝነስ ብዙ ዋጋ ያስከፍላቸዋል።

በየቀኑ አዝናኝ ቪዲዮዎች ለማግኘት የቲክቶክ አካውንቴን follow ያድርጉ 👇👇👇

https://www.tiktok.com/@mistrekewakibt?_t=8qfUQ0i3r09&_r=1

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

27 Oct, 17:31


የእናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???

♐️♐️♐️ሳጁታሪየስ(ቀውስ እሳት)♐️♐️♐️♐️

( ከህዳር 14 እስከ ታህሳስ 12 የተወለዱ)

»» ሳጁታሪየሶች ነፃነትን አፍቃሪ፣ ከማንኛውም ተፅዕኖ መላቀቅ የሚፈልጉ፣ በሆነ ሳጥን ውስጥ መሆንና ባለፈበት ባህልና ህግ መመራት የሚጠሉ ናቸው። አብረው ከእነሱ ጋር የሚሰሩ ሰዎች እንደ ግሩፕ ብዙ ስኬትን ያስመዘግባሉ፣። በአስተዳደርነት ሆነ በካንፓኒው ባለቤትነት ሚመራው ህግ እያለ ፈታ ያለ የስራ አከባቢ በዙሪያቸው ካለ፣ ፈታ ብለው እየዞሩ ነው መስራትን የሚፈልጉት፣ ከመስሪያ ቤቱ ውጪም ሆነው ሊሆን ይችላል የሚሰሩት።

ሳጁታሪየሶች ብዙ ነጻነትን በሚሰጥ ሙያ ላይ ቢሠማሩ ይመረጣል፡፡ ተለጣጭና ሁለገብ ስለሆኑም ከአንድ በላይ በሆነ ሥራም ይሠማራሉ፡፡ የገቢ ምንጫቸውንም በዚሁ ሳቢያ ያሰፉታል፡፡ ሁለት አይነት ሙያ ለለውጥና  ለአይነት ያላቸውን ጥማትም ያረካላቸዋል፡፡

»» ህግ መስበርና አዲስ ነገርን መፍጠር ላይ ጎበዝ ናቸው። ሀቀኛ፣ በሙሉ ሀይላቸው የሚጠቀሙና የራሳቸውን ፍልስፍና የሚከተሉ ናቸው። ውሳኔ ላይም ፈጣን፣ ተራማጅና ትክክለኛ ናቸው። ብዙ አማኝ ሳጁተሪየሶች አሉ፣ ሲበዛም ተጓዥ ናቸው።

አንድ ቦታ ከሚጎልት ሥራ ይልቅ ከቦታ ቦታ የሚያንቀሳቅስ ሙያ ጤና ይሰጣቸዋል፡፡ የጉዞ ወኪልነት ሥራ ይስማማቸዋል፡፡ አእምሯቸውን በቅጡ ስለሚያሠሩትም ሳጁታሪየሶች በምሁራዊ ሥራ ውስጥ በብዛት ይታያሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ የህግ ባለሙያነት አንዱ ነው፡፡ ጥቂት የማይባሉትም የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮችና የሁለተኛ ደረጃ አስተማሪዎች ናቸው፡፡ የህፃናት ይልቅ በእድሜ ከፍ ያሉትን ቢያስተምሩ ይመረጣል፡፡

የመጻሕፍት ህትመት፤ የላይብረሪ እና የጽሕፈት ሥራዎች የሳጁታሪየስ ግዛቶች ናቸው:: መጻህፍት ነክ የሆኑ ሙያዎች ሁሉ ለሳጁታሪየሶች ይስማሟቸዋል፡፡

ሳጁታሪየሶች ማለፊያ ባልደራሶችም (የፈረስ አሰልጣኞች) ይወጣቸዋል፡፡ ሀብታም ከሆኑም የራሳቸው ፈረሶች ይኖራቸዋል፡፡ ጽኑ አፍቃሬ እንስሳት በመሆናቸውም ማለፊያ የእንስሳት ሀኪሞች ይሆናሉ፡፡ በውሻ እርባታም ይሳባሉ፡፡ የራሱን ውሻ የማያሳድግ ሳጁታሪየስ ብዙም አይገኝ፡፡

ብዙ ሳጁታሪየሶች ጥብቅ የሆነ የሀይማኖተኝነት ዝንባሌን ያሳያሉ፡፡ በሰበኩ ጊዜ ምእመኑ ከቁሳዊው ህይወት ይልቅ ወደ መንፈሳዊው ህይወት እንዲያደላ ያደርጉታል፡፡ የዓለማችን ታሪክ በብዙ የሳጁታሪየስ ቀሳውስትና ነቢያት የተሞላ ነው፡፡

ሳጁታሪየሶች ወደ ስፖርትም ያዘነብላሉ፡፡ ጥቂት የማይባሉትም ፕሮፌሽናል ስፖርተኞች ይሆናሉ፡፡ ከፈረሰኝነት በዘለለም እውቅ አትሌቶች ይወጣቸዋል፡፡

ወደ ኪነጥበቡ የሚያዘነብሉት ሳጁታሪየሶች የብዙ ረዣዥም ልቦለዶች ደራሲዎች ይሆናሉ፡፡ በእያንዳንዱ ሳጁታሪየስ ውስጥ ቢያንስ አንድ መጽሐፍ አለ ማለት ሳይቻል ኣይቀርም፡፡

»» ወጣ ያሉ ሲሆኑ፣ ቀልድም ይወዳሉ፣ ይቀልዳሉም። ጥሩ ተወዳጅነትም አላቸው፣ እየሰሩና እያሳዩ ነው የሚሰሩት። ለእያንዳንዱ ነገር ስለማይጨነቁ፣ ስለወደቀች ቆሻሻና ትናንሽ ነገር ላያስተውሉ ይችላሉ። የተለመደ ነገር መስራት ቶሎ ነው ስልችት ሚላቸው። ሁሌም ለወጥ ያለና እድገት ያለው ፍልስፍና ነው የሚፈልጉት።

ቋንቋዎችን በቀላሉ ይማራሉ፡፡ የዚህ ክሂል ማለፊያ አስተርጓሚዎች ያደርጋቸዋል፡፡ አስተርጓሚነቱ የጉዞ እድልንም ስለሚከፍት ሙያው በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ የሚሉትን አይነት ይሆናል፡፡

እንደ ብዙዎች ሰዎች ሁሉ አንዳንድ ሳጁታሪየሶች በወላጆች አስገዳጅነት በማይፈልጉት ሙያ ይሰማራሉ፡፡ የዚህ አደጋም ብዙ ነውና ስህተቱ በእንጭጩ ቢቀጭ ይመከራል፡፡ በማይስማማቸው ሙያ የሚሠማሩ ሳጁታሪየሶች ከሌሎች ኮከቦች በበለጠ ተጎጂ ይሆናሉ። ምክሩን ወላጅም ይስማ! ምክሩ ደግሞ ለሁሉም ኮከቦች ነው፡፡ ልጆቻችን ራሳቸውን እንዲሆኑ እንጂ እኛን እንዲሆኑ አይደለም መጣር ያለብን፡፡

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ለየት ያለ ነገር ማምጣት የሚችሉ፣ ተስፈኛ፣ ቀጥተኛና ነፃነታቸውን በእንቅስቃሴና ራሳቸውን በመግለፅ ዘና የሚሉ እንዲሁም ፈልገው የገቡበትንና የሰሩትን ስራ ምርጥ አድርገው መስራት የሚችሉ ናቸው።

√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» ኢንተርፕሬነርሺፕ ፣ ፓይለት፣ ስፖርት ኢንዱስትሪ፣ ፖሊስ ኦፊሰር፣ ሆስተስ፣ ሚኒስተር፣ የእንስሳት አሰልጣኝ፣ ኤዲተር፣ ህዝብ ግንኙነት፣ አሰልጣኝና ማንኛውንም አይነት ስራ ከጉዞ ጋ በተገናኘ፣ ዲፕሎማት፣ ፕሮፌሰር፣ ሰባኪ፣ ሪፖርተር፣የጉዞ ወኪልነት፣የህግ ባለሙያ፣ የዩንቨርሲቲ አስተማሪ፣የመጻሕፍት ህትመት፣የላይብረሪ እና የጽህፈት ሥራዎች፣ የእንስሳት ሀኪም፣  ደራሲነት፣ አስተርጓሚ፣አስጎብኚ ፣ ሳይንቲስትና ደላላ መሆን ይችላሉ።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» ድግግሞሽ የበዛበት፣ የሙሉ ቀን የቢሮ ውስጥ ወይም የጠረቤዛ ላይ ስራ ።

በየቀኑ አዝናኝ ቪዲዮዎች ለማግኘት የቲክቶክ አካውንቴን follow ያድርጉ 👇👇👇

https://www.tiktok.com/@mistrekewakibt?_t=8qfUQ0i3r09&_r=1

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

26 Oct, 17:01


የእናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ???

♏️♏️♏️ ስኮርፒዮ♏️♏️♏️♏️

( ከጥቅምት 14 እስከ ህዳር 13 የተወለዱ)

»» ስኮርፒዮዎች ሁሉንም ነገር በጥልቅና እውቀት በተሞላበት ነገር መጠን ማወቅ ይፈልጋሉ፣ ነገሮችንም አስፍተው ነው የሚያዩት፣ የሰዎችን ችግር መረዳትና ድጋፍ ማደረግ ላይም ጎበዝ ናቸው፣ በዚህም ቋሚ ተማኝነትና የረጅም ግዜ ጓደኝነትን ይፈጥራሉ። ዶ/ር ፓራኪሶ እንደሚሉት ከሆነ ፣ ስኮርፒዮዎች የቴራፒስት እውቀት ስላላቸው የሰውን የውስጥ ችግር መረዳት እንደሚችሉም ይናገራሉ።

ስኮርፒዮዎች ጠንካራ ሰራተኞች ናቸው፡፡ በህይወት ያላቸው ጽኑ ዓላማ በየትኛውም ሙያ ቢሆን ቀልድ የማያውቁ ታታሪዎች ያደርጋቸዋል፡፡ በኮሌጅ፣ በዩኒቨርሲቲም ሆነ በየትኛውም ሥልጠና ላይ፣ ቀንና ሌሊቱን እያገናኙ ያጠናሉ፡፡ ቆራጥነታቸው በትምህርትም ሆነ በሥራ ላይ እድገትን እንዲያስመዘግቡ ይረዳቸዋል፡፡ ዋናው ነገር የሚሠሩት ሥራ ጠቃሚ ነው ብለው ማሰባቸውም ነው፡፡ ጥቃቅንና ተራ ነገሮችን ይጠላሉ፡፡ ማለፊያ የንግድ ሠዎች ይወጣቸዋል፡፡ በኢንሹራንስና በስቶክ ኤክስቼንጅ በመሳሰሉት ሙያዎች ይሠማራሉ፡፡

በእነርሱ ዘንድ ተከድኖ የማይከፈትና ተሸፍኖ የማይገለጥ ነገር  ስለማይኖር ስኮርፒዮዎች ታላላቅ የምርምርና የጥናት ሰዎች ይሆናሉ፡፡ በተመሳሳይም ወደ ወንጀል ምርመራ ሙያ ይሳባሉ፡፡ በፖሊስ ሠራዊት ውስጥም በብዛት ይገባሉ፡፡ እዚህ ላይ አስገራሚው ነገር ወደ አጥፊው የኮከባቸው ገፅታ የሚያዘነብሉ ስኮርፒዮዎች ወደ ወንጀል ተግባር መሠማራታቸው ነው:: በዚህ ሳቢያም ወንጀል መርማሪው ስኮርፒዮ ወንጀለኛውን ስኮርፒዮ ሲያሳድድ ይኖራል፡፡

የስለላ ሙያም በስኮርፒዮ ኮከብ ግዛት ውስጥ ይወድቃል። የዓለማችን እውቅ ሰላዮችም ብዙዎች ስኮርፒዮዎች እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ ብዙ የስለላ ታሪክ መጻህፍትን የተረጎመልን ማሞ ውድነህ ስኮርፒዮ ናቸው::


ስኮርፒዮ ራሱን በዲሲፕሊን ገርቶ ሌሎችንም ይገራል፡፡ የተዋጣለት ወታደር የሚሆነውም በዚሁ ሳቢያ ነው፡፡ ፈቃደ ብርቱነቱ ወደ ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግም ያደርሰዋል። የምድር ጦርም ይሁን የባህር ኃይል ለስኮርፒዮ ተመራጮች ናቸው::

»» በዛ ላይ የሌሎችን ሚስጥር መጠበቅ ላይ ጎበዝ ናቸው፣ እንደው በአጠቃላይ ስኮዎች ምን አይነት ስራ የሚወዱ ይመስላቹዋል? በቦንብ የቆሰለን ሰው የሚረዱ? ወይስ ውስብስብ ቀዶ ጥገናዎችን በስኬት የሚያደርጉ? እመኑኝ ስኮዎች በየትኛውም የስራ ዘርፍ ላይ ቢሆን ትፈልጓቸዋላቹ፣ እስከ ጥግ ትኩረት አድርጎ መስራትን ያውቁበታል።

ስኮርፒዮዎች ብቁ ተንታኞችና ሳይካትሪስቶችም ይሆናሉ።በዚህ ሙያ ሲሰማሩ ውስብስቡን የሰው ልጅ አእምሮ አብጠልጥለው ይረዱታል፡፡ የቀዶ ጥገናን ሥራም እንደ ስኮርፒዮ በቅልጥፍናና በእውቀት የሚያከናውን አለ ለማለት ይቸግራል፡፡ ከሁሉም ሙያ ደግሞ ይኸው የቀዶ ጥገና ህከምና የሚስማማቸው ይመስላል፡፡

»» ነገር ግን አጠገባቸው አታንዣቡ፣ ነፃነትንና የሰራተኞቻቸውን እምነት ይፈልጋሉ፣ ግለኝነታቸውም እንዲጠበቅላቸው ይፈልጋሉ፣ ይሄ ማለት ከእነሱ ፍቃድ ውጪ ማንም ሰው ስራቸውን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ አይፈልጉም።

√√ ጥሩ እሴቶች

»» ታታሪ፣ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው፣ እምቅ ብቃትና ቆራጥነት፣ እንዲሁም ብዙ ግዜ ሰውን ሳይጠብቁ ይሰራሉ። ነገር ግን በጣም የሚጓጓለት ነገር ቢሆን ይመርጣሉ።

√√ ስኬታማ የስራ መስክ

»» ሳይኮሎጂስት፣ ህግ አዋቂ፣ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሰራተኛ፣ መርማሪ ፖሊስ፣ አስተማሪ፣ ሳይንቲስት፣ ሳርጂዮን፣ ፊዚስት፣ ፖሎቲከኛ፣ ፀሐፊ፣ ቴራፒስት፣ንግድ፣ኢንሹራንስናስቶክ ኤክስቼንጅ፣ስለላ፣ ውትድርና፣ተንታኝነትና ሳይካትሪስት፣ቀዶ ጥገና ስራ፣ ዶክተርና እንዲሁም አስትሮሎጂና አንድ አንድ ጥበባት ላይ ጎበዝ ናቸው።

√√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች

»» ትልቅ እውቀት ሳይኖራቸው የሚሰሩት ስራና ሳያምኑበት የሚገቡበትን ነገር መስራት ስኬታማ አያደርጋቸውም።

በየቀኑ አዝናኝ ቪዲዮዎች ለማግኘት የቲክቶክ አካውንቴን follow ያድርጉ 👇👇👇

https://www.tiktok.com/@mistrekewakibt?_t=8qfUQ0i3r09&_r=1

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

26 Oct, 16:41


የሽኝት መርሐግብር!...

የታላቁ የእግር ኳስ ሰው አሥራት ኃይሌ የሽኝት መርሐ ግብር ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል።

በትናንትናው ዕለት ህልፈተ ህይወታቸው የተሰማው የቀድሞ ተጫዋች እና አሰልጣኝ አሥራት ኃይሌ ሥርዓተ ቀብር ነገ ይካሄዳል።

ቦሌ ከሚገኘው መኖርያ ቤት 5:00 ላይ በመነሳት ከ6:00-7:00 ታሪክ በሰሩበት አዲስ አበባ ስታዲየም የሽኝት መርሐ ግብር የሚከናወን ሲሆን በመቀጠል 7:00 ላይ ለገሀር በሚገኘው መድሀኔዓለም የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን የፀሎት መርሐ ግብር ተከናውኖ ሥርዓተ ቀብራቸው ከቀኑ 9:00 በጴጥሮስ ጳውሎስ መካነ መቃብር ይካሄዳል።

መላው የስፖርት አፍቃሪም የሀገር ባለውለታው አሥራት ኃይሌ የሽኝት መርሐ ግብር እና ሥርዓተ ቀብር ላይ እንዲገኝ ጥሪ ቀርቧል። 
አስተባባሪ ኮሚቴው

Via ድሬ ቲዩብ

ሚስጥረ ከዋክብት/THE SECRET OF ZODIAC

25 Oct, 17:44


ዜና እረፍት 😢

ታላቁ የኢትዮጵያ የእግርኳስ አባት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በኢትዮጵያ እግርኳስ ስማቸው በወርቅ ቀለም በደማቅ ታሪካቸው ከተፃፈላቸው የእግርኳስ ሰዎች መካከል አንዱ የነበረው አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ (ጎራዴው) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ሚስጥረ ከዋክብት በአሰልጣኙ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን ይመኛል።

ምንጭ 433 ኢትዮጵያ

16,789

subscribers

511

photos

17

videos