ታሪክ ይሰራል ጀብድም ይፈጸማል። ታሪክ ሰሪ አለ ጀብድም ፈጻሚ አለ። ይህ ብቻ ግን አይደለም በትግሉ ውስጥ ለአማራ ህዝብ ሸክም አቅላይ የሚመስሉ ሸክም የሆኑም አሉ። የነሱ ታሪክም ይዘገባል ታሪክ ሆኖ እንደ ጎንደሬ በጋሻው ይፃፋል። ለምን ሳይሉ የረሸኑ ያስረሸኑ ይጠየቃሉ በታሪካቸውም ጥቁር ነጥብ ሆኖ ከባንዳነት የበለጡ ባተሌ ባንዶች ከህሊናቸው ወርደው ሆዳደር የሆኑ ሆዳቸው ሞልቶም ብልት አደር የሆኑ ብለን በታሪክ መዝገብ እንዘግበዋለን። መሪም ሁን ተመሪ ታሪክ ነውና ይዘገባል። በየ አቅጣጫው ያላችሁ የአማራን ሸክም እናቀላለን ብላችሁ ሸክም የሆናችሁብን ሰዎች ውረዱልን። ምርኮኛን የለቀቃችሁም ጊዜ ሲሰጠን ልንጠይቅ በታሪክ መዝገብ መዝግበነዋል። ወንድሜ ያለኸው በስሙ የነገድህበት ሥራ ብለህ ያለምግብ ታስሮ የሚሰቃየው ብልቱ ከሁለት የተሰነጠቀው ጀግናውና መስዋዕት የሆነው ወንድሜ ታሪክ ተዘግቧል። ያንተ የአስመሳይና የሸቃጩም ታሪክ ተመዝግቧል። ሴትና ሥጋን ጠገብሁ ያልኸው ታሪክም ተመዝግቧል። ባጠቃላይ በአማራ ትግል ውስጥ መጥፎና መልካም ታሪኮች ይፃፋሉ።
የተፈጸመ ድርጊትና የተሰራ ጀብድም ታሪካችን ሆኖ ወይ እንመሰገንበታለን አሊያ ደግሞ ዘርማንዝራችን ይረገምበታል ታሪክ ያልሆነ ትግል የለንምና የምትበድሉ ሰዎች ታሪካችሁን ብቻ ሳይሆን ትግላችን አታበላሹ !!!!!
የተሰራ ያልተመዘገበ እና ታሪክ የማይሆን የለም።
Join👇👇👇👇👇
https://t.me/dad122123