============//===========
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ስድስት የተለያዩ ሠነዶችን ለሚያዘጋጁ አመራሮች እና ሠራተኞች ከጥቅምት 05 ቀን 2017 ጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ ተግባር ተኮር ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
ተግባር ተኮር ስልጠናው የተለያዩ ስትራቴጂዎች እና መመሪያዎችን ለማዘጋጀት የሚያግዙ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን በስልጠናዉ ጎን ለጎን አስተዳደሩ ወደ ኢንቨስትመንት ዉስጥ በስፋት እንዲሳተፍ የሚያግዝ የኢንቨስትመንት ስትራቴጂ፣ የአስተዳደሩን ገጽታ የሚገነባ እና ተቋማዊ ሚናውን አጉልቶ የሚያሳይ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ፣ የአዋጭነት ዳሰሳ ጥናት፣ የሥራ አፈጻጸም ምዘና መመሪያ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍቻ መመሪያ እንዲሁም የዜጎች ቻርተር እየተዘጋጀ ይገኛል።
በዚህ ተግበራ ተኮር ስልጠና እና ስትራቴጂ እና መመሪያ ዝግጅት ስራ ላይ 35 የአስተዳደሩ አመራሮች፣ የስራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
//****
ጥቅምት 8 / 2017
ቢሾፍቱ