South Radio And Television agency @southradioandtelevisionagency Channel on Telegram

South Radio And Television agency

@southradioandtelevisionagency


South Radio and Television Agency is SNNPRS Ethiopia Government Owned media and Broadcasting service Company, which has 10 branch stations in the region.

South Radio And Television agency (English)

Welcome to South Radio and Television Agency, the premier media and broadcasting service company in SNNPRS Ethiopia! With 10 branch stations across the region, we are dedicated to providing our viewers and listeners with high-quality programming and news coverage. Who are we? South Radio and Television Agency is a government-owned media organization that aims to inform, educate, and entertain the public. Our dedicated team of professionals works tirelessly to bring you the latest news, engaging entertainment, and thought-provoking discussions. What do we do? At South Radio and Television Agency, we strive to be the voice of the people, offering a platform for diverse perspectives and opinions. From breaking news updates to in-depth investigative reports, we cover a wide range of topics to keep our audience informed and engaged. Whether you're tuning in to one of our radio stations or watching our television programs, you can trust that South Radio and Television Agency is committed to delivering accurate, reliable, and impartial content. Join us in our mission to promote dialogue, foster understanding, and empower communities across the region. Stay connected with us on our Telegram channel @southradioandtelevisionagency to receive the latest updates, behind-the-scenes glimpses, and exclusive content. Don't miss out on the opportunity to be part of the conversation and stay informed about the issues that matter to you. Thank you for choosing South Radio and Television Agency as your source for news and entertainment. Together, we can shape the future of media and broadcasting in SNNPRS Ethiopia!

South Radio And Television agency

21 Nov, 14:15


በአፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እና ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የተመራ ልዑክ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን በድምቀት ለማክበር እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን እየተመለከቱ ይገኛል

በአፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እና ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁንከበደ የተመራ ልዑክ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን በድምቀት ለማክበር እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን እየተመለከቱ ይገኛል።

ልዑካኑ በዓሉን ለማክበር እየተዘጋጀ የሚገኘውን ስታዲየም ፣ ስምፖዚየም የሚካሄድበትን የጋሞ ባህልና ምርም መዕከል ጨምሮ ሌሎች ዝግጅቶችን እየጎበኙ ይገኛል።

ምንጭ ፡ የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ

South Radio And Television agency

21 Nov, 14:14


በሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በክልሉ ዉስጥ ለሚገኙ ወረዳዎች እህል የሚወቃ የማሽን ድጋፍ አደረገ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በክልሉ ዉስጥ ለሚገኙ ወረዳዎች እህል የሚወቃ የማሽን ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፍ የተደረገው በክልሉ በአራቱም ዞኖች ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች በማህበር ለተደራጁ ወጣቶች መሆኑን ተገልጿል።

በድጋፍ የተበረከተው ማሽን ገብስና ስንዴን የሚወቃ ሲሆን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ለተሰጠው ትኩረት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወትም ተጠቁሟል።

ድጋፍ የተደረገዉ በአራቱ ዞን ዉስጥ ለሚገኙ ለ15 ወረዳዎች ሲሆን ማሽኑ በሰዓት እስከ 40 ኩንታል አህል የመዉቃት አቅም አንዳለው ተገልጿል።

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት ግብርና የሚሻሻለው የተሻለ ተክኖሎጂ ስንጠቀም መሆኑን ገልጸው ጉልበትን በማይጨርስና ጊዜን የሚቆጥብ መካናይዜሽን መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።

አርሶ አደሮች በየወረዳ የተሰጠውን ማሽን በአግባቡ ተጠቅመው እህልን ከብክነት በመጠበቅ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የሲዳማ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

South Radio And Television agency

21 Nov, 14:12


ከተረጅነት ለመላቀቅ እና በምግብ ራስን ለመቻል ግብርና ዋነኛ መሠረት ነው - የኮሬ ዞን አስተዳደር

ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ከተረጅነት ለመላቀቅ እና በምግብ ራስን ለመቻል ግብርና ዋነኛ መሠረት መሆኑን የኮሬ ዞን አስተዳደር ገለጸ፡፡

"የምርታማነት እምርታ ለቤተሰብ ብልጽግና በአዲስ እይታ" በሚል መሪ ቃል የወቅታዊ ሥራዎች የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሬ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ እንዳሉት፤ ህዝባችንን ከተረጅነት ለማላቀቅ ምሰሷችን የሆነውን ግብርናን በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ መምራት ከተረጅነት ወደ ምርታማነት የምናደርገውን ጉዞ አጠናክረን ለማስቀጠል እና ከድህነት ለመላቀቅ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።

ምርታማነትን ለማሳደግ በተለይ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችንን በማዘመን፣ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ፣ ኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴን ተግባራዊ ማድረግ እና ሰራተኞችን በሚገባ ወደ ሥራ ማስገባት ያስፈልገል ነው ያሉት አስተዳዳሪው።

የኮሬ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አስታረቀኝ አንደባ በበኩላቸው፤ ግብርና እንደ ሀገር  ባደጉት ሀገራት ተርታ ለመሰለፍና  ያስቀመጥነውን ግብ ለማሳካት በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ለገበያ ምርት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለውጭ ምንዛሪ የሚሆኑ ምርቶችን ከማምረት ረገድ ትርጉም ያለው ዘርፍ መሆኑን ገልጸዋል።

ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://web.facebook.com/southradioandtelevisionagency/posts/pfbid02QntvpZHHPbgjikmd4EJRntdH7reGn8UoHviMpiRMHo5XwugdeRs2kJ7uK17NknJNl

South Radio And Television agency

21 Nov, 12:50


ብልጽግና ፓርቲ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የጀመራቸውን የተለያዩ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ብልጽግና ፓርቲ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የጀመራቸውን የተለያዩ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

የሀድያ ዞን የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ የሴቶችና ወጣት አደረጃጀቶች የፓርቲውን 5ኛ አመት የምስረታ በዓል በማስመልከት በሆሳዕና ከተማና በሌሞ ወረዳ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የመሰረተ ልማትና የግብርና ልማት ሌማት ትሩፋት ውጤቶችን ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የሀድያ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ይርጋ ሀንዲሶ እንደገለጹት፤ ፓርቲው እንደ ሀገር ሁሉ ዐቀፍ የልማት ተግባራትን በማከናወን የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።

የህብረተሰቡን የምግብ ዋስትና በዘላቂነት ማረጋገጥ እንዲቻል በሌማት ትሩፋትና ሌሎችም ተግባራት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ ይርጋ ጠቁመዋል::
''የፓርቲው አመራሮችና አባላት በዞኑ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ያሉበትን ደረጃ በመመልከት ጉድለቶችን ለማረምና ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠልን ዓላማ ያደረገ የመስክ ምልከታ እንደሆነም አቶ ይርጋ አመላክተዋል፡፡

ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://web.facebook.com/southradioandtelevisionagency/posts/pfbid0PhSpt2gPSLK8oNcvQBKJqwCnR6asE1nkEoadVZC5peLCoHZkM7t5Phk8s2fp9xTql

South Radio And Television agency

21 Nov, 12:49


"የሀሳብ ልዕልና፤ ለሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ ብልጽግና ፓርቲ የተመሰረተበትን 5ኛ ዓመት በማስመልከት በምስራቅ ጉራጌ ዞን ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍል የመኖሪያ የቤት ግንባታ ተጠናቆ የቁልፍ ርክክብ ተደረገ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በክረምት ወራት በበጎ ፍቃድ አገልግሎት የተገነቡ የአረጋውያንንና የአቅመ ደካሞች ቤቶችን የብልጽግና ፓርቲ የተመሰረተበትን 5ኛ ዓመት በማስመልከት ቁልፍ አስረክበዋል።


የዞኑ የ2016 የክምረት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያና የበጋ ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡


የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ሰው ተኮር ስራዎችን ቅድሚያ በመስጠት የሚሰራው መንግስታችን የአረጋውያንንና የአቅመ ደካሞች ቤቶችን ገንብቶ እያስረከበ የቤት ባለቤት እያደረገ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።


በርክክቡ ወቅት የክልሉ፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞንና የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር አስተዳደር አመራሮችና ሌሎች አካላት ተገኝተዋል።


ምንጭ ፡ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬን ቢሮ

South Radio And Television agency

21 Nov, 12:47


በከተሞች የሚስተዋሉትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ሰፊ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በከተሞች የሚስተዋሉትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ሰፊ ድርሻ እንዳለው በባስኬቶ ዞን የላስካ ከተማ አስተዳደር ገለጸ።

የላስካ ከተማ አስተዳደር ከተማ አቀፍ የልማት፣ መልካም አስተዳደርና የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

የላስካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር አንለይ ወንድፍራው እንደተናገሩት፤ የላስካ ከተማ ከወቅቱ ጋር እኩል እየዘመነች የምትጓዝ ከተማ እንድትሆን ንቁ የህብረተሰብ ተሳትፎ ያስፈልጋል።

ከንቲባው በ2017 የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራትን ዕቅድ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በቀረበው እቅድ ዙሪያና ከዚህ ቀደም ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ በተሳታፊዎች ሐሳብ አስተያየት ተሰጥቶበታል።

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪና የዞኑ አስተዳዳሪ ተወካይ ኢንጂነር ዘማች ካንሶ በበኩላቸው፤ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ተቀናጅቶ በመፍታት የብዙ ፀጋ ባለቤት የሆነችውን ከተማን ካደጉ ከተሞች ተርታ ማሰለፍ ይገባል ብለዋል።

ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://web.facebook.com/southradioandtelevisionagency/posts/pfbid0TvQQWcYsmdboEAn7XTS88VRnZj6vnhkp6G3PViowQrJtxNn3kDaPRuZxXH99LETZl

South Radio And Television agency

21 Nov, 12:23


የበጎ ፍቃድ አገልግሎትን ይበልጥ አጠናክሮ በማስቀጠል የህዝቦችን አብሮነት ማሳደግ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቡቶ አኒቶ ገለፁ

በክልሉ የሳጃ ክላስተር ቢሮዎች ለአቅመ ደካማ አረጋውያን የመኖሪያ ቤት ገንብተው አስረክበዋል::

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሄረሰቦች ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ እንዳሉት፤ በሳጃ ክላስተር የሚገኙ ቢሮዎች በመተባበር ለአቅመ ደካማ አረጋውያን ቤት ገንብተው አስረክበዋል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራው የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ አመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የወንድማማችነት እና አብሮነት ተግባር እንዲጎለብት ለማስቻል መሆኑንም አፈ ጉባኤው አብራርተዋል።

የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ እጅጉ እንደገለፁት፤ የኢትዮጵያን ከፍታ ማረጋገጥ የሚቻለው በመተጋገዝ በአንድነት እና በመደጋገፍ ነው ብለዋል።

የሳጃ ክላስተር ሴክተር መስሪያ ቤቶች ላሳዩት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

በበጎ ፈቃድ ስራው ከመኖሪያ ቤት ግንባታው በተጨማሪ የቤት ቁሳቁስ፣ የተማሪዎች የመማሪያ ደብተር እና የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

South Radio And Television agency

21 Nov, 12:05


በክልሉ የኮሪደር ልማት የቅድመ ዝግጅት ስራው በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው

ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በኮሪደር ልማት በሚተገበሩ ስራዎች አፈጻጸም እና በተዛማጅ የከተማ የልማት ስራዎች ላይ ከክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የስራ ኃላፊዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በምክክር መድረኩ እንደገለጹት በክልሉ የኮሪደር ልማት የቅድመ ዝግጅት ስራው በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል።

የኮሪደር ልማቱ ለህዝብ የሚሰራ እንደመሆኑ የጋራ ተግባቦት መፍጠር ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለተግባራዊነቱ የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል።

የኮሪደር ልማት ስራው ውጤታማ እንዲሆን ግልጽ ደረጃ ተቀምጦለታል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ከዋና መንገድ የሚኖረው ርቀት፣ የህንጻ ከፍታ፣ የቀለም አይነት፣ የመብራት አይነቶች እና የበጀት ምንጭ ገላጭ በሆነ መንገድ በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ላይ መመላከቱን ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

የኮሪደር ልማቱ የሚመራበትን ስርዓት ለማጠናከር መመሪያ ማዘጋጀት ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ዘርፉን የሚደግፉ አመራሮች እንደሚመደቡም ጠቁመዋል።

የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማጠናከር የኮሪደር ልማት ስራው ወደፊት ወደ ሌሎች ከተሞች እና ወደ ገጠር አካባቢዎች ሊስፋፉ እንደሚችሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።

ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://web.facebook.com/southradioandtelevisionagency/posts/pfbid02ko2zMVq9Tf1yiPr72XL3TZPqNcQFiCq5SVu6xZUA5YXcRjkFPaGdqJpoAFVNdpjpl

South Radio And Television agency

21 Nov, 12:04


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ለ350 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ቢሮው ከኦሞ ባንክ ጋር በትብብር የተዘጋጀ የብድር አስመላሽ ግብረ ሀይል መድረክ በሆሳዕና ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ ባስተላለፉት መልዕክት በክልሉ 350 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በየደረጃው በቅንጅት በተሰራ ስራ 3 ሺህ 170 ገደማ መሰረተ ልማት የተሟላላቸው የማምረቻና የመሸጫ ሼዶችን ኢንተርፕራይዞች ማስተላለፍ መቻሉን መረጃዎች ያሳያሉ ብለዋል።

መንግስት ግብዓት በማቅረብ የክህሎትና አመለካከት ማነቆዎችን በመፍታት በርካታ ኢንተርፕራይዞች ሀብት ፈጥረው ወደ ኢንዱስትሪ የተሸጋገሩ መሆናቸውን ቢሮ ኃላፊው ገልጸዋል።

በክልሉ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አክመል አህመዲን ክልሉ የያዘውን የስራ ዕድል ፈጠራ ግብ እንዲያሳካ በብድር የተሰራጨውን ገንዘብ ለመሰብሰብና ያልተላለፉ ሼዶችን ለማስመለስ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኦሞ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብርሃም አላሮ ባንኩ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት የስራ ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍን ለማገዝ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ እንደቆየ ተናግው፤ አሁንም ከክልሉ ጋር በትብብር ለመስራት ባንኩ ዝግጁ መሆኑን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

በመድረኩ ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ የዞንና የልዩ ወረዳ የስራ ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

South Radio And Television agency

21 Nov, 11:44


ማህበራዊ ሚዲያን በአግባቡ በመምራት እና በመጠቀም የአካባቢን ገጽታ መገንባት እንደሚገባ ተጠቆመ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ማህበራዊ ሚዲያን በአግባቡ በመምራት እና በመጠቀም የአካባቢን ገጽታ መገንባት እንደሚገባ የቡርጂ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ጠቁሟል፡፡

መምሪያው በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና ስነ-ምግባር ዙሪያ የግንዛቤ ሥልጠና ለባለድርሻ አካላት ሰጥቷል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የቡርጂ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ኮሬ አዶ፤ ሚዲያ ለሀገር ገፅታ ግንባታ ያለውን ጥቅም በመረዳት በአግባቡ መጠቀም አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

በቡርጂ ዞን ያለውን እምቅ ሀብት ለዓለም ለማስተዋወቅ እና ልማቱን ለማፋጠን ሚዲያዎች ወሳኝ መሆናቸውን ተረድተን ለበጎ ዓላማ ብቻ ማዋል እንደሚገባ አክለዋል።

የቡርጂ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን መመሪያ ኃላፊ አቶ አቤል አይላ እንዳሉት፤ ሚዲያ በአግባቡ ከተመራ እድገትን የሚያፋጥን፣ በአግባቡ ካልተመራ ደግሞ አጥፊ መሣሪያ መሆኑን ተረድተን በኃላፊነት እና በተጠያቂነት መንፈስ በጥንቃቄ ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል።

በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ውስጥ የማህበራዊ ሚዲያ ባለሙያ የሆኑት በአቶ ደጀኔ ፈጠነ የተዘጋጀው ሚዲያ ያለው ጥቅምና ጉዳት እንዲሁም የሚዲያ አማራጮችን ተጠቅመን በዞኑ የሚገኙ ሀብቶችን የማስተዋወቅ ሥራ መሥራት እንደሚገባ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://web.facebook.com/southradioandtelevisionagency/posts/pfbid0iSrKTzaMDKSzWXGBRHbeL6zQ85N4K5MBsRVt1fVuq59LdRbWTjkWqNS7wAPShYHql

South Radio And Television agency

21 Nov, 10:12


የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ግምገማ እየተካሄደ ነው

ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በአርባምንጭ ከተማ 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየገመገሙ ነው፡፡

በዚሁ ወቅት አቶ አገኘሁ ተሻገር÷ በአርባምንጭ ከተማ በዓሉ እንዲከበር ሲወሰን መሰረታዊ መነሻዎች ነበሩት ብለዋል፡፡

ራስን በራስ ለማስተዳደር የተጠየቀው ጥያቄ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ የተመለሰበት እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ከ76 ብሔር ብሔረሰቦች 32ቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መገኘታቸው አንዱ ምክንያት መሆኑንም አንስተዋል፡፡

አርባምንጭ በየጊዜው እያደገ የሚገኝ ከተማ መሆኑ እንዲሁም ከፍተኛ የቱሪዝም ፍሰት ያለበት መሆኑ ተመራጭ እንዳደረገው ገልፀዋል።

በዓሉ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዓል በመሆኑ በድምቀት ለማክበር ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችም እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ ጠቅሰው÷ በዓሉ መከበሩ የክልሉን አቅም እና ፀጋ ለማስተዋወቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው÷ በዓሉን በተሻለ እና ለሀገር ትምህርት በሚሆን መልኩ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀዋል።

ውይይቱም የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገምና በቀሪ ስራዎች ዙሪያ ለመነጋገር እና የመስክ ጉብኝት ለማድረግ ያለመ ለመሆኑ ተመላክቷል፡፡

South Radio And Television agency

21 Nov, 09:58


ዩኤንዲፒ አህጉራዊ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል በአዲስ አበባ ለመገንባት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) አህጉራዊ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል በአዲስ አበባ ለመገንባት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከዩኤንዲፒ ፕሮጀክት ጋር አምራች ኢንዱስትሪውን በሚያሳልጡ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ዙሪያ አብሮ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱም ዩኤንዲፒ ኢትዮጵያ ውስጥ በአምራች ኢንዱስትሪ ዙሪያ ያሉ የፈጠራ ስራዎችን ለመደገፍና አጠቃላይ የአፍሪካን አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርታማነትን ለመጨመር የአህጉሩን የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል አዲስ አበባ ላይ ለመገንባት ጽኑ ፍላጎት እንዳለው መግለጹን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ዩኤንዲፒ በበርካታ የዓለም ሀገራት ቀጣይነት ያለው ዕድገትን ለማምጣትና ድህነትን ለመቀነስ፣ የሴቶችን ተሳትፎ ለማረጋገጥ፣ በፍትህና በመልካም አስተዳደር ዙሪያዎች ድጋፍ የሚያደርግ ዓለም አቀፍ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል።

South Radio And Television agency

21 Nov, 09:54


የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዓመቱ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ አየር መንገዶች ማኅበር የዓመቱ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን አሸንፏል፡፡

አየር መንገዱ በማኀበሩ በዓለም አቀፍ አገልግሎት የዓመቱ ምርጥ አየር መንገድ ተብሎ ሲሸለም የአሁኑ ለስምንተኛ ጊዜ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሽልማቱን ያሸነፈው በግብጽ ካይሮ በተካሄደው 56ተኛው የማኀበሩ አጠቃላይ ስብሰባ ላይ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

South Radio And Television agency

21 Nov, 09:42


የአዳሪ ትምህርት ቤቶች መስፋፋት ጥራት ያለው ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እንደሚያስችል ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአዳሪ ትምህርት ቤቶች መስፋፋት በክልሉ ጥራት ያለውና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት ያስችላል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ የኤሶል ልዩ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ት/ቤት የክልሉ ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባየሁ ታደስ በተገኙበት ተመርቆ ተከፍቷል።

የኣሪ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳግም መኮንን እንደገለፁት እንደ ሀገር የገጠመንን የትምህርት ስብራት ለመጠገን በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት እየተተገበሩ ያሉ ሥራዎች አበረታች መሆኑን ገልፀው፥ ትምህርት ቤቱ ለዚህ እንዲበቃ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ በበኩላቸው ትምህርት ለሁለንተናዊ ለውጥ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን በማመን ከወላይታ ሊቃ ት/ቤትና ከአርባምንጭ ባይራ ት/ቤት ተሞክሮ በመውስድ ለዚህ መብቃቱን አስታውሰዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ እንዲህ አይነት አዳሪ ት/ቤቶች ለክልላችን ህዝቦች ትልቅ አቅምና ዕድል መሆኑን ተናግረው በሁሉም አከባቢ እንዲህ አይነት አዳሪ ት/ቤቶች ሊስፋፉ እንደሚገባና ሊጠናከሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://web.facebook.com/photo/?fbid=985403790292683&set=pcb.985404473625948

South Radio And Television agency

21 Nov, 09:40


የትምህርት ጥራትና ውጤት መሻሻል ዙሪያ የሚተገበሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ አሳሰበ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የትምህርት ጥራትና ውጤት መሻሻል ዙሪያ የሚተገበሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ አሳስበዋል።

በኣሪ ዞን ኤሶል ልዩ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት መርቀው ወደ ሥራ ባስገቡት ወቅት ነው ዶ/ር አበባየሁ ይህንን ያሳሰቡት።

አዳሪ ትምህርት ቤቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ9ኛ ክፍል 50 ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማር ሥራውን አሀዱ ብሎ መጀመር የሚያስችል ፕሮግራም ተካሂዷል።

የበጀት ዓመቱ የመማር ማስተማር ሥራውን ባሉበት ትምህርት ቤት ሲከታተሉ ቆይተው አዳሪ ትምህርት ቤቱ ያወጣውን ፈተና ተቀብለው ወደ ማዕከሉ እንዲገቡና ከህዳር 13/2017 ዓ.ም ጀምሮ የክፍል መማር ማስተማር ሥራው እንዲጀመር ዝግጅት መደረጉን የኣሪ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ዳግም መኮንን ገልፀዋል።


የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ በበኩላቸው፤ ትምህርት የሁሉም ነገር መሠረት መሆኑን ጠቁመው በዘርፉ እንደ ሀገር ወጥ የሆነ ውጤት መመዝገብ እንዲችል ዞኑ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

ዞኑን፣ ክልሉንና ሀገርን ጠቅሞ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚሆኑ ዜጎችን ለማፍራት ዞኑ ልዩ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ማቋቆሙን ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።

ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://web.facebook.com/photo/?fbid=985402050292857&set=pcb.985403006959428

South Radio And Television agency

21 Nov, 09:14


የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://web.facebook.com/photo/?fbid=985389540294108&set=pcb.985390193627376

South Radio And Television agency

21 Nov, 09:00


የጀርመን ሀገር የፓርላማ አባላት የኢትዮጵያን የጤና ስርዓት ለማሻሻል እያደረጉ ያሉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጀርመን ሀገር የፓርላማ አባላት የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎት ስርዓት ተሞክሮ ለመመልከትና ሊደረጉ በሚገቡ ወሳኝ ድጋፎችን አስመልክቶ ከሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ጋር ምክክር አድርገዋል።

በምክክሩም DSW የተሰኘ የጀርመን ሀገር ግብረ-ሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ ላለፉት ሀያ ዓመታት የሰራቸው ስራዎች ምን ያህል ውጤታማ ነው የሚለውን በጋራ በመገምገም በዋናነት የወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ጤና ላይ የተከናወኑ ተግባራት ላይ እና በቀጣይም በግብረ ሰናይ ድርጅቱ በኩል የሚሰጡ አገልግሎቶችና የሚደረጉ ድጋፎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ እንደነበር ዶ/ር ደረጀ አስታውቀዋል።

ድርጅቱ በቢሾፍቱ ከተማ የወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ጤናማ አኗኗር ላይ አቅም ማጎልበቻ ማሰልጠኛ ማዕከል ከፍቶ እየሰራ ያለና እና የህክምና መስጫ ክሊኒክ እንዳለው የጠቀሱት ዶ/ር ደረጀ እነዚህንም የአገልግሎት ማዕከላት ለወጣቶችና አፍላ ወጣቶች በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠናዎችንና የስነ ተዋልዶና ህክምና አገልግሎት እንደሚሰጡ አክለው በአዲስ አበባ የሚገኙ የወጣቶች ህክምና መስጫ ተቋማትንና በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚሰሩ ወጣቶችንም ጤና ሁኔታ እንዲሁም ለወጣቶች የስነ ተዋልዶና አገልግሎት የሚያስፈልጉ ግብዓት አቅርቦትን በአካል ተገኝተው መጎብኘታቸውን ተናግረዋል።

ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://web.facebook.com/photo/?fbid=985381940294868&set=pcb.985382813628114

South Radio And Television agency

21 Nov, 08:47


በክልሉ በኮሪደር ልማት እና በሌሎች በከተማ ልማት በሚተገበሩ ስራዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት እየተደረገ ነው

ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በክልሉ በኮሪደር ልማት በሚተገበሩ ስራዎች አፈጻጸም እና በተዛማጅ የከተማ የልማት ስራዎች ላይ ከክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።

በመድረኩ የኮሪደር ልማት ዝግጅት እና አፈጻጸም፣ በአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት፣ በሰባቱ የክልል ማዕከላት የቢሮ ግንባታ፣ በከተሞች ተግባራዊ ስለሚደረጉት ሞዴል የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ፣ የከተማ ግብርና አፈጻጸም እና ዝግጅት ላይ ላይ ያተኮረ ውይይት መሆኑን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

South Radio And Television agency

21 Nov, 08:33


እምቅ ሀገራዊ ሀብቶቻችን በተሻጋሪ እሳቢያችን በማልማት እንደ ሀገር የተጀመረውን የዕድገት ጉዞ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) እምቅ ሀገራዊ ሀብቶቻችን በተሻጋሪ እሳቢያችን በማልማት እንደ ሀገር የተጀመረውን የዕድገት ጉዞ ማስቀጠል አለብን ሲሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ ተናገሩ፡፡

ኢንጂነር አክልሉ በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ በከተማና መሠረተ ልማት እንቅስቃሴዎች ዙሪያ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ የውይይት መድረክ እንዳሉት፤ የለውጡ መንግስት መምጣትን ተከትሎ ለሀገሪቱ የምጣኔ ሀብት ዕድገትና ለህዝቡ የጋራ ተጠቃሚነት ፋይዳ ያላቸውን እሳቤዎችን በማምጣት ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡

እነዚህን እሳቤዎች ተከትሎ እንደ ሀገር ያሉንን ሀብቶች በመጠቀም የተጀመረውን እንቅስቃሴ ለማስቀጠል ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ነው ኢንጂነር አክሊሉ ያሳሰቡት፡፡

የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የዲላ ከተማን ሁለንተናዊ ዕድገት ከሌሎች አቻ ከተሞች ጋር እኩል ለማራመድ የተጀመሩ ሥራዎች ቢኖሩም በሚፈለገው ደረጃ ልማቱን ለማፋጠን የህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል፡፡

በውይይቱም የሀይማኖት አባቶችና የባህል ሽማግሌዎችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ዘጋቢ፡ ሳሙኤል በቀለ - ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

4,053

subscribers

18,986

photos

40

videos