EEU HARARI REGION

@eeuharariregion


www.eeu.gov.et
ብርሃን ለሁሉም

EEU HARARI REGION

16 Oct, 16:55


ከሁለት ሳምንት በኋላ መስመሩ ዳግም ተገናኝቷል
………///……….
በስርቆት ምክንያት ላለፉት ሁለት ሳምንታት አገልግሎቱ ተስተጓጉሎ የነበረው የቆቃ-ሁርሶ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ማምሻውን አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ ሁለት ሪጅን የኃይል ማስተላለፊያዎችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ዘበርጋ እንደገለፁት የተቋረጠውን መስመር መልሶ ለማገናኘት ከፍተኛ ርብርብ ሲደረግ ቆይቷል።

ከሪጅኑ በተጨማሪ የሦስት ሪጅኖች ባለሙያዎችን በቅንጅት በማሳተፍ የተከናወነው የጥገና ሥራ የምስራቅ ኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ከፈረቃ ወጥተው ኃይል እንዲያገኙ ማስቻሉን ዳይሬከረተሩ ገልፀዋል።

በጥገና ሥራው ላይ የተሳተፉ ሁሉንም ባለሙያዎችና የአዋሽ 7 ኪሎ ከተማ አስተዳደርን አመስግነዋል።

የአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ተደጋጋሚ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ስርቆት ከሚፈፀምባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ ነው።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

EEU HARARI REGION

12 Oct, 17:04


ከቆቃ- ሁርሶ በተዘረጋው መስመር ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን ርብርብ እየተደረገ ነው
………///……….
በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ የወደቀውን ባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመጠገን ኃይል የተቋረጠባቸው አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ ሁለት ሪጅን የኃይል ማስተላለፊያዎችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ አስታወቀ።

በመምሪያው የማስተላለፊያ መስመር ጥገና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጎሣዬ ደምሴ እንደገለፁት ከቆቃ ሁርሶ በተዘረጋው የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የተፈፀመው ስርቆት በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ለሚገኙ አንዳንድ ከተሞች የኃይል መቋረጥ ምክንያት ሆኗል።

ጉዳት የደረሰበትን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ መልሶ ለማቆም የወደቀውን ምሰሶ የመፈታታት ሥራ መጀመሩን የተናገሩት አቶ ጎሳዬ ምሰሶውን መልሶ በማቆም በቀጣይ ሳምንት የመጀመሪያዎቹ ቀናት አካባቢዎቹ ኃይል እንዲያገኙ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሪጅኑ 12 ባለሙያዎች በጥገና ሥራው ላይ እየተሳተፉ ቢሆንም ሥራውን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ከማዕከላዊ አንድ እና ሦስት ሪጅን እንዲሁም ከምስራቅ አንድ ሪጅን ተጨማሪ ባለሙያዎች ቡድኑን እንዲቀላቀሉ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

የጥገና ሥራው ሙሉ በሙሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስም ከመስመሩ ኃይል ሲያገኙ የነበሩ ከተሞችና አካባቢዎች በፈረቃ ኤሌክትሪክ የማድረግ ሥራው እንደሚቀጥል ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

ለጥገና ሥራው የቅርብ ድጋፍ እያደረገ ያለውን የአዋሽ 7 ኪሎ ከተማ አስተዳደር እና ከንቲባውን በሪጅኑ ስም አመስግነዋል፡፡

በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በኃይል ማስተላለፊያ ተሸካሚ ምሰሶ አካላት ላይ እየተፈፀሙ የሚገኙ የስርቆት ወንጀሎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የመስተዳድር እና የፀጥታ አካላት ለመሰረተ ልማቶቹ ተገቢውን ጥበቃና ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም

EEU HARARI REGION

12 Oct, 09:12


የሐዘን መግለጫ
**
የሐረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አግልግሎት የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ሊቀመንበር በመሆን ለረጅም አመታት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ በለጠ ሽፈራው ለረጅም ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው  ዛሬ ከዚህ አለም በሞት ተለይተውናል።

አቶ በለጠ ሽፈራው በሐረሪ ሪጅን ሰራተኞች እና የስራ መሪዎች እጅጉን የሚወዱ እና ለሰራተኛው መብትና ግዴታ ሁሌም ከፊት በመሆን ቀዳሚ እንደነበሩ ይታወቃል።

የሐረሪ ሪጅን ሰራተኞች ለመላው  ለቤተሰቦቹ እና ወዳጆቹ መፅናናትን ይመኛሉ።

EEU HARARI REGION

11 Oct, 07:55


ውድ ደንበኞቻችን***

እሁድ 3-2-2017 ከማለዳው 12:00 እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ድረስ እነዚህ ከተሞች ማለትም ሀረማያ:ሐረር :ጅጅጋ:ደገሀቡር:ፊቅ  የከፍተኛ መስመር ጥገና ስለሚደረግ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚቋረጥ መሆኑን እየገለፅን ሁሉም ህብረተሰብ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳውቃለን::
#ምንጭ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ምስራቅ ሪጅን

EEU HARARI REGION

11 Oct, 05:50


ለቅደመ ጥገና ስራ ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦትን ማሳወቅ ይመለከታል::
****

ቅዳሜ በቀን 2-2-2017 ዓ.ም ከጠዋቱ  
3፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት እነዚህ አካባቢዎች  ቀበሌ 15:16:17: በከፊል ደግሞ 13:18: ደከር ኮንዶሚንየሜ ቢራ እና ሐማሬሳ ዘይት ፍብሪካ  የኤሌክትሪክ አገልግሎት በስራ ምክንያት የሚቋረጥ መሆኑን እየገለፅን ሁሉም ህብረተሰብ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳውቃለን።

#የሐረሪክልልኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUHarrariregion
ቴሌግራም፡https://t.me/eeuharariregion
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et/

EEU HARARI REGION

06 Oct, 06:43


ለቅደመ ጥገና ስራ ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦትን ማሳወቅ ይመለከታል::
****

ሰኞ በቀን 27-1-2017 ዓ.ም ከጠዋቱ  
3፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት እነዚህ አካባቢዎች ቲቲ አይ ኮንዶሚንየም እና ቀበሌ07:08:09:10: በከፊል  የኤሌክትሪክ አገልግሎት በስራ ምክንያት የሚቋረጥ መሆኑን እየገለፅን ሁሉም ህብረተሰብ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳውቃለን።

#የሐረሪክልልኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ የተቋማችን መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ እነዚህን የትስስር ገፆቻችንን ይወዳጁ፡-

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/EEUHarrariregion
ቴሌግራም፡https://t.me/eeuharariregion
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/c/EthiopianElectricUtility
ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et/

EEU HARARI REGION

03 Oct, 11:26


የሐረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ አቶ ፈሪድ አብዱሰላም በቦታቸው አዲስ ከተሾሙት ወ/ሮ ቤተልሄም ጨቡድ የስራ ርክክብ አደርገዋል።

አቶ ፈሪድ አብዱሰላም አዲስ ለመጡት ለቢሮ ኃላፊ መልካም የስራ ዘመን በመመኘት በቀጣይም ራጅኑን በአስፈላጊው ነገር ሁሉ እገዛ እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።

አቶ ፈሪድ አብዱሰላም በሐረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚነት ለስድስት አመታት ያገለገሉ ሲሆን አሁን ደግሞ ተቋሙ አዲስ በሰራው ሪፎርም ወደ ዋና ቢሮ በሌላ የስራ ሀላፊነት መመደባቸው ይታወቃል።

#የሐረሪክልልኤሌክትሪክአገልግሎት