Prosperity Party - ብልፅግና @prosperity2022 Channel on Telegram

Prosperity Party - ብልፅግና

@prosperity2022


This is an official telegram channel of prosperity party.

Prosperity Party - ብልፅግና (Amharic)

በስልጠና መፈታተኛ ቴሌግራም ከብልፅግና ፖምታ ለመኖር እና ለበልፅግና ቦታዎች ማወቅ ያለበትን ቴሌግራም እቅም ለመልኩ ሆኖ በመሠረት ተመልክቼዋል። ስለ ብልፃግን ፖምታ በእንስሳት የተመለሱትን ሕንፄታዊ መረጃዎችን ማግኘትና ከተለያዩ ህብረተሰብ አመራርቶት የተባለውን ሕንፄታን ለማበቃት አሁኗን ማስተማር እንችላለን።

Prosperity Party - ብልፅግና

18 Dec, 13:53


“በህብረት ሆነን እንበለጽጋለን፤ በልጽገንም በህብረት እንኖራለን"

የፓርቲያችን ዋነኛ ዓላማ ህብረ ብሔራዊነቱ የተጠበቀ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት ነው። ህብረ ብሔራዊ ስንል የብሔር፣ የሃይማኖት ወይም ሌላ ማንነቶችን ያቀፈና ማንንም ያላገለለ ማህበረሰብ ማለታችን ነው።

የፓርቲያችን ህብረ ብሔራዊነት በሁሉን አቀፍነት፣ በብዝኃ ልሳንነት እና በአሳታፊነት ሊገለጽ ይገባል ብሎ ፓርቲያችን ያምናል።

ህብረ ብሔራዊ አንድነት ብዝኃነትን እንደጸጋ የሚመለከት ለሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዕውቅና የሚሰጥና ካላቸው የታሪክ ትሥሥር፣ ተመሳሳይ አሁናዊ ሁኔታ፣ የጋራ ጥቅም እና ተስፋ በመነሣት ጠንካራ ህብረትና ትብብር ሊኖራቸው ይገባል የሚል ዕሴት ነው።

ህብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ማንነታችን እርስ በርሱ የተጋመደ፣ የተሠናሰለ እና የተዋሐደ መሆኑን አመላካች ነው። ህብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ዕጣ ፈንታችን እጅጉን የተቆራኘ መሆኑን በመገንዘብ ለጋራ ዓላማና ግብ አብረን መቆም፣ አብረን መሥራት፣ መደጋገፍ እና መተጋገዝ እንደሚገባን የሚያስገነዝብ አመለካከት ነው።

ህብረ ብሔራዊ፣ አንድነት ታሪካዊና ነባራዊ በደሎች ከማድበስበስ ይልቅ ታርመው እንዲሄዱ፣ ይህም ለቁርሾ ሳይሆን ወዳጅነትን ለማጠናከር እንዲውል የሚያደርግ አካሄድ ነው።

ህብረ ብሔራዊ አንድነት፣ የሚከፋፍሉ እና የሚያጣሉ ትርክቶችን ከማጉላት ይልቅ የሚያቀራርቡና የሚያስተሣሥሩንን እውነታዎች በማጉላት፣ ከትናንት ጠቃሚ ትምህርቶችን በመውሰድ እንዲሁም ዛሬና ነገ ላይ በማተኮር እህታዊ/ወንድማዊ ህብረትን በብሔሮች መካከል ማጠናከርን ይመርጣል።

ህብረ ብሔራዊ አንድነት ብዙ ሆነን አንድ፣ አንድ ሆነንም ብዙ የምንሆንበት፣ ለጋራ ግብና ዓላማ የምንደመርበት ቀመር ነው። በብዝኃነታችን ደምቀን፣ በአንድነታችን በርትተን ወደፊት የምንራመድበት የውበትና የጥንካሬያችን ምንጭ ነው።

ፍትሕ ከሰፈነ፣ ሰብአዊ ክብር ከጎለበተ እና ብልጽግና ከመጣ እንደ ሀገር የመቀጠል ተስፋችን ይለመልማል። ሆኖም ግን ኅብረ ብሔራዊ አብሮነት እነዚህ ምሦሶዎች ከተሳኩ በኋላ የሚመጣ ብቻ ሳይሆን ለዓላማዎች ስኬትም ዓይነተኛ ድርሻ የሚወጣ አስቻይ ዐቅም በመሆኑ ፓርቲያችን “በህብረት ሆነን እንበለጽጋለን፤ በልጽገንም በህብረት እንኖራለን” በሚል መርሕ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማረጋገጥ በከፍተኛ ትኩረት ይሠራል።

መልካም ሳምንት እንዲሆንላችሁ ተመኘን!!

#prosperity

Prosperity Party - ብልፅግና

18 Dec, 13:46


ትርክቶች የትናንት ታሪኮችን እንደ እርሾ በመጠቀም ዛሬ ላይ ለምንፈልገው አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ ፍላጎቶቻችን የምንጠቀምባቸው፣ፍላጎቶችን የምናሰባስብባቸው መሳሪያዎች ናቸው።

ትርክት ተቀባይነት የሚኖረው ስለ ማህበረሰቡ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ግልፅ በሆነ የጊዜና የድርጊት ፍሰት ሲቀርብ፣ድርጊቱ ደግሞ ትርጉም ባለው ሁኔታ መቀመጥ ሲችል ነው።

ትርክት የአብሮነት መሰረት ነው!! ሰዎችን ከየት እንደተነሱ እና ወዴት እንደሚደርሱ የሚያመለክታቸው ትርክት ነው።

አዎንታዊ ትርክት በህዝብ ውስጥ መነሳሳትን አብሮነትን እና አንድነትን የሚፈጥር የሀገር ታሪክ የወደፊት ተስፋዋን እና ዛሬ ላይ የሚኖረውን ሚና እና የሚከሰቱ ክስተቶችን የምንመለከትበት መነፅር ነው።

ፓርቲያችን እንደ ሀገር "ብሔራዊነት"አዎንታዊ የሆነ ትርክት እንደሆነ በማመን የሀገራችን ገዢ ትርክት እንዲሆን በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

"ብሔራዊነት" ማለት ህገ መንግስታዊነትን መሰረት ያደረገ ኃብረ ብሔራዊ አንድነት ማለት ነው።

ህገ መንግስታዊነት ማለት ደግሞ ህዝቦች ተግባብተውና ተስማምተው በህገ መንግስታቸው ላይ ባስቀመጧቸው እሴቶች መሰረት ሀገረ መንግስቱን ለመገንባት መቻል ነው።

ህብረ ብሔራዊ አንድነት ማለት ደግሞ የኢትዮጵያውያንን የብሔር፣የቋንቋ፣የሀይማኖት፣የፆታ፣የአስተሳሰብ፣የታሪክ ብዝሀነትን እንደ ጌጥ እንደ ፀጋ የሚቀበል፣እነዚህን ማንነቶች አስተሳስሮ፣አስተባብሮ የያዘ ሀገራዊ አንድነት አለ ብሎ የሚያምን ነው።

ብዝሀነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው፣አንድነቱም ብዝሀነቱን ሳይጠቀልለው ብዝሀነቱ ፀጋ፣ጌጥ አንድነቱም ኋይል ብርታት እንደሆነ የሚቀበል ነው።

ብልፅግና ብሔራዊነት ገዢ ትርክቱ እንዲሆን የፈለገበት ምክንያትም አማካይ በመሆኑ፣በጋራ ነገሮቻችን ላይ ስለሚያተኩር፣ለሁሉም እኩል እድል ስለሚሰጥ እንዲሁም ሀገራዊ መግባባትን ማምጣት ስለሚችል ነው።

Prosperity Party - ብልፅግና

29 Nov, 12:42


ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት እንዲቻል የአመራሩን አቅም ለማጎልበት በትኩረት ይሰራል፡- አቶ አደም ፋራህ
***************

ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት በየደረጃው ያሉትን የአመራር አባላት አቅም የማጎልበት ተግባር ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚደንትና የፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ።

አቶ አዳም ፋራህ በጎንደር የስልጠና ማዕከል እየተሳተፉ ለሚገኙ 4ኛው ዙር ሰልጣኞች ባስተላለፉት መልዕክት ላይ እንዳመለከቱት፤ እንደ ሀገር ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ተቋማዊ አቅምን የሚያዳብሩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል።

ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስትን በመገንባት ሂደት ብዝሃነትንና ህብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝም ስርዓትን ማጠናከር ብሎም ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህንን በተግባር ለማረጋገጥ በየደረጃው ያሉትን የአመራር አባላት አቅም በማጎልበት የማብቃት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የጠራ እሳቤና ትክክለኛ እሴቶች ተግባራዊ ያደረጉ የአመራር አባላት የህዝብ ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የአመራር አባላት ተልዕኮውን በውጤታማነት እንዲፈጽም የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

የአመራር አባላቱን በወቅታዊ ሀገራዊና ዓለማ አቀፍ ጉዳዮች ላይ ማወያየት የጠራ የጋራ ራዕይና አመለካከትን ለማስፈን ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አቶ አዳም ፋራህ ገልጸዋል።

''ስልጠናው ዓላማውን በማሳካትና ውስጠ አንድነትን በማጠናከር የአመራር አባላቱን ተነሳሽነት በመፍጠር ውጤታማ ነው'' ብለዋል።

አባላቱ ከስልጠናው በሚያገኙት አቅም፣ እውቀትና ክህሎት በመታገዝ እንደ ሀገር የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት መረባረብ እንዳለባቸውም ማሳሰባቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

''ስልጠናው ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጎልበት ጠንካራ ሃገረ መንግስት ለመገንባት የሚያስችል ነው'' ያሉት ደግሞ የስልጠናው ተሳታፊ አቶ አዲሱ ሰለሞን ናቸው።

ሌላው ተሳታፊ አቶ መሃዲ ኡመር በበኩቸው፤ ''ሀገራችን ከገጠማት ችግር ፈጥና ልትሻገር የምትችለው ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ስናጠናክር ብቻ መሆኑን ስልጠናው ግንዛቤ የፈጠረ ነው'' ብለዋል።

''ከዕዳ ወደ ምንዳ'' በሚል መሪ ሃሳብ በጎንደር የስልጠና ማዕከል እየተካሄደ ባለው ስልጠና ከ1ሺ 200 በላይ የመንግስት አመራር አባላት በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ተመልክቷል።

Prosperity Party - ብልፅግና

29 Nov, 12:11


በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግስት ሰው ተኮር የሆኑ ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎች እና ፕሮግራሞችን በመቅረፅ የህብረተሰባችንን ኑሮ በሁለንተናዊ መልኩ የሚያሻሽሉ እና የሚደግፉ ተግባራትን በመከወን ላይ ይገኛል።

ከዚህም መካከል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎቻችን መሰረታዊ የሆነ የምገባ አቅርቦት የሚያገኙበት በኑሮ ጫና እና በድህነት ምክንያት በምግብ እጦት እንዳይጎዱ በማሰብ ተግባራዊ የተደረገው የምገባ ማዕከላት ግንባታ አንዱ ነው።

በዚህ የምገባ ስርአት ዜጎች ልክ እንደ ቤታቸው ቁርስ፣ምሳ እና እራት በቀን 3 ጊዜ የሚመገቡበት ማእከላት በማዘጋጀት ስኬታማ ተግባራትን መከወን ችለናል።

ይህም ተግባር በአለምአቀፍ መድረኮች ሽልማትን እስከማስገኘት ድረስ ያደረሰ እና በምሳሌያዊ ተሞክሮ ጭምር ለበርካታ ሀገራት በልምድ ግብአትነት የተወሰደ ሰው ተኮር ተግባር ነው።

አሁን ላይ ይህ ተግባር ተጠናክሮ ይሰፋ ዘንድ የተለያዩ እርምጃዎችም እየተወሰዱ ይገኛል።

በአበይትነት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ግንባታ በዛሬው እለት አስጀምረዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ከሚሰራቸው ሰው ተኮር ስራዎች እና የለውጡ ትሩፋት አካል የሆነው የአዲስ አበባ ከተማ ተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከላትን ልምድ ማስፋት እንደሚገባ ክብርት ከንቲባ አዳነች አበቤ ገልፀዋል።

በዛሬው እለት ለግንባታ መሰረት የተጣለው የተስፋ ብርሃን የኮምቦልቻ ምገባ ቅርንጫፍ የምገባ ማዕከል ባለሀብቶችንና ተቋማትን በማስተባበር የተጀመረ ሲሆን ከሰው ተኮር አላማው በተጨማሪ አንዳችን ለአንዳችን የቆምንበት የህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ምሳሌያዊ ተግባር ማሳያ እንደሚሆን እሙን ነው።

#prosperity

Prosperity Party - ብልፅግና

20 Apr, 02:08


ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤም ኤፍ ባወጣው የ2023 የኢኮኖሚ ምጣኔያዊ ሪፖርት መሰረት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በ5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

የሀገራችን ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 156.08 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ በዚህም ከዓለም ሀገራት 59ኛ ደረጃ መቀመጥ ችላለች፡፡ 

እንደ ብልፅግና ፓርቲ ሀገራችን ባለፉት አመታት ውስጥ በከባድ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ችግሮች እየተፈተነች ቢሆን ታላላቅ ድሎችን የማስመዝገብ ጉዟችንን አጠናክረን ለመቀጠል ያለንን ቁርጠኝነት ያሳየንበት ጊዜ ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከድህረ ጦርነት በኋላ ሊያጋጥማት የሚችሉ መንኮታኮቶችን ቀድመን በመረዳት በጦርነት ወቅትም ቢሆን ስንዴን ለውጪ ገበያ ኤክስፖርት ለማድረግ ይፋ ያደረግነው እቅድ ከፍተኛ ፍሬ አፍርቶ ለኢኮኖሚ እድገታችን ግብአት መሆን ችሏል።

በቡና፣ በቀንድ ከብቶች፣ በጥራጥሬ እና በቅመማ ቅመም ምርቶች ላይ የፈጠርነው የግብርና አብዮት በግብርናው ዘርፍ ላይ በተግባር ላይ ከዋለው የሪፎርም ስራዎች ጋር ተዳምሮ አሁን ላይ የተገኘው ውጤት አመርቂ እንዲሆን አስችሎታል።

ተጨማሪ የገቢ ምንጮችን በመፍጠር  የሌማት ትሩፋት እና አረንጓዴ አሻራን የመሰሉ ሀገር አቀፍ የልማት ንቅናቄዎችን በመፍጠር ምርታማነትን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ እንዲቻል ከራስ አልፎ የውጪ ገበያ ሊቀርብ የሚችል የኢኮኖሚ ግብአት መጓደል እንዳይኖር ሰፊ ስራዎችን ስንሰራ ቆይተናል። በርካታ ውጤቶችም ተመዝግበዋል።

እንደ ሀገር ያስመዘገብነው የምጣኔ ሀብት ደረጃ በጎ ሆኖ ሳለ በቀጣይ የኑሮ ውድነትን የመሰሉ ፈተናዎች አኮኖሚያችን ላይ ጥቁር ጠባሳ እንዳይጥሉ በከፍተኛ የሀላፊነት ስሜት በመንቀሳቀስ በዜጎች ዘንድ ትርጉም ያለው ለውጥ ሊያመጣ የሚችል የኢኮኖሚ ስርአት ማስመዝገብ እንደሚገባን ፓርቲያችን ብልፅግና በጥብቅ ያምናል።

በቀጣይም የኑሮ ውድነትንና የስራ እድል ፈጠራን ጨምሮ ሌሎች አንገብጋቢ የሆኑ ችግሮችን ከሕዝባችን ጋር በመሆን ለመፍታት የተጠናከረ ስራ  መስራታችንን ይቀጥላል።

በተጨማሪም በማእድን ፣ በኢንዱስትሪው፣ በማኒዩፋክቸሪንግ ዘርፍ ተጨማሪ እንቅስቃሴዎችን በማከናወን ጠንካራ የኢኮኖሚ ስርአት ለመገንባት ከመላው ህዝባችን እና ወዳጅ ሀገራት ጋር በትብብር የምንንቀሳቀስ ይሆናል።

እንደ ሀገርም የኢኮኖሚ እድገት ማነቆ ሊሆኑ የሚችሉ የፀጥታ መደፍረስ የሰላም ሁኔታ ላይ አሁን በጀመርነው ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እየፈታን በመሄድ ተጨማሪ ኢንቬስተሮች ወደ ሀገራችን በመሳብ መዋእለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በማድረግ እና ለዜጎቻችን የስራ እድል በመፍጠር ጠንካራ የኢኮኖሚ ስርአት የመገንባቱን ሂደት አጠናክረን እናስቀጥላለን።

#prosperity

Prosperity Party - ብልፅግና

06 Apr, 09:50


ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ትውልድ ተሻጋሪ የልማት ቱርፋት ነው።ይህ ትውልድ እድለኛ ነው እንዲህ ያለ ዘመን ተሻጋሪ አገራዊ ፕሮጀክት መገንባት በመቻሉ። ይህ ትውልድ እንደታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለ ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ፕሮጀክት ላይ አሻራውን ማሳረፍ የሚችልበት አጋጣሚ ስለተፈጠረለት ደስታው ልዩ ነው።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ ለአገራችን ዜጎች ብሔራዊ መግባባት በመጫር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትንና የትብብር መድረክ የፈጠረ ነው።የታላቁ ህዳሴ ግድብ መሠረት ከተጣለ ጀምሮ የተወሰኑ መሰናክሎች ቢኖሩም ከፍተኛ ዕድገት እያሳየ መጥቶ እነሆ ወደ መጠናቀቁ ደርሷል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት አምስት ዓመታት ከሰራቸው ውጤታማ ተግባራት አንዱ የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ አንድነታችንን ያረጋገጥንበት ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መካከል ያለው መልካም ግንኙነት እንዲዳብር እና የህዝቦችን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ለማሳየት እድል የፈጠረ ነው፡፡

#prosperity

Prosperity Party - ብልፅግና

04 Apr, 05:24


"ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ በተሰራው ስራ የተከፈለውን መስዕዋትነት ዓለም ሁሉ የሚያውቀው ነው፣ የኢትዮጵያ የመፍረስ ስጋት አልፏል። ኢትዮጵያን የሚያፀኑ የህግ አስፈፃሚ አካላት ያሉበት ቁመና እና የተቋቋሙበት መንገድ ለዚህ ዋቢ ናቸው።"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

Prosperity Party - ብልፅግና

03 Apr, 06:16


በመጋቢት 2010 የተጀመረው ለውጥ እነሆ ድፍን አምስተኛ አመቱን ይዟል።ባሳለፍናቸው 5 የለውጥ አመታት ነገሮች አልጋ በአልጋ አልነበሩም።ሀገራችንን በሁለንተናዊ አቅጣጫ የሚፈትኑ በርካታ አጋጣሚዎች መፍጠራቸው አይቀሬ ነበር።

የተፈጥሮ አደጋ፣ሰው ሰራሽ ግጭቶች፣የታጠቁ ሀይሎች የፈጠሩት ቀውስ፣የፅንፈኞች የክፋት በትር፣የኮቪድ ወረርሽኝ፣በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ጦርነት ለውጡን በከፍተኛ ሁኔታ የተፈታተኑ ክስተቶች ነበሩ።

እነዚህ ሁሉ እንቅፋቶች ጫናቸው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማሳሳት፣ማህበራዊ መስተጋብርን በመበጣጠስ የህዝባችን የአንድነት ስሜት በመሸርሸር፣የተቋማትን የማስፈፀም ብቃት በማቀጨጭ አሉታዊ ተፅእኖ ማሳደራቸው አልቀረም።

ሆኖም እንደብልፅግና ፓርቲ ጠንካራ ውሳኔዎችን በመወሰን መንግስታዊ የመሪነት ብቃታችንን በፈተናዎች ውስጥ አጠናክሮ በማስቀጠል ሊፈጠሩ የሚችሉ በርካታ ብሔራዊ አደጋዎችን መመከት እና አሉታዊ ተፅኗቸውን መከላከል ችለናል።

እንደ ሀገር የተጀመረው ለውጥ እንዳይደናቀፍ እና በህዝብ ዘንድ የጫረው የተስፋ ጭላንጭል እንዳይመክን በፈተናዎች ውስጥ እያለፍን ጠንካራ ተቋማትን ለመገንባት፣ኢኮኖሚያችንን ከውድቀት ለመታደግ፣የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ ለማስቀጠል፣ህብረ ብሔራዊ አንድነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት መላው ህዝባችንን በማስተባበር በርካታ ስኬቶችን አስመዝግበናል።

ጦርነት ሳይበግረን፣ኮቪድ ሳያስቆመን የተጋረጡበን የዲፕሎማሲ ጫናዎች አቅማችንን ሳያሰልሉት የሀገረ መንግስታችንን ህልውና ላለማስደፈር ያደረግናቸው በርካታ ጥረቶች ፍሬ ማፍራት ችለዋል።

በህዝባችን የለውጥ መሻት የተጀመረው ጉዞ ብልፅግና ፓርቲን ወልዶ፣የዴሞክራሲ ባህላችንን አሻሽሎ፣ኢትዮጵያን ከብተና ስጋት ታድጎ፣በግብርና፣በኢንዱስትሪው በቴክኖሎጂው ዘርፍ ሊታዩ የሚችሉ ተጨባጭ ውጤቶችን አስመዝግቦ እነሆ መገስገሱን ቀጥሏል።

ተስፋ፣አንድነት፣ወንድማማችነት፣ፍቅር፣መተሳሰብ፣ብልፅግና፣የለውጡ ቀደምት መገለጫዎች ሆነው እነሆ ጉዟችንን ከጀመርን ድፍን አምስት አመታት ተቆጥረዋል።

መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ🌻🌻🌻

Prosperity Party - ብልፅግና

02 Apr, 15:27


የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ትሩፋቶች በአዲስ አበባ ባለፉት 5 አመታት በጥራትም ይሁን በፍጥነት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በርካታ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል፡፡
እነዚህን ፕሮጀክቶች ይህን በመሰለ አጭር ጽሁፈ ዘርዝሮ መጨረስ የማይቻል ነው፡፡
ይህ ጽሁፍ በአዲስ አበባ ክተማ ከተሰሩ የልማት ስራዎቸ መካከል ጥቂቶቹን ለማስታወስ ይሞክራል፡፡

#የአንድነት ፓርክ

የአንድነት ፓርክ ግንባታ እ.ኤ.አ. በ2018 በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተጀመረ እና ጥቅምት 10/2011 በይፋ ተመርቆ ለህዝብ ክፍት ሆኗል።
የአንድነት ፓርክ በታላቁ ቤተ መንግስት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ ታሪካዊ፣ተፈጥሮአዊ እና ባህላዊ ቦታዎችን ያቀፈ ነው።የአንድነት ፓርክ የሚገኝበት ታላቁ ቤተ መንግስት በ1887 የተመሰረተ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሳይቆጠሩ ቤተ መንግሥቱ የሰባት ኢትዮጵያውያን መሪዎች የመኖሪያና የሥራ ቦታ ሆኖ አገልግሏል። ቤተ መንግሥቱ በ40 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን የነበሩ እልፍ አእላፍ ታሪካዊ ሕንፃዎችና እፅዋትን ይዟል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የአንድነት ፓርኪንግ ፕሮጀክት በ9,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ይገኛል።
ፕሮጀክቱ አምፊቲያትር፣ ባህላዊ ሬስቶራንቶች፣ ሱቆች እና ሌሎች መስህቦችን ያካተተ ነው።
የፓርኪንግ ህንጻው ለብሄራዊ ቤተ መንግስት፣ ለሳይንስ ሙዚየም፣ ለወዳጅነት ስኩዌር ምዕራፍ 2 እና እና ለሌሎችም የልማት መዳረሻዎች ከመስቀል አደባባይ እስከ አብርሆት ግራንድ ቤተመጻሕፍት የጎብኚዎች ቀለበት ማዕከል ሆኖ ያገለግላል።

#የወዳጅነት ፓርክ
የወዳጅነት ፓርክ የባህል ማዕከላትን፣ የስነ ጥበብ ጋለሪ እና የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቦታዎችን ያካተተ 58 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የእንጦት-አቃቂ ሪቨርሳይድ ውበት ፕሮጀክት አካል ነው።
የእግር ኳስ እና የቅርጫት ኳስ መጫወቻ ሜዳዎችን ጨምሮ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ የመዝናኛ መገልገያዎችን እና የመጫወቻ ሜዳዎችን ያካተተ ነው።

#የእንጦጦ ፓርክ
በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሃሳበ አመንጪነተ የተጀመረው የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት አካል የሆነው የእንጦጦ ፓርክ ግንባታ አንድ ዓመት ተኩል ገደማ የተጠናቀቀ ነው፡፡ የእንጦጦ ፓርክ፤ በ5 የግንባታ ሳይቶች ላይ በርካታ መዝናኛዎችን ያካተተ ነው፡፡
ከእንጦጦ እስከ አቃቂ የሚዘልቀው የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት አካል የሆነው የእንጦጦ ፓርክ ከ2 መቶ አመታት በላይ የቆዩ ታሪካዊ ቅርሶችን ያካተተ ከኢትዮጵያ ግዙፉ የአርት ጋለሪ የሚገኝበት ነው።

በ5 ሳይቶች ተከፋፍሎ የተገነባው የእንጦጦ ፓርክ፤ በውስጡ የፈረስ መጋለቢያ ሜዳ እስከነ ፈረሶች ጋጣው፣ ባህላዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችና በቀድሞ ነገስታት የግብር አዳራሽ አምሳል የተሰሩ ባህላዊ ምግብ ቤቶችን ጨምሮ ዘመናዊ ካፊቴሪያዎች እንዲሁም ለጥንዶችና በቡድን ለሚዝናኑ የተዘጋጁ መናፈሻዎች፣ የህዋ መመልከቻ ማማና፣ የብስክሌት መጓጓዣና ሌሎችንም ይዟል።

# የዓድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ፕሮጀክት
የዓድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ፕሮጀክት በአዲስ አበባ መሀል ፒያሳ ላይ እየተካሄደ ነው። የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ፕሮጀክት ኢትዮጵያውያን የአባቶቻቸውን ድል አክብረው ለትውልድ የሚተላለፉበት የጥንካሬ፣ የጀግንነት እና የነጻነት ማሳያ ነው።
ፕሮጀከቱ በ4.6 ቢሊዮን ብር ግንባታው እየተሳለጠ ነው፡፡

#የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት
ይህ ፕሮጀክት በመደበኛነት ከሚሰጠው አገልግሎቶች ጎን ለጎን በአሁኑ ጊዜ ከ 1380 በላይ መኪናዎችን በአንድ ጊዜ የማቆም አቅም አለው ። የከተማው ሜጋ ፕሮጀክቶች አስተዳደር ጽህፈት ቤት ፕሮጀክቱን በመግቢያው ላይ በተቀመጠው ጊዜ ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት በመንቀሳቀሱ በፍጥነት ተጠናቆ ለአገለግሎት ብቁ ለመሆን ችሏል፡፡ ኘሮጀክቱ ኃይማኖታዊ፣ መዝናኛና ሌሎች ህዝባዊ ዝግጅቶችን ለማክበር ማእከላዊ ቦታ ሆኖ ከማገልገል ተጨማሪ በከተማዋ የሚታየውን የመኪና ማቆሚያ ቦታ እጥረትን ለመፍታት ያስችላል። ፕሮጀከቱ በ2.5 ቢሊዮን ብር የተከናወነ ነው፡፡

#የህዝብ ቤተመፃህፍት ፕሮጀክት
በከተማ አስተዳደሩ እየተካሄዱ ካሉት ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የህዝብ ቤተመፃህፍት ፕሮጀክት በፍጥነት እየተካሄደ ያለው ሲሆን 1 ቢሊየን 115,977,250 በጀት ተይዞ እየተካሄደ ነው፡፡
ይህ ፕሮጀክት የከተማው ወጣቶች ቤተመፃህፍትን ከማግኘት ጋር የተያያዙ ችግሮችን እና በጤንነታቸው እና በአእምሯዊ ፋኩልቲ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያላቸውን ተግባራትን የሚቀርፍ ነው። በ1.8 ሄክታር መሬት ላይ የተዘረጋው ይህ ቤተመፃህፍት 35000 ተጠቃሚዎችን ለ113 አውቶሞቢሎች የመኪና ማቆሚያ ቦታ የሚያስተናግድ ሲሆን ዘመናዊ የአይሲቲ ፋሲሊቲዎችንም ያካተተ ነው።

#የሳይንስ ሙዚየም በአዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሳይንስ ሙዚየም 250 ካሬ ስፋት ያለው ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እድሳት ፕሮጀክት
የከተማ አስተዳደሩ በ57 አመት ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የማዘጋጃ ቤቱን ዋና መስሪያ ቤት ለማደስ በአጠቃላይ 2.2 ቢሊዮን ብር ፈሰስ አድርጓል።
የእድሳት ስራው የመሬት አቀማመጥ፣ ቢሮዎችን እና ባለ 850 መቀመጫዎች ያሉት የቲያትር አዳራሽ ማደስ እንዲሁም በማዘጋጃ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የልጆች መጫወቻ ስፍራን የመሳሰሉ አዳዲስ መገልገያዎችን በመገንባት 50,000Sqm አካባቢን ያካተተ ነው።

#በአዲስ አበባ የተጠናቀቁ የመንገድ ፕሮጀክቶች፡-
ከቁስቋም እስከ እንጦጦ - 4.3 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 16 ሜትር ስፋት፣ ከእግረኛ መንገድ ጋር
ሽሮ ሜዳ እስከ ቁስቋም - 2.6 ኪሜ ርዝመት እና 30 ሜትር ስፋት
ወሎ ሰፈር እስከ ዑራኤል - 1.4 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 35 ሜትር ስፋት
ላ ጋሬ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ አደባባይ - 1.56 ኪሜ ርዝመት እና 13 ሜትር ስፋት
ከገርጂ ሮባ እስከ መብራት ሃይል - 973ሜ ርዝመትና 30ሜ
ከወይራ እስከ ቤቴል - 1.4 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 20 ሜትር ስፋት
ሲኤምሲ ሚካኤል በላይ ማለፍ - 680ሜ ርዝመት እና 30ሜ
ራስ ደስታ እስከ ቀጨኔ - 2.5 ኪሜ ርዝመት እና 20 ሜትር ስፋት
ኃይሌ ጋርመንት እስከ ጀሞ - 4.5 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 120 ሜትር ስፋት ያለው የብስክሌት ትራክ፣ የእግረኛ መንገድ፣ አረንጓዴ ቦታ እና የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ያለው

#prosperity

5,628

subscribers

775

photos

14

videos