Ethio Book Review @etbookreview Channel on Telegram

Ethio Book Review

@etbookreview


The largest Ethiopian Digital Book Platform. Visit https://ethiobookreview.com

Ethio Book Review (English)

Welcome to Ethio Book Review, the largest Ethiopian Digital Book Platform that is dedicated to promoting Ethiopian literature and authors. Our Telegram channel, @etbookreview, is the go-to destination for book lovers who are looking to discover new Ethiopian books, connect with like-minded individuals, and engage in meaningful discussions about literature. Who is Ethio Book Review? We are a team of passionate readers and advocates for Ethiopian literature. Our goal is to create a thriving community that celebrates the rich literary heritage of Ethiopia and supports local authors by providing them with a platform to showcase their work. What is Ethio Book Review? We are more than just a digital book platform - we are a hub for all things Ethiopian literature. On our channel, you will find book reviews, author interviews, reading recommendations, literary events, and much more. Whether you are an avid reader looking for your next favorite book or an aspiring writer seeking inspiration, Ethio Book Review has something for everyone. Join us on our journey to promote Ethiopian literature and culture. Visit our website at https://ethiobookreview.com to explore our collection of digital books and stay updated on the latest literary news and events. Don't miss out on the opportunity to immerse yourself in the vibrant world of Ethiopian literature - join Ethio Book Review today!

Ethio Book Review

21 Nov, 02:20


ትችሉ ነበር አሁንም ትችላላችሁ!

አንዳንድ ሰዎች የእሳቤ ሂደት ይህንን ይመስላል፡-

“እንደምችል አውቀዋለሁ” በሚል ጠንካራ እሳቤ ይጀምራሉ፡፡

ትንሽ ተራምደው ያልጠበቁት ሁኔታ ሲገጥማቸው ቀስ በቀስ፣ “የምችል ይመስለኛል” ወደሚለው የጥርጣሬ ዘር ወዳለበት እሳቤ ወረድ ይላሉ፡፡

ብዙም ሳይቆዩ፣ “የምችል ይመስለኝ ነበር” ወደሚለው ደከም ወዳለ እሳቤ ይንሸራተታሉ፡፡

በመጨረሻ “አልችል” በማለት ጭራሹኑ ያቆሙታል፡፡

አንባቢዎቼ!!! ይህ ለብዙዎች ውድቀት ምክንያት የሆነ የእሳቤ ሂደት ለእናንተ አልተፈቀደላችሁም፡፡

እንደምንችል እናውቀው ነበር! እንችል ነበር! አሁንም እንችላለን!
በርቱና . . .

1. አንድን ነገር ከመጀመራችሁ በፊት ደካማ ጎናችሁ ላይ ሳይሆን ዝንባሌያችሁና ብርቱ ጎናችሁ ላይ አተኩሩ፡፡

2. የምትጀምሩት ነገር ውጤታማ የሚያደርጋችሁ እስከሆነ ድረስ እንቅፋት እንደሚያጋጥማችሁ አትዘንጉ፡፡

3. ካለማቋረጥ ራሳችሁን አሻሽሉ፡፡

4. ስትወድቁም ሆነ ስትሳሳቱ ከልምምዱ የምታገኙትን ትምህርታችሁን ያዙና ወደፊት ቀጥሉ፡፡

5. በፍጹም ተስፋ አትቁረጡ፡፡

Source: Dreyob

Ethio Book Review

10 Nov, 10:34


አዲስ መንፈሳዊ መጽሐፍ በ ዲያቆን Henok Haile

የኤፌሶን ወንዝ ቅዳሜ ለሁሉም መጽሐፍ መደብሮች ትሰራጫለች።
👉🏻 የገፅ ብዛት 268
👉🏻 የሽፋን ዋጋ 400ብር
👉🏻 21 ስብከቶችና ዘለግ ያሉ ጥናታዊ ጽሑፎች
ሙሉ ገቢው ለግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን ሕንፃ ቤተ መቅደስ እድሳት የሚውል።

https://www.ethiobookreview.com/book/ye-epheson-wenz-diakon-henock-haile

Ethio Book Review

09 Nov, 16:00


Kitaabni "ABUURRAA ADDUNYAA" jettu Hirkoo Yooseef Tarrafaatiin kan barrooftee dha. Mata dureewwan garaa garaa kan of keessatti qabattu yoo taatu xurree milkaa'inaa kan namatti agarsiiftuu fi "Hayyoonni maal jedhan?" Jechuudhaan dhaamsa isaanii nu yaadachiifti. Barreessichi yaada ofii isaa fi beektota addunyaa bifa walaloo fi jechoota nama onnachiisaniin kan guutteen addunyaa nama abuursifti.

Argachuuf geessituu kana fayyadamaa:
https://www.ethiobookreview.com/book/abuurraa-addunyaa-hirko-yoseph

Ethio Book Review

08 Nov, 02:19


እንደምንም ብላችሁ ጀምሩት!

አንድን ማድረግ ያለባችሁ ነገር ትክክለኛ ነገር መሆኑን እና ወቅቱ እንደሆነ እርግጠኛ ከሆናችሁ . . .

• ሰዎች ሁሉ እስከሚደግፏችሁና በርቱ እስከሚሏችሁ ድረስ አትጠብቁ! ብቻችሁንም ቢሆን ጀምሩት!

• የፍርሃት ስሜት ሙሉ ለሙሉ ከእናንተ እስከሚወገድ ድረስ አትጠብቁ! እየሰጋችሁም ቢሆን ጀምሩት!

• ሁሉም ነገር እስከሚሟላላችሁ ድረስ አትጠብቁ! የአቅርቦት እጥረት እያላችሁም ቢሆን ጀምሩት!

• ሙዳችሁ ጥሩ እስከሚሆን አትጠብቁ! የስሜት ውጣውረድ እያለባችሁም ቢሆን ጀምሩት!

ያልተጀመረ ነገር አይቀጥልምና ጀምሩት!

ያልተሞከረ ነገር ይሳካና አይሳካ አይታወቅምና ሞክሩት!

ያልተንቀሳቀሰ ነገር እንደቆመ ይቀራልና አንቀሳቅሱት!

Source: Dr Eyob

Ethio Book Review

04 Nov, 06:56


#Ethiopia አዲስ ልብወለድ e-መጽሐፍ ከ የአብፀጋ አምባው በ 56ብር / 5$ ብቻ እነሆ ተብላችኋል።

በአሸዋው ላይ እየተራመደ የሚመጣ የብዙ ሰው የጫማ ኮቴ መሰማት ጀመረ። ሁሉም በፍርሃትና በጉጉት ድምፁን ወደሰማበት አቅጣጫ እያሰገገ ተመለከተ።
የአስኪድ ጦር ከጨለማው አቅጣጫ ብቅ አለ ። የጄሊ ፊሽ ምስል ያለበት ሰማያዊ ባንዲራ ይዘው የጦር መሳሪያቸውን እንደታጠቁ በተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ሲያልፉ ሕዝቡ በአክብሮት እጅ ነሳ።

የአስኪድ ጦር አባላት ቁጥራቸው ከ 20 አይበልጥም። ሁሉም ሴቶች ሲሆኑ በኩራት ነበር በሕዝቡ ፊት የሚራመዱት። እነዚህ የተመረጡ ጦረኞች ናቸው። ሐገር ከመጠበቅ ውጪ ሌላ ስራ የላቸውም። ከነሱ ውጪ ያሉት ሴቶች ግን ጦረኛም አራሽ ገበሬም ሆነው ነው የሚያገለግሉት። በዕድሜ ገፋ ያሉት ሴቶች ደግሞ የንግስቷን ልጆች በሞግዚትነት ያሳድጋሉ።

የአስኪድ ጦር መንደሯን አልፎ ከመሄዱ በፊት አንዲት ልጅ ድምፅዋን ዝግ አድርጋ ብሔራዊ መዝሙራቸውን መዘመር ጀመረች። እሷን ተከትሎ ቀስ በቀስ ሁሉም መዘሙር ጀመረ።

ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ፡ https://www.ethiobookreview.com/book/sabawuyan-yeabtsega-ambaw

Ethio Book Review

01 Oct, 04:15


ኤክሴ ናት ከተለያየን ነፍፍፍፍፍ....ፍፍፍ ግዜ ሆኖናል። ከነፍፍ ጊዜ በኋላ ተደዋውለን ሻይ እየጠጣን ነው። በዝብዘባችን መሃል ለምን ያኔ ተውሺኝ አልኳት

"honestly speaking  ያኔ መተው ነበረብኝ" ብላ ፀዴ ፈገግታ ፈገግ አለች ።

"ይብራራ"- አልኮት
ጥቂት ፈገግታ እና ብዙ  ጭፍግግታ በተላበሰ ፊቴ ።

"ጭንቅሌህ ሃሳብ አልባ ነበር። የማይጥምህን ሃሳብ ነፍስህ ተረጋግታ አትሰማም ።አንተ ያልፈለከው ካልሆነ ነፍስህ ትቅበዘበዛለች😢ሁሌ ከአንተ የፈለቀ ሃሳብ ትክክለኛ እና አዳኝ ይመስልሃል። soft dictator ነህ። አምባገነንነትህ እንደእኔ አራዳ ያልሆነ ካልሆነ አይባንነውም።ነፍስህ ሊብራል አይደለችም።

ፍቅርህ እጅ መንሻህ ነበር ።
መከራከርያ፤መደራደርያህ፤ማፅናኛህ ፤መፅናኛህ  ፍቅር ነበር ። ፍቅር ከእውነት የሚበልጥ ይመስልካል። ቅናትክ ፈጣጣ ነበር ። ስሜትህን አሁንም አሁንም ታንፀባርቃለህ።

emotional intelligence ይጎልሃል ።
የሆነው ሆኖ አሁን ቢሆን ኖሮ አልተውክም ነበር። ያኔ ሙሉ ሰው ፍለጋ ላይ ነበርኩ።
ሙሉ የሚባል  concept አለመኖሩን ለመረዳት ብዙ ነፍስ ጋር ተዋሃድኩ ይሁን እንጂ ጉድለት መልክ እና ይዘቱን እየቀያየረ ሁሉም ጋር እንዳለ ተከሰተልኝ።

ጉድለት ይዞ ምሉዕ ፍለጋ መባተል ያለመብሰል ምልክት ነበር።
አለመብሰል ነበር ያዳከረኝ 🚶‍♀🚶‍♀🚶‍♀
ትላንት  ካንተ ጋር ለመሆን ፍላጎት  አልነበረኝም ፤ ዛሬ ደሞ እድሉ የለኝም ።
ጭንቅላቷ ሰላብኝ። ከነፍስ ነፍስ መባተሏ እንዳበሰላት ገባኝ ። 

ማሳሰብያ፦
የመለያየት ምክንያት ፍፁም ነፍስ ፍለጋ መባተል ነው፦
አለመብሰል በረከታችንን ያሳጣናል


Source: noahbookdelivery

Ethio Book Review

18 Sep, 04:06


“እሺ” እና “እምቢ”

ሕይወት ተፈጥሯዊ ሂደቷን እንድትቀጥልና ሁኔታዎች በራሳቸው መስመር እየያዙ እንዲሄዱ መለማመድ የምንችላቸው ሁለት ልምምዶች አሉ፡፡ እነዚህ ልምምዶች ከለመድናቸው እጅግ ቀላል የሆኑ፣ ካላወቅንበት ግን የሚከብዱ ልምምዶች ናቸው፡፡

1. ለተገቢው ነገር “እሺ” ማለት፡- በሕይወታችን መልካም ነገሮች እንዲገቡ በሩን የሚከፍተው ቁልፍ!

በሚገባና በተረጋጋ መንፈስ አስባችሁበት ትክክለኛ እንደሆነ ላመናችሁበት ነገር “እሺ” ማለት ሌሎች መልካም ነገሮች እየተወለዱ የሚሄዱበትን መስመር ይከፍትላችኋል፡፡

2. ተገቢ ላልሆነ ነገር “እምቢ” ማለት፡- በሕይወታችን ጤና-ቢስ ነገሮች እንዳይገቡ በሩን የሚዘጋው ቁልፍ!

በሚገባና በተረጋጋ መንፈስ አስባችሁበት ትክክለኛ እንዳልሆነ ላመናችሁት ነገር “እምቢ” ማለት ደግሞ በሕይወታችሁ መልካም ያልሆኑ ነገሮች እየተበራከቱ እንዳይሄዱ መንገዱን ይዘጋዋል፡፡

እነዚህ ሁለት ልምምዶች ፍርሃትን አልፎ መሄድን ይጠይቃሉ፡፡

በአንድ ጎኑ፣ “እሺ” ለምንለው ነገር ብቁ ባንሆንስ፣ ባይሳካስ፣ በኋላ ብጸጸትስ . . . እና የመሳሰሉትን ፍርሃቶች ማስወገድን ይጠይቃል፡፡

በሌላ ጎኑ ደግሞ “እምቢ” በማለታችን ምክንያት ችግር ቢደርስብንስ፣ እድል ቢያመልጠንስ፣ ሰዎች ቢቀየሙንስ . . . እና የመሳሰሉትን ፍርሃቶች ማስወገድን ይጠይቃል፡፡

Source: Dr Eyob Mamo

Ethio Book Review

17 Sep, 06:42


ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ። ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ከልብ አዝኛለሁ። ያቆዩት ውርስ እና ቅርስ ፀንቶ እንዲቀጥል ነፍሳቸውም በሰላም እንድታርፍ እመኛለሁ።

Professor Beyene Petros embodied the spirit of peaceful political struggle, playing a pivotal role in fostering a culture of non-violence and constructive political dialogue in Ethiopia. I am deeply saddened to hear of his passing after a prolonged period of medical care. May his legacy endure, and may he rest in eternal peace.

Ethio Book Review

15 Sep, 11:31


እንዴት አገኛችሁት?

Ethio Book Review

15 Sep, 10:03


በዚህ ዓመት . . .

ራሳችሁን ያላዘጋጃችሁለትን ነገር ለምናችሁ ለጊዜው እጃችሁ ከምታስገቡ ይልቅ፣ ራሳችሁን በማሳደጋችሁና በማሻሻላችሁ ምክንያት ነገሩ ወደ እናንተ ቢመጣና እስከወዲያኛው ቢቆይ ይሻላችኋል፡፡

Ethio Book Review

13 Sep, 13:08


Cowards experience death multiple times before their final demise.
'
ለተጨማሪ ጠቃሚ አባባሎችና ምክሮች፡ https://www.ethiobookreview.com/amharic-quotes

Ethio Book Review

11 Sep, 04:57


Happy Ethiopian New Year 2017

እንኳን ለ2017 አዲሱ አመት አደረሳችሁ

Baga bara haaraan isin gahe

Ethio Book Review

10 Sep, 09:50


እንኳን ለ 2017 ዓ.ም አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ!

ዘመኑ የሰለም፣ የፍቅር፣ የስኬት እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!

መልካም በዓል!

www.ethiobookreview.com

Ethio Book Review

06 Sep, 13:34


በቃ ተወው!

Ethio Book Review

06 Sep, 09:21


For you

Ethio Book Review

04 Sep, 07:28


አንዳንዴ ህይወት በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ትሞላለች፣ ግን ደግሞ አንዳንዴ ቀለል ያሉ ጥቅሶችና ንግግሮች አስተሳሰባችንን ለውጠው ቀናችንን ብሩህ ልያደርግልን ይችልላሉ።
እርስዎስ ምን ሀሳብ አለዎት?

https://www.ethiobookreview.com/amharic-quotes

Ethio Book Review

04 Sep, 04:00


ይሞክሩት

Ethio Book Review

03 Sep, 17:13


ይህንን አባባል እንዴት ያዪታል?

Ethio Book Review

02 Sep, 12:55


የንባብ ጥቅም

1. ከቀደሙት ዘመናት ጋር ያገናኛል፡፡የቀደሙት የተጻፉጽሑፎች በዚያ ዘመን ስለነበሩ ታሪክና ሥራ በግልጽ እንድናውቅ ያደርጉናል፡፡

2. ጥሩ እውቀት እንዲኖረን ያደርጉናል፡፡
3. አንድ ወጥ ቋንቋና ዕውቀትን ያስጨብጣል፡፡የቀደሙጸሐፊዎችን አባባል እንድንጠቀምበት ይረዳናል፡፡
4. ሰው የሦስት ዘመን ውክልና ያለው በመሆኑ ያለፉትንና የወደፊቱን እንዲኖር ያደርጉታል፡፡

አንብቡ ለማለት ያክል ነው!
www.ethiobookreview.com