የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት ማካሄዱ ይፋ ተደርጓል።
ጉባኤው ኢንጅነር ሀይለእየሱስ ፍስሀን የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንትነት አድርጎ መሾሙን አስታውቋል።
በተጨማሪም አርቲስት ማስተዋል ወንደሰን ም/ፕሬዘዳትነት እንዲሁም አርቲስት ሀረገወይን አሰፋን አቃቤ ነዋይ ሆነው ተመርጠዋል።
ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት አመታት በስራ አስፈፃሚነት የሚመሩ ፕሬዘዳንቱን ጨምሮ 9 ስራ አስፈፃሚዎች በጉባኤተኛው መመረጣቸው ተገልጿል።
ምንጭ - የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
https://t.me/TV_VARISH
https://t.me/TV_VARISH