ጤና ሚኒስትር ኢትዮጵያ @minister_of_health_ethiopia Channel on Telegram

ጤና ሚኒስትር ኢትዮጵያ

@minister_of_health_ethiopia


ጤና ሚኒስትር ኢትዮጵያ (Amharic)

ጤና ሚኒስትር ኢትዮጵያ ለማንኛውም ሰው የምርጫ መነሻ እና የተዛረበት ችሎታ እንዲሆን፣ ሴራችኬባል ወይም የኮራና ሸኮሞች አገናኝ ሆነው የሚከተለውን የጤና እና ጥናት መረጃውን እንዲሰራ እና ወደ ዝናሪን እንዲሄድ የምርጫ እንዲሆን በፕሮፌሰክ በመተግበል የሚወስዳቸውን መረጃዎች ከፊል ተከታታይ በመቀበራት ነው። ከዚህም በመላክ እና በመረጃ ቦርድ ውስጥ ከባቢሎን ለእርምጃው የጻፍርና ምግብናዎችን ለማድረግ የሆነውን የምርጫ መረጃዎችን በጥረት ለማያዳር እና ለማከበርና በመረጃዎች ምንዛሬ የሆነውን የሕይወታ እና የመደራ መንገድ ያደርጋል።

ጤና ሚኒስትር ኢትዮጵያ

25 Oct, 20:43


የወባ በሽታ
#malariaprevention
#malariaawareness
https://t.me/MINISTER_OF_HEALTH_ETHIOPIA

ጤና ሚኒስትር ኢትዮጵያ

24 Oct, 20:56


ንፁህ እጆች ለጤናችን ዋስትና ናቸው!
#safehands
https://t.me/MINISTER_OF_HEALTH_ETHIOPIA

ጤና ሚኒስትር ኢትዮጵያ

21 Oct, 20:20


የጤና ሚኒስቴር ወርሃዊ የመንገድ ላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ-ግብር ተካሄደ።
#HealthyLiving

ጤና ሚኒስትር ኢትዮጵያ

20 Oct, 17:53


በትግራይ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወባ በሽታን የመከላከል ተግባር በቅንጅት እየተከናወነ ነዉ።
https://t.me/MINISTER_OF_HEALTH_ETHIOPIA

ጤና ሚኒስትር ኢትዮጵያ

19 Oct, 20:39


በጎፋ ዞን መሬት መንሸራተት ድንገተኛ አደጋ ለተጋለጠ ህብረተሰብ 3.1 ሚልዮን ዶለር የህክምና ቁሰቁስ ድጋፍ ካደረገው በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር ለድንገተኛ አደገ ተገለጭ ህብራተሰብ እና የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት የህክምና ቁሳቁስ እና የመድሃኒት አቅርቦትን ለማሻሻል የሚያስችል ውይይት ተካሄደ
__

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በጎፋ ዞን በማሬት መንሸራታት አደጋ ጎዳት ለደረሰባቸው ህብረተሰብ ክፍሎች ጤና አገልግት የሚውል የ3.1 ሚልዮን ዶለር የህክምና ቁሰቁስና መድሀኒት ከለገሰውና መቀመጨውን አሜርካን አገር ከሆነው በጎአድራጎት ድርጅት ዳይሬክት ሪሊፍ፣ የአፍሪካ ሪጅናል ዳይሬክተር ጄፍሪ ሳሙኤል ጋር ባደረጉት ውይይት በጎፋ ዞንና ተመሳሳይ የድንገተኛ አደጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የህክምና ቁሳቁስ እና መድሃኒት አቅርቦትን በማሻሻል የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ማሻሻል ዙሪያ መክረዋል፡፡

ዳይረክት ሪሊፍ እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ ኢትዮጵያ በመድሃኒት አቅርቦት የሃገር ውስጥ ፍላጎትን ከሟሟላት ባለፈ ለሌሎችየአፍሪካ ሃገራትም የሚተርፍ አቅምን ለመገንባት እየሰራች መሆኑን በመግለጽ በዘርፉ ከዳይሬክት ሪሊፍ ጋር በቅርበት ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር መቅደስ በውይይት መድረኩ ጤና ሚኒስቴር የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎትን ይበልጥ ማጠናከር በሚችልበት መንገድ እና ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ቁጥጥር፣ እንዲሁም በድንገኛ አደጋ ለሚከሰቱ ችግሮች ምላሽ አሰጣጥ ፈጣን እንዲሆን ማስቻል እና ማጠናከር ላይ መክረዋል፡፡ በተጨማሪም በሃገር ውስጥ በቀላሉ ማግኘት የማይቻሉ ወሳኝ መድሃኒቶች አቅርቦትን ለማሻሻል ከድርጅቱ ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በግጭት እና ሌሎች ምክንያቶች የተጎዱ ተቋማትን ለማቋቋምና በተሻለ ለመገንባት ያላትን ቁርጠኝነት የገለጹት በጤና ሚኒስቴር የማህበረሰብ ተሳትፎ እና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ እስራኤል አታሮ፤ በገጠር የሚገኝ የማህበረሰብ ክፍልን በተሻለ ተደረሽ የሚያደርገውን የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ለማሻሻል ቴክኖሎጂን እና ፈጠራን (ኢኖቬሽን) መጠቀም አስፈላጊነትን አብራርተዋል፡፡

በአገራችን 80 በመቶ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል መሰራተዊ የጤና አገልግሎት የሚየገኙት በመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎት መሆኑን በመግለጽ በድንገኛ አደጋ ለሚከሰቱ የጤና ችግረም አፋጣኝ ምለሽ መስጠትም ሆነ የህብረተሰቡን ጤና ተደረሽ መድረግ የሚቻለው መሰራተዊ የጤና አገልግሎትን ማጠናከር ሲቻል መሆኑን በመጥቀስ እርደታ ሰጭ ድርጅቱ በዚህ ዙሪያ ለይ ድግፍ እንደሚያደርግ የጠቆሙት ደግሞ በጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ሻሎ ዳባ ሲሆኑ፤ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ መክረዋል፡፡

ዳይሬክት ሪሊፍ በኢትዮጵያ ላለፉት 17 አመታት ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የገለጹት የዳይሬክት ሪሊፍ፣ የአፍሪካ ሪጅናል ዳይሬክተር ጄፍሪ ሳሙኤል፤ እስከአሁን ከለገሰዉ 3.1 ሚልዮን ዶለር የህክሚና ቁሰቁስ በተጨማሪ ወደፊት ይበልጥ ለመደገፍ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ ድርጅታቸው ድንገተኛ አደጋ ምላሽ፣ በሽታ መከላከል፣ መቆጣጠር እና ህክምና፣ የማህበረሰብ ጤና፣ እና የጤና ስርአትን ማጠናከር ላይ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር መስራታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

Website: moh.gov.et
Telgram https://t.me/MINISTER_OF_HEALTH_ETHIOPIA
Twitter: x.com/fmohealth
Tiktok: moh ethiopia

ጤና ሚኒስትር ኢትዮጵያ

18 Oct, 20:32


ወቅታዊ ጉንፋን እና ጉንፋን መሰል የመተፈንሻ አካላት ህመም በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ
___

የጉንፋን ሕመም በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጎሮሮን እና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ።

ሪኖ ቫይረስ ለጉንፉን መከሰት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ኮሮና፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ደግሞ ለጉንፉን መሰል ህመሞች መከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸዉ። ከተጠቀሱት ቫይረሶችም ለጉንፋን ሕመም መከሰት 50 በመቶ ድርሻውን የሚይዘው ሪኖ ቫይረስ ነው፡፡ በደረቅ ነፋሳማ ወቅት የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን “ሙከስ መምብሬን” ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡ የክረምት ወራት ወይም የዝናብ ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ መስከረምን ጨምሮ በጥቅምትና ህዳር ወራት እንደዚህ አይነት ጉንፋን መሰል ህመም የሚጠበቅ ነው፡፡

ሕመሙ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈውም በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ እንደሆነና በተጨማሪም ሰዎች ቫይረሱ ያረፈበትን የበር እጀታ፣ ጠረጴዛ ወይም በሕመምተኛው የተነካካንን ሰው እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ ለመተላለፍ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ነው።

የጉንፋን ሕመም የመጀመሪያ ምልክቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት ተላላፊ ሊሆን ይችላል፤ ሕመሙ ከጀመረ ከ 5 እስከ 10 ባሉት ቀናት ደግሞ ሕመምተኛው ቫይረሱን ያስተላልፋል። ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ እስከ 2 ሳምንት ሊቆይ ይችላል። ምልክቶቹም እንደ የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታትና ጉሮሮን መከርከር፣ ማስነጠስ፣ አይን ማሳከክ እና መቅላት፣ ማስታወክ፣ ከፍ ሲልም የትንፋሽ ማጠር፣ ከፍተኛ ድካምና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።

በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከ2003 ዓ ም ጀምሮ የእንፍሉዌንዛ እና መሰል የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ቅኝትና ምላሽ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች እየተሰራ ይገኛል። ከመስከረም ወር ጀምሮ መሰል ህመም ተሰምቷቸው ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ናሙና ከሰጡት ታካሚዎች ውስጥ አር ኤስ ቪ የተገኘባቸዉ ቁጥር የመጨመር ሁኔታ ያሳያል፡፡ በዚሁ ወቅት የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም (አር ኤስ ቪ) በተለይ በህጻናት ላይ በብዛት የተከሰተ ሲሆን ለዚህም ወቅቱ ትምህርት ቤት የተከፈተበት በመሆኑ ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ባለፈዉ 1 ወር ዉስጥ ተመርምረዉ አር ኤስ ቪ ከተገኘባቸዉ ታካሚዎች መካከል 84% ያክሉ እድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች ነዉ። እንደዚሁም ባለፈዉ ሳምንት ለአር ኤስ ቪ ከተመረመሩት 81 ናሙናዎች 49 (60.5%) ያህሉ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ በሽታው የመዛመት እድሉ ከፍ ሊል እንደሚችል፤ በተለይ ቀዳሚ ተጎጅ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ ህጻናትና አረጋውያን ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያሉባቸው ሕሙማን ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው እና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራና ህክምና ሊያደርጉ ይገባል፡፡ በተጨማሪም የጉንፋን ሕመም የጆሮ ኢንፌክሽን እና የሳንባ ምች ሕመምን ጨምሮ ለተለያዩ ሕመሞች ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ጉንፋን መሰል በሽታን ከምንከላከልባቸው መንገዶች መካከልም የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፣ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) በማድረግና በዕለት ኑሯችን የምንጠቀምባቸውን በከባቢዎቻችን የሚገኙ ቁሳቁሶችን ማጽዳት እና የብዙሃን ማጓጓዣ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታዉን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድና ጠንከር ያለ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምክር አና ዕርዳታ ማግኘት አለበት፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በ952 እና 8335 ነጻ የስልክ መስመር መደወል የሚቻል መሆኑን እያስታወስን ሕብረተሰቡ ሊከተላቸው የሚያስፈልጉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን አስመልክቶ ዝርዝር መግለጫ እና መረጃዎችን በየጊዜው የምንሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።

ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት
Telgram :https://t.me/MINISTER_OF_HEALTH_ETHIOPIA
Website: moh.gov.et
Twitter: x.com/fmohealth

ጤና ሚኒስትር ኢትዮጵያ

18 Oct, 20:27


በአራት ክልሎች ብቻ እየተሰጠ የሚገኘውን የፊስቱላ ህክምናን በማስፋፋት የአገልግሎቱን ተደራሽ ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ።

https://t.me/MINISTER_OF_HEALTH_ETHIOPIA

ጤና ሚኒስትር ኢትዮጵያ

17 Oct, 19:00


#ትኩረት🚨

ከሰሞኑን በርካታ ሰዎች በተለይ ትንንሽ ህጻናት በጉንፋን እና በጉንፋን መሰል የመተንፈሻ አካላት ህመም እየተያዙ ይገኛሉ።

ይህንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመክቶ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ያጋራ መግለጫ ልከዋል።

ምን አሉ ?

➡️ የጉንፋን ሕመም በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጎሮሮን እና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ።

➡️ ሪኖ ቫይረስ ለጉንፉን መከሰት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ኮሮና፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ደግሞ ለጉንፉን መሰል ህመሞች መከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸዉ። ከተጠቀሱት ቫይረሶችም ለጉንፋን ሕመም መከሰት 50 በመቶ ድርሻውን የሚይዘው ሪኖ ቫይረስ ነው፡፡ በደረቅ ነፋሳማ ወቅት የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን “ ሙከስ መምብሬን ” ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡

➡️ የክረምት ወራት ወይም የዝናብ ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ መስከረምን ጨምሮ በጥቅምትና ህዳር ወራት እንደዚህ አይነት ጉንፋን መሰል ህመም የሚጠበቅ ነው፡፡

➡️ ሕመሙ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ እንደሆነና በተጨማሪም ሰዎች ቫይረሱ ያረፈበትን የበር እጀታ፣ ጠረጴዛ ወይም በሕመምተኛው የተነካካንን ሰው እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ ለመተላለፍ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ነው።

➡️ የጉንፋን ሕመም የመጀመሪያ ምልክቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት ተላላፊ ሊሆን ይችላል፤ ሕመሙ ከጀመረ ከ 5 እስከ 10 ባሉት ቀናት ደግሞ ሕመምተኛው ቫይረሱን ያስተላልፋል።

➡️ ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ እስከ 2 ሳምንት ሊቆይ ይችላል። ምልክቶቹም እንደ ፦
° የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣
° ሳል፣
° ትኩሳት፣
° ራስ ምታትና ጉሮሮን መከርከር፣
° ማስነጠስ፣
° አይን ማሳከክ እና መቅላት፣
° ማስታወክ፣
° ከፍ ሲልም የትንፋሽ ማጠር፣
° ከፍተኛ ድካምና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።

➡️ ከመስከረም ወር ጀምሮ መሰል ህመም ተሰምቷቸው ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ናሙና ከሰጡት ታካሚዎች ውስጥ አር ኤስ ቪ የተገኘባቸዉ ቁጥር የመጨመር ሁኔታ ያሳያል፡፡ በዚሁ ወቅት የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም (አር ኤስ ቪ) በተለይ በህጻናት ላይ በብዛት የተከሰተ ሲሆን ለዚህም ወቅቱ ትምህርት ቤት የተከፈተበት በመሆኑ ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

➡️ ባለፈዉ 1 ወር ዉስጥ ተመርምረዉ አር ኤስ ቪ ከተገኘባቸዉ ታካሚዎች መካከል 84% ያክሉ እድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች ነዉ። እንደዚሁም ባለፈዉ ሳምንት ለአር ኤስ ቪ ከተመረመሩት 81 ናሙናዎች 49 (60.5%) ያህሉ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

➡️ አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ በሽታው የመዛመት እድሉ ከፍ ሊል እንደሚችል፤ በተለይ ቀዳሚ ተጎጅ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ ህጻናትና አረጋውያን ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያሉባቸው ሕሙማን ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው እና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራና ህክምና ሊያደርጉ ይገባል።

➡️ የጉንፋን ሕመም የጆሮ ኢንፌክሽን እና የሳንባ ምች ሕመምን ጨምሮ ለተለያዩ ሕመሞች ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ጉንፋን መሰል በሽታን የምንከላከልባቸው መንገዶች ምንድናቸው ?
° የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፣
° ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) ማድረግ
° በዕለት ኑሯችን የምንጠቀምባቸውን በከባቢዎቻችን የሚገኙ ቁሳቁሶችን ማጽዳት
° የብዙሃን ማጓጓዣ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታዉን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡


#ማሳሰቢያ ፦ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድና ጠንከር ያለ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምክር አና ዕርዳታ ማግኘት አለበት፡፡

#MoH #EPHI

@tikvahethiopia

ጤና ሚኒስትር ኢትዮጵያ

13 Sep, 20:45


የጤና ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ከብሄራዊ መታወቂያ አገልገግሎት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

https://t.me/MINISTER_OF_HEALTH_ETHIOPIA

6,993

subscribers

390

photos

4

videos