ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 @ethiobestzena Channel on Telegram

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

@ethiobestzena


🇪🇹🇪🇹🇪🇹ስለ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀን በቀን የሚወጡ ዜናዎችን እና እንዲሁም አለም አቀፍ መረጃዎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን 🙏ሰላምና ፍቅር ለእናት ሀገራችን ይሁን

👉 ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ @Gebrel or @Wizbeki7 ያናግሩን።

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 (Amharic)

ይህን ዓላማ በተለያዩ ዜና ቦታዎች እና ሁኔታዎች በኢትዮጵያ ቀናት በቀናት የተወጡት መረጃዎችን እና እንዲሁም አለም አቀፍ መረጃዎችን እንዲያናግሩ እርዳለን። ኢትዮ ቤስት ዜና የእናት ሀገራችንን በሰላምና ፍቅር ያስተማሩ የሚያስፈልጋቸው ቦታዎችን ለመስራት እና ለመከታት ይበልጥ ነው። እናት ሀገራችንን የሚገልጽውን መረጃዎችን ከ @Gebrel ወይም @Wizbeki7 በመጫን ካፈቀረው እምበር በቀጣይ እና በእርምጃ ይመልሳል።

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Nov, 11:12


ዛሬ ጠዋት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ተቃውሞ መነሳቱ ተሰማ።

ተማሪዎቹ ይህንን የተቃውሞው ድምፅ ያሰሙት በህዝባችን ላይ ግድያ ይቁም በሚል ምክንያት ሲሆን ተማሪዎቹ ቁርሳቸውን ሳይበሉ ነው ወደ ተቃውሞ እንደወጡ ለማወቅ የተቻለው።

ተቃውሞው እንዳይባባስ የፀጥታ ሀይሎች ጥረት አድርገዋል።

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Nov, 09:14


በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ ተጀመረ‼️

የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም ዛሬ በይፋ በተጀመረው ስራ፣ በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ተሃድሶ ማዕከላት ማስገባት መጀመሩን የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ተሀድሶ ማዕከላት ለመግባት በእጃቸው ያለውን ቀላል ትጥቅ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።

በዚሁ መሰረት የመጀመሪያው ዙር የነፍስ ወከፍ እና የቡድን ጦር መሳሪያዎች ርክክብም የአፍሪካ ህብረት፣የመንግስታቱ ድርጅትና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች በተገኙበት ተከናውኗል።

በመቐለ፣ እዳጋ ሀሙስ እና ዓድዋ የመጀመሪያ ዙር ተዋጊዎች ስልጠና የሚወስዱባቸው ማዕከላት መዘጋጀታቸውን የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን በትናንትናው ዕለት ማስታወቁ ይታወሳል።

የቀድሞ ተዋጊዎች በተዘጋጁ ማዕከላት ስልጠናዎችን ከወሰዱ በኋላ የመቋቋሚያ ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ማህበረሰቡ በመቀላቀል መደበኛ ሕይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል ተብሏል።

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Nov, 05:54


አሜሪካ በዩክሬን የሚገኝ ኤምባሲዋን ዘጋች

ውሳኔው ሩሲያ ልትፈፅመው የምትችለውን የአየር ጥቃት ከግምት ውስጥ በማስገባት የተወሰደ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህንንም ታሳቢ በማድረግ ስፔን፣ ጣሊያን እና ግሪክ እንዲሁ በዩክሬን የሚገኝ ኤምባሲያቸውን የዘጉ ሀገራት ናቸው፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን ሚሳኤል የመጠቀም ፍቃድ ከሰጡ ከ2 ቀናት በኋላ ዩክሬን በምእራባዊ የሩሲያ ድንበር ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ተጠቅሷል፡፡

ዩክሬን ወደሩሲያ ዘልቆ መግባት የሚችል አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤል ጥቅም ላይ ስታውል የመጀመሪያው ነው፡፡

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የመጀመሪያው ጥቃት ውጤታማነትን በመግለፅ በቀጣይ 3 ሺህ የክሩዝ ሚሳኤሎችን እንደሚያዘጋጁ ጠቁመዋል፡፡

ይህን ተከትሎ ሩሲያ የኒውኩሌር መርኃ ግብር ፖሊሲዋ ላይ ማሻሻያ ማድረጓን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

ማሻሻያው ለዩክሬን የሚሳኤል መሳሪያ ድጋፍ የሚያደርግ ሀገር በጦርነቱ በቀጥታ እንደተሳተፈ ይደነግጋል፡፡

በተጨማሪም ፑቲን ከዓለም ትልቁ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ጥቃት እንዲያደርስ ለማዘዝ የሚያስችላቸውን ቅድመ ሁኔታ የሚሰጥ ነው፡፡

ጆ ባይደን ያሳለፉት ውሳኔ ጦርነቱን አቀጣጣይ መሆኑን የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጨምሮ የፖለቲካው ተዋንያን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

21 Nov, 05:54


🤩የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን (ኅዳር 12/2017 ዓ.ም)

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Nov, 19:32


ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለራስ ገዟ ሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና ሊሰጡ እንደሚችል ተነገረ።

የቀድሞ የብሪታንያ መከላከያ ሚኒስትር ሰር ጋቪን ዊሊያምሰን በቀይ ባህር ላይ ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ቦታ ስላላት የሶማሌላንድ ይፋዊ እውቅና ከትራምፕ የፖሊሲ ሀላፊዎች ጋር መነጋገራቸውን ለኢንዲፔንደንት ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ትራምፕ በመጪው ጥር ስልጣን በያዙበት ፍጥነት ለሀርጌሳ እውቅናን ሊሰጡ ይችላሉ ነው ያሉት።በ1991 ከሶማሊያ የተገነጠለችው ሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና እንድታገኝ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩት የቀድሞ ሚኒስትር ከትራምፕ የፖሊሲ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርገው እንደነበር ገልጸዋል።

በውይይቱም ለሀርጌሳ እውቅና መስጠት በቀጠናው ባሉ የውሀ አካላት እና አካባቢው ላይ ሊኖር የሚችለውን በጎ ተጽዕኖ ማስረዳታቸውን ነው የተናገሩት።ትራምፕ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ከወሰኗቸው የመጨረሻ ውሳኔዎች መካከል የአሜሪካን ጦር ከሶማሊያ ማስወጣት የሚለው አንዱ ነበር ሆኖም ይህ ውሳኔ በባይደን አስተዳደር ተሽሯል።

የቀድሞ የእንግሊዝ ቀኝ ግዛት የነበረችው ሶማሊላንድ ከብሪታንያ ጋር ያላትን የጠበቀ ግንኙነት ያስቀጠለች ሲሆን የሀገርነት እውቅናን ለማግኝት የተለያዩ ባለስልጣናትን እንደምትጠቀም ይነገራል።የቀድሞ ሚኒስትር ለኢንዲፔንደንት እንደተናገሩት ትራምፕ እውቅናውን የሚሰጡ ከሆነ የቀጠናውን ጂኦፖለቲካ የሚቀይረው ይሆናል።

የሞቃዲሾን የሶማሊላንድ ይገባኛል ጥያቄ የሚደግፉት የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እውቅና እንዲሰጣት የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል። ምንም እንኳን ሶማሊያ የአለም አቀፍ የባህር ላይ ወንበዴ እና የሽብርተኝነት ማዕከል ብትሆንም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህንን አቋም አስቀጥለዋል።

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Nov, 19:30


ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እና ገንዘብ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለች‼️

በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እና ገንዘብ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን የፈጸመችው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አያት ዞን 1 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ነው።

ተጠርጣሪዋ በደላላ አማካኝነት በቤት ሰራተኝነት ከተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት በሶስተኛ ቀን ቆይታዋ የግል ተበዳይ ወደ ስራ በሄዱበት ወቅት አጋጣሚውን በመጠቀም በቤቱ ውስጥ የተቀመጠውን የተለያዩ ሀገራት ገንዘብ እንዲሁም የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጥ ሰርቃ ትሰወራለች።

ይህን ተከትሎም የግል ተበዳይ የተፈፀመባቸውን የወንጀል ድርጊት ለመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ያመለክታሉ፡።

ተጠርጣሪዋ የወንጀል ድርጊቱን ከፈፀመች በኋላ የግል ተበዳይ ጋር ከመቀጠሯ በፊት በክፍለ ከተማው ወረዳ 14 አባዶ አካባቢ ለሦስት ወራት ተከራይታው በነበረ ኮንዶሚኒየም ቤት ትደበቃለች።

የፖሊስ አባላት ባደረጉት ክትትል ከሰረቀቻቸው የተለያዩ አልባሳት፣ የሴትና የወንድ ጫማዎች፣ 18 ሺህ የአሜሪካ ዶላርና የህንድ ሩፒ፣ የወርቅና ልዩ ልዩ ጌጣጌጥ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሏን ከክፍለ ከተማው የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

በተጨማሪም ተጠርጣሪዋ በሁለት የተለያዩ ስሞች የነዋሪነት መታወቂያ እንደተገኘባትም ተገልጿል።

ተጠርጣሪዋ በእጇ ላይ የተገኘውን የውጭ አገራት ገንዘብ ከየት ያመጣችው እንደሆነ ፖሊስ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በተለይ ለEBC DOTSTREAM ገልፀዋል።

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Nov, 11:03


የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ያሳለፈውን የቪዛ እገዳ ለማንሳት የተግባር እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ተጠየቀ

4ኛው የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ሕብረት የጋራ የሥራ ቡድን ስብሰባ ትላንት ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተካሂዷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በስብሰባ ላይ “የአውሮፓ ሕብረት ከአሁን በፊት በኢትዮጵያውያን ላይ ያሳለፈውን የቪዛ እገዳ ለማንሳት የተግባር እንቅስቃሴ ማድረግ ይገባዋል” ሲሉ ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከስድስት ወራት በፊት የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ለኢትዮጵያውያን በጊዜያዊነት ወደ አውሮፓ የመግቢያ ቪዛ ፈቃድ መስጠት የሚከልክል ውሳኔ ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ማሳለፉን መዘገባችን ይታወሳል፤ ለክልከላው የሰጠው ምክንያት ከኢትዮጵያ መንግስት በቂ ትብብር እያገኘሁ ባለመሆኑ ነው የሚል ነበር።

በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት እዚህ ውሳኔ ላይ ያደረሰው በህብረቱ ሀገራት በህገወጥነት በሚቆዩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ዙሪያ “ከሀገሪቱ መንግስት በቂ ትብብር እያገኘሁ ባለመሆኑ ነው” የሚል ነበር።

ህብረቱ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል የቪዛ እገዳው አንዱ ሲሆን ኢትዮጵያውያን ቪዛ ለማግኘት የሚጠብቁት ጊዜ ከ15 የሥራ ቀናት ወደ 45 የሥራ ቀናት ከፍ እንዲል የሚለው ይገኝበታል።

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ትላንት በተካሄደው የጋራ የሥራ ቡድን ስብሰባ ወቅት ሕብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ያሳለፈውን የቪዛ እገዳ ለማንሳት የተግባር እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ጠይቀዋል ተብሏል።

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Nov, 11:01


የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ማዕከላት የማስገባት ሒደት ነገ ይጀመራል

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በሰጡት መግለጫ÷ ተቋሙ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ማሳካት የሚያስችልና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ፕሮግራምና ፕሮጀክቶች መቅረጹን ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሠረትም ከሰባት ክልሎች ከ371 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ማዕከላት ለማስገባት የመለየት ሥራ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

በሁለት ዓመታት ውስጥ በሚከናወነው የቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ሥራ ከ760 ሚሊየን ዶላር በላይ በጀት መያዙን አንስተዋል፡፡

ከነገ ሕዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮም በመጀመሪያው ምዕራፍ በትግራይ 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ በይፋ ይጀመራል ብለዋል፡፡

ለመጀመሪያው ዙር ማስፈጸሚያ ሃብት ከመንግስትና ከለጋሾች መገኘቱን ጠቁመው÷ የተሃድሶ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ለ6 ቀናት ወደ ማዕከላት ገብተው የዲጅታል ምዝገባና ማረጋገጥ፣ የሳይኮ-ሶሻልና የሲቪክ ተሃድሶ ስልጠና እንደሚወስዱ ነው ያስረዱት፡፡

የተሃድሶ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ወደ ማህበረሰቡ ሲመለሱ ለመሠረታዊ ፍጆታ እንዳይቸገሩ የመልሶ ማቀላቀል ክፍያ እንደሚሰጣቸውም አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Nov, 08:39


🚨ጥንቃቄ

➟" ተግባራችሁ በህግ የሚያስጠይቅ ነው። ይህን ተገንዝባችሁ ከእኩይ ተግባራችሁ ታቀቡ " - ጤና ሚኒስቴር

➟ከሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የስኳር ህመምን ጨምሮ ሃሰተኛ የጤና መረጃዎች ሃላፊነት በጎደላቸው አካላት እየተለቀቁ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

" ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሰዓታት ውስጥ የስኳር በሽታን ማጥፋት ተችሏል " በሚል ሰሞኑን እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ከእዉነት የራቀና አሳሳች መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

አሁን አሁን የህክምና ሞያ ሳይኖራቸውና ለሚሠጡት አገልግሎትም ህጋዊ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው በየማህበራዊ ሚዲያው ላይ እየወጡ ማህበረሰቡን የሚጎዱ፣ ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚለቁ አካላት ተበራክተዋል ብሏል።

ይህ ተግባር ደግሞ ማህበረሰቡን በእጅጉ እየጎዳና ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ከመዳረግ አልፎ ፈውስ ፈላጊ ዜጎችን ላይ ከፍተኛና የተወሳሰበ የጤና ችግር እየፈጠረ እንደሚገኝ አስገብዟል።

በዚህ መሰል ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አካላት ይህ ተግባር በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ተገንዝበው ከእኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

ማህበረሰቡ ምንጫቸው ካልተረጋገጠ አካላት የሚላኩ መልእክቶችን እንዲመረምር ፤ አገልግሎቶችንም ከመጠቀሙ በፊት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተብሏል።

➟አስፋላጊ ሆኖ ሲገኝም በ "[email protected]" ላይ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡

ሀሰተኛ የጤና መረጃ ከፍተኛ ቀውስ የሚፈጥር በመሆኑ ዜጎች ሀሰተኛ የጤና መረጃ የሚያሰራጩትን በመጠቆም ስለ ጤናው የጤና ባለሙያን ብቻ በማማከር ጤንነቱን እንዲጠብቅ መልዕክት ተላልፏል።

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Nov, 08:39


አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ከትላንት ጀምሮ መሾማቸው ተሰምቷል።

አምባሳደር ሽፈራው ወደ ህብረት ስራ ኮሚሽነርነት እስከ ተሾሙበት ጊዜ ድረስ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ ቆይተዋል።

የኢትዮጵያ ኅበረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ከወር በፊት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ፤ ኢህአዴግ ከመፍረሱ በፊት በተለያዩ የክልልና የፌዴራል የስልጣን እርከኖች ላይ ኢህአዴግ ፈርሶ ብልፅግና ከመጣም በኃላ በተለያዩ የስልጣን እርከኖች ላይ ተሹመው እየሰሩ ናቸው።

በሌላ በኩል ፤ በአምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ምትክ አህመድ አብተው (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ከትላንት ጀምሮ እንደ ተሾሙ ሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ዘግቧል።

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Nov, 08:37


🚨እንድታውቁት

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች አገልግሎት ለማግኘት " ፋይዳ " ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ ተደርጎ እየተሰራበት ነው።

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Nov, 08:36


ሩሲያ ዩክሬን በአሜሪካ ሚሳኤል ለፈጸመችው ጥቃት የአጸፋ ርምጃ እንደምትወስድ አስታወቀች

ዩክሬን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሰጡት ፍቃድ መሠረት አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎችን በትናንትናው ዕለት ወደ ሩሲያ ማስወንጨፏ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም ዘርፈ ብዙ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ይበልጥ መባባሱ ነው የተነገረው፡፡

በዛሬው ዕለትም ሩሲያ ዩክሬን በአሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤል ለፈጸመችው ጥቃት ተመጣጣኝ አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች፡፡

የረጅም ርቀት ሚሳኤል ጥቃቱንም የምዕራባውያን ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ስትል ሩሲያ መወንጀሏን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ድርጊቱ ምዕራባውያን በሞስኮ ላይ የጀመሩት አዲስ የጦርነት ምዕራፍ መሆኑንና ለዚህም በየደረጃው ተመጣጣኝ ርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቃለች፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በምስራቃዊ ዩክሬን እየጨመረ የመጣውን የሩሲያ ወታደሮችን እንቅስቃሴ ለመገደብ የሚያስችል ጸረ-ሰው ፈንጂዎችን ለዩክሬን ለመስጠት መስማማታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ባይደን በዩክሬን ግዛት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል ጸረ-ሰው ፈንጅ ለመስጠት ቢስማሙም በዩክሬን በኩል ፈንጂውን የመጠቀም ፍላጎት እንደሌለ ተጠቁሟል።

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Nov, 08:36


ለቀጣይ 10 ቀናት አብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ደረቅ ፀሐያማና ነፋሻማ ይሆናሉ

ኢንስቲትዩቱ ለሚቀጥሉት 10 ቀናት በሰሜን፣ ሰሜን ምሥራቅ፣ ምሥራቅ፣ መካከለኛው እና የደቡብ ደጋማ ቦታዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ እንደሚዘወተር ገልጾ፤ አልፎ አልፎ የማስከተል ጥንካሬ እንደሚኖረውም ጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅና የደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ተብሏል፡፡

በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ለዝናብ መፈጠር አመቺ ሁኔታ የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ቀጣይነት እንደሚኖራቸውም ተነስቷል፡፡

በፀሃይ ሀይል ታግዞ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በተለይም በደቡብ ምዕራብና በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተስፋፋና ሰፊ ቦታዎችን የሚያካትት ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል ነው የተባለው፡፡

በሌላ በኩል በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት ወቅቱን ያልጠበቀ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

20 Nov, 04:54


🤩የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን (ኅዳር 11/2017 ዓ.ም)