ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ @bethel_tube Channel on Telegram

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

@bethel_tube


የቤተክርስቲያንችንን ትውፊት እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ጹሑፎች ግጥሞች ትረካዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ መልዕክት ያላቸው መንፈሳዊ ወጎች ይተላለፉበታል። በተጨማሪም ኪነጥበባዊ ለዛን የተላበሱ አዝናኝና አስተማሪ ፅሑፎችም የሚቀርቡበት ቻናል ነው።

ሀሳብ አስተያየታችሁን @Belica_Addis ላይ ፃፉልን።

………… ©ቤትኤል ቤተ-እግዚአብሔር …………

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ (Amharic)

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ የቤተክርስቲያንችንን ትውፊት እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ጹሑፎች ግጥሞች ትረካዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ መልዕክት ያላቸው መንፈሳዊ ወጎች ይተላለፉበታል። በተጨማሪም ኪነጥበባዊ ለዛን የተላበሱ አዝናኝና አስተማሪ ፅሑፎችም የሚቀርቡበት ቻናል ነው። ሀሳብ አስተያየታችሁን @Belica_Addis ላይ ፃፉልን።

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

14 Aug, 05:28


‹‹በጒብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ›› (መክብብ ፲፪፥፩)

ያለማቋረጥ ሲሔዱም ሲቀመጡም፣ሲበሉም ሲጠጡም፣ ሲሠሩም ሲያርፉም ማሰብ ግን ሕይወትም፣ ጤናም፣ የደስታም ምንጭ ነው፡፡
እግዚአብሔርን ማሰብ – መልካም ነገርን መናገር
ማሰብ ከመናገር ጋር የአንድ ሳንቲም ገጽታ ነው፤ ሰው የሚናገረው ያሰበውን ነውና፡፡  ማሰብና መናገር ያላቸውን አንድነት ልበ አምላክ ነቢዩ ዳዊት ከተናገረው ኃይለ ቃል መረዳት ይቻላል፡፡  ‹‹አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል? በቅንነት የሚሄድ ጽድቅንም የሚያደርግ፣ በልቡም እውነትን የሚናገር›› በማለት የተናገረውን ቃል እናስተውል፡፡ ሰው በልቡናው ያስባል እንጂ አይናገርም፤ ሆኖም ግን በአንደበት የሚነገረው በልቡና የታሰበ ነውና በልቡም እውነትን የሚናገር ብሎ ተናገረ፡፡ (መዝ. ፲፬፥፩-፪)
በጉብዝናችን ወራት ፈጣሪያችንን እንድናስብ የሚረዳን አንደበታችን ከክፉ ከልክለን ሽንገላንም ከእኛ አርቀን ሰዎችን የሚያጽናና የሚያረጋጋ መልካም ነገርንም ብቻ ስንናገር ነው፡፡  እግዚአብሔርን የማሰብ አንዱ መገለጫ መልካም ነገር መናገር ነው፡፡  መጽሐፍ ‹‹እግዚአብሔር መልካም ነው›› ብሎ እንደተናገረ ስለ እግዚአብሔር ቸርነት፣ ታላቅነትና መጋቢነት የሚናገር መልካም ነገር ተናገረ፡፡ (ናሆ. ፩፥፯)
እግዚአብሔር ስለሚወደውና ስለሚፈቅደው ነገር ብቻ መናገር እግዚአብሔርን ማሰብ ነው፡፡  ዛሬ ላይ ብዙዎቻችን እግዚአብሔርን ማሰብ ስላቆምን ከአንደበታችን የሚወጣው ቃል ሁሉ ስድብ፣  ትችት፣  ነቀፋ፣ ሐሜት፣ ሽንገላ፣ ተረብና የመሳሰሉት ሆነዋል፡፡  ነቢዩ ዳዊት ‹‹ጉሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ሸነገሉ፤ ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤  አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶዋል  …. እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው የለም›› ብሎ እንደተናገረው የእኛም ነገር እንዲሁ ሆኗል፡፡ (መዝ. ፲፫፥፬-፮)
እግዚአብሔርን የሚያስብ ወጣት የሚናገረውን ያውቃል፡፡ አንደበቱም የተገራና በመልካም ነገር የተቀመመ ነው፡፡ ሰውን የሚያስደነግጥ፣ የከፋውን የሚያባብስ፣  በወገኖች መካከል ልዩነትን የሚያሰፋና ጠብ የሚጭር ነገር ከአንደበቱ አይወጣም፡፡ እየጮኸ፣ ጎረቤት እያወከ፣ ሰዎችን እያሳቀቀ፣ የሰዎችን ክብር እየነካ፣ በሌላው የአካል መጉደል እያሾፈ አይናገርም፡፡ ‹‹በአፍ ይጠፉ በለፈለፉ›› እንደሚባለውም በአንደበቱ ምክንያት የማይገባውን እየተናገረ በራሱና በማኅበረሰቡም ሆነ በሀገሩ ላይ ጥፋትና መጠፋፋትን አያመጣም፡፡ የምንናገረውን ለማወቅ ፈጣሪያችን ልዑል እግዚአብሔርን እናስብ፡፡  እግዚአብሔርን ማሰብ ስላቆምን ስለተውነውም ሰዎች በድለውንም ይሁን ሳይበድሉን የስድብ ናዳ እናወርድባቸዋለን፡፡  በአንድ ሰው ስሕተት አባቱ፣ እናቱ፣ ወንድሞቹ በመጣበት ነገድ፣ የተወለደበት መንደር ሳይቀረን በስድብ እናጥረገርጋቸዋለን፡፡  እግዚአብሔርን ማሰብ ስላቆምን የምንናገረው እያንዳንዱ ነገር ሰዎች ላይ ምን ዓይነት አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በሀገርም ላይ ምን ዓይነት ጥፋት ይዞ እንደሚመጣ ማስተዋል ተስኖናል፡፡  ጥቂት የማንባል ወጣቶች እግዚአብሔርን ማሰብ እንደሞት ስለምንቆጥረው የሞት ምክንያት የሆኑ አያሌ ነገሮች ከአጠገባችን ቆመዋል፡፡  ሽማግሎዎችን እንሳደባለን፤ አካል በጎደላቸው እንሳለቃለን፤ ችሎታ የጎደለውን እናሸማቅቃለን፤  ከደረስንበት ያልደረሰውን እናቃልላለን፡፡
እግዚአብሔርን  ማሰብ- ከመከራ ሁሉ መዳኛ መንገድ ነው፡፡
ጠቢቡ ሰሎሞን ‹‹በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ›› ብሎ የተናገረበትን ምክንያት ሲገልጥ የመጀመሪያ ምክንያት አድርጎ ያቀረበው ‹‹የጭንቀት ቀን ሳይመጣ›› የሚል ነው፡፡ በወጣትነት በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚገጥሙንን የጭንቀት ፈተናዎች የምንወጣው በተለያዩ አደንዛዥ ዕፅ ሱሶች ውስጥ በመደበቅ፣ አልኮል መጠጦችን በማብዛት፣ መፍትሔ ብለን የምንወስዳቸው ሌሎች ችግር አምጪ አማራጮች ውስጥ በመግባትና ሌሎች መሰል ድርጊቶችን በመከወን መሆን የለበትም፡፡ የጭንቀት መድኃኒቱ እግዚአብሔርን ማሰብና እንደ ፈቃዱም መመላለስ ነው፡፡ የወጣትነት ዕድሜ ካለፈ በኋላም ለሚገጥመን የሽምግልና ጭንቀት መድኃኒቱ የወጣትነት ዕድሜን አካሄድ ማስተካከል እንደሆነ የሥነ ልቡና ባለሙያዎችም ሳይቀሩ ይመክራሉ፡፡ ነቢዩ ዳዊት ‹‹ጎልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው›› ብሎ እንዳስተማረውም በኋለኛው ዘመን የሚኖረንን መዳረሻ የሠመረና ትርጉም ያለው የሚያደርገው በወጣትነት ዘመናችን ከእግዚአብሔር ጋር እንዲኖረን የምናደርገው መልካም አኗኗር ነው፡፡ በወጣትነት ያልዘሩትን በሽምግልና አያጭዱትም፡፡ በጉብዝና ያላረሙትን በዕርግና አያስተካክሉትም፡፡ (መዝ. ፻፲፰፥፱)
ጠቢቡ ሰሎሞን በጉብዝና ወራት ፈጣሪን የማሰብ ምክንያት አድርጎ ያቀረበው ሌላኛው ምክንያት ‹‹ደስ አያሰኙኝም የምትላቸው ዓመታት ሳይደርሱ፤ ፀሐይና ብርሃን ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ፥ ደመናትም ከዝናብ በኋላ ሳይመለሱ፤……….አፈርም ወደነበረበት ምድር ሳይመለስ÷ ነፍስም ወደሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ›› የሚል ነው፡፡ በፀሐይ በጨረቃና በከዋክብት የተመሰለ ማግኘት፣ ማሸነፍ፣ ነግዶ ማትረፍ፣ ሮጦ ማምለጥ፣ ወድቆ መነሣት የሚቻልበት የወጣትነት ጊዜ በእርጅና በድካም በደዌና ከፍ ሲልም በሞት ይደመደማል፡፡ በብርሃን ጀምረን በብርሃን፤ በድል ጀምረን በድል እንድንፈጽም ታናሽ የሆነ ጅማሬያችን እጅግ የበዛ እንዲሆን በጉብዝናችን ወራት ፈጣሪያችን ልዑል እግዚአብሔርን በመንገዳችንና በተግባራችን ሁሉ እናስብ፤ ከእርሱ ጋር እንኑር፤ ስለ እርሱም እንናገር!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር


ዛሬ ላይ ነገን ለማነጽ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ድምጽ ልንገነባ ነው። #ሚዲያችንን_ይደግፉ

▭▭▭▭▭▭▭▭ ©ቤትኤል ዘተዋህዶ ሚዲያ (BZM) ▭▭▭▭▭▭▭▭

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

11 Jul, 19:53


ድንግል ሆይ፣ እነሆ ንጉስ ካከበረሽ: የሚንቅሽ ማነው?

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

16 May, 04:49


"ውኃውም ጥልቅ ነበረ" - መጋቤ ሃይማኖት መምህር ተስፋዬ ሞሲሳ | New Orthodox Sibket By Memhir...
https://youtube.com/watch?v=OsAHz6jR2ow&si=QekE3n2tc7BKIVXu

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

03 May, 03:00


https://youtu.be/H0qNXm6wMsw?si=-pZ3aKNf0GGYH_V2

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

29 Apr, 03:56


የሕማማት ዝማሬ - "ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ" - የማርያም ሐዘን - ዘማሪ ዲያቆን ዳዊት ወርቅዬ | Ethiopi...
https://youtube.com/watch?v=Z6meE0GxBkc&si=VvZG-YtQeF1LZ_5g

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

27 Apr, 20:29


🌿 "ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ"  መዝ 8÷2 🌿

🌿
እንኳን አደረሳችሁ 🌿
🌿 ሆሳዕና በአርያም 🌿

🌿 "በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ  ነው!" 🌿 መዝ 117፥25 🌿

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

27 Apr, 09:52


"ትፈልገኛለህ" - ገጣሚ ክብሮም (ኬቢሻ) | New Ethiopian Orthodox Poem by Kebisha - ኬቢ...
https://youtube.com/watch?v=T1ihXl1L7iE&si=nb7OOLeKoTk2xf6K

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

25 Apr, 19:12


የፌስቡክ ገፃችንን ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61558615513475

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

19 Apr, 23:29


"ትፈልገኛለህ" - ገጣሚ ክብሮም (ኬቢሻ) | New Ethiopian Orthodox Poem by Kebisha - ኬቢ...
https://youtube.com/watch?v=T1ihXl1L7iE&si=nb7OOLeKoTk2xf6K

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

15 Apr, 18:55


https://vm.tiktok.com/ZMMC5hkYV/

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

05 Apr, 18:12


"ማረኝ መመኪያዬ" - ዘማሪት ሰላማዊት ተክሉ | New Ethiopian Orthodox Mezmur by Selamawi...
https://youtube.com/watch?v=wfGaKur5OG8&si=rjTqZ28CXlBjzqFy

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

03 Apr, 16:00


https://youtu.be/2n8XHKxgpSo?si=dbfQJvPZ2PGadI3B

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

25 Mar, 22:08


https://youtu.be/XQSNo4vjfy0?si=MymvKZScKYpFGsUu

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

21 Mar, 19:08


https://youtu.be/4P2GIo-7yEU?si=7R1weOqHtrKWZWay

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

20 Mar, 11:18


https://youtu.be/T0XLAUtMvK8?si=0NBE5l5RbPDYDZJW

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

16 Mar, 15:06


👉👉ከእኛ ቀድማችሁ ተኮነናችሁ

👉ዛሬ ከቤተክርስቲያን ስመለስ በቤተክርስቲያን ባየውና በሰማው ነገር ላይ የተበሳጨ ከአንድ ወጣት ጋር መንገድ ላይ ተገናኘን

ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ጸድቃችሁ ታጸድቁናላችሁ ብለን ስንጠብቅ ከእኛ ቀድማችሁ ተኮነናችሁ አለኝ

እኔም ለጊዜው ስላልገባኝ እንዴት በምን ምክንያት እንዲህ ልትል ቻልክ አልሁት

እሱም ቀበል አደረገና ሰው በቁሙ ሲኮነን ያለእድር ሙቶ ሲቀበር በዓይኔ አየሁኝ ሲል ደገመው

👉ከዚህ አያይዞ እንዴት አምሳ እና ስልሳ አቢያተ ክርስቲያናት በወደሙበት ካህናት መነኮሳት የአብነት ተማሪዎች በጥይት ተደብድበው በሞቱበት ዘመን እና ሰዓት ለቤተክርስቲያን እንደዚህ ዘመን ምቹ ጊዜ የለም ትላላችሁ አለኝ እና ከዚህ በላይ ምን ኩነኔ አለ ? አለኝ

በእኔ ቦታ ሁናችሁ ይህን ቋንቋ ብትሰሙ ምን አይነት ስሜት ሊሰማችሁ እንደሚችል አላውቅም

👉እኔ ግን ለጊዜው ይህ ቃል ከአንድ የሲኖዶስ አባል ሁኖ መገኘቱ እራሴን እስከ መጥላት ደረስኩኝ አፈርኩኝ ተሸማቀቁኝ ምድር ጠበበኝ መደበቂያ አጣሁኝ እኔን አይመለከተኝም ለማለት ዳዳሁ ነገር ግን ብፁዕ አባታችን በሚባል ሰው ይህ ድርጊት ተፈጽሞ አይመለከተኝም ማለት ቅሌት መሰለኝ

እግዚአብሔር ከእንዲህ አይነት ዳግም ሞት ይሰውረን 🤲🤲🤲