⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️ @eotc_spritual_books Channel on Telegram

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

@eotc_spritual_books


በዚህ ቻናል የሚቀርቡ

፩.ተከታታይ የቤተክርስቲያን ትምህርቶች ፣

፪. መንፈሳዊ መጻሕፍት ጥቆማ፤

፫. የተለያዩ አጫጭር የቤተክርስቲያን መጣጥፎች ፣ ወጎች ፣ ታሪኮች ፤

፬. ለተለያዩ ጥያቄዎች መልስ እና ወቅታዊ ትምህርቶችን እንማማራለን ፣

፭. ዘወትር #ቃለ_ወንጌል የእለቱ(በግፃዌ) ይቀርባሉ።


ለጥያቄ @Temechache ላይ ይላኩ

መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ (Amharic)

እንኳን ለአንዳንድ ቢሆን ስለዚህ ቻናል የሚቀርቡ። እዚህ ጥንቃቄ መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ የሚለውን የቤተክርስቲያን ትምህርቶችን አቆታቸዋል። በዚህ ቻናል፤ ከእንዴት አንዳንድን እንወቅ? የሚለውን መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንቅስቃሴ ይላኩ። ስለመንፈሳዊ መጻሕፍት፤ የቤተክርስቲያን ታሪኮችን እና መጻሕፍት ጥቆማን ከማጥፋት እና በጥቆማ የሚሰጥባቸውን መጣጥፎችን እንቅስቃሴ ይላኩ። በቤተክርስቲያን መጻናት እንማማራለን፤ ሰልካካለሁ። ምንም በእውነታ በአማርኛ ከሶስተኛ ወርቂ በኀገር እዚህ ዘወትር #ቃለ_ወንጌል የእለቱን (በግፃዌ) ይለዋል። ለጥያቄ @Temechache ላይ ይላኩ።

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

13 Feb, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

13 Feb, 03:45


#ቃለ_ወንጌል

06/06/2017
ማቴዎስ 26:6-17


ጌታችን ኢየሱስም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ፥ ዋጋው እጅግ ብዙ የሆነ ሽቱ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብርሌ የያዘች ሴት ወደ እርሱ መጣች፤ ጌታችን ኢየሱስም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው። ደቀ መዛሙርቱም ይህን ባዩ ጊዜ ተቈጥተው እንዲህ አሉ፥ “ይህች ሴት ለምን ይህን ያህል ሽቱ አጠፋች? ይህ በብዙ ዋጋ ተሸጦ ለድሆች ምጽዋት ይሰጥ ዘንድ ይቻል ነበርና።” ጌታችን ኢየሱስም ዐወቀባቸውና እንዲህ አላቸው፥ “ይህችን ሴት ለምን ታደክሙአታላችሁ? ለእኔ መልካም ሥራ ሠርታልኛለችና።

ድሆችንስ ዘወትር ታገኙአቸዋላችሁ፤ በወደዳችሁም ጊዜ በጎ ታደርጉላቸዋላችሁ፤ እኔን ግን ዘወትር የምታገኙኝ አይደለም። "እርስዋ ይህን በራሴ ላይ ያፈሰሰችውን ሽቱ ለቀብሬ አደረገችው። "እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ወንጌል በዓለሙ ሁሉ በሚሰበክበት ቦታ ይህች ሴት ያደረገችው ለእርስዋ መታሰቢያ ሆኖ ይነገራል።”


ከዚህም በኋላ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት አንዱ ይሁዳ የሚባለው የአስቆሮቱ ሰው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ። “ምን ትሰጡኛላችሁ? እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው። እነርሱም ሠላሳ ብር መዘኑለት፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ለእነርሱ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ ምቹ ጊዜ ይሻ ነበር።


                                 ምስባክ
                           መዝሙር ፵፬:፰-፱

ከርቤ ወቀንዐት ወሰሊሖት እምነ አልባሲከ

እምክቡዳነ አቅርንት ዘእምኔሆሙ አሥተፌሥሐከ

አዋልደ ንግሥት ለክብርከ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

12 Feb, 09:26


ያዕቆብ ፪÷፳-፳፬

#አንተ_ከንቱ_ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን? አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን? እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?

መጽሐፍም፦ አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።
#ሰው_በእምነት_ብቻ_ሳይሆን_በሥራ_እንዲጸድቅ_ታያላችሁ


¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

12 Feb, 09:03


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

12 Feb, 03:21


#ቃለ_ወንጌል

ዘነነዌ ረቡዕ
ማቴዎስ 16:1-5


ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም ከሰማይ ምልክትን ያሳያቸው ዘንድ ሊፈትኑት መጡ። ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥

“በመሸ ጊዜ ሰማዩ ቀልቷልና ጊዜው ብራ ነው ትላላችሁ። በነጋም ጊዜ ሰማዩ ደምኖ ቀልቷልና ዛሬስ ይዘንማል ትላላችሁ፤ እናንተ ግብዞች፥ የሰማዩን ፊት መተርጐም ታውቃላችሁ፤ የዘመኑንስ ምልክት እንዴት አታውቁም? ክፉና፤ አመንዝራ ትውልድ ምልክትን ትሻለች፤ ምልክት ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር አይሰጣትም” ከዚህም በኋላ ትቶአቸው ሄደ።

ምስባክ
                  መዝሙር ፵፩ : ፯ – ፰

ኵሉ ማዕበልከ ወሞገድክ እንተ ላእሌየ ኀለፈ

መዓልተ ይኤዝዝ እግዚአብሔር ሣህሎ ወሌሊተ ይነግር

እምኀቤየ ብዕዐተ ሕይወትየ ለእግዚአብሔር

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

11 Feb, 09:26


“ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው እህትህን አትናቃት ምንም ይሁን ምን ሰውን አትናቅ ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከው እንደሆነ በለው (አስተውል)።

እንዴት? ያልከኝ እንደሆነ ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ሆኗል የክርስቶስ ሕዋስ ከሆነ ደግሞ እርሱን ናቅከው ማለት ክርስቶስን ናቅከው ማለት ነውና ወንድምህን የምትንቅ ከሆነ በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣እራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትን ቀላቅለው እንዳጠጡት፣ በፊቱ ላይ ከተፉበት፣ ሰዎች በምንም አትተናነሥም ስለዚህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ


   ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

11 Feb, 09:03


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

11 Feb, 03:06


#ቃለ_ወንጌል

ዘነነዌ ሠሉስ
ሉቃስ 11:29-23


ብዙ ሕዝብም በተሰበሰቡ ጊዜ እንዲህ ይል ጀመር፦ይህ ትውልድ ክፉ ነው ምልክት ይፈልጋል ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም፡፡

ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆናቸው እንዲሁ ደግሞ የሰው ልጅ ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል፡፡ ንግሥተ አዜብ በፍርድ ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋራ ተነሥታ ትፈርድባቸዋለች የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና እንሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።

ምስባክ
መዝሙር 63:9-10

ወፈርሃ ኵሉ ሰብእ

ወነገሩ ግብረ እግዚአብሔር

ወአዕመሩ ምግባሮ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

10 Feb, 09:26


‹‹ትህትናን ውደዷት ኃጢአታችሁን የምትሸፍን ናትና፡፡ ሁሉም ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ቢሆንም ከኃጢአቶች ሁሉ መጥፎ የሆነው ግን የልብ ትዕቢት ነው:: ራሳችሁን አዋቂ አድርጋችሁ ከፍ ከፍ አታድርጉ፡፡ ይህን ምታድረጉ ከሆነ ጥረታችሁ ሁሉ ፍሬ አልባ ይሆናል፡፡››
                             አባ እንጦንስ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

10 Feb, 09:03


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

10 Feb, 03:08


#ቃለ_ወንጌል

ዘነነዌ ሰኑይ
            ማቴዎስ 12:38-43


በዚያን ጊዜ ከጻፊዎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና፦መምህር ሆይ ከአንተ ምልክት እንድናይእንወዳለን አሉ። እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።

ዮናስ በዓሣ ዐንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል። የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋራ ተነሥተው ይፈርዱበታል በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተዋልና እንሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ፡፡ ንግሥተ አዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋራ ተነሥታ ትፈርድበታለች የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና እንሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ
አለ።


                             ምስባክ
                       መዝሙር ፪ ቍ. ፲፪

አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዓዕ እግዚአብሔር

ወኢትትኀጐሉ እምፍኖተ ጽድቅ

ሶበ ነደት ፍጡነ መዓቱ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

09 Feb, 09:36


+++ ጣዕም የሌለው ስብከት ++

ወደ ከተማችን አንድ ሰባኪ ሊሰብክ መጣ ፣ የመጣው ለመስበክ ፈልጎ አልነበረም፡፡ እኛን ለማዳን ጉጉት አድሮበት ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ሊያሰማን ጓጉቶ አልነበረም፡፡ በግድ ተገፍትሮ ፣ ተተፍቶ ፣ ተወርውሮ የመጣ ዓይነት ሰው ነበር፡፡ ወደ መሃል ከተማም አልገባም የከተማችን አንድ ሦስተኛውን ብቻ ከተጓዘ በኋላ ስብከቱን ጀመረ፡፡ የሰበከው ስብከት  ሰላምታ የለውም ፣ መግቢያ የለውም ፣ መውጫም የለውም ፣ ማጽናኛም የለውም ፣ ‹ንስሓ ግቡ› የሚል አዋጅ የለውም፡፡ በጩኸት የተናገረው አንድ አስደንጋጭ ዐረፍተ ነገር ብቻ ነበር ‹‹በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች!!›› ከነነዌ ነዋሪዎች አንዱ የነነዌን ታሪክ ቢጽፈው የሚጽፈው እንዲህ ነበር፡፡

የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሕዛብ ናቸው፡፡ ዮናስ ደግሞ እነርሱ የማያውቁትን አምላክ የሚያመልክ ነቢይ ነው፡፡ ዮናስ ወደ እነርሱ የመጣው የማዳን ተልዕኮ ይዞ አልነበረም፡፡ ወደ አሕዛብ መላኩ አላስደሰተውም፡፡ ዮናስ ወደ ነነዌ የመጣው እንደ ሌላ ሰባኪ በየትኛውም ትራንስፖርት ተጉዞ ሳይሆን በዓሣ አንበሪ ወደ ነነዌ ተተፍቶ ነው፡፡ የተተፋ ሰባኪ እንዴት ደስ ብሎት ይሰብካል? እንኳን ስብከት ይቅርና ማንኛውም ሥራ ያለ ፍላጎት እንዴት ሊሳካ ይችላል? ዮናስ የነነዌ ሕዝብ እንዲድን ፍላጎትም አልነበረውም፡፡ እንዲያውም ከመጀመሪያውም ፍርሃቱ ‹ትጠፋላችሁ› ብሎ ተናግሮ ሳይጠፉ ቢቀሩስ የሚል ነበር፡፡

ዮናስ ወደ ከተማይቱ  ዘልቆ ሲገባም በፍላጎት አልሰበከም ፤ የሰበከው ስብከት ተስፋ የሚያስቆርጥ ፣ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ነበር፡፡ የነነዌ ሰዎች የማያውቁትን አምላክ እንዲያውቁ ዕድል የሚሠጥ ትምህርት አልተሠጣቸውም፡፡ ዮናስም እንደ ኖኅ ‹ይኼንን ያህል ዘመን ተሠጥቷችኋል ተመለሱ› ብሎ አልሰበከም፡፡ መርከብ ሠርቶ ግቡም አላላቸውም፡፡ ‹በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች› ብሎ ጮኸ፡፡

የነነዌ ሰዎች ግን ‹ማን ነው የሚገለብጣት?› ‹ለምን ትገለበጣለች?› ‹ለመሆኑ አንተ ማን ነህ?› ‹ዝም ብሎ ትገለበጣላችሁ ይባላል? መጀመሪያ ትምህርት አይቀድምም?› አላሉም፡፡ራሳቸውን እንጂ ሰባኪውንና ስብከቱን ለመገምገም ጊዜ አልነበራቸውም፡፡ ‹‹እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ››

አንድ ላይ ኃጢአት መሥራት ቀላል ነው ፤ አንድ ላይ ንስሓ መግባት ግን ይከብዳል፡፡ በሀገር ደረጃ ንስሓ መግባት ግን እጅግ ያስደንቃል፡፡ ‹ነነዌ የምትገለበጥ ከሆነ ሀገር እንቀይር› አላሉም ፤ ሀገር ከመቀየር ይልቅ ራሳቸውን መቀየር እንደሚሻል ተረድተው ነበር፡፡ ሁሉም እኩል ልቡ ተሰበረ ፤ ሁሉም ማቅ ለበሰ፡፡

የሰባኪው ስብከት ጣዕም የለውም ብለው አላማረሩም ፣ ‹ተስፋ የሚሠጥ ስብከት መቼ ሰማን› አላሉም፡፡ ሰባኪው እያዋዛ አላስተማራቸውም ፣ ምሳሌ አልነገራቸውም ፣ ቅኔ አልተቀኘላቸውም ፣ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ‹‹የተላከላቸው ጨካኝ ሐኪም ነበር ፤ የያዘው መድኃኒትም የሚያቃጥል ነበር ፤ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ቃል ተናገራቸው ፤ እነርሱ ግን አቁስሏቸው ተፈወሱ››   

የነነዌ ሰዎች ንስሓ ከላይ እስከታች ነበር፡፡ ነገሥታቱ ሳይቀር ማቅ ለበሱ፡፡ ‹‹ነነዌ ትገለበጣለች› ብሎ ሲናገር ንጉሡ ወታደሮች ልኮ ዮናስን ማሰር ይችል ነበር፡፡ ‹‹ምን በሀገራችን ላይ ታሟርታለህ?›› ብለው አፉን አላፈኑትም፡፡ መፍትሔውን ንገረን ያለውም የለም ፤ ችግሩ እነርሱ ናቸውና መፍትሔውንም ያውቁታል፡፡ ስለዚህ ራሳቸውን መውቀስ ወደዱ፡፡

ሀገሪቱ በአንድ ልብ አለቀሰች፡፡  ንጉሡ ፡- ሰዎችና እንስሶች አንዳች አይቅመሱ! ብሎ አዋጅ አስነገረ፡፡ ከቤተ መንግሥት ጾም የሚታወጅባት ነነዌ እንዴት የታደለች ናት? ‹‹መኳንንቶችሽ ማልደው የሚበሉ አገር ሆይ ወዮልሽ›› ተብሎ ከተጻፈ መኳንንቶችዋ የሚጾሙላት ሀገር እንዴት የታደለች ትሆን? (መክ. 10፡16) መቼም ሕዝብ ብቻ መጾሙ ነገሥታት ቢበሉ የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን እየበሉ የሚጾምን ሕዝብ መምራት እንዴት ይቻላል? ሲጠጡ እያደሩስ ሲጸልይ የሚያድርን ሕዝብ መምራት እንዴት ይቻላል?

ንጉሥሽ ላንቺ ማቅ ለብሶ ያለቀሰልሽ ፣ እንስሳት ሳይቀር የጾሙልሽ ነነዌ ሆይ ምንኛ የታደልሽ ነሽ? ሕዝብሽ ጾም ሲታወጅ የማያላግጡ ፣ ‹እኔ በፈለግሁበት ጊዜ ነው የምጾመው› ብለው የማይመጻደቁ ፣ እንኳን ከቤተ ክህነት ይቅርና ከቤተ መንግሥት የታወጀን ጾም በትሕትና የሚጾሙብሽ ነነዌ ሆይ ምንኛ የታደልሽ ነሽ? የዋሐን ሕጻናትን ጡት ከልክለው የፈጣሪን ርኅሩኅ ልብ የሚያስጨንቁ ፣ እንስሳትን ከውኃ ከልክለው ለምህላ የታጠቁ የነነዌ ሰዎች ምንኛ ድንቅ ናቸው፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም ያቺን ከተማ በዓይነ ሕሊናው በጎበኛት ጊዜ እንዲህ ብሏል ፡-
‹‹የንጉሥ ቤት ግብዣ ተቋረጠ ፣ ንጉሥ ማቅ ለበሰ ፤ ንጉሥ ማቅ ከለበሰ ደግሞ የጌጥ ልብስ ይለብሳል፡፡ በዚያን ጊዜ በነነዌ ወርቃችሁን ብትጥሉ ማንም አይሰርቀውም፤ ሀብታችሁ ያለበትን ቤት ክፍት ትታችሁ ብትሔዱ ማንም ዘው ብሎ አይገባም፡፡ ወንዶች ወደ ሴቶች በምኞት አይመለከቱም ፤ ሴቶችም የሚያያቸውን ለመማረክ ጌጦቻቸውን አላደረጉም፡፡ ከልጆቻቸው ጋር አብረው ወደ መቃብር ሊወርዱ ነውና አረጋውያን በላያቸው አመድን ነሰነሱ፡፡ ወላጆች በልጆቻቸው ጥያቄ ተጨነቁ ፤ አብርሃም ልጁ ይስሐቅ ‹የመሥዋዕቱ በግ ወዴት ነው› ሲለው የተጨነቀው ጭንቀት በነነዌ ወላጆች ተደገመ››   

ሶርያዊው የበተ መንግሥቱን ሁኔታም እንዲህ ይሥለዋል፡፡ 

‹‹የነነዌ ንጉሥ ወታደሮቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸውም ፡- ይህ ድል እንደተጎናጸፍንባቸው ውጊያዎቻችን አይደለም ፤ ከባዕድ ሀገር በተሰማው ዜና ኃያላኖቻችን ሳይቀሩ ተብረክርከዋል ፤ አንድ ዕብራዊ መጥቶ በቃሉ አብረከረከን፡፡የጀግኖች እናት ነነዌ አንድን ለብቻው የመጣ ደካማ ሰው ቃል ፈርታለች፡፡
ስለዚህ ወገኖቼ ፤ የማይፈርስ አጥር እንገንባ ፤ ይህች አጥር ንስሓ ናት ፤ ሥውር ጦርነት ታውጆብናልና ራሳችንን ሥውር መሣሪያ እናድርግ!!››

ዮናስ በነነዌ መመለስ ደስ አልተሰኘም ፤ ትንቢቱ ስለማይፈጸምለት ብቻ አይደለም፡፡ ‹‹የእስራኤል ሽማግሌዎች በሚቀማጠሉባት ሰዓት የነነዌ ሽማግሌዎች ሲያለቅሱ አየ ፤ ጽዮን በዝሙት እንደ ሰም ስትቀልጥ ነነዌ ታነባ ነበር›› እስራኤል ከፈጣሪ በራቁበት ሰዓት አሕዛብ የንስሓ ዕንባ ሲታጠቡ ሲያይ ክብር ከእስራኤል መልቀቁን አይቶ ተከፋ፡፡
ዮናስ እስከመጨረሻው ሰዓት የነነዌን መጥፋት ይጠባበቅ ነበር፡፡ ዮናስ ነነዌ የምትገለበጥበትን ቀን ሲቆጥር ነነዌ ደግሞ ኃጢአትዋን ትቆጥር ነበር፡፡

ዮናስ ስለ ነነዌ እንደ ሙሴ ‹እነርሱን ከምታጠፋ እኔን አጥፋኝ› አላለም ፤ በተቃራኒው ‹እነርሱን ካላጠፋህ እኔን አጥፋኝ› እስከማለት ደረሰ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ነነዌን ወከሎ ነቢዩን እንዲህ ይለዋል ፡-
‹‹አንተ ዕብራዊ ሆይ ሁላችን ብንጠፋ ምን ይጠቅምሃል? አንተ ሰባኪ ሆይ በሁላችን መሞትስ ምን የተሻለ ነገር ይገኛል? የማቴ ልጅ ሆይ ወደ መቃብር በጸጥታ ብንወርድ ምን ታገኛለህ? በቃልህ ፈውሰኸን ልናመሰግንህ ስንመጣ ለምን ታዝናለህ? ዕጣህ ነነዌን ተናግሮ ያጠፋት ከመባል ይልቅ ተናግሮ ያተረፋት መባል ቢሆን አይሻልህም? መላእክት በሰማይ ሲደሰቱ አንተ ለምን ታዝናለህ? ዮናስ ሆይ ከእንግዲህ በስምህ የምትጠራ ናትና ነነዌን አመስግናት››

በእርግጥም ዮናስ በሽተኛ አክሞ ስለዳነለት የሚበሳጭ ሐኪም ሆነ፡፡ የነነዌ ሰዎች ግን የሰባኪው ማንነት ፣ የስብከቱ ውበት አልባነት ፣ የአነጋገሩ ለዛ ምክንያት ሳይሆናቸው ተስፋ በ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

09 Feb, 09:04


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

09 Feb, 03:00


#ቃለ_ወንጌል

ሉቃስ 2:42-ፍጻሜ


አሥራ ሁለት ዓመትም በሞላው ጊዜ እንደ አስለመዱ ወደ ኢየሩሳሌም ለበዓል ወጡ። ሥራቸውንም ጨርሰው ተመለሱ፤ ሕፃኑ ጌታችን ኢየሱስ ግን በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፤ ዮሴፍና እናቱም አላወቁም ነበር። "በመንገድም ከሰዎች ጋር ያለ መስሎአቸው ነበር፤ የአንድ ቀን መንገድንም ከሄዱ በኋላ ዕለቱን ከዘመዶቹ፥ ከሚያውቁትም ዘንድ ፈለጉት። ባላገኙትም ጊዜ እ ፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።ከዚህም በኋላ በሦስተኛው ቀን በቤተ መቅደስ በሊቃውንት መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውና ሲጠይቃቸው አገኙት።

የሰሙትም ሁሉ አስተዋይነቱንና አመላለሱን ያደንቁ ነበር። በአዩትም ጊዜ ደነገጡ፤ እናቱም፡ “ልጄ፥ ለምን እንዲህ አደረግኸን? እነሆ አባትህም፥፤ እኔም ስንፈልግህ ደከምን” አለችው። "እርሱም፥ “ለምን ትፈልጉኛላችሁ? በአባቴ ቤት ልኖር እንደሚገባኝ አላወቃችሁምን?” አላቸው። እነርሱ ግን የነገራቸውን ቃል አላስተዋሉም። ከእነርሱም ጋር ሂዶ ወደ ናዝሬት ወረደ፤ ይታዘዝላቸውም ነበር፤ እናቱ ግን ይህን ሁሉ ነገር ትጠብቀው፥ በልብዋም ታኖረው፤ ነበር። ጌታችን ኢየሱስም በእግዚአብሔር ዘንድ፥ በሰውም ዘንድ፥ በጥበብና በአካል በሞገስም አደገ

ምስባክ
መዝ· ፻፵፯ : ፩ – ፪

ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር

ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጽዮን

እስመ አጽንዐ መናስግተ ኆኃትኪ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

08 Feb, 11:36


++ በሰንበት መፍረስ ++

የኢያሪኮ ሰዎች የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ኃይል በመናቃቸው ምንኛ ተጎዱ?!  እርሱ ዓለምን የፈጠረ መሆኑን ስላላመኑ እንዳልተፈጠሩ የሆኑት የኢያሪኮ ሰዎች መጨረሻ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡

ቅጥራቸው ከመፍረሱ በፊት እስራኤል የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ለስድስት ቀናት ያህል በዝምታ ኢያሪኮን ዞሯት፡፡ ዓለምን በስድስት ቀናት የፈጠረውን ጌታ እንዲያስተውሉ ስድስት የዝምታ ቀናት ተሠጧቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ግን ጮኹ የኢያሪኮም ቅጥር ፈረሰ፡፡

ሰባተኛ ቀን የዕረፍት ቀን ነው፡፡ ለኢያሪኮ ግን የመፍረስ ቀን ሆነባት፡፡ ሰባተኛ ቀን ፈጣሪን ለሚያምኑ የተቀደሰ ቀን ነበር ፤ ለኢያሪኮ ኝ የመረገም ቀን ሆነባት፡፡
እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ ባየበት ሰባተኛ ቀን ኢያሪኮ ግን ከፉ እንደሆነች ታየባት፡፡

እግዚአብሔር የሌለበት ሕይወት እንዲህ ነው፡፡ ወዳጄ እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ከሌለ የሰንበት ቀን የነፍስህ ዕረፍት ቀን መሆኑ ይቀርና እንደ ኢያሪኮ የመፍረስ ቀን ይሆናል፡፡ በዚያ ቅዱስ ቀን ቅጥርህን በመጠጥ ፣ ብስካር ብዝሙት ስታፈርስ ትውልና ታድራለህ፡፡ ራስህን አንድደህ ትሞቃለህ ፤ እያራገብህ ትቃጠላለህ፡፡ ታቦት ይዘው ቢዞሩህም የኃጢአት ግንብን አጥረሃልና አትሰማም፡፡ በላይህ ላይ ቢቀደስብህም እንደ ኢያሪኮ ሰዎች ካህናቱን እያየህ ‘ዝም ብሎ መዞር ምንድር ነው?’ እያልክ ትስቃለህ፡፡ የካህናቱ የቅዳሴ ዜማ ለአንተ የሚያፈርስ ጩኸት ይሆንብሃል፡፡ የኢያሪኮ ሰው ከመሆን ፣ በሰንበት ፈራሽ ከመሆን ያድንህ!

ቅዳሴያችን መካከል ካህኑ ዕጣን እያጠኑ ዞረው ሲመለሱ የዚህች አጭር ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የሆነውን ይህንን ጸሎት ይጸልያሉ፦  አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ አስቀድመህ በባሪያህ በነዌ ልጅ በኢያሱ እጅ የኢያሪኮን ግንብ እንዳፈረስከው የእኔንና የሕዝብህን የኃጢአታችንን ግንብ አፍርሰው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 9 /2012 ዓ.ም.
ቪክቶሪያ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

08 Feb, 09:02


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

08 Feb, 02:57


#ቃለ_ወንጌል

1/06/2017
ዮሐንስ 15:26-17


“እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ ጰራቅሊጦስ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመስክራል። “እናንተም ትመሰክራላችሁ፤ ከጥንት ጀምሮ ከእኔ ጋር ኑራችኋልና።

“እንዳትሰናከሉ ይህን ነገርኋችሁ። "ከምኵራባቸው ያስወጡአችኋል፤ ደግሞም እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። 'ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንም፥ እኔንም ስላላወቁ ነው። ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ እኔ እንደ ነገርኋችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ነገርኋችሁ አስቀድሜ ግን ይህን አልነገርክኋችሁም ነበር ከእናንተ ጋር ነበርሁና አሁን ግን ወደ ላከኝ ወደ አብ እሄዳለሁ፤ ከእናንተ አንዱ እንኳ ወዴት ትሄዳለህ?” ብሎ አይጠይቀኝም። ነገር ግን ይህን ስለነገርኋችሁ በልባችሁ ኀዘን ሞላ።

"እኔ በእውነት የሚሆነውን እነግራችኋለሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻላችኋል፤ እኔ ካልሄድሁ ጰራቅሊጦስ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ከሄድሁ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። እርሱም በመጣ ጊዜ ዓለምን ስለ ኀጢአትና ስለ ጽድቅ፡ ስለ ፍርድም ይዘልፈዋል። “ስለ ኅጢኣት፡ በእኔ አላመኑምና ነው፣ 'ስለ ጽድቅ፥ እኔ ወደ ኣብ እሄዳለሁና፤ እንግዲህ ወዲህም አታዩምኝምና ነው ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዢ ይፈረድበታልና ነው።

“የምነግራችሁ ብዙ ነገር ነበረኝ፣ ነገርግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም። "ያ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ግን ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ እርሱ ከራሱ አይናገርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። እርሱም እኔን ያከብረኛል፤ ከእኔ ወስዶ ይነግራችኋልና። ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህም ከእኔ ወስዶ ይነግራችኋል አልኋችሁ።

“ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታዩኝምም፤ ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እንደገናም ታዩኛላችሁ፤ ወደ አብ እሄዳለሁና
”።
 
                                 ምስባክ
                          መዝሙር ፴፪ : ፭ - ፮

ሣህሉ ለእግዚአብሔር መልዐ ምድረ

ወበቃለ እግዚአብሔር ጸንዐ ሰማያት

ወእምእስትንፋሰ አፉሁ ኵሉ ኃይሎሙ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

07 Feb, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

07 Feb, 03:06


#ቃለ_ወንጌል

30/05/2017
ሉቃስ 22:26-31

በወሰዱትም ጊዜ የቀሬና ሰው ስምዖንን ከዱር ሲመለስ ያዙት፤ ከጌታችን ከኢየሱስም በስተኋላ መስቀሉን አሸከሙት። ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፤ ሴቶችም “ዋይ ዋይ” እያሉ ያዝኑለትና ያለቅሱለት ነበሩ። ጌታችን ኢየሱስም መለስ ብሎ እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች ሆይ፥ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ እንጂ ለእኔስ አታልቅሱልኝ። መካኖች፥ ያልወለዱ ማኅፀኖችና ያላጠቡ ጡቶችም የተመሰገኑ ናቸው የሚሉበት ወራት ይመጣልና። ያንጊዜም ተራሮችን በላያችን ውደቁ፤ ኮረብቶችንም ሰውሩን ይሉአቸዋል።


                         መዝ· ፵፬ : ፲፬ – ፲፭

ወይወስዱ ለንጉሥ ደናግለ ድኅሬሃ

ወቢጻሂ ይወስዱ ለከ

ወይወስድዎን በትፍሥሕት ወበሐሤት

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

06 Feb, 10:59


+ ድንገት የተበጠሰ ገመድ +

የደብረ ዳሞ ገዳም በገመድ ብቻ የሚወጣ እጅግ ጥንታዊ ገዳም ነው:: ይህንን አቡነ አረጋዊ በዘንዶ የወጡትን ታላቅ ገዳም ለመውጣት በግንባታው ወቅት በአፄ ገብረ መስቀል የተሠራ ደረጃ ነበረው:: ሆኖም አቡነ አረጋዊ ደረጃውን ዳህምሞ (አፍርሰው) ብለው በማዘዛቸው እስከ አሁን ድረስ በገመድ የሚወጣበት ገዳም ሆኖአል::

የደብረ ዳሞ መውጫ ገመድ እጅግ ወፍራም ሲሆን እስከ አሁን ድረስ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተንጠላጥለው ወጥተው ወርደውበታል:: ይህ እጅግ ወፍራም ገመድ ለዘመናት ሲያገለግል ተበጥሶ ሰው ጥሎ አያውቅም:: በታሪክ የማይዘነጋና መሃል ላይ የተበጠሰበትና ሰው የጣለበት ቀን አለ:: (የዲያቢሎስ መተናኮል ነው የሚል አለ)

በዚያ ቀን በተበጠሰው ገመድ ላይ የወረደው መንገደኛ ጻድቁ አባ ተክለ ሃይማኖት ነበሩ:: መነኮሳቱን ተሰናብተው በዚያ ገመድ ሲወርዱ ተበጥሶ የማያውቀው ገመድ ድንገት ተበጠሰ:: ከላይ የሚያዩት አባቶች ቁልቁል እያዩ በድንጋጤ ጮኹ:: ሆኖም እግዚአብሔር ለጻድቁ የብርሃን ክንፍ ሠጥቶአቸው ከተበጠሰው ገመድ ተለይተው እንደ መልአክ በርረው ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ወርደው መሬት ላይ አረፉ:: ባረፉባት ሥፍራም ቤተ ክርስቲያን ተሠራባት::

ወዳጄ በሕይወትህ ድንገት የተበጠሰ ገመድ የለም? ሳትጠብቀው የተበጠሰ ገመድ ማንም ላይ ሳይበጠስ አንተ ላይ የጨከነ ገመድ የለም? ምን ዓይነት ገመድ አትበለኝ:: የእንጀራ ገመድ የኑሮ ገመድ የትምህርት ገመድ የፈለግኸው ገመድ በለው:: እሱን ተጠምጥመህ ይዘህ ወደ አንዳች ቦታ ለመድረስ የተማመንክበት ተስፋህን ሙሉ በሙሉ የጣልክበት ገመድ የለም? ድንገት ተበጥሶ ዙሪያው ገደል አልሆነብህም? ሰዎች ማንም ላይ ያልተበጠሰ ገመድ አንተ ላይ ሲበጠስ አይተው "ምኑ ዕድለ ቢስ ነው?" ብለው የተደነቁብህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "ከባሕር አደጋ ተርፎ ዕባብ የነደፈው እንዴት ኃጢአተኛ ቢሆን ነው?" ብለው በትዝብት ዓይን እንዲያዩህ ያደረገ በሕይወትህ ሳታስበው ተበጥሶ ዙሪያው ገደል የሆነ ሥፍራ ላይ የጣለህ የሕይወት ገመድ ይኖር ይሆናል::

በዕድልህ አትማረር በሕይወትህ ድንገት የሚበጠስብህ ገመድ የምትወድቅበት ሳይሆን ክንፍ አውጥተህ የምትበርበት ነው:: ፈጣሪ የተማመንክበትን የምታየውን ገመድ እንዲበጠስብህ ከፈቀደ ያላየኸውን ክንፍ ሊሠጥህ እንጂ ሊጥልህ አይደለም::  የሕይወትህን ገመድ የተበጠሰበትን ቀን "እግዚአብሔር ለመልካም አሰበው" ብለህ እንደ ዮሴፍ ታመሰግንበታለህ::
ገመድህን የሚበጥሰው ከገደል ሊጥልህ ሳይሆን በክንፍ አብቅሎ ሊተክልህ ነው:: የሚተክልህ በበረሃ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ነው:: ተራ ተክል የምትሆን እንዳይመስልህ:: የሃይማኖት ተክል (ተክለ ሃይማኖት) ትሆናለህ:: ተክለ መንፈስ ቅዱስ ተክለ ወልድ ተክለ አብ ትሆናለህ:: አብ የተከለው ደግሞ አይነቀልም!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 24 2013 ዓ ም

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

06 Feb, 09:05


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

06 Feb, 07:33


#ቃለ_ወንጌል

29/05/2017
ዮሐንስ 1:7-15

እርሱም ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምን ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክርነት መጣ። ስለ ብርሃን ምስክር ሊሆን መጣ እንጂ እርሱ ራሱ ብርሃን አልነበረም።

"ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃንስ ወደ ዓለም የመጣው ነው። በዓለም ነበረ፤ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፤ ዓለሙ ግን አላወቀውም። “ወደ ወገኖቹ መጣ፤ ወገኖቹ ግን አልተ ቀበሉትም። ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ሥልጣንን ሰጣቸው። "እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከሥጋዊና ከደማዊ ግብር ወይም ከወንድና ከሴት፤ ፈቃድ አልተወለዱም።

ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእኛም አደረ፤ ለአ ባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብሩን አየን፤ ጸጋንና እውነትን የተመላ ነው።

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

05 Feb, 09:57


+ አባቶቻችን እንዲህ አሉ +

"እሳትና ውኃን ማዋሐድ እንደማይቻል በሌሎች ኃጢአት መፍረድም በራስ ኃጢአት ከመጸጸት ጋር አብሮ አይሔድም" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው" አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ

"እግዚአብሔር ለኃጢአተኛ ሰው ያለው ፍቅር
ጻድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል"
አባ አርሳኒ

"ሕፃን ልጅ እናቱ ስታጥበው ያለቅሳል:: ሕፃን እምነት (ትንሽ እምነት) ያላቸው ሰዎችም ነፍሳቸውን የሚያጥብ መከራ ሲመጣባቸው እግዚአብሔርን ያማርራሉ"  አባ ስምዖን

"ዕለትን የሠጠህ እርሱ ለእለት የሚበቃህንም ይሠጥሃል"  ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

"እጅግ ምርጡ ጸሎት "ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ" ማለት ነው"
ባሕታዊ ቴዎፋን

"ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንጹሕ ብትሆንም አትናቀው:: ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድም ብሏል"  አባ ቴዎዶር

"አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ ብታይ እንኳን አትፍረድበት:: አንዳንዴ ዓይንህም ሊሳሳት ይችላል"
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"ለኃጢአተኛው ክንፍህን ዘርጋለት:: ኃጢአቱን ልትሸከምለት ባትችል እንኳን ሸፍንለት"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

ከአበው አንዱን ትሕትና ምንድርን ነው? ብለው ጠየቁት:: እርሱም "ትሕትና ማለት ወንድምህ በበደለህ ጊዜ እርሱ ይቅርታ ሳይጠይቅህ በፊት ቀድመህ ይቅር ማለት ነው" አለ::

"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ" አባ ኤፍሬም አረጋዊ [ If you don’t forgive, forget heaven]

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 22 2013 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

05 Feb, 09:03


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

05 Feb, 03:16


#ቃለ_ወንጌል

28/05/2017
ማቴዎስ 15:32-ፍጻሜ

ጌታችን ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ፥ “እነዚህ ሰዎች ያሳዝኑኛል፤ በዚህ ከእኔ ጋር ከዋሉ ሦስት ቀን ነውና፤ የሚበሉትም የላቸውም፤ በመንገድ እንዳይደክሙ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልወድም” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም፥ “ይህን ያህል ሕዝብ የሚያጠግብ እንጀራ በምድረበዳ ከወዴት እናገኛለን?” አሉት።

"ጌታችን ኢየሱስም፥ “ስንት እንጀራ አላችሁ?” አላቸው፤ እነርሱም፥ “ሰባት እንጀራ፥ ጥቂትም ዓሣ” አሉት። ሕዝቡንም በምድር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤ ሰባቱን እንጀራና ዓሣውን ይዞ አመሰገነ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ አቀረቡ። ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቍርስራሽ ሰባት ቅርጫት ሙሉ አነሡ። የበሉት ሰዎችም ከሴቶችና ከልጆች በቀር አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ። ሕዝቡንም አሰናብቶ ወደ ታንኳው ገባ፤ ወደ መጌዶል አገርም ሄደ።

ምስባክ
መዝ ፸፯ : ፳፬ – ፳፭

አዝነመ ሎሙ መና ይብልዑ

ወወሀቦሙ ኅብስተ ሰማይ

ወኅብስተ መላእክቲሁ በልዑ እጓለ እመሕያው

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

04 Feb, 09:57


#አንድ_በጣም_ትልቅ_ቆሻሻ_የጫነ_ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ  "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል።

ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው  ቤት አለ። የምን ቤት? ልብህ ነዋ፤ ማን ይኖርበታል አልኸኝ? እግዚአብሔር ነዋ። አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም?

እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል
?

🌸🌸🌸

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

04 Feb, 09:05


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

04 Feb, 03:58


# መድኃኔዓለም

ላሚቱ ማምለጥ እየቻለች ስለ አንካሳ ጥጃዋ ብላ (አንካሳ ጥጃዋን ከአውሬው ለማዳን ብላ) ስትሄድ እርሷንም አውሬ ይበላታል። ይህችን ላምም መድኃኔዓለም መስሏታል ይላሉ አንድ ባለቅኔ።

በይነ ጣዕዋሃ ሐንካስ ትትበላዕ ላሕም አምሥጦ ዘይትከሀላ።
ለይእቲ ላሕም መድኃኔዓለም ተመሰላ።
ላም ጥጃዋን አንካሳ ጥጃዋን ከአውሬ ለማዳን ብላ በአውሬው ትበላለች።ይህ ላም ለጥጃዋ ያላትን ፍቅር የምትገልጥበት ነው። ፍቅር ማለት አብሮ መብላት አብሮ መጫወት ብቻ አይደለም።

አብሮ መሞትም ጭምር ነው። የሌላውን ችግርም አብሮ መቅመስ ነው። ይህ ነው ሕያው ፍቅር።
መድኃኔዓለምም አዳምን ለማዳን በመስቀል ተሠቀለ። እርሱ ምንም በደል ሳይኖርበት በደለኛ አዳምን
ያድን ዘንድ ተሠቀለ። እኛን ከዘላለም ስቃይ ከሲኦል እና ከመከራ ከኀዘንና ከሰቆቃ ሊያድነን ንጹሐ ባሕርይ እርሱ ስለ እኛ ተሰቀለ። ሱኑቱዩ በሃይማኖተ አበው ሞተ ክርስቶስ በሞተ ዚአነ ከመ ይቅትሎ ለሞት በሞቱ ብሏል።
አይ ፍቅር

💚@Eotc_spritual_books💚
💛@Eotc_spritual_books💛
❤️@Eotc_spritual_books❤️

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

04 Feb, 02:48


#ቃለ_ወንጌል

27/05/2017
ማቴዎስ 11:7-15

እነዚያም ከሄዱ በኋላ፥ ጌታችን ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ለሕዝቡ እንዲህ ይላቸው ጀመረ፥ “ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጥታችኋል? ከነፋስ የተነሣ የሚወዛወዘውን ሸንበቆ ነውን? ፤ወይስ ምን ልታዩ ወጥታችኋል? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን ነውን? እነሆ፥ ቀጭን ልብስ የሚ ለብሱስ በነገሥታት ቤቶች አሉ። ምን ልታዩ ወጥታችኋል? ነቢይን ነውን? አዎን፤ እሱ ከነቢይ እጅግ ይበልጣል እላችኋለሁ። እነሆ፥ እኔ በፊትህ መንገድህን የሚጠርግ መልእክተኛዬን በአንተ ፊት እልካለሁ ተብሎ ስለ እርሱ የተጻፈለት ይህ ነውና።

“እውነት እላችኋለሁ፤ ሴቶች ከወለዱአቸው ወገን ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን የሚያንሰው ይበልጠዋል። «ከመጥምቁ ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፤ የተገፉትም ይናጠቁአታል። "ነቢያትም ሁሉ፥ ኦሪትም እስከ ዮሐንስ ትንቢትን ተናግረዋልና። ልትቀበሉትስ ብትወድዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው።

ምስባክ
መዝሙር 45:22-23

እስመ በእንቲአሁ ይቀትሉነ ኵሎ ዓሚረ

ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ

ንቃሕ እግዚኦ ለምንት ትነውም

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

03 Feb, 12:25


“ከልቦቻችን በማይነቀሉ የፍቅሩ ችንካሮች ተቸነከርን:: ያዝነው አንለቀውም እርሱም አቀፈን አልተወንም:: ወደ እርሱ በሃይማኖት አቀረበን:: ከእርሱም ወደ ቀኝ ወደ ግራ አንሸሽም:: እንደ ቀለበት በልባችን እንደ ማኅተም በክንዳችን አኖርነው:: እንደ ዕንቁ በልባችን ሳጥን አስቀመጥነው:: እንደ ወርቅ በሕሊናችን መዝገብ አኖርነው::

እንደ ግምጃ ለበስነው:: እንደ ሐር ግምጃ ተጎናጸፍነው:: እንደ ወታደር ሰይፍ ታጠቅነው:: ለጦር ዕቃ እንደተዘጋጀ የድል ጋሻ ተደገፍነው:: ተከዜና ግዮን በኢሎል ወር እንደሚሞሉ ፍቅሩ በልባችን መልቶአል:: እንደ መከር ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ እንደ ክረምት ጊዜም የጤግሮስ ወንዝ ስንዴ ሲያሹት እንደሚሆን እንደ ኤፍራጥስ ወንዝ ልባችንን በወንጌል ፈሳሽነት አረሰረሰው:: መርከባችንንም በሃይማኖት ወንዝ አስዋኘው"

ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
መጽሐፈ ምሥጢር 24:20

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

03 Feb, 09:03


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

03 Feb, 02:57


#ቃለ_ወንጌል

26/05/2017
ሉቃስ 11:1-19

ከዚህም በኋላ በአንዲት ቦታ ጸለየ፤ ጸሎቱን በጨረሰ ጊዜም ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ አስተማራቸው ጸሎት አስተምረን” አለው። 'እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “በምትጸልዩበት ጊዜ እንዲህ በሉ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነ እንዲሁም በምድር ይሁን። 'የዕለት ምግባችንን በየዕለቱ ስጠን። "እኛም የበደለንን ሁሉ ይቅር እንድንል በደላችንን ይቅር በለን፤ አቤቱ፥ ወደ ፈተና አታግባን፤ ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ።”

እንዲህም አላቸው፥ “ከመካከላችሁ ወዳጅ ያለው ሰው ቢኖር በመንፈቀ ሌሊትም ወደ እርሱ ሄዶ እንዲህ ቢለው:- “ወዳጄ ሆይ ሦስት እንጀራ አበድረኝ። 'ወዳጄ ከመንገድ መጥቶብኛልና የማቀርብለት የለኝም። ያ ወዳጁም ከውስጥ ሆኖ፦ “አትዘብዝበኝ፤ ደጁን አጥብቀን ዘግተናል፤ ልጆችም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ተኝተዋል እሰጥህ ዘንድ መነሳት አልችልም” ይለዋልን? ወዳጁ ስለሆነ ሊሰጠው ባይነሣ እንኳ እንዳይዘበዝበው ተነሥቶ የወደደውን ያህል ይሰጠዋል። እኔም እላችኋለሁ:-ለምኑ፥ ይሰጣችኋልም፤ ፈልጉ፥ ታገኛላች ሁም፣ ደጅ ምቱ፥ ይከፈትላችኋልም። የሚለምን ሁሉ ይሰጠዋልና፤ የሚፈልግም ያገኛ ልና፤ ደጅ ለሚመታም ይከፈትለታልና። “ከአናንተ መካከል ልጁ ዳቦ የሚለምነው አባት ቢኖር ድንጋይ ይሰጠዋልን? ዓሣ ቢለምነውስ በዓሣ ፋንታ እባብን ይሰጠዋልን? “ወይስ ዕንቍላል ቢለምነው በዕንቍላል ፋንታ ጊንጥ ይሰጠዋልን? “እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠትን የምታውቁ ከሆነ፥ የሰማይ አባታችሁማ ለሚለምኑት መልካሙን ሀብተ መንፈስ ቅዱስ፤ እንዴት አብዝቶ ይሰጣቸው ይሆን?”

"ዲዳና ደንቆሮ፤ ጋኔንንም ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም በወጣ ጊዜ ዲዳና ደንቆሮ የነበረው ተና ገረ፤ ሰዎችም አደነቁ። ነገር ግን ከመካከላቸው፥ “በአጋንንት አለቃ በብዔል ዜቡል አጋንንትን ያወጣቸዋል” ያሉ ነበሩ፤ እርሱም መልሶ፥ “ሰይጣን ሰይጣንን ማውጣት እንደ ምን ይቻለዋል?” አላቸው። "ሌሎችም ሊፈትኑት ከእርሱ ዘንድ ከሰማይ ምልክትን ይፈልጉ ነበር። “እርሱ ግን የሚያስቡትን ዐወቀባቸውና እንዲህ አላቸው፥ “እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁሉ ትጠፋለች፤ ቤትም እርስ በርሱ ቢለያይ ያ ቤት ይወድቃል። ።ሰይጣንስ እርስ በርሱ ከተለያየ መንግሥቱ እንዴት ይጸናል? በአጋንንት አለቃ በብዔል ዜቡል አጋንንትን ያወጣል ትላላችሁና።

ምስባክ
መዝሙር 65:13-14

እበውዕ ቤተከ ምስለ መባዕየ

ወእሁብ ብፅዓትየ ዘነበብኩ በአፉየ

ዘእቤ በከናፍርየ አመ ምንዳቤየ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

02 Feb, 09:02


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

02 Feb, 03:04


#ቃለ_ወንጌል

ሉቃስ 2:42-ፍጻሜ

     ዐሥራ ሁለት ዓመትም በሞላው ጊዜ እንደ አስለመዱ ወደ ኢየሩሳሌም ለበዓል ወጡ። ሥራቸውንም ጨርሰው ተመለሱ፤ ሕፃኑ ጌታችን ኢየሱስ ግን በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፤ ዮሴፍና እናቱም አላወቁም ነበር። በመንገድም ከሰዎች ጋር ያለ መስሎአቸው ነበር፤ ያንድ ቀን መንገድንም ከሄዱ በኋላ ዕለቱን ከዘመዶቹ፥ ከሚያውቁትም ዘንድ ፈለጉት። ባላገኙትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። " ከዚህም በኋላ በሦስተኛው ቀን በቤተ መቅደስ በሊቃውንት መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውና ሲጠይቃቸው አገኙት። "የሰሙትም ሁሉ አስተዋይነቱንና አመላለሱን ያደንቁ ነበር።

በአዩትም ጊዜ ደነገጡ፤ እናቱም፡ “ልጄ፥ ለምን እንዲህ አደረግኸን? እነሆ አባትህም፥ እኔም ስንፈልግህ ደከምን” አለችው። "እርሱም፥ “ለምን ትፈልጉኛላችሁ? በአባቴ ቤት ልኖር እንደሚገባኝ አላወቃችሁምን?” አላቸው። እነርሱ ግን የነገራቸውን ቃል አላስተዋሉም። "ከእነርሱም ጋር ሂዶ ወደ ናዝሬት ወረደ፤ ይታዘዝላቸውም ነበር፤ እናቱ ግን ይህን ሁሉ ነገር ትጠብቀው፥ በልብዋም ታኖረው፤ ነበር። ጌታችን ኢየሱስም በእግዚአብሔር ዘንድ፥ በሰውም ዘንድ፥ በጥበብና በአካል በሞገስም አደገ


                                ምስባክ
                        መዝሙር 117:27-28

እግዚአብሔር እግዚእ አስተርአየ ለነ

ግበሩ በዐለ በትፍሥሕት በኀበ እለ ያስተሐምምዎ

እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

01 Feb, 10:57


+++ለአባ የትናንቱ+++

ያለ ማወቅ ፅልመት አገሩን ሲወርሰዉ
ማን ነበር ትዉሉዱን በወንጌል ያረሰዉ?
አባ ተክለ ሃይማኖት አባ የትናንቱ
ትዝ አለኝ ተጋድሎዉ ዉል አለኝ ሕይዎቱ
በቆላ በደጋ የተንከራተትኸዉ
የሃይማኖት ተክል ዞረህ የተከልኸዉ
የኢትዮጵያ ፀሐይ አባ ተክለ አብ
እስቲ መለስ ብዬ ገድልህን ላስብ
የክህደት ጨለማ ባንተ ሲርቅ
የሃይማኖት ብርሃን ሲያንፀባርቅ
በቀንና ሌሊት ከላይ ታች ዞረህ
ሕዝቡን አደረስከዉ አስተምረህ መክረህ

ስንት ነበር አባ የጉዞ አበልህ?
ያረፍህበት ስፍራ የተዘጋጀልህ
የት ነበር መኝታዉ ጎን ማሳረፊያህ
ንገረኝ እባክህ ማን ነበር የሸኘህ

እሳት አባቴ ሆይ እኔ አመድ ልጅህ
በዘመኔ ቋንቋ እስቲ ልጠይቅህ?


ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

01 Feb, 09:02


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

24 Jan, 09:53


+ የተቀደሰው የሩጫ ውድድር +

እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሩጫ ብሔራዊ ኩራት በሆነበት ሀገር መቼም የሩጫ ነገር ብናወራ ሰሚ አናጣም:: ሮጦ ሀገር ማስጠራት : ሮጦ ብዙ ሀብት ማፍራትና ለሀገር መትረፍ የቻሉ ውድ አትሌቶቻችንን በፍቅር እናያቸዋለን::  "በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ" የሚለው ቅዱስ ቃል ለነፍስ ቢነገርም ኢትዮጵያ ውስጥ ግን "ታገኙ ዘንድ ሩጡ" የሚለው መርሕ "ሮጬ ባለፈልኝ" በሚሉ ተስፈኞች ይተገበራል:: (1ቆሮ 9:24)

ዛሬ ግን በሁለት ሰዎች መካከል የተደረገ ቅዱስ ሩጫ ትዝ አለኝ::  በትንሣኤ ዕለት የተደረገ ቅዱስ እሽቅድምድም በዓይነ ሕሊናዬ መጣ::
ከዓሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መካከል ሁለቱ የተሳተፉበት ዳኛም ተመልካችም የሌለበት የትንሣኤ ዕለት ሩጫ!!!

ሴቶች ወደ ጌታ መቃብር ደርሰው ሲመለሱ ጌታ በመቃብር እንደሌለ ለደቀ መዛሙርቱ ነገሩአቸው::
ስለዚህ ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ መቃብሩ ሔዱ::

"ሁለቱም አብረው ሮጡ፤ ሌላው ደቀ መዝሙርም ከጴጥሮስ ይልቅ ፈጥኖ ወደ ፊት ሮጠና አስቀድሞ ከመቃብሩ ደረሰ" ዮሐ 20:4

በዚህ ቀን በተደረገው ቅዱስ ሩጫ የ58 ዓመቱ ጎልማሳ ጴጥሮስ ከ28 ዓመቱ ወጣት ዮሐንስ ጋር ወደ ጌታ መቃብር ሮጡ:: ሐሙስ ማታ ጌታውን የካደው ጴጥሮስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታውን ከተከተለው ዮሐንስ ጋር አብሮ ወደ መቃብሩ ሮጠ::

ጴጥሮስ ሆይ ወደ ጌታህ መቃብር በሩጫ ስትገሰግስ ምን እያሰብህ ይሆን? ሐሙስ በካድከው ጊዜ ቀና ብለው ያዩህ ዓይኖቹ በሕሊናህ መጥተው ይሆን?
ወደ መቃብሩ ስትሮጥ "ጌታ ሆይ በአፌ ክጄሃለሁ በእግሮቼ ግን አልክድህም" ብለህ አስበህ ይሆን? "በባሕር ላይ ያራመድኸው እግሬ : አጎንብሰህ ያጠብከው እግሬ ወደ አንተ ለመሮጥ አይደክመውም" ብለህ ይሆን? መቃብሩ ሥር ተደፍተህ ለማልቀስ የሐሙሱን ዕንባህን በመግነዙ ለማበስ አስበህ ይሆን?

ብቻ ጴጥሮስ ከዮሐንስ ጋር ወደ መቃብሩ ሮጠ:: ዮሐንስ በጉልበቱ ገና ወጣት ቢሆንም : እንደ ጴጥሮስ ጸጸት የማይቆጠቁጠው ድል አድራጊ ቢሆንም ጴጥሮስ አብሮ ከመሮጥ ወደኁዋላ አላለም::

ብቻ መቃብሩ ልድረስ እንጂ ቢቀድመኝም እከተለዋለሁ:: እንደርሱ እስከ መስቀል ባልጸናም ለመቃብሩ ግን ዳግም እታገላለሁ ብሎ ጴጥሮስ ሮጠ::

በዚህ ቅዱስ ሩጫ አርብ የወንድ ለቅሶን ያፈሰሰው ዮሐንስ በዕንባ በደከሙ ዓይኖቹ በኀዘን በጠቆረ ፊቱ እያማተረ ወደ ጌታ መቃብር ገሠገሠ:: በዚያች ዕለት ጌታን እንዴት እንደ ገረፉት አይቶአል:: እንዴት እንደ ቸነከሩት ተመልክቶአል:: አሁን ደግሞ መስቀል ሥር ቆመው በዋሉ እግሮቹ ወደ መቃብሩ እየሮጠ ነው::

ወንድሜ ሆይ ጴጥሮስና ዮሐንስን ወደ ጌታ መቃብር ሲሮጡ እያቸው:: አንተና ጉዋደኞችህስ ወዴት ትሮጣላችሁ? የእናንተ እሽቅድምድም ወደ ጌታ መቃብር ነው? የት ለመሔድ ትፎካከራላችሁ? የት እንገስግስ ትባባላላችሁ?

ወጣቱ ዮሐንስ ጎልማሳውን ጴጥሮስን ቀድሞ ከጌታ መቃብር ደረሰ:: የጌታን መግነዝም አየ:: ወደ ውስጥ ግን ሳይገባ ቆሞ ጴጥሮስን ጠበቀው:: ጴጥሮስ ዘግይቶ ቢደርስም ከዮሐንስ ቀድሞ ወደ መቃብሩ ገባ::

ከእኔ የበረታ መንፈሳዊ ጉልበት ያለህ ወንድሜ ሆይ ብትቀድመኝ እንኩዋን አትፍረድብኝ:: ጨክነህ ጥለኸኝ ወደ ጌታ ማረፊያ እንዳትገባ:: የዘገየሁት ኃጢአት እግሬን አስሮት ነውና ብርቱው ወንድሜ ሆይ እባክህን ጠብቀኝ::  ድክመቴን አይተህ አትናቀኝ መጎተቴን አይተህ አትፍረድብኝ:: አደራህን ብቻህን ወደ ጌታ ደስታ እንዳትገባ:: አደራህን በንስሓ እስክበረታ ጠብቀኝ:: እንኩዋን አንተ አብረኸኝ ሩጫ የጀመርክ ወንድሜ ቀርቶ ከእኔ ቀድመው ሩጫቸውን የጨረሱት እንኩዋን ብቻቸውን ወደ ዘላለማዊ ደስታ እንዳይገቡ በገነት ሆነው እኔን ይጠብቁኝ የለ?

ነቢዩ እንደተናገረ :-
     አቤቱ፥ ስምህን አመሰግን ዘንድ፤
   ነፍሴን ከወህኒ አውጣት፤
   ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ፡
   ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ። (መዝ 142:7)

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 16 2013 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

24 Jan, 09:05


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

24 Jan, 03:31


#ቃለ_ወንጌል

16/05/2017
ዮሐንስ 5:25-33

     እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ቃል የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም ይድናሉ። ለአብ በራሱ ሕይወት እንዳለው፣ እንዲሁም ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጠው። የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ነውና ይፈርድ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠው።

“በመቃብር ያሉ ሁሉ ቃሉን የሚሰሙባት ጊዜ ትመጣለችና ስለዚህ አታድንቁ። ፳፱መል ካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፥ ክፉ የሠሩም ለፍርድ ትንሣኤ ይነሣሉ። “እኔ ከራሴ አንዳች አደርግ ዘንድ አልችልም፤ እንደ ሰማሁ እፈር ዳለሁ እንጂ፤ ፍርዴም እውነት ነው፤ የላከኝን ፈቃድ እንጂ የእኔን ፈቃድ አልሻምና

“እኔ ለራሴ ብመሰክር ምስክርነቴ እውነት አይደለም። ነገር ግን ለእኔ የሚመሰክር ሌላ ነው፤ ስለ እኔ የሚመሰክረው ምስክርነቱም እውነት እንደሆነ አውቃለሁ።

                            ምስባክ
                       መዝሙር 39:4-5

ብፁዕ ብእሲ ዘስመ እግዚአብሔር ትውክልቱ

ወዘኢነጸረ ውስተ ከንቱ ውስተ መዓት ወሐሰት

ብዙኀ ገበርከ እግዚኦ ኣምላኪየ መንክረከ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

23 Jan, 09:04


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

23 Jan, 03:53


#ቃለ_ወንጌል

15/05/2017
ማቴዎስ 18:1-12

በዚያችም ሰዓት የጌታችን ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት፥ “በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማነው?” እያሉ ወደ እርሱ ቀረቡ። ሕፃንንም ጠርቶ በመካከላቸው አቆመው። "እንዲህም አለ፥ “እውነት እላችኋለሁ፤ ካልተመለሳችሁ፥ እንደዚህም ሕፃን ካልሆናችሁ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም። 'እንደዚህም ሕፃን ራሱን ዝቅ ያደረገ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ ይህ ነው። እንደዚህም ያለውን አንድ ሕፃን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል። ፣በእኔ ከሚያምኑ ከእነዚህ ከታናናሾች አንዱን የሚያሰናክል አህያ የሚፈጭበት ወፍጮ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር ቢሰጥም ይሻለዋል።

“ከሚመጣው ማሰናከያ የተነሣ ለዓለም ወዮለት ማሰናከያ ግድ ይመጣልና፤ ነገር ግን ማሰናከያን ለሚያመጣት ለዚያ ሰው ወዮለት። እጅህ ወይም እግርህ ብታስትህ ከአንተ ቈርጠህ ጣላት፤ ሁለት እጅ ወይም ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ዘለዓለም እሳት ከምትጣል፥ አንካሳ ወይም ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻልሃልና። 'ዐይንህ ብታስትህ ከአንተ አውጥተህ ጣላት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ዘለዓለም ገሃነመ እሳት ከምትጣል፥ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻልሃልና።

“ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁልጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ። የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና::

ምስባክ
መዝሙር 65:12-13

አኅለፍከነ ማዕከለ እሳት ወማይ

ወአውፃእከነ ውስተ ዕረፍት

እበውዕ ቤተከ ምስለ መባዕየ

ትርጉም

በእሳትና በውኃ መካከል አሳለፍኸን

ወደ ዕረፍትም አወጣኸን

መባዬን ይዤ ወደ ቤትህ እገባለሁ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

22 Jan, 09:03


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

22 Jan, 09:03


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

22 Jan, 03:11


#ቃለ_ወንጌል

14/05/2017
ማርቆስ 10:29-31


ዮሐንስ 3:29-ፍጻሜ

ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ ምድር ሄደ፤ በዚያም እያጠመቀ አብሮአቸው ተቀመጠ። ዮሐንስም በዮርዳኖስ ማዶ፤ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን ያጠምቅ ነበር፤ በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና፤ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ እየመጡ ያጠምቃቸው ነበር። "ዮሐንስ ገና ወደ ወኅኒ ቤት አልገባም ነበርና

ከዚህም በኋላ በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል ስለ ማንጻት ክርክር ሆነ፤ ወደ ዮሐንስም ሄደው፥ “መምህር ሆይ፥ በዮርዳኖስ ማዶ ካንተ ጋር የነበረው፥ አንተም የመሰከርህለት እርሱ እነሆ፥ ያጠምቃል፤ ሁሉም ወደ እርሱ ይሄዳል” አሉት። “ዮሐንስም መልሶ እንዲህ አለ፥ “ሰው ከሰማይ ካልተሰጠው በስተቀር እርሱ ራሱ ጸጋን ገንዘብ ሊያደርግ ምንም አይችልም። እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፤ ነገር ግን እንድሰብክለት ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ እንዳልኋችሁ እናንተ ራሳችሁ ምስክሮች ናችሁ። ሙሽራ ያለችው ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው የሙሽራው ሚዜ ግን በሙሽራው ቃል እጅግ ደስ ይለዋል፤ የእኔ ደስታ አሁን ተፈጸመች። የእርሱ ትበዛለች፤ የእኔ ግን ታንስ ዘንድ ይገባል።”

ከላይ የመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የተገኘውም ምድራዊ ነው፤ የምድሩንም ይናገራል፤ ከሰማይ የመጣው ግን ከሁሉ በላይ ነው። ባየውና በሰማው ይመሰክራል፤ ነገር ግን ምስክርነቱን የሚቀበለው የለም። ምስክርነቱን የተቀበለ ግን እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ። እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና። አብ ልጁን ይወዳልና፣ ሁሉን በእጁ ሰጠው። በወልድ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር የቍጣ መቅሠፍት በላዩ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።

ምስባክ
መዝሙር 78:10

ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ

በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲክ ዘተክዕወ

ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን

ትርጉም

አሕዛብ አምላካቸው ወዴት ነው እንዳይሉን

የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል

በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይዩ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

21 Jan, 17:16


መጥኖ መመገብ

ሆዱን የሚሞላ ሰው የፍትወት ባሪያ ይሆናል :: ለከፈለ ህብስት ከታዘዘና ከተገዛበት ግን በዚህ ባርነት የተያዘም ቢሆን ሊያሸንፍ ከወደደ ሁሉንም ድል ይነሳቸዋል ::

ይኸውም ስስት የዝሙት ምንጭ ነው :: በእርሱ ምክንያት በማይሰጡት ሰዎች ላይ የሚቆጣና የማይታዘዝ ቁጡ ውሻ  ይጮሃል:: በወንድሞች መካከል ሆድን ይሞላ ዘንድ ይጎመጃል::

በሆድ ምክንያት ነፍስ መግደልና ወደ ሲኦል የሚያደርስ ክፋት ሁሉ ይደረጋል :: እንዳታሽ ችግርን ይህቺን ነፍሰ ገዳይ ጅብ የሆነችንን እናስቸግራት ::

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

21 Jan, 11:05


ቃና ዘገሊላ በዓል

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

21 Jan, 10:58


የጥምቀት በዓል በፎቶ #6 ዝዋይ/ባቱ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

21 Jan, 10:56


የጥምቀት በዓል በፎቶ #5 አዲስ አበባ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

21 Jan, 10:53


የጥምቀት በዓል በፎቶ #4 ጎንደር

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

11 Jan, 10:39


+ ኢየሱስ እናቱን ተቆጥቷት ይሆንን? +

የቃና ሰርግ ቤት ታሪክ ለጊዜው እናቆየውና አንድ ልጅ በአደባባይ በሰዎች ፊት እናቱን በምንም ምክንያት ቢቆጣ እንኳን ከሃይማኖት አንጻር ከሥነ ምግባርም አንጻር የሚደገፍ ሥራ አይደለም፡፡ ክብር ይግባውና ጌታችን ‹እናቱን በቁጣ ተናገራት› የሚለው አስተሳሰብም እንዲሁ ብዙ የሚያመጣው ጣጣ አለ፡፡ ‹‹እናትና አባትህን አክብር›› ‹‹እናቱን የሰደበ ይሙት›› የሚለውን ሕግ የሠራ አምላክ ‹እኔን ምሰሉ› እያለ ለሰው ልጆች አርኣያ ሊሆን በመጣበት በዚህ ዓለም ራሱ እናቱን በአደባባይ በሰው ፊት ያቃልላታል ብሎ ማሰብ እጅግ ከባድና ለብዙ ሰዎች የኃጢአትን በር ወለል አድርጎ ከፍቶ መረን የሚለቅ ነው፡፡ (ዘጸ. ፳፥፲፪ ፣ ፳፩፥ )

እመቤታችንን የጎዱ መስሏቸው ‹ጌታ እናቱን ተቆጣ› ብለው የሚሰብኩ ሰዎችም ሳያውቁት እየተናገሩ ያሉት በእመቤታችን ላይ ሳይሆን በራሱ በጌታችን ላይ ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ማን ነው?›› ብሎ የተናገረ ንጹሐ ባሕርይ ነው፡፡ (ዮሐ. ፰፥፵፮) ‹የሚጤስን የጧፍ ክር የማያጠፋ ፣ የተቀጠቀጠ ሸንበቆን የማይሰብር› በአነጋገሩ ጭምት ነው፡፡ ስንክሳሩም ‹‹ወንድሜ ምእመን ሆይ ጌታችን ለንጽሕት እናቱ ለድንግል ማርያም ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ጊዜዬ ገና አልደረሰም በማለቱ የክብርት እናቱን ቃል እንዳቃለለ አታስብ›› ይላል፡፡ (ስንክ. ጥር ፲፪ ቁ. ፵)

በማስከተልም ‹‹ጌታችን የሰማያዊውና የመለኮታዊ አባቱን ክብር እንደጠበቀ ይታወቅ ዘንድ እንዲሁ ከእርስዋ ፍጹም ሥጋንና ፍጽምት ነፍስን ነሥቶ ከመለኮቱ ጋር ያዋሐደውን የእናቱን ክብር ጠበቀ፡፡ በወንጌል ይታዘዛትና ይላላካት ነበር ተብሎ እንደተጻፈ›› ይላል፡፡ (ስንክ.ጥር ፲፪ ቁ. ፵፪)

በእርግጥም ጌታችን የባሕርይ አባቱን አብን ክብር እንደጠበቀ በራሱ አንደበት ‹‹አባቴን አከብራለሁ›› ሲል ተናግሯል፡፡ (ዮሐ. ፰፥፵፱) ለእመቤታችንና ለአሳዳጊው ዮሴፍም እንዲሁ ‹‹ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ሉቃ. ፪፥፶፩) እመቤታችን በቃና ዘገሊላ ስለ ወይኑ የነገረችውም የልጅዋን መታዘዝ በልብዋ ትጠብቀው ስለነበር እና እንደሚታዘዛት ታስብ ስለነበር ነው፡፡

እስቲ ነገሩን ሌሎች ከሚያዩበት ማዕዘን ለመመልከት እንሞክር፡፡ እውነት ግን ጌታችን እናቱን ሊቆጣ የሚችልበት ምን ምክንያት ነበረው? ከላይ እንደተመለከትነው የለመነችው ስለ ራስዋ ጥቅም አይደለም፡፡ በዚያ ላይ ልመናዋ ከሚያስፈልግ ነገር ውጪ ይደረግ የተባለ አላስፈላጊ የቅንጦት ልመና አይደለም፡፡ በሰርግ ቤት ሙሽሮችን ለዕድሜ ልክ ውርደት ሊዳርግ የሚችል የወይን ጠጅ እጥረት በተከሰተበት ሰዓት ‹ወይን እኮ የላቸውም› ብሎ ማመልከት እንኳን በሩኅሩኁ አምላክ ፊት ይቅርና በእኛ በጨካኞቹ የሰው ልጆች ፊት እንኳን ሊያስቆጣ የሚችል ነገር አይደለም፡፡

የለመነችው እንደ አይሁድ ምልክት ለማየት ጓጉታ አይደለም፡፡ እንደ ፈሪሳዊያንና ሰዱቃውያን ‹አይተን እንድናምንህ ምን ምልክት ትሠራለህ?› ‹ከሰማይ ምልክት ልናይ እንወዳለን› የሚል የፈተና ጥያቄ አልጠየቀችም፡፡ (ማቴ. ፲፮፥፩ ፤ዮሐ. ፮፥፳) ተአምር የማየት ምኞት አድሮበት እንደጠየቀው እንደ ሄሮድስም በአጋጣሚው ልጠቀምና ተአምር ልይ ብላም አይደለም፡፡ (ሉቃ. ፳፫፥፰) ደግሞስ ያለ ወንድ ዘር በማኅጸንዋ አድሮ በታተመ ድንግልና ሲወለድ ያየች እናት ሌላ ምን ተአምር ሊያስደንቃት ይችላል?

የሰርጋቸው ቀን የኀዘናቸው ቀን ሊሆን ስለተቃረበ ሙሽሮች ተጨንቃ መለመንዋ እንዴት የሚያስቆጣ ሊሆን ይችላል? ያለጊዜው ስለለመነችውና ስለቸኮለች ተቆጣት እንዳንል ልመናዋን ትንሽ ብታዘገየው ኖሮ ነገሩ ይፋ እየሆነ ፣ ሙሽሮቹ መዋረዳቸው ነው፡፡ ስለዚህ የደረሰችው በሰዓቱ ነው፡፡

የጌታችን አሠራር እንዲህ አልነበረም፡፡ የቅዱስ ጴጥሮስ አማት በንዳድ በታመመች ጊዜ እንዲፈውሳት ሲለምኑት እሺ ብሎ ንዳዱን ገሥፆ አላቀቃት፡፡ (ሉቃ.፬፥፴፱) የአንድ መቶ አለቃ ልጅ በታመመ ጊዜ የአይሁድ ሽማግሌዎች ሊያማልዱ በመቶ አለቃው ተልከው መጡ፡፡ ጌታችን ከይሁዳ ነገድ መሆኑን በማሰብም ‹‹ይህን ልታደርግለት ይገባዋል፤ ሕዝባችንን ይወዳልና ምኵራብም ራሱ ሠርቶልናል ብለው አጽንተው ለመኑት። ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ሄደ።›› የመቶ አለቃውንም ልጅ በመጨረሻ ፈወሰው፡፡ (ሉቃ. ፯፥፪-፮) እነዚህ ሰዎች ተአምር እንዲያደርግ ሲጠይቁት እሺ ያለ ጌታ እናቱ ስትለምነው ይቆጣል ብለን እንዴት እንቀበል? የአይሁድን ሽማግሌዎች እንኳን ያልተቆጣውን ጌታ በምን አንደበታችን እናቱን ተቆጣ ልንለው ይቻለናል?

ከሁሉ በላይ ቅዱስ ዳዊት ‹‹ጸሎቴን ያልከለከለኝ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን›› እንዳለው በረከሰ አንደበታችን ፣ በሚወላውል ልባችን ፣ በሚባክን ሃሳባችን ወደ እርሱ የምንጸልየውን የእኛን የኃጢአተኞቹን ጸሎት ለምን ጸለያችሁ ብሎ ያልከለከለ አምላክ ንጽሕት እናቱ በፍጹም ትሕትና ለለመነችው ልመና የቁጣ ምላሽ ሠጠ ማለት እንዴት እንደፍራለን? ዳዊት ‹‹በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማኝ የልመናዬን ድምፅ አደመጠ›› ብሏል፡፡ እርሱ በልቡ በደል ስለሌለ ጌታ ከሰማው በሃሳብዋ ድንግል የሆነች እናቱን እንዴት አልሰማትም እንላለን? (መዝ. ፷፮፥፲፱-፳)

እመቤታችን የጠየቀችው ይህን ያህል የማይጠየቅ ነገር ነው እንዴ? የመንግሥትህን እኩሌታ ፣ የሥልጣንህን ፈንታ ሥጠኝ አላለችውም፡፡ የጠየቀችው ስለ ድሆቹ ሙሽሮች ነው፡፡ እኛ በረባ ባልረባው ስንዘበዝበው የምንውለውና የምናድረው ታጋሽ አምላክ ለእናቱ ለእኛ የሠጠውን ነገር ይነሣል ማለት ፈጽሞ አይታሰብም፡፡ ‹አብን አሳየንና ይበቃናል› ፤ ‹እሳት ከሰማይ ወርዶ ሕዝቡን ያጥፋቸው› ፤ ‹በግራ ቀኝህ አስቀምጠን› የሚሉ ደቀ መዛሙርትን ታግሶ ለሦስት ዓመት ከሦስት ወራት ያስከተለ ጌታ ቅድስት እናቱ ተገቢ ልመና በተገቢ ሰዓት ስትለምነው ሊቆጣ አይችልም፡፡

እንደ ወንጌሉ ብቻ ከሔድን ደግሞ እመቤታችን ከዚህ በፊትና በኋላ ምንም ነገር ስትለምነው አልተጻፈም፡፡ በወንጌል ለተጻፈው ለዚህ ብቸኛ ልመናዋም መልሱ ቁጣ ነው ብለን አምነን መቀመጥ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ፈጽሞ የሚዋጥልን ሃሳብ አይደለም፡፡ በልጅነትዋ ወልዳው ለተሰደደችው ፣ በነፍስዋ የኀዘን ሰይፍ ላለፈባት እናቱ አንዴ ብትለምነው ተቆጣ ብለን እንዴት እንናገራለን?

ጌታችን በዚህ ሰርግ ቤት እንኳንስ እንዲህ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ የሚተረጉመው ‹ከአንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ› የሚል የአክብሮት ንግግር ተናግሮ ቀርቶ ፤ ለእናቱ የተናገረው በቀጥታና በግልፅ የቁጣ ንግግር ቢሆን ኖሮ እንኳን ጾመን ጸልየን ፣ ወድቀን ተነሥተን ምሥጢራዊ ትርጉሙን እንፈልጋለን እንጂ ሰማይና ምድር ቢነዋወጥ ‹ጌታ እናቱን ተቆጣ› ብለን አናምንም!!!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ቃና ዘገሊላ ገጽ 81

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

11 Jan, 09:04


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

11 Jan, 03:38


#ቃለ_ወንጌል

03/05/2017
ማቴዎስ 2:13-ፍጻሜ


እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፥ “ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይሻዋልና ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ምድረ ግብፅ ሽሽ፤ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ኑር” አለው፤ "እርሱም በሌሊት ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ ግብፅ ሄደ። ።ከእግዚአብሔር ዘንድ “ልጄን ከግብፅ ጠራሁት” ተብሎ በነቢይ የተ ነገረው ይፈጸም ዘንድ፣ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።

ከዚህም በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተዘባበቱበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቈጣና ጭፍራዎቹን ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን ልክ ሁለት ዓመት የሆናቸውን፥ ከዚያም የሚያንሱትን፥ በቤተ ልሔምና በአውራጃዎችዋ ሁሉ የነበሩትን ሕፃናት አስገደለ። "ያንጊዜ፥ በነቢዩ በኤርምያስ የተነገረው ተፈጸመ፤ እንዲህ ሲል፦ “ራሔል ስለ ልጆችዋ ስታለቅስ ብዙ ልቅሶና ዋይታ በራማ ተሰማ፣ መጽናናትንም እንቢ አለች፤ ልጆችዋ የሉምና።”

“ሄሮድስም በሞተ ጊዜ እነሆ፥ የእግዚእ ብሔር መልአክ በግብፅ ሀገር ለዮሴፍ በሕ ልም ታየው። እንዲህ ሲል፡ “የሕፃኑን ነፍስ የሚሹ ሙተዋልና፥ ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ።” እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ እስራኤል ምድር ገባ። “አርኬላኦስም በአባቱ በሄሮድስ ፋንታ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ ለመሄድ ፈራ፤ በሕልምም ተገልጦለት ወደ ገሊላ አውራጃ ሄደ። በነቢያት “ልጄ ናዝራዊ ይባላል” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ናዝሬት ወደ ምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።
 
                                    ምስባክ
                            መዝሙር 43:22-23

እስመ በእንቲአሁ ይቀትሉነ ኩሎ አሚረ

ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ

ንቃዕ እግዚኦ ለምንት ትነው

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

10 Jan, 09:04


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

10 Jan, 03:41


#ቃለ_ወንጌል

02/05/2017
ማቴዎስ 23:13-23

እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ጸሎታችሁን በማብዛት ምክንያት የመበለቶችን ገንዘብ ስለምትበሉ ወዮላችሁ! ስለዚህ ጽኑ ፍርድን ትቀበላላችሁ። እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ! እናንተም አትገቡም፤ የሚገቡትንም ከመግባት ትከለክሉአቸዋላችሁ። እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳው ያን፥ አንድን ሰው ለማሳመን ባሕሩንና የብሱን ስለምትዞሩ ወዮላችሁ! ካመነም በኋላ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የገሃነም ልጅ ታደርጉታላችሁ።

"በቤተ መቅደስ የሚምል ኀጢአት የለበትም፤ በቤተ-መቅደስ ወርቅ የሚምል ግን ይበድላል የምትሉ ዕውራን መሪዎች እናንተ ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! ”እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ የትኛው ይበልጣል? ወርቁ ነውን? ወይስ ወርቁን የሚቀድ ሰው ቤተ መቅደስ? ፤ደግማችሁም በመሠዊ ያው የሚምል አይበድልም፤ በላዩ በአለው በመ ሥዋዕቱ የሚምል ግን ይበድላል ትላላችሁ። "እናንተ ሰነፎችና ዕውራን፥ የትኛው ይበልጣል? መሥዋዕቱ ነውን? ወይንስ መሥዋዕቱን የሚቀድሰው መሠዊያው? በመሠዊያው የሚምል በእርሱ ይምላል፤ በእርሱ ላይም ባለው ሁሉ ይምላል። “በቤተ መቅደስም የሚምል በእርሱና በውስጡ በሚኖረው ሁሉ ይምላል


ምስባክ
መዝሙር 93:21-22

ወይንዕዋ ለነፍሰ ጻድቅ

ወይኴንን ደመ ንጹሐ

ወኮነኒ እግዚአብሔር ፀወንየ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

09 Jan, 10:59


+ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር+

የመጀመሪያው ሰማዕት ዲያቆን እስጢፋኖስን በግፍ ከቤተ ሳይዳ መግቢያ ከአንበሳ በር አውጥተው በድንጋይ ወግረው በግፍ እንዴት እንደገደሉት ዝርዝር ታሪኩ በሐዋርያት ሥራ ላይ ተጽፎአል:: የታሪኩ ማብቂያ ላይ ያለው ዐረፍተ ነገር እስጢፋኖስን በጭካኔ በድንጋይ ከቀጠቀጡት ሰዎች ጋር አብሮ ባይቀጠቅጠውም የሌላ አንድ ተሳታፊ ስም ተጠቅሶአል::  "ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር" (ሐዋ. 7:60)

በዚያች የምታሳዝን ዕለት ራሳቸው ከሳሽ ራሳቸው ፈራጅ የነበሩት ጸሐፍት በጭካኔ ታውረው ሆ ብለው በእስጢፋኖስ ላይ ተነሥተውበት ነበር:: በዚያ ባለ ብዙ ተስፋ ወጣት ላይ የድንጋይ ዶፍ ሲያወርዱ ትንሽ እንኳን አልዘገነናቸውም:: ይቅር በላቸው ከማለት ውጪ ክፉ ያልወጣውን ምስኪን ክርስቲያን ወጣት ያለ ርኅራኄ ቀጥቅጠው ገደሉት::

በዚያች ዕለት ሳውል ተሳትፎው ምን ነበር? እርግጥ ነው በእጁ ድንጋይ አልያዘም:: በእስጢፋኖስ ጭንቅላት ላይ ጉዳት ለማድረስ እጆቹን አላስወነጨፈም::  ነገር ግን አንድ እውነታ መካድ አይቻልም:: ሳውል በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ስለነበር በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ከእስጢፋኖስ ሞት ጋር ስሙ አብሮ ተነሥቶአል::

የሰው ልጅ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት ፍጹም አዛኝ መልአክ መሆን እንደሚችል ሁሉ ሁኔታው ከተመቻቸለት ፍጹም አውሬ የመሆን እምቅ ችሎታ ያለው ፍጡር ነው:: ጭካኔም ሆነ ርኅራኄ ከየትኛውም ዘር ብትወለድ ሊኖርህ የሚችል ነገር ሲሆን  በሕግ በሃይማኖትና በሰብአዊነት መርሆች  ካልተገታ በስተቀር የሰው ልጅ የማያደርገው ክፉ ነገር እንደሌለ የዓለም ታሪክ ያስረዳል::

በዘመናችን የምናየው የንጹሐን ግድያ ላይ በቀጥታ የሚሳተፉና ብዙ እስጢፋኖሶችን በግፍ የሚገድሉ ጨካኞች አሉ:: በሕግ የሚጠየቁትም የሚቀጡትም እንደዚህ ያሉት ቀጥተኛ ተሳታፊዎች ናቸው::

ሆኖም በእኛ ሀገር በቁጥር እጅግ የሚበዙት እስጢፋኖስ ላይ ድንጋይ ከወረወሩት አይሁድ ይልቅ በእስጢፋኖስ መገደል የተስማሙት ሰዎች ናቸው:: ከሩቅ ሆኖ "ተነሣ በለው" ማለት ያም ባይሆን "እዚህ ሰፈር ሰው ተገደለ" ሲባል "እዚያ ሰፈርስ ሞቶ የለ ወይ?" እያሉ ለማካካስ መሞከር : ይበለው ይበላት ብሎ መናገርም በእስጢፋኖስ መገደል መስማማት ነው::

ወዳጄ በክፋት ውስጥ በቀጥታ መሳተፍም : ከሩቅ ሆኖ ቃላት መወራወርም : ጥላቻን መዝራትም : ሌላውን እየናቁ ራስን መኮፈስም ዞሮ ዞሮ በፈጣሪ ፊት ስለ ንጹሐን ደም ማስጠየቁ አይቀርም::

እስጢፋኖስን የመሰሉ በግፍ የተገደሉ ሁሉም ሰማዕታት በፈጣሪ ዙፋን ፊት ቆመው "እስከመቼ አትፈርድም?" ማለታቸው ስለማይቀር ሳናውቀው ዕዳ በራሳችን ላይ እንዳናከማች ከየትኛውም የጥላቻ ንትርክ ራሳችንን እናውጣ::

እስጢፋኖስ ሲገደል ሳውል የተስማማ ቢሆንም በመጨረሻ ግን "ይቅር በላቸው" በሚለው የእስጢፋኖስ ጸሎት ምክንያት በክርስቲያኖች መገደል ከመስማማት ወጥቶ በክርስትናው መከራ የተቀበለ ሐዋርያ ሆነ::
በጣም የሚደንቀው የእስጢፋኖስን ቤተሰቦችም ያጠመቀው በልጃቸው መገደል ተስማምቶ የነበረው ሳውል (ጳውሎስ) ነበረ:: የልጃችን ደም አለበት ሳይሉ ይቅር ብለው የተጠመቁት ጥፋትን በጥፋት ማረም እንደማይቻል ተረድተው ነበር:: ክርስትና ዘር ቆጥሮ የእኔን ወገን እንዲህ አድርገሃል ብሎ የመበቀል ሕይወት ሳይሆን
ባለፈ የጥላቻ ቁስል ማነከስን ትቶ በይቅርታ ዛሬና ነገን መኖር ነው:: ለትውልድ ቂም ማውረስ ለልጅ መርዝ ከማጠጣት አይተናነስም : ይቅርታን ማስተማር ግን ለልጅ በሰማይም በምድርም ርስት እንዲያገኝ ማድረግ ነው::

ኢትዮጵያ እግር አውጥታ ከእኛ እንዳትሸሽ እነዚህ ሦስት ነገሮች ከእንግዲህ በሀገራችን አይኑሩ

- በግፍ የሚገደል እስጢፋኖስ
- በግፍ የሚገድሉ ፈሪሳውያን
- በእስጢፋኖስ መገደል የሚስማሙ ሳውሎች

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሐምሌ 9 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

09 Jan, 09:03


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

09 Jan, 02:59


#ቃለ_ወንጌል

01/05/2017
ማቴዎስ 21:33-ፍጻሜ


“ሌላ ምሳሌ ስሙ፤ ባለቤት ሰው ወይንን ተክለ፡ ቅጥርም ቀጠረለት፤ መጭመቂያም አስቆፈረለት ግንብም ሠራለት፤ ለገባሮችም ሰጥቷአየው ሄደ የሚያፈራበት ወራት በደረሰ ጊዜም፥ ከወይኑ ፍሬ ያመጡለት ዘንድ አገልጋዮችን ወደ ገባሮቹ ላከ። ገባሮቹም አገልጋዮ ቹን ይዘው፥ አንዱን በበትር ደበደቡት፤ አንዱንም ገደሉት፤ ሌላውንም በድንጋይ መቱት። ከዚያም በኋላ ከቀደሙት የሚበዙ ሌሎች አገልጋዮችን ላከ፤ እነርሱንም እንዲሁ አደረጉባቸው። በኋላም ልጄንስ ይፈሩት ይሆናል ብሎ ልጁን ላከ። ገባሮቹም ልጁን ባዩት ጊዜ እርስ በርሳቸው፦ እነሆ፥ ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ እንግደለውና ርስቱን እንውረስ ተባባሉ። ይዘውም ከወይኑ ቦታ ወደ ውጭ አውጥተው ገደሉት። “እንግዲህ የወይኑ ቦታ ባለቤት በመጣ ጊዜ እነዚህን ገባሮች ምን ያደርጋቸዋል?” እነርሱም፥ “ክፉዎችን በክፉ ያጠ ፋቸዋል፤ ወይኑንም በየጊዜው ፍሬውን ለሚሰ ጡት ለሌሎች ገባሮች ይሰጣል” አሉት።

ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፡ “በመጻሕፍት ያለውን ያነበባችሁበት ጊዜ የለ ምን? ግንበኞች የናቁአት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ሆነች፤ ይህቺም ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆነች፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ናት። "ስለዚህም እላ ችኋለሁ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች፤ ፍሬዋንም ለሚያደርጉ ለአሕዛብ ትሰጣለች። በዚያችም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፤ በላዩ የምትወድቅበትንም ትፈጨዋለች።

የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ምሳሌዎቹን በሰሙ ጊዜ፥ ስለ እነርሱ እንደተናገረ ዐወቁ። ሊይዙትም ሲፈልጉ ሕዝቡን ፈሩአቸው፤ በእነርሱ ዘንድ እንደ ነቢይ ነበርና


ምስባክ
መዝሙር 20:3-4

እስመ በጻሕኮ በበረከት ሠናይ

ወአንበርከ አክሊለ ዲበ ርእሱ ዘእምዕንቍ ክቡር

ሐይወ ሰአለከ ወወሀብኮ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

08 Jan, 09:02


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

08 Jan, 03:10


#ቃለ_ወንጌል

30/04/2017
ማቴዎስ 2:1-13


በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በይሁዳ ክፍል በቤተ ልሔም ጌታችን ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። (እንዲህ ሲሉ፥ “ኮከቡን በምሥራቅ አይተን እንሰግድለት ዘንድ መጥተናልና፥ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?” ንጕሥ ሄሮድስም በሰማ ጊዜ ደነገጠ፤ ኢየሩሳሌምም በመላዋ ከእርሱ ጋር ደነገጠች። 'የካህናት አለቆችንና የሕዝቡን ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ “ክርስቶስ በየት ይወለዳል?” ብሎ ጠየቃቸው። እንዲህም አሉት፤ “በይሁዳ ክፍል በቤተልሔም ነው፣ በነቢይ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና። የይሁዳ ምድር፥ አንቺ ቤተ ልሔም ከይሁዳ አለቆች፤ ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራ ኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና።”

'ከዚህም በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠራቸው፤ ኮከቡ የታየበትንም ዘመን ከእነርሱ ተረዳ። “ሂዳችሁ የዚያን ሕፃን ነገር ርግጡን መርምሩ ያገኛችሁትም እንደሆነ እኔም መጥቼ እሰግድለት ዘንድ በእኔ በኩል ተመልሳችሁ ንገሩኝ” ብሎ ወደ ቤተ ልሔም ሰደዳቸው። "እነርሱም ከንጉሡ ሰምተው ሄዱ፣ እነሆ፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ በአለበት ቦታ ላይ ደርሶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር። ኮከቡንም አይተው ታላቅ ደስታ ደስ አላቸው። “ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አገኙት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው ወርቅና ዕጣን፥ ከርቤም፥ እጅ መንሻ አቀረቡለት። ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ነገራናቸው፤ በሌላ መንገድም ወደ ሀገራቸው ሄዱ



ምስባክ
                         መዝሙር 78:10-11

👉   ወይርአዪ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ

       በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ

       ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

07 Jan, 07:22


አእላፋት

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

06 Jan, 21:21


🎆እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ🔔🎉

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

06 Jan, 11:30


💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
ሥርዓተ ማኅሌት ዘልደት
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአጻብኢክሙ እለ እምአጽፋር ኢይትሌለዩ፤ ለቤትክሙ ሥላሴ ዘኢየኃልቅ ንዋዩ፤ አመ አብዓልክሙ ሰብአ ድኅረ አንደዩ ጌጋዩ፤ ዘኢርእዩ እምቅድመ ዮም መላእክተ ሰማይ ርእዩ፤ ወአግብርተ ሰብእ መላእክት ተሰምዩ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ርእይዎ ኖሎት አእኮትዎ መላእክት፤ ለዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ።
@EOTCmahlet
ወረብ
'ርእይዎ ኖሎት'/፪/ አእኮትዎ መላእክት/፪/
ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል/፪/
@EOTCmahlet
ዘጣእሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፤ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ።
@EOTCmahlet
ነግሥ
ሰላም ለልደትከ ኦ አማኑኤል፤ ዘቀዳሚ ወዘደኃሪ ብሉየ መዋዕል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘአብ ቃል፤ እፎ እፎ አግመረተከ ድንግል፤ ወእፎ እንዘ አምላክ ሰከብከ በጎል።
@EOTCmahlet
ዚቅ
በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ፤ ውስተ ማኅጸነ ድንግል ኃደረ፤ እፎ ተሴሰየ ሀሊበ ከመ ሕፃናት።
@EOTCmahlet
ወረብ
በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ ኃደረ ማኅጸነ ድንግል/፪/
እፎ 'ተሴሰየ'/፪/ ሀሊበ ከመ ሕፃናት ተሴሰየ/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ ኢየሱስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሐላ ዘኢይሔሱ፤ ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሱ፤ አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቄጸል በርእሱ፤ አህጉረ ፀር ወረሰ ኢያሱ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ንሰብከ ወልደ እምዘርዓ ዳዊት ዘመጽአ፤ ወተወልደ በሥጋ ሰብእ፤ እንዘ ኢየዓርቅ እመንበረ ስብሐቲሁ፣ ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኀደረ ሥጋ ኮነ ወተወልደ፤ ትጉኃን የአምኑ ልደቶ፤ ወሱራፌል ይቀውሙ ዓውዶ፤ መጽአ ይቤዝወነ ውስተ ዓለም የሀበነ ሰላመ፤ ጋዳ ያበውዑ ቁርባነ።
@EOTCmahlet
ወረብ
'ውስተ ማኅጸነ ድንግል ኃደረ'/፪/ ሥጋ ኮነ/፪/
ወተወልደ በሥጋ ሰብእ ሥጋ ሰብእ በሥጋ ሰብእ/፪/
@EOTCmahlet
ዘበአታ፦
ወልድ ተወልደ መድኃኒነ ፤ጥዩቀ እምዘርዓ ዳዊት፤ በቤተልሔም ዘይሁዳ
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ወልድ ተወልደ መድኃኒነ ጥዩቀ ወልድ ተወልደ
እምዘርዓ ዳዊት ቤተልሔም በቤተልሔም

@EOTCmahlet
መልክአ ኢየሱስ
ሰላም ለአጽፋረ እዴከ ዘኅበሪሆን ፀዓዳ፤ በምገባር ወግእዝ እለ ይትዋሐዳ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስፍና አባሉ ለይሁዳ፤ ለመንግሥትከ ሰፋኒት እንዘ ይትመሐለሉ ዓውዳ፤ ሰብአ ሰገል አወፈዩ ጋዳ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
አንፈርዓጹ ሰብአ ሰገል፤ አምኃሆሙ አምጽኡ መድምመ፤ ረኪቦሙ ሕፃነ ዘተወልደ ለነ።
@EOTCmahlet
እመላለስ፦
አንፈርዓጹ ሰብአ ሰገል/፬/
አምኃሁ አምጽኡ መድምመ/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ ኢየሱስ
እምኲሉ ይኄይስ በሥላሴከ ተአምኖ፤ ወበወላዲትከ ተማኅፅኖ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ እምቤተ መንግሥት ወተክህኖ፤ ተሰብኦትከ እመቦ ዘያስተሐቅር መኒኖ፤ ያንኮርኲር ታሕት ደይን ግዱፈ ከዊኖ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ወካዕበ ተማኅፀነ በማርያም እምከ፤ እንተ ይእቲ እግዝእትነ፤ ወትምክሕተ ዘመድነ በወሊዶተ ዚአከ።
@EOTCmahlet
ወረብ
'ትምክሕተ ዘመድነ'/፪/ በወሊዶተ ዚአከ/፪/
ይእቲ 'እግዝእትነ'/፪/ ማርያም ድንግል/፪/
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
ኦ ዝ መንክር በዘዚአኪ አምሳል፤ ኮከበ ትንቢት ዘቦቱ መልክአ ሕፃን ሥዑል፤ ሠረቀ ያርኢ ተአምረኪ ድንግል፤ ወመርሖሙ ለሰብአ ሰገል እምርሑቅ ደወል፤ ጽጌኪ ኀበ ሀሎ ይሰክብ በጎል።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ወኖሎት በቤተ ልሔም፤ አንከሩ እምዘርእዩ ወሰምዑ፤ ሰብአ ሰገል ርእዮሙ ኮከበ፤ መጽኡ እምርኁቅ ብሔር፤ ከመ ይስግዱ ለወልድኪ ወይግነዩ ለኪ።
@EOTCmahlet
ወረብ
በኮከብ መጽኡ ሰብአ ሰገል/፪/
ይስግዱ ለአማኑኤል ይስግዱ/፪/
@EOTCmahlet
አንገርጋሪ
ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ፤ እምቅድስት ድንግል፤ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ዘሎቱ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ፤ አማን፤ መንክር ስብሐተ ልደቱ።
@EOTCmahlet
አመላለስ
'አማን በአማን'/፪/ መንክር 'አማን በአማን'/፪//፩/
መንክር ስብሐተ ልደቱ/፬/
@EOTCmahlet
ወረብ
ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ/፪/
እምቅድስት 'ድንግል'/፪/ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ/፪/
@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም
ተወልደ ኢየሱስ በቤተ ልሔም ዘይሁዳ፤ አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ፤ ሰብአ ሰገል አምጽኡ ሎቱ ጋዳ፤ ወይትኃሠያ አዋልደ ይሁዳ።

አመላለስ፦
ሰብአ ሰገል አምጽኡ ሎቱ ጋዳ፤[፪]
ወይትኃሠያ አዋልደ ይሁዳ።[፬]
@EOTCmahlet
ወረብ
ተወልደ ኢየሱስ 'በቤተ ልሔም'/፪/ ዘይሁዳ በቤተ ልሔም/፪/
አዋልደ ጢሮስ 'አሜሃ ይሰግዳ'/፪/ በቤተ ልሔም/፪/
@EOTCmahlet
ዕዝል
በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ፤ ውስተ ማኅጸነ ድንግል ኃደረ፤ ዮም ተወልደ፤ እግዚእ ወመድኅን፤ ቤዛ ኲሉ ዓለም።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አመላለስ
ቤዛ ኲሉ ዓለም ዮም ተወልደ/፪/
'ቤዛ ኲሉ ዓለም'/፪/ ዮም ተወልደ/፬/
@EOTCmahlet
ሰላም
ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ፤ ንሰብክ ወልደ እምዘርዓ ዳዊት ዘመጽአ፤ ወተወልደ በሥጋ ሰብእ፤ እንዘ ኢየዓርቅ እመንበረ ስብሐቲሁ፤ ውስተ ማኅጸነ ድንግል ኃደረ ሥጋ ኮነ ወተወልደ፤ ትጉሃን የአምኑ ልደቶ፤ ወሱራፌል ይቀውሙ ዓውዶ፤ መጽአ ይቤዝወነ ውስተ ዓለም የሀበነ ሰላመ፤ ጋዳ ያበውዑ ቁርባነ።

🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

@EOTCmahlet
#Join & share

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

06 Jan, 09:05


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

06 Jan, 06:35


🌟🌟🌟በገና አባት የተሸፈነ ቅዱስ አባት🌟🌟🌟

+++ቅዱስ ኒቆላዎስ ገባሬ መንክራት (St.Nicholas the wonder worker)+++

ቅዱስ ኒቆላዎስ (St.Nicholas-Santa Claus) በሮማ መንግስት ዘመን በኤዥያ ውስጥ በምትገኝ ሜራ በምትባል አገር (የአሁኗ ቱርክ) ግሪካዊ ከሆኑ ክርስቲያን ቤተሰቦቹ ተወለደ፡፡ የዚህም ቅዱስ እናቱ ጦና (Tona) አባቱ ኤጲፋንዮስ ይባላሉ፡፡ እኒህም እግዚአብሔርን የሚፈሩና ባለጠጎችም ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከሞቱ በኋላ ንብረታቸውን የሚያወርሱት፣ ለልባቸውም ደስታን የሚመግብ ልጅ አልነበራቸውም፡፡ ዕድሜያቸው እየገፋ በመምጣቱም ምክንያት በተስፋ መቁረጥ ተከበው ይኖሩ ነበር፡፡ በልብ መታሰቡ በቃል መነገሩ ከፍ ከፍ ያለ አምላክ በእርጅና ዘመናቸው ልክ ጻድቁ ዘካርያስና ሚስቱ ኤልሳቤጥን እንደጎበኘ እነርሱንም በቸርነቱ ጎበኛው፡፡ ቅዱስ የሆነም ልጅን ሰጣቸው፡፡ ይህም ልጅ ገና ታናሽ ሳለ መንፈሰ እግዚአብሔር የሞላበት ነበር፡፡ ዕድሜውም ለትምህርት በደረሰ ጊዜ ዕውቀትና ጥበብን ይቀስም ዘንድ ወደ መምህራን የተላከ ቢሆንም፣ ከመምህሩ ከተማረው ይልቅ ከመንፈስ ቅዱስ የተረዳው ይበልጥ ነበር፡፡

መሠረታዊ የሆኑትን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርቶች በልጅነቱ ተምሮ በማጠናቀቁ በዲቁና መዓርግ ተሾመ፡፡ በኋላም የአጎቱ ልጅ አበምኔት በሆነበት በአንዱ ገዳም አርዑተ ምንኩስናን (የምንኩስናን ቆብ) ጭኖ የቅድስና እና የትሕርምት ሕይወትን ኖሯል፡፡ በአሥራ ዘጠኝ ዓመቱም የቆሞስነትን መዓርግ አግኝቷል፡፡

ለዚህም ቅዱስ አባት እግዚአብሔር ተአምር እና ድንቅን የማድረግ ፤ሕሙማንንም የመፈወስ ታላቅ ጸጋ ሰጥቶታል፡፡

#ለጋስ (የስጦታ) አባት

በሜራ ከተማ የሚኖር ቀድሞ ባለጠጋ የነበረ በኋላ ግን ሃብት ንብረቱን ያጣ አንድ ሰው ነበረ፡፡ በድህነቱ ምክንያት ሊድራቸው ያልቻለ ሦስት ዕድሜያቸው ለጋብቻ የደረሱ ሴቶች ልጆች ነበሩት፡፡ ሰይጣንም እነዚህን ልጆቹን በዝሙት ሥራ ገንዘብ እየሰበሰቡ ሕይወታቸውን እንዲመሩ ያደርጋቸው ዘንድ ክፉ ሐሳብን በሕሊናው አመጣበት፡፡ እግዚአብሔርም በዚህ ሰው ልቡና ውስጥ ሰይጣን የተከለበትን ክፉ ሐሳብ እና ምን ሊያደርግ እንደተነሣሣ ለቅዱስ ኒቆላዎስ ገለጠለት፡፡

     ቅዱስ ኒቆላዎስም የእናት የአባቱ ገንዘብ ከሆነው ላይ መቶ ዲናር ወስዶ በስልቻ (sack) ጠቅልሎ ማንም ሳያየው በምሽት ወደዚያ ደሃ ሰው ቤት በመሄድ በመስኮት በኩል ወረወረለት፡፡ ያም ደሃ ከየት እንደመጣ ያላወቀውን 100 ዲናር በቤቱ ባገኘ ጊዜ ተደነቀ አምላኩንም አመሰገነ፡፡ ያሰበውንም ክፉ ሐሳብ ተወ። በገንዘብ እጦት ምክንያትም ከትዳር የዘገየችውን የመጀመሪያ ልጁን ዳረ፡፡ በሌላም ቀን ቅዱስ ኒቆላዎስ ሁለተኛ ልጁን መዳር ይችል ዘንድ፣ አሁንም ተጨማሪ መቶ ዲናር ገንዘብ በጥቅል ስልቻ አድርጎ በመስኮቱ በኩል ወረወረለት፡፡ ይህንንም ገንዘብ ዳግመኛ በቤቱ ያገኘው ደሃ ሰው እንዲህ ያለውን ቸርነት በስውር የሚያደርገው ምን ዓይነት ሰው እንደሆነ አይቶ ያውቅ ዘንድ ጉጉት አደረበት፡፡ ቤቱንም በንቃት መከታተል ጀመረ፡፡

ቅዱስ ኒቆላዎስም እንደ ለመደው ለሦስተኛ ጊዜ መቶውን ዲናር የያዘውን ስልቻ በመስኮት ሲወረውር ወዲያው ተዘጋጅቶ ይጠብቀው የነበረው ሰው ፈጥኖ በሩጫ ከቤቱ ወጣ። ሊያየው ይመኘው የነበረ ያንንም ቸር ሰው ሊቀ ጳጳሱ ኒቆላዎስ ሆኖ አገኘው፡፡ ከእግሩ ስርም ተደፍቶ ልጆቹን ከድህነት እና ከኃጢአት ሕይወት ስለታደገለት ሊያመሰግነው ቢሞክርም ቅዱስ ኒቆላዎስ ግን ምስጋናውን እምቢ አለ፡፡ ይህን ሐሳብ በልቡ ያኖረ እግዚአብሔርንም ያመሰግን ዘንድ ለመነው፡፡

        ከዚህ ታሪክ በተጨማሪም ለሕፃናት እና ለተቸገሩ ሰዎች ያደረገው ልግስና የብዙ ብዙ ነው። ለዚህም ይመስላል በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት መታሰቢያውን በልግስና የሚያከብሩት። 

       በአጠቃላይ ይህ ቅዱስ አባት በዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ ስለ እምነቱ ብዙ ስቃይ እና እስራት ደርሶበታል፡፡ ፋታ በማይሰጥ መከራ እና ግርፋት ውስጥ እያለ የራሱን ሕመም ከማዳመጥ ይልቅ በውጪ ላሉ ለልጆቹ ምዕመናን የሚያበረታታ እና በእምነታቸው እንዲጸኑ የሚያደርግ መልእክትን ይጽፍላቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ኒቆላዎስ በ325 ዓ.ም ለአውግዞተ አርዮስ ከተበሰቡት 318ቱ ሊቃውንት መካከል አንዱ የነበረ የዚህች ኦርቶዶክሳዊት እምነት ባለውለታ ነው፡፡ ከአርባ ዓመታት በላይ በሊቀ ጵጵስና መንበር በጎቹን ከነጣቂ ተኩላ እየጠበቀ ቤተ ክርስቲያንን ካገለገለ በኋላ በሰማንያ ዓመቱ አርፏል፡፡

(ቅዱስ ኒቆላዎስ በእኛ (በኢትዮጽያ) የስንክሳር መጽሐፍ ላይ የእረፍቱ መታሰቢያ የሚያዝያ ወር በገባ በአስራ አምስተኛው ቀን እንደሆነ ተመዝግቧል፡፡ ኒቆላዎስም ማለት ‹መዋኤ ሕዝብ - ሕዝብን የሚያሸንፍ› ማለት ነው።)

       የልደት በዓል እግዚአብሔር አብ ልጁን ለዓለም የሰጠበት በመሆኑ ‹የሥጦታ በዓል› በመባል ይጠራል፡፡ ይህንንም በማሰብ ለድሆች በመራራት ለተቸገሩት ቸርነት በማድረግ እናከብረው ዘንድ ምሳሌ እንዲሆነን ቅዱስ ኒቆላዎስን እናስባለን፡፡ ምንም ዓለም አፈ ታሪክ አድርጋ ብታወራውም፣ የዚህንም ቅዱስ ማንነት እንዳይታወቅ በፈጠረቻቸው ተረቶች ብታጠለሸውም እኛ ግን የ‹ገና አባት› ብላ ከሰየመቻቸው የፈጠራ ሰው ጀርባ እውነተኛ የሆነውን ይህን ቅዱስ አባት እናስበዋለን፡፡

+++++ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛ ኃጢአተኞቹንም በዚህ ጻድቅ ሰው ጸሎት ይማረን!!!+++

ምንጭ:– -መጽሐፈ ስንክሳር
              -Coptic synaxarium

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

06 Jan, 03:10


#ቃለ_ወንጌል

28/04/2017
            ማቴዎስ 1
:1-18

     የዳዊት ልጅ፥ የአብርሃም ልጅ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ መጽሐፍ፤ ፤አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ። 'ይሁዳም ከትእማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮምም አራምን ወለደ። አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ። ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ። ፤እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ።

፤ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤ ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓ ምም አብያን ወለደ፤ አብያም አሳፍን ወለደ። አሳፍም ኢዮሳፍጥን ወለደ፤ ኢዮሳፍጥም ኢዮ ራምን ወለደ፤ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ። ፤ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤ አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ። ፤ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፤ ምናሴም አሞጽን ወለደ፤ አሞጽም፤ ኢዮስያስን ወለደ። “ኢዮስ ያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ።

  ከባቢሎን ምርኮም በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ። “ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ፤ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ። አዛርም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ።  ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማትያንን ወለደ፤ ማትያንም ያዕቆብን ወለደ።  ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለ ጌታ ኢየሱስ ከእርስዋ የተወለደ የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ።

እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት ዐሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ ዐሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ ዐሥራ አራት ትውልድ ነው። ትውልድም ሁሉ ከአ ብርሃም እስከ ክርስቶስ ዐርባ ሁለት ትውልድ ነው


                                ምስባክ
    መዝሙር 75:15-16


የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቀ ዓረብ

ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ

ወኵሎ ዓሚረ ይድኅርዎ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

05 Jan, 09:05


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

05 Jan, 03:24


#ቃለ_ወንጌል

     ዮሐንስ 10:1-22

    “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ወደ በጎች ስፍራ በበሩ የማይገባ፥ በሌላም በኩል የሚ ገባ ሌባ፥ ወንበዴም ነው። በበሩ የሚገባ ግን የበጎች ጠባቂ ነው። ለእርሱ በረኛው ይከፍ ትለታል፤ በጎቹም ቃሉን ይሰሙታል፤ እር ሱም በጎቹን በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ አው ጥቶም ያሰማራቸዋል። ሁሉንም አውጥቶ ባሰማራቸው ጊዜ በፊት በፊታቸው ይሄዳል፤ በጎ ቹም ይከተሉታል፤ ቃሉን ያውቃሉና። ሌላውን ግን ይሸሹታል እንጂ አይከተሉትም፤ የሌ ላውን ቃሉን አያውቁምና። ጌታችን ኢየሱ ስም ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገ ራቸውን አላወቁም። ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ እንዲህ አላ ቸው፥ እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ የበጎች በር እኔ ነኝ። ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ነገር ግን፣ በጎች አልሰሙአቸውም። እውነተኛዉ የበጎች በር እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩልም የሚገባ ይድናል፤ ይገ ባልም ይወጣልም፤ መሰማርያም ያገኛል። ፤ሌባ ግን ሊሰርቅና ሊያርድ፥ ሊያጠፋም ካልሆነ በቀር አይመጣም፤ እኔ ግን የዘለዓለም፤ ሕይ ወትን እንዲያገኙ፥ እጅግም እንዲበዛላቸው መጣሁ።

“ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍሱን ይሰጣል።ጠባቂያይደለ፥ በጎቹም ገንዘቡ ያይደሉ ምንደኛ ግን፥ ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም መጥቶ በጎቹን ይነጥቃቸዋል፥ ይበትናቸዋ ልም። ምንደኛስ ይሸሻል፤ ስለ በጎቹም አያዝንም፤ ምንደኛ ነውና። "ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆኑትን መንጋዎቼን አውቃለሁ፤ የእኔ የሆኑትም ያውቁኛል። አብ እኔን እንደሚያው ቀኝ እኔም አብን አውቀዋለሁ፤ ለበጎችም ቤዛ አድርጌ ሰውነቴን አሳልፌ እሰጣለሁ። ከዚህ ቦታ ያይደሉ ሌሎች በጎችም አሉኝ፤ እነር ሱንም ወደዚህ አመጣቸው ዘንድ ይገባኛል፤ ቃሌንም ይሰሙኛል፤ ለአንድ እረኛም አንድ መንጋ ይሆናሉ።

”ስለዚህም፤ አብ ይወድደ ኛል፥ እንደ ገና አስነሣት ዘንድ እኔ ነፍሴን እሰ ጣለሁና። *ከእኔ ማንም አይወስዳትም፤ ነገር ግን እኔ በፈቃዴ እሰጣታለሁ፤ እኔ ላኖራት ሥልጣን አለኝ፤ መልሼ እወስዳት ዘንድ ሥልጣን አለኝና፤ ይህንም ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበ ልሁ።” አይሁድ ለሁለተኛ ጊዜ ስለ መለያየታቸው "ስለዚህም ነገር አይሁድ እንደገና እርስ በር ሳቸው ተለያዩ። “ከእነርሱም ብዙዎች፥ “ጋኔን ይዞት ያብዳል፤ ለምንስ ታዳምጡታላችሁ?” አሉ። ሌሎችም ይህ ነገር ጋኔን ከያዘው ሰው የሚገኝ አይደለም፤ ጋኔን የዕዉሮችን ዐይን ማብራት ይችላልን?” አሉ።

ምስባክ
መዝሙር 78:1-2

ኖላዊሆሙ ለእስራኤል ለእስራኤል አጽምዕ

ዘይርዕዮሙ ከመ አባግዐ ዮሴፍ


ዘይነብር ላዕለ ኪሩቤል አስተርእየ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

04 Jan, 10:20


#ኢየሱስ_ክርስቶስ

ሳትደክም ሁሉን ትሸከማለህ ፣ ሳታጎድል ለሁሉ ትመግባለህ ፣ ዝም ሳትል ለሁሉ ታስባለህ።

ሳትጎድል ለሁሉ ትሰጣለህ ፣ ሳትነጥፍ ለሁሉ ታረካለህ  ፣ ሳትዘነጋ ሁሉን ታስባለህ።

ሳትተኛ ሁሉን ትጠብቃለህ ፣ ቸል ሳትል ሁሉን ትሰማለህ ፣ ሳትቀበል ለሁሉ ትሰጠዋለህ።

ባዕድ የማይሰጠው ክቡር ፣ የማያዙት ፈጣሪ ፣ የማይሾሙት ንጉስ ፣ የማይነቅፉት ጌታ ፣ የማያበድሩት አምላክ ፣ የማይሰጡት ባለጸጋ ፣ ኸማያልቅው ገንዘቡ 
የሚሰጣ።

ቅዳሴ_ዮሐንስ_ወልደነጎድጓድ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

04 Jan, 09:05


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

04 Jan, 04:31


#ቃለ_ወንጌል

26/04/2017
ማቴዎስ 25:1-14


ያንጊዜም መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ለመቀበል የወጡ ዐሥሩን ደናግል ትመስላለች። ከእነርሱም ውስጥ አምስቱ ሰነፎች፥ አምስቱም ልባሞች ነበሩ። ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ዘይት አልያዙም ነበር። ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮቻቸው ዘይት ይዘው ነበር። ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉም አንቀላፉና ተኙ። መንፈቀ ሌሊት በሆነም ጊዜ “እነሆ ሙሽራ መጣ፤ ልትቀበሉት ውጡ” የሚል ጩኸት ሆነ። ያንጊዜ እነዚያ ደናግል ሁሉ ነቁና መብራታቸውን አዘጋጁ። እነዚያ ሰነፎችም ልባሞችን፦ መብራታችን ሊጠፋብን ነውና ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው። ልባሞ ችም፦ ለእኛና ለእናንተ የሚበቃ የለም፤ ነገር ግን ወደሚሸጡ ሂዱና ለራሳችሁ ግዙ ብለው መለሱላቸው። ሊገዙም እንደ ሄዱ ሙሽራው መጣ፤ እነዚያም የተዘጋጁት ከእርሱ ጋር ወደ ሰርጉ ገቡ፤ ደጁም ተዘጋ። በኋላም እነዚያ ደናግል መጥተው፦ አቤቱ አቤቱ ክፈትልን አሉ። እርሱ ግን መልሶ፦ እውነት እላች ጓለሁ፤ አላውቃችሁም አላቸው። "እንግዲህ ትጉ፤ የሰው ልጅ የሚመጣባትን ቀኒቱንና ሰዓ ቲቱን አታውቁምና
::

                ምስባክ
            መዝሙር 44:9-10

አዋልደ ንግሥት ለክብርከ

ወትቀውም ንግሥት በየማንከ

በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት

              ትርጉም

የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው

በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና፡

ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

03 Jan, 17:02


+ አባቶቻችን እንዲህ አሉ +

"በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው" ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ

🍀-🌼-🍀-🌼-🍀-🌼-🍀

"ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል" ቅዱስ ቆጵሮሳዊ

🍀-🌼-🍀-🌼-🍀-🌼-🍀

"ሰዎች የሚያብዱበትና እንደነሱ ያላበደ ሰው ሲያዩ "እንደኛ ስላልሆንክ አብደሃል" የሚሉበት ዘመን ይመጣል"
ቅዱስ እንጦንዮስ

"መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም"
ቅዱስ ባስልዮስ

🍀-🌼-🍀-🌼-🍀-🌼-🍀
"ይህንን ካስታወስክ በሰው መፍረድ ታቆማለህ:: ይሁዳ ሐዋርያ ነበር:: ከጌታ ቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ነፍሰ ገዳይ ነበር" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

🍀-🌼-🍀-🌼-🍀-🌼-🍀

"የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው"
ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ

🍀-🌼-🍀-🌼-🍀-🌼-🍀

"እግዚአብሔር ለአብርሃም "ከሀገርህ ውጣ ከወገኖችህ"ተለይ ብሎት ነበር። በዚህ ጥሪ እግዚአብሔር ሁላችንንም የተወለድንበት ዘር እንድንተው ይጠራናል። ሰማዕቱ ዮስጦስ (100 AD-165 AD)

🍀-🌼-🍀-🌼-🍀-🌼-🍀

"ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር" ሊቁ ጠርጡለስ

🍀-🌼-🍀-🌼-🍀-🌼-🍀

‹‹ይጸልያል ነገር ግን የሌሎችን ጸሎትም ይሰማል፡፡ ያለቅሳል የሌሎችን ዕንባ ግን ያብሳል፡፡ ሰው ነውና አልዓዛር ወዴት እንደተቀበረ ጠየቀ፡፡ አምላክ ነውና አልዓዛርን ከሞት አስነሣ፡፡ እርሱ በርካሽ ዋጋ ያውም በሠላሳ ብር ብቻ ተሸጠ፡፡ ነገር ግን ዓለምን በውድ ዋጋ በከበረ ደሙ ገዛ፡፡ እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ እርሱ ግን የእስራኤል እረኛ የዓለምም ሁሉ ጠባቂ ነበረ፡፡ እንደ በግ ዝም አለ ነገር ግን እርሱ በምድረ በዳ በሚጮኽ ሰው ድምፅ የተሰበከ ቃል ነበር፡፡ እርሱ የተሰቃየና የቆሰለ ነበር ፤ ሁሉንም በሽታና ቁስል ግን ይፈውስ ነበር›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ

🍀-🌼-🍀-🌼-🍀-🌼-🍀

"ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ፡፡ አቤቱ ሆይ የውጭ ተክል አታድርገኝ፡፡ የጽድቅ ተክል አድርገኝ፡፡ የኃጢአት አይደለም፡፡ የዕውነት ተክል አድርገኝ የሐሰት አይደለም የፍቅር ተክል አድርገኝ የጽል አይደለም፡፡

የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና የምትጋርደኝ፡፡ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፡፡ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከኔም አርቀው ሥርዓትህን የሚሠሩትን ያበባቸውን ፍጻሜ እንዳፈራ አድርገኝ" ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

🌼🍀-🍀🌼-🌼🍀-🍀🌼-🌼🍀

👇👇👇👇

https://t.me/Eotc_spritual_books

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

03 Jan, 09:06


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

03 Jan, 06:47


#ቃለ_ወንጌል

25/04/2017
ማቴዎስ 13:36-44


ከዚህም በኋላ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው “የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጒምልን” አሉት። እርሱም መልሶ አላቸው፤ “መልካም ዘርን የዘራ የሰው ልጅ ነው። እርሻውም ዓለም ነው፤ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው። የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም ፍጻሜ ነው፤ አጫጆ ቹም መላእክት ናቸው። “እንግዲህ አስቀድሞ እንክርዳዱን እንደሚለቅሙት፥ በእሳትም እንደሚያቃጥሉት በዚህ ዓለም ፍጻሜም እንዲሁ ይሆናል። የሰው ልጅም መላእክቱን ይልካል፤ ከመንግሥቱም ዐላውያንንና በደልን የሚያደርጉትን ሁሉ ይሰበስባሉ። ወደ እሳት ጒድጓድም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። ያንጊዜም ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ፤ ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ
::"

ምስባክ
መዝሙር 78:2-3

ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊተ ገዳም

ወከዐዉ ደሞሙ ከመ ማይ ዐውዳ ለኢየሩሳሌም

ወኀጥኡ ዘይቀብሮሙ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

02 Jan, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

02 Jan, 03:10


#ቃለ_ወንጌል

24/04/2017
ማቴዎስ 18:1-12


      በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን? አሉት። ሕፃንም ጠርቶ በመካከላቸው አቆመ፡ እንዲህም አለ እውነት እላችኋለሁ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም። እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ፥ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው። እንደዚህም ያለውን አንድ ሕፃን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር።

ወዮ ለዓለም ስለ ማሰናከያ፤ ማሰናከያ ሳይመጣ አይቀርምና፥ ነገር ግን በእርሱ ጠንቅ ማሰናከያ ለሚመጣበት ለዚያ ሰው ወዮለት። እጅህ ወይም እግርህ ብታሰናክልህ፥ ቈርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት እጅ ወይም ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል ይልቅ አንካሳ ወይም ጉንድሽ ሆነህ ወደ ህይወት መግባት ይሻልሀል። ዓይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት ዓይን ኖሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትጣል ይልቅ አንዲት ዓይን ኖራህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል። ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና። የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቶአል
::

ምስባክ
መዝሙር 8:2-3

እም አፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ

በእንተ ጸላኢ

ከመትንስቶ ለጸላኢ ወለገፋኢ

          

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

01 Jan, 11:09


"ድንግል ሆይ! አንገታቸውን እንደሚያረዝሙ እንደ እብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም:: በቅድስናና በንጽሕና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ::

ድንግል ሆይ! ምድራዊ ሕብስትን የተመገብሽ አይደለም:: ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ሕብስትን እንጂ::
ድንግል ሆይ! ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም:: ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን እንጂ::" †††


#ቅዳሴ_ማርያም

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

01 Jan, 09:05


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

01 Jan, 03:02


#ቃለ_ወንጌል

23/04/2017
ማቴዎስ 22:31-ፍጻሜ



ስለ ሙታን መነሣት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ እንዲህ ተብሎ የተነገረውን አላነበባችሁምን? እኔ እግዚአብሔር የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ እንግዲህ የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም።”

ሕዝቡም ሰምተው ትምህርቱን አደነቁ። ፈሪሳውያንም ሰዱቃውያንን ምላሽ እንዳሳ ጣቸው በሰሙ ጊዜ በአንድነት ወደ እሱ ተሰ በሰቡ። ከመካከላቸውም አንድ ሕግ ዐዋቂ ሊፈትነው ጠየቀው። “መምህር ሆይ፥ ከኦሪት ማንኛይቱ ትእዛዝ ትበልጣለች?” አለው። ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “አምላክህ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ኀይልህ ውደደው። ታላቂቱና የመጀመሪያይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። የምትመስላት ሁለተኛይቱም ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትለው ናት። “ኦሪትና ነቢያት ሁሉ በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ጸን ተዋል።”

ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ ጌታችን ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው፦ “ስለ ክርስቶስ ምን ትላላችሁ? የማን ልጅ ነው?” እነርሱም፥ “የዳዊት ልጅ ነው” አሉት። ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “እንግዲያ እርሱ ራሱ ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ እንዴት እንዲህ አለ? “ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስከ አደርጋቸው ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው። እርሱ ራሱ ዳዊት “ጌታዬ” ያለው፥ እንግዲህ እንዴት ልጁ ይሆነዋል?” አንድም ቃል እንኳ ሊመልስለት የቻለ የለም፤ ከዚያች ቀንም ጀምሮ ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም


                                 ምስባክ
                         መዝሙር 18:12-13

ለስሒት መኑ ይሌብዋ

እምኅቡዓትየ አንጽሐኒ

ወእምነኪር መሐኮ ለገብርከ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

31 Dec, 10:52


ኢየሱስ ክርስቶስ፡-

“ጨለማን ያሳደደው ብርሃን ዓለምን ሁሉ ያበራው ፋና የማይነዋወጥ መሰረትና የማይፈርስ ግንብ የማይሰበር መርከብና የማይሰረቅ ማህደር የለዘበ ቀንበርና የቀለለ ሽክም እርሱ ለአባቱ ኃይል ጥበቡም የሚሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

“ለሁሉ ያስባል፤ ሁሉንም ያጠግባል ለዕውራን ያዩ ዘንድ ብርሃንን ይሰጣቸዋል፡፡ የተዘጉ መስኮቶችን ይከፍታል ህሙማንን ይሰማቸዋል፡፡ የተደፈነችውን ጆሮ እንድትሰማ ያደርጋል፡፡ ከሰውነት የለምፅን ልብሶች ገፍፎ የስጋን መጎናፀፊያ ያለብሳል፡፡ የደረቀውን የእጅ ክንድ ያቀናል፣ የአንካሳውን እግር እንዲሄድ ያደርጋል ነፍስን ወደ ሕዋስዋ ይመልሳታል መንፈስንም በማደሪያዋ ያኖራታል፡፡ አለቆች ባሏቸው አጋንንት የእርያን መንጋ ያሰጥማል ከደከመችውም ሰውነት ደዌን ያርቃል፡፡

“ከክንፍህ የጽድቅ ፀሐይና የጥቅም ምንጭ የሚወጣ የጽድቅ ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንተ ጌትነትና ክብር ምስጋናም ይገባሃል ለዘላለሙ አሜን፡፡”

(ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ)

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

31 Dec, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

31 Dec, 03:15


#ቃለ_ወንጌል

22/04/2017

   ሉቃስ 1:3-57


     ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥ ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት። ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና። ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።

ማርያምም እንዲህ አለች ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው። ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል። በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤ ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤ የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል። ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል። ማርያምም ሦስት ወር የሚያህል በእርስዋ ዘንድ ተቀመጠች ወደ ቤትዋም ተመለሰች።


                              ምስባክ
  መዝ 44:16-17


ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ

ወትሰይሚዮሙ መላእክት ለኵሉ ምድር

ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

30 Dec, 11:01


መንፈሳዊ እድገት የምትወጣጣበት መሰላል አይደለም፤ መንፈሳዊ እድገት ያለማቋረጥ የምትከተለው ጉዞ ነው!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

30 Dec, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

29 Dec, 10:01


ዓለም የእግዚአብሔር ልጅ መሆንና አለመሆን የምትለየው ምግባርህንና ባህሪህን አይታ ነው። ምግባርህ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን ያሳያል?

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

29 Dec, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

29 Dec, 03:45


#ቃለ_ወንጌል


ዮሐንስ 1:1-19

    በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች። ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።

ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ። ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ፥ እርሱ ብርሃን አልነበረም። ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር። በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም። የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም። ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።

ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ እንዲህም ብሎ ጮኸ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ። እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና፤ ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ። መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።

                          ምስባክ
                 መዝሙር 42:3-4

ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ

እማንቱ ይምርሓኒ ወይሰዳኒ ደብረ መቅደስከ

ወውስተ አብያቲከ እግዚእ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

28 Dec, 10:12


ለነገሩ ለወላዋዩ ናቡከደነፆር ምን መልስ ይሠጣል፡፡ ታሪኩን ስናነብ እንደ ናቡከደነፆር ተገለባባጭ ሰው የለም፡፡ ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ሁለት ላይ ለፈጣሪ መሰከረ ፣ ምዕራፍ ሦስት ላይ ካደ ፣ ምዕራፍ ሦስት መጨረሻ ላይ አምኖ መሰከረ ፣ ምዕራፍ አራት መጀመሪያ ላይ ለፈጣሪ እንደ መዘመር ቃጣው በሕልሙ መልአክ እስከማየት ደርሶ ስለ ፈጣሪ ኃያልነት መሰከረ ፣ ምዕራፍ አራት መጨረሻ ላይ ግን ‹‹ይህች በጉልበቴ ብርታት ለግርማዬ ክብር የሠራኋት ታላቂቱ ባቢሎን አይደለችምን?›› ብሎ ተኮፍሶ እንደ እንስሳ ሣር እስኪግጥ ድረስ ተቀጥቷል፡፡ ስለዚህ ሦስቱ ወጣቶች ‹አምላካችሁ ማን ነው?› ሲላቸው መልስ ልንሠጥህ አያስፈልገንም ፤ አንተው ማን እንደሆነ ሣር ስትግጥ ታየዋለህ አሉት፡፡ እግዚአብሔር ማን ነው ያሉ እነፈርኦን የደረሰባቸው ባይገባህ አንተ ላይ ደርሶ ታየዋለህ ሲሉ ‹እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም› አሉት፡፡

ሦስቱ ወጣቶች አምላካችሁ ማን ነው የሚለውን ባይመልሱም ይህንን ግን አሉ ‹‹ንጉሥ ሆይ አምላካችን ከሚነድደው ከእቶኑ እሳት ያድነን ዘንድ ይችላል ከእጅህም ያድነናል› ንጉሥ ሆይ አምላካችን ኃይሉ ከእሳት በላይ ነው፡፡ ያለ እሳት ማንደድ ያለ ውኃ ማብረድ ይችላል፡፡ ከእሳቱ ያድነናል ፤ ‹ከእሳቱ ቢያድናችሁ ምን ዋጋ አለው ፤ ከእሳት ብታመልጡ ከእኔ አታመልጡም› ብለህ ታስብ እንደሆን ‹‹ከእጅህም ያድነናል›› አሉት፡፡

‹‹ነገር ግን ንጉሥ ሆይ እርሱ ባያድነንም አማልክትህን እንደማናመልክ እወቅ›› አሉት፡፡ ወጣቶቹ ‹ባያድነንም› ያሉት ተጠራጥረው አይደለም፡፡ ለጣዖት ከመስገድ ሞት ይሻለናል ፣ ለጣዖት በመስገድ የምንጎዳው ጉዳት በእሳት ተቃጥለን ከምንጎዳው አይብስም ፣ የዘላለም እሳት ከሚፈጀን የአንተ እሳት ቢፈጀን እንመርጣለን ለማለት ነበር፡፡ በዚያ ላይ ሦስቱ ወጣቶች ‹ያድነን ዘንድ ይችላል› አሉ እንጂ ‹እንድናለን› አላሉም፡፡ የፈጣሪያቸውን የማዳን ኃይል በእርግጠኝነት ተናገሩ እንጂ ከዚህ እሳት እንደሚድኑ በእርግጠኝነት አልተናገሩም፡፡ ይህም ከትሕትናቸው የተነሣ ነበር፡፡ እግዚአብሔር መላእክቱን ስለ እኔ ያዝዝልኛል ያድነኛል ብሎ ወደ ሞት ራስን መሥጠት ጌታችን ለዲያቢሎስ እንዳለው ጌታ አምላክን መፈታተን ነው፡፡ ስለዚህ ሦስቱ ወጣቶች ‹ባያድነን እንኳን› ሲሉ ምግባራችን ከልክሎት ባያድነን እንኳን ያልዳነው በኃጢአታችን ነው እንጂ አምላካችን ማዳን ተስኖት እንዳይመስልህ አሉት፡፡

እነዚህ ወጣቶች ምንኛ ያስደንቃሉ ፤ ስለ ትንሣኤ ሙታን ባልተሰበከበት በዚያ ዘመን ፣ ምንም እንኳን ሥቃይ የማይነካቸው ቢሆንም እንኳን ጻድቃንም ቢሆኑ ወደ ሲኦል በሚወርዱበት በዚያ ዘመን ተስፋ ሳይኖር ተስፋ አድርገው እንደ ሐዲስ ኪዳን ሰው ወደ ሞት የሔዱት እነዚህ ወጣቶች ምንኛ ክቡራን ናቸው፡፡ ለዚህም ነው ሰማዕቱ ዮስጦስ (Justine the martyr) ‹‹ከክርስቶስ በፊት የነበሩ ክርስቲያኖች›› (Christians before Christ) የሚላቸው፡፡

★ መርጦ የሚያነድ እሳት ★

ናቡከደነፆር በወጣቶቹ መልስ እጅግ ተበሳጨ ፤ የሚነድደውን እሳት ሰባት እጥፍ እንዲያደርጉት አዘዘ፡፡ ልፋ ሲለው ነው እንጂ እሳቱ ሰባት እጅም ቢሆን ፣ አንድ እጅም ቢሆን ለሦስቱ ወጣቶች መቃጠል ያው መቃጠል ነው፡፡ የባቢሎንን ማገዶ ከማባከን በቀር ሦስቱ ወጣቶች የሚሞቱት ሞትም ያው አንድ ሞት ነው፡፡ የተፈለገው ግን እንዲፈሩ ነበር፡፡ ሰይጣን አሠራሩ እንዲህ ነው ፤ እምነታችን ሲጨምር እሳቱ ሰባት እጥፍ ይጨምራል፡፡ ‹ያድነናል› የሚለው ምስክርነታችን ናቡከደነፆሮችን ያስቆጣል፡፡ በሥልጣናቸው የሚነድደውን እሳት መጨመር እንጂ የእኛን እምነት መቀነስ አይችሉም፡፡ ሦስቱን ወጣቶች ከሰናፊላቸው ፣ ከቀሚሳቸውና ከመጎናጸፊያቸው ከቀረው ልብሳቸውም ጋር እንዲታሠሩ ተደረገ፡፡ ያ ሁሉ ልብስ አብሮአቸው እንዲታሰር የተፈለገው ሥቃያቸውን የበለጠ ለማብዛት ፣ እግራቸው መታሰሩም ሳይንፈራገጡ እንዲቃጠሉ ለማድረግ ነበር፡፡ በዚህ አሰቃቂ ሁኔታ ሦስቱን ወጣቶች ወደ እሳት ጨመሯቸው፡፡ ከእሳቱ ኃይል የተነሣ ‹የጣሏቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው›

ሦስቱን ወጣቶች እሳት ውስጥ ሲገቡ ከእስራቸው ተፈትተው ሲመላለሱ ታዩ ፤ ናቡከደነፆር ባላዋቂ አነጋገር ‹የአማልክት ልጅ› ያለውን ‹የእግዚአብሔር ልጆች› ተብለው ከሚጠሩት መላእክት አንዱ የሆነውን መልአኩን ልኮ የእሳቱን ኃይል አጠፋ፡፡ ‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሠፍራል ያድናቸውማል› የተባለውም ተፈጸመ፡፡ ‹የአማልክት ልጅ› የተባለው የመልአኩ መውረድ የወልደ እግዚአብሔር የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ፣ የመምጣቱና የሰውን ልጅ ከሲኦል እሳት የማዳኑ ሥራ ምሳሌ ሆኖ ይኖራል፡፡

ሦስቱ ወጣቶች ልብስ አልብሰው የጨመሯቸው እንዲሰቃዩ ነበር ፤ ሆኖም ለሥቃይ የለበሱት ልብስ ለዝማሬ ሆናቸው፡፡ መቼም ዕርቃን ሆኖ ዝማሬ የለም፡፡ አልብሰው ባይከቷቸው ኖሮ ሲወጡ ዕርቃናቸውን በወጡ ነበር፡፡ የሚያስደንቀው እነዚህ ሦስት ዕፀ ጳጦሶች እንኳን ሊቃጠሉ ጭስ ጭስ እንኳን አይሉም ነበር፡፡
የባቢሎን እሳት አስደናቂ እሳት ነው፡፡ ከእሳቱ ውስጥ እያሉ እሳቱ ያቃጠለው የታሰሩበትን ገመድ ብቻ ነበር፡፡ ከዚያ ውጪ የጣሏቸውን ሰዎች ወላፈኑ ገደላቸው፡፡ ሰዎችን ወደ እሳት መገፍተር ቀላል ነው፤ እሳቱ ግን ገፍታሪዎቹን ሊያቃጥል ይችላል፡፡ ‹‹እሳት በላዒ ለአማፅያን ለእለ ይክህዱ ስሞ ፤ ወእሳት ማኅየዊ ለርቱዓነ ልብ ለእለ ይገብሩ ፈቃዶ›› (ስሙን ለሚክዱ ለአመጸኞች የሚባላ እሳት ነው ፤ፈቃዱን ለሚሠሩ ልባቸው ለቀና የሚያድን እሳት ነው) የሚለው የአባ ሕርያቆስ ቅዳሴ በብሉይ ኪዳን ቢሆን ለባቢሎን እሳት ይሠራ ነበር፡፡

ሦስቱ ወጣቶች እሳት ውስጥ ገብተው የመውጣታቸው ታሪክ በጥላቻና በዘረኝነት እሳት እየነደድን ባለንበት በዚህ ዘመን ሆነን ስንመለከተው መልእክቱ ብዙ ነው፡፡ በሚነድደው እሳት ላይ የእያንዳንዳችን ድርሻ ምንድር ነው? አንዳንድ ሰው ‹ይለይለት ካልደፈረሰ አይጠራም› ይላል፡፡ በስድብ በጥላቻ በነቀፋ ከሩቅም ከቅርብም ሆኖ የሚያባብስ ሰው እንግዲህ እሳቱን ሰባት እጥፍ ከሚጨምሩት የናቡከደነፆር አሽከሮች አይለይም፡፡ በዚያ ላይ ይለይለት ብለህ የምትጨምረው እሳት ወላፈኑ አንተኑ ማቃጠሉ አይቀርም፡፡ ያለነውም የምንኖረውም እሳቱ ውስጥ ሆነው ‹‹የምናመልከው አምላክ ሊያድነን ይችላል›› ብለው በሚጸልዩ ሰዎች ነው፡፡ ጸሎት መፍትሔ ነው ሲባል በሚያስቀን በናቡከደነፆሮች ሳይሆን ዳዊቱን በማያስታጉሉ አናንያ አዛርያና ሚሳኤሎች ነው፡፡

እሳት ውስጥ ገብተው የወጡት እነዚህ አርበኞች ከጸሎቱ ባሻገር አንድ ልብ ነበሩ፡፡ በሙሉ ትንቢተ ዳንኤል ላይ ‹አናንያ እንዲህ አለ ፤ አዛርያም እንዲህ አለ› የሚል አልተጻፈም፡፡ ሦስት ሲሆኑ እንደ አንድ ሰው ሲናገሩ ሲሰሙ ፣ አብረው ሲጾሙ ፣ አብረው ሲሾሙ ፣ አብረው ሲታሰሩ ፣ አብረው ከእሳት ሲገቡ አብረው ሲወጡ ፣ አብረው ሲዘምሩ ነው ያየናቸው፡፡ አንድ ልብ ሳይሆኑ ከእሳት መውጣት አይቻልም፡፡ አናንያና አዛርያ ተፋቅረው ሚሳኤልን ቢጠሉት ኖሮ በሃሳብ ባይስማሙ ኖሮ ተቃጥለው ይቀሩ ነበር፡፡ ‹‹መልአኩን የላከ በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ የአናንያ የአዛርያ የሚሳኤል አምላክ ይባረክ›› (ዳን. 3፡28)

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 19/2011 ዓ.ም
ኦስሎ ኖርዌይ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

28 Dec, 10:12


+ ከክርስቶስ በፊት የነበሩ ክርስቲያኖች +
++++++++++++++++++++++++++++

👉🏽. የቆሎ ተማሪዎች

ንጉሥ ናቡከደነፆር እስራኤልን ድል ነሥቶ በግዞት ወደ ባቢሎን በወሰዳቸው ጊዜ ሕዝቡን ለአመጽ እንዳያነሣሡበት ከነገሥታትና መሳፍንት ወገን የሆኑትን ፣ መልከ መልካሞቹን ፣ ወጣቶቹንና ብሩሕ አእምሮ ያላቸውን መርጦ ከሕዝቡ ለይቶ በቤተ መንግሥቱ ሰበሰበ፡፡ ዓላማው ወጣቶቹ የሀገሩን ቋንቋ ከተማሩና በቤተ መንግሥት በምቾት ከኖሩ የወገኖቻቸው መከራ እንደማይሰማቸው በማሰብ ነበር፡፡ ከሰው ልጅ የሚበዛው እርሱ እስከተመቸውና ጥቅሙ እስካልተነካበት ድረስ የሌላው ወገኑ ጩኸት ስለማይሰማው ናቡከደነፆር እስራኤልን ለማፈን የተጠቀመው አደገኛ ስልት ነበረ፡፡ ይህ ስልት ግን በሦስቱ ወጣቶች በአናንያ በአዛርያና ሚሳኤል ላይ አልሠራም፡፡ ገና ከጅምሩ በቤተ መንግሥት የቀረበላቸውን ‹ጮማና ጠጅ አንበላም ጥሬ ይሠጠን› ብለው በድብቅ ‹የቆሎ ተማሪዎች› ሆኑ፡፡

መቼም የቤተ መንግሥትን እንጀራ አንዴ አትልመደው እንጂ የለመድከው እንደሆነ ንጉሡ ምንም አድርግ ቢልህ ታደርጋለህ፡፡ የቤተ መንግሥት ምግብ መዘዙ ብዙ ነው፡፡ ‹‹ኦርዮም ከንጉሡ ቤት ሲወጣ ማለፊያ እንጀራ ተከትሎት ሄደ›› ተብሎ እንደተጻፈ እንኳን የናቡከደነፆር ቤተ መንግሥት ምግብ ይቅርና የንጉሥ ዳዊት ቤተ መንግሥት ምግብም እንደ ኦርዮ ሞትን ሊያስከትልም ይችላል፡፡ ከቤተ መንግሥት የሚሠጥህን ምግብ አገኘሁ ብለህ ደስ ቢልህም ያ ምግብ የመጨረሻ ራትህ ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ ነገ ክፉ ነገር አድርግ ቢሉህ እምቢ ለማለት ትቸገራለህ፡፡ ስለዚህ ሦስቱ ወጣቶች ጥሬ ቆርጥመው ሊማሩ ወሰኑ፡፡ ከዚህ በኋላ ነው ሦስቱን ወጣቶች ከንጉሡ ጋር የሚያጋፍጥ ነገር የመጣው፡፡

ከዚህ በኋላ ናቡከደነፆር ሕልም አለመ ፤ ሆኖም ሕልሙ ጠፋበት፡፡ አስማተኞቹን ሰብስቦ ‹ሕልሜን ከነፍቺው ንገሩኝ› ብሎ አፋጠጣቸው፡፡ ግራ ገባቸው ፤ ሕልሙን ተናግሮ ቢሆን ‹ሲሳይ ነው ፣ ዕድሜ ነው ፣ ጸጋ ነው› ብሎ ማለፍ ይቻል ነበር፡፡ አሁን ግን ‹ሕልሜን ውለዱ› አለ፡፡ አልነግር ሲሉት ሊገድላቸው ወሰነ፡፡ በዚህ መካከል ሦስቱ ወጣቶች ከአጎታቸው ዳንኤል ጋር ሆነው መፍትሔ አመጡ፡፡ እነርሱ በጸሎት ሲተጉ እግዚአብሔር ሕልሙን ከነትርጓሜው ለዳንኤል ገለጠለት፡፡
ንጉሡ በዘነጋው ሕልሙ ያየው ‹ራሱ የወርቅ ፣ የቀረው አካሉ የብር ፣ የናስ ፣ የብረትና ሸክላ የሆነ ትልቅ ምስል ነበር› ዳንኤል ሕልሙን ለንጉሡ ከነገረው በኋላ እንዲህ ብሎ ፈታለት፡፡ ‹ንጉሥ ሆይ ባየኸው ሕልም ላይ በሥልጣን ከሁሉ በላይ አድርጎሃልና የወርቁ ራስ አንተ ነህ ፤ ከዚያ በታች ያየኻቸው ደግሞ ከአንተ በኃይል የሚያንሡ ከአንተ በኋላ የሚነሡ ነገሥታት ናቸው›› ብሎ እርሱና ከእርሱ በኋላ የሚነሡ ነገሥታት እንዴት መንግሥታቸው እንደሚያልፍ ሕልሙን ከነዝርዝር ፍቺው ነገረው፡፡ በዚህም ንጉሡ ደስ አለውና ዳንኤልን ከፍ ከፍ አደረገው ፤ ሦስቱን ወጣቶችም በአውራጃ ሥራ ላይ አዛዦች አድርጎ ሾማቸው፡፡

★ እንደ ንጉሡ አጎንብሱ ★

ናቡከደነፆር ዳንኤል ከፈታለት ረዥም ሕልም ውስጥ ግን ከአእምሮው ያልጠፋችው ‹ወርቁ አንተ ነህ› የምትለው ዓረፍተ ነገር ነበረች፡፡ መቼም እኛ ወርቅ የሆንንበት ቅኔ ከልባችን አይጠፋም፡፡ ስለዚህ ራስ ወዳዱ ናቡከደነፆር ከረዥሙ ሕልም ውስጥ ‹ወርቁ አንተ ነህ› የምትለዋ ብቻ ልቡን ነካችው፡፡ ባልንጀራህን ‹እንደ ራስህ ውደድ› ስለሚል ራስን መውደድ ጥፋት አይደለም፡፡ ራስን መውደድ በጣም ከፍ እያለ ሲመጣ ግን ‹ፀሐይ የምትወጣው እኔን ለማየት ነው› እስከማለት ያስደርሳል፡፡ ናቡከደነፆር በራሱ ፍቅር ወደቀ ፣ ራሱን አቅፎ ለመሳም ቃጣው ፤ በመጨረሻም ‹እኔ ወርቅ ነኝ› የምትለው አሳቡ አድጋ በዱራ ሜዳ ላይ ትልቅ የወርቅ ሐውልት ሆነች፡፡ ‹ለዚህ ጣዖት የማይሰግድ ሰው ወደ እሳት ይጣላል› የሚል አዋጅ አወጀ፡፡ የመለከትና የእንቢልታ የመሰንቆና የክራር የበገናንና የዋሽንት የዘፈን ድምፅ በሀገሩ ተሰማ፡፡ ሕዝቡ ወደ ዕቶን እሳት ትጣላለህ ከሚል ማስፈራሪያ ጋር ስሜቱን የሚነካ ሙዚቃም ሲሰማ ያለማመንታት ታዘዘ፡፡ በዚህ አዋጅ ምክንያት በድፍን ባቢሎን የሚኖሩ እስራኤላዊያንም ጭምር ሁሉም ለወርቁ ምስል ሰገዱ፡፡

የአውራጃ ሹመኞች የሆኑት የቤተ መንግሥት ጾመኞች ሦስቱ ወጣቶች ግን አልሰገዱም፡፡ ሁሉም ሲሰግድ አለመስገድ ፣ ሁሉም ሲያጨበጭብ እጅን መሰብሰብ ፣ ሁሉ ሲስቅ መኮሳተር ጽናት የሚጠይቅ ነው፡፡ ‹ከሀገሩ የወጣ ሰው እስኪመለስ ድረስ ፤ ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ› ብለው መተረት አልፈለጉም፡፡ ሀገሩ ሁሉ ከሰገደ በእነዚህ ወጣቶች ለይቶ የሚፈርድባቸው ሰው አልነበረም፡፡ ከእስራኤል ወገን ብዙ ሽማግሌዎች ብዙ መጽሐፍ አዋቂዎች አገጎንብሰው ቢሰግዱም እነዚህ ወጣቶች አልሰገዱም፡፡ ‹‹ከእኛ ብዙ የሚያውቁት እነ እገሌ እነእገሌ ከሰገዱ እኛ ለምን እንጠቆራለን? ከሰው ተለይተን ምን እንፈጥራለን? የአውራጃ ገዢ አድርጎ ሾሞን የለ አሁን እንቢ ብንል ውለታ ቢስ መሆን አይሆንብንም? ስገዱ ያለው ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው እንጂ ጣዖት አምልኩ አላለንም ፤ እሳት ውስጥ ከምንገባ ይህችን ቀን አጎንብሰን ብናልፋትስ ፣ ዋናው ልብ ነው›› ብለው ራሳቸውን ሊያሞኙ አልፈለጉም፡፡ ሁሉ ባጎነበሰበት ቀን አንሰግድም ብለው ቆሙ፡፡

★ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው? ★

ናቡከደነፆር ሦስቱ ወጣቶች እንዳልሰገዱ ሲነገረው ቁጣው ነደደና አስጠራቸው፡፡ ‹‹የምሰማው እውነት ነውን?›› አለ ፤ እንዲያስተባብሉ ዕድል ሲሠጥ፡፡ ‹አሁንም የመለከትና የእንቢልታ የመሰንቆና የክራር የበገናንና የዋሽንት የዘፈን ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ብትሰግዱ መልካም ነው›› አለ፡፡ መቼም በመጽሐፍ ቅዱስ እንደ ናቡከደነፆር የሙዚቃን ስሜት ቀስቃሽነት የተረዳ ሰው ያለ አይመስልም፡፡ ‹‹በሉ ሙዚቃው ድጋሚ ይከፈትልሃል ትጨፍራላችሁ›› የሚል ይመስላል፡፡ ስገዱ ከማለቱ ሙዚቃውን ስትሰሙ ማለቱ ይገርማል፡፡ ከዚያ ማስፈራሪያ ጨመረበት ‹‹ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው? ብሎ ተናገራቸው።

ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው? ለሚለው ለንጉሡ ጥያቄ ሦስቱ ወጣቶች ‹‹ናቡከደነፆር ሆይ በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም›› አሉት፡፡ ምን ማለታቸው ነው? ለምን አይመልሱለትም? ይህንን ያሉበት ምክንያት ናቡከደነፆር ከጥቂት ጊዜ በፊት ሕልም አልሞ በተፈታለት ጊዜ ደስ ብሎት ‹‹አምላካችሁ የአማልክት አምላክ የነገሥታትም ጌታ ምሥጢርም ገላጭ ነው›› ብሎ መስክሮ ስለነበር ነው፡፡ (ዳን 2፡47) አሁን ደግሞ ተገልብጦ ‹ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው?› አላቸው፡፡ ስለዚህ ሦስቱ ወጣቶች ትናንት ያመሰገነውን አምላክ እንደማያውቀው ሲሆን ላንተ መልስ አያስፈልግህም አሉት፡፡ አንዳንድ ሰዎች ትናንት ያመለኩትን አምላክ ዛሬ እንደማያውቁ ሆነው ሲጠይቁ ፣ ትናንት ያመኑበትን ዛሬ ክደው ሲያናንቁ ‹‹በዚህ ነገር እንመልስላቸው ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም››

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

28 Dec, 10:00


ስለ ኃይማኖት መከራከር እንዳለብህ ነው የምታስበው? ስለ እምነት መከራከር ቀይ መስመር ነው፤ ፍጹም ቀይ መስመር። እባክህን ስለእምነት አትከራከር!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

28 Dec, 09:00


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

24 Dec, 16:02


ቅዱሳን ነቢያት

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

24 Dec, 10:27


አትፍረድ! ያ ሰው በምን አይነት መከራና ስቃይ ውስጥ እያለፈ እንደሆነ አታውቅምና ፈጽሞ ፈራጅ አትሁን።

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

24 Dec, 09:00


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

24 Dec, 03:42


#ቃለ_ወንጌል

15/04/2017
               
  ሉቃስ 15:11-25

   
እንዲህም አለ አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት። ከእነርሱም ታናሹ አባቱን አባቴ ሆይ፥ ከገንዘብህ የሚደርሰኝን ክፍል ስጠኝ አለው። ገንዘቡንም አካፈላቸው። ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሹ ልጅ ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፥ ከዚያም እያባከነ ገንዘቡን በተነ። ሁሉንም ከከሰረ በኋላ በዚያች አገር ጽኑ ራብ ሆነ፥ እርሱም ይጨነቅ ጀመር። ሄዶም ከዚያች አገር ሰዎች ከአንዱ ጋር ተዳበለ፥ እርሱም እሪያ ሊያሰማራ ወደ ሜዳ ሰደደው። እሪያዎችም ከሚበሉት አሰር ሊጠግብ ይመኝ ነበር፥ የሚሰጠውም አልነበረም። ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ።

ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ። ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው። ልጁም አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም አለው። አባቱ ግን ባሪያዎቹን አለ ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አምጡና አልብሱት፥ ለእጁ ቀለበት ለእግሩም ጫማ ስጡ፤ የሰባውን ፊሪዳ አምጥታችሁ እረዱት፥ እንብላም ደስም ይበለን፤
ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም። ደስም ይላቸው ጀመር

                          ምስባክ
        
           መዝሙር 30:12-13

ቀብፁኒ እምልብ ከመ ዘሞተ

ወኮንኩ ከመ ንዋይ ዘተኀጕለ

እስመ ሰማዕኩ ድምፀ ብዙኃን እለ ዐገቱኒ ዐውድየ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

23 Dec, 10:42


እግዚአብሔር የማትችለውን ግዴታ አይሰጥህም! ሸክምህ ከአቅምህ በላይ ሆኖ በተሰማህ ቁጥር፤ አንተ ያላየኸው እግዚአብሔር ግን ያየብህ ትልቅ አቅም ውስጥህ እንዳለ እወቅ።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

23 Dec, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

22 Dec, 12:40


አንተ ለሕይወትህ ካቀድከው የተሻለ እግዚአብሔር እንደሚያቅድልህ ታውቃለህ? አንተ ስለአንተ ልትሳሳት ትችላለህ፤ እግዚአብሔር ግን አይሳሳትም። አንተ ስለሕይወትህ ስታቅድ ልትሳሳት ወይም ያነሰውን ልታስብ ትችላለህ፤ እግዚአብሔር ግን ላንተ የሚገባውንና የተሻለውን በፍጹም ትክክለኛነት ያዘጋጅልሃል።

©ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

22 Dec, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

21 Dec, 10:36


"ከምግባራት ሁሉ ታላቁ ጸሎት ነው ነገር ግን የእርሱ መሠረቱ ጾም ነው፡፡ የምንጾምበት ምክንያት ርኩስ የሆነውን የሰይጣንን መንፈስ በነፍሳችን ውስጥ እንዳያድር ለመጠበቅ ነው፡፡ ሥጋችንን ለጾም ባስገዛነው ጊዜ ነፍሳችን ነፃነትን፤ ጥንካሬን፣ ሰላምን፣ ንጽሕናን እንዲሁም እውቀትን ለመለየት እንድትበቃ ትሆናለች፡፡"

(ጻድቁ ዮሐንስ ዘክሮስታንድ)

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

21 Dec, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

20 Dec, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

19 Dec, 10:43


ውዳሴ ማርያም የሚጸልይና የማይጸልይ
 

   💠💠💠💠💠

የእመቤታችን ውዳሴ ማርያም የዕለቱን ውዳሴ ማርያም በየዕለቱ የሚጸልይ ሰው የእናት አባቱን ርስት የወረሰ ይመስላል።

የሰባቱን ዕለት ውዳሴ ማርያም በእድሜዋ ልክ በየዕለቱ  የሚጸልይ ደግሞ የዘመዶቹን ጨምሮ የወረሰ ይመስላል።

እመቤታችን ሳያመሰግን የሚውል ሰው ምን ይመስላል ቢሉ፦

ከሰው ቤት ድግስ ተጠርቶ ሂዶ በር ላይ ሲደርስ ውኃ ተደፍቶበት፥ ተቆጥቶ የሚመለስ፤  እንቅፋት እየመታው እየወደቀ እየተነሣ እየተሰበረ የሚሄድ ይመስላል።

ያ ሰው ካለመብላቱ በላይ እየተሰበረ እንደሄደ እመቤታችን የማያመሰግንም በመከራ ሥጋ ላይ መከራ ነፍስ ይጸናበታል። በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም ይጨመርበታል።
       እኛ ግን፦
"አማንኬ ይደልወኬ አስተብፅዖ እስመ ኮንኪ እሞ ለእግዚአብሔር አዶናይ -የከሃሊ ኩሉ እግዚአብሔር እናት ሆነሻልና ብፅዕት መባል በእውነት ይገባሻል" እንላታለን።

    #ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን_ግርማ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

19 Dec, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

19 Dec, 03:29


#ቃለ_ወንጌል

10/04/2017
                  
                        ማቴዎስ 6:1-5


    ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም። እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ምጽዋት ስታደርግ ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን ቀኝህ የምትሠራውን ግራህ አትወቅ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል::


                          ምስባክ
                መዝሙር 111:9-10

👉ዘረወ ወወሀበ ለነዳይ


   ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም

   ወይትሌዓል ቀርኑ በክብር

                   ትርጉም

👉በተነ ለችግረኞችም ሰጠ

   ጽድቁ ለዘላለም ዓለም ይኖራል

   ቀንዱ በክብር ከፍ ከፍ ይላ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

18 Dec, 10:43


+ ድንገት የተበጠሰ ገመድ +

የደብረ ዳሞ ገዳም በገመድ ብቻ የሚወጣ እጅግ ጥንታዊ ገዳም ነው:: ይህንን አቡነ አረጋዊ በዘንዶ የወጡትን ታላቅ ገዳም ለመውጣት በግንባታው ወቅት በአፄ ገብረ መስቀል የተሠራ ደረጃ ነበረው:: ሆኖም አቡነ አረጋዊ ደረጃውን ዳህምሞ (አፍርሰው) ብለው በማዘዛቸው እስከ አሁን ድረስ በገመድ የሚወጣበት ገዳም ሆኖአል::

የደብረ ዳሞ መውጫ ገመድ እጅግ ወፍራም ሲሆን እስከ አሁን ድረስ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተንጠላጥለው ወጥተው ወርደውበታል:: ይህ እጅግ ወፍራም ገመድ ለዘመናት ሲያገለግል ተበጥሶ ሰው ጥሎ አያውቅም:: በታሪክ የማይዘነጋና መሃል ላይ የተበጠሰበትና ሰው የጣለበት ቀን አለ:: (የዲያቢሎስ መተናኮል ነው የሚል አለ)

በዚያ ቀን በተበጠሰው ገመድ ላይ የወረደው መንገደኛ ጻድቁ አባ ተክለ ሃይማኖት ነበሩ:: መነኮሳቱን ተሰናብተው በዚያ ገመድ ሲወርዱ ተበጥሶ የማያውቀው ገመድ ድንገት ተበጠሰ:: ከላይ የሚያዩት አባቶች ቁልቁል እያዩ በድንጋጤ ጮኹ:: ሆኖም እግዚአብሔር ለጻድቁ የብርሃን ክንፍ ሠጥቶአቸው ከተበጠሰው ገመድ ተለይተው እንደ መልአክ በርረው ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ወርደው መሬት ላይ አረፉ:: ባረፉባት ሥፍራም ቤተ ክርስቲያን ተሠራባት::

ወዳጄ በሕይወትህ ድንገት የተበጠሰ ገመድ የለም? ሳትጠብቀው የተበጠሰ ገመድ ማንም ላይ ሳይበጠስ አንተ ላይ የጨከነ ገመድ የለም? ምን ዓይነት ገመድ አትበለኝ:: የእንጀራ ገመድ የኑሮ ገመድ የትምህርት ገመድ የፈለግኸው ገመድ በለው:: እሱን ተጠምጥመህ ይዘህ ወደ አንዳች ቦታ ለመድረስ የተማመንክበት ተስፋህን ሙሉ በሙሉ የጣልክበት ገመድ የለም? ድንገት ተበጥሶ ዙሪያው ገደል አልሆነብህም? ሰዎች ማንም ላይ ያልተበጠሰ ገመድ አንተ ላይ ሲበጠስ አይተው "ምኑ ዕድለ ቢስ ነው?" ብለው የተደነቁብህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "ከባሕር አደጋ ተርፎ ዕባብ የነደፈው እንዴት ኃጢአተኛ ቢሆን ነው?" ብለው በትዝብት ዓይን እንዲያዩህ ያደረገ በሕይወትህ ሳታስበው ተበጥሶ ዙሪያው ገደል የሆነ ሥፍራ ላይ የጣለህ የሕይወት ገመድ ይኖር ይሆናል::

በዕድልህ አትማረር በሕይወትህ ድንገት የሚበጠስብህ ገመድ የምትወድቅበት ሳይሆን ክንፍ አውጥተህ የምትበርበት ነው:: ፈጣሪ የተማመንክበትን የምታየውን ገመድ እንዲበጠስብህ ከፈቀደ ያላየኸውን ክንፍ ሊሠጥህ እንጂ ሊጥልህ አይደለም::  የሕይወትህን ገመድ የተበጠሰበትን ቀን "እግዚአብሔር ለመልካም አሰበው" ብለህ እንደ ዮሴፍ ታመሰግንበታለህ::
ገመድህን የሚበጥሰው ከገደል ሊጥልህ ሳይሆን በክንፍ አብቅሎ ሊተክልህ ነው:: የሚተክልህ በበረሃ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ነው:: ተራ ተክል የምትሆን እንዳይመስልህ:: የሃይማኖት ተክል (ተክለ ሃይማኖት) ትሆናለህ:: ተክለ መንፈስ ቅዱስ ተክለ ወልድ ተክለ አብ ትሆናለህ:: አብ የተከለው ደግሞ አይነቀልም!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

23 Nov, 19:43


ጾመ ነቢያት ነገ እሑድ ኅዳር 15 ይገባል።

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

23 Nov, 16:02


"ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው፤ ስለዚህ ነፍሴ ፈለገቻቸው።"
መዝሙር ፻፲፰ ቊጥር ፻፳፱

ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ ለኅዳር ሚናስ በደረሰው ዝማሬ ላይ "ንሕነሰ ብነ ሰማዕት ዘየዓውዱነ ከመ ደመና ንግድፍ እምላዕሌነ ኵሎ ክበደ ወሁከተ ኃጢአት፡፡" በማለት እንደ ተናገረው በዙሪያችን እንደ ደመና የከበቡን እጅግ በርካታ ሰማዕታት አሉን፡፡ ሕይወትን ለሰጣቸው እስከ ሞት ለወደዳቸው ለአምላካቸው ራሳቸውን መሥዋዕት አድርገው ካቀረቡ በአሚነ ክርስቶስ ታላቅ መከራ ከተቀበሉ ከቅዱሳን ሰማዕታት አንዱ ገባሬ ተአምራት ወመንክራት ማር ሚናስ ነው፡፡

ኅዳር ፲፭ ቀን የገባሬ ተአምራት የሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ በዓለ ዕረፍት ይከበራል፡፡ ቅዱስ ሚናስ በዐራተኛ መቶ ክፍለ ዘመን በሃያ ዐራት ዓመቱ ሰማዕትነትን የተቀበለ ግብፃዊ ነው፡፡ ግብፃውያን ለቅዱስ ሚናስ የተለያ ፍቅር አላቸው፡፡ ቅዱስ ሚናስን ማር ሚና(አቡ ሚና) በማለት ይጠሩታል፡፡ ማር ማለት ቅዱስ ማለት ነው፡፡ ሴትን ቅድስት ለማለት ደግሞ ማርታ ይላሉ፡፡ ቅዱስ ሚናስ አባቱ አውዶስዮስ እናቱ አውፌምያ ይባላሉ፡፡ የቅዱስ ሚናስ እናት መካን ስለነበረች በጣም ታዝን እግዚአብሔር ልጅ እንዲሰጣት ትለምን ነበር፡፡

እግዚአብሔርም የልመናዋን ቃል ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጣት።
ቅዱስ ሚናስ አባትና እናቱን በልጅነት ጊዜ በሞት ባጣ ጊዜ ከእነርሱ የወረሰውን ሀብት ንብረት ሸጦ ለድሆች አከፋፈለ፣ ይኽንን ዓለም ንቆ መነነ። በዘመኑ አምልኮተ ጣኦት ተስፋፍቶ ነበር፡፡ በነገሥታቱ ለጣኦት እንዲሰግድ ሲጠየቅ ለጣኦት አልሰግድም በማለቱ አንገቱን በሰይፍ ተቀልቶ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጅቷል፡፡

ምእመናን የሰማዕቱ ራስ ላይ ብዙ ሽቱ አርከፍክፈው በከበሩ ልብሶች ገንዘው በሣጥን ውስጥ አኖሩት፡፡ ቅዱስ ሚናስ አንገቱን በሰይፍ እንዲመታ ያዘዘው ንጉሥ ሥጋው በእሳት እንዲቃጠል ፈረዶበት ነበር፡፡ ነገር ግን እሳቱ በቅዱስ ሚናስ ላይ አንዳች ኃይል ስላልነበረው ከሥጋው ምንም ምን አላቃጠለም፤ በሥጋውም ላይ ምንም ምን የእሳት ቃጠሎ ምልክት አልታየበትም፤ ወዳጆቹም በዚኽ ነገር እጅግ ተደነቁ፡፡ ሰማዕቱ በሕይወተ ሥጋ ከተቀበለው መከራ ይልቅ ከዕረፍቱ በኋላ በሥጋው የደረሰበት መንገላታት ታላቅ ነው ።

የተወደደው ሰማዕት የቅዱስ ሚናስ ተጋድሎውን የፈጸመው በዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ ኅዳር ፲፭ ቀን ፫፻፩ ዓ.ም. ነው። በዚኽን ዕለትም ታላቁ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሥክር ቅዱስ ሚናስ ሦስት የድል አክሊላትን ተቀዳጀ፡፡ ዳግመኛም በዚኽን ዕለት ተወዳጁ ሰማዕት ቅዱስ ሚናስ ከድል ነሺዎች ከማኅበረ በኵር ጋር ስሙ ተጻፈ፡፡

ቅዱሳን አባቶቻችን በመጽሐፈ ሲኖዶስ ዳግመኛም በመጽሐፈ ዲድስቅልያ ታመሰተደነቁ፡፡ ደማቸውን ያፈሰሱትን፣ አንገታቸውን ለስለት፣ ዠርባቸውን ለግርፋት፣ ሰውነታቸውን ለእሳት አሳልፈው የሰጡ ቅዱሳን ሰማዕታትን መታሰቢያ እናከብር ዘንድ አዝዘውናል፡፡ በዚኽም መሠረት አንዲት፣ ቅድስት፣ ሐዋርያዊትና ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በሰማዕትነት ደሙ የተወደደ ልጅ የኾናትን ጣፋጭ መዓዛ ያለው ሽቱ የኾነውን ሰማዕቱን ቅዱስ ሚናስን ታከበረዋለች፤ የከበረ ስሙንም ጠርታ ታመሰግነዋለች፡፡

ከዘመነ አኲስም ዠምሮ የገባሬ ተአምር ቅዱስ ሚናስ በዓለ ዕረፍቱ ይከበራል፡፡ ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድም ለኅዳር ፲፭ በደረሰው መዋሥዕት ላይ "ዘመነነ ክብረ ዘበምድር ዘበሰማያት አብደረ፤ ሚናስ ኅሩይ ሐራሁ ለክርስቶስ ሰማዕተ ኮነ በጽድቅ፡፡ (ሰማያዊውን ክብር አስበልጦ ምድራዊውን ክብር ናቀ፤ የተወደደውና የተመረጠው የክርስቶስ ወታደር ሚናስ በእውነት የክርስቶስ ምሥክር ኾነ፡፡)" በማለት እንደ ወርቅ አንከብሎ እንደ ሸማ ጠቅልሎ የሰማዕቱን ሕይወትና ተጋድሎ በአጭሩ ገልጾታል፡፡

ዳግመኛም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በዚኹ ድርሰቱ "ሚናስ ሰማዕት ኅሩይ፤ በታእካ ሰማይ ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ፡፡ (በሰማያዊው አዳራሽ በመንግሥተ ሰማያት የተመረጥኽ ሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ ስለ እኛ ለምንልን፤ ጸልይልን፡፡)" በማለት ገባሬ መንክራት ቅዱስ ሚናስ በተሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት እንዲያማልደን፤ ጸሎቱና ረድኤቱ እንዳይለየን፣ በረከቱ እንዲያድርብንና በአማላጅነቱ እንዲጠብቀን የተማሕጸኖ ጸሎት አቅርቦለታል፡፡ እኛም ቅዱስ ያሬድን አብነት አድርገን ዘወትር ክቡር ስሙን እየጠራን "የተመረጥኽ ሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ ስለ እኛ የፈጣሪህን ይቅርታና ቸርነትን ለምንልን፤ ጸጋውን እንዲያበዛልን ሥርየተ ኃጢአትን እንዲሰጠን ጸልይልን፡፡" በማለት እንማልደዋለን፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በደሙ ልጅ የኾነላትን ይኽን ታላቅ ሰማዕት ጽሌ ቀርጻ፣ ገድል ጽፋ፣ በአረፍተ መቅደስ ሥዕሉን ሥላ፣ ዕጣን በማሳረግ መሥዋዕት በመሠዋት፣ ዝክር በመዘከር ታከብረዋለች። የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ሚናስ በዓለ ዕረፍቱም በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት መሥዋዕት በመሠዋት፣ ዕጣን በማሳረግ፣ መብራት በማብራትና በስሙ ዝክር በመዘከር ይከበራል።

ማር ሚና በሀገራችን በጣና ቂርቆስ ከሰማዕቱ ከቅዱስ ቂርቆስና ከቅዱስ እስጢፋኖስ ጋር ቤተ መቅደስ ታንጾለት ነበር፡፡ ከባህር ዳር ከተማ በግምት ፳፫ ኪ. ሜ. ርቀት ላይ ከአቡነ ሐራ ድንግል ገዳም አካባቢ በስሙ የታነጸ ቤተ ክርስቲያን ይገኛል፡፡ በተለምዶ አካባቢውም "ሚናስ"እየተባለ ይጠራል። ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል የቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን በአፄ ፋሲል ዘመነ መንግሥት መታነጹን ያስረዳል፤ በዓሉሎለ ዕረፍቱ በዚያ ይከበራል። በተጨማሪም በደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ባቦጋያ መድኃኔ ዓለም፣ በለገ ጣፎ በዳሌ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፣ በሐዋሳ በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዐት በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝማሬ ይከበራል።

በግብጽ በተለያዩ ከተሞች የቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ይገኛል፡፡ ብዙ ክርስቲያኖችም ልጆቻቸውን በስሙ ይጠራሉ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ስድስተኛ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ፓትረያርክ ከመኾናቸው አስቀድሞ መጠሪያ ስማቸው አባ ሚናስ ነበር፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ስድስተኛ ከቅዱስ ሚናስ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ስለ ነበራቸው በስሙ ታላቅ ገዳም አንጸው የከበረ ሥጋውን በዚያ አኑረዋል፡፡ በሰማዕቱ ማር ሚና ጸሎትና አጋዥነት ድንቅ ድንቅ ተአምራት ያደርጉ ነበር፣ ልጅ ያጡ እናቶችም በእርሱ አማላጅነት ልጆች እንዲያገኙና ስማቸውንም ሚናስ እንዲሏቸው ይነግሯቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ሚናስ እጅግ ፈጣን ተራዳኢ ሰማዕት በመኾኑ ዛሬም ብዙዎች በጸሎቱና በአማላጅነቱ ተጠቅመናል፡፡

ቤተ ክርስቲያን ዘወትር በጸሎተ ቅዳሴ ፍጻሜ ንፍቁ ካህን "ወዕቀቦሙ ..." የሚለውን ጸሎት ሲጸልዩ በረከታቸው እንዲያድብን ከሚዘረዘሩት ሰማዕታት አንዱ ሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ ነው፡፡ የሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ ጸሎትና በረከት ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋር ትኹን፤ ገቢረ ተአምራቱ ፈጥኖ ይደረግልን፡፡ አሜን፡፡

የአባቶቻችን ጥርጥር የሌለባት የቀናች ሃይማኖታቸው፣ ድል የማትነሣ ተጋድሏቸው የመንግሥቱ ወራሽ እንድንኾን ያብቃን፡፡ አሜን፡፡

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

23 Nov, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

23 Nov, 03:44


#ቃለ_ወንጌል

14/03/2017
ዮሐንስ 4:47-ፍጻሜ


እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ ሰምቶ ልጁ ሊሞት ስላለው ወደ እርሱ ሄደ ወርዶም እንዲፈውስለት ለመነው። ስለዚህም ኢየሱስ ምልክትና ድንቅ ነገር ካላያችሁ ከቶ አታምኑም አለው። ሹሙም ጌታ ሆይ፥ ብላቴናዬ ሳይሞት ውረድ አለው። ኢየሱስም ሂድ፤ ልጅህ በሕይወት አለ አለው። ሰውዬውም ኢየሱስ የነገረውን ቃል አምኖ ሄደ። እርሱም ሲወርድ ሳለ ባሮቹ ተገናኙትና ብላቴናህ በሕይወት አለ ብለው ነገሩት።

እርሱም በጎ የሆነበትን ሰዓት ጠየቃቸው፤ እነርሱም ትናንት በሰባት ሰዓት ንዳዱ ለቀቀው አሉት። አባቱም ኢየሱስ ልጅህ በሕይወት አለ ባለው በዚያ ሰዓት እንደ ሆነ አወቀ፤ እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር አመነ። ይህም ደግሞ ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ መጥቶ ያደረገው ሁለተኛ ምልክት ነው::

ምስባክ
መዝሙር 26:10-11

እስመ አቡየ ወእምየ ገደፉኒ

ወእግዚአብሔር ተወክፈኒ

ምርሀኒ እግዚኦ ፍኖተከ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

22 Nov, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

22 Nov, 03:52


#ቃለ_ወንጌል

13/03/2017

ማቴዎስ 25:31-ፍጻሜ


የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።

ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።

ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።

ጻድቃንም መልሰው ይሉታል ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ? እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ? ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን? ንጉሡም መልሶ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።

በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ። ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።

እነርሱ ደግሞ ይመልሱና ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል።

ያን ጊዜ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል። እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ::

ምስባክ
መዝሙር 102:20-22

👉ባርክዎ ለእግዚአብሔር ኵልክሙ መላእክቲሁ

ጽኑዓን ወኃያላን እለ ትገብሩ ቃሎ

ወእለ ትሰምዑ ቃለ ነገሩ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

21 Nov, 09:00


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

20 Nov, 16:20


ኦ ሚካኤል ኦ ሚካኤል ኦ መተንብል
ካህነ አርያም ትሰመይ ቢጸ ሱራፌል
ዘእምርኡሳን ረሑስ ወዘእምልዑላን ልዑል
ጊዜ ጸዋእኩከ ቅረበነ በምህረት ወሳህል።

◈◈◈◈◈◈◈
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

20 Nov, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

20 Nov, 03:14


#ቃለ_ወንጌል

11/03/2017
                     ሉቃስ 18:1-9


ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥ እንዲህ ሲል በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ። በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር። አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥ ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ። ጌታም አለዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ።

እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?

ምስባክ
                   መዝሙር 44:9-10

አዋልደ ንግሥት ለክብርከ

ወትቀውም ንግሥት በየማንከ

በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

19 Nov, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

19 Nov, 03:52


#ቃለ_ወንጌል

10/03/2017
ማቴዎስ 25:1-14

በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች። ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ። ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤ ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ። ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።

እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ። በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ። ሰነፎቹም ልባሞቹን መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው።ልባሞቹ ግን መልሰው ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሉአቸው።

ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፥ ደጁም ተዘጋ። በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ክፈትልን አሉ። እርሱ ግን መልሶ

እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ::

ምስባክ
መዝሙር 68:10-11

👉ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ

ወኮነኒ ጽእለተ

ለበስኩ ሠቀ ወኮንክዎሙ ነገረ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

18 Nov, 12:24


ሰይጣን የኢዮብን ሀብት ሲያወድምበት ፣ ዐሥር ልጆቹን ሲገድልበት ፣ ጤናውን ሲወስድበት አንድ ነገር ግን አልነካበትም::

ሚስቱን::

ለምን?

ሚስቱን ያልነካው ምናልባት ነገረኛ ቢጤ ስለሆነች ከኢዮብ መከራ ውስጥ ተቆጥራ ይሆን?  ሰይጣን ሚስቱን ያልነጠቀው " ታንገብግበው" ብሎ ይሆን?  

ጠቢቡ "በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው" ይላል:: ምሳ.27:15 ምናልባት በሰይጣን እይታ ኢዮብን ለማማረር ሚስቱ መቆየት ነበረባት ይሆን?

በእርግጥ የኢዮብ ሚስት "ፈጣሪን ሰድበህ ሙት" የምትል መሆንዋን ስናይ ለኢዮብ ፈተና እንድትሆን ይሆናል ሳንል አንቀርም:: ሰይጣንም እንዲህ ብናስብ አይጠላም::

ነገሩ ግን ወዲህ ነው:: ሰይጣን የኢዮብን ሚስት እንዳይነካት ያደረገው የራሱ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነበር::

"ሕይወቱን ተወው እንጂ እነሆ እርሱ በእጅህ ነው" ብሎ እግዚአብሔር ለሰይጣን አስጠንቅቆት ነበር:: ሕይወቱን አትንካ የተባለው ሰይጣን ሌላውን ሁሉ ሲያጠፋ ሚስቱን ግን ያልነካው ሚስት ሕይወት ስለሆነች ነው:: ሚስቱን መንካትም ራሱን ኢዮብን መንካት ነበር:: አዎ ሚስት ሕይወት ናት:: እንደ ኢዮብ ሚስት ብትከፋም እንደ ምሳ. 31ዋ ሚስት መልካም ብትሆንም ሕይወት ናት:: ሕይወት ደስታም ኀዘንም አለበት::  "ሕይወት እንዲህ ናት" c'est la vie እንዲል ፈረንሳይ:: ራሱ ኢዮብም "በምድር ላይ የሰው ሕይወት ብርቱ ሰልፍ አይደለምን?" ብሎአል:: ኢዮ. 7:1

አዳምም አለ :-

"ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ ናት"

"አዳምም ሔዋንን ሕይወቴ ነሽ ይላት ነበር"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

18 Nov, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

18 Nov, 02:30


#ቃለ_ወንጌል

09/03/2017

     ዮሐንስ 10:25-ፍጻሜ


   ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል ነገርኋችሁ፡ አታምኑምም፡ እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ይህ ስለ እኔ ይመሰክራል፤ እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም። በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤ እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።

የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም። እኔና አብ አንድ ነን።

አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ። ኢየሱስ ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ ማናቸው ሥራ ትወግሩኛላችሁ? ብሎ መለሰላቸው።አይሁድም ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት።

ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው እኔ አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን? መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፡ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን ትሳደባለህ ትሉታላችሁን? እኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ፤ ባደርገው ግን፥ እኔን ስንኳ ባታምኑ አብ በእኔ እንደ ሆነ እኔም በአብ እንደ ሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ።

እንግዲህ ደግመው ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም ወጣ። ዮሐንስም በመጀመሪያ ያጠምቅበት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ እንደ ገና ሄደ በዚያም ኖረ። ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ መጥተው ዮሐንስ አንድ ምልክት ስንኳ አላደረገም፥ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነበረ፡ አሉ። በዚያም ብዙዎች በእርሱ አመኑ::


                              ምስባክ
                        መዝሙር 72:8-9


👉ወነበቡ ዓመፃ ውስተ ዓርያም

     ወአንበሩ ውስተ ሰማይ አፉሆሙ

     ወአንሶሰወ ውስተ ምድር ልሳኖሙ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

17 Nov, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

16 Nov, 09:00


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

16 Nov, 03:49


#ቃለ_ወንጌል

07/03/2017
ማቴዎስ 10:16-ፍጻሜ


እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤ ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ። አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና።

ወንድምም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ ይገድሉአቸውማል። በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም። ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፥ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም። ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው! እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና። በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ። ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።

ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል። እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ። ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ። በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም። ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤ ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል። ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።

ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል። እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም::

ምስባክ
                                 መዝሙር 78:10-11

ወይርአዪ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ

በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ

ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

15 Nov, 09:22


#ቃለ_ወንጌል

06/03/2017
ማቴዎስ 2:19-ፍጻሜ

ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ። እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ። በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ መሄድን ፈራ፤ በሕልምም ተረድቶ ወደ ገሊላ አገር ሄደ፤ በነቢያት ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ::

ምስባክ
መዝሙር 36:35-36

ርእክዎ ለኃጥእ ዐብየ ወተለዐለ ከመ አርዝ ሊባኖስ

ወሶበ እገብእ ኀጣእክዎ

ኀሠሥኩ ወኢረከብኩ መካኖ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

15 Nov, 03:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

14 Nov, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

14 Nov, 03:30


#ቃለ_ወንጌል

05/03/2017
                ዮሐንስ 19:31-ፍጻሜ


      አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ሆነ ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት። ጭፍሮችም መጥተው የፊተኛውን ጭን ከእርሱም ጋር የተሰቀለውን የሌላውን ጭን ሰበሩ፤ ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም፤ ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውኃ ወጣ።

ያየውም መስክሮአል፤ ምስክሩም እውነት ነው፤ እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል። ይህ የሆነ ከእርሱ አጥንት አይሰበርም የሚል የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው። ደግሞም ሌላው መጽሐፍ የወጉትን ያዩታል ይላል። ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት።

ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ። ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ። የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት። በተሰቀለበትም ስፍራ አትክልት ነበረ፥ በአትክልቱም ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ። ስለዚህ መቃብሩ ቅርብ ነበረና ስለ አይሁድ ማዘጋጀት ቀን ኢየሱስን በዚያ አኖሩት::

                                          ምስባክ
                                    መዝሙር 24:7-8

ኃጢአትየ ዘበንዕስየ ወዕበድየ ኢትዝክር ሊተ

ወበከመ ሣህልከ ተዘከረኒ

በእንተ ምሕረትከ እግዚኦ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

13 Nov, 16:56


የቅዱሳን አማልጅነት....
እኛ አግዚአብሔርን ስንለምን....

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

13 Nov, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

12 Nov, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

12 Nov, 03:25


#ቃለ_ወንጌል

ማቴዎስ 12 ÷9-14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
ከዚያም አልፎ ወደ ምኩራባቸው ገባ። ¹⁰ እነሆም፥ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤ ይከሱትም ዘንድ። በሰንበት መፈወስt ተፈቅዶአልን? ብለው ጠየቁት። ¹¹ እርሱ ግን፦ ከእናንተ አንድ በግ ያለው በሰንበት በጉድጓድ ቢወድቅበት፥ ይዞ የማያወጣው ሰው ማን ነው?

¹² እንግዲህ ሰው ከበግ ይልቅ እንደምን አይበልጥም! ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዶአል አላቸው። ¹³ ከዚያም በኋላ ሰውየውን፦ እጅህን ዘርጋ አለው። ዘረጋትም፥ እንደ ሁለተኛይቱም ደህና ሆነች። ¹⁴ ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት።

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

11 Nov, 18:30


#ኦርቶዶክሳዊነት

ሰይጣንን አምርረን እንደምንጠላው እውነት ነው። ነገር ግን የፈለገ ብንጠላው የበለጠ ሰው ይጠላው ዘንድ ብለን ያልሆነውን ነው አንልም። ለመጠላት የሚያበቃ የራሱ በቂ ማንነት አለውና። ለምሳሌ ረቂቁ ሰይጣን ከአንዲት ሴት ጋር ተገናኝቶ ክፉ ልጅ ወለደ አንልም። የረቂቁ ሰይጣን መውለጃ ወይም መሽኛ የለውምና። እርሱን ለማስጠላት ብለን ያልሆነውን ነው አንልም። ኦርቶዶክሳዊነት ሁሉን እንደአመጣጡ መመለስ ነው። ባለፈው ጊዜ እነአባ ሳዊሮስ ቀኖና አፍርሰው አንቀጽ ጠቅሰን ስሕተት መሆናቸውን ስንናገር አንዳንድ ሰዎች "ኦሮሞ ስለሆኑ ነው" የሚል ውሸት ፈጠሩ። ከዐውድ ወጥተው የራሳቸውን ዐውድ ፈጠሩ። ጽሑፋችንን ከዐውዱ አውጥተው (detaching the text from the context) እንዲሉ ጽሑፋችንን ንግግራችንን ከዐውዱ ለይተው ለማሳሳት ሞከሩ። ይህ ኦርቶዶክሳዊነት አይደለም።

መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ለአባ ተክለ ሃይማኖት የተሳሳተ ትምህርት መልስ ሲሰጡ አክብሮታቸው እንዳለ ሆኖ ነው። ጉዳዩን ነቅሰው ይሞግቱታል። ኦርቶዶክሳዊነት እንዲህ ነውና። ባለጉዳዩን ከጉዳዩ ነጥሎ ለማጥቃት መጣር የደካሞች መንገድ ነው። ጌታ ኃጢአተኛን እንደሚወድ ኃጢአትን እንደሚጠላ ተነግሯል። ለኦርቶዶክሳዊነት መለኪያው ሐሳቡ ምን ያህል እውነት ነው የሚለው ነው እንጂ ሐሳቡን ምን ያህል ሰው ይወደዋል የሚል አይደለም። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ሐዋርያት፣ ቅዱሳን ሊቃውንት ያስተማሩን ይህንን ነው። እውነታውን ሲናገሩ ሐዋርያት የተናገሩትን እውነት በተለያየ ምክንያት መሸከም ያልቻሉ ሰዎች ሐዋርያትን ይሳደቡ፣ ክፉ ስም ይሰጡ፣ ይደበድቡ፣ ይገድሉ ነበረ። ብንሰድባቸው፣ ብንገድላቸው፣ ክፉ ስም ብንሰጣቸው፣ ብንደበድባቸው የያዙትን እውነት ከመመስከር ይታቀባሉ ብለው ስላሰቡ ነው። ሐዋርያዊነት ግን ምንም ነገር ቢመጣ እስከ ሞት የሚታመኑለት እንጂ ሺ ዓመት ለማይኖርባት ዓለም አድር ባይ ሆኖ መኖር አይደለም።

አይሁድ መጽሐፍ ላይ ያልተጻፈ ራሳቸው የጨመሩት ወግ ነበራቸው። ያንን ወግ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ልክ እንዳልሆነ ቢነግራቸው ጠሉት። ሕዝብን አነሣስተው እስከመሰቀል አደረሱት። እውነት በአደባባይ ተሰቀለች። ሁልጊዜም እውነት አሸናፊ ናት። ቀጥ ያለ አመለካከት ይኑረን። ከመፍረድና ከመተቸት በፊት ያልገባንን በሥርዓት እንጠይቅ። አንድን ጉዳይ ምን ያህል አውቀዋለሁ የሚለውን ሳንረዳ በመጽሐፍ ሳይሆን ልማድን ብቻ መሠረት አድርገን ለመንቀፍ አንቸኩል። ከጉዳዩ አናፈንግጥ። የማናውቀው ጉዳይ ካለ አናውቀውም እንበል። እንደ ሦስቱ መስማት የተሳናቸው ሰዎች አንሁን። አንዱ መስማት የተሳነው ፍየል ጠፍታው ሊፈልግ ሲሄድ አንዲት መስማት የተሳናት እናት ጤፍ ስታርም ያገኛታል። እና ፍየል አየሽ ወይ ብሎ ሲጠይቃት ያው መስማት ሰለማትችል አረም እንዴት ነው ብሎኝ ይሆናል ብላ በግምት ይህንን አረምኩ ብላ በጣቷ እየጠቆመች ታሳየዋለች። እርሱም ፍየሊቱ ያለችበትን የጠቆመችው መስሎት ወደ ጠቆመችው ቦታ ሲሄድ ፍየሏ ተሰብራ ያገኛታል። ፍየሊቱን ይዞ መጥቶ ተገኝታለች ለአንቺ ሸልሜሻለሁ ይላታል። ከዚያ አንቺ ነሽ የሰበርሽው ያላት መስሏት እረ እኔ አልሰበርኳትም ብላ ተከራከረች። ጉዳዩ ምንድን ነው ብሎ ሌላ መስማት የተሳነው ሰው ይመጣል። እና አትከራከሩ ያዘለችው ልጅ አንተን ስለሚመስል እመን የአንተ ልጅ ነው አለው ይባላል። በልጁ የተጣሉ መስሎት።

ሁሉም የየራሳቸውን ስሜት ብቻ ተከትለው ተናገሩ እንጂ እውነታው ከሁሉም አልነበረም። ጉዳዩን ቀጥታ መመለስ እንጂ ከጉዳዩ ያፈነገጡ ሌላ ሐሳቦችን መናገር አይገባም። መምህራን ደግሞ አድርባይነትን መጸየፍ አለብን። እወደድ ባይነትን ትተን እውነታው ላይ ማተኮር ይገባል። ሞት ካልቀረ እውነቱን ተናግሮ መሞት ነው። እውነትን መናገር ከሞት ያድናል። አድር ባይ መሆን ደግሞ ሞትን ይፈጥራል። ርቱዕ እንሁን። ወደነፈሰበት መንፈስ ሳይሆን እውነታውን መያዝ ይገባል። አንዳንድ መምህራን በሰዎች ስድብ ተማረው የራቁ አይቻለሁ። ስሕተት ነው። ሰው የፈለገውን ይናገር። እግዚአብሔር የሰጠውን ነጻ ፈቃድ አንከልክለው። ራሱ ካልተጎዳበት እስከፈለገው ድረስ ይሳደብ ይናገር። የሚጨምርልን ክብር እንጂ የሚቀነስብን ነገር የለም። መፍራት ያለብን ሙገሳን ከንቱ ውዳሴን ነው እንጂ መሰደብንማ ከሽልማት ነው መቁጠር ያለብን። የትዕግሥትን ዋጋ የሚያሰጠን ድንቅ ስጦታ እንደሆነ ነው ማሰብ ያለብን። የሚያኖረን እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ልናፍረውም ልንፈራውም የሚገባን እርሱን ነው። ጌታ አይሁድ እንዳይቀየሙ ብሎ ያልተናገረው እውነት የለም።

ኦርቶዶክሳዊ እንሁን።

© በትረ ማርያም አበባው
(የመጻሕፍተ ብሉያት፣ የመጻሕፍተ መነኮሳት፣ የመጻሕፍተ ሊቃውንት ትርጓሜ መምህር)

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

11 Nov, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

11 Nov, 03:09


#ቃለ_ወንጌል

02/03/2017
ዮሐንስ ፲÷፩-፳፪

እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤ በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው። ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል። የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና። ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ምን እንደ ሆነ አላስተዋሉም። ኢየሱስም ደግሞ አላቸው እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ። ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም።

በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል። ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል በጎቹንም ይበትናቸዋል። ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።

መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ። ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ። ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ። እንግዲህ ከዚህ ቃል የተነሣ በአይሁድ መካከል እንደ ገና መለያየት ሆነ። ከእነርሱም ብዙዎች ጋኔን አለበት፡ አብዶአልም፤ ስለ ምንስ ትሰሙታላችሁ? አሉ። ሌሎችም ይህ ጋኔን ያለበት ሰው ቃል አይደለም፤ ጋኔን የዕውሮችን ዓይኖች ሊከፍት ይችላልን? አሉ።

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

10 Nov, 22:06


https://youtube.com/shorts/AE2e7CSUoHo?si=MhoOuFpnC1unsF1f

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

10 Nov, 10:37


ንብ የምትሞተው መቼ ነው?
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

“የጥበበኛ ነፍስ መገለጫዋ ይሄ ነውና ሁል ጊዜ የምታመሰግኑ ሁኑ፡፡ ክፉ ደረሰባችሁን? ይህስ እናንተ ከፈቀዳችሁ ክፉ አይደለም፡፡ ሁል ጊዜ አመስግኑ፤ ክፉ የሆነባችሁም መልካም ይሆንላችኋል፡፡ ከተወደደው ኢዮብ ጋር ሆናችሁ “የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን” እያላችሁ አመስግኑ /ኢዮብ.1፥21/፡፡

እስኪ ንገሩኝ! ደረሰብኝ የምትሉት ክፉ ነገር ምንድነው? በሽታ ነውን? ታድያ ይሄ እኮ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሥጋችን መዋቲና ለስቃይ የተጋለጠ ነውና፡፡ ሀብት ንብረት ማግኘት አለብኝ የሚል መሻት ነውን? ታድያ ይሄ እኮ ምግኘት የሚቻል ነው፤ ካገኙት በኋላ ግን መልሶ የሚጠፋና በዚህ ዓለም ብቻ የሚቀር ነው፡፡ ከወንድሞች የሚደርስ ሐሜትና የሐሰት ወቀሳ ነውን? ታድያ ተጐጂዎቹ’ኮ የሚያሙንና በሐሰት የሚመሰክሩብን እንጂ እኛው አይደለንም፡፡ “ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ ትሞታለች” እንዲል ተጐጂዎቹ ይህን ኃጢአት የሚሠሩት እንጂ እኛው አይደለንም /ሕዝ.18፥4/፡፡ ተጐጂው ምንም በደል ሳይኖርበት ክፉ የሚደርስበት ሰው ሳይሆን ክፉ የሚያደርሰው ሰው ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ምዉት በሆነ ሰው ልትቈጡ አይገባም፤ ከዚያ ይልቅ ከሞት ይድን ዘንድ ልትጸልዩለት ይገባል፡፡

ንብ መቼ እንደምትሞት አይታችሁ ታውቃላችሁን? የምትሞተው ሌላውን ስትናደፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር በዚህች ፍጥረት በወንድሞቻችን ላይ ልንቈጣ እንዳይገባን ያስተምረናል፡፡ እኛው የምንቈጣ (የምንናደፍ) ከሆነ ግን ቀድመን የምንሞተው እኛው ነን፡፡ ስንቈጣቸው የጐዳናቸው ይመስለን ይሆናል፤ ነገር ግን እንደዚያች ንብ ተጐጂዎቹ እኛው ነን፡፡”

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

10 Nov, 09:00


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

09 Nov, 10:18


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

09 Nov, 03:54


#ቃለ_ወንጌል

30/02/2017
           
ማቴዎስ 16÷24-ፍጻሜ

    በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል። እውነት እላችኋለሁ፥ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ
አሉ::

  ምስባክ
                                 መዝሙር 26:6-7

ናሁ ይእዜ አልዐለ እግዚአብሔር ርእስየ ዲበ ጸላእትየ

ዖድኩ ወሦዕኩ ውስተ ደብተራሁ መሥዋዕተ

ወየበብኩ ሎቱ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

08 Nov, 12:31


#የጌታ_ስቅለት_በአበው

"አደምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" #ቅዳሴ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

“እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማሥተሥረይ መከራ ተቀበለ እንዳለ፣ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲሆን በሥጋ የታመመ ነው፤ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል አለ፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ሁሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን፡፡” #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ሊቀ_ጳጳስ

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡›› #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

‹‹ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፤ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዐት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዛ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ›› #ቅዱስ_ቄርሎስ_ዘእስክንድርያ
    
‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ሁሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለሁሉ ሕይወትን ሰጠ››  #ቅዱስ_አቡሊዲስ_ዘሮም

‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፣ ተጠማ እንጂ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን ከመጸብሐን ጋር በላ ጠጣ፤ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፤ እጁን እግሩን ተቸነከረ፤ ጎኑን በጦር ተወጋ፤ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ /ወጣ/፡፡›› #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳሪያ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

08 Nov, 09:00


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

08 Nov, 03:44


#ቃለ_ወንጌል

29/02/2017
ማርቆስ ፰÷፴፬-ፍጻ-፱:፩-፪


ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ እንዲህ አላቸው በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል። ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? በዚህም በዘማዊና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል............ ..

......እውነት እላችኋለሁ፥ በዚህ ከቆሙት ሰዎች የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ስትመጣ እስኪያዩ ድረስ፥ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ፡ አላቸው። ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ልብሱም አንጸባረቀ
::

ምስባክ
መዝሙር 17:39-40

ወታቀንተኒ ኃይለ በፀብዕ

አዕቀፅኮሙ ለኵሎሙ እለ ቆሙ ላዕሌየ በመትሕቴየ


ወመጠውከኒ ዘባኖሙ ለፀርየ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

07 Nov, 16:48


#reposted 😇😇😇😇

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

26 Oct, 14:29


🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ማህሌተ ጽጌ ዘራብዕ ሣምንት በዓለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁

ለማንኛውም ወርኃዊ እና ዓመታዊ ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
.....................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

@EOTCmahlet
መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም።
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
ብፁዕ እስጢፋኖስ ምስለ ኵሎሙ ቅዱሳን፤ለከ የዓርጉ ስብሐተ እግዚአ ለሰንበት አሠርጎካ ለምድር በስነ ጽጌያት፤ወሠራዕከ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ጸዐዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ ።
@EOTCmahlet
ወረብ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እንዘ ተሐቅፊዮ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ/፪/
ንዒ ርግብየ  ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ቃልኪ አዳም ይጥዕመኒ እምአስካለ ወይን አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናግሮ በዓምደ ደመና እሞሙ ይእቲ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናገሮ በዓምደ ደመና።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ  ማርያም  ቀጸላ  መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ይእቲ ተዓቢ እምአንስት እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት መድኃኒቶሙ ለነገሥት አክሊል ንጹሕ ለካህናት ብርሃኖሙ ለከዋክብት ።
@EOTCmahlet
ማሕሌተ ጽጌ
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም ይገብር መንክረ፤እንዘ ጻእረ ሞት ያረስዕ ወያሰተጥዕም መሪረ፤በመአዛ ጽጌኪሰ ለዘበአውደ ስምዕ ሰክረ፤ውግረተ አዕባን ይመስሎ ኀሠረ፤እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ።
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ውግረተ አዕባን ውግረተ አዕባን ኀሠረ ይመስሎ ይመስሎ ኀሠረ/፪/
ለዘበአውደ ስምዕ ሰክረ በመአዛ ጽጌኪ እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ/፪/
ዚቅ
ሐሙ ርኀቡ ጸምዑ ወተመንደቡ፤ ዘኢይደልዎ ለዓለም ረከቡ፤ ቦ እለ በእሳት ወቦ እለ በኵናት፤ ቦ እለ በውግረተ ዕብን ወቦ እለ በመጥባሕት ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ አስበ ፃማሆሙ ነሥኡ ሰማዕት ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ፅጌ፦
ዘንተ(ዘኒ) ስብሐተ ወዘንተ(ወዘኒ) ማኅሌተ፤ተአምርኪ ጸገየ ወፈረየ ሊተ፤ከመ እሰብሕ ዳግመ እንዘ እጸውር ፀበርተ፤ምስለ እለ ሐፀቡ ኣልባሲሆሙ በደመ በግዑ ድርገተ፤ውስተ ባሕረ ማኅው ድንግል ክፍልኒ ቁመተ።
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ምስለ እለ ሐጸቡ አልባሲሆሙ አልባሲሆሙ በደመ በግዑ/፪/
ክፍልኒ ቁመተ ድንግል ድንግል ውስተ ባህረ ማኅው/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
ገጹ ብሩህ ከመ ፀሐይ ወእምኵሉ ስነ ሠርጐ ሰማይ ለጊዮርጊስ ኅሩይ ዘተወልደ እመንፈስ ቅዱስ ወማይ አልባሲሁ በደመ በግዕ ዘሐፀበ ወእምሠረቅት መርዔቶ ዓቀበ ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ሰቆቋወ ድንግል
ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤ኢየሱስ ግፉዕ  ምስካዮሙ ለግፉዓን፤እግዚአብሔር ማኅደር  ዘአልቦ  ከመ  ነዳያን፤ ኢየሱስ ነግድ  ወፈላሲ እንዘ ውእቱ ሕጻን፤ወልደ አብ ፍቁር  ዘበኀበ ሰብእ ምኑን፤መኃልየ  ብካይ ኮነኒ ዘእሙ  ኃዘን።
@EOTCmahlet
ወረብ
ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን/፪/
መኃልየ ብካይ ኮነኒ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
አንተ ውእቱ ምርጕዞሙ ለጻድቃን፤ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤መርሶሙ ለእለ ይትሀወኩ፤ብርሃነ ፍጹማን ወልደ አምላክ ሕያው ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መዝሙር
በ፭
ጳጳሳት ቀሳውስት ወዲያቆናት፤ሊቃነ ካህናት ሥዩማነ ቤተክርስቲያን፤እለ ሎሙ ሕግ ወሎሙ ሥርዓት፤ብፁዕ እስጢፋኖስ ምስለ ኵሎሙ ቅዱሳን፤ለከ የዓርጉ ስብሐተ፤ እግዚኣ ለሰንበት አሠርጎካ ለምድር በስነ ጽጌያት፤ወሠራዕኮ ሰንበተ ለሰብአ ዕረፍተ፤ ወብውህ ለከ ትኅድግ ኃጢአተ ረቢ ንብለከ ረቢ፤ሊቅ ነአምን ብከ ።


🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCmahlet👈                 
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @EOTCmahlet
    # Join & share

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

26 Oct, 09:23


አንድ ምድራዊ ንጉሥ "ጠላቱን ያልወደደ ሠው በሞት ይቀጣል" ብሎ ዐዋጅ ቢያውጅ ኹሉም ሠው በዐካለ ሥጋ ላለመሞት ሢል ሕጉን ለመጠበቅ የሚፋጠን ዐይደለምን?

ወዮ! ምድራውያን ነገሥታት በሥጋዊ ሞት ዕንዳይቀጡን ብለን ፈርተን የሚያወጡትን ሕግ ለመፈፀም የምንፋጠን ኾነን ሣለ፥ ለነገሥታት ንጉሥ ለ እግዚአብሔር ሕግ ዐለመታዘዛችን ዕንደ ምን ያለ ወቀሣ ያመጣብን ይኾን?

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

26 Oct, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

ድንግል እንዴት ቻልሺው ያንን ህማም 🙏🙏🙏

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

26 Oct, 03:41


#ቃለ_ወንጌል

16/02/2017
              ማቴዎስ ፭÷፩-፲፮


      ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና። የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና። ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና። የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።

ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና። የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና። ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና። እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል::


                             ምስባክ
                       መዝሙር 21:4-5

ኪያከ ተወከሉ አበዊነ

ተወከሉከኒ ወአድኀንኮሙ

ኀቤከ ጸርሑ ወድኅኑ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

25 Oct, 17:32


"ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ሁሉ ግን የሚጠቅም አይደለም ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ነገር ግን ሁሉ የሚያንጽ አይደለም"
1ቆሮ10÷23

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

25 Oct, 09:00


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

ድንግል እንዴት ቻልሺው ያንን ህማም 🙏🙏🙏

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

25 Oct, 03:26


#ቃለ_ወንጌል

15/02/2017

ማቴ ፲፰÷፲፪-፳


ምን ይመስላችኋል? ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢባዝን፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን? ቢያገኘውም፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልባዘኑቱ ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል።

እንደዚሁ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ በሰማያት ያለው አባታችሁ ፈቃድ አይደለም። ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።

እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል። ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል። ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና::
ምስባክ
መዝሙር 21:22-23

እነግሮሙ ስመከ ለአኀውየ

በማዕከለ ማኅበር እሴብሐከ

እለ ትፈርኅዎ ለእግዚአብሔር ሰብሕዎ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

24 Oct, 11:38


"መጥፎ ቀን እና ጥሩ ቀን የሚባል ነገር የለም። ያለው ጸሎት አድርገህ የወጣህበት ቀን እና ጸሎት ሳታደርግ የወጣህበት ቀን ነው። ያልጸለይክባቸው ቀናት በክፉ ምኞትና የሥጋ ፍላጎት የተሞሉ ስለሆኑ ክፉ ቀናት ናቸው።"


— ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

24 Oct, 09:00


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

ድንግል እንዴት ቻልሺው ያንን ህማም 🙏🙏🙏

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

23 Oct, 09:52


#ቃለ_ወንጌል

13/02/2017

ሉቃስ ፲፪÷፳፯-፴፪

አበቦችን እንዴት እንዲያድጉ ተመልከቱ፤ አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዲቱ አለበሰም። እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን በሜዳ የሆነውን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጐደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት? እናንተም የምትበሉትን የምትጠጡትንም አትፈልጉ፥ አታወላውሉም፤ ይህንስ ሁሉ በዓለም ያሉ አሕዛብ ይፈልጉታልና፤ የእናንተም አባት ይህ እንዲያስፈልጋችሁ ያውቃል። ዳሩ ግን መንግሥቱን ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል::

ምስባክ
መዝሙር 91:12-13

ጸድቅሰ ከመ በቀልት ይፈረ

ወይበዝን ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ

ትኩላን እሙንቱ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

23 Oct, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

ድንግል እንዴት ቻልሺው ያንን ህማም 🙏🙏🙏

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

22 Oct, 09:49


በሽታ ከሰው ወደ ሰው እንደሚጋባ ሁሉ ጤንነትም ከሰው ወደ ሰው ይጋባል ጤናማ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር መዋል ጤናማ ያደርጋል!

መጽሐፍም እንዲህ ይላል “ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።” መዝሙር 18፥25-26


አብራችሁ የምትውሏቸው ሰዎች በእናተ ሕይወት ላይ በጎም ክፉም ተጽኖ አላቸው። ማንነታችሁ የሚወሰነው አብራችሁ በምትውሏቸው ሰዎች ነውና አብሯችሁ የሚውሉ ሰዎችን ምረጡ ። መልካም ነገር እንኳን ቢኖራችሁ “አትሳቱ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።” 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥33 እና ተጠንቀቁ::

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

22 Oct, 09:00


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

ድንግል እንዴት ቻልሺው ያንን ህማም 🙏🙏🙏

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

22 Oct, 03:51


#ቃለ_ወንጌል

12/02/2017
ማቴዎስ ፱÷፱-፴፪

ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው። በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ እነሆ፥ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች መጥተው ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብረው ተቀመጡ። ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል? አሉአቸው።

ኢየሱስም ሰምቶ ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤ ነገር ግን ሄዳችሁ፦ ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም፡ ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና አላቸው። በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ። በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።

በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ። ይህንም ሲነግራቸው፥ አንድ መኰንን መጥቶ ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች እያለ ሰገደለት። ኢየሱስም ተነሥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተከተለው። እነሆም፥ ከአሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም የሚፈስሳት ሴት በኋላው ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤ በልብዋ ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ፥ እድናለሁ ትል ነበረችና። ኢየሱስም ዘወር ብሎ አያትና ልጄ ሆይ፥ አይዞሽ፤ እምነትሽ አድኖሻል አላት። ሴቲቱም ከዚያች ሰዓት ጀምራ ዳነች። ኢየሱስም ወደ መኰንኑ ቤት በደረሰ ጊዜ፥ እምቢልተኞችንና የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ፈቀቅ በሉ አላቸው። በጣምም ሳቁበት።

ሕዝቡን ግን ከአስወጡ በኋላ ገብቶ እጅዋን ያዛት፥ ብላቴናይቱም ተነሣች። ያም ዝና ወደዚያ አገር ሁሉ ወጣ። ኢየሱስም ከዚያ ሲያልፍ ሁለት ዕውሮች የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረን ብለው እየጮሁ ተከተሉት። ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፥ ኢየሱስም ይህን ማድረግ እንድችል ታምናላችሁን? አላቸው። አዎን፥ ጌታ ሆይ አሉት። በዚያን ጊዜ እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ ብሎ ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ። ዓይኖቻቸውም ተከፈቱ። ኢየሱስም ማንም እንዳያውቅ ተጠንቀቁ ብሎ በብርቱ አዘዛቸው። እነርሱ ግን ወጥተው በዚያ አገር ሁሉ ስለ እርሱ አወሩ::

ምስባክ
                            መዝሙር 83:6-7

እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ

ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል

ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

21 Oct, 09:51


"ዝንብ ነን ንብ? "

በሰው ላይ የሚፈርዱትን ዝንቦች እንዳልኳቸውና ይህንንም ያልኩት በተገቢ እንደሆነ አስታውሳቸዋለሁ። ዝንቦች ማንዣበባቸውና ውሏቸው በሌሎች ቁስል ላይ እንደሆነ ሆነ ሁሉ ከሳሾች የሆኑ ሰዎችም የሌሎችን በኃጢያት የቆሰለ አካል ይነክሳሉ። በዚህም የኃጢያትን በሽታ ቀስመው ወደ ጤነኛ ሰው ያስተላልፋሉ።

ከዚህ በተቃራኒ የሚያደርጉት ደግሞ ንቦች ብዬ ሰይሜቸዋለው። በሽታን ሳይሆን ማር የሚሰሩበትን አበባ ይቀስሙ ዘንድ በታላቅ ትጋት ሆነው ወደ ቅዱሳን የሕይወትና የተጋድሎ የአባባ መስክ ይበራሉና።"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

21 Oct, 09:00


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

ድንግል እንዴት ቻልሺው ያንን ህማም 🙏🙏🙏

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

21 Oct, 05:08


የመስቀል ዓይነቶች ፡ ክፍል ፩

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

21 Oct, 03:00


#ቃለ_ወንጌል

11/02/2017
                  ማቴዎስ ፭÷፲፩-፲፮

      ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።

እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል::

ቅዳሴ :-   ዘእግዝእትነ  (ማርያም)   
  
                                 ምስባክ
                            መዝሙር 83:6-7

እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ

ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል

ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

20 Oct, 09:18


3ተኛ ሳምንት ማህሌተ ፅጌ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

20 Oct, 09:10


ክርስቲያን” ተብለህ መጠራትህ ዋስትና አይኾንህም፤ ዋስትና የሚኾንህ …

በመንገድ ዳር ላይ ዘርን የሚዘሩ ሰዎች ምንም የሚያገኙት ጥቅም እንደ ሌለ ኹሉ፥ እኛም ለልጅነታችን የሚገባ’ ምግባር ከሌለን ክርስቲያኖች ተብለን ከመጠራት የምናገኘው በቁዔት የለም፡፡ ይህ እንዴት ይኾናል የምትለኝ ከኾነም የጌታችን ወንድም የተባለው ያዕቆብን ምስክር አድርጌ እነግርሃለሁ፡፡ እርሱ፡- “ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው” ብሎአልና (ያዕ.2፡17)፡፡ ስለዚህ ለእኛ (ለክርስቲያኖች) ምግባር መያዝ ግዴታ ነው፡፡ ምግባር ከሌለን ግን “ክርስቲያን” የሚለው ስም ለእኛ የሚፈይደው ምንም ነገር የለም፡፡

በዚህ ተደነቅህን? እንኪያስ ንገረኝ ! በዓውደ ውጊያ የማይሳተፍ፣ ለሚመግበው ንጉሥም የማይዋጋ ከኾነ አንድ ወታደር ወታደር ተብሎ ቢጠራ ምን ጥቅም አለው? ለንጉሡ ክብር የማይዋጋ ከኾነስ ወታደር ተብሎ ባይጠራ ይሻለዋል፡፡ ይህ ሰው በንጉሡ የሚመገብ ኾኖ እያለ፥ ነገር ግን ንጉሡ በጠላቱ ላይ ድል እንዲያደርግ የማይዋጋ ከኾነ እንዴት ከቅጣት ሊያመልጥ ይችላል? ንጉሡን ምሳሌ አድርጌ ልናገረው የፈለግሁትስ ምንድን ነው? ልለው የፈልገሁት እግዚአብሔር በትንሹ ስለ ገዛ ነፍሳችን እንድንጠነቀቅ (ምግባር መያዝ እንድንችል) ኃይል (ዓቅም) ሰጥቶናል ነው፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

20 Oct, 09:01


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

ድንግል እንዴት ቻልሺው ያንን ህማም 🙏🙏🙏

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

19 Oct, 10:45


🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ስርዓተ ማሕሌት ዘሣልሳይ ጽጌ በዓለ መስቀል
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ  በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡
@EOTCmahlet
ዚቅ
ዝኬ ዘተዘርዓ ቃለ ጽድቅ በትውክልተ መስቀል፤ ወፍሬሁኒ ኮነ መንፈሰ ህይወት፤ ተስፋሆሙ ለእለ ድኅኑ፤ ወበጽጌሁ አርዓየ ገሃደ አምሳለ ልብሰተ መለኮት፤ ዕቊረ ማየ ልብን፤ ጽጌ ወይን ተስፋሆሙ ለጻድቃን።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል፤ ወጸገይኪ ጽጌ በኢተሰቅዮ ማይ ወጠል፤ ወበእንተዝ ያሬድ መዓርዒረ ቃል፤ ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ወይብል፤ ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል።
@EOTCmahlet
ወረብ፦
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል/፪/
ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ያሬድ ወይብል ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ወባቲ ይገብሩ ተአምረ በውስተ አህዛብ እስመ አርአያ መስቀል ይዕቲ
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤ካዕበ (ወካዕበ) ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤ ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ።
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እም/፪/
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet 
ዚቅ
እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ወእምኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ከመ ትኩኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለመ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ
@EOTCmahlet
ወረብ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ተመየጢ ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ በአምሳለ ወርቅ ይግበሩ ለኪ ኮሰኮሰ ዘብሩር፤ አመ ወለደቶ አርአያ ወሰደቶ፤ በትእምርተ መስቀል፤ ትፍሥሕትኪ ውእቱ፤ ብርሃንኪ ውእቱ ሰላምኪ።
@EOTCmahlet
ዓዲ ዚቅ
ወይቤላ ንዒ ንሑር፤ኀበ ደብረ ከርቤ ውስተ አውግረ ስኂን፤ እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ነያ ሠናይት ወነያ አዳም፤ አግዓዚት ማርያም ጽርሕ ንጽሕት፤ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤  ወዲበ ርእሳኒ አክሊል፤ ፅሑፍ በትምህርተ መስቀል
@EOTCmahlet
ዓዲ ዚቅ፦
በወርቅ ወበዕንቍ ወበከርከዴን፤ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት፤ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ፤ትርሢተ መንግሥቱ አንቲ መድኃኒቶሙ ለነገሥት
@EOTCmahlet
ሰቆቃወ ድንግል
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም/፪/
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ተዓይል/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤ አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤ እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ፤እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ
@EOTCmahlet
ወረብ፦
አመ አመ አጒየይኪ ዕጓለኪ በሐቂፍ/2/
እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ/2/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ሰቆቋወ ድንግል(ሌላ)
ኀበ አዕረፍኪ እግዝዕትየ ማርያም ታሕተ ጽላሎተ ዕፅ እምፃማ፤ፈያት ክልኤቱ ሶበ በጽሑኪ በግርማ፤እምትሕዝብተ ሞቱ ማሕየዊ ለወልድኪ ንጉሠ ራማ፤እፎኑ አዕይንትኪ ማያተ አንብዕ አዝንማ፤አዕይትየ ለገብርኪ ክልኤሆን ይጽለማ
@EOTCmahlet
ዚቅ
ሐፃቤ ርስሐትየ ይኩን አንብዕኪ ዘአንፀፍፀፈ ዲበ ምድር አመ ወልድኪ ይፄዓር በመልዕልተ
@EOTCmahlet
መዝሙር፦
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፣ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘዓቀምከ፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወከመ ወሬዛ ኀይል መላትሒሁ፤ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ሰማይ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ  በከዋክብት ሠማይ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኩሉ ዕለት፤ማ፦ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፥ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ።
@EOTCmahlet
አመላለስ
@EOTCmahlet
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ/፪/
ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ/፪/

🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCmahlet👈                 
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @EOTCmahlet
    # Join & share

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

19 Oct, 09:00


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

ድንግል እንዴት ቻልሺው ያንን ህማም 🙏🙏🙏

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

18 Oct, 10:21


የእግዚአብሔር ፍቅር በልብህ ውስጥ ጠልቆ ከገባ ድካምህ ይጠፋል ።

ከእግዚአብሔርና ከትእዛዛቱ የበለጠ ኃጢአትን የምትወድ ከሆነ ደካማ ትሆናለህ ። ነገር ግን ፍቅሩ ወደ ልብህ ከገባ በውስጥህ ያለውን የኃጢአት ፍቅር አውጥቶ ይጥለዋል ። ስለሆነም ማንኛውንም ዓይነት ፈተና ለመቃወም ብርቱ ትሆናለህ ።

"ንስሓ ማለት ፍላጎትን በፍላጎት መቀየር ማለት ነው ።" ይህ ማለት የእግዚአብሔር ፍቅር የአለምን ፍቅር ይተካል ማለት ነው ። ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ፍቅር የሚመሩህን ማንኛውም አይነት መንፈሳዊ መንገዶች ሁሉ ተከተል ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን ከሚወዱት ጋር ተባበር !  እርሱን ስለ ወደዱት ሰዎች የተጻፈውንም አንብብ ! በመጨረሻም ምሳሌያቸውን ተከተል ።

   # አቡነ_ሺኖዳ_ሳልሳዊ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

18 Oct, 09:00


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

ድንግል እንዴት ቻልሺው ያንን ህማም 🙏🙏🙏

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

17 Oct, 11:19


"ቤተክርስትያንን መርዳት ከፈለክ ሌሎችን ለማረም ከማሰብ በፊት በቅድሚያ እራስን ማስተካከል ይበጃል። እራስህን ካስተካከልክ አንድ የቤተክርስትያን ክፍል ዳነ ወይም ተስተካከለ ማለት ነው። ሁሉም ሰው ይህን ማድረግ ከቻለ ቤተክርስትያን ጤናማ ትሆናለች። ስለዚህ ላስተዋለው ሰው ሌሎች ላይ መፍረድ እጅግ በጣም ቀላል ነው እራስን ማስተካከል ግን ጥረት ይጠይቃል።"

#ቅዱስ_ፓሲዮስ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

17 Oct, 09:00


🕰🔔
፮:     6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ጌታችን ለእኛ ብሎ በመስቀል የተሰቀለባት ሰዓት ነው ።
ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ (አቡነ ዘበሰማያት ) እንድገም።

    በቀራንዮን ያ ተራራ የጌታ   ድካሙን 💔💔💔እያሰብን እንጸልይ ለኛነው የተከፈለው !!!

ድንግል እንዴት ቻልሺው ያንን ህማም 🙏🙏🙏

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

17 Oct, 03:14


#ቃለ_ወንጌል

07/02/2017
ማቴ፲፱÷፳፭-ፍጻሜ

ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው እጅግ ተገረሙና እንኪያስ ማን ሊድን ይችላል? አሉ። ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው።በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን? አለው። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ።

ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል። ነገር ግን ብዙዎቹ ፊተኞች ኋለኞች፥ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ::


ቅዳሴ:- ፫ቱ ምእት

ምስባክ
መዝሙር 35:17-18

ጸርሑ ጻድቃን ወእግዚአብሔር ሰምዖሙ

ወእምኵሉ ምንዳቤሆሙ አድኀኖሙ

ቅሩብ እግዚአብሔር ለየዋሃነ ልብ

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️

16 Oct, 11:16


በልቅሶና በጩኸት የወርቅና የብር መፈተን የሆነ መፈተንሽ እንደ ምን ያለ ፍጹም ድንቅ ነገር ነው? ... የፈጣሪ የኢየሱስ እናት ሆይ! ቀን በፀሐይ ሐሩር፣ ሌሊትም ፍጹም ምሳሌ በሌለው ውርጭ ልምላሜያዊ ሰውነትሽ እንደ ምን ጠወለገ?... 'ከመ ዘእሳት ዘሐቅል ሕሊናየ ውእየ' ... እመቤቴ ማርያም ሆይ! ሀገርን የሚጠብቁ ሰዎች 'የእኔንና የተወደደ ልጄን ልብስ ገፈፉ' በማለት በተናገርሽው ነገርሽ ሕሊናዬ እንደ በረሓ እሳት ተቃጠለ..... እንደ ውኃ ፈሰስሁ፤ ዐጥንቴ ሁሉም ተበተነ፤ ኃይሌም እንደ ገል ልምላሜን ዐጥቶ ደረቀ፤ ምላሴም በጉረሮዬ ውስጥ ደረቀ"


(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)