ዘመድኩን በቀለ @ethiopianorto7 Channel on Telegram

ዘመድኩን በቀለ

@ethiopianorto7


የዘመድኩን በቀለ ጦሟሩን እንደወረደ የሚለቀቅበት ስለሆነ ሁላችሁም ዘመዴን አድናቂዎች ተቀላቀሉት ጆይን አድርጉት ሸሩን ትታችሁ ሼር አድርጉት

ዘመድኩን በቀለ (Amharic)

በዚህ የማንኛውም ቀን የዘመናዊ እና ሊቀ ኢትዮጵያን ሳይከተለው ዘመድኩን በቀለ በወንድማኔዎቹ ላይ እንደመጣው እና ድረስኩን በጣም ተቀላቀልባችሁ ሆናችሁለው መልዕክት አገሬ የኢትዮጵያ ራሱን የሚሾም ሲሆን የሚመልሰን እናወሳሰን ይህ ዓለም ላይ ነው በሚል ጊዜ መለወጥ ያላችሁ። ዘመንኩን አድናቂዎች በሚሰጡት ዓለም የሚቀላቅሱ እና መመዝገብ ያላችሁን ትእዛዞች እንዲደምስሉ ሆኗል። ለቀሩት የዘመዴን ተመን በሚሉት ህፃናት እና ቁምፊዎች ያግኙንማለች። በአንዳንድ ቀናት በተለያዩ ዘመዶች በቂጣን ዘመን መሰረት በጤናዬ በሀገራችን ምዕራፍ ሕጻኒቶች ላይ ግልጽ እና መሀከልንን እንዲሆኑ የተሰጠን እናትም እና ወንድገድ ኬፖሊዎችን እና የትኩሳት ሕይወቶችን እናወራለን።

ዘመድኩን በቀለ

13 Jan, 08:42


"…በውጭ ባሉ ሰዎች ላይ መፍረድ ምን አግዶኝ? በውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን? በውጭ ባሉቱ ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት። 1ኛ ቆሮ 5፥ 12-12

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

13 Jan, 05:12


"…ፊልተር የሚሉህ ሶዬ ግን የሥራሕን ይስጥህ… የበሰጨ ሰው፣ በዐማራ ደም የሚነግድ ፀረ ዐማራ ጎጃም አሰዳቢ ሰው መሳይ በሸንጎ የግብዳ ቅሌታም ሰው እንዲህ የ80 ዓመቷን አዛውንት አዝማሪ ከነ ደም ሥሯ ፍጥጥ አድርጎ በአደባባይ ማስጣት ተገቢ ነው? ፊልተር ሆይ የሥራህን ይስጥህ።

"…ይህቺን በሸዋ ፋኖ ስም ብር ሰብስባ ቆርጥማ የበላች፣ ከታናሽ እህቷ ብር ሠርቃ ቁማር ቤት የምትውል አሰዳቢ ጋለሞታ፣ ታላቁን የዐማራ ሕዝብ፣ ብሎም የጎጃም ሕዝብ በጋለሞታዊ ስድቧ እንዲሸማቀቅ ያደረገች፣ የአርበኛ ዘመነ ካሤ፣ የክርስቲያን ታደለ ጠላት የሆነችና መውደቂያዋን እኔ ክንድ ላይ ያደረጋትን አዝማሪት እንዲህ ታጋልጣት?

"…አልሚዬ እያየኋት ጨለለች። የጎጃም ዐማሮችም ዘመዴን አንሰድብም አሏት። የሸዋም ዐማሮች እንደዚያው። ሸንጎዎችም ኃይላቸው ደከመ። ክንፋቸውን ሰበርኩት።

• እኔ ዘንድሮ ፈጣሪ ይቅር ይበለኝ እንጂ በዚህች ሴትዮ ብቻ ነፍሴ ገነት የምትገባ ነው የሚመስለኝ። 😂

ዘመድኩን በቀለ

13 Jan, 05:12


መርምሯቸው እስኪ…?

"…አይ አስረስ መዓረይ ብታጣ ብታጣ ይሄን የወንድ አልጫ የሆነ ሸመልመሌ ሶዬ መልምልህ ታሰማራለህ? ደግሞ እኮ ሹመቱ ራሱ፣ (የዲየስጶራ አደረጃጀት አባላት ቁጥጥር ዘርፍ ኃላፉ) ብሎ እኮ ነው የሾመው።

"…ሰሞኑን ተመስገን ጥሩነህ ለእነ አልማዝ ባለጭራዋ፣ ለእነ ባናና፣ ለእነ ዐማራ ዛሬ የጎጃሙን ዘመዴ ስላበላሸብን ከእሱ ውጡና ወደ ሸዋና ወሎ ላይ አጀንዳ ፈጥራችሁ አነታርኩ ብሎ አጀንዳ እንዳወረደላቸው ነው የተሰማው። እናም ሰሞኑን ሸዋና ወሎ በእነ ጋለሞታዋ አልማዝ ባለጭራው ይረገጣል። እንደ ጉድ ነው የሚረግጡት። "ምን ሸዋ ደግሞ አንድ ካቻማሊ ኦቶቡስ ለማይሞላ ሕዝብ የምን መጨነቅ ነው አላሉም? ሸዋ ግግም። ለእናንተ ለሸንጎዎች ተደርበን ዘመዴን አንሰድብምብም ብሎ ግግም። የጎጃም ዐማራና አገውም በዘመዴ የመጣውን ወደ ውጪ ብለው ግግም። አይ ጎጄ መለኛው።

"…ለዚህ ሸዋንና ወሎን ለመረገጥም ሲባል ይሄ ሰገጤ የፋራ አራዳው ዳቪድ ብዙነህ ተብዬ ርጥብ በብአዴን በተመረጠ በማግሥቱ "ዘመዴ የሸዋ ዐማራ ነው። አውቀዋለሁ" ከቺሳ አላለም። መረጃ አምጣ ሲባል ስለሸዋ አንቆለጳጵሼ የጻፍኩትን እንደ መረጃ ይዞ ከች። አያመጣም ነበር ጎንደርን ሞቼ እንደምወዳት የጻፍኩበትን። አያመጣም ነበር ስለ ጎጃም አራቅቄ፣ ስለ ወሎ ቤተ ዐማራ ተጠብቤ የጻፍኩትን ለምን አያመጣም ነበር? ቀሽም።

"…ስም ዝርዝሩን እዩና የአስረስ መዓረይን የዳያስጶራ ኔትወርክ ተዋወቁቸው። ስንቶቹን ታውቋቸው ይሆን? ከዚህ ውስጥ ግን ሁላቸውም ሸንጎ፣ ቅባትና ፀረ ዐማሮች ናቸው ማለትም አይደለም። ምርጥ የዐማራ ያውም የጎጃም አገው እና ዐማራ ልጆችም ይኖሩበት ይሆናል።

• የዐማራ አንድነት መቼም አይመጣም የሚል ሰው የጎጃም ዳያስጶራ አደራጅ ሲሆን እግዚአብሔር ያሳያችሁ። 😂😂😂

"…ጃልቆቱ ወዲ አስገዶም ነኝ ከባህርዳር።

ዘመድኩን በቀለ

13 Jan, 05:12


አመሻችሁን…?

"…ከየት ሆናችሁ ነው ቴሌግራሜን የምትከታተሉት?

• አለን ዘመዴ፣ ከመቀሌ፣ ከቦሌ፣ ከሰላሌ፣ ከሞላሌ፣ ከጉለሌ፣ ከሸጎሌ፣ አለን ከጎንደር፣ ከባህርዳር፣ ከደብረታቦር፣ ከአፋር፣ ከሐረር፣ አለን ከጂጋ፣ ከወለጋ፣ ከማርቆስ፣ ከደሴ፣ ከከሚሴ፣ አለን ከአዲስ አበባ፣ ባሌ ጎባ፣ ከአዳባ፣ አለን ከእዚህና ከዚያ፣ አለን ከስሉልታ፣ ከሚኒሱታ ሱታ።

• ቆይቼ ስለ ዳቪድ ብዙነህ እነግራችሁና በስሱ እከንተዋለሁ። አላችሁ አየደደል?

"…ቴሌግራማችንን እንደ ተለቭዥን መቀወጥ እኮ እንችላለን። አይደለም እንዴ? እደግመዋለሁ አላችሁ አይደል?

ዘመድኩን በቀለ

13 Jan, 05:12


ለዛሬ የመጨረሻ መልእክቴ…

"…ነገ ሰኞ የእረፍት ቀኔ ነው። ከእግዚአብሔር ሰላምታው በኋላ 1ሺ ሰዎች አመስግነው ሲጨርሱ የቤቴንም በር የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁንም እቆልፈዋለሁ። የምንገናኘው ማክሰኞ ጠዋት በርእሰ አንቀጻችን ነው። ከመሰነባበታችን በፊት ግን አፋጎን ምክር ልለግሰው።

"…ወዳጆቼ የእኔ ጎጃም መግባት ቢጠቅማችሁ እንጂ አይጎዳችሁም። እኔ እንደሌላው በውሸት ፕሮፓጋንዳ ሕዝብን ማደንዘዝ አልፈልግም። ሸዋ፣ ወሎና ጎንደር ገብቼ ኮሶ እንደጋትኳቸው እናንተ ጋር ጎጃም ገብቼ ማር አልግትህም፣ ወተትም አላስጎነጭህም። እንዲያሽርህ አድርጌ መቅመቆ ነው የማጠጣህ የምግትህም። ምን ታመጣለህ?

"…የፎቶ ቦለጢቃ ይብቃ። የውሸት ሰበር ዜና ይብቃ። የሕዝቡን መከራና ሰቆቃ አታራዝሙ። በውስጣችሁ የተሰገሰጉትን የትሪፕል ኤ፣ የብአዴን፣ የኢዜማ፣ የግንቦት ሰባት፣ የብልፅግናና የወያኔ ኤጀንቶችን በቶሎ አጽዱ። ሠራዊቱ የወታደር ቁመና ይኑረው። በካምፕ ጠርንፉት። ሞባይል ጠርንፉ። የመዋጋት አቅም፣ መሳሪያ፣ ወኔና ጀብዱ መሥራት የሚችል ሕዝብ ይዛችሁ በተኩላ አታስበሉት። ጀግኖቹን የበላይ ዘለቀና የእጅጉ ዘለቀን የአንበሳ መንጋ በበጎች መንጋ አትምሩት። አንበሳን መምራት ያለበት አንበሳ ብቻ ነው።

"…እስቲ ጨክናችሁ ድርጅታዊ ጉባኤ ጥሩ። ራሳችሁን ገምግሙ። የደከመውን ቀይሩት። ገና ምኑም ላልተያዘ ሥልጣን በቤተሰብ በጓደኛ ተቋሙን አትሙሉት። የሚሞትላችሁ አልጠፋ፣ እንዴት ሌባና ዘራፊን መሪ አድርጋችሁ ታስቀምጣላችሁ? እንዴት የትግሬ ምርኮኛን የሚሸጥ ፋኖ ታፈራላችሁ? ነውር እኮ ነው።

"…በፌስቡክ፣ በቴሌግራም፣ በዩቱዩብ፣ በቴሌቭዥን የሚበዙት የጎጃም ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ናቸው። እንዴት ሕዝቡ በራሱ ልጆች ሲዘረፍ፣ ሲገደል አስችሏቸው ባዶ ዲስኩር ሲደሰኩሩ ይውላሉ?

• ስደበኝ ተንጫጫ እኔ ግን አልፋታህም።

ዘመድኩን በቀለ

13 Jan, 05:12


• አልንበረከክምን ምን አመጣው…?

"…የጀግናውን የበላይ ዘለቀን መንደር ለኦነግ ሰጥቶ ፈርጥጦ፣ በጀግናው በላይ ዘለቀን ሃውልት ቀሚስ አስለብሶ ፈርጥጦ፣ ስንትና ስንት የጀግና ጀግና የጎጃም ዐማራ አስቀርጥፎ በልቶ፣ 24/7 ሳምንቱን ሙሉ፣ 365 ቀናትን የማይቋረጥ ኢንተርኔት ፌስቡክ ላይ ተጥደህ ውለህ፣ ወለጋ ገብተህ ዐማራን ለማስጨረስ የሴራ ቦለጢቃ ጎንጉነህ ስታበቃ፣ በገረድ ተላላኪህ በአልማዝ ባለጭራዋ ኔትወርክህ የጎጃም ዐማራን ሕዝብ ከወንድም ዐማራ ሕዝብ ጋር ስታናክስ ከርመህ፣ አንት ሴረኛ በወንዱ በጀግናው በበላይ ዘለቀ ስም መወሸቅ አይቻልም። ተላላኪ የብአዴን ብልፅግና አሽከር የትኛው ስብዕናህ ነው የሚገደለው ባክህ። ስብዕና ሲኖርህ እኮ ነው ስብዕናህ የሚሞተው። የታል ስብዕናህ? አንድ ሰው ደጋግሞ አልወድቅም አልሰበርም አልንበረከክም ካለ ውስጡ ተንኮታኩቶ አልቋል ማለት ነው። ወደህ ነው የምትሰበረው? ወደህ ነው የምትንኮታከተው። 😂😂

"…የዐማራ የአንድነት ቤት እንዳይገነባ አንተ እና አስረስ በሠራችሁት የመጎተትና የማጨናገፍ ሴራ ገና በምድር አይደለም በሰማይ በቅድስት ሥላሴ ፊት ትጠየቃታለህ።

"…ለማንኛውም እኔ ጎጃም ከገባሁ በኋላ ባይጠራም በብዙ ወንጀላችሁ ቀንሷል። ሕዝቡ ፋኖን እንዲጠላ እንዲጸየፍ ያደረጋችሁትን ሴራ እናከሽፈውና የእነ ሻለቃ ዝናቡን የተጋድሎ ዘመን እንመልሰዋለን። ጎጃምን የኦሮሙማ ሠራዊት መፈንጫ አድርገህ ስታበቃ አሁንም አፍ አለኝ ብለህ ስትወበራ አለማፈርህ። ይገርማል።

"…ገና ለፍርድ የምትቀርቡ የፋኖን መልካም ስም የገደላችሁ አረመኔዎች ትኖራላችሁ። በፎቶ ቦለጢቃ፣ በጋለሞታ አክቲቭዝም፣ በላም አለኝ በሰማይ ትግል አይመራም። ሂድ መጀመሪያ ቀበሌህን ነፃ አውጣ።

• ጋለሞቶቹ የሸንጎ የሽንት ጨርቆች አልቅሱ።

• ጃልቆቱ ወዲ አስገዶም ነኝ ከባህርዳር…😂

ዘመድኩን በቀለ

13 Jan, 05:12


"…ታዲዬ ሄኒዬም እያረመኝ ነው። 😂

"…ባንዲራው የማነው የሚለውን ጥያቄዬን ሄኒዬ መልሶልኛል። ሁሉም ከቴሌግራሜ ወጥተው አንድ የቀረኝ ወዳጄ ሄኖክ ነው ብዬ ነበር። አልተሳሳትኩም ሄኖኬ ከእኔጋር መሆኑን በሚሰጠኝ ማረሚያ እያየሁ ነው።

"…አልማዝ ባለጭራዋ የዘመድኩን ቴሌግራም ተከታታይ ቀነሰ እያለች ስትወበራ፣ ሌሎቹን ከዘመዴ ፔጅ ውጡ እያለች ስትቀሰቅስ ትውልና እሷ ግን ከእኔው ፔጅ ተጥዳ እነ አማራ ዛሬን ስታስተነትን ትውላለች። ጉራጌው አሌክስ ፋኖም ሰሞኑን ከቤቷ ጠፍቷል። ሙን ኡኖ ነው።

"…ለማንኛውም እኔ አሁን በምናቤ ያለሁበት ሆቴል በመከላከያ፣ በፌደራል ፎሊስ፣ በአድማ ብተናና በሚሊሻ ተከቧል። አንደኛው ፎሊስ ራሴኑ ዘመድኩንን አይተኸዋል ብሎ አይጠይቀኝም? 😂 ኧረ አላየሁትም አልኩታ ምኔ ሞኝ ነው። ዘመድኩንን ባሕርዳር እየፈለጉት ነው። እኔ ራሱ ካየሁት እጠቁማቸዋለሁ። ኤትአባቱንስና የሲዳማና የአዳማ ባንዲራ የማይለይ ጃልቆቱ ወዲ አስገዶም። መጠቆም ነው።

"…ማነሽ እህት ዓለም አስተናጋጅ እስቲ ዓሣውን ድገሚኝ። ማነህ ፎሊስ ነፍሴ ዘመድኩንን እስክታገኙት ዓሣ እንብላ…ብሊስ…🙏🙏🙏

• እንዲህ እንዲህ እየተጫወትን ባሕርዳር እናመሻለን።

ዘመድኩን በቀለ

13 Jan, 05:12


"…ወይ ጉድ አንቺም ከሰው ተቆጥረሽ ፉን ፉን ትያለሽ…? …ታሰርሽ በተባለ ጊዜ አባትሽ ደውለው እኔ ላይ ነበር ያለቅሱ የነበረው። አንቺ ፌካም ዘራፊ። አንቺ ነሽ ከአዝማሪት አልማዝ ባለጭራዋ ጋር ሆነሽ ጓ የምትዪው። ደፋር ነሽ።

"…ሕዝቡ ለትግሉ ብሎ የሰጠው ብር የት ገባ? ወጥሬ እጠይቅሻለሁ። ያቺ የጎንደሯ መደዴ ንግሥት ተብዬዋ ጋለሞታ በዐማራ ፋኖ ስም ባካበተችው ገንዘብ ቡና ቤት ከፍታ ሽርሙ*ናን በአዲስ አበባ ስታስፋፋ ከርማ ወገቧ ላይ ስቆምባት መላኩ አለበል ወደ ኡጋንዳ ላካት። አንቺ ደፋሯ ሰገጤ ምሥራቅ ጎጃም ተባለ ብለሽ "ኧረ ተይ ውረጅ፣ ውረጅ እስኪሉሽ እነ አልማዜ በስሙኒ ሁለቴዎች ወበራሽ። አይደለም የፋኖ ማንትስ የፈለግሽው ውሽማ ብትሆኚ አያገባኝም፣ አይመለከተኝም። በጓሮ ሳትልከሰከሺ ፊትለፊት ግጠሚኝ ከፈለግሽ። ቀሽም።

"…ዛሬ ባህርዳር ማደሬ ነው። መስተንግዶው በዛብኝ። የሌቦቹን ኔትወርክ ዘርጋፊው የባሕርዳር ዐማራ ወዳለሁበት ሆቴል እየጎረፈ ነው። የጎንደር ስኳድ፣ በተለይ የደቡብ ጎንደር ስኳድ ባሕርዳር ባለሥልጣን ነው። ዳኛ ነው። ፖሊስ ነው። የጎጃም ዐማራን ፍዳ የሚያበላውን ግሩፕ በደንብ እያየሁት ነው። ሰው የሚያግተውን ግሩፕ ደርሼበታለሁ። መቼም ዘንድሮ ጉድ ነው።

"…ፋኖ ማንችሎት ጨቅላ ልጅ ማግባቱን አግብቷል። ከዐማራ ፋኖ በጎጃም የተባረረው ግን በሌላ ምክንያት ነው። ምክንያቱን አሁን አልናገርም። ቲና የምትባይ ወለወልቱ መጎጥ ሴትዮ ግን ብታርፊ ይሻልሻል። እኔ የአባትሽ የአቶ በላይ አክባሪ ነኝ። እረፊ ከአባትሽ አታቀያይሚኝ። ነግሬሻለሁ።

"…የባሕርዳር ዓሣ ሲያምር፣ ሲጣፍጥ በናታችሁ። ማደሬ ነው በቃ ባህርዳር። ያረፍኩበት ሆቴልም ሸጋ ነው። የአልጋ እንኳ ልክፈል ብል ሞተን ነው ቆመን አላሉኝም?

• ማነህ የሆዳሽ ወይም የገወቻውን ልጅ አስገባልኝ። ና ግባ ወንድም ዓለም።

ዘመድኩን በቀለ

12 Jan, 13:48


በመንገዴ ላይ…

"…እዚያው ባህርዳር ነኝ። ሚኒሻዎች ይመረቃሉ ሲሉኝ እስቲ ልያቸው ብዬ ገብቼ ነበር። ሚሊሻ የተባሉት ጠብደል ጠብደል ጎረምሶች መሆናቸውን ሳይ ሚሊሻ እንዲህ ነው እንዴ? ብዬ ልጠይቅ ብዬ ባንዳ ብለው ዕዳ ቢከቱኝስ ብዬ ጮጋ አልኩኝ።

"…ቆይቼ ፎቶ ላነሳቸው ስል በማስክ ተሸፋፍነዋል። ኢቦላ ገባ እንዴ ብዬ እኔም ጠዋት ባህርዳር ጊዮርጊስ ስሳለም የለበስኳትን ነጠላዬን ተከናነብኩኝ።

"…ተመራቂዎቹ በኦሮሚኛ፣ በትግሪኛ፣ በቅማንትኛ፣ በአገው ሸንጎኛ እና አለቃቸው በአማርኛ ሲያወራ ሳይ በቋንቋ የዳበረ የብአዴን ሚሊሻ ስላየሁ ተደምሜ እየወጣሁ ነው።

• ባህርዳር ምሳ የት ልብላ ጠቁሙኝ እስኪ። እንቁጣጣሽ ነበር ዱሮ ደስ የሚለኝ። ጠቁሙኝ እስኪ።

• ኒንጃ ሚሊሾቹ እየጨፈሩ አለፉኝ። ሲሸቱ አይጣል ነው። ሰው እንዲህ በቁሙ ይጠነባል? የፈጣሪ ያለህ።

• በሉ ምሳ የት ልብላ?

ዘመድኩን በቀለ

12 Jan, 13:30


ዓባይ ማዶ ነኝ

"…ከአባይ ማዶ እስከ ክምር ድንጋይ ያለውን የአስረስ መዓረይና የዘራፊውን ትስስር እየሰማሁ ነው። ከአዲስ አበባ ዋና ወኪሎቹ እነ ቲና በላይ እና የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ የነበረው እና አሁን ግን አዲስ አበባ ተቀምጦ አክቲቪስት የሆነውን የእነ ስዩም ተሾመን ጓደኛ የእነ በላይነህ ጌታቸው ክፉ ሥራ መረጃም እየተቀበልኩኝ ነው።

"…ፋኖ ማንችሎት ከዐማራ ፋኖ በጎጃም መባረሩንም ያረጋገጥኩት እዚሁ ዓባይ ማዶ ሆኜ ነው። የዐማራ ፋኖ በጎጃም ተሃድሶ ካላደረገ በጣም ትልቅ አደጋ እንደተጋረጠበትም እያየሁ እየሰማሁ ነው።

"…የብአዴን ተራ ፖሊስ የነበረ፣ ተራ የአብን አባል የነበረ፣ የዐማራ ተማሪዎች ማኅበር አባል የነበሩ፣ የከሱ፣ የጠወለጉ ራብ ያጠቃቸው ይመስሉ የነበሩ ግለሰቦች በፋኖ ስም የወርቅ ሰዓት፣ የወርቅ ቀለበቶች፣ ሀብሎችና አይፎን 15 የሞባይል ስልክ ተሸክመው የሚዞሩ ዘራፊ ፋኖ መሳይ ዘራፊ ፎልፋሎችን በጊዜ ካላጠራ ትግሉ በ100 ዓመትም አያልቅ።

"…ጎጃም ብቻ አይደለም፣ ሸዋም፣ ወሎም፣ ጎንደርም ሌባ እና ጎታችን በጊዜ መመንጠር አለበት። ሌባ ሌባውን በመስመሩ ላይ እየተከታተልኩት ነው።

• ወደ መርጦ ለማርያም እየተመለስኩ ነው።

ዘመድኩን በቀለ

12 Jan, 13:30


ወራጅ አለ…?

"…መልሱኝ አልኳቸው ጀልባ ያከራዩኝን ጎረምሶች። መልሱኝ ወደ ባሕርዳር፣ ወደ ሽንብጥ ሚካኤል። ምን ጉድ ነው የገጠመኝ።

• ም ጋሼ አለኝ ጨበሬያሙ ጩሎ

~ ዕቃ ረሳሁ፣ ባስቦርቴ ሁቴል ነው፣ ፈረንካዬም እዚያው ነው። መልሱኝ አልኳቸው። 

• እሺ ጋሼ ይረጋጉ ብለው እየመለሱኝ ነው።

"…ጣና ሐይቅ ላይ፣ በኢትዮጵያ ምድር የምን ሀገር ባንዲራ ነው ብዬ ልጠይቃቸው ፈልጌ ነበር። ደግሞ ምን አገባህ ብለው ቢያግቱኝስ ብዬ ጮጋ አልኩ።

"…ድሮ ድሮ በየቦታው የሚታየው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ነበር። ዜጋ ሲቀበር፣ ለደቦ ሥራ፣ ለጽዋ ማኅበር፣ ለክብረ በዓል፣ በመሂና፣ በጀልባ፣ በሁቴል፣ በመድረኮች ሁሉ ሰንደቅ ዓላማዋ ይውለበለብ ነበር። አሁንስ፣ አሁንማ…

"…በትግራይ የሮም ካቶሊኩ የአማሪካው የኪሰንጀር ወራሽ ሲኖዶሰ ሰላማ፣ የጎንደሩና የጎጃሞቹ የፖለቲካ ቅማንትና አገው ሸንጎዎቹ ቅባቴና የትግሬ ዲቃሎቹ ስኳዶች፣ በኦሮሚያ የወሃቢ እስላሙና የብልፄ ቤንጤ፣ በደቡብም የኬሲንጀር ደቀ መዛሙርቶቹ ቤንጤዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማን አንይ ብለዋል። አዲስ አበባ ጃንደረባው በሮም ካቶሊክ እና በጎጃሙ ቅባት ፈንድ ባዘጋጀው የመንፈሳዊ ጭፈራ መሳይ ምሽት ዐውደ ምሕረቱ ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሳይውለበለብ ነው የቀረው። መለከት ይነፉ የነበሩ ጥቂት ልጆች ከያዙት በቀር ወፍ የለም።

"…በቦሌው የጃንደረባው ዝማሬ ዘንድሮ አክሱም ጽዮን የቀሩትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አስቀምጦ "ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን" እያስባለ ትግሬዎቹን ሲያስለቅሳቸው ነበር ያመሸው። እኔንም አንጀቴን ነው የበሉኝ። ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን አለ ሄኖኬ። 😂 አይደል…? የሚሞተው፣ የሚታረደው፣ በራብ የደቀቀው ዐማራና አገው አያስለቅስም አይደል? ወይ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን…

"…ባንዲራው ግን የየት ሀገር ነው…?

ዘመድኩን በቀለ

07 Jan, 11:18


የልደት በዓልን

"…ከአዲስ አበባ በስተ ሰሜን አቅጣጫ፣ በ364 ኪሜ ርቀት ላይ በአሁኑ ምሥራቅ ጎጃም በድሮው የጎጃም ክፍለ ሀገር በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ርእሰ ከተማ በሆነችው በመርጡለ ማርያም ገዳም እያከበርኩ ነው።

"…ሕገ ልቡናም፣ ሕገ ኦሪትም፣ የሀዲስ ኪዳንም ኪዳናት የተፈጸሙባት፣ ክብሯ ከአክሱም ጽዮን፣ ከተድባበ ማርያም፣ ከጣና ቂርቆስ እኩል በሆነው በአክሱማውያኑ የኢትዮጵያ ነገሥታት በአብርሃ ወአፅብሃ ድንቅ ሕንጻ ባጌጠችዋ ከተማ እያከበርኩ ነው።

"…መርጡለ ማርያም በኢትዮጵያ የከተሞች ታሪክ ሺ ዘመናትን ያስቆጠረች ጥንታዊት ከተማም ናት። በሺ ዘመናት ታሪኳ በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን በቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት ከእስራኤል ታቦተ ጽዮንን ተከትለው የመጡ የኦሪት ካህናት የሰፈሩባት። ህሩያን አብርሃ ወአጽብሃን ተከትለው የመጡት ከሳቴ ብርሃን ሰላማ ወንጌለ ክርስቶስን ሰብከው አጥምቀው ክህነት ሰጥተው የሾሙባትም ናት መርጡለ ማርያም።

"…መርጡለ ማርያም በዘመናት ውስጥ አራት ጊዜ ስሟን ቀይራለች።መጀመሪያ ሀገረ ሰላም ነበር ተብላ የምትጠራው፣ ቀጥሎ ሀገረ እግዚአብሔር፣ ከዚያም ጽርሐ አርያም በመጨረሻም አሁን የምትጠራበትን ርእሰ ርኡሳን መርጡለ ማርያም ተብላ ተጠርታ ይህ ስሟ ፀንቶላታል።

"…ዛሬ በዓል ነው። ጭቅጭቅ፣ ንትርክ፣ ንዝንዝም የለም። እኔም ከቤተሰቦቼ ጋር እዚያው በመንፈስ ሳከብር ነው የምውለው። ዛሬ ሰላም ነው። ቲክቶክም፣ ተለቭጅንም ላይ አልወጣም። የእሁድ ሰው ይበለን። ከነገ ጀምሮ ግን የጎጃም ጉብኝቴ መረር፣ ኮምጨጭ ብሎ በጎጃም ምድር በቴሌግራም ላይ ይቀጥላል። ርእሰ አንቀጻችንም መረር፣ ኮምጨጭ ብሎ ይቀጥላል። እስከዚያው ድረስ በያላችሁበት መልካም በዓል ይሁንላችሁ።

• ሻሎም…! ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ

07 Jan, 07:18


እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ…!

"…ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ? ቃልን ወሰነችው። ልደቱንም ዘር አልቀደመውም። በመወለዱም ድንግልናዋን አልለወጠም። ቃል ከአብ ያለ ድካም ወጣ። ከድንግልም ያለ ህማም ተወለደ። ሰብአሰገል ሰገዱለት። አምላክ ነውና ዕጣን አመጡለት። ንጉሥም ነውና ወርቅ አመጡለት። ስለኛ በፈቃዱ ለተቀበለው መዳኛችን ለሆነው ሞቱም ከርቤ አመጡለት። እርሱ ቸርና ሰውን ወዳጅ የሆነ አንድ እርሱ ብቻ ነው። ቅድስት ሆይ ለምኚልን።

"…ቤዛ ይስሐቅ በግዕ ከኅቱም ዕፀ ሳቤቅ እንደተገኘ፤ ለእስራኤልም በበረሀ ውስጥ ከኅቱም አለት ውኃ እንደ ፈለቀ፤ የተደነቀች የአሮን በትርም እንደለመለመችና እንደ አፈራች፤ በሶምሶንም እጅ ውስጥ ከአህያ መንጋጋ አጥንት ውኃ እንደ ፈሰሰ፤ እንዲሁ የጌታችን ልደት በኅቱም ድንግልና ሆነ። በዕፀ ጳጦስ ውስጥ እሳት እንደ ነደደች ዕፂቱም እንዳልተቃጠለች እንዲሁ የመለኮቱ እሳት ድንግልን አላቃጠላትም። ለእርሱም ከቸር አባቱ ከማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነት ክብር ምስጋና ሰጊድ ከርሱ ጋር በትክክልነት ይገባል ለዘላለሙ አሜን።

"…በዓለ ጌናን ስናከብር በኀዘን በመከራ፣ በጭንቅ፣ በራብና በጥም፣ በሰቀቀን፣ በስደት፣ በወኅኒ ቤት፣ በአልጋ ቁራኛ በደዌ ደኛ፣ በፅኑ ህመም ተይዘው፣ በየቤቱ፣ በየጎዳናው፣ በየሆስፒታሉና በፀበል ስፍራዎች ሁሉ ያሉትን፣ ከሞቀ ቤትና ንብረታቸው ተፈናቅለው በየጥሻው የወደቁትን በማሰብ፣ በመንከባከብ፣ በመጠየቅ፣ በመጎብኘትና ማዕድ በማጋራት ይሁን። ሀገራችን ኢትዮጵያንና ጎረቤቶቿን፣ መላውንም ዓለም ሁሉ ሰላማዊው ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ያድርግልን። አሜን።

"…እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለአምላካችንና ለፈጣሪያችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን

ዘመድኩን በቀለ

06 Jan, 10:16


"…እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን? እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን? የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል። የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፡— እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው፥ ባታንጐራጕርም፥ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፥ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፥ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል። እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ። ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም፡— ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድን አዳሽ ትባላለህ። ኢሳ 58፥ 61-2

“…ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።” ዕብ 13፥16

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

05 Jan, 16:21


• አላችሁ አይደል…?

• ገባ ገባ በሉማ…!

ዘመድኩን በቀለ

05 Jan, 16:19


"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ምሽት 1:20 ላይ ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• የዛሬውም መርሀ ግብራችን እንደወትሮው ሁሉ ልዩ ነው። ሁለት መርሀ ግብር ነው የሚኖረኝ።

1ኛ፦ የሻምበል ማማር ጌትነት ጉዳይ።

2ኛ፦ የጎጃም ጉብኝቴ ቀጣይ ክፍል።

•ዩቲዩብ👉 https://youtu.be/bQtDz0gxlDw

• ሮኩ/ Roku: 👉 https://my.roku.com/account/add?channel=merejatv

•ትዊተር👉 https://twitter.com/MerejaTV

•Mereja TV: https://mereja.tv


"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ

05 Jan, 15:26


ማስታወቂያ…

"…በዛሬው የዕለተ እሁድ የመረጃ ቴቪ የነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ ላይ "የሻምበል መማር ጌትነት ጉዳይ እና የተጀመረው የጎጃም ጉብኝቴ ቀጣይ ክፍል ይቀርባል።

• ጠብቁኝ…!

ዘመድኩን በቀለ

05 Jan, 13:29


መልካም…

"…በክርስቶስ ቅዱስ መስቀል መረገጥ ኢትዮጵያ በመሬት መንቀጥቀጥ እየተናጠች ነው። በተለይ 4 ኪሎ በሚገኘው በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለጥር 7 ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና ምእመናን በተገኙበት በኢትዮጵያ ምድር በታላቅ ክብር የቆየውን ቅዱስ መስቀል በይፋ በመርገጥ ቤተ ክርስቲያን ፀረ ክርስቶስነቷን በይፋ የምታወጅበት ዕለት ይሆናል ተብሎ ስለሚጠበቅ የመሬት መንቀጥቀጡ ይቀጥላል። እርግፍግፍ፣ ውድም ያደርገናል። ምህላ የሚኖረው የሃይማኖት አባቶቹ በእግዚአብሔር መኖር ሲያምኑ እኮ ነው። ምህላም የለም ይቅርታ ምህረትም የለም። መስቀሉን እንዳዋረድነው እንዋረዳለን። በራብ፣ በጦርነት፣ በጭንቅም እንኖራለን።

"…ሌላው እኔ ዘመዴ ከሸዋ፣ ከወሎና ከጎንደር መልስ ጎጃም ለጉብኝት መግባቴ ሰማይ ምድሩን በአዋራ አንቀጥቅጦታል። ጫጫታው በዝቷል። ግን ምንም መፍጠር አይችሉም። ጎጃም እቆያለሁ። እበድ፣ ፍረጥ፣ ዝለል፣ ጩህ፣ አጓራ ደንታዬ አይደለም። "ደመቀ ዘውዱን፣ እስክንድር ነጋን፣ ሃብታሙ አያሌውን፣ አበበ በለውን፣ የጎንደርን ስኳድ ስነካ ከተፈጠረው ጫጫታና ግርግር አይበልጥም የጎጃሙ። በመጨረሻ ዘመዴ እውነቱን ነው ብለህ ልትፀፀት አጉል ደርሰህ አትንፈራገጥ። የእስክንድር ነጋ ጠባቂ ጎጃም ምን ይሠራል? እስክንድርስ ደቡብ ጎንደር ምን ይሠራል? አርበኛ ዘመነ ካሤ ይሄ ሁሉ ድራማ በዙሪያው ሲሠራ ያውቃል? የዛሬው የመረጃ ቲቪ ዝግጅቴ ልዩ ነው የሚሆነው። እስከዚያው ላታስቆሙኝ ተንጫጩ።

"…እያየኸኝ፣ እየሰማኸኝ በዝረራ አሸንፍህሃለሁ። ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ናት። የጎጃም ፋኖን ከከበበው ጭራቅ እታደገዋለሁ። ባህርዳር፣ ኢንጂባራና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ ጫካና አሜሪካ የመሸገውን ፀረ ጎጃም ዐማራ ሁሉ አውጥቼ አሰጣዋለሁ። ማርያምን ብዬ ማልኩ እኮ። አለቀ።

ዘመድኩን በቀለ

05 Jan, 10:56


"…ኢየሱስም መልሶ፡— ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤ በሌሊት የሚመላለስ ቢኖር ግን ብርሃን በእርሱ ስለ ሌለ ይሰናከላል፡ አላቸው። ዮሐ 11፥ 9-10

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

05 Jan, 06:32


እህህ… አሄሄ… ምን አስባችሁ ኖ…?

• ጎርጎራ ቴቪዎች
• እስማኤል ዳውድ
• ከፍያለው ጌቱ
• አማኑኤል አብነት ነው በአጠቃላይ በብዕር ስማቸው "በላይነህ ሰጣርጌ" ከይኸነው የሸበሉ ጋር ምን አስበው እንደጻፉ ከላይ ገብታችሁ በፔጃቸው አንብቡ።

"…በቀደም ዕለት ናትናኤል መኮንን ተስፋዬ ወልደ ሥላሴን ጠቅሶ ስለ አበጀ በለው የጻፈው ለምን እንደሆነ ብትሰሙ ትስቃላችሁ። እሳቱ ብዕረኛስ ማን ይመስላችኋል። አዛኜን እመ አምላክ ምስክሬናት ዘመነ ካሤን የእናቱ ጸሎት ይሰውረው። ይከልለው።

"…እኔ እኮ የሆነች ሰቀዝ አድርጌ መታ የማደርጋትን ጉዳይ ከብሮግራሜ በፊት ትመጣለች ብዬ አልገመትኩም ነበር። አዴ አልማዝ ዳኛቾ መገርሳ እና ጠበቃ አስረስ ማዕረይ ደንግጠው አካሄዴ ስላላማራቸው ነገሮችን ሁሉ አፈጣጠነብኝ እንጂ እኔ እንኳን ትንሽ ዞር ዞር ብዬ፣ እየጎሻሸምኩ፣ ባህርዳር እና ደብረ ማርቆስ ኢንጂባራ ዩኒቨርሲቲ የመሸገውን የፖለቲካውን ቅማንት የትግሬ ዲቃላውን ስኳድ እና ሌላውን ፀረ ዐማራና ፀረ አገው አናሳ ገዳይ ሸንጎ ወቅጬ ነበር ወደ ዐማራ ፋኖ በጎጃም ሙሉ ዳሰሳ ልገባ፣ ነገሮች እንዲስተካከሉ ምክረ ሓሳብ ልሰጥ የነበረው። እነሱ ግን ይሄ ሰው አያያዙ አላማረንም ብለው አፈጣጠኑት።  ብቻዬን እመታቸዋለሁ። አዛኜን እሰብራቸዋለሁ።

• አሁን ወደ እነ በላይነህ ሰጣርጌ  ልጥፍ ልምጣ።

"…እነ Belayneh Setarge Gizaw እና ይኼነው የሸበሉ ወደለጠፏት ልጥፍ እንምጣ። እነ በላይነህ ሦስት ስለሆኑ ተውአቸው። ይኼነው የሸበሉን ግን የግድ እጠቅሰዋለሁ። ይኼነው የሸበል በረንታው የጥላሁን አበጀ አጋር ማለት ነው። ፕሮፋይል ፒክቸሩን በዘመነ ፎቶ አድርጎ የሚሸቅል፣ ለዘመነ ካሤ ብቻ እንዲደርስ የተሰጠውን "ጥብቅ ሰነድ ለአስረስ ማረ አሳልፎ ሲሰጥ የኖረ ከብት መሰሪ ነው። ሰነዱን ሌላ ቀን እመጣበታለሁ። "…በጠበቃው ጉዳይ የመጀመሪያም የመጨረሻም ፅሁፍ ነው ብለው እነ ሰጣርጌ በኅብረት የጻፉትን ሂዳችሁ አንብቡ። እነ አማኑኤል አብነት ጥላሁን አበጀን ነፃ ሲያወጡት ዋሉና በመጨረሻ በጦመሩት ጦማር ላይ በስተ መጨረሻው አንቀጽ ላይ ምን አሉ?

• እሱም ከአምስት ጊዜ በላይ ከድሮን እና ከጥይት በተአምር ተርፏል።  [ ከማን ጋር አቻ ልታደርጉት? ]

• በተደጋጋሚ የዚህ ዘመቻ ዒላማ ተደርጎ ሲቀጠቀጥ አላስችለኝ ብሎ መረጃ ፈልፍየ የመጣሁት የአማራ ህዝብ እውነተኛ ልጆቹን እንዲያውቅ እና እንዲጠብቅ ስለምፈልግ ነው። [ ዘመነ ካሤ ሁለት ዓመት ሙሉ በአልማዜ ጭምር ሲቀጠቀጥ የጻፈለት አለ?]

• አሁን ደግሞ በኦርቶዶክስ ኃይማኖት ስር የተሰባሰቡ የስልጣን ጥመኞች አዲስ ዘመቻ ከፍተውበታል። [ አስረስ ኦርቶዶክስ አይደለም እንዴ?] ብቻ እንዲህና እንዲህ ሲሉ ይቆዩና በመጨረሻ ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል እንዲሉ ሰካራሞች የሸበሉና ሰጥ አድርጌ እንዲህ ይላሉ።

"…የእሱ [የአስረስ ማለታቸው ነው] መልካም ስም እና ዝና እንድሁም የፓለቲካ ስብዕና ተነካ ማለት እኛም ተነካን ማለት ነው። በዚህ ትግል በፓለቲካው ክንፍ ከራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ ቀጥሎ ቅቡልነት ያለው መሪ ነው። [ ከዘመነ ካሤ ቀጥሎ ቅቡልነት ያለው መሪ ነው] ሌሎች የሉም ማለት ነው? ከምሥራቅ ጎጃም ሸሽቶ ምዕራብ ጎጃም የከተመው እዚያም አለቃ መሆኑ ሳይረሳ።] ይቀጥሉና እነ የሸበሉ እንዲህ ይላሉ።

"…ራስ አርበኛው የሚበልጠውም [ አስረስን ማለት ነው] ዘለግ ላለ ጊዜ ጠብመንጃ ስለነከሰ እንጅ የንባብ አቅማቸው እና ንስርነታቸው ተመሳሳይ ነው:: የአማራ ፋኖ የፓለቲካ ክንፍ ከዚህ ንስር ሌላ በማን ሊዘወር ታስቦ የዚህን ያክል እንደተዘመተበት ግራ ነው የገባኝ ይላሉ እነ ሰጥ አድርጌ። ይሄ ማለት ለእኔ የሚገባኝ [ አስረስ መዓረይም ከዘመነ ካሤ አያንስም። እኩል ናቸው። ሌሎች በድሮን ቢሞቱም። ነገም ዘመነ አንድ ነገር ቢሆን የጎጃም ዐማራ ሆይ አትዘን፣ አትስጋ፣ ወንድ እናቱ የወለደችው አስረስን የመሰለ የዘመነ አቻ አለልህ እያሉት ነው። ፈረንሳይኛው ለእኔ በደንብ ነው የሚገባኝ።

"…አስረስ እለዋለሁ። አቤት ዘመዴ ይለኛል። አንድነቱ እንዳይመጣ ለምን ትጎትተዋለህ? ምን አስበህ ነው? እለዋለሁ። አስረስም መለሰልኝ። ብዙውን ትቼ ጥቂቷን ልንገራችሁ። "…ዘመዴ አንድነቱን እኔ አይደለሁም ያጎተትኩት። ከእኛ ውስጥ እነ እንትና ናቸው። የእኛ አመራሮችም አንድነቱ እንዲፈጥን አስጨንቀውናል። እኔም ዘመነ እስካለ ድረስ የትኛውም ሥልጣን ቢሰጠኝ ከሥሩ ስለሆንኩ አይተወኝም። እናም በቃ አዎ አዘግይተነዋል፣ እናፋጥነዋለን ነበር ያለኝ። ውሸት ይበል አስረስ ወጥቶ ለመሳይ መኮንን።

"…ቆይ እኔ የምለው ለድርጅቱ ነው መጨነቅ ወይስ ለግለሰቦቹ። የዐማራ ፋኖ በጎጃም ነው እንደ ተቋም መገንባት ያለበት ወይስ አስረስ መዓረይ? አርበኛ ዘመነ ካሤ ላይ ሀገር ምድሩ ሲዘምትበት ምነዋ የዚህን ያህል መንጋው ወጥቶ አልተከላከለለት? ምን እየተካሄደ እንዳለ አልገብቶኝም። ከምር አልገብቶኝም ልል አልኩና እኔማ ከገባኝ ቆየ። አይ የሸበሉና እነ ሰጣርጌ።

• እናንተስ ምን ትላላችሁ…?  …ሊበላ…?

ዘመድኩን በቀለ

04 Jan, 21:30


"…ይህቺን ነገር እያያችሁ ቆዩኝና የሆነች ጥያቄ ለጥፌላችሁ ቤቴን ቆልፌ ስትብሰለሰሉ ታድራላችሁ። ከዚያ ነገ በዕለተ ሰንበት ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ አስቀድሼ ከወጣሁ በኋላ እንገናኛለን።

• እያያችኋት ቆዩኝ። ከ10 ደቂቃ በኋላ ጥያቄዬን እለጥፍላችኋለሁ።

ዘመድኩን በቀለ

04 Jan, 21:30


"…በነገራችን ታች…

"…እነዚህ ጎርጎራ ቲቪ ብለው የመጡ ናቸው መሀል ላይ ያለው እስማኤል ዳውድ ነው ፣ ቀዩ ከፍያለው ጌቱ ይባላል። የመርዓዊ ሰው ነው። ኡጋንዳ በወንድሙ የሆነ ካምፓኒ አለው ይባላል። ሦስተኛው አማኑኤል አብነት ነው። አማኑኤል አብነት እና እስማኤል ዳውድ ወዳጆቼ የነበሩ ናቸው። በተለይ አማኑኤል አብነት በሰኔ 15 ጉዳይ ፍዳውን ባየ ጊዜ እኔ ነበርኩ አጽናኙ። አሁን በቀደም ዕለት ለቤቲ አግዞ ሰድቦኝ፣ መልሶ አጠፋው። እስማኤልም የቅድስተ ማርያም ልጅ ነው። ወዳጄ ነው። ሰሞኑን ታሞ አልጋ ላይ የከረመ ልጅ ነው።

"… እነዚህ ሦስት ሰዎች ናቸው "በላይነህ ሰጣርጌ" በሚል የመንፈስ ስም የሚጽፉት። በላይነህ ሰጣርጌ የጋራ የብዕር ስም መሆኑ ነው። በላይነህ ወሎ ነው ያለው፣ ሸዋ ነው ያለው ብለው ብዙ ሰዎች ግራ ይጋባሉ። በላይዬ እነዚህ ናቸው። አሁን እነዚህ ሦስቱ ወፎች የጻፉትን ቆይቼ እለጥፍላችኋለሁ።

• ዘመነ ካሤን ግን ፈጣሪ ይጠብቀው።

ዘመድኩን በቀለ

01 Jan, 02:37


መልካም…

"…እዚያው ጎጃም ነኝ። ዞር ዞር እያልኩ ነው። ከጀመርኩት ከጎጃም ከጉብኝቴ እኔን ለማስተጓጎል እነ ሰሎሞን ባለ ሃውልቱ፣ እነ እሼ ገጠሬው፣ ፋራው፣ 100 ኪሎው ሰገጤ ስኳዱ ዊኒጥ ዊኒጥ ቢሉም፣ እነርሱ ዓመታት የለፉበትን አጀንዳ እኔ በሰከንድ ዶግ አመድ አደረግኩትና አሳረፍኳቸው።

"…እኔ አማኝ ነኝ፣ እኔ ሃይማኖት አለኝ፣ እኔ ቃልኪዳኔን አላፈርስም። ሰማይ ዝቅ፣ መሬት ከፍ ቢል ፍግም ብዬ ወደ መቃብር እገባታለሁ እንጂ ዐማራን ከዐማራ የሚያቃቅር፣ የሚያጋጭ ተግባር ውስጥ አልገባትም። እኔ እንደ ስኳድ ከሃዲ አይደለሁም። እኔ ሰው ነኝ። ያውም ሙሉ የምሥራቅ ሰው። የሐረርጌ ቆቱ። አቦ ተዉና ሃይ ምንድነው ሳ…

"…ይህቺ ከሃዲ፣ የህዳር አህያ፣ አልማዝ ባለ ጭራ፣ የዐማራ መልክ፣ ቁመና፣ ስብዕና የሌላት፣ የስኳድ ገረድ፣ የሸንጎ አሽከር፣ የተመስገን ጥሩነህ ተከፋይ፣ የጥላሁን አበጀ ኮልኮሌ ፍላጎቷ ሌላ ነው። የንፁሐን ደም በእጇ ነው። ዐማራን በዚህ መጠን እንዳወረደች እያየኋት ትዋረዳለች። አርበኛ ዘመነ ካሤ በሁሉ እንዲጠላ እንደ ደከመች የእናቱ የእማሆይ አምላክ አር የነካት ቆሻሻ እንጨት ያደርጋታል። ደግሞ እኮ ዘርዓ ያዕቆብ የሰጣትን ትወና መተወን ራሱ አልቻለችበትም። እንባ ከየት ይምጣ አልማዜ? አልማዝ ባለጭራ።

"…ለጎጃም ዐማራ ግን ቆሜ ነው ያጨበጨብኩት። ስክን፣ ቁጥብ ብለው ሁሉን መረመሩ። በትእግስታቸውም ይኸው እሸቱ ገጠሬው የለጠፈውን አነሣው። የት ይገቡ? ምን ይውጣቸው?

"…የሚጠብቀኝ አይተኛም የሚለውን መዝሙር ከፍቼ፣ ጸሎት አድርጌ ሥራዬን የምጀምረው እንዲሁ በከንቱ መስሎሃል እንዴ? ብኩርናዬን በምስር ወጥ የማልሸጥ፣ ምስጢር ጠባቂ፣ ምንም የማይደልለኝ የተዋሕዶ ልጅ ነኝ።

• ገተቶቹ ሲዝረከረኩ እያያችሁ እናንተ ደግሞ በተራችሁ እስቲ ተንፒሱ…! ጀምሩ።

ዘመድኩን በቀለ

31 Dec, 16:35


👆 …መሥራት። እኛም እሱን ማስቀረት። ዓለም ቀውጢ ሆነች። ዋን ዐማራ ዘርዓ ያዕቆብ አበደ፣ ዋይ ዋይ አሉ። ጭራሽ ዛሬ ሙሉውን ለቀቁትና ገላገሉኝ።

"…የቪድዮው ምስጢር አሁንም እኔ ጋር ነው ያለው። ዘመዴ ጋላ ነው ብለው፣ ዘመዴ ኦሮሞ ነው ብለው፣ ዘመዴ የአይተ አስገዶም ልጅ ትግሬ ነው ብለው። ዘመዴ ማይም ነው፣ አልተስተማረም ብለው፣ ዘመዴ ዕብድ ነው፣ መራታ ነው ብለው። በእኔ በኩል ጎጃምንና ጎንደርን ለማፋጀት ብለው፣ ቪድዮው ኑዛዜ ነው ብለው ለእኔ አድርሰው ለዘላለም ደም ሊያፋስሱ የነበሩት ዥልጦች ዘመዴ ማን እንደሆነ ዐላወቁም ነበር። ዘመዴ ዘመዴ ነው። እኔ ዘመድኩን በቀለ አክሊለ ገብርኤል፣ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የሐረርጌው መራታ፣ የምሥራቁ ሰው፣ ባለማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ፣ አንድ ለእናቱ ሺ ለጠላቱ የዐማራ የነፍጠኛው ወዳጅ ወድጄና ፈቅጄ ማንም ሳያስገድደኝ ሳይከፍለኝ፣ ሳይቀጥረኝ፣ በፈቃዴ የዐማራን ሾተላይ እነቅል ዘንድ፣ በዐማራ ላይ የሚዶለትን ሴራ አፈራርስ ዘንድ፣ የዳዊት ወንጭፍ፣ ጠጠሩንም ሆኜ በዐማራ ላይ የቆመውን ጎልያድ በስመ ሥላሴ አጋድም ዘንድ የተላኩ መሆኔን ነው ብዙዎች ያላወቁት። እንደዚያ ነኝ።

"…የቪድዮው ምስጢር እንኳንም ራሳቸው አወጡት እንጂ እሑድ በመረጃ ቲቪ በነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር ይተረካል። ሺድዮው እንዴት ተቀረጸው? በማን ፈቃድ ነው የተቀረጸው? ማን ቀረጸው? መማር የት ክልል ነበር የሚኖረው? እንዴት ከነበረበት ክልል ወጥቶ ደቡብ ጎንደር ሄዶ ተገደለ? ተዋናዮቹ እነማን ናቸው? ቪድዮው መጀመሪያ ተቀርጾ ሳለ አይ እንዲህ አይደለም፣ አስተካክሎ ሌላ ይቀረጽ ተብሎ ይሄ አሁን የተቀረጸው ቪድዮ ለሁለተኛ ጊዜ እንዴት ተቀረጸ? ከአሜሪካ መማርን ሰብኮ ጎንደር ያስገደሉት እነማን ናቸው? ይሄን የቪድዮ ፋይል ከኮምፒዩተሩ ውስጥ ያወጣውና የወሰደው የአብን አባል ማነው? እይተ አያሌው መንበር ይሄን ቪድዮ እንዳወጣው ከእኔ ጋር ሲጻጻፍ የነበረው ቴክስት እና የእኔ ምላሽ ምን ነበር? የሚለውን በዝርዝር በመረጃ አስደግፌ እመጣበታለሁ። እኔ ዘመዴ ነኝ። የዐማራው ታማኝ ዘመድ። ቃልኪዳኔን የማላፈርስ። ስለዚህ የመማር ገዳዮች ራሳቸውን በራሳቸው እንደገደሉ ነው የምቆጥረው። ዓሣ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል።

"…በዚህ ቪድዮ ምክንያት የሚጣላ፣ የሚገዳደል ዐማራ ግን የለም። በዚህ ቪድዮ ምክንያት የሚቆም የዐማራ ትግል የለም። አርበኛ ዘመነ ካሤ፣ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ፣ አርበኛ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባ ገና ለገና አንድ ላይ ገጥመው፣ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ አንድ ሆኖ እኛ ቦታ ልናጣ ነው ብለው ተንቀዥቅዠው የሞት ሞትሞቱ። ጎጄ መለኛው፣ የፖለቲካ ነቢያቱ ሀገር ጎንደር አንድ ሆነው ዐማራነት ያስከብራሉ። አሳምነው ጽጌን እየከሰሱ፣ ከኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀቤ ጋር ወዳጅ ለመሆን የሚላላጠው፣ ሀብቴ ወልዴ ከስሶ ሙሃቤን ሊበላ ያሰፈሰፈው ስኳድ ከሰረ። የሞት ሞት ሞተ። አበቃ። አሁን የዐማራ አንድነት ይወለዳል፣ የዐማራም፣ የኢትዮጵያም ትንሣኤ ይበሠራል። መርገምቱ እስኳድ ወደቀ። ወደቀ። እኔ ዘመዴም ጣልኳቸው። ደመሰስኳቸው። ይሄ ርእሰ አንቀጽ ለታሪክ ይቀመጥ። በየቀኑ ታሪክ ነው የማሳያችሁ። ይኸው ነው።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

• ይደፈርሳል… ግን ደግሞ ይጠራል…

•••

ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ታሕሳስ 22/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

ዘመድኩን በቀለ

31 Dec, 16:35


👆 "…እኔ ጎጃም ከገባሁ በኋላ ግን አርበኛ ዘመነ ካሤን የሚሳደቡት፣ የሚያዋርዱት ፀረ ጎጃም ዐማራ፣ ፀረ ዘመነ ካሤ ኃይላት በሙሉ ጠፉ። ይኸው በሕይወት ዘመኑ አርበኛ ዘመነ ካሤ ሳይሰደብ ለ1 ሳምንት ሆነው። ዘርአ ያዕቆብም አኪላም መርዝ እንደ ቀመሰ ውሻ አኘከዚያ እዚህ ቤት ከመክለፍለፍ በቀር ዘመነን እና የጎጃም ዐማራ ፋኖን ለመስደብ ፋታ አጡ። ጠይቁ እስቲ፣ ዘመዴ ጎጃም ከገባ ወዲህ ምን ከባድ ጉድ አጋጠማችሁ ነው ዘመነን መስደብ ያቆማችሁት በሏቸው። እነ እስኳድ፣ እነ ዋን አዋራ፣ የአገው ሸንጎ ዘመነን መስደብ ማብጠልጠሉን ትተው በአልማዝ ባለ ጭራዋ ቤት ተኮልኩለው እሷ ስትሰድበኝ እነሱ ራሳቸውን በራሳቸው ያረካሉ። ግፈኞች እኮ ናቸው።
ምክንያቱም የበላይ አዛዣቸው አልማዝ ባለጭራ ትእዛዝ አላወረደችም። ጭራሽ ለራሷ ጉድ ፈልቶባት ተወጥራ እሷን ለማዳን አጋሮቿ ወደላይ ወደታች ሲሯሯጡ እነሱም ጉዱ ውስጥ ገብተው ቅልጥ ብለው ቀለጡ። ግልፅ ነው? ገባችሁ ኣ…?

"…ከዘመነ ካሤ የተማርኩት ሳያቋርጥ መጸለይን ነው። የእናቱ የእማሆይ ጸሎት፣ ቅንነቱ፣ ዐማራ መሆኑ፣ መገፋቱ፣ መገፈፉ ንቅንቅ የማያደርገው መሆኑ። ዘመዴ ተቸኝ፣ በአደባባይ ውቀሰኝ። ሰው እንዴት ትችት ይፈራል? ያላየነው፣ ያልገባን ካለ እናስተካክላለን። በእኔ በኩል፣ እኔ ዘመነን በተመለከተ ችግር ነው፣ ስህተት ነው ያልከውን ነገር ባገኘህብኝ ጊዜ ሁሉ ለሕዝባችን ስትል እንዳትራራልኝ፣ እንዳታልፈኝ፣ በወርቅ ቀለም የታተመ ማኅተሜን አሳርፌ ፈቅጄልሃለሁ ነው ያለኝ። ከአስረስም፣ ከየቆየ ሞላም የሰማሁት ተመሳሳይ ነው። ችግሮች አሉ። ችግሮቹ ግን ከዐማራ ፋኖ በጎጃም እጅ የወጡ አይደሉም። ይስተካከላሉ። ሆኖም ለእኛ ያልታየን ነገር ሊኖር ስለሚችል እንተች። ተቸን ዘመዴ ነው።ያሉኝ። እንዲህ ዓይነት ቃል ከዚህ ቀደም የሰማሁት ከዋርካው ምሬ ወዳጆ፣ ከምሬ ቀኝ እጅ ከአቤ ነበር። ደሳለኝና ዶክተር አብደላም እንዲሁ። ባዬም ቀናውም እንዲሁ። ይግርማል።

"…ጎንደር ስኳድን ስነካ የዳያስጶራው መንጋ ስኳድ እንደ ንብ ነበር የሰፈረብኝ። የዳያስጶራው ጎንደር ዐማራ ደንግጦ ዝም ነው ያለኝ። ስኳዱ ባዶ በርሜል፣ ባዶ ቆርቆሮ ነውና ጩኸቱ አደገኛ ነው። በ12 ዓመቱ ዶክትሬቱን የተቀበለው ፓስተር ሁላ ወራዳ ሆኖ ነው የተገኘው። በድርጅቶቹ ማኅተም ሰርቆ መግለጫ ሁላ ነው ያወጣብኝ። ኋላ ላይ አርበኛ ሀብቴ ወልዴና አርበኛ ባዬ ቀናው ሁለቱም በጋራ እኛ መግለጫውን አላወጣንም ብለው ኩም አድርገው ገላገሉልኝ። ያን የውሸት መግለጫ ግን ኢትዮ 360 እና እነ ሲሳይ ሙሉ እስከዛሬ ለጥፈውት ይታያሉ። ወይ ንቅንቅ ዘመዴ።

"…ጎጃም ስገባ ግን ከዚያች "ቅዳሜ ገበያ ሄዳ እስከአሁን ካልተመለሰችው አልማዝ ባለ ጭራዋ በቀር ሁሉም ክትት አሉ። የጎጃም ቲክታከሮች አንደበታቸው የተገራ ሆነ፣ በትዊተር ስፔስ መንደር ያሉት የጎጃም ዐማሮች በሙሉም እኔን ትተው በግፍ የታሠሩትንና ህክምና ተከልክለው በግፍ የሚሰቃዩትን የዐማራ እስረኞች፣ እነ ክርስቲያን ታደለ፣ እነ ዮሐንስ ቧ ያለውን ፎቶ ለጥፈው ስለ እነሱ ነበር የሚጮሁት። እነ ሄኖክ፣ እነ ዓባይና ጣና፣ እነ ወዳጄ ታዬ እና ሌሎችም ቢሆን "ዘመዴ ገና ምኑንም ሳይናገር፣ ያለውን ሳንሰማ አንሰድበውም፣ አንናገረውም ብለው ወገሙ። የጎንደር ስኳድ እና አልማዝ ባለጭራዋ የጎጃምን ስኳድ ቢጎተጉቱ፣ ቢጨቀጭቁ አልሰማችሁም አላቸው። ጠረቀማቸው። ነደዳቸው። በሰጩ። ተበሳጩ። ጭራሽ እሁድ በመረጃ ቲቪ የሚጠቅማቸውን ነገር ያገኙ እንደሁ ብለው ቢጠብቁኝ ወፍ የለም ሆነባቸው። ዘመነ ካሤ ይወቀሳል፣ አስረስ ይተቻል፣ ዝናቡ ይወቀሳል ብለው ቢጠብቁ፣ ቢጠብቁ ወፍ። እኔ ጎጃም ገብቼ ሌባ፣ ዘራፊ ወቅሼ ጉብኝቴን እቀጥላለሁ ብዬ መርሀ ግብሬን ስጨርስ እንጥላቸው ወረደች። ከዚያ የመታነቂያ ገመዳቸው ወደሆነ አጀንዳ የመጨረሻ ግብአተ መሬታቸውን ወደሚፈጽመው አዘቅት ሰተት ብለው ገቡ።

"…ስኳድ ዶር ደረጄ የቲክቶክ ቤት ከፈተ። እስኳድ በሙሉ ተሰበሰበ። ሰኔ 15 አጀንዳ ይሁን ብለው ወሰኑ። የጎጃም ባለሀብቶችን፣ የጎጃም ብአዴኖችን፣ እነ ዘመነ ካሤን እንመታበታለን ብለው አጀንዳ ቀርጸው ገቡበት። እኔም መጨረሻቸውን ልይ ብዬ መቀሴን ይዤ እየቀዳኋቸው ተቀመጥኩኝ። መሃል ላይ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የአብንን የተለመነ ዶላር ቆርጥሞ በልቷል የሚባለው የስኳድ መሳፍንት ባዘዘው የሌለ ፋውል ገባ። ማኖ ነካ። ኢሪጎሬ ለእኔ ተሰጠ። "በሰኔ 15 ጉዳይ አስቻለው ደሴ፣ ሀብቴ ወልዴም ጥፋተኛ ናቸው" ብሎ መሴ አፈረጠው። ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ዘልሎ ገብቶ አቁም፣ ቢለው ምን ቢለው የፈሰሰ ውኃ ሆነ። እኔም ቀድቼ ያዝኩት። የጎንደር ዐማሮችም አዚማቸው ተገፈፈ። የስኳድ አካሄድ ተገለጠላቸው። በፋፍዴን በኩል መጥተው ውባንተን የበሉት፣ ሀብቴ ሳይበላ ቀደማቸው። አበዱ። ይኸው ስሙን ወደማጥፋት ገቡ። ለእኔ ግን ጮማ ድል ነበር።

"…ከዚያ ዘመዴ የመማርን ኑዛዜ በልቷል። ኑዛዜውን ይልቀቅልን ብለው መጮህ ጀመሩ። እኔ ዝም፣ ጭጭ። በኋላ የወርቅ እንቁላል የሚጥልልኝ ቄብ ዶሮዬ አፄ ዘርአ ያእቆብ ነቢዩ ትግሬው ሲንቀዠቀዥ በውስጥ መስመር በእሱ ቤት እኔን ፋራውን፣ እኔ ማይሙን ዘመዴን መመርመሩ ነው "የሆነ መረጃ ደርሶኛል፣ ራስህን ጠብቅ ብሎ ከማስዶከክ መሞከር፣ እንዲያውም ሰኞ የጠፋኸው እሱን ሰምተህ ነው ብሎ ጓ ማለት፣ እኔም አላግጬበት እፀ አስለፍልፍ ሰጥቼው ሙድ መያዝ፣ ቆይተው በእሸቱ ገጠሬ ቲክቶክ ገጽ ላይ "የመማርን" ቪድዮ ቆርጠው መልቀቅ። ከዚያስ ከዚያ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ጎጃም፣ ክፍት አፍ ማይሟን የህዳር አህያ ግቢ፣ ግቢ ብለው ጃስ ማለት። እኔና ወፎቼም ሰሎሞን ሃውልቴን እየቀረጽን፣ በዚያውም አልማዝ ባለጭራ "እያለቀስሽ ተውኚ" ተብሎ የተሰጣትን ገፀ ባሕሪ ለመተወን ከች ማለት። የሌለ እንባ ከየት ይምጣ? ስትለፋደድ ብትውል ማን ይስማት። ወዲያው በጓሮ በር ዘርአ ያእቆብ መጥቶ ዘመዴ ይሄ ቪድዮ አንተ እጅ ከነበረ ማን ለቀቀው ማለት። እኔም ማን ለቀቀው ብዬ መልሼ መጠየቅ። አፄም መልሶ እሸቱ ገጠሬው ነው ማለት። ታዲያ እኔ ካልለቀቅኩት እኔን ለምን ትጠይቀኛለህ እሱኑ የለቀቀውን ጠይቅ ብዬ መመለስ። ሞኙ አፄው እሺ ዘመዴ ብሎ ቤት ከፍቶ እሸቱ ገጠሬው ና ብሎ መጥራት። ነገሩ ውሉ ጠፋ። ተደበላለቀ።

"…አልማዝ ባለጭራ ከወሎዋ ወሃቢይ ቴምር በቀር ዐማራ ሁሉ አይንሽን ላፈር ማለት። ወዳጄ ዩሪ ድንገት አልማዝ ባለጭራ ቤት መግባት። ቤቲ አትሳሳቺ "ዘመድኩን ሊሰጣቸው አይችልም። ዘመድኩን ሊያወጣው ቢፈልግ ገና ድሮ ነበር የሚያወጣው፣ እናም ደግሞ ለስኳድ፣ ላደቀቃቸው፣ የፖለቲካ ሞት ለገደላቸው ለስኳዶች ምን ይሁነኝ ብሎ ነው የሚሰጠው ማለት። ቤቲ አበደቻ። ከእኛ ከጎጃሞች ሲጣላ ጊዜ ጎጃሞችን ለመበቀል ብሎ ነው ያወጣው ብላ መፎግላት። ከዚያ በፊት ሰሎምን ባለ ሃውልቱ በተደጋጋሚ እኔ ጋር መደወል። እኔም እነ ሰሎምን ጋር ወዳለ ወፌ ደውዬ ሃውልቴ እየደወለ ነው። ምን ሆኖ ነው ማለት። ተወው፣ ስልኩን እንዳታነሣ፣ አንተን አናግሮ ሊቀዳህ ነው። የሰኔ 15 ቱን ቪድዮ፣ የመማርን ኑዛዜ ብለው ቀደም ሲል ልከውልህ አንተን ጨቅጭቀው አላወጣ ያልከውን ሊያወጡት ነው። ሰሎሞን ባለሃውልቱም ቪድዮ ሠርቷል፣ ከርስተይ ተስፋዬም ጋር የሠሩትን ቪድዮ እንካ ያዘው ብሎ መላክ። ክርስቲያን መሳዩ ሰሌ ባለ ሃውልቱም ማይሙ ሆዬ ሳት ብሎት "ነገ የሚለቀቅ አንድ ቪድዮ አለ። ገንዘብ አልከፍለው ስላሉት ሊለቀው ነው ብሎ ቪድዮ…👇

ዘመድኩን በቀለ

31 Dec, 16:32


"ርእሰ አንቀጽ"

"…በምስጋና እጀምራለሁ። ቆሜ በማጨብጨብ እጀምራለሁ። የዐማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ከጥልቅ እንቅልፍ በመንቃቱ፣ በየትኛውም አጀንዳ የማይጠለፍ፣ የማይቆም፣ የማይሸበር መሆን በመጀመሩ ቆሜ አጨበጭባለሁ። በተለይ ጎጃም። አድናቆቴ ልዩ ነው። አክብሮቴ ምስጋናዬም ይድረሳችሁ። ከምር እውነቴን ነው።

"…ለጉብኝት ሸዋ ነበርኩ። በሸዋ ቆይታዬ የሸዋ ዐማራ፣ የንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ፣ የዓምደ ጽዮን፣ የእምዬ ምኒሊክ ልጆች በክብር ነበር የተቀበሉኝ። ነገር ግን በሸዋ ቆይታዬ የሸዋ ልጆችን ማስክ፣ ጭንብል ለብሰው ፈተና ዮሆኑብኝ ስሁላውያን፣ የጎንደር ዐማራን ያጫጩ፣ የጨፈለቁ፣ ቢሮአቸውን መቀሌና አዲግራት አድርገው የነበሩት የፖለቲካው ቅማንትና የትግሬ ዲቃሎቹ ዐማራ መሳይ አሞሮቹ ነበሩ። ከሸዋ በላይ ሸዋ ሆነው ዋይ ዋይ አሉ። እነ ልጅ ተድላን የመሰሉ የሸዋ ዓምዶች ባይኖሩ ኖሮ የስኳዱ ጫጫታ አደንቋሪ፣ አዋኪ ነበር።

"…የሸዋውን ጉብኝቴን ለማደናቀፍ ጃል ሀብታሙ አያሌው አፍራሳ፣ አይተ አበበ በላው እስክስ፣ ኢትዮ 360 እና አዲስ ድምጽ በሚባል ሚዲያ ሁላ ነው ዘምተውብኝ የነበረው። ግማሽ ጎንደሬ፣ ግማሽ ጎጃሜው ስሁቱ ሾተላይ፣ የዐማራ ከፋፋይ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጎንደሬው ሸዋ ተቀምጦ ሸዋን ለሁለት አባላው፣ የሸዋ መኳንንቱን አሰግድ መኮንንን በሀብታሙ አፍራሳ፣ ባሳሚ ቅማንቴ፣ በመከራው ማሞ፣ በአበበ ጢሞ አዋክበው ለጅብ አሳልፈው ሰጡ። የጎንደሩ ስኳድ በቡድንድ ተደራጅቶ በፓስተር ምስጋናው ቡራኬና ጸሎት እኔ ላይ ተሰማራ። ከሸዋ በላይ ለሸዋ አልቃሽ፣ አዛኝ ሆነው አዋከቡኝ። እነጃል ሀብታሙ አዲስ ድምጽም በጃል እስክንድር በኩል ሆነው በጋሽ አሰግድ ላይ ዘመቱ። ውጊያው ከባድ ነበር። የጻድቃኔዋ ማርያም፣ የደብረ ብርሃኑ ቅድስት ሥላሴ፣ ሚጣቅ አማኑኤል፣ ኢቲኪሳ ተክለሃይማኖት፣ ሳማ ሰንበት፣ የሸንኮራው ዮሐንስ፣ የአርመኒያው ቅዱስ መርቆሬዎስ፣ የጣርመበሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የአርበሀራ መድኃኔዓለም፣ እመጓ፣ መንዝ ቅዱስ ኡራኤል የጻድቁ መልከ ጸዴቅ፣ የዘብሩ ገብርኤል አባቶች ጸሎት ረድቶች አደቀቅኳቸው። ድምጥማጣቸውን አጠፋኋቸው።

"…የሸዋ ጉብኝቴን በድል ካጠናቀቅኩ በኋላ በቀጥታ የሄድኩት ወደ ወሎ ነበር። በዚያም ስኳድ ከጥቂት እኔን ጠል ከሆኑ የወሎ የወሃቢያ እስላሞች ጋር ሆኖ ጠበቀኝ። ወዳጄን፣ አክባሪዬን ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባውን፣ እነ ወዳጄ ፋኖ ኑረዲንን ገንጥሎ ጠበቀኝ። ነገር ግን አንዲትም ጥይት ሳልታኮስ፣ ፈንጂም ሳላፈነዳ፣ ስኳድን በተሳካ ቀዶ ጥገና ከወሎ ላይ ቀፍፌ በሰላም ለወሎ ጤና ሰጥቼ ከወሎ ቤተ ዐማራ ወጣሁ። በላቤ ያገለገልኳቸው፣ ላንቃዬ እስኪሰነጠቅ ለምኜ ያስገነባኋት የኮምቦልቻዋ ማርያም እናቴ ረዳችኝ። በብዙ የተባረኩባቸው የደሴ መድኃኔዓለም፣ የደሴ ኪዳነምህረት፣ የኩታበር አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ የደሴ ገብርኤል፣ የሀይቅ እስጢፋኖስ፣ የጅብ አሥራው ሚካኤል፣ ወልድያ ኪዳነምሕረት፣ የራማዋ ኪዳነምህረት፣ የአሸተን ማርያም፣ የቅዱስ ላሊበላ፣ የቅዱስ ነአኩቶ ለአብ፣ የዛዚያ ሥላሴ፣ የቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ፣ የወለደድቢት ኪዳነምህረት፣ የአቡነ አሮን አባቶች ጸሎት ረዳኝ፣ አገዘኝ። አንድ ለእናቱ፣ ሺ ለጠላቱም አደረገኝ። ታድዬ። እንደኔ ዕድለኛ አለን?

"…ጉዞ ወደ ጎንደር ሆነ። ለከባድ ፍልሚያ ራሴን አዘጋጅቼ ወደ ጎንደር ገስግሼ ገባሁ። በአፄ ቴዎድሮስ በጀግናው ሀገር ከስሁላውያን ከፖለቲካው ቅማንትና ከትግሬ ዲቃሎቹ ስኳዶች ጋር ልፋለም ገባሁ። በእውነት ጎንደር በደረስኩ ጊዜ የጎንደር ሕዝብ፣ የጎንደር ሊቃውንት በንጉሥ ክብር ነበር የተቀበሉኝ። ከስኳድ ጋር ልዋጋ ጎንደር መግባቴን የሰሙ ሁሉ ለእኔ ማዘን፣ መጨነቃቸው ያሳዝናቸው ነበር። የጎንደር ሕዝብ ጎንደር ተወልደው የጎንደር ዐማራን በዋጡ ስኳዶች ተረግጦ ይገዛ ስለነበር በእርግጥ ያሳዝን ነበር። ቀበሌ ስሄድ ስኳድ፣ ወረዳ ስገባ ስኳድ፣ እድር ስሄድ እስኳድ፣ ፖሊስ፣ ፍርድ ቤት ብሔድ እስኳድ፣ ዮኒቨርሲቲ ብገባ እስኳድ፣ አብን ጽሕፈት ቤት፣ ብአዴን ብልጽግና ቢሮ ብገባም ስኳድ፣ በላይ ብወጣ በታች ሕዝቡ በጥቂት ስኳዶች ታንቆ መላወሻ አጥቶ ሲሰቃይ አሳዘነኝ። ከወልቃይት እስከ ባሕርዳር ደቡብ ጎንደር፣ ከአዲስ አበባ እስከ ኡጋንዳ ካምፓላ፣ ከዚያም አሜሪካ ድረስ የተዘረጋው መረብ እጅ ከባድ ነበር። ያንን ለመበጣጠስ እግዚአብሔር ካልረዳ አይሆንምና የእግዚአብሔርን እርዳታ ፍለጋ ጎንደር ከዚህ ቀደም ያገለገልኩባቸው፣ የተባረኩባቸው ቅዱሳን ጋር የሙጥኝ አልኩኝ።

"…በራብ በጥም የጎበኘኋት ቤተልሄም፣ ደሜንም ላቤንም ላፈሰስኩባት ዙርአምባ፣ ለወፍ ዋሻ ኪዳነ ምሕረት አባቶቼ ጸልዩልኝ አልኳቸው፣ ጋይንት ሥላሴ፣ ውቅሮ መድኃኔዓለም፣ ጨጨሆ መድኃኔዓለም፣ ጎንደር አርባአራቱ፣ ዋልድባ ዳልሽሃ፣ ወልድባ አብረንታንት፣ ወልድባ ሰቋር አመለከትኩኝ፣ ደብረ ሃዊ ቅዱስ ያሬድ ገዳም መልእክት ሰደድኩኝ፣ ጣና ቂርቆስ፣ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ፣ ዛራ ሚካኤል አቤት አቤት አልኩኝ። ጸሎት ልመናዬ ተሰማ። ግጠም፣ ግጠም፣ በአህያ መንጋጋ እንደ ሳምሶን ሺውን አጋድመው ተባልኩ። ኃይል ተሰጠኝ፣ አንበሳውን ስኳድ በእርግጫ፣ ነብሩን ስኳድ በጡጫ እነርተው ጀመር። ዘመዴ አለቀለት፣ ስኳድን የማይነካውን ነክቶ አበቃለት። የማይነካ ነካ ብለው ብዙዎች "አይ የሰው ልጅ መጨረሻ፣ እንዳማረ አይገድል" ብለው ተረቱብኝ፣ ወጣ ወጣና እንደ ሸምበቆ፣ ተንከባለለ እንደ ሙቀጫም ብለው ተረቱብኝ። ከጥቂቶች በቀር ከጎኔ የሚቆም ጠፋ። ሁሉም ሸሸኝ። በፔይፓልና በዶነር ቦክስ የሚያግዙኝ ሁላ የሚለግሱኝን 5 እና 10 ዶላር አቆሙብኝ። ስድቡ፣ ዘለፋው፣ እንደ ናዳ ወረደብኝ። እኔ ግን ወጥሬ ከዘርፈ ብዙው ስኳድ ጋር ገጠምኩኝ። ከጎኔ ቆሞ ድሆችን የሚረዳው የስውዲኑ ወዳጄ አቶ ቴዎድሮስም ለቀበሮ ሜዳ ቃል የገባውን መቶ ሺ ብሮች ከለከለ፣ ጆሮዬ ላይ ስልክ ዘጋ። የለንደኑ ስኳድ ጎፈር መንገሻም ዘለፋ ጦማር ላከልኝ፣ ጫጫታው በዛ። በእነ ወረምቲቲ የቲክቶክ ሴተኛ አዳሪ በእነ ቤታዮ ተሞለጭኩ።

"…እነ ዶክተር ደረጄ ወበሩብኝ፣ እነ ሚኪ ጠሽ እሪሪሪ አንጓይ ፍስስ አሉብኝ፣ እነ እስክስ አበበ በላው ዘፈኑብኝ። እነ እሸቱ ገጠሬው ተለፋደዱብኝ፣ እነ አያሌው መንበር፣ እነ መሳፍንት አዘዘው፣ እነ ፓስተር ምስጋናው ውለው አደሩብኝ፣ አፍንጮ ከኡጋንዳ፣ እነ አይተ ሙላት አድኖ ከካምፓላ የስድብ ሚሳኤላቸውን አስወነጨፉብኝ። ዓለሙ ሁሉ ደነገጠልኝ። በዚያ ላይ የትግሬ ቅቦቹ እነ ዋን ዐማራ በጀትም በጀትም ደበደቡኝ። አይረን ማኑ ዘመዴ ግን አክሊለ ገብርኤል መክቶ፣ መክቶ አንክቶ ለቀቃቸው። ቅደሚከፊት ከኋላዬ የምላት ዘወትር የምማጸናት የጌታዬ እናት ድንግል ማርያም አገዘችኝ። ምስኪኑ የጎንደር ዘአማራ ከጎኔ ቆመ። የነደደብኝን እሳት መከተልኝ። አበረደልኝ። ሽፋን ሰጠኝ፣ መንገድም መራኝ። አይዞን ዘመዴ ብሎም አበረታኝ። እነ ሰሎሞን ባለሃውልት ቀጥ ብለው ሚሳኤላቸውን ገትረው ሊያስወነጭፉብኝ ዝግጁ መሆናቸውን ላኩብኝ። እኔም ዓለም ይወቀው ብዬ ለጠፍኩ። ሰለሞን ይተኩሳል ብዬ ስጠብቅ ረጭቶ፣ ረጭቶ ራሱን አበላሽቶ አረፈው። እኔም በሳቅ። ብቻ ከባድ ነበር። እየቆየ ሲመጣ ግን አሸናፊነቴ ተረጋገጠ። በድል ወጣሁ። እስክንድርን ከጎንደር ዐማራ እጁን ቆርጬ፣ የሀብታሙ አርፋሳን ምላስ፣ የአበበ በላውን ወገብ ዛላ ቆርጬ በድል ወጣሁ። በመጨረሻም እነ አርበኛ መሳፍንት ዳዊታቸውን እየደገሙ፣ መስቀላቸውን ተሸክመው ተገለጡ። አጋንንቱን ስኳድ አማትበው በታተኑት። ኃብቴ ወልዴንና…👇

ዘመድኩን በቀለ

31 Dec, 16:32


👆 …ባዬ ቀናን አስታረቁ። ደረጄ በላይና ሰሎሞን አጠናው፣ ብሮፌሰሮቹ ተንጫጩ። በአጭርም ተቀጩ። ጎንደር የአንድነት ጉዞውን ስጨርስ ሳልቆስል ከጎንደር ተከብሬ ወጣሁ። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ከጎንደር መልስ ጉዞዬን ወደ ጎጃም ነው ያደረግኩት። በቀጥታ ነው ከጎንደር ተነሥቼ ባሕርዳር የገባሁት። ሁላችሁ እንደምታውቁት የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ ነው እኔ ወደ ጎጃም የዘልቅኩት። ከጎንደር ጦርነት መልስ ስለሆነ ትንሽ ልረፍ፣ ላገግም ብዬ ነበር ወደ ጎጃም መግባቴን የተናገርኩት። በጎጃምም ግጥሚያ ካለ ልገጥም፣ ልዋጋ፣ እንደ ጎንደሩ ስኳድ የጎጃሙም ሸንጎ ቢገጥመኝ ብዬ ቀደም ብዬ ተዘጋጅቼ ነበር የገባሁት ጎጃም። እንደ ወትሮው በሌሎቹም የዐማራ ግዛቶች ሳደርግ እንደነበረው ሁሉ በጎጃምም ወደ ውጊያም፣ ወደ ምርመራም ከመግባቴ በፊት በአንድም በሌላም ላቤን ወዳፈሰስኩባቸው፣ ዘወትር በጸሎታቸው ወደሚያስቡኝ ገዳማትና አድባራት ነበር መልእክት የላኩት። ዲማ ጊዮርጊስ፣ ደብረወርቅ ማርያም፣ መርጦለማርያም፣ ደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተ ሰላም ጊዮርጊስ፣ በሕርዳር አዲሱ ሚካኤል፣ ባሕርዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ጣና ደብረ ማርያም፣ ሽምብጥ ቅዱስ ሚካኤል፣ ማረፊያዬ፣ ምሽጌ፣ ድካም ማቅለያዬ ወደ ሆነው የጣና ገዳማት በሙሉ መልእክት ልኬ ዞር ዞር ማለት ጀመርኩ።

"…ጎጃም መግባቴን የሰማው የቆሰለውና ከሞት የተረፈው የጎንደሩ ስኳድ የሴራ ዶሴውን ሸክፎ እየተንፏቀቀ ጎጃም ገባ። አላስፈራኝም። ማወቅ የምፈልገው ነገር ግን ነበረ። ማነው ለጎንደሩ ስኳድ፣ ለወሎው ወሃቢያ፣ ለሸዋው ስኳድ፣ በጎጃም አድራሽ ፈረስ? ማነው የህዳር አህያ ሆኖ የሚጫነው? በማለት እሱን ለማወቅ ነበር ሥራ የጀመርኩት። የአገው ሸንጎ የስኳድ ገረድ፣ የስኳድ ባርያ መሆኑን ባውቅም የስኳዱን በጎጃም ያለ አህያ ግን ለማወቅ ጓጓሁ። እናም እሱን ወደ መውጣት፣ ወደ መግለጡ ሄድኩኝ። የአቡነ ኤስዎስጣቴዎስንና የዘርዓ ብሩክን ፀበል ረጨት ረጨት ማድረግ ጀመርኩ። ወዲያው ከስዊዘርላንድ አንዷ አሮጌ የህዳር አህያ ማናፋት ጀመረች። ተንበጫበጨችም። ዕፀ አስለፍልፌን ቀምሳ ነው መሰለኝ ዋይዋይ ማለት ጀመረች።

"…እኔ ዘመዴ በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎንደር የዐማራውን ሾተላይ ባንዳ ሁላ ነጣጥዬ ስላደቀቅኩ፣ ነጣጥዬም ስለመታሁ ጎጃም ስገባ ብዙም አልተቸገርኩም። ምክንያቱም የወሎው ወሃቢያ ሁለት ፍሬ ሆኖ ሊያግዝ ቢመጣ ነው። እንደገመትኩትም ወሮ ቴምር ብቻ ናት ከወሎ አዝማሪዋን አልማዝ ባለ ጭራዋን ለማገዝ የመጣችው። ከጎንደር ቁስለኛው እስኳድ ነው እየተንፏቀቀ ቢመጣ፣ እሱን መውገር አያቅተኝም። በቁሙ ያልቻለኝ ክራንች ተደግፎ፣ ዊልቸር ላይ ተጎልቶ ምንአባቱ ሊያመጣ? ከጀርባ ዋን ዐማራ ከዋን ዐማራም አኪላ ድንጉጡ ጠፍቷል። አምሀ ሙላው ወደ ወለጋ ሄዶ ነበር እዚያም አስወጥቼዋለሁ። ሮቤል ነፍሶበታል። የቀረው አይደክሜው፣ ተብታባው ትግራወይቲው አፄ ዘርአ ያዕቆብ ብቻ ነው። ዘርአ ያእቆብ ነቢዩ ቢመጣም ይዞ የሚመጣው የጎንደሩን ስኳድ መደዴ፣ መኪና ውስጥ ቁጭ ብሎ ላይቭ እየሠራ መኪናውን የተዘረፈው ሽንታም፣ ገገማ፣ ድልብ የወንድ ድብኝት የመሰለውን ሀራ፣ ሀራ፣ አልጫውን የትግሬ ዲቃላ የበሰበሰውን ባናናን፣ ጃል ሀብታሙ አዲስ ድምጽን እና የጠነቡ፣ የገሙ፣ የሸተቱ፣ የዐማራ ትግል አደናቃፊ የሸተቱ ፀረ ጎጃም ዐማራ መሳይ አሞሮችን ነው። እናም ስጋት በጎጃም የለብኝም ብዬ ነው በእውነት ደስ ብሎኝ የገባሁት። ነገር ግን የተደበቀ አይጠፋም እና ለማንኛውም የአዝማሪዋን ድልብ ፀረ ጎጃም ዐማራውን ኔትወርክ ማወቅ ስለፈለግሁ የተለመደውን የተበታተነ ጉንዳንና ቁጫጭ መሰብሰቢያ ልፋጭ ቁራጭ የአጀንዳ ሥጋዬን ጎጃም ምድር ላይ ወርወር አደረግኩ። እንደጠበቅኩት ባይሆንም አማኑኤል አብነት ከካናዳ፣ ግርማ አየለ፣ መንቆረር ኢንሳይደር፣ እና ጥቂት ውዳቂ የሸንጎ ርዝራዦች ብቻ ብቅ ብቅ አሉ። አቅመ ቢስ፣ ደካማ፣ ቀጭን፣ የተቀቀለ ፓስታ የመሰሉ ናቸው ብቅ ብቅ ያሉት። አሮጊቷም እነሱን ተማምና ያዙኝ ልቀቁኝ አለች። ጎጄ መለኛው ጭጭ። ዝም። እረጭ። ነቀለች። አበደች። የዊግ ጸጉሯ፣ የብብቷና የብሽሽቷም ፀጉር እስኪረግፍ ድረስ ተወራጨች። እኔም በሳቅ።

"…ጎጃም እንደገባሁ መጣሁልህ ጎጄ። የጎጃም ፋኖ መጣሁብህ ብዬ ብፎክር፣ ባቅራራ አረኤዲያ ማን ሰምቶች። ጭራሽ አስረስ ማረ ደውሎ ተቆጣ። እንዴት ብትንቀን ነው? እንዴት ብትደፍረን ነው በፆም የምትመጣው? ጠላው ጥንስስ ላይ ነው። ጠጁም እንደዚያው፣ ጎጃም ደርሰህ ጮማ ሳትቆርጥ፣ ቅቤውን ሳትቀምስ ምን አስበህ ነው? ልታሰድበን ነው ፍላጎትህ ብሎ ወበራብኝ። ኧረ እኔ ልገመግማችሁ፣ ልዋጋ፣ ልፋለማችሁ ነው የመጣሁት፣ ብዙ ችግር አላ ልሟገት ነው የመጣሁት አልኩት። ገና እኮ ጦርነት ልገጥማችሁ ሁላ እችላለሁ ጠበቃ አስረስ አልኩት። እሱ መብትህ ነው። ግጠመን፣ ሞግተን፣ መርምረን፣ እሱ አላሳሰበንም፣ ከሩቅ የመጣህ እንግዳ እንዴት በጾም፣ እንዴት ያለ ጮማ ወደኛ ትመጣለህ። ልክ አይደለህም። ለማንኛውም በቆይታህ እርዳታችንን የምትፈልግ ከሆነ ከላይ እስከታች አለን። አስጎብኚም የሚያስፈልግህ አይመስለንም እንደፈለግክ ጎብኝ። ስህተት ነው የምትለውን በሙሉ ዠልጠው። እኔንም፣ ዘመነንም ቢሆን አትማረን አለኝ። እኔም አልኩት። ትናንት የቆየ ሞላም ደውሎ እንኳን ደህና መጣህ ዘመዴ። ተናገር እንሰማሃለን ነበር ያለኝ። ተመካክራችሁ ነው እንዴ የጠበቃችሁኝ ብዬ ተገረምኩ። ማርሸትስ የት አለ? እባካችሁ መልሱልን ብዬም ማመልከቻ አስገባሁ። የተማጽኖ ጥያቄም አቀረብኩ። ይበቃዋል ቅጣቱም ብዬ እሪሪ አልኩኝ።

"…የጎንደር ስኳድ፣ አፄ ዘርአ ያዕቆብ፣ ቅዳሜ ገበያ አንድ ላይ ሆነው ከጎጃም በላይ አለቀሱ። ጮሁ፣ አበዱ። ሰሚ ግን አጡ። እንደማይሆንላቸው ሲያውቁ ጭራሽ ራሳቸውን እንደ ጻድቅ፣ እንደ ገለልተኛም ቆጥረው ብቅ አሉ። የሚያጅባቸው የጎጃም ዐማራና አገው ሲያጡ እንዲህ ማለት ጀመሩ። "ዘመድኩን ጎንደር ትቃጠላለች ብሎ ሲሰድበን፣ አንበሳ ስታወርዱለት አልነበር፣ ዛሬ ወደ እናንተ ሲመጣ ቻሉት ብለው አረፉት። አበበ በላው እስክስ ራሱ ተናግረን ነበር፣ ከጎንደር በኋላ ወደ ጎጃም ይመጣል ብለን ተናግረን ነበር ብሎ በእስክንድር የሳተላይት ቲቪ ደሰኮረ። እነ ቤታዮም ፊኒሺንጎ ያለቀበት የሀብታም ቪላ መስላ አቀረሸች። ቤቴ አልማዝ ባለጭራዋ ጭራዋን እየቆላች ብቻዋን ቀረች። ዘርአ ያዕቆብ ለእኔም፣ ለእሷም በውስጥ መስመር እየላከ እሷ እንድትሳሳት እያደረገ አፈር ከድሜ አስጋጣት። ጎጃሞች ድረሱልኝ፣ ወሎ ሸዋ፣ ጎንደር ብትል ወፍ። ጋሽ መሳፍንት ተከበቡ ብላ የትግሬ ልሳኑን የኢትዮ ፎረምን ቅርሻት ብታሰማ ወፍ። ወደ ላይ ወደታች ብትል ማን ይድረስላት። በመጨረሻ ግን በቴዲ ሃዋሳ ቤት ሥርዓተ ቀብሩን የፈጸምኩት፣ በቁሙ የቀበርኩትና የመንደር ዶሮ ጠባቂ አድርጌ ያስቀረሁት፣ አሁን ጢረታ የወጡ መበለቶች የእርቅ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆነው ዮኒ ማኛ ብሽሽትና ብብት ስር ተወሸቀች። ይሕች ፀረ ዐማራ አገው ሸንጎ፣ የኦሮሞ ዲቃላ የበለጠ በጎጃሞች ተናቀች። መሬት ያለው ኔትወርኳም ተበጠሰ፣ ጥላሁን አበጀም ራቃት፣ ሸሻት። ይሞታል እንዴ? ወፍ ጠፋ።…👇

ዘመድኩን በቀለ

31 Dec, 15:40


"…ጠብቅ… ከፍለኸኝ፣ ቀጥረኸኝ እኮ አይደለም የምጽፍልህ። በፈቃዴ ነው፣ ወድጄ፣ ፈቅጄ ነው የምጽፍልህ። ቶሎ በል ዘመዴ፣ ፍጠን እንጂ ዘመዴ፣ ኧረ ቆየህ ትለኛለህ እንዴ? ሥነ ሥርዓት ያዝ። ሚልኢላል ኢሄ።

"…ዓይኔ እንባ እያፈሰሰ፣ ጣቴ ደርቆ፣ ምሳ ሳልበላ እኮ ነው ከአእምሮዬ አፍልቄ፣ ፊደል መርጬ፣ ለሆሄያቱ ተጠንቅቄ፣ አስሬ ለክቼ አንዴ ቆርጬ የምጽፍልህ። አንድ መስመር መልእክት አሰካክተህ ሀሳብህን መግለጽ የማትችል አውርቶ አደር ሁላ ተረጋጋ።

"…ጎጃም እኮ ነው ያለሁት። የሊቃውንቱ ሀገር። የጀግኖቹ ሀገር። ጎንደር ላይ የሰበርኩት ስኳድ ዊልቸር ላይ ሆኖ ጎጃም ጠብቆኝ እሱን እየመከርኩ ነው። ስኳድ ሸንጎንና የህዳር አህያዋን አሮጌዋን አልማዝ ባለጭራን እያስጓራት ስለሆነ ሰሎሞን መንግሥት ምኗን ቅቤ ቀባት ብሎኝ ቅቤ እየፈልኩ ነው። ሥነ ሥርዓት አልኳችሁ።

"…የልብ ምታቸው እየጨመረ፣ ደም ግፊታቸው ከፍ እያለ የሚጠብቁኝ ስንትና ስንት የዐማራ ጠላቶችን በመዝግየቴ ልምሾ፣ ሽባ እያደርግኩ ነውና አትጨቅጭቁኝ።

"…ሰኔ 15 እኮ የቅዱስ ቂርቆስ ወርሀዊ በዓል ነው። ሊበላ…?😂 …ዘመዴ ፋራ ነው፣ ዘመዴ ዕብድ ነው፣ ዘመዴ ማይም ነው፣ እንግሊዝ አፍ አይችልም ብለህ ልትበላ…? ነስሎሃል?

"…ወዳጆቼ ግን እየጠበቃችሁኝ ነው አይደል? ጮማ ታሪክ ነው የምተርክላችሁ። በትእግስት ጠብቁኝ እሺ? እኔ ዘመዴ ነኝ እንጂ አቤ እስክስ፣ ሀብትሽ አፍራሳ፣ ሰሎሞን ባለ ሃውልቱ፣ አልማዝ ባለ ጭራ፣ እሸቱ ገጠሬው፣ አፄ ዘርሽ ነቤክስ አይደለሁም። የደበረህ ንካው።

• ከወዳጆቼ እኔ ማነኝ…?

ዘመድኩን በቀለ

31 Dec, 13:20


"…እንዲህም አላቸው፦ መብራትን ከዕንቅብ ወይስ ከአልጋ በታች ሊያኖሩት ያመጡታልን? በመቅረዝ ላይ ሊያኖሩት አይደለምን? እንዲገለጥ ባይሆን የተሰወረ የለምና፤ ወደ ግልጥ እንዲመጣ እንጂ የተሸሸገ የለም። የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ። ማር 4 ፥ 21-23

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

31 Dec, 13:20


“…መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም።” 1ኛ ቆሮ 2፥15

"…ዛሬም እዚያው ጎጃም ነው የምቆየው። እስከ ጥምቀት እዚያው ነው የምቆየው። አርበኛ አስረስ ማረ እንዳለኝ "በፆሞ፣ ከቅቤ ከጮማው፣ ከጠላው፣ ከጠጁ ሳትጋበዝ በቶሎ እንዳትወጣ፣ ጎጃምን ተንፈላሰስበት እንዳለኝ እንደዚያው እየተንፈላሰስኩበት ነው። አቤት የጎጃም መስተንግዶ ገራሚ ነው። ማርሸትም ወደ ቃል አቀባይነቱ የተመለሰው እዚያው ጎጃም ሆኜ ነው። አንት የማትረባ ሳትደውልልኝ ምን ሁነህ ነው? ቆይማ ላግኝህ ብቻ።

"…የዳያስጶራው የጎጃም ዐማራም እየደወለ ዘመዴ ቲሊሊ፣ ሞጣ ሳትገባ፣ ደጀን ሳታርፍ፣ ማርቆስ ደብረወርቅ ሳታድር፣ ፍኖተሰላም፣ አማኑኤል፣ ብቸና፣ ባህርዳር፣ ቡሬ፣ ጅጋ፣ መርጦለማርያም ሳትደርስ እንዳትወጣ አደራ እያለኝ ነው። አቅም በፈቀደ እኔም ለማዳረስ፣ ለመጎብኘት እሞክራለሁ እያልኩ እየመለስኩ ነው።

"…የነብሩን ጭራ፣ የጎንደርና የጎጃምን ጠላት፣ ዘንዶውን አንገቱ ላይ በጦማር ጦሬ ወግቼ ይዤዋለሁ። ፈጥርቄ ነው የያዝኩት። በጥድፊያ ቀሽም አጀንዳ የጎጃም ጉዙዬን ለማስተጓጎል ሲላላጡ ዓይቼ ስቄባቸዋለሁ። ጎጃም ዐማራ አሰዳቢዋ ጋለሞታዋ ቤተልሄም (አልማዝ) ዳኛቸው መገርሳ ነው ወዬሳ፣ መሳፍንት ባዘዘው፣ ሳሚ ቃኜ ቲዩብ፣ ዶር ደረጀ፣ ዶር ፓስተር ምስጋናው፣ ሰሎሞን ባለ ሃውልቱ፣ ርስተይ ተስፋይ፣ ትግራዋይቲው አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ነቢዩ፣ አያሌው መንበር፣ እሸቱ ገጠሬው ታጥባችሁ፣ ታጥናችሁ ጠብቁኝ።

"…እውነቱ ሌላ ነው። ጊዜውም ገና ነው። ጎጃምና ጎንደርን በዚህ መልክ ለማጣላት የቧቸርከው አቶ መልካሙም ከስረሃል። በእኔ በኩል ልታሳኩት ፈልጋችሁ የነበረው ጎንደርና ጎጃምን የማባላት ዕቅድም ከሽፏል። እነ ዘመነም ሥራ ላይ ናቸው። ወጥር የጎጃም ፋኖ።

"…ርዕሰ አንቀጹ ይከተላል። ዝግጁ ናችሁ…? 🫡

ዘመድኩን በቀለ

30 Dec, 10:06


"…በምትገቡባትም በማናቸይቱም ከተማ ወይም መንደር፥ በዚያ የሚገባው ማን እንደ ሆነ በጥንቃቄ መርምሩ። ማቴ 10 ፥11

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

30 Dec, 04:45


"…ከአንድ የቆየ የአልማዝ ባለጭራዋ ሙዚቃ በኋላ እንመለሳለን።

• አይ ፊልተር የሥራህን ይስጥህ…😁

~ እየተደነሳችሁ…!

• ቱ… ሞቻታለኋ እኔ ዘመድኩን አስገዶም አይደለኋትም በሕይወት እያለሁ መንሱር እግር አዝማሪማ የዐማራ ፋኖን ቦለጢቃ አይመራትም። አያቦካትምም 😂

ዘመድኩን በቀለ

30 Dec, 04:45


"…በጣም ነው እንዴ ያሳበድኳት…?

"…ሁለት ፀረ ጎጃም ዐማራዎች፣ ሁለት የዘመዴ ሰለባዎችን ሳላጨልል የቀረሁ እንደሁ ቱ…እኔ የአስገዶም ልጅ አይደለኋትም። 😂። እንቅልፍ ነው የማሳጣሽ። ገና የንፁሐን የዐማራ ወጣቶች ደም ይፈረድብሻል።

"…ዐማራም፣ ጎጃምም በእነዚህ ሸንጎዎች አይዋረድም። የአደይ ፀሐይ ልጅ ዮኒም አያድንሽም። ገና አብረሽው ስትሠሪ የነበረው ጃልወያም፣ የሕፃኗ የፌቨን አባት አወትም ይመጡልሻል። ግን አያድኑሽም።

"…ዛሬ ስዊዘርላንድ ገብርኤል ቅዳሴ ሄደሽ እንደተኛሽ ጨረስሽ። ቲክቶክ ላይ ስታቀረሺ አድረሽ እንዴት ነቅተሽ ታስቀድሺ። አሁንም በጊዜ ተኚ። ውለሽ አደርሽበት እኮ።

"…በቲክቶክ በዐማራ ስም ስትዘርፊ "መቼም በቤትሽ ያለውን ችግር ስለማውቅ ተዉአት ልጇን ታሳድግበት ቢቸግራት ነው ስልልሽ የኖርኩት እኮ ስለምታሳዝኚኝ ነው። ከእንግዲህ ግን የለም።

"…አልማዝዬ ከእንግዲህ ጎንደርንም፣ ወሎንም፣ ሸዋንም አትሰድቢም። ክፍት አፍሽን በፋኖዎችም ላይ አትከፍቺም። የወየሳ ነው የመገርሳ ልጅ አንቺ የደጉ ዐማራ፣ የጨዋ የሞራል፣ የግብረገብ ከፍታ ላይ ያለው ዐማራ መለኪያ፣ መገለጫም አትሆኚም። ነገርኩሽ።

"…እኔኑ ስትሰድቢ ትከርሚያታለሽ። ቢያንስ ቲፎዞ ለመፈለግ ስትዪ ከዐማራ ላይ ዓይንሽን አንስተሽ እኔ ላይ ትከርሚያለሽ። ከነከስኩ ነከስኩ ነው ሳላደማሽ አልፋታሽም። ጠብቂኝ፣ እንደባተትሽ ጠብቂኝ። በሰቀቀን ነው የማኖርሽ። እንዲሁ አጨልሌሽ ጥግሽን አስይዝሻለሁ።

"…ከምር እውነትም እኔ የአስገዶም ልጅ አይደለኋትም።😂 ዮኒዬ ግን በደንብ አጽናናት። አንተን ቴዲ ሃዋሳ ቤት ስቀብርህ እሷ ስትስቅብህ ነበር። በሕይወት ቆይተህ ይኸው እጅህ ላይ ጣላት። አንተን ከዐማራ ቦለጢቃ ነቅዬ አውጥቼ የሴቶች አስታራቂ ኮሚሽነር አድርጌ ሰብሬ እንዳስቀረሁህም ንገራት።

• ዘመዴ ነኝ ወዲ አስገዶም። 😂

ዘመድኩን በቀለ

30 Dec, 04:45


"…ደኅና ዋሉልኝ አማሪካ እና ካናዳዎች።

"…እኔ ማለት እንዲህ ነኝ። በአንድ ድንጋይ ነፍ ወፍ እርግፍ። ከለከፍኩህ ለከፍኩህ ነው። በቁምህ ነው የምቀብርህ። የዐማራና የኢትዮጵያን፣ የተዋሕዶን ጠላቶች በምድር ፍርዳቸውን፣ ፍዳቸውንም የምሰጠው እኔ ዘመዴ አክሊለ ገብርኤል ነኝ። ስማ እንዳትነሣ አድርጌ ነው የምሰብርህ። አንድ ለእናቱ ሺ ለጠላቱ ሲባል አልሰማህም እንዴ?

• ተረሳሽ ወይ…? 😂😂

• ዘመዴ ነኝ ወዲ አስገዶም አስነቀልቲው።

ዘመድኩን በቀለ

29 Dec, 19:23


"…ጥያቄ ነው…?

• አልማዜ… እኔ ማንነኝ…? 😂

ዘመድኩን በቀለ

29 Dec, 16:40


ጀምረናል ገባ ገባ በሉማ…

"…አላችሁ አይደል…?

ዘመድኩን በቀለ

29 Dec, 16:40


"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ምሽት 1:15 ላይ ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• የዛሬውም መርሀ ግብራችን እንደወትሮው ሁሉ ልዩ ነው። ጎጃም ነኝ። ጎጃም ጉብኝት ላይ ነኝ። በዚህ መስተንግዶአቸው እስከ ጥምቀት ድረስ ሳልቆይ አልቀርም። ለማንኛውም ዛሬም እንደሁልጊዜው ነጭ ነጯን እውነት ስናጣጥም እናመሻለን። ተከታተሉን።

•ዩቲዩብ👉 https://youtu.be/CUiPLPxxsfc

• ሮኩ/ Roku: 👉 https://my.roku.com/account/add?channel=merejatv

•ትዊተር👉 https://twitter.com/MerejaTV

•Mereja TV: https://mereja.tv


"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ

29 Dec, 15:37


ሦስት አትሉልኝም…፫

"…ጠበቃ አዲሱ ጌታነህ የጠበቃ አስረስ፣ የካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ወዳጅ ነው። እኔ ዘመድኩን በቀለን እስከ ደም አጥንቱ ድረስ ነው የሚጠላኝ፣ የሚፀየፈኝ። ገና ወደ ጎጃም መምጣቴ ነው ስል ዛሩ ነው የተነሣበት። ይሄ የትግሬ ዲቃላ፣ ያረጀ አሮጌ የብአዴን ጅብ። አጓራ አልኳችሁ። ሳልነካው አጓራ።

"…ገና ለገና ከእስር አመለጠ ተብሎ ስለተሸጠው የትፍሬው ኮሎኔል ኪሮስ ያሬድ የሆነ ነገር ይናገራል ብሎ ነው የወበራብኝ። ኮሎኔሉን ያስመለጡ ተብለው የተጠረጠሩት በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ነበር በጎጃም ፋኖ። በሕግ ቁጥጥር ስር የነበሩትም ተታኩሰው ወኅኒ ሰብረው አመለጡ ተባለ። ካመለጡት መካከል የእስክንድር ነጋ የጎጃም ወኪል ነው የተባለ አንድ ሰው እና ሌሎች ናቸው አመለጡ የተባለው። ይሄ ባንዳ ቀድሞ ወጥቶ ኦሮሞዋን የጠንቋይ ልጅ ጋለሞታዋን አዝማሪት አልማዝ ዳኛቸውን በስድብ ታስቆመኝ ይመስል ውረጂበት ብሎ ፈትቶ ላከብኝ። እኔ ዘመዴ በስድብ ልደነግጥ…? ኧረኤዲያ…!

"…መዓዛ መሀመድን ደውዬ እጠይቃታለሁ። ጓደኛዋ ስለሆነ ምን ኡኖ ነው እላታለሁ ብዬ ሳስብ ገና አስቤም ሳልጨርስ "ቤተልሄም ዳኛቸው ዘውዴ ዘመዴን መርዙን አስተፍታዋለች…! ጎጃም በርህን ዝጋ ብሎ አልለጠፈም ይሄ እኚኚብላ የመሰለ ፊት ባለቤት።

"…አንድ የሕግ ባለሙያ ነኝ ባይ፣ የተማርኩ ነኝ ባይ፣ እንዴት እኔ ዘመዴ ማን እንደሆንኩ አያውቅም ግን? እኔ ዘመዴ በጋለሞታ፣ በሰው ባል ፀር መንደሬ፣ በጎጃም አሰዳቢ ስድብ የምቆም ይመስልሃል? ዥልጥ ነገር ነህ።

"…በርህን ዝጋ አላለም። ወዴት ነው የሚዘጋው? ገባሁ እኮ። ጎጃም ነኝ። ጥላሁን አበጀን ሳልገልጠው፣ የጎጃምን እሾህ ሳልነቅል፣ ዘመነ ካሤን አንቆ አላላውስ ያለውን ወጥመድ ሳልሰብር ከጎጃም መች እወጣና…?

• ዘመዴ እኮ ነኝ አስነቀልቲው…

ዘመድኩን በቀለ

24 Nov, 17:49


"…ደርጉ ክንፉ፣ ቅንጁቱ ክንፉ፣ ግንቦት 7ቱ ክንፉ፣ አርበኞች ግንቦት 7ቱ ክንፉ፣ ኢዜማው ክንፉ፣ ከኦሮሙማው በቀለ ገርባ ጋር ሲማግጥ የከረመው ክንፉ፣ በመጨረሻ የጎንደር ስኳድ የወሎ ተወካይ የእስክንድር ደቀ መዝሙር ነኝ ብሎ ፍጥጥ ብሎ መጣ። 😂😂

"…ዘመነ ካሤን፣ ምሬ ወዳጆን፣ ጋሽ አሰግድን፣ ባዬና ሳሚን፣ እነ አስረስ ማሬን ሲሞልጭ፣ ማይሙን መከታውን፣ ኮሎኔል ሙሃቤንና ሀብቴ ወልዴን ሲያወድስ ይውል ያድር ጀመረለኝ።

"…እሱ ደርግ ሆኖ አገዛዙ ያስረሸናቸውን ሰዎች ትናንት ስኳዶች ሲዘክሩ ሳይ ፈጣጣነታቸው ነው የገረመኝ። ክንፉ የሸዋ ሰዎችን ኪስ ለማጠብ፣ ሸዋን በእስክንድር በኩል እጅ እግሩን አስሮ ዳግም ሊገድላቸው በሸዋዎች ላይ ሲቆምር ዝም ብሎ ማየት ኃጢአትም፣ ወንጀልም ነው።

"…የዐማራ ፋኖ ትግል ኮተታም ሓሳቦችን እያራገፈ፣ ደርግና ፌክ ኢትዮጵያኒስቶችን፣ ግንቦቴዎችንም እየሞገተ ጥጋቸውን እያስያዘ ወደፊት መቀጠል አማራጭ የሌለው ምርጫው ነው።

• እስክንድር ከእነደነዚህ ዓይነቶቹ ጋር ለምን ተጣበቀ ብለን ስንጠይቅ መልሱን በቀላሉ ለማግኘት እንቸገራለን። እስክንድር ከአምሳሉ አስናቀ ውጪ ገንዘብ ያዥ የማይመድበው እንኳ እሺ ገቢው የቤተሰብ ስለሆነ ነው እንበል። እስክንድር ከደርጉ ክንፉ ጋር ምን አስቦ ነው አንሶላ የሚጋፈፈው?

• ተመልሼ እመጣለሁ።

ዘመድኩን በቀለ

24 Nov, 17:49


"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ምሽት 1:30 ላይ ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• የዛሬው ልዩ ነው።

• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/ek9N_moT0Tk
• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaTV
• Mereja TV: https://mereja.tv
• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ

24 Nov, 17:49


ወፍ የለም…😂

"…የጎንደሩ አባት አርበኛ ለጎንደር ዐማራም ሆነ ለመላው ዐማራ ፈውስ የሚሆን የምሥራች ብሥራት ያሰሙበት ታላቅ ዜና እስከአሁን ዐማራ ነኝ የሚል የዳያስጶራ ያልበሰለ ጥሬ ገተት የሚከተላቸው ግንቦቴዎቹ እነ መሳይ መኮንን እና የብራኑ ነጋ ሻንጣ ተሸካሚ ነው እያሉ እነ የዲሲ ግብረ ኃይሎች የሚነቁሩት ደሬ ሀብተ ወልድ የድሮዎቹ ግንቦቴዎች እስከ አሁን ትንፍሽ አላሉም።

"…ሁሉም ቦለጢቃ ነው የሚሠራው። ቦለጢቃውን የሚያበላሽበት ነገር ሲመጣ ወባ እንደያዘው ሰው ነው የሚያንዘፈዝፈው። ይደበቃል። ይሸሻጋል። እንደ ሀብትሽ አይነቱ እና እንደ አበበ በለው አይነቱ ደግሞ ይከሳል። በቁሙ ይሟሟል።

"…ኡጋንዳ ያሉት እነ በለጠ አልዘገቡትም። ውብአንተ ይሙት፣ ይደምሰስ ብለው ዜና ሠርተው የነበሩት ሁላ ደንግጠዋል። ሽንት በሽንት ነው የሆኑት። ዐማራ ላይ ተጣብቀው፣ ዐማራ መስለው ዐማራውን ይቀፍሉ የነበሩት ሁላ ቀዝቃዛ ውኃ እንደተደፋበት ሰው ከውኃ እንደወጣች አይጥ ነው መስለው የማያቸው።

"…ኢትዮ ፎረም ነሽ፣ ኢትዮ ኒውስ፣ ኢትዮ ፎከስ፣ ኢትዮ 251፣ ደሬ ኒውስ፣ ኢትዮ 360፣ እስክስ አበበ አዲስ ድምጽ፣ ወላ ሃንቲ ነገር የለም። ዝም ጭጭ ነው ያስባላቸው። ዐማራው እነዚህን ነው በሰብስክራይብ የሚደግፋቸው፣ በጎፈንድሚ የሚቀልባቸው። የዳያስጶራው ዐማራ እኮ ምስኪን ነው። አብዛኛው በጅሎች የሚነዳ ቀንድና ጭራ የሌለው ምስኪን ወደ አራጆቹ ቄራ ለመታረጃው የሚሆን ቢለዋ አዋጥቶ ገዝቶ የሚነዳ ከፍት ነው። ብልጦች፣ ንቁ፣ ገራሞች፣ ብልሆች፣ ጠቢቦች ጥቂቶች ናቸው።

"…አሁን ይሄ ጮማ ዜና ባላየ ባልሰማ የሚታለፍ ነው። ድርጅቱ በዚህ ገባ በዚህ ወጣ ሲል የከረመው መንጋ ዐማራን ቀፋይ የሚዲያ ጋለሞታ ሁላ ይሄን ጮማ ዜና እንዴት እየሄድክ እለፍ ብሎ ጮጋ አለው?

• አይገርምላችሁም ግን…?

ዘመድኩን በቀለ

24 Nov, 17:49


"…ዛሬማ ደስ ደስ እያለኝ እኔ ዘመዴ ገብቻለሁ… እናንተስ?

• ላልሰማ እያሰማችሁ ገባ ገባ በሉና ነጭ ነጯን እናውጋ እስኪ… ሃኣ…?😂

• ዘመዴ እንዴነህ 👏👏👏 አለው አለው እና… ዘመዴ ዘመዴ ዘመዴ😁😁

ዘመድኩን በቀለ

24 Nov, 17:49


መልካም…

"…ዛሬም የመረጃ ቴሌቭዥን ሳምንታዊው የነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር ሞቅና ደመቅ ካሉ መርሀ ግብሮቹ ጋር የሚጠብቃችሁ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ መሆኑን ለማሳሰብ እገደዳለሁ። በኋላ አላየንም፣ አልሰማንም እንዳትሉ…

"…ይልቅ ትናንት በተቀበል መርሀ ግብራችን ላይ የጀመርኩላችሁን የደርጉን አክሮባቲስት ቅንጅት፣ ከዚያ ግንቦቴ፣ ከዚያ ኢዜማ አሁን ምን እንደሆነ ሳልነግራችሁ ነበር ሰዓት የገደበን እና የጣና ቴቪ ዶፍቶሮችን የዙም ስብሰባ ለመስማት ስንል የተለያየነው። ስብሰባውም እንደጠበቅነው አልሆነም። ተበተኑ። እኔም ደክሞኝ ተኛሁ።

• አሁን ቶሎ ቶሎ መልሱልኝና የዚህን አክሮባቲስት ሶዬ መጨረሻ ብነግራችሁስ? ምን ይመስላችኋል? በነገራችን ላይ ሰውዬው ተጽዕና ፈጣሪ ሆኖ አይደለም። ተናግሮ ሚስቱን ማሳመን እንኳ የማይችል ምስኪን ነው። ነገር ግን የዐማራ ትግል እንዴት ባሉ ሰዎች ሊጠለፍ እንደነበር ለማሳየት ስለፈለግኩ ነው ይሄን ያመጣሁት። ሶዬው ደግሞ በዘመዴ ስሜ ተጠራ ብሎ የባሳ ተኮፍሶ እንዳይፈነዳ ሊመከርም ይገባዋል። ፎር ኤግዛምፕል እንዲል ሱሬ ለኤግዛምፕልነት እንዳመጣሁት ይታወቅ።

• ደርጉ ተገልብጦ ምን ቢሆን ጥሩ ነው? 😂

ዘመድኩን በቀለ

24 Nov, 17:49


"…የዐማራ ፋኖና የኦሮሞ ቄሮ ከወያኔ ጋር ተቧቅሶ ያመጣውን የተቀማ ለውጥ፣ የተለጠፈ ለውጥ ደርጉ ክንፉ ወዳጄ "እናመሰግናለን አርበኞች ግንቦት 7" በማለት ነው በኤርትራ በረሀ የሻአቢያን ፍየል ሲጠብቅ የነበረውን ግንቦቴ የሚያመሰግነው።

"…ዐማራ ሲታረድ እኔ ብቻዬን ኡኡ ብዬ ስጮህ ይሄ ደርግ ሰውዬ እኔን ዘረኛ ነው፣ ፀረ ሰላም ነው ሲለኝ የነበረ አብዮት ጠባቂ ፊት የመሰለ ሶዬ ነው።

"…የእሱ አለቃ ኢህአፓው ብራኑ ነጋ የአቢይ ገሌ ገረድ ሆኖ ሲገባ ክንፉ ሆዬ ተገለበጠላችኋ። መገልበጡ ባልከፋ ጩኸቴን ቀምቶ ከእሱም ብሶ ሊጋተተኝ ፈለገላችኋ። 😂😂

"…እኔ ዘመዴ እኮ እነ ክንፉ ወዳጄ በ2 ሜትር ከ20 አልጋ ላይ፣ በሜትር ከ70 ቁመታቸው ሜትር ከ10 ብርድ ልብስ እና አንሶላ ለብሰው ከብልጽግና ጋር ተጋድመው ሲገለሙቱ ኧረ ተዉ ተዉ ኃጢአት ነው ንስሀ ግቡ ስላቸው እንደ ዲጄ ቆጥረውኝ ወደ እግር ሲስቡት ከአንገት፣ ወደ አንገት ሲስቡት ከእግር እያጠረ ብርድ ከሚያስመታቸው አጭር ብርድልብስና አንሶላ ጋር እየታገሉ ሲድቡኝ የነበሩ ናቸው።

"…ይሄኔ አንተም ይሄን ጦማር የምታነብ ያኔ ከብልፅግና ጋር ያለአቻ ጋብቻ ፍቅር መስርተህ ስትርመጠመጥ የነበርክ ጉደኛ ትሆናለህ። ትሆኛለሽ። ሳትዋሹ ተናገሩ። ዛሬ ደርሰው የዐማራ ተቆርቋሪ ነኝ ሲሉ ወደ ላይ ወደ ታች ይታገለኛል። 😂። መቆርቆራቸው ባልከፋ የሚያስቀኝ እኔ የፋኖ ትግል መሥራቹን ዘመዴን መክሰሳቸው ነው የሚያስቀኝ።

"…ወደ ጉዳያችን እንመለስ… በመጨረሻም ደርጉ ግምቦቴው ክንፉ ማረፊያውን የት ቢያደርግ ጥሩ ነው?

• ጋሽ መሳፍንትን ብዬ እምላለሁ 😂 በ10 ደቂቃ ውስጥ ተመልሼ እነግራችኋለሁ።እመለሳለሁ።

ዘመድኩን በቀለ

24 Nov, 10:37


"…የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም። ሉቃ 8፥17

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

24 Nov, 06:45


ኧረ ዲያ አላለም…😂

ዘመድኩን በቀለ

24 Nov, 06:45


ልመክራቸው ነኝ…!

"…ሆስቱ ሳሚ ነው። ሳሙኤል አበበ። የልብስ አራዳ ነገር ነው። ሰው ፀጉርን አፈርዞ እንዴት እርጥብ መቶ ኪሎ ፋራ መስሎ ይገለጣል? በእውነት ነውር ነው።

"…ከምር የክፍለ ሀገር ልጅ መሆን አንዳንዴ መታደል ነው። የዋሕ ናቸው። ችግሩ እንደኔ ዓይነቱን ቅጠል እና ፍየል እየበላ ያደገ የሐረር ልጅ፣ በዚያ ላይ ከአዋሽ ማዶ ተወልዶ አዲስ አበባ ዳጃች ውቤ፣ ማርገጃ ያደገ ልጅ፣ ውኃ ጠብሶ እየበላ የኖረ ልጅ ፊት አራዳ አራዳ ልጫወት ሲሉ ብቻ ነው የሚበሰጨኝ።

"…ሳሚ የጋሻው መርሻ ፍሬንድ ነው። አየህ ስኳድ ገዢው ባርቲ ውስጥ አገኘሁ ተሻገርና መላኩ አለበል ሆኖ ቦታ ይዟል። በዐማራ ድርጅት በአብን ውስጥ ጋሻው መርሻ፣ መልካሙ ሹምዬና፣ ጣሂር አሕመድ ሆኖ ቦታ ይዟል። አሁን ደግሞ ፋኖ ካሸነፈ ብሎ ፋፍዴንን ጎንደር፣ ሸዋን በእስክንድር አንቆ ይዞ ነበር። አይ እስኳድ። አበበ በለው፣ የዐማራ ማኅበራት አብዛኛዎቹ የስኳድ ተዘዋሪ ናቸው። በዝርዝር እመጣበታለሁ።

"…ለማንኛውም ሸዋ ነው ገንዘብ ያለው ብላችሁ ሸዋ ላይ ያፈሰሳችሁት ጊዜም ቀለጠባችሁ። ስብሰባ እንዲህ አይመራም። ታጋሽ መሆን ነው ያለባችሁ። ሁሉን ሰው አባራችሁ ብቻችሁን ብታለቅሱ ምን ትጠቀማላችሁ? አበበ በለው ማስታወቂያችንን ነገረ ብለህ ትፈነድቅ ሳሚዬ? 😂😂 አቤ ዋናው ስኳድ አይደል እንዴ? ባያስተላልፍላችሁ ነበር የሚገርመኝ።

"…ደግነቱ እኔ ከአመራራቹ መካከል አንዱ ስለሆንኩ ልታስወጡኝ አትችሉም። ቀሽሞች ናችሁ። ሰልጠን በሉ። የመረጃ ብክነት አትፍጠሩ። እኔ እንድበጠብጣችሁ ተመቻችታችሁ አትገኙ። እየመከርኳችሁ ነው። አሁን ያ ልጅ ምስጋናው ጴንጤ ስለሆነ ለምንድነው ፋኖዎችን መስቀል አታድርጉ የሚለው ብሎ ስለጠየቀ ምጣት ነበረበት?

• በል የአውሮጳው ወዳጄ መቅዳትህን ቀጥል። እኔ ደከመኝ ልተኛ ነው። ደኅና እደሩልኝ።

ዘመድኩን በቀለ

20 Nov, 04:16


እውነቱን ተጋፈጡት…

"…ብዙ ሰዎች ይሄን የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ቃለ መጠይቅ ሊንክ እየላኩ ዘመዴ እስኪ አዳምጠው ይሉኛል። ዓይቼው ምላሽ ሳልሰጥ ዝም እላለሁ። ተደጋገመ፣ አሁንም ዝም። አሜሪካ የሚገኝ አንድ አብሮአደጌ እና በዚህ በጀርመን የሚኖሩ አንድ ወዳጄም ይሄንኑ ሊንክ ላኩልኝ። ለእነርሱ ግን መለስኩላቸው። ከዚያ በችርቻሮ ከምመልስ ለምን በጅምላ አልመልስም ብዬ መጣሁ።

"…ለማንኛውም ይሄ የኮሎኔሉና የጋዜጠኛ በለጠ ካሣ ቃለመጠይቅ የቆየ ነው። አሁን እኮ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ናዝሬት አዳማ ደርሶ ከመጣ በኋላ ሰውነቱ ውልቅ ብሎ ከስቷል። ጋዜጠኛ በለጠ ካሣም ከኢትዮጵያ ተሰድዶ ኡጋንዳ ከገባ ዓመት አለፈው። እናም የቆየ ቃለመጠይቅ እያመጡ ይሄ ሕዝብ አንድ ጊዜ ሾርት ሚሞሪያም ተብሏል ተብሎ በሕዝብ የማወቅ መብት ላይ መቀለድ፣ ማላገጥ፣ ማሾፍ ትክክል አይደለም። ነውር ነው።

"…በወልቃይት ጉዳይ እኮ ምን እንደሰሙ ባላውቅም እነ አያሌው መንበር፣ ፓስተር ምስጋናው አንዱዓለም፣ ሙሉዓለም፣ ሙላት አድኖ፣ ጋሻው መርሻ፣ ሲሳይ ሙሉ፣ እነ ጥላሁን ጽጌ ወዘተ፣ ሁሉም ዝም ጭጭ ብለዋል። 😂 ትዊተር ስፔስ ላይ ይንጫጩ የነበሩት ጫጫቴያሞች ሁሉም ኩምሽሽ ካሉ ቆዩ። ስለወያኔ ኃጢአት እንኳ መጻፍ ያቆሙ ሞልተዋል። ስለወልቃይት ጉዳይ የአሸቦ ዕቃው ሲሳይ አልታሰብም እንኳ ጮጋ ብሏል።

"…ይልቅ ጎንደሬ ነኝ፣ የጎንደር ዐማራ ነኝ ሲል የከረመው ግሪሳ በሙሉ ሰሞኑን ወልቃይት ነህ ዐማራ? ወልቃይቴ ነህ ትግሬ? ተብሎ ሳይጠየቅ እኔ ወልቃይቴ ነኝ የሚሉ በዝተዋል? ምን ቢሰሙ ነው በአንድ ጊዜ ከዐማራነት፣ ከጎንደሬነትም ዘጭ ብለው "ወልቃይቴ" ነኝ ማለት የጀመሩት ብሎ መጠየቅ ይበጃል። በወልቃይት መከላከያና የደመቀ የተከዜ ዘብ ጦር እንጂ ፋኖ እንኳ የለም።

• ምን ለማለት ፈልጌ ነው? ቃለመጠይቁ የቆየ ነው። አከተመ።

ዘመድኩን በቀለ

20 Nov, 04:16


ቀን 10/3/2017 ዓ.ም

"…ከዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከመሀመድ ቢሆነኝ ክፍለ ጦር በ7ለ70 ብርጌድ የተሰጠ የአቋም መግለጫ…

"…የነገ ጠዋት ርእሰ አንቀጻችን ነው። ሙሉውን ጠዋት ይጠብቁ። ነገ ጠዋት ከእግዚአብሔር ሰላምታ 1ሺ ሰው ከመሰገነ በኋላ በዚሁ በቴሌግራም ገጼ ይቀርብላችኋል።
 

ዘመድኩን በቀለ

19 Nov, 17:14


"…ቁምነገር ጠይቄ በቁምነገር ምላሽ የሰጡኝ እጅግ በጣም ጥቂቶች ናቸው። ሊመሰገኑም ይገባል። አንዳንዶቻችሁ ደግሞ በኢንቦክስ በውስጥ መስመር ማውራት የምትችሉትን ነገር በአደባባይ፣ ስንት ቁምነገር በሚወራበት ፔጅ ላይ ከርእሱ ጋር የማይገናኝ ሓሳብ አንሥታችሁ ስትጨቃጨቁ ሁላ አያለሁ። ይሄ ቢስተካከል ጥሩ ነው። ፔጁ የቀልድ፣ የነቆራም ቀን አለው አይደል? የግል ጉዳያችሁን በውስጥ መስመር አውሩ።

"…ስለመርካቶ እያወራን ነው። አትቀልዱ። የተደገሰው ድግስ ቀላል አይደለም። በቀልድ፣ በዋዛ፣ ፈዛዛም፣ በቧልትም አትለፉት። ፔጁን ለሚያነቡ ሰዎች ግሩም ሓሳብ ለማዋጣት አቅምና ጊዜ ያጠራችሁ ሰዎች ቢቻል ዝም ብትሉ መልካም ነው።

"…እውነት ነው መርካቶ ሃይማኖት ታይቶ፣ አንገትህ ላይ መስቀልና ክር ካለ የ100 ብሩን ዕቃ 500 ብር እንደሚያስገዙ ከተነገረ ቆየ። "ለሁሉ ሽጥ፣ ከራስህ ወገን ግዛ" ብለው በተለይ እስላሞቹ፣ አሁን ደግሞ ፕሮዎቹ ኢኮኖሚውንም፣ አስመጪና ላኪነቱንም ጭምር በመቆጣጠር በተለይ ኦርቶዶክሱን ክፍል ሸማች ብቻ አድርገው እንደቆረቆዙት ይነገራል። እሱ እንዳለ ሆኖ ግን መርካቶ ኦሮሞ የለም ብሎ ነገሩን በሚዲያ ማጮህ ቀጥሎ ምንድን ቢያስቡ፣ ወይም ቢያቅዱ ነው።

"…ንግድ ክህሎት እና የፀጋ ስጦታ እንጂ የሚያስፈልገው ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ጉራጌና ዐማራ መሆን በራሱ ምን ይፈይድልሃል? በዘመነ ወያኔ ከግብር ነፃ የተደረጉ በዘራቸው ትግሬ የነበሩ ነጋዴዎች እርግጥ ነው ተጠቃሚ ነበሩ። ሥርዓቱ ሲወድቅ ግን አብረው ነው የወደቁት። ኦሮሞም ለወያኔ የተደረገው ይደረግልኝ እያለ ነው። የእኔ ምክር ሥርዓቱ ሲወድቅ ትወድቃለህና ይልቅ በፀጋህ ጠንክረህ ሥራ።

• ዛፍ ቆራጭ
• ጣሪያ ቀዳጅ
• አራሽ
• ቀዳሽ
• ተኳሽ
• ደጓሽ ወዘተ ሁሉም በፀጋው ቢኖር እላለሁ። ድግሱ ግን ሌላ ይመስላል።

• ከሳትኩ ልታረም…

ዘመድኩን በቀለ

19 Nov, 14:50


ሦስት ነገር…

፩፦ አገዛዙ የሚለው ነጋዴው ሱቁን የዘጋው በደረሰኝ ሽጥ ስንለው በደረሰኝ አልሸጥም ብሏል። ስለዚህ በግድ በኃይልም ቢሆን በደረሰኝ እንዲሸጥ ይደረጋል ነው የሚለው የሚሉ አሉ።

፪ኛ፦ ነጋዴው ሱቄን የዘጋሁት ከየት እንደመጡ የማይታወቁ ኃይሎች በየጊዜው እየመጡ ንብረታችንን ጭነው ያለከልካይ ስለሚወስዱብን፣ በየቀኑ መዋጮ እያሉ ስላሰለቹን፣ ስላዛጉን ነው የዘጋነው ነው የሚሉት የሚሉም አሉ?

፫ኛ፦ ሌሎች ሦስተኛ ሓሳብ የሚሰጡት ደግሞ "ወያኔ ኦሮሞን ከመርካቶ ነቅላ አባርራለች፣ በመርካቶ የኦሮሞ ነጋዴ የለም። በመርካቶ ጉራጌ፣ ትግሬና ዐማሮች ናቸው የሚነግዱት። እናም ይሄን ለማመጣጠን ትግሬዎቹ ጉራጌንና ኦሮሞን አፈናቅለው ንግዱን እንደተቆጣጠሩት አሁንም በዘመነ ኦሮሞ መርካቶን ከጉራጌ፣ ከትግሬና ከዐማራ አጽድተን፣ ወይም አመጣጥነን ኦሮሞን በመጨመር መርካቶን የሁላችንም እንድትሆን እናደርጋታለን ነው የሚሉት የሚሉም አሉ። ስለዚህ የትኛው ነው ትክክል?

"…የእኔ ሓሳብ አቢይ አሕመድ በሦስተኛው የኮሪደር ልማት ልክ ከዚህ በፊት ፒያሳንና ካዛንቺስን እንዳጸዳው አሁንም በእሳትም፣ በግርግርም ይሞክረውና፣ የነጋዴውን ኅብረት፣ አንድነት፣ ሙቀት ከለካ በኋላ በግሬደር ያርሰዋል። የሰው ወኔ እንደተሰለበ ስላወቀ፣ በሁለት ሳምንት ውስጥ መርካቶን ለቅቀህ ውጣ ይለዋል። ከዚህ በፊት አትክልት ተራን እንዳደረገው ማለት ነው። እንደዚያ የሚያደርግ ይመስለኛል።

• የዚህ ነገር መጨረሻው ምን ይሆን…?

ዘመድኩን በቀለ

19 Nov, 14:50


ስለ መርካቶ እናውራ አስቲ…

"…ትናንት በአዲስ አበባ መርካቶ የመርካቶ ነጋዴዎች ሱቃቸውን ዘግተው ነበር ሲባል ሰምቼ ነበር። ግርግርም ሁላ ተፈጥሮ ነበር ነው የተባለው። ነጋዴዎቹ ሱቃቸውን ለምንድነው የዘጉት…? ምንሆነው ነው? ምን በደል ተፈጽሞባቸው ነው? ትናንት ሱቅ የዘጉት ዛሬስ ከፍተዋል ወይስ ዛሬም ሱቃቸውን እንደዘጉ ነው?

"…እስቲ ስለ መርካቶ የምታውቁትን ሁሉ ስጋታችሁን ጭምር አስረዱን። ጥፋቱ የማንነው? የአገዛዙ ወይስ የነጋዴው? ጎበዝ ለመርካቶ ምን ታቅዶላት ይሆን…? …ከቦታው፣ ከሁኔታው ለራቅን ለእንደ እኔ ዓይነቱ እስቲ ገለጻ ስጡን።

• አመሰግናለሁ።

ዘመድኩን በቀለ

19 Nov, 14:50


የአወሮጳው ምች…

"…በኢትዮጵያ ተልባ፣ ቅባት ያለበት ምግብ በልተህ፣ አፍህን ሳትታጠብ ወጥተህ ፀሐይ ቢያገኝህ ምች ድብን አድርጎ ይመታሃል። ከዚያ ነው ዳማከሴ እና ፌጦ ጤና አዳምም ወደመተሻሸት፣ ጨምቀህ ወደመቀባባት የምትሄደው። የአውሮጳው ምች ግን ይለያል። ብርድ፣ ቅዝቃዜ ምች ሆኖ ሲያጠናግር ያየሁት እዚህ ነው። ትናንት ረፋድ ላይ በሳሎን ቤቴ ሶፋ ላይ ጋደም ብዬ ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከ7 ለ70 ብርጌድ የተላከልኝን ከእዙ የመለየት መግለጫ አነብባለሁ። ከወትሮው የተለየ የሚቆረጣጥም ብርድ ተሰማኝ፣ ልብስ ደራረብኩ፣ ለቤቱ ሙቀት የሚሰጠውን ሃይሱንግ ይሉታል ከፈትኩ፣ ወባ እንደያዘው ሰው ያንዘፈዝፈኝ፣ ይቆረጣጥመኝ ጀመር። ላብ በላብ። ኤሌክትሪክ እንደያዘው ሰው ነው የሚያንዘረዝረኝ። ቆይቼ ነው በመጋረጃ የተሸፈነውን የተከፈተ መስኮት ዓይቼ የምቹን ምንጭ ያወቅኩት። ጭራሽ ወደ ጉንፋንነት ሁላ ሊቀየር? ጉድ እኮ ነው።

"…የትም ሳልወጣ፣ ቤቴ ተቀምጬ ጉሮሮዬን ከረከረኝ፣ ምኔ ሞኝ ነው ዳይ ወደ ፍልሚያው። እነ ነጭ ሽንኩርት፣ እነ ዝንጅብል፣ እነ ማር ከያሉበት ተጠርተው እንዲመጡ አደረግሁ። አፍልቼ በላይ በላዩ ለቀቅኩበት፣ ዘመዴ ዳይ ተሸፋፍነህ ተኛ ብዬ መክሬው ተሸፋፍኜ ለጥ። ላቡ እንደ ስቲም ባዝ አጥለቀለቀኝ፣ ሳሉም በፈላው የዝንጅብልና የነጭ ሽንኩርት ሠራዊት ተመከተ። እንደ ጎጃም እስክስታ ከእግር ጥፍሬ እስከ ራስ ፀጉሬ ድረስ እንደ ጎንደሬዋ እንዬ እንቅጥቅጥ ያደርገኝ፣ እንደ ባለ ዛር ይወዘውዘኝ የነበረውም ቆመ። ቀጥ ነው ያለው። በዚህ ላይ ዕለተ ሰኞ የእረፍት ቀኔ መሆኑም በጀኝ እርፍ ብዬ ዋልኩ። አደርኩም። ዛሬ እንደተደበደበ ሰው ሰውነቴ ከመጓጎሉ፣ ድምጼ ጎረምሳ እንደዋጠ ሰው ከመጎርነኑ በቀር ሰላሜን አገኝቻለሁ። የአውሮጳ ምች አደገኛ ነው። እኔ በዚህ ዕድሜዬም መድኃኒት አልጠቀምም። እነ ነጭ ሽንኩርት፣ እነ ዝንጅብል፣ እነ ፌጦ፣ እነ ማር፣ ጤናአዳምና ዳማከሴን ያቆይልኝ። ውኃ አፍልቼ ትንሽ ጨው ጠብ አድርጌበት ታጥኜው ተሸፋፍኜ እተኛለሁ። ሲነጋ ዳይ ጤና ይስጥልኝ ነው።

"…ከዚህ የተነሣ ዓይኔ እንባ እያቀረረ ርእሰ አንቀጻችንን አሳምሬ፣ አሰካክቼ መጻፍ አልሆንልህ አለኝ። ቢሆንም ግን ቤታችን ጭር ብሎ እንዳይውል አንዳንድ ነገሮችን በማንሣት አጫጭር መረጃዎችንም ወደ እናንተ በማድረስ በመረጃዎቹም ላይ እየተወያየን ለማምሸት እንሞክራለን።

• የዛሬው ቲክቶክም ይለፈኝ። ግን እንወያያለን። ከ20 ደቂቃ በኋላ በጥያቄ እመለሳለሁ።

ዘመድኩን በቀለ

19 Nov, 10:29


“…ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር፤” ምሳ 23፥17

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

18 Nov, 19:42


"…አመሰግናለሁ ምስጌ…🙏🙏🙏

"…በትናንትናው ምሽት የመረጃ ቴቪ ሳምንታዊው የነጭ ነጯን ከዘመዴ መርሀ ግብር ላይ… በትግል ሜዳ ያላችሁ ታጋዮች ዘመኑ አደገኛ ነውና በቲክቶክ ላይ አትግቡ፣ ለእናንተም ለታጋይ ጓደኞቻችሁም ጦስ ትሆናላችሁ፣ በራስ ስህተት ለምን በአጭር ትቀጫላችሁ ብዬ ምስጌንና ሌላ አንድ አርቲስት ወንድሙንም ምክር ለግሼ ነበር። እናም ሁለቱም ወንድሞች ከጎጃም ምድር ሆነው ምክሬን ተቀብለው ሁለተኛ ላይቭ አንገባም ብለውኛል።

• ምክሬን ስለሰማችሁ አመሰግናችኋለሁ። 🙏🙏🙏

• ድል ለእናንተ…!
• የሞትን ባሕር ያሻግራችሁ…!

"…በመጨረሻም መርካቶ ጓ ብሏል አሉ። ሲደግመው ነገም ከደገመው ነው መጻፍ። ከሸዋ አንድ ብርጌድ ተገንጥሎ ወጥቷል። መግለጫውንም ልከውልኛል። በስልክም ደውለው አውርተውኛል። በነገው መደበኛ የቴሌግራም እና የቲክቶክ መርሀ ግብራችን ላይ እየተወያየንበት ውለን እናመሻለን።

"…የካዛንቺስ፣ የአራት ኪሎ ልጅ ተነሥ፣ ጥፋ ሲባል ብድግ ያለው እልም ብሎም የጠፋው ደንታ ስለሌለው ነው። የመርካቶን ልጅ መነካካት እንደ ካሳንችስ ልጆች ቀላል አይደለም። የሕይወትን ትርጉም፣ የቤተሰብ ሓላፊነትን፣ በላቡ፣ በወዙ፣ እንቅልፉን አጥቶ ሠርቶ የሚበላን መርኬ መነካካት ምላሹ ከባድ ነው። ለማንኛውም በመርካቶ ደም መፍሰስ ከጀመረ የነገሩ ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል። ግን ደግሞ ነገም ይደግሙታል ወይ ነው ጥያቄው?

• ምስጌ ግን በድጋሚ አመሰግናለሁ።

ዘመድኩን በቀለ

18 Nov, 19:42


“…እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ።” መዝ 3፥5

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

18 Nov, 07:46


የመርሀ ግብር ሰዓት ለውጥ…

"…በእኔ በዘመዳችሁ በኩል ተዘጋጅቶ በመረጃ የሳታላይት ተለቭዥን የቀጥታ ስርጭት ሚቀርብላችሁ ተናፋቂውና ተጠባቂው " ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" የተሰኘው ሳምንታዊው የዕለተ እሑድ መርሀ ግብራችን ከዛሬ ህዳር 8/2017 ዓም ጀምሮ የሰዓት ለውጥ በማድረግ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ የሚቀርብ ይሆናል።

"…በነገራችን ላይ ዛሬ ወልቃይት ነበር ያረፈድኩት። በወልቃይት ባለ አምባሻውም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዳይሰቀል የተከለከለው ለምንድነው? የጎንደር ጃኖ በመልበስ ጎንደሬ መሆን ይቻላል እንዴ? እነ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በስተመጨረሻ ሰንደቋን መንው ደበቋት፣ ሸሿት፣ ከስብሰባ ማዕከላትና ከአደባባዮች ላይ ምነው አራቋት?

• ለማንኛውም የሰዓት ለውጡን እንዳትረሱት። ምሽት 1:00 ሰዓት ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር ይጀምራል።

ዘመድኩን በቀለ

18 Nov, 07:46


"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ምሽት 1:15 ላይ ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• የዛሬው ዝግጅታችን ደግሞ እጅግ ሞቅ ደመቅ ያለ ነው። ተሰብስባችሁ ጠብቁኝ። ከበድ፣ ከበድ ያሉ መረጃዎችም የሚለቀቁበት ዕለት ነው ዛሬ።

• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/tOwBnDIMQgA
• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaTV
• Mereja TV: https://mereja.tv
• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ

18 Nov, 07:46


አላችሁ አይደል…?

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

• ጀምረናል ገባ ገባ በሉማ

"…ሻሎም !  ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ

17 Nov, 12:31


"… ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው።ሰቆ ኤር 3፥ 22-23።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችጀሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

17 Nov, 03:30


ተቀበል…8

"…ዛሬ ባሕርዳር ውስጥ በተከሰከሰችው ሂሊኮፕተር ውስጥ የነበሩት እነማን ይሆኑ? ጠይቅልን ተብዬ ነው።

• እየኮመታችሁ…!

ዘመድኩን በቀለ

17 Nov, 03:30


ተቀበል…9

"…የሁለት ቀን እንቅልፍ አለብኝ። ነገ ምሽት ደግሞ የመረጃ ቴሌቭዥን የነጭ ነጯን የቴሌቭዥን መርሀ ግብር አለብኝ። እናም በጊዜ ልተኛ።

• ደኅና እደሩልኝ።

ዘመድኩን በቀለ

16 Nov, 18:03


ተቀበል…6

ሀብታሙ አፍራሳ አንሥቶታል…

"…አዝማሪ አበበ በለው ጎንደሬ ስለሆነ የዐማራን ትግል የሚከፋፍሉትን፣ ጎጃምን በዘመነ ካሤ ምክንያት እንደ ሕዝብ የሚጠሉትን፣ ፋኖ ዳዊት ደግሞ፣ መስቀል አንጠልጥሎ ለምን ይዋጋል ብሎ በግልጽ ፀረ ኦርቶዶክስነቱን ላስመሰከረው ለፓስተር ምስጋናው ጣና ቴቪ በግልጽ ማስታወቂያ ሠርቷል።

"…የአበበ በለውን ማስታወቂያ መሥራት ተከትሎ አበበ በለውን ጆሮውን ጠምዝዞ ቁጭ ብድግ አድርጎ የሚያሽቆጠቁጠው ሀብታሙ አያሌውም ማስታወቂያውን ሠርቶት ነበር። ስኳድና ሀብታሙ አይንእና ናጫ ቢሆኑም አሁን ግን አለቃቸው ዶር አምሳሉ አስናቀ የባልደራስም፣ የግምባሩም ገንዘብ እያለቀ ስለሆነ ሰብሰብ ብላችሁ ወደ አንድ ምጡ ብሎ የበረሀው መሪያቸው እስክንድር ነጋም በማዘዙ ምክንያት ነው የግድ ወደ አንድ ለመምጣት የሚታትሩት።

"…ሀብትሽ የዓየሩን ፀባይ ካየ በኋላ ግን የአራዳ ልጅ ስለሆነ የእነ ምስጋናውን ማስታወቂያ ከፔጁ ላይ አንሥቶታል። አሁን ከእኔ ልጥፍ በኋላ ዶር አምሳሉ ተቆጥቶት መልሶ ካልለጠፈው በቀር ለጊዜው አንሥቶታል።

• እየነቆራችሁ…

ዘመድኩን በቀለ

16 Nov, 18:03


ተቀበል…5

"…በመጨረሻም እስከዛሬ ድረስ በጭልጋ ወረዳ የገጠር ቀበሌው የደንቢያ የጎንደር ዐማራ ነኝ ሲል የከረመውና የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው አዝማሪ ደፋሩ ፀረ ዐማራ አበበ በለው ጭንብሉ ተገለጠ።

"…አሁን አቤ በግልጽ እስኳድ እንደሆነ እና የፖለቲካው ቅማንት የፀረ ዐማራው የፓስተር ምስጋናው አንዷለም የጣና ቴቪ ሼር እንዳለው በግልፅ እየገለጸ ነው። ጣና ቴቪ በተለይም በጎጃም እና በወሎ ፋኖ ላይ ለሚሠራው የመከፋፈል ሴራ አዝማሪ አበበ በለው ሓላፊነቱን ይወስዳል። ጣና ቲቪ የጎጃም ፋኖን ለመከፋፈል የሕዝባዊ ድርጅቱ ጎጃም ዕዝ እያለ ለሚሠራው ዘገባም አዝማሪ አበበ በለው ሓላፊነት ይወስዳል።

"…እኔ የነከስኩት ሰው መጨረሻው አያምርም። መጀመሪያ ላይ ሄጵ የሚልብኝ ቢበዛም መጨረሻ ላይ ማሸነፌ አይቀርም።

• ነቆራ እየነቆራችሁ…😂

ዘመድኩን በቀለ

16 Nov, 18:03


ተቀበል…4

"…አንባቢ ተመልካች አድማጮቻችን በቀድሚያ ይሄን አጅግ አስተማሪ የሆነ ቪድዮ ደጋግማችሁ ተመልከቱት። ከዚያ ቪድዮውን ዓይታችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ ከቪድዮው ያገኛችሁትን ቁምነገር በገባችሁ መጠን ግጥም ግጠሙበት። 😂

• ከቪድዮው ምን ተማራችሁ? አትፍሩ በግጥም ግለጹት። ቤት ይምታ እንጂ ሽግር የለውም። ግጥምን ማንም ከእናቱ ሆድ ተምሮ አልወጣም። ሞክሩት። ኤት አባቱንስና።

• ተቀበል…

ዘመድኩን በቀለ

16 Nov, 17:23


ተቀበል…3

"…የተቀበል ኤዲቶሪያል ቦርድ ይሄ የዮኒልታዛር 500 የፔንስዮን የፈውስ አገልግሎት በተቀበል ገጣምያን ለአዝማሪው ግጥም ተሰጥቶት ይገጠምበት ዘንድ ወደ እናንተ ተላልፏል።

• ግጠሙበት፣ ግጠሙለት…

• ከ100 ኮመንት በኋላ በአዲስ ተቀበል እከሰታለሁ። እየገጠማችሁ።

"…ግጥም መግጠም ካልቻላችሁ በጨዋ ደንብ ነቆራም፣ ትችትም፣ ምክርም ይቻላል።

ዘመድኩን በቀለ

16 Nov, 14:02


ተቀበል… 2

"…ባሕርዳር ላይ ሂሊፕተሯ ነዳጅ ጨርሳ ወደቀች…😂

ዘመድኩን በቀለ

16 Nov, 13:29


ተቀበል… 1

ካባ ለበሰ አሉ ብርሃኑ ጁላ
ዲሽቃ ታጥቆ ገብቶ ተማርኮ በዱላ

"…ተቀበል… አንተው…

እየገጠማችሁ…

ዘመድኩን በቀለ

16 Nov, 13:06


መልካም…

"…የቅዳሜ ከሰዓት "የተቀበል" መርሀ ግብራችን አሁን በይፋ ተጀምሯል። ትናንት እና ከትናንት ወዲያ ሌሊት እስከንጋት ድረስ በትዊተር ስፔስ ስሜ ተደጋግሞ ስለተጠራ የተጠራሁበት ቤት በአካል ገብቼ የፌክ ኢትዮጵያኒስቱን ግሪሳ፣ የጎንደር ዐማራ ካንሰር የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላውን የስኳድ መንጋ፣ ፀረ ዐማራ እና በኮሎኔል ርስተይ ተስፋይ እህት በወሮ የሺ የሚመራውን የዋን ዐማራ ገዳይ ቡድን፣ እነደእነ አቶ ወዳጄ የመሳሰሉትን ጥርብ ፍልጥ የደርግ ጨፍጫፊ ወታደር፣ የግንቦት 7፣ ኋላ ኢዜማ፣ አሁን ደግሞ የእስክንድር ደጋፊ የሆነ ሰካራም የኒውዮር ገልቱ የሆነ የራሱን ትውልድ ቀርጥፎ በልቶ የአሁኑን ትውልድ ሊበላ ያሰፈሰፈ፣ የመጪው ትውልድ የዕድሉ ደንቃራ የሆነ ፀረ ዐማራ እከክ ልክ ሳስገባ፣ ሥርዓት ሳስይዝ አምሽቼ ሊነጋ ሲል ተኝቼ አርፍጄ ነው የተነሣሁት።

"… የስፔሱን ባለቤት በብዕር ስሟ ዳማከሴን እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ። አምርራ ትጠላኝ የነበረች እህት ብትሆንም የቤቷ አለቃ ሁላ አድርጋ ሥልጣን እስከመስጠት ስለደረሰች ዝቅ ብዬ እጅ ነሥቼ አመሰግናታለሁ። ከሀብታሙ በቀለ፣ ከአዲስ አበባ፣ ከጄ ብሩ፣ እና ከሌሎች ጋር አብሮ ለመሥራት የሚከብዱ ስላልሆነም አመሰግናለሁ። እስክንድር ስር የተኮለኮለውን የስኳድ እና የግንቦቴ መንጋ ግን አልፋታቸውም። ለጌዜው የእነዚህ ገተቶች አለቃና መድኃኒታቸው ነኝ። አለቀ። ምንም አባህ አታመጣም።

"…ወደዛሬው መርሀ ግብራችን ስንመለስ…

• ግጥም
• ነቆራ
• መረጃ
• ጥቆማ
• ጥያቄና መልስ ያላቸው ውይይቶች ይኖሩናል። የሚያስቁ፣ ፈገግ የሚያሰኙ አጫጭር ቪድዮዎችን፣ ጥቅሶችን፣ ሥዕሎችንም በውስጥ መስመር ላኩ። እኔ ለመቶ ሺ አድማጭ ተመልካቾቼ በመለጠፍ ዘና ፈታ ስንል እናመሻለን።

• አሁን ለአዝማሪው የመነሻ ግጥም ስጡት።

• 1…2…3 ጀምሩ

ዘመድኩን በቀለ

16 Nov, 10:57


"…መለኮት ግን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም ነው። አንድ አምላክ አንዲት መንግሥት አንዲት ሥልጣን አንዲት አገዛዝ ነው። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስባሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይናገራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይወዳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመክራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይናገራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይፈጽማሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይሠራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስማማሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያከናውናሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይልካሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያሠለጥናሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ምስክር ይሆናሉ።

"…አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሰውን ያስባሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያለምዳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመክራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያነጻሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያከብራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸናሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስጨንቃሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስተምራሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይጋርዳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያለብሳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ባለሟል ያደርጋሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይቀመጣሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይፈርዳሉ። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይመረምራሉ።

"…እንዲህ እናምናለን እንዲህም እንታመናለን፤ አንድነትን ሳንለይ የተለየ እንዳይሆን። የተቀላቀለ እንዳይሆን እንለይ። ቅዳሴ ማርያም

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

16 Nov, 05:38


መልካም…

"…ውይይቱ ይቀጥላል። በወልቃይት ጉዳይም አሁን አሁን ማንንም ሳትፈሩና ማንንም ሳታፍሩ ደፈር ብላችሁ መነጋገር መጀመራችሁም ያስመሰግናችኋል።

"…ነገ የተቀበል መርሀ ግብራችን የሚቀርብብት ዕለት ነው። ቅዳሜ ከሰዓት የተቀበል መርሀ ግብር የሚሆኖ ግጥም፣ ቅኔ፣ አጫጭር አስቂኝ ቪድዮዎችን አዘጋጅታችሁ ጠብቁን።

• ማሳሰቢያ፦

"…ፎቶው ባልተዛር ጋር ከሚባለው ሶዬ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። ደግሞ ክፉ ነገር እያሰባችሁ እንዳታስቀስፉኝ።

• እየጸለያችሁ…🙏🙏🙏

ዘመድኩን በቀለ

15 Nov, 19:21


"…መልካም…

"…13 ሺ ሰው አንብቦት… 13 ፍሬ ሰዎች ደግሞ ብው 😡 ብሎ የተናደደበት የዛሬው የሳምንቱ መጨረሻ የዕለተ አርብ ርእሰ አንቀጻችን አሁን ደግሞ በእናንተ በመንደሬ ነዋሪዎች ብዕር ይተች፣ ይበረበር፣ ይብጠረጠር ዘንድ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን ወደ መክፈት አመራለሁ። በጨዋ ደንብ አስተያየት ለመስጠት ከወዲሁ ተዘጋጁ።

"…ርእሰ አንቀጹ ከተጻፈ በኋላ ወደ አንድነት ለመምጣት ወደ መጨረሻው ምዕራፍ በደረሱት አራቱ የዐማራ ግዛት ፋኖዎች መካከል የጎንደሩ በባዬ ቀናው የሚመራው የዐማራ ፋኖ በእነ ሀብቴ ወልዴ አማካኝነት የሚመራው የዐማራ ፋኖ ከእስክንድር ነጋ አዲሱ ድርጅት እለያለሁ በማለት እነ ባዬን እያዘገያቸው ነው ብዬ ያጋራሁት መረጃ "ዘመዴ ትንሽ ይሰተካከል" በማለት መሬት ላይ ካሉት የጎጃም ፋኖ አመራሮች በኩል መረጃው ደርሶኛል።

"…አመራሩ በነገረኝ መሠረት እስከ መስከረም ድረስ በነበረው ሁናቴ እውነት ነው መዘግየቱ የመጣው በጎንደር ፋኖ በእነ ባዬ በኩል ነው። የአሁኑ መዘግየት ግን የመጣው በእኛው በጎጃም የዐማራ ፋኖ በኩል ነው። አንድነቱ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየተጠጋ ስለሆነ ላለመሳሳት እና ደግሞም ደጋግመን አስበን መወሰን ስላለብን ነው የዘገየነው። አሁን ጨርሰናል። በቶሎም መልስ እንሰጣለን ብለን ከቀጠርነው ቀንም ጥቂት ቀን አሳልፈናል። ሁሉን ጉዳይ ስለጨረስን በቅርቡ ለሕዝባችን ታለቅ የሆነውን የምሥራች እናበሥራለን" በማለት ለመዝገየቱ ራሳቸውን ተጠያቂ አድርገው መረጃውን አጋርተውኛል። አለቀ።

"…ጎበዝ ፍጠኑ። አንድ ሁኑ። የአሜሪካም ሆነ ሌሎች የአውሮጳ መንግሥታት የእናንተን አንድነት እና ወጥ ድርጅት በጉጉት እየጠበቁ ነው። አዎ ድርጅት የግድ ነው። ፍጠኑ። ማረሚያውም በዚህ ተስተካክሏል።

"…በሉ እናንተ ደግሞ ጀምሩ። አንድ ሁለት ሦስት… ጀምሩ…!

ዘመድኩን በቀለ

15 Nov, 19:21


"ርእሰ አንቀጽ"

"…ሰሞኑን ታዝባችሁልኝ ከሆነ በሸዋ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ስር የሚተዳደረው የእነመከታው ፋኖ ቡድን በተደጋጋሚ ወደተለያዩ ሚዲያዎች እየወጣ ስለፋኖ አንድነት፣ ከአንድነት ውጪ ሌላ ምርጫና አማራጭም እንደሌለ፣ ሳይጠየቅ እየለፈለፈ ነው። ከእነ ምሬ ወዳጆ ጋር፣ ከእነ ዘመነ ካሤ ጋር፣ ከእነ ኢንጂነር ደሳለኝ ጋር በጋራ ለመሥራት እየተነጋገርን፣ በደንብ እየሄድንበት ነው የሚል መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል። ይሄንኑ መግለጫም በጎንደሩ ስኳድ በፓስተር ምስጋናው ሚዲያና በመሳይ መኮንን ሚዲያ ላይ በመቅረብ አቤ ጢሞና መምህሩ ሲደሰኩሩም ተሰምቷል። አለቃቸው ፋኖ መከታውም በቪድዮ መልእክት ወጥቶ ከወንድሞቻችን ጋር በግድ ከመታረቅ፣ አንድ ከመሆን በቀር ሌላ አማራጭ የለንም ሲል ተሰምቷል።

"…ምኞቱ ጥሩ ነው። ጥሩም ነበር። ነገር ግን ምንድነው ዛሬ እንደዚህ ታስሮ እንደተፈታ ሰው እንደ ግሪሳ ወፍ ከነ ወጥተው ዋይዋይ ያስባላቸው? ምን ሆነው? ምን አግኝተው ነው እንዲህ አደባባይ አውጥቶ የፍቅር፣ የአንድነት ሰባኪ ያደረጋቸው? ድንገቴው ነገር ምንድነው? ይሄንን ለመመርመር ሞክሬ ነበር። ያገኘሁት መልስ ግን እነርሱ ከሚያወሩት በእጅጉ የተለየ ነው። መሬት ላይ ያለው የኃይል አሰላለፍ ነው እነ መከታውን የአቡኤን መገበሪያ እንደበላ ሰው ያስለፈልፋቸው የጀመረው። ብዙ ሰዎች በሸዋ ጉዳይ የሸዋን ፖለቲካና የሸዋ ፋኖን እንቅስቃሴ የሚከታተሉ አካላት ነገሩ በደንብ ይገባቸዋል። ለምን የእባብ መርዝ እንደቀመሰ ፍየል ማርከሻውን ፍለጋ እንደሚንጠራወዙ ይገባቸዋል።

"…እነመከታው በእስክንድር ምክንያት ደጋፊ አጥተዋል። በእስክንድር ምክንያት በሳምንት ይፈስላቸው የነበረውን 20 እና 30 ሺ ዶላር አጥተዋል። እነ መከታው ከተዋጊ ፋኖዎቻቸው በእስክንድር ጉዳይ ለሚነሳባቸው ጥያቄ ምንም ዓይነት ምላሽ ባለመስጠታቸው ከእነ መከታው የፋኖ አደረጃጀት የሚወጡ ብርጌዶች፣ ተዋጊዎች ዕለት ዕለት እየጨመሩ መምጣት፣ ክፍለ ጦሮችም ከጠቅላይ ዕዙ ለመለየት መግለጫ ማውጣት መጀመራቸው፣ እነሱ ተንፈላሰው ይኖሩበት የነበረው ቀጠና በተዋጊ ዕጦት መሳሳት መጀመሩ አሳስቧቸዋል። እስክንድርን ይዘው ሚልዮን ዶላሮችን ለማፈስ፣ እስክንድርን ይዘው በድርድር በአቋራጭ ሥልጣን ለማግኘት በመጓጓት የሠሩት ስህተት ከባድ አርታኢሌ የሆነ ስጋት ውስጥ ከትቷቸዋል። እናም ስለዚህ ያላቸው አማራጭ ሳይጠየቁ መለፍለፍ፣ ሳይለመኑ የሰላም፣ የአንድነት ሰባኪ መሆን ብቻ ነው። ግን ረፍዷል።

"…እነመከታውን ነግሬአቸው ነበር። የሸዋ ተወላጅ ግማሽ ሚልዮን ዶላር የረዷቸው ሰዎችም ነግረዋቸው ነበረ። ከጎንደር ስኳድ ከፖለቲካው ቅማንት ከትግሬ ዲቃሎች ጋር ያላችሁን ግኑኝነትም አቁሙ ተብለው ነበረ። እስክንድርን ከመካከላችሁ አውጡት፣ ወይም በእናንተ ስር ገብቶ ይታገል፣ ሸዋ ተቀምጦ፣ በመከታው ጀሌ እየተጠበቀ፣ በሸዋ ግንባሩ፣ ሠራዊቱ፣ እያለ እንደ ኢንኪዩቤተር የፖለቲካ ጫጩት፣ ያውም የማያድጉ፣ ካካቸው የበዛ የፖለቲካ ድርጅት አይፈልፍል ቢባሉም አልሰሙም። ምክር ናቁ። በሽምግልናው ወቅት እነ መከታው የወከሉት ፓስተር ዮናስን ነበር። እነ ደሳለኝ የወከሉት ደግሞ ዶር አብደላን ነበር። እነ ዶር አብደላ የጠየቁት አንዲት ጥያቄ ብቻ ነበር። እነ መከታው የወሰዱብንን አንዲት የግላችን ንብረት መልሱልን። እነ መከታው የወከሉት ፓስተር ዮናስ ግን ስለዚህ ነገር የማውቀው ነገር የለም። እነ አሰግድ በእኛ ስር ከገቡ ይግቡ፣ ካልገቡ ግን አንለማመጣቸውም። እነሱን ለመደመስስ ግማሽ ሰዓት አይፈጅብንም ነበር ያለኝ። በሁለቱም በኩል መሬት ላይ የተመደቡትን ሽማግሌዎች ይሄ የእነ መከታው ፓስተር ነው አፈር ከደቼ ያበላው እና በትእቢት ነገርየውን እንዳይሆን ያደረገው። አሁን እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም የሸዋ ፖለቲካ የእነ መከታው ደጋፊ ሆነው ሲመጡ ነጥቦቹን ስገጣጥም ያገኘሁት ሥዕል የሚያሳየኝ የሸዋ፣ የእነ መከታው ትግል በብልፅግና ወንጌል ፓስተሮች ጭምር መጠለፉን ነው።

"…የሆነው ሆኖ የዐማራ ትግል የግዱን እየጠራ ይመጣል። በረሀ ወርጃለሁ ብሎ ጺምን ኦ እየተቆረጡ፣ ሁሌ ሥጋ፣ ሁሌ ፍየል እየበሉ፣ ስቴኪኒ ይዘው እየዞሩ፣ ሚስቶቻቸውን እና ገርል ፍሬንዶቻቸውን አቅፈው እየተኙ፣ አንዲት ከተማ ሳያስለቅቁ፣ የገበሬ ከብትና ፍየል፣ ሙክት ብግ ዳያስጶራ ደም ተፍቶ የሚልከውን በሸነና እያሉበት መቀጠል አይቻልም። እንደ ላስታ፣ እንደ የዐማራ ፋኖ በወሎ ልጆች ያለ ውጭ እርዳታ ሙጫና በለስ፣ አጋምና ቀጋ እየበሉ በመታገል ጠላትን ድል ማድረግ ይቻላል። እንደነመከታው እና እስክንድር ገጠር ተቀምጦ በዐማራ ፋኖ ትግል ቦርጭን አንዘርጥጦ ጽድት ብሎ መንገማሸር ፌር አይደለም። ሊወገዝ ይገባል። የህልውና ትግል ያለበት ፋኖ ዶላር ሲቀርበት ዋይዋይ አይልም። ፋኖነትን ለኑሮ ማሸነፊያ ማድረግ ስህተት ነው። ትልቅ ጥፋትም ነው። ደያስጶራው በዚህ በኩል ስሜታዊ፣ ደንታቢስ ሆኖ ሳይሆን መርምሮ፣ አጥንቶ፣ በዐማራ የፋኖ ትግል ውስጥ በተጨባጭ የሚታይ፣ የሚዳሰስ፣ የሚጨበጥ ትግል በማድረግ ላይ ያሉትን ፋኖዎች ለይቶ በማውጣት እርዳታ ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል አለበት። የሸዋ ተወላጅ የዐማራ ዳያስጶራዎች ያደረጉትም ይሄንኑ ነው። እነመከታውን ይረዱ፣ ይደገፉ ነበር። እነመከታው ጠገቡ፣ ወበሩ፣ የእስክንድርን ሚልዮን ብር ሊቀራመቱ ምራቃቸውን ዋጡ። ስለዚህ ቋሚ ደጋፊዎቻቸውን አሳዘኑ። የሸዋ ተወላጆችም እነመከታው ትእቢታቸው ጣሪያ ሲነካ ሽፍት አደረጉ። ወደ እነ ደሳለኝ ፊታቸውን አዞሩ። ወደከሰም፣ ወደ ቡልጋ ፊታቸውን አዞሩ። አሁን የእስክንድር የለመንለት ዶላር ሲጠር እነመከታው ኪሳቸው ባዶ ሲሆን፣ ሲራቆት፣ እነ ፓስተር ምስጋናውም ዱዲ ሳንቲም እንደማይሰጧቸው ሲያውቁ በየሚዲያው ወጥተው ከዘመነ ካሤ ጋር ልንታረቅ ነው። ከነ ምሬ ወዳጆ ጋር አንድ ልንሆን ነው፣ ከእነ ደሳለኝ ጋር ልንተቃቀፍ፣ ልንሳሳም ነው… ብላ ብላ…  ፓስተር ዮናስን ምን አልኩት። ታያለህ ዮኒዬ ኃይል የእግዚአብሔር ነው። እንዲህ እንደታበያችሁ ቀን መጥቶ ዘጭ ብላችሁ አፈር ደቼ ባትግጡ ምናለ ዘመዴ በለኝ ብዬ ነው እቅጩን የነገርኩት። የሆነውም የተናገርኩት ነው። ትእቢት እንዲህ ብርድ ብሎ ሲታይ ደስስ ሲል።

"…ከዚህ ሁሉ በኋላ በዛሬው ዕለት የእነ መከታው ቡድን በሸዋሮቢት ከመከላከያ ጋር እየተዋደቀ መሆኑን ይፋ አድርጎ በእነ መዓዛ መሀመድ ሮሀ ሚዲያ ሲዘገብ ታይቷል። በአካባቢው ምንድነው የሆነው? የእነ መከታው ጦር መከላከያ ላይ ለምን ተኮሳችሁ እያለ ፋኖዎችን የሚቀጣው ቡድን እንዴት ደፍሮ ተዋጋ ብዬ ወደ አከባቢው ደውዬ ነበር። ያገኘሁት መረጃ የሚያሳየው እነመከታው እንዳልተዋጉ፣ ወደ መጨረሻው አካባቢ ሕዝቡ አስገድዶ ዲሽቃ እንዲሰጥ እንዳስደረገና፣ ቅር እያለው ዲሽቃ ይዞ የእነ መከታው ቡድን ወደ ስፍራው እንደሄደ ነው የተነገረው። የጦርነቱም መነሻ በአካባቢው ያለ የመከላከያ ኃይል በሸዋሮቢት ዙሪ ዝም ብሎ በዘፈቀደ የተኮሰው መድፍ አንድ ደገኛ የዐማራ ገበሬ ይገድላል። በሁኔታው የተበሳጨው የሸዋ ሮቢት ዙሪያ ገበሬ መከላከያን ባለው መሳሪያ ይገጥመዋል። ከዚያም መከላከያው ያልጠበቀው ዱብ ዕዳ ይገጥመዋል። መከላከያው ተረፈረፈ። ከዳር ቁጭ ብሎ የሚያየውም የመከታው ጦር በአስቸኳይ እንዲቀላቀላቸው ጥሪ ገበሬው አቀረበ። ሳይወዱ በግዳቸው ዲሽቃ ይዘው መጥተዋል። የሆነው ይሄው ነው ብለዋል የአካባቢው የመረጃ ምንጮቼ። …👇① ከታች ይቀጥላል…

ዘመድኩን በቀለ

15 Nov, 19:21


👆② ከላይኛው የቀጠለ… "…ሌላው የወልቃይት ጉዳይ ነው። እኔ ኮሎኔል ደመከ ዘውዱን በግልጽ ጥያቄ ሳነሣበት ጎንደሬ ነኝ የሚል ዐማራውም፣ የትግሬ ዲቃላ ስኳዱም እሪሪ ብሎ ነበር የጮኸብኝ። ደመቀ ትግሬ ነው። ፕላን ቢ አድርገው ትግሬዎቹ ለክፉ ቀን ያስቀመጡት ልጃቸው ነው። ደመቀ ከወልቃይት ዐማራን ያጸዳ ሰው ነው። ወልቃይትን ጎንደሬ ዳግም ይበላል። መከላከያ ከወልቃይት እየተነሠሣ ነው የጎንደር ዐማራን የሚጨፈጭፈው። ደመቀ ዘውዱ ብልጽግና ነው። ደመቀ ዘውዱ አሳልፎ ወልቃይትን ለወያኔ ይሰጣል ብዬ ስለፈልፍ አፈር ከድሜ የምግጥ አይደለሁም እንጂ አፈር ከድሜ እኔን ለማስጋጥ የተሰለፈውን ሕዝብ ታስታውሳላችሁ። አይደል ምእመናን።

"…ይኸው ትናንት ዐማራው ጎንደሬ በወልቃይት ምክንያት የወጣውን ዜና ተመልክቶ ምንድነው ነገሩ? ምን ጉድ ነው የመጣብን? ምን ዓይነት ነገር ነው? what's going on, ምንድነው የምንሰማው ነገር፣ ምንድነው የምናየው ነገር በማለት ዋይዋይ ሲሉ ነው የዋሉት። የትግራይ አክቲቪስቶች እንደ ትልቅ ድል ቆጥረውት "ተመዛበልቲ ወደ ገዛኦም ተመሊሳ" እያሉ ሲዘግቡ፣ በማይካድራ ጭፍጨፋ፣ በወልቃይት ጭፍጨፋ ተሳትፈው የነበሩ የወያኔ የጦር መኮንኖች አቢይ አሕመድ በላከላቸው አውሮጵላን ተሳፍረው ወልቃይት ሲደርሱ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አውሮጵላን ጣቢያ ድረስ ሄዶ ሲቀበላቸው የተለቀቀው ፎቶ የጎንደርን ዐማራ ጆሮ ጭው ሲያደርግ ነው የዋለው።

"…ባይገርምላችሁ ጎንደሬ ሆነው ሁል ጊዜ ስለወያኔ ብቻ የሚጽፉ ፔጆች ላይ ሄድኩኝ። እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ፔጅ ላይ ገባሁ ምንም ወፍ የለም። የወልቃይት ጉዳይ፣ የኮሎኔል ደመቀም ጉዳይ ቀይ መስመራችን ነው ብሎ በሚታወቀው ፉከራው የሚታወቀው ባህርዳር አድጎ ፀረ ጎጃሜ የሆነው የደቡብ ጎንደሩ አያሌው መንበር ፔጅ ገባሁ። እንደውም የዛሬ ስድስት ቀን የማይካድራን ጭፍጨፋ ከለጠፈ በኋላ ምን እንደሰማ አይታወቅም ድራሽ አባቱ ነው የጠፋው። ሙላት አድኖ ቤት ገባሁ ወፍ የለም። ሙላት የፈራ ይመለስ ዛሬም ጎጃሜን ነው የሚወቅሰው። አረጋ ከበደ ብራኑ ጁላን ሸለመው ብሎ ነው የሚያለቅሰው። ሲሳይ አልታሰብ የአሸቦ ዕቃው ወዳጄ ቤት ገባሁ። ወፍ የለም። ሙሉዓለም ገረ መድህን ኡጋንዳ ሆኖ ትንፍሽ አላለም። ብቻ what's going on የሚል ብቻ ነው የበዛው። ኮሎኔል ርስተይ ተስፋይ እና አስፋው አብርሃ ብቻ ናቸው ደፍረው እንኳን በደኅና መጻዕኮም ኮሎኔሎታት ብጻይ አሐወይ ብለው የተነፈሱት።

"…የጎንደር የዐማራን ፋኖ ለ3 የከፈሉት ሁሉ ዛሬ ጮቤ እየረገጡ ነው። ወልቃይትን ነጻ ለማውጣት የሞቱ የጎጃም፣ የሸዋ፣ የወሎ እና የጎንደር ዐማሮችን ነፍስ ይማር። ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይከፋሽ ነው አይደል የሚባለው? ጎንደር ለዳግም ስደት ተዘጋጅ አልያም አንድ ሆነህ ጠላትን ለመጋፈጥ ተዘጋጅ። ባርነት ወይም ነፃነት ምርጫው የአንተው ነው። ዳግም ከመጡ ግን ለዘር አያስተርፉህም። ይሄን በደንብ ዕወቅ። ተረዳ። ወልቃይት ላይ አያቆሙም። ከአክሱም እንዳባረሩህና ጎንደር እንደወሸቁህ አሁን ከጎንደርም ድራሽ አባትህን ነው የሚያጠፉህ። አዲስ አበባና ኡጋንዳ መሰደድ አያዋጣም። ወደ አሜሪካና አውስትራሊያ፣ ወደ አውሮጳም መሰደድ አያዋጣም። ትግሬውን ኮሎኔል ደመቀ በጎንደር ዐማራ ስም ሲሸውድህ ፋራ ዥል፣ ዥልጥ ሆነህ ከተሸወድክ በኋላ አሁን ማለቃቀሱ ዋጋ የለውም። የፈሰሰ ውኃ አይታፈስም። በዚሁ ከቀጠለ በቅርቡ ወልቃይት የወያኔ ይሆናል። መዝግቡልኝ።

"…ስኳዶች አትደበቁ። ውጡና ተናገሩ። የእኔ ጦማር ያበሳጫል፣ ደም ያፈላል፣ ይጎረብጣል። ግን ኮሶ ነው ያሽራችኋል። ግን መድኃኒት ነው ይፈውሳችኋል። አትደበቁ። የማይነጋ መስሏችሁ ነው ቋት ውስጥ ያራችሁት እናንት በጠጣም ፀረ ጎንደሬ፣ ፀረ ዐማሮች። አሁን የት ትደበቁ? የት ትገቡ? ውጡና ተንፍሱ። ተናገሩ። በአፄ ቴዎድሮስ ስም እየማሉ፣ በጎንደር ሙዚቃ እየደነሱ፣ በፋሲል ግንብ እያጌጡ ወልቃይትን አደንዝዘው ያሳጧችሁን ለይታችሁ ውቀሱ። ጎንደሬዎች ትደነዝዙ ዘንድ የመገጭ ግድብ ይሠራላችኋል። የፋሲል ግንብ፣ የከተማዋ አውራ መንገድ በኮሪደር ልማት ቀለም፣ በመብራት ይሸቆጠቆጥላችኋል። እሱን እያያችሁ ወልቃይትን ይረከቡአችኋል። ይሄን ስላልኩ ፎክር፣ አቅራራ አሉህ አንት እስኳን ፀረ ጎንደር ዐማራ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው። ፎክር።

"…በመጨረሻም ዐራቱም የዐማራ ፋኖ ዕዞች ወደ አንድ ለመምጣት የጀመሩትን ጉዞ ዐውቃለሁ። የወሎው በምሬ ወዳጆ፣ የጎንደሩ በባዬ ቀናው፣ የጎጃሙ በዘመነ ካሤ እና የሸዋው በኢንጂነር ደሳለኝ የሚመሩት ዕዞች ማለት ነው። ብዙ መንገድ ሄደዋል፣ ለፍተዋል፣ ደክመዋል። እየጣሩም ነው። ነገር ግን አሁን ላይ እነዚህ ዕዞች ወደ አንድነት እንዳይመጡ አንደኛው ዕዝ ላይ ሴራ እየተሴረ እንደሆነ እየሰማሁ ነው። ይኸውም ዕዝ የጎንደሩ የእነ ባዬ ቀናው ዕዝ እንደሆነም እየሰማሁ ነው። ይሄን ወደ አንድነት እንዳይመጡ የመጎተት ሴራው ደግሞ በጎንደሩ በእነ ባዬ ቀናው የጎንደር ፋኖ በኩል ይመስላል። ምክንያቱ ደግሞ አንድነቱን እያዘገየው ያለው በሴራ ነው ተብሏል። ሴራውም የተጎነጎነው የእነ ሀብቴ ወልዴ ቡድን ከእስክንድር ነጋ ድርጅት መውጣቱን በይፋ በግልፅ ሳይናገሩ፣ በጎን የጉንደር እዝ ወደ አንድ ልንመጣ ነው እያሉ የእነ ባየ ቀናው ዕዝ ከእነ ዘመነ፣ ከእነ ኢንጂነር ደሳለኝ ሲያስብ ሽዋ፣ ከእነ ምሬ ወዳጆ ጋር ሊመሰርቱ ያሰቡት የፋኖ ኃይል ላይ እንቅፋት እየሆኑ መሆናቸው ነው የተሰማው። ለማንኛውም ጥንቃቄ ያስፈልጋል። እስር ቤት ያሉትም ከእስርቤት መልእክት እየላኩ አንድነቱን ባያዘገዩት ይመረጣል።

"…ለጊዜው ሊመጣ ከጫፍ የደረሰውን አንድነት አርበኛ ዘመነ ካሤን በመግደል ለማስተጎገል ታስቦ ነበር። እሱን እግዚአብሔር አከሽፎታል። ቀጣዩንም ሴራ እግዚአብሔር ያከሽፈዋል። ዝርዝሩን የምጽፈው ጉዳዩ አደገኛ አዝማሚያ ሲይዝ ብቻ ነው። መቼም የምለው ይገባችኋል። አለቀ።

• በዐማራ ትግል ላይ ደንቃራ የሆኑትን ሾተላዮች በሙሉ በጋራ ሆነን በእውነት ሰፌድ እናበጥራቸዋለን…!

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

•••

ሻሎም.!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ህዳር 6/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

ዘመድኩን በቀለ

15 Nov, 14:28


መልካም…

"…አሁን ደግሞ ወደ ርእሰ አንቀጻችን ነው የምንሄደው። ዛሬ የሳምንቱ መጨረሻ የሥራ ቀን ነው። እኛም ርእሰ አንቀጽ እስከ ማክሰኞ ድረስ አይኖረንም። ለዛሬ ይሄ የመጨረሻው ርእሰ አንቀጻችን ነው ማለት ነው።

"…በዛሬው ርዕሰ አንቀጻችን ሦስት አጀንዳዎችን መርጠን እንወያይበታለን። አንደኛው አጀንዳ
የእስክንድር ነጋ ድርጅት የመረጣቸው የፋኖ አደረጃጀቶች ፍርስርሳችው ሊወጣ ምልክት እየታየነ ስለመሆኑና በተለይ የነመከታው ፋኖ በየሚዲያ ብቅ እያለ "አንድ ነን፣ አንድነት ልንፈጥር ነው፣ ልዩነታችን የሓሳብ ነው፣ ተስማምተናል እያሉ ሲለፈልፉ የሚታዩት፣ ከአወነ ዘመነ፣ ከእነ ምሬ፣ ከእነ ባዬ እና ከእነ ደሳለኝ ጋር ልንስማማ ነው ብለው መለፍለፋቸው ከጤና አንጻር እንዴት ይታያል የሚለውን የዱፍትርና ልምዳችንን ተጠቅመን እንመረምረዋለን።

"…ሌላው የወልቃይት ጉዳይ ነው እሱንም እንዳስሳለን። በመጨረሻም ዐራቱም የዐማራ ፋኖ ዕዞች ወደ አንድ ለመምጣት የጀመሩትን ጉዞ ዐውቃለሁ። ነገር ግን እነዚህ ዕዞች ወደ አንድነት እንዳይመጡ አንደኛው ዕዝ ላይ ሴራ እየተሴረ እንደሆነ እየሰማሁ ነው። የትኛው ዕዝ ነው እየተሴረበት ያለው የሚለውን ርእሰ አንቀጹ ላይ ለዛሬ ጠቆም አድርጌ አልፋለሁ። ሊመጣ ከጫፍ የደረሰውን አንድነት አርበኛ ዘመነ ካሤን በመግደል ለማስተጎገል ታስቦ ነበር። እሱን እግዚአብሔር አከሽፎታል። አሁን የሚዘገየው ለምንድነው? አብረን እናየዋለን።

"• ፊልድ ማረሻው ዘመዴ ነኝ። እህሳ ነጭ ነጯን ርእሰ አንቀጼን ለማንበብ፣ አንብባችሁም እናንተም ሓሳባችሁን ለማካፈል ዝግጁ ናችሁ?

• 100 ፍሬ ሰው ዝግጁ ነኝ ይበል። ትእዛዝ ነው።

ዘመድኩን በቀለ

15 Nov, 11:45


"…አምላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥ ስምህንም ለዘላለም ዓለምም እባርካለሁ። በየቀኑ ሁሉ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም ለዘላለም ዓለምም አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው፤ ለታላቅነቱም ፍጻሜ የለውም። መዝ 145፥

"…እግዚአብሔር ዓለቴ አምባዬ መድኃኒቴ ነው፤ እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ፤ ጋሻዬና የረድኤቴ ቀንድ፥ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ፥ መድኃኒቴ ሆይ፥ ከግፍ ሥራ ታድነኛለህ። ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ ከጠላቶቼም እድናለሁ። 2ኛ ሳሙ 22፥ 2-4 “…ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።” 2ኛ ቆሮ 9፥15

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

15 Nov, 04:30


አይ ስኳድ 😂              

"… በእኔ ጉዳይ ሊወያዩ ገብተው ጌታሰፋው እና ራስተፈሪ ጭቅጭቅ ውስጥ ገቡላችሁ እኔ ልናገር እኔ ልናገር በሚል። በሉ ተስማሙና ቦጭቁኝ። 😂
ጌታስፋው ቀጥል።

"…ርእስ አመራረጣቸው ራሱ ገዳይ ነው። ዘመድኩንና ዘመነ ካሤ ይሉልሃል። አይ ዘመዴ ምኑ ጉደኛ ሰው ነህ። 😁

• እስቲ ልስማችሁ።

ዘመድኩን በቀለ

14 Nov, 21:39


"…የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው ስኳድ በወልቃይ ጉዳይ ትንሽም እንኳን ቢሆን ይተነፍሳል ብዬ በየቤታቸው ብዘር ባፈጥ፣ ብሽከረከር፣ ምንም ወፍ የለም። ምንም አልኳችሁ። 😂

"…አያሌው ቀይ መስመር ቤት ገባሁ፣ የአሸቦ ዕቃው ሲሳይ አልታሰብ ቤት ገባሁ። ጭራሽ ትንፍሽ አይልም። ሙላት አድኖ የፈራ ይመለስ ሰፈር ሄድኩኝ ኧረ ምንም። ሚስተር ባናና ኢትዮጵያ ገብቶ ሰሞኑን ጭራሽ መቀሌ ነበር አሉ። ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ቤት ብገባ ጸሎትም፣ መዝሙርም የለም። በልሣን እንኳ አይናገረም። ምን ጉድ ነው?

"…አስፋው አብርሃና ርስተይ ተስፋይ ብቻ ናቸው ትንሽም ብትሆን ተጋግዘው ጫር ጫር ያደረጉት። ሙሉዓለም ገረመድህን ዝም፣ ጭጭ፣ ሰለሞን ቦጋለ (ሃውልቲ) ራሱ ዝም። እነ ፈትሊም ትዊተር ስፔስ ላይ ጭጭ ምን አስበው ነው ግን…?

"…ስኳድ የትግሬው ዲቃላ ጎጃምን ሲረግም፣ ዘመነ ካሤን ሲሳደብ፣ ሸዋ ገብቶ አሰግድ ሲያሳድድ፣ ወሎ ምሬ ላይ ሲያሟርት፣ ደቡብ ጎንደር ፍሮፌሰር ልኮ ባንክ ሲያዘርፍ ይውላል። የአዜብ መስፍን ዘመዶች አቢይ አሕመድ ሮጲላና ሂሊኮፍቶር ልኮ ወልቃይት አስገብቷቸዋል።

"…ከናዝሬት አዳማ የብልፅግና ሥልጠና መልስ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ከህመሙ ጋር እየታገለ ሥራውን እየሠራ ነው። እኔ ደግሞ ምን አግብቶኝ ነው የምቀበጣጥረው። ስኳዶች ግን ተንፍሱ እንጂ። ያልገባን ነገር ካለም አስረዱን እንጂ። የምን ዝም፣ ጭጭ ነው? ሃኣ…?

• ርስተይ ግን ያቀንአለኪ…!😂

ዘመድኩን በቀለ

14 Nov, 21:07


አቤ ጥሩ እያጫወተኝ ነው።

"…ዘመዴ ምላሽ አልሰጥህም እያለ ነገር ግን በቀን ሁለቴ ምላሽ እየሰጠኝ ነው… በመልስ አሰጣጡ ላይ ግን ጥሩ መሻሻል አሳይቷል። በዚህ ምላሹ ላይ ሌሎችን አግዙኝ፣ ፋኖ መግለጫ ያውጡልኝ፣ የዐማራ ማኅበራት ሰብሰብ ብለን መግለጫ እናውጣበት፣ የመረጃ ቲቪ ባለቤቶች ዘመድኩንን አውሩዱልኝ ካልሆነ በቤታችሁ ሰልፍ ነው የምወጣው አላለም። አቤ ዐማራ ስላልሆነ የአማርኛ ፊደል ለምን ተሳሳተ ብዬ አላስጨንቀውም። የሆነው ሆኖ ለጠየቅኩት ጥያቄ ሳይወድ በግዱ በፈለገው መንገድ እየመለሰለኝ ስለሆነ አክብሮቴ ላቅ ያለ ነው።

"…አቤ ያልመለሰልኝ ጥያቄዎችም አሉ። ኢትዮጵያውያን ሬስቶራንት ከተጠቀምክ በኋላ ለተጠቀምክበት ክፍያ የማትፈጽመው ለምንድነው? የሬስቶራንት ባለቤቶችን ለምን ታሳቅቃለህ? ሌሎች ሰዎች እንዲከፍሉልህ ለምን ትጠብቃለህ? ለሠራተኞች ቲፕ ለምን አትሰጥም? ዋ ከተቋቋመ ጀምሮ፣ አንተ ብቻ መሪ የሆንከው? በአንተ ሰምም ያስመዘገብከው ለምንድነው? 30 ዓመት ሙሉ አንተ ብቻህን የአዲስ ድምጽ ፕሬዝዳንት ለምን ሆንክ?

"…አቤ አሜሪካ ከመጣህ ጀምሮ ታክሲና ቁማር ቤት እየሠራህ ያልቀየርከውን ቶዮታ ፒረስ መኪና ዋን ባቋቋምክ በአጭር ጊዜ ውስጥ የ80 ሺህ ዶላር ቴስላ መኪናና የሚሊየን ዶላር ቤት ገንዘብ ከየት አምጥተህ ገዛህ? የት ተምሮ ራሱን ጋዜጠኛ እያለ እንደሚጠራም አልነገረኝም። ስለዚህ የጠየቅኩትን ጥያቄ ካልመለሰ ግን እንዳመነ ይቆጠራል ማለት ነው። በቀጣይ ደግሞ ለነዚህ ምላሽ እንደሚሰጠኝ ተስፋ አደርጋለሁ። እየመረጡ መመለስ አይቻልም። ገና ስለ ኦዲት፣ አደገኛውን ነገረ ጋብቻ አነሳለሁ። ኢየሩሳሌም የሄደበትን ብር አልከፍል ብሎ የጉዞ ወኪሉ ሀብታሙንና ኢየሩሳሌም ያሉ መነኮስ ሽምግልና ልከውበት ቀርጥፎ ክዶ ማስቀሩትም አልተነገረም።

አመድኩን ነቀለ ነኝ። ከመዶሻ ሰፈር።

ዘመድኩን በቀለ

11 Nov, 09:28


"…በትእግስት ጠብቁን…

"…መላቀቅ የለም ብለው ከሳታላይቱ ጋር እየታገሉ ነው ቴክኒሽያኖቹ። ወደ 2ሺ ሰው ዩቱዩብ ላይ እየጠበቀ ነው። ቀጥሎ የማቀርበው ነው ጣጣ ያመጣብኝ። ከዛሬ በኋላ መርሀ ግብሬን ቀድሞ ማስተዋወቅ አቆማለሁ።

• ወይ ንቅንቅ…💪 አላችሁ አይደል?

ዘመድኩን በቀለ

11 Nov, 09:28


“…የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለች…። ” ማቴ 27፥64

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

10 Nov, 17:39


"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ምሽት 2:30 ላይ ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ዛሬ ግሩም ግሩም የሆኑ መርሀ ግብሮች ናቸው የሚጠብቋችሁ።

• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/f9fnW5M3AUk
• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaTV
• Mereja TV: https://mereja.tv
• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ

10 Nov, 17:39


"…አላችሁ አይደል…?

• እስቲ ገባ ገባ በሉ ።

ዘመድኩን በቀለ

10 Nov, 16:21


ይሄ የለንደን ፋኖ ነው…!

"…እንደ እከደከን ማንችሎት፣ በብልጠትም ሆነ በጉልበት አበጀ ጥላሁን ጉግሣ ቤት ገብቶ ለሽ ብሎ ተኝቶ የነበረው ዐማራ የእንቅልፍ አዚሙ ተወግዶለት በመጨረሻው ሰዓት ከጥልቅ እንቅልፉ ነቅቶ በት በት እያለ ነው። እኔም ስለቴን ለለንደኗ ማርያም ላስገባ ነኝ ማለት ነው። የለንደኗ ማርያም አሁንም የቀረውን ዝንጉ፣ ዳተኛ፣ አለቅላቂ፣ ወሬኛ፣ ሸውከኛ፣ ፈሪ፣ አስመሳይ፣ ገተት፣ ሆዳም፣ ማይም፣ የወገኑ ስቃይ የማይሰማው፣ ራስወዳድ ዐማራን አዚሙን አስወግደሽ አንድ ላይ እንዲህ ካቆምሽው ስለቴን አስገባለሁ።

"…እነ አዲስ፣ እነ ወርቁ ብቻቸውን ይጮሁበት፣ እነ ያየሽህራድ ብቻቸውን ዋይዋይ ይሉለት የነበረው ዐማራ ከፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ጉያ በተአምራት ተፈልቅቆ ወጥቶ እንዲህ ሲቀውጠው እንደማየት ምን የሚያስደስት ሌላ ነገር አለ?

"…አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አወሮጳ፣ አፍሪካም በሙሉ ይቀጥላል። ዐማራ ለመነሣት የፈጀውን ማገዶ ቢፈጅም መነሣቱ አይቀሬ እንደሆነ ዐውቅ ነበር። አሁንም ይቀራል። በዛሬ ምሽት የመረጃ ቲቪ መርሀ ግብሬ ይሄም ይዳሰሳል።

• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁኝ…!

ዘመድኩን በቀለ

10 Nov, 16:12


"…ይገደል…

"…ይሄ ከወለጋ ናዝሬት ድረስ የመጣው የዋቃ ጉራቻ አራጅ ምን ዓይነት አሰቃቂና አረመኔያዊ ወንጀል ቢሠራ ነው የናዝሬት ሕዝብ እንዲህ አውራ ጎዳና ላይ ወጥቶ ይገደል፣ ይገደል፣ ይገደል ብሎ የሚጮኸው?

• የምሽት 2:00 ሰዓት ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር የመረጃ ቴሌቭዥን የቀጥታ ስርጭቴ ምላሹን ይዞላችሁ ይጠብቃችኋል።

• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁኝ።

ዘመድኩን በቀለ

10 Nov, 14:09


ይሄ መረገም ነው…

"…ደግነት መልክ ቢኖረው እሷን ነው የሚመስለው ተብሎ በያያ፣ ኢትዮጵያዊቷ ማዘርትሬዛ በፓስተር ምስጋናው አንዷለም ተብሎ ፕሮፓጋንዳ የተሠራላት፣ በእናቷ አዲስ ዘመን ግማሽ ቅማንቴ በአባቷ ኦሮሞ የደርግ ወታደር ልጅ እንደሆነች በሚነገርላትና ልክ እንደ እስክንድር ነጋ ስሟንም መልኳንም ፀረ ዐማራው ቡድን ቀባብቶ የዐማራ ሾተላይ አድርጎ ያዘጋጃት፣ በኢንተርኔት ላይ ማፍያዋ በተደራጁ የጎንደር ፀረ ዐማራ ኔትውርኮች አማካኝነት በተቸገሩ ዐማሮች ስም በቲክቶክ ወዘተ ዶላር ከዳያስጰራው በመግፈፍ ለተቸገሩት ዐማሮች ሳያደርሱ ይበሉ፣ ይሸቅጡ የነበሩት ቡድኖች በግፍ የሰበሰቡትን ብር ሳይበሉ በአገዛዙ ቁጥጥር ስር መዋል ጀምረዋል።

"…በተለይ ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ላይ ፈስሰው በቁማቸው ትል የሚረግፍባቸውን የዐማራ ፋኖ ተፈናቃዮች ታስታውሳላችሁ። እነ መማር አለባቸው እና በእሷ ጀርባ የነበሩት የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎች 1ሚልዮን ብር ሰብስበው እንዳስቀሩባቸውም እንደነገርኳችሁ ታስታውሳላችሁ። ዋነኛው የመማር አለባቸው የጎንደር የዘረፋ ወኪልንም እነ አያሌው መንበር ለተፈናቃዮቹ መርዳትን እንደ ነውር ቆጥረው አፋቸውን በከፈቱብኝ ወቅት የጎንደሩን ወኪላቸውን ቢያንስ እግዚአብሔር ፍርዱን እስኪሰጥህ ዝም በል ማለቴም ይታወሳል።

"…ይህው ዛሬ በጎንደር የእነ መማርን ተወካይ በባንኩ ውስጥም ከ14 ሚልዮን ብር በላይ ዘጭ ብሎ፣ የተለያዩ መኪኖችንም በስሙ ገዝቶ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል። ፋኖዎች ገንዘባችንን ስጠን እያሉት፣ ለድሆቹም የተዋጣውን ብር ሳይሰጥ ብሩ የአገዛዙ ቀለብ ሆነ።

• እነ ምስጋናው አንዷለም ሆይ…! አቦ እግዚአብሔር አምላክ የእጃችሁን ይስጣችሁ። በማታው የመረጃ ቴቬ የነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ በሰፊው እመጣበታለሁ።

ዘመድኩን በቀለ

10 Nov, 12:22


ተቀበል…9

"…በመጨረሻም…በመጨረሻም ያ ሞኝ መስሎ፣ ሀገር መውደዱ እንደ ፈሪም እንደ ፋራም፣ አንዳንዴም እንደ አድርባይ አስቆጥሮት፣ ታላቋን ሀገር ኢትዮጵያን ይመራ ዘንድ ሕፃን መሆኑን ያልተማረ ማይም መሆኑንም እያወቀ፣ ጨቅላ ቢሆንም ግድየለም እየታገዘ ያድጋል፣ ይሁን ብሎ ድጋፍ ሰጥቶ፣ አንድም ኢትዮጵያን ስሟን እየጠራ፣ ሰንደቋን ለብሶ እየማለ እየተገዘ ቢያየው አያታለለኝማ አይሆንም፣ ግድየለም ጊዜ መስጠትም አይከፋም፣ አያስከፋም፣ ሽግርም የለውም፣ በማለት ለበሸሻሻው አራዳ ለአራጁ አቢይ አሕመድና ለአረመኔ ግሩፖቹ ዕድል የሰጠው፣ ያ በጊዜ አልነቃ ብሎ ጭራሽ እየሰደበኝ ጨጓራዬን ሲልጠኝ የከረመው ታላቁ የዐማራ ሕዝብ አሁን ትእግስቱ አልቆ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማድረግ ማስታወቂያ ለጥፎ ቀጠሮ ይዞ ተነሥቷል።

"…ሰልፉ ዓለም አቀፍ ነው። ትግል ጠላፊ ግንቦቴ፣ ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች፣ ግንባሩና ታፋና ጭኑም ግን ሰልፉን ሊመሩት አይገባም። አይፈቀድላቸውምም። ሰልፉን ዐማሮችን ይመለከታል፣ ዐማሮችም ይመሩታል። ለዐማራ ያዘኑ፣ ነግ በኔ ብለው ያሉም ቤርቤረሰቦች ግን በሰልፉ ላይ በመሳተፍ ለዐማራ ሕዝብ አጋርነታቸውን ያሳዩታል ተብሎም ይጠበቃል።

• መግደርደር የለም፣ ወጥር ዐማራ…! 💪💪🏿💪🏿👏

ዘመድኩን በቀለ

10 Nov, 12:22


ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

"…ድንግል ሆይ…! ርጉም በኾነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ ጋራ ካገር ወደ አገር ስትሸሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ረኀቡንና ጥሙን፣ ችግሩንና ጒዳቱን ከርሱ ጋራ የደረሰብሽን ጸዋትወ መከራ ኹሉ አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ከዐይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ፤ ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ፣ መዐትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ፤ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥኣን አሳስቢ ለንጹሓን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ።

"…ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ሆይ ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን፤ አእምሮውን ጥበቡን ፍቅርሽን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን፡፡"

"…የእመቤታችንን ፍቅሯን በልቦናችን ጣዕሟን በአንደበታችን ያሳድርብን። ምልጃና ጸሎቷ ረድኤት በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን። የአሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያን በምልጃዋ ትጠብቅልን።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

09 Nov, 20:00


ተቀበል…7

"…አየህልኝ ይሄን ጎንደሬ የቴዲ ልጅ…!

"…የሕዝብ ብዛቷ 2 ሚልዮን የማይሞላው የተባበሩት ኤምሬትስ አቢይ አሕመድን አቅፋ ደግፋ ድሮንና ቦንብ እየሰጠች የዐማራን ሕዝብ እያስፈጀችው ነው። ትግሬን አስፈጅታ ከጨረሰች በኋላ ወደ ዐማራው ነው የዞረችው።

"…ትናንት ዐመዳም ደሀ፣ የግመል ቂጥ ተከታይ የነበረ ሕዝብ ባለቤት የነበረችው ሚጢጢዋ አረብ ለኦሮሙማው አገዛዝ አግዛ በተለይ ጥንታዊውን እስልምናና፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮችን ለማጥፋት ቆርጣ የተነሣች ብር ልቧን የደፈነባት ሀገር ናት።

"…ይህቺ ሚጢጢ ደፋር ሀበሻን አትንኩ የሚልውን የነቢዩአን ቃል ችላ በማለት ሀገሬ ላይ ቦንብ ማዝነብ ከጀመረች ውላ አድራለች። ይሕቺን ጥገበኛ፣ ደፋር የአረመኔ አራጅ ደጋፊ ነው ለንደን ላይ ሁለት የለንደን ፋኖዎች እንዲህ ብጥብጥ ያደረጓት።

"…ተመልከት ዐማራን፣ ተመልከተው ልቡን፣ ተመልከተው ድፍረቱን፣ ተመልከተው ይሄን ግልብ ብር ልቡን የደፈነው ዊጢምጢማም ዓረብ መግቢያ ሲያሳጣው? አንበሳ የለንደን ፋኖ። 👏👏👏

"…እንግዲህ እኒህ ሁለት ዐማሮች ዐረቦቹን ለንደን ላይ እንዲህ ብጥብጥ ካደረጉ ለንደን ላይ የሚኖረው በመቶ ሺ የሚቆጠር ዐማራ ቢወጣ ብላችሁ አስባችሁታል?

"…አሁን ዶናልድ ትራምፕን በደንብ መጠቀም ነው። የታረዱ የዐማራ ቄሶችና፣ የታረዱ የዐማራ ሼኮችን፣ ቤተ ክርስቲያንና መስጊድ በቪድዮ ማሳያት ነው። አሁን ወደ ኋላ ማለት የለም። ገፋ ማድረግ ነው። ይሄን ኢትዮጵያ ዐማራ ገድሎ ዋሽንግተን ለሾፒንግ የሚመጣ የብልፅግና አራጁ እንዲህ ማንቆራጠጥ ነው።

• እስቲ በማርያም… ለለንደን ፋኖ ለአፄ ቴዎድሮስ ልጆች አንደዜ ሞራል። 👏👏👏👏👏

ዘመድኩን በቀለ

09 Nov, 19:31


ተቀበል…6

"…ዐማራ እንዲህ ጥርሱን ነክሶ በባዶ እጁ ከቱርክ፣ ከሳዑዲ፣ ከኢራንና ከሳዑዲ አረቢያ በሚላክ የአቢይ አሕመድ ድሮን ጋር የሚዋጋው የሚሳፈጠው ለቄንጥ አይደለም። አሁን ተሰልፈህ ብትስቅበት፣ በቲክቶክ ስትሰድበው፣ ስትፎትተው ውለህ ብታድር መስሚያው ጥጥ ነው። ደንታውም አይደለም። አባቴ አሁን እሱ ጥርሱን ነክሶ፣ ወገቡን ታጥቆ ለይመለስ ተነሥቷል። የቀን፣ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው እንጂ እመነኝ ዐማራ ድብን አድርጎ በዝረራ ያሸንፋል።

"…አልሙት፣ አልፈናቀል፣ ደመከልብ አልሁን፣ አልዘረፍ፣ የዜግነት መብቴም የሕግ የበላይነትም ይከበር ብሎ በመጠየቁ እነ ትግሬው አባ ሰረቀ ሳይቀሩ "ዐማራ የሚባል ዘር የለም፣ ከዚያም ከዚህም ተለቃቅሞ የመጣ ልቅምቃሚ ነው ብለው ፍትህ ስለጠየቀ ብቻ ከፍ ዝቅ አድርገው በድፍረት አፋቸውን ሞልተው ሰደቡት። ተላገዱበት። ወዳጄ ያ "የለም" የሚሉትን ዐማራ ግን ቤቱ ድረስ ሄደው ሊያጠፉት ሲፈልጉ "ዐማራ የት ነው? ሂድ ወደ ክልልህ በማለት ሲጨፈጭፉት ይታያሉ። እንደ ጫጩት እኮ ነው የፈጁት። ይሄ አልበቃ ብሏቸው በሦስት ሳምንትም ሱሪውን እናስፈታዋለን ብለው ቤቱ ደጃፉ ድረስ ቢሄዱም ይኸው አጅሬው ዐማራ ለኅልውናው ሲል የእህቱን፣ የሚስት የእናቱን በግፍ መታረድ እያሰበ እንዲህ እንደከፍት እየነዳው ይገኛል።

"…የጊዜ፣ የቀን ጉዳይ ነው እንጂ ማርያምን ስልህ ዐማራው ድብን አድርጎ ያሸንፋል።

• እየኮመታችሁ…

ዘመድኩን በቀለ

26 Oct, 12:42


“…እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው።” 1ኛ ተሰ 5፥11

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

26 Oct, 12:42


ተቀበል…

"…በይፋ ተጀምሯል።

• ግጥም ስጡት… አልችልም አትበሉ። ሞክሩ። ማንም በእናቱ ሆድ ግጥም ተምሮ ለምዶ የወጣ የለም። ሞክሩ…

…ያዝ እንግዲህ…

ዘመድኩን በቀለ

26 Oct, 12:42


ተቀበል…
ሰይፉ ይልማ

እንደ ዥዋዥዌ ሆኗል ነገሩ፣
ካይሮና ዱባይ ነው ውሎና አዳሩ፣
UNን ሲጠጋ ብሪክስ ይታየዋል፣
ብሪክስን ሲጠጋ UN ይታየዋል
ወይ ደሞዝ አልጨመረ ወይ ዝም አላለን
በመንታ ምላሱ አርጎ አወናበደን።

እኔ

እሱ ግራ ገብቶት እኛን ግራቀኝ አጋባን 😂

ተቀበል!

ዘመድኩን በቀለ

26 Oct, 12:42


መልካም…

"…ዛሬ ዕለቱ ዕለተ ቀዳሚት ሰንበትም አይደል…? አዎ… እነደዚያ ነው። ቅዳሜ ከሰዓት ታዲያ በቤታችን በጉጉት በናፍቆት የሚጠበቅ ለየት ያለ መርሀ ግብር ነው ያለን። ግጥም፣ ቅኔ፣ ቀልድ፣ ነቆራ፣ ፉገራ የበዛበት ረሀ የሆነ መርሀ ግብር ነው።

• እሱም ምንድነው…?

ዘመድኩን በቀለ

25 Oct, 23:09


"…የሜጀር ጀነራል ውብአንተ ልጅ የሜጀር ጀነራል ውብአንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ተመስገን ውብአንተ አባተ ይናገራል።

"…ውብአንተ የተሰዋበትን የዐማራ ፋኖ በጎንደርን ለእስክንድር ነጋ አሳልፎ በመስጠት በፋፍዴን ቁጥጥር ስር ለማድረግ ለሚዳክሩት ለአባቱ ገዳይ አስገዳዮችም መልእክት አለው።

"…የጎንደር ፋኖ ለምን መስቀል በደረቱ ላይ አደረገ ብሎ እያበደ ያለው የጠንቋዩ ልጅ ፓስተር ምስጌም እንዲያዳምጠው ላኩለት። ፍናፍንቱ አያሎ መንበሬም ቢሰማው አይከፋም። የወልቃይት የሰሊጥ ቦለጢቀኞች ስሁላውያን የፖለቲካው ቅማንት ዐማራ መሳይ ጆፌ ዐሞራ የትግሬ ዲቃሎችም ቢሰሙት ይፈወሳሉ።

"…ሙሉውን መልእክቱን እሁድ ምሽት በመረጃ ቴቪ ሳምንታዊ የነጭ ነጫ ብርግራሜ ጠብኡኝ። በነገራችን የቲክቶክ ዐማሮች እያኮራችሁኝ ነው። አጀንዳ መቀበል ቀረ። የጠንቋይ ልጆች ፀረ ዐማሮቹ ማዕተብ በጣሾቹ እነ ምስጌ ተላልጠው አጀንዳ ብለው ይመጣሉ አዳሜና ሔዋኔ ኢግኖር ገጭቶ ጭራሽ አስደማሚ የዐማራ ታሪክ በቲክቶክ ሌክቸር ይኮሞኩማል። ይሄ ነው መብሰል። ይሄ ነው አንደኝነት። ይሄ ነው መቅደም።

"…በዐማራ ስም አጁዛው ሁሉ ቢንጫጫ አትስሙት። መርካቶ ተቃጠለ፣ እስክንድር ተነነ፣ አፍራሰ መነነ፣ ዋቅጅራ ጎፈነነ፣ አኪላ ቀረነነ፣ አያገባህም። ኢግኖር ግጨው። ወዳጄ የራስህን አጀንዳ ፈጥረህ እንደ ዶክተር ሀብታሙ፣ እንደ ጋሽ ተክሌ ፒፕሉን አንጫጫ። አለቀ።

"…ሌሊቱን ይሄን እየሰማችሁ እደሩ። የነገ ሰው ይበለንና ከምስጋናው በኋላ መንደራችን እንቀውጠዋለን።

"…አንተ የሞትክ ደግሞ ናና "ዘመዴ ዘመነ ሞቷል ያልከው እውነት ነው እንዴ?" ብለህ አዝገኝ አሉህ። የማትረባ። የእኔ ልጆች፣ ጓደኞች፣ ወዳጆች በቲክቶክ መቀሶች አጀንዳ መደንገጥ ሳይሆን መሳቅ ነው የጀመርነው።

• እየሰማችሁ በሰላም እደሩልኝ። 🖐🖐🖐

ዘመድኩን በቀለ

25 Oct, 16:40


መልካም…

"…ለእሁድ ምሽት የመረጃ ቴቪ መርሀ ግብሬ ካስቀረሁት በቀር ለዛሬ የራሴን ሓሳብ በርእሰ አንቀጽ መልክ ተንፍሼዋለሁ። ቀጥሎ እናንተ ደግሞ ለታሪክ የሚቀመጥ የበሰለ አስተያየታችሁን ትሰጡ ዘንድ ትጋበዛላችሁ።

"…ለወትሮ በምጽፈው ርዕሰ አንቀጽ ስር 😡 ብው ብለው ይናደዱ የነበሩ የፔጄ ላይ አልቅቶች በዛሬው ርእሰ አንቀጽ ላይ እንጥላቸው እስኪታይ 😁 ሲገለፍጡ ታይተዋል። የሆነው ሆኖ የሚበሳጨውም የሚገለፍጠውም ሰው ቁጥር መቀነሱ በራሱ ግቤን እያሳካሁ መሆኔን አመላካች ነው። ችክ ምንችክ፣ ድርቅ፣ ድፍር ብዬ መጋተቴም ጠቅሞኛል።

"…እንቀጥላለን። በትግራይና በመሀል ሀገርም የተደፈራችሁ፣ ግብረ ሰዶም የተፈጸመባችሁ ዲያቆናትና ሕጻናትም ለማይቀረው ቤተ ክርስቲያንን የማዳን የመጨረሻ መንፈሳዊ ዘመቻ ተዘጋጁ። የምስልና ድምጽ መረጃዎችም እንደአሰፈላጊነታቸው ይቀርባሉ። እነ አማኑም ደፈር በሉ። ቀልድ የለም።

“…እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥”ማቴ 24፥15። ቅድስት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምንም አትሆንም። ምንም አልኳችሁ። በአገዛዙ ድጋፍ ነውረኞች ቤተ ክርስቲያኒቱ አናት ላይ እየተጸዳዱ ስታዩም አትጨነቁ፣ አትገረሙ። ለጥቂት ጊዜ ነው።

"…ጥቂቶች ደንግጠው እምነታቸውን ሊቀይሩ ይችሉ ይሆናል። ስለ ውባንተ ሞት የተናገርኩትን ቪድዮ ቆራርጠው፣ ዘመነ ሞተ ትላላችሁና ላይሞት ነው እንዴ የተፈጠረው? የምለውን ቪድዮ ቆርጠው ለጥፈው እሱን አይቶ ማገናዘብ የማይችለውን ሲያስለቅሱት እንደሚውሉት ዓይነት ሰዎች ጥቂት የዋሆችን ሊሸውዱ ይችሉ ይሆናል። አበደን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ግን በሴረኞቹ እምብርት ላይ ሰንደቅ ዓላማዋን እየሰካች ጉዞዋን ወደፊት ትቀጥላለች። ይብላኝ ለወንድኛ አዳሪና ለዘራፊ ቀማኛ ሌቦች።

•1…2…3… ጀምሩ

ዘመድኩን በቀለ

25 Oct, 13:47


👆 ② ከላይኛው የቀጠለ… …በየቤታቸው ምሽቱን በመግባት እያንዳንዳቸውን ብፁዓን ሊቃነጳጳሳት በማስፈራራት ልክ እንዳገቧቸውም ነው የተሰማው። ለዚህ ነው እሁድ በማሰማችሁ የበቃሉ ንግግር ላይ ስምዎን ይናገሩ ብለው የሲኖዶሱ አባላት ሲጠይቁት በቃሉ ነኝ የቦሌ መድኃኔዓለም ዋና ጸሐፊ ብሎ ሲመልስ ሙሉ ጉባኤው ከፍ ባለ ድምፅ ያጉረመረመው። ትሰሙታላችሁ። ትናንት ግን የጉደሩ ዳዊት ሮቶ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ሆኖ ማምሸቱ ነው የተነገረው። አይ ጊዜ…

"…የምሽቱ የመንግሥትና የጋንግስተሮቹ ወከባ በዚህ መልኩ ከተፈጸመ በኋላ በማግሥቱ ተበዳዮች ድምጻቸው እንዳይሰማ በተከለከለበት ጉባኤ ላይ የጎንደሩ ስኳድ ግርር ብለን ገብተን ውሳኔውን ማስቀልበስ አለብን ብሎ በሀገረ ስብከቱ ስብሰባ ላይ በተናገረው መሠረት በዳዮቹ በአለቃቸው በብፁዕ አቡነ ሄኖክ ፈቃድ ግርር ብለው እንዲገቡ ተደርጎ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ላይ የስድብ መዓት ሲያወርዱባቸው መዋላቸው ነው የተሰማው። በትግሬዎች ዘንድ የተለየ ክብር የሚሰጣቸውና ሰሞኑን በወይዘሮ እጅጋየሁ ከበደ አፍ ሁላ ሲንቆለጳጰሱ የከረሙት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በፓትርያርኩና በምልዓተ ጉባኤው ፊት አንደዜ በጨዋ ደንብ ሌላ ጊዜ በነውጠኝነት ሲውረገረጉ፣ ሲዝቱ፣ ሲያስፈራሩ ሁሉ መዋላቸው ነው የተሰማው። እኔ የማሰማችሁ ትክክለኛ ጥያቄ የጠየቁበት የድምፅ ቅጂ ነው። በቀጥታ እኔ የደረሰኝ መረጃ ባይኖርም በሚዲያ ደረሰን ያሉ አካላት እንደተናገሩት እና እንደሰማነው ግን "ከዚህ በፊት ሥልጣነ ክህነታችንን ገፍፋችሁ፣ አዋርዳችሁ አባራችሁናል። በትግራይ ግን ያንን አላደረጋችሁም። አሁን ግን ያንን ማድረግ አትችሉም። አንፈቅድላችሁምም። እንዲያውም እኛ በተራችን እናንተን አባረን፣ ካስፈለገም አዲስ ፓትርያርክ መርጠን ልንቀጥል እንችላለን።" እስከማለት መድረሳቸው ነው የተነገረው። የአቡነ ሳዊሮስ ሹመኛው አቡነ ኤጲፋንዮስም "ዱላ ልንማዘዝ ሁላ ስለምንችል ተጠንቀቁ" እስከማለት መድረሳቸው ነው የተነገረው። ይሄ ሁላ ሲሆን ሊቃነጳጳሳቱም፣ የስብሰባው መሪ ቅዱስ ፓትርያርኩም ሆነ በብፁዕ አቡነ አብርሃም ምትክ ጉባኤውን እንዲመሩ የተመደቡት አባ ያሬድ ሊያስቆሟቸው አልሞከሩም ተብሏል።

"…በጉባኤው ላይ ባለፈው የኦሮሚያ ቤተ ክህነትን በመክፈል የተወገዙትና ኋላ ላይ በይቅርታ የተመለሱት ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ፦ እናንት ተከሳሾችም ልክ እንደ ከሳሾቹ በመረጃ ስጡን። "በቃል ያለ ሳይሆን በጽሑፍ መረጃው ይሰጠን። እሱን አይተን ነው መፍረድ የምንችለው እንጂ እንዲሁ በቃል ብቻ ሰምተን መፍረድ የለብንም" ያሉ ሲሆን አቡነ ሳዊሮስም "የአቡነ ዜናማርቆስን ሓሳብ በመደገፍ እናንተም በቃል ሳይሆን ሰነዱን ስጡን እና አይተን እንፍረድ በማለት መልስ ሰጥተዋል። አቡነ ማርቆስም፣ ትናንት የቀረበውም ቢሆን ተከሳሾች ባልነበሩበት መቅረብ እንዳልነበረበት ተችተው አሁንም ተከሳሽ በሌለበት ከሳሽ ብቻ መደመጥ የለበትም። ሁለቱም ቀርበው ብለው ጠይቀዋል። ይጠየቁ። አቡነ ኤርሚያስም ተመሳሳይ ሓሳብ አንጸባርቀዋል። አቡነ ሉቃስ ደግሞ እኔ ጥያቄ ያለኝ ለእናንተ ነው በማለት ማፍያውን ግሩፕ የጠየቁ ሲሆን "ሁላችሁም ወጣ የተባለውን ሕግ አምርራችሁ ስትወቅሱት አይቻለሁ። እንደ እናንተ አበባል መተዳደሪያ ደንቡ ነው ጥፋተኛ ወይስ ከሕጉ ውስጥ ይሄና ያ አንቀጽ ይሻሻልልን የምትሉት አለ? ብለው የጠየቁ ሲሆን በግሩፑ በኩል የተሰጠ ምላሽ አልነበረም። በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ አብርሃም፦ ለቀረበባቸው፣ ስድብ፣ ዛቻ፣ ዘለፋ አመስግነው ከሳሾቹ በሚቀጥለው ሲመጡ እንደ ቤት ሥራ ይዘው እንዲመጡ በአደባባይ በግልጽ ጥያቄ አቅርበዋል። "በእኔ ሥልጣን፣ በእኔ ፊርማ የእኔ የቤተሰብ አባል የተባለ በቃልም ይሁን፣ በጽሑፍ ቅጠሩ ብዬ ያዘዝኩት፣ የቀጠርኩት ካለ ይዛችሁ እንድትመጡ። ሌላው አላወቅነውም፣ ከሚዲያ ነው የሰማነው የምትሉትም የመዝገብ ቁጥር ይዞ፣ ቀንና ማኅተም ያረፈበት ደብዳቤ አልደረሰንም የምትሉም ከሆነ ይዛችሁ አቅርቡ። በተረፈ ለዛቻችሁና ማስፈራራቱ ቦታም አልሰጠው፣ ፍርዱንም ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ በማለት ንግግራቸውን ፈጽመዋል።

"…ብፁዕ አቡነ አብርሃምም ያ ብዙ ጊዜ በሁሉ ዘንድ የሚደነቅላቸውንና በሁሉም ዘንድ የሚታወቁበትን ስሜትን በመቆጣጠር ሁሉን እንደ አመጣጡ የማሳላፍ ፀጋቸውን በመጠቀም የትናንቱንም የትግሬዎቹን እና የኦሮሞዎቹን የተደራጀ አስደንጋጭ ሱናሚ የመሰለ የቁጣ ማእበል በትእግስታቸው ገስጸው በትህትና ማሳለፋቸው ነው የተነገረው። እኔ ባልሰማውም ለብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በሰጡት የዛቻ የማስፈራራት መልስም "ግድ የለም የሚሰነብተውን እግዚአብሔር ያውቃል" በማለት ጉባኤውን ፀጥ ማሰኘታቸውም ነው የተሰማው። በነገራችን ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከዚህ በፊት መርካቶ ራጉኤል አስተዳዳሪ በነበሩ ጊዜ ራጉኤሎች የሸሏማቸውን ወርቆች ለእኔ አይገባም በማለት በወቅቱ ፓትርያርክ ለነበሩት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እንደሸለሙ ይነገራል። አሜሪካ ተመድበው ሳለም ብፁዕ አቡነ አብርሃምና ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በአስቸኳይ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ በቅዱስ ሲኖዶሱና በወቅቱ ፓትርያርክ በነበሩት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲታዘዙ፣ ኦሮሞው አቡነ ኤውስጣቴዎስ አልመለስም ብለው በዚያው ሲቀሩ ዐማራው ብፁዕ አቡነ አብርሃም ግን "ይሄን ሥልጣን የሰጠችኝ እናት ቤተ ክርስቲያን ናት፣ ወደዚህም የላከችኝ እሷው ናት፣ አሁንም ተመለስ ያለችኝም እናት ቤተ ክርስቲያን ናት። እናም ተመልሼ ሄጄ እሷ ይመጥንሃል ብላ በመደበችኝ ቦታ እሠራለሁ በማለት ብዙዎች ወቅቱ ጥሩ አይደለም ወደ ሀገር ቤት አይሂዱ፣ አይመለሱ ቢሏቸውም እምቢኝ ብለው ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ቁርጠኛ የቤተ ክርስቲያን አባትም ናቸው። አቡነ አብርሃም ወደ ሀገር ቤትም እንደተመለሱ በወቅቱ ምሥራቅ ሐረርጌ የተመደቡ ሲሆን በዚያም የልማት አርበኝነታቸውን አስመስክረው ኋላ ላይ አሁን ወዳሉበት ወደ ባሕርዳር ሀገረ ስብከት ተመድበዋል። እነ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስም በዝሙት ምክንያት ከተባረሩባት ሀገረ አሜሪካ ኦነግ ወደ ሀገር ቤት ሲገባ ከኦነግ ጋር አብረው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው ገብተዋል። ከገቡም በኋላ የኦሮሚያ ቤተ ክህነትን በመቋቋም የጨረቃ ጳጳሳትን በመሾም በኦሮሚያ የብዙ ክርስቲያኖችን ደም አስፈስሰዋል። ቅዱስ ሲኖዶሱም ዘመኑ የኦሮሞ ነውና በማለት ለአቡኑ በውግዘት የተያዘውን ሥልጣነ ጵጵስናቸውን ከነሙሉ ክብሩና ማዕረጉ መልሶላቸዋል። አሁን ደም አስፈሳሹ ሊቀጳጳስ ምእመናንና ካህናትን እያቆረቡ፣ ሥልጣነ ክህነትም እየሰጡ ዘና ፈታ ብለው ደመ ወዛቸውን እየበሉ ፈታ፣ ዘና ብለው ይኖራሉ።

"…በመጨረሻም ከጉዳዩ ጋር በምንም መልኩ በማይገናኝ ሁኔታ ለብቻቸው ያስቀሯቸውን ብፁዕ አቡነ አብርሃምን አቡነ ሳዊሮስ ምን እንደተሰማቸው ባይታወቅም መልሰው ከአቡነ ሄኖክ ጋር ታረቁ ብለው አሪፍ ካርታ ይዘው ቢመጡም ብጹዕ አቡነ አብርሃም ግን እኔ የተጣላሁት ሰው የለኝም። እኔ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠኝን ሓላፊነት ነው በሕግና በመመሪያ እያስፈጸምኩ ያለሁት በማለት ነገሩን በተለመደው ትእግስታቸው በማሳለፍ ዛሬም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ክብር እንደ ቀድሞው ከግል ስሜት በጸዳ መልኩ ማስከበራቸው ነው የተሰማው። በብዙ ነገር ብበሽቅባቸውም በፅናታቸው ግን መደመሜን መካድ አልችልም። ነገሩ በዚህ ከተቋጨ እንግዲህ እኔ ዘመዴም አጥፊዎች በዚህ መልኩ ተደራጅተው ባለጊዜነታቸውን ማሳየት ከቻሉ፣…👇 ② ከታች ይቀጥላል…

ዘመድኩን በቀለ

25 Oct, 13:47


👆③  ከላይኛው የቀጠለ… …ዛሬ ምንም ለውጥ ባናመጣ እኔም እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነቴ በቀጣይ በቴሌቭዥንም ሆነ በቴሌግራም ገጼ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን ነውር፣ ዘረፋና ሌብነት፣ ሴሰኝነትም ሁሉ ለታሪክ ይቀመጥ ዘንድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ እጀምራለሁ። የሰው ልጅ እንዴት እንደሚሸጥም አሳያችኋለሁ። ሌሎች ሌሎች ነውሮችንም በይፋ በማቅረብ ሰው ባይቀጣቸው፣ እነሱ ባይፈሩ፣ ባያፍሩ ወዳጅ ዘመድ ያፍርባቸው ዘንድ በይፋ እንተጋተጋለን። ጥቂቶች እንዴት ምእመናን በሚሰጡት የሙዳየ ምጽዋት ገንዘብ በሸነና እንደሚሉ፣ ግንባታቸውን ሁሉ ከነ ሞዴላ ሞዴል መኪኖቻቸው እንደመምባቸዋለን። ትግሬና ኦሮሞ ገጥሟል። ዐማራ ፈዝዟል። እሱንም እናያለን።

•ትግራ -አክሱም

"…በትግራይ ከማእከላዊው መንግሥት የተገፋውን ህወሓትን ተከትሎ ጫካ ገብቶ የነበረው የትግራይ ቤተ ክህነትም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በይፋ መለየቱንና የራሱን የጨረቃ የጨበራ ሲኖዶስ ማቋቋሙንም በትናንትናው ዕለት በይፋ አሳውቋል። በኦሮሚያ አጋሮቻቸው ቀድሞ የተነሣውና ለጊዜው ደም አፋስሶ ሴራው የከሸፈበት ቡድን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን እቅፍ ከተመለሰ በኋላ በዚያው በኦሮሚያው መንገድ ሄዶ የጳጳሳት መዓት በመሾም በትግራይ እንደ አሸን ያፈላውና ያፈሰሰው የትግሬው ከሳቴ ብርሃን መንበረ ሰላማ ቡድን እነ አባ ሰራቂን የመሰለ የኢትዮጵያና ዐማራ ጠል መናፍቅ ፀረ ማርያም ግለሰቦችን ይዞ የራሱን የትግራይ ሲኖዶስ ማቋቋሙን በመግለጫ ጭምር አረጋግጧል። ይሄ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን "ጣልቃ ገብነቷን ታቁምልኝ" ሁላ ብሎ ሲወበራና ትኩረት ፍለጋ ሲላላጥ ውሏል።

"…በፖለቲካው ቢሮክራሲ በኩል ከሀገረ ኢትዮጵያ ያልተገነጠለችውና አሁን ድረስ በጀት ከማዕከላዊው መንግሥት የሚመደብላት፣ ስልክና ባንክ፣ መብራትም፣ ደሞዝም ጭምር ከኢትዮጵያ የሚላክላት፣ ያለ እርዳታ ሕዝቧ መላወስ መቆየት የማይቻላት፣ ትርፍ አምራች ያልሆነችውን ትግራይን በሃይማኖቱ በኩል አዲሶቹ የትግራይ የጨረቃ ጳጳሳት ከፖለቲከኞቹ በፊት አስቀድመው በይፋ ትግራይን እንደ ሀገር በመቁጠርና በመጥራት በይፋ ከኢትዮጵያ መገንጠሏን እና መለየቷን ዐውጀዋል። ይሄን የሚቃወም አንድም የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ፣ የዋናው ሲኖዶስ ድምጽ የለም። ኦሮሞዎቹ ላይ እንደተያዘው አቋም በእነዚህኞቹ ላይ ግን አልተያዘም። እነ አቡነ ሳዊሮስ በአንድ በኩል እውነት አላቸው። የሚያስቀው ነገር ትግራይ ቤተ ክህነት ተብሎ በተቋቋመው አካል በኩልም አሁንም ድረስ ደሞዝ ከአዲስ አበባ የሚበሉ፣ እዚህ አዲስ አበባም ሆነው ደሞዝ የሚበሉ፣ ሁለት ቤት ያላቸው ሰዎች መኖራቸው ነው። ዐማራ ጉራጌ እና ሌላው ኦሮሞ ወላይታው በሚያዋጣው የሙዳየ ምጽዋት ገንዘብ እነ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ መሻኮታቸው ሳያንስ የትግሬ ነፃ አውጪዎችና ኦሮሞዎቹ በሃላል ሲራኮቱ እንደማየትም የሚያሳፍር ምን ነገር አለ? ቆይ ግን ምጸዋት መስጠቱ ቢያቆም ምን ሊውጣቸው ነው? ለካህናቱ የንስሀ ልጆቻቸው ደሞዝ እየከፈሉ ብሩ ቤተ ክህነት ሳይገባ አገልግሎቱ ቢቀጥል በምን ሊደባደቡ ነው? አስቂኝ እኮ ነው።

"…ይሳካላቸው አይሳካላቸው ባላውቅም ትግሬዎቹ እና ኦሮሞዎች አዲስ ሀገረ ግንባታ ላይ እንደሆኑ ይሰማኛል። በትግሬና በኦሮሞ ፅንፈኞች በኩል የሚታየው፣ የሚሰማውም ኢትዮጵያ ጠልነት፣ ሰንደቅ ዓላማ ጠልነት ወዘተ የመሳሰሉት ነገራት እየታዩም ቢሆን ዐማራውም ሌላውም ሕዝብ በዝምታ በአርምሞ መመልከቱን ቀጥሏል። የጎንደሩ ፀረ ዐማራ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ፣ የፖለቲካው አገው ሸንጎ አፍቃሬ ኦሮሞ ወትግሬ ዲቃላው አገው ሸንጎ ዐማራውን እንደ ነገድ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደተቋም በሁለመናው ሽባ አድርገው ለአስገድዶ መደፈር እያዘጋጁ ይገኛል። በሩሲያና በዩክሬን ጦርነት እየተጎዱ ያሉት ኦርቶዶክሳውያኑ ናቸው። በሶሪያ ጦርነት የወደሙት ኦርቶዶክሳውያኑ ናቸው። በኢትዮጵያም ታርጌት የተደረገችው ታላቋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት። በጁንታው ጦርነት ከትግሬም፣ ከዐማራም የተፈጁት ኦርቶዶክሳውያኑ ናቸው። ደፈር ተብሎ መወያየት ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ካልተጀመረ ነገርየው ደስስ አይልም። ትግሬው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስና ኦሮሞው አቡነ ሄኖክ እኮ ቅዱስ ሲኖዶሱ የሚያነሣን ከሆነ አዲስ አበባን ይዘን እንገነጠላለን እስከማለት የደፈሩት ከኋላ የልብ ልብ የሚሰጣቸው ፀረ ኢትዮጵያ ኃይል ስላለ ነው።

"…እደግመዋለሁ ጳጳሳቱ ሁላ የሚጣሉት በምእመናኑ የአስራትና የሙዳየ ምጽዋት ብር በስለት ገንዘብ ጭምር ነው። ጠላ ጠምቃ፣ እንጨት ተሸክማ፣ አረብ ሀገር ተቃጥላ፣ ጉሊት ሽጣ፣ ከመንግሥት ደሞዙ፣ ከንግድ ሥራው ከልጆቹ ሆድ ቆጥቦ ለእግዚአብሔር በሚሰጠው ብር እኮ ነው እንዲህ የሚፎገሉት። እንዲህ የሚተራመሱት። ዘግናኝ ነው። የሲሲሊ ማፍያዎች እንኳ እንዲህ ጨካኝ ናቸው ማለት ያስደፍራል። ሦስት፣ ሁለት ቦታ ደሞዝ የሚበሉ። የቤተ ክርስቲያን መሬትና ሀብት በድፍረት የሚሸጡ፣ ቤተሰቦቻቸውን በየቦታው የሚቀጥሩ። ታሞ በፈቃድ ላይ ባለ ካህን ምትክ ሞቷል ብለው ማስታወቂያ አውጥተው የሥራ መደቡን በቁሙ የሚሸጡ፣ በዝውውር ሰበብ ሚልዮኖችን የሚሰበስቡ፣ ለቤተ ክርስቲያን ይሰጥልኝ የተባለ ኮንዶሚንየም ቀርጥፈው ሽጠው የሚበሉ፣ የራሳቸው ሙዳየ ምጽዋት ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ላይ አስቀምጠው በኪሳቸው የሚያስገቡ፣ የሥዕለት ብርና ወርቅ ተሸክመው ወርቅ ቤት ለወርቅ ቤት ለመሸጥ የሚዞሩ። ባለ ፎቆች፣ ባለ ቪላዎች፣ ባለ ዘመናዊ የሚልዮን ብር የመኪና ባለቤቶች ሁሉ የሚጋደሉት በሙዳየ ምጽዋት ብር መሆኑ ነው።

"…የሚገርመው ግን ሁሉም ጤና የላቸውም። በቤታቸው ሰላም የላቸውም። ብሩን ዘርፈው አከማችተዋል ጤና ስለሌላቸው ግን ሀኪም እና ኪኒና ላይ ይጨርሱታል። የሙዳይ ምጸዋቱን ብር አይን አይኑን እንዳዩት ሳይበሉም፣ ሳይነኩትም እንዲሁ እንደ ጓጉ ያልፋሉ። ያርፋሉም። ሁሌ መድኃኒት እንደቃሙ ነው። መርፌ እንደተወጉ ነው። ችግር ድኅነት በስፍራው ላይ እንዳስቀመጣቸው ያውቃሉና ለሃይማኖት ብዙም ግድ የላቸውም። ዘወትር የቴዲ አፍሮን ካሴት እያስከፈቱ እያንጎራጎሩ የሚሄዱ አባት ቢያንስ አንድ ሃይማኖቱን የሚንቅ፣ ኋላም የሚመነፍቅ ነፍስ አፍርተዋል። አሁን ይሄን ሹፌር ዘፈን ኃጢአት ነው ብትሉት በምን ይሰማችኋል። እኒህ ሲሞቱ ወራሻቸው ሌላ ነው። የማይወልዱት፣ የማያገቡት፣ ሞቻለሁ ብለው የተገነዙት ገንዘቡን አከማችተው ይዘው በህጋዊ ጋብቻ በተቀደሰ ትዳር ልጅ አፍርተው የሚኖሩትን የካህናት ኑሮ አመሰቃቅለው፣ አመድ፣ አፈርም በትነውበት የሰበሰቡትን ብር ሳይበሉት ሴት ወይዛዝርቶች ተከፋፍለውት ያርፋሉ።

"…እኔ የምሰጋው፣ የምፈራውም በትግሬዎቹ አባቶች ጋጠወጥነት እያሳዩ ባለውም ድፍረት የተነሣ ዐማራውም እንደ ትግሬዎቹና ኦሮሞዎቹ ተማርሮ፣ መሰደብ፣ መገፋቱ በዝቶ፣ እኔም የራሴን ሲኖዶስ እመሰርታለሁ እንዳይል ብቻ ነው። አገዛዙም እየሠራ፣ እያበረታታ ያለውም እሱን ነው። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በማስተሳሰር ከከረሙት ገመዶች መካከል ሁሉም ተበጣጥሶ አሁን የቀሩት በዋነኝነት ሁለት ናቸው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናቸው። አየር መንገዱም እየተንገታገተ አለ። ቤተ ክርስቲያኒቱም በትግሬና በኦሮሞ ፅንፈኞች እየተወቀረች አለች።

• ለዛሬ ይብቃኝ…!

•••

ሻሎም.!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ጥቅምት 15/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

ዘመድኩን በቀለ

25 Oct, 13:47


"ርእሰ አንቀጽ"

"…በትናንትናው ዕለት በኢትዮጵያ በትግራይ እና በአዲስ አበባ ሁለት ገራሚ ለአቅመ አጀንዳነት የሚበቃ ዜናዎች ሲንሸራሸሩ ውለዋል። የአዲስ አበባው የጉልበተኞች፣ የአገዛዙ ማፍያ ካድሬዎች፣ ዘመን መጣልኝ፣ አኬር ቆመልኝ ባይ ባለጊዜዎች በአምስት ኪሎ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጊቢ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ የታየ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በትግራይ አክሱም ከተማ ራሱን አቴንሽን፣ ትኩረት ፍለጋ የሚያላልጠው የትግሬው "መንበረ ሰላማ" ወደ ሲኖዶስነት አድጌአለሁና ሀገር ይወቅልኝ ብሎ ሲንበጫበጭ የዋለበት ነው። ሁለቱንም በስሱ ለማየት እንሞክራለን። ሙሉ የድምጽና የምስል መረጃዎችን በዕለተ እሁድ ምሽት 2:00 ሰዓት ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር የመረጃ ቴሌቭዥን መርሀ ግብሬ ላይ ይዤላችሁ እቀርባለሁ። አሁን ከአዲስ አበባው እንጀምር።

"…ጥቅምት 12/2017 ዓም በጸሎት የተጀመረው የወርሀ ጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ አዲስ ቅጥር፣ የሠራተኞች እድገት እና ዝውውር፣ ከመደበኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ ሌላ ወጪ እንዲቆም በመወሰን፦1.ቡፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ 2.ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስና 3.ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ ከ4 ተጨማሪ ሊቃውንት ጋር በመሆን ችግሩን በዝርዝር በማጥናት ለግንቦት የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ እንዲያቀርቡ በመወሰን የዕለቱን ስብሰባ ማጠናቀቁም ተነግሯል። ትናንት በቪድዮ የተደገፈ የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ከቀረበ በኋላ በእንባ፣ በቁጭት፣ በንዴት ሲላቀሱ ያመሹት ብፁዓን አባቶች መሽቶ ከነጋ በኋላ በዛሬው ዕለት በዝምታ ተውጠው ማሳለፋቸው ተሰምቷል። ዛሬ ለሲኖዶሱ መልስ እንሰጣለን ብለው በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የሚመራ 19 የሀገረ ስብከቱ ሰዎች ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደሄዱ የተነገረ ሲሆን 19ኙም ቢገቡ ቦታም ስለማይበቃ ተብሎ 14ቱ እንዲገቡ እንደተፈቀደላቸውም ተሰምቷል።

"…ከ7 ክፍለ ከተማ የተሰበሰበ ከቤተ ክህነቱ የወለድ ተቀማጭ የተወሰደ ነው የተባለ 20 ሚልዮን ብር ወጪ አድርገው ምሽቱን በየሊቃነ ጳጳሳቱ ቤት እየዞሩ ብር ለሚያስፈልጋቸው አባቶች ሲበትኑ እንዳመሹ የሚነገርላቸው የአዲስ አበባው የሀገረ ስብከቱ ማፍያ ቡድን በቦሌ ክፍለ ከተማው ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሩፋኤል አስተባባሪነት፣ በጎደሩ ባለ ጊዜ ኦሮሞ ነኝ ባይ ዳዊት ሮቶ፣ በሀገረ በቀለ፣ በሥራ አስኪያጁ የማነ፣ በቦሌ መድኃኔዓለሙ ስኳድ በበቃሉ እና በሸጎሌ ኪዳነ ምሕረቱ አለቃ አማካኝነት በግንባር ቀርበው ለቅዱስ ሲኖዶሱ ምላሽ መስጠታቸውን የደረሰኝ ሙሉ የድምጽ መረጃ ያመለክታል። ድሮ ድሮ በሁሉ ቦታ በእድር ዳኝነት፣ በታክሲ ተራ አስከባሪነት ሁሉ ከፊት ትግሬ ይቀድም እንደነበረው ሁሉ አሁን ደግሞ ጊዜው የኦሮሞ ነው በሚል ሁሉን የመቅደም መብት ለኦሮሞ ነኝ ባይ በመሰጠቱ በዚሁ አግባብ ከሁሉ ነገር ፊት ከፊት የሚቆመው ባለ ጊዜ ነኝ ባዩ የጉደሩ ዳዊት ሮቶ በድፍረት አፉን እየከፈተ እንደ ብራቅ በብልግና ጠባይ ሲጮህ መዋሉ ነው የተሰማው። አጀንዳው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ላይ የቀረበን የሙስና ጉዳይ አጣርቶ እንዲያቀርብ በሲኖዶሱ የተወሰነ ጉዳይ ቢሆንም ጋንግስተሮቹ ግን ወቅቱ ዐማራን የመውቀሻ፣ ከዐማራም ጎጃም ዐማራን የማዋረጃ ዘመን ነውና እንጠቀምበት በማለት በማይመለከታቸው ጉዳይ ባህርዳርን ከተማንና እና ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ሲያዋክቡ መዋላቸው ነው የታየው። በበቀደም ዕለቱ የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ላይ ይታይ በነበረው ዶክመንተሪ እና የተጎጂዎች ምስክርነት በቪድዮ እያዩ ሲያለቅሱና ሲያዝኑ የነበሩት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም በትናንትናው ዕለት በነበረው የጋንግስተሮቹ የመልስ ምት ወቅት አንደበታቸው እንደ ዲዳ ተለጉሞ፣ በአርምሞ ጸሎት ላይ እንዳለ ባሕታዊ በዝምታ ተውጠው እንደ ቆረበ ሰው አፋቸውን ሸፍነው ማሳለፋቸው ነው የተነገረው። የተሰማውም።

"…በግንቦቱ ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ እነ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል "በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰው እየተሸጠ ነው። ሙስናው ዘግናኝ ነው። ይሄ መንፈሳዊ ጉባኤ አንድ ውሳኔ ወስኖ ይውጣ" ብለው ሁሉም በሊቀጳጳሱ አቤቱታ ላይ ስምም ሆነው አጀንዳውን ለመያዝ ፈቃደኝነታቸውን ሲያሳዩ በወቅቱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ነበሩ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን የሥራ አስኪያጅነት ሥልጣናቸውን ተጠቅመው በአቡነ ሄኖክ የሚመራውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጉዳይ "ሌላ ጊዜ እናየዋለን፣ አሁን በሌሎች አጀንዳዎች ላይ እንነጋገር" በማለት በአጀንዳው ላይ ቀዝቃዛ ውኃ ቸልሰው የሀገረ ስብከቱን መከራ እንዲራዘም ያደረጉት። ትናንት ግን ብፁዕ አቡነ አብርሃም ብቻቸውን ቀሩ። የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በተጀመረ ዕለት ብፁዕ አቡነ ሄኖክ "ቅራኔ ስላለን" ብፁዕ አቡነ አብርሃም ጉባኤውን መምራት የለባቸውም። ጉባኤውን ቅዱስ ፓትርያርኩ ራስዎ ይምሩት ብለው ተቃውሞና ግርግር በማንሣታቸው ምክንያት ቅዱስ ፓትርያርኩም እኔ አርጅቻለሁ፣ ከመሩም ሥልጣኑ የአቡነ አብርሃም ነው። እንዴ ለምን ብለው? ለመሟገት ቢሞክሩም ጫናው ስለበዛ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከጉባኤው መሪነት እንዲገለሉ ተደርጎ በምትካቸው ቅዱስ ፓትርያርኩና አባ ያሬድ ጉባኤውን እንዲመሩ መደረጉም ነበር የተሰማው። ትናንት ግን የባሰ ባይተዋርነት እስኪሰማቸው ድረስ ሲዘለፉ መዋላቸው ከምር ብዙዎች ከጉባኤው በኋላ በግሌ ነግረውኛል። ለእኔ የምትነግሩኝን ለምን እዚያው አትናገሩም ስላቸውም "እዚያ ለመናገር ደግሞ ሌላ ችግር አለ" ነው መልሳቸው የብዙዎቹ።

"…ከትግራዩ ጦርነት መልስ በተካሄዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ስበሰባዎች ላይ አቡነ አብርሃምን በግልጽ ፋኖ፣ ሌሎች ከዐማራ ወገን የመጡትንም በማንነታቸው በማሸማቀቅ ይታወቁ የነበሩት የጋምቤላው ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በትናንትናው ጉባኤ ላይ በአንፃራዊነት የሰከኑ እንደሆነ ሲነገር፣ በእሳቸው ምትክ ኦሮሞዎቹ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከኦሮሞም የደራ አማራው እና በቅርቡ ኦሮሞ ነኝ ብለው በኦሮሙማ የተጠመቁት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በጨረቃ ጵጵስናው ወቅት ሾመዋቸው ዕርቅ ሲፈጸም ውግዘታቸው ተነሥቶላቸው በፖለቲካዊ ውሳኔ ጵጵስና የተቸራቸው አዲስ ገቢዎቹ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ እና አቡነ ኤጲፋንዮስ ሲወበሩ መዋላቸው ነው የተሰማው። ከስብሰባው ቀደም ብሎ የኦሮሙማው የፌደራል ፖሊስ አዛዥ መርደረሩ ደምመላሽ ገብረ ሚካኤል ብፁዓን ሊቃነጳጳሳቱን ተራ በተራ ወደ ቢሮው እያስጠራ የሰው መሸጥ፣ መለወጥ፣ የባርያ ንግድ ክስ የቀረበባቸውን የወለጋ ተወላጁን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከቱን ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክን ለማንሣት መሞከር ክፉኛ ከመንግሥት ጋር እንደሚያጣላቸው መናገሩና ማስፈራራቱም በሌሎች ሚዲያዎች ተዘግቦአል።

"…ይሄ ማስፈራሪያ በቂ አይደለም ያሉት የደቡብ ጎንደሩ የስኳድ ተወካይና የቦሌ መድኃኔዓለሙ ዋና ጸሐፊ አቶ በቃሉ ልክ በዘመነ ህወሓት ጊዜ ህወሓት ታደርገው እንደነበረው ሁሉ አሁንም እንደዚያው ማድረግ ይኖርብናል። ጳጳሳቱ ሲበዛ ራስወዳድና ፈሪ ናቸው፣ አንዳንዶቹ ልጆች አሏቸው፣ ለልጆቻቸው ሲሉ በሕይወት መቆየት የሚፈልጉ አሉ። በድህነት የኖሩ ስለሆነ አሁን ካሉበት የምቾት ዞን ሊወርዱ አይፈቅዱም። እምነት ያላቸው ጥቂቶች ናቸው። እናም በየቤታቸው ተገብቶ ፈሪውን በማስፈራራት፣ ደካማውን በማሸማቀቅ፣ ተገዳዳሪውን ከ20 ሚልዮኑ ላይ በመቦጨቅ፣ በጣም አክራሪውን ከፍ ሲል በመጎሸም ልክ እናግባቸው በማለት ከኦሮሞ ደኅንነቶች ጋር በዋዜማው…👇 ① ከታች ይቀጥላል…

ዘመድኩን በቀለ

25 Oct, 12:49


መልካም…

"…በምዕራብ ሸዋው ማፍያ በጉደሩ ባለ ጊዜ በራሱ አነጋገር "ደፋር መደዴው" ዳዊት ሮቶ እጅ የወደቀችው የዘመናችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በትናንትናው ዕለት የነበረውን የቅዱስ ሲኖዶስ ሲያንቀጠቅጡ የዋሉበትን ሙሉ የድምፅ ሪከርድ እየሰማሁ ነበር ከትናንት ምሽት ጀምሮ ስደመም የቆየሁት።

"…ያ መንፈስ ቅዱስ ይመራዋል ብለን ትናንትም፣ ዛሬ አሁንም፣ ነገም የምናምነው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በተራ ማፍያና የዱርዬ ስብስብ እንዲህ ውጥንቅጡ ወጥቶ የጨበራ ተስካር ሲመስል እንደማየት የሚያቆስል፣ የሚያም ነገር ግን የለም። ከምር እኔ በጣም ነው ያዘንኩት።

"…ደርግ በመግደል፣ በመውረስ፣ ወያኔ በመክፈል፣ በመደብደብ፣ በመግደል፣ በመዝረፍ ያስቀጠለችውን ታላቋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማጥፋት ሴራ አሁን ደግሞ በአሕዛብና በመናፍቃን ጥርቅሙ ፀረ ኢትዮጵያ፣ ፀረ ኦርቶዶክሱ ኢሊዩሚናቲ የኦሮሞ ብልፅግና በሃላል እንዲህ ተዋርዳለች።

"…እኔ በድምጽ ባለኝ መረጃ በትናንቱ የማፍያዎቹ ድንፋታ ላይ ብፁዕ አቡነ ዜናማርቆስ፣ አቡነ ሳዊሮስ፣ አቡነ ኤልያስ የአርባ ምንጩ፣ አቡነ ኤርሚያስና ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ሚዛናዊ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። ከሳሽም፣ ተከሳሽም ይቅረብ፣ ከሳሾች ትናንት በመረጃ፣ በማስረጃ እንዳቀረቡት ሁሉ ተከሳሾችም እንዲህ በጩኸት፣ በግርግርና በቃል ሳይሆን በጽሑፍ፣ በሰነድ መረጃቸውን ያቅርቡ ሲሉ ነው ያደመጥኳቸው።

"…ብፁዕ አቡነ አብርሃም በተለየ መልኩ በተቀደሰው ጉባኤ ፊት በማንም ሰካራም ዱርዬ ሲሰደቡ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ ለማስቆም አለመሞከሩን ስታዩም ታዝናላችሁ። ብፁዕ አቡነ ሄኖክን ለመከላከል ብፁዕ አቡነ አብርሃምን በቦሌው ጸሐፊ በጎንደሩ ስኳድ በበቃሉ አፍ በሲኖዶሱ ፊት ማሰደብ ግፍም፣ ነውርም ነው።

• ርእሰ አንቀጽ ይቀጥላል… እናንተስ ግን ዝግጁ ናችሁ አይደል…?

ዘመድኩን በቀለ

25 Oct, 09:46


“…አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይደለምን? ” 1 ዜና 22፥18

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

ዘመድኩን በቀለ

24 Oct, 20:28


አሁንም ጥያቄ ነው…?

"…ጎንደር ደባርቅ ከተማ ዲዲቲ መርዝ ጠጥተው፣ እየተሰቀሉ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል የሚል ዜና አንብኤላሁ። አዲስ አበባም ከካድሬ በስተቀር ሌላው የአእምሮ ታማሚ ይበዛዋል፣ አማኑኤል ሆስፒታልም ታካሚው ከአቅሜ በላይ ነው እያለ ነው። ሁሉም እየዬ እያለ ነው።

"…በመርካቶም ቢሆን ኦሮሞውም፣ ጉራጌ፣ ዐማራና ትግሬ፣ ብሔር ብሔረሰቡ ሁላ ነው ገሚሱ ነግዶ፣ ገሚሱ ተሸክሞ፣ ገሚሱ ደልሎ፣ ሌባውም በለስ ከቀናው ሰርቆ ሆዱን ሞልቶ የሚኖርባት። እና መርካቶም ከወደመ። በክፍለሀገርም ተዟዙሮ መሥራት ካልተቻለ ምን ተሻለ?

"…እንደ ትግሬ በጅምላ አንዴ በመቶ ሺም ተገድለህ፣ እንደ ዐማራ በቁጥቁጥ በድሮን በወታደር ተጨፍጭፈህ፣ ከቤትህ፣ ከቀዬህ ተጠርገህ፣ በቁጥቁጥም ሞተህ፣ ተገድለህ ምኑ ነው የሚያስፈራው? መዋጮ አልሰጥ ካልክስ ምንድነው የሚያደርጉህ? ለኦሮሞ ሚሊሻ ዩኒፎርም አንተ ምን አገባህ? ለሚሊሻ በቆሎ አዋጡ ማለትስ ፌር ነው ወይ…?

• እንደ ትግሬ በጅምላ፣ እንደ ዐማራም በየተራ መገደሉ ካልቀረ አትግደሉን ብሎ እንደ ሕዝብ ወጥቶ ለመጠየቅ ዋናው ችግር የሆነው ነገር ምንድነው?

"…ሌላው ያልገባኝ ነገር እሺ እንደተባለው ኦሮሞው የኦሮሞ ቄሮ ጉራጌው፣ ዐማራና ትግሬ፣ ደቡቡ ተፈናቅሎ እሱ ሱቅም፣ ሆቴልም ገነባ፣ ወረሰም እንበል። ሌላውን አደህይቶ ማን በሆቴሉ ሊዝናናበት ነው? ሱቁስ ያፈናቀልከው ከደኸየ አንተ ኦሮሞው ታቅፈኸው ልትኖር ነውን? ሥራ አጥ ከበዛ ወታደር ይሆንልኛል ብሎ ሒሳብ መሥራቱስ እስከመቼ ነው የሚያዋጣቸው?

• ግን ምን ኦነው ነው?

ዘመድኩን በቀለ

24 Oct, 20:28


"…ብለን ነበር እውነት ነው። ነገር ግን ከላይ መመሪያ ስላልወረደልን ከቻልን በሚቀጥለው ህዳር ወር ላይ እንደምንም ብለን እንሞክርላችኋለን ተብላችኋል አሉ።

"…እንደልቡ በነበረው የብር ኅተመቱ ጉዳይ ላይ የዓለም ባንክ ቆንጠጥ ያለ ቁጥጥር ማድረጉ አጣብቂኝ ውስጥ ሳያስገባው አይቀርም። ብሪክስም ቶሎ ብድር የመስጠት ቁመና ላይ አልደረሰም። ለማንኛውም የመስከረምም፣ ጥቅምትም ወር ታሳቢ ተደርጎ ይከፈላል የተባለው ደሞዝ ለህዳር መቀጠሩን ነው የሰማሁት።

• የሰማሁትን ውሸት ያድርገው። 🙏🙏🙏

ዘመድኩን በቀለ

24 Oct, 20:28


"…እሺ አሁን ደግሞ ሌላ ጨዋታ እናምጣ…

"…ታላቂቱን ሀገር እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ ጎትቶ እየፈጠፈጣት የሚገኘው የብልግናው አገዛዝ ከወርሀ ጥቅምት ጀምሮ የመንግሥት ሠራተኞች በአዲሱ የደሞዝ ሥርዓት መክፈል እጀምራለሁ ብሎ ነበር አይደል…?

ዘመድኩን በቀለ

24 Oct, 20:28


ደግሞ የገረመኝን ነገር ልንገራችሁ

"…በነገዱ ስልጤ የመርካቶ የቦምብ ተራ ነጋዴ ነው። በአስቸኳይ ጉምሩክ ድረስ እንድትመጣ ብለው ይደውሉለታል። ተነሥቶ ይሄዳል። ጉምሩክ እንደደረሰ ቀጥል ብለው አፍነው ይወስዱታል። ከዚያ መጀመሪያ በእጁ ላይ የ1 ሚልዮን ብር ቼክ ነበረ ጻፍ አሉትና አጽፈው አወጡበት። ቀጥሎ 6 ሚልዮን ብር አምጣ አሉት። ለሚስቱ ነግሮ፣ ከጓደኞቹም ተለምኖ የተባለው ብር በባንክ ተላልፎ ተሰጣቸው። አፋኞቹ ከጉምሩክ ጊቢ አንድ ሰው አፍነው በአንድ ቀን ጀምበር 7 ሚልዮን ብር ቀምተው ከበሩ። ሰውየው ደግሞ በዚያው ቅፅበት የደሀ ደሀ ሆኖ አረፈው። ሰዎች ለምን ለፖሊስ አታመለክቱም ሲሏቸው ኧረ ድምፅ ቀንስ…።

"…ሌላ አንድ ልጨምርላችሁ። አሁንም ከወደ ጉራጌ ክልል የ1 ቤተሰብ አባላት የሆኑ አጎት አክስት ዘመድ ተጨምሮ ወደ 17 ያህል ሰው በኦነግ ሸኔ ታግቶ 17 ሚልዮን ብር ተጠየቀባቸው። ገንዘቡ እስኪሰባሰብ ድረስ ሁለት ሦስት ቀን ፈጀ። በመሃል አጋቾቹ ከታገቱት መሃል በሁሉ ዘንድ ተወዳጅ ናቸው የተባሉትን መርጠው አንድ ሦስቱን አረዱ። ሌሎቹ እንዳይታረዱ ቤተሰብ አጋቾቹን ጫካ ድረስ ሄደው አስረከቡአቸው። የሄዱት 4 ሰዎችም ታግተው ለእነሱም ተከፍሎ ተለቀው ወጡ።

"…የተለቀቁት በሙሉ ቀዬአቸውን ጥለው ወደ ተሰደዱ። ጉራጌው ለመፈናቀል 20 ሚልዮን ከፍሎ፣ ሦስት ሰው አሳርዶ ተሰደደ። አዲስ አበባ ለቅሶ ወደተቀመጡ የሟች ቤተሰቦች ጋር እኔ የማውቃቸው ሰዎች ለቅሶ ለመድረስ ሄዱ። የሟች ታላቅ ወንድም የብልፅግና አባል፣ የአቢይ አሕመድ የግል አምላኪ ነው አሉ። እናም ምን ቢል ጥሩ ነው። በቃ ኅዘን አናብዛ። ይሄ ሁላ የሚደረገው አቢይን እንዲጠላ ለማድረግ ነው። ዝም በሉ፣ ለሚዲያም አትናገሩ። ሃሌ ሉያ። ሌላም የምነግራችሁ የገረመኝ ነገር አለ። እቀጥላለሁ።

• ፍርሃታችን ግን የጤና ነው…?

ዘመድኩን በቀለ

24 Oct, 20:28


"…ሌላው…

"…ሌላው ደግሞ አሁን እየበለፀገችዋ ነው ተብሎ በሚነገረን አዲሲቷ ኦሮጲያ ኢትዮጵያችን "መዋጮ" የሚባል አዲስ ኪስ ማጠቢያ መቅሰፍት በዝቷል፣ መጥቷልም አሉ። ብዙ ሰው ትንሽ ትንሽ እየተማረረ ነውም አሉ። በተለይ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልሎች መዋጮ ጠያቂው እንደጉድ ነው የሚተራመሰው ሁላ አሉ። አንደኛው ቀበሌ እየጠየቀ ሌላኛው በር ላይ ቆሞ ተራ ይጠብቃል አሉኝ። ወረፋ ነው አሉ መዋጮ። 😂

"…ቦታው የት እንደሆነ ረሳሁት እንጂ አስፋልት ላይ ለቆመ የመንገድ መብራት ሁላ ከቀበሌ ነን ያሉ አካላት መጥተው "ለመብራቱ ክፈሉ" መዋጮም አውጡ ተብለናል ያለኝም ሰው አለ።

"…እምቢ ካልክ ደግሞ እዚያው ቆሞ "ቤትህን ኖ ማፈርሶ" ይልሃልም አሉ። ነጋዴው በተለይ መድረሻ ጠፍቶታልም ይላሉ አንዳንዶች።

• የመዋጮው ነገር እውነት ነው እንዴ?
• መዋጮው ለምን ለምንድነው…?
• ደረሰኝስ አለው…?

"…ለጠቅላላ እውቀት ብዬ ነው።