Brook Fekadu @brookfekaduu Channel on Telegram

Brook Fekadu

@brookfekaduu


ለአስተያየቶ http://t.me/BrookFekadu_bot

Brook Fekadu (Amharic)

በተጨማሪ ስም 'Brook Fekadu' እና የተለያዩ አፕ መረጃዎችን በተቀላቀሉ ጠንከር እና እንደገና ለማግኘት በስፖርት በተጠቀምለት 'brookfekaduu' እና በዚህ የእኮ አፕላይን አለምገና'ኦ http://t.me/BrookFekadu_bot' ማታወቅን እና አመልካች በሚሉ የአገልግሎቶች ላኪዎችን ለመረጃን ይደሰቱ። 'Brook Fekadu' ለባለቤት እስከ ስእላችን ለማለፍ ለቍጥር ቁጥር አልተመለከቱም። ስለሆነ ከዋና ሥራችን ጋር የተለያዩ የቪዲዮዎችን እና የተገለጸውን የማጣመር እና ክፍሌ ለማስገንባት ሼር ያንብቡ።

Brook Fekadu

15 Sep, 09:45


ከዛሬ1499 አመታት በፊት ነበር ያ የአለም ብርሀን የምድር ፈርጥ የሠው ልጆች ሁሉ አይነታ የነብያት መደምደሚያ የአላህ ወዳጅ ገና ያኔ.....ያኔ ሳንፈጠር "ሳያዩኝ ያመኑብኝ ወንድሞቼ ናፈቁኝ"ብለው የተከዙት አሽረፈል ኸልቅ ጨረቃ የተገመሰላቸው🌙🌙የዛፉ ጉቶ ያለቀሰላቸው ጠላት ሳይቀር በፍቅራቸው የተንበረከከላቸው ነብይ ሳይቀር ኡመታቸው ለመሆን የተመኘው ምርጡ መሪ ወደዚህች ምድር ብቅ አሉ። ያኔ ፍትህ ሰፈነ የምድርም ሚዛን ተስተካከለ ምድርም በሰማይ ፎከረች እኛም የኚህ ምርጥ ነብይ ዑመት የመሆንን እድል አገኘን አልሀምዱሊላህ።🥰🥰

اللَّهُــمَّ ᷂صَلِّ ᷂وَسَـــلِّمْ ᷂وَبَارِك ᷂على ᷂نَبِيِّنَـــا ᷂مُحمَّد

Brook Fekadu

09 Aug, 04:34


{۞ ٱللَّهُ نُورُ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِۚ مَثَلُ نُورِهِۦ كَمِشۡكَوٰةࣲ فِیهَا مِصۡبَاحٌۖ ٱلۡمِصۡبَاحُ فِی زُجَاجَةٍۖ ٱلزُّجَاجَةُ كَأَنَّهَا كَوۡكَبࣱ دُرِّیࣱّ یُوقَدُ مِن شَجَرَةࣲ مُّبَـٰرَكَةࣲ زَیۡتُونَةࣲ لَّا شَرۡقِیَّةࣲ وَلَا غَرۡبِیَّةࣲ یَكَادُ زَیۡتُهَا یُضِیۤءُ وَلَوۡ لَمۡ تَمۡسَسۡهُ نَارࣱۚ }
አላህ የሰማያትና የምድር አብሪ ነው፡፡ የብርሃኑ ምሳሌ በውስጧ መብራት እንዳለባት (ዝግ) መስኮት፣ መብራቱ በብርጭቆ ውስጥ የኾነ፣ ብርጭቆይቱ ፍፁም ሉላዊ ኮከብ የምትመሰል፣ ምሥራቃዊው ምዕራባዊም ካልኾነች ከተባረከች የወይራ ዛፍ ዘይቷ እሳት ባይነካውም እንኳ ሊያበራ የሚቀርብ ከኾነች (ዘይት) የሚቃጠል እንደ ሆነ (መብራት) ነው፡፡ (ይህ) በብርሃን ላይ የኾነ ብርሃን ነው።

ሱረቱ ኑር 35

ያራህማን የእሳት ነን እንዳንል በዚ የዱንያን ፍንጣሪ እሳት እንኳን በማይችል ሰውነታችን ላይ የጀሀነምን ቅጣት መቋቋም አንችልም😢😢የጀነት ነን እንዳንል ስራችን ለዛ ደረጃ አይስተካከልም እና በእዝነትህ በመሀርታህ በውዴታህ ከልልና በጀነትህ አቀማጥለን....ያንተንም ፊት ከሚያዩት ምርጥ ባሮችህ አድርገን ጌታዬዋ አደራህን::

Brook Fekadu

03 Aug, 17:51


አቡበክር ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) የአላህ መልዕክተኛን (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አላቸው፡- ‹‹በሶላቴ ውስጥ ሳለሁ የማደርገው ፀሎት
ያስተምሩኝ፡፡›› (እርሳቸውም) እንዲህ በል አሉት፡- ‹‹አላህ ሆይ! እኔ ነፍሴን በርካታ በደል በድያለሁ፡፡ ከአንተ በቀር ወንጀልን የሚምር የለምና ካንተ የሆነን ምህረት አቡበክር ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ/ሃ) የአላህ መልዕክተኛን (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አላቸው፡- ‹‹በሶላቴ ውስጥ ሳለሁ የማደርገው ፀሎት ያስተምሩኝ፡፡›› (እርሳቸውም) እንዲህ በል አሉት፡- ‹‹አላህ ሆይ! እኔ ነፍሴን በርካታ በደል በድያለሁ፡፡ ከአንተ በቀር ወንጀልን የሚምር የለምና ካንተ የሆነን ምህረት ማረኝ ፡፡››

ቡኻሪ

Brook Fekadu

28 Jun, 23:06


The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 17 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.

Brook Fekadu

18 May, 16:37


ሰላም ሰላም ውዶቼ
በዚህ ቻናል በተቻለኝ አቅም እናንተን ያዝናናል ያስደስታል እንዲሁም ቁም ነገር ያስጨብጣል ብዬ የማስባቸውን የተለያዩ ፅሁፎችና መጣጥፎች ፣ አጫጭር ልቦለድ ፣ ግጥሞች፣ ለናንተ ይጠቅማሉ ብዬ የማስበውን የህይወት ተሞክሮ መንገዶችን ባጠቃላይ ጥበብን በዚህ ቻናል እንኮመክማለን ። ወዳጅ ጓደኛችሁን ወደ ቻናሌ ጋብዙልኝማ.. ከወዲሁ የከበረ ምስጋና🙏


https://t.me/yetezeberarekugesoch1

Brook Fekadu

30 Apr, 19:54


#ሪዝቅ_ሰፊ_ነው

በሲሳይ (ሪዝቅ) የተደራጀ እምነት መያዝ ከተውሒድ ግንዛቤዎች መካከል አንዱ ነው። በርካቶቻችን በሚታዩ ቁሳዊ ነገሮች በተለይም በገንዘብ ላይ ብቻ የሚታይ ሲሳይ ላይ እናተኩራለን። ኢማሙ ሸዕራዊ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) ስለሪዝቅ ሲመክሩ የተሟላ ሪዝቅ ማለት የልጆች መስተካከል ነው፣ አስፈላጊ የሚባለው ደግሞ የጤንነት ሪዝቅ ነው ዝቅተኛው ሪዝቅ የገንዘብ ነው። በማለት የሪዝቅ እሳቤን እንድናሰፋው ይጠቁማሉ።

አንዳንዴ የምታወራው ነገር የሚገባው ጓደኛ ማግኘት ትልቅ ሪዝቅህ ነው፣ በኪስህ ብር ሞልቶ በቁስ ሀብት ተንበሻብሸህ ሰው ይጠርብህ ይኾናል ስታገኘው የምትደሰትበት ሰውም ማግኘት ሪዝቅህ ነው። የምትደሰትበት ሥራህ፣ የሚያዝናኑህ ልጆችህ፣ ሕይወትን የምታቀልልህ ባለቤትህ ሪዝቆች ናቸው። መስጂድ የመቀመጥ ዕድልህ፣ ለብቻህ የመዝናናት፣ የማንበብና በመንገድ ላይ እየተራመድክ የምታገኘው አየርህ ኹሉ የአላህ ጸጋና ሪዝቅ ናቸው። ምን የርሱ ያልኾነ አልለ። የሚያስቅ ብዙ ነገር እያለህ መሳቅ ሊከብድህ ይችላል፣ መተኛት ፈልገህ መኝታ ላይ ብትገኝም ዕንቅልፍ እምቢ ብሎህ ይኾናል። ብዙ የሚያስለቅስ ገጠመኝ ይኖርሀል ግና ማልቀስ ተስኖሀል ከእነዚህ ነገሮች መጠበቅ በራሱ ከአላህ ጸጋዎች ናቸው።

« እነሆ እርሱም አስሳቀ፣አስለቀሰም።» አልነጅም፤43

ሳቃችን ከርሱ የተሰጠን ጸጋ ነው፣ ለቅሶኣችንም ከርሱ የተሰጠን ሪዝቅ ነው። እንባ ከስንት ውስጣዊ ንዳድ ያድናል?! እንባ የደረቀበት ሰው ንዳዱ በምን ይበርዳል። ፈገግታ ሲሰለብ የሰው ልጅ በምን ሀይል ያገኛል። አላህ ጥልቅና ደቂቅ በኾኑ ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ፍጡራኑን በእዝነቱ የሚያካብ አምላክ ነው። የሰው ልጅ ከላዩ ላይ ያለውን ዝንብ እንኳን ለማባረር ከጌታ የእዝነት እርዳታ ፈላጊ ነው። ያሉንን ጸጋዎችና ሪዝቆች እንዳንመለከት የሚያደርገው እርጉሙ ሰይጣንና የገዛ ነፍስያችን ነው።

አላህ ያለንን ያሳየና

አላህ ይህን ባርነት ያስረዳን
Best Kerim

Brook Fekadu

05 Jan, 12:44


https://t.me/bariibrand

Brook Fekadu

01 Dec, 13:08


መዲና ዉስጥ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ።

ታላቅየዉ ሀብታም ሲሆን ታናሹ ምንም አልነበረውም።

ታናሹ ወንድም ነብያችን (ሠዐወ) ጋር ቁጭ ብሎ ለመማር እንደሚፈልግ ለታላቅ ወንድሙ ይነግረዎል። ታላቅየዉም ይስማማና እሱ ጋር እየኖረ መማር እንዲችል ይፈቅዳል። ጊዜ እየሄደ ሲመጣ Complaint ማድረግ ጀማመረ። እኔ ቤት ተቀምጦ፣ የእኔን ምግብ እየበላ ብሎ ወቀሳ ለማቅረብ ረሱል (ሠዐወ) ዘንድ ሄዶ የእኔ ቤት ዉስጥ ፣ የእኔን ገንዘብ ፣ የእኔን ምግብ ብሎ አለቃቀሰ፤ ነብያችን (ሠዐወ) እንዲህ አሉት :-

አላህ እኮ ይሄንን ሁሉ ሀብት የሰጠክ በታናሽ ወንድምህ ሰበብ ነዉ። አሉት

ከዚህ ምን እንረዳለን አላህ ሀብትም ሆነ ፀጋ ሲሰጠን ስለሚገባንና ስለለፋን ብቻ ላይሆን ይችላል ፤ አንዳንዴም እኛ ጋር ጠጋ ባሉ ሠዎች ሊሆን ስለሚችል የእኔ የእኔ አንበል።

Brook Fekadu

12 Nov, 19:19


ኢስላም Busy ሚያደርግ ሀይማኖት ነዉ!!

Busy ለመሆን ካልተዘጋጀክ ዉስጡ ያለዉን ሰላም አታገኘውም።

Brook Fekadu

09 Nov, 05:31


ትልቁ ችግር ዱዓ ለአላህ አድርገን፤ ተወኩል ሠዉ ላይ ማድረጋችን ነዉ። ሰዉ እኮ Only ሰበብ ከዛ ያለፈ Role የለዉም።

Brook Fekadu

09 Nov, 02:59


ዱዓ ስታደርግ ነዉ፤ የሚያስፈልግህን ምታዉቀዉ

Brook Fekadu

02 Nov, 11:06


س/هل يجوز التطبيع عند عدم القدرة ؟
ጥያቄ/ አቅም ያነሰን( ደካማ) ከሆንን ከፅዮናዊቷ ወራሪ ጋር ግንኙነታችን (እንደ ሉኣላዊ ሀገር ቆጥረናት) ማስማማትና አብረን መቀጠል እንችላለን?

ج/ الجواب: لا ؛ لأن من لا يستطيع الزواج لا يجوز له الزنا
መልስ/ አይቻልም። ምክንያቱም ማግባት ላልቻለ ሰው ዝሙት አይፈቀድለትምና።

سيدي الشيخ الشهيد أحمد ياسين رضي الله عنه
ሸሂድ ሸይኽ አህመድ ያሲን (ረህመቱላሂ ዐለይሂ)

Brook Fekadu

28 Oct, 20:10


የሳዑዲን መንግስት መተቸት አልያም መንቀፍ ለመካና መዲና ክብር መንሳት አይደለም።

መካ፣ መዲና አቅሳ የዓለም ሙስሊም ሀብቶች እንጂ የመንግስት ቱሪስት መስዕቦች አይደሉም!!!

Brook Fekadu

27 Oct, 14:05


ዱዓ ማለት አንተ በፈለከዉ እና ባሰብከዉ መንገድ ብቻ ይሳካልክ ዘንድ አላህን መጠየቅ አይደለም።

ዱዓ ባርነትህን ይበልጥ ያስታዉስሃል ፤ ባሪያ ደግሞ ጌታዉን ሲጠይቅ በአዛዥ ስነልቦና ከሆነ መታረም ይገባዋል።

እንደዉም Nouman Ali khan "Revive your Heart" የሚል መፅሀፉ ላይ እንዲህ ይላል።
" ዱዓ ካፌ ገብተክ እንደምታዘዉ ምግብ አይደለም ፤ ለምግብክ ገንዘብ ከፍለሃል ለዱዓ ግን ምንም ሳትከፍል እንዲሰጥክ የከፈልከዉን ነገር ጥያቄ ማቅረብ ብቻ ነዉ።'' ይላል

በጋዛ ጉዳይ የዓለም ሙስሊም ዱዓ ስላደረገ ብቻ የፈጠነ ድል መጠበቅ ሞኝነት ነዉ።

አላህ የራሱ ተርቲብ እና ስርዓትን ለዱንያ ዘርግቷል። እኛ እሱን መጠየቅ ፣ መለመን፣ ድፍት ብለን ዱዓ ማድረግ ሃላፊነታችን ነዉ።

ቀጥሎም አላህ ዉጤቱን ያሳምረዉ ብለን እንጠብቃለን።

Brook Fekadu

26 Oct, 07:23


አላህ ሆይ አንተን በመገዛቴ ደስተኛ ነኝ፤በሰጠሀኝ ፀጋዎች አመሰግንሃለሁ።ልቤ ያንተ ቤት ብቻ ትሆን ዘንድ እማፀንሃለዉ።ዓለም ፊት ቆሜ ስላንተ ቸርነት ለማዉራት አላፍርም። የኔ ወዱድ ባንተ እርዳታ እዚህ ደርሻለሁ፤ ባንተም እዝነት ወደ ተሻለው እሄዳለሁ።

በአላህ አምላክነት ፣በእስልምና ሀይማኖትነት ፣በሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ) መልዕክተኝነት ፍፁም ደስተኛ ነኝ!!