አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ @abizeeotc Channel on Telegram

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

@abizeeotc


ለአስተያየት ለጥያቄ በግል ለማውራት @abigezenige ይህን ይጠቀሙ።

ሐምሌ 27/11 ዓ᎐ም

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ (Amharic)

ከተአምራት አሳኝ እስከ መስከረም 27 ቀን 2011 ዓ.ም ዓባኹሓለይ ዘክቡና ዘሕማቕ ነውና ዝጠቅሞ በአስተያየት በቆራረረ አጋማሽ ፎሎዎች ያበአልከ ነው። ማለት ለአዳዲስ መረጃ ለጥያቄ በግል ለማውራት @abigezenige ይህን ይጠቀሙ።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

23 Jan, 18:12


እንዴት ነህ አቤኒ እንኳን አደረሰህ ለእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል። እናቴ ኪዳነ ምህረት ለእናቴ ያደረገችላትን ተዓምር ለመመስከር ነው ። ከ 1 አመት በፊት ሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት ሄጄ ነበር እና የማር እምነቷን ይዤ ወደ እቤት መጣሁ እና ወላጅ እናቴ ከ20 አመት በላይ የምናውቀው ከኋላ አንገቷ ስር የሆነች ጥቁር ምልክት ነበረቻት እና እኛ ማርያም ስማት ነው እያልን ሳለ ከ 15 አመት በፊት ያቺ ቦታ እያበጠችና እየጠጠረች መጣች እናቴም ሀኪም ቤት ስትሄድ ሰርጀሪ አሏት እሷም ስለፈራች ተወችው እና እብጠቱ ና ጠጠር ያለ መሆኑ እየጨመረ ይሄድ ነበር። ታድያ ለእናቴ የሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት የማር ዕምነቷን እርሷ ታድንሻለች ብዙ ምስክርነት አይ ቻለሁ እዛ ብዬ ሰጠኋት እና መቀባት በጀመረች በ3ኛው ቀን ያ ጥቁሩ ምልክት ያለው ሳይሆን ከሱ ዝቅ ብሎ ያለው ንፁህ ቆዳ ላይ ፍም መሰለ እያለ እያለ ልክ በ 5ኛው ቀን ፈረጠ። አቤኒ የፈረጠው ነገር የሚያስፈራ የሚዘገንን ሽታው እጅጉን የሚሰነፍጥ ከሰው ሰውነት የሚወጣ የማይመስል ነገር ለ7ቀን ሙሉ ሲወጣ ነበር እና በእናቴ በሰሚነሸ ኪዳነ ምህረት ተዓምራዊ የማር እምነቷ እናቴ ከ20 አመት በላይ ተሸክማው ከነበረ ምንነቱ ካልታወቀ በሽታ ተፈወሰችልኝ። እልልልልልልልልልልልልልልልልልል ብላችሁ ኪዳነ ምህረትን አመስግኑልኝ። ከ እናቴ አንገት ላይ የወጣውን ምንነቱ ያልታወቀ ፈሳሽን ምስሉን ከታች አስቀምጬዋለሁ(ይሄ ምስል መጠኑ እየቀነሰ ሲመጣ ለምስክርነት ላስቀምጠው ብዬ የመጨረሻዎቹ ቀናት ላይ ያነሳሁት ነዉ ። የመጀመሪያውማ አይወራ ይሄን የመሰለ ጎርፍ ነበር ። ልብሷ እየበሰበሰ በቀን2-3 ጊዜ ቲ ሸርት ትቀይር ነበር )
አደራ አቤኒ መስክርለኝ🙏

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

22 Jan, 16:09


ጥር 21 ለእማዋይሽ ክብረ በዓል ለ2 ሰው የመቁረቢያ ልብስ እንዲሁም ደግሞ በ አቤኔዘር ዘተዋሕዶ የዝክር መርሐግብር የቻላችሁትን በመለገስ መሳተፍ ይቻላል። 1000145090176 አቤኔዘር ገዛኸኝ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

22 Jan, 06:56


ጥር 18 ዓመታዊውን የቅዱስ ጊዮርጊስን ክብረ በዓል በበርሚል ጊዮርጊስ እናክብር።
መነሻ ጥር 16 መመለሻ ጥር 25
የጉዞ ዋጋ 15ሺ ብር በአውሮፕላን ነው ጉዞው
093 314 3133

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

21 Jan, 13:36


ሰውን ምንም እንኳ ከአፈር ቢፈጠር ሰው እንጂ አፈር እንደማንለው ታቦትንም እንጨት ነው አንልም።
ታቦት የእግዚአብሔር ማደርያ ነው።
እንኳን አደረሳችሁ ቤተሰብ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

20 Jan, 07:02


"መጥምቁ ዮሐንስ የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም ነበር።" ሉቃ.1:15
አንተስ? አንቺስ?
የማንን በዓል እያከበርክ ይሆን እስክትሰክር የምትጠጣው?
አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

18 Jan, 07:04


Facebook ላይ 300ሺ ቤተሰብ ሞልተናል።
የቴሌግራምም ቤተሰቦቼ ከ10ሺ አልፈናል።
እግዚአብሔር ይመስገን
እንኳን አደረሳችሁ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

17 Jan, 18:19


ታቦት እንጨት ነው ጣውላ ነው ቅብርጥሶ የሚሉ ሰዎች ያስቁኛል። እኛ ታቦት መብረቅ ነው ልዩ ፍጥረት ነው ብለን አላስተማርንም አልተማርንምም። ለዚያም ነው ከሰው መርጦ ለክህነት ከእንጨት መርጦ ለታቦት የሚል የጥንት አባባል ያለን።
ፈጣሪ ሰው ሆነ ፈጣሪ ተወለደ ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ወለደች ከማለት ሌላ ድንቅ ነገር አትፈልጉ።

@abizeeotc

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

17 Jan, 17:11


በነገራችን ላይ ነገ ታቦት ሲወጣ አንዳንዶች ታቦት ምንድነው ብለው ሲጠይቋችሁ የምትሰጧቸው አጭር መልስ፦
'ታቦት የጌታ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም መሰዊያ ቅዱስ ጠረጴዛ ነው' በሏቸው።


ዕብ.13:10

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

17 Jan, 14:29


ባህል ወይስ ሃይማኖት
ይህ ባህል ነው ባህሉም ኤርትራ ውስጥ ዲያቆን ሲያገባ፣ የሚፈጸም ስርአት ነው።
የጎሽ ቀንድ ምልክትነቱ፣ ጎሽ በህይወቱ አንድ ሴት ብቻ ነው የሚኖረው። አስገራሚው ነገር ጎሽ ሚስቱን በሞት ቢያጣ እንኳ ሌላ ሴት ጎሽ አያገባም። ስለዚህ ዲያቆን አንዴ ካገባ ሌላ ማግባት እንደሌለበት ለማሳየት ነው !

በኤርትራ ብቻ ሳይሆን አልፎ አልፎ በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎችም ስርዓቱ ይፈጸማል ....

በድጋሚ ለማስታወስ ይህ ባህል ነው፥ የቤተክርስቲያን ስርዐት አይደለም። ግን ምሳሌው ይበል የሚያሰኝ የሚደንቅም ነው ....።

በነገራችን ላይ ቤተክርስቲያን ጥንቅቅ ተደርጋ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተሞሸረች ተጠናቃም የተሰራች ናትና ለሁሉ ትክክለኛ መልስ አላት ::

ባህልና የቤተክርስቲያን ስርዓት የሚጋጭባችሁም አይነ ልቦናችሁን ያብራላችሁ ከማለት እና ስለ እናንተ ከልብ ከመጸለይ ውጭ ምንም ልንላችሁ አንችልም።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

16 Jan, 19:59


ነገ አርብ እስከ ምሽት 12:00 ይጾማል፥ ቅዳሜ ከጥሉላት (ከፍስክ ምግቦች ይጾማል።)

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

16 Jan, 15:33


ጥር 16 ከ በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ አይቀርም
ኑ ወደ ተአምረኛው በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር አብረን እንጓዝ
ታላቅ የበረከት ጉዞ ወደ በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር
እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ጥር 16/2017 ቀን ተነስተን ጥር 25/2017ቀን የምንመለስበት ጥር 18 የቅዱስ ጊዮርጊስ በአለ ንግስን አክብረን የምንመለስበት ስንሄድ እስከ ባህር ዳር ድረስ በፕሌን በመጓዝ ከባህር ዳር በኋላ ደግሞ የማኅበሩን ባስ ትራንስፖርት በመጠቀም ጉዞ ወደ በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር ያዘጋጀን ሲሆን ምዝገባም ሊጠናቀቅ ስለሆነ ቶሎ ቶሎ ተመዝገቡ
ትራንስፖርት ዋጋ 15,000 ሺህ ብር ነው ።
▶️ ቀኑ ሲቃረብ የፕሌን ዋጋ ስለሚጨምር በጊዜ ይመዝገቡ ።
0933143133
0918222560

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

15 Jan, 17:43


https://youtu.be/cg3XZ_zt8bw?si=IxNVe7lfQxASmz18

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

15 Jan, 05:34


1.
ማን ፈጠረን?
Eenyutu nu uume?
መን እዩ ፈጢሩና?

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

14 Jan, 11:16


https://youtu.be/7sPqdrU--ew?si=ghgilnoAZh8I59IS

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

13 Jan, 16:11


የጥር ሥላሴን ዝክር አብረን እንዘክር እንጂ 😃
1000145090176 አቤኔዘር ገዛኸኝ +251933143133

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

08 Jan, 20:43


#እየመጣን_ነው https://t.me/Apostolicfathers1 በቴሌግራም #ተቀላቀሉን ቲክቶክም አለን✝️

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

07 Jan, 11:48


https://youtu.be/DIrrKOYl374?si=8vnP3fcsuSFjsgr9

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

07 Jan, 11:07


https://youtu.be/AvKDQxxDyoc?si=1F5ySJw9-oOS7K_t

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

05 Jan, 13:55


+251933143133
+251918222560

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

05 Jan, 13:31


እንደተለመደው ለአዲስ ዓመት ለገና እና ለፋሲካ የምናደርገው ለጥቂት እናቶች የበዓል ስጦታ ዛሬ ለገና በዓል ጀምሬያለሁ እግዚአብሔር ቢፈቅድ እስከ ማታ ቢያንስ ለ3 ሰው ካገኘሁ ይበቃል። inbox አውሩኝ።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

04 Jan, 15:04


እግዚአብሔር ይመስገን
ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለድንግል ማርያም ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ገና ለሚቆርቡ ሰዎች የተቀበልኳችሁ ገንዘብ አገልግሎት ላይ ውሏል።
የሰበሰብኩት የ4 ሰው ነው ቀሪውን እጠብቃችኋለሁ 😃

በቪዲዮ ደግሞ ምርቃቱን አደርሳችኋለሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ 🤗🥰

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

03 Jan, 16:43


ከግብረ ሰዶም እና ከዘመድ ጋር መተኛት እኩል እጅግ አጸያፊው ሚስት ያገባን ወንድ መመኘት ከእርሱ ጋርም መተኛት።
ይህ ዘመናዊ የሴተኛ አዳሪነት ሙያ ነው
እነኚህ ሴቶች የቤተሰብ በዓድ አምልኮ ውጤቶች ናቸው

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

02 Jan, 16:12


የአጋንንት ተፈጥሮ ወድቆ አለመነሳት ነው፥ የመላእክት ተፈጥሮ አለመውደቅ ነው፤
የሰው ልጅ ተፈጥሮ ደግሞ ወድቆ መነሳት ነው።

ተፈጥሯችን የአጋንንት እንዳይሆን ንስሐ እንግባ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

01 Jan, 06:12


እግዚአብሔር ቢፈቅድ ዛሬ እስኪ ስለ በርሚል ጊዮርጊስ ጠበል ትንሽ እነግራችኋለሁ፥ በተለይ ስንጠመቅ ለምን እንታሰራለን የሚለውን...። ቀጣይ ጉዞ ጥር 3/2017 ነው መሄድ የምትፈልጉ 0933143133 ደውሉ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

31 Dec, 18:40


እግዚአብሔር ይመስገን ታህሳስ ገብርኤልን ዘክረናል።
በቀጣይ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ጥር ሥላሴንና አስተርዮ ማርያምን እንዘክራለን።
በነገራችን ላይ እነዚህንም በዓላት ዘክሬ አላውቅም።
አብረን እንዘክር።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

30 Dec, 13:33


ለጸበልተኛዋ ተገኝቷል፥ ቀሪዎቹን...

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

30 Dec, 13:10


ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 6 ሰው አስቆርበኝ ብለው መጥተዋል።
5 የኮሌጅ ተማሪዎች 1 ደግሞ ጸበልተኛ።
የተለመደው ተሳትፎ እፈልጋለሁ።
ስለ እመቤታችን። አመሰግናለሁ
1000145090176 Abenezer Gezahegn
+251933143133

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

28 Dec, 05:06


https://youtu.be/QIzfJoewZ1o?si=1vlcxxtzLPzRVzXo

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

27 Dec, 08:41


ለጥምቀት በዓል ከፈለጉ ይዘዙን።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

27 Dec, 07:56


መቁጠሪያ።
በእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ሙስባህ በእኛ ቤተክርስቲያን አጠራር ደግሞ መቁጠሪያ በቤተ ክርስቲያን ማመስገኛ መፀለያ ነው።

መቁጠሪያ የሚሰራው ከማንኛውም ዛፍ ሳይሆን ከወይራ እና ከፍየለ ፈጅ እፅዋቶች እንደሆነ የገዳም አባቶች ይናገራሉ።

ይህም ምሳሌነቱ:-
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋት ያስቡበታል እንዲሁም በወይራ እና በፍየለፈጅ እፅዋቶች መገረፉን ያመሰጥራሉ።

ከሦስት ሰዓት የተጀመረው የክርስቶስ መከራ ሥድስት ሰዓት በመስቀል ተሰቅሎ እስከ ዘጠኝ ሰዓት መዋሉን የነበረውን ግፍ እና መከራ እያሰቡ ገዳማውያን አባቶች አርብ አርብ እራሳቸውን ሰውረው በመቁጠሪያ ሰውነታቸውን ይመቱታል።

ዋናው የመቁጠሪያ አላማ ማመስገኛ ሲሆን በገዳም ያሉ አባቶች የፀለዩበት መቁጠሪያ አጋንትን ያስጨንቃል ጴጥሮስ በጥላው ጳውሎስ በልብሱ ዘርፍ ድውይ እንደፈወሱ ሙት እንዳስነሱ ሁሉ በተመረጡ አባቶቻችን ገዳማውያን የተፀለየበት መቁጠሪያ ዛሬም ተዓምር ይሰራል።

ምስሉን ለማነጻጸሪያ ተጠቀምኩበት እንጂ የተለየ ሃሳብ የለውም ይልቁንስ መቁጠሪያን ከገዳም አባቶች ተባርኮ የመጣውን ማንኛውም የክርስትና እምነት ተከታይ ቢጠቀምበት ሥርዓት አያፈርስም ይልቁንም በጸሎት እንዲተጋ ያግዘዋል።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

26 Dec, 07:50


የአእላፋት ዝማሬ መሳተፍ ፈልጋችሁ ነገር ግን በቦታ ርቀት በተለያየ ምክንያት ከመሃል ከተማ ወደ ሌላ ቦታ ለሄዱ የተዋሕዶ ልጆች የተዘጋጀ።

ትራንስፖርት ደርሶ መልስ 300 ብር

መነሻ ቱሉዲምቱ ጠዋት 5:00 ሰዓት
የምናልፍባቸው መንገዶች
ኮዬፈጬ አደባባይ
ፕሮጀክት 16
ጎሮ አደባባይ
ፊጋ
መገናኛ
ለመመዝገብ +251933143133 telegram t.me/abigezenige
አዘጋጅ አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

26 Dec, 07:18


ምን እንደሚያሳዝነኝ ልንገራችሁ?😥
በመጀመሪያ ግን እንደምን አደራችሁን? 🤗
የሚያሳዝነኝ በቅዳሴ ሰዓት የጌታ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደምን ጥቂት ሰው ብቻ ተቀብሎ ሲመለስ።
ምናለ ሁላችንም ብንቆርብ 😥

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

25 Dec, 06:53


https://youtu.be/zWl7D62qOu8?si=3D7H82W9tB4lddiS

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

24 Dec, 10:48


እህቶች ሱሪ መልበስ ለማቆም ካሰባችሁ አንድ መፍትሔ፦
በተለይ እመቤታችን በምትታሰብባቸው ቀናት በ1 በ16 እና በ21 ቀሚስ ለመልበስ ሞክሩ። ወንድሞች ቀሚስ ስጦታ በመስጠት አበረታቷቸው።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

22 Dec, 06:21


የክብር እንግድነት ግብዣ ከአቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ
ዛሬ የወንድሜ የደስታ ቀኑ ነው:: በታህሳስ ወር ሁለት መርሐ ግብር አለን:: ዛሬ ታህሳስ 13 በአዲሱ አልበሙ ዙሪያ የምክክርና የቅድመ ምርቃት መርሐ ግብር ኮሚቴው አዘጋጅቷል:: ተወዳጁ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ ከአዲሱ የዝማሬ አልበሙ ከተካተቱ ዝማሬዎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ ከወዳጆቹ ጋር የሚዘምረው ዛሬ ነው::

በቦታው ለመገኘት የምትፈልጉ ሰዎች ጥቂት ካርድ ስላለን መመዝገብ ትችላላችሁ:: በውስጥ መስመር ከአቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ ብለው መልእክትዎን ያስቀምጡ:: በ +251713395512 SMS ይላኩ:: እናሳውቃለን::

ተመሰገን ተመስገን
ለምስጋና ስላሰባሰብከን
እግዚአብሔር ተመስገን

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

21 Dec, 19:02


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዩቲዩብ ገንዘብ ስለሚከፍል ብቻ የግለሰቦችን ጓዳ ለመስማት በሚዘገንን መልኩ ቃለ መጠይቅ በማድርግ ግለሰቦች ወደ ያልተፈለገ ስሜት መክተት የዚህ ዘመን አስነዋሪ ተግባር ሆኗል ። ማህበራዊ እሴቶች ተፋልሰዋል።

የሚሰጡት ርዕስ የሚያሳዩት thumbnail እና የሚያነሷቸው ሃሳቦች አብዛኛው የፈጠራ ድርሰቶች (ድራማ) ቢሆኑም ይህ የአእምሮ washing በዚህ ከቀጠለ ነገ ከነገ ወዲያ በትክክል ቢፈጸሙ ስንኳ ማንም ልብ የማይላቸው ይህማ ቆየኮ ከተጀመረ ተብሎ ትኩረት እንዳያገኙ ያደርጋል ።

ከእነዚህ ውስጥ ለምሳሌ
የግለሰቦች ወይም የአንድ ቤተሰብ ታሪኮችን፥ አባት ልጁን አገባ፥ እናትና ልጅ ግብረ ስጋ ግንኙነት ፈጸሙ፥ እህታማቾች ወይም ወንድማማቾች ተጋቡ፥ ሴት ወንድን ልጅ ደፈረች፥ አንዲት ሴት ከሁለት ወንድ ጋር ተኛች፥ እከሌ የሚባል አዲስ ሃይማኖት ተፈበረከ፥ and so on....

የሚሰጡት ርዕስ እንዳለ ሆኖ የዩቲዩብ ድራማ ጨምሮ የሚለጠፉት ተመልካች መሳቢያ ምስሎች ወንድና ሴት ተኝተው፥ ሴቷ ከራቁት ያልተናነሰ ልብስ ለብሳ፥ ወዘተ....
በዚያው ልክ ተመልካቹም የትየለሌ ነው።

ምን ይሻለናል ወደየት እየሄድን ነው? እውነት እንደሚባለው የመጨረሻው ዘመን ሲቃረብ እውነት ትከስማለች ሀሰት ትነግሳለች የሚባለው እየተፈጸመ ይሆን?

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

01 Dec, 13:24


ሰይጣንን ማናደድ ትፈልጋላችሁ?
የሰው ወሬ ንቀት ትችት ስድብ ማሽሟጠጥ ጸብ ወዘተ አትስሙ በራሳችሁ ጉዳይ ላይ ብቻ አተኩሩ። በተለይ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ አንብቡ።

50 ሰው የሚሳተፍበት
ይህን ከታች የሚታየውን መጽሐፍ ቅዱስ በ100 ብር
ዛሬ ብቻ የሚቆይ ዕለታዊ እድል።
ከ1 ቁጥር እስከ 50 ቁጥር የፈለጉትን ይምረጡ።

በንግድ ባንክ 1000510909635
በአቢሲኒያ ባንክ 47056497
በዳሽን ባንክ 5085757192011
በቴሌብር +251933143133
አቤኔዘር ገዛኸኝ ብለው በተለያዩ አማራጮች ዕጣውን መቁረጥ ይቻላል።
የከፈሉትን ገንዘብ በቴሌግራም በዋትሳፕ ወይም በሚሴንጀር አማራጮች በአንዱ ሪሲት ከመረጡት ቁጥር ጋር እንዲሁም ሙሉ ስምና ስልክ በቴሌግራም link t.me/abigezenige መላክ።
የተያዙ ቁጥሮች
1
3
5
6
7
8
9
10
12
16
17
18
19
21
22
23
24
26
27
29
30
34
44
46
50

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

01 Dec, 08:36


50 ሰው የሚሳተፍበት
ይህን በእጄ የያዝኩት መጽሐፍ ቅዱስ በ100 ብር
ዛሬ ብቻ የሚቆይ ዕለታዊ እድል።
ከ1 ቁጥር እስከ 50 ቁጥር የፈለጉትን ይምረጡ።

በንግድ ባንክ 1000510909635
በአቢሲኒያ ባንክ 47056497
በዳሽን ባንክ 5085757192011
በቴሌብር
+251933143133
አቤኔዘር ገዛኸኝ ብለው በተለያዩ አማራጮች ዕጣውን መቁረጥ ይቻላል።
የከፈሉትን ገንዘብ በቴሌግራም በዋትሳፕ ወይም በሚሴንጀር አማራጮች በአንዱ ሪሲት ከመረጡት ቁጥር ጋር እንዲሁም ሙሉ ስምና ስልክ በቴሌግራም link
t.me/abigezenige መላክ።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

30 Nov, 19:27


ክፍል 7 ነገ ይቀጥላል

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

30 Nov, 16:04


https://youtu.be/A6gruNm13ug?si=hL8bC1XP9D_ShMJr

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

30 Nov, 14:46


ለጸሎት ቦታ የሚሆኑ መብራት ያላቸው ቅዱሳን ስዕላት በተመጣጣኝ ዋጋ @abigezenige

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

30 Nov, 09:02


ቤተሰብ እንዴት ናችሁልኝ። ዛሬ እመቤታችን ናት አንድ ነገር ላስቸግራችሁ ነው።
ይህን ከታች የሚታየው ከአልሙኒየም የተሰራው ከ10-20 ደቂቃ በፍጥነት ሻማ የሚያመርት ማሽን እንድትገዙኝ እጠይቃለሁ።
ብሩ አስቸኳይ ስለተፈለገ ነው ❤️
+251933143133 ደውሉልኝ።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

30 Nov, 08:23


"ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥..." (መዝ.87:5)
"ልጄ ሆይ በርታ ሰውም ሁን፤ " (1ነገ. 2:3)
"እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤" (ሉቃ.1:48)

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

30 Nov, 05:45


https://youtu.be/IGYODXJg2Wc?si=32X9k-lIImIkrtyw

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

29 Nov, 11:30


ለቀጣይ የአእላፋት ዝማሬ እንዲህ የሚያማምሩ ነጭ ልብሶችን የወንድም የሴትም በተመጣጣኝ ዋጋ እናቀርባለን።
@abigezenige ላይ ጻፉልኝ።
https://t.me/abizeeotcgift አቤኔዘር የባህል አልባሳትና መንፈሳዊ ስጦታዎች online shop

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

28 Nov, 17:55


ለቀጣይ የአእላፋት ዝማሬ እንዲህ የሚያማምሩ ነጭ ልብሶችን የወንድም የሴትም በተመጣጣኝ ዋጋ እናቀርባለን።
@abigezenige ላይ ጻፉልኝ።
https://t.me/abizeeotcgift አቤኔዘር የባህል አልባሳትና መንፈሳዊ ስጦታዎች online shop

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

28 Nov, 16:07


https://youtu.be/Oq0HoHd-Epc?si=X1CsMwtOBKTyzQ6Z

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

26 Nov, 12:58


https://youtu.be/mj9Gm22zdAY?si=KzA1vyvO8UiBWXuC

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

24 Nov, 12:20


በአነስተኛ ክፍያ ባሉበት ሆነው እውቀትን ይገብዩ። ለመመዝገብ ሊንኩን ተጭነው በመግባት መማር እፈልጋለሁ ብለው ይፃፉ።
👇
https://t.me/+WrWwg2Or0tJhOWE0

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

24 Nov, 06:16


17. መስፍኑም በአራት በኩል ወጥራችሁ እሠሩትና በከብት ጠፍር ግረፉት፤ አንተ ወታደር ሁንና ወደ ንጉሡ ትእዛዝ ተመለስ በሉት አለ። ብፁዕ ሚናስም የክርስቶስ ወታደር ብሆን ወደ ታላቁ ንጉሥ ወደ ክርስቶስም ብመለስ ይሻለኛል አለ። ያን ጊዜም ደሙ በወደቀበት ምድር እስኪሟላ ድረስ ጽኑ ግርፋትን ገረፈው። መስፍኑም ሥጋህ ሰግርፋት ፈጽሞ ከመቆራረጡ በፊት ለአማልክት መሥዋዕት ሠዋ አለው።

18. ብፁዕ ሚናስም አመፅን የምትመክር ሰው ሆይ በክፉ ሥቃይህም አልመለስም ሂድ። የሚቻለው ረዳቴ እግዚአብሔርም ይህችን ስቃይ ፈውስ ያደርጋታል አለው ገዢውም በደነደነ ልቡናው ደግማችሁ ግረፉት በዕንጨትም ስቀሉት ሥጋውንም ቆራርጡት አለ ሲቆራርጡትም ገዢው ሚናስ ሆይ በዚህ ሥቃይ ደነገጥህን ይህ ግርፋትስ ታወቀህን አለው።

19. ቅዱስ ሚናስም በዚህ ስቃይ ሐሳቤን የምትለውጠው መሰለህን አለው። እኔ የክርስቶስ ወታደር ነኝ እንድበረታም ይረዳኛል አለው ገዢውም እንደገና አሰቃዩት፤ ሌላ ንጉሥ ካለህ ንጉሥህን አሳይም በሉት አላቸው ቅዱስ ሚናስም ሰማያዊውን ንጉሥ ተሳደባለህን አለው። ገዢውምአምላክ ማን ነው የምትለውን አላውቀውም አለው። ብፁዕ ሚናስም በቅድምና የነበረና ሁሉን የፈጠረ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው አለው። መስፍኑም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነገሥታቱ እንደተቈጡ አላወቅህምን አለው። ክርስቶስን የሚጠራም ሁሉ እንዲፈረድባቸው አዘዙ። ስሙን ለማመስገን ለምን

ትበረታለህ።

21. ቅዱስ ሚናስምቢቈጡ በእኔ ምን አገባህ፤ እኔ ይህን መገዛት ዘወትር ልጠብቀው እሻለሁ። ከዚህ ከንቱ ዓለምም እድናለሁ፤ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አለና። “የክርስቶስን ፍቅርን ማን ያስተወኛል፤ ኀዘን ነውን፣ ችግር ነውን፣ መራቆት ነውን” የእግዚአብሔርን አገልጋይ ማሸነፍ የሚቻለው እንደሌለ ዐውቃለሁ አለው። ገዢውም በሌላ አካል እንደ ሚሠቃይ እነሆ ለመከራ ተዘጋጅተሃል አለው።

22 ገዢውም ሚናስ ሆይ ላአማልክት ሠዋ፤ አንተንም አከብርሃለሁ አለው። ቅዱስ ሚናስም ለጥፋት ሰዎች ስጥ እኔ ግን የሚጠብቀኝን ክብር እቀበላለሁ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነው ተብሎ ተጽፏልና የአንተው ክብር ምሳሌ ነው በእግዚአብሔር ዘንድም ከንቱ ነው። በእግዚአብሔር ማክበርና ለገናንነቱ መገዛት እነርሱም የተቀደሰ ብርሃንን ሕይወትን ወራሾች ያደርጉናል።

23. ገዢውም የሰማዕቱ የሚናስ የሃይማኖቱን ጽንአት በተመለከተ ጊዜ ይገድሉት ዘንድ አሰበ፡ እንዲህ የሚል ፍርድንም በእርሱ ላይ ፈረደለንጉሡ የማይታዘዝ ለአማልክት የማይሰዋ ይህ በደለኛ ወታደር ሚናስን ወደ ሞት ፍርድ ይወስዱት ዘንድ እኛ አዝነናል ለአማልክተ ይሰዋ ዘንድ አልሰማምና ዳግመኛም ሥጋውን ከእንሰሳት ይጨምሩት ዘንድ አዝዘናል አለ።

24. ያን ጊዜም ብፁዕ ሰማዕት ሚናስን ወደ መገደያ ቦታው ወሰዱት የሀገሩ ሰዎችም ሁሉ የቅዱስ ሚናስን ምስክርነት እየተደሰተም በብሩህ ፊት ወደ ሞት ሲሄድ ይመለከቱት ዘንድ ተከተሉት ። ለክርስቲያኖች አርአያም ነበር ለሚያውቃቸውም ሃይማኖትን ያስተምራቸው ነበር። ስለ መንግሥተ ሰማያትም ያስብ ነበር። ያገኘው መከራም አልነበረም በእግዚአብሔር ተማመነ ወደ እርሱም ተማጸነ እንጂ በእርሱ ላይ እንደ ፈረዱበትም ላፍርዱ ተፋጠነ።

25. ለዚህ በጎ ነገር ዝግጁ ያደረገው ክርስቶስንም ጠራ። ፊቱንም ወደ ሰማይ አንጋጠጠ ጸጋውን በመተማመን የተቀደሱ እጆቹንም ዘረጋ። የሰማይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አመሰግንሃላሁ አልተውኸኝምና፤ ጠላት ያጠፋኝ ዘንድም ከእኔ አልራቅህምና የተቀደስ ስምህን እንዳልክድም ነጻነት/ጥንካሬን አደልኸኝ ዛሬም በዚህችን ሰዓት ጠብቀኝ እስከመጨረሻውም ትዕግሥቱን አድለኝ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ነፍሴ ተቀበላት በየጊዜያቱም ለአንተ እሰግዳለሁ አለ።

26. ይህን ነገር ከተናገረ በኋላም ወደ ምስክርነቱ ቦታ /ወደ ሰማዕትነቱ ቦታ/ ሄዶ። ፈጥኖም አንገቱን ሰጠ። በሰይፍም መቱት ራሱም ከአንገቱ ተለየ። ወታደሮችም የተቀደሰ ሥጋውንተሸከሙት፤ ከእሳትም ጣሉት። ያመኑ ወንድሞች ወታደሮች በዚያ ነበሩ። ፈጽመውም ብዙዎች ነበሩ እሳቱንም አጠፉ አስከሬኑንም በተከበሩ ልብሶችና በብዙ ሽቱም ገነዙት ከእነርሱ ወደ አንዱ ቤት ወሰዱት ትዕግሥትን ያደለው እግዚአብሔርን እያመሰገኑም በፍጹም ደስታ ወደሳጥን አስገቡት በሰውነቱም የእሳት ምልክት አልነበረበትም።

27. ምስክርነቱም ኅዳር ዐሥራ አምስት ቀን እንዲህ ተፈጸመ። ወደ እውነተኛው ንጉሥ ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሄደ ክብርና ምስጋና ከሃሊነትም ለእርሱ ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።

ይህ አዲስና ብፁዕ የሚሆን የተከበረው ሰማዕት ሚናስም በኃይሉ ፍፁም ነው አቋሙና ሃይማኖቱም ፍጹም ነው ከታናሽነቱና ከጎልማሳነቱ ጀምሮም ጸባዩ ደግ ነው። የዋህ ይቅር ባይ እንግዳና ድሆችንም ወዳጅ ነበር። አስቀድመን እንደተናገርነው ምስክርነቱ ከተፈጸመ በኃላም አምስቱን ሀገሮች ይወጉ ዘንድ ሠራዊቱ መጡ።

መርዩጥ የተባለችዋ ሀገርና አውራጃወች ታወኩ። የመርገጥን ሰዎች ይረዷቸው ዘንድ ከአፍራቅያ ወደ እስክንድርያ ወታደሮች እንዲመጡ ትእዛዝ ወጣ።

28. መስፍኑ አትናሲስም ረዳትና አዳኝ ይሆነው ዘንድ የቅዱስ ሚናስን አስከሬን ሊወሰድ ወደደ። አስከሬኑ ያለበትን በር ከፈተና ታላቅ ብርሃንን አበራ ከሰዎቹ ወገን እንዳይከለክሉትም ሰውሮ መርከብ አወጣውና ሄደ። ከባሕር መካከል ሲደርሱም በባሕሩ ውስጥ የሚያስደነግጡ አራዊትታዩዋቸው። አንገታቸውም ታላቅና ረጃጅም ነበር፤ ፊታቸውም እንደ ግመል ፊት ነበር። በውስጥ ያለውን ይወስዱ ዘንድም አንገታቸውን አስረዝመው ወደ መርከቡ ይመለከቱ ነበር። በፊታቸውም ከቅዱስ ሚናስ አስከሬን የእሳት ጦር ወጣ፤ ሸሽተውም በባሕር ተሰወሩ።

29. ከዚህ በኋላም ተመለሱ። ዳግመኛም ይህ የእሳት ጦር ከለከላቸው። ከዚህ በኋም ሰገዱለት ሄዱም። በባሕር ያሉ የመርከቡ ሰዎችም ሁሉ አደነቁ በእግዚአብሔርም አመኑ ሰማዕቱ ሚናስንም ፈጽመው አመስገኑ። በአስከሬኑ ድነዋልና ከአምስት ቀን በኋላም እስክንድርያ ደረሱና ከዚያ አወጡት። ከእስክንድርያ እስከ መርዩጥ ሐይቅ ድረስም ከእነርሱ ጋር ወደመርከቡ አስወጡት። በዚያም ከሽፍቶች ጋር ተጣሉ።

30. ቅዱስ ሚናስንም ማለዱት በአስከሬኑም ሽፍቶችን አሸነፏቸው። የመርዩጥ አውራጃ ከምትሆን ሚስቲን እስከሚደርሱ ድረስም በአማላጅነቱ አጠፏቸው። ገዢው ወደ አፍራቅያ ሊመለስ በፈለገ ጊዜም አስከሬኑን ከእርሱ ጋር ሊወስደው ወደደ። በግመልም ጫነው ግመሉም ሊንቀሳቀስ አልቻለም በሌላ ግመልም ጫኑት መንቀሳቀስ አልቻለም እንደዚሁም ሁሉ በእነርሱ ዘንድ ባሉት ግመሎች ሁሉ ጫኑት ማንሣት የቻለ ግን የለም።

31. ገዢው አትናሲስም አዘነ። እግዚአብሔር እንደሆነም ተረዳ በዚያም ተወው እንደወታደር ሆኖ በሚያውቀው በዚያ አርአያም በእንጨቱ ላይ የሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስን ሥዕል አዘጋጀ።
ግመልየሚመስሉ የአራዊትን ሥዕልም ከእግሩ በታች አዘጋጀ ሰገደለትም ያችን ሥዕልም ስለ አማላጅነቱ ከቅዱስ ሚናስ አስከሬን አስቀመጣት።

32. ከዚያ በኋላም በባሕር ድኅነትና መጠጊያ ትሆነው ዘንድ ከእነርሱ ጋር ወሰዳት። አስከሬኑም ከማይነቅዝና ከማያረጅ ዕንጨት ሳጥን ሠራ። በዚያ ቦታም ቀበረው ከሠራዊቱ ጋርም ወደ ሀገሩ ተመለሰ። እግዚአብሔር በወደደ ጊዜምበቅዱስ ሚናስ አስከሬን ኃይሉን ተአምራቱን ይገልጥ ነበር።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

24 Nov, 06:16


የቅዱስ ሚናስ ገድል

1. አንድ አምላክ በሆኑ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም የሚነበብ ቅዱስ፣ ብፁዕ፣ ጽኑእና ተጋዳይ የሚሆን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕት የቅዱስ ሚናስ ምስክርነቱ ይህ ነው። ጸሎቱ ከሁላችን ጋር ትሁን ለዘለዓለሙ አሜን። ይህ ቅዱስ ሰማዕቱ ሚናስ ሀገሩ ግብጽ ነው። ስሟም ቄጥዋ ይባላል። በገዢው ስምም በውስጧ አዳራሽን ሠራ፤ ቅጥሮቿንም አጠበቀ።

2 የቅዱስ ሚናስ አባቱ ስምም አዶክሲስ ይባላል የእናቱ ስምም አፎምያ ይባላል፤ ክርስቲያናት ነበሩ። አውዶክሲስንም ሰው ይወደው ነበር። ወንድሙ አንጣልዮስም በእርሱ ላይ ዋነ፣ በንጉሡ በአብራኪዮስ ዘንድም ነገር ሠራ፤ ንጉሡም በአፍራቅያ ሾመው፣ባለጸጋም ነበር። ከእስክንድርያም ሀብቱንና ሚስቱን ወደ አፍራቅያ ወሰደ። ልጅ ስላልነበራቸውም ከሚበቱ ጋር ያዝኑ ነበር።

3. ከዚህ በኋላም ሚስቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደች። ለዘለዓለሙ ክብርና ምስጋና ይግባውና የአብ ቃሉ የጌታችንና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል ነበርና፧ ምስጋና ለእርሱ ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።

4. ሰዎች ከቅድስት እመቤታችን ይባረኩ ዘንድ ልጆቻቸውን ሲያመጡ በተመለከተች ጊዜም ጽኑ ለቅሶን አለቀሰች። ጸለየች ለመነች፣ ተማጸነች፣ከእመቤታችን ከማርያም ሥዕልም አሜን የሚል ቃልን ሰማች። ከዚህ በኋላም ጸነሰች፤ ልጅም ወለደች፤ ስሙንም ሚናስ አለችው። ይህን ስም ከሃይማኖት ከማመን የተነሣ አግኝታዋለችና፤ አባቱም ስለ እርሱ ተደሰተ። ከእስር ቤት የነበሩ ወንጀለኞችንም ፈታ ለድሆችም ብዙ ገንዘብ መጸወተ።

5. ባደገ ጊዜ የሚያስፈልገውን መለኮታዊ ጥበብ ያለባቸውን መጻሕፍት አስተማረው ይጾምና ይጸልይም ነበር። ዐሥራ አንድ ዓመት ሲሆነውም አባቱ ሞተ ከሦስት ዓመት በኋላም እናቱ ሞተች በብቸኝነቱም ፈጽሞ አዘነ፤ የሙት ልጅም ሆነ ገንዘቡን ሁሉ መጸወተ በጾምና በጸሎት ተወስኖም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደ።

6. ከአባቱ ሰኋላ በአፍራቅያ የተሾመው ገዢም ፈጽሞ ይወደው ነበር ሰግድም ወሰደው ወታደርም አደረገው ያን ጊዜም ዕድሜው ዐሥራ አምስት ዓመት ነበር ከእነርሱ በታችም እንደራሱ አድርጎ ሾመው በጋይዮስ በአውልርዮስ፣ በፍልስዮስና በመግሲማኖስ ዘመነ መንግሥትም ለረከሱ አማልክት ይገዙ ዘንድ ሕዝቡን ጠራቸው ትእዛዛቸውም እጅጉን የከፋ ነበር። መጻሕፍትንም ጸፉ፤ በየሀገሩም ሁሉ ላኩ። ግዛታቸው ከአፍራቅያ ሀገሮች የምትሆን እስከ ቈጠላም ንስ ነበር።

7 ያን ጊዜ በዚያ አርኮሪቆስ አብዳዲቆን፤ ምልያኖስ ይገዙ ነበሩ ትእዛዙን የሚያስፈጽሙ ወታደሮችም ነበሩ። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕት የሆነ ብፁዕ ሚናስም በእውነት ከእነርሱ ጋር ነበር። በመካከላቸውም እንደ ኮከብ ያበራነበር፤ ሹማምንቱም በደብዳቤው የተጻፈውን ትእዛዝ ለመፈጸም ተፋጠኑ ጽሕፈቱም እንዲህ ይል ነበር። ቅን ፍርድን ስለሚሰጡ አማልክት በመታዘዛችሁ ሁላችሁም ደስ ይበላችሁ እኛም በመትጋት /በመጨነቅ በማምለክ በቀርጥ ይሠዉላቸው ዘንድ ወደድን።

8. ስለዚህም ለሁሉም ሹማምንት ለሁሉም ሀገር ወታደር ሴቱም ሕጻናቱም ሳይቀር ፍፁም ትጋትና በስግደት ትእዛዙን ይፈጽሙ ዘንድ አምላክ የወሰነውን ትእዛዝ የማይቀበለውን ያለምንም ርኅራኄ በስቃያት ሁሉ ያሰቃዩት ዘንድ በሥልጣናችን አዝዘናል የሚል ነበር።

9. ያን ጊዜም ከሐድያኑ አማልክትን ማምለክን ይቀበሉ ዘንድ ለወንዶችም ለሴቶችም አሰምተው ተናገሩ። ወደ እነርሱም ይመለሱ ዘንድ ስለ እነርሱም ታላቅ ሁከት ሆነ። የክፉ ነገሥታትን ትእዛዝ ይፈጽሙ ዘንድም ሁሉንም በማታለል ግድ ይላቸው ነበር። ቅዱስ ሚናስም ይህን በተመለከተ ጊዜ ወደ ገዳም ሄዶ በዚያም እያገለገለ ተቀመጠ። በዚህች ሀገር ኃጢአትን በደልን አየሁ፤ ርቄም ሸሸሁ። አምላኬ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስን አገለግለው ዘንድም በገዳም ኖርሁ አለ። በዚያም በጽኑ ስቃይ በአገልግሎት ጸንቶ ብዙ ዘመን ቆየ።

10. ከዚህ በኋላም የእግዚአብሔር ጸጋ በእርሱ ላይ አደረ ሰማይ ሲከፈትም ተመለከተ። ውስጡም የብርሃን አክሊልን በተሸመውና ምስክርነታቸውን ሰማዕትነታቸውን ባከናወኑ ሰዎች ራስ ላይ በሚያኖሩ ብርሃናውያን መላእክት የተሞላነበር። በታላቅ ክብርም እንደ ፀሐይ እያበሩ ያሳርጓቸውነበር።

11 ከዚህ በኋላም ቅዱስ ሚናስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰማዕት ይሆን ዘንድ እንዲህ ሲጸልይ ከሰማይ ቃል ጠራው። ሚናስ ሆይ አንተ ብፁዕ ነህ። ተጠርተሃል፤ ከታናሽነትህ ጀምሮም እስከ ዛሬ ድረስ በጎ ኅሊናን ገንዘብህ አድርገሃልና። በፍቅራቸው ያደግህ አንተ በተቀደሰች ሥላሴ አምሳል የማይጠፉሦስት አክሊሎችን ትቀዳጃለህ። አንዱ ስለ ድንግልናህ ነው፣ አንዱ ስለ ምናኔህ ነው፣ አንዱም ስለ ምስክርነትህ ነው። ከብዙ ሰማዕታት የበለጠ ይሆናል፤ ስምህም ክቡር ነው።

12. ብዙ ሰዎችም ከሁሉም ሀገር ይመጣሉ፤ በግብጽ ምድር በስምህ ወደታነፀችዋ ቤተ ክርስቲያንህም ይገሠግሣሉ ኃይልን ድንቅ ነገርን ተአምርን ከተቀደሰው ሥጋህ የሚደረገውን ፈውስም ይመለከታሉ አለው። ያን ጊዜም ይህን ነገር ሰምቶ ፍጹም ደስታን ተደሰተ፤ ተነሣም። ከሐዲዎቹ ለጨዋታ ተሰብስበው እያሉም በመንፈስ ከፍ ከፍ አለ መኳንንቱም ሰውም ሁሉ በተሰበሰቡበትም ይዘምር ጀመር። ወደ ሚያጎሳቁሉኝ ሰዎች መጣሁ ስለ እኔ ለሚጠይቁ ሰዎች ተገኘሁ አለ። እነርሱም ደነገጡ ዝምም አሉ በክርስቲያናዊ አለባበስ በተመለከቱ ጊዜም ተጋድሎውን አደነቁ።

13. ገዢውም አንተ ማን ነህ አለው። ቅዱስ ሚናስም የፍጥረቱ ሁሉ ንጉሥ የሚሆን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ነኝ አለው፡ገዢውም ልጄ ሆይ በዚህ ዓይነት አለባበስ ከዚህ የገባህ አንተ ልዩነህን፤ ሕዝቡንስ በትምህርትህ ከመገዛት ትከለክላቸዋለህን አለው። የሚያውቁትም ነበሩ ገዢውንም ይህን ወታደር እናውቀዋለን። በአውጣዲቆን ዘንድ ነበር አሉት ገዢውም ወታደር ነህን አለው፡

14. ቅዱስ ሚናስም አዎ፧ በፊት ወታደር ነበርሁ። ስለካዳችሁ ግን ተውኋችሁ አለው። ገዢውም የተለየህ ወይም ክርስቲያን ካልሆንህ ለምን ተውኸው አለው። ገዢውም ያስሩት ዘንድ አዘዘው። በማግስቱም ወደ አደባባይ አመጣውና ከሐዲው ገዢ ወደዚህ ሜዳ ትገባ ዘንድ እንዴት ደፈርህ፤ ተግሣጽ እንደሚያደርግ እኔ ክርስቲያን ነኝ በማለትህ ነገሥታን አዋረድሃቸው። እስኪ ንገረኝ ወታደሬ መሆንን ለምን እንቢ አልህ፤ ይህን ያህል ግዜ ቆየህ? የትስ መጣህ አለው።

15. ቅዱስ ሚናስም እኔ ከግብጽ ሰዎች ወገን ነኝ የሰማያዊው ንጉሥ ወታደር ለመሆን ስለፈለግሁም ኃላፊ ጠፊ የሆኑ አማልክትን ተውሁ አለው። መስፍኑም እስከ ዛሬ ድረስ የትቆየህ አለው። ቅዱስ ሚናስም እግዚአብሔርን ከማያውቁት ጋር ከምጠፋ በጫካ ከአንበሶች ጋር ብኖር ወደድሁ አለው። በእጃቸው አመጽን ከተሞሉ ለሕይወቴ ጠላት ከሆኑ ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን አታጥፋት የሚል ጽሑፍ አለና አለው።

16. ገዢውም ዛሬም ለአማልክት ሠዋ አንተ ወታደር ስለሆንክ ጥፋትህን ይቅር እንልሃለን። ሰውዬ ሆይ ክርስቲያናዊ ወታደር መሆንህን እንደ ተውህም በራስህ ማል፤ ቀርበህም ለአማልክት ሠዋ ወደ ሹመትህም ተመለስ ራስህንም ከስቃይ ጠብቅአለው። ቅዱስ ሚናስም እኔ የነገሥታትን ንጉሥ ላገለግል እወዳለሁ። ከሞት ይልቅ የነጻነትን አክሊልም እቀዳጃለሁ፤ በማስፈራራት ወደምትፈልገው የምትወስደኝም አይምሰልህ። ለአምላኬ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስለተገዛሁ ስቃንዩን ሁሉ ቀላል አድርጌዋለሁና አለው። .

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

24 Nov, 06:16


33. የሚያነክስ ሰውም ወደዚያ ቦታ ሄደ። በሰማዕቱ በቅዱስ ሚናስ መቃብር ላይ የሚያበራ ብርሃንንም ተመለከተ። ወደ እርሱም ቀረበና ተጠጋው፤ በዚያም መንገደኞች ቁመው ነበሩ አባቱም ፈለገውና በዚያ አገኘው መታውም በፊታቸውም እየዘለለ ሮጠ። እግሩም ዳነ በዚያ ያሉ ሰዎችም አደነቁ ልጁም ያየውን ነገራቸው እግዚአብሔርም ዓይኖቻቸውን ገለጠ። መብራቲቱንም ስታበራ ተመላከቷት አመኑም።

34. የተለያየ ደዌ ያለባቸውም በአንድነት ከሀገራቸው ወጡና ወደ ቅዱስ አባ ሚናስ መቃብር መጡ። በእግዚአብሔር ኃይል በቅዱስ ሚናስ አማላጅነትም ተፈወሱ። ታላቅ ደስታም ሆነ ዜናውም በመርዩጥ ተሰማ በዚያ ያሉት ደዌ ያደረባቸውም ጋኔን ያላባቸውም ሁሉ ወደ እርሱ እየሄዱ ፈጽመው ይፈወሱ ነበር።

35. ያን ጊዜም በመቃብሩ ላይ እንደ ድንኳን ያለች ቤተ ክርስቲያን ሠሩ። በውስጡም በአዩትአምሳል መብራት ሰቀሉ፤ በዘይት ተነክሮም በቀንም በሌሊትም ያበራ ነበር። ከመብራቱ ዘይት የተቀባ ሁሉ ይፈወስ ነበር። ከመብራቱ ዘይት ወደሩቅ ቦታ ወስደው ሲቀቡት በሽተኛው ሰው ካለበት ደዌ ይፈወስ ነበር። ሕዝቡ ወደ እርሷ

ይሰበሰቡና በውስጧ በዓልን ያዘጋጁ ዘንድም እግዚአብሔርን በሚወድ በንጉሡ በታኦስ እርዳታ በእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አትናስዮስ ዘመን በዚያ ቤት ክርስቲያን ተሠራች።

36. የቤተ ክርስቲያኗ ሥራ ከተፈጸመ በኋላም ቅዱስ ሊቀ ጳጳሳቱ ካህናቱን ሰበሰባቸው። የሰማዕቱ የሚናስን አስከሬን በውስጡ አስቀመጠ። በንጉሡ በቅዱስ ቴዎዶስዮስና በሊቀ ጳጳሳቱ በአባ ቴዎፍሎስ ዘመንም ቀደሳት በአከበራት/። በቅዱስ ሚናስ ስም ከሚሰበሰቡት ሕዝቦች ብዛት የተነሣም በእመቤታችን በቅድስት ማርያም ስም በዚያ ቦታ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ተሠራች።

37. በንጉሡ በዜኖን ዘመንም ወደ እርሷ መጣ። በዚያም ቤቶችን ሠሩለት በዚያ ቤታቸውን ይሠሩ ዘንድም ከተማውን አዘዙ። የግብጽ ሀገር ገዢዎችም በዚያ ቤታቸውን ሠሩ። ከሚታየው ተአምር ብዛት የተነሣም ዘወትር ወደ እርሷ ይመጡ ነበር። በሊቀጳጳሱ በጢሞቴዎስ ዘመንም በዚያች ታላቅ ሀገር ይህ ተደረገ (ተፈጸመ)። ንጉሡ ዜኖንም ስም አወጣላት፤ በዚያም ፈጽመው ብዙ ሰዎች ነበሩ።

38. ጻድቁ ንጉሥምከኢሎፍላውያን ይጠብቋት ዘንድ ቤተ ክርስቲያንንና ወደ እርሷ የሚመጡ . ሕዝቦችን ይጠብቁ ዘንድ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችበዚያ እንዲኖሩ አዘዘ። ከመርዩጥ ግብርም ለምግባቸው አዘዘ፤ የተዘጋጀውን ምግብም ወደ እርሷ ለሚመጡትና ለድሆች አዘዘ፤ በየዓመቱ እንዲወስዱም አዘዘ። በእንደዚህ ዓይነት ሥርዓትም እስከ ሮሙ ንጉሥ እስከ ሕርቃል ዘመን ድረስ ቆዩ። ከእርሱም ወደ ቅዱሱ ሰማዕት ቤተ ክርስቲያን እየሄዱ አሕዛብ የግብጽን ሀገር ገዙ ።

39. ተአምራትን ይገልጥላቸው ነበር። ወደ እርሱም መባ ያመጡ ነበር፤ የልባቸውን መሻትም ያደርግላቸው ነበር። ባደረገላቸውም ጊዜ ፈጽመው ይደሰቱ ነበር። የተአምራቱና የሥነ ምግባሩ ዜና የጸሎቱ ኃይል በእግዚአብሔር ዘንድ እስከ ዓለም ዳርቻ ደርሷልና። እግዚአብሔር አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም በቅድስት ድንግል ማርያም በሰማዕታትና በቅዱሳን አማላጅነት እኛን የጥምቀት ልጆች ይጠብቀን ዘንድ እንለምነው አሜን።

40. የቅዱስ ሚናስ ተጋድሎ ተፈጸመ እግዚአብሔር በጸሎቱ ይጠብቀን አሜን። የቅዱስ አባ ሚናስ ተአምርም በዐሥራ አምስት ቀን ተጻፈ። በዚያን ዕለትም ይነበባል። በዐሥራ ስምንት ቀንም ሐዋርያው ፊልጶስ ነው። ከሐዋርያት ገድል ወስደህም በእግዚአብሔር ሰላም ኅዳር ዐሥራ ስምንት ቀን አንብብ አሜን፤ አሜን። ይሁን፤ ይደረግ።

#ቅዱስ_ሚናስ #orthodox #tewahedo #አቤኔዘርዘተዋሕዶ አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

22 Nov, 07:24


የባህል ልብስ ወይም የስጦታ እቃ ከእኔ መግዛት የምትፈልጉ ይህን አዲሱን channel ተቀላቀሉ
https://t.me/abizeeotcgift

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

21 Nov, 19:43


ሁለተኛውን ዙር በቀጥታ ስርጭት አውጥተናል።
ለሶስት እጣ እነዚህን ተደጋጋሚ ቁጥሮች አውጥተናል ግን ከ1ኛው እጣ በስተቀር ሌሎች ያልተቆረጡ እጣዎች ሆነዋል።
1ኛ እጣ 100 ቁጥር ተቆርጧል።
ለተሳተፋችሁ በሙሉ እግዚአብሔር ያክብርልኝ። ቅዱስ ሚካኤል በወጣ ይተካላችሁ።
ለሶስተኛው ዙር ያገናኘን።
አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

20 Nov, 20:01


☞ ኅዳር 12 እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ሆኖ ለተሾመት አመታዊ በአል አደረሳችሁ፡፡
☞በኀዳር በ12 ቀን የመጀመሪያ በዓሉ ነው፡፡
☞በዚህ ቀን እግዚአብሔር በሰማይ ሁሉ በላይ አድርጎ ሾሞታልና፡፡
☞ስለ ትሕትናው ሰለ መታዘዙ ፤ጌታውን የናቀ፤ያቀለለ፤ በጎ ነገርን የሚጠላ ሰይጣንን ድል ሰለነሣ፡፡
☞ዳግመኛም በትንሣኤ ጊዜ የማይፈጸም ታላቅ ክብር ይሰጠዋል፡፡
☞ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ በመጀመሪያው ዓዋጅ ሹመትን እንደሰጠው፡፡
☞ዳግመኛ በሁለተኛው ዓዋጅ ጊዜ በሰይጣን ምክር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰቀሉት በሐሰተኞች በአይሁድ ላይ ክብርን ገናንትን ይሠጠዋል፡፡
]ክርስቶስ ከሙታን አልተነሣም ብለው የሚክዱትን ቅድስ ሚካኤል ክፋዎች ወደ ተዘጉበት ይጨምራቸዋል፡፡
☞ትንሣኤ ሙታንን ያመኑ የጥምቀት ልጆች ጻድቃንን ወደ ገነት ያገባቸዋል፤ ወደ አብ፤ ወደ ክርስቶስም ያቀርባቸዋል፡፡ ሰለነሱም ደስ ይለዋል፡፡
]ለመናገር በማይቻል ፍጽም ክብር የመላእክት አለቃ ቅድስ ሚካኤል ያከበረው ቅድመ ዓለም የነበረ እግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስም ነው፤ ከቀድሞው ይልቅ የሚበልጥ ክብር በሰማይ ባሉ መላእክት ላይ ፈጽም አከበረው፡፡
☞የመላእክት አለቃ ቅድስ ሚካኤልን ወደ ወደደው ሁሉ ይለከዋል፡፡
☞ዳግመኛ በበዓሉ ቀን ቅድስ ሚካኤል ይመጣል፡፡ ክብር ምስጋና ይግባውና በእግዚአብሔር ፈቃድ ክንፎቹን ወደ ሲኦል ያወርዳል፤ ወደ ላይም ያወጣቸዋል፡፡
☞ኃጥኣንም እግዚአብሔር ይቅር ያላቸው የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል ሠራዊት ይሆናሉ አንድ ጊዜ በክንፋ የሚያወጣቸው ቁጥር ሰፍር የላቸውም፡፡
☞የፈጣሪውንም ስም ጠርተው (አምላከ ሚካኤል ብለው ለድኆችና ለችግረኞቾ ጥቂት ሰለ መፀወቱ ያወጣቸው የኃጥአን ነፍሳት ብዙዎች ናቸው፡፡
☞በመላአክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ስምም ለድሀ፤ለችግረኛ አንድ እንጀራ ስለሰጡም ሰዎች ወደ ሲኦል እንዳይጨምሯቸው ይለምንላቸዋል፡፡
]ሰለ ኃጢአታቸውም ሥርየትን ምሕረትንና ይቅርታን ከጌታችን ከእየሱስ ክርስቶስ ያገኙ ዘንድ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያቀርባቸዋል፡፡
☞በቅዱስ ሚካኤል ስም በጎ ሥራ የሚሠሩትን ሁሉ ይቅር ባይ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ አይተዋቸውም፤ አይጥላቸውም፡፡
☞ወንድሞቼ ሆይ ሰሙኝ ልንገራችሁ፤ በእዝነ ልቡናችሁም በማስተዋል አዳምጡኝ፤ ክቡር ገናና የመላአክት አለቃ የሆነ የቅድስ ሚካኤል መታሰቢያ አድርጉ፡፡ ፋጻሜ የሌለው ደስታንና የዘለዓለም ሕይወትን ታገኙ ዘንድ፡፡
☞ምሕረትን ለሰው የሚጠቡቁ መላአክትም በኅዳር 12ቀን በአብ በመንጦላዕቱ ፊት ይሰበሰባሉ በዚህ ጊዜ የመላዕክት አለቃን ቅድስ ሚካኤልን ከአብ ከመንጦላዕቱ ውስጥ በወጣ ጊዜ ይቅር ባይ አብ የሰጠውን ለብሶ ያያሉ መሪያቸው ፍቅር አንድነትን የሚያስገኝላቸው ይቅርታን የሚያመጣላቸው አለቃቸው ነውና፡፡
☞በመላእክት አለቃ በቅድስ ሚካኤል ስም ለቤተ ክርስቲያን እጅ መነሻ፤ ዕጣንም ሰምም ቢሆን ሌላጠጌጥም ቢሆን ቢሰጥ፡፡ አንድ እንጀራ አስከ መስጠት ደርሶ በጎ ሥራ የሠራ ሁሉ፤ ይህም ባይሆን ለድሀ ጥዋ ውኃ በእጅ ቢሰጥ ሰለሱ ከመለመን ቅድስ ሚካኤል አያርፍም፡፡ ኃጢአቱ እንደባሕር አሸዋ፤ እንደሣር ቅጠል ቢበዛ ይሠረይለታል፡፡
☞ቅዱስ ሚካኤል መታሰቢያውን ሰለሚያደርጉ ሰዎች ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ይለምናልና፡፡ በጽሎቱ ረድኤት በኃይሉ፤ በክንዱ በጸጋው በፍቅሩ ለዘለዓለሙ ይሠወራቸዋል ይጠብቃቸዋል፡፡
☞የመላአክት አለቃ ለአንተ ሰላም እላለሁ፡፡
☞ጨካኝ ያይደለህ ለሁሉ የምትራራ አለቃችን ሚካኤል ባልንህ ቁጥር ጣዋት ማታ በረዲኤትህ ጥላ ሰውረን፡፡
☞ይህን መጽሐፍ በብራ የጻፈውን በደራሲነት ያስጻፈው፤ ያነበበውን በቀና አንደበቱ የተረጎመውን፤ቃሉን በእዝነ ሕሊና የሰማውን ከጠብ ከክርክር ሁሉ የምታስታርቅ እናቱ ማርያም በማላጅነቷ እግዚአብሔር በቸርነቱ ቅዱስ ሚካኤል በተራዳይነቱ በአንድነት ይቅር ይበሉን፡፡

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

20 Nov, 17:17


እግዚአብሔር ቢፈቅድ ነገ በዚህ ሰዓት እጣው ይወጣል።

2ኛ ዙር እጣ

1ኛ እጣ የአክሱም ጽዮን ማርያም ጉዞ ሙሉ ክፍያ፥ የበርሚል ጊዮርጊስ ጉዞ ግማሽ ክፍያ ወይም በገና መሰንቆ ክራር [በምርጫ አንዱን]

2ኛ እጣ በወርቀ ዘቦ ወይም በ epoxy ያማረ ስዕለ አድኖ [በምርጫ አንዱን]

3ኛ እጣ የተደጎሰ የጸሎት መጽሐፍ [በምርጫ አንዱን]

በ200 ብር 200 ሰው የሚያሳትፍ እጣ

ከ200 ቁጥሮች ውስጥ የመረጡትን [ቀድሞ ያልተያዘ] ቁጥር መያዝ ይሆናል። በመጨረሻም በቀጥታ ስርጭት እጣው ይወጣል።

ያልተያዙ ቁጥሮች
31-62
65-71
75-87
89-95
97-98
101-118
130-149
151-154
156-169
172-173
175-187
189-196

ከቁጥር 0-200 ካሉ ቁጥሮች ውስጥ በእጣ መቁረጫ በ 200 ብር
በንግድ ባንክ 1000510909635
በአቢሲኒያ ባንክ 47056497
በዳሽን ባንክ 5085757192011
በቴሌብር +251933143133
አቤኔዘር ገዛኸኝ ብለው በተለያዩ አማራጮች ዕጣውን መቁረጥ ይቻላል።
የከፈሉትን ገንዘብ በቴሌግራም በዋትሳፕ ወይም በሚሴንጀር አማራጮች በአንዱ ሪሲት ከመረጡት ቁጥር ጋር እንዲሁም ሙሉ ስምና ስልክ በቴሌግራም link t.me/abigezenige መላክ።

ገቢው
ከእጣው የሚገኘው ገቢ ቅዱስ ቁርባን መቀበያ ነጭ ልብስ መግዣ ይሆናል

​ዕጣው የሚወጣው ሕዳር 12/2017 ምሽት 2:00 ሰዓት ይሆናል።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

20 Nov, 06:00


የፊታችን እሁድ ሕዳር 15/2017 ዓ.ም ለሚጀምረው የነቢያት "የገና ጾም" መያዣ
ንስሐ ግቡ።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

20 Nov, 05:01


https://youtu.be/oejA7md3NOg

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

19 Nov, 17:21


እነሆ እጣው ሊወጣ አንድ ቀን ብቻ ቀረው
2ኛ ዙር እጣ

1ኛ እጣ የአክሱም ጽዮን ማርያም ጉዞ ሙሉ ክፍያ፥ የበርሚል ጊዮርጊስ ጉዞ ግማሽ ክፍያ ወይም በገና መሰንቆ ክራር [በምርጫ አንዱን]

2ኛ እጣ በወርቀ ዘቦ ወይም በ epoxy ያማረ ስዕለ አድኖ [በምርጫ አንዱን]

3ኛ እጣ የተደጎሰ የጸሎት መጽሐፍ [በምርጫ አንዱን]

በ200 ብር 200 ሰው የሚያሳትፍ እጣ

ከ200 ቁጥሮች ውስጥ የመረጡትን [ቀድሞ ያልተያዘ] ቁጥር መያዝ ይሆናል። በመጨረሻም በቀጥታ ስርጭት እጣው ይወጣል።

ያልተያዙ ቁጥሮች
31-62
65-71
75-87
89-95
97-98
101-118
130-149
151-154
156-169
172-173
175-187
189-196

ከቁጥር 0-200 ካሉ ቁጥሮች ውስጥ በእጣ መቁረጫ በ 200 ብር
በንግድ ባንክ 1000510909635
በአቢሲኒያ ባንክ 47056497
በዳሽን ባንክ 5085757192011
በቴሌብር +251933143133
አቤኔዘር ገዛኸኝ ብለው በተለያዩ አማራጮች ዕጣውን መቁረጥ ይቻላል።
የከፈሉትን ገንዘብ በቴሌግራም በዋትሳፕ ወይም በሚሴንጀር አማራጮች በአንዱ ሪሲት ከመረጡት ቁጥር ጋር እንዲሁም ሙሉ ስምና ስልክ በቴሌግራም link t.me/abigezenige መላክ።

ገቢው
ከእጣው የሚገኘው ገቢ ቅዱስ ቁርባን መቀበያ ነጭ ልብስ መግዣ ይሆናል

​ዕጣው የሚወጣው ሕዳር 12/2017 ምሽት 2:00 ሰዓት ይሆናል።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

19 Nov, 15:28


ኢየሱስ ሆይ ከሀገራችን ሒድልን

ሰዎች ኢየሱስን በብዙ ምክንያት ለምነውታል:: "ማረኝ" "ዓይኔን አብራልኝ" "ልጄን ፈውስልኝ" "ሙት አስነሣልኝ" ብለው የጮኹ ብዙዎች ናቸው:: የጌርጌሴኖን ሰዎች ግን ጌታን በአንድ ላይ ተሰብስበው "ከሀገራቸው እንዲሔድላቸው ለመኑት" ማቴ. 8:34

"ኢየሱስ ሆይ ውጣልን ! : ኢየሱስ ሆይ ሒድልን : ኢየሱስ ሆይ አትድረስብን : ኢየሱስ ሆይ አትምጣብን ! " የሚል ድምፅ እያሰሙ ተረባረቡበት::

ውጣልን ያሰኛቸው ሁለት ጋኔን የያዛቸውን ሰዎች ከላያቸው አጋንንቱን አውጥቶ ወደ አሳማ መንጋ እንዲገቡ በፈቀደ ጊዜ አጋንንቱ አሳማዎቹን ወደ ገደል እንዲገቡ ስላደረጉ ነበር::

ጌታችን አጋንንቱ ወደ አሳማ መንጋ እንዲገቡና ገደልም እንዲሰዱአቸው በመተዉ ትልቅ መልእክትን ለሰው ልጅ አስተላልፎ ነበር::

አጋንንቱ ወደ አሳማው ከመሔዳቸው በፊት ሁለት ሰዎች ላይ ነበሩ:: እነዚያን ሰዎች ላይ ቢቆዩም ግን ሰዎቹን ወደ ገደል አልከተቱአቸውም:: ልክ አሳማዎቹ ላይ እንደሰፈሩ ግን ወደ ገደል ጨመሩአቸው:: ክርስቶስ በዚህ ያስረዳን "እኔ በቸርነቴ ባልከለክለው ሰይጣን በእያንዳንዳችሁ ላይ ያለው ዕቅድ በቅጽበት ወደ ገደል እስከ መጨመር የጨከነ ነው" የሚል ነው:: ሰዎቹን ገደል እንዳይሰድ የከለከለው እሱ ነበር:: ዛሬም እኛን ከአፋፉ ላይ ሆነን ወደ ገደል ያልወረድነው "ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው" በተጨማሪም ሰይጣንም እንኳን በሰው ልጅ ላይ ቀርቶ በአሳማ ላይ እንኳን እንደፈለገ የመስፈር ሥልጣን እንደሌለውም በዚህ ታሪክ ተረዳን::

የጌርጌሴኖን ሰዎች ግማሾቹ ጌታችንን ስለኃይሉ በትሕትና ፈርተውት ግማሾቹ ደግሞ በአሳማዎቹ መሞት ተበሳጭተው ክርስቶስን ውጣልን አሉት:: ክርስቶስ የሰው ልጅ ከሚሰቃይ ጊዜያዊው ንብረት ቢጠፋ ይሻላል ብሎ ቅድሚያ ሲሠጥ ሰዎቹ ደግሞ ንብረታችን ከሚወድም ሁለቱ ሰዎች ጋኔን ቢጫወትባቸው እንመርጣለን ብለው ውጣልን አሉት::

አሣማ ቆሻሻ እንስሳ ነው:: በግእዝ ሕሱም ሐሳማ ማለት አስቀያሚ ማለት ነው:: ቆሻሻ ወዳዱ ሰይጣን ወደ ማደሪያው ገብቶ ሕዝቡንም በጌታ ላይ አሳመፀ:: ሕዝቡም ኢየሱስ ሆይ ሒድልን አሉት::
ጌታ ሆይ ከእኛ ጋር እደር ጌታ ሆይ ቶሎ ና ተብሎ ለሚዘመርለት ጌታ ሒድልንን አዜሙለት::

አፍ አውጥተን አንበለው እንጂ እኛም ጌታችንን ብዙ ጊዜ "ሒድልን" ብለነው እናውቃለን::

ወዳጄ አንተስ “ክርስትና በአፍንጫዬ ይውጣ" ብለህ አታውቅም? ያም ባይሆን መንፈሳዊ ነገር ማሰብ ወይም መዝሙር መስማት የማትፈልግበት ቀን ወይም ቃሉን ማዳመጥ የምትሸሽበት ቀን የለም? ዛሬስ ይቅርብኝ ብለህ ከልብህ ሀገር ኢየሱስን እንዲሔድልህ የለመንክበት ቀን : በቂም በቀል ልብህ ቆስሎ አኩርፈህ የይቅር ባዩን ጌታ ስሙን መስማት የጠላህበት ዕለት የለም?

ነጋዴው ከንግዱ ላይ ኢየሱስ ዘወር ቢልለት አይጠላም:: ኢየሱስ ከመጣ ገደል የሚጨምራቸው ብዙ ቆሻሻ ሥራዎች ያሉበት ሰው ጌታን ከሥራው ቦታ ዞር በልልኝ ይለዋል:: ሌብነት ማሟረት ጥንቆላ ዝሙት ሙስና የሚባሉ አሳማዎችን ገደል እንዳይገቡ ለመንከባከብ ስንል የናዝሬቱን መድኃኒት ዘወር በልልን ብለን የተማጸንን ብዙዎች ነን::

እንደፈለግን ለመኖር ከቆሸሸ አሳማ ጋር ለመዋል መርጠን በሀገራችን ላይ አጋንንት ሲጨፍሩ ሳያስከፋን የጌታችንን መምጣት ግን ያልፈለግን ብዙዎች ነን:: ከእኛ መካከል እንደ አሳማ የከፋ ልማዱ እና ሱሱ ወደ ጥልቅ እንዳይወረወርበት ፈርቶ የሚሸሽ ስንት አለ? የጌታችንን ቃል ለመስማት የማንፈልግ መንፈሳዊ ነገር ስንሰማ ጆሮአችንን የምንደፍን "ሒድልን እባክህ" ብለን የምንለምን ስንቶች ነን::

ጌታ ሆይ ክፋትን መርጠን ከሀገራችን ሒድልን ከቀዬያችን ውጣልን ስላልንህ አትቀየመን:: በሽተኛ ሲነጫነጭ ክፉ የሚያናግረው በሽታው ነው እንደሚባለው ክፉ የሚያናግረን ኃጢአታችን ነውና አትቀየመን:: የኃጢአት ፍቅር እንደ አሣማ ፍቅር ከባድ ነው:: ሽታው ቢከረፋም እኛ ግን ለምደነዋልና በቀላሉ መላቀቅ አቅቶናል::

አንተ ግን ሒድልን ብንልህም አትስማን:: አሳማ ኃጢአታችንን ከሚፈትኑን አጋንንት ጋር ወደ ጥልቁ ጣልልን:: ያን ጊዜ ነቢዩ የተናገረው ቃል ይፈጸማል:-

"ተመልሶ ይምረናል፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል"
ሚክ 7:19

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

18 Nov, 17:17


ሶስት ቀናት ብቻ ቀሩት
ክራር ወይም በገና አልያም መሰንቆ በ200 ብር ብቻ ይሸለሙ።
በ200 ብር ብቻ።
አቤኔዘር ዘተዋሕዶ 2ኛው ዙር እጣ
1ኛ እጣ የአክሱም ጽዮን ማርያም ጉዞ ሙሉ ክፍያ፥ የበርሚል ጊዮርጊስ ጉዞ ግማሽ ክፍያ ወይም በገና መሰንቆ ክራር [በምርጫ አንዱን]

2ኛ እጣ በወርቀ ዘቦ ወይም በ epoxy ያማረ ስዕለ አድኖ [በምርጫ አንዱን]

3ኛ እጣ የተደጎሰ የጸሎት መጽሐፍ [በምርጫ አንዱን]

እጣው የሚወጣው ሕዳር 12 ምሽት 2:00 በፌስቡክ ቀጥታ ስርጭት ነው።

ከቁጥር 0-200 ካሉ ቁጥሮች ውስጥ በእጣ መቁረጫ በ 200 ብር
በንግድ ባንክ 1000510909635
በአቢሲኒያ ባንክ 47056497
በዳሽን ባንክ 5085757192011
በቴሌብር +251933143133
አቤኔዘር ገዛኸኝ ብለው በተለያዩ አማራጮች ዕጣውን መቁረጥ ይቻላል።
የከፈሉትን ገንዘብ በቴሌግራም በዋትሳፕ ወይም በሚሴንጀር አማራጮች በአንዱ ሪሲት ከመረጡት ቁጥር ጋር እንዲሁም ሙሉ ስምና ስልክ በቴሌግራም link t.me/abigezenige መላክ።

ገቢው
ከእጣው የሚገኘው ገቢ ቅዱስ ቁርባን መቀበያ ነጭ ልብስ መግዣ ይሆናል

ያልተያዙ ቁጥሮች
31-63
65-71
73
75-87
89-98
101-118
128-149
151-154
156-169
172-173
175-187
189-196

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

18 Nov, 14:36


በተለይ አንዳንድ እህቶች ከገጠር በቀጥታ ወደ አረብ ሀገር ይሄዳሉ። አረብ ሀገር ሲሄዱ መንፈሳዊ ትምህርቶችን መከታተል ይጀምራሉ ከዚያም ወደ ውጊያ ይገባሉ፥ ያን ጊዜ ከቤተሰብ ከመጣባቸው ዛር ዓይነ ጥላና የአረብ ሀገር ሰይጣን ጋር ከፍተኛ ግብግብ ይገጥማሉ በዚህ መሃል አጥማቂ ሲያገኙ ሌላ ታሪክ።
ሰውን አትከተሉ❗️
መምህር ግርማ በአንድ ወቅት እንዲ አሉ፦
" እኔ ያለሁበት ድረስ መምጣት አያስፈልጋችሁም የማስተምረውን ትምህርት አዳምጡ ንስሐ ግቡ ተጠመቁ የአምልኮ ሕይወት ይኑራችሁ ከዚያ ቅዱስ ቁርባን ተቀበሉ።"
እኔም እደግምላችኋለሁ ሰውን መውደድና ማክበር ተፈጥሯዊም ሰዋዊም መንፈሳዊም ግዴታና ውዴታችን ነው ነገር ግን ግለሰብን በራስ ላይ መሾም ጣኦት አምላኪነት ነው።
#ተመለሱ።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

17 Nov, 16:12


ከሕዳር 14/2017 እስከ ሕዳር 22/2017 ዓ.ም ቆይታችን አምስት ቀናት በተዓምረኛው በበርሚል ጊዮርጊስ እና ምርት ደለጎ ቅድስት ኪዳነምህረት ጠበል አንጠበላለን።
መመዝገቢያ ቁጥር +251933143133

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

11 Nov, 09:23


የዝሙት ቪዲዮ የሚያይ ሰው ሴሰኛ፥ chat sex የሚያደርግ ሰው የሴጋ ተጠቂ፥ የፕሮቴስታንት መዝሙር የሚሰማ ሰው ደግሞ ጴንጤ ይሆናል።
ሶስቱም ሃጢያት ናቸው፥ ራሳችሁን ጠብቁ።
አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

10 Nov, 18:42


ለበረኃው ጂኒ ራሴን ዳርኩ ክፍል 6

ወደቤት እንደሄድኩ እንደተባልኩት በጣሪያዬ አድርጌ ተኛሁ ። ጠፍቶ የከረመው ባሌ ፤ በጠዋት መጣ ። ሁሌም እንደሚያደርገው ፤ ስሜን አቆላምጦ እየተጣራ ወደውስጥ ዘለቀ ። ድምፁን ስሰማ ደስ አለኝ ፤ አልደብቅህም ናፍቆኝ'ም ነበር ።መሄድ እንደምትፈልግ ግን ደግሞ የማትራመድ አይነት ሰው ነኝ አይደል ? ብትፈርድብኝም አሊዝብህም ። ብቻ ፤ ቤት ውስጥ ሲገባ የናፍቆት ድምፁ በንኖ መነጫነጭ ጀመረ ።

ፊቱን አኮስሶ ምንድነው ቤቱ የሚሸተው?! አለ ። እንደተኛሁና እንዳልሰማሁት ፥ ዝም አልኹ ። የሚሸት ምንም ነገር በቤት ውስጥ አላደረኹም ። እየተነጫነጨ ከቤት ሲወጣ ፤ እየተንጠራራሁ ተከትዬው ወጣሁ ። በሱ መታቀፍ ፥ አሰኝቶኝ ነበር ። ደጃፍ ላይ እንደወጣሁ ፤ ወደራሱ ስቦ ሽጉጥ አደረገኝ ፤ ተለጠፍኩበት ። ትንሽ እንደቆየን ከገላው በሀይል አላቅቆ ገፈተረኝ ፥ አይኑ በጥቁር ደም እንደመሞላት ብሎ ነበር ።  የግቢውን በር በርግዶ ፤ ወጥቶ ሄደ ። ደስ'ም ብሎኛል ፥ ቅርም ብሎኛል ።

ጠዋት ጠጪ የተባልኩትን ፥ ትቼ በጉጉት እጠብቀው ጀመር ። በር-በሩን እያየሁ ፤ እላዬ ላይ መሸ ። ወደማታ ፤ ተመለሰ ። የግቢው አምፖል ተበላሽቶ እየተርገበገበ ቢሆንም ጨረቃዋ ከመብራት ባልተናነሰ ግቢውን ወለል አድርጋዋለች ። በር ተንኳኩቶ ከተፈትኹ ፤ ባሌ ነበር ። ከቅድሙ በተሻለ መረጋጋት ይታይበታል ።  አይኔን ለረጅም ደቂቃዎች ከተመለከተ በኋላ ...  እዚህ ቤት ግን ምንድነው የተፈጠረው ? አለኝ ። እንዴ! ምን ተፈጠረ ? አልኩ ። ተረጋግቶ ፥ እኔንጃ ፤ ቤቴ እንደድሮ ደስ አልልህ አለኝ ! ብሎ መለሰለኝ ። እንደነገር ነገሩ ብዙ  ባባብለውም ፤ ሳያድር ስሞኝ ብቻ ሄደ ።

ለሊት ዘጠኝ ሰዓት ፤ በቀጠሮዬ መሰረት ወደ ቤተክርስትያን ሄድኩ ። ስሄድ ፥ እንደበቀደም ለታው የተለየ ጉጉት አልነበረኝም ። የቤተሰቤን ጉዳይ ተመካክረው ነበር የጠበቁኝ ። እያንዳንዱን የቤተሰብ አባል ወደ ቅዱስ ያሬድ ገዳም እንዲሄዱ አበክረሽ ንገሪያቸው ! አሉኝ ። በነጋታው ፤ ከተባልኩት ምንም ሳልጓደል አደረግሁ።

ለቤተሰብ ሳስረዳ ፤ ከእናቴ ያገኘሁት መልስ ግን በጭራሽ ያልጠበኩት ነበር ።  አርፈሽ ተቀመጪ ! ያለኝን ሁሉ ቀምተሺኛል ! የቀረኝን እንድታሳጪኝ አልፈቅድም !

እናቴ እራሷ መሆኗን ለማመን ተቸገርኩ ፥ ለእናቴ ንብረትና ገንዘብ ከኔ ነብስ በላይ ሲያሳስባት ምን ልበል  ከልጇ መዳን በላይ የሷን ድሎት መረጠች ። ተናድጄ ኃይለቃል መወርወር ጀመርኩ ። ዝም ብላ ስትሰማኝ ከዚህ በፊት ነግሬያት የማላቃቸውን የደበቅኳቸውን ነገሮች ሁሉ መተረክ ጀመርኩ ።

እናቴ ግን ለምነግራት ነገር አዲስ አልነበረችም ። የለቅሶው ቀን ፤ ሁሉንም ነገር አውቄያለሁ ! አለችኝ ፤ ደነገጥኹ ። ለማስረዳት መጣጣር ጀመርኩ ። እመኚኝ እማ !  ለሐብት ብቻ ብዬ እስከዛሬ በበረሃ አልኖርኩም ። ምኑን ከምን እንዳዞረብኝ አላውቅም ፥ እወደው ነበር ። ከዚህ በኋላ ግን መውደዱም ሀብቱም በአፍንጫዬ ይውጣ ! እባክሽ ተለመኚኝ ? አልዃት ። በፌዝ ድምፅ ፥ ይሄን ማሰብ የነበረብሽ ባሌንና ልጄን ስትገፊ ነው  ! ብላ ስልኩን እላዬ ላይ ዘጋችብኝ ።

ሁሉ ነገር መልሶ ጨለመብኝ ። በጨለማ አለም ስትኖር እንንደደዚህ ነው ። የነጋ ይመስልሃል እንጂ ጨርሶ አይነጋም ፤ ወገግ እንዳለ መልሶ ይጨልማል ። ለትንሹ ወንድሜም ሆነ እህቶቼ ገፊ መሆኔን ነግራቸዋለች ። ስደውል ፥ አርፈሽ ባልሽን ይዘሽ ተቀመጪ ! አሉኝ ።

የቀሩኝ ወገን አባ ፤ ናቸው ። ከእህታቸው ፥ ልቅምቃሚ ሳንቲም እንደበለጠባቸውና በቤተሰቤ እንደተካድኩ ምንም ሳላስቀር እያለቀስኩ ነገርኳቸው ። አዝነው ራሴን ዳበሱኝ ። ለቅሶ አፍንጫዬን ደፍኖት መተንፈስ እስኪያቅተኝ እየተንሰቀሰቅኹ ነበር ። አይዞሽ ፤ አንቺን እናስመልጥሻለን ! አሉኝ ። የፊታችን ሰኞ ለ ሰባት ቀን እኛም በቅዱስ ያሬድ ያሉ አባቶችም ፀሎት ይይዛሉ ። ይሄ ሁሉ ላንቺ ሲባል ነው ። በማግሰኞ አንቺ ከዛቤት ጨርቄን ማቄን ሳትይ ትወጪያለሽ ! ተስማማሁ ።

ከቀሚሴ ተንሸራቶ የወደቀ ስልኬን አነሳሁ ፤ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ሆኗል ። ተሰኛባብቻቸው ፥ ፈጣሪዬ የዛሬን አውጣኝ እያልኩ ተሳልሜ ወጣሁ ። የቤተክርስቲያኒቱን መሻገሪያ እልፍ እንዳልኩ የአስፓልት መሻገሪያ ላይ ከባሌ ጋር ተገጣጠምን ።  ደነገጥኩ ። ምን ትሰሪያለሽ ?! አለኝ ። እየተንተባተብኩ ፥ እ... ልሳለም...መጥቼ ! አልኩት ።

- ከመቼ ጀምሮ ... ?

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

09 Nov, 17:48


ለሕዳር 6 ለሚቆርቡ ሰዎች የመቁረቢያ ልብስ መግዣ ከ100 ብር ጀምሮ የተለመደውን ድጋፍ ያድርጉ።
ሙሉ የመቁረቢያ ልብስ 5ሺ ብር እርስዎ ከ100 ብር ጀምሮ የቻሉትን ያግዙ። 1000145090176 አቤኔዘር

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

09 Nov, 14:33


https://youtu.be/C1vddLqtbnk?si=AVp6usdphtvRJ8id

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

09 Nov, 07:09


2ኛ ዙር እጣ

1ኛ እጣ የአክሱም ጽዮን ማርያም ጉዞ ሙሉ ክፍያ፥ የበርሚል ጊዮርጊስ ጉዞ ግማሽ ክፍያ ወይም በገና መሰንቆ ክራር [በምርጫ አንዱን]

2ኛ እጣ በወርቀ ዘቦ ወይም በ epoxy ያማረ ስዕለ አድኖ [በምርጫ አንዱን]

3ኛ እጣ የተደጎሰ የጸሎት መጽሐፍ [በምርጫ አንዱን]

በ200 ብር 200 ሰው የሚያሳትፍ እጣ

ከ200 ቁጥሮች ውስጥ የመረጡትን [ቀድሞ ያልተያዘ] ቁጥር መያዝ ይሆናል። በመጨረሻም በቀጥታ ስርጭት እጣው ይወጣል።

የተያዙ ቁጥሮች
7
21
27
28
121
127
17
22
25
10
197
12
16
3
19
6
29

ከቁጥር 0-200 ካሉ ቁጥሮች ውስጥ በእጣ መቁረጫ በ 200 ብር
በንግድ ባንክ 1000510909635
በአቢሲኒያ ባንክ 47056497
በዳሽን ባንክ 5085757192011
በቴሌብር +251933143133
አቤኔዘር ገዛኸኝ ብለው በተለያዩ አማራጮች ዕጣውን መቁረጥ ይቻላል።
የከፈሉትን ገንዘብ በቴሌግራም በዋትሳፕ ወይም በሚሴንጀር አማራጮች በአንዱ ሪሲት ከመረጡት ቁጥር ጋር እንዲሁም ሙሉ ስምና ስልክ በቴሌግራም link t.me/abigezenige መላክ።

ገቢው
ከእጣው የሚገኘው ገቢ ቅዱስ ቁርባን መቀበያ ነጭ ልብስ መግዣ ይሆናል

​ዕጣው የሚወጣው ሕዳር 12/2017 ምሽት 2:00 ሰዓት ይሆናል።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

08 Nov, 19:46


Facebook/Telegram ላይ እንዲህ በደንብ ከማገልገሌ በፊት በ ሰንበት ትምህርት አገልግሎት እስከ 18 ዓመት እድሜ ያላቸውን ታዳጊዎች አገለግል ነበር።
በአገልግሎቴ በተለይ ከዚህ እድሜያቸው ጀምሮ ከቀለም ትምህርትና ከኮርሱ በተጨማሪ የአምልኮ ሕይወት እንዲኖራቸው ራሳቸውን ከመና,*' እንዲጠብቁ እና በተለይ ከዛኛው ቤት የሚነሱላቸውን ጥያቄዎች በመመለስ እና በጸሎት ሰዓት የሚፈትነንን ጠላት እንዴት ማሸነፍ እንደሚገባ አስታውሳቸው ነበር።
ፎቶ ከአምስት ዓመት በፊት በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስትያናት የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት አገልግሎት ላይ።
@abizeeotc

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

08 Nov, 11:25


2ኛ ዙር እጣ

1ኛ እጣ የአክሱም ጽዮን ማርያም ጉዞ ሙሉ ክፍያ፥ የበርሚል ጊዮርጊስ ጉዞ ግማሽ ክፍያ ወይም በገና መሰንቆ ክራር [በምርጫ አንዱን]

2ኛ እጣ በወርቀ ዘቦ ወይም በ epoxy ያማረ ስዕለ አድኖ [በምርጫ አንዱን]

3ኛ እጣ የተደጎሰ የጸሎት መጽሐፍ [በምርጫ አንዱን]

በ200 ብር 200 ሰው የሚያሳትፍ እጣ

ከ200 ቁጥሮች ውስጥ የመረጡትን [ቀድሞ ያልተያዘ] ቁጥር መያዝ ይሆናል። በመጨረሻም በቀጥታ ስርጭት እጣው ይወጣል።

የተያዙ ቁጥሮች

7
21
27
28
121
127
17
22
25
10
ከቁጥር 0-200 ካሉ ቁጥሮች ውስጥ በእጣ መቁረጫ በ 200 ብር
በንግድ ባንክ 1000510909635
በአቢሲኒያ ባንክ 47056497
በዳሽን ባንክ 5085757192011
በቴሌብር +251933143133
አቤኔዘር ገዛኸኝ ብለው በተለያዩ አማራጮች ዕጣውን መቁረጥ ይቻላል።
የከፈሉትን ገንዘብ በቴሌግራም በዋትሳፕ ወይም በሚሴንጀር አማራጮች በአንዱ ሪሲት ከመረጡት ቁጥር ጋር እንዲሁም ሙሉ ስምና ስልክ በቴሌግራም link t.me/abigezenige መላክ።

ገቢው
ከእጣው የሚገኘው ገቢ ቅዱስ ቁርባን መቀበያ ነጭ ልብስ መግዣ ይሆናል

​ዕጣው የሚወጣው ሕዳር 12/2017 ምሽት 2:00 ሰዓት ይሆናል።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

07 Nov, 17:56


ቡዳ በዘር የሚተላለፍ የአጋንንት ዓይነት ነው።

አንድ ሰው በቡዳ ከተበላ የሚያሳየው ምልክቶች፦

- በልብሱ ከሆነ የሚለብሰው ልብስ ለዓይኑ ያስጠላዋል፥ የተለያዩ ተባዮች ይገኙበታል፥ በመሆኑም ይወደው የነበረውን ልብስ ለዓይኑ ያስጠላዋል

- በስራውና በትምህርቱ ከሆነ ልዝብ ሰነፍ እና ቀርፋፋ በስራውም ሆነ በትምህርቱ ውጤታማ የማይሆን ያደርገዋል ወደ ስራና ትምህርት ከሚሄድ ጊዜውን በሌላ ነገር ማሳለፍ ያስደስተዋል።

- በመልክ ከሆነ ፊት ላይ ድንገተኛ ሽፍታ፥ ብጉር [ከወጣትነት ከሚታየው የተለየ] ፊት መጠቋቆር፥ ዓይን አካባቢ መጥቆርና መቅላት ያስከትላል።

- በምግብ ከሆነ ይወዱት የነበረውን ምግብ መጥላትና መተው፥ ደፍረው ቢበሉት ስንኳ ለጤና መታወክ ይዳርጋል። ሽታው ጣዕሙ ያቅለሸልሻቸዋል። [ነፍሰ ጡሮችን አይመለከትም።]

- በሰውነት ከሆነ የሚያምር ሰውነት አካላችን መክሳት መጠውለግ

- በሰፈር ከሆነ በሰፈር ውስጥ የምንታይ ከብዙዎች ጋር የምንግባባ እና መልካም ቅርርብ ካለን ያን ሰፈራችንን መጥላትና ከቤት አለመውጣት ከሌላ ቦታ ወደ ሰፈር ሲገቡ ማስጠላት።

- ሕጻናት በቡዳ ሲበሉ እስከ ሞት ሊያደርሳቸውም ይችላል። በሌሊት ጥርስ ማንቀጫቀጭ ከፍተኛ የሆድ ቁርጠት ሕመም እና መሰል ምልክቶችም ሊታዩ ይችላሉ

- እንስሳትም በቡዳ ሲበሉ ሊሞቱ ይችላሉ።

መፍትሔ
በተለይ ሕጻናትን ማስጠመቅና ቅዱስ ቁርባን በተከታታይ እንዲወስዱ ማድረግ አዋቂዎች የአምልኮ ሕይወታችሁን ማጠንከር ይገባል።
የባህላዊ ሕክምና ለአጋንንት ማስለቀቂያ አይመከርም።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

04 Nov, 06:32


https://youtu.be/BaA7OhzxHZc?si=2MYleTNXJqg4mIop

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

03 Nov, 07:30


https://youtu.be/9t5jzqZtRRI?si=s9vKNdjrs_0K_1AM

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

02 Nov, 17:07


በ አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ እጣ መርሐግብር በአንደኛው ዙር አንደኛ እጣ ተሸላሚ በ300 ብር እጣ Tariku Teshome Gelashe  የክራር ሽልማቱን ዛሬ ተረክቧል።
ሁለተኛውን ዙር እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ሰኞ እንጀምራለን።
የሁለተኛና ሶስተኛ ተሸላሚዎችም ከሩቅ ቦታ ስለሆነ ሽልማቱ ተቀምጦ ይጠብቃቸዋል።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

01 Nov, 19:06


[ ለበረኃ ጂኒ ፥ ራሴን ዳርኩ | ክፍል 4 ]

ከልዑል ዘወልደ ገፅ የተወሰደ 'እውነተኛ ታሪክ'

ሌሎችና ተመሳሳይ ታሪኮችን በፍጥነት ለማግኘት በቴሌግራም
t.me/abizeeotc ይቀላቀላሉ።

እየተብሰለሰልኩ ፤ ድንገት የግቢው በር ተንኳኳ ። ለማኝ ነበር ። የማነው ደፋር የኔቢጤ ? አንኳኩቶ የሚለምን ብዬ ትክ ብዬ አየሁት ። ሰረቅ አርጎ አይቶኝ ፥ ሥለ ቅዱስ ያሬድ ! አለኝ ። ሰውነቴ መብረቅ እንደመታው ከላይ እስከታች ፥ ነዘረኝ ። ምንም ሳይል አተኹሮ ሲያየኝ ፥ ምልክት እንደሆነ ተገለጠልኝ ። ጥሩ ግዜ እየመጣ እንደሆነ ገመትኹ ። የኔ ወንድም ፤ አባ ከመዳኒያአለም ልከውህ ነው ?

አስታወስኩ ። ከሲሪንቃ ለመጡት አባት አድራሻዬን ነግሪያቸው ነበር ። በተላከው ነዳይ በኩል መልዕክት ላኩኝ ፤ ለሊቱን ዘጠኝ ሰዓት እንዳለፈ ፥ እንደምመጣ ። በሩን ዘግቼ ወደ ግቢዬ ስመለስ ፤ የሶስቱ ትንንሽ ወንድማሞች ነገር አሳሰበኝ ።

ብዙም ሳይቆይ ግን ባሌ መጣ ። እንደልጅ ከልጆቹ እየተላፋ ፥ ግቢው ውስጥ አብሮን ዋለ ። ለአለቃው ኢፍትር የሚገብረው ነብስ ብዛት አንሶበት ፥ እንደተጨነቀ ግን ያስታውቅበታል ። ሲጨነቅ አረመኔነቱን ሁሉ እረሳለትና ፥ መልሶ ያሳዝነኛል ።

ቀኑን ሙሉ ከእኔና ከልጆቹ ጋር ዋለና ተቃቅፈን ተኛን ። ቀን ላይ ፥ የስልኬን አላርም ዘጠኝ ሰዓት ከአምስት ላይ ሞልቼው ነበር ። ቀድሜ ነቃሁ ፤ ጎኔ የለም ። መኝታ ቤቱ በሩ ተበርግዶ ንፋስ እየገባ ነበር ፥ ባሌ ወደአለሙ ሄዶ ነው ። ወደ እንግዳው አባ ፥ ወደ መድሃኒአለም የሰርክ ጉዞ ጀመርኩ ። በዛ ውድቅት ለሊት ፥ ከኔ በቀር የሚንቀሳቀስ ፍጡር በአገሩ የለም ።

አባ ፥ የቤተክርሶትያኑ በር ላይ ተቀበሉኝ ። ሰላም ከተባባልን በኋላ መፍትሄው ምንድነው አልኳቸው ፤ እንደማሰብ ብለው መሳፈሪያ ስጭኝና "ቅዱስ ያሬድ" ሄጄ እምነቱን (እንደተጠቀለለ) አመጣልሻለው ! አሉኝ ። የእምነቱ ቃል ኪዳን ከክፉ ነገሮች እና ከአደጋ ፣ ከብዙ ነሮች ይሰውራል ። ሰይጣንም ሆነ ፥ ማንኛውም የክፉ ነገድ ወደ አንተ መጠጋት አይችልም ።

በሀሳባቸው ተስማማው ። እኔ ነገ አምሳ'ሺ ብር ከባንክ አውጥቼ እሰጦታለው ፤ ሄደው አፀልየው ያምጡልኝ ። በመድሃኒያለም ቅጥር ከዚህ አዘቅት ካወጣኸኝ ብዬ ለያሬድ ተሳልኩ ። በነጋታውም በሰው-በሰው ብሩን ሰጥቼ ፥ የሚገዛዛ እቃ ሸምቼ ተመለስኩ ። ባሌ ልጆቹን ከደላላው ጋር ይዞ እየወጣ ነበር ። ከመኪናው ወርዶ ፤ መውረጃችን ጋር መኪና ሙሉ ሰው እያፈጠጠብን ሳመኝ ።

ለሶስት ቀን አልመጣም ! የሚጠብቁሽ አሉ ! አለኝ ። ከማነው የምትጠበቂው ? ። ወደጨለማው አለም የገባ ሰው ከሁሉም በተለየ ለጥቃት ተጋላጭ ነው ። እኔ አንኳን የማውቃቸው ፥ ጋኔንና ሰይጣንን ጂኒን ጨምሮ ወደ አምስት ነገድ እንዳለ ነግሬህ ? ሰው እንደመሆኔ ባልጠበኩት ሁኔታ ልጠቃ እችላለው ። ልቤ እያዘነ ( ለሱ አዘንኩ እንጂ ለራሴ አልፈራሁም) ተሰናበትኩት ።

ከሶስቱ በአንዱም ቀን ከቤቴ ሳልወጣ ፤ ባለቤቴ ተመልሶ መጣ ። ሲመጣ ደላላው አብሮት ስለነበር ቡና አፈላሁ ። የሄደበትን እንደማላውቅ ሁሉ ፥ መንገድ ተሳካላቹ ? አልኹ ። ደላላው ፤ ከወሎ ተጭነው ቀድመው የገቡ ጅቡቲ ፤ ይጠብቁን ነበር ፥ አለ ። የባሌን አይን አየሁ ፥ ጭንቀቱ የጠፋ ይመስላል ፤ ደስ አለኝ ። ግን ደግሞ የመን ሳይገቡ ለቀይ ባህር የተገበሩትን ጨቅላዎች አስቤ መዋዠቄ አልቀረም።

በሳምንቱ ሃያ ኤርትራውያን'ን ጨምሮ ሁሉም እንደሞቱ ዜና ሰማሁ ። ይኼን ክፉ ዜና ሰምቼ በቆረዘዝኩ በወሩ ፥ የግቢ በር ተንኳኳ ። በር ስከፍት ፥ ልጅ እግር መነኩሴ በኔ ትይዩ ቆሟል (የበቀደሙ ነዳይ አይደለም) ። በልጅ መነኩሴ እቀናለሁ ። በተለያየ መስመር ላይ ስለሆንን ብቻ ሳይሆን ፥ መመነንና ራሴን ለእየሱስ መዳር ፥ የልጅነቴ ህልም ነበር ።

ተጨማትሮ የከረመው ፈቴ ፥ እንዳየሁት ፈካ ። መነኩሴውን ፥ ወደረከሰ ግቢ ከማስገባ ከበሩ መልሼ የሰፈሩ መውጫ ድረስ እያወራን ሸኘሁት። አባቴ ፥ ምን ነበር ?

አባታችን ነው የላኩኝ ! አለ ። ስልክሽን ደጋግሜ መታሁ ፥ አይሰራም ። ልጄ ፤ እኔም ላንቺ እንቅልፍ ካጣሁኝ ከረምኩ ። በመጪው አርብ ሎጊያ እደርሳለሁ ። ያንኑ ቀን ለሊት መጥተሽ እምነትሽን እንድትወስጂ ! እስከዛው ፈጣሪ ይጠብቅሽ ! የሚል መልዕክት ነበር ። አባ ፥ ሚስጥሬን እንደጠበቁ ነበር መልዕክት የላኩት ።

አመስግኜ ፥ የመልዕክተኛውን እጅ ተሳልሜ ቀና ስል ከባለቤቴ ጋር አይን-ለአይን ተያየን ። መነኩሴውን ቶሎ ብለህ ጥፋ ! አልኩት ፤ ወደጀርባው ዞረ ፤ የሚታየው ፍየል ነው ።

ሰላም የነበርኩ ሰው ፥ መለዋወጤ አስደንግጦታል ። እኔ ወደቤታችን ሩጫ በቀረው እርምጃ በረርኩ ። መነኩሴው ሊከተለኝ ሲሞክር ፥ ተመለስ ! ብዬ አምባረኹበት ። ደግሞ ደነገጠ ፥ ለእኔ የሚታየኝ መች ይታየውና?! በሩን ከፍቼ ወደቤቴ ስሮጥ ፥ ሀይለኛ ንፋስ በሩን ዘጋው ፤ ግውውው ።

ይቀጥላል

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

01 Nov, 07:50


መተት
አንድ ሰው መተት ሲደገምበት ሦስት ነገሮች አሉ፡፡
አንደኛው አስመታቹ /እኛ ላይ የሚያስደርገው ሰው/ ነው፡፡
ሁለተኛ መታቹ /ደጋሚው፣ጠንቋዩ/ ነው፡፡ /ዘዳ 18÷11/
ሦስተኛ በመተት ውስጣችን የሚገባው አጋንንት ነው፡፡
ስለዚህ አንድ ሰው መተት ተሠራበት ማለት ከራሱ ተፈጥሮአዊ ጠባይ በተጨማሪ ቢያንስ የሁለት ሰውና የአጋንንትን ጠባይ ይዋረሳል ማለት ነው፡፡

መተት በቤተሰብ ሲመተት

1. ተነጋግሮ መግባባት የለም።
* እናት ልጇ የሚናገረው አይጥማት አባት ልጁ ምንም ቢያደርግለት አይወድም።
* ታናሽና ታላቅ ያለ ምክንያት ደመኛ ይሆናሉ። ወንድማማች ወይም እህትማማች መሆናቸውን ጭምር ይረሳሉ።
ምናልባት እግዚአብሔር ብሎ ከቤተሰቡ አንድ ሰው ነቅቶ መንፈሳዊ ሕይወት ላይ ቢጠነክር ሌላ ስም ይሰጡታል ነገር ግን እርሱ ሁሉን ችሎ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ቢያደርግ የቤተሰቡ ነጻ አውጪ ይሆናል።

2. ከቤተሰብ ይልቅ ለጓደኛው ወይም ለጎረቤቱ ፈጥኖ ይደርሳል።
* እህቱ የፓድ መግዣ እንኳ እስክታጣ ብትቸገር ዞር ብሎ ሳያያት ከጓደኞቹ ጋር ሲዝናኑ የሚከፍለው እርሱ ነው፥ እናቱ የቤት ወጪ ብትጠይቀው ስንኳ ሳይሰጥ ቀርቶ ለጎረቤቱ ሊረዳ ይችላል።

3. ከ2 ቁጥር በተቃራኒው ልጅ ቤተሰብ ይደሰታል ብሎ ለቤተሰቡ የተቻለውን ሲያደርግ ያደረገውን ሁሉ ያሳንሱበታል ያጣጥሉበታል ምንም ቢያደርግ ከቤተሰቡ ከምስጋና ይልቅ ሌላ ቀን በሞራል እንዳያደርግ ያሰነካክሉበታል።

4. ከቤቱ አባወራ ጀምሮ በበሽታ ይሰቃያሉ። በተለይ ሴት ልጃቸው በሯን ዘግታ ልክ እንደ አዕምሮ ታማሚ ከአልጋ አትነሳም፥ ዘወትር በእምባና በብቸኝነት ራሷን ታሰቃያለች።
ወንድ ልጃቸው በሱስ እና በዝሙት ይሰቃያል።

5. በበዓላት ወቅት ደህና ሲስቁ ሲጫወቱ ከቆዩ መጨረሻቸው ጸብ ይሆናል፥
ብዙውን ጊዜ በዓላት ሲደርስ ገንዘብ በማሳጣት በሌላም ምክንያቶች በዓሉ ደብዝዞ እንዲዋል እና የቤተሰብ ጭቅጭቅ ሲያስከትል ይህን አልፈው ቤታቸው ሞልቶ ተትረፍርፎ በዓሉን በደስታ ከዋሉ ምሽት ላይ ድንገተኛ ጸብ ይጀመራል እስከ ደም መቃባት ሊያደርሳቸው ይችላል [ይህ በቤተሰብ ዛርም ይከሰታል]

ከዚህ ሁሉ ለመላቀቅ መፍትሄው የቤተሰብ የጸሎት ጊዜ ማዘጋጀት መልካም ነው፥ አስቀድሜ እንዳልኳችሁ የቤተሰቡ ነጻ አውጪ ምንም እንኳ ቤተሰቡ ቢያጥላሉበትም የክርስትና ስማቸውን በእጁ ላይ እየጻፈ ቢሰግድ ቢጠመቅ ንስሐ ገብቶ ቢቆርብ የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ከችግራቸው ሊያወጣቸው ይችላል።

ይቆየን።

@abizeeotc

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

31 Oct, 20:05


[ ለበረኃ ጂኒ ፥ ራሴን ዳርኹ ] ክፍል ፫

ከ ልዑል ዘወልደ ገፅ የተወሰደ 'እውነተኛ ታሪክ'

በሁለት ቀን ልዩነት ሁለት ቤተሰቤን ልቀብር ነው ። በአባቴ ሳልስት (በወንድሜ የቀብር ቀን) ፥ አባቴ ክፍል ገብቼ ፥ አ...ባ...ቴ ፤ የኔ አባት ይቅር በለኝ ! ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ ። ፀፀት መሸከሚያ ጫንቃዬ ተሰብሮ ደነዝ ለቅሶ ነው የማለቅሰው ። እናቴ ከጀርባዬ መጥታ ፥ ተቃቅፈን አለቀስን ። ፊቴን በሁለት እጇ ይዛ ፤ ልጄ እፈራለሁ ! አለች ። ፈራሁ ፥ ትተሽሽን አትሂጂ !

እንዴት ብዬ ልንገርህ ፤ የልመና ድምጿ እስካሁን ጭንቅላቴ ውስጥ አለ ። በቂ ሀብት አለን ፤ ይበቃናል ። ከባልሽ ጋር እዚህ ሁኚልኝ ልጄ ! ከባልሽ ጋር አለች ? እኔ ብቻ ምንም አላወራም ። የኔን ጥፋት እና እሱን ያየሁበት ቀን እየረገምኩ ፥ እየተብሰለሰልኩ ፥ እናቴ እየደጋገመች አትጂብኝ እያለች ፥ እጇ ላይ አሸለብኩ ።

የአባቴና እሷ አልጋ ላይ አስተኝታኝ ፤ ከእንግዶች ጋር ለመተኛት ሄደች ። ለቀናት በድካም ውስጥ ሆኜ ያልተኛሁትን እንቅልፍ ተኛሁ ፤ አታምንም ነገር አለሜን አላውቅም ።

ጠዋት ስነሳ ፥ ትንሿ እህቴ በስስት እያየቺኝ ነቃሁ ። ምነው እማ ? አይ ምንም ፥ ተነሳሽ ? ባልሽና ጓደኞቹ ለለቅሶ መጥተው ነው ፥ ድንኳን ነው ያሉት ! አለች። ደነገጥኩ ፣ በርሬ ስሄድ ደቂቃ የወሰደብኝ አይመስለኝም። እሱን ጨምሮ አምስት ሆነው አንደኛው ድንኳን ውስጥ ተቀምጠዋል። ከነበረ ሰው ፥ የግማሹ ዓይን እነሱ ላይ ነው።

ቆንጆ ናቸው ። በጣም ተጨነኩኝ ፥ ምን ብዬ ልሂድ ? ምንስ ነው የማወራው? ከአፌ አንድ ቃል ማውጣት ተሳነኝ ። ባሌን እንደመገላመጥ አይቸው ፤ ከእናቴ ጎን ሄጄ ተቀመጥኩ ። እናቴ ፥ ሂጂ እንጂ ከባልሽ ! ትላለች ። እንዳልሰማ ሆንኩ ፣ እንግዶችሽ ጋር ሂጂ ! ስትለኝ ፤ ለሁሉም ይሰማ ነበር ። ድንጋጤና ንዴት ገላዬ ላይ ተቀላቅለው ፥ የሆነ መናገር የማልችለው ስሜት ሰሩ ።

ቆይቶ ግን ድንጋጤ አሸነፈኝ ፤ አንገቴን ስዳብስ ባዶ ነበር ፤ ማዕተቤ በቦታው የለም ። ተመልሼ ፤ የተኛሁበት የአባቴ ክፍል ውስጥ ፈለኩ ፥ የለም ። ትንሿ እህቴን (እማ ነው የምላት) ጠርቼ ፥ ማህተቤን አይተሻል ?! አልኩ ። አብራሽ የመጣችው ጓደኛሽ ፥ ለሊት ማህተቤ አነቀኝ ጠበበኝ እያለች ነው ብላኝ ፥ አብረን በምላጭ ቆርጠንልሻል ! አለች። ምን?!!! ሚጡ ፥ አንቆሽ እኮ በጣም ስታንኮራፊ ነበር ፤ አለች። እንዴት ብዬ ፥ እኔ ከማንም ጋር አልመጣሁም ! ልበላት ፥ የእሱ ስራ እንደሆነ ገብቶኝ ወደ ድንኳኑ ተመለስኩ ።

የወንድሜ ቀብር ሰአት ደረሰና ፥ ቤተሰብ ያለበት መኪና ውስጥ ልገባ ስል ጎተት አድርጎ ፤ ሚስት ከባሏ ጋር ነው የምትሄደው ! አለኝ ። እነሱ ከቅጥር ውጪ ቀርተው ፤ ቀበርን ። ወደቤት እየተመለስን ከኔ ጋር ጣዕም የሚኖረን በተመሳሳይ ጠለል ስንሆን ነው ። ምን ማለት ነው እሱ ? ስትሞች ! ነብስሽ ለኢፍቲር ስጦታ ትሰጣለች ። እኔ ብዙ ተንገላታሁ ፤ ከዚህ በላይ መጠበቅ እየደከመኝ ነው ።

ፈጥጬ ቀረኹ ፥ ቀዝቃዛ ሽንት ጠብ ሲለኝ ይታወቀኛል ፤ ሊገለኝ ነው ። ከአሁም አሁን ተገለበጥን ፤ አንዱ መታጠፊያ ላይ እያልኩ መንገድ ሳትን እያልኩ ቤት ደረስን ። ለቀስተኛውን ከኋላ ጥዬ በወላጆቼ ክፍል ማልቀስ ጀመርኩ ። ከየት መጣ ሳልለው ፥ አጠገቤ ተገትሯል ። አየሽ ትዕዛዜን እምቢ ማለት ፤ ምን እንዳመጣ ?! ምንም ማለት ስለማልችል ፥ ዝም ብዬ አየዋለሁ ።

አባትሽ ታንቆ አልሞተም ፤ እኛ ነን አንቀን ከገድልነው በኋላ እንደ ታነቀ ሁሉ የሰቀልነው። ወንድምሽ ላይም ፤ እኔ ነኝ ማሽን የጣልኩት ። ለምን እንደሆነ እንጃ ፥ አውቄያለሁ ! ማለት አልፈለኩም ። ሌላ የሚጠቅም ሚስጥር ያዝ ፤ ሠይጣን የሚያነበው ከአፍ የወጣን ነው ። በልብህ ያለን እንዳያይ ታውሯል ። መልካም መንፈስ አጠገብህ ከሌለ በቀር በስስት ያሰብከውን ነገር ፥ በአፍ-ቃልህ ለራስህም ሆነ ለሰዎች አትንገር ።

አክስቴ ወደ ክፍሉ ስትመጣ ፤ ነገ በጠዋት ተነስተሽ ወደ ሎጊያ ፥ አለበዚያ ሁሉንም ቀብረሽ ብቻሽን ስትቀሪ ትመጫለሽ ! ብሎኝ ወጣ። ሊመሻሽ ሲል አልጋ ላይ የነበሩ አክስቶቼን እጅ ነስተው ሄዱ ።

ሰዓታቸው እየደረሰ ነበር ፤ ከመሸ እንደሰው መሆን አይችሉም ። ሉሌ ፤ ማታ የአውሬ ቀን ነው የሚባለው እውነት ነው ። እኔ በማውቀው እንኳ የማያደርጉት የለም ። ከሁሉ የሚዘገንነኝ የሰው ሞት ሱሰኝነታቸው ናቸው ። አንተ እንደምትለን ጠቋር ፣ አዳል ሞቲ ፣ አዮ ሞሚና አይነት አይደሉም። እኔ እየነገርኩህ ያለኹት አዛዥ ስላላቸው ጂኒዎች እንጂ ተራ ዛሮች አይደለም ። ይሄ ቡና ፣ ቅቤ ፣ ሽቶ ፣ ዶሮ ምናምን ላይ አይልከሰከሱም ። የሚፈልጉት አንድና አንድ ነገር ፤ የሰው ደምና ትንፋሽ ነው።

ለመበልፀግ ፤ ሰው እንደነገር ነገሩ ፤ ትገብራለህ ባለፀጋ ያደርጉሃል ። ወሰን አልባ ናቸው ፤ ድንበርና ዘር አይገድባቸውም ። አብረውክ ቅዳሴ ሊቆሙ ይችላሉ ። ሙስሊም ከሆንክም ፥ አብረውክ ቁርዐን ካንተ በላይ ይቀራሉ ። ነገር ግን አባታችን ሆይ ! (ፀሎት) አይሉም ፥ ከቁርዐንም ላይ'ም የሆነ-የሆነ ክፍል አለ ፥ እሱን ለይተው አይቀሩም ። እና ደሞ ፤ የሌት ኪዳንና የሌሊት ኣዛን አይወዱም። ከ ሌሊት 9-12 የሚከፈት የመንፈስ በር አለ ። በዛ ሰዓት ተራ ጋኔኖችን እንጂ እኔ የማወራልህን ጂኒዎች አታገኝም ። እርግጠኛ አይደለሁም ፤ ግን ቀይ ባህር ፥ ወደ ኢፍቲር የሚሄዱ ይመስለኛል ።

የወንድሜን ሰልስት ሳላወጣ እናቴን ተሰናበትኳት ፤ ከአንጀቷ ስታዝንብኝ ይታወቀኛል ፤ ምርጫ አልነበረኝም ። ለአርባው እንደምመጣ ተናግሬ ፤ ዳግም ላለመባባት ወደኋላ ሳልዞር ከአደግኹበት ቤት ወጣሁ ። እያለቀሰች እሺ ለአርባው ቀደም ብለሽ ነይ አለች ።

በምድር ላይ የእናትን ፍርሃት እያዩ ምንም ካለማድረግ በላይ መሸነፍ የለም ። የኔ እናት እየዋሸኋት እንደነበርና ለአርባ እንደማልመጣ ከአኳኋኔ መገመት አልቻለችም ።

ወደ ሎጊያ ተመለስኩ ። መምጣቴን የሰማው የቤቱ አከራይ ማምሻውን መጥቶ ቤቱን እፈልገዋለሁ ፤ ልቀቂ አለኝ ። አላቅማማሁም ፤ ባለቤቴ ማታ ሲመጣ ውጡ ተብለናል ብዬ ነገርኩት ። መልስ አልሰጠኝም ፤ ምን ማድረግ እንዳለብን ሳናወራ እንዲሁ አቅፎኝ ተኛ ። ጀርባዬን እንደሰጠሁት አይኔን ሳልከድን ስምንት ሊሆን ሲል እንቅልፍ ሸለብ አደረገኝ ።

ጠዋት ስነቃ ፥ እንደተለመደው ብቻዬን ነኝ ። ሁሌም አንድ ላይ ተኝተን ፥ በለሊት ሲሄድ ዳናው አይሰማኝም ። ስጋ ልገዛ ከሰፈር ወጥቼ ወደ ባጃጅ ተራ ሄድኹ ። አስፋልት ላይ የተሸፈነ ሬሳ ከበው ፥ ሰዎች ሲጯጯሁ አየሁ ። ከጅቡቲ የመጣ የጭነት መኪና ድንገት ወጣባቸው ምናምን እያሉ ያወራሉ ። ለወሬ ተጠጋሁ ፤ ታምናለህ ሉሌ አከራያችን ናቸው ።

ፈጣሪም ሲፈጥረኝ የስቃይ ሳንቲም አድርጎ ነው ። አለ አይደል ፤ በኔ የንፁሃን ነብስ እንዲገዛ ምክንያት እንድሆን ። ከዚህ የተለየ የህይወት ትርጉም የለኝም ። ሌላ ትልቅ የፀፀት ድሪቶ ከነበሩት ፀፀቶቼ በላዬ ተከመረ ።

ቀና ስል ፥ የተሰበሰበው ሰው መሃል ባሌን አየሁት ። ልገዛ የወጣሁበትን ጉዳይ ትቼ ፥ እንደፈረደብኝ ልነፋረቅ ወደቤቴ ሮጥኩ ። ቤት እንደደረስኩ ግን እንደሌላው ግዜ ተደፍቼ አላለቀስኩም ። ድንጋጤ ይሁን ሴራ መጎንጎን እንጃ ፥ እህል ሳልቀምስ አልጋዬ ላይ እንደተጎለትኩ ስብሰለሰል ዋልኩ ።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

31 Oct, 20:05


እዚህ ጋር በፍፁም የማይገባኝን ነገር ልንገርህ ፤ እንዳትታዘበኝ ። ብዙ አስብና የባሌን መልክ ውል ሲለኝ ያሰብኩትን ሀሳብ እፈራለሁ ። የአባቴንና የወንድሜን ገዳይ ፣ የመዓት ግፍ ደም ያለበትን ጂኒ እኔ ልረዳው በማልችለው ምክንያት ፥ እወደው ነበር ። አዎ ልዑል ፥ ይሄን ሁሉ ነገር አድርጎም ፥ እወደዋለው ።

ባለቤቴ በዛን ቀን ፥ ማታ ወደቤት አልመጣም ። አልጋዬ ላይ እንዳለሁ ለሰዓታት ጠብቄው ፥ ከለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ከቤት ወጣሁ ። እንዴት እንደሆነ አላውቅም ፤ እግሬ ቀጥታ ወደ ሎጊያ መድሃኒያለም እየመራኝ ነው ። ባሌም ሆነ ጋሻጃግሬዎቹ በዛ ሰዓት ምድር ላይ እንደማይኖሩ እያወኩም ፥ ልቤን ፍርሃት-ፍርሃት ይለዋል ።

ከጨረቃ ድንግዝግዝ በቀር ብዙ የሚታይ ፥ ከውሾችና እንቁራሪት ጩኸት በቀር የሚሰማ ፤ በመንገዴ የለም ። ደርሼ ወደ መድሀኒአለም እነንደገባሁ ፥ ካህን ወይ በቃ አንድ አባት በአይኔ መፈለግ ጀመርኩ ። እግዚአብሔር ሲረዳኝ ከ ሲሪንቃ ወደ ሎጊያ የመጡ ሶስት አባቶች ሶታት ቆመው እየፀለዩ አየሁ ። ጠጋ አልኩና ፥ ሰላም ብዬ አዋራዋቸው ። እየተንተባተብኩ ፥ የቅዱስ ያሬድ እምነት የት ነው የማገኘው ? ብዬ ጠየኩ ።

ሁሉም ግራ ተጋብተው አዩኝ ። አንደኛው አባት ፤ ልጄ አውቀሽዋል ግን ቦታውን ? በጣም ሩቅ እኮ ነው ! ከዚህ አዲስ አበባ ሄደሽ ፥ ከዛ ደግሞ ጎንደር ታቀኝና ወደ ደባርቅ የሙሉ ቀን መንገድ ትጓዣለሽ ። እሱም ቀላል ምንገድ አይደለም ፥ አስራ ሰባት ጉብታና ተራራ ወጥተሽ ነው ከያሬድ የምትደርሺው ። እሳቸው ወሬያቸውን ሳይጨርሱ በፊት ፤ እኔ ተስፋዬን ቆሮጫለሁ ።

የእኛ አድራሻ ሲሪንቃ-አርሴማ ናት ። ቆይ አንቺ እምነቱን ለምንሽ እንዲሆን ፈልገሽ ነው ? አሉኝ ። ሁሉንም ታሪክ ፥ ምንም ሳላስቀር ነገርኳቸው ። አዘኑልኝ ፥ አንደኛው አብረውኝ ሁሉ አለቀሱ ። እያወራን ፥ ድንገት ስልኬን ሳይ ሳይ አስራ አንድ ከፈረቃ ይላል ።

ነገ በተመሳሳይ ሰዓት እንደምመጣ ተናግሬ በቅጡ እንኳ ሳልሰናበታቸው ወደቤት መንደፋደፍ ጀመርኩ ። ባለቤቴ አብሮኝ በማያድር ቀናት ፥ ሁሌም ጠዋት አስራ ሁለት ላይ ይመጣል ። የእውር ድንብሬን ሮጬ ፥ ከቤት ገብቼ እንቅልፌን ተኛሁ ።

ጠዋት ላይ በግቢዬ በር ላይ ግርግር ሰማሁ ። አርባ የሚደርሱ ታዳጊ ወንዶች እየተጨቃጨቁ ነው ፤ የተለመደ ነበር ። ባለቤቴ ፌቨር የሰራለት (ጂኒ እንደሆነ አያውቅም) ሰው አሻጋሪ ደላላ አለ ። በሆነ-ሆነ ግዜ ወደ ጅቡቲ የሚያሻግራቸውን ሰዎች የሚያራግፈው እኛ ግቢ ነው ።

አስራ አምስት የሚሆኑ ልጆች ፥ ተቀበልኩት ። ከአዲስአበባ ከመጡት አብዛኞቹ የፈረንሳይ እና የቤላ ማዞሪያ ልጆች ናቸው ። ከአንድ ቤት ውስጥ ሶስት ወንድማማቾች ነበሩበት ፤ አይ የእናት መከራ ። ከመካከላቸው ውስጥ ምን ያህሉና ማንኛቸው ለቀይ ባህር እንደሚገበሩ አላውቅም ። ትንሽ ስንግባባ ፥ ይበልጥ አሳዝነውኝ ቢያንስ ትንንሾቹ እንዲቀሩ ውሸት ማሰብ ጀመርኩ ።

እየተብሰለሰልኩ ፤ ድንገት የግቢው በር ተንኳኳ ። ለማኝ ነበር ። የማነው ደፋር የኔቢጤ ? አንኳኩቶ የሚለምን ብዬ ትክ ብዬ አየሁት ። ሰረቅ አርጎ አይቶኝ ፥ ሥለ ቅዱስ ያሬድ ! አለኝ ። ሰውነቴ መብረቅ እንደመታው ከላይ እስከታች ፥ ነዘረኝ ። ምንም ሳይል አተኹሮ ሲያየኝ ፥ ምልክት እንደሆነ ተገለጠልኝ ። ጥሩ ግዜ እየመጣ እንደሆነ ገመትኹ ። የኔ ወንድም ፤ አባ ከመዳኒያአለም ልከውህ ነው ?

ይቀጥላል

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

31 Oct, 19:06


[ ለበረኃ ጂኒ ፥ ራሴን ዳርኹ ] ክፍል ፪

ከ ልዑል ዘወልደ ገፅ የተወሰደ 'እውነተኛ ታሪክ'

ለወንድሜ ስደውል ስልኩ አይሰራም ፤ ጓደኛው ጋር ደወልኩ ። ከብዙ ማስጠበቅ በኋላ ፤ ፍርሃት በነገሰበት ድምፅ ሰላም ሚጡ አለኝ ። ዛሬ ጠዋት ማሽን ወድቆበት ደሴ ሆስፒታል ነን ፤ ቀላል መስሎን አልነገርኩሽም ። አሁን ግን እንደዛ እየመሰለኝ አይደለም ፤ አንቺው ከደወልሽኝ አይቀር ፥ነይ ! አለኝ ። ሰማይ ሲከደነብኝ ፥ ነገር አለሙ ሲገለባበጥብኝ ይታወቀኛል ።

የት እንደምሄድ ግራ ገባኝ ፤ ሟች አባቴን ልቅበር ወይስ አደጋ ያገኘው ወንድሜ ጋር ? ህይወቴ ሁሉ ቅዠት ሆኖብኝ ናውዤ ቁጭ አልኩ ። ልብስ እላዬ ላይ አድፏል ፤ ከቀየርኩ አራተኛ ቀኔ ሆኗል ። ልቤ ስትመታ ፥ ተነስቼ መጣደፍ ጀመርኩ ። እንዴትኒ ወዴት እንደምሄድ ሳልወስን ፥ ያስፈልጉኛል ብዬ ያሰብኳቸውን ነገሮች ከየመሳብያው ሰበሰብኩ ።

ልሂድ በድንጋጤ ከቤት ልወጣ ስል ሰፈራችን በአሸን ጂኒዎች ተከቧል ። አውቃቸዋለሁ ፤ እንዳላየ ወደ መኪናዬ ሮጬ ገባሁ ። በሬን ገጥሜ ስፖኪዮ ሳስተካክል ፤ ባለቤቴ የኋላው ወንበር ላይ አየሁት ። ደረቅኹ ። ለሰኮንዶች አይናችን ሳይከደን ከተፋጠጥን በኋላ ፤ ምን ብዬሽ ነበር ? አለኝ ። ፕራዶ መኪና እንድገዛ የሆንኩት በሱ ነው ። መኪናዬ'ን በገዛሁ በሁለተኛው ቀን ግን እንዳልጠቀም ከለከለኝ ።

ምን ብዬሽ ነበር ?! የሚለው ጥያቄ ተከትሎ ፤ መልስ ሳልሰጠው እሪ ብዬ አለቀስኩ ። ቁልፉ መኪናው ውስጦ እንዳለ እየተነፋረቅኹ ወርጄ ቤቴ ገባሁ ። የማልወጣው ፤ ማጥ ውስጥ ገብቻለሁ ።

ሰይጣን ፌየርነስ አያውቅም በአንድ የተሳሳተ እርምጃ ፤ መቶ ቅጣት ሊቀጣህ ይችላል ። እዚህ ላይ የነሱን ትልቅ ሚስጥር ልንገርህ ፤ የላይኛው እርከን አዛዦች ካልሆኑ በቀር ተራ ጂኒዎችና አጋንንት ቁጥር ላይ መሐይም ናቸው ።

ከሁለት ስጋዎቼ ፤ አንዱም ጋር ሳልሆን እያለቀስኩ ባዶ ሆዴን አደርኩ ። በነጋታው እናቴ ፥ ደወለች ። አንቺን እኮ ነው ለቀብር የምንጠብቀው !!! አለች ። ምን ልበላት ? እያለቀስኩ የወንድሜን ሁኔታ ነገርኳትና ፤ እዚህ ማንም ስለሌለው አልመጣም አልኳት ። የሰማችኝ መስሎኝ ብዙ እያወራሁ ፥ በስልኩ ውስጥ ሲጯጯሁ ሰማሁ ። እናቴ ፥ በድንጋጤ ወደቀች ።

አንድ ሀዘን ከብዷት ፥ እንደደህና ነገር በላዩ ደረቤላት ለምን አትወድቅ ? ሀዘን ላይ ሀዘን ጨመርኩ ። አይምሮዬ በትክክል እያሰራ አልነበረም ፤ እንደማልቀስ ይሁን እንደመሳቅ ያደረገኝ አሁን ላይ በደንብ ትዛ አይለኝም ። ቆይተው ፤ መልሰው በመደወል ወሃ እንዳደረጉላትና ደህና መሆኗን ነገሩኝ ።

ባሌና ጀሌዎቹ ፤ ግቢው ውስጥ እየቃሙ ነው ። ቀጥ ብዬ ወደሱ በመሄድ ፥ ለወንድሜ መድረስ እፈልጋለሁ አልኩት ። ቀና ብሎ ሳያየኝ ፥ አውልቂና ትሄጃለሽ አለ ። ምኑን ? ማዕተብሽን ። እንዲህ ሲለኝ ፥ እኔ እንዳደረኩ ራሱ ረስቼው ነበር ። የልብልብ ተሰማኝ ፤ ከዚህ በኋላ ምን ሊያሳጣኝ ብዬ እፈራዋለሁ ? ምን እንዳይቀርብኝ ብዬ እታዘዘዋለው ? አላወልቅም ብዬ ፥ አምባረኩበት ።

የመጣው ይምጣ ! ብዬ ወደመኪናዬ ለሁለተኛ ግዜ ሄድኩ ። የግቢዬን በር በላያቸው እየዘጋሁ ፥ መሄዱን ሂጂ በኋላ ግን እንዳታዝኚ አለኝ ። እንዳልሰማሁ ፥ መኪናዬን አስነስቼ ወደ ደሴ መሄድ ጀመርኩ ። ሉሌ ፤ ፈሪ ስለሆንኩ ራሴን መግደል ፤ አልችልም ። ከሱ መጥቶ መንገድ ላይ ቢገለብጠኝና ብሞት ግን ደስታዬ ወደር የለውም ።

የእውር ድንብር ስነዳ ስንት የገጠር ፍየልና አህያ ስቼ ደሴ ገባሁ ። ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል የተኛ ወንድሜ ጋር ገባሁ ። ከሰዓታት በፊት ፥ ኢንቴንሲቭ ኬር ዩኒት ውስጥ ገብቷል ። ከአሁን ላይ የተየገረኝን ሰዓት ስቀንስ ከሎጊያ የተነሳሁበት ነው ። ተንበርክኬ ፤ ፊቴን እየቧጠጥኩ ማልቀስ ጀመርኩ ፤ ባሌ ... ተለመነኝ! ...የኔ ፈጣሪ ! ... የኔ ኋያል! ...ይቅር በለኝ !! እያልኩ መጮህ ጀመርኩ ። የተሰበሰቡት ሰዎች ግራ ገብቷቸዋል ፤ የገዛ ወንድሜን ባሌ የምል መስሏቸዋል ።

ወንድሜን አልማረውም ። ሲያየው የነበረ ዶክተር ወደኔ መጥቶ ፤ አዝናለሁ ወንድምሽ አርፏል አለኝ ። ምድርና ሰማዩ ተደበላለቀብኝ ፤ ሆስፒታሉን በጩኸት አቀለጥኩት ። አረርኩ ። ተቃጠልኩ ።

ከሆስፒታሉ የሬሳ ማውጫ ሳፅፍ አጠገቤ ማንም አልነበረም ። ከዛ ሁሉ ፤ ጀምኣው አንድ የሱ ጓደኛ እንኳን አላላቀሰኝም ። ይሄም የቅጣቴ አካል መሆኑ ነው ። ወደሬሳ ክፍል ስመለስ ፤ ከርሱ ውጪ ማንም አልነበረም ። የነርሶች መቀመጫ ላይ እግሩን አጣምሮ ተቀምጧል ። የኔ ባል ፥ የኔ ሁሉን አድራጊ ፥ የኔ ቀናተኛ ፥ የኔ ሐያል ...!

በፊት ብሆን ፥ ላንቀው እዳዳ ነበር ፤ ደቃቃ ብሆንም ልቤ ተራራ ናት ። አሁን ግን ንዶት አመድ ሆኛለሁ ፤ አልታገልም ። ቢላ ሰጥቶ ፥አሁን አይንሽን ጠንቁያት ቢለኝ ፥ አለማመንታት እጠነቁላታለው ።እንዳየሁት ፥ እግሬን ብርክ ብርክ አለኝ ፤ ተርበተበትኩ ።

ተጠግቼው ፥ ተንበረከኩ ። ትንፋሼን ሰብስቤ ...አንተ ንጉሥ ፤ አንተ የእፍሪት አሽኸር (እፍሪት ፥ የኔባልና ጀሌዎቹ የሚሰግዱለትና በመቀመቅ ያለ ጌታ ነው። ስለርሱ የሚያውቁ ካሉ ይንገሩህ) ተለመነኝ ። እያሞጋገስኩ ፥ ለመንኩት ። ስለእፍሪት ብለህ ፤ የአንድ ወንድሜን ሬሳ ልቅበር ?!

የሳልስቱ ቀን ማታ ፤ ሎጊያ እንዳገኝሽ ! ብሎኝ ወጣ ። አንዴ እንኳ አይኔን አላየኝም ። መኪናዬን ይዞ ተመለሰ ። እኔን እኔ ብቻ የማያቸው ጋሻጃግሬ ጂኒዎች ጋር ተወኝ (ሉሌ ፤ ሰይጣንና ጂኒ እንዳይምታቱብህ ፤ ይለያያል) ።

አባዱላ ተኮናትሬ ፤ ለስንትና ስንት አመት ወደተውኳት አዲስ አበባ ጉዞ ተጀመረ ። ታናሽ እህቴ ጋር ደወልኩ ። በተዘጋጋ ድምፅ ምን አይነት አውሬ ነሽ አለቺኝ ? አባን ቀብረው እየተመለሱ ነበር ። ልክ ነበረች ፥ አሁን አውሬ ነኝ ፤ ፈሪ አውሬ ። ነገር ግን ምንም አይነት ተጨማሪ ወሬ የማስተናግድበት አቅም ላይ አልነበርኩም ።

አዳምጪኝ ! ብዬ ጮህኹ። ስልኩን ፥ ለአክስቴ ሰጠቻት ። አባቴን እንዳረዳቺኝ የእህቷን ልጅ አረዳኋት ። የወንድሜን ሬሳ ይዤ እየመጣሁ ነው ፤ አመሻሽ ላይ እገባለሁ ! ...

ካልኩት ሰዓት በጣም አምሽተን ፤ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ካሳንችስ ደረስን ። በዛ ለሊት ፤ ያ ሁሉ ሰው ተሰብስቦ ሬሳ ሲጠብቅ ፤ ያሳደገኝ የግቢ ገብርዔል አመታዊ በዓል ይመስላል ። እገባበት ጠፋኝ ፤ ፀፀት እግሬን አስሮት ከጋቢና በሰው እርዳታ ወረድኹ ።

እብድ እያሉ ማልቀስ ፈልጌ ነበር ። ልክ ቢወራጭ እንደሚሞት ሰው ቆላለፈኝ ። እዚህ ጋር ፥ አንድ ሚስጥር ልጨምርልህ ። የቁጥ ቁጥ ፥ እርም ለማውጣት የምትሆን ሐዘን ትታለፋለህ እንጂ ፤ እንደኔ እግሩ ለገባ ሰው ሐዘን አይፈቀድም ። ሁለት አይደለም ፥ ለምን የሙሉ ቤተኛህ ሬሳ አይወጣም ! ...

ይቀጥላል

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

31 Oct, 17:43


[ ለበረኃ ጂኒ ፥ ራሴን ዳርኹ ]

ከ ልዑል ዘወልደ ገፅ የተወሰደ 'እውነተኛ ታሪክ'

የአስራ ስድስት አመት ልጅ እያለሁ ከ ወንድሜ ( ኮንስትራክሽን - መንገድ - ይሰራ ነበር ) ጋር ወደ አፋር ሄድን ። አፋር እንደደረስን ፥ ሎጊያ ከምትባል ከተማ ቤት ተከራይተን ኑሮ ተጀመረ ። አምስት ወር ሳይሆነን ፤ አከራያችን ቤቱን ልቀቁ አሉን ። ሌላ ቤት መፈለግ በጀመርን በሁለተኛው ቀን ፥ አንድ ቆንጆ ጊቢ ውስጥ አገኘን ። ስድስት ሰርቪሶች ሲኖሩት የጥገኛዋ ቤት እኛን እየጠበቀች ነበር ፤ ገባን ።

አንድ ቀን ከጓደኛዬ ጋር ልንዝናና ወጥተን እየተዝናናን መሸብን ፤ ሙቀት ስለሆነ ቢራ እንደጉድ ይገባልሃል ። ለሊቱ ሲያጋምስ ግዜ ፥ ጓደኛዬን ተሰናብቼ ወደቤት መጣሁ ። ግቢ ስገባ ስድስት ሰዎች ቁመታቸው ሶስት ሜትር ይሆናል ፥ እሳት አንድደው ይጫወታሉ ።

እኔ ሞቅ እንደማለት ብሎኝ ስለነበር ፥ የአንዱ ተከራይ ዘመድ ይሆናሉ ብዬ ፤ አልፌያቸው ገባሁ ። አፋር በጣም ሙቀት በመሆኑ ፤ ሁሉም የሚተኛው በረንዳ ላይ ነው ። እኔም ፍራሼን አውጥቼ ከነሱ ፊት ለፊት አንጥፊ ተኛው ። ጠዋት ስነሳ እነዛ የሚያማምሩ ወንዶች የሉም ፤ እሳት ሲነድበት የነበረ ቦታ ሄዳድኹ ፥ ምንም አመድ የለም ።

ደነገጥኩጬ ራሴን መጠራጠር መረጥኹ ፤ ለማንም አላወራሁም ። ማታ ግን የተፈጠረውን ነገር እያንዳንዷን አስታውሳለሁ ። በማግስቱ ማታ ከመጡ እንደው ብዬ ጠበቅኹ ፤ የመጣ የለም ።

ያየኋቸው ፍጡራን ውበት ልነግርህ አልችልም ፤ በጣም ውብ የሚባል ወንዶች ናቸው ። ሲቆይ ግዜ ረሳሁት ። በሳምንኑ ሀሙስ ቀን ፥ ቅድም ያልኩኽ ጓደኛዬ ቤት አምሽቼ ፤ ግማሽ መንገድ የሚሆን ሸኝታኝ ተመለሰች።

ግቢያችንን ከፍቼ ወደውስጥ ስዘልቅ የመችለታዎቹ ሰዎች ፥ ሁሉም አሉ ። እንዳየኋቸው ደነገጥኩ ። ክብ ሰርተው ጫት እየቃሙ ነበር ። ሠላም ! ለማለት ስሞክር አፌ እይንቀሳቀስም ፥ ማውራትም አልቻልኩም ። ሁለቴ ሞክሬ ሲያቅተኝ ግዜ ፥ ወደ ውጪ ወደነበር ፍራሼ አመራው ። ልቤ እየደለቀች ፥ ድርያዬን ሰብስቤ አረፍ ስል ፥ አንደኛው ፈገግ ብሎ እያየኝ ነው ።

ድርብ ጥርሱ እንዴት እንደሚያምር ልነግርህ አልችልም። በረንዳዬ ላይ እጄን ተደግፌ እያየሁት ፥ እንዴት እንደሆነ አላውቅም ልቤ ወደደው ። ፈዝዤ ፥ እያየሁት አንጎላጀጀኝና ተኛሁ ። ከመተኛቴ በፊትና በኋላ በነበረው ቅፅበት የተከናወነ የማስታውሰው ነገር የለም ።

ጠዋት ፀሀይ አይኔን ወግቶኝ ስነሳ ፤ የነገርኩሆ ሰዎች በቦታው የሉም ። አሁን ግን እንደመችለት አይነት ስሜት እየተሰማኝ አልነበረም ።ከበታቸው የቀረ አመድ ባላገኝም የልጁ ፈገግታ አይኔ ላይ አለ ፥ እውነት እንደነበር እርግጠኛ ነኝ ።

አርብ ለሊት ፤ የትም ሳልሄድ ቁጭ ብዬ ጠበኳቸው ። አላሳፈሩኝም መጡ ። ቁመታቸው ከቤቶቹ ጣሪያ ያልፋል ፤ ደነገጥኩ ። የሆነ ያልገባኝ ነገር አለ ፤ ፈገግተኛውን ልጅ ሳየው ግን መመራመሬን እርግፍ አርጌ ተውኹ ። ዛሬ ከሌላው ግዜ በተለየ ፥ አብረዋቸው ሴቶች ነበሩ ።

እኔ ግን ፥ እንደተለመደው መንቀሳቀስም ሆነ ማውራት አልቻልኩም ። ከማየት በቀር ፥ በተቀመጥኩበት ሽባ ሆንኩ ። እነሱ ግን እያዩኝ ይስቃሉ ፥ አንዴ በአፋረኛ እና በ አማርኛ እየቀላቀሉ ያወራሉ ።

ድንገት ፥ የአንደኛዋ ተከራይ በር ከፍታ ወደ እነሱ አቅጣጫ ቆሻሻ ውኃ ደፋች ። ለሷ አይታዩም መሰለኝ ፥ ስትደፋ ግን እሳታቸው ላይ እና ሁለቱ ፍጡሮች ላይ ነበር ። እኔን መለስ ብላ አይታኝ ፤ አንቺ አተኝም? ! አለች ። ሽባ በመሆኔ ምንም መመለስ አልቻልኩም ። በሩን ዘጋች ፤ በጣም ተናደዱ ። ሴቷ ፍጡር ወደ ልጅቷ ቤቷ እየገሰገሰች ገብታ ስትወጣ አየዋት ። እኔና ቆንጅየው ፍጡር እየተያየን እንደመችለት ፈዝዤ ፥ እንቅልፍ ወሰደኝ ።

ለሊት ዘጠኝ ሰዓት ይሆናል ፤ ውኃ የደፋችው ልጅ በጣም በሀይለኛ ትጮኽ ጀመረ ። ሁሉም ተከራይ ፥ ተነሳ ። እኔ በጩኸቷ ባንኜ ስነሳ ፍጡራኑ የሉም ። ፍርሀት ከጩኸቷ ጋር ሲደመርብኝ ግዜ ሰውነቴን ወረረኝ ። ጎረቤቴ ፥ ህፃን ልጅ አለቻት ። ህፃኗ ፥ ከሷ ብሳ እንጥሏ እስኪበጠስ ከእናቷ እኩል ተርገበገበች ። ጎረቤት ተደናግጦ ፥ ዘምዘምም ፀበልም ተደረጋላቸው ። እኔ ያየሁትን እንዴት ብዬ ልናገር ?

እንዲህ እያለ ፤ ከፍጡራኑ ተላመድን ። በሁለተኛው ቀን ይመስለኛል ፥ ሴቷ ፍጡር ቀጥ ብላ ወደኔ መጣች ። አመጣጧ ያስፈራል ፥ አይን አይኔን እያየች ከአጠገቤ ቁጢጥ አለች ። ከትላንት ወዲያ እጣቢ የደፋችብኝን'ን ጎረቤትሽ ፥ ከዚህ ግቢ ውጪ በያት ! ይሄን የማታደርግ ከሆነ ፥ ልጇን እገላታለሁ ! አለች።

እሰማታለሁ እንጂ ፤ ከጭንቅላት እስከ እግሬ ሽባ ሆኛለሁ ። በነጋታው ጠዋት ስነሳ ፥ ፊት ለፊታችን ወዳለ ባለሱቅ ሄጄ የሆነውን ምንም ሳላስቀር ነገርኩት ። ቤቱ ከተሰራ አመት እንደሆነውና ከዛ በፊት የከተማው ቆሻሻ መጣያ ስለነበር ሰይጣን ይሆናል አለኝ ። አጥወለወለኝ ። እዛው እንዳለሁ ፤ ለሷም ለመንገር ቤቱንም ለመልቀቅ ወሰንኩ ።

ስረጋጋ ለጎረቤቴ ገብቼ ፥ ነገርኳት ። እሷ ግን እንደበሽተኛ አይታኝ ፥ እምቢ አለች ። ቀን ቤት እየፈለኩ ፥ ማታ ተሳቅቄ ማደር ጀመርኩ ። በሁለተኛው ቀን ህፃን ልጇ በተኛችበት ሞተች ። የሚገርምህ ፤ ለኔ ስም ወጣልኝ ፤ እንደሟርተኛ የግቢው ሰው ሁሉ ሸሸኝ ።

የቀብሯ እለት ማታ ፤ በተኛሁበት (ቤቴ ውስጥ ነው የተኛኹት) እንደሰመመን አርጎኝ ስባንን ሰይጣኖቹ ተከታትለው ወደኔ መጡ ። ፈገግተኛው ሰይጣን አለልምዱ ልክ አልነበረም ። አይኑ ደም ለብሶ ፥ ከዚህ ቤት የለቀቅሽ እለት መቃብርሽን ትምሻለሽ አለኝ ።

አንድ ያመነኝ ሰው ባለሱቁ ስለነበር ፥ ጠዋት ወደሱ ሄድኩ ። እሱም ፥ አዲስ ነገር ነገረኝ ። ምናልባት ፥ እንዲህ የሚቀያየሩ የአፋር ጎሳዎች አሉ ። ሰውም ፣ ሰይጣንም ፣ እንስሳም ይሆናሉ ! አለኝ ። በጣም ሲጨንቀኝ ግዜ ወደወንድሜ ደወልኹ ፤ እሱ ግን ቀልዶብኝ እንድረጋጋ ነግሮኝ ዘጋሁ ።

ከሐሳቤ ጋር እየተሟገትኹ ፤ ቁርስ ልበላ ወደሆነ ምግብ ቤት ስገባ ማታ የሚታየኝ ሰይጣን ሌላ ወንበር ላይ ተቀምጧል ። ደነገጥኩ ፤ በድፍረት ወደእኔ መጥቶ ሰላም አለኝ ። እንደወደደኝና መተዋወቅ እንደሚፈልግ ፥ እሱም ለሎጊያ አዲስ እንደሆነ ምናምን አወራኝ ።

የአይኔን ወዳጅ ፥ በቀን ካገኘሁት በኋላ ፥ ለሊት የሚመጡት ነገር ቀረ ። እሱ ነገር መቅረቱ ከጭንቀት ስለገላገለኝ በቀን እየደጋገምን መገናኘት ጀመርን ። እየተግባባን መጣንና ፥ ማታ ስለሚሆነው ነገር ሁሉ ነገርኩት ፤ ሙድ ያዘብኝ ።

እቤት ፤ የምታምር ድመት መጣች ፤ ሳያት ደስ አለኝ ። በተፈጠረው ኹነት ከግቢ ሰዎች ጋር ስለማላወራ ጓደኛ ያገኘሁ መሰለኝ ። ልጁ (ስሙን ብነግርህ ደስ ይለኝ ነበር ፤ ስለፈራሁ ይቅር ) ሁሉ ነገሬን ተቆጣጥሮኛል ወይም በቃ ወደድኹት ።

የሆነ ነገር ግን ግራ ይገባኝ ጀመር ። እሱ ወደቤት ከመጣ ድመቷ ጭራሽ ትጠፋለች ። እሱ እግሩ ሲወጣ ጠብቃ ደሞ ትመጣለች ። ወንድሜ ከአዋሽ ሲመጣ ልነግረው ፈልጌ ፥ እንዳያጣጥልብኝ ፈርቼ ተውኹት ። እየተጫወትን አመሸን ። የቤቱ ሙቀት ለሁለት አይደለም ፥ ለብቻ ራሱ አያስተኛም ። በረንዳ ላይ ፍራሽ አንጥፎ ልንተኛ ስንዘጋጅ ፥ ያልኩህ ድመት መጥታ የወንድሜን እግር መቦጨር ጀመረች ።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

31 Oct, 17:43


በእግሩ ሲመታት ፥ አንተ እየገዘፈች መጣች ። በመታት ቁጥር ወደ ትልቅ አውሬ እየሆነች ስትመጣ ፥ ጮህን ። ጎረቤት ተሰበሰቦ አነር ! አነር ! እያለ አባረራት ። ካባረሯት በኋላ ግን ጡሩንባ ተነፋ ። ለምን አትልም ? እንቅልፍ እንዳተኙ ! በጣም ሙቀት አለ ፥ ተብሎ። እንደዚህ ተብሎ ከተኛህ ሙቀት አፍኖ ይገልሀል ። ይሄና የቅድሙ ነገር ሰበብ ሆኖን ከግቢው ሰዎች ጋር ተሰብስበን ።

በነጋታው ፤ ወንድሜ ወደከተማ ሲወጣ ጠብቆ የወንድ ጓደኛዬ መጣ ። እግሩን ያመመው ይመስላል ! ምን አገኘህ ? ስለው ፥ ለምን እንደማታውቂ ትሆኛለሽ ! አለ ::
አይን አይኑን እያየሁ ስወዘጋገብበት ፤ ዥንጉርጉሯ ድመት እኔ ነኝ !" አለኝ ። አፌ ተንቀጠቀጠና እንደተለመደው ተለጎመ ። እሱ ግን ማውራቱን አላቆመም ። ይኸውልሽ ! እኔ ፈልጌው አይደለም እንደዚህ የምሆነው የቆየ ! የአያቶቻችን እርግማን ነው ። ካንቺ ጋር በፈጠርኩት ነገር በመላው ቤተሰቤ እየተሰደብኩ ነው ። ነገር ግን ከምንምና ከማንም በላይ ወድጄሻለሁ ! ምን ማድረግ እንዳለብኝ ራሱ አላውቅም ! ብሎ ተንሰቀሰቀ ።

እንደዛም እያለቀሰ ፥ እንደፈራሁት ሲገባው ቁጣ ጀመረው ። ፊቱ የሚለዋወጥበት ፍጥነት ፥ አታምንም ። ወንድምሽ ፈገግ እያለ ፥ ወንድምሽ እንዲሞት ትፈልጊያለሽ ? ከኔ መለያየት ያሰብሽ ቀን ይሞታል !!! አለኝ ።

እኔ በእምነቴም ጠንካራ አይደለሁም ። ነገር ግን ስለነሱ በድፍረት ማጣራት ጀመርኩ ። ከጠበኹት በላይ ብዙ ሰው ውስጥ ውስጡን ፥ ያውቃቸዋል ። የአለቃቸው ግብር ራሱ ምን እንደሆነ ተነገረኝ ። በባህር ወደ የመን የሚሻገሩ ስደተኞች ? ዜና ሰምተህ የምታውቅ ከሆነ ወደ ሊብያ ሲሻገሩ ከሚሞቱት ወደ የመን ሲሻገሩ የሚበሉ ነፍሳት ይበዛሉ ።

ወደኔ ታሪክ ስመልስህ ፤ ብቸኛ ወንድሜ እንዲሞትብኝ ስላልፈለኩ ፥ ከሰይጣን ጋር መዳራቴን ቀጠልኩ ። (ምን ምን እንደሚያረጋት ፤ ከፅሁፉ ላይ ተቆርጧል) ስጦታ ግን ሁሌም ያመጣልኛል ። ወንድሜ እስኪገርመው ድረስ ፥ ብር ኖረኝ ። አዲስአበባ ለአጎቴ ልጅ ውክልና ልኬ ሳርቤት ገብርኤል ቤት ገዛሁ ። እኔ ግን ከሎጊያ ለመውጣት አልተፈቀደልኝም ።

በሎጊያ እኔን የተናገረኝ ፣ የተጣላኝ ወይ ያስቀየመኝ ካለ አይሰነብትም ። ወሬ ሲበዛብኝ ግዜ ፥ ቀስ እያልኹ ፥ የጊቢውን ተከራይ ሁሉ አባረርኹ ። በፊት የሚያውቀኝ ሰው እስኪገርመው ድረስ ፥ ሳልፈልግ ባህሪዬ እየተቀያየረ መጣ ። እንደዚህ እያልን ፥ ለስምንት አመት ቀጥለን ፥ የህዳር ሚካኤል እለት አንድ ነገር ተፈጠረ ።

እኔ ህዳር ዘጠኝ ፥ ባሌን አስፈቅጄ ወደ ደሴ (ደቡብ ወሎ) እቃ ለመግዛት ሄድኩ ። ደሴ ፥ ከሎጊያ ብዙ አይርቅም ፥ ቅርብ ነው ። ወደ ደሴ ስሄድ ግን ድመቴም አብራኝ በዘንቢል ተጓዘች (የምን ድመቴ ባሌ ልበለው እንጂ) ። ደሴ የምትኖር ጓደኛዬ ጋር አረፍኩ ፤ ድመቷ ሳላያት ወርዳ ከበራቸው ቀርታለች ። የጓደኛዬ አባት ሼክ ይሁን ኡላማ አላውቅም ፥ ብቻ በአረብ ገንዳ መስጂድ ትልቅ ክብር ያላቸው ናቸው ።

ሶስት ቀን ከሷ ክፍል ሳልወጣ ቆይቼ ፥ ሲደብተኝ ግቢው በር ጋር ቆምኩ ። ሰው ፥ ነጠላውን አጣፍቶ ይርመሰመሳል ። የቀኑን ንግስ አስቤ-አስቤ ፥ ከሆነ ግሮሰሪ የሚወጣ መዝሙር ስሰማ መጣልኝ ፤ ለካ ህዳር 12 የአመት ሚካኤል ኖሯል ። ሰዎቹን ተከትዬ በደመነፍስ ሄድኹ ። በትርምስ ውስጥ ፥ ልክ ቤተክርስቲያኑን ሳየው አይኔ እምባ አቀረረ ።

አንድ ልቤ ሂጅ ግቢ ይለኛል ፤ ግን ደግሞ በጣም ፈራው ። ልክ ፥ወደ ቤተክርስቲያኑ ልጠጋ ስል ድመቴ እንዴት ተከትላኝ እንደመጣች አላውቅም እግሬን ቧጨረችኝ ፥ ነጠላ ጫማዬ እስኪቀላ አደምታኛለች ። ተናድጄ ፥ በእልህ ወደ ቤተክርስትያኑ ሄድኩ ። ደሜ አልቆም ብሎ ፥ እግሬ በጣም ሲደማ ግዜ ጎንበስ ብዬ በድሪያዬ ጫፍ ያዝኩት ። እንዳጎነበስኩ ታቦት መዞር ጀመረ ፤ ታቦቱን እንዳየሁ እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ ። በቀሚሴ ያፈንኩት ደም እንደመቆም ሲል ፥ የታቦቱ በረከት እንዳያመልጠኝ ሮጥኩ ። ወደ ቤተክርስትያኑ በር ልገባ ስል ግን የሆነ ነገር ይመልሰኛል ። በኃይል ስጠጋው ፥ በተጠጋሁበት ሀይል ልክ መልሶ ገፈተረኝ ።

ማርያምን ሆድ ባሰኝ ። ሚካኤልዬ ምን ያህል ቢጠላኝ ነው ? የሚገፈትረኝ ። ፈጣሪ ምን ያህል ቢፀየፈኝ ነው የሰይጣን ሚስት የሆንኩት ። እንደዚ እያልኩ ጮህኩ ፤

" መፅሐፍ ቅዱስ ላይ የተፃፈው ሁሉ ውሸት ነው ! ከመቶ በጎች አንዷ ብትጠፋበት ሊፈልግ አልወጣም ? ያ ሁሉ ውሸት ነው ! እግዚአብሔር አይወደንም " በለቅሶዬና በጩኸቴ መሀል ሳግ ይተናነቀኛል ። " ለምን ፈጠርከኝ?! ውሸታም ነህ !! አንተ እውነት ብትሆን እኔን ታድነኝ ነበር !!

ሰው ሁሉ ሸሸኝ ፤ በነጠላቸው አፋቸውን እየሸፈኑ ከንፈራቸውን መጠጡ ። የሰው አይን ሲበዛብኝ ፥ መረጋጋት እንደምንም ተረጋጋሁ ። በዚህ መሃል የሆነች ሴት (በሰላሳዎቹ ያለች) አጠገቤ መጣችና እንደናቴ ንፍጤን እየጠረገች አባበለችኝ ፤ ደረቷ ላይ ተደፍቼ ልቤ እስትወጣ ደግሜ ተንሰቀሰቅኹ ።

ሲቆምልኝ ፥ ለምን አለነጠላ መጣሽ ? ለምን አንገትሽ ላይ ማህተብ የለም ? አለችኝ ። ኖሮኝ አያቅም ! አልኳት ። ከአንገቷ ላይ ወፍራም ማዕተብ አወለቀችና በጄ አስያዘችኝ ። ይኼውልሽ ፤ በዚ ማዕተብ ውስጥ የራስ ዳሽን ተራራው ቅዱስ ያሬድ የእምነት አፈር አለ ፤ የከርመር መስቀል ነው ። አይዞሽ ! ከሁሉም ነገር ይሰውርሻል ፥ ይጠብቅሻል ። ያሰብሽውን በልብሽ ጠይቂና ከተሳካ ስለትሽን ይዘሽ ትሄጃለሽ ! አለች ።

ዝም ብዬ ሳያት ፥ ከጄ ላይ አንስታ አንገቴ ላይ አሰረችልኝ ፤ ደንዝዤ ቆሜ ፥ ከአጠገቤ እንደሄደችም አላስተዋልኩም ። ወደጓደኛዬ ቤት በቀስታ እየተመለስኩ የመንገድ ዳር የሱቅ ዣንጥላ ስር የሆነ ሰው ቆሟል ፤ ባሌ ።

ፊቴን አያይም ፤ እንዳቀረቀረ ወደኔ መጣ ። ደርቄ ፥ ጠበኹት ። ሰላምም ሳይለኝ አንገትሽ ላይ የቋጠርሽውን ምናምንት በጥሽ ! አለኝ ። አንገቱን ወደመሬት እንዳቀረቀረ ነው ። አላወልቅም ! ግደለኝ !! ብዬ አምባረኩበት ። እየተጨቃጨቅን ፥ ከጣሪያ ላይ ሲጣሉ የነበሩ ድመቶች ፥ ተገለባብጠው እላያችን ላይ ወደቁ ።

ድመቶቹ ከአጠገቤ እንደአውሬ ተነካከሱ ። ሁለት መስለውክ ነው አይደል ? ዘጠኝ አስር ይሆናሉ ። ምንም ፍርሀት አልተሰማኝም ፤ ማዕተቤን አላወልቅም ብዬ ደግሜ ጮህኩበት ። የታባሽ እንደምትቀሪ ፤ አያለሁ ስለቅጣትሽ ስትመለሽ እናወራለን ! ብሎኝ ሄደ።

ሚካኤል ሰፈር ሲጣሉ ከነበሩት ውስጥ ሶስት ድመቶች ተከተሉኝ ። እንዳለየኋቸው ሆኜ ፥ ጓደኛዬ ቤት ስገባ በሩን በሀይል ጠረቀምኩት ። በሩ ሲጮህ ፤ ጓደኛዬ (ስሟን መጥራት አስፈላጊ አይደለም) መንጓጓቱን ሰምታ እየሮጠች ወጣች ።

የት ሄደሽ ነበር ? መልስ የለኝም ! ምን ሆኖ ነው ድርያሽ ቀይ የሆነው ? ዝም ። ሁለመናዬ ከፀጉሬ መንጨባረር ጋር ተደምሮ ያበድኩ ስለመሰላት ፤ እሷም ዝም አለች ። ገብቼ ፥ ቦርሳና የፕላስቲክ ዘምቢሌን ማስተካከል ጀመርኩ ። በፍርሃት አፏ ተያይዞ ስሜን ስትጠራኝ ፤ መሄድ አለብኝ !! አልኳት ።

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

31 Oct, 17:43


ከመጣሁበትን አንድም ነገር ሳላደርግ ፤ ለመመለስ ወደመናኸርያ ገሰገስኩ ። ሆኖልኝ እየወጣ የነበረ በራሪ መኪና አገኘሁ ፤ እነዛ ድመቶች እየተከተሉኝ ነበር ። በመስኮት እያየኋቸው ሳይገቡ መኪናው ተነሳ ። ስለዚህ ቆይቼ ሳውቅ ፥ ሶስት መቶ የድመት አሽከሮች አሉት ። ከነሱ ውስጥ ግማሾቹ መቀያየር ይችላሉ ። ወደ ሰው ልጅነት ሲለወጡ ፥ አለ አይደል በተጋነነ ይረዝማሉ እንጂ ፤ ሁሉም ቆንጆ ናቸው ። ባሌ ሰይጣን እንደሆነ ከኔ ውጪ ማንም አያውቅም ። ወንድሜ ራሱ ፥ የጅቡቲ ሞጃ እንደሆነ እንጂ ከማሳልፈው ታሪክ አንድ አያውቅም ።

ሎጊያ ቤቴ እንደደረስኩ ፤ አገር ምድሩ ጭር ብሏል ። ሰፈሬን ጨርሼ ግቢዬን ከፍቼ ገባሁ ። እነዛ ሶስት ድመቶች እርስ በርስ እየተላፉ ነበር ።እንዳላየሁ ሆኘ ስጠጋቸው ፥ ይሸሹኛል ። ማን እንደሰጠኝ እንጃ ፥ የማላቀውን ድፍረት አግንቻለሁ ፤ አላቅም ! ተስፋ መቁረጡ መሰለኝ ።

በጣም ደክሞኝ ስለነበር ፤ ልብሴን ሁሉ ሳልቀይር አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ ። በህይወቴ እንዲህ አይነት እንቅልፍ ተኝቼ አላውቅም ። ጠዋት እራሱ የቀሰቀሰኝ ፤ ስልክ ነው ። የማላውቀው ቁጥር ነበር ። ሄሎ ስል ፤ አክስቴ ድምጿ እየተንቀጠቀጠ ስሜን ጠራች ።

ደነገጥኹ ፤ ምንም ሳትለኝ ...ምነው ? ምን ተፈጠረ? አልኳት ። አባትሽ ደክሟል ! አለች ። አፍንጫዬን ደም-ደም አለኝና ፥ እሪሪሪ ብዬ አለቀስኩ ። ሳለቅስ ፥ አክስቴ አብራኝ ፤ የኔ መከታ ! የኔ መከታ !! እያለች ማልቀስ ጀመረች ። እንደሞተ እሷ ምንም ሳትቀጥልልኝ አውቄያለሁ ። ሚጡዬ ! አባትሽ ጥሎን ሄደ ! አባትሽ ትላንት ራሱን አነቀ'ኮ ...ሚጡዬ!!!

ወንድሜን ለማዳን ስበር ወደሎጊያ መጥቼ ፥ ያልጠበኩትን አባቴን እንደሰው እግሩ ስር ሆኜ ሳልጦረው ፥ ወሰዱብኝ ። እንዲሁ በአይኔ እንደዋለ ፤ እንዲሁ እንደናፈኩት በራሴ እጅ በገባሁት ጣጣ አመለጠኝ ። አክስቴ እያላቀሰች ፥ ድንገት ጆሮዋ ላይ ስልኩን ጠረቀምኩት ። ወንድሜ የት ነው ? ጣቴ ተሳስሮ ቁጥሩን መፃፍ እንኳ አቃተኝ ፤ ደወልኩ ....

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

31 Oct, 06:32


https://youtu.be/hq44LTTqggo?si=8FkKuKTHnYB-Ohkh

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

29 Oct, 17:23


በየዓመቱ እንደለመድነው ጥቅምት 27 ዓመታዊ የአባታችን የመድኃኔዓለምን ክብረ በዓል ዝክር ከእኔ ጋር መዘከር የምትፈልጉ በዋትሳፕ ኢሞ ቴሌግራም inbox አድርጉልኝ።
@abigezenige

አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

25 Oct, 13:19


የመጨረሻ ምዝገባ እያደረግኩ ነው። ወደ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት ገዳም ነገ ዕለተ ቅዳሜ ለምናደርገው ጉዞ አብሮ ለመጓዝ
0967511102 እና 0933143133 ይደውሉ