Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ) @jawisame Channel on Telegram

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

@jawisame


ይህ ቴሌግራም ቻናል ጥር 19/2015 ዓ.ም የተከፈተ ነው።
ዋና አላማው እውነተኛ እና ፈጣን መረጃዎችን ማድረስ ሲሆን በዋናነት ለአማራ እና ለመላው ኢትዮጵያ ኩራት የሆነውን የአማራ ፋኖ በመረጃ መደገፍ ነው።

Great Ethiopia for Africa!

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ) (Amharic)

ይህ ቴሌግራም ቻናል ጥር 19/2015 ዓ.ም የተከፈተ ነው። ዋና አላማው እውነተኛ እና ፈጣን መረጃዎችን ማድረስ ሲሆን በዋናነት ለአማራ እና ለመላው ኢትዮጵያ ኩራት የሆነውን የአማራ ፋኖ በመረጃ መደገፍ ነው። Great Ethiopia for Africa!

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

05 Jul, 10:16


ሰበር ዜና❗️

የአማራ ፋኖ በአንድ አደረጃጀት ተዋቀረ !
///////
አርበኛ ዘመነ ካሴ ---- የአማራ ፋኖ ዋና ሰብሳቢ

አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ---- የአማራ ፋኖ ምክትል ሰብሳቢ

ሻለቃ ፋኖ ዝናቡ ልንገረው ---- የአማራ ፋኖ ዘመቻ መምሪያ

እስክንድር ነጋ ---- የአማራ ፋኖ ውጭ ጉዳይ ጉዳይ ግንኙነት እና ምክትል ሰብሳቢ

ፋኖ ሃብቴ ወልዴ ---- የአማራ ፋኖ ሎጀስቲክ መምሪያ ሃላፊ

ፋኖ ማስረሻ ሰጤ ---- የአማራ ፋኖ ምክትል ሎጀስቲክ መምሪያ

ዋርካው ምሬ ወዳጆ ---- የአማራ ፋኖ ወታደራዊ ጉዳይ ሃላፊ (ጦር መሪ)

ፋኖ አሰግድ መኮነን ---- የአማራ ፋኖ ምክትል ወታደራዊ ሀላፊ (ምክትል ጦር መሪ)

ፋኖ አስረስ ማረ ዳምጤ ---- ምክትል የውጭ ጉዳይ አማካሪ እና ፓለቲካ ዘርፍ

ፋኖ መከታው ማሞ ---- የአማራ ፋኖ ዘመቻ መምሪያ ሃላፊ

ፋኖ ፈንታሁን ሞሐባው ---- የአማራ ፋኖ መረጃና ደህንነት ሃላፊ

ፋኖ በየነ ---- የአማራ ፋኖ ምክትል መረጃና ደህንነት ሃላፊ

ፋኖ ማርሸት ፀሐዩ ----- የአማራ ፋኖ ሚዲያና ፕሮፓጋንዳ ክንፍ ሃላፊ

ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ----- የአማራ ፋኖ ምክትል ህዝብ ግንኙነት

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው -----የአማራ ፋኖ የውጭ ጉዳይ ግንኙነት አማካሪ

ኢንጂነር ይልቃል፣ አቶ ዩሐንስ ቦያሌው እና ወ/ሮ መስከረም አበራ ----- የአማራ ፋኖ አጠቃላይ አማካሪ ይሆናሉ ተብሏል።

#ማሳሰቢያ:- ይህ ዘገባ በጃዊሳ ሚዲያ የተሰራ ሲሆን ዋናውን መግለጫ በቅርቡ የምንዘግብ መሆኑን እና የቦታ ቅይይር እንዲሁም የአደረጃጀት ለውጥ ካለ የምናሳውቅ ይሆናል።

ለጊዜው በዚህ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን እና በቀጣይ ያልተካተቱ የፋኖ አመራሮችን እና ሌሎች ወደፊት መምጣት ያለባቸውን ጀግኖች ጨምሮ ሲጠቃለል አጠቃላይ መግለጫ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀት ስያሜ ጋር የሚስጥ ይሆናል።

አንድ መሆናችን በእጅጉ የሚያስደስት ሆኖ ቅሬታ ሊፈጥሩ ይችላሉ ከሚባሉት አንድ አንድ ነገሮች ሊጠኑ እንደሚገባ እናምናለን። በተለይ እንደ አንድ የአማራ ፋኖ ታጋይ የብአዴን አመራሮችን ወደፊት የማምጣቱ ጉዳይ በደንብ ሊታሰብበት ይገባል።

ብአዴኖች በትክክል የአማራ ፋኖ ትግል አላማው ገብቷቸው ከሆነ በንስሃ ተመልሰው ለህዝብ መሬት ወርደው መስዋትነት መክፈል አለባቸው የሚል ሃሳብም ማንፀባረቅ እንወዳለን።

ያም ሆኖ ይህ ከድል ማግስት ሁሉም ባጠፋው ጥፋት ልክ እስኪቀጣ ድረስ ለአማራ ፋኖ ትግል ወሳኝ እስከሆነ ድረስ አይደለም ከብአዴን ጋር ከሰይጣን ጋርም ቢሆን አብረን እንሰራለን።

በዚህ ጉዳይ ትግሉን ወደ ኃላ የሚጎትቱ አካላት የሚፈጠሩ ከሆነ ከድርጅቱ በቀጥታ እንደሚሰናበቱ መጥቀስ እንፈልጋለን።

ከዚህ በላይ ደስታ በዚህ ትግል ውስጥ እንደሌለ ስለተረዳን ይህንን ካበሰርን በኃላ ነገ እንኳ #ብንሞት የማይፀፅተን መሆኑን እየገለፅን አንድነታችን የሚያስደስታችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን🙏

#አንዳንድ ሚዲያዎች ገና ካሁኑ መርዝ መትፋት ጀምረዋል🤣። እኛ የዘገብንው መረጃ ትክክለኛና ተገምግሞ ያለቀለት ሆኖ አስቀድመን ያወጣንው ደግሞ ቅሬታ ካለ እና መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ሃሳብ እንድትሰጡበት ጭምር ነው። የመዋቅር ለውጥ የተደረገ እንደሆነ #ማሳሰቢያ በሚል ከላይ አስቀምጠናል።

እነ ኢንጅነር ፋኖ ማንችሎት እሱባለውን፣ ፋኖ ወንድሙ ማሩን፣ ኮማንዶ ፋኖ ፍቅሩን እና ፋኖ አበበ ፂሞን ጨምሮ ሌሎች ጀግኖችን የሚያጠቃልል ሰፊ አደረጃጀት እየተሰራ ነው። ከዛ በፊት ግን በብአዴን ላይ ያላችሁን ሀሳብ እንድትሰነዝሩ መረጃው ቀድሞ ለእናንተ ደርሷል።

የመረጃ ምንጭ እንኳ ሳይጠቅስ መረጃ ሲቃርም የከረመው የሚዲያ አንቂ ሁሉ የፋኖ ታጋይ ልምሰል ቢል እንደማሾፍ ይወሰዳል። የመረጃ ምንጭህ ሲቀነጭር ሚዲያ ላይ አታላክክ ደውል እና ጠይቅ📞

ይህንን መረጃ በእኛ ሚዲያ አስቀድመን ማውጣታችን ከብአዴን የፀዳ አደረጃጅት እንዲኖር ቢረዳ እንጂ ክፋት የለውም !

እውነታው ይህ ነው! በሃሳቡ ከተግባቡ አጠቃላይ መግለጫ በቅርቡ ይሰጣሉ .....


©ጃዊሳ ሚዲያ

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

05 Jul, 08:16


ሰበር ዜና ......... Is Loading 📥


©ጃዊሳ ሚዲያ

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

04 Jul, 11:39


አስደሳች ዜናም በሉት የምስራች እነሆ !❗️

ጀነራሉ ስራ ላይ ናቸው፤ ትግሉ ይቀጥላል !

ጀነራል ተፈራ ማሞን ከግንባር እንዲህ በፈገግታ ስናያቸው የሚሰማን ደስታ ወደር የለውም ! ለጠላት ደግሞ ሬት ነው፤ ማነህ አገዛዙ ዳይፐር አዘጋጅ🤣

የአማራ ባንዳ ሚሊሻ እና አድማ ብተና ከወንድሞችህ ጋር አብረህ የምትታገልበት ጊዜው አሁን ነውና በፍጥነት ወደ ፋኖ እንድትቀላቀሉ በዚህ አጋጣሚ ማሳሰብ እንወዳለን።

#ማሳሰቢያ:- ይህ ቪዲዮ የተለቀቀው የቦታ ቅያሬ ካደረግን በኃላ መሆኑን ማስገንዘብ እንፈልጋለን።


ሙሉውን ገለፃ በቅርቡ #በጃዊሳ_ሚዲያ ይጠብቁን፤ እስከዛው ሰላም ሁኑ🙏


©ጃዊሳ ሚዲያ

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

04 Jul, 05:26


ሰበር !

በአንድ ወሳኝ ቦታ (.....) የአገዛዙ ሰራዊት ቆፍሮት የነበረው አደገኛ ምሽግ በጀግኖች ተሰብሯል። ጠላት እየፈረጠጠ እኛም እየተከተልንው ነው።


ይቀጥላል💪

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

03 Jul, 19:18


ያሰለጠነህ ጀነራል ተፈራ ማሞ ወደ ፋኖ ሲቀላቀል አንተ ምን ትሰራለህ?

በግዜ ምርጫህን ካላስተካከልክ አጣ ፈንታህ እናትህ ተበርቅሶ መሞት እድለኛ ከሆንክ መትረፍ ነው።

አሁንም አድማ ብተና ተብዬ ሁሉ በፍጥነት ወደ ፋኖ እንድትቀላቀሉ እናሳስባለን።

©ጃዊሳ ሚዲያ

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

03 Jul, 19:07


መግለጫዋ በኔትወርክ ምክንያት የዘገየች ናት

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

03 Jul, 18:59


ከሰሞኑ !

አማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ልጂ እያሱ ክፍለጦር
ሰሜን ወሎ ሀብሩ ወርዳን ኢላ እና ሊብሶ ከተማ ባለፈው ማታ ጀምሮ እልህ አስጨራሽ ውጊያ ካደረገ ቡሃላ ከተሞችን መቆጣጠሩን የክፍለጦሩ ዋና አዛሽ ሻለቃ ደምሌ ጫፋጭ ወይም ጥንቅሹ አሳውቋል።

ይቀጥላል

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

03 Jul, 18:56


ጀነራሉ !

አብዛኛዎቻችሁ ጀነራል ተፈራ ማሞ ወደ ፋኖ እንደተቀላቀለ ሰምታችኅል። የሰማችሁት ግን አሁድ ወይ ቅዳሜ ይሆናል። ነገሩን በሚስጢር ይዘንው እንጂ ከተቀላቀሉ ሰንበትበት ብሏል።

ዋናው ቁምነገሩ ከአዲስአበባ በምን አይነት ድንቅ ኦፕሬሽን ወደ ፋኖ እንደተቀላቀሉ ብታውቁ ደግሞ አገዛዙ የመጨረሻ እንዳከተመለት ማሳያ ነው።

ለማነኛውም አሁን የታሰበውን ቦታ ደርሰው ከወንድሞች ጋር ስለቀጣዩ የትግል ምዕራፍ እየመከሩ ነው።

ይህንን ተከትሎ የቀድሞው ልዩ ሃይል የአሁኑ አድማ ብተና በገፍ ወደ ፋኖ እየተቀላቀሉ ይገኛሉ። የአድማ ብተና መሪዎች በስልክ ጥሪ እየተደረገላቸው እየመጡ ነው።

በቅርቡ ሁሉም ይፈርሳል። እምቢ ያለውን ደግሞ አናቱን በጥይት እናፈርሰዋለን።

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

03 Jul, 18:56


ኩታ-ገጠም የጋራ ግንባር
_/////_
በምስራቅ ጎጃም ዞን
የእነማይ እና እናርጅ እናውጋ ወረዳ  ፋኖዎች  በስነ-ምድራዊ አቀማመጥ ኩታ-ገጠም በሆኑ ቀበሌዎች እና የገጠር ማዕከላት ጥምር አሰላለፍ መፍጠር እንዳለባቸው እንመክራለን።

ጠላት በሚያሰማራው ወታደራዊ አቅሙ ላይ በዝቅተኛ መስዕዋትነት በቀላሉ ብልጫ ወስዶ አዳክሞ ለመደምሰስ ኩታ-ገጠም የጋራ ሀይል አሰላፍ መፍጠር ለነገ የሚባል አይደለም።

ለአብነት፦
1) ጥምረት አንድ

፨ የእነማይ ወረዳ: ወይራ፣ጠልማ፣ዲማ እና ለምጨን ቀበሌ ፋኖዎች እና
፨ የእናርጅ እናውጋ ወረዳ: ተንጉማ፣ቡሽትኮኛ፣እናርጅ መስቀል እና ገደብ ቀበሌ ፋኖዎች ጋር የጋራ ግንባር መፍጠር።

2).ጥምረት ሁለት

፨ የእነማይ ወረዳ: ጠልማ፣መንግስቶ፣ቀሸምሽ፣ የቀበኃና ቀበሌ ፋኖዎች እና
፨ የእናርጅ እናውጋ ወረዳ : አባጀምበር፣ሰኞገበያ፣ዱገደል፣ የጎሳ እና ይናጭ ቀበሌ ፋኖዎች ጋር ተቀናጅቶ መስራት እስካሁን ከመጣንበት የትግል ሂደት በላይ ውጤታማ ያደርጋል።

የአገዛዙ ጦር ከሚያደርገው ዝግጅት አንጻር በውጊያ እቅዱ ጠልማ የተባለችውን ቀበሌ እንደ ወታደራዊ ገዢ ስፍራ ሊጠቀምባት ያሰበ ይመስላል።
የሁለቱም ወረዳ ቆላ እና ደጋማ ቀጠና ፋኖዎች በመስቀለኛ መንገድ ላይ የምትገኘውን 'ጠልማ' ቀበሌ በትኩረት ሊያይዋት ይገባል። የማጥቃትና መከላከል እቅዱም ከጠልማ ቀበሌ አንጻር የተቃኘ ቢሆን ይጠቅማል ።
=========//===========

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

03 Jul, 18:56


ትኩረት ለጎጃም አባይ በርሃ !
///// \\\\
ከሰሞኑ በደምብ ቀምሶ የተመለሰው የጁላ ሰራዊት አሁንም በሌላ አቅጣጫ ለመግባት እየሞከረ ስለሆነ ትኩረት እንዳይለየን ለማሳሰብ እንወዳለን።

ጠላት የፋኖ ዋና ቤዝ ሆኖ የቆየውን የአባይ ሸለቆ ዙሪያ ገባ ቀበሌዎች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መስዕዋት ከፍሎ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ዝግጅት ያደረገበትን ኦፕሬሽን ጀምሯል።

ለዚህ ኦፕሬሽን በተለያዩ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች በለብ ለብ አሰልጥኖ ያስመረቀቸውን ከ20ሺ በላይ ሰራዊት ጨምሮ  ከሁሉም ክልሎች የተውጣጣ ልዩ ሀይሉን አግተልትሎ በአጠቃላይ ያለ የሌለ ኃይሉን ይዞ  ለአንድ ዙር ውጊያ ቢያንስ ለዘጠኝ ቀናት እየተዋጋ የሚያቆየውን ስንቅ እና በቂ ተተኳሽ ይዞ የምስራቅ ጎጃም ዞን ከኦሮሚያ ክልል በሚያዋስነው ደጀን ወረዳ በኩል አባይ በርሃ/ሸለቆ ገብቷል፡፡

ጠላት የያዘው  እቅድ ሰፊ ነው፡፡ በአሳለፍነው አንድ አመት ካየነው ሁሉ የተለየ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል።  ይህን ኦፕሬሽን የተለየ  የሚያደርገው በደጀን ጉብያ በርሃ ተጀምሮ ወደ ደጋማ ስፍራዎች ለመስፋፋት ከፍተኜ ፍላጎት መኖሩ ነው።

አገዛዙ የአባይን ሸለቆ ለመቆጣጠር ዛሬ ሰኔ 19/2016 የጀመረው ኦፕሬሽን ከተሳካለት በሁለት አቅጣጫ ውጊያውን አስፋፍቶ ህዝብ እየጨፈጨፈ ለመቀጠል አልሞ እየሰራ ነው፡፡

ይኸውም፦
1ኛ.  ከደጀን ጉበያ ቀበሌ ተነስቶ ወደ ሸበል በረንታ-ለምጨን (እነማይ) -ገደብ (እናርጅእናውጋ) - ሶማ (እናርጅ እናውጋ) - ወሪያ መስቀል (እነብሴ ሳርምድር) - የጎንቻ፣ሁለትእጁ እነብሴ እና ጎንጅ ቆለላ ወረዳዎችን አካሎ ጭስ አባይ ይደርሳል።

በዚህ ቀጠና የወሎ እና  ቤጌምድር አባይ ሸለቆ አዋሳኝ ወረዳዎችንና ቀበሌዎችን ያካትታል።

2ኛ. ከደጀን ጉብያ ተነስቶ ወደ አዋበል - (ኮርክ) ባሶሊበን - አነደድ - ሞተራ (ጎዛምን) - ስላሴ( ደብረ ኤሊያስ) - ዋድ እየሱስ (ደንበጫ) - መንዝ (ጃቢጠህናን) - ቁጭ(ቡሬ) ያጠቃልላል።

የአምሐራ ፋኖ በጎጃም ሁሉም ክፍለጦሮች፣ ብርጌዶች፣ሻለቃዎች በተጠንቀቅ ቆመው፣ በአንድ ትንፋሽ ፣ በአንድ ተናባቢ እቅድ፣ በሆታ፣በእልልታ፣ በጥሩንባ ተጠራርቶ መራራው ክፉ ቀን በድል ሊሻገረው ይገባል።

ጠላት የጀመረው የመጨረሻ ዙር የማጥቃት እንቅስቃሴ ከእስካሁኑ ሁሉ የተለየ ባህሪ ስላለው በተቀናጀ ክንድ መክቶ በመልሶ ማጥቃት ማደባየት ያስፈልጋል ፡፡

አገዛዙ በያዝነው ሳምንት በአዲስ አበባ እና ባህርዳር ከተሞች ሆዳም አምሐራዎችን ከየወረዳው ሰብስቦ ያደረጋቸው ስብሰባዎች በህዝባችን ላይ መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ ለመፈጸም  አመላካች ነበር። አገዛዙ ለሰላም እጃችንን ብንዘረጋም ሰሚ አጥተናል፣ ተው ብለን ብናስተምርም፣ብንመክርም ሰሚ አጥተናል ከዚህ በኋላ እምቢ አልገዛም ያለውን ህዝብ በሀይል፣በጉልበት ለማንበርከክ ወደ እርምጃ ገብተናል የሚል አቅጣጫ ተይዞ የገቡበት ነው። 
ህዝባችን በዚህ ጨካኝ አገዛዝ የታቀደለትን የጭካኔ  ጥግ አውቆ በነቂስ ወጥቶ የድርሻውን አስተዋጽኦ የማድረግ የሞራል ግዴታ ላይ ነን። 

ለዚህ ጊዜ ያልሆነ ትጥቅ፣
ለዚህ ጊዜ ያልሆነ ጉልበት
ለዚህ ጊዜ ያልሆነ እውቀት
ለዚህ ጊዜው ያልሆነ ሀብት  በአፍንጫችን ይውጣ። 

--------------------//------------------------

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

03 Jul, 18:33


ሰላም ውዶች🙏

መጣን....

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

24 Jun, 22:22


ድሉ እንደቀጠለ ነው❗️

ዛሬ በጎጃም በአምስት ቀጠናዎች ላይ ከበባድ ውጊያ ተደርጓል። ጠላት ኔትወርክ አጥፍቶ ለማጥቃት ቢሞክርም ከመደምሰስ አልተረፈም።

በሸዋ፣ ወሎ-ቤተአምሐራ እና ጎንደር ላይም በተመሳሳይ በርካታ ስፍራዎች ላይ አልፎ አልፎ መረር ያለ የአጭር ጊዜ ተኩስ ልውውጥ እና የተሳካ ደፈጣ ተደርጓል።

ውጤቱ በሁሉም ቦታዎች እንደሁልግዜውም አስተማማኝ ነበር። በጎጃም የተደረገው ውጊያ ከበድ ያለ እና ጠላት እንደለመደው አብዛኛውን ሰራዊት ያጣበት ሆኖ ውሏል።

ከዚህ በኃላ አስቀድመን እንደነገርናችሁ በአራቱም አቅጣጫ እጅግ ከባድ ውጊያ የምናደርግበት እና ጠላትን ለመጨረሻ ጊዜ የምናበረክክበት ጊዜ በመሆኑ ሁሉም አማራ ይዘጋጅ።

ከላይ በቪዲዩ እንደምታዩት የአማራ ፋኖ ተኩሶ አይስትም። ውድ የጀግኖች ደጋፊዎች በሙሉ ፋኖ ጠላትን እንዴት አልሞ እንደሚመታ እና እንደሚጥል ቦታው ላይ ሁናችሁ ብታዩ እንዴት ደስ እንደሚላችሁ ይገባናል።

በእኛ ቀጠና ስር ብቻ ከ23 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ከመሬት በታች ሲሆን ከ11 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ከከባድ እስከ ቀላል ቁስለኛውን ይዞ ፈርጥጧል።

ድምፃችንን አጥፍተን የምንሰራበት ጊዜው አሁን ነው። በወሬ ሳይሆን በተግባር ኢንተርኔት ስናገኝ የሜዳውን ጨዋታ እናስቃኛችኃለን።

ለማነኛውም እኛ ስራ ላይ ነን❗️ በተግባር የምንገልፅላችሁ ግን ደግሞ ወቅቱን የሚጠብቅ በርካታ ዝርዝር መረጃዎችን እየሰነድን ነው።


ሰላም ሁኑ🙏 



®ጃዊሳ ሚዲያ

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

24 Jun, 21:54


የአማራ ፋኖ ጀግንነት ከዘር ነው❗️

የንግስት ፀሐይቱን ወኔ ከተላበሱት ምርጥ ጀግና እህቶቻችን መካከል እነ ባርች ተጠቃሾች ናቸው።

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

24 Jun, 21:45


ጋሽ አረቄ እንዴት ነሽ🤣

ለአማራ ህዝብ/ለተማሪዎች አስበህ ነውያ ሁሉ ንፁሃን ሲጨፈጨፍ የት ነበርሽ አረቂያም❗️

ተኛ በለው እኛ ስራ ላይ ነን💪

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

24 Jun, 21:42


አሸንፈናል ስንልህ ካላመንክ ይሄው ፋኖን አጥፍተንዋል ብለው በሰጡት መግለጫ እባካችሁ አደራድሩን እያሉ ልመና ውስጥ ተጠምደዋል።

ጠላት እየተቀበረ ነው የመጨረሻው ሰዓት ድርድር እያልክ ብትቀባጥር ማን ይሰማሃል🤣

የብልፅግና አህያ ሁላ ለመደራደርም ሆነ ለመነጋገር በመጀመሪያ የአማራን መሬት ለቀህ መውጣት ብቸኛው አማራጭ ነው።

ለዛም እንኳ እድሉ ካለህ ነው፤ አሁን ላይ ድርድር የምትለዋን ካርድ የሳብክ ለህዝብ አስበህ ሳይሆን ስልጣንህን ለማትረፍ ስትል እንደሆነ እናውቀዋለን።

ይህ ሁሉ ጣረሞት የምቱ ውጤት ነው💪

ይቀጥላል .....

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

24 Jun, 12:04


አዴት እና ቲሊሊ በጀግናው የአማራ ፋኖ እጅ ገብተዋል !
------------------///-------------------------------
ለፋኖ እንደ ወርቃማ የትግል ወቅት የሚታየው የክረምት ወራት መቃረቡን ተከትሎ የአምሐራ ፋኖ በጎጃም ከመከላከል ወደ ማጥቃት የተሸጋገረበትን እርምጃ መውሰድ ጀምሯል፡፡

  ትላንት ሰኔ 16/2016 የጎጃም እዝ 5ኛ ክፍለ ጦር በጠላት ላይ በወሰደው መብረቃዊ እርምጃ የቲሊሊ ከተማ መቆጣጠሩ ይታወሳል፡፡

  ዛሬ ሰኔ 17/2016 የጎጃም እዝ 1ኛ ክፍለ ጦር የታቀደ ጥቃት መክፈት የአዴት ከተማ ተቆጣጥሯል፡፡

ለበርካታ ወራት በሎጅስቲክስ፣ ወታደራዊ መዋቅር አደረጃጀት፣ ድህንነት መዋቅር ዝርጋታ ፣ ኢንዶክትሪኔሽን ስራ፣ ስልጠና (በኮማንዶ እና መሰረታዊ ውትድርና ደረጃ)፣ ፋይናንስ አቅርቦት ሰፊ ዝግጅት ሲያደርግ የከረመው የአምሐራ ፋኖ በጎጃም በያዛቸው ወታደራዊ ቤዞች ራሱን ሲከላከል ቆይቶ ተጠባቂውን ማጥቃት መጀመሩን የሚያሳዩ እርምጃዎችን መውሰድ ጀምሯል፡፡

  ከዚህ በኋላ አይኖች ሁሉ ወደ ጎጃም ይሆናሉ፤

  እጅ በአፍ የሚያስጭኑ የፋኖ ወታደራዊ ጀብዶችን የምንሰማበት ጊዜ ከፊታችን ተደቅኗል፣

  ጥቅም ላይ የማይውል መሳሪያ አይኖርም ተብሏል፡፡
                 //ድል ለአምሐራ ህዝብ//




©ጃዊሳ ሚዲያ

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

24 Jun, 12:03


የባህርዳሩ ስብሰባ !
\\\\\\\\\\\\\///////////////
የሰላም ኮንፈረንስ በሚል ብአዴን በባህርዳር ከተማ የሰበሰባቸው ሰዎች ወትሮውንም ቢሆን ህዝብ የሚውቃቸው የቀበሌ አቃጣሪዎች ናቸው፡፡

በመለስ ዜናዊ ሞት ደረታቸውን እየደቁ ያነቡ፣ የህዝቡን በኑሮ መጎሳቆል ለመሸፋፈን በበጥቂት ውሎ አበል ልማቱ፣እድገቱ እያሉ ያደነቆሩን ኩሊዎች ናቸው፡፡

የአምሐራ ህዝብ በዚህ ስብሰባ የተሳተፉ የእድሜ ልክ ባንዳዎች ከየት እንደመጡ መለየት አለበት፡፡ መለየት እና መመንጠር ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡

እኔ አንገቴን ልድፋ ላቀርቅርልሽ የሚለውን ሙዚቃ ለአበባው ታደሰ ጋብዙት🤣


©ጃዊሳ ሚዲያ

Jawisa Media (ጃዊሳ ሚድያ)

24 Jun, 12:00


https://rumble.com/v53epxo-308056524.html