ክፍል 10
ፈዲላም እየሮጠች በመውጣት ለአባቷ ደውላ የተፈጠረውን ነገር ሁሉ ነገረችው መሀመድም በፍጥነት መኪናውን አስተስቶ ወደነ ፈዲላ ቤት ሄደ። ሳሙኤልም ቁጭ ብሎ ቀጥሎም ምን ሊፈጠር እንደሚችል ያስብ ነበር። ፈዲላም ልቧ እጅጉን ተሰብሮ እዛው በረንዳ ደረጃው ላይ ቁጭ ብላ ታለቅስ ነበር።
መሀመድም እንደደረሰ "ልጄ! .... " እያለ ወደ በረንዳአ በፍጥነት ደረሰ ፈዲላም መሀመድ ላይ ጥምጥም ብላ "አባ ሳሚ ጥሎኝ ሊሄድ ነው!" ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ።
መሀመድ፡- አታልቅሺ ልጄ ለምን ታለቅሻለሽ ሳሚ ጥሎሽ ወዴትም አይሄድም
ፈዲላም፡- አይ አባ ሊሄድ ነው ይህም ያንተ ምክንያት ነው አንተ ስለ ሀይማኖት ባታነሳበት ኖሮ እንዲህ ባላደረገ ነበር።" ብላ ጮኸችበት
መሀመድ፡- ተረጋጊ ልጄ ቆይ ሳሚን ላናግረው
አላትና ወደ ቤት ገባ ሳሎን ማንም የለም ነበርና መኝታ ቤት ይሆናል ብሎ ሲሄድ አገኘው።
መሀመድ፡- ሰላም ነው ሳሙኤል እንደምን አደርክ?
ሳሙኤል፡- ውይ አባ መጣህ እንዴ? እግዚአብሔር ይመስገን
መሀመድ፡- ጥሩ ሳሙኤል ከፈዲላ የምሰማው ነገር ምንድነው?
ሳሙኤል፡- አዎን አባ እኔና ፈዲላ ልንፋታ ነው!
መሀመድ፡- ለምን?
ሳሙኤል፡- ከእዚህ በላይ አምላኬን ላሳዝነው አልፈልግም
መሀመድ፡- ይህ ምን ማለት ነው?
ሳሙኤል፡- ይህ ማለት ከዛሬ ጀምሮ የንሰሀ ይወት ልጀምር ነው ማለት ነው
መሀመድ፡- ይህንማ እኔ ልሰጥህ ነበር ድክመትህ ነው እንጂ ማምለክ ያለብህን የአለማትን አምላክ ላሳውቅህ ነበር
ሳሙኤል፡- አየህ አባ አንዱም ይህ ነው ከፈዲላ ጋር እንድፋታ የሚያደርገኝ ነገር
መሀመድ፡- እሺ እሺ ተወው በቃ ልጅ ሳሙኤል! ከፈዲላ ጋር እርቅ አውርዱ
ሳሙኤል፡- መጀመሪያውንም አልተጣላንም አባ መፋታት ማለት መጣላት አይደለም
መሀመድ፡- እሺ አትፋቱ
ሳሙኤል፡- አልችልም!
መሀመድ፡- የፍቅር መስዋእት እስከዚህ ድረስ ነው በቃ?
ሳሙኤል፡- የፍቅርን መስዋእትማ በመስቀል ከተሰዋው በላይ ያሳየኝ የለም እኔም ስለሱ እሰዋ ዘንድ ነፍሴን እጠብቃለሁ
መሀመድ፡- አይ ልጅ ሳሙኤል ተረጋግተህ አስብበት በኋላ ሊከነክንህ ይችላል
ሳሙኤል፡- አስብቤታለሁ አሁን ሻንጣዬን ላዘጋጅ ነው ካላስቸገርኩህ ሄደህ ፈዲላን በወረቀቱ ላይ የፍቺን ፌርማ እንትፈርም አስማማት
መሀመድ፡- ኧረ ልጅ ሳሙኤል ተው! እንደ አባትነት ነው ምመክርህ ለትንሽ ነገር ብለህ ትዳርን የሚያህል ነገር አታፍርስ
ሳሙኤል፡- ለኔ ትንሹ ነገር የእዚህ አለም ህይወት ነው እኔ ለእዚህ አለም እንግዳ ነኝ እንግዳም በሰው ቤት አይቆይም ሌላ የሚሄድበት ቤት አለው በእንግዳነት ባለበት ቤት ሆኖ ሳለ ግን የሚጠብቀውን ቤቱን ከረሳው ከዛ ቤት ተባሯል
መሀመድ፡- ከምትለው አንዳችም አልገባኝም ግን እሺ ይሁን ፈዲላ ጋር ልሂድ
ሳሙኤልም ሻንጣ አዘጋጀና ቁምሳጥን ውስጥ ያሉትን ልብሶቹን ወደ ሻንጣው ይከት ጀመር። መሀመድም ወደ ፈዲላ ሄደ ቁጭ ብላ ትተክዝ ነበር
መሀመድ፡- ልጄ ተይ እንጂ
ፈዲላ፡- ሳሚ ጥሎኝ ሊሄድ ነው
መሀመድ፡- ይሂዳ በአለም ውስጥ ሳሙኤል ብቻ አይደለም ወንድ ያለው እራስሽን እሱ ላይ ጥገኛ አታድርጊ ልጄ አሁን ቀጥሎ ሊመጣ ላለው ነገር አስቢ
ፈዲላ፡- አባ ነግሬህ ነበር አይደል? ይህ የማን ጥፋት ነው?
መሀመድ፡- ተይ ልጄ ጥፋቱን በእኔ አታድርጊው ሳሙኤል ሊፋታሽ የፈለገው አምላኩን ማሳዘን ማቆም እንዳለበት አስቦ እንጂ እኔ ስለ ሀይማኖት ስላነሳሁበት አይደለም እሱንም ነግሮኛል
ፈዲላ፡- እሺ አሁን ምን ሊውጠኝ ነው?
መሀመድ፡- ምንም የሚያስፈራ ነገር የለም ነይ ተነሺ ልጄ ተረጋጊ ያለ ነገር ነው።
ፈዲላ፡- እሺ አባ
መሀመድ፡- እኛ ጋር ትቆያለሽ ወይንስ?
ፈዲላ፡- መፋታት ካለብን እሱ ሳይሆን እኔ ነኝ ከቤት መውጣት ያለብኝ ምክንያቱም ቤቱን እኔን ከማግባቱ በፊት በላቡ የሰራው ነው
መሀመድ፡- እንደሱ ካልሽም ጥሩ ልጄ እኛ ቤት እስከፈለግሽበት ቀን ድረስ መቆየት ትችያለሽ
አላትና ወደ ቤት ይዟት ገባ። ሳሙኤልም ልብሱን ከቶ ከጨረሰ በኋላ ወደ ሳሎን ሻንጣውን እየነዳ መጣ ፈዲላም ስታዬው በድጋሚ ፊቷ በእምባ ተመላ።
መሀመድ፡- ልጄ ቁጭ ብለህ ግን ብታስብበት አይሻልም?
ሳሙኤል፡- መናገር ያለብኝን ተናግሬያለው አባ ፈዲላ ከእኔ ጋር በመፋታቷ እንዲህ ስሜቷ ሊጎዳ አይገባም በእዚህ ፀባዩኣ ከእኔ የተሻለ ጥሩ ባል ታገኛለች........ ተይ ፈዲላ የምትወጂኝ ከሆነ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማኝ አታድርጊ ምክንያቴ ሰልችተኝ ወይም አስጠልተሽኝ እንዳልሆነ ደጋግሜ ነግሬሻለሁ ልቦናሽም ያውቀዋል!
መሀመድ፡- አዎ ልጄ እንዲህ ልትጎጂ አይገባም
ፈዲላ፡- እሺ ግን አንተ ሳትሆን እኔ ነኝ ከእዚህ ቤት መውጣት ያለብኝ ይህ ያንተ ቤት ነው
ሳሙኤል፡- ተይ ፈዲላ እኔ ሆቴል አርፋለሁ ችግር የለውም ይህን ቤት እንደ ስጦታ ቁጠሪው
ፈዲላ፡- አይሆንም ! ና አባ ልብስን በመክተት አግዘኝ
አለችና ወደ መኝታ ቤት ገባች አባቷም ተከትሏት ገባ። ሳሙኤልም በእዚህ ሁኔታዋ ሊከራከራት ስላልፈለገ ሶፋው ላይ ቁጭ አለ። ልብሷንም ከአባቷ ጋር አዘገጃጅታ ከጨረሰች በኋላ ወደ ሳሎን ሻንጣውን እየነዳች መጣች።
ፈዲላም ልቧ እየተሰበረ "ለነበረን ጊዜ ሁሉ አመሰግናለሁ" አለችና እያለቀሰች ወደ ውጪ ወጣች። መሀመድም ሻንጣውን እየነዳ "በል ልጅ ሳሙኤል ሰላም ሁን ውሳኔህ ወደ መጥፎ ነገር እንደማይመራህ ተስፋ አደርጋለሁ"።
ሳሙኤልም እዛው ቁጭ እንዳለ ስለ ብዙ ነገር አሰበብ
ይቀጥላል.............
@nubeberhanuenmelales